Thursday, January 23, 2014

አንባ ገነኑን የወያኔን መንግስት በቃ ልንለው ይገባል (ገዛኸኝ አበበ ከኖርዌይ )

ከገዛኸኝ አበበ
January 22/2014

ማብቄያ የሌለው የወያኔ አረመናዌ ድርጊት ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ በመጣበት በዚህ ጊዜ ሰሞኑን ለእራሴ አንድ ጥያቄ ጠየቁትኝ እስከመቼ ነው የወያኔ መቀለጃ እና መጫወቻ ሆነን የምንኖረው እስከመቼ ነው ወያኔ ህዝባችንን እያሰቃየ እና እየጨቆነ የሚኖረው እስከመቼ ነው ዜጓች መብታቸው ታፍኖና ነጻነታቸው ተረግጦ በሃገራቸው መብታቸው ሳይከበር እንደ ዜጋ ሳይሆን እንደ ሁለተኛ ዜጋ እየተቋጠሩ የሚኖሮት እኔ እንደማስበው በአሁኑ ጊዜ ሀገራችንን እየመራ ያለው የወያኔ መንግስት  ኢትዮጵያንና ኢትዮጵያውነትን ሊያጠፋ የተነሳ መንግስት ይመስለኛል ግን እስከ መቼ ነው የወያኔ ኢህአዲግ መንግስት በዚህ ርኩስ ባህሪውና ድርጊቱ የሚቀጥለው ? በቃልንለው ይገባል::

መቼም ይህ ጥያቄ የሁላችንም ሀገር ወዳድ እና ነጻነት ናፋቂ ኢትዮጵያኖች ጥያቄ ይሆናል ብዬ አስባለው እስከመቼ _?

 እኛ ኢትዮጵያኖች መብታችን ተረግጦ  ነጻነታችን ተገፎ በዲሞክራሲ ቸነፈር ተመተን መኖር ከጀመርን ይኸው ከድፍን ሁለት አስር አመታቶች በላይ አስቆጠርን በእነዚህ  ዓመታቶች ብዙዎች ለዲሞክራሲ፤ ለፍትህና ለነፃነት ታግለዋል አሁንም ቡዙዎች በሚችሉት መንገድ ሁሉ ይኼ ዘረኛውን እና አንባ ገነኑን የወያኔን መንግስት እየተፋለሙት ይገኛሉ::ነገር ግን ለዲሞክራሲ፤ ለፍትህና ለነፃነት የታገሉ ብዙዎች  በብዙ ሺህ የሚቆጠሩ  ዜጎች አልቀዋል፤ ለስደትም ተዳርገው ለብዙ መከራ ሰለባ ሆነዋል፡፡ ቁጥራቸው እጅግ ብዙ የሆነ የሀገሪቷ ዜጓች ደግሞ በአሁኑ ሰዓት በሀገሪቱ በሚገኙ እስር ቤቶች ታስረው በወያኔ ካድሬዎች ጭካኔ የተሞላበት ኢ ሰበአዊ ድርጊት እየተፈጸመባቸው በሰቃይ እና በመከራ ውስጥ ሲገኙ አንዳንዶቹም በሚደርስባቸው ስቃይ እና በወያኔ መጥፎ ሴራ እዛው ወህኒ ቤት ውስጥ እይውታቸው እያለፈ ይገኛል:: ለዚህ ማሰረጃ የሚሆነን  በቅርቡ ከጅጅጋ 25 ኪሜ ገደማ እርቃ በምትገኘው ቀብሪበያህ እስር ቤት ውስጥ የሞቱት ከ40 በላይ የሚሆኑ ንጹሃን ኢትዮጵያ ዜጓቻችን ምስክር ነው:: አረ ስንቱ ይዘረዘራል የወያኔ መንግስት በኢትዮጵያ ህዝብ ላይ እያደረሰ ያለው በደል ቢዘረዘር ማለቂያ የለውም :: ወያኔ በስልጣን በቆየባቸው በእነዚህ አመታቶች ከጊዜ ወደ ጊዜ ነገሮች መሻሻል እና መስተካከል ሲገባቸው ነገሮች ሁሉ በተገላቢጦሽ  እስራቱ፣ግድያው፣ስደቱ፣ድህነቱ ፣ ሁሉ ነገር እየባሰ እና ከጊዜ ወደ ጊዚ እየጨመረ መምጣቱ ሀገራችን ኢትዮጵያ በጣም አሳሳቤና አስጌ  ሁኔታ ላይ እንደምትገኝ አመልካች ነገር ነው::

ወያኔዎች እኔ ከሞትኩኝ ሰርዶ አይብቀል እንደሚባለው  የሀገሬቱን ሀብት እየዘረፉ እና እየቦጠቦጦ እንዳሻቸው መኖርን አልበቃም ብሏቸው ቅንጣትም ያክል ስለ ኢትዮጵያም ቢሆን ስለ ኢትዮጵያዊነት ግድ እንደሌላቸው በሚያሳይ መንገድ  በማን አለብኝነትና በግድ የለሽነት  ለግል እና ለእራሳቸው የፖለቲካ ጥቅም ቀደምት አባቶቻችን ለሀገራችን ዳር ድንበር መስዋዕት የሆኑለትን እና ደማቸውን ያፈሰሱለትን መሬታችንን ድንበራችንን እንኮን ሳይቀር ለባህድ አገራት በመስጠት ላይ እንዳሉ ሲሰማ ማንንም ኢትዮጵያዊ የሆነ ዜጋ ሁሉ የሚያስቆጣ እና የሚያንገበግብ ነው ብዬ አስባለው:: በጣም የሚገርመው እና የሚያሳዝነው ነገር ወያኔዎች  የገዛ ወገኖቻችንን የሀገሪቱን ዜጓች ሀብት እና ንብረት ካፈሩበት ሀገርና መሬት ላይ ሀብትና ንብረታቸውን እየዘረፉና ቤታቸውን እየፈረሱ ከሚኖሩበት ቄዬ እያባረሩ ለውጭ አገር ሰዎች ደግሞ የሀገሬቷን መሬት እየቸበቸቡ መኖርን የለመዱበት ተግባራቸው መሆኑ ነው :: 
እያደር ብዙ ይሰማል እንደሚባለው የወያኔን መንግስት  አሁንም ዝም ካልነው ሌላ ብዙ አስርት የመከራ አመታትን መጋፈጥ ሊኖርብን ነው፡፡ እስከመቼ ዝም እንደ ምንለው ግን ወገን አይገባኝም ፡፡ ወያኔ እያደረገው ስላለው አረመናዊ ድርጊቶ ፋታ ልንሰጠው አይገባም ::  አሁንም ህፃን፤ ወጣት፤  ጐልምሳና አዛውንት ወገኖቻችን ሲረግፍ፤ ሲሰደዱ ፣ የኢትዮጵያ ገጽታ ሲበላሽና ፣ በደምና በአጥንት መስዋዕትነት ተከብሮ የቆየውን የሃገራችንን ዳር ድንበር የወያኔ መንግስት ለባዕድ አሳልፎ ሲሰጥ ማየት ከሆነ ህልማችን መልካም! ግን ይህንን የሚያልምም ሆነ የሚመኝ ንፁህ ኢትዮጵያዊ ያለ አይመስለኝም፤ ከራሳቸው ከወያኔ ሆድደር ካድሬዎች በስተቀር፡፡ ስለዚህ ወገኔ ሆይ ይህንን መንግስት ዝም ብለን ልናየው አይገባም፡፡ ወይም እንደ ፈለገ ሊፈነጭብን ቦታ መስጠት የለብንም፡፡ እስካሁን በኢትዮጵያ ህዝብ ላይ ያደረሰው ጭቆናና በደል እንዲያውም በምን አለብኝነት የኢትዮጵያን ቅርጽ እና ታሪክ የሚያበላሸውን የወያኔ እንቅስቃሴ  ሁሉም የኢትዮጵያ ዜጋ ዘር፣ ጎሳና ፆታ ሳይለይ ኢትዮጵያንና ኢትዮጵያውነትን እያጠፋ ባለው በወያኔ መንግስት ላይ ሆ ብለን በአንድነት በመነሳትና በመጮህ ይበቃል ልንለው እና ልናስቆመው  የግድ ነው፡፡ 

በቃ በቃ በቃ !!!

      ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኖራለች!!!

Thursday, January 9, 2014

የቀደምቶቹን ወንጀል ለማጋለጥ መቃብር ሲምስ የኖረው ወያኔ በራሱ ጦር ካምፕ ውስጥ የተገኘውን አስከሬን መደበቅ ለምን አሰፈለገው?አዲስ አበባ ከተማ ውስጥ ፈረንሳይ ለጋሲዮን በሚገኘው የክብርዘበኛ ጦር ካምፕ ውስጥ ማንነታቸው ያልታወቁ የ6 ዜጎች አስከሬን ለመንገድ ሥራ በተሠማሩ ቆፋሪዎች አማካኝነት መገኘቱ የሰሞኑ አሳዛኝ ዜና ነው።
አንድ አይነት ቀለም ባላቸው ብርድ ልብሶች ተጠቅልለው ከተገኙ 6 አስከሬኖች የመጀመሪያዎቹ ሁለት ሰለባዎች ታስረውበት የነበረው የእጅ ሰንሰለታቸው እንኳ እንዳልወለቀና ከተቀሩት የአንዱ እጆች ደግሞ የፍጥኝ ወደ ኋላ እንደታሰሩ መገኘታችው ግድያው በቅርብ እንደተፈፀም አንዱ አስረጂ ነው።
በእንዲህ አይነት ጭካኔ የተገደሉ ዜጎች አስከሬን መገኘት በመንግሥት ተብየው አካል ካለመገለጹም በላይ ግቢውን በማስተዳደር ላይ የሚገኘው 3ኛ ክፈለ ጦርም ሆነ በግብር ከፋይ ገንዘብ የሚተዳደሩ መገናኛ ብዙሃን እስከዛሬ አንድም ቃል መተንፈስ አለመፈለጋቸው ጉዳዩን እጅግ የሚያሳዝን ብቻ ሳይሆን የሚያስገርምም አድርጎታል። ይባስ ተብሎም በመንገድ ሥራ ቁፋሮው የበለጠ አስከሬን ሊወጣ ይችላል በሚል ስጋት አካባቢው በፖሊስ እንዲታጠር ከተደረገ በኋላ ሥራውም እንዲቋረጥ ተደርጓል።
በፓለቲካ መስመር ልዩነት ምክንያት ደርግ ያለ ርህራሄ የጨፈጨፋቸውን ከመቃብር እያወጣ ዘመድ አዝማድ በማላቀስ የፖለቲካ ትርፍ ለማግኘት ሲዳክር የኖረ አገዛዝ በእንዲህ አይነት አሳዛኝ ሁኔታና አጋጣሚ የተገኘውን የጅምላ አስከሬን አይቶ አንዳላየ ለማለፍ መሞከሩ ለምን ይሆን?
አብዛኛው የአዲስ አበባ ነዋሪ እንደሚያስታውሰው የክብር ዘበኛ ጦር ካምፕ በመባል የሚታወቀው የጃን ሜዳ 3ኛ ክፍለ ጦር ግቢ ድህረ ምርጫ 97 ወያኔ ለጅምላ እስር ቤትነት ከተጠቀመባቸው የማጎሪያ ቦታዎች አንዱ ነበር። ከዚያን ጊዜ በፊትና በኋላም ቢሆን ካምፑ በወያኔ ጠላትነት ተፈረጀ በጸጥታ ሠራተኞች ከታገቱ በኋላ አድራሻቸው እስከዛሬ ተሰውሮ ላሉ በርካቶች በምስጢር እስርቤትነት በማገልገል ላይ ከሚገኙ ወታደራዊ ካምፖች አንዱ እንደሆ ይታወቃል።
ዘመድ አዝማዶቻቸው ይመለሳሉ ብለው ሲጠብቋቸው ሳይመለሱ እንደወጡ የሚቀሩ በርካታ ዜጎች አሉ። በእንዲህ ሁኔታ ወጥተው ከቀሩ መካከል ከሰሞኑ የስድስቱ መቃብር በአጋጣሚ ተገኝቷል። የተገነዙበት ብርድ ልብስ ይነትብና ምንም ዓይነት ብልሽት ሳይደርስበት መገኝቱ ግዲያው በህወሃት ዘመነ መንግስት ስለመፈፀሙ ጥሩ ማስረጃ ነው። ለህወሃት ሰው መግደል ሥራ እንጂ ወንጀል አይደለም። በህወሃት ነፍሰ ገዳይ ይሞገሳል ይሾማል እንጂ አይወቀሰም አይጠየቅም። የስድስቱ ስዎች አስከሬን ሲገኝ መንግስትነኝ የሚለው ህወሃት አይቶ እንዳላየ መሆን ብቻ ሳይሆን ሌሎች አካላትም የሥፍራውን ሚስጢር እንዳያዩ ከልክሏል።በቁጥጥሩ ሥር ያሉ መገናኛ ብዙሃንም ዜናውን እንዳይናገሩ ታግደዋል። ህወሃት ከሚሰራቸው አስገራሚ ወንጀሎች መካከል አንዱይሄው ነው። ይሄ ግድያ በሌላ አካል ተፈፅሞ ቢሆን ኑሮ በረከት ስምዖንና እና ሺመልስ ከማል እየተፈራረቁ ያደነቁሩን ነበር።ይሄ የራሳቸው የእጅ ሥራነውና አይነገርም። የሄንንም የሚናገር እንደ ኢሳት ያለ ነፃ ሚዲያ ካለም ይታፈናል። አሸባሪም እየተባለ ይፈረጃል።
ግንቦት ሰባት የፍትህ የነጻነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ እነዚህ ዜጎች በህወሃት ተግድለው እንደተጣሉ ያምናል። ውሎ አድሮ እውነቱ እስከሚወጣ ድረስ ግን ዜጎች በሙሉ ይሄን ግድ በተመለከተ መረጃ የመሰብሰብና የማሰረጫት ሥራችውን አጠናክረው እንዲቀጥሉ እናሳስባለን። ይሄን ወንጀል የፈፀሙ አካላት መጠየቅ አለባቸው። የዜጎች ደም እንዲሁ በከንቱ ፈሶ መቅረት የለበትም።
ለኢትዮጵያ ህዝብ መብትና ጥቅም እንታገላለን የሚሉ የፖለቲካና የስቪክ ድርጅቶች እንዲሁም ለሰው ልጆች የሰብአዊ መብት የሚሟገቱ ሁሉ የተገኘው አስከሬን በአስቸኳይ ተመርምሮ ማንነታቸው ለቤተሰቦቻቸውና ለወዳጅ ዘመዶቻቸው እንዲገለጽ፤ ተጨማሪ አስከሬን ሊገኝ ይችላል በሚልስጋት የመንገድ ቁፋሮውን ከሰዎች እይታውጪ ለማካሄድ እንዲቋረጥ የተደረገው ሥራ ለህዝብ እይታ ግልጽ በሆነመንገድ በአስቸኳይ እንዲጀመር የመጠየቅ ሃላፊነታቸውን እንዲወጡ ግንቦት 7 ያሳስባል::
በዚህአጋጣሚ ወያኔ ሥልጣን ከተቆጣጠረበት ጊዜጀምሮ በሱማሌ፣ በጋምቤላ፣ በአዋሳ፣ በጎንደር፣ በአዲስ አበባና ሌሎች የአገራችን ክፍሎች በጠራራ ጸሃይ ካስጨፈጨፋቸው በተጨማሪ በፖለቲካ እምነታቸው ምክንያት ታግተው በየእሥርቤቱ የተወረወሩትንና ከታገቱበት ዕለት ጀምሮ እስከ ዛሬ የደረሱበት ያልታወቁ ወገኖቻችንን ዝርዝር በአስቸኳይ ያሳውቅ ብለን አንመክረውም።እኛ ግን ህወሃት የደበቀውን ወንጀል ሁሉ ህዝብ እንዲያውቀው ለማድረግ ያለምንም ማቅማማት ጠንክረን እየሰራን ነው። መንግስት ነኝ ብሎ በሥልጣን ላይ የሚወጣ ማንኛውም አካል የህዝብ አገልጋይ እንጂ ነፍሰገዳይ እንዳይሆን የጀመርነው ትግል ተጠናክሮ ይቀጥላል።
እንግዲህ ህወሃት በህዝባችንና በአገራችን ላይ የሚፈጽመውን ሰቆቃ ለማስቆም ግንቦት 7 የጀመረውን የነጻነት ትግል አጠናክሮ እንደሚቀጥል እያስታወቅን እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ እንዲህ በየቦታው ተገድሎ ከመጣል ራሱን ለመታደግ ሲል የነፃነቱ ትግል አካል እንዲሆን ጥሪያችንን አሁንም ደግመን እናቀርባለን::
ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ !!

የኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር ሠራዊት ወታደራዊ ጥቃት ፈፀመ፡፡

በሀገራችን ላይ የተንሠራፋውን አምባገነናዊ ሥርዓት ገርስሶ ለመጣል የመጨረሻ አማራጭ የሆነውን የትጥቅ ትግል በማካሄድ ላይ የሚገኘው የኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር ሠራዊት በጠላት ላይ የሚወስዳቸውን ወታደራዊ የማጥቃት እርምጃዎች አጠናክሮ በመቀጠል በታህሳስ 23 ቀን 2006 ዓ/ም በሰሜን ጎንደር በላይ አርማጭሆ ወረዳ ልዩ ስሙ ገራርዋ ባምብላ ወንዝ በተባለው ቦታ መሽጎ የአካባቢውን ህብረተሰብ ሲያሰቃይና ሲያንገላታ ከነበረው የወያኔ 24ኛ ቴዎድሮስ ክ/ጦር እና ከፀረ-ሽምቅ ታጣቂ ኃይሎች ጋር ባደረገው ውጊያ 24 የጠላት ወታደሮችን ገድሎ 11 በማቁሰል የግንባሩ ሠራዊት አንፀባራቂ ድል አስመዝግቧል፡፡ በዚሁ ዕለትም በተደረገው እልህ አስጨራሸ ውጊያ የወያኔ 24ኛ ቴዎድሮስ ክ/ጦር ከኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር ሠራዊት የሚደርስበትን የተኩስ ናዳ መቋቋም ተስኖት ሙትና ቁስለኛውን እያዝረከረከ እግሬ አውጪኝ በማለት መፈርጠጡን ታውቋል::
ይህ በእንዲሀ እንዳለ የአካባቢው ነዋሪዎች የኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር ሠራዊት በጠላት ላይ ባስመዘገበው ከፍተኛ ወታደራዊ ድል መደሰታቸውና ወደፊትም ሀገራዊና ሕዝባዊ አላማን አንግቦ የህብረተሰቡን እምባ በማበስ ግንባር ቀደም በመሆን ለሀገርና ለወገን ደራሽነቱን እያስመሰከረ የሚገኘውን የኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር ሠራዊትን በመደገፍ የቆመለትን አላማ ከግብ ለማድረስ ዝግጁ መሆናቸውን ገልፀው ግንባሩ በተከታታይ ጊዜያቶች የሚወስዳቸው ወታደራዊ ጥቃቶችና የሚያስመዘግባቸው አንፀባራዊ ድሎች የወገንን አንጀት በማራስ በአንፃሩ ደግሞ የጠላትን አንገት በማስደፋቱ እጅግ ደስተኛ መሆናቸውንም ገልፀዋል፡፡
በመጨረሻም የአካባቢው ህብረተሰብ ለኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር ሠራዊት የጀግና አቀባበል ያደረጉለት ሲሆን ወታደራዊ የማጥቃት እርምጃው ተጠናክሮ እንዲቀጥል የበኩላቸውን አስተዋፅኦ ለማበርከት ከግንባሩ ሠራዊት ጎን በመሰለፍ ሀገራዊ ግዴታቸውን ለመወጣት ቆርጠው መነሳታቸውን አስታውቀዋል፡፡
 የኢትዮዽያ ህዝብ አርበኞች ግንባር

Wednesday, January 8, 2014

በኢትዮጵያ መንግስት የሚታገዘው እና እራሱን ነጻ ፕሬስ ነኝ የሚለው የጋዜጠኞች ግሩፕ እስክንድር አይፈታም ብለው አመጹ

January8/2014
 
 በኢትዮጵያ መንግስት  የሚታገዘው እና የበረከት ስምኦን ሁለተኛ ድምጽ እየተባለ የሚጠራው የኢትዮጵያ ጋዜጠኞች ስብስብ  እስክንድር ነጋ አይፈታም ሲሉ ለመንግስት ጉዳዮች መምሪያ ገልጸዋል  ከዓለም አቀፍ የጋዜጠኞች መብት ተከራካሪ ተቋማትም እስክንድር ነጋ ሽብርተኝትን፣ ፋሺዝምንና ናዚዝምን በሚያበረታታ እንቅስቃሴና አስነዋሪ ተግባራት ውስጥ ሲሳተፍ የቆየ ከመሆኑ ሌላ በጋዜጠኝነት ሙያም በየትኛውም ሚዲያ እንደማይሠራ በመረጋገጡ ምንም ዓይነት ድጋፍና እገዛ እንደማያደርጉ ወስነዋል ሲሉ የሽብር ወሬአቸውን ሲነዙ የቆዩ እንደሆነ የሚያሳየው ይሄው ዘገባ የኢትዮጵያን ህዝብ እንዳስቆጣ አንዳንድ ህብረተሰቦች ለማለዳ ታይምስ በፌስቡክ ፔጅ ገልጸዋል ።
 
        እንደማህበር እራሱን የሚጠራው እና የቀድሞው የጋዜጠኞች ማህበር  ፈርሶአል እያለ ህብረተሰብን ግራ የሚያጋባው እና በአለም አቀፍ እውቅና የሌለው ይሄው በእነ አቶ ወንደሰን እና አንተነህ ፣ በአቶ በረከት ስምኦን እርዳታ በ1997 አመተ ምህረት የቀድሞውን የኢትዮጵያ ነጻ ጋዜጠኞች ማህበር ለማፍረስ ሲባል ያቋቋሙት ግለሰቦች የማህበሩን ማህተም እና ሌሎች ቁሳቁሶች ገንዘብ ጭምር በመዝረፍ እና በማሸሸ ፣በመንግስት ማህተሙ ተነጠቀ በማለት በመንግስት መገናኛ ብዙሃኖች ዜና በማወጅ እራሳቸውን የነጻው ፕሬስ መገናኛ ነን ሲሉ መግለጻቸውን ጠቁመው ከመንግስት ጎን ለጎን አብረው ጉዞአቸውን እንደቀጠሉ ይታወሳል ። በሌላም በኩል በአዲስ ዘመን ላይ አሁንም በነጻው ጋዜጠኖች ላይ ከፍተኛ የሆነ ጦርነት አውጀውባቸዋል ይሄውም በመጼሄቶች ላይ የሚታተመው ስራ በሙሉ የጽንፈኛ ፖለቲከኞችን የሚያንጸባርቅ ሃሳብ የሚያትሙ ናቸው ሲሉ አውግዘዋቸዋል ።መንግስት  የነጻ መረጃ  በማይሰጥበት አገር ላይ እንደገና ጋዜጠኖች ፈልፍለው የሚያወጡትን ወሬ አሸባሪ ነው እያለ መክሰስ ከጀመረ ረጂም ጊዜያትን እንዳስቆጠረ የሚታወስ ነው ።አዲስ ጉዳይ ፣ፋክት ፣ሎሚ ቆንጆ ጃኖ እንቁ እና ሊያ የተሰኞትን መጽሄቶች የተቃዋሚ ፓርቲ ልሳኖች ናቸው በማለት የፈረጇቸው ሲሆን  የሁሉም አሉታዊ ተጽእኖ የሚያርፈው መረጃን አዛብቶ በማቅረብ እና ፖለቲከኞችን በመደገፍ ነው ሲሉ አትቶአል ። አሁንም በድጋሚ እንዲህ አይነቱ ክስ ሊፈጠር የሚችለው ሚዛናዊ የሆነ መረጃን በሃገሪቱ ማፍለቅ ሲችአል እና መንግስት ለነጻው ፕሬስ አስፈላጊውን መረጃ   መስጠት ሲችል እና ለዚያ ምላሽ ከተቃዋሚዎቹም ወገኖች የሚቀርቡትን እኩል በማገናዘብ ማቅረብ ሲችሉ ሲሆን በሌላ ወገን ደግሞ መንግስት የሰጠውን አባሪ የህትመት ጽሁፍ ተዛብቶ ሲያገኘው ብቻ መሆኑን ለማወቅ ያልተረዱ የመንግስት መገናኛ ብዙሃኖች እና የመንግስት አካሎች እኛ ነጻ ነን ሊሉን ይሞክራሉ ።  አጠቃላይ መረጃውን የማለዳ ታይምስ የደረሰው ሲሆን ይህንንም አያይዞ አቅርቦላችኋል ።
የኢትዮጵያ ጋዜጠኞች ኅብረትና ዓለም አቀፍ ተቋማት የእስክንድር ነጋን የይፈታ ጥያቄ ውድቅ አደረጉት የቀድሞው የኢትዮጵያ ነፃ ፕሬስ ጋዜጠኞች ማኅበር ከአይ ኤፍ ኢ ኤክስ አባልነት ታገደ
በኢትዮጵያ ውስጥ በፈፀመው የሽብር ወንጀል ተፈርዶበት በእስር ላይ የሚገኘው እስክንድር ነጋ ጋዜጠኛ ነበር ብሎ ለመቀበል የማህበር ድጋፍና እገዛ ለማድረግ እንደሚቸገር የኢትዮጵያ ጋዜጠኞች ኅብረት ፕሬዚዳንትና የምሥራቅ አፍሪካ ጋዜጠኞች ማህበር ምክትል ፕሬዚዳንት ጋዜጠኛ አንተነህ አብርሃም ገለጹ፡፡
ምክትል ፕሬዚዳንቱ ጋዜጠኛ አንተነህ አብርሃም ከጋዜጣው ሪፖርተር ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ እንዳሉት፤ ዓለም አቀፍ የጋዜጠኞች መብት ተከራካሪ ተቋማትም እስክንድር ነጋ ሽብርተኝትን፣ ፋሺዝምንና ናዚዝምን በሚያበረታታ እንቅስቃሴና አስነዋሪ ተግባራት ውስጥ ሲሳተፍ የቆየ ከመሆኑ ሌላ በጋዜጠኝነት ሙያም በየትኛውም ሚዲያ እንደማይሠራ በመረጋገጡ ምንም ዓይነት ድጋፍና እገዛ እንደማያደርጉ ወስነዋል።
ከምርጫ 97 ጋር በተያያዘ በሚያቀርባቸው ጽሑፎቹ ምክንያት የጋዜጣ ድርጅቱ እንዲፈርስ በሕግ የተወሰነበት እስክንድር ነጋ፤ ከ1997 .ም ወዲህ በጋዜጠኝነት ላይ እንደተሰማራ ካለመታወቁም በላይ የመላ አማራ ድርጅት የተሰኘ ፓርቲ የቅስቀሳና ፕሮፓጋንዳ ኃላፊ እንደነበረም ፕሬዚዳንቱ ያስታውሳሉ። በእነዚህና ተያያዥ ምክንያቶች በማህበር ደረጃ እገዛ ለማድረግ የሚቻልበት ሁኔታ ዝግ እንደሆነበት አስረድተዋል፡፡
እርሳቸው ተካፋይበሆኑበት የዓለም ጋዜጠኞች ፌዴሬሽን (አይ.አፍ.ጠቅላላ ጉባዔ ላይ አንዱ መነጋገሪያ የእስክንድር ነጋ ጉዳይ እንደነበረም ጠቅሰው፤ «በወቅቱም ጉባዔው «እስክንድር ይፈታ» የተሰኘ ዘመቻ እንዲካሄድ የቀረበውን የሞሽንሃሳብ በከፍተኛ ድምፅ ውድቅ አድርጎታል» ሲሉ ገልጸዋል፡፡
በተመሳሳይ ሁኔታም በካምቦዲያ የዓለም ሃሳብን በነፃ የመግለጽና የፕሬስ ነፃነት ጉዳይ ላይ የሚሠሩ ሁሉም ተቋማት ባካሄዱት ጠቅላላ ጉባዔ፤ በቀድሞው የኢትዮጵያ ነፃ ጋዜጠኞች ማህበር ፕሬዚዳንት ክፍሌ ሙላት የቀረበውና በሲፒጄ በኩል የተደገፈው«እስክንድር ይፈታ» ሞሽንአብዛኛዎቹ የእስክንድር ተሳታፊዎች ሽብርተኝነትን፣ ፋሺዝምንና ናዚዝምን የሚያበረታቱ ሥራዎች ላይ ነበረ በማለታቸው የቀረበውን የሞሽን ሃሳብ ውድቅ አድርገውታል ብለዋል፡፡እንደ ምክትል ፕሬዚዳንቱ ገለጻ፤ የካምቦዲያው ጉባዔ የኢትዮጵያ ነፃ ፕሬስ ጋዜጠኞች ማህበር ህልውናው ያከተመ በመሆኑና በ IFEX አባልነት መቀጠል አለበት በሚል በሲፒጄ ተደግፎ የቀረበውን ጥያቄ በከፍተኛ ድምፅ ውድቅ በማድረግ በክፍሌ ሙላት የሚመራው ኢነጋማ ከአባልነት ተሰናብቷል፡፡ ቀደም ሲልም ሌሎች የዓለም አቀፍ ጋዜጠኞች መብት ተሟጋቾች በክፍሌ ሙላት የሚመራውን ኢነጋማ ከአባልነት እንዳሰናበቱት አቶ አንተነህ ጨምረው ገልጸዋል፡፡
በአሜሪካ የሚገኘውና የጋዜጠኞች ተከላካይ ኮሚቴ (Committee to Protect Journalists (CPJ)) በሚል ስያሜ የሚጠራው ቡድን ራሱን በኢትዮጵያ መንግሥት ተቃዋሚነት ያደራጀና በጋዜጠኝነት ሙያ አሳብቦ በኢትዮጵያ ውስጥ የሥርዓት ለውጥ ለማምጣት የሚተጋ አንድ የኢትዮጵያ ተቃዋሚ አካል እንደሆነ ጋዜጠኛ አንተነህ አመልክተዋል።
ይሄው ድርጅት የማንም ውክልናና እውቅና ሳይኖረው የኢትዮጵያን ጋዜጠኞች የሚወክል በማስመሰል በሀገር ውስጥ ካለው እውነታ ተቃራኒ የሆኑ አፍራሽ ሥራዎችን ከማከናወን አልፎ ለኢትዮጵያ ጋዜጠኞች አንዳችም ድጋፍ አድርጎ እንደማያውቅ ተናግረዋል፡፡
የኢትዮጵያ ብሔራዊ የጋዜጠኞች ኅብረት ኃላፊነት ከሚሰማውና ለአባላቱ ተጠሪ ከሆነው ዓለም አቀፍ የጋዜጠኞች ፌዴሬሽን ጋር በቅርበት በሀገር ውስጥ ባከናወናቸው የውይይትና የድርድር ሥራዎች በርካታ ውጤቶችን አግኝቷል ያሉት አቶ አንተነህ፤ ሲፒጄ ግን ኒውዮርክ ላይ ሆኖ ከመንግሥትጋር የጀመርናቸውን ድርድሮችና መልካም ሁኔታዎች የሚያበላሹ መግለጫዎችን በማውጣት የመንግሥትንና የጋዜጠኞችን ግንኙነት ለማበላሸት እየተሯሯጠ ይገኛል ሲሉ ወቅሰዋል፡፡
ሲፒጄ የኢትዮጵያ ጋዜጠኞች ከሀገር እንዲኮበልሉ እያበረታታና ለስቃይ እየዳረጋቸው መሆኑን ጠቁመው፤ ኅብረቱ በቀጣይ ድርጅቱ የሚያካሂደውን አፍራሽ እንቅስቃሴ ካላቋረጠ አሠራሩን እየተከታተለ ለማውገዝ እንደሚገደድ ነው ያስገነዘቡት።
የኢትዮጵያ ብሔራዊ የጋዜጠኞች ኅብረት በሀገር ውስጥ ምንም ዓይነት ጋዜጠኛ እንዳይታሰርና ሌሎች ጉዳቶች እንዳይደርሱበት በቅርበት እየተከታተለ እገዛ በማድረግና የሚፈጠሩ አለመግባባቶችም እንዲፈቱ ተቀራርቦ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በሰላም በመሥራት ላይ እንደሚገኝ አስታውቀዋል፡፡
በሀገራችን በእስር ላይ የሚገኙት ጋዜጠኞች ርእዮት ዓለሙና ውብሸት ታዬ መሆናቸውን ጠቁመው፤ ኅብረቱ እነዚህ ጋዜጠኞች በመንግሥት ላይ በሚፈጠር ጫናና ተጽዕኖ ሳይሆን ሕግ በሚፈቅደው አግባብ በይቅርታም ይሁን በምህረት እንዲለቀቁ ጥረት በማድረግ ላይ መሆኑን ገልጸዋል።
እንደ ጋዜጠኛ አንተነህ ገለጻ፤ በተለያዩ መንገዶች የኢትዮጵያን መንግሥት ለማዳከምና የሥርዓት ለውጥ በኢትዮጵያ ለማምጣት በግልጽ እየሠራ ያለው ሲፒጄ፤ በተለያዩ መድረኮች በኢትዮጵያ ብሔራዊ የጋዜጠኞች ኅብረት ላይ አሉታዊ ጫና ለመፍጠር ይሞክራል፡፡ ይህም የሆነው መንግሥትን ከሥልጣን ለማባረር ኅብረቱ ሊተባበረው ባለመቻሉና በሙያ ጉዳዮች ላይ ብቻ አተኩሮ ከመሥራት ውጪ የፖለቲከኞች መሣሪያ ለመሆን ፈቃደኛ ባለመሆኑ እንደሆነም ጋዜጠኛ አንተነህ አስረድተዋል፡፡
«አሁን ሲፒጄ የያዛቸው አብዛኛዎቹ አፍራሽ እቅስቃሴዎች ተጋልጠዋል፤ ሌሎች ዴሞክራሲያዊ የሆኑ ዓለም አቀፍ ተቋማትም ሃሳቡን የማይጋሩ በመሆናቸው ሲፒጄ ብቻውን እንደ ውሃ ላይ ቄጤማ እየዋለለ ይገኛል»ብለዋል፡፡
ሲፒጄ በእውነት ለኢትዮጵያ ጋዜጠኞች የሚቆረቆር ከሆነ በሀገር ውስጥ ለምንገኘው ጋዜጠኞች ድጋፍ ማድረግ ይኖርበት ነበር ያሉት ፕሬዚዳንቱ፤ «ድርጅቱ በስማችንና በሙያችን ይነግድብናል እንጂ አንዳች የፈየደው ነገር የለም» በማለት ድርጊቱን ኮንነዋል፡፡

በጅዳ እና አካባቢው የኢትዮጵያውያን ክራሞት

 

saudi ethio j
ካሳለፍነው ወር ጀምሮ ወደ ሃገራቸው እንዲገቡ በተደረገው ጥሪ እጃቸውን የሰጡ መኖሪያና የስራ ፈቃድ የነበራቸው ዜጎች ባቀረቡት ቅሬታ “ወደ ሃገር እንዳንገባ ተደርገን እየተጉላላን ነው!” ብለውኛል። በቀን በሚሰጠው ደረቅ ብስኩትና ጥራቱ ባልተጠበቀ ሩዝ መጉዳታቸውን የገለጹልኝ ሲሆን መፍትሔ የሚሰጠን የኢትዮጵያ መንግስትም ሆነ የሳውዲ መንግስት ተወካዮች አጥተው ቀን በጸሃይ ፣ ማታ በብርድና በቁር እንግልት እንደደረሰባቸው ተናግረዋል። ወደ ሃገር እንግባ ብለው በተደረገው ጥሪ እጃቸውን የሰጡት መኖሪያና የስራ ፈቃድ የነበራቸው ዜጎች እዚህ በጅዳ ሽሜሲ ብቻ ሳይሆን በሪያድ እስር ቤቶች እንዳሉ እንግልት እየደረሰብን ያሉ ነዋሪዎች ምሬታቸውን ገልጸውልኛል።
ሁከት በጅዳ የንጉስ አብድልአዚአዚዝ አውሮፕላን ማረፊያ-
ከጅዳ መካው የሽሜሲ መጠለያ ተነስተው ወደ ሃገር ለመሳፈር  በጅዳ የንጉስ አብድልአዚአዚዝ አየር መንገድ ማረፊያ አውሮፕላን ማረፊያ የደረሱ ቁጥራቸው 1500 በላይ የሆኑ ኢትዮጵያውያን “የያዛችሁት እቃ ከሚፈቀደው ኪሎ በላይ ነው!” በሚል የተፈጠረው አለመግባባት  ማክሰኞ ከቀትር በኋላ መጠነኛ ሁከት ተቀስቅሶ እንደነበር እና ከሰአታት በኋላ መረጋጋቱን ተደጋጋሚ መረጃ ደርሶኛል።  የማክሰኞው ሁከት መነሻ የተመላሾችን የተከማቸ እቃ ለማየት ወደ ቦታው የደረሱትን የኢትዮጵያ አየር መንገድ ሃላፊ በቦታው መድረሳቸውን ተከትሎ ሲሆን በእንግልቱ የተበሳጩት ዜጎች ሁከት መቀስቀሳቸው በአይን እማዘኞች ተደጋጋሚ የስልክ ጥሪ  ለመረዳት ችያለሁ። የአይን እማኞች አክለውም ዜጎች ከሃላፊው ጋር ሊጋጩ ሲሉ በጸጥታ አስከባሪዎች ብርታት መትረፋቸውን ከቦታው  በሰአቱ የደረሰኝ መረጃ ያስረዳል። ግርግሩ ለሰአት ያህል የቀጠለ ቢሆንም በሰውና በንብረት ላይ ጉዳት አልደረሰም። ሁኔታውን ለማረጋጋት በቦታው የተገኙ ፈጥኖ ደራሽ ፖሊሶች ማረጋጋት ከፈጠሩ እና ሁኔታው ከተረጋጋ በኋላ የአየር መንገዱን ሃላፊ ለጥያቄ ወስደዋቸው እንደነበርና ሃላፊውን ለማስለቀቅ የጅዳ ቆንስል ሃላፊዎች እና ጅዳ የመጡት የሪያዱ አንባሳደር ወደ ቦታው በመንቀሳቀስ ከሰአታት በኋላ ሃላፊውን ይዘው ምሽት ላይ መመለሳቸውን ተጨባጭ መረጃ ደርሶኛል።saudi ethio j1
የሃላፊውን ለጥያቄ መቅረብ ተከትሎ በጉዳዩ ዙሪያ ያነጋገርኳቸው አንድ ውስጥ አዋቂ ሲናገሩ “  በአውሮፕላን አቅርቦት እጥረት እና እቃችን ሳንይዝ ወይም በአደራ ተቀብሎ ወደ ሃገር የሚያስተላልፍልን እስካላገኘን ወደ ሃገር አንገባም ያሉትን ዜጎች ጉዳይ እንዲመለከቱ በቆንስላው ጥያቄ ወደ አየር ማረፊያው ያቀኑት የአየር መንገዱ ሃላፊ ስለ ዜጎች መጉላላት መረጃ እንዳልነበራቸውና በቦታው ሲደርሱ ከሁከቱ ጋር ተያይዞ ግራ ተጋብተው ታይተዋል።” በማለት ሲያስረዱ በቆንሰሉና በአየር መንገዱ ሃላፊዎች መካከል የመረጃ ክፍተት መኖሩን ገላልጠው አጫውተውኛል።
ይህ በእንዲህ እንዳለ ከዚህ በፊት ከ40 ኪሎ በላይ እቃ መውሰድ አትችሉም የተባሉ ዜጎች እቃ ሃጅ ተርሚናል በሚባለው የአየር መንገዱ ማረፊያ ቦታ በብዛት ተዝረክርኮ እነወደሚገኝና የብዙዎች እቃ አድራሻ እንደሌለው የአይን እማኞች ገልጸውልኛል።  “አድራሻ ያለውን እቃም በሚመለከት የጅዳ ቆንስል ሰብስበን እንልከዋለን የሚል ቃል ከመስጠት ባለፈ ምንም አይነት ተጨባጭ እርምጃ እንዳልወሰዱም” በማለት እማኞች ገልጸውልኛል።
ከአስር ቀናት ያላነሰ እንግልታቸውን  በማስረዳት የተገፊ ድምጻቸውን እንዳሰማላቸው እንባቸውን እያዘሩና በብስጭት ያስረዱኝ ወገኖች በበኩላቸው “የአውሮፕላኑን ወጭ የሳውዲ መንግስት ከቻለ የኢትዮጵያ መንግስት እቃችን ይዘን እንድንገባ ለምን አላመቻቸልንም?  ሌላው ቢቀር መንግስት በሻንጣው መጫንና ለሳምታት ብስኩት እየተሰጠንና በውሃና ምግብ ግዠ የያዝነውን ገንዘብ ስናጠፋና ስንሰቃይ በዚህ ካልረዳን ወገኖቸ ማለቱ አልገባንም! ዜጎች አይደልንም?” ሲሉ በማጠየቅ በተጎዳ ሰሜት ገልጸውልኛል። ከዚህ ጋር በተያያዘ አንድ ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው ወንድም እንደገለጹልኝ  ዜጎችን ማጓጓዙ እንደ በፊቱ በፍጥነት ባይከወንም አልፎ አልፎ መቶና ከመቶ በላይ ዜጎች በተገኘ የበረራ ክፍት ቦታ እየተላኩ መሆኑን በማስረዳት  ከቀን ወደ ቀን እየተባባሰ የመጣውን ይህንን ችግር የቆንስሉ ሰራተኞች በተደጋጋሚ ለቆንስል ሃላፊዎች ማሰማታቸውን በመግለጽ መፍትሔ ግን እስካሁን አለመሰጠቱን አክለው ገልጸውልኛል።
የካርጎ መዘጋት መዘዝና የነዋሪዎች ሮሮ-saudi ethio j2
የአየር መንገድ የካርጎ አገልግሎት ለወራት መሰናከል ተከትሎ በኢትዮጵያ አየር መንገድና በእቃ አቅራቢ የካርጎ ኤጀንቶች በደል ደረሰብን የሚሉ ዜጎች  ቅሬታ እያሰሙ ነው። ይህ ችግርም በነዋሪዎችና በካርጎ ኤጀንሲ ሰራተኞች መካከል ውዝግብ ማስከተሉ አልቀረም። የአየር መንገድ ወደ ኢትዮጵያ የሚደረገው ጉዞ ከስድስት ወራት በላይ ምክንያቱ ግልጽ ባልሆነ ምክንያት ከተዘጋ በኋላ ሰሞኑን ስራ መጀመሩ እየተሰማ ነው። ያም ሆኖ በጅዳ ዙሪያ ያሉ የካርጎ ኤጀንሲዎች “ወደ ኢትዮጵያ የካርጎ ግልጋሎት በተለያዩ አቅጣጫዎች እንሰጣለን!” በሚል ከፍተኛ ገንዘብ ለእቃው ማስጫኛ እየተቀበሉ እቃውን ቢረከቡም ከስድስት እሰከ አስር ወራት ለሚቆይ ጊዜ እቃውን በመጋዘ ቃላቸውን ጠብቀው እንዳላደረሱላቸው የመጫኛ ማስረጃቸውን እያሳዩ ቅሬታቸውን የገለጹልኝ በርካታ ዎች ናቸው። የሳውዲ ውጡ ህግ ከተነገረ ጀምሮና ከዚያም ወዲህ በተሰጠው የሰባት ወር የምህረት ጊዜ ጠቃሚ የሚሏቸውን ጥሪት እቃቸውን ለካርጎ ቢያስረክቡም አንድም በካርጎው መዘጋት በተጓዳኝ በካርጎ ኤጀንሲዎች ለአንድ ኪሎ እስከ 10 ሪያል በመክፈል እቃቸውን ቢያስገቡም እቃቸውን ደህንነት በማያውቁበት ደረጃ በንብረታቸው ላይ ብክነት እንዳስከተለባቸው እያዘኑ ሮሯቸውን አጫውተውኛል።
በጀዛን የዜጎች እንቢታ እና የህግ ታሳሪዎች ሮሮ -
በጀዛን “ወደ ሃገር እንግባ!” የሚሉ ነዋሪዎችን ጥሪ ተከትሎ የመጓጓዣ ሰነድ ለመስራት የጅዳ ቆንስል መስሪያ ቤት ተወካይ ዲፕሎማት ወደ ቦታው ያቀኑ ቢሆንም “ድረሱልን!” ሲሉ የነበሩ ዜጎች የውሃ ሽታ መሆናቸውን የኮሚቴውን በፊስ ቡክ መኖሩን የሚያሳውቀን የወገን ለወገን saudi ethio j3የህዝብ ግንኙነት ፊስ ቡክ ጠቁሞናል።  በጀዛን የሚገኙ የህግ እስረኞችም በህግ ተይዘው ፍርድ ከተሰጣቸው በኋላ ለአመታት የሚጉላሉ እና በጥርጣሬ ተይዘው ፍርድ ቤት ያልቀረቡ ዜጎች የድረሱልን ጥሪ ዛሬም አላቆመም። “ትኩረቱ ሁሉ ወደ ሃገር ተመላሾች መሆኑ ብቻ ሳይሆን ድሮም ተረስተናል አሁንም ተረስተናል!” እያሉ ነው!  በጀዛን ዙሪያ ባሳለፍነው ሳምንት መረጃ ያቀበለን የወገን ለወገን ደራሽ የህዝብ ግንኙነቱ ገጽ ባስተላለፈው መረጃ ወደ ሃገር ቤት ለመሄድ ሰላላሳዩት ዜጎች ትኩረት በመስጠት የዜጎችን ወደ ሃላፊዎች ለመቅረብ እና ለመሸኘት ፍላጎት አለማሳየታቸውን ሲገልጽም “እነሆ ግዜው ደረሰና የሁለቱም ሃገር መንግስታት ሁኔታዎችን አስተካክለው በሰማት (አሻራ) የሚሰጡበት ቦታ ተበጅቶላቸው ከቆንስላ ፅ/ቤት ተወካይ በቆንስል አህመድ የሚመራ ቡድን ለዜጎቻችን እዚያው እንዲሰራላቸው በማሰብ ወደ ጂዛን ተጓዙ። አሁንም እዚያው ናቸው። ነገር ግን ነገሮች እንደታሰቡ እየሄዱ አይደለም። ታስቦላቸው የተሄደላቸው ወገኖች እየወጡ አይደለም የሚል አሳሳቢ ዜና ሰማን። አሁን ባለው ሁኔታ ወደ ማቆያ የሚገቡት ሰዎች በቀን መቶም እንደማይደርሱ ተገለፀልን። ከጂዳ ለዚህ ጉዳይ የተንቀሳቀሰው ልኡካን አሁንም ለማገልገል ይጠብቃል፡ ምንም የሚታይ ነገር ግን የለም። በጂዛን አጎራባች ወደ ሆኑ ከተሞችም ከአካባቢው ማህበረሰብ አምስት አምስት ሰዎች ለቅስቀሳ ተልከዋል። ቢሆንም ወገናችን ዜጎቻችን የሚወጡ አይነት አይደለም። በጣም ሚገርም ነው።” ይላል።  የህግ ታሳሪዎች በበኩላቸው የቆንስል ሃላፊዎችን አነጋግረዋቸው “ለእናንተ ጉዳይ አልመጣንም!” እንዳሏቸው ገልጸውልኛል። የህዝብ ግንኙነቱ ዜጎች ወደ ኋላ ስላፈገፈጉበት ጉዳይም ሆነ በደል ደረሰብን ስለሚሉ ህጋዊ ታራሚዎች የሰጠው መረጃ የለም ። በወገን ለወገን ደራሽ ኮሚቴ ለአንድ ወር በስራ አስፈጻሚነት የሰራሁ መሆኑ የሚታወስ ሲሆን ለቆንስል ሃላፊዎች ያቀረብኩት የዜጎች አቤቱታ እንዲታረም በተደጋጋሚ አሳስቤ የነዋሪውን አቤቱታ በጀርመን ራዲዮ በማቅረቤ በተወሰደ የ “በዲሲፕሊን!” እርምጃ ከኮሚቴው አባልነት በተጽዕኖ መነሳቴ ይታወሳል!
የውጭ ጉዳይ ልዑካን በጅዳ:-
በሳውዲ አረቢያ የሪያድ ኢንባሲ አምባሳደርን ጨምሮ ሶስት አባላትን የያዘው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ቡድን ከሶስት ቀናት በፊት ጅዳ ገብተዋል። ልዑካኑ በእስካሁኑ ቆይታቸው የኢህአዴግ የድርጅት አባላትንና የጅዳ ቆንስል ሃላፊዎችን በዝግ ያነጋገሩ ሲሆን የውይይታቸው ትኩረት በመጡበት የዜጎችን ወደ ሃገር መግባት ጉዳይ የማፋጠን ስራ ይሁን በሌላ ተዛማጅ ጉዳይ የሚታወቅ ነገር የለም። የልዑካን ቡድኑsaudi ethio j4 አባላት በእስካሁን ቆይታቸው አደጋውን ለመከላከል በጅዳ ቆንስል ሃላፊዎች የተቋቋመውን የወገን ለወገን ደራሽ ጊዜያዊ ኮሚቴ እስካሁን ያላነጋገሩ መሆኑ ታውቋል። የልዑካኑ ቡድንን ኮሚቴውን አለማነጋገሩ ቅያሞት የገባቸው አንዳንድ አባላት በበኩላቸው የዜጎች እንግልት በቅንጅት ጉድለት እየተበራከተ በሄደበት በዚህ አጋጣሚ ኮሚቴው ንቁ ተሳትፎ ማድረግ ላልቻለበት ሁኔታ የቆንስሉ እና የአመራሩ ድክመት እንደሆነ በማስረዳት እያደር ለይስሙላ የተቋቋመ እንጅ ወገንን ለመርዳት ከመካዝን ያለውን ውሃ ለማደል እንኳ አቅም አጥቷል በሚል ከማህበረሰቡ ወቀሳ እየቀረበበት መሆኑን በግልጽ አጫውተውኛል።
በሳውዲ አረቢያ የሪያድ ኢንባሲ አምባሳደርን ጨምሮ ሶስት አባላትን የያዘው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ልዑክ በጅዳ ቆንስል የመንግስታችን ተወካዮች ለተጠቀሱትና በከባቢው ላሉ ችግሮች አፋጣኝ እርምጃ ካልወሰዱ አደጋውን መታደግ ከማንችልበት ደረጃ እንዳይደረስ የብዙ ነዋሪዎች ስጋት ሆኗል። የሳውዲ መንግስትን እና የኢትዮጵያ ኢንባሲና ቆንስል በማስታወቂያ ብቻ የተደገፈ ተደጋጋሚ ማስጠንቀቂያ ተከትሎ “ሰነድ የሌላችሁ ዜጎቸወ ከሳውዲ ውጡ!” በሚል ማስተላለፋቸው አይዘነጋም። ያም ሆኖ ነዋሪው በርካታ ያልተሟሉ ቅድመ ሁኔታዎችን በማቅረብ ለመውጣቱ ጥሪ “አሻፈረኝ!”  ያሉትን በሽዎች የሚቆጠሩ ነዋሪዎች ሮሮ እና ጥያቄ ለመስማትና አፋጣኝ የመፍየትሔ እርምጃ ለመውሰድም የመንግስት ሃላፊዎች ህዝባዊ አስቸኳይ ጥሪ በመጥራት መፍትሔ ያመላክቱ ዘንድ ደግሜ ደጋግሜ እመክራለሁ!
ዛሬም የመረጃ ክፍተቱ ይዘጋ፣ የምንናገረው ተጨባጭ መረጃ መሆኑን አጣርታችሁ መፍትሔ አፈላልጉ ስል ደጋግሜ “ጀሮ ያለው ይስማ!” እላለሁ !
ቸር ያሰማን!
ነቢዩ ሲራ

 
 

እስራኤል ውስጥ የሚገኙ በሺዎች የሚቆጠሩ አፍሪካውያን የተቃውሞ ሰልፍ እያደረጉ ነው

ታህሳስ ፳፰( ሃያ ስምንት )ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ካለፉት ሶስት ቀናት ጀምሮ የስራ ማቆም አድማ እና የተቃውሞ ሰልፍ በማድረግ ላይ የሚገኙት በአስር ሺዎች የሚቆጠሩት አፍሪካውያን የእስራኤል መንግስት ያወጣውን አዲስ ህግ እንዲቀይር፣ የታሰሩት እስረኞች እንዲፈቱ እንዲሁም የስደተኞች ጉዳይ በጅምላ ከሚታይ ይልቅ በግለሰብ ደረጃ ታይቶ ውሳኔ እንዲሰጥበት የሚሉት እንደሚገኙበት በሰልፉ ላይ ተገኝቶ የነበረው አቶ አቦየ አስምረው ለኢሳት ገልጸዋል።
“በሰላማዊ ሰልፍ ውጤት ሊመጣ ይችላል ተብሎ ይጠበቃል?” ተብሎ የተጠየቀው አቶ አቦየ፣ ተቃውሞው በዚህ ከቀጠለ ምናልባትም መፍትሄ ሊመጣ ይችላል ብሎአል። ቁጥራቸው አነስተኛ ቢሆንም ኢትዮጵያውያንም በሰልፉ ላይ ተገኝተዋል
በሰልፉ ላይ ከተገኙት አብዛኞቹ የኤርትራና የሱዳን ስደተኞች መሆናቸው ተገልጿል።

Sunday, January 5, 2014

የጨቅላዎች ሁካታ !

ምንሊክ መጓዙን የምትጠይቁኝ፤
ፊትም አላለፈ ኋላም አይገኝ።
ካለፉት ሳምንታት ወዲህ የማንነት ቀውስ ዋግ እንደመታው አገዳ ያኮሰሳቸው የበታችነት ስነልቦናቸውን ታሪክ በማፍረስና ጀግኖችን በመዝለፍ የሚጠገን የመሰላቸው አንዳንድ ተማርን ነን ባይ ደካሞች ዛሬን በድቅድቅ የባርነት ጨለማ አሳራቸውን እያዩ ፤ በራሳቸው ላይ የተጫነውን የአገዛዝ የጭቆና ቀንበር ለማንሳት ብርቱ ጥረት ከማድረግ ይልቅ ወደኋላ ተጉዘው የነጻነትን ብርሃን ፤ የዘመናዊነትን ጎዳና፤ የአንድነትን መሠረት ከወረሪና ከተስፋፊ ቅኝ ገዠ አውሮፓውያን በብርቱ ታግለው የክብርን አክሊል፤ የኩራትን መንፈስ ያወረሱንን ደጋጎቹን አባቶች የሚያንጓጥጥ ከስደት ፤ ከረሃብና ፤ ከውርደት በዚህ ዘመን እንኳ ለራሱ መቀዳጀት ያልቻለ ደካማና ልፍስፍስ ህብረተሰብ ጀግኖች አባቶቻችንን ለመዝለፍ ሲንጠራራ ይበልጥ እየተዋረደ መሆኑን እንኳ አለመረዳቱ የሚያሳዝን ከመሆን አልፎ የዛችን ታላቅ ሃገር ኢትዮጽያዊ ዜጋ መጻዊ ሕላዌ ፈተና የሚደቅን በሌሎች ሃገሮች የታየው አይነት የእርስ በእርስ መተላለቅን የሚጋብዝ አደገኛ አካሄድ የጥቂት ጨቅላዎች ሁካታ ነው በሚል ልናልፈው ብንሞክርም እንኳ የዚህ የጥፋትና የጥላቻ ግብረሃይል ሃገሪቷን በሚመራው ወገን የጀርባ ድጋፍ ያለው በመሆኑ አሁን ባለው የጽንፈኝነት መንገድ ከቀጠለ የሚያስከትለው አደጋ ቀላል ባለመሆኑ በነዚህ ጨለምተኞች ዙሪያ ወገንን የማንቃት እንቅስቃሴ እንዲያግዝ ሁሉም የበኩሉን ማለት ይኖርበታል የሚል እምነት አለኝ ።Ethiopian king Atse Menelik
ውሃን ድንጋይ ያናግረዋል አበው እንዲሉ በአሮጌ የታሪክ ቡልኮ ተጀቡነው ዘመኑን መዋጀት ያልቻሉት በትላንትና የቅናትና ጥላቻ ችንካር ላይ ተቀርቅረው ዘመን ተቀባብሎ የለወጠውን በሃውርታዊ ውህድ ህብረተሰብ ለመበታተን በተጋነነና ሁን ተብሎ በተፈበረከ የጥላቻ ድርሰት ታውረው ለከፋፍለህ ግዛው ፋሽስታዊ የወንበዴዎች አገዛዝ ህዝብ ስቃዩ እንዲረዝም እያደረጉ ያሉት የምሁር ደንቆሮዎች ዘመናቸውን የፈጁበት የጥላቻ ጉዞ ጡረታም ሲወጡ ሊተዋቸው አለመቻሉ እጅግ የሚያሳዝን ከመሆኑም በላይ የግማሽ ክፍለ ዘመን የከሸፈና የዘቀጠ አስተሳሰባቸውን ለትውልድ ለማውረስ የተጀመረው መቃብር የመቆፈር ፖለቲካ አሳፋሪ ከመሆኑም በላይ ትርምስ የመፍጠር አላማ ያነገበ በመሆኑ አጀንዳቸው ውሃ የማይቋጥርና ፤ ለጆሮ የሚቆረፍድ ቢሆንም ልካቸውን እንዲያውቁና አደብ እንዲገዙ ለማድረግ እውነቱን ይነገራቸው ዘንድ ስልጡን በሆነ መንገድ መንገሩ ተገቢ ነው።
ታላቁን ገናናውንና በጥቁር ሕዝብ ዘንድ የነጻነት ጮራ ፈንጣቂ ሞራሉ ለተሰበረው ውርደት እንደመጎናጸፊያ ለደረበው ተስፋው ተሟጦ በባርነት እንደ እንስሳ እየተረገጠ መኖርን ህይወቱ አድርጎ አያሌ ዘመናትን ለተሻገረው ድፍን የአፍሪካ ህዝብ የነጻነት ተምሳሌት በመሆን የአባቶቹን ታሪክ የደገመው ጀግናው የጣሊያን ጌታ የንጉሶች ንጉስ (King of Kings) የሆነው እምዬ ምንሊክ በማንም ወፍ ዘራሽ መደዴ የባንዳ ልጆችና የማንነት ቀውስ ባኮሰሰው ታሪክ በራዠ እንደ ጥጃ መለመላውን ከመሄድ ሱሪ እንኳ ያጠለቀለትን ጥቁሩን አንበሳ ሲሰድብ ዉሎ ሲሰድብ ቢያድር ሀውልት ቢያቆም ድርሳናት ቢጠረዝ አንዲት ጋት ያህል ክብሩን ሊቀንስ የማይችል በመሆኑ በዚህ የክፋት አቦከብሬ የጫጫታ ተግባር ለተጠመዳችሁ መድረሻቸው ሃፍረት ነው።
የገናናውን ታላቅ የጥቁር ሕዝቦች ንጉስ የእምዬ ሚኒሊክ መቶኛ አመት እና የታላቁ አፍረካዊ የነጻነት ታጋይ የማንዴላ እረፍት መገጣጠም ያጫራቸው የሃሳብ ንትርኮች ውስጥ በራሳችን ሃገር ዜጎች ምኒልክን በማሰነስ ማንዴላን የማወደስ ስራ የተጠመዱ የእንግዴ ልጆች የዘነጉት ወጣቱ የጥበብ ሰው (እድሜውን ያርዝምልን በጥበብና በማስተዋል አምላክ ያቆይልን) ጥቁር ሰው በሚለው የሙዚቃ አልበሙ ያሰፈረውን ታላቅ አባባል ልዋስና ‘’ የፊቱ ከሌለ የለም የኋላው ‘’ እንዳለው የማዴላን የትግል መንፈስ ያጠነከረው ሞራሉን የገራው ጥቁር የነጭ አሽከር ነው የሚለውን ዘመናት የተሻገረውን ክፉ መንፈስ እንዲሰበር የረዳው ነጭም ጥቁርም እኩል በአርአያ እግዚያብሄር የተፈጠረ እኩልነትና ነጻነት የመቀዳጀት መብት ያለው ሰብዓዊ ፍጡር መሆኑን ከማን ተማረ ፈር ቀዳጁስ ማን ሆነና ! ለመሆኑ ከጥቁር የአፍሪካ አሃጉር ከኢትዮጽያ በስተቀር ማነው ነጻ የነበረው ከመላው የእስያ የአፍሪካና የካሪቢያን ሃገራት ውስጥ የትኛው መሪ ነው የአውሮፓን ቅኝ ገዠ ወራሪ ሃይል አሸንፎ ያንበረከከው ከምኒሊክ ሌላ ማን የሚጠቀሰ አለ ነው፤ ለዚህ ነው ሚኒሊክ የኢትዮጽያ ብቻ ሳይሆን የዓለም ጥቁር ህዝቦች የነጻነት ፋና ወጊ ነው የሚያስብለው ። የማንዴላ ብርታት ፤ የነማርቲን ሉተር ኪንግ ሞራል ፤ የነማርኮስ ጋርቪ ፤ የነጆሞኬንያታ ፤ የነነኩሩሃማ በጭቆናው ዘመን ለነበሩት ተራማጆችና ፓን አፍሪካኒስቶች የትግል መነሻ የሞራላቸው መዳረሻ አድዋ ላይ የተገኘው አኩሪ ድል እኮ ነው። ይህ ዛሬ ባሪያ ነበርን ተረገጥን ጡታችን ተቆረጠ ፤ሱሪያችን ወለቀ ፤ ተዋርደን ነበር ወዘተ የሚሉት መቃብር ቆፋሪ የድኩማን ግሪሳዎች የራሳቸው አልበቃ ብሎ ታላቁን የኦሮሞ ሕዝብ በዚህ የቆረፈደ አሮጌ የተረት ቡልኮ ለመጨመር መመኮራቸው ሃገር ወዳዶች ተረድተው ይህን ሴራ የፖለቲካና የዘር ልዩነት ሳንል ማክሸፍ ካልተቻለ ሊፈጥረው የሚችለው አደጋ ቀላል አለመሆኑን መገንዘብ ይኖርብናል ።
እነዚህ የመቶ አመት ሂሳብ ለማወራረድ በቧልት የተሞላ የታሪክ አዛባ የሚዝቁት ጥቂት የትላንት እስረኞች የዛሬም ተጨቋኞች ስለህብረተሰብ ጥንቅር ስለ ስነመንግስትና በአለም ውስጥ ያሉ ሃገራት በምን አይነት መንገድ የዛሬውን ቅርጽ ይዘው እንደወጡ ሊያውቁ የሚችሉበት የእውቀት አድማስ እንኳን ለምሁራን ለተራው ዜጋም ሊጠፋ የማይችል እውነት ሆኖ እያለ ህዝብን በህዝብ ላይ ለማነሳሳት በተዛባ መልኩ እየተረኩ ያለው አደገኛ ተረት ውሎ አድሮ እንወክለዋለን የሚሉትን ወገን አንገት የሚያስደፋና የማያኮራ የማይጠቅም በመሆኑ ከድርጊታቸው ቢታቀቡ መልካም ነው ። የአሁኒቷ አለም ሃገራት ከሞላ ጎደል አሁን የያዙትን ቅርጽ ይዘው እንዲገኙ ያደረጋቸው በጦርነትና በወረራ በተደረገ ደም አፋሳሽ በሆነ ወታደራዊ ንቅናቄ የመሆኑ እውነት በታሪክ የታወቀ ነው። በኢትዮጽያም የሆነው ይህው ነው። የኢትዮጽያ ደግሞ ከሌሎቹም በተለየ መልኩ የግዛት ወሰኗ ሰፊውን የአፍሪካን ቀንድ ያካለለ እንደነበር አያሌ የታሪክ ማስረጃዎችን ማቅረብ ይቻላል። ኢትዮጽያ የግዛት ወሰኗን አስከብራና ነጻነቷን ጠብቃ ከመኖሯም በላይ ፍትህ የተጓደለባቸውን ህዝቦች ቀይ ባህር ተሻግራ የአሁኒቷ የመን ሃገረ ናግራን የሚኖሩ ወገኖችን ለመታደገ በአፄ ካሌብ ዘመን የተደረገው የድል ዘመቻ ኢትዮጽያ የአካባቢው ግዛቶች ባለቤት ከመሆኗም በላይ በአካባቢው ጂኦ ፖለቲካ ላይ የበላይነት የነበራት ሃያል ሃገር እንደነበረች ከታሪክ የሚረዳ ወገን አጼ ሚኒሊክ ከሰሜን ወደ ደቡብ ያደረጉት እንቅስቃሴ የቀደምት የአባቶቻቸውን የወሰን ግዛት የማስከበርን ታሪካዊ ሃላፊነት መወጣት እንጂ የዛሬዎቹ የፋሽስትና የባንዳ ርዝራዦችና ነጭ አምላኪ የታሪክ አተላዎች እንደሚቀባጥሩት የሚኒሊክ የደቡብ ወታደራዊ ንቅናቄ ወረራና ሌላ ሃገር ላይ የተደረገ ዘመቻ አለመሆኑን በብዙ ማስረጃ አቅርቦ ለመከራከር አዳጋች ባይሆንም የተጀመረው የጥላቻ ዘመቻ ኢትዮጽያዊነትን የካደ ስልጡን ውይይት የማያስተናግድ በጠባብነት የተመራ ጨለምተኝነት የነገሰበት በመሆኑ ሂደቱን በጥንቃቄ መከታተል ተገቢ ይመስለኛል።
የዛሬዎቹ የማንነት ቀውስ የደፈጠጣቸው በበታችነት የስነልቦና ደዌ የተጠቁት የምናባዊቷ ኦሮሚያ ደቀመዛሙርት በወያኔው የጥላቻና የተንኮል ታሪክ ጸሃፊ ተስፋዬ ገብረዓብ በተባለ ሃሳዊ ተፈብርኮና ተደርሶ የተሰጣቸውን የውርደት መድብል ታሪክ ብለው ትውልዱን በማደናገርና በቂም በቀል ተነስቶ እርስ በእርስ እንዲተላለቅ የጀመሩት ዘመቻ አስተዋዩ የኦሮሞ ሕዝብ ታሪኩንና ማንነቱን በቅጡ የሚያውቅ በመሆኑ በከሰሩ ኦነጎችና በተንበርካኪ የወያኔ ሎሌዎች የተጀመረው ሃገር አፍራሽ ዘመቻ ባለመተባበር እንደሚያከሽፈው የሚያጠራጥር ባይሆንም ይህን የባርነት መንፈስ የተጫናቸውን ታሪክ አርካሽ አልጫ ስብስብ ወደ ቀልቡ እንዲመለስ ለማስገንዘብ ጥቂተ ማለቱ ተገቢ ሲሆን ከዛ ባለፈ በወያኔ ምርኮኛ የደርግ አስር አለቆች የሚመራው ድኩማኑን የህወሃት አገልጋይ ኦህዴድ ሆነ ከ50 አመታት በላይ የአንድ ትውልድ እድሜ ያስቆጠረው ጡረተኛው የኦነግ ቡድን በአንድ ቀን ጀንበር መቶ ሃያ ሺ ጦሩን ያስማረከ ልፍስፍስና የተበታተነ የምሁር ሃይል በሚኒሊክ መቃብር ላይ ጡረታውን ላማስከበር የጀመረውን የጅል የወሬ ዘመቻ ፍጻሜው ከመሳቂያነት የማያልፍ በመሆኑ አጀንዳው ሳይንዛዛ በአጭር ዘግቶ የዚህን እኩይ ሴራ ቀማሪ በሆነው የወያኔን አገዛዝ ወደ ማስወገድ ትኩረታችንን ማድረጉ ላይ ሁሉንም ወገን ግንዛቤ ሊጨብጥ ይገባል።
ወገኖቼ በዚህ በ21ኛው ክፍለ ዘመን ነጻ ከወጡ የአንደ ትውልድ ዘመን እንኳ ያልሞላቸው ሃገራት በአስተዳደር በኢኮኖሚና በስልጣኔ በልጠውን እኛ ግን ቢያንስ ሃሰባችንን እንኳ በነጻነት መግለጽ የማንችልበት ረሀብተኛ ስደተኛና በሃገሩም እስረኛ በሆንበት የውርደትና የጉስቁልና መቀመቅ ውስጥ መከራራችንን እያየን ያለን ህዝብ ሆነን ክብርን ኩራትን ሰው የመሆንን ጸጋ ትተውልን ያለፉትን አባቶች መልካም ስራቸውን አንግበን መጥፎ ስራቸውን ለታሪክ ትተን ከወደቅንበት ለመነሳት እጅ ለእጅ ተያይዘን መቆም ሲገባን በዘርና በጎጥ ተቧድኖ የእንካሰላምታ ግብግብ መግጠማችን ክብር የተውልንን አባቶች መስደብ ምን የሚባል ፖለቲካ ነው! ፋይዳውስ ምንድን ነው? ዛሬ በዚህ ዘመን ምን የተቀዳጀንው ነገር አለና ነው? ያሳዝናል በዓለም ቁጥር አንድ ከሆነ በምጽዋት ህይወቱን ከሚገፋ ህብረተሰብ የማይጠበቅ እንደ ህዝብ አሳፋሪ የታሪክ ጠርዝ ላይ ቆመናል። አፄ ሚሊክን በምንም አይነት ልሳን ብንሰድብ የጥቁር ሕዝብ ንጉስ የመሆናቸውን እውነት የአውሮፓ ሃያላንን የማንበርከኩን ሃቅ ማንም ቅናትና የበታችነት ስነልቦና የተጫናቸው እንጭጮች ጫጫታ ሊፍቀው አይችልም። ሃይለስላሴን ለማዋረድ የተነሳው ትውልድ ራሱ ተዋርዶ እርስ በእርስ ተባልቶ ማለቁን አይተናል። የተረፈውም ያራገበው አብዮት ተቀልብሶና ተሸንፎ በቁሙ በውርደትና በእስር ማቆ አይቶታል። ሃይለስላሴ ግን ከማክበርም አልፎ የሚያመልካቸው የጥቁር ሕዝብ እንዳይኖር ከቶስ ማድረግ የሚችለው ማነው? በዋልጌ ዜጋው የተዋረደው የሃይለስላሴ አጥንት እንደ አማልክት እንዲከብር ራስ ተፈሪያውያንና የካሪቢያንና የአፍሪካ ሕዝቦች ልብ ውስጥ የኩራት ሃውልቱን አኑሮ ይኖራል። በዘረኞችና በበታችነት ስነልቦና እስረኞች ንጉሰ ነገስት ሃይለስላሴ ብርቱ ጥረትና ትግል ለመመስረት የበቃው የአፍሪካ ህብረት የዚህን የአፍሪካ ኩራትና ሃዋርያ በገዛ ሃገሩ ሃውልቱ እንዳይቆም ቢደረግም ውለታቸውን ባልዘነጉ መላው ጥቁር ሕዝቦች የማይዘነጋ አሻራ ከማኖሩም በላይ በናይሮቢ ኬንያ በስሙ ጎዳና ተሰይሞ (Haile Selassie Avenue) ስሙ እንዳይጠራ ማስቀረት የሚችለው ማን ነው?።
የሻብያ ፍጥረት የወያኔ አሽከር የሆኑት አንዳንድ በአሮሞ ስም የሚነግዱት ተንበርካኪ የእንግዴ ልጆች ሳይወለድ የሞተው ሊሳካም ከቶም የማይችለው ተምኔታዊው የጽንፈኞቹ የህልም አለም ምናባዊቷ የኦሮሚያ ሉዓላዊነት እንደለመዱት በአሶሳ በወተር በአርባጉጉ በአሰቦት ሰውበላው ድርጅታቸው ኦነግ አሮጊቶችና ሴቶች ላይ የፈጸመውን የጭካኔ ተግባር እንደግመዋለን የሚለው የሜንጫ ፉከራቸው በዚህ ዘመን ለመድገም መሞከሩ ሊያስከትል የሚችለው ዋጋ ቀላል አለመሆኑን የሚረዱት ይመስለኛል ። ከዛ ባለፈ መቶ አመት ወደ ኋላ ተጉዘው የጀመሩት ተረትና እያቆሙ ያለው የተንኮል ሃውልት የሚኒሊክን ስም የሚያጎድፍ ከመሰላቸው በጣም ተሳስተዋል። ንጉስ ሚኒሊክ ጠላቱም የመሰከረለት ጀግናና ለአሸነፋቸው ምህረትን ማድረግ ልምዱ ያደረገ ለመሆኑ ለተሸናፊው ንጉስ ጦና እና ለምርኮኛው የፋሽስት ጣሊያን ጀነራሎች ያሳየው ምህረትና ደግነት ዓለም የመሰከረለት በመሆኑ ሚኒሊክን ለማሳነስ ጡት ቆረጣ የከተቱት ኦነጎች የዘነጉት ያለና የነበረ አጉል ባህልና ታሪካቸው እና ያፈሰሱት ደም ያልደረቀ በብዙ ማስረጃ የተደገፈ መረጃ ያለ በመሆኑ አጀንዳው ወደእናንተ ተመልሶ ክስም ሆነ ክርክር ለመክፈት ከበቂ በላይ በመሆኑ ባለፈ ጉዳይ መነታረኩ ሊጠቅማችሁ እንደማይችል ወገናዊ ምክሬንም ልገልጽ እወዳለሁ።
ታሪክ እንምዘዝ ከተባለም አይጠቅምም እንጂ ብዙ ነገሮች ማንሳት ይቻላል። እዚህ ላይ ከመቶ አመት በፊት በነበረው የአመለካከት ኋላ ቀርነት አንጻር በዘመኑ ይካሄድ ከነበረው አስገራሚ ነገር አንደ መጽሄት ላይ ያነበብኩትን ብቻ ጠቅሼ ማለፍ እወዳለሁ ፤ የጅማው ባላባት አባ ጅፋር በአስተዳደራቸው ዘመን አምስት ባርያ (በአምስት ሰዎች) በአስራሁለት ሶሎግ ውሻ እንደለወጡ የሚነገር ታሪክ ተጽፎ አይቻለሁ። ይህ ማለት እኝህ የጅማ ባላባት ከዘመኑ ከነበረው የአስተሳሰብ ሚዛን አንጻር እንደታላቅ ወንጀል ሊቆጠርና ሊያወግዛቸው የሚሞክር የዚህ ዘመን ሊቅ ቢኖር መሣቂያ ከመሆን አያልፍም። በዚያ ዘመን ባርያ መሸጥና መለወጥ ፋሽን የነበረበት የሰው ልጅ የአመለካከት አድማሱ ያልሰፋ በነበረበት በዚያ ግዜ የተደረጉትን በዛሬ ሚዛን እንለካ ከተባለ ማለቂያ ወደሌለው ትርምስ የሚከት በመሆኑ ታሪክን ለ ታሪክነቱ መተው ይገባል። ይህን መንገድ የተከተሉት የዛሬይቱ ልዕለ ሃያሏ አሜሪካ ትላንት የጥቁር ሕዝቦች የቁም መቃብር የሰቆቃ ምድር እንዳልነበረች ዛሬ ያንን አሮጌ ታሪክ ወደኋላ ትተው በፍቅርና በአንድነት የዓለም መሪ የሆኑበት አቅም ገንብተዋል ። ትላንት በጥቁር ወንድሞቻችን በባርነት ሰንሰለት ታስረው የገነቡት ቤተመንግስት ታሪክ ተለውጦ በቆዳ ቀለም ይሰጥ የነበረው የመሪነት ቦታ የሃሰብ የበላይነት መሰረት ባደረገ ዘመናዊ መስፈሪያ መለካት በመቻላቸው ያ ርኩስ ታሪክ ተሽሮ ይህው ተምሳሌትነቱ ለዓለም ያንጸባረቀው የፕሬዘደንት ኦባማ ምርጫ አይተናል። ኦባማ ኦቫል ቢሮ ውስጥ ተሰቅሎ የሚታየው የጆርጅ ዋሽንግተን ፎቶ ከተሰቀለበት የቆየው ለኦባማ ነገድ ለጥቁር አፍሪካውያን የተመቸ ሆኖ አልነበረም ፤ እንዲያውም ጆርጅ ዋሽንግተንና የቀደሙት ዝነኞቹ የሜሪካ መንግስት ቀራጮች አብዛኞቹ የባሪያ አሳዳሪዎች እንደነበሩ የሃገሪቱ ታሪክ ሰነድ ውስጥ በይፋ ተቀምጦ ይገኛል። ዛሬ ዲሞክራት መሆን የመሰልጠን ምልክት የመሆኑን ያህል ከዛሬ መቶ አመት በፊት የባሪያ አሳደሪ መሆን እንደ ዘመኑ አመለካከት የጨዋነት መግለጫ ነበር። ነጻነቱን ያስከበሩለት ክብሩን የጠበቁለት የዛሬው የኔ አልጫ ትውልድ የሚዘለፉት የፖለቲካ ጨቅላዎች የሚያውካኩባቸው የትላንት መሪዎቻችን ይህን አይነት ተግባር ያልነበራቸው ጀግንነትን ከሃይማኖት የተላበሱት የኢትዮጽያ ነገስታት የባሪያ ንግድን በአዎጅ ከልክለው ስለመኖራቸው ታሪክ ምስክር ነው።
በአሁኑ ወቅት በሃገራችን አጀንዳ በመፈብረክ የስልጣን እድሜውን ለማርዘም የማይፈነቅለው ድንጋይ እንደሌለ የተረጋገጠለትና ማናቸውንም አይነት እርምጃ በመውሰድ ለስልጣኑ ሕልውና ዘብ በመቆም ሃይማኖትን በሃይማኖት ብሄርን በብሄር በማናከስ የመጣበትን ተጽዕኖ ለማለፍ ዛሬን ብቻ በማየት ሃገር አፍራሽ በሆነ ተግባር የተጠመደው ታሪክ አርካሹ የሱዳን አሽከር የአረብ አገልጋይ የሆነው የወያኔ ማፍያ ቡድን ሰሞኑን ከጀርባ በመሆን ተላላኪዎቹን መቃብር እንደ ፍልፈል እያስቆፈረ የሚኒሊክን ዘመን አስታኮ የተጀመረው የፀረ አማራ ፕሮፓጋንዳ ዘመቻ ተጠናክሮ የቴዲ አፍሮን የፍቅር የሙዚቃ ጉዞ ለማደናቀፍ ስፖንሰሩን ቢራ ጠማቂ ድርጅት በተጽዕኖ ስር በማዋል ጥቂት ጽንፈኛ የኦሮሞ ብሄርተኞችን በማነቃቃት እየተካሄደ ያለው ዘመቻ ወያኔዎች ያስደሰታቸው መሆኑን ከልሳኖቻቸው የሰሞኑ ዘገባ መረዳት ይቻላል። አበው የቆጡን አወርድ ብላ የብብቷን ጣለች እንዲሉ ወያኔዎች ኦሮሞውን በአማራው ላይ በማነሳሳት በዳር ተመልካችነት የሰላም ግዜ ለማግኘት እያቀናበረች ያለችው ሴራ በቀጣይ ምን ሊያስከትል እንደሚችልና የሚነደው እሳት ራሷን ወያኔንም ጭምር ይዞ ሊያወድም የሚችል መሆኑን ያልተረዱት የጥላቻ መንፈስ አይናቸውን የጋረዳቸው ወያኔዎች አማራውን ለማስጠቃትና ምኒልክን ለማወረድ የተነሳውን መንጋ ጽንፈኛ በልምድ ታጅቦ ወደ እነሱ የዘርና የሃይማኖት አጀንዳውን ይዞ ወደ እነሱ ሊመለስ እንደሚችል አለማረዳታቸው ምን ያህል የወያኔን የፖለቲካ ዘገምተኛነት የሚያሳይ ነው።
የተጀመረው ጉንጭ አልፋ ፖለቲካ መሬት ከረገጠ የጥላቻው ቅስቀሳ ወደ ግጭት ካመራ የአማራው ህዝብ ላለፉት 22 አመታት ታግሶና ችሎ እንደተቀመጠው የሚፈጸምበትን ጥቃት ዝም ብሎ እንደማያየው ሊረዱት ይገባል። አማራው በታሪኩ ራሱን ሲከላከል የኖረና ሃገሩንም ከሌሎች ወንድሞቹ ኢትዮጽያውያን ጋር በጋራ እንደጠበቀ ሁሉ ዛሬ ትጥቁን ፈቷል አልተደራጀምና በቀላሉ ልናጠቃው እንችላለን በሚል መንገድ የሚቃጣበትን ጥቃት ሕልውናውን ለማስጠበቅ ማናቸውንም ዋጋ ከፍሎ በአሸናፊነት እንደሚወጣ የማያጠራጥር ቢሆንም ፤ ይህ ህዝባዊ ቁጣ ከተቀጣጠለ ለማንኛውም ኢትዮጽያዊ ዜጋ ብቻ ሳይሆን ለአፍሪካ ቀንድ ጭምር የሚተርፍ ሰደድ እሳት እንደሚያስነሳ ቅን የሆነ ዜጋ ተገንዝቦ ይህን የክፋትና እርስ በእርስ እንድንጫራረስ የተሰጠንን ርኩስ አጀንዳ በግዜ አደብ እንዲይዝ መደረግ የሚገባው ጥረት ማድረግ በሁሉም ጽንፎች ያሉ ወገኖች እርጋታ እንዲያደርጉና በተለይ ወጣት ምሁራኖች በዚህ የወንድማማቾች ፖለቲካዊ ጡዘት ለማርገብ ከስሜት ባሻገር ስልጡን የሆነ ውይይት በየማህበራዊ መድረኮች በማድረግ ሰላም ለማስፈን የሚቻለውን ማድረግ ይኖርብታል።
ኢትዮጽያ በክብር ለዘላለም ትኑር!!!
አሜን

Saturday, January 4, 2014

የማይመስል ነገር ለሚስትህ አትንገር! ኢቲቪ ስለ ኢሳት


ዶክመንታሪ ብሎ ዝም! አስቡት እስኪ ኢሃዲግን በሚያክል አፋኝ መንግስት በኢቲቪ ኢሳት ሲብጠለጠል፣’ኢሳት ማለት የኢትዮጵያ ህይዝብ እውነተኛ የመረጃ ወፍጮ ነው!’Ethiopian Satellite Television (ESAT)

ለምን ግን በዚህ ሰአት ስለ ኢሳት ዶክመንታሪ መስራት አስፈለገ?
-ኢሳት ከተመሰረተ አንስቶ እስካሁን ድረስ በእውነተኛ መረጃ ምንጭነት በመላው የኢትዮጵያ አንጀት ውስጥ ተደላድሎ መቀመጡን ስልሚያውቁ!
-ይከስማል ይጠፋል አቅሙ ይዳከማል ሲሉት እንደ ወይን ጠጅ ከለት እለት እየበሰለና እየጎመራ መምጣቱን ስላዩ!
-በመላው ኢትዮጵያ የሚገኙ ተምልካቾች ለኢሳት በመደወል በሚሰጡት አስተያየት ህዝቡ በሚገባ እየተከታተለው መሆኑን ስላረጋገጡ!
-ከዚህ ቀደም ከሰባት ጊዜ በላይ ጃም በማደርግ እና በዲፕሎማሲያዊ መንገድ ኢሳት ወደ ኢትዮጵያ የሚያደርገውን ስርጭት ቢያቛርጡም ኢሳት ግን የተለያዩ የሳተላይት አማራጮችን በመጠቀም ከአንድ አመት በላይ(እስካሁን) ያለ ምንም ችግር ወደ ኢትዮጵያ ማሰራጨ ስለቻለና አሁን ካለው የኢኮኖሚ ሁኔታ አንጻር ጃም ማድረግ ከፍተኛ ወጪ ስለሚጠይቅ!
-ህዝብን አደንቁሮ በኢቲቪ ፕሮፓጋንዳ ብቻ የህዝብን አምሮ ለማደደብ በሚደርገው ጥረት ኢሳት ነጻ ሃሳብ በማነሸራሸር እንቅፋት ስለሆነ!
ባጠቃላይ ኢሳት ለህዝብ እውነትን በመግለጽ ለስረአቱ የእግር እሳት መሆኑ ስለታመነበት:- የኢሳትን ይዘት ተንትኖ እና እውነቱ ይህ ሆኖ ሳለ ኢሳት ግን እንዲህ ይላል በሚል አመክኖዋዊ አስተሳሰብ ከመሞገት ይልቅ፣ ግንቦት ሰባት አሸባሪነው ኢሳት ደግሞ የግንቦት ሰባት ነው ስለዚህ ኢሳት አሸባሪ ነው ብለው ከደመደሙ በኋላ ህዝቡ አሳትን መከታተል እንደ ሽብርትኛነት አድርጎ ቆጥሮት መከታተሉን እንዲያቆም ለማግባባት ቀጥሎም ለማስገደድ ያመች ዘንድ የተሰራ ድራማ ነው! የዘፈን ዳር ዳሩ እስክሳ ነው ትል ነበር አያቴ! የሚገርመው ግን አቶ ሃይለማሪያም እንዳሉት “ግንቦት ሰባት በቅዠትላይ የተመሰረተ ድርጅት” ከሆነ ይህን ያክል ተከታታይ ድራማዎች በመስራት ምን አደከማቸው? በራሱ ጊዜ ከእንቅሉ ይባንንላቸው የለም እንዴ?
እናንት አሸባሪ ኢሳቶች ሆይ ህዝብን እልል እያስባላችሁ አንባገነኖችን እያሸበራችሁ ነውና በርቱ! በርቱ! በርቱ!
ቢታኒያ አለማየሁ

 

አንድ ለአምስት – ከቃሊቲ ዉጭ ሌላ ቃሊቲ

ወያኔ የጫካ ዉስጥ ኑሮ በቃኝ ብሎ አዲስ አበባን ከረገጠ በኋላ ኢትዮጵያ ዉስጥ ብዙ አዳዲስ ቃላት ተፈጥረዋል፤ አንዳንድ አብረናቸዉ ያደግናቸዉ ቃላትና የቦታ ስሞች ደግሞ እየፋፉ መጥተዉ የሌሎች ሰፋ ያሉ ሀሳቦች መግለጫ ሆነዋል። ለምሳሌ የዛሬ ሃያ አምስት አመት ኮሌጅ የጨረሰ ልጅ አባቱን ቃሊቲ መግባቴ ነዉ ብሎ ቢነግረዉ አባቱ . . . . ምንዉ ስራ አገኘህ እንዴ ብሎ ከመጠየቅ ዉጭ በልጁ አባባል በፍጹም አይደነግጥም። ዛሬ ግን “ዕድሜ ለወያኔ” ቃሊቲ ሲባል የማይደነግጥ ኢትዮጵያዊ የለም። በፋብሪካ ማዕከልነቷ ትታወቅ የነበረችዉ ቃሊቲ ዛሬ አጥሩ ዉስጥ ወያኔ አፍኖ የከተታቸዉ ሰላማዊ ዜጎች ከአጥሩ ዉጭ ደግሞ የእነዚሁ ሰላማዊ ዜጎች ቤተሰቦች የሚተራመሱበት የጭንቅና የመከራ አምባ ሆናለች። አዎ ቃሊቲ እንደ አልባኒያዋ ቡሪልና እንደ ሩሲያዋ ሳይቤሪያ ዜጎችን ለማፈንና በዜጎች ላይ ሰቆቃ ለመፈጸም ሆን ተብላ እንደገና የተፈጠረችና አለፍላጎቷ አስቀያሚ ገጽታ የተከናነበች ከተማ ሆናለች። ቃሊቲ ታሪክ ከክፋታቸዉና ከጭካኔያቸዉ ዉጭ በፍጹም የማያስታዉሳቸዉን የሩሲያዉን ጆሴፍ ስታሊንና የአልባኒያዉን ኤንቨር ሆዣን እኛ ኢትዮጵያዉያን አለዝምድናችን በግድ እንድናስታዉሳቸዉ የተገደድንባት የአምባገነንነት ተምሳሌት ናት። የሚገረመዉ ቃሊቲ ወያኔ ተሸክሞ ካመጠልን የጆሴፍ ስታሊንና ኢንቨር ሆዣ መንታ ትዝታዎች አንዷ ናት። ጆሴፍ ስታሊንና ኢንቨር ሆዣ የሩሲያንና የአልባኒያን ህዝብ እስር ቤት ዉስጥ ብቻ አልነበረም ያሰሩት፤ አንድ ለአምስት በሚሉት ማለቂያ በሌለዉ ሰንሰለታቸዉ በመኖሪያ ቤቱ ዉስጥ፤ በሚሰራበት ፋብሪካ ዉስጥ፤ በሚማርበት ት/ቤቶች ዉስጥና በተደራጀበት ገበሬ ማህበር ዉስጥ ጭምር ጭምድድ አድርገዉ አስረዉታል።
የኢትዮጵያን ህዝብ የሚረገጡትንና እንደ እንስሳ እየታሰሩ የሚገረፉበትን መንገድ ለማወቅና ልምድ ለመቅሰም አልባኒያ ድረስ የሄዱት ዘረኞቹ የወያኔ መሪዎች ከአልባኒያ ይዘዉብን የመጡት ቃሊቲን ብቻ አይደለም፤ ከቃሊቲ ዉጭ ህዝብን በሰንሰለት ማስር የሚያስችላቸዉን “አንድ ለአምስት” አደረጃትም ይዘዉ መጥተዉ ኢትዮጵያ ዉስጥ ተግባራዊ አድርገዋል። አንድ ለአምስት ወያኔ ምንም ይበለዉ ምን በግንብና በሽቦ አጥር ያልታጠረ ሰፊ እስር ቤት ነዉ፤ ወይም አንድ ለአምስት – ከቃሊቲ ዉጭ የሚገኝ ሌላ ቃሊቲ ነዉ። ወያኔ የኢትዮጵያን ህዝብ በአንድ ለአምስት ሰንሰለት ማሰር ከጀመረ ቆይቷል። ዛሬ ወያኔ ይህንን የእነ ስታሊንን የመከራ ማራዘሚያ ገመድ ከገመደብን ከአመታት በኋላ “እንድ ለአምስትን” እንደገና ማንሳት የፈለግነዉ ጉዳዩ አዲስ ሆኖብን ሳይሆን ሁለት ነገሮች አሳስበዉን ነዉ፤ አንደኛዉ ወያኔ የ“እንድ ለአምስት” አደረጃጀትን የህብረተሰባችን መሰረት ወደ ሆነዉ ወደ ቤተሰብ ደራጃ ሲያወርደዉ በማየታችን ሲሆን፤ ሁለተኛዉ ደግሞ “እሾክን በእሾክ” እንዲሉ የኢትዮጵያ ህዝብ ከወያኔ ዘርኝነት፤ሰቆቃና ጭቆና ለመላቀቅ ወያኔ የፈጠረዉን አንድ ለአምስት አደረጃት በመሰላልነት ተጠቅሞ እራሱን እንዲያደራጅና ለወሳኙ ፍልሚያ እራሱን እንዲያዘጋጅ ለማሳሰብ ነዉ።
ወያኔ ነገረ ስራዉ ሁሉ ከጉልበትና ከሀይል ጋር የተያያዘ ነዉ፤ ስልጣን የያዘዉ በጠመንጃ ሀይል ነዉ፤ ስልጣን ላይ የቆየዉ በጠመንጃ ሀይል ነዉ። የኢትዮጵያን ህዝብ አንድ ለአምስት እያለ የሚያደራጀዉም በሀይል እያስገደደ ነዉ እንጂ የኢትዮጵያ ህዝብማ በወያኔ ስር መደራጀት ቀርቶ ወያኔ ድርጅቱ ብቻ ሳይሆን ወያኔ የሚባል ቃሉ እራሱ ከምድረ ኢትዮጵያ ቢጠፋ ደስታዉን አይችለዉም። የሚገርመዉ ወያኔ በዚያ ጠመንጃ በጨበጠበት እጁ የጻፈዉ ህገ መንግስት አንቀጽ 31 ማንኛዉም ሰዉ ለማንኛዉም አላማ በማህበር የመደራጀት መብት አለዉ ይላል፤ ሆኖም ይህ ህገመንግስታዊ መብት ለይስሙላ የተቀመጠ የባዶ ቃላት ክምር ነዉ እንጂ ኢትዮጵያ ዉስጥ ህዝብ በራሱ ፈቃድ መደራጀትም አለመደራጀትም አይችልም። ለመሆኑ ወያኔ በፍጹም በማይመለከተዉ በቤተሰብ ጉዳይ ጣልቃ የሚገባዉ ለምንድነዉ? እኛስ ኢትዮጵያዉያን ይህንን የወያኔ ጣልቃ ገብነት እንዴት አድርገን ነዉ እራሳችንን ነጻ ለማዉጣት የምንጠቀምበት?
በቅርቡ የቦሌ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ ለወረዳ ሁለት የላከዉን የቤተሰብ ማቋቋሚያ ቅጽ አስመልክቶ በሰጠዉ ተጨማሪ ማብራሪያ የቤተሰብ ፖሊስ መመስረት አስፈላጊ መሆኑን ጠቅሶ በቤተሰብ መካካል ለሚፈጠሩ አለመግባባቶችና ማህበራዊ ችግሮች መፍትሄዉ ቤተሰብን አንድ ለአምስት ማደራጀት እንደሆነ ተናግሯል። ባለፈዉ ሳምንት አጋማሽ ላይ የወያኔ ባለስልጣኖች በዳግማዊ ሚኒልክ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ዉስጥ ከየትምህርት ቤቱ ለተሰባሰቡ ርዕሰ መምህራንና ሱፐርቫይዘሮች አዲሱን አደረጃጀት አስመልክተዉ በሰጡት መግለጫ በቅርቡ ወደ ሁሉም ትምህርት ቤቶች ይወርዳል ብለዉ ካሉት የኮማንድ ፖስት አደረጃጀት በተጨማሪ “ትራንስፎርሜሺን ፎረም” እና “የልማት ቡድን” የሚባሉ አደረጃጀቶችም እንዳሉ ለማወቅ ተችሏል። የወያኔ ዘረኞች ስም እየቀያየሩ ኮማንድ ፖስት አሉት፤ “ትራንስፎርሜሺን ፎረም” ወይም “የልማት ቡድን” የሁሉም አደረጃጀት ተቀዳሚ ተግባር “አንድ ለአምስት” ተብሎ የተጀመረዉን አደረጃጀት ለማጠናከርና ለማስቀጠል ነዉ።
የኢትዮጵያ ህዝብ ይህንን ወይኔ ለራሱ እኩይ አላማ ሲል የጀመረዉንና ሁሉንም የህብረተሰብ ክፍል በማጠቃለል ላይ የሚገኘዉን የአንድ ለአምስት አደረጃጀት ወደ “ሚሊዮኖች ለሚሊዮኖች” አደረጀጃት በመቀየር ወያኔን እሱ እራሱ በፈጠረዉ ሰንሰለት ለማሰር ከአሁን የተሻለ ግዜ የሚያገኝ አይመስለንም። “አንድ ለአምስት” ከዛሬ በኋላ ወያኔ ኢትዮጵያዉያንን የሚሰልልበት ሳይሆን ኢትዮጵዉያን የወያኔን የስለላ መረብ የሚበጣጥሱበት፤ የማይተዋወቁ የትግል ጓደኞች የሚተዋወቁበት፤ ድርጅት የናፈቃቸዉ ኢትዮጵያዉያን እራሳቸዉን ከወያኔ አፈና ነጻ ለማዉጣት የሚደራጁበት የዝግጅት ቦታ መሆን አለበት። ወያኔ አንድ ለአምስት ያደራጀዉ የመንግሰት ሰራተኞችን፤ ተማሪዎችን፤ አርሶ አደሮችንና የከተማ ነዋሪዎችን እየነጣጠለ ለየብቻቸዉ ቢሆንም የኢትዮጵያ ህዝብ ግን ይህንን ወያኔ የፈጠረለትን መድረክ በመጠቀምና የወያኔን የልዩነት ግድግዳ በመሰባበር አንድ ለአምስትን የመገናኛዉና የመደራጃዉ መድረክ ማድረግ አለበት።
ወያኔ ስፍር ቁጥር የሌለዉ የአደረጃጀት አይነቶች እያመጣ የኢትዮጵያን ህዝብ እንደ ቋጠሮ የሚቋጥረዉ እሱ ሊነግረን እንደሚፈልገዉ ለኢትዮጵያ ህዝብ ደህንነት ተጨንቆ ወይም ለአገርና ለህዝብ ሰላምና ዕድገት አስቦ አይደለም። ወያኔ ለህዘብ ሰላምና ደህንነት የሚያስብ ቢሆን ኖሮ ማድረግ ያለበት የኢትዮጵያን ህዝብ መብትና ነጻነት ማክበር እንጂ ኮማንድ ፖስትና አንድ ለአምስት እያለ ህዝብን በማይታይ ሰንሰለት ማሰር አይደለም። ኮሚኒስቶች ከግማሽ ምዕተ አመት በላይ ዜጎቻቸዉን ያሰቃዩበት “አንድ ለአምስት” አደራጃጀት አራት ሰዎች አንዱ በሌላዉ ላይ ስለላ እያካሄድ ለአምስተኛዉ ሰዉ መረጃ የሚያቀብሉበት ጓደኛን ከጓደኛ፤ ተማሪን ከአስተማሪ፤ አንዱን ሰራተኛ ከሌላዉ ሰራተኛ ጋር የሚያጋጭና በህብረተሰብ መካከከል መተማመን እንዳይኖር የሚያደርግ የስቃይ ሰንሰለት ነዉ። ወያኔ ይህንን የስቃይ ሰንሰለት በየቦታዉ ሲዘረጋ ከርሞ ዘንድሮ ካልጠፋ ቦታ ወደ ቤተሰብ ደረጃ እያወረደዉ ይገኛል። ፓርላማዉን ጨምሮ የኢትዮጵያን የፖለቲካ ስልጣን፤ መከላከያዉን፤ ደህንነቱንና የአገሪቱን የኤኮኖሚ መዋቅር ሙሉ በሙሉ የሚቆጣጠረዉ ወያኔ ይህ ሁሉ አልበቃ ብሎት ፈጣሪ ለአባትና ለእናት የሰጠዉን ብቸኛ ሀላፊነት የራሱ ለማድረግ አንድ ለአምስትን በየቤተሰቡ ለመዘርጋት እየሞከረ ነዉ።
“ፈጣሪ ሊያጠፋዉ የፈለገዉን ያሳብደዋል” ተረት ወያኔን በትክክል የሚገልጸዉ የአባቶቻችን ተረት ነዉ። በእብደት ቢባል፤ በጭቆና፤በዘረኝነት፤ በትዕቢት፤ ወይም ህዝብን በመበደልና አገር በመበተን አገራችን ኢትዮጵያ ከወያኔ የባሰ እብድ በፍጹም ሊመጣባት አይችልም። ይህ ለይቶለት ያበደ ስርዐት የአንድ ለአምስት አደረጃጀትን ብቻ ሳይሆን ካሁን በኋላ የሚወስዳቸዉን ማንኛዉም አይነት እርምጃዎች የኢትዮጵያ ህዝብ እራሱን ከባርነት ነጻ ለማዉጣት መጠቀም መቻል አለበት። ወያኔ በጠመንጃ ሀይል ከቀማን መብቶች አንዱ የመደራጀት መብት ነዉ፤ ሆኖም ለራሱ በሚያመች መንገድ አንድ ለአምስት እያለ እያደራጀን ነዉ። የኢትዮጵያ ህዝብ ይህንን የወያኔን አንድ ለአምስት አደረጃጀት ተጠቅሞ እራሱን ለማደራጀትና ከወያኔ የአፈና ሰንሰለት ለመላቀቅ አመቺ አጋጣሚ ተፈጥሮለታል። ወጣቱ፤ገበሬዉ፤ሠራተኛዉ፤ አስተማሪዉና የከተማ ነዋሪዉ ማህበረሰብ የየራሱን የጎበዝ አለቆች እየመረጠ ወያኔን እራሱ በገመደዉ ገመድ ማሰር ካለበት ግዜዉ አሁን ነዉ።
ከፋሺስት ጣሊያን ወረረ አገራችንን ያዳኗት ጀግኖች አባቶቻችን መሪ የለንም ብለዉ ጠላትን ዝም ብለዉ አልተመለከቱም። እነ በላይ ዘለቀ፤ አብዲሳ አጋና ጃገማ ኬሎ የጎበዝ አለቃ መርጠዉ እራሳቸዉን አደራጅተዉ ነዉ አገራችንን ከአደጋ ያዳኗት። በአምስቱ የትግልና የአርበኝነት ዘመን በትጥቅ፤ በቁሳቁስና በዘመናዊነት የሚበልጣቸዉን የፋሺስት ጣሊያን ጦር አሳፍረዉ ወደመጣበት የመለሱት አባቶቻችን ለድል የበቁት ፋሺስት ጣሊያን በፈጠረዉ የድርጅት መዋቅር ዉስጥ እራሳቸዉን አደራጅተዉ ነዉ። አብዲሳ አጋ ጣሊያንን ያርበደበደዉ በጣሊያን ተራሮችና በረሃዎች ዉስጥ ነዉ። ዘርዓይ ደረስ የጣሊያኖችን አንገት የቀላዉ በሮም አደባባዮች ዉሰጥ ነዉ። ዛሬ በወያኔ ጥቁር ፋሺስቶች እየተገዛ ቁም ስቅሉን የሚያየዉ ኢትዮጵያዊ የእነዚህ ጀግኖች የልጅ ልጅ ነዉና የአባቶቹን ታሪክ በመድገም ወያኔ በፈጠራቸዉ ድርጅቶች ዉስጥ እየተደራጀ እራሱን፤ አገሩንና ወገኑን ነፃ ማዉጣት አለበት።
ወያኔን በህዝባዊ አመጽም ሆነ በህዝባዊ እምቢተኝነት ወይም በሁለቱም የትግል ስልቶች ታግሎ አገራችንን ነጻ ለማዉጣት ከዉጭ የሚመጣ ሀይል የለም፤ ነጻ አዉጪዉም በሚገኘዉ ነጻነት ተጠቃሚዉም ያለዉ እዚያዉ ኢትዮጵያ ዉስጥ ነዉ። ነፃነት ያለትግል ትግል ደግሞ ያለ ድርጅት በፍጹም የሚታሰቡ ነገሮች አይደሉም። ከአላማ ጽናት ቀጥሎ አንድ ህዝብ ነፃኑቱን እንዲጎናጸፍ የሚያስችለዉ ድርጅታዊ ብቃቱ ነዉ፤ ወያኔ የኢትዮጵያ ህዝብ ከሱ ፈቃድና ፍላጎት ዉጭ እንዳይደራጅ አጥብቆ የሚታገለዉ ይህንን ሀቅ በሚገባ ስለሚረዳ ነዉ። ሆኖም የኢትዮጵያ ህዝብ ነፃነቱን ለመቀዳጀት መታገል ለመታገል ደግሞ ወያኔ ፈቀደም አልፈቀደ ህዝብ በመረጠዉና ይበጀኛል ብሎ ባሰበዉ መንገድ ሁሉ መደራጀት አለበት። የኢትዮጵያ ህዝብ በወያኔ ሰላዮችና ካድሬዎች ተከብቦ እንደሚኖር የታወቀ ነዉ፤ ሆኖም ይህንን ከበባ ጥሶ ለመዉጣት ወያኔ እራሱ ያመቻቸዉ መንገድ አለ፤ እሱም ከሰራተኛና ከገበሬዉ ተነስቶ ቤተሰብ ድረስ የወረደዉ የወያኔ “አንድ ለአምስት” አደረጃጀት መዋቅር ነዉ።
የኢትዮጵያ ህዝብ ባለፉት 35 አመታት በሁለት አምባገነን ስርዐቶች ዉስጥ አልፏልና ስለአምባገነኖችና ስለ አምባገነንነት ብዙ ልምድ አለዉ። ወያኔ የኢትዮጵያን ህዝብ አንድ ወጥ በሆነ ድርጅታዊ መዋቅር ዉስጥ የሚያደራጀዉ የህዝብን ስነ ልቦና ለመስበርና ህዝብ በፍርሀት ደመና ተዉጦ እየሰገደ እንዲኖር ለማድርግ ነዉ። የኢትዮጵያ ህዝብ ግን የወያኔን ማንነት በሚገባ የተረዳዉ ስለሆነ የተገነባ ሞራል ያለዉና በራሱ የሚተማመን ህዝብ ነዉ፤ ስለሆነም ወያኔ የፈጠረዉን የድርጅት ጋጋታ እራሱን ነፃ ለማዉጣት ይጠቀምበታል የሚል ሙሉ እምነት አለን። ያለፈቃዳቸዉና ያለ እምነታቸዉ በግዴታ በአንድ ለአምስት ከተደራጁ ሰዎች ከአስር ዘጠኙ ወያኔን የሚቃወሙና የወያኔን ስርዐት ለማፍረስ የሚታገሉ ሰዎች ናቸዉ። እነዚህ ሰዎች ወያኔ ለስለላና ለጭቆና ያዋቀረውን የ“አንድ ለአምስት” አደረጃጀት ወያኔን እራሱን ለመታገልና ብሎም ለማዳከም እንደ መሣሪያ ተጠቅመዉ ይህንን አስከፊ ስርዐት ከጀርባቸዉ ላይ አ
 

የኢህአዴግ ባለስልጣናት ለኢሳት ቃለምልልስ እንዳይሰጡ ታዘዙ

ታህሳስ ፳፭( ሃያ አምስት )ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ባለስልጣናቱ ማንኛውንም ቃለምልልስ ለኢሳት ቢሰጡ በአሸባሪነት ይከሰሳሉ። የባለስልጣኖች አንደኛው መገምገሚያም ለኢሳት መረጃ በመስጠት እንደሚወሰን ከኢህአዴግ የመረጃ ክፍል የደረሰን መረጃ ያመለክቷል። መመሪያው ለህዝብ ግንኙነት ሰራተኞች፣ ለደህንነት ሰራተኞች፣ ለመንግስት ባለስልጣናት እና ለ ኮሚኒኬሽን ባለሙያዎች መተላለፉ ታውቋል።
የመንግስት ባለስልጣናት ለኢሳት መረጃ በመስጠት ድርጅቱን ህጋዊነት እያላበሱትና ሌሎችም ዜጎች አንዲናገሩበት እያደፋፈሩ ነው የሚል ምክንያት መሰጠቱ ታውቋል። ባለስልጣናቱ ከኢሳት በተጨማሪ ለአሜሪካ ድምጽ እና ለአንዳንድ ስማቸው ያልተጠቀሰ ድረገጾችም መረጃ እንዳይሰጡ ታዘዋል። መመሪያውን ያወጡት የብሄራዊ የመረጃ ደህንነት እና ኮሚኬሽን መስሪያ ቤት በጋራ በመሆን ነው። በዚህ ዙሪያ ተጨማሪ ዘገባ በሚቀጥሉት ቀናት ይኖረናል።

Thursday, January 2, 2014

ለ18 ዓመታት በስራ ላይ የቆየው ሕግ ሕገመንግስትን ይጥሳል ተባለ

ታህሳስ ፳፬( ሃያ አራት )ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የፌዴሬሽን ምክርቤት ላለፉት 18 ዓመታት በስራ ላይ የነበረውና የቀድሞ ጠ/ሚኒስትር አቶ ታምራት ላይኔን ጨምሮ የተለያዩ ባለስልጣናት ጉዳያቸው የታየበት የፌዴራል ፍርድ ቤቶች ማቋቋሚያ አዋጅ ቁጥር 25/88 አንቀጽ 8  ተራ ቁጥር 1 እና የተሻሻለው የጸረ ሙስና ልዩ የማስረጃ ሕግ አዋጅ ቁጥር 434/97 አንቀጽ 7 ተራቁጥር 1 ሕገመንግስቱን እንደሚጥሱ በመወሰን የመላኩ ፈንታን አቤቱታ ውድቅ አደረገ፡፡
የፌዴራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት 15ኛ ወንጀል ችሎት በሙስና ወንጀል የተከሰሱት አቶ መላኩ ፈንታ የኢትዮጽያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር በነበሩበት ጊዜ በሚኒስትር ማዕረግ ሆነው ሲሰሩ ስለቆዩ የተከሰሱበት ጉዳይ መታየት ያለበት በፌዴራል ጠቅላይ ፍርድቤት ነው ወይስ በፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በሚለው ጭብጥ ላይ የግራ ቀኙን ክርክር ካደመጠ በሃላ ለጉዳዩ አግባብነት ያላቸው የፌዴራል ፍርድ ቤቶች ማቋቋሚያ አዋጅ ቁጥር
25/88 አንቀጽ 8-1 እና የተሻሻለው የጸረ ሙስና ልዩ የማስረጃ ሕግ አዋጅ ቁጥር 434/97 አንቀጽ 7-1
የህገመንግስቱን አንቀጽ 20-6 ይጥሳሉ ወይስ አይጥሱም የሚለው ነጥብ ሕገመንግስታዊ ትርጉም ያስፈልገዋል በማለት ለሕገመንግስት ጉዳዮች አጣሪ ጉባዔና ለምክርቤቱ በመራው መሠረት ጉዳዩ የፌዴሬሽን ምክርቤትን አባላትን በዛሬው ዕለት ለሁለት ከፍሎ አከራክሮአል፡፡
በፍርድ ቤቱ ትዕዛዝ መሰረት የሕገመንግስት አጣሪ ጉባዔ ጉዳዩን መርምሮ እነመላኩ ፈንታ ያነሱት ጭብጥ የህገመንግስት ትርጉም ያስፈልገዋል በሚል ውሳኔ ካሳለፈ በኃላ ከትላንት በስቲያ እና በትናትናው ዕለት በምክርቤቱ
የሕገመንግስትና የክልሎች ጉዳይ ቋሚ ኮሚቴ በጉዳዩ ላይ ተወያይቶ የደረሰበትን የውሳኔ ሃሳብ በዛሬው ዕለት ለፌዴሬሽን ምክርቤት አቅርቧል፡፡
በውሳኔ ሃሳቡ ላይ እንደተመለከተው የህገመንግስት አጣሪ ጉባዔ በሕገመንግስቱ አንቀጽ 84 እና በአዋጅ ቁጥር
789/2005 በተሰጠው ስልጣን መሰረት የተመራለት የትርጉም ጥያቄ መርምሮ ሰዎች የመንግስት ባለስልጣን
በመሆናቸው ብቻ ከሌሎች ተለይተው በፌዴራል ጠቅላይ ፍርድቤት ክሳቸው እንዲታይ ማድረግ የህገመንግስቱን አንቀጽ
20 -6 ማለትም ይግባኝ የማቅረብ መብትን ስለሚጥስ፣ እንዲሁም በተመሳሳይ ወንጀል ድርጊት የተከሰሱ ሰዎች መካከል አንዱ የይግባኝ መብት እንዲያገኝ ሌላው ይህን መብት እንዳያገኝ የሚፈቅድ ሕግ በመሆኑ፣ በተጨማሪም የህገመንግስቱ አንቀጽ 25 ሰዎች ሁሉ በሕግ ፊት እኩል ናቸው ፣በማናቸውም ሁኔታ በመከሰሳቸው ልዩነት አይደረግም የሚለውን የህገመንግስት ድንጋጌ መጣስ ስለሚሆን የአዋጅ ቁጥር 25/88 አንቀጽ 8-1 እና የተሻሻለው የጸረ ሙስና ልዩ የማስረጃ ሕግ አዋጅ ቁጥር 434/97 አንቀጽ 7-1 ድንጋጌዎች በሕገመንግስቱ አንቀጽ 9-1 ማለትም ሕገመንግስቱ የሕጎች ሁሉ የበላይ መሆኑን የሚያሳውን ድንጋጌ ተፈጻሚ እንዳይሆኑ ያደርጋል በማለት የውሳኔ ሃሳቡን አቅርቧል፡፡
በዚህ መሰረት ቋሚ ኮምቴው ከአጣሪ ጉባዔውና በጹሑፍ ከቀረበው የውሳኔ ሃሳብ በተጨማሪ የጉባዔው አባላት ቀርበው ለቋሚ ኮምቴው እንዲያስረዱ ተደርጎ ቋሚ ኮምቴው በጉዳዩ ላይ በቂ ውይይት ካደረገ በሃላ የውሳኔው ሃሳብ በአብላጫ ድምጽ እንደተቀበለው ታውቋል፡፡ምክርቤቱ ዛሬ በጉዳዩ ላይ በተወያየበት ወቅት ምክርቤቱን ለሁለት የከፈሉ ሃሳቦች ተንሸራሽረዋል፡፡ በተለይ አቶ መላኩ ፈንታ ያቀረቡትን ጥያቄ ትክክለኝነቱን በማረጋገጥ የተሟገቱ ወገኖች እንዳስረዱት የፌዴራል ፍርድ ቤቶች ማቋቋሚያ አዋጅ ቁጥር 25/88 አንቀጽ 8(1) ባለስጣናት ከስራ ጋር በተገናኘ ወንጀል ፈጽመው ሲገኙ ጉዳያቸው
በፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት እንደሚታይ እንደሚደነግግ፣ አዋጅ ቁጥር 434/97 አንቀጽ 7(1) በተመሳሳይ ሁኔታ
ይህንኑ ድንጋጌ እውቅና እንደሚሰጥ፣ በተለይ አዋጅ ቁጥር 25/88 ከወጣ 18 ዓመታት የቆጠረ መሆኑን በማስታወስ በዚህ ሕግ የቀድሞ ጠ/ሚኒስትር አቶ ታምራት ላይኔን ጨምሮ ሌሎች ባለሰልጣናት ጉዳያቸው የታየበት እንደነበር አስታውሰዋል፡፡
ሕጉ በወቅቱ ሲወጣ መንፈሱ ባለስልጣናት የሕዝብ ጥቅም በሚጎዳ ወንጀል ውስጥ ገብተው ሲገኙ
ለሕዝብ ጥቅም ሲባል ጉዳያቸው ብቃት ባላቸው የፌዴራል ጠ/ፍ/ቤት ዳኞች እንዲታይ፣ጉዳዩም በአፋጣኝ እንዲታይ በማሰብ መሆኑን በመግለጽ ይህ ሁኔታ በምንም መልኩ የህገመንግስት ጥሰትን አያስከትልም ሲሉ ተከራክረዋል፡፡
አዋጆች ሲወጡ ተመክሮበት፣የተለያዩ ጉዳዩ የሚመለከታቸው ወገኖች ተሳትፈውበት እንደሆነ ያስታወሱት የምክርቤቱ አባላት ይህ አንቀጽ ከሕገመንግስቱ ጋር ይጋጫል ሲባልም ሕግ አውጪው አካል ሕገመንግስትን የሚጻረር ሕጎችን
በዘፈቀደ ያወጣል የሚል መልዕክት ያለው አደገኛ ውሳኔ ነው ያሉ ሲሆን ስህተት ነው ከተባለ በዚህ ሕግ ለተጎዱ ወገኖች ተጠያቂው ወገን ማን ነው ሲሉም ጠይቀዋል፡፡ ሌላ አስተያየት ሰጪም በ1988 ዓ.ም የወጣ ሕግ እስካሁን
ቆይቶ ሕገመንግስቱን የጣሰ ነው እያልን ነው ወይ ሲሉም በአግራሞት ጠይቀዋል፡፡ አንዳንዶቹም ጉዳዩ እንደገና ጊዜ ተሰጥቶት ቢታይ ይሻላል የሚል ሃሳብ አንጸባርቀዋል፡፡
አዋጅ ቁጥር 25/88 እና አዋጅ ቁጥር 434/97 ውስጥ የሚገኙት አንቀጾች ከህገመንግስቱ ጋር እንደሚጣረስ የውሳኔ ሃሳብ ያቀረበው ቋሚ ኮምቴ አባላት አንቀጾቹ የይግባኝ መብትን የሚያሳጡ፣ የሰዎችን በሕግ ፊት እኩል የመሆን ሕገመንግስታዊ ድንጋጌ የሚጥሱ መሆናቸውን በመጥቀስ የእነመላኩ ፈንታን ጥያቄ ውድቅ አድርገዋል፡፡
ምክርቤቱም በዚህ ጉዳይ ከተወያየ በሃላ አንቀጾቹ ከሕገመንግስቱ ጋር ይጻረራሉ በማለት በመወሰን የእነመላኩን አቤቱታ ውድቅ አድርጓል፡፡ በዚሁ ውሳኔ መሰረት የአቶ መላኩ ክስ በነበረበት ከፍተኛ ፍርድ ቤት  15ኛ ወንጀል ችሎት እየታየ የሚቆይ ይሆናል፡፡
የፌዴራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት 15ኛ ወንጀል ችሎት ታህሳስ 22/2006 ባስቻለው ችሎት በእነመላኩ ፈንታ መዝገብ ላይ የተነሳውን የሕገ-መንግስት ትርጓሜ ተጣርቶ እንዳልደረሰውና የፌዴሬሽን ምክርቤት ለታህሳስ 24 ቀን 2006 ዓ.ም በጉዳዩ ላይ ለመምከር አስቸኳይ ስብሰባ መጥራቱን በደብዳቤ እንደተገለጸለት፣ ውጤቱም ታውቆ ወደ ክርክር ለመግባት እንዲያስችል የነብዩ መሐመድ ልደት(መውሊድ) በማይውልበት ጥር 5 ወይም 6 ቀን 2006 ዓ.ም በጉዳዩ ላይ የመጨረሻ ውሳኔ ለመስጠት ተለዋጭ ቀጠሮ መያዙ ይታወሳል።
                         

የወያኔን “አንድ ለአምስቶች” ወያኔን ለማዳከም እንጠቀምባቸው

January2/2014

ወያኔ የኢትዮጵያን ሕዝብ ለመቆጣጠር እንዲያመቸው “አንድ ለአምስት” አደረጃጀትእያደራጀው ነው።  ይህ አደረጃጀት  ስታሊን ለሠላሳ ዓመታት ሶቭየት ኅብረትን፤ ኤንቨር ሆዣ ደግሞ ለአርባ ዓመታት አልባኒያን ጠፍረው የገዙበት ስልት ነው። በዚህ የአገዛዝ ስልት መሠረት እያንዳንዱ ሰው በመዋቅር ተይዞ አራቱ ለአንዱ መረጃ የሚያቀብሉበት ሥርዓት ይዘረጋል።   
ሕዝብን በድርጅት አባልነት ስም በመዋቅር ማስገባት ለአንባገነኖች የሚሰጠው ዋነኛ ጥቅም የማኅበረሰብን ስነልቦና መስበሩ ነው። ይህ አወቃቀር ዜጎች የአምባገነኑን መንግሥት ኃይል መጠን በላይ አግዝፈው፤ ራሳቸውን ደግሞ አንኳሰው እንዲመለከቱ ያደርጋቸዋል። ዜጎች፣ “መንግሥት እያንዳንዱን ነገር አብጠርጥሮ ያውቃል” በሚል የፍራቻ ቆፈን እንዲያዙ ያደርጋቸዋል። እያንዳንዱ ሰው ጓደኛውን እንዲጠረጥር በማድረግ አምባገነኖች የስለላ ተቋማቸዉ ጠንካራና ሁሉን-አዋቂ እንዲመስል ያደርጉታል።
ይሁን እንጂ የማኅበረሰብ ስነልቦና ካልተሰበረ፤ በፍራቻ ፋንታ በራስ መተማመን ከዳበረ ማንም ያደራጀው ማን ነፃ ህሊና ያላቸው አባላት ድርጅቱን ራሳቸውን ነፃ ለማውጣት ይጠቀሙበታል። አሁን በደረስንበት ሁኔታ ይህንን በአገራችን ተግባራዊ የማድረግ ሰፊ እድል አለን።  የኢትዮጵያ ሕዝብ ከወያኔ ፍራቻ እራሱን ነፃ እያወጣ ነው። ወያኔ ከስታሊንም ሆነ ከኤንቨር ሆዣ በተለየ መንገድየአመለካከትና የርዕዮተዓለም ጉዳይ የሚያሳስበዉ ሀይል አይደለም።ቢያሳስበውም የሕዝብን ቀልብ የሚይይዝበት ምንምነገር የለውም። ይህ ባህሪይዉ ነዉ ነው ወያኔ በእጅጉ የተጠላ ኃይል እንዲሆን ያደረገው። 
እንዲህ በግዴታ እንጂ በእምነት ያልተሰባሰቡ ሰዎች ባሉበት ሁኔታ ተመሳሳይ ፀረ-ወያኔ አቋም ያላቸው ሰዎች በአንድ “አንድ ለአምስት” ሕዋስ ውስጥ የመገኘታቸው አጋጣሚ የጎላ ነው።  እነዚህ አባላት በግልጽ ከተነጋገሩበት ሕዋሱን ለፀረ-ወያኔ ትግል ሊጠቀሙበት ይችላሉ።  በመሆኑም ወያኔን ለመጨቆኛ መሣሪያነት ያዋቀረውን “አንድ ለአምስት” ራሱ ወያኔን መታገያ ብሎም ማዳከሚያ መሣሪያ ማድረግ ይቻላል። “አንድ ለአምስትን” በሽፋንነት በመጠቀም ውስጥ ውስጡን መጀራጀት በስፋት  ልንይዘዉና ልንሰራበት የሚገባ ስትራቴጄ ነው።
የወያኔ “አንድ አምስት” የኑሯችን አካል እየሆነ መጥቷል። በአንዳንድ ቦታዎች አለመደራጀት ሥራ የሚያሳጣ እየሆነ ነው።  በማናቸውም ምክንያት ራሳቸውን ወያኔ ጉያ ውስጥ ያገኙ የሕዝብ ወገኖች ካሁን በኋላ መሥራት ያለባቸው ወያኔን ከውስጥ ሆኖ የማዳከምን ሥራ ማፋጠን ነው። ለዚህ ደግሞ እንደ “አንድ ለአምስት” አመቺ የሆነ መዋቅር አይገኝም።
በአሁኑ ሰዓት ግንቦት 7 ሕዋሳቶቹን በሁሉም ቦታ ለማዋቀር ከፍተኛ ጥረት እያደረገ ይገኛል፤በዚህም መሠረት  የግንቦት 7 ሕዋሶች በሁሉም የአገሪቱ አካባቢ ባልተማከለ መልኩ በብዛት እየተመሠረቱ ነው። ከዚህ ህዋሳቶችን ከመዘርጋት ሥራ ጎን ለጎን ህዝቡ በያለበት የወያኔንየራሱንመዋቅር በመጠቀም ወያኔንና ስርዐቱን መገዝገዝ አለበት።
ይህንን ለማድረግ የግንቦት 7ን መመሪያ መጠበቅ አያስፈልግም። እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ በራሱ መንገድተግባራዊ ሊያደርገው የ የሚችለዉ ነገር ነው።
በመሆኑም ግንቦት 7፡ የፍትህ፣ የነፃነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ የወያኔ “አንድ ለአምስቶችን” ወያኔን ለማዳከም እንጠቀምባቸው የሚል ጥሪ ያቀርባል።
ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ!!!

በህወሀት ውስጥ የሚገኙ አክራሪ የሚባሉት ቡድኖች የመከላከያ አዛዥነቱ ከህወሀት እንዳይወጣ ለማድረግ ሲጥሩ መክረማቸው ተሰማ

ታህሳስ ፳፬( ሃያ አራት )ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በመከላከያ ውስጥ የሚገኙ ወታደራዊ አዛዦች ለኢሳት እንደገለጹት የህወሀት ባለስልጣናት ጄኔራል ሳሞራ የኑስን ለመተካት የተሻለ ቦታ ላይ የነበሩትን ጄ/ል አበባው ታደሰን አድማ ለማድረግ አስበዋል በሚል ሰበብ ማእረጋቸውን እንደያዙ የሚሰጣቸው ሃላፊነት እንዲቀነስና ከውድድር ውጭ እንዲሆኑ አድርገዋል። ለዚህም ስራ ጄኔራል ማሞ ሀይለማርያም እና ጄኔራል ሰሐረ መኮንን ተባባሪ መሆናቸውን ገልጸዋል።
ሶስቱ ጄኔራሎች “ጄኔራል ሳሞራ የኑስ በመከላከያ ውስጥ ያለውን ሙስና ለመከላከል ብቃቱ ጎሏቸዋል በሚል እንደተነጋገሩና ጉዳዩ በወታደራዊ ደህንነት መምሪያ ክፍል ሲታይ ቆይቶ በመጨረሻም ይፋ ተደርጎ” ሶስቱም ጄኔራሎች በያዙት ማእረግ ሃለፊነታቸው ቀንሶ እንዲሰሩ ተወስኖባቸዋል። ይሁን እንጅ ጄ/ል ሞላ እና ጄ/ል ሳህረ ከጄኔራል አበባው ጋር በአድማው የተሳተፉት ሆን ተብሎ ጄ/ሉን ከስልጣን ተፎካካሪነት ለማስወጣትና ፍትሀዊ ውሳኔ የተላለፈ መሆኑን ለተቀሩት የሰራዊቱ አባላት ለማሳየት መሆኑን ወታደራዊ ምንጮች ገልጸዋል።
ጄ/ል ሳሞራን ይተካሉ ተብለው የሚታሰቡት በቅርቡ የሌ/ጄ ማእረግ ያገኙት ጄ/ል ዮሃንስ ገብረመስቀል ናቸው። የተለያዩ ወታደራዊ አዛዦችን በማነጋገር ስለነበረው ሙሉ ድራማ ከዜናው በሁዋላ የምናቀርብ መሆኑን እንገልጻለን።

በኢትዮጵያ የተወሰኑ የቻይና ኩባንያዎች ከባለስልጣናት ጋር በመመሳጠር ስራ እየከለከሉን ነው ሲሉ 18 የቻይና ኩባንያዎች አመለከቱ

 

ታህሳስ ፳፫( ሃያ ሦስት )ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ሪፖርተር ባወጣው ዘገባ 18 የቻይና ኩባንያዎች ቤጂንግ ለሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ በግልባጭ ደግሞ ለጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት በላኩት ደብዳቤ ቀደም ብለው ወደ ኢትዮጵያ የገቡ የቻይና ኩባንያዎች ከአንዳንድ ባለስልጣናት ጋር በመመሳጠር ስራ እንዳናገኝ እንቅፋት ፈጥረዋል ብለዋል።

ኩባንያዎቹ የተሰማሩባቸው መስኮች የኃይል፣ የመስኖ፣ የመንገድና የንፁህ የመጠጥ ውኃ ግንባታዎች መሆናቸውን የዘገበው ጋዜጣው፣ በእነዚህ የመሠረተ ልማት ዘርፎች የተሰማሩት የቻይና ኩባንያዎች የኢትዮጵያ መንግሥት የተወሰኑ ባለሥልጣናት ቀደም ብለው ለገቡ የቻይና ኩባንያዎች ያለ ውድድር ሥራ እንደሚሰጡዋቸው፣ ደካማ የሥራ አፈጻጸም እያለባቸውም አንዱን ሥራ ሳይጨርሱ ተጨማሪ ሥራዎችን በላይ በላዩ ይሰጧቸዋል የሚል ቅሬታቸውን ዘርዝርው ለመንግስት አቅርበዋል።
ጥቂት ነባር የቻይና ኩባንያዎች በኢትዮጵያ መንግሥት ገንዘብ የሚሰሩ ፕሮጀክቶችን የመያዝ እንዲሁም ከቻይና መንግሥት በሚገኝ ብድር የሚገነቡ ፕሮጀክቶችን የመቆጣጠር አዝማሚያ እያሳዩ መምጣታቸውን ጠቅሰዋል።

ነባር ኩባንያዎች ሥራዎችን የሚያገኙት ከተወሰኑ ከፍተኛ የመንግሥት ባለሥልጣናት ጋር በመመሳጠር ነው የሚሉት አዲሶቹ ኩባንያዎች፣ ለሌሎች ኩባንያዎች ክፍት ሳይደረግ በቀላሉ በቢሊዮን የሚቆጠር ዋጋ ያለው ሥራ እንደሚሰጣቸውም ገልጸዋል።
ከኢትዮጵያ መንግሥት አንዳንድ ባለሥልጣናት በተጨማሪ ቻይና ኤምባሲ ውስጥ ቦታ ያላቸው ግለሰቦችም ለተወሰኑ የቻይና ኩባንያዎች እንደሚያዳሉ ያስረዳሉ ሲል ዘገባው ጠቅሷል፡፡
ሌሎቹን በመግፋት የተወሰኑትን የሚተባበሩ በመሆኑ ብዙኃኑ የቻይና ኩባንያዎች ኢትዮጵያ ውስጥ ሥራ ማግኘት እንዳይችሉ መደረጉንም በመግለጽ መንግሥት ከፍተኛ ገንዘብ እንዲያጣ ከመደረጉም በላይ፣ ተስፋ የተጣለባቸው ፕሮጀክቶች ደካማ አፈጻጸም ባላቸው ኩባንያዎች እጅ እየወደቁ  እንደሚገኙ ተገልጿል።

አዲሶቹ ኩባንያዎች እንደሚሉት፣ ኢትዮጵያ ውስጥ የገቡት አብዛኞቹ የቻይና ኩባንያዎች አነስተኛና መለስተኛ አቅም ያላቸው ናቸው፡፡ ጉዳዩን የቻይናና የኢትዮጵያ መንግሥታት ተረድተው መፍትሔ እንዲሰጧቸው አዲሶቹ ኩባንያዎች ጠይቀዋል።
ዘገባውን ተከትሎ አስተያየታቸውን የጠየቅናቸው የኢኮኖሚ ባለሙያው ዶ/ር ታደሰ ብሩ እንዳሉት፣ በኢትዮጵያ ውስጥ እየተገነቡ በጥራት ጉድለት ምክንያት ለሚፈርሱት መንገዶችና ህንጻዎች ከቻይና ኩባንዎች በላይ የኢትዮጵያ መንግስት ባለስልጣናት ናቸው ብለዋል። ዘገባው በከፍተኛ የኢትዮጵያ መንግስት ባለስልጣናትና በቻይና ኩባንያዎች መካከል ያለውን የሙስና ትስስር ያሳያል በማለት ዶ/ር ታደሰ ገልጸዋል