Monday, December 30, 2013

አሳዛኝ ግፍ የስምንት አመቷ ስለእናት ማስረሻ ቀኝ እጇ ላይ በጥይት ተመታች የአንድነት ጠቅላላ ጉባኤ አባላትን እንባ ያስራጨውን ክስተት ይመልከቱDecember 30/2013

የስምንት አመቷ ስለእናት ማስረሻ ቀኝ እጇ ላይ በጥይት ተመታች፡፡ባለቤታቸውን በሞት የተነጠቁትና ምንም የማታውቀውን ህጻን ልጃቸውን አካለ ጎደሎ ያደረገባቸውን ጥይት ማን እንደተኮሰው ለማወቅ ለዳባት ወረዳ ፖሊስ ጣቢያ አቤት ሲሉ ‹‹ባለቤትዎ ሽፍታ እንደሆኑ መረጃ ስለደረሰን ግድያውን የፈጸመው የጸረ ሽብር ግብር ሃይል ነው››ተብለዋል፡፡
‹‹ሽፍታ እንዴት ባለ80 ቆርቆሮ ቤት ይሰራል?
ልጆቹን ያስተምራል?
ሞዴል አርሶ አደር ተብሎ ይሸለለማል?
በየት አገር በብአዴን ስብሰባ ላይ እንድትገኝ ተብሎ በደብዳቤ ይጠራል?
እንዴት ሽፍታ የመለስ ዜናዊን አደራ ለመወጣት በምንችልበት ሁኔታ ለመወያያት እንድንነጋገር ይባላል? ››
ጥያቄዎቹን ፖሊሶቹ ሊመልሱላቸው ባለመቻላቸው ወደ ክልሉ አስተዳደር አምርተዋል፡፡ክልሉ ለዞኑ ዞኑ ለወረዳው ደብዳቤ እየጻፈ እስካሁን ድረስ የአቶ ማስረሻ እውነተኛ የግድያ መንስኤ መታወቅ አልቻለም፡፡
ይህች ህጻንና ቤተሰቦቿ የሁላችሁንም ወገንተኝነት በአክብሮት ይጠይቃሉ
ሰሜን ጎንደር ዳባት ወረዳ ነዋሪ የነበሩት የ55 ዓመቱ አቶ ማስረሻ ጥላሁን የተመሰከረላቸው አርሶ አደር ገበሬ በመሆናቸው የክልሉ ግብርና ጽ/ቤት ሞዴል አርሶ አደር በማለት ሸልሟቸዋል፡፡የሁለት ወንድና የአምስት ሴት ልጆች አባት የሆኑት አቶ ማስረሻ ወሰኔን ገፍተሃል የሚል ክስ ቀርቦባቸው በዳባት ፍርድ ቤት 300 ብር መቀጮ ተጥሎባቸው በመክፈል ወደ እርሻቸው ቢመለሱም የገበሬ ቀበሌ ማህበሩ ሊያስቀምጣቸው አልቻለም፡፡
ጥቅምት 15/2006ዓ.ም ከሁለተኛ ልጃቸው ሰለሞን ማስረሻ ጋር አትክልት ተክለው አመሻሹ ለይ ተዳክመው መኖሪያ ቤታቸው ገብተዋል፡፡ማለዳ 12፡00 ከመኝታው ባላቋረጠው የውሾች ጩህት ከእንቅልፉ ተነሳው ሰለሞን በሩን ከፍቶ ሲወጣ የጥይት እሩምታ ይወርድበታል፡፡አባት ልጄን ብለው የሌሊት ልብሳቸውን እንደለበሱ ወደ ውጪ ሲወጡ የጥይቶቹ አቅጣጫ ወደ እርሳቸው በመዞሩ ማን እንደተኮሰባቸውና ማን እንደመታቸው ለማየት እንኳን ሳይታደሉ ይህችን ጨካኝ አለም ተሰናበቱ፡፡
መኖሪያ ቤቱ ላይ በሚወርደው የጥይት እሩምታ የተነሳ ሁለት ላሞችና አንዲት ጊደር ተገደሉ፡፡የስምንት አመቷ ስለእናት ማስረሻ ቀኝ እጇ ላይ በጥይት ተመታች፡፡

በአዲስ አበባ የቅርብ ጊዜ የጅምላ መቃብር ተገኘ

December 30, 2013
ሁኔ አቢሲኒያዊ
ነገሩ የተከሰተው አርብ እና ቅዳሜ እለት ነው ከስድት ኪሎ ወደ ፈረንሳይ በሚወስደው መንገድ ላይ በሚገኘው የጃንሜዳ ጦር ካምፕ(በቀድሞ ስሙ ሦስተኛ ሻለቃ) ግቢ ውስጥ በትንሹ ወደ 6 የሚጠጉ አስከሬኖች በብርድልብስ እንደተጠቀለሉ ተገኝተዋል! አስከሬኖቹ ሊገኙ የቻሉት ለመንገድ ስራ የጦር ካምፑ ግቢ አጥር ወደ ውስጥ ፈርሶ መቆፈር ነበረበት፡፡ በዚህ ሂደት ላይ ነው እንግዲህ በስካቫተር ሲቆፈር በመጀመሪያ ሁለት አስከሬኖች በብርድልብስ እንደተጠቀለሉ ተንከባለሉ፡፡ በዚህ የተደናገጡት ሰራተኞች ለጊዜው ስራቸን ያቋረጡ ሲሆን በበነጋው ቅዳሜ እለት ረፋዱ ላይ በሌላ አቅጣጫ ቁፋሮ ሲያደርጉ በዛም በኩል እዲሁ በብርድ ልብስ የተጠቀለሉ አራት አስከሬኖች በተመሳሳይ ሁኔታ ከአፈሩ ዉስጥ ተገኙ፡፡A mass grave in Addis Ababa, Ethiopia
በዚህ መሃል ከጦር ካምፑ አካባቢ የተወሰኑ መኮንኖችና ከፍተኛ ማዕረግ(ጄነራሎች)በትከሻቸው ላይ ያለባቸው ሰዎች ወደ ቦታው በመምጣት ስራው እንዲቆም ትእዛዝ ያስተላለፉ ሲሆን በአካባቢው የነበረውንም ሰው ከቦታው አባረው በትነዋል፡፡ በስፋራው ተገኝተው ሁኔታውን ሲከታተሉ እና በስራው ላይም ተሳታፊ የነበሩ ለሰማያዊ ፓርቲ ቅርብ የነበሩ ሰዎች ፎቶ ለማንሳት ጥረት ቢያደርጉም በወታደሮቹ ተመናጭቀዉ ክልከላ ደርሶባቸዋል፡፡ እንደምንጮቻችን እና የምስል ማስረጃዎች ከሆነ አስከሬኖቹ የተጠቀለሉበት ብርድልብስ አንዳችም ሳይቀደድና ሳይበሰብስ ከነአዲስነቱ መገኘቱ ጅምላ ግድያው በቅርቡ የተፈፀመ ሊሆን እንደሚችል ከፍተኛ ጥርጣሬን አሳድሯል! በጉዳዩ ላይ ማጣራት ለማድረግ ሙከራ ያደረጉት የሰማያዊ ፓርቲ አባሎችንም ፊት እንደተነሳቸውና ለማናገርም ፈቃደኛ የሆነ ሰው አለማግኘታቸዉንም እንዳዉም ቦታውን ባስቸኳይ እንዲለቁ ከሀይለ ቃል ጋር መታዘዛቸውንም ጨምረውተናግረዋል፡፡
ከወታደሮቹ መሀከል የሆነ አንድ ስምና ሀላፊነቱ ለጊዜው ያልታወቀ ምናልባትም የግቢው አዛዥ ሊሆን የሚችል ሰው ይህ ግቢ ሶስት ስርዓቶችን ያገለገለ በመሆኑ የማናቸው እንደሆነ ለማወቅ ባይቻልም ሰዎች በመሆናቸው ክቡር ናቸውና አፈር አልብሷቸው ብሎ ትእዛዝ ሲሰጥ የሰሙ የአይን ምስክሮች ለምንጫችን ስለሁኔታው አስረድተዋል! በሁኔታው በአካባቢው የነበሩ ሰዎች በእጅጉ ያዘኑና የተደናገጡ ሲሆን የሚመለከታቸው አካላትና መንግስት ይህን ጉዳይ አጣርተው ለህዝብ ይፋ እንዲሆን አስተያየት ሲሰጡም ተደምጠዋል! በአሁኑ ሰዓት በስፍራው ምንም አይነት የስራ እንቅስቃሴ አይታይም፡፡ አካባቢውም በቆርቆሮ ተከልሏል፡፡
ተጨማሪ ብርድልብሱ ደብረ ብርሃን ሲሆን ዲዛይኑ በኢህአዲግ ዘመን በቅርብ የተጀመረው ነው!
ሁኔ አቢሲኒያዊ
ከፒተርቦሮው ዩ.ኬ

በቁም እስር ላይ ያሉት ብጹእ ኣቡነ ማቲያስ ከአሜሪካን መልስ በደህንነት ቢሮ ለ72 ሰአታት ታስረው ነበር::

December 30/2013
ኢትዮጵያ ውስጥ ኢትዮጵያዊ አሸባሪ የለም::" ብጹእ አቡነ ማትያስ
 
"ከኦሮሞ እና አማራ ጳጳሳት ጋር ትፈተፍታላችሁ::" አቶ ጸጋዬ በርሄ ..የአፋኝ ደህንነቶች ሹም
በጳጳሳቶች እና በፌዴራሉ ሚኒስትሮች መካከል በስብሰባ ላይ በተነሳው አለመግባባት እና የጳጳሶቹ ድምጽ በደል እና ግፍን በማስተጋባቱ እንዲሁም ለመጣው ችግር ሁሉ ተጠያቂው የኢሕኣዴግ መንግስት ነው:ማለታቸውን ተከትሎ እንዲሁም ጳጳሱ አሜሪካን ተጉዘው ከመጡ በኋላ የሚያሳዩትን የቁጥብነት ባሕሪ ተከትሎ እንዲሁም በቤተክህነት ውስጥ የሚወስዱትን አስተዳደራዊ እርምጃ ያልጣመው ኢሕኣዴግ በአቶ ጸጋዬ በርሄ የሚመራው የአፈና እና የቶርች ቡድን ብጹእ አቡነ ማትያስን ለ72 ሰአታት በደህንነት ቢሮ በቁጣ እና በስድብ በማስጠንቀቂያ አሰቃይተው እና አንገላተው ወደ መኖሪያቸው እንደመለሱዋቸው ከደህንነት ቢሮ ምንጮቻችን ገልጸዋል::ጻጻሱ ለ72 ሰአታት ከመኖሪያቸው ሲታጡ በጠቅላይ ቤተክህነት ውስጥ ካድሬ ቄሶች አቡኑ ለህክምና ውጪ አገር ሂደዋል የሚል ወሬ ሲያስወሩ ነበር::
ብጹ አቡነ ማትያስ በደህንነት ቢሮ ውስጥ በተሰጣቸው ማስጠንቀቂያ መሰረት ከአገሪቱ የመንግስት አካልት ጋር እንዲሁም ከጠቅላይ ቤተክህነት ውስጥ ካሉ የትግራይ ተወላጆች ጋር በቅርበት እንዲሰሩ የተነገራቸው ሲሆን በዙሪያቸው ያሉ የሲኖዶስ አባላትን ፊት እንዳይሰቷቸው እና አማራ እና ኦሮሞ ጳጳሳቶች እንቅስቃሴያቸው ሁሉ ከአቡነ መልከጻዲቅ እና ከተቃዋሚ ሃይላት መሆኑ አውቀው ጥንቃቄ እንዲወስዱ እንዲሁም አስተዳደራዊ ስራዎችን ለንብረዑድ ኤልያስ አብርሃ እንዲያስረክቡ ተነግሯቸዋል:: ከሳቸው ጋር በረዳትነት አቡነ ሳሙኤል እንዲሰሩ መመሪያ የተሰጣቸው መሆኑ ታውቋል::
 
ብጹእ አቡነ ማቲያስ በደህንነት ቢሮ የአቶ ጸጋዬ በርሄ ቡድን ማስፈራሪያ ሲሰጣቸው ፊታቸውን ቅጭም አድርገው በሃዘን እና በቁጭት ስሜት ያዳምጡ እንደነበር ታይተዋል:: መልስ ሲሰጡ የነበሩት እጅግ ዘግይተው በትካዜ እንደነበር ታውቋል::አሸባሪዎችን መዋጋት አለብዎ ሲባሉ በኢትዮጵያ ምድር ኢትዮጵያዊ አሸባሪ የለም ብለው የመለሱት አቡኑ አብዛኛው መልሶቻቸው "...እስኪ ካላችሁ ይሁን እግዛብሄር እንደፈቀደው...' የሚል እንደነበር የደህንነት ቢሮ ምንጮች ጠቁመውናል::
በዚህም መሰረት አቡነ ማትያስ የፖለቲካ ፍጆታ በሚያስፈልጋቸው መንፈሳዊ ስብሰባ ላይ አይገኙም:: በተገኙበትም ቦታ ደሞ ስለ ልማት ካልሆነ በቀር ስለ አስተዳደራዊ ጉዳይ እና ስለ ብሶት ቀስቃሽ ንግግር እንዳያደርጉ ተነግሯቸዋል:: በአሁኑ ወቅት ማንኛውም የአገር ውስጥ እንቅስቃሴያቸው በደህንነት አይን ስር ያለ ሲሆን የቁም እስር ላይ ናቸው::

 

Sunday, December 29, 2013

ትግሉ የሁሉንም ተሳትፎ የሚጠይቅበት ወሳኝ ምእራፍ ላይ ደርሷል

December 29/2013
ራሱን የብሄረ አማራ ዲሞክራሲያዊ ንቅናቄ (ብአዴን) ብሎ የሚጠራው ድርጅት በከፍተኛ የፖለቲካ ኪሳራ ውስጥ ገብቷል። የህወሃትን ዙፋን ከመጠበቅ ባለፈ ምንም ሚና የሌላቸው የብአዴን አመራሮች ያለፉትን ሶስት ወራት በተለያዩ መንገዶች የድርጅቱን አባሎች ሲገመግም ከርመዋል። በግምገማዎች ላይ እንደተረጋገጠው ብአዴን የህወሀትን ዙፋን ሊሸከሙ የሚችሉ ወጣቶችን ኮትኩቶ ለማሳደግ አለመቻሉ ነው። በብአዴን ውስጥ ለሚታየው የውስጥ ትርምስ በድርጅቱ ውስጥ የሚገኙ የግንቦት7 አባላትና ደጋፊዎች እየተጫወቱት ያለው ሚና በሌሎች ድርጅቶች ውስጥ ላሉ የንቅናቄው አባላት ጥሩ ትምህርት የሚሰጥ ነው። የንቅናቄው አባሎችና ደጋፊዎች በድርጅቱ ውስጥ የታቀፉ ወጣቶችን የፖለቲካ ግንዛቤ ከማሳደግ ጀምሮ ፣ የንቅናቄውን መረብ እስከ ወረዳዎች በመዘርጋት ከፍተኛ ሚና በመጫወት ላይ ናቸው። ሰሞኑን በገሀድ በየግምገማዎች ላይ ሲነገር እንደነበረው ብአዴን እወክለዋለሁ ከሚለው የአማራ ህዝብ ሙሉ በሙሉ ተነጥሎ በአየር ላይ የተነሳፈፈ ድርጅት ሆኗል።
ይህን እውነታ ዘግይተው የተረዱት የብአዴን ዙፋን ጠባቂ አመራሮች የሚይዙትን የሚጨብጡትን በማጣት የተለያዩ ውሳኔዎችን እያሳለፉ ነው። ታማኝ የሚሉዋቸውን ካድሬዎች በየወረዳዎች በመላክ በግንቦት7 የሚጠረጠሩትን ወይም የግንቦት7 አባሎች ናቸው ተብለው ከሚገመቱ ሰዎች ጋር በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ መንገድ ግንኙነት አላቸው ተብሎ የሚታሰቡትን ሰዎች በመያዝና በማሰቃየት ሌላው ወጣት ንቅናቄውን እንዳይቀላቀል ለማድረግ እቅድ ነድፈው ለመንቀሳቀስ አስበዋል። እንዲሁም አንድ ለአምስት የተባለውን አደረጃጀት በመስሪያ ቤቶች፣ በቤተሰብ፣ በትምህርት ቤቶችና በተለያዩ ተቋማት ላይ በስፋት በማውረድ፣ የሰውን የእለት ተእለት እንቅስቃሴ ለመቆጣጠር አልመዋል። ወጣቱ አካባቢውን እየለቀቀ ግንቦት7ን ለመቀላቀል የሚያደርገውን እንቅስቃሴ የአካባቢ ፖሊሶችንና የድንበር ጠባቂዎችን በማጠናከር ለመቆጣጠር ውሳኔ አሳልፈዋል።
በድርጅቱ ውስጥ የግንቦት7 ደጋፊዎች ናቸው ተብለው የሚጠረጠሩትን ወይም ዝንባሌ አላቸው የሚባሉትን ሁሉ ነቅሶ በማውጣት ለብአዴን ነፍስ ለመዝራት ሙከራ እየተደረገ ነው። እነዚህን ውሳኔዎች ያስፈጽማሉ የተባሉ በጭካኔያቸው ፣ በጎጠኝነታቸውና በንቅዘታቸው የሚታወቁትን የእነሱ ታማኝ ካድሬዎችን ወደ ፊት ለማምጣት በማሰብ ሰሞኑን ሹም ሽር አድርገዋል። ጉልቻ ቢቀያየር ወጥ አያጣፍጥም እንደሚባለው የሰዎች መለዋወጥ የብአዴንን ህልውና ከክስመት የሚታደገው አይሆንም።
ለመሆኑ ብአዴን የህወሀትን ዙፋን ከመጠበቅ በስተቀር ባለፉት 22 አመታት እወክለዋለሁ ለሚለው ህዝብ ምን ሰራ? ብአዴን ባለፉት 22 ዓመታት ከሰራቸው አሳፋሪ ስራዎች መካከል ሰፊው የአገራችን መሬት ለሱዳን ተላልፎ ሲሰጥ የስምምነት ፊርማውን ማስቀመጡ ነው። ከዚህ በተጨማሪ እወክለዋለሁ የሚለው የአማራ ህዝብ ከቦታ ቦታ ሲፈናቀል፣ ለአመታት ህዝቡ በኤድስና በወባ እንደቅጠል ሲረግፍ ፣ ወጣቱ ስራ አጥቶ በአደገኛ እጾች ደንዝዞና ተስፋ ቆርጦ የወጣትነት እድሜውን በከንቱ ሲያሳልፍ ብአዴን ዞር ብሎ ለማየት ፈቃደኛ አልሆነም።
የብአዴን ዙፋን ጠባቂነት የሰለቻቸው የድርጅቱ አባላት በተለያዩ ጊዜያት የውስጥ ትግል ሲያደርጉ ቆይተዋል። ብዙዎች በህወሀትና በተላለኪው ብአዴን የጸጥታ ሀይሎች ተገድለዋል፣ አንዳንዶች ድርጀቱን ለቀው ወጥተዋል፣ አንዳንዶች አሁንም በእስር ላይ ይገኛሉ።
ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በብአዴን ውስጥ ብቻ ሳይሆን በመላ አገራችን ስር ነቀል ለውጥ ለማምጣት ፈቃደኝነታቸውን አሳይተው በግንቦት7 ስር ታቅፈው በመንቀሳቀስ ላይ ያሉት ወጣት አባላት የቀድሞ አባሎች የጀመሩትን ትግል በተደራጀና ስርአት ባለው መልኩ ለማስኬድ የጀመሩት ትግል ንቅናቄው በትኩረት የሚከታተለው ነው። ይህ ትግል ተጠናክሮ በሌሎች ድርጅቶችም ተግባራዊ እንዲሆን ግንቦት7 በተለያዩ የኢህአዴግ ድርጅቶች ውስጥ ላሉ አባሎቹ ጥሪውን ያስተላልፋል።
ግንቦት7 መላውን የኢትዮጵያ ህዝብ ከዘረኛው፣ ዘራፊውና ራዕይ አልባው የህወሀት ጎጠኛ አገዛዝ ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ለመገላገል እና በምትኩ የሁሉም የምትሆን ዲሞክራሲያዊት ኢትዮጵያን ለመገንባት የጀመረውን ትግል ከመቼውም ጊዜ በላይ አጠናክሮ ቀጥሏል። በዚህ ወሳኝ የትግል ምእራፍ ወቅት የሁሉም ኢትዮጵያዊ ተሳትፎ አስፈላጊ ነው ብሎ ንቅናቄው እንደሚያምን በተደጋጋሚ ሲገልጽ ቆይቷል። በተለይም በኢህአዴግ ድርጅቶች ውስጥ ታቅፈው በመንቀሳቀስ ላይ ያሉ እውነተኛ የስርአት ለውጥ እንዲመጣ የሚፈልጉ ሀይሎች የብአዴን ወጣት የግንቦት7 አባላት እያሳዩት ካሉት እንቅስቃሴ ልምድ በመውሰድ በውስጥ የሚያደርጉትን ትግል አጠንክረው እንዲገፉበት ንቅናቄያችን ጥሪውን ያቀርባል።
ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ!!

የአማራ ዴሞክራሲያዊ ኃይል ንቅናቄ ለሱዳን ተላልፎ በተሰጠው መሬት ዙሪያ መግለጫ አወጣ

December 29/2013

የአማራ ዴ/ኃ/ን ለሱዳን ተላልፎ በተሰጠው መሬት ዙሪያ “ዳሩ ካልተጠበቀ መሃሉ ዳር ይሆናል” የሚል መግለጫ አወጣ
ጋዜጣዊ መግለጫ
“ዳሩ ካልተጠበቀ መሃሉ ዳር ይሆናል”!!
 
ከአማራ ዴሞክራሲያዊ ኃይል ንቅናቄ (አዴኃን) የተሰጠ መግለጫ
ታህሣሥ 10 ቀን 2006 ዓ.ም.
 
በዓለም ላይ እስከአሁን የተከሰቱ መንግሥታት (ቅኝ ገዥዎችን ጨምሮ) ጨቋኝ (አምባገነን)፣ በዝበዥ፣ ዘራፊ (በሙስና የተዘፈቀ) … ወዘተ ሊሆኑ ይችላሉ። አሁን ኢትዮጵያን በመግዛት ላይ እንዳለው የትግሬ ዘረኛ ቡድን የሚገዛትን ሀገርና ሕዝብ የሚጠላና ሀገሩንም ለማጥፋት 24 ሰዓት የሚሠራ መንግሥት ግን እስከ አሁን በታሪክ አልታየም። ወደፊትም ከወያኔ በስተቀር የሚገዛትን ሀገር፣ ታሪኳንና ሕዝቧን የሚጠላና ሆን ብሎ ለማጥፋትም ቀን – ተሌት የሚጥር መንግሥት በምድር ላይ ይከሰታል ብለን አናምንም። ይህ የትግሬ ዘረኛ ቡድን ኢትዮጵያንና ሕዝቧን መጥላቱን የሚያሳይ የድርጊቱን ሥንክሣር መዘርዘር ቢቻልም፣ በአሁኑ ሰዓት የተከሰቱ ሁለት ታላላቅ ብሔራዊ ጉዳዮችን ብቻ እንኳ ብናይ ዘረኛው ቡድን ምን ያህል የሚገዛትን ሀገርና ሕዝቧን አምርሮ እንደሚጠላ ፍንትው አድርገው ያሳያሉ፦
 
በሣዑዲ አረቢያ የወገኖቻችን ደም በግፍ ሲፈስስ፣ እህቶቻችን ያለርህራሄ በቡድን ሲደፈሩ፣ በ21ኛው ክ/ዘመን በሰው ልጅ ላይ የፈፀማል ተብሎ የማይታሰብ ኢሰብአዊ ግፍ ሲፈፀምባቸውና በአጠቃላይ በሀገሪቱ ላይ ብሔራዊ ውርደት ሲደርስ የትግሬው ዘረኛ ቡድን “የሣዑዲ አረቢያ መንግሥት በሀገሩ ላይ ይህንን ማድረግ መብቱ ነው” ነበር ያለው።
በዚህ ሰቅጣጭ ሐዘን ውስጥ ተውጠንና በስቃይ ላይ ያሉ ወገኖቻችንን ለመርዳት ላይ ታች በምንልበት ጊዜ ኢትዮጵያን ለማጥፋት ታጥቆ የተነሳው የትግሬው ዘረኛ ቡድን አባቶቻችን ደማቸውን በማፍሰስና አጥንታቸውን በመከስከስ ጠብቀው ያቆዩትን 1600 ኪ/ሜ ርዝመትና ከ20-60 ኪ/ሜ ወደ ኢትዮጵያ ጥልቆ የሚገባውን ከሱዳን የሚያዋስነውን ድንበራችንን በሕገወጥነት ከኢትዮጵያ ሕዝብ ጀርባ ፈርሞ ለሱዳን አስረከበ። ምንም እንኳን በሚስጥር ሊይዘው ቢሞክርም የድንምበር ማካለሉ ከጥር ወር 2006 እስከ መስከረም 2007 ችካል በመቸከል እንደሚጠናቀቅ ታውቋል።
 
የአማራ ዴሞክራሲያዊ ኃይል ንቅናቄ (አዴኃን) ይህንን ከኢትዮጵያ ሕዝብ ጀርባ የሚደረግ ሕገወጥ የድንበር ክለላ አጥብቆ መቃወምና ማውገዝ ብቻ ሳይሆን እንዳባቶቹ ደሙን አፍስሶና አጥንቱን ከስክሶ ታሪካዊ ድንበሩን ለማስከበር ቆርጦ ተነስቷል። ባንዳ የባንዳ ልጆች ከአባቶቻቸው የወረሱትን ሀገር የማጥፋትና የመሸጥ ውርስ ተግባራዊ ሲያደርጉ እኛ የአርበኛ ልጆች ነን የመንል ይህንን ደባ ዝም ብለን ብንመለከት ድንበር ላይ የተከሰከሰው የአባቶቻችን አጥንት እሾህ ሆኖ ይዎጋናል። በመሆኑም በአካባቢው ያላችሁ ታጋይ ኃይሎችና የገፈቱ ቀማሽ የሆንከው የኢትዮጵያ ሕዝብ፣ በርስቱና በሚስቱ ያልሞተ ወንድ ልጅ ወንድ አይደለምና ወንድ ልጅ ነኝ ያልክ ሁሉ ተባበረን፣ ከዚህ በላይ የሞት ሞት የለምና።
 
አዴኃን ይህንን ድርጊት አምርሮ የሚቃወመው እንዲያው በጭፍኑ ኢትዮጵያ ከሱዳን ጋር ሕጋዊ የሆነ ድንበር አይኑራት ብሎ አይደለም። የድንበር ስምምነቱ ኢትዮጵያን ጎድቶ ሱዳንን የሚጠቅም፣ ከ110 ዓመታት በፊት የፈረሰና ሕጋዊ ያልሆነ ውልን መሠረት ያደረገ፣ በጉዳዩ ላይ ጥልቅ ጥናት ያደረጉ ኢትዮጵያውያንን ጥናትና ውትወታ ግንዛቤ ውስጥ ያላስገባና በአጠቃላይ ከኢትዮጵያ ሕዝብ ጀርባ በደባና በሕገወጥነት የተፈረመ ውል በመሆኑ እንጅ።
 
በጉዳዩ ላይ ጥልቅ ጥናት ያደረገው የኢትዮጵያ የድንበር ኮሚቴና ከዚያ በፊትም ጥናት ያደረጉ የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ምሑራን እንደሚሉን ከሆነ ይህ ዛሬ የትግሬው ዘረኛ ቡድን ከኢትዮጵያ ሕዝብ ጀርባ ለተፈራረመው ውል ዋቢ የሚያደርገው ውል በዳግማዊ አፄ ምኒልክና በጊዜው የሱዳን ቅኝ ገዥ በነበረችው እንግሊዝ መካከል የተፈረመው እ.አ.አ 1902 ነበር። አፄ ምኒልክ ይህንን ውል የፈረሙት በኃይል ተገድደውና በይዞታቸው ሥር የነበሩ ብዙ መሬቶችን ለቀው ነበር። በዓመቱ በ1903 የእንግሊዙ የጦር መኮንን ሻለቃ ጉዊን ድንበሩን ከስምምነቱ ውጭ ብቻውን ሄዶ ከመከለሉም በላይ አፄ ምኒልክ ተገድደውም ቢሆን የፈረሙትን ካርታ አዛብቶ ኢትዮጵያን እየጎዳ ችካል ቸከለ።
ይህንንም ሻለቃ ጉዊን ከተሰጠው ሥልጣን በላይ ሄዶ መሥመሩን በማዛባት ከኢትዮጵያ መሬት እንደወሰደ በራሱ ሪፖረት ላይ በግልፅ ሳይደብቅ ጽፏል። እንግሊዞችም በ1902 የተፈረመበትን ካርታ ጥለው በችካሉ መሠረት በ1903 አዲስ ካርታ በመሥራት እነርሱ ከፈረሙበት በኋላ አፄ ምኒልክን ለማስፈረም ቢሞክሩም ከስምምነት ውጭ ለተቸከለው የጉዊን ክለላ ዕውቅና በመንፈግ ሳይፈርሙበት ቀርተዋል። የትግሬው ዘረኛ ቡድን አፄ ምኒልክ፣ አፄ ኃይለሥላሴና ደርግ የጉዊንን መሥመር ተቀብለዋል እያለ የሚያላዝነው ይህንን የመሰለውን ሐቅ በመካድ ነው። ይህንንም ዓይን ያወጣ የወያኔን ቅጥፈት አዴኃን ብቻ ሳይሆን ሰኞ 19 ኖቬምበር 2007 (እ.አ.አ.) ሱዳን ትሪቢዩን የተባለ ጋዜጣም “ድንበሩን አስመልክቶ የሱዳን መንግሥት ከቀደምት የኢትዮጵያ መንግሥታት ጋር የነበረው ግንኙነት ቀና አልነበረም። በድንበሩ ጉዳይ ላይ ለመነጋገር የመጀመሪያው ፈቃደኛ መንግሥት ገዥው የኢሕአዴግ መንግሥት ብቻ ነው” በማለት መሥክሮበታል።
 
ጥሪ፦
ውድ የኢትዮጵያ ሕዝብ ሆይ! የፖለቲካ ድርጅቶችና የሲቪክ ማህበራትም ጭምር፣ ይህ ከኢትዮጵያ ሕዝብ ጀርባ በሀገር ከሃዲው የትግሬ ዘረኛ ቡድ ከጎንደር፣ ከጎጃም፣ ከወለጋና ከኢሊባቡር ክፍለ ሀገሮች ተቆርሶ ለሱዳን የሚሰጠው ለም መሬት የክፍለ ሀገራት ተወላጆቹ መሬት ብቻ አይደለም፤ የአንተም የኢትዮጵያዊው መሬት እንጅ። በመሆኑም አዴኃን ይህንን በባንዳ ልጆች የተጋረጥብንን ኢትዮጵያን የማጥፋት ታላቅ አደጋ ለመቀልበስ ስንል ያሉንን ጥቃቅን ልዩነቶች ወደጎን በመተው፣ ከምንጊዜውም በላይ እጅ ለእጅ ተያይዘንና ያለንን አቅም ሁሉ አስተባብረን በመነሳት የዜግነት ግዴታችን እንድንወጣ አስቸኳይ ጥሪውን ያስተላልፋል። “ዳሩ ክልተጠበቀ፣ መሀሉ ዳር ይሆናል” እንደሚባለው የትግሬውን ዘረኛ ቡድን በተባበረ ክንድ ዛሬውኑ ካላስወገድነው በስተቀር እናት ሀገራችን ኢትዮጵያን የማፈራረስ ዕኩይ ተልዕኮው የድንበር መሬቶችን እየቆረሰ ለጎረቤት ሀገራት በመስጠት ብቻ ያቆማል ብሎ ማሰብ ፍፁም የዋህነት ነው።
ለመከላከያ ሠራዊት፣ የፖሊስ ኃይልና የኢሕአዴግ ደጋፊዎች፣ እናንተ የምትደግፉት ሀገር አጥፊው የትግሬ ዘረኛ ቡድን አባቶቻችን ደረታቸውን ለጦር፣ እግራቸውን ለጠጠር ሰጥተው በደማቸው ያቆዩአትን ይህችን ጥንታዊትና ታሪካዊት ሀገራችንን እያጠፋት እንደሆነ ለእናነተ የተሠወረ አይደለም። ይህንን ሀገር የማጥፋት ወንጀል የሚፈፅመው ደግሞ እናንተን በመሣሪያነት በመጠቀም ስለሆነ ይህንን ተገንዝባችሁ አሁኑኑ ከሕዝባችንና አደጋውን ለመቀልበስ ከሚታገሉ ኃይሎች ጎን በመቆም ሀገራችሁን እንድትታደጉ ስናሳስብ፣ ጥሪያችን ችላ በማለት ለሀገር አጥፊው ቡድን ተባባሪነታችሁን ከቀጠላችሁበት ግን ታሪክና ሕዝብ ይቅር እንደማይላችሁ በጥብቅ ልናስጠነቅቃችሁ እንወዳለን።
 
ለብአዴን አባላት፦ “እሣት አመድ ይወልዳል” እንደተባለው ካልሆነ በስተቀር፣ አባቶቻችሁ ኢትዮጵያን ከሚያጠፋ ጠላት ጋር ተባብረው እናት ሀገራቸውን አላጠፉም፤ ይልቁንም ደማቸውን አፍስሰውና አጥንታቸውን ከስክሰው የታፈረችና አንድነቷ የተጠበቀ ኢትዮጵያን ለእናንተ አስረከቧችሁ እንጅ። እናንተ ግን የጀግኖች አባቶቻችሁ የባሕሪ ልጆች መሆን አቅቷችሁና አደራቸውን በልታችሁ ኢትዮጵያን ለማፈራረስና አማራን ለማጥፋት ቆርጦ ለተነሳው የትግሬ ዘረኛ ቡድን አሽከር ሆናችሁ እናት ሀገራችሁንና ወገናችሁን እያጠፋችሁ ነው። “ለእንጀራየ፣ ለልጆቼና ለቤተሰቦቼ ስል ወይም ተገድጀ ነው ይህንን የማደርገው” የሚለው ውሃ የማይቋጥር ምክንያት እንደማያዋጣችሁ አውቃችሁ የጋራ ሀገራችንንና ወገናችንን ለመታደግ አብራችሁት እንደትቆሙ አዴኃን ከልብ የመነጨ የሀገር አድን ጥሪ ያቀርብላችኋል።
 
ወንድም ለሆነው የሱዳን ሕዝብ፦ የኢትዮጵያና የሱዳን ሕዝብ ለብዙ ሺህ ዘመናት ከአንድ ወንዝ ከተቀዳ ውሃ እየጠጣ፣ በመከባበር ላይ በተመሠረተና በመልካም ጉርብትና አንዱ ለሌላው የችግር ጊዜ ደራሽ ሆኖ የኖረ ወንድማማች ሕዝብ ነው። ነገር ግን ዛሬ የትግሬው ዘረኛ ቡድን በሀገር ውስጥ የሚገኙ ነገዶችን እርስ በእርሳቸው ከማናከስ አልፎ የኢትዮጵያን ሕዝብ በተለይም የአማራውን ነገድ ወንድም ከሆነው የሱዳን ሕዝብም ለማናከስ ቆርጦ የተነሳ በመሆኑ ከኢትዮጵያ ሕዝብ ዕውቅና ውጭ የተፈረመን የድንበር ስምምነት እንዳይቀበል በጥብቅ እናሳስባለን።
 
በመጨረሻም የዓለም ምንግሥታትና ዓለም – አቀፍ ሠላም ወዳድ ሕብረተሰብም የወያኔ ዘረኛ ቡድን ኢትዮጵያንና የኢትዮጵያን ሕዝብ ፈፅሞ እንደማይወክልና አሁን ከሱዳን መንግሥት ጋር በድብቅ የተፈራረመውንም የድንበር ስምምነት ንቅናቄያችን አዴኃን እና የኢትዮጵያ ሕዝብ እንደማያውቁት ተገንዝበው ስምምነቱ አሁንም ይሁን ወደፊት በሁለቱ ሀገራት ሕዝብ መካከል የሚፈጠረውን ቀውስ ከግምት ውስጥ በማስገባት ለስምምነቱ ዕውቅና እንዳይሰጡና በኢትዮጵያ ሕዝብ ላይ የሚፈፀመውን ይህንን ሤራ እንዲቃወሙ አዴኃን ጥሪውን ያስተላልፋል።
በደም የተረከብናትን ሀገር በደም እንጠብቃታለን!!

Tuesday, December 24, 2013

በእስር ላይ የሚገኙት የሙስሊም መፍትሄ አፈላላጊ አባላት በእስር ቤት ስቃይ እንደተፈጸመባቸው ገለጹ

ኢሳት ዜና :-በማእከላዊ እስር ቤት ውስጥ ከፍተኛ የሆነ የስነልቦናዊ እና አካላዊ ስቃይ አድርሰውብናል የሚሉት በእስር ላይ የሚገኙት የሙስሊሙ የመፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ አባላት፣ የደረሱባቸውን በደሎች ዘርዝርው አቅርበዋል።  ” ከአስራ አራት ሰአት በላይ ያለ እረፍት ቀጥ ብለን እንድንቆም በማድረግ፣ ጀርባችን ሰንበር እስኪያወጣ እና እስኪገሸለጥ ራቁታችንን በሽቦ በመግረፍ፣ በሰንሰለት በማሰር እና አይናችንን በጨርቅ በመሸፈን የውስጥ እግራችን እስከሚላጥ ገልብጦ በመግረፍ፣ ቀንና ማታ አሰቃቂ በሆነ ምርመራ እና ድብደባ እንቅልፍ በመንሳት፣ ሃይማኖታችንንና ክብራችንን በመንካት፣ ጺማችንን በመንጨትና እንድንላጭ በማስገደድ፣ እንዲሁም ሶላት በመከልከል፣ ቤተሰብ፣ ጠበቃ ፣ሀኪምና ሀይማኖት አባት እንዳናገኝ በማድረግ፣ ከአቅም በላይ የሆነን ስፖርት በግድ በማሰራት፣ ብልት በመግረፍ፣ ” ልጅህን እንገለዋለን! ሚስትህን አስረን በፊትህ ቶርች እናደርጋታለን! ብልትህ ላይ ሀይላንድ በማንጠልጠል ማሀን እናደርግሀለን” ሲሉ በማስፈራራት ከፍተኛ ስቃይ አድርሰውብናል ብለዋል።
በህገመንግስቱ አንቀጽ 18 ንኡስ አንቀጽ 1 ” ማንኛውም ጭካሄ ከተሞላበት፣ ኢሰብአዊ ከሆነ ወይም ክብርን ከሚያዋርድ አያያዝ ወይም ቅጣት የመጠበቅ መብት አለው” ቢልም፣ እኛ ግን ” ዜጎች መሆናችንን ጥርጣሬ ውስጥ በሚከት መልኩ ከያዙን በሁዋላ በማእከላዊ በክረምት ቀርቶ በበጋ እንኳን ቅዝቃዜው በማይቻለው ” ሳይቤሪያ” ተብሎ በሚጠራው ጨለማ ክፍል ለ3 ዋር አገሩው መቋቋም የሚአዳግተውን የማሰቃያ ስልታቸውን በመጠቀም አላሰብነውንና ያልሰራነውን ” እመኑ! ተናገሩ! ፈርሙ! ብለው አስገድደውናል”  ሲሉ በመግለጫቸው ጠቀስዋል።
ፍርድ ቤት ስቃዩን እንዲያስቆምልን ብንጠይቅም፣ ያገኘነው ውጤት ግን ወደ ማእከላዊ ስንመለስ ከመርማሪዎቹ በቀልና ተጨማሪ ስቃይ ነበር፣ የሚሉት ኮሚቴዎቹ፣ አሰቃዮቻችን ስለህገመንግስቱ እና መብት ስንናገር ” ህገ-መንግስቱን ቀደህ ጣለው፣ እኛ መስዋትንት ከፍለን ነው እዚህ የመታነው በማለት ለህግም ሆነ ለሰው ክብር ዴንታ እንደሌላቸው አሳይተውናል” ሲሉ አክለዋል።
ከቤተሰብ፣ ከጠበቃና ከሀኪም ጋር እንዳንገናኝ አድረገው የፈጸሙብን የህግ ጥሰት እና አስገድደው በማስፈረም እና ድምጽና ምስላችንን በመቅረጽ የፈጸሙብን በደል በወንጀለኛ መቅጫ ህግ ቁጥር 424 መሰረት እስከ አስር አመት የ አስቀጣ ኢ-ሰብአዊ ተግባር ቢሆንም የፖሊሱም፣ አቃቢህጉም ፣ የፍርድ ቤቱም አለቃ በሆነውና የፍትህ ስርአቱን ሰብስቦ በያዘው ገዢው ፓርቲ አምባገነንነት በተቃራኒው እኛ ተከሳሽ ሆነን ጉዳያችን በፍርድ ቤት በመታየት ላይ ይገኛል ብለዋል።
መንግስት በአግባቡ ሊተውነው ያልቻለውን አሳፋሪ የፍርድ ቤት ድራማውን ህዝብ እንዳያይበት ለመሸሸግ በመገደዱ የተከሰሱ ሰዎች ክስ ከቀረበባቸው በሁዋላ ተገቢ በሆነ አጭር ጊዜ ውስጥ በመደበኛ ፍርድ ቤት ለህዝብ ግልጽ በሆነ ችሎት የመስማት መብት አላቸው የሚለውን ህገመንግስታዊ መብት በመጣስ ችሎቱ ዝግ እንዲሆን ተደርጎ ቆይቷል የሚሉት የሙስሊሙ መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ አባላት፣  በዝግ ችሎቱ የምስክር መስሚያ ጊዜ ብዙ አስገራሚ ድራማዎችን አይተናል፣ አቃቢ ህግ ዳኞች የሚሰጡትን ብይን እንደማይቀበሉ እስከመግለጽ የደረሱበትን እና ምስክሮችን ማለት ያለባቸውን አሰልጥነዋቸው እንደሚያመጡ አምልጧቸው የተናገሩበትን አጋጣሚ ” መታዘባቸውን ይገልጻሉ።
የኮሚቲው አባላት ” በሙስሊሞች መካከል እና በሙስሊሙና በክርስቲያኑ መካከል የታየውን አንድነትና መከባበር በጋራ መጠበቅ እንደሚያስፈልግ መክረዋል።  በጽናት ሰላማዊ የመብት ትግሉን የሚቀጥሉ መሆናቸውንና የሚያስከፍለውን መስዋትንት ሁሉ ለመክፈል ዝግጁ መሆናቸውንም ተናግረዋል። ለቀጣዩ ሰላማዊ የመብት ትግል እርከንም  በሙሉ ዝግጅት ላይ መሆናቸውን” ገልጸው፣ መንግስት በማእከላዊ እስር ቤቶች የሚፈጸሙትን ኢ-ሰብአዊ ድርጊቶች እንዲያስቆምና የህሊና እስረኞችን እንዲለቅ ጠይቀዋል።

Sunday, December 22, 2013

ሻምበል ፍቅረሥላሴ ወግደረስ ጻፉ


December 22, 2013ክንፉ አሰፋ
ፀሃይ አሳታሚ ድርጅት በታኅሣሥ 16, 2006 ዓ/ም (Dec. 25, 2013) የቀድሞ የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር የነበሩትን የሻምበል ፍቅረሥላሴ ወግደረስን ‘እኛና አብዮቱ’ የሚል መጽሃፍ ለገበያ እንደሚያበቃ አስታወቀ። ሻምበል ፍቅረሥላሴ እንደ ደርግ አባልነታቸው በጋራ ያመኑበትን፣ የተማከሩትን፣ የወሰኑትን፣ የሰሩትን፣ የገጠማቸውንና በቅርብ በዓይን ምስክርነት ያዩትን ተንትነው በ‘እኛና አብዮቱ’ ያስነብቡናል። የራሳቸውን ዕይታ ያካፍሉናል።New book by Fkreselase Wegderes
ልጅ ሆነን አንድ አባባል እሰማ ነበር።”አበላል እንደ ደርግ አባል። አለባበስ እንደ ፍቅረሥላሴ ወግደረስ!” – የሚል። በተለይ በኔ ትውልድ ያለን ሰዎች፣ ከዚህ ውጭ ስለኝህ ሰው የምናውቀው ብዙም ነገር አልነበረም። ግና እኝህ ሰው በልባቸው መክሊት ለአመታት የቋጠሩትን መረጃ ጀባ ሲሉን፤”… አጻጻፍም እንደ ፍቅረሥላሴ ወግደረስ” የሚያሰኝ ሆኖ አገኘሁት።
ሻምበል ፍቅረሥላሴ ወግደረስ ለአስራ አምስት ዓመታት አብዮቱን ሲመሩ ቆይተው ወደ መጨረሻው ከሥልጣን በጡረታ ስም እንዲሰናበቱ ተደርገዋል። ደርግን በጣለው በወያኔ መንግሥትም ለ፳ ዓመታት ታስረው፣ የሞት ፍርድ የተበየነባቸውና በመጨረሻ ፍርዱ ወደ ዕድሜ ልክ ተዛውሮላቸው ከእሥር ቤት በአመክሮ የወጡ ግለሰብ ናቸው።
ጸሃፊው በድራማ መልክ በመጽሃፋቸው ካሰፈሩዋቸው እውነታዎችና ግለ-ሂሶች ውስጥ አንዳንዶቹን ለአንባቢያን ማካፈሉ አይከፋም። ደርጎች መፈንቅለ መንግስት አድርገው ሲያበቁ ቀዳማዊ ሃይለስላሴ ዘንድ ቀርበው ከንጉሱ የገጠማቸውን አስገራሚ ምላሽ ሻምበል ፍቅረሥላሴ ወግደረስ በመጽሃፋቸው እንዲህ ሲሉ አስፍረዋል።
የፖለቲካ እሥረኞች በሙሉ እንዲፊቱ የሚለው ጥያቄ እንደተነበበ ንጉሡ ጣልቃ ገብተውለመሆኑ የፖለቲካ እሥረኞቹ እነማን ናቸው?” የሚል ጥያቄ አቀረቡ።በእርግጥ የምናውቃቸው የፖለቲካ እሥረኞች ባይኖሩም ማንኛውም የፖለቲካ እሥረኛ እንዲፈታ ነው የምንጠይቀውአሉ ሻለቃ ተስፋዬ ገብረኪዳን። ንጉሡ ራሳቸውን ነቅነቅ አድርገው ጽሑፉን የሚያነበውን የደርግ አባል እየተመለከቱአልገባችሁም!” ብለው ዝም አሉ። በእርግጥም አልገባንም። ተማሪዎችና የተለየ ዓላማ የነበራቸው የተማሩ ሰዎች የሰነዘሩትን መፈክር ብቻ ነበር ይዘን ንጉሡ ፊት የቀረብነው። በፖለቲካ እሥረኝነት ስም በከፍተኛ ደረጃ ለጣሊያን ወራሪ መንግሥት በባንዳነት አድረው አገራችንን የወጉ፣ ለቅኝ ተገዥነትም የዳረጉትን እንደ ኃይለሥላሴ ጉግሳ ያሉ ወንጀለኞች የፖለቲካ እሥረኞች ተብለው ከግዞትና ከእሥር ቤት አስወጥተን እንደ ጀግና ራሳቸውን እንዲቆጥሩ አደረግናቸው።
የነ ጄነራል ተፈሪ በንቲ ጉዳይን አስመልክቶ የሰፈረው ታሪክ ደግሞ እንዲህ ይነበባል።
“በሊቀመንበርነት ስብሰባውን የሚመሩት ጄነራል ተፈሪየቋሚ ኮሚቴው’በዛሬው ቀን የሚወያይበትን ጉዳይ አስመልክቶ የመቶ አለቃ ዓለማየሁ የደርጉ ዋና ፀሐፊ ይገልጽልናል’ ብለው ስብሰባው መጀመሩን ካበሰሩ በኋላ ዓለማየሁ በአጀንዳው ላይ አጭር ገለጣ ማድረግ ሲጀምር ስልክ ተደወለ። ስልኩ /ኮሎኔል መንግሥቱ አጠገብ ስለነበር ወዲያው ቅጭል እንዳለ መነጋገሪያውን በማንሳት ሃሎ አሉ። ከሌላው ጫፍ ማን እንደደወለ አላወቀንም። በኋላ እንደታወቀው /ኮሎኔል ዳንኤል ነበር የደወለው። ምን እንደተነጋገሩ አልተሰማም። /ኮሎኔል መንግሥቱ ብቻእሺ እሺብለው ስልኩን ዘጉት። ስልኩን እንደዘጉይቅርታ ስልኩ የተደወለው ከጎንደር ነው። ጎንደር ውስጥ ችግር አለ። እናንተ ቀጥሉብለው ከጀርባቸው ባለው በር በኩል ውልቅ አሉ። በዚህን ጊዜ ዓለማየሁና ሞገስ ጥርጣሬ የገባቸው መሰለ። ዓለማየሁ ንግግሩን አቋርጦ በመስኮት በኩል ውጭ ውጭዉን መመልከት ጀመረ። ዓይኖቹ አላርፍ አሉ። ግራና ቀኝ ይመለከታል። አጠገቡ ያሉትን ሰዎች ሁሉ በጥርጣሬ ተመለከተ። ሻምበል ሞገስም በር በሩን ይመለከታል። ከአሁን አሁን አንድ ችግር ይከሰታል የሚል ፍርሃት ያደረበት ይመስላል። ሁሉም የኢሕአፓ አባላትና ደጋፊዎች ፈርተዋል። እንደፈሩት አልቀረም /ኮሎኔል መንግሥቱ ከወጡ ሁለት ደቂቃ እንኳን አልሞላም ከበስተጀርባ ባለው ኮሪደር የወታደሮችን እርምጃ ሰማን። ወታደሮች ሲንቀሳቀሱ በፊት ለፊታችን ባሉት መስኮቶች በኩል ተመለከትን። በዚህን ጊዜ ፍስሐ ደስታተከብበናልአለ። ወዲያው ሁለቱም በሮች በኃይል ተበረገዱ። ሁላችንም ደነገጥን፣ ቀልባችን ተገፈፈ፣ እጢአችንም የወደቀ መሰለን። ድርቅ ብለን በተቀመጥንበት ቀረን።…
ሻምበል ፍቅረሥላሴ ወግደረስ ሰለ ልጅ ሚካኤልን አስተዋይነት ሲያስታውሱ እንዲህ የሚል ግለሂስም ያስነብቡናል።
እኛ በችኮላ ውሳኔ መስጠታችን፣ ሕዝቡን በደንብ አለማወቃችን፣ ሰፊ የሕዝብ አመራር ልምድ ማጣታችን፣ የአገርና የውጭውን ፖለቲካ ውስብሰባዊ ግንኙነት አለመገንዘባችን፣ የመንግሥትን አሠራር ደንብና ሥርዓት አለመረዳታችን፣ የፖለቲካና ኢኮኖሚ ጥመርታዊ ግንኙነትን መመልከት አለመቻላችን፣ የተለያየ ገንቢም ሆነ አፍራሽ ተልዕኮ ያላቸው ኃይሎች ተጽዕኖ እንደሚያሳድሩብ ያለማጤናችን፣ በየዋህነትና በቅንነት ብቻ እንደምንሠራ በመገንዘባቸው ሊሆን ይችላል ልጅ ሚካኤል ከእኛ ጋር መቆየት የሚችሉት ለአጭር ጊዜ ብቻ እንደሚሆን የጠቆሙት…
በወቅቱ ስለ ህዝቡ የእርስ በርስ መጨካከንና መወነጃጀል ባሰፈሩት ክፍል ውስጥ እንዲህ የሚል ታሪክ እናገኛለን።
Former Ethiopian Official Fkreselasie Wegderes..የሥራ ዕድገት የተከለከለ፣ በሌብነትም ሆነ በስካር ወይም በሌላ ጥፋት የተቀጣ፣ በግል ጉዳይም ሆነ በመንግሥት ሥራ ከአለቃው ጋር የተጣላ፣ በአጋጣሚው ተጠቅሞ አዲስ ሹመት ወይንም ዕድገት ለማግኘት የሚፈልግ ሁሉ ጠቋሚ፣ ወንጃይ፣ ከሳሽ፣ ተበዳይ ነው።
የተወሰነ ጥቅም ለማግኘት ወይም ሌላውን ለመጉዳት ብለውኢትዮጵያ ትቅደምን ይቃወማል፣ ከታሠሩት ባለሥልጣናት ወይም ሚኒስትሮች የቅርብ ዝምድና አለው። ስለሆነም ሥራ ይበድላል፣ ሠራተኛውን ያጉላላል፣ ውሳኔ አይሰጥምበማለት አለቆቻቸውን የሚከሱ፣ የሚወነጅሉ በርካታ ናቸው። ለደርግ አባላት ቤታቸው ድረስ በመሄድ በማስረጃ የተደገፈ ቢሆንም ባይሆንም ተቆርቋሪ በመምሰል የክስ ማመልከቻ የሚያቀርቡም ነበሩ። እንታሠራለን ብለው በፍርሃት የተደበቁ ባለሥልጣናትን የቅርብ ዘመዶቻቸው ወይም አሽከሮቻቸው ወይም ጎረቤቶቻቸው ደርግ ጽሕፈት ቤት ድረስ በመምጣት ያጋልጧቸው ነበር። የመሥሪያ ቤቶችን ሰነዶች ፎቶ ኮፒ በማድረግ ወይም ሰነዱን እንዳለ ከፋይሉ አውጥተው በማቅረብበመንግሥት ንብረት፣ ሀብት ወይንም ገንዘብ ላይ አላግባብ ተወስኗልብለው ጥቆማና መረጃ የሚያቀርቡም ነበሩ። ሠራተኞች አሠሪዎቻቸውን ይከሳሉ፣ ይወነጅላሉ። ገበሬዎች ለዘመናት በደል አደረሱብን የሚሏቸውን የአካባቢ ባለሥልጣናት ይወነጅላሉ። ውንጀላው በርካታ ነው።
አሽከሮች፣ ዘበኞች፣ ገረዶችመረጃ ይሰጣሉ፣ ይጠቁማሉ። የተደበቀ የጦር መሣሪያ፣ የተደበቀ ገንዘብ፣ ወደሌላ ቦታ የተወሰደ ወይም የሸሸ ሀብት እንዳለም የሚጠቁሙን እነሱ ናቸው። በአንድ ቦታ በርከት ያሉ ሰዎች ተሰብስበው ምሽት ከአሳላፉሲያድሙ ነበርብለው ከነስም ዝርዝራቸው መረጃውን ደርግ ጽሕፈት ቤት ድረስ ያመጣሉ።እኛ እስከዛሬ የበይ ተመልካች ነበርን ዛሬ ዕድሜ ለእናንተ እንጀራ ሊወጣልን ነው! ከእናንተ ጎን ተሰልፈን አቆርቋዦቹን እንታገላለን! በማንኛውም ጊዜ ትዕዛዝ ብትሰጡን ለመፈጸም ዝግጁ ነን!” እያሉ ታማኝነታቸውንና ተባባሪነታቸውን የሚገልጡም ብዙዎች ነበሩ። በጣም የሚያስደንቀው አባቶቻቸውን፣ ልጆቻቸውን፣ ወንድሞቻቸውን፣ እህቶቻቸውን፣ ባሎቻቸውን፣ ሚስቶቻቸውን በመክሰስ፣ በመወንጀል፣ በማጋለጥ፣ በመጠቆም ብሎም በማሳሰር ጉዳት ያደረሱ በርካቶች መሆናቸው ነው።
እንግዲህ ስለ አዲሱ ‘እኛና አብዮቱ’ መጽሃፍ ይህንን ካልኩ ቀሪውን ለአንባቢ መተው ይበጃል። ሁሉም ሰው መጽሃፉን አንብቦ የራሱን ፍርድ ይስጥ።
ህይወት በሩጫ ትመሰላለች። የተፈጥሮ ህግጋት ነውና የሰው ልጅ እስትንፋሱ እስኪቋረጥ ይሮጣል። ከዚያም ሩጫውን ይጨርሳል። ሩጫውን ሳይጨርስ በልቡ ቋጥኝ የያዘውን እምቅ ቋጠሮ የሚተነፍስ ደግሞ እድለኛ ነው። በአንጻሩ ደግሞ በአእምሮውየቋጠረውን የእውቀት ምስጢር ሳያካፍል የሚያልፍ ሁሉ ያሳዝናል። ያለውን የወረወረ ንፉግ አይደለምና መንቀፍም ካለብን የሚወረውረውን ሳይሆን የማይወረውረውን ነው። መተቸት ካለብነም ሃሳቡን እንጂ ግለሰቡን ባይሆን ይመረጣል። በሃሳብ ላይ መወያየትና መተሻሸት ደግሞ አዋቂነት ነው።
በመጨረሻም የመጽሃፉ አርታኢ ኤልያስ ወንድሙ በመግቢያው ላይ ባሰፈረው መልእክት ጽሁፌን ልቋጭ።
የተማረ፣ ያወቀና ያደገ ትውልድና ዜጋ ምልክቱ የተጻፈን ማንበቡ፣ ያነበበውን ማብላላቱና ካነበበው ውስጥ ስንዴውን ከእንክርዳዱ መለየቱ ሲሆን፤ እራሱም አስተውሎና አገናዝቦ መጻፉ ደግሞ መማሩን ብቻ ሳይሆን መመራመሩንና ማወቁን የሚያሳይ ታላቅ ተግባር ነው። ለዚህም ደግሞ ግላዊ ነጻነት ያስፈልገዋልና ጫንቃው ላይ ያሉትን ግላዊና ታሪካዊ ቀንበሮች የሰበረ ነጻ ሰው መሆን ይጠበቅበታል። ትምህርትና ዕውቀት አስተዋይነትንና ጥልቀትን ከራስ በላይ ለትውልድ አሳቢነትን የሚያመለክት ታላቅ ኃላፊነት ነው። ለዚህም እንደ ትናንቱ ‘የተማረ ይግደለን’ ሳይሆን፤ የተማረ ያስተምረን፣ ያስተዳድረን ብሎም ይምራን በምንልበት ዘመን ከምናነብበው ውስጥ ያልተስማማንበትን በጨዋነት የመቃወም፣ የፈቀድነውን እንደ ስሜታችን የመደገፍና ተሳሳተ የምንለውን ለእርማት መጠቆም ግላዊ መብታችን ነው።…
* ፀሃይ አሳታሚ ድርጅት ከዚህ በፊት የቀድሞው የኢትዮጵያ ፕሬዝዳንት ኮሎኔል መንግስቱ ኃይለማርያምን፣ የቀድሞውን የህወሃት መሪ ዶ/ር አረጋዊ በርሄን፣ የቀድሞውን የኢህአፓን አመራር አባል የዶ/ር መላኩ ገኝን፣ የቀድሞው ሚንስትር የአቶ ተካልኝ ገዳሙን መጽሃፍትና ከስልሳ በላይ የሆኑ በኢትዮጵያ ታሪክና ጥናት ላይ ያተኮሩ መጽሃፍትን ማሳታሙ ይታወሳል። ‘እኛና አብዮቱ’ የሚለው ይህ አዲስ መጽሃፍ በwww.tsehaipublishers.com ድረገጽና በቀርቡ በየሱቁ አንደሚገኝ ከሎስ አንጀነሰ የደረሰን ዘገባ አስታውቋል። ሁላችንም ገዘተን እናንብብ።
መጽሃፉን አንብቤ እንደጨረስኩ በሂሳዊ ግምገማ እመለስበታለሁ።


Sunday, December 22, 2013ሻምበል ፍቅረሥላሴ ወግደረስ ጻፉ

December 22, 2013ክንፉ አሰፋ
ፀሃይ አሳታሚ ድርጅት በታኅሣሥ 16, 2006 ዓ/ም (Dec. 25, 2013) የቀድሞ የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር የነበሩትን የሻምበል ፍቅረሥላሴ ወግደረስን ‘እኛና አብዮቱ’ የሚል መጽሃፍ ለገበያ እንደሚያበቃ አስታወቀ። ሻምበል ፍቅረሥላሴ እንደ ደርግ አባልነታቸው በጋራ ያመኑበትን፣ የተማከሩትን፣ የወሰኑትን፣ የሰሩትን፣ የገጠማቸውንና በቅርብ በዓይን ምስክርነት ያዩትን ተንትነው በ‘እኛና አብዮቱ’ ያስነብቡናል። የራሳቸውን ዕይታ ያካፍሉናል።New book by Fkreselase Wegderes
ልጅ ሆነን አንድ አባባል እሰማ ነበር።”አበላል እንደ ደርግ አባል። አለባበስ እንደ ፍቅረሥላሴ ወግደረስ!” – የሚል። በተለይ በኔ ትውልድ ያለን ሰዎች፣ ከዚህ ውጭ ስለኝህ ሰው የምናውቀው ብዙም ነገር አልነበረም። ግና እኝህ ሰው በልባቸው መክሊት ለአመታት የቋጠሩትን መረጃ ጀባ ሲሉን፤”… አጻጻፍም እንደ ፍቅረሥላሴ ወግደረስ” የሚያሰኝ ሆኖ አገኘሁት።
ሻምበል ፍቅረሥላሴ ወግደረስ ለአስራ አምስት ዓመታት አብዮቱን ሲመሩ ቆይተው ወደ መጨረሻው ከሥልጣን በጡረታ ስም እንዲሰናበቱ ተደርገዋል። ደርግን በጣለው በወያኔ መንግሥትም ለ፳ ዓመታት ታስረው፣ የሞት ፍርድ የተበየነባቸውና በመጨረሻ ፍርዱ ወደ ዕድሜ ልክ ተዛውሮላቸው ከእሥር ቤት በአመክሮ የወጡ ግለሰብ ናቸው።
ጸሃፊው በድራማ መልክ በመጽሃፋቸው ካሰፈሩዋቸው እውነታዎችና ግለ-ሂሶች ውስጥ አንዳንዶቹን ለአንባቢያን ማካፈሉ አይከፋም። ደርጎች መፈንቅለ መንግስት አድርገው ሲያበቁ ቀዳማዊ ሃይለስላሴ ዘንድ ቀርበው ከንጉሱ የገጠማቸውን አስገራሚ ምላሽ ሻምበል ፍቅረሥላሴ ወግደረስ በመጽሃፋቸው እንዲህ ሲሉ አስፍረዋል።
የፖለቲካ እሥረኞች በሙሉ እንዲፊቱ የሚለው ጥያቄ እንደተነበበ ንጉሡ ጣልቃ ገብተውለመሆኑ የፖለቲካ እሥረኞቹ እነማን ናቸው?” የሚል ጥያቄ አቀረቡ።በእርግጥ የምናውቃቸው የፖለቲካ እሥረኞች ባይኖሩም ማንኛውም የፖለቲካ እሥረኛ እንዲፈታ ነው የምንጠይቀውአሉ ሻለቃ ተስፋዬ ገብረኪዳን። ንጉሡ ራሳቸውን ነቅነቅ አድርገው ጽሑፉን የሚያነበውን የደርግ አባል እየተመለከቱአልገባችሁም!” ብለው ዝም አሉ። በእርግጥም አልገባንም። ተማሪዎችና የተለየ ዓላማ የነበራቸው የተማሩ ሰዎች የሰነዘሩትን መፈክር ብቻ ነበር ይዘን ንጉሡ ፊት የቀረብነው። በፖለቲካ እሥረኝነት ስም በከፍተኛ ደረጃ ለጣሊያን ወራሪ መንግሥት በባንዳነት አድረው አገራችንን የወጉ፣ ለቅኝ ተገዥነትም የዳረጉትን እንደ ኃይለሥላሴ ጉግሳ ያሉ ወንጀለኞች የፖለቲካ እሥረኞች ተብለው ከግዞትና ከእሥር ቤት አስወጥተን እንደ ጀግና ራሳቸውን እንዲቆጥሩ አደረግናቸው።
የነ ጄነራል ተፈሪ በንቲ ጉዳይን አስመልክቶ የሰፈረው ታሪክ ደግሞ እንዲህ ይነበባል።
“በሊቀመንበርነት ስብሰባውን የሚመሩት ጄነራል ተፈሪየቋሚ ኮሚቴው’በዛሬው ቀን የሚወያይበትን ጉዳይ አስመልክቶ የመቶ አለቃ ዓለማየሁ የደርጉ ዋና ፀሐፊ ይገልጽልናል’ ብለው ስብሰባው መጀመሩን ካበሰሩ በኋላ ዓለማየሁ በአጀንዳው ላይ አጭር ገለጣ ማድረግ ሲጀምር ስልክ ተደወለ። ስልኩ /ኮሎኔል መንግሥቱ አጠገብ ስለነበር ወዲያው ቅጭል እንዳለ መነጋገሪያውን በማንሳት ሃሎ አሉ። ከሌላው ጫፍ ማን እንደደወለ አላወቀንም። በኋላ እንደታወቀው /ኮሎኔል ዳንኤል ነበር የደወለው። ምን እንደተነጋገሩ አልተሰማም። /ኮሎኔል መንግሥቱ ብቻእሺ እሺብለው ስልኩን ዘጉት። ስልኩን እንደዘጉይቅርታ ስልኩ የተደወለው ከጎንደር ነው። ጎንደር ውስጥ ችግር አለ። እናንተ ቀጥሉብለው ከጀርባቸው ባለው በር በኩል ውልቅ አሉ። በዚህን ጊዜ ዓለማየሁና ሞገስ ጥርጣሬ የገባቸው መሰለ። ዓለማየሁ ንግግሩን አቋርጦ በመስኮት በኩል ውጭ ውጭዉን መመልከት ጀመረ። ዓይኖቹ አላርፍ አሉ። ግራና ቀኝ ይመለከታል። አጠገቡ ያሉትን ሰዎች ሁሉ በጥርጣሬ ተመለከተ። ሻምበል ሞገስም በር በሩን ይመለከታል። ከአሁን አሁን አንድ ችግር ይከሰታል የሚል ፍርሃት ያደረበት ይመስላል። ሁሉም የኢሕአፓ አባላትና ደጋፊዎች ፈርተዋል። እንደፈሩት አልቀረም /ኮሎኔል መንግሥቱ ከወጡ ሁለት ደቂቃ እንኳን አልሞላም ከበስተጀርባ ባለው ኮሪደር የወታደሮችን እርምጃ ሰማን። ወታደሮች ሲንቀሳቀሱ በፊት ለፊታችን ባሉት መስኮቶች በኩል ተመለከትን። በዚህን ጊዜ ፍስሐ ደስታተከብበናልአለ። ወዲያው ሁለቱም በሮች በኃይል ተበረገዱ። ሁላችንም ደነገጥን፣ ቀልባችን ተገፈፈ፣ እጢአችንም የወደቀ መሰለን። ድርቅ ብለን በተቀመጥንበት ቀረን።…
ሻምበል ፍቅረሥላሴ ወግደረስ ሰለ ልጅ ሚካኤልን አስተዋይነት ሲያስታውሱ እንዲህ የሚል ግለሂስም ያስነብቡናል።
እኛ በችኮላ ውሳኔ መስጠታችን፣ ሕዝቡን በደንብ አለማወቃችን፣ ሰፊ የሕዝብ አመራር ልምድ ማጣታችን፣ የአገርና የውጭውን ፖለቲካ ውስብሰባዊ ግንኙነት አለመገንዘባችን፣ የመንግሥትን አሠራር ደንብና ሥርዓት አለመረዳታችን፣ የፖለቲካና ኢኮኖሚ ጥመርታዊ ግንኙነትን መመልከት አለመቻላችን፣ የተለያየ ገንቢም ሆነ አፍራሽ ተልዕኮ ያላቸው ኃይሎች ተጽዕኖ እንደሚያሳድሩብ ያለማጤናችን፣ በየዋህነትና በቅንነት ብቻ እንደምንሠራ በመገንዘባቸው ሊሆን ይችላል ልጅ ሚካኤል ከእኛ ጋር መቆየት የሚችሉት ለአጭር ጊዜ ብቻ እንደሚሆን የጠቆሙት…
በወቅቱ ስለ ህዝቡ የእርስ በርስ መጨካከንና መወነጃጀል ባሰፈሩት ክፍል ውስጥ እንዲህ የሚል ታሪክ እናገኛለን።
Former Ethiopian Official Fkreselasie Wegderes..የሥራ ዕድገት የተከለከለ፣ በሌብነትም ሆነ በስካር ወይም በሌላ ጥፋት የተቀጣ፣ በግል ጉዳይም ሆነ በመንግሥት ሥራ ከአለቃው ጋር የተጣላ፣ በአጋጣሚው ተጠቅሞ አዲስ ሹመት ወይንም ዕድገት ለማግኘት የሚፈልግ ሁሉ ጠቋሚ፣ ወንጃይ፣ ከሳሽ፣ ተበዳይ ነው።
የተወሰነ ጥቅም ለማግኘት ወይም ሌላውን ለመጉዳት ብለውኢትዮጵያ ትቅደምን ይቃወማል፣ ከታሠሩት ባለሥልጣናት ወይም ሚኒስትሮች የቅርብ ዝምድና አለው። ስለሆነም ሥራ ይበድላል፣ ሠራተኛውን ያጉላላል፣ ውሳኔ አይሰጥምበማለት አለቆቻቸውን የሚከሱ፣ የሚወነጅሉ በርካታ ናቸው። ለደርግ አባላት ቤታቸው ድረስ በመሄድ በማስረጃ የተደገፈ ቢሆንም ባይሆንም ተቆርቋሪ በመምሰል የክስ ማመልከቻ የሚያቀርቡም ነበሩ። እንታሠራለን ብለው በፍርሃት የተደበቁ ባለሥልጣናትን የቅርብ ዘመዶቻቸው ወይም አሽከሮቻቸው ወይም ጎረቤቶቻቸው ደርግ ጽሕፈት ቤት ድረስ በመምጣት ያጋልጧቸው ነበር። የመሥሪያ ቤቶችን ሰነዶች ፎቶ ኮፒ በማድረግ ወይም ሰነዱን እንዳለ ከፋይሉ አውጥተው በማቅረብበመንግሥት ንብረት፣ ሀብት ወይንም ገንዘብ ላይ አላግባብ ተወስኗልብለው ጥቆማና መረጃ የሚያቀርቡም ነበሩ። ሠራተኞች አሠሪዎቻቸውን ይከሳሉ፣ ይወነጅላሉ። ገበሬዎች ለዘመናት በደል አደረሱብን የሚሏቸውን የአካባቢ ባለሥልጣናት ይወነጅላሉ። ውንጀላው በርካታ ነው።
አሽከሮች፣ ዘበኞች፣ ገረዶችመረጃ ይሰጣሉ፣ ይጠቁማሉ። የተደበቀ የጦር መሣሪያ፣ የተደበቀ ገንዘብ፣ ወደሌላ ቦታ የተወሰደ ወይም የሸሸ ሀብት እንዳለም የሚጠቁሙን እነሱ ናቸው። በአንድ ቦታ በርከት ያሉ ሰዎች ተሰብስበው ምሽት ከአሳላፉሲያድሙ ነበርብለው ከነስም ዝርዝራቸው መረጃውን ደርግ ጽሕፈት ቤት ድረስ ያመጣሉ።እኛ እስከዛሬ የበይ ተመልካች ነበርን ዛሬ ዕድሜ ለእናንተ እንጀራ ሊወጣልን ነው! ከእናንተ ጎን ተሰልፈን አቆርቋዦቹን እንታገላለን! በማንኛውም ጊዜ ትዕዛዝ ብትሰጡን ለመፈጸም ዝግጁ ነን!” እያሉ ታማኝነታቸውንና ተባባሪነታቸውን የሚገልጡም ብዙዎች ነበሩ። በጣም የሚያስደንቀው አባቶቻቸውን፣ ልጆቻቸውን፣ ወንድሞቻቸውን፣ እህቶቻቸውን፣ ባሎቻቸውን፣ ሚስቶቻቸውን በመክሰስ፣ በመወንጀል፣ በማጋለጥ፣ በመጠቆም ብሎም በማሳሰር ጉዳት ያደረሱ በርካቶች መሆናቸው ነው።
እንግዲህ ስለ አዲሱ ‘እኛና አብዮቱ’ መጽሃፍ ይህንን ካልኩ ቀሪውን ለአንባቢ መተው ይበጃል። ሁሉም ሰው መጽሃፉን አንብቦ የራሱን ፍርድ ይስጥ።
ህይወት በሩጫ ትመሰላለች። የተፈጥሮ ህግጋት ነውና የሰው ልጅ እስትንፋሱ እስኪቋረጥ ይሮጣል። ከዚያም ሩጫውን ይጨርሳል። ሩጫውን ሳይጨርስ በልቡ ቋጥኝ የያዘውን እምቅ ቋጠሮ የሚተነፍስ ደግሞ እድለኛ ነው። በአንጻሩ ደግሞ በአእምሮውየቋጠረውን የእውቀት ምስጢር ሳያካፍል የሚያልፍ ሁሉ ያሳዝናል። ያለውን የወረወረ ንፉግ አይደለምና መንቀፍም ካለብን የሚወረውረውን ሳይሆን የማይወረውረውን ነው። መተቸት ካለብነም ሃሳቡን እንጂ ግለሰቡን ባይሆን ይመረጣል። በሃሳብ ላይ መወያየትና መተሻሸት ደግሞ አዋቂነት ነው።
በመጨረሻም የመጽሃፉ አርታኢ ኤልያስ ወንድሙ በመግቢያው ላይ ባሰፈረው መልእክት ጽሁፌን ልቋጭ።
የተማረ፣ ያወቀና ያደገ ትውልድና ዜጋ ምልክቱ የተጻፈን ማንበቡ፣ ያነበበውን ማብላላቱና ካነበበው ውስጥ ስንዴውን ከእንክርዳዱ መለየቱ ሲሆን፤ እራሱም አስተውሎና አገናዝቦ መጻፉ ደግሞ መማሩን ብቻ ሳይሆን መመራመሩንና ማወቁን የሚያሳይ ታላቅ ተግባር ነው። ለዚህም ደግሞ ግላዊ ነጻነት ያስፈልገዋልና ጫንቃው ላይ ያሉትን ግላዊና ታሪካዊ ቀንበሮች የሰበረ ነጻ ሰው መሆን ይጠበቅበታል። ትምህርትና ዕውቀት አስተዋይነትንና ጥልቀትን ከራስ በላይ ለትውልድ አሳቢነትን የሚያመለክት ታላቅ ኃላፊነት ነው። ለዚህም እንደ ትናንቱ ‘የተማረ ይግደለን’ ሳይሆን፤ የተማረ ያስተምረን፣ ያስተዳድረን ብሎም ይምራን በምንልበት ዘመን ከምናነብበው ውስጥ ያልተስማማንበትን በጨዋነት የመቃወም፣ የፈቀድነውን እንደ ስሜታችን የመደገፍና ተሳሳተ የምንለውን ለእርማት መጠቆም ግላዊ መብታችን ነው።…
* ፀሃይ አሳታሚ ድርጅት ከዚህ በፊት የቀድሞው የኢትዮጵያ ፕሬዝዳንት ኮሎኔል መንግስቱ ኃይለማርያምን፣ የቀድሞውን የህወሃት መሪ ዶ/ር አረጋዊ በርሄን፣ የቀድሞውን የኢህአፓን አመራር አባል የዶ/ር መላኩ ገኝን፣ የቀድሞው ሚንስትር የአቶ ተካልኝ ገዳሙን መጽሃፍትና ከስልሳ በላይ የሆኑ በኢትዮጵያ ታሪክና ጥናት ላይ ያተኮሩ መጽሃፍትን ማሳታሙ ይታወሳል። ‘እኛና አብዮቱ’ የሚለው ይህ አዲስ መጽሃፍ በwww.tsehaipublishers.com ድረገጽና በቀርቡ በየሱቁ አንደሚገኝ ከሎስ አንጀነሰ የደረሰን ዘገባ አስታውቋል። ሁላችንም ገዘተን እናንብብ።
መጽሃፉን አንብቤ እንደጨረስኩ በሂሳዊ ግምገማ እመለስበታለሁ።

በሳውዲ አረቢያ በኢትዮጵያውያኑ ላይ ያነጣጠረው ዘመቻ ተጠናክሮ ቀጥሏል !

December 22/2013

በጅዳ የኢትዮጵያ ቆንስላ አንባሳደር ዘነበ ከበደ የሚመሩት የመንግስት ሹማምንቶች ጅዳ ከተማ ውስጥ፡መሽገዋል ያሏቸው 80 ሺህ ኢትዮጵያውያን እጃቸውን በሰላም ካልሰጡ የመንፉሃው አይነት እልቂት እንደሚጠብቃቸው ሲያሞርቱ ! ሪያድ በኢትዮጵያው አንባሳደር መሃመድ ሃሰን የሚመራው ቡድን የሚያሰማው « ጅብ ከሄድ ውሻ ጮህ ጥሪ » ድብቅ አጀንዳ ያለው መሆኑ ተገለጸ !
ከ9 ሚልዮን በላይ የተለያዩ የውጭ፡ሃገር ዜጎች በጥገኝ ነት እንደሚኖሩባት የምትታወቀው ሳውዲ አረቢያ በህገወጥ መንገድ የሚኖሩ የውጭ ሃገር ዜጎች የመኖሪያ ፈቃዶቻቸውን እንዲያስተካከሉ የተሰጠ የ 7 ወር የግዜ ገደብ መጠናቀቅን ተከትሎ የሳውዲ ጸጥታ ሃይሎች ኢትዮጵያውያኑ ላይ ብቻ ባነጣጠረ እርምጃ እስካሁን ቁጥሩ በወል ለማይታወቅ ወገናችን አሰቃቂ ህልፈተ ህይወት ስቃይ እና መከራ ምክንያት መሆኑ ይታወቃል። በተለይ ሪያድ ከተማ በተለምዶ መንፉሃ እይተባለ የሚጠራ ሰፈር ሃገራቸው ለመግባት ጥያቄ ባቀረቡ ወገኖቻችን እና በሳውዲ ጸጥታ ሃይሎች መሃከል በተነሳ ግጭት አያሌ እህቶቻችን በአረብ ጎረምሷች ተደፍረዋል እህቶቻቸውን እና ሚስቶቻቸውን ለመከላከል ጩሀታቸውን ያሰሙ ንጽሃን ወገኖች በአሰቃቂ ሁኔታ በሳንጃ እና በጓራዴ ተገድለዋል ፡፤

ይህንንም ተከትሎ በመቶ ሺህ የሚቆጠሩ ወገኖቻች ከአሰቃቂው ጥቃት እርሳቸውን ለመታደግ ከዳር እስከዳር «ሆ »ብለው አደባባይ በመውጣት የሳውዲ አረቢያ አውራጎዳናዎችን በማጨናነቅ የአለምን መገናኛ ብዙን ሽፋን በማጝት በሳውዲ አረቢያ በጠራራ ፀሃይ እና በሌሊት በወገኖቻችን ላይ ሲፈጸም የነበረው ጭፍጨፋ ስቃይ እና በደል በሃገር ውስጥ እና በውጭ ሃገር የሚገኙ ወገኖቻቸውን ዘንድ ቁጣን በመቀስቀስ በሳውዲ መንግስት ላይ ባደረጉት ተጸዕኖ በማን አለብኝነት በወገኖቻችን ላይ ሲፈጸም የነረውን ኢሰባዊ ድርጊት ለግዜውም ቢሆን ጋብ እንዲል አስችሏል።

የኢትዮጵያኑ አለማቀፍ ቁጣ ያስደነገጠው የሳውዲ አረቢያን መንግስት በሚልዮን ለሚቆጠሩ የውጭ፡ሃገር ያወጣው ህግ በኢትዮጵያውያኑ ላይ ብቻ እንዲያትኩር አስገድዶታል። ይህ በዚህ እንዳለ እስካሁን በመቶሺህ የሚቆጠሩ ኢትዮጵያ ውያን ስደተኞች የስውዲ አረቢያን ምድር በሰላም ለቀው ለሃገራቸው እንደብቁ የሚናገሩ ምንጮች አሁንም 80 ሺህ ህገወጥ ኢትዮጵያውያን ጅዳ ጣይፈ መካ መዲና ከተሞች ውስጥ መሸገዋል ተብሎ በጅዳ የኢትዮጵያ ቆንስላ ጽ/ቤት እይተሰጠ ያለው መግለጫ ቅንነት የጎደለው መሆኑንን ይገልጻሉ። በሃጂ እና ኡምራ አሊያም በባህር ወደ ሳውዲ ምድር ድንበር አቅርጠው ገብተውል ተብለው የሚነገርላቸው ኢትዮጵያውያን ያሉበትን ሁኔታ የማይዘረዘርው በጅዳ የኢትዮጵያ ቆንላ የመንግስት ሹማምቶች መግለጫ ህገወጥ የተባሉት ወገኖች በግዜ እጃቸውን ሰጠተው ወደ ሃገር ካልተመልሱ በሪያድ መንፉሃ የተከስተው አይነት አልቂት እንደሚገጥማቸው አስጠንቅቀዋል።

ይህ በቆንስል ዘነበ ከበደ የሚመራው ጽ/ቤት ሰሞኑንን እያሰማን ያለው ጩህት ወገናዊነት የጎደለው እና ሳውዲያኖቹ በኢትዮጵያውያኑ ላይ ብቻ በማነጣጠር መኖሪያ ፈቃድ ያላቸውን ኢትዮጵያውያን ጭምር ከሳውዲ ምድር ጠራርጎ ለማስወጣት የተያዘ እቅድ አንዱ አካል መሆኑንን የሚናገሩ የጅዳ ነዋሪዎች የመኖሪያ ፈቃድ ያላቸው ወገኖች በሳውዲ ምድር በሰላም ሰርቶ የመኖር ህልውናቸው አስተማማኝ ባልሆነበት አጋጣሚ እንደዚህ አይነት መግለጫ ማውጣት ሃላፊነት የጎደለው መሆኑንን ይናገራሉ። እንዚህ ወገኖች የጅዳው ቆንስላ ጽ/ቤት እንደዚህ አይነት አስገራሚ መረጃ በአረብኛ እና በአማርኛ ቋንቋ በተዘጋጁ በራሪ ወረቅቶች ቅስቀሳ ማካሄዱ ትላንት ሪያድ ከተማ መንፉሃ ውስጥ፡ቆጨራ እና ሳንጃ ታጥቀዋል የሚል የተሳስተ መለዕክት በማስተላለፍ ወገኖቻቸውን ካስፈጁት በሳውዲ አረቢያ የኢትዮጵያው አንባሳደር መሃመድ ሃሰን ከፈጸሙት ስህተት የማይለይ መሆኑንን ይገልጻሉ።

በሌላ በኩል ሰሞኑንን በሪያድ የኢትዮጵያ ኤንባሲ በየጥጋጥጉ ማስታወቂያዎችን በመለጠፍ እና በራሪ ወረቀቶች በመበትን እያሰማ ያለው የተለመደ የአዞ እንባ « ጅብ ከሄደ ውሻ ጮህ » መሆኑንን የሚገልጹ የአካባቢው ነዋሪዎች የምህረቱን አዋጅ ተከትሎ ጉዳዮቻቸውን እስካሁን ማስፈጸም ተስኗቸው በሳውዲ አረቢያ ውስጥ ለመኖር የሚያስችሏቸውን ማመዘኛ ያላሞሉ ወገኖች በሪያድ የኢትዮጵያ ኮሚኒቲ እየቀረቡ ምዝገባ እንዲያካሂዱ የሚለው መለዕክት ለኢትዮጵያውያኑ ታስቦ ሳይሆን ዲፕሎማቱ የተለመደውን ድብቅ አጀንዳቸውን በቀሪው ኢትዮጵያዊ ወገናችን ላይ ለማስፈጸም እንደሆነ ይናገራሉ።

በተለያዩ አቅጣጫዎች ያለደረስኝ፡በወገኖቻችን ሽፋን በመቶሺ የሚቆጠሩ ሪያሎችን በመሰብሰብ ላይ የሚገኘው በሪያድ የኢትዮጵያ ኤንባሲ ዲፕሎማቶች ከተጠቀሱት ወገኖች ኪስ ለተለያዩ ገዳዮች ማስፈጸሚ የሚውል ገንዘብ ለመሰብሰብ እቀድ እንዳላቸው ውስጥ አዋቂ ምንጮች ይገልጻሉ። ውጭ ጉዳይ ሚንስትር ክቡር ቴድሮስ አድሃኖም በወገኖቻችን ላይ ለተፈጸመው አስቃቂ ግድያ ግፍ እና በደል ተመጣጣኝ እርምጃ እንደሚወስድ የገቡትን ቃል ከፖለቲካ ግበአትነት እንደማያልፍ የሚናገሩ ወገኖች የኢትዮጵያ መንግስት በሳውዲ አረቢያ መንግስት ላይ ያሳረፈው ምንም አይነት ዲፕሎማሲያዊ ተጸኖ ባለመኖሩ ሳውዲያኑ ለኢትዮጵያውያኑ ያላቸው ጥላቻ አገርሽቶ በሪያድ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን «በሪስፖንሰሮቻቸው» የመኖሪያ ፈቃዳቻቸው በመሰረዙ አያሌ ወገኖች ለህገወጥነት እይተዳረጉ መሆናቸው ይነገራል።

በጋዜጠኛርዕዮት አለሙ ጉዳይ… የፍርድ ብይኑ ለዳኛው በጽሁፍ እንደተሰጠው ተጋለጠ!!

December 22/2013

EMF=ርዕዮት አለሙ ጋዜጠኛ ናት። ሆኖም የኢህአዴግ ስርአት ወጣቷን ጋዜጠኛ “አሸባሪ” በማለት ክስ ከመሰረቱባት በኋላ፤ የ14 አመት እስራት ፈርደውባታል። ይህ ብይን እንደተሰጠ… የፖለቲካ ውሳኔ እንጂ የዳኞች ውሳኔ እንዳልሆነ ውስጥ ውስጡን ሲወራ ነበር። ይህ ወሬ እውነት መሆኑን የሚያረጋግጡ መረጃዎች እየተገኙ መሆናቸውን በተለይ የቤተሰብ ምንጮች ገልጸዋል።

qqየጋዜጠኛ ርዕዮት አለሙ ታናሽ እህት እንዳሳወቀችው ከሆነ፡ “በዚህ ሂደት ያገኘኋቸው ሁለት ማስረጃዎች አሉ፡፡ አንደኛው በዳኛው የተነበበው የጥፋተኝነት ውሳኔ የእጅ ጽሁፍ ሲሆን ሁለተኛው የዳኛው የእጅ ጽሁፍ ናቸው፡፡ እነዚህ ሁለት ማስረጃዎች በእርግጥም የጥፋተኝነት ውሳኔው በዳኛው እንዳልተጻፈ የሚያረጋግጡ ሆነው አግኝቻቸዋለሁ” ብላለች።

አሁን ብዙዎችን እያነጋገረ ያለው፤ “ከችሎቱ ጀርባ ያለው ድብቅ ዳኛ ማነው?” የሚለው ይሆናል። ይህ በ’ጅ ጽሁፍ ተጽፎ የተሰጠ ብይን የማን እጅ ጽሁፍ ይሆን? ጋዜጠኛ ርዕዮት አለሙ ላይ ብይን በተሰጠበት ወቅት፤ አቶ መለስ በህይወት ነበሩ… የሳቸው ይሆን? ወይንስ የሽመልስ ከማል እጅ ጽሁፍ ነው?

ህዝቡ በዚህ ጉዳይ የራሱን ትዝብት እንዲወስድ፤ በተለይም የፍርድ ውሳኔው ጸሃፊው ማን እንደነበር ለማወቅ ይህ ደብዳቤ ይፋ ይሆናል። ይህ መረጃ ለህዝብ ይፋ የሚሆነው ጋዜጠኛ ርዕዮት የታሰረችበት 30ኛ ወር በታስቦ በሚልበት፤ ታህሳስ 14 2006 ዓ.ም መሆኑ ታውቋል

Wednesday, December 18, 2013

የግንቦት7 ህዝባዊ ሀይል “መጪው አመት ህዝብን የመታደግ እርምጃ የሚወሰድበት አመት ይሆናል” አለ

December18/2013
 (ስምንት)ቀን ፳፻፮ /  ኢሳት ዜና :-ህዝባዊ ሀይሉ የተመሰረተበትን አንደኛ አመት በማስመልከት ባወጣው መግለጫ ” ያለፈው አንድ አመት የመሰባሰብ ድርጅት መሰረታዊ የሆኑ የፖለቲካና የወታደራዊ ስልጠና የተሰጠበት፣ የድርጅት ማጠናከሪያና የማጥራት ሂደት የተካሄደበት ” ነበር ብሎአል። መጪውን አመት የተለየ የሚያደርገው ህዝባዊ ሀይሉ በህዝብ ላይ በሚደርሰው ግፍና ውርደት ከሚሰማው ከፍተኛ ብስጭትና ቁጭት አልፎ ባለፈው አመት ሊደርስላቸው ያልቻለውን የአገራችንን ግፉአን ህዝቦች መታደግ የሚችልበትን እርምጃዎች መውሰድ የሚችልበት መሆኑ ነው” የሚለው ህዝባዊ ሀይሉ፣ በዚህ የህዝባዊ ሀይሉ የአንደኛ አመት ምስረታ ክብረ በአል ወቅት ለወገንም ለጠላትም በግልጽ እንዲያውቀው የምንፈልገው ይህን ሃቅ ነው ብሎአል።
ህዝባዊ ሀይሉ ” ለተራ የፕሮፓጋንዳ ፍጆታ ስንል በቂ ዝግጅት ያልተደረገበት የሃገሪቱን ውድ ልጆች በከንቱ የሚማግድ ጀብደኛ እንቅስቃሴ  አናደርግም። በውሸት ተስፋ  ህዝብን አንመግብም።  አይናችንን ከዋናው የኢትዮጵያና  የህዝቧ  ጠላት ከሆነው ከወያኔ ላይ አንስተን በሌሎች  ወያኔን እቃወማለሁ በሚሉ ሃይሎች ላይ አንተክልም። ከወያኔ ሌላ ወደ ጎን የምንዋጋው፣ የምንጨቃጨው አታካራ የምንገጥመው ምንም ሃይል አይኖርም። ወያኔን ለመምታት ህዝባዊ ሃይሉ የጨበጠው  ቡጢ ወገኖቻችን በፍቅር ለመጨበጥ የሚዘረጉ ጣቶች  እንዳሉት በጸረ ወያኔ ዴሞክራሲያዊ ትግሉ  ከልባቸው ለመተባበር ለሚፈልጉ ሃይሎች ሁሉ ግልጽ እናደርጋለን።” ሲል አትቷል።
በግንቦት7 ህዝባዊ ሀይል አመራሮች ላይ መንግስት የመግደል ሙከራ ማድረጉና መክሸፉ ይታወሳል።  በቅርቡ ደግሞ ከአመራሩ ጋር ለመደራደር ጥያቄ ማቅረቡና ንቅናቄው ውድቅ ማድረጉ ይታወቃል።

ገዢው ፓርቲ ከፍተኛ አመራሮቹ ማኅበራዊ ድረ ገጽ እንዲጠቀሙ መከረ

December 18/2013
ገዢው ፓርቲ ኢህአዴግ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝን ጨምሮ ከፍተኛ የአመራር አካላት፣ የመንግስት ተቋማት እና የመንግስት ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች የማሕበራዊ ድረ ገጽን እንዲጠቀሙ መከረ።
ዳንኤል ብርሃኔ በብሎጉ የኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶክተር ቴዎድሮስ አድሃኖም ጠቅሶ እንደዘገበው ዶ/ር ቴዎድሮስ በማሕበረዊ ድረ ገጽ እያደረጉትን ያለውን የመረጃ አጠቃቀም በተመለከተ በስፋት የሚወራው ወሬ መሰረተ ቢስ መሆኑን አስነብቧል።
ዶክተር ቴዎድሮስ ለብሎጉ በሰጡት አስተያየት፤ “በሶሻል ሚዲያ ድረ ገጽ በመጠቀሜ አንድም የተከፋ ጓድ የለም። በርግጥ በቅርቡ በከፍተኛ የመንግስት ኃላፊዎች ጠቅላይ ሚኒስትሩን ጨምሮ በተደረገ ስብሰባ ላይ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር እንደተቋም እንዲሁም በከፍተኛ የስራ ኃላፊዎቹ በኩል የማሕበራዊ ድረ ገጽ አጠቃቀማቸው በጥሩ ምሳሌ የሚነሳ መሆኑ ተነግሯል” ማለታቸውን አስነብቧል።
አያይዘውም ከሳዑዲ ተመላሽ በሆኑ ዜጎች ጉዳይ ላይ የሰነዘሩት ሃሳብ ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ጋር ተመሳሳይ መሆኑንም አክለዋል።
የአዲስ አበባ ኢሕአዴግ ወጣቶች ሊግ ከወራቶች በፊት በከፍተኛ ሁኔታ ማሕበራዊ ድረ ገጽ እየተጠቀሙ መሆናቸውን ብሎጉ ገልጿል።
በተመሳሳይም የገዢው ፓርቲ ጽ/ቤት የማሕበራዊ ድረ ገጽ ክፍል ማቋቋሙን ሚኒስትሩ ተናግረዋል።
ዶ/ር ቴዎድሮስ በተለይ በማኅበራዊ ድረገጾች (በቲዊተርና ፌስቡክ) እያደረጉ ያሉትን ተሳትፎ ራሳቸውን ለመሸጥ ተጠቅመውበታል በሚል በፓርቲያቸው መገምገማቸውን በተለይ የማኅበራዊ ድረገጾች መወያያ ርዕሰ ጉዳይ ሆኖ መሰንበቱ የሚታወስ ነው።
ሀገር ወዳድ ኢትዮዽያን ይህን የወያኔ ስርሀት እስክናስውግድ ድረስ ትግላችንን በሁሉም መስክ አጠናክረን መቀጠል ይገባናል። በሶሻል ሚዲያና ብሎግ እያሳየን ያለነው ትግል የኢትዮዽያ ህዝብ ትክክለኛ መረጃ እንዲያገኝ ከፍተኛ አስተዋፆ ማበርከቱና ዘረኛውን የወያኔ ጉጂሌን ኢሰባዊ ድርጊቱን በማጋለጥ እየተወጣነው ያለው ተግባር በጣም ስላሳሰባቸው የወያኔ ባለስልጣናትና የወጣቶች ሊግ የሚባለው ሆድ አደሮች  ስራችንንና ትግላችንን ሊያቆሙት አይገባም እዲያውም በተጠናከረ መልኩ ልንታገላቸው ይገባል እላለው።

Monday, December 16, 2013

ታላቅ ህዝባዊ ስብሰባ በኖርዎይ በርገን ከተማ በደመቀ ሁኔታ ተካሔደ

December 16/2013


2በበርገን ከተማ ለመጀመርያ ግዜ በዲሞክራሲያዊ ለውጥ በኢትዮጵያ የድጋፍ ድርጅት ኖርዎይ  በርገን ቅርንጫፍ አስተናጋጅነት በዲሴምበር 14፥2013 የተዘጋጀው ህዝባዊ ስብሰባ በደመቀ ሁኔታ የተጠናቀቀ ሲሆን ከ100 በላይ የሚገመት ህዝብ የተገኘ ሲሆን ከተለያዩ የኖርዎይ ከተሞች የተሰባሰቡ ኢትዮጵያውያን በዝግጅቱም ላይ ተገኝተዋል፥፥
በዝግጅቱ ላይ ተጋባዥ እንግዶች የነበሩት
1ኛ. ዶ/ር ታደሰ ብሩ የግንቦት7 የፍትህ፣ የነፃነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ ስራ አስፈጻሚ አባል
2ኛ. አቶ ዮሃንስ አለሙ የዲሞክራሲያዊ ለውጥ በኢትዮጵያ ድጋፍ ድርጅት በኖርዎይ  ዋና ሊቀመንበር
3ኛ. ዶ/ር ሙሉአለም አዳም የዲሞክራሲያዊ ለውጥ በኢትዮጵያ ድጋፍ በኖርዎይ የድርጅት አባል ናቸው፥፥
የውይይት መድረኩ ከመጀመሩ በፊት በሳውዲ አረቢያ እየተሰቃዩ፥ እየተገደሉ እንዲሁም በግፍ ኢሰብአዊ ድርጊት ለተፈፀመባቸው ወገኖቻችን የአንድ ደቂቃ የህሊና ፀሎት በማድረግ የተጀመረ ሲሆን የዲሞክራሲያዊ ለውጥ በኢትዮጵያ የድጋፍ ድርጅት ኖርዎይ  የበርገን  ቅርንጫፍ ጽ/ት ሰብሳቢ አቶ ሹሜ ወርቁ አጭር የመክፈቻ ንግግር ካረጉ በኋዋላ ተጋባዥ እንግዶቹ በየተራ ስለሚመሩአቸው ድርጅቶችና የወቅቱን የሃገራችንን አስከፊ የፖለቲካ ሁኔታ በተመለከተና ሁሉም የተቃዋሚ የፖለቲካ ድርጅቶች አብረው በስምምነት የሚሰሩበትን ሁኔታ ማምጣት እንዳለብን እንዲሁም ስለ  መደራጀት አስፈላጊነት ሰፋ ያለ ማብራርያ  ሰጥተዋል፥፥
ዶ/ር ታደሰ ብሩ ስለ ግንቦት 7 የፍትህ፣ የነፃነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ ዓላማ ራእይና ግብ እንዲሁም ስለውጭ እምቢተኝነት ሰፋ ያለ ማብራሪያ ከሰጡ  በኋላ ሁሉም ኢትዮያዊ ግንቦት7ትን እንዲቀላቀልና ሃገራችን ኢትዮጵያ ከገባችበት አዘቅት ውስጥ ተባብረን እንታደጋት በማለት  ጥሪ ያቀረቡ ሲሆን እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ በተለያዩ ድርጅቶች ስር ተደራጅቶና ታቅፎ መንቀሳቀሱ ያለውን ጠቀሜታና የሐይማኖትና የሲቪክ ማህበራትን ማደራጀትና ማጠናከር ጠቃሚ መሆኑን አሳስበዋል፥፥ ፥፥
 አቶ ዮሃንስ አለሙ የዲሞክራሲያዊ ለውጥ በኢትዮጵያ ድጋፍ ድርጅት በኖርዎይ  ዋና ሊቀመንበር ስለ ዲሞክራሲያዊ ለውጥ በኢትዮጵያ አመሰራረትና የደረሰበትን ደረጃ እንዲሁም ያከናወናቸውን ተግባራት በተመለከተ በሰፊው ገለጻ  ያደረጉ ሲሆን  ከህዝቡም  ለቀረበላቸው ጥያቄም  ምላሽ ሰጥተዋል፥፥
በተጨማሪም ዶ/ር ሙሉዓለም አዳም በኖርዎይ የስደተኞች አኗኗር ዙሪያ ያለውን ችግር እንዲሁም ሁሉም የተቃቃሚ ድርጅቶች አንድ ላይ ሆነው እንዲሰሩ ጥሪ ያቀረቡ ሲሆን በመጨረሻም የዲሞክራሲያዊ ለውጥ በኢትዮጵያ የድጋፍ ድርጅት ኖርዎይ የበርገን ቅርንጫፍ በተቋቋመ በአጭር ግዜ ውስጥ የደረሰበት ደረጃም በእጅጉ አስደሳች እንደሆነ በመግለፅ ያላቸውን አድናቆት ገልጸው ህዝቡ ለነጻነት ለሚደረገው  ትግል ከፍተኛ አስተዋጽኦ ማድረግ እንዳለበት አሳስበዋል፥፥
እንዲሁም በዝግጅቱ ላይ በሐና ሰመረ ሐቅ ተሰደደ በሚል ርእስ አጭር ግጥም የቀረበ ሲሆን በመቀጠልም በሎሚታ ገብረሚካኤል በምስል በተደገፈ በቀረበው የኢትዮጵያ የታሪክ ጉዞ ከነገስታት ስርአት እስከ ሐገራችን በወያኔ አገዛዝ ስር ወድቃ አሁን የደረሰችበትን ሁኔታ የሚያሳይ ዘገባ ለታዳሚው ቀርቧል፥፥
በመጨረሻም ለእንግዶቹ የተለያዩ ጥያቄዎች ቀርቦ ውይይት ከተደረገ በኋላ ዝግጅቱ የግንቦት 7 ህዝባዊ ሐይል መዝሙርን በመዘበር በተሳካ ሁኔታ ተጠናቋል፥፥
የዲሞክራሲያዊ ለውጥ በኢትዮጵያ የድጋፍ ድርጅት ኖርዎይ  የበርገን  ቅርንጫፍ ጽ/ት

ይሄ ተንኮል ግን የህወሓት ዕድሜ ያራዝማል የሚል ግምት የለኝም።

December 16/2013
ባለፈው ቅዳሜ ዓረና መድረክ በጠራው ህዝባዊ ስብሰባ ለመሳተፍ ወደ ማይጨው ከተማ ተጉዤ ነበር። ከመቀሌ -ማይጨው በመኪና የሦስት ሰዓት ጉዞ ነው። ከሰባት ዓመት በፊት የማውቃት ማይጨው ምንም አልተቀየረችም። ብዙ የህወሓት ባለስልጣናት እዛው ማይጨው ነበሩ። ስብሰባዎችና ስልጠናዎች ነበሯቸው።
ቅዳሜ ከማይጨው ወጣቶች ጋር ተገናኝቼ ነበር። ወጣቶቹ ለውጥ ይፈልጋሉ። ግን ይፈራሉ። የሰለማዊ ትግል ዉጤታማነት ይጠራጠራሉ። ህወሓት በምርጫ ስልጣን ሊያስረክብ ይችላል ብለው አያምኑም። በሰለማዊ መንገድ ከሚቃወሙ በትጥቅ ትግል ቢሳተፉ ይመርጣሉ። ምክንያቱም በትጥቅ ትግል ህወሓት ከስልጣን የሚባረርበት ዕድል ሊኖር ይችላል ብለው ያስባሉ።
Abraha Destaበማይጨው የሚገኙ የመንግስት ሰራተኞችም (በተለይ መምህራንና የግብርና ሰራተኞች) በስርዓቱ ቅሬታ አላቸው። የራያ አከባቢ ተወላጆች የሆኑ የህወሓት ካድሬዎችም በስርዓቱ ደስተኞች አይደሉም። ሁሉም ለውጥ ይፈልጋሉ። ግን ዓረና ህወሓትን ታግሎ ሊያሽንፈው ይችላል የሚል እምነት የላቸውም። በራያ ቦታ የሚገኙ የህወሓት አባላት (የራያ ተወላጆች) ህወሓትን ማሸነፍ የሚችል ተቃዋሚ ፓርቲ ካገኙ ህወሓትን እንደሚቃወሙ ይገልፃሉ።
የህወሓት መሪዎችም ይህንን ያውቃሉ። እንደዉጤቱም ህወሓት ከሌላ አከባቢ ታማኝ ካድሬዎች እየላከ የራሱ አባላት ይሰልላል፣ ይቀጣል፣ ያባርራል። በዚህ መንገድ የራያ ህዝብ በራሱ ሰዎች እንዲበደል ይደረጋል። የራያ ተወላጆች የሆኑ የመንግስት ሰራተኞች ለእንጀራቸው ሲሉ ህዝብ ይበድላሉ። ህዝብ ካልበደሉ ይቀጣሉ፣ ይባረራሉ፣ ሌላ የሚተዳደሩብት የስራ መስክ የላቸውም።
የራያ ቦታ በህወሓት ከተረሱ አከባቢዎች አንዱ ነው። የራያ ህዝብ የክረምት ምግብ የነበረ ‘በለስ’ ለምርምር ተብሎ በገባ የሀር ትል ምክንያት ከጥቅም ዉጭ ሁነዋል። መንግስት የበለስ ጉዳቱ ለማካካስ የወሰደው እርምጃ የለም። በብዙ የራያ ቦታዎች የዉኃ ችግር አለ። የዉኃ ችግሩ ለመቅረፍ ብዙ ጉድጓዶች የተቆፈሩ ቢሆንም የዉኃ ቦይ ማስገባት ባለመቻሉ እስካሁን የዉኃ አገልግሎት የማያገኙ የራያ ቦታዎች አሉ።
ከዓመታት በፊት ለመስኖ እርሻ እንዲዉል በጥናት መሰረት የተመረጠ ‘የጎልጎል ራያ’ ሜዳም እስካሁን አልተተገበረም። የህወሓት መሪዎች ጎልጎል ራያን በመስኖ የማልማት ዕቅድ ሰርዘውታል። ፕሮጀክቱ ለመሰረዝ የሰጡት ምክንያት በራያ የሚገኝ ዉኃ ‘ጨዋማ’ ስለሆነ ለመስኖ ጥቅም አይውልም የሚል ነበር። የሚገርመው ነገር ደግሞ አሁን ጎልጎል ራያ በኢንቨስትመንት ስም ለባለ ሃብቶች እየተሸጠ ነው የሚገኘው። ስለዚህ የህወሓት ሰዎች የጎልጎል ራያን በመስኖ የማልማት ፕሮጀክት የሰረዙበት ምክንያት ሰፊ ለም መሬቱ ለባለሃብቶች ለመሸጥ ስለፈለጉ ሊሆን ይችላል።
የራያ ህዝብ ጀግናው ጥላሁን ይግዛውን ለመዘከር ሐውልት ለመገንባት ተብሎ ከራያ ተወላጆች ወደ 700,000 ብር የሚጠጋ ገንዘብ ከሰባት ዓመት በፊት የተሰበሰበ ሲሆን እስካሁን ድረስ ምንም ነገር አልተሰራም። የራያ ህዝብ ለጥላሁን ይግዛው ሐውልት ለመስራት የተሰበሰበ ገንዘብ የት እንዳለ ማወቅ ይፈልጋል፣ ይጠይቃል። አስተዳዳሪዎቹ የሰጡት መልስ ገንዘቡ ለኮብልስቶን አውለነዋል የሚል ነበር። ህዝቡም ኮብልስቶን የራሱ በጀት እንዳለው ሲከራከር ደግሞ አስተዳዳሪዎቹ ገንዘቡ የት እንዳለ እንደማያውቁ ይናገራሉ።
በማይጨው አከባቢ በሚገኙ ተቋማትም የሙስና አሰራሮች መኖራቸው ኗሪዎች ይናገራሉ። በዚሁ ምክንያት የችፑድ ፋብሪካ፣ ማይጨው ግብርና ኮሌጅና ማይጨው ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ በተመሳሳይ ሁኔታና ወቅት የዳታ ኮምፒተሮች እንዲጠፉ ተደርገዋል። የዳታ ኮምፒተሮች እንዲጠፉ ሲደረግ ተቋማቱ ኦዲት እንዳይደረጉ ይረዳል። ኦዲት ካልተደረጉ ሙስና መሰራቱና አለመሰራቱ ለማወቅ ይከብዳል። የሙስና ጉዳይ ይፈተሽ።
ቅዳሜ ማይጨው በነበርኩበት ሰዓት በከተማው የኢንተርኔት አገልግሎት አልነበረም። ለዚህም ነበር ስለ ማይጨው ሁኔታ በወቅቱ መፃፍ ያልቻልኩ (ኢንተርኔት መጠቀም የሚቻለው በሞባይል ብቻ ነበር)። በወቅቱ የዓረና የማይጨው ከተማ አባላት የማይጨው ህዝብ ዓረና ፓርቲ በጠራው የእሁድ ህዝባዊ ስብሰባ እንዲሳተፍ ይቀሰቅሱ ነበር። ህዝቡም ለዓረና ጥሩ አመለካከት ነበረው። የዓረና አባላት ‘ዓረና’ የሚል ፅሑፍ ያለው ነጭ ቲ-ሸርት ለብሰው ነበር የሚቀሰቅሱ።
የህወሓት ሰዎችም ህዝብ በዓረና ስብሰባ እንዳይሳተፍ ለማድረግ የራሳቸው ቅስቀሳ ጀመሩ። ህወሓቶች ትልቅ ስፒከር ተጠቅመው በዕለተ እሁድ (በዓረና ስብሰባ) በማይጨው ከተማ የእግር ኳስ ውድድር ስላለ መላው ወጣት ተጫዋቾችን እንዲደግፍና እንዲያበራታታ ያውጁ ነበር።
የራያ ተወላጆች ያልሆኑ ካድሬዎች ለራያዎቹ በእሁድ ቀን በሚደረገው የዓረና ስብሰባ ሰው እንዳይሳተፍ እንዲመክሩና እንዲያስፈራሩ ተነገራቸው (ይህ መረጃ የተገኘው ከካድሬዎቹ ከራሳቸው ነው)። በስብሰባው የተሳተፈም እንዲመዘግቡ ትእዛዝ ተሰጣቸው። በተጨማሪም ሰው ለመያዝ ሲባል የተለያዩ ያልታሰቡ የህዝብ ስብሰባዎች ተጠሩ። አብዛኛው የማይጨው ወጣት በራሳቸው ስብሰባ እንዲገኝ አዘዙት። የችኮማዮና የመኾኒ ‘ስራ አጥ’ ወጣቶች ‘ስራ እንዲሰጣቸው’ ለእሁድ ስብሰባ ተጠሩ። እሁድ በስብሰባው የተገኘ ስራ እንደሚሰጠው፣ ያልተገኘ ግን ስራ እንደማያገኝ ተነገረው።
የማይጨው ህዝብም ለህወሓት ታሪክ ለመጀመርያ ግዜ የሙዚቃ ባንድ እንደሚመጣለት ሲነገረው ነበር። ህወሓት በማይጨው ከተማ የሙዚቃ ኮንሰርት ሲያዘጋጅ (ወይ አዘጋጃለሁ ሲል) ለመጀመርያ ግዜ ነው። ይህም ዓረና ህዝባዊ ስብሰባ በጠራበት ቀን ነው። እሁድ ቀን በስብሰባው ተሳታፊ ስለነበርን ህወሓቶች የራሳቸው ስብሰባ ስለማካሄዳቸው ሙሉ መረጃ አልነበረኝም። የሙዚቃ ኮንሰርቱ ስለ መሳካቱም እርግጠኛ አይደለሁም። የሙዚቃ ኮንሰርቱ ያልታቀደና ያልታሰበበት ስለነበረ ያልተሳካ ሙከራ ሊሆን ይችላል (ከተጋበዙት ሙዚቀኞች ቅሬታ ያሰሙ ነበሩ፤ በቂ ግዜ ስላልተሰጣቸው)።
እሁድ ጠዋት ሰው ዓረና ወደ ጠራው ስብሰባ መግባት ከመጀመሩ በፊት የተወሰኑ የፀጥታና የፕሮፓጋንዳ ሐላፊዎች አደራሹ አከባቢ ተሰብስበው ነበር። ወደነሱ አከባቢ ስንሄድ ተበትነው ጠፉ። አብዛኞቹ የማይጨው ካድሬዎችና ፖሊሶች ግን ተባብረውናል። ተሳታፊ እንዲሰልሉና እንዲያስፈራሩ የተላኩ ካድሬዎች ከጎናችን ነበሩ። ‘እንደምንም ብላቹ ህወሓትን ማባረር የምትችሉ ከሆነ ከጎናቹ ነን’ ይሉን ነበር። ላደረጉልን ትብብር እናመሰግናለን። ህወሓትን ከስልጣን ማባረር የምንችል ግን ሁላችን ስንተባበር ነው።
ህዝብ ወደ አደራሹ ገባ። ስብሰባውም ተጀመረ። እኛ ስለ ህወሓት መጥፎነትና የለውጥ አስፈላጊነት አወራን። ህዝቡም አስተያየት ሰጠ። ከህዝቡ የተረዳነው ነገር ቢኖር የራያ ህዝብ የህወሓትን መጥፎነት ከኛ በላይ ያውቃል። የህዝቡ ጥያቄ ህወሓትን እንዴት ከስልጣን ማውረድ ይቻላል? ዓረናስ አንዴ እየመጣ፣ ብዙ ግዜ እየጠፋ ህወሓትን ማሸነፍ ይችላል ወይ? ዓረናን ብንደግፍና ህወሓትን ከስልጣን ማባረር ባንችል ዋስትናችን ምንድነው? ህወሓት ሽፍታ ነው፤ ሊያጠፋን ይችላል ወዘተ የሚሉ ሐሳቦች ተነስተዋል።
ህዝቡ በሰጠው አስተያየትና ትንተና ተገርምያለሁ። ህዝቡ ለውጥ ይፈልጋል። በህወሓት መሪነት እምነት የለውም። ህዝቡ ያጣው ነገር ህወሓትን ሊያባርር የሚችል ዓቅም ያለው የተቃዋሚ ፓርቲን ነው። ህዝቡ የሚመራው ፓርቲ ካገኘ ለመታገል ዝግጁ ነው። ዓረና ቆራጥነት ካለው ህዝቡ ከዓረና ጎን ተሰልፎ እንደሚታገል ቃል ገብተዋል።
የማይጨው ስብሰባ ለየት የሚያደርገው ተሰብሳቢው በሙሉ የህወሓት ተቃዋሚ መሆኑ ነው። የህወሓት ካድሬዎች አልነበሩም። ሁላችን በአንድነት ለመታገል ቃል ስንገባ በአደራሹ የነበረ ሁሉ ቃሉ ሰጠ። አብረን ለመታገል ቃል ገባን። (ኩልና ብሓባር ንምቅላስ ንዓሪ ኢልና ዓረና)። ሦስት ሰዓት ተኩል የጀመረ ስብሰባችን ዘጠኝ ሰዓት ተኩል ተጠናቀቀ።
እኔ የተረዳሁት ነገር አለ። የህወሓት ስጋት ዓረና አይደለም። የህወሓት ስጋት የህዝብ ማወቅ ነው። ህወሓት የትግራይ ህዝብ የፖለቲካ እውቀት እንዲኖረው አይፈልግም። ምክንያቱም የትግራይ ህዝብ የፖለቲካ ንቃተ ህሊናው ከፍ ካደረገ ለህወሓት ካድሬዎች አሜን ብሎ አይገዛም። ካልተገዛ ደግሞ የህወሓቶች ህልውና ያበቃል። የህወሓቶች ጥረት ህዝብ በስብሰባው እንዳይሳተፍና አማራጭ ሐሳብ እንዳይሰማ መከልከል ነበር። ህወሓት የሚሰጋው ዓረና እንዳይቃወመው ሳይሆን ህዝቡ ፖለቲካ አውቆ እንዳይቃወመው ነው።
ይሄ ተንኮል ግን የህወሓት ዕድሜ ያራዝማል የሚል ግምት የለኝም።
It is so!!!

Sunday, December 15, 2013

በማንዴላ ሞት መንግሥቱን ከግፍ ለማንፃት? በልጅግ ዓሊ

December 15/2013


የማንዴላን ሕልፈተ ሕይወት ተመልክቶ በዓለም ደረጃ የሚያስደንቅ ሁኔታ ስናይ ሰነበትን። ማንዴላ የሠራውን መስራት ሳይሆን እሱ የታሰረበትን ዓላማ በተጻራሪ የሚተገብሩ ሁሉ በቀብሩ ላይ ለመገኘት ከተደበቁበት ብቅ ብቅ ማለታቸው የሚስደምም ነው።

በተለይ አንዳንዶቹ በተለያየ የመገናኛ ዘዴዎች ስለ ማንዴላ ጥሩ ምግባር ቃለ መጠይቅ የሰጡትን ስናጤናቸው ብዙ የሚያስተዛዝብ ሁኔታዎችን እንገነዘባለን። በሺህ መጽሐፍ፣ በሽህ ሬዲዩ ቢታገዙም በደም የወየበ ታሪካቸውን የማይሰርዝላቸው ፋሽሽቶች ይህችን ወቅት ተጠቅመው ለሕዝብ ሃሳቢ ሆነው ለመታየት መራወጣቸው የሚገረም ነው። ይህንን ወቅት ለመጠቀም “እኔም ነበርኩበት“ የሚለው ፋሽሽቱ መንግሥቱ ኃይለማርያምም ሳይቀር ከዚምባዌ ድምጹን አስምቷል።

ታሪክ እንደ ማንዴላ ያለውን ጀግናን ሲያከብር ቡከን ፋሽስትንም ሲኮንን ይኖራል። ይህንን መቀየር የሚችል ማንም አይኖርም። ማንዴላ እንዲህ የተወደደውን ያህል እነ ሒትለር፣ እነ ሙሶሎኒ ፣ እነ እስታሊን ደግሞ ሲኮነኑና ሲወገዙ ኖረዋል። ለወደፊቱም እንዲሁ። ታሪክ በሠሩት ግፍ ብዛት ከትውልድ ትውልድ እየተሸጋገረ ሲያወግዛቸው ይኖራል።

የማንዴላ ሞት ዜና በጎላበት ጀምበር በጀርመንም የናዚ ፋሽሽቶች መሪ ሒትለር ሲነሳ መሰንበቱ አንድ ሌላ አስገራሚ ክስተት ሆኗል። ትግሌ (ማይን ካንፍ ፣Mein Kampf ) ሒትለር እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር 1923 በመንግሥት ግልበጣ ሙከራ ምክንያት ታስሮ በነበረበት ወቅት የጻፈው መጽሐፍ ነው። ይህ መጽሐፍ እንደ ናዚዎች ማኒፌሰቶ ሆኖ ይታያል። መጽሐፉ በአይሁዳውያን ላይ ጥላቻን የሚያስፋፋና ጀርመኖች ምስራቅ አውሮፓንን መውረር እንዳለባቸው የሚቀሰቅስ ነው። በጀርመን ሕግ በተደነገገው መሠረት ይህን መጽሐፍ መልሶ የማሳተም መብት እገዳ (copy right) በ2015 ዓ.ም ያልቃል። ስለሆነም ማንም የፈለገ አካል የማሳተም መብት ይኖረዋል።

ይህንን ድንጋጌ በሚመለከት ጀርመን ውስጥ የጦፈ ክርክር ሲከናወን ሰንብቷል። እንደተለመደው የናዚ ደጋፊዎች ሒትለር ሃገሩን ይወድ ነበር፣ ለሃገሩ ጥሩ ሰርቷል . . . ወዘተ. የሚል ለሒትለር በታሪክ ጥሩ ቦታ ለመስጠት እንቅልፍ አጥተው ሰንብተዋል። ደጋፊዎቹ መጽሐፉን እንደገና ለማሳተም ሲታገሉ በተቃራኒው የቆሙት ደግሞ በሒትለር የተፈጸመውን ግፍ እያነሱ እንደ ሒትለር ዓይነት በዓለም ውስጥ ዳግም እንዳይነሳ መጽሐፉ መልሶ መታተም እንዳይችል ሲታገሉ ተስተውሏል።

በጀርመን ሃገር ባይረን ተብሎ በሚጠራው ክፍለ ሃገር ግን በ2015 የሚልቀውን የማሳተም መብት በመጠቀም የሒትለር መጽሐፍ እንደገና ለማሳተም የተደረገው ጥረት ከሽፏል። የባየር አስተዳዳሪዎች በሒትለር የተጨፈጨፉትን በማክበር መጽሐፉን እንደገና ማሳተም ኢ-ሰባዓዊነት ነው ሲሉ ወስነዋል።


የክፍለ ሃገሩ መንግሥት ብዙ በሒትለር የተጎዱ ቤተሰቦችን አነጋርግሮ ይህንን መጽሐፍ ማሳተም በቤተሰቦቹ ላይ ሕመምን መቀስቀስ እንደሚሆን አሳምኖ ማሳተምም ሆነ ማባዛትን እንደገና ከልክሏል። ይህ ውሳኔ ፋሽሽቶችን ለሚቃወሙ ጀርመኖች ትልቅ ድል ነው።

ይህ ዓይነት ትግል የሚደረገው በጀርመን ብቻ መሆን የለበትም። በእኛም ሃገር ይህ ዐይነቱ አመለካከት ሊዳብር ይገባል። ወያኔ ስልጣን ከወጣ በኋላ የተጀመረውን የጎጠኝነት ፖለቲካ ለመቃወም የተጀመረው ትግል የመንግሥቱ ኃይለማርያምን ወንጀል ለጊዜው ወደ ጎን አድርጎ ትግሉ በወያኔ ላይ ትኩረት ሰጥቶ ቀጥሏል። ግን ይህ ሃገርን የማስቀደም ክቡር ዓላማ በመንግሥቱ ደጋፊዎች ሲጣስና የመንግሥቱን አረመኔነት ለማድበስብስ የሚደረገው ጥረት ብልጭ ድርግም ማለት ከጀመረ ሰነባብቷል።

የፋሽሽቱ ደጋፊዎች መሪያቸው ከወደቀ በኋላ ስለ መሪያቸው ትልቅነት ማውራት የተለመደ ባህሪያቸው መሆኑንም ታዝበናል። እዚሁ ጀርመን ውስጥ ሒትለር ሃገሩን ይወድ ነበር እንደሚሉት የፋሽሽት ደጋፎዎች ማለት ነው። የሒትለር ደጋፊዎች ለዚህም ድጋፋቸው የሚያቀርቡት ምክንያት ባንድ ወቅት ከየሃገሩ በሰበሰባቸው እስረኞች ያሰራው አውራ መንገድ (Autobahn) ሁል ጊዜ ይጠቀሳል። “ሒትለር ቢኖር ኖሮ ጀርመን የትና የት በደረስች ነበር“ በማለት ዓመኔታ ለመሸመት ይጥራሉ።

እነዚህ የአስተሳሰብ-ደሃ ጀርመኖች በዴሞክራሲ ካገኙት የዓለም የኤኮኖሚ ትልቅነት ይልቅ የእነርሱ ዘር ትልቅነት ላይ የተመረኮዘው የሒትለር ዓላማ ታላቅነትን የሚያጎናጽፋቸው ይመስላቸዋል። ለዚህም የሒትለርን መሪ መፈክር አንግበው ሲጓዙ ይታያሉ። በአሁኑ ሰዓት ያለውን የዓለም ሥርዓትና ይህም ሥርዓት ለጀርመን ሕዝብ የሰጠውን ጥቅም የሚያውቀው የጀርመን ሕዝብ ሥርዓቱን በማናጋት ይህንን የተንደላቀቀ ኑሮውን ለማበላሸት የሚጥሩትን ወገኖች ዕድሉ እንዲሰጣቸው ብዙሃኑ የጀርመን ህዝብ ፍላጎት የለውም።

ፋሽሽቶችን ከፍ አድርጎ ለማሳየት የሚደረገው ጥረት በጀርመን ብቻ ሳይሆን በኢጣሊያም ይታያል። በቅርብ ጊዜ ግራዚያኒ ሐውልት ተሰርቶለታል። ሞሶሎኒንም እንደ ጀግና የሚቆጥሩ አልታጡም። በተለይ በፋሽሽቱ ሥርዓት ጥቅም ያገኙ የነበሩ ወገኖች የሌላው ሕብረተሰብ ቁስል አይሰማቸውም። ይልቁንም እንጨት ሊሰዱበት ይፈልጋሉ።

በእኛም ሃገር የሚስተዋለው ከዚህ የተለየ አይደለም። “መንግሥቱ ሃገር ወዳድ ነው “፣ “መንግሥቱ ቢኖር እንዲህ አይደረግም“፣ “መንግሥቱ ቆራጥ ነበር“. . . . ሌላም ሌላም ብዙ ከሥርዓቱ ጥቅመኞች የምንሰማው ባዶ ጩኽት አለ። ቆራጥነቱንም በፍርጠጣው፤ ሃገር ወዳድነቱም የተማረ የሰው ኃይል እንዳይኖር በቀይ ሽብርና በሌሎቹ የግድያ ዘዴዎቹ አስመስክሯል። ወንጀሉ የመንገድ ላይ ስጦ ሆኖ የተመለከትነው ነው። ለሃገራቸው አንድነትና ልዋላዊነት አጽማቸውን ሲከሰክሱ የነበሩ ጀግኖች በመንግሥቱ ነፍስ ገዳዮች ከሃዲ እየተባሉ ሲገደሉ፣ ፈሪ ፈርጣጩ ቡከን ጀግና ተብሎ ሲወደስ መስማት ውርደትም ሃፍረትም ይሆናል። እነዚህ ጀግኖችን እየሰደቡ ይጽፉ የነበሩ አሁን ደግሞ በውጭ ሃገር የዚህ ፋሽሽት ቆዳ ለማዋደድ የሚደርጉት ጥረት የሚያሳፍር ነው። ለመሆኑ በዚህ ዓይነት ክህደት ይች ሃገር ከወያኔ ነጻ ትወጣለች ብለው ያስቡ ይሆን?

የመንግሥቱ ደጋፊዎች ሰሞኑን የኔልሰን ማንዴላን ሕልፈተ ሕይወት ምክንያት በማድረግ የሃገራችንን ፋሽሽት አረመኔው መንግሥቱን ቃለ መጠይቅ በማድረግ ፋሽሽታዊ የሆነውን ገጽታውን እንደገና ለማደስ ጥረት አድርገዋል። ደጋፊዎቹ ይህንን ቡከን ፋሽሽት ከሃገሩ አልፎ ለዓለም አቀፍ ጭቆና እንደታገለ ሊነግሩን ይፈልጋሉ። እነዚህ የመገናኛ ዘዴዎች መንግሥቱን ቃለ መጠይቅ በማድረግ በመንግሥቱ በግፍ የተገደሉትን ወገኖች መልሰው ለመግደል ይጥራሉ። በሕይዎት በተረፉትና የወላድ መኻን በሆኑት ወላጆች ቁስል ላይ ጨው እየነሰነሱ መሆናቸን እንዲገነዘቡ አስታዋሽ የሚሹ ይመስላሉ። እንደ ባየር ክፍለ ሀገር ጀርመኖች የሌሎች ሃዘን ሳይሰማቸው የዚህን አረመኔ ፋሽሽታዊ ገጽታ ለማሳመር ጥረት አድርገዋል። ይህ ደግሞ የሚያሳፍር እንጂ የሚያኮራ ድርጊት አይሆንም። ከማሳፈርም አልፎ በመንግስቱ ኃይለማርያም የተገደሉትን ሰማዕታት መልሶ እንደመግደል መግደል ይቆጠራል። በሃገር ላይ የተሰራ ወንጀልም ነው።

በቃለ መጠይቃቸው ላይ ማንዴላን የጦር ሥልት በማስተማር ትልቅ ጥረት ያደረጉትን እነ ጀኔራል ታደሰ ብሩን ለምን መንግሥቱ ራሱ እንደገደላቸው እንኳን ማንሳት አልፈለጉም። ሳያውቁት ቀርተው አይደለም ነገሩን ሳያነሱት የቀሩት። እንደተለመደው መጠየቅ የሚገባቸውን ሃቆች በመሸፈን የፋሽሽቱን ቆዳ የሌለውን መልክ እንዲኖረው ለማድረግ እንጂ።


እነዚህ የሬዲዮ ጣቢያ ሃላፊዎች የመንግሥቱ ጉዳይ መነሳት ለጸረ ወያኔው ትግል ከፋፋይ መሆኑ አይታያቸውም። ከፋፋይ መሆኑም ቢያውቁም ከመንግሥቱ ይበልጥ ሃገር በወያኔ ብትፈርስ ድንታ እንደሌላቸው ነው ድርጊታቸው የሚያሳየን። የብዙሃኑ ጸረ ወያኔ ትግል መንግሥቱን ሥልጣን ላይ ወይም ደጋፊዎቹን ስልጣን ላይ ለመመለስ እንዳልሆነ ግልጽ ነው። ትግላችን ዘረኝነትን አጥፍተን ዴሞክራሲን መገንባት መሆኑ ያልገባቸው ካሉ ትልቅ ስህተት ላይ ወድቀዋል። በኢሠፓ አባልነታቸው እንደገና ወደ ስልጣን ተመልሰን እንወጣለን ብለው አስበው ከሆነ ተስፋ ሊቆርጡ ይገባል። ምንም ይሁን ምን ወደ ኋላ አንመለስም።

መንግሥቱ በሃገር መክዳት ለፍርድ መቅረብ እንጂ እንደ ጀግና በየቦታው ቃለ መጠይቅ እየተደረገለት የእሱ ቆዳ ተገልብጦ እንዲለበስ ጥረት መደረግ የለበትም። ከሃገር ሰርቆና ዘርፎ በፈረጠጠው ገንዘብ የሚገዛው የዕውቅና የሃገር ወዳድነት ጃኖም ሊኖር አይገባም። የወንጀለኛ ቆዳ እንጂ። ንፁህ ነን የሚሉ ካሉ በዚህ ጉዳይ ላይ ራሳቸውን ከፋሽሽቱ በመነጠል ግልጽ የሆነ አቋማቸውን ሊያሰሙ ይገባል።

በተለይ በሕዝብ ገንዘብ የተቋቋመ እንደ ኢሳት ዓይነት የዜና ማሰራጫ በመንግሥቱ ግፍ የተሰራባቸው ሁሉ እርዳታቸውን የለገሱት መሆኑን አስተዳዳሪዎቹ ልብ ሊሉት ይገባል። እርዳታቸውን ለጠላታቸው ማስተዋወቂያ ሲያደርጉት ሊያጡት የሚችሉትን ድጋፍ መመዘን ብልዕነት ነው። ለምን ቢባል ጥያቄው የሞራል ጥያቄ ነውና!! አሊያ ግን የኢሳትን ዓላማ ጥርጣሬ ውስጥ ይከተዋል።


ለኢሳት ገንዘብ በማሰባሰብ ጥረት ያደረጉ “የሰበዓዊ መብት ታጋይ ነን” የሚሉ ደግሞ ይህ ድርጊታቸው ለሁሉም የሰው ዘር ሰብዓዊ መብት መከበር እንዳልቆሙ ያጋልጣቸዋል። ያገኙት ተሰሚነትም ፀሐይ እንደነካው በረዶ ሊቀልጥ ይችላል።

ይህንን አረመኔ ለፍርድ ይቅረብ ብለው ሲናገሩ ያልተሰሙ፣ በመንግሥቱ ስለተጨፈጨፉት ሲናገሩ ያልተደመጡ፣ ለፍትህ ያልቆሙ፤ ዛሬ ለዚህ አረመኔ መድረክ መስጠታቸው የሃገሪቱ ዜጎች ሁሉ በእኩል አይን እንደማያዩ ድርጊታቸው አጉልቶ ያሳየናል። ሌላው ቢቀር ማንዴላን በሚመለከት ባለውለታዎች ሲነሱ ጀኔራል ታደሰ ብሩም ሆነ ማንዴላን በብዙ የደገፉ የቀዳማዊ ኃይለስላሴ መንግስት ባለስልጣናት የአሟሟት ሁኔታም መጠቀስ ነበረበት። ታሪክ ግማሽ የለውምና ሙሉው የኢትዮጵያውያን አስተዋጽኦ በዘገባው መካተት ነበረበት።


ወያኔን አስወግደን ሃገራችንን ዴሞክራሲያዊት እናደርጋታለን ብለን የምናስብ ሁሉ ከደርግና ከመንግስቱ ኃይለማርያም ፋሽሽታዊ ወንጀል ራሳችንን ነጥለን መንግሥቱም ይሁን ወያኔን የህዝብ ጠላትነታቸውን አውቀን ካልሄድን ሃገራችንን ከወያኔ ጭቆና ነጻ የምናወጣበትን ቀን እናራዝመዋለን። ትግሉ ጥርት ብሎ ለዴሞክራሲ ካልሆነ በስተቀር ከሃገር በተሰረቀ ገንዘብ መልሰን ስልጣን እንወጣለን በሚል እቅድ መጓዝ በሃገሪቱ ውስጥ ሊነሳ የሚችለውን ችግር አለማጤን ይሆናል። ማንም ከድጡ ወደ ማጡ መሄድ የሚፈልግ አይኖርም።

መንግሥቱን ለቃለ መጠይቅ የጠሩ የሬዲዮ ጣቢያዎች ይህንን በማድረጋቸው ምን ያህል ከወያኔ ጋር የሚደረገውን ትግል እንደከፋፈሉ ካልተረዱ የሚያሳዝን ነው። በዚሁ አጋጣሚም የሕዝብ ድጋፍ እንደሚያጡ ሊረዱት ይገባል። ነጻ ፕረስ ሃላፊነት የጎደለው ፋሽሽቶችን ማመጻደቂያ ሊሆን አይገባምና ከዚህ መጥፎ ምግባር መቆጠብ አስተዋይነት ይመስለኛል።

ሂትለር፤ ጀኔራል ፍራንኮ፤ ሞሶሎኒ፤ መለስ ዜናዊ፤ መንግስቱ ኃይለማርያም፤ (በቁም የሞተ) ሁሉም ፋሽሽቶች ሞተዋል። ስማቸው ግን ከታሪክ ጠባሳ ገጾች አይፋቅም። ባንጻሩ ጋንዲ፤ ማንዴላ፤ ማርቲን ሉተር ኪንግና ሌሎቹም ጀግኖች ሞተዋል። ግን ሰማዕታት ናቸው። ታሪካቸውም በጀግንነት የወርቅ ቀለም ተጽፎ ትውልድ ሲወራረሰው ይኖራል። የሁለቱም ወገኖች ስም ከመቅበር በላይ ውሏል። ሆኖም የፋሽሽቶቹ የነ ሂትለር በፀረ-ህዝብነት፤ የነማንዴላ ግን በህዝባዊነት!!

በፋሽሽቶች ለተጨፈጨፉ ሁሉ የሚያስብ በሰላም ይክረም !

ታህሳስ 2006

Beljig.ali@gmail.com