Tuesday, March 27, 2018

የወያኔ ፀረ-ኢትዮጵያዊነት ገሀድ ወጣ፤ ለጋራ ጥያቄ የጋራ ትግል ያስፈልጋል።


የወያኔ ፀ-ኢትዮጵያዊነት ገሀድ ወጣ፤ ለጋራ ጥያቄ የጋራ ትግል ያስፈልጋል።
መጋቢት14 ቀን 2010ዓ.ም
page1image3965569840 page1image3965570240
የወያኔ ዘረኛ፣ መድልኦዊ የአምባገነን አገዛዝ ኢትዮጵያ አገራችንን የባሕር በር አልባ ያደረገ፣ መሬታችንን ለሱዳን አሳልፎ የሰጣ፣ አንዲሁም የአገሪቱን ለም መሬቶች ለባዕዳን ፣ ለአራብ፣ለሕንድ፤ ለቱርክ፣ ለማሌዢያ፣ --- ወ.ዘ.ተ ለብዙ ዓመታት ከመቸብቸብ አልፎ ገንዘቡን የበላ፣ የአገሪቱ የስልጣኔ ምንጭና እድገት መሰረት የሆነውን ትምህርት ለመግዳል ባለው መሠሪ ዓላማ ትውልድ ገዳይ የትምህርት ፖሊሲ በባለሙያዎች ሳይሆን በካድሬዎቹ አማካይነት አንዲቀረጽ በማድረግ ትምህርት ላይ ትልቅ ወንጀል የፈጸመ፣ የአገሪቱን ታሪክ ለማጥፋት ባለው ቁርጠኛ አቋሙ በዩኒቨርሲቲዎች፣ በኮሌጆች፣ በሀለተኛ ፣ በመለስተኛና በአንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የታሪክ ትምህርት እንዳይሰጥ ወይም የውሸት ታሪክ ትምህርት እንዲሰጥ ያደረገና በሕዝቡ ዘንድ ተወዳጅ ከሆኑት ከድርጅት መሪዎች እስክ ግለሰብ ድረስ የገደለና ያስገደለ የማፊያ ቡድን ነው። በነዚህ ታላላቅ አገራዊ ወንጀሎችና ክህደት ነው ወያኔ ጸረ-ኢትዮጵያ፣ ጸረ-ኢትዮጵያዊነትና ጸረ-ሕዝብ ነው የተባለው። ይህን የክህደት ተፈጥሮአዊ ተግባሩን ወያኔ ከስልጣን በሕዝብ ትግል እስከሚወገድ ድረስ ይቀጥላል እንጂ ይተዋል ብሎ መጠበቅ የዋህነት ነው።
ወያኔና ተባበሪ ተላጣፊ ድርጅቶች በስብሰናል የኢትዮጵያ ሕዝብን ይቅርታ እንጠይቃለን ያሉቡት ቃል ውሎ ሳያድር መሰሪው ወያኔ የአስቸኳይ ጊዚያዊ አዋጅ በማወጅ ቅዳሜ መጋቢት 1 ቀን 2010 ዓም በደቡቡ የአገራችን ክፍል በቦረና ዞን በሞያሌ ከተማ የወያኔ አጋአዚ ነፍሰ ገዳይ ጦር ቤት ለቤት በማሳስ፣ በመንገድ ላይ ሰላማዊ እንቅስቃሴ በሚያካሄዱ ዜጎቻችን፣ በቡና ቤት፣ በሻይ ቤቶች ፣ በገበያና በሱቅ ሆነው መደበኛ ስራቸውን ሲያከናውኑ በነበሩ የ7 እና የ10ዓመት ህፃነትን ጨምሮ ከ13 በላይ ዜጎችን አልሞ በመተኮስ በግፍ ሕይወታቸውን አጥፍቷል። በርካቶችንም አቁስሏል።
በዚህ የግፍ ግድያ ወቅት የሙያ አጋራችን የሆነው በ2008 ዓም በኦሮሚያ ክልል በትምህርት ቤቱ ውስጥ ላበረከተው ትልቅ የትምህርት ስራና ላሳያው የሙያ ስነምግባር ሁለተኛ ደረጃ ተሸላሚ ፣ በአካባቢው ሕዝብ፣ በትምህርት ቤቱ ማህበረሰብ ተወዳጅ ፣ የአንድ ልጅ አባት ፣ የ34 ዓመት ጎልማሳ ርዕሳ መምህር የነበረው/የሆነው ታምሩ ነጌሶ በእረፍት ቀኑ ቅዳሜ መጋቢት 1 ቀን 2010 ዓም ጊዜውን ሰውቶ በመዶ ሚጎ ት/ቤት ውስጥ ከተወሰኑ መምህራን ነገር ያደርገው የነበረውን የትምህርት ስራ ጨርሶ ወደ ቤቱ ሲመለስ መንገድ በማቋረጥ እያለ የአግኣዚ ነፍሰ ገዳይ ጦር በሶስት ጥይት ደብድቦ ሕይወቱ እንዲጠፋ አድርጓል።
ይህን የወያኔን የግፍ ግድያና የጅምላ ጭፍጨፋ በመሸሽ ከ60ሺ በላይ ኢትዮጵያውያን ወደ ጎረቤት አገር ኬኒያ ሊሰደዱ በቅተዋል።የወያኔን ዘረኛ ድርጊት የሞያሌ ከተማ ካንቲባ ለመገናኛ ብዙኃን እንደገለጹት ሠራዊቱ የባእድ ጦር እንጂ የኢትዮጵያ አይመስልም ብለዋል። ታዲያ በዚህ ድርጊቱ ወያኔ ኢትዮጵያዊ ነው? ለኢትዮጵያ ሕዝብ የቆመ ነው? ቀደም ሲልም በተለያዩ ቦታዎች ይኖሩ የነበሩ ኢትዮጵያዉያንን ከትውልድ ቄያቸው ክኖሩበት ስፍራ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያንን እንዲፈናቀሉ ያደረገ ፀረ-ሕዝብ ዘረኛ ቡድን ነው። ላለፉት 27 ዓመታት ወያኔ ኢትዮጵያዊ አይደለም የተባለው እነሆ ዛሬ ገሀድ ወጣ። ሰላማዊ ሕዝብ በወያኔ ሠራዊት በጠራራ ጸሐይ በጥይት እየተደበደበ ይገኛል። በስደት የኢትዮጵያ መምህራን ማህበር አባላት አስተባባሪ ኮሚቴ ይህን የወያኔን በቦረና በሞያሌ ከተማ ህዝብ ላይ የፈጸመውን አራማኔያዊ ግድያ፣ በሕዝብ ላይ ያደረሰውን የአካል ማቁሰልና ጉዳት፣ ማፈናቀልን በጥብቅ ያወግዛል፤ ይኮንናል። እንዲሁም በሌሎች ቦታዎች በጎንዳር፣ በወልቂጤ፣ በነቀምት፣ በደምቢዶሎ ---ወ.ዘተ በሚገኙ ኢትዮጵያዉያን ወገኖቻችን ላይ የፈጸመውን ግድያ፣ አስራት፣ የመሬት ቅሚያ፣ የትምህርት ክፍለ ጊዜያት ብክነትን፣የተማሪዎችና የመምህራን እስርን፣ የአካዳሚክ ነፃነት መታጣትን በጥብቅ ይቃወማል። 
በአሁኑ ሰዓት የወያኔ አገዛዝ ከምንጊዜውም በላይ በፖለቲካ ፣ በኢኮኖሚና በማህበራዊ ቀውሶች ውስጥ ተዘፍቆ ይገኛል። የሕዝቡ በወያኔ አልገዛም፣ እምቢ አሻፈረኝ በማለት የጀመረውን ሕዝባዊ ሰላማዊ ትግል፣ ከጊዜ ወደ ጊዜ፣ ከቀን ወደ ቀን እያደገ የመጣበት፣በወያኔና በኢትዮጵያ ሕዝብ መካከል ያለው ቅራኔ ከመክረሩ የተነሳ ሊበጠስ የተቃረበበት ጊዜ ላይ እንገኛለን።
በሌላ በኩል ደግሞ የወያኔ አገዛዝ እንደቀድሞው ሊገዛ ያልቻለበት በሁሉም መስክ በኢትዮጵያውያን ዘንድ ተቀባይነትን ያጣበትና እየተዳከመ የመጣበት ሁኔታ ይስተዋላል። እኩል ባልሆኑ ኃይሎች መካከል የእኩልነት ሁኔታ የተፈጠረበት ክስተት ነው( Equilibrium between unequal forces)። ለስርዓት ለውጥ ነባራዊ ሁኔታዎች የተሟሉበት ነገ ግን ይህን የሕዝቡን ትግል ከዳር ለማድረስ ህሊናዊ ሁኔታዎች ያልተሟሉበት በሂዳትም ክፍተቱን ለመሙላት ትግል እየተካሄደ ያለበት ሁኔታ ላይ ደርሰናል።
የሕዝቡ ጥያቄ ከአካባቢ የውስጥ ጥያቄዎች በመዝለል አገራዊ ቅርዕ እየያዘ የመጣበት ሁኔታ ይታያል።ወያኔ በቃ፣( Down Down Woyane) ወያኔ ይወደም ፣በወያኔ አንገዛም ፣ ሁሉንም ያካተተ የሽግግር መንግስት ይቋቋም ፣ የአዋጅ ጋጋተ የሕዝቡን ትግል አይገታም፣ ስር ነቀል ለውጥ ይደረግ ወያኔ ይወገድ የሚሉ ሕዝባዊ መፈክሮች በስፋት እየተስተጋቡ ይገኛሉ። የቀረው ይህን ወሳኝና ወቅታዊ መፈክሮችን በማንገብ በየአቅጣጫው በሁሉም ስፍራ እየተፋፋመ ያለውን የሕዝቡን እምቢተኝነት የአልገዛም ባይነት እርምጃዎችን ከግብ ለማድረስ ትግሉን ማስተባበርና ማስተሳሰር ነው። ለጋራ ጥያቄ የጋራ ትግል ያስፈልጋል። ስለዚህ በተለያዩ ቦታዎች በተለያዩ ስሞች በግንበር ቀደምተኝነት ትግሉን የሚካያሄዱ ወጣቶች በጋራ-በህብረት እንዲነሱ ማድረግና መርዳት የጊዜው ጥያቄ ነው። አገራችን ኢትዮጵያ የሁላችንም ናት ከወጣቶቹ ጎን ሁላችንም መቆም አለብን። ለወጣቶቹ የቅርብ አጋዥ ኃይል መምህራን ናቸው። መምህራን በ1966ቱ አብዮት ወቅት ከወጣቶች ጎን በመቆም ለለውጡ መወለድ አስተዋጽኦ እንዳደረጉ ሁሉ ዛሬም የትግል ልምዳቸውን በመጠቀም በሰሜን በደቡብ፣ በምስራቅ በምዕራብ እንዲሁም በመሐል አገር እየተቀጣጠለ በወጣቱ ግንባር ቀደምተኝነት የሚካሄደውን ትግል አገር አቀፍ ቅርዕ እንዲይዝ ማስተባበርና ማያያዝ ታሪካዊ ግዴታቸው ነው።መምህራን በሁሉም ቦታ የስራ ማቆም አድማ በማድረግ ትግሉ ይበልጥ ጉልበት እንዲያገኝ የድርሻቸውን እንዲወጡ በስደት የኢትዮጵያ መምህራን ማህበር አባላት አስተባባሪ ኮሚቴ በዚህ ወሳኝ የትግል ወቅት ጥሪውን ያቀርባል።
ሕዝባዊ አመጹ ተፋፍሞ ይቀጥል!!!
የወያኔ ነፍሰ ገዳይ አጋአዚ ጦር ለፍርድ መቅረቡ የማይቀር ነው!!! ለጋራ ጥያቄዎችንን መልስ ለማግኘት የጋራ ትግል ይስፈልጋል!!! 

Sunday, February 4, 2018

ትግላችን መራራ ቢሆንም፣ግብአችን ዕሩቅ አይሆንም!!(ዳዊት ተመስገን,ከኖርዌ )

04 February 2018
እንናገራለን እንጂ አንማታም የ ገር ፍቅር ከሰዎች ፍቅርና ከሰው ሰውኛ ጉዳዮች ይነጥላል እንዴ?የህወሓት አካል የሆኑት የኦህዴድና የብአዴን ሞግዚቶች ስለ ኢትዮጵያ አንድነት ስብከት የ መሩት ትንሽ ሰነባብቷል።ሰውየውከአነጋገሩ ክትነትና ከሚሰጠው ጣዕመ ምስጢር የተነሳ ሲሰሙትና ሲያዳምጡት ቢውሉ ቢያድሩ አይሰለችም
ምክኒያቱም የኢትዮጵያ አንድነት ሲጠራ ደስ ይላል።ነገር ግን ኢትዮጵያን በመጥራት ብቻ ያለ ትግበራ ይሆናል እንዴ?እኔን ግራ የገባኝ ከ27 ዓመት በኃላ የኢትዮጵያ አንድነት የሚለው አባባል ያውም በባህር ዳር ስብሰባ ላይ
ለአማራው ሕዝብ ኢትዮጵያዊነት ሲሰብኩ ለቀባሪው አረዱት አይሆንም ብዬ ነው።
ሐሰትና ስንቅ እያደር ይቀላል እንዳይሆን እሰጋለሁ ወይም ደግሞ ከእሪያ በግ እንደማይወለድ ሁሉ ከሐሰተኛም ሕልምም ቁም ነገር አይገኝም እንዳይሆን።
ጦርነታችሁ ስጋና ደም ሆነው ከሚታዩ ጋር ሳይሆን ከጨለማ ገዢዎች እንጂ እንዳለው የጨለማ ገዢ
ከሆነው ከድንቁርና ከውሸት ጋር ከተላበሰው ከህወሓት ግብግብ ገጥሞ ሲያሸንፉ እኛ ያኔ የዓይን ምስክር መሆን
እንችላለን።የህወሓት የጋሻ ጃግሬ ሆነው እንዲህ ቢሉን ያስገደዳቸው የሕዝብ ሐብቱ አንድነቱ፣የትውልድ ጉልበቱ
ኀብረቱ ስለሆነ ብቻ ነው።በሌላ አነጋገር ህወሓት ሕዝባዊ አመፅ ስለተገደደ እንጂ ምነዋ የአኖሌ ሃውልት ጡት
የተሰራበት ቦታ ሄደው ወይም አንቦ፣ወለጋ፣ትግራይ ላይ ነው የኢትዮጵያ አንድነት መስበክ ያለባቸው ምከኒያቱ
ኢትዮጵያዊነት የተናነቃቸው እዚህ ክልል ላይ እንጂ ኢትዮጵያዊነት ለአማራው አይሰበክም የምለው።
በእኔ በኩል አመንዝራ ካሏት ብትቆርብም አያምኖት ነው በጣም የሚገርመው ኦህዴድና ብአዴን የሚባሉ
የህወሓት ደቀ መዝሙሮች የጎጃምን ሕዝብ በኢትዮጵያዊነት ካላጠመኳችሁ በማለታቸው ምነው ከረፈደ ለማለት
ነው።መቼስ ድሮ በአባቶቻችን ጊዜ እንዲህ ይባል ነበር ባሪያ ሦስቱን ነገሮች ካላወቀ ታዝዞ መኖርን አይችልም
ዕረፍትንም አያገኝም።እነሱም የሚመራውና የሚቃኘው፣ታማኝነት እንደ ቸር ጠባቂ ሆኖ የሚጠብቀው ተግሣጽ
ከመጥፎ ልማድ የሚመልሰው ፍርሃት ናቸው።ባሪያ እየተሰደበ ቢገዛ ይበረታል፣እየተሳደበ ቢገዛ ግን አይበረታም።
ይህ አባባል አሁን አይሰራም እነዚህ የህወሓት ሞግዚቶች ኦህዴድም ሆነ ብአዴን የኦሮሞና የአማራውን ሕዝብ
አይወክሉም።የኢትዮጵያን ትግል ለማኮላሽት በአገዛዙ ከሚጎዱ ሰዎች ይልቅ በአገዛዙ ምክኒያት የሚጠቀሙ ይባዛሉ
ልበል የኢትዮጵያን ሕዝብ ትግል አቅጣጫ ለማሳትና ብሎም ጠላት ወያኔ ትንፋሽ እንዲወስድ የተደረገ አባባል ነው
የምለው።አዳዲስ የትግል ስልቶችን በመ መር ወጣቱ ንቃታቸውና ብቃታቸውን በማቀናበር እንዲሁም በማቀላጠፍ
በተለያየ ስልት ጉድ የሚባልላቸውን ሰዎች በታትኖ ምንም ትግሉ አቅም እንሌለው ሰው እንዲኖሩ የሚያደርግ አንድ
አስቸጋሪና እጅግ የተለመደ ችግር ቢኖር የትኩረት ችግር ነው።እንደምናውቀው እስከ አፍንጫው ድረስ ዘመናዊ
መሣሪያ ታጥቆ የመጣው ጠላት ፋሺስት ኢጣልያ ወራሪ አፈር ግጦ ድል የተመታበትን የዓድዋ ዘመቻን ዘወር ብለን
ብናስተውል የኢትዮጵያ ሕዝብ አንድ አካል አንድ አምሳል ሆነው ጠላትን ድል ማድረጋቸው እንገነዘባለን።ምነው
ቢሉ እምየ ምንሊክ የክተት አዋጅ ባስነገሩበት ጊዜ ሳያመነታ አፈፍ ብሎ የተነሳው ወገን ቀደም ሲል በተለያዩ
ጹሁፎቼ ገልጨዋለሁ።የ ግንነት ባሕርይው በነባራዊነት የደነደነ ስሜቱም ከፍቅረ  ገር ጋር በእጅጉ የላቀ በመሆኑ
ነው።ኢትዮጵያዊ ስሜት ይህ መሆኑ እየታወቀና የገድል ባለቤታቸውንም የማይታበል ሆኖ ሳለ አንዳንድ ጉዳይ
ተሰምቶ እንደማይታወቅ እንግዳ ሊሆንብን አይገባም።በእኛ በአሁኑ ጊዜ የሚያሳዝነው በአጭሩ የወደፊት
ተመልካችነት ሊኖረን አልቻለም።
ስለዚህ ዘወትር ከራሳችን ይልቅ ወደኃላ ተመልካችና አወዳሽ ነን እዚህ ላይ ልትገነዘቡልኝ የምፈልገው ለትግሉ
መስዋዕት የሆኑትን ወይም ኢትዮጵያ  ገራችንን ላቆዮልን አባቶቻችንን ለማለት ፈልጌ አይደለም የወደፊቱን በጉጉት
የምንመለከት የወደፊቱ ብርሃን እንዳይጠፋ የምንባዝን የምንደክም አይደለንም።በትክክል በኢትዮጵያ ሕዝብ
ሳይመረጡ ነገር ግን ህወሓት በሞግዚትነት የሰየማቸው የኢትዮጵያ አንድነት በማለታቸው በጣም ደስ ያሰኛል።
እውን ጥላቻን አስወግዶ ከሞግዚትነት ወደ ኢትዮጵያዊነት መጣን ሲሉ እነዚህ ወንበዴዎች ደስ የሚያሰኝ ቢሆንም
ነገር ግን በግማሽ እውነታን ይዞ ኢትዮጵያዊ ነኝ ማለት አይቻልም።ህወሓት በበኩሉ ሁሉም በየዘሩ ከረጢት
እየተፈላለገ እንዲቋጠር ያልማሰው ስር ያልነቀለው ድንጋይ የለም።ከህወሓት ጋር ተቀናጅቶ የሚኖር በየወቅቱ
እየተበረዘና እየተንጋደዱ ቃላትና ንዑስ ሐረጎችን እውነተኛ ትርጉም በማስመሰል የሚንቀሳቀሱትን በሚገባ መረዳት
ያለብን ይመስለኛል።በኢትዮጵያዊው ዜጋ ደምና አጥንት የተገነባውን አንድነትና ተዋሕዶ የተዛመደውን ነጥሎ
ለማውጣት የማይቻለውን የተፈጥሮ  ግንነት ለማደስና ስርዓት ለማስያዝ የተሠራ መሆኑን ለመገመት አያዳግትም።
እንዳለመታደል ሆኖ ነው እንጂ በእርግጥም ሲያስቡትም ዛሬም ቢሆን ነገ እስከ መጭረሻውም ድረስ አትንኩኝ
ባይነት ከኢትዮጵያዊነት ባሕርይ ሊነጠል አይችልም።ብሎም ቢሆን ዘመን እየተቆጠረ ዘመን ሲተካ ይህ ኩሩነትና
 ገር ወዳድነት ባሕርይ ከነባራዊነቱ ፈቀቅ በማለት እንዳያውክ አሁንም ወጣቱ ትውልድ ያባቶቹን  ግንነት
እንዲወርስ ማድረጉ አማራጭ የሌለው ተግባር ነው።በኢትዮጵያ ውስጥ በግፍ በጥይት ተደብድበው የወደቁ
ብዙዎች ናቸው፣ነገር ግን በነገረ ሠሪ አንደበት እንደጠፉት ባይሆንም ቅኑ።
ሰዎች ከሚወቅሳቸው ዳኞች ይልቅ የገዛ ህሊናቸው እየወቀሰ የሚያሰቃያቸው እጅግ ብዙ ቢኖሩም።የእውነተኛ
ተግባር ምንጩ ኢትዮጵያዊ ማንነት ነው ስለዚህም የምናደርጋቸው ነገሮች እንደየ ሰው ሁኔታ የሚለዋወጡ ከሆነ
እነዚህ የምናደርጋቸው ነገሮች ከእውነተኛነት የመነጩ ሳይሆኑ ከጥቅም ከፍርሃት ወይም ከተለያየ የራስ ወዳድነት
አመለካከቶች የመነጩ እንደሆኑ ጠቋሚ ነው።አክባሪ ኢትዮጵያዊ ማንነት ያለው ሰው የዘርን የሃብትን የዕውቀትንና
የመሳሰሉትን ሁኔታዎች ሳያይ ሁሉንም እኩል ያከብራል።እንቅስቃሴ የሌለው የሌሊት ህልም ቅዠት ነው።እርምጃ
የማይወሰድበት የቀን ህልም ደግሞ ድንዛዜ ነው።እውነቱ ይህ ነው አንድ ሰዉ ከእንቅልፉ ሲነቃ ይህንና ያንን
አለምሁ ካለ በኃላ ሌላ ህልም ለማለም ተመልሶ የሚተኛ ከሆነ ከቅዠት ያለፈ ኑሮ የለውም።እንዲሁም አንድ ሰው
ቀን ቁጭ ብሎ በአይነ ህሊናው እየበረረ ይህንና ያንን ሊያደርግ ራሱን የማየት ልማድ ቢኖረውና ይህ ውስጡ
የሚጓጓለት ነገር በወረቀት ሊጽፍ እቅድ ሊያወጣለትና ከአንድ ደረጃ ወደሌላኛው ደረጃ የማይንቀሳቀስ ካልሆነ ይህ
ሰው ከድንዛዜ አያልፍም።አንድ ነገር ወደ ጋሃዱ ዓለም ከመምጣቱ በፊት በመ መሪያ በጽንሱ ሃሳብ ግን ሊጨበጥና
ሊደረስበት የሚችለው ሲታቀድበትና ስንንቀሳቀስበት መሆኑን አንዘንጋ ከማንም ያልተበደርከውን አንድን በውስጥህ
የበቀለ ጽኑ ፍላጎት ለይተህ እወቀው ከዚያም ፍላጎት አንጻር እቅድን በማውጣት የመ መሪያውን እርምጃ ተራመድ
ብዙ ሳትቆይ ሁኔታህ ሲለወጥ ማየትህ የማይቀር ነው።
በአሁኑ ሰዓት ብዙዎች ስልጣን ላይ ያሉ መዝባሪዎች ዘላቂ የኢትዮጵያን ጥቅም ፋላጊ እንጂ፣ዘላቂ የኢትዮጵያ
ወዳጅ አይደሉም።ለአማራው ምንታዌ እንደማይጠቅመው ያውቃል ኢትዮጵያ አንድነት እንጂ የኢትዮጵያዊ
ምስጢር በአንድነት ገላጭነት ካልታወቀ በስተቀር መረዳት አይቻልም።የስልጣንና የገንዘብ ሌላው አዕይንተ
አዕምሮቸውን በስግብግብነት መንጦላት ጋርዶ፣ዕዝነ ልቡናቸውን በአልጠገብ ባይነት ቡሽ ደፍኖ፣እግሮቻቸውን
በምኞት ፈረስ ከኢትዮጵያዊነት አንድነት ለይተዉ ለወያኔ ተገዥነት እራሳቸዉን አሳልፈዉ ሰጥተው ኢትዮጵያዊነት
ሲሉን እንዴት ነው በእኛ ውስጥ ታአማኒነት ሊኖራቸው የሚችለው።ስልጣንና ገንዘብን መውደድ የክፋት ሁሉ ስር
ነው የሚለው ቃል ተቀይሮ ስልጣንና ገንዘብ የደም ስር ነው በሚለው ብሂል ከተተካ ውሎ አድሯል።ዛሬ በ ገራችን
ኢትዮጵያ ከስልጣንና ገንዘብ ከመውደድ የተነሳ ነፍስ ሲጠፋ፣እውነት ተደብቆ ሐሰት ሲነግሥ ማየት አዲስ ነገር
አይደለም።የስልጣንና የገንዘብ ፍቅር ያነሆለለው ሰው ስለ ኢትዮጵያዊ አንድነት ነገር የሚያስብበት ጊዜ አለው ብዬ
እምነት የለኝም።የድሮ አባቶቻችን ሁለመናቸውን ለሕዝብ ክብርና ለ ገር ፍቅር ሰጥተው የሕዝብን እሮሮ
አድማጭና ተግባሪ የሆኑ መሪዎች የበቀለባት በኢትዮዽያ የታሪክ ገጾች ላይ ሰፍሮ ይገኛሉ።
የኢትዮጵያን ሕዝብን እስከ መቼ ማታለል ይቻላል ኦህዴድና ብአዴን የህወሓት ሞግዚቶች ናቸው እንጂ ምንም
ሊያመጡ አይችሉም።ከሞግዚትነት ወደ ኢትዮጵያዊነት ለመምጣት ማሰባቸው ባይከፋም ነገር ግን እነሱ
እራሳቸውን ከህወሓት አግልለው ከኢትዮጵያ ሕዝብ ጎራ ሆነው አረንጓዴ፣ቢጫ፣ቀይ ሰንደቅ ባንዲራችንን ለብሰው
እስካልቆሙ ድረስ የሕዝባዊ አመጹን ለማዳከም የሚያደርጉት ሴራ ጉዞአችን መራራ ግብአችንን ዕሩቅ
አያደርገውም።ሮበርት ሙጋቤ ጊዜ ነው እንጂ ቁም ነገራም፣ኖርኩኝስ ማለት አያኮራም ሲል አልሰሙትም
እንዴ።ማንም የህወሓት አሽከር እንዲህ ነው እንዲያ ነው ሲለን ለውጥ ይመጣል ብለን ካሰብን ማስተዋል ተስኖናል
ማለት ነው።ውኃ ተመልሶ ወደ ኃላው ቢሄድ(ቢፈስ) ዎፎች አለ ክንፍ ቢበሩ፣ቁራ እንደበረዶ ቢነጣ ህወሓት አዋቂ
ሊሆን እንደማይችል ጠማማነቱን ቢተው ነብር ዥንጉርጉርነቱን ቢለቅ ህወሓት ክፋታቸውን አይተውም።ስለዚህ
ማስተዋል እኮ የራቀውን ለማቅረብ የቀረበውን ለማራቅ የሚያገለግል የልብ መነጽር ነው።ይህ ትግል ፋና ወጊ በሆነ
ስር የሰደደ ተሞክሮና ለ27 ዓመት በኢትዮጵያ ሕዝብ በደረሰባቸው ስቃይ የተቀሰቀሰ በሕይወት የመኖር መብት
ብሎም የወያኔ ግባተ መሬት የስርዓት ለውጥ ትግል ነው።
የወያኔ አምባገነን አገዛዝ በኢትዮጵያ ሕዝብ ትግል ይወገዳል!!

Monday, November 27, 2017

ለመጪው ትውልድ አይለጉት ሐኬት---- ዴሞክራሲያ

ዴሞ ቅጽ 43 ቁ 1

መስከረም/ጥቅምት 2010 ዓ.ም
ለመጪው ትውልድ አይለጉት ሐኬት
ታሪክ ራሱን ይደግማል ተብሏል። ሲደግም ግን መቸም ቢሆን ያለፈው መቶ በመቶ ቅጂ እንደማይሆንም እንዲሁ ተነግሯል። የኅብረተሰብ ዕድገት ሕግ የሁኔታዎችን ለውጥ ግድ የሚል ነውና ታሪክ መመሳሰሉ አንድ ነው የሚያስብል አይደለም ።የአንድ ሀገር ሁኔታም ከሌላው ተወራራሽና ተመሳሳይ--ወይም አንድ ወጥ- ሊሆን እንደማይችልም የታወቀ ነው። የጅምላ ድምዳሜ ወደ ስህተት ሊያመራ የሚችል መሆኑን መገንዘብ የሚገባው ለዚህ ነው። ለዚህም ነው የየካቲትን አብዮት መደናቀፍ ካለፉ መፈንቅሎች ጋር ለማመሳሰል ሆነ በግፍና አምባገነንነት፤በአረመኔነትንና በፋሺስትነት ያላቸው መመሳሰል እንዳለ ሆኖ የወያኔን የስልጣን ንጥቂያ ከ 66ኡ የሻለቆች አብዮትን ማጅራት ምት ጋር አንድ ማድረጉ የማይቻለው።
የየካቲት አብዮት ጽኑ መሠረትና ምክንያት ይዞ የፈነዳ ቢሆንም ግቡን ስላልመታ ከሚቀርቡት አሉታዊ ትችቶች አንዱ ጊዜው አልነበረም የሚል ነበር ። ዛሬም የወያኔ አገዛዝ በሞት አፋፉ ላይ ደርሶ ባለበት ሁኔታ ለመተካት የተዘጋጀ ኃይል የለምና ውድቀቱ ወቅታዊና ጠቃሚ አይሆንም የሚሉ ብቅ ብቅ እያሉ ነው ። በቅድሚያ ማጤን ያለብን አቢይ ጉዳይ አብዮት ወይም ስር ነቀል ለውጥ ወይም የሥዓአት ቅየራ የሚመጣው በማንም ውሳኔ ሳይሆን ባለው ተጨባጭ ሁኔታ መሠረት ሕዝብ በሚያደርገው ትግል ወይም አመጽ ነው። ትግል ወይም የአብዮት ፍንዳታ አልተዘጋጀንምና ቆይ ተብሎ ሊታገድ የሚችል አይደለም ። በውስጥ ውስጥም ሆነ በብቅ ጥልቅ ለዓመታት ሲግም ሲያስገመግም የቆየውን የአብዮት ፍንዳታ በሚያጎመራ ጊዜ ግብታዊ የሚል የተሳሳተ ቅጽል መስጠት የተለመደ ቢሆንም የአብዮት ፍንዳታ--የሕዝብ አመጽ ወቅቱን ጠብቆ የሚመጣ ነው ። ለምሳሌ በቦልሼቪክ ፓርቲ መሪነት የተካሄደው ታላቁ የሩስያ አብዮት ከመፈንዳቱ ስድስት ወር በፊት ሌኒን ራሱ ሁናቴዎች ገና ናቸውና ብዙ መስራት አለብን ያለው ሊጠቀስ የሚችል ሲሆን አብዮትን የሚጠብቁትም ቢሆን መቸ እንደሚፈነዳ አያውቁም የሚለውን አስተሳሰብ ትክክለኛነት የሚያረጋግጥ ይሆናል። የየካቲት አብዮት ሲፈነዳ የህቡዕ እንቅስቃሴ በማድረግና ድርጅቱን በመገንባት ተግባር ተጠምዶ የነበረው ኢሕአፓ ገና ሁለት ዓመቱ ነበር ። በወቅቱ በተቻለው መጠን ትግሉን ሊያጠናክርና አቅጣጫ ሊያስይዝ ቢሞክርም የደርግን መፈንቅለ መንግሥት ሊያግድም ሆነ የድል ቅሚያውንም ሊያስቆምና ሊያከሽፍ አልቻለም ። ሆኖም የሕዝብ ጥያቄዎች መሠረታዊ ነበሩና፤ በወቅቱ ምላሽም ያገኙ አልነበሩምና ጸረ ደርጉን ትግል በስፋት በማካሄድና ትግሉን በመቀጠል ታሪካዊ ምዕራፎችን ጽፏል ። በቅድሚያ በመሠረቱ እስካዛሬም ምላሽ ያጣው የሕዝብ ጥያቄ ዴሞክራሲ ለሰፊው ሕዝብ አለገደብ የሚል ነበርና የደርግ ሕገ ወጥ ሥልጣን ይህንን መሠረታዊ ፍላጎት ተጻሮ የቆመ ሆነ ። ደርግ ዴሞክራሲን ማፈን ብቻ ሳይሆን ያሰበና ያሳሰበ ወንጀለኛ ነው ብሎ አፋኝ አዋጆችን አዥጎድጉዶ የግፍ አገዛዙን
ጀመረ ። በዚህም የተባበሩት ሁሉ ወደዱም ጠሉም --ዛሬ ለወያኔ ተባባሪዎች እንድምንላቸው ሁሉ--የወንጀሉ ተባባሪ ሆነው አልፈዋል ። ቀጥሎ የተከሰተውን ሁሉም የሚያውቀው ነው።
የየካቲት አብዮት ለምን ፈነዳ ? አብዮት በዘፈቀደና በአልባሌ ምክንያቶች የሚፈነዳ አይደለም ። ታምቆ ቢቆይም፤ ውስጥ ውስጡን እንደ እሳተ ገሞራ ቢያጉረመርም አብዮት የቆዩና መሠረታዊ የሕዝብ ቅራኔዎች ነጸብራቅና ፍንዳታ ነው። ፍናዳታው እውን ይሆን ዘንድ ሕዝብ አልገዛም በቃ ብሎ መነሳት አለበት። ገዢው መደብም እንደበፊቱ እንዳፈተተው ተንደላቆ የሚገዛበት ሁኔታ መዳከም ይገባዋል ። ሕዝብም በተወሰነ ደረጃ ለማመጽ ድፍረትን ኅብረትን ማግኘት ይኖርበታል ። እነዚህ ሁኔታዎች ሲሟሉና አብዩት ሲፈነዳ ለድል አስፈላጊ ሆኖ የሚገኘው የድርጅትና የኅብረቱ ጥያቄ ይሆናል። በየካቲት 66 ይህን ሁኔታ ከማሟላት አኳያ ግልጽ ድክመትና ጉድለት ነበርና ደርግ የተባለው የታጠቀ አድሃሪ ቡድን የሕዝብ ድል ሊቀማ ቻለ ። የቻይናም፤የሩስያም፤ የካቲትም ሁሉ አለጊዜያቸው የመጡ አብዮቶች ተብለዋል ። አብዮትን ማቆየትና ማስወገድም የሚቻለው በሥልጣን ያለው ሥርዓት መሠረታዊ ለውጥ ካደረገ ብቻ ነው ። አድሃሪ አገዛዞች ይህን ማድረግ ካልቻሉ አብዮት አየቀሬ ነው። አጼ ኃይለሥላሴ የለውጥን አስፈላጊነት ሊረዱ ባለመቻላቸው፤ መሠረታዊ ለውጥ ለማካሄድ ፈቃደኛ ሊሆኑ ባለመቻላቸው፤ ለመጣው አመጽ ማብረጃና ማስተንፈሻ የሚሆን ባለማቅረባቸው አብዮቱ ፈነዳባቸው ። መሬት ለአራሹ፤ ሕዝባዊ መንግስት፤ዴሞክራሲ አለገደብ ለጭቁኖች፤ ሉአላዊነት ለኢትዮጵያ፤ እኩልነት በሁሉም መስክና ፍትሐዊ አስተዳደር የሚሉትሕዝባዊ ጥያቄዎች--እንኳን ያኔም ዛሬም ቢሆን መፍትሔ ያገኙ አይደሉምና-- በዚህ የተነሳ አብዮት መፈንዳቱ ጊዜውና ወቅቱ ነበር ። ያን ትውልድ አብዮት አመጣብን ብለው የሚያወግዙትና የሚያላዝኑበት አንድም የወዳቂው ሥርዓት ተጠቃሚዎችና አዳናቂዎች ሲሆኑ በሌላም በኩል የለውጥ ተጻራሪዎች መሆናቸው ከወዲያው ታውቆ የተወገዙበት ነው ። ያን ሥርዓት እየጎዱትና ለውድቀት የዳረጉት ራሳቸው የሥርዓቱ ባለቤቶች ናቸው ። ወቅቱ የጠየቀውን ለውጥ ቢያደርጉ ኖሮ ሂደቱ ሌላ በሆነ ነበር ። የተቃዋሚዎቹ መፈክሮች ምላሽ አግኝተው አቀጣጣይነታቸውና አብዮት ቀስቃሽነታቸውም ባለተከሰተ ነበር ማለትም እንችላለን ።ለአንገብጋቢ የሕዝብ ጥያቄዎች ምላሽ ሰጠተው በነበር የየካቲት አብዮት ባልመጣባቸው ነበርም ማለት እንችላለን።
የየካቲት አብዮት ሊከሰት የቻለባቸውና በኋላ የአብዮቱ መፈክሮቹ የሆኑት ዋና ዋና ጥያቄዎች ዛሬም ምላሽ ያላገኙ ጉዳዮች ናቸው ። አብዮቱን ካቀጣጠሉት ዋና ዋና ጥያቄዎች መከካል መሬት ለአራሹ፤ ዴምክራሲ ለጭቁኑ፤ ሉዓላዊነት ለኢትዮጵያ፤ ሕዝባዊ መንግስት ወዘት የሚሉት ይገኙባቸዋል። ምላሽ ባለማግኘታቸው ትግሉ ቀጠለ ። እስከዛሬ። እነዚህ መፈክሮችና ጥያቄዎች ደግሞ የሕዝብ ብሶት አንጽባራቂ ነበሩና፤ ችላ ተብለው ከርመው ቆይተዋልና በነበረው ተጨባጭ ሁኔ ታ ሕዝብ በቃኝ ብሎ ምላሽ ሊጠይቅ ሲነሳ--አብዮት ሲፈነዳ-- ገዢው ቡድን ወራጅ አለ ተብሎ ሊጨብጠው ሊይዘው ተስኖት ሲወጠር እውን የሆነው እውነታ ተጨባጩ ሁኔታ ያመጣው እንጂ የተወሰኑ ተራማጅ ወጣቶች ከብብታችው ስበው ያወጡት ክስተት አልነበረም ። ያ ትውልድ የተበላሹ ገዢዎችና ሥርዓቶች ያመጡትን ሀገራዊ ችግር ተጋፍጦ ለችግሮቹ መፍትሔ ለመሰጠት ጥረት አደረገ እንጂ ያልነበረን ችግር ፈጥሮ ሊያሰፍን አልተንቀሳቀሰም ። ለምንስ ማለቱ ቦታው ነው ። ምን ሊጠቀም? ምን ሊፈይድ ? ለተረከበው ችግር መፍትሔ ለማግኘት ሲነሳ ስህተት ፈጸመ በሚል ሊወቀስ ቢችልም የችግሩ ፈጣሪ ግን ከቶም የሚሆን አይደለም ። የኢትዮጵያን ተጨባጭ ሁኔታ በተመለከተ ምን መደረግ ነበረበት ለሚለው ወሳኝ ጥያቄ ምላሽ ሊሰጥ የጣረው ትውልድ ሊወቀስ ሳይሆን ሊመሰገን የሚገባው ሲሆን ለአቅዋሙ ደሙን ያፈሰሰ በመሆኑ ማንም--በተለይም ሀገርን ለመታደግ ትንሿን ጣቱንም ያላንቀሳቀሰው--ሊወቅሰው ሊያወግዘው የሚችልበት የሞራል የበላይነት የለውም ። ለማንኛውም
ሀገር ገንቢ መንገድን የቀየሰው ትውልድ ዕድል ተነፍጎት፤ ታፍኖና ተጨፍጭፎ በመገኘቱ ለሀገራችን የነበረው ብሩህ ተስፋ ከስሞ ደርግ የተባለው መርገም በሀገራችን ላይ ሰፍኖ-- ከርሞብን፤ ለወያኔ ጨለማ አሳልፎም ሰጥቶናል፤ዳርጎናል ። በዚህ ረገድ ወያኔ የደርግ ውላጅ ነው ማለቱ አከራካሪም የሚሆን አይደለም።
ይህን በተመለከተ የሐምሌ 2001 ዴሞክራሲያ (ቅጽ 34 ቁጥር 39) የሚከተለውን አስፍሮ እንደነበር መጥቀስ እንፈልጋለን፣
" የስድሳ ስድስቱ የኢትዮጵያዊ አብዮታዊ ትውልድ በብሔርም ሆነ በሃይማኖት ሳይከፋፈል ባንድ ላይ ተባብሮ የቆመው ለሀገሩና ለዜጎቿ መልካምን በማሰብ ነበር። ለዚህም አይከፍሉ መስዋዕትነት ከፍሏል ። ያ ሁሉ እንደ ቅጠል የረገፈው ምሁርና ወጣት ለሀገሩ የነበረው ራዕይ በብሩህ ተስፋ፤ በሀገር አንድነትና በሕዝብ እኩልነት ላይ የተመሠረተ ነበር ። ታዲያ ከደርግ ባለስልጣኖችና ጀሌዎች ይህንን ለኢትዮጵያ ብሩህ ተስፋ አንግቦ የቆመውን አዲስ ትውልድ እየጨፈጨፉ ኢትዮጵያን ለመከፋፈልና ለመቆራረስ ዓላማ አድርጎ የተነሳውን ጠባብ ብሔረተኛ ድርጅት ሰተት ብሎ አዲስ አበባ በመግባት ዓላማውን በተግባር እንዲተረጉም ዕድል ሰጡት ። ወደዱም ጠሉት በተጨባጭ ተባበሩት ። በአሁኑ ወቅት አንዳንድ የመረጃ ሰነዶች እንደሚመሰክሩት ሕሊናቸውን በመሸጥ ከወያኔ ጋር ተባብረው የውስጥ መረጃ በማቀበል አሳፋሪ ድርጊት የፈጸሙት የደርግ ባለሥልጣናት ቁጥራቸው ጥቂት አይደለም። እነኚህ ደግሞ ለሀገር የቆመውን ኃይል በማጥፋት ብቻ ሳይወሰኑ ተተኪውን ትውልድም ጭምር እያወደሙ፤ኢትዮጵያን ለአውዳሚ ተምች አሳልፈው አስረክበዋል ። ይኽም ደግሞ ከጠፉም በኋላ የጥፋታቸው ጠንቅ እንዲቀጥል ሆኗል ። የኢትዮጵያን ጉዳይ የኋላ ልጅ ይጨነቅበት እንዳይሉ እንኳ የኋላ ልጅ እንዲተርፍ አላደረጉም ። መጪው ትውልድ በጠፋበት ኃላፊነት ይሰጠው ቢባል እንኳን የሚለጋለት ሀኬት ሊኖር አይችልም--አልቋልና ። ለአንድ ህገር ከሚወረሱት ውርሶች መካከል የኋላ ልጅ ይጨነቅበት የሚባለው ነገር፤ሀገር እንደ ሀገር ለመቀጠል እንዳትችል የሚደረግ ጠላትነት ነው ። በግድ ኢትዮጵያ ሀገራችን የነገን ተረካቢ ትውልድ እንድትፈጥር ዕድል ሊሰጣት ይገባል"።
ደርግ ተብዬው ይህን ዕድል አልሰጣትም--ወያኔ ለሚባል በሽታ ዳረጋት እንጂ ። በየካቲቱ ትውልድና በአብዮቱ ላይ ሊጨፍሩ የተነሱ የወያኔ አጋሮችና የደርግ የወንጀል ተካፋዮዎች አብዮቱ ያነሳው ጥያቄ ሁሉ ከመስመር ውጪ ነው ወይም በደፈናው የሆነ ርዕዮተ ዓለም ጭፍን ነጸብራቅ ነው ሊሉ እስካዛሬ አልተቻላቸውም ። ፊውዳሊዚም ይውደም፤ መሬትም ለአራሹ ይሁን መባሉ አግባብ አልነበረም ካላሉ በስተቀር ። የዘውድ አገዛዝ ተገርስሶ ሕዝብ የዴምክራሲ ባለቤት መሆኑ ሐጢያት ነው ለማለት ካልደፈሩ በቀር ። የእኩልነት ጥያቄ ሲነሳም በየዘርፉ ጭቆና መኖሩን በወቅቱ የነበረው ተጨባጭ ሁኔታ በሀቅ የሚመሰክር ሲሆን ይህንን መካድ የሕዝብን መብትና ፍላጎት መጻረር ካልሆነ በስተቀር ሌላ ትርጉም አልነበረውም ። የሀገራችንም ሉዓላዊነት ይከበር የሚለው ጥያቄ ያኔም ዛሬም እንደሌሎቹ ጥያቄዎች ሁሉ ምላሽ አጥቶ የሀገራችንን ችግሮች ገላጭ ሆኖ ይገኛል ። እናም የካቲት ጊዜውን የጠበቀ አብዮት ነበረ ። ያ ትውልድም ግዳጁን ተሸክሞ ከፍተኛ ዋጋን ከፍሎ ሀገሩን ሊታደግና አብዮቱንም ሊያስከብር መነሳቱና አልፎም የህይወት መስዋእትነት መክፈሉ የሚደነቅ እንጂ የያኔ ፈርጣጮችና የወንጀል ተባባሪዎች ዛሪ እንደሚጥሩት የሚወቀስ ከቶም አልነበረም፤አይደለምም ። የየካቲት አብዮት የሕዝብና የሀገርን አንድነት መሠረት አድርጎ የፈነዳና የተካሄደ ነው ። ቀን ሲደርስ አምባ ይፈርስ ነው ። በሁኔታው ሂደት የሕዝብ ኃይሎች ተጠናክረው አብዮቱን ሊጠብቁ ባልመቻላቸውና ድል በመቀመታቸው ዛሬም በተስፋ ቆራጭነት በመጠቃት ድል እንቀማለን ብሎ ሙሾ ከወዲሁ ከመደርደር ድላችንን የማንቀማበትን ቅድመ ሁኔታ ጸንቶ ማዘጋጀት እንዳለብን ታሪክም ያስተምረናል ።
ለማንኛውም የታሪክ ግዳጁን ተቀብሎ ውድ ህይወቱን ለሀገሩ የሰጠውን ትውልድ እንደ አርአያ በመቀበል ፈንታ ወደ 40 ዓመት ታሪክ ተመልሶ --ያውም የተከለሰን ታሪክ በማቀንቀን- ያውም ያንን ትግል የሚያስንቅ ምንም ዓይነት ግብግብ ሳይታይ- - ወቀሳና ውግዘት መደርደር የሚያስገምት እንጂ ሌላ ትርጉም የለውም ። ከዚህ ባሻገር ደግሞ ጊዜ የሰጠው ቅል በመሆን የኋላ መብራትን ቦግ አድርጎ እንዲህ ቢሆን ኖር ፤ ይህ ቢደረግ ኖሮ ዓይነት ግምገማ ጥሩና ትክክለኛ ግንዛቤን የሚሰጥ አይደለም ። መንግስቱም መለስም ጭራሽ ባይወለዱ ኖሮስ እንዳይከተል!
በየካቲት 1966 የአብዮቱ ፍንዳታ ይጠብቁት የነበሩትን ሳይቀር ድንገተኛ ግብታዊ ስለሆነባቸው በዚያ ወቅት ኢሕአፓ በበቂ ተደራጅቶ፤ተመክሮ አካብቶ፤ ተዘጋጅቶ የተገኘ ባለመሆኑ አብዮቱን ማጅራት መትተው ጥቂት ምርጥ መኮንኖች-- ራሳቸውን ደርግ ብለው ሰይመው በኃይል የሕዝብን ድል ሊነጥቁና በሥልጣን ሊሰየሙ ችለዋል ። ኢሕአፓ አብዮቱ ሞግዚት አያሻውምና ሁሉን የሚያሳታፍ ጊዜያው ሕዝባዊ መንግሥት ይመሥረት በሚል ሕዝብን አደራጅቶ ታሪክ የመዘገበውን ትግል አካሂዷል ። ይህን የዴሞክራሲያዊ ሽግግር አማራጭ ደርግና የምሁር አጋሮቹ እምቢኝ ብለው ባይጥሉትና በድርጅቱም ላይ አፈና ለማካሄድ ባይወስኑ ኖሮ የታሪክ ሂደት ሌላ ሊሆን እንደሚችል ማንም ሊከራከር አይችልም ። ሁሉን አቀፍ መፍትሔ መመረጡ ሥልጣን በተወሰነ ቡድን እጅ ገብታ የጭቆና ሥርዓት በአዲስ መልክ እንዳይቀጥል እንደነበረም የተገለጸ ነበር ። ይህ አማራጭ በመጣሉ ደርግ ራሱን የአብዮቱ ጠባቂና ሞግዚት ብሎ ሰይሞ ሙሉ ሥልጣንንም በእጁ ለማስገባት ወደ ደም ማፍሰስ ተሸጋገረ ።ያስከተለውን አስከፊ ሁኔታ ታሪክ መዝግቦታል ። በሽግግሩ ዕቅድ ኢሕአፓ ያኔ ተሓህት ይባል የነበረውን ወያኔ፤ ኦነግን፤ልዩ ልዩ ቡድኖችና የሕዝብ ማኅበራትን፤ወታደሮችና መኮንኖችን፤ታዋቂ ግለሰቦችን ወዘተ ባካተተ መልኩ አማራጩን ማቅረቡም የሚታወስ ነው ። ዛሬም ወቅታዊ ሁኔታው ይህን አማራጭ ግድ የሚለው ወያኔና ሕዝብ ተፋጠው ባሉበት፤ወያኔ ዘረኝነትንና የርስ በርስ ግጭትን አስፋፍቶ ባለበት፤ አሁንም ወታደሩና የጸጥታው ክፍል በወያኔ ቁጥጥር ስር ባለበትና ጦሩ ወደ ሕዝብ ጎራ ባልገባበት ሁኔታ ተቃዋሚ ኃይሎች ተባብረው ከፍተኛ ብስለትና ጥበብን በማሳየት በወሳኝነት በሚካሄደው ግብግብ በአሸናፊነት መውጣት ይጠበቅባቸዋል ።
ከ 15 ዓመት በፊት የነበረውን ሐቅ ስናቀርብ የጻፍነው ዛሬ ለዛሬም የሚሰራና መሠረት ያለው ሆኖ እናገኘዋለን ፤ "የተቃዋሚ ሃይሎች ኅብረት ቀዳማይ ተግባር ለሽግግር ወቅት የሚያስፈልጉትን ዝግጅቶች ማሟላትና ለአጭር፤ ለመካከለኛ ለሩቅ ጊዜ የሚሆኑ አጀንዳዎችን መንደፍ ይሆናል። ይህንንም ለማድረግ የኅሊናም ይሁን ነባራዊ ሁኔታዎች ዛሬ በሀገሪቷ ተሟልተው ይገኛሉ ማለት ይቻላል ። ዘረኛ የወያኔ ቡድን እየተፍረከረከ ይገኛል። "
በሚል የሀገራችንን አስከፊ ሁኔታና የወያኔን ግፍ ከዘረዘረ በኋላ መሠረታዊ ና የሚያመረቃ ለውጥ ለማምጣትም ዋስትናው የሽግግር መንግሥት ነው ሲልም ደምድሞ ነበር ።ዛሬም የተለየ መፍትሔና አካሄድ ሊኖር አይገባንም ማለት ነው። ቀድሞ የነበሩትን ችግሮች ለመፍታት የታቀዱት ሁሉ በሥራ ባለመዋላቸው ጭቆናና ቀውስ፤ችግርና ግፍ ኑሮአችንን አጅበው ቆይተዋል ። የነበረውን የእኩልነት አለመኖር ችግር በፌዴራላዊ አወቃቀርና በዴሞክራሲና እኩልነት ለመፍታት የታለመውን እቅድ ወያኔ ወደ ጎን አድርጎት በትግሬ የበላይነት በተለጣፊ ቅፍቀፋ እና በአንቀጽ 39ኝ ግንጠላና ጠባብነት ተክቶ አበለሻሸው ። ለዚህም ነው በዚህ ጥያቄ ዙሪያ ጽንፍ የያዙትን በዴሞክራሲና በኢትዮጵያ አንድነትን በማይንድ አወቃቀር ዙሪያ አብረን መሰለፍ

እንችላለን የምንላችው ። መሬት ለአራሹ ዛሬም ምላሽን የሚጠብቅ ጉዳይ ሆኗል ። የሠርቶ አደሩ ሕዝብ መብት ተረግጧል፤ የሃይማኖት እኩልነትና የአማኞች መብትም ተደፍሯል፤የፖለቲካ እስረኞች ቁጥር ብዙ ብዙ ሺ ነው። ሕዝብ ተበዝብዞ ለረሃብና ለስቃይ ተዳርጓል... ወዘተ። ባጠቃላይም የየካቲት ጥያቄዎች እንኳን መፍትሔ ሊያገኙ ቀርቶ በየዘርፉ ተባብሰው፤ ሕዝባችንም አንዱ አምባገንን ሲሄድ የከፋውና የባሰው እየመጣበት ከዛሬውስ የትላንቱ ይሻላል ወደሚል አሳዛኝ ድምዳሜና ምጸት እየተዳረገ ይገኛል።
በአንክሮና አንገብጋቢነት የሚቀርበው የኅብረት ጉዳይ ባሉት ውስብስብ ችግሮች የተነሳ አሁንም አስፈላጊና ወሳኝ ሆኖ የሚገኝ ነው ። በደርግ ውድቀት ዋዜማ የኅብረትን ችግር ምላሽ ለመስጠት በመካከላቸው ከፍተኛ የሆነ ጠብና ግጭት የነበራቸው ቡድኖችና ድርጅቶች ሳይቀሩ ሁሉም ኅብረት ሊመሰርቱ ሲዋደቁ ወያኔ፤ሻዕቢያና ለነሱ ያደሩ ምሁሮች እንቅፋት ሆነው የኅብረት ምስረታውን ለማደናቀፍ መጣራቸው ታሪክ የመዘገበው ነው ። ኢዴኅቅ ዘግይቶ ሲቋቋምም ከመቅጽበት ወያኔም አሜሪካም ሊያፈርሱት መነሳታቸው የሚታወቅ ሲሆን ከይሲው ወያኔ ለሥልጣን ሲበቃ በኅበረቱ ከተሰለፉት አባል ድርጅቶች ውስጥ የተወሰኑት ወደ ወያኔ ጉያ የገቡ መሆናቸውም ሐቅ ነው። የወያኔ የሥስልጣን ባለቤት እንዳይሆን ለማስቆምም ሆነ ለማገድ አልተቻለም ። ኢሠፓ ከላይ እስከታች ተፍረክርኮ፤ዋና መሪው በሚያሳፍር ሁኔታ የሀገር ሀብት ዘርፎ ፈርጥጦ፤ ጦሩ ፈርሶ ለወያኔ ሁሉ ነገር አመቻችቶ እንደሰጠ ደግሞ የምንረሳው አይደለም ። የኢሕአፓ ጦርም በወያኔ ፤ ሻዕቢያና ሱዳን ትብብርና በራሱም ድክመትም ሊመታ ቻለ ። ጸረ ወያኔውን የከተሞች ትግልም ምሁሮችና ጠባቦች ነጥለው በማዳከማቸው ሁኔታው ለወያኔ አመች ሆኖ ዘረኝነትን ተጠቅሞና አፈናን አጠናክሮ ሥልጣኑን ለማደላደል ችሏል። ይህን ወያኔን በሥልጣን በከፍተኛ ደረጃ ያገለገለውን የዘረኝነትና ሕዝብን የመከፋፈል ፖለቲካ በማጀብ በጸረ አማራነትና ኢትዮጵያዊነትን በመካድ የተሰማሩት ኃይሎች ሁሉ- ወደዱም ጠሉም- ለወያኔ የሥልጣን ዘመን መራዘም ከፍተኛ ጠቀሜታ አበርክተዋል። ወደ 1997 ዓ.ም. አካባቢ ብቅ ያሉት ኅብረትና ቅንጅት ሁለትነታቸው ራሱ የድክመታቸው ነጸብራቅ ሆኖ ፤አስፈላጊውን አንድነት አጥተው ግን በትግላቸው ወያኔን በምርጫ ቢያሸንፉም ድላቸውን ለማስከበር ዝግጅቱም ጽናትም እንዳልነበራቸው የተከተለው ሁኔታ ገሃድ አድርጎታል ። ካቸነፍን በኋላ ድላችንን ወያኔ ቢቀማስ ለሚለው ስጋት ይሰጥ የነበረው መልስ አሜሪካ አይፈቅድለትምና ብዙ የሚያሳስብ አይደለም የሚለው ከመሰረቱ የተሣተ ድምዳሜ ነበር ማለት ይቻላል። ልጁ ቀማኛ አባቱ ዳኛ ሆኖ ፍትህን መሻት ማለት ነው። ወይኔ ብዙ ሕዝብ ፈጅቶ እንደተፈራው ከሥልጣን አልወርድም ብሎ ሲደነፋ ይህን በመቃወም የሙት ከተማ አድማ ቢጠራ ይህን ያፈረሱት ራሳቸው የተቃዋሚ ድርጅቶች መሪዎች መሆናቸውንም የምንረሳው አይደለም ። የወያኔ የክፍፍል ዓላማ በጎንደር ሕዝብ ታሪካዊ መፈክር ተሰርዞ፤ የሕዝብ ኅብረት በኢትዮጵዊነት ተጠናክሮ በመጣበት በአሁኑ ጊዜ የሥልጣን መሠረቱ እየተንገዳገደ ያለው ወያኔ ሕዝብን ለመከፋፈል አሁንም ከመወራጨቱ ባሻገር ኢትዮጵያን የእርስ በርስ ደም መፋሰስ አውድማ አድርጎ ካልሆነለትም ትግራይን ገንጥሎ ሊፈረጥጥ (የጎንደርማ የወሎን ለም መሬቶች ጠቅልሎ ከሱዳንም ተዋሳኝ ሆኖ የለ!) ተዘጋጅቷልና የተቃዋሚና ሀገር ወዳድ ኃይሎች ኅብረት ቀነ ቀጠሮ የማይሰጥ፤ለመጪው ትውልድ የማይለጋ ሐኬት ሆኖ ይገኛል። የተቃዋሚና የአገር ወዳድ ኃይሎች ኅበረት እየተንገዳገደ ያለውን የወያኔ ዘረኛና ከፋፋይ አገዛዝ ከሥሩ ለማስወገድም ሆነ ወደ ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት የሚወስደውን የሽግግር ሂደት ሰላማዊ፤ የተረጋጋና ውጤታማ እንዲሆን ለማድረግ ቁልፍ ሚና ይኖረዋል።
ከሽግግሩ ሂደትም ርዕስ ጋር ከዚህ ቀደም ያቀረብነውን አንድ አቢይ ጉዳይ አሁንም ደግመን ማቅረብ አስፈላጊ ሆኖ አግኝተነዋል ፤
"በሽግግሩ ሂደት የፖለቲካ ድርጅቶች ብቻ ሳይሆኑ በእውቀታቸው፤በተመክሯቸው በሀገር ወዳድነታቸውና በዲሞክራሲ ዕምነታቸው እንከን ሊወጣባቸው የማይችሉ የኅብረተሰብ ክፍሎች ሊሳተፉ የሚችሉበት መመዘኛ/መድረክ ቢኖር መሰረተ ሰፊ የሽግግር ወቅት ይሆናል እንላለን ። ይህም ማለት የመንግሥት፤ የኤኮኖሚውንና የሲቪል ኅብረተሰቡን ሚና በሚዛን አስተካክለው የሚያዩና የሚተረጉሙ ክፍሎች ከተሳተፉበት ለዴሞክራሲያዊው ሂደት አቅጣጫ ያረጋግጣል፤ይሰምራል ማለት ነው ።በዕርግጥም በአንድ ሀገር ውስጥ መሠረታዊ ለውጥ ለማምጣት ካስፈለገ የመንግሥትና የሲቪል ኅብረተሰቡን ሚና በግልጽ ተለይቶ መደንገግ ይኖርበታል ። በሀገራችን የዴሞክራሲ ሂደትና ዕድገት በአመዛኙ ሊረጋገጥ የሚችለው የሲቪል ኅብረተሰቡ ሙሉ ተሳትፎ ሲረጋገጥ ነው። የዴሞክራሲንና የነጻነትን ዋስትናና ማረጋገጫ ለማስገኘት የሲቪል ኅብረተሰቡና በነጻ የሚንቀሳቀሱ ተሳታፊ ሕዝባዊ ተቋማት እንዲኖሩ የግድ ነው ። ሚዛኑ ያላጋደለ ቁጥጥር የመንግሥትን ኃይል ለመገደብ ዋስትና አለው ። በሕዝብ ፍላጎትና ተሳትፎ ላይ የተማከለ የማኅበራዊ ኑሮና የኤኮኖሚ ዕድገት ዕውን እንዲሆን ከተፈለገ ሁሉን ሊያሳትፉ የሚችሉ የኅብረተስብ ልዩ ልዩ ድርጅቶች በመላ ሀገሪቱ መስፋፋት አለባቸው ብለን እናምናለን ። ለዚህ ሁሉ ዘር መዘራት ያለበት በሽግግሩ ውቅት ቢሆን ተገቢ ይሆናል ።" ዴሞ ነሐሴ 1995
ስለ ሽግግሩ ከኅብረቱ በእኩል ማቅረባችን ጋሪውን ከፈረሱ ማስቀደማችን ሳይሆን ለሽግግሩ ወሳኝ የሆነውን ኅብረት ስናነሳ ሽግግሩንም በዕይታችን ማስገባቱ የግድ በመሆኑ ነው ። በተጨማሪም የሕዝብን ሚና--ወሳኝነትና የውሳኔ ባለቤትነት--ተገቢውን ቦታ ለመስጠት፤ በምርጦች ሕዝቡ ወደ ጥግ እንዳይደረግ ያለንን ጽኑ ፍላጎት ጫና ለመስጠትና የነገ ኢትዮጵያ ዕጣ አቅጣጫዋ የሕዝብ ውሳኔ ውጤት መሆን አለበት ለማለት ነው። ፈረሱማ ኅብረት ነው ። ተከታዩ የሽግግር መንግስት ነው ። ከዚህም አንጻርጥሪያችን ከዴሞክራሲናኢትዮጵያአንጻርበሁሉምጉዳይበጥሞናተወያይተንመፍትሔእንፈልግነው--ለጋራሀገራችን ።
ያሉትን መለስተኛ ልዩነቶች ወደ ጎን በመተው ለሀገር ጠቃሚ የሆነ ኅብረት መመስረት ይገባል ብቻ ሳይሆን ይቻላልም ።ይህ ግን ግለኝነትን አቸንፎ ሀገርን ማፍቀርና ማስቀደምን ይጠይቃል ።ከሁሉም በላይ ኢትዮጵያ፤ ከሁሉም በፊት ሕዝባችን ካልን ሌሎች ጉዳዮች ፤ የሀሳብና የአቋም ልዩነቶች ክብደታቸው ይቀንሳል ። በሀገራችን ህልውና ላይ የተጋረጠውን አደጋ ከመጋተርና ከማስወገድ በፊት ሊቀድም የሚችል ምንም ግዳጅ የለም። አደጋውን ለማስወገድ መሳሪያ የሚሆነውን ኅብረት ከመመስረት የሚያግድ ምንም ጉዳይና ችግር ሊኖር አይችልም፤ አይገባም ማለት ነው ። ኅብረቱ እውን ከሆነ የሽግግሩ ሂደትም ቀና አቅጣጫን ይዞ መጓዙ የማያቀር ነው ። ተቃዋሚዎች ዓላማ የላቸውም፤ተከፋፍለዋል፤ወያኔ ከተወገደ ሕዝብ ያልቃል፤ለመሆኑ ማን ወያኔን ሊተካ ይችላል የሚሉት ተስፋ አስቆራጭ አነጋገሮች ሁሉ ያከትማሉ ማለት ነው ። ወያኔን አስወግዶ ሀገርን በፍትህና በዲሞክራሲ ለማስተዳደር--እንደ ወያኔ ለማጥፋት ለመበጥበጥ ሳይሆን--ችሎታውና ከዚያም በላይ ፍላጎቱ እንዳለን ሳናወላውል የተናገርነው ነው ።
የኢትዮጵያ ሕዝብ አቸናፊ ይሆናል !

Finote Democracy Radio.


#Finote Democracy ፍካሬ ዜና ህዳር 17 ቀን 2010 ዓ.ም.. (26 November 2017 Weekly NEWS SUMMARY)
#ርዕሰ ዜና #ህፃናት ገዳዩ ወያኔ፣ የህፃናት ቀንን ማክበሩ አነጋጋሪ ነው ተባለ #የውጪ ምንዛሪ ኦና መሆን የወያኔን የደም ስሮች እየገደለ መሆኑ ተሰማ #የወያኔ ፓርላማ ወና እየሆነ መሄዱ ተጋለጠ #የኮካ ኮላ ኩባንያ ስኳር መዘረፉ ታወቀ #ከቻይና ውዳቂ የሆኑ የኤች. አይ.ቪ. መመርመሪያ ቁሶቁሶች ግዢ መፈጸሙ አነጋጋሪ ሆኗል #ወያኔ ከኳታር ጋር መፈጣጠሙ መዘዝ አለው እየተባለ ነው ##ዝርዝር ዜናዎች##
#ህፃናት ገዳዩ ወያኔ፣ የህፃናት ቀንን ማክበሩ አነጋጋሪ ነው ተባለ
 በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ህፃናት በርሀብ አለንጋ እየተገረፉ፣ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ሕፃናት በከተሞች በልመና፣ በጣም ዝቅተኛ በሆነ የጎዳ ላይ ንግድ እየተራወጡ ባሉበት፣ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ሕፃናት ትምህርት እንዳያገኙ በሆኑበት፣ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ሕጻናት በተለያዩ በሽታዎች እየማቀቁ ባለበት የዓለም የህፃናት ቀን በወያኔ አጋፋሪነት መከበሩ ገድሎ መቆንጠጥ ነው ተብሏል፡፡ ዛሬ ወያኔ በሚገዛት ኢትዮጵያ እድሜያቸው ከአንድ አመት በታች የሆኑ ህፃናት በመላው ኢትዮጵያ በወላጆቻቸው ድህነት ምክንያት ወይ ለልመና፣ ወይ ህፃናቱ በእራሳቸው እየተራወጡ የእለት ጉርሳቸውን ሲቃርሙ እንደሚውሉ የሚታወቅ በመሆኑ በርካታ የፖለቲካ አዋቂዎች ወያኔን በህፃናት ገዳይነት ይከሳሉ፡፡ ሕዝባዊ አመጾች በተካሄዱባቸው በርካታ አካባቢዎች የወያኔ የክብር ዘብ የሆነው አረመኔው አጋዚ ጦር በርካታ ወጣቶችን በአልሞ ተኳሾት በመግደሉ ወያኔን የህፃናት ገዳይ ያደርገዋል የሚሉ ብዙዎች ናቸው፡፡ ከዚህ በሻገርም ወያኔ በጉዲፈቻ ስም ህፃናትን እንደ ሸቀጥ እየቸበቸበ መሆኑ የሚታወቅ ነው፡፡ በርካታ ሕህፃናት ለአደንዛዥ እጽ ሱሰኝነት ተጋልጠዋል፡፡ ወያኔ የእናቶችንና የህፃናትን ሞትን መቀነሱን ለፖለቲካ
ተረፌታ ቢለፍፍም ሀቁ ተወልደው ሁለተኛ አመት ልደታው ሳይሞላ የሚቀጠፉ ህፃናት ቁጥርን ቤት ይቁጠረው የሚያሰኝ ነው የሚሉ ብዙዎች መሆናውን ተገንዝበናል፡፡ ባለፈው ሳምንት የተከበረው የዓለም ህፃናት ቀን በህፃናት ገዳዩ በወያኔ ሊከበር አይገባውም ነበር ተብሏል፡፡
#የውጪ ምንዛሪ ኦና መሆን የወያኔን የደም ስሮች እየገደለ መሆኑ ተሰማ
 በብሔራዊ ባንክ ለመጠባበቂያ ተይዞ የነበረው የውጪ ምንዛሪ በተለያዩ የወያኔ ቁንጮዎች ተሟጦ በመወሰዱ በአሁኑ ወቅት አንድም ዓይነት የውጪ ንግድ መፈጸም ፈጹም እማይቻልበት ደረጃ መድረሱ እየተነገረ ነው፡፡ በውጪ ምንዛሪ እጥረት የባህር ትራንስፖርት ድርጅት እንቅስቃሴ እየተሽመደመደ መሆኑ ተጋለጧል፡፡ ለህይወት እጅግ አስፈላጊ የሆኑ መድሀኒቶች በውጪ ምንዛሪ እጥረት ሰበብ ወደ ሀገር ውስጥ መግባት ማቆማቸው በስፋት ይወራል፡፡
#የወያኔ ፓርላማ ወና እየሆነ መሄዱ ተጋለጠ
 የወያኔ ፓርላማ ወንበሮች በየጊዜው በአብዛኛው ቦዶ ሆነው መታየታቸው የተለመደ ነው፡፡ በዚህ ባሳለፍነው ሳምንት የወያኔ ፓርላማ አባላት በዛት ከግማሽ በታች መውረዱ የወያኔ አባላት የእርስ በእርስ መናቆር ውጤት እንደሆነ ታጋለጠ፡፡ ከአምስት መቶ አራባ ሰባት አባላት ውስጥ ግማሹ እንኳ አለመገኘቱ የወያኔ መሰነጣጠቅ ምልክት መሆኑን የሚያስረዱ ብዙዎች ናቸው፡፡
#የኮካ ኮላ ኩባንያ ስኳር መዘረፉ ታወቀ
 የስኳር እጥረት በርካታ ቀውስ እያስከተለና ህብረተሰቡን ለግጭት እየዳረገ መሆኑ አሳሳቢ እንደሆነ ብዙዎች ይናገራሉ፡፡ የኮካ ኮላ ፋብሪካ ባህር ዳር ለሚገኘው ፋብሪካው በአራት ካሚዮን ሰባት መቶ ሃያ ኩንታል ስኳር ሰሜን ሸዋ፣ ጎሀ-ጽዮን፣ ከአዲስ አበባ አንድ መቶ ሰማንያ ኪሎ ሜትር እርቀት ላይ የምትገኘው ወረ ጃርሶ ወረዳን አቋጠው እንዳያልፉ በአካባቢው የፖሊስ ኃይሎች መታገታቸውና ስኳሩም እንዲራገፍ መደረጉ ታውቋል፡፡ ይህ ሁኔታ ከደረሰው የስኳር እጥረት ጋር በተያዘ የተደረገ መሆኑ የሚታወቅ ሲሆን አነጋጋሪው ጉዳይ ግን የድርጊቱ ፈጻሚዎች የደምብ ልብስ የለበሱ የወያኔ የፀጥታ ኃይሎች መሆናቸው የወያኔ የእዝ ስንሰለት እየተልፈሰፈሰ መሆኑን የሚሳይ ነው ተብሏል፡፡ 
#ከቻይና ውዳቂ የሆኑ የኤች. አይ.ቪ. መመርመሪያ ቁሶቁሶች ግዢ መፈጸሙ አነጋጋሪ ሆኗል
 የኤች.ኤ.ቪ. ስርጭት እንደ ወረርሽኝ በአስደንጋጭ ሁኔታ እየተስፋፋ ባለበት ወያኔ ደረጃቸው ዝቅ ያሉ የበሽታው መመርመሪያ ማሳሪያዎች ከደረጃቸው ዝቅ ያሉ መሆናቸው ብቻ ሳይሆን እጅግ በጣም ውዳቂ መሆናቸው ተጋለጠ፡፡ እነዚህ ቁሳቁሶች ያቀረበው ቤጅንግ ዋንቲ ባዮሎጂካል ኢንተርፕራዝ የተሰኘ ድርጅት ሲሆን የቀረቡት የኤች.ኤ.ቪ መመርመሪያ መሳሪዎች ደረጃቸው በእጅጉ ዝቅ ያሉ መሆናቸው ታውቋል፡፡ አስተያየት ሰጪዎች እንደሚሉት እንደዚህ የመሰሉ የቻይና የንግድ ድርጅቶች እንዲህ ያሉ ውዳቂ ሸቀጦችን ለማቅረብ የሚያደፋፍራቸው ምን ጊዜም ከጀርባቸው ያሉት የወያኔ ቁንጮዎች እንደሆኑ የሚታወቅ ነው ተብሏል፡፡
#የኢትዮጵያ ትምህርት ቤቶች በደረጃቸው እጅግ የወደቁ መሆናቸው ተሰማ 
 ወያኔ የሀገራችንን የትምህርት ጥራት እመቀ እመቃት በመክቱተቱ በሀገር አቀፍ ደረጃና በዓለም አቀፍ ደረጃ ውግዘት እየወረደበት መሆኑ የሚታወቅ ነው፡፡ በቅርቡ በትምህርት ቤቶች የትምህርት አሰጣጥን አስመልክቶ የተካሄደ ጥናት ይፋ እንዳደረገው ዘጠና አራት ከመቶው የሚሆኑት ትምህርት ቤቶች የትምህርት አሰጣጥ ደረጃቸው ከመደበኛው መስፈርት እጅግ በጣም የወረደ መሆኑን ይፋ አድርጓል፡፡ የወያኔ ቁንጮዎች በገንዘብ የተገዙ ሁለተኛና ሦስተኛ ዲግሪዎች ባለቤት በሆኑባት ሀገር ወያኔ በስልጣን እስካለ ድረስ ትምህርት እየተልከሰከሰ እንጂ እየጠራ አይሄድም ተብሏል፡፡
#ወያኔ ከኳታር ጋር መፈጣጠሙ መዘዝ አለው እየተባለ ነው
 ይህ የወያኔና የኳታር ጋብቻ የፖለቲካ እንደምታ እንዳለው በስፋት እየተነገረ ነው፡፡ በሳዑዲና በግብፅ የሚሽከረከሩት የባህረ-ሰላጤው ሀገራ ኳታርን ማግለላቸውና በአሸባሪው አይ ሲ ስ እረዳትነት መወንጀሏ የሚታወስ ሲሆን በዚህ ሳቢያ ኳታር አሰብ ወደብ ያሰፈረችውን ጦሯን ማስወጣቷ የሚታወቅ ነው፡፡ ወያኔ የውጪ ምንዛሪ እጥረቱን ለመቅረፍ በሚል ጭፍን አስተሳሰብና የግብፅን ተጽእኖ መቋቋም እንዲያስችል በሚል ከኳታ ጋር የጭፍን የተደረገው መፈራረም ሳይደርቅ ከሳዑዲና ከሸሪኮቿ ወያኔን ቀስፎ የሚይዝ ተጽእኖ እንደሚያደርሱ ይጠበቃል ተብሏል፡፡ 
#ለዝርዝር ዜናዎች > ከታች ይጫኑ (to listen detail news click below)
To Read: http://www.finote.org/Fikarezena.pdf
To Listen PART 1: http://www.finote.org/TodayPart1.mp3

Sunday, November 5, 2017

ህወሃት ከየመን አቶ አንዳርጋቸው ፅጌን እንጂ የታገሉለትን አላማ መጥለፍ አልቻለም


ንያም ሉጌታ ከኖርዌ
ዘረኞቹ ህወሃት ወያኔዎች የምንወዳትን ትዮጵያ  ገራችንን ደግመው ደጋግመው እንዳያደሙት የህዝባችን መከራና ስቃይ እንዲያቆም ገዳዮቻችንን አጥፊዎቻችንን ሊፋረዳቸው ህይወቱና በቤተሰቦቹ የጨከነ የስርዓቱን የውድቀት ምዕራፍ ወደፊት ያፋጠነ ወደፊት እንጂ ወደ ላ የምንመለስባት ላ ኢትዮጵያ እንደሌለን እውነታውን አስረግጦ ያስገነዘበን አንዳርጋቸው ፅጌ ዛሬ በወያኔ ህወሃት ውድቀት ዋዜማ ልናስታውሰው ይገባል።

ዳኛውም ዝንጀ ፍርድ ቤቱም ገደል እምን ላይ ተሁኖ ይነገራል በደል እንዲሉ በሀገራችን ውስጥ ምንም ዓይነት ፍትህ እኩልነትና ዲሞክራሲ እንደሌለና ዜጎች በመናገራቸው የሚታሰሩበት የሚገደሉበት በዘራቸው ምክንያት እንደ ጠላት የሚፈረጁበት ከአንድ አካባቢ የመጡ ሰዎች ቻ  ገሪቱን ኢኮኖሚዋን ስልጣኑን ተቆጣጥረው ሌላውን ኢትዮጵያዊ የበይ ተመልካች አድርገው ወያኔዎች ሲጨርሱት ሲያስፈልጋቸው በጥይት ሲደፉት ይህንን እውነት ቀድሞ የተረዳው ያስቆጣው ያንገበገበው አንድአርጋቸው ፅጌ ፍትህ በዛች  ገር ላይ እንዲሰፍን በማለት የኔ የሚለውን ነገ ሁሉ ላይ ጨክኖ ህወሀት (ወያኔን) ሊፋለም እስከ ህይወት መስዋአትነት ሊከፍል እርሱ ሞቶ ሌላውን ኢትዮጵያዊ ነፃ ሊያወጣ ሁሉን ጥሎ ዳ ገብቶ አምባገኑን የወያኔ ስርዐትን ሊታገል የወሰነና የታገለ ሁሌም በኢትዮጵያዊያን ልብ
ውስጥ ያለ ታላቅ ታጋይ ነው አንድአርጋቸው ፅጌ፡፡

እርሱ ነዶ ብርሀን ነ የድርሻውን ያለውን ሁሉ ለአንዲት ኢትዮጵያ ከፈለ። አምባገነኑ ስርዐት የአንዳርጋቸው ፅጌን አቅምና ችሎታ ጠንቅቆ ስለሚያውቅ እንቅልፍ ነስቶትና ስጋቱንም ከጫፍ አድርሶት እንደነበር ግልፅ ነው፡፡ ይህንን ታላቅ ታጋይ ወጥመድ ውስጥ ለማስገባት የህወሀት (ወያኔ) የስለላ ተም በሚልዮን የሚቆጠርን ዶላር ከማውጣት  ምሮ ብዙ ድካምና ዋጋ እንዳሰከፈለው ግልፅ ነው ለዚህም ነው በታሪክ ታይቶ በማይታወቅ መልኩ ሀገራትን አርጦ በመሄድ ጠለፋን ያካሄደው የታጋይ አንድአርጋቸው ፅጌን ተፅእኖ ፈጣሪነትና ለሕወሀት ወያኔ ራስ ምታት እንደነበር የሚያሳይ ግልፅ ትእይንት ነው።

አንድአርጋቸው ፅጌ ዛሬም ቢሆን በልባችን ውስጥ ያለ  ግና ነው ባለው ፅኑ አምና ቆራጥነት አልበገሬነት የወያኔን አምባገነንና አፋኝ ስርዐትን እንቅልፍ የነሳ የቁርጥ ቀን ልጅ እንዲሁም የኢትዮጵያዊያን ባለውለታ ነው፡፡ ለሁሉም ነፃነት ናፋቂና ታጋይ ኢትዮጵያዊ ለትግል ጉዞ አርአያ በመሆን የቆራጥነትን ጥግ ያሳየ መሪ ነው፡፡

አቶ አንድአርጋቸው ፅጌ ከማንም በተሻለ ሁኔታ የወያኔ (ሕወ ት) መሰሪ አሰራርን ጠንቅቆ የሚያውቅ እና ኢትዮጵያ  ገራችንን ወደ ድቅድቅ ጨለማ እየከተትዋት እንደሆነ የተረዳ ሰው ነው ዛሬ ላይም ለነፃነት፣ ለአንድነት ፣ ለዲሞክራሲ መከበር የምንታገል ኢትዮጵያዊያን ትግል ማለት ምን እንደሆነ በደንብ የተረዳነው ከአንድአርጋቸው ፅጌ የህይወት ቆራጥነት ነው ለነፃነት የሚከፍሉ መስዋዕትነት ግራ ቀኝን ማየት መመልከት አይጠይቅም፡፡ በጠቅላላ ትኩረት እና  ሳብን ግብ ላይ ማድረግን ብቻ ነው የሚፈልገው።

ይህ አጥፊ ስርዐት ላለፉት 26 አመታት ኢትዮጵያዊያን ላይ የቀበራቸው ፈንጂዎች ኢትዮጵያዊያን ላይ ሳይሆን ራሱ ላይ እያፈነዳ እየፈ ው ይገኛል።  ግናው ታጋይ አንድአርጋቸው ፅጌን ቢያስሩም እርሱን የቆመለትን አላማ ማሰር አልቻሉም ለዚህም ነው ከሃገር ውስጥ ሆነ ከውጭ  ገራት ወያኔን ገዝግዞ ሊጥለው የደረሰው አዲሱ ነፃነት ፈላጊው ትውልድ ያነገበው የፍትህ የዲሞክራሲ ጥያቄና ስርዐቱንም ከስልጣን የማስወገድ ትግል አቶ አንድአርገቸው ፅጌ ዋጋ የከፈለለትና ማየት የሚናፍቀው የነበር ነው ዛሬ ላይ ግን የእርሱ ህልም እውን ሊሆን የወያኔ የከፋፍለህ ግዛ ዘመን ሊያበቃ ዘረኝነቱም ሊጭ ቀብሩ ሊፈፀም 11ኛ ሰዐት ላይ እንገኛለን፡፡


የነፃነት አባት የሆነውን አንድአርጋቸው ፅጌና ሌሎች ብዙ ዋጋ የከፈሉ ኢትዮጵያዊያንን የታሰሩ የተገደሉ አሁንም ድረስ በየ እስር ቤቱ የሚገኙትን ጨምሮ ሁሉንም ማስታወስ ያስፈልጋል፡፡ ሃገራችንን ኢትዮጵያን ሕወ ት ወያኔ አጥፍቶ ሳይጨርሳት ታጋይ አንድአርጋቸው ፅጌ እና ከፍተኛ የተቀዋሚ አመራሮችን ጨምሮ ህዝብን በማደራ ት እንዲሁም በማስተማርና ግንዛቤው እንዲጨምር በማድረግ የእያንዳንዳቸውን ድርሻ ቀድመው ተወተዋል ዛሬ የምናየው ህዝባዊ እንቢተኛነትና የነፃነት ትግል በእነ አቶ አንድአርጋቸው ፅጌ የመመካከርና የመተባበር አ ንዳ የመጣ ውጤት ነው፡፡

አሁን በምናየው የሃገራችን ሁኔታ ኢትዮጵያዊነት መንፈስ እንዲያሸንፍ አንድነት  ይል እንደሆነ ዘረኛውንና አሸባሪውን የወያኔ ስርዐት በዘረጋው የመከፋፈል እና የመበታተን ሃሳብ ውጤታማ እንዳይሆን ይህንን የሕወ ት (ወያኔ) ራ ቀድሞ በማጋለጥ አቶ አንድአርጋቸው
ፅጌ ዋነኛና ቀዳሚ ነው፡፡ አንድአርጋቸው ፅጌ ለሃሩና ለወገኑ ቆመ እንጂ ወገኑንና  ገሩን ለገንዘብና ለንዋይ አልሸጠም ለግል ክብሩ አልተጨነቀም የኢትዮጵያ ህዝብን እንደ መገር ከተጣበቀበት ስርዐት
ለመገላል የከፈለውን ዋጋ እንዲሁም ለዜጎች መብትና ነፃነት መከበር የነበረውን አስተዋፅኦ
የትግል አጋሮቹና ኢትዮጵያዊያን ጠንቅቆ ያውቃል፡፡

የወያኔ (ሕወሀት) ግፍና በደል የህዝባችን ዕሮሮ ማብቂያ ዋዜማ ላይ የደረስነው ቆራጥና ለአላማው ብርቱ የነበረው አንድአርጋቸው ፅጌ ያነገበውን አላማ ይዘን በፍጥነት ለመጓዝ ስለቻልን ነው ከዚህ በኋላ ያረጀው ስርዐት ምንም እድል ፋንታ የለውም በኢትዮጵያ ህዝብ እምቢተኛነት የተሸነፈ ነው፡፡አርቆ መቅበር ብቻ ነው የሚያስፈልገው።

ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ!!!

Saturday, October 28, 2017

ኢትዮጵያውያኑን አማራን እያደኑ መግደል ይቁም!!! ( ቢንያም ሙሉጌታ ከኖርዌ )በሀገራችን ኢትዮጵያ በአራቱም አቅጣጫ ህወሃት ወያኔን እየናጠ የሚገኘው ተቃውሞ አምባ ገነኖቹ የህወሃት ወያኔ ባለስልጣናትን የስልጣን ዘመናቸው ማብቂያ ደውል መሆኑን አረጋግጦላቸዋል።

በውድቀት አፋፍ ላይ የሚገኘው ህወሃት ወያኔ በሁሉም አቅጣጫ የኢትዮጵያ ክፍል ላይ የተነሳበትን ተቃውሞዎች መልካቸውን ቀይረው ወደ እርስ በርስ ግጭት እንዲያመራ ለማድረግ ሲሞክር በከፊልም ሲሳካለት እየተመለከትን ነው ህወሃት ወያኔ እኔ ከሞትኩ ሰርዶ አይብቀል የሚለው አቋሙ በግልጽ ታይቷል።

ለዚህም እንደማሳያ ሁለት ወር ባልሞላ ጊዜ ውስጥ በኦሮምያና ሶማሊያ ክልል በወያኔ ህወሃት መሪነት የተነሱት የእርስ በርስ ግጭቶች ማስታወስ ያስፈልጋል። ዜጎች ከገዛ ሀገራቸው ሲፈናቀሉ ከመቶ በላይ የሚሆኑ ኦሮሞዎች ከሱማሊያ ክልል ሀብት ንብረታቸው ተዘርፈው ሲሰደዱ ሴቶቻቸው በሱማሊያ ሚሊሻ ሲደፈሩ ሲገደሉ አይተናል።

ታዲያ ይህ ሁሉ አምባገነኑ ህወሃት ስልጣኑን ለማራዘም የሚጠቀምበት እንደሆነ ለሁሉም ኢትዮጵያዊ የተደበቀ አይደለም። ህወሃት ወያኔ ኢትዮጵያን ለማተራመስ ቀርፆ በሚጠቀመው ፖሊሲ መሠረት በሁሉም የኢትዮጵያ ክልሎች ላይ የዜጎችን ዘርን ተገን ያደረገ የእርስ በርስ ግጭት እያነሳሳ ይገኛል።

ባሳለፍናቸው ሁለት ቀናቶች ውስጥ እንኳን በኢሊባቡር 20 በላይ አማሮች በግማሽ ቀን ውስጥ ተጨፍጭፈዋል ተገለዋል በኢሊባቡር ወረዳዎች የአማራ ተወላጅ የሆነ ተለይተው እየተጠቁ እንደሆነ የተጎጂ ቤተሰቦች ሲናገሩ አድምጠናል። ስርዓቱን በመቃወም የተጀመረው የተቃውሞ ሰልፍ በህወሃት ወያኔዎች ሰርጎ ገብነት ሆን ተብሎ አላማውን እንዲስት ተደርጉዋል።

በኢሊባቡር ደጋ የተፈናቀሉ አማራ ሴቶች በተሰደዱበት ጫካ ውስጥ እንዳሉ ሁለት ነፍሰጡሮች መውለዳቸው ተነግሯል። በጅማ ዞን ሊዪ ወረዳ የአማራ ተወላጆች ንብረት እየወደመ እንደሆነ አድምጠናል ብዙ ወራትን ያስቆጠረው የአማራ ተወላጆች ላይ ያነጣጠረ ጥቃትም የአማራ ልጆች ከትምህርት ገበታ ጭምር አስተጓጉሎ እንዲታገዱ አድርጉዋል።
ሀላፊነቱን መውሰድ ያለባቸው የዚህ ሁሉ ሴራና ተንኮል አቀናባሪዎች የህወሃት ወያኔ ቱባ ባለስልጣናት ናቸው። ሴራቸውና ተንኮላቸው ተግባራዊ እንዲሆን ትዕዛዝ የሰጡት እነዚሁ ህወሃቶች የሚፈልጉት ደም መፋሰስና ግጭት ብቻ ነው።

ስለዚህ አማራው ሆነ ሌላው ኢትዮጵያዊ በንፁሃን ወገኑ ላይ የደረሰውን ጅምላ ጭፍጨፋ አፀፋውን በመመለስ መቃወም ይገባዋል። ህወሃት ወያኔ ሲገድለን ሲያስገድለን 26 ዓመታት አስቆጥሯል ለገደለን ላስገደለን ጠላታችን ህወሃት ርህራሄ ፍፁም አያስፈልግም። በህወሃት ወያኔ ምክን ያት ከዚህ በኃላ ደሀው ኢትዮጵያዊ ወገናችን ተቸግሮ ተሰቃይቶ መኖር ሊበቃው ይገባል።

ወያኔ የውድቀት ጫፍ ላይ ያደረሰው የገዛ ማንነቱና ባህሪው ነው የአንድ ዘር የበላይነትን አንግሶ ሌላውን ኢትዮጵያዊ ዜጋ እንደ መጤ ወይም እንደ ሁለተኛ ዜጋ በበታችነት ዐይን እያየ የአንድ አካባቢ ሰዎችን ተጠቃሚ ያደረገ ሲስተም ዘርግቶ ሌላውን ያገለለችና ተጠቃሚ ያላደረገች ኢትዮጵያ ለመፍጠር ሲሞክር ከመላው ኢትዮጵያዊ የመረረ ተቃውሞዎች አንገዛም ህወሃት ወያኔ በቃን የሚል መልእክት እየተስተጋባ ነው ያለው።

ብዙ ተምሮ ስራ ያጣ ወጣት ሀገሪቱን ሞልቷል የውትድርና ልምድ ባላቸው የወያኔ ባለስልጣናት የምትመራው ሀገር ኢትዮጵያ ዛሬም አድጋለች እያሉ ህዝቡን ሊያደነቁሩት ሲሞክሩ ታዝበናል። ውስን የወያኔ አገልጋዮችና ባለስልጣናት የሀገሪቱን ኢኮኖሚ ተቆጣጥረው ቀሪውን የሀገሪቱን ዜጋ በርሀብ ጠብሰውት የበይ ተመልካች ሆኖ ባለበት በዚህ ሰዓት ይህ የተራበ ሕዝብ መሪውን ሊበላ ደርሷል።አሁን በሀገራችን ያለው ነውጥ ወደ ለውጥ ለመቀየር ሁሉም ዜጋ በአንድነት ተነስቷል። ህወሃት ወያኔ ለመውደቅ መንገዳገድ ጀምሯል የተንገዳገደውን አምባ ገነኑን ስርዓት የመጣል ሀላፊነት የህዝቡ ነው የለውጡም ባለቤት የሚሆነው ህዝቡ ነው።

የወያኔ ህወሃት ድርጅት አባላት በተናጠል ከወያኔ ጋር በማበር ህዝቡን የምታስጨፈጭፉት የኢትዮጵያ ህዝብ ሲደማ ምሽቱን ዳንኪራ የምትመቱ በገንዘብና በሌላም በሁሉ አቅጣጫ ከጎናቸው ያላችሁ ከአንድ አካባቢ የተሰበሰባችሁ እየሰራችሁ ያለው ታሪክ ተመዝግቦ የሚቀመጥ በደል ግፍ ትልቅ ዋጋ የሚያስከፍላችሁ መሆኑን እወቁት።

አሁን የተጀመረው ህዝባዊ እንቅስቃሴ አድማሱን በማስፋፋት ትግሉን ወደ መጨረሻ ደረጃ ላይ መግፋቱ ልብ ልንል ይገባል የመጨረሻውን ውጤት ማሳመር እንዲቻል ትግሉን መደገፍ አለብን።

   

                           ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ!!!