Tuesday, February 18, 2014

የኢትዮጵያ አየር መንገድ የተጠለፈበትን ምክንያት ለማወቅ የሚደረጉ እንቅስቃሴዎች እንደቀጠሉ ነው

አየር መንገዱ ከአዲስ አበባ ወደ ሮም ጣሊያን በማምራት ላይ በነበረበት ጊዜ  ረዳት አብራሪው የጉዞውን አቅጣጫ በመቀየር ጄኔቭ አውሮፓላን ማረፊያ በማሳረፍ እጁን ለፖሊስ ሰጥቷል።
የኢትዮጵያ መንግስት የኮሚኒኬሽን ባለስልጣን የሆኑት ሬድዋን ሁሴን አየር መንገዱ የተጠለፈው ሱዳን በቆመበት ጊዜ በተሳፈሩ ማንነታቸው ያልታወቁ ሰዎች ነው በማለት መጀመሪያ ላይ ለረዩተርስ መግለጫ ቢሰጡም፣ የስዊዘርላንድ ፖሊስ ግን ፈጥኖ ጠላፊው የአየር መንገዱ ረዳት አብራሪ መሆኑንና የደህንነት ስጋት እንዳለበት በመግለጽ እጁን በሰላም መስጠቱን አስታውቀዋል።
በአለም የጠለፋ ታሪክ ያልተመደ ክስተት ነው የተባለው ይህ የአውሮፕላን ጠለፋ፣ የፖለቲካ ይዘት ያለው ሳይሆን እንደማይቀር ይገመታል።
ማንነቱ ያልታወቀው ረዳት ፓይለት በ30 ዎቹ የእድሜ ክልል ውስጥ የሚገኝ ሲሆን፣ ጄኔቭ አውሮፕላን ማረፊያ እንደደረሰ በመስኮት በኩል በመውጣት እጁን በሰላም ለፖሊስ ሰጥቷል። ፖሊስ እንዳስታወቀውም ጠላፊው ምንም አይነት የጦር መሳሪያ አልያዘም።
በአውሮፕላኑ ውስጥ በነበሩ ተሳፋሪዎች ላይ ምንም አይነት ጉዳትም አልደረሰም።
ጄኔቭ የሚገኘው የኢሳት ወኪል እንደዘገበው ምንም እንኳ ጄኔቫ አየር ማረፊያ ከሰአታት በሁዋላ ተራግገቶ ስራውን ለማከናወን የቻለ ቢሆንም፣ በኢትዮጵያ ሰአት አቆጣጠር እስከ ቀኑ 9 ሰአት ድረስ ተሳፋሪዎች ወደ ሮም አልተመለሱም፣ አውሮፕላኑም ባለበት ቆሞ ይታይ ነበር። ከቀኑ 9 ሰአት ከሰላሳ አካባቢ አውሮፕላኑ ለጥገና ወይም ተሰፋራዎችን ወደ ሮም ለመመለስ ሲንቀሳቀስ መታየቱን ወኪላችን ገልጾ፣ ጠላፊውን ለማግኘት የተደረገው ሙከራ በፖሊስ ጥብቅ ቁጥጥር የተነሳ ሊሳካ አልቻለም።
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ሰራተኞች በተለያዩ ጊዜያት በአስተዳደሩ እንደሚማሩ ይታወቃል። አለማቀፍ የመገናኛ ብዙሀን በኢትዮጵያ ውስጥ የሚታየውን የሰብአዊ መብቶች ጥሰት በማንሳት ጠለፋውን ከፖለቲካ ጋር በማያያዝ ለማየት እየሞከሩ ነው።
ረዳት ፓይለቱ አላማው ጥገኝነት መጠየቅ ቢሆን ኖሮ አውሮፕላኑን ሮም ላይ ካሳረፈ በሁዋላ ጄኔቭ ገብቶ በሰላም እጁን መስጠት ይችል እንደነበር ጁኔቭ የሚገኙ አንዳንድ አስተያየት ሰጪ ይናገራሉ።  ረዳት ፓይለቱ ይህ እድል እያለው እና አውሮፕላን መጥለፍ ወንጀል መሆኑን እያወቀ እንዲህ አይነት እርምጃ ለመውሰድ የተነሳሳው አንድ ከባድ ምክንያት ቢኖረው ነው በማለት እኝሁ አስተያየት ሰጪ ገልጸዋል።
በስዊዝ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ጠበቆች ረዳት ፓይለቱን ለማግኘትና ጠበቃ ቐጥረው ለመከራከር ፍላጎት እንዳላቸው ለኢሳት ገልጸዋል።
ስቱዲዮ ከመግባታችን በፊት በአውሮፕላኑ ወስጥ ተሳፍራ የነበረች አንዲት ወጣት አግኝተናል። ወጣቱዋ እንደምትለው አውሮፐላኑ የተጠለፈው ከሮም ወደ ሚላን በሚመበርበት ጊዜ ነው። ሮም ማረፉንና መንገደኞችን ማሳፈሩን ወጣቷ ተናግራለች። አቶ ሬድዋን በበኩላቸው አውሮፐላኑ ሮም ሳያርፍ ወደ ጄኔቭ መሄዱን ተናግረዋል። ወጣቱዋ አብራሪው ረጅም ና ጠይም መሆኑንሮም ላይ ሻንጣውን ማውረዱንና ፊቱ ላይ አለመረጋጋት ይታይበት እንደነበር ገልጻለች።
ኢሳት ዜና

Friday, February 14, 2014

የትምህርት ተቌማት የእውቀት ወይስ የፖለቲካ ሜዳ!?Feb 14 at 4:22 PM
የትምህርት ተቌማት የእውቀት ወይስ የፖለቲካ ሜዳ!?

ከቅዱስ ዮሃንስ

ትምህርት  ዜጎችን  ሁለንተናዊ  በሆነ  መልኩ  በመቅረጽ  ለራሳቸው፣  ለማህበረሰባቸውና  ለሃገራቸው  ጠቃሚ  ዜጋ
እንዲሆኑ  የሚያግዝ  የእውቀት  ማሸጋገርያ  ስልት  ነው፡፡  ዛሬ  በስልጣኔ  የገሰገሱ  የአለም  ሀገራት  የዕድገታቸው
ዋነኛ  መነሻ  ትምህርት  ምርምርና  የቴክኖሎጂ  ሽግግር  ነው።  ግብርና፣  ኢንዱስትሪ፣  የአገልግሎት  ፓኬጅም  ሆነ
ሌሎች  የኢኮኖሚ  ዘርፎች  በዘመናዊ  አኳሃን  እንዲመነደጉ  ከተፈለገ  በተግባር  የታገዘ፣  ፈጠራና  ክህሎትን
የሚያዳብር ጥራት ያለው ትምህርት እጅግ ወሳኝ ነው፡፡
የትምህርት  መሰረት  በኢትዮጵያ  ውስጥ  መጣል  ከጀመረ  ከመቶ  ዓመታት  በላይ  የተቆጠረ  ሲሆን  ከሁለተኛው
አለም  ጦርነት  በፊት  ትምህርት  የሚሰጠው  በመንግስትና  በሃይማኖት  ተቋማት  ዙርያ  ለአስተዳደራዊ  ክህሎት፣
ለቀኖናና  ለሃይማኖት  እውቀት  ሲባል  እንደነበረ  ጥናቶች  ይገልጻሉ፡፡  ከሁለተኛው  ዓለም  ጦርነት  በኋላ  የአፄ
ሃይለ  ስላሴ  ስርዓት  ዘመናዊ  ትምህርትን  በተደራጀ  መልኩ  በትምህርት  ቤቶች  ውስጥ  እንዲሰጡ  ሁኔታዎችን
ያመቻቸ  ቢሆንም  የትምህርት  ቤቶች  እድገት  ከማህበረሰቡም  ሆነ  ከሃይማኖት  ተቋማት  በገጠመው  ተጽእኖ
ምክንያት  የመስፋፋቱ  እድል  አዝጋሚ  ሆኖ  ቆይቷል፡፡  በደርግ  ወቅቱም  ቢሆን  የነበረው  አጣዳፊ  ጉዳይ  አብዮቱ
በመሆኑ  በመማርና  ማስተማር  ላይ  የነበሩትን  መምህራንና  ተማሪዎች  በነቂስ  አሰልፎ  አብዮቱን  ለማስተዋወቅ
በሚል  ሰበብ  ወደ  እድገት  በሕብረት  የዕውቅትና  የስራ  ዘመቻ  አዘመተ፡፡  ከብዙ  ጥረት  በኋላ  እራሱን  በጥቂቱም
ቢሆን  ማጎልበት  የጀመረው  የትምህርት  ስርዓት  ከባድ  ፈተና  ውስጥ  ወደቀ፡፡  በማያባራ  ዘመቻ፣  ግድያ፣  አፈናና
ጦርነት  ተተብትቦ  እራሱን  ፋታ  የተነሳው  ደርግ፤  በቂ  ትምህርት  ቤቶችን  ለመገንባትና  መምህራንን  ለማብቃት
ጊዜ  አልነበረውም፡፡  በዚህም  ምክንያት  መምህር  አልነበሩም፡፡  ትምህርት  ቤቶችና  ለመማር  ማስተማር  ሂደቱ
በሚያስፈልጉ  ግብአቶችና  ቁሳቁሶች  አልተሟሉም፡፡  የትምህርት  ስርዓቱ  በአጠቃላይ  እርቃኑን  እንደቀረ  ነበር፡፡
ይህንንም ተከትሎ የኢትዮጵያ የትምህርት ስርዓተ ውድቀት አንድ ተብሎ ተጀመረ፡፡
የኢትዮጵያን  የትምህርት  ስርዓት  ተብትበውና  ቀስፈው  የያዙት  ችግሮች  ከደርግ  ጋር  ተዳብለው  ስር  እየሰደዱ
ቆይተው፣ ዛሬም በኢህአዴግ ውስጥ በመሸጋገር ማጣፊያ እንዳጠራቸው ቀጥለዋል ፡፡ የመማር ማስተማር ሂደቱ
በደርግ  ስርዓት  የለከፈው  የማጥራት  ሳይሆን  በማብዛት፣  በማዳረስ  ላይ  የመተማመን  በሽታ  ዛሬም  ወያኔን  ቀስፎ
እንደያዘው  ይገኛል፡፡  ትምህርትን  ለሁሉም  ዜጐች  በስፋት  የማድረስ  ተልዕኮን  እንደያዘ  የሚያስበው  ወያኔ፤
የትምህርቱን  የጥራት  ደረጃ  ለዚህ  ግቡ  ሲል  እየጨፈለቀው  ስለመሆኑ  ብዙ  ጥናቶች  አረጋግጠዋል።  ሀገሪቱ
ካስቀመጠችው  አነስተኛ  ማለፊያ  ነጥብ  እጅግ  ያነሰ  ውጤት  የሚያመጡ  ተማሪዎች  ከመጀመሪያ  እስከ  ሁለተኛ
ደረጃ  ባሉት  የትምህርት  እርከኖች  ቁጥራቸው  እየበዛ  መምጣቱ  ሳያንስ፤  ወደ  መሰናዶ  ትምህርት  የገቡት  በሙሉ
ለሙሉ  በሚባል  መልኩ  ወደ  ዩኒቨርስቲ  የሚገቡበት  አሳፋሪ  ሁኔታ  ተፈጥሯል።  ለየትምህርት  ክፍሎቹ
በማይመጥኑ  መምህራን  መማር፣  በአነስተኛ  ደረጃ  መሟላት  ይገባቸው  የነበሩት  የትምህርት  መሳሪያዎች  እጦት
አልፎም  የአካዳሚያዊ  ነፃነት  በፖለቲካዊው  ስርዓት  በጥልቁ  መጣስ፤  የኢትዮጵያ  ትምህርት  ተቋማት  መሰረታዊ
መለዮ  ሆኗል።  የዚህ  ፅሁፍ  ዋና  ትኩረት የትምህርት  ስርአቱን  ቀስፈው  የያዙት  ችግሮችን  አንድ  በአንድ  ነቅሶ
ማሳየትና መዳሰስ  ሳይሆን፤  ለስርአቱ  ውድቀት  በተለይም  ለጥራቱ  ዝቅጠት  ግንባር  ቀደም  መንስኤዏች ተብለው
ከሚፈረጁት መካከል ትምህርትን ለፖለቲካ ፍጆታ መጠቀም ላይ ትኩረት ያደርጋል። 
የወያኔ  መንግስት  ትምህርትና  የትምህርት  ተቋማትን  ለፖለቲካ  ፍጆታ  በመጠቀሙ  ላይ  ይገኛል፡፡  በአሁኑ  ወቅት
የመምህራን  አመራረጥ  በተለይም  ለከፍተኛ  ትምህርት  አስተማሪነት  የሚታጩ  መምህራን  የመለኪያው  ዋና
መስፈርት  የፖለቲካ  አቋም  መሆኑን  መመልከት  ይቻላል።  ወያኔ  በዘረጋው  የትምህርት  ዘርፍ  ከሁለተኛ  ደረጃ
ት/ቤት  ጀምሮ  እስከ  ከፍተኛ  ተቋማት  ድረስ  መምህራን  የሚመለመሉት  በፖለቲካ  መስፈርት  ነው።  በነዚህ
የትምህርት  ደረጃዎች  ችግሮች  በቀጥታ  ከትምህርት  ጋር  የተያያዙ  መሆናቸው  እየቀረ  ፖለቲካዊ  ይዘት
እየተጎናፀፉ  መጥተዋል፡፡  የወያኔ  የካድሬ  እንቁላል  መጣል  እና  የረጅም  ጊዜ  አሕዳዊ  አገዛዝ  ፍላጎት  የራስ
መከላከል  ሥራዎች  በይፋ  ይጀመራሉ፡፡ ባለፈው  በደርግ  ስርዓት  ውስጥም  ትምህርቱ  ከሶሻሊዝም  ርዕዩተ  ዓለም
ውጪ  አልነበረም።  አሁንም  ቢሆን  ትምህርትና  ተቋማት  በፖለቲካውና  በአብዮታዊ  ዴሞክራሲ  ርዕዮተ  -ዓለም
የተቃኙ  ናቸው።  ከዚህም  በላይ  መንግስት  ዩኒቨርስቲ  መክፈትን  እንደ  ፖለቲካዊ  አፍ  የማዘጊያ  ስልት  ተጠቅሞ
የፖለቲካ ድጋፍና ታማኝነትን እንደማግኛ መሳሪያ እየተገለገለበት ነው፡፡ ዛሬ በሃገራችን ቁጥራቸው በርከት ያሉ 
ዩኒቨርስቲዎች ተገንብተው አገልግሎት በመስጠት ላይ መገኘታቸው እሰይ የሚያስብል ቢሆንም እጅግ አሳዛኙ 
ነገር  ግን  ሁሉም  ተቋማት  በፖለቲካ  ተተብትበው  የእውቀት  አምባ  መሆናቸው  ቀርቶ  የካድሬ  መፈልፈያ
ተቋማት መሆናቸው ነው። ይህም የትምህርት ጥራቱን እንዲያሽቆለቁል አድርጐታል።
ወያኔ  በዩኒቨርስቲዎች  እና  በሁለተኛ  ደረጃ  ትምህርት  ቤቶች  ውስጥ  ያሉ  ተማሪዎች  በነጻነት  እንዲያስቡ
አይፈለግም፤  አይፈቀድምም፡፡  እንኳን  ተማሪዎቹ  ይቅርና  መምህራኑ  ጭምር  በነጻነት  የሚያስተምሩትን
ለመምረጥ  አይደፍሩም፡፡  በንድፈ-ሐሳብ  ደረጃ  ለተማሪዎቻቸው  የሚያስተላልፉትን  እውቀት  ሀገሪቷ  ላይ  ካለ
ነባራዊ ሁኔታ አንጻር ተንትኖ ለማስረዳት የሚደፍሩት ጥቂቶች ብቻ ናቸው፡፡ ክፍል ውስጥ ለሚያስተምሩትም 
ሆነ  ለሚናገሩት  ነገር  ልክ  በቤተ  ክህነት  ውስጥ  የአምላክን  ቃል  እንደሚሰብክ  ሰባኪ  ጥንቃቄን  ማድረግ  ግድ
ይላቸዋል።  ይህ  ሁሉ የሚሆነው  የተዘረጋውን  አስጨናቂ  የአምባገነን  ስርአት  ከመፍራት፤  የተናገሩት  ነገር ገዥው
ፓርቲን  የሚነቅፍ  (የማይደግፍ)  ከሆነ  ያለአግባብ  ስም  ተለጥፎባቸው  የእንጅራ  ገመዳቸውን  ስለሚበጠስ  ነው።
በለፈለፉ  ባፍ  ይጠፉ  ይባል  የለ።  ከክፍል  ውጪም  በተቋማቱ  አመራሮች  ለሚፈፀሙ  የአሰራር  ስህተቶች  እና
በደሎች  ለመተቸት  እምብዛም  ፈቃደኛ  አይደሉም፡፡  ምክንያቱም  አመራር  ተብለው  የሚሾሙት  የትምህርት
ተቌማት  ባስልጣናት  የተሻለ  እውቀትና  ልምድ  ያላቸው  ሰዎች  ሳይሆኑ  የመንግስት  ቀኝ  እጅ  በመሆን
የሚያገለግሉት  የወያኔ  ግልገል  ካድሬ  ናቸው።  እነዚህ  አካላት  በሚያስተዳድሩት  መምህራን  ላይ  ኢፍትሃዊ
እርምጃ ቢወስዱም ማንም ሃይ ባይ የላቸውም።
ተማሪዎች  በአብዛኛው  ለትምህርታቸው  የሚሰጡት  ትኩረት  እና  ውጤታቸው  ምንም  አያስጨንቃቸው፤
ደንታቸውም  አደለምም  ለማለት  ያስደፍራል።  ከዚህ  ይልቅ  የወጣቶች  ሊግ  እና  ማንኛውንም  የመሪው  ፓርቲ
ተደራሽነት  የሚያሳድጉ/የሚያጠናክሩ  ሥራዎች  ላይ  ንቁ  ተሳታፊ  በመሆን  ታትረው  ይሰራሉ።  ይህም
በጓደኞቻቸው  ላይ  የበላይነትን  እንዲያገኙ  ከማድረጉም  በላይ  ተሰሚነትን  በትምህርት  ቤት  ኃላፊዎች
ያስገኝላቸዋል፤  ከበድ  ሲልም  የንግድ  እና  የፖለቲካ  ሥራ  እንዲያገኙ  ይመቻችላቸዋል፡፡  ይህ  በትምህርት  ዘርፍ
ላይ  የተዘረጋው  ስርዓት  ለተማሪዎች  የሚያስተላልፈው  መልእክት  ግልፅ  ነው፡፡  በትምህርት  ተግቶ  እውቀት
ሸምቶ  ሀገሪቷን  ለመጥቀም  ከመታተር  ይልቅ  ርካሽ  የፖለቲካ  ተወዳጅነት  ማግኘት  የስኬት  መንገድ  አቋራጭ
መሆኑን  ነው፡፡  ለትምህርት  ትኩረት  መስጠት  ያለውን  ጥቅም  ተረድተው  ይሻለኛል  ብለው  የሕይወት
መስመራቸውን የሚያስተካክሉት ተማሪዎች ቁጥር እጅግ በሚያሳዝን ሁኔታ አሽቆልቁሏል።   
በአሁኑ  ወቅት  ወያኔ  በመላ  ሀገሪቱ  ውስጥ  ከሚገኙ  የከፍተኛ  ትምህርት  ተቋማት  ከሚማሩት  ውስጥ  85% 
የሚሆኑ  አባላት  እንዳሉት  እና  በእያንዳንዱ  የትምህርት  ክፍሎች  ውስጥ  ህዋስ  እንደዘረጋ  ይገልፃል፡፡  እንግዲህ
ይህ  ፐርሰንት  በመመልከት  አብዛኞቹ  የከፍተኛ  ትምህርት  ተቋማት  ተማሪዎች  የስርዓቱ  አካል  እና  አስፈጻሚ
እንደሆኑ  መናገር  ይቻላል፡፡  እጅግ  አሳዛኙ  እውነታው  ግን  እነዚህ  ሁሉ  አባላት  ወደ  ድርጅቱ  የተቀላቀሉት
በፍላጐት  ሳይሆን  በግዳጅ  ብሎም  በሃገሪቱ  የተዘረጋው  አላፈናፍን  ያለው  አስጨናቂው  ስርአት
የሚያስከትልባቸውን  የከፋ  መዘዝ  ለመሸሽ  ከመፈለግ  መሆኑ  ነው።  ከዚህ  ጋር  ተያይዞ  በዩንቨርስቲዎች  ውስጥ
እየታየ  ያለው  አዲስ  ገፅታ፤  የተማሪዎች  ጊዜያቸውን  በህዋስ  ውይይት  እና  ግምገማ  ማዋላቸው፣  ከአባላት  ሁሉ
ልቆ  ለመታየት  የሚደረግ  ጥረት፣  ከትምህርት  ውጤታቸው  ይልቅ፤  በአባልነታቸው  ወደሚሰጣቸውን  ነጥብ
መጨነቅና  አብዝቶ  ማተኮር፣  ሲብስም  የትምህርት  ጊዜያቸውን  መሉ  በሙሉ  ለማለት  በሚያስደፍር  መልኩ
ለፓርቲ  ተግባራት  በማዋል  የመጡበትን  ዋነኛ  የትምህርት  አላማ  በመሸሽ፤  ብቁ  የካድሬ  ምሩቃን  ሆነው
ለመውጣት  ወ.ዘ.ተ  መሽቀዳደም  የተማሪዎች  መገለጫዎች  ናቸው፡፡  ይህም  የተሻለ  ስራ  እንዲያገኙ  ያግዛቸዋል፤
በተቃራኒው ይህንን የሚሸሹ ምሩቃን ለስራ ማጣት እና ለከፋ ችግር እየተጋለጡ ይገኛሉ።
በመጨረሻም  መንግስት  ትምህርትና  ተቋማቱን  የፖለቲካ  ሜዳ ከማድረግ መታቀብ አለበት፤  ከካድሬዎችም  ነፃ
ማድረግና  የእውቀት  አምባ  ብቻ  ሆነው  መቀጠል  ይኖርባቸዋል።  በዘርፉ  ያለው  የፖለቲካ  ጣልቃ  ገብነት
መስተካከል  እንደሚገባው፣  ተማሪዎችና  መምህራኖች  አካዳሚክ  ነፃነት  ማግኘት  እንዳለባቸው፣  ተቋማቱ
ዕውቀት  የሚገበይባቸው  እንጂ  የፖለቲካ  ማራመጃ  ሜዳ  መሆን  እንደሌለባቸው፣  የትምህርት  ሥራ  ሙያ  እንጂ
ፖለቲካ  አለመሆኑ፣  እንዲሁም  በመልካም  ተምሳሌትነት  ሊጠቀሱ  የሚገቡ  የልሂቃን  /Elite/  ት/ቤቶችና
ዩኒቨርስቲዎች  ሊፈጠሩ  ይገባል።  ትምህርት  በዋናነት  መፍትሄ  ሰጪ  ዕውቀት  ካላስጨበጠና  ችግር  ፈቺ  መሳሪያ
ካልሆነ ለብዙሃኑ እንደሚታደል መሰረታዊ ሸቀጥ ካየነው አደጋው የከፋ የሀገር እድገት እንቅፋት ከመሆን የዘለለ
ሚና  እንደማይጫወት  ይታወቃል፡፡  ስለዚህ  የትምህርት  ስርአታችን  ከተደቀነበት  ከፖለቲካ  ተፅዕኖ  ማላቀቅ  ግድ
ነው።  ይህ  ብቻ  ሲሆን  አምራችና  በእውቀት  የዳበረ  ዜጋ  ማፍራት  ይቻላል።  ትምህርት  ቤቶች  (ከፍተኛ
የትምህርት  ተቋማትን  ጨምሮ)  በግልፅም  ሆነ  በስውር  የአንድ  የፖለቲካ  ፓርቲ  ወይም  ገዥ  አካል  ፖለቲካዊ
አጀንዳ ማስፈፀሚያ መሆን የለባቸውም፡፡ ይህ ከሆነ ግን አሁን በሃገራችን እየተስተዋለ እንዳለው ውድቀቱ የከፋ
ነው።
ኢትዮጵያችን በክብር ለዘላለም ትኑር!!!
ለአስተያየትዎ: kiduszethiopia@gmail.com ይጠቀሙ። 

Wednesday, February 12, 2014

ሰው ለሆኑ ሰዎች በሙሉ! (በጋዜጠኛ ውብሸት ታዬ፤ ከዝዋይ ማረሚያ ቤት)

February 11, 2014

የነገሮች ሁሉ መድረሻ እስር ቤቶች እየሆኑ መጥተዋል፡፡

‹‹ይህንን ስለመሳሰሉ ጉዳዮች መወያየት ክልክል ነው፡፡›› በማለት በተንጎላጀጀ ድምፅ ጠባቂው ተናገረ፡፡ ቀጠል አደረገናም ‹‹መነጋገር የምትችሉት ስለቤተሰብ ጉዳዮች ብቻ ነው›› በማለት ተናገረ፡፡ ይህን ከላይ ያለውን ሐሳብ የሚመለከት ማንኛውም አንባቢ፣ ጉዳይ የተፈፀመው እዚህችው እማማ ኢትዮጵያ ሰማይ ስር ባሉ አጃኢበኛ እስር ቤቶች፣ ቤተሰብ መጠየቂያው እንደሆነ መጣራቱ አይቀርም፡፡Ethiopian journalist Woubshet Tayemes journalist
ይሁንና በመግቢያው ላይ ያለው ጽሑፍ ተቀንጭቦ የተወሰደ ‹እናት› ከተሰኘውና እ.ኤ.አ. በ1906 ከታተመው የስመ ጥሩው ሩስያዊ ደራሲ ማክሲም ጎርኪይ ታሪካዊ ልቦለድ ገፅ 102 ላይ ነው፡፡ የዛሬ 108 ዓመት አካባቢ ማለት ነው፡፡ አቤት ርቀቱ!… ይህ ርቀት ግን ለእኛ ምንም ማለት ያልሆነ ይመስላል፤ ለምን? ቢሉ ዛሬም ይህንንና ይህን የመሳሰለውን አስፍተን እየሠራን እንገኛለን፡፡ እንዲያውም በአንዳንድ ሁኔታዎች እየተጓዝን ያለነው የቁልቁለት ሩጫ በእጅጉ አሳሳቢ ሆኖ ይገኛል፡፡
የነገሮች ሁሉ መድረሻ እስር ቤቶች እየሆኑ መጥተዋል፡፡
‹ጠበቅ ያለ እርምጃ፣ የማያዳግም እርምጃ፣ የማስወገድ እርምጃ፣…› ወዘተ የሞሉ ከሕግ መርሕዎች ሳይሆን ከጥላቻ ፖለቲካ የሚመነጩ ፀያፍ አነጋገሮችን በሕዝብ የመገናኛ ዘዴዎች ሲተላለፉ እየሰማን እየታዘብን ነው፡፡ ቃል በቃል ‹ቀይ ሽብር ይፋፋም› ብሎ ማወጅ የቀራቸው የሕግም የግብረገብም ሚዛን ያልወጣላቸው ቀረርቶች በተለይ በእስር ቤት የምንገኝ ኢትዮጵያውያንን እየሰበሰቡን ይገኛሉ፡፡
ዝዋይ የአገራችን ‹ሳይቤሪያ ግዞት›
በኢ.ቴ.ቪ. የአብዮታዊ እርምጃ ፕሮግራሞች በቀረቡ ማግስት አሁን በዝርዝር ብለው የብዙ ቤተሰቦችን ስሜት ሊያሸማቅቁ የሚችሉ ሰቆቃና እንግልቶች በአስደማሚ ስልት ተቀናብረው ተፈፃሚ ይሆናሉ፡፡ እስኪ የተወሰኑትን እንይ፡፡ ማንኛውም ታሳሪ ቤተሰብ በቅርብ ሊጎበኘው በሚችለው እስር ቤት ይታሰር የሚለው ሕግ የተሻረው በእኛ ላይ ነው፡፡ ዝዋይ የአገራችን ‹ሳይቤሪያ ግዞት› ማለት ናት፡፡ ቤተሰብ ያን ያህል የበርሃ ጉዞ አቋርጦ የእኛዋ ሳይቤሪያ ሲደርስ በአድካሚና ግብረ-ገብ በጎደለው ፍተሻ መከራውን ማየቱ አንሶ ጆሮ ግንዱ ላይ በቆሙ የቤተሰብ አገናኞች ቤተሰባዊ ገመናውን አሳልፎ ይሰጣል፡፡ ሕፃናት ልጆች ወላጆቻቸው አንድ ላይ ሆነው ናፍቆታቸውን መወጣት አይችሉም፡፡ አንዳንድ ጊዜ ፖሊሶቹ ሲዘናጉልን ልጆቻችንን አቅፈን እንስማለን፡፡ ይህ ከሆነ ቁጣና ዘለፋው ምንም አይደለም፡፡ ግን በሁኔታው ሕፃናቱ ክፉኛ ይበረግጋሉ፣ የእኛ ስጋት ይጋባባቸዋል፤ በዚህም መንፈሳቸው እርብሽብሽ ብሎ ወደቤታቸው ይመለሳሉ፡፡
ሁኔታው በዚህ አያበቃም፡፡ ምንም እንኳን የመጠየቂያ ሰዓቱ በግልፅ የተቀመጠ ቢሆን ከቤተሰቦቻችን ጋር ገና መነጋገር ስንጀምር ‹‹በቃ… ቶሎ ጨርሱ›› የሚባልባቸው ጊዜዎች ብዙ ናቸው፡፡ ቀጥሎ የሚመጣው የእስር ቤት ማኅበራዊ ጉዳዮችን ማለትም ለሳሙና፣ ለምግብ ማጣፈጫ፣ ለሻይ ለቡና፣ ለውስጥ አልባሳት፣ ለውኃ ማከሚያ/ውኃ አጋር/ ወዘተ፤ ገንዘብ የሚያስፈልገን ቢሆንም እና እንደሚያስፈልጉ ቢታወቅም ጉዳዩ ለይቶለት የማሰቃየት፣ ማንገላታት፣ መበቀል ሆኗልና ለአንድ ወር ከአንድ መቶ ብር በላይ መጠቀም እንዳንችል የተከለከልን የመሆኑ አሳፋሪ ሐቅ ነው፡፡ ይህ እየተፈፀመ ያለው ደግሞ ዝዋይ እስር ቤት ውስጥ ብቻ ነው፡፡ በዚህ የተነሳም ለመግለጽ በሚከብድ ሁኔታ ሰብኣዊ ክብራችንን የማዋረድ ሙከራዎች እየተፈፀሙ ነው፡፡
በአገራችን ላይ እኔ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርቴን የጨረስኩት ዝዋይ በመሆኑ ብዙ ወዳጅ ዘመዶቼ በእዚህ ይገኛሉ፡፡ ሆኖም ለአካባቢው ነዋሪዎች በሳምንት እንዲጠይቁን የተፈቀደላቸው አንድ ቀን /ረቡዕ/ ብቻ ሲሆን ‹‹የት ነው የምታውቁት? እንዴት አወቃችሁት? ምንድን ነው የሚያመላልሳችሁ?›› በሚሉትና በሌሎችም ጥያቄዎች ተደናግጠው መምጣቱን እርግፍ አድርገው ትተውታል፡፡
ሀገሩ ሞቃታማ ነውና በዚያ ላይ በእያንዳንዱ ቤት እስከ 150 ሰው ይታሰርበታል፡፡ ይህ ሁሉ ተደማምሮ እስረኛው የቱንም ያህል ፅዳቱን ለመጠበቅ ቢሞክርም የተባዩ መርመስመስ የእነ ትኋን እንዲህ መራባት፤ ለማሰብ እንኳን ይዘገንናል፡፡ ሌሊቱን ሙሉ ገላን ሲቆፍሩ ማደር ነው፡፡ ሊናገሩት ይከብዳል፣ አንባቢንም ቅር ያሰኛል፤ ግን ይህ የፊልም ትረካ ሳይሆን በእማማ ኢትዮጵያ ልጆች ላይ ሆን ተብሎ እየተፈፀመ ያለ ደባ ነው፡፡ […] ግን የባሰ አታምጣ ማለት ነው!
የዝዋይን ልጅ ውሃ ጠማው
ግን የባሰ ነገር አለ፡፡ አፈር ቅጠል የማይል ምግብ ይቀርብናል፡፡ ‹በደንባራ በቅሎ ቃጭል ተጨምሮ› ከፍተኛ የውኃ እጥረት /ዝዋይ ሀይቅ አናት ላይ ተቀምጠን/ አለ፡፡ የእስር እስር እንዲሉ ጄኔራል መኮንኖቹን ጨምሮ አብዛኛዎቹ አባሪዎቻቸውና ሌሎች ሌሎች የተወሰንን እስረኞች የምንገኘው በልዩ ቅጣት ጭለማ ቤት ውስጥ ነው፡፡ ይህንን ሁሉ እንደምንም ለመቋቋም ጥረት ማድረግ ይቻል ይሆናል፡፡ አዲሱ ስልት ግን መዘዙ በጣም አደገኛ በመሆኑ እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ፣ እያንዳንዱ ሃይማኖት ያለው፣ ፈርሐ እግዚአብሔር ያለው፣ እያንዳንዱ የመሠረታዊ ሰብኣዊ መብቶችና ነጻነቶች መከበር የሚያሳስበው እያንዳንዱ ሰው የሆነ ሰው ሁሉ ሊያውቀው ይገባል ስንል ድምፃችንን እናሰማለን፤ በሕክምና ንፍገት ወደሞት እየተገፋን ነው፡፡
ሕመም ካልታከመ መጨረሻው ሞት ነው፡፡ የሞቱም ሰዎች አሉ!
ከወር በፊት ገደማ ወጣቱ የአንድነት ፓርቲ አባል ናትናኤል መኮንን ለሕክምና በሪፈር ወደ ቃሊቲ ተልኮ የነበረ ቢሆንም፣ የዛኑ ዕለት ሕክምናውን ተነፍጎ ከሌሊቱ 5፡00 ሰዓት አካባቢ እንዲመለስ ተደርጓል፡፡ እስካሁን በሕመሙ እየተሰቃየ ይገኛል፡፡ የኢብአፓ ሊቀመንበር የነበረው ዘሪሁን ገ/እግዚአብሔር እንደዚሁ ለተጨማሪ ሕክምና ሪፈር ተብሎ ሲጠባበቅ ከቆየ በኋላ ዘዴው ተፈፃሚ ሆነበት እጁን አጣጥፎ ተቀምጧል፡፡ ከሕመሙ ጋር በተያያዘ በአካሉ ላይ አሳሳቢ ሁኔታ እየታየበት ይገኛል፡፡ ከዚህ ቀደም ገልጬው የነበረው የእኔ የኩላሊት ሕመም አሁን ለመቀመጥም፣ ለመንቀሳቀስ እያወከኝ የሚገኝ ሲሆን፣ እኔን ከቃሊቲ ዝዋይ ለማምጣት የተደረገው የተቀናጀ መረብ ሩብ ያህሉን ለሰብኣዊነት አውለውት ቢሆን ኖሮ እኔም ፋታ፣ እነሱም እርካታ ባገኙ ነበር፡፡ ሕመም ካልታከመ መጨረሻው ሞት ነው፡፡ የሞቱም ሰዎች አሉ!
የጄኔራል መኮንኖቹ አባሪዎች የነበሩት ኮረኔል ተስፋዬ ኃይሉ እና ኢንጂነር ክፍሌ ስንሻው፣ በዶክተር መረራ በሚመራው ኦሕኮ ፓርቲ አባል የነበሩት አሕመድ ነጃሺ፣ በጭለማ ቤት የከረመው ተስፋሀን ጨመዳ፣ የቤንሻንጉሉ አዛውንት ወዘተ ተገቢውን ሕክምና በማጣት ሕይወታቸውን ያጡ የእማማ ኢትዮጵያ ልጆች ናቸው፡፡ እንዴት ሕክምና ይከለከላል!? ግፍና ጭቆና ተቃውመው ደማቸውን ያፈሰሱና አጥንታቸውን የከሰከሱ ታጋዮችን በሥልጣን ማግስት ከፍርድ በመለስ በየእስር ቤቱ ያሉ ኢትዮጵያዊ ወገኖቻቸው በሕክምና እጦት ሲረግፉ በእርካታ ማርመምን ከየት ተማሩት!? የኢትዮጵያ ሕዝብስ ምን ይላል!? ሰው የሆኑ ሰዎች ሁሉ ከቶ ምን ይላሉ!?
እግዚአብሔር ኢትዮጵያን ይባርክ!
ምንጭ ኢትዮ-ምኅዳር ጋዜጣ

ትግራዊ ማንነት ካለ ኢትዮጵያዊ ማንነትም አለ! (አብርሃ ደስታ)

February 12, 2014
“ኢትዮጵያዊ ነኝ፤ ኢትዮጵያዊ ማንነት አለኝ” ብዬ ስል የራሴ (የግሌ) ማንነት የለኝም ማለት አይደለም። የአከባቢ ማንነት የለኝም ማለት አይደለም። የክልል (የብሄር) ማንነት የለኝም ማለት አይደለም። ወይም እነዚህ የተለያየ ደረጃ ያላቸው ማንነቶቼ መጥፋት አለባቸው ማለት አይደለም። እኔ ኢትዮጵያዊ ነኝ ስል የራሴን ማንነት አልቀበልም ማለት አይደለም። የራሴ ማንነት ስላለኝ ነው ኢትዮጵያዊ ማንነት ሊኖረኝ የቻለው። እኔ የግል ማንነት ባይኖረኝ ኑሮ ኢትዮጵያዊ አልሆንም ነበር። ምክንያቱም የግል ማንነት ከሌለኝ የሀገር ማንነት ሊኖረኝ አይችልም። እያንዳንዱ ሰው የግሉ የሆነ ማንነት አለው። የግሉ ማንነት ስላለው ነው ኢትዮጵያዊ ማንነት ያለው። ኢትዮጵያዊ ማንነት ራሱ የቻለ የሁላችን የጋራ ማንነት ነው።
Abraha Desta the facebook
አብረሃ ደስታ
የትግራይ ማንነት ካለን የኢትዮጵያ ማንነት ለምን አይኖረንም? “ትግራዮች አንድ ነን” ካልን “ኢትዮጵያውያን አንድ ነን” ብንል ችግሩ ምንድነው? ኢትዮጵያዊነትኮ ከብሄር (ከክልል) ሰፋ ያለ ሀገራዊ ማንነት ነው። ሀገራዊ ማንነታችንን ብንቀበል ችግሩ ምንድነው?
ኢትዮጵያውያን አንድ አይደለንም አትበሉኝ። ምክንያቱም ኢትዮጵያውያን አንድ ካልሆንን ትግራዮችም አንድ አይደለንም፤ አማራዎችም አንድ አይደለንም፣ ኦሮሞዎችም አንድ አይደለንም። አንድ የሆነ አይኖርም።
“ኢትዮጵያውያን አንድ አይደለንም ምክንያቱም የተለያየ ታሪክና ባህል አለን” አትበሉኝ። ምክንያቱም እያንዳንዱ ግለሰብ፣ አውራጃ፣ ክልል (ብሄር) ወዘተ…ም የተለያየ ታሪክና ባህል ሊኖረው ይችላል። ኢትዮጵያውያን የተለያየ ባህልና ታሪክ ስላለን አንድ አይደለንም ካላችሁኝ ኦሮሞዎችም አንድ አይደሉም እላቸዋለሁ፤ ምክንያቱም የወለጋ ኦሮሞዎች፣ የሸዋ ኦሮሞዎችና የአርሲ ኦሮሞዎች የተለያየ ታሪክና ባህል አላቸው።
ኢትዮጵያውያን የተለያየ ባህልና ታሪክ ስላለን አንድ አይደለንም ካላችሁኝ አማራዎችም አንድ አይደሉም እላቸዋለሁ፤ ምክንያቱም ወለየዎች፣ ጎጃሞችና ጎንደሬዎችም የተለያየ ታሪክና ባህል አላቸው።
ኢትዮጵያውያን የተለያየ ባህልና ታሪክ ስላለን አንድ አይደለንም ካላችሁኝ ትግራዮችም አንድ አይደሉም እላቸዋለሁኝ፤ ምክንያቱም ተምቤኖች፣ ዓድዋዎች፣ ዓጋሜዎች፣ ራያዎች፣ ወልቃይቶች የተለያየ ታሪክና ባህል አላቸው።
“የተለያየነው በቋንቋ ነው” ካላችሁኝ። የተለያየ ቋንቋ የማንነት መለያ መስፈርት ከሆነና እኛ ኢትዮጵያውያን የተለያየ ቋንቋ ስለምንናገር የተለያየን ከሆንን ትግራዮችም አንድ አይደለንም። ምክንያቱም የትግራይ ህዝብ አንድ ቋንቋ ብቻ የሚናገር ህዝብ አይደለም፤ አንድ ዓይነት ባህል ያለው ህዝብ አይደለም። ምሳሌ ኢሮብ (ቋንቋ ሳሆ) የራሳቸው ቋንቋና ማንነት አላቸው። ግን በትግራይ ክልል ዉስጥ ናቸው። በትግራይ ኩናማዎች አሉ (ወልቃይቶች ጨምሮ)። የራሳቸው ባህል አላቸው። ራያዎች የራሳቸው የሚኮሩበት ባህል አላቸው። ስለዚህ በትግራይ ክልል የተለያዩ ባህሎችና ቋንቋዎች አሉ። ግን ትግራዮች (ተጋሩ) አንድ ነን። ተጋሩ አንድ ነን ስንል አንድ ቋንቋ፣ አንድ ባህል ብቻ አለን ማለታችን አይደለም፤ ተጋሩ አንድ ነን ስልን ሌላ ቋንቋ፣ ማንነት፣ ባህል ወዘተ ያላቸው ህዝቦች እውቅና አንሰጥም ማለት አይደለም። ማንነታቸው እንዲቀይሩ እናስገድዳቸዋለን ማለትም አይደለም። ተጋሩ አንድ ነን ስንል የግላችን ማንነት ጠብቀን የጋራ በሆነ የትግራይ ማንነት በአንድነትና በእኩልነት እንኖራለን ማለት ብቻ ነው።
ተጋሩ አንድ ነን። ኢትዮጵያውያንም አንድ ነን። የተለያየ ቋንቋ መናገራችን የተለያየን ስለመሆናችን ማረጋገጫ ሊሆን አይችልም። ስለ ኢትዮጵያዊ ማንነት ስናወራ ስለ ሌሎች ማንነቶች እውቅና እየሰጠን ነው። ምክንያቱም የያንዳንዳችን ማንነት ከሌለ የጋራ ማንነታችን አይኖርም። የያንዳንዱ ግለሰብ ማንነት ካከበርን የሁሉም ኢትዮጵያዊ ማንነት እናከብራለን። ምክንያቱም ኢትዮጵያዊ ማንነት ማለትኮ የኛ ማንነት ማለት ነው። “እኛ” ማን ነን? እኛ ሁላችን ነን።
ኢትዮጵያዊ ማንነት ከሌለ የክልል (ብሄር) ማንነትም አይኖርም። ኢትዮጵያዊ ማንነት አለ፤ ምክንያቱም የያንዳንዳችን ኢትዮጵያውያን የየግላችን ማንነት አለን።
ኢትዮጵያዊ ማንነትን ስናስቀድም ሁሉም ኢትዮጵያውያንን እናስቀድማለን። የዓድዋ ወይ የራያ ወይ የኢሮብ ማንነት ብናስቀድም እያስቀደምነው ያለነው ህዝብ የአንድ ወረዳ ወይ አከባቢ ብቻ ነው የሚሆነው። የትግራይ ማንነት ብናስቀድምም የምናስቀድመው የትግራይ ህዝብ ብቻ ነው የሚሆነው። ትንሽ ጠበብ ያለ ነው። ሌሎችስ ለምን እንተዋቸዋለን? ሌሎች (አማራዎች፣ ኦሮሞዎች፣ ሶማሌዎች፣ ደቡቦች፣ ዓፋሮች፣ ጋምቤላዎች፣ ቤኑሻንጉሎች፣ ጋምቤላዎች፣ ሃረሪዎች ወዘተ) ለምን በእኩል ዓይን አናስቀድማቸውም?
የትግራይን ማንነት የሚያስቀድም ሁሉ የኢትዮጵያ ማንነትም ማስቀደም አለበት። ምክንያቱም የትግራይን ማንነት ስታስቀድም የሌሎች ወገኖች ማንነት ትተወዋለህ። የኢትዮጵያ ማንነት ስታስቀድም ግን የሁሉም የኢትዮጵያ ህዝቦች (የትግራይ ጨምሮ) ማንነት ነው የምታስቀድመው።
በኢትዮጵያዊ ማንነት የማምነው ሁሉንም ኢትዮጵያውያን ማስቀደምና ማክበር ስላለብኝ ነው። በኢትዮጵያ ዉስጥ እየኖረ የራሱን ብሄር የሚያስቀድም ሰው በሁሉም ብሄሮች (ኢትዮጵያውያን) እኩልነት አያምንም ማለት ነው። በብሄሮች እኩልነት የማያምን ደግሞ የኢትዮጵያን አንድነት ማስጠበቅ አይችልም። ምክንያቱም እኩልነት ከሌለ አንድነት የለም። አንድነት ከሌለ ሀገር የለም። ሀገር ከሌለ ሉአላዊነት የለም። ሉአላዊነት ከሌለ የህዝብ ደህንነት አይጠበቅም። ስለዚህ ኢትዮጵያዊ ማንነት የማያስቀድም ለህዝብ አይበጅም።
አንድ የወረደ ሐሳብ ላንሳ።
የቡድን (የብሄር) መብትን የሚያስቀድመው የኢህአዴግ መንግስት የኢትዮጵያ ብሄር፣ ብሄረሰቦችና ህዝቦች እኩልነት እንዳረጋገጠ ይተርክልናል። ግን በትክክል የኢህአዴግ መንግስት ሁሉንም ብሄሮች በእኩል ዓይን ያያል? ትንሽ እንውረድና …!
በፓርላመንታዊ ስርዓት (ኢህአዴግ የሚከተለው ዓይነት) የሀገር ከፍተኛው የፖለቲካ ስልጣን ጠቅላይ ሚኒስተርነት ነው። ሁሉም ብሄር፣ ብሄረሰቦች እኩል ናቸው ካልን ለዚህ ከፍተኛ የሀገር ፖለቲካዊ ስልጣን እኩል ዕድል አግኝተው መወዳድር አለባቸው።
ታድያ በኢህአዴግ ዘመነ ስልጣን አንድ የዓፋር ወይ የሶማሌ ወይ የቤኑሻንጉል ጉሙዝ ወይ የሃረሪ ወዘተ ተወላጅ የጠቅላይ ሚኒስተርነቱን ስልጣን ለመያዝ ከሌሎች ኢትዮጵያውያን ጋር በእኩልነት የመወዳደር ዕድል አለው? በኢህአዴግ ዘመን ዓፋር ወይ ሶማል ወይ ጋምቤላ ጠቅላይ ሚኒስተር ሊኖረን ይችላል? አይችልም። ለምን?
የሀገር ጠቅላይ ሚኒስተር ሁኖ መመረጥ የሚችለው የገዢው ፓርቲ አባል የሆነ ብቻ ነው። አባል መሆን ብቻ በቂ አይደለም። የፓርቲው ሊቀመንበር መሆን አለበት። የፓርቲ ሊቀመንበር የሚመረጠው ከፓርቲው አባል ፓርቲዎች ነው። የኢህአዴግ አባል ፓርቲዎች የደቡብ፣ ትግራይ፣ አማራና ኦሮምያ ብሄር ተወላጆች ብቻ ናቸው። ድርጅቶቹ ብሄር መሰረት ያደረጉ ናቸው። ስለዚህ በኢህአዴግኛ አሰራር አንድ የዓፋር ወይ የሶማል ወይ የቤኑሻንጉል ወይ የጋምቤላ ተወላጅ ጠቅላይ ሚኒስተር የመሆን ዕድል ወይ መብት የለውም። ይሄ ነው እኩልነት!?
በግለሰባዊ ኢትዮጵያዊ አስተሳሰብ ግን ሁሉም ኢትዮጵያዊ ለማንኛውም ስልጣን ወይ ሐላፊነት እኩል የመወዳደር ዕድል ይኖረዋል። አንድ ኢትዮጵያዊ የሚመዘነው እንደ ሰው (እንደ ዜጋ) እንጂ በመጣበት ብሄር ወይ አከባቢ ወይ በሚናገረው ቋንቋ መሰረት አይደለም። ስልጣን ለመያዝ ወይ ስራ ለማግኘት ኢትዮጵያዊ ዜጋ መሆኑ ብቻ በቂ ነው። ከሌላው ጋር በትምህርት ደረጃው፣ በብቃቱ ወዘተ ይወዳደራል። ምክንያቱም ሁላችን እኩል ነን። ለሁሉም ነገር እኩል ዕድል ይኖረናል።
ስለዚህ ኢትዮጵያዊ ማንነት ማስቀደም የምንፈልገው ሁሉም ዜጋ በእኩል ዓይን ማየት ስለምንፈልግና ጠንካራ ሀገር መመስረት ስላለብን ነው።
ትግራዊ ማንነት ካለ ኢትዮጵያዊ ማንነትም አለ!
ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር።

Tuesday, February 11, 2014

በአዲስ አበባ በሌሊት የሚጻፉ የተቃውሞ ጽሁፎች ቁጥር እየጨመረ ነው

የካቲት ፫ (ሦስት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ከታህሳስ ወር 2006 ዓም ጀምሮ በመዲናዋ  ሌሊት የሚጻፉ  የተቃውሞ ጽሁፎችን ማየት የተለመደ እየሆነ መምጣቱን ነዋሪዎች ይናገራሉ።
ትናንት ሌሊት በአስኮ መስመር ጀኔራል ዊንጌት ከሚገኘው አደባባይ ጀምሮ አወሊያ፣ካኦጄጄ፣ አስኮ የሚወስደውን ዋና መንገዱን በመሃል በሚከፍለው እስከ 2.5 ሜትር ቁመት ባለው ግድግዳ ላይ የሙስሊሙን የመብት ጥያቄና የትግል ቀጣይነት የሚያንፀባርቁ ጽሁፎች በተለያዩ ቀለማት ተጽፈው ዛሬ ህዝብ ሲያነባቸው ታይቷል።
በአዲስ አበባ ጦር ሀይሎች፣ ወይራ ሠፈር ፣ አዉጉሥታ፣ቤቴል እና ሌሎችም አከባቢዎች ተመሳሳይ መልእክቶችን ያዘሉ ጽሁፎች ተለጥፈው ማደራቸውን ለማወቅ ተችሎአል፡፡
የመንግስት የጸጥታ ሃይሎች ጽሁፎችን በተመሳሳይ ቀለም ለማጥፋት ሙከራ እንደሚያደርጉ አልሆን ሲልም ስሚንቶ በመለጠፍ ለማጥፋት እንደሚሞክሩ ነዋሪዎች ይገልጻሉ።

መንግስት በአገሪቱ እየታየ ላለው ረሀብ በቂ ዝግጅት እያደረገ አለመሆኑን መረጃዎች አመለከቱ

የካቲት ፬ (አራት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ከፍተኛ የግብርና ምርት  እንደተገኘ በመንግስት የመገናኛ ብዙሀን በሚገለጽበት በአሁኑ ወቅት ከ3 ሚሊዮን በላይ ዜጎች አስቸኳይ የምግብ እርዳታ ካላገኙ ህይወታቸው አደጋ ላይ እንደሚወድቅ መረጃዎች አመልከተዋል። የዓለም ባንክ መረጃዎች እንደሚጠቁሙት በመግብ ለስራ የታቀፉ ዜጎችን ሳይጨምር ከ3 ሚሎዮን ያላነሱ ኢትዮጵያውያን አስቸኳይ የምግብ እርዳታ ያስፈልጋቸዋል። በምስራቅ አማራ፣ በደቡብ ምስራቅ ትግራይ፣ በአፋር እና ኦሮምያ የተከሰተውን ረሀብ ለማስታገስ ከ400 ሚሊዮን ሜትሪክ ቶን በላይ እርዳታ ያስፈልጋል።
የአለማቀፉ ማህበረሰብ ድጋፍ አነስተኛ በሆነበት ሁኔታ በዚህ አመት ከፍተኛ የሆነ የሰብአዊ ጉዳት ሊደርስ እንደሚችል ነው ባለሙያዎች ያስጠነቀቁት። የኢትዮጵያ መንግስት ለፖለቲካ ፍጆታ በሚል በአገሪቱ የተለያዩ አካባቢዎች የተከሰተውን ረሀብ በመደበቅ ላይ ነው ያሉት ወገኖች፣ በረሀብ የተጎዱት ዜጎች ትክክለኛ አሀዝ ከተጠቀሰው ቁጥር በእጅጉ እንደሚልቅ እየተናገሩነው።
ኤን ቢ ሲ በቅርቡ ባወጣው ዘገባ በብዙ ሚሊዮን የሚቆጠሩ ኢትዮጵያን የሞት ደመና እንዳንዣበበባቸው ገልጿል። ከ20 አመት በፊት አቶ መለስ ዜናዊ የኢትዮጵያ ህዝብ በቀን ሶስት ጊዜ ሲበላ ማየት እንደሚፈልጉ ፣ ከ3 አመት በፊት ደግሞ ኢትዮጵያን በአምስት አመታት ውስጥ በምግብ ራሱን ለማስቻል እቅድ መታቀዱ ተገልጾ ነበር። አሁን ያሉት መረጃዎች እንደሚያመለክትቱት ከ23  አመታት የውጭ እርዳታ በሁዋላ አገሪቱ ቀጣይ አመታትንም ከእርዳታ ስንዴ አትላቀቅም።

Monday, February 3, 2014

ጥር ፳፮ (ሃያ ስድት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ከውስጥ አዋቂ ምንጮች ለማዎቅ እንደተቻለው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በአዲስ አበባ ከተማ ውስጥ የሚታየውን የመኖሪያ ቤቶች ችግር በዘላቂነት ለማቃለል በሚል ከዚህ በፊት ከነበረው የ 20/80 የጋራ መኖሪያ ቤት ልማት ፕሮግራም በተጨማሪ በአማራጭ የ 10/90 አነስተኛ ገቢ ላላቸው የህብረተሰብ ክፍሎች እና ለመለስተኛና መካከለኛ ገቢ ላላቸው በ40/60 የቁጠባ ቤት ፕሮግራም መቅረጹን ተከትሎ እስከ አንድ ሚሊዮን የሚጠጋ ህዝብ ተመዝግቦ ነበር።
ይሁን እንጅ በአሁኑ ወቅት እጅግ በርካታ ቁጥር ያላቸው የተለያዩ የቤት ልማት ፕሮግራም ተሳታፊ ዜጎች ከፕሮግራሙ እየወጡ መሆኑ ታውቋል። ይህን ዜና እስካጠናከርንበት ጊዜ ድረስ ከ30 ሺ በላይ የሚሆኑ ነዋሪዎች ገንዘባቸውን ከባንክ አውጥተዋል።
ባንክ ቤቶች ከዚህ በፊት ለምዝገባ ስራ ሲጨናነቁ ከነበረው ባልተናነሰ በአሁኑ ጊዜ በከፍተኛ የስራ ጫና ውስጥ እንዳሉና ለዚህ አገልግሎት ብቻ አንድ መስኮት ለመልቀቅ እንደተገደዱ የደረሰን መረጃ ያመለክታል።
የ20 /80፣ የ10/90 እና የ40/60 ቤቶችን ለመገንባት ከገንዘብ እጥረት በተጨማሪ የቦታ እጥረት ማጋጠሙን ኢሳት የውስጥ መረጃዎችን በማሰባሰብ መዘገቡ ይታወሳል። በተለይም የኦሮሚያ ክልል በአዲስ አበባ ዙሪያ ያሉ ከተሞችን በአዲስ አበባ ታላቁ ካርታ ውስጥ ለማስገባት ፈቃደኛ ሆኖ ባለመገኘቱ የፕሮጀክቱ ተፈጻሚነት አደጋ ውስጥ ወድቋል።
መንግስት ወደ 10 ቢሊዮን ብር የሚጠጋ ገንዘብ ከባንክ በመበደር ቤቶችን ለመስራት ቢያስብም፣ ንግድ ባንክ በርካታ የብድር አገልግሎቶችን በመሰረዝ ለማግኘት የቻለው 6 ቢሊዮን ብር ነው። መንግስት በተለይ 40 በ60ን ተግባራዊ ለማድረግ ያወጣው እቅድ ቅጅው ለኢሳት ደርሶአል። በዚህ እስካሁን ይፋ ባልተደረገው እቅድ የቤቶች ዋጋ ቀድሞ ከተያዘለት በእጥፍ ጨምሮ በግል ከሚሰሩ ቤቶችም ጋር ሲነጻጸር እጅግ ውድ ሆኖ ተግኝቷል።

በቦዲና በኮንሶ ብሄረሰቦች መካከል በተነሳው ግጭት የ4 ሰዎች ህይወት አለፈ

ጥር ፳፮ (ሃያ ስድት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ግጭቱ የተከሰተው ባለፈው ሳምንት ሲሆን፣ ለግጭቱ መነሻ የሆነውም ኮንሶዎች ባጋጠማቸው የመሬት እጥረት ሳቢያ ወደ ቦዲዮች አካባቢ ሄደው በመስፈራቸው መሆኑን የአካባቢው ምንጮች ይገልጻሉ።
በግጭቱ ከሁለቱም ወገኖች 4 ሰዎች ሲሞቱ፣ 3 ኮንሶዎች እና አንድ ፖሊስ ቆስለዋል። 72 ቤቶችም እንዲሁ ተቃጥለዋል።
ከዚህ በፊት ሁለቱ ብሄረሰቦች በተደጋጋሚ ሲጋጩ ቆይተዋል። ቀደም ሲል መንግስት የኮንሶ ሰፋሪዎችን ወደ ቦዴ አካባቢ በመውሰድ ማስፈሩ በአካባቢው ለሚታየው ችግር መንስኤ መሆኑን የአካባቢው ነዋሪዎች ገልጸዋል። በአሁኑ ጊዜ የፌደራል ፖሊስ ገብቶ አካባቢውን ተቆጣጥሮታል።
ይህ በእንዲህ እንዳለ በጅንካ መብራት ለረጅም ጊዜ በመቋረጡ ህብረተሰቡ ለከፍተኛ ችግር ተጋልጧል። የከተማዋ ነዋሪዎች እንደገለጹት በአራት ቀናት አንድ ጊዜ የሚመጣው መብራት፣ ለከፍተኛ የኢኮኖሚ ችግር ዳርጓቸዋል።

ህወሓት ከመለስ ጋር አብሮ ተቀብሯል

February 3, 2014
ከነፃነከነፃነት አድማሱ
ይህ የያዝነው ወርሓ ለካቲት “የህወሓት ልደት የትግራይ ህዝብ ልደት ነው፣ ህወሓት ብቸኛ የትግራይ ህዝብ ነፃ አውጪ ነው፣ የትግራይ ህዝብ ታሪክ ከደደቢት ይጀምራል፣ የህወሓት አላማና ፍላጎት የትግራይ ህዝብ አላማና ፍላጎት ነው፣ የትግራይ ህዝብ ከህወሓት ሌላ አማራጭ የለውም ዙሪያው ሁሉ ገደል ወይም ጠላት ነው፣ በአጠቃላይ የትግራይ ህዝብ ህልውና ከህወሓት ህልውና ጋር የተቆራኘና ድርጅቱ ስልጣን ላይ ሲኖር ትግራይም የምትኖር ድርጅቱ ከጠፋ ወይም ስልጣን ላይ ከሌለ ደግሞ የትግራይ ህዝብም አብሮ የሚጠፋ ነው”……..እያሉ በመስበክ በሰማእታት መቃብር ላይ ቆሞው የውሸት ድራማ የሚሰሩበት፣ በትግራይ ህዝብ ደምና አንጡራ ሃብት ላይ የሚነግዱበት፣ በድምሩ “ጆሮውን ቆርጠው የሰጡት ውሻ ሥጋ የሰጡት ይመስለዋል” እንዲሉ የትግራይ ህዝብ ብሄራዊ ክብሩ፣ ዳር ድንበሩንና ብሄራዊ ጥቅሙን ለባዕድ ሽጠው ሲያበቁ ነፃ አውጥተናሃል!! ልማት አምጥተንልሃል!! እያሉ የሚዘምሩበትና የሚመፃደቁበት የካቲት 11 በዓል እየመጣ ነው። ይህ ዓይነቱ ጭፍን ፕሮፓጋንዳ መርዝ ደግሞ ዛሬ የመጣ ባህል አይደለም። ህወሓት ከተፈጠረበት ቀን አንስቶ እስካሁን ድረስ ለአርባ ዓመታት ያህል ለጀሮ
እስከሚሰለች ድረስ በካድሬዎቹ አማካይነት ነጋ ጠባ በዚያች በተቀደሰች ምድር ትግራይ በአሁኑ በሃያ አንደኛ ክፍለ ዘመን የሚሰበክ የደደቢት የአደንቁረህ ግዛ ፍልስፍና መሆኑን ተራ የገጠር እረኛም ሳይቀር ያውቀዋል።Tigray People Front, TPLF
ይሁን እንጂ ህወሓት ከድርጅትነት ወደ ቡድናዊ አምባ ገነንነት፣ በኋላም ከቡድናዊ አገዛዝ ወደ ፍፁም የቤተሰባዊ መዝርፊያና የማፈኛ የግል ኩባንያ ሆኖ ከተሸጋገረ ወዲህ እኖሆ ዓሰርቱ ዓመታት አስቆጥሯል። በመጨረሻም “ጊዜ ዳኛ ታሪክ ምስክሩ ነውና” ድርጅቱ ከባለቤቱ ከቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስቴር መለስ ዜናዊ ጋር አብሮ ግብኣተ መሬት ገብቷል። ላይመለስ አብሮ ተቀብሯል። አሁን ያለው “በድርቆሽ የተሞላ ህይወት የሌለው የቆዳ ግሳንግስ ወደ(ዓርሲ)” ተለውጦ ባንድ በኩል በአቶ ስብሓት ነጋ የ80 ዓመት ጎበዝ አለቃ የሚመራ ሲሆን በሌላ በኩል ደግሞ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ በኤርትራውያን የሚገፋ አሮጌ ጋሪና በወታደር የሚጠበቅ የደረቀ ሬሳ ሆኖ ቀርቷል” የሚሉ ብዙዎች በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን ናቸው።
ይህ ምን ያህል እውነትነት አለው? አንድ የፓለቲካ ድርጅት ሞቷል ወይም ህይወት የለዉም ሲባልስ ምን ሲሆን ነው? ህወሓት ከበረሃ ጀግንነት ወደ ዱር አራዊትነት የተቀየረበት ጊዜስ መቼ ነው? እውነት የጥቂት ወሮ-በላና ከሃዲ መሪዎች በረሃ የገቡበትን ቀን የታላቁ የትግራይ ህዝብ ልደት ነውን? የትግራይ ህዝብ ከሌላው ሰማንያ ሚሊዮን የኢትዮጵያ ህዝብ ምን የተለየ ጥቅም ስላገኘ ነው የአንድ መርሲነሪ የፓለቲካ ድርጅት ልደት የህዝቡን ብሄራዊ በዓል ተደርጎ የሚያከብረው? ለመሆኑ የትግላችን ውጤት ነው እየተባለ የሚነገርለት ሕገ መንግስት እውነት ለትግራይ ህዝብ ይመለከተዋልን? የሚሉና ሌሎች ተዛማጅ ጥያቄዎችን እንድንመልስ ግድ ይለናል።
ወደ ዋናው የጥያቄው መልስና አርእስተ ጉዳይ ከመግባቴ በፊት ግን ለአንባቢዎቼና ለነፃ ሚዲያ ደንበኞቼ በአክብሮት የምጠይቀው በዚሁ ፅሑፍ ዙሪያ በመቃወምም ሆነ በመደገፍ ከቂም በቀል፣ ከስሜታዊ አስተሳሰብ፣ ከጭፍን ደጋፊነት፣ በአጠቃላይ የግለ ስብእና፣ የሃሳብ ነፃነትና
ሰብኣዊ መብት በማይጋፋ መልኩ በዋናው ጉዳይ ላይ ያተኰረ ክርክር ወይም ሃሳብ ቢያቀርቡ ለመማማርና በቂ መልስ ለመስጠት ዝግጁ መሆኔን በዚሁ አጋጣሚ ለመግለፅ እወዳለሁ። ፍርሃትን አስወግዶ የህሊና ባርነትን ሰብሮ በመውጣት የሀገርና የህዝብ ወገን ሆኖ መከራከር፣ ለሃቅ መመስከርና በፅናት መቆም ምንኛ ያኰራል!!!
በዘመነ መሳፍንት አንዲት የጎጃም አልቃሽ ““ጎጃሜ ቡዳ ነው ቡዳ ነው ስትሉ ስትሉ አላየህም ወይ ትግሬ እርስ በርስ ሲባሉ” ብላ ተናግራለች” በማለት ከዛሬ አስራ አንድ ዓመት በፊት የህወሓት አመራር ለሁለት ተሰንጥቆ ሲፈረካከስ ያዩ አንድ አዛውንት ያለፉትን የትግራይ ባላባቶችና መሳፍንቶች ታሪክ ከህወሓት ታሪክ ጋር በማነፃፀር እንደዋዛ አጫውተውኝ እንደነበር አስታውሳለሁ። በሌላ መልኩ ደግሞ ስለ ህዝቡ ጀግንነት፣ ጨዋነት፣ ታጋሽነትና አትንኩኝ ባይነት እያስታወሱ የዛሬው ትውልድ ግን ሐሙት የፈሰሰ እንዲሁ ወኔው ተኰላሽቶ መቅረቱ በጣም ያሳዘናቸው መሆኑን በቁጭት ገልፀውልኛል። ነገር ግን በወቅቱ የነገሩኝን ሁሉ ብዙም ልብ አላልኩትም ነበር። በኋላ ግን ስለ ህወሓት የተፃፉ መፃሕፍቶች በተለይም የቀድሞ የህወሓት ታጋይና አታጋይ የነበሩት አቶ አስገደ ገብረ ስላሴ የፃፉትን ጋህዲ በሚል ሶስት ተከታታይ መፃሕፍቶችን ሳነብ “ማየት ማመን ነውና” የትግሉ ባለቤትና የድርጅቱን መስራች የነበሩት ሰዎች እንኳን ሳይቀር የመሰከሩለት ህወሓት ከተፈጠረበት ቀን ጀምሮ እስካሁን ድረስ ተግባሩ ሲመረመር ከላይ አዛውንቱ የነገሩኝ አባባል በትክክል የሚገልፅ መሆኑን ለመረዳት ችያለሁ።
“የህወሓት ታሪክ የርስ በርስ መላላት፣ ህዝብ ለህዝብ የማናቆርና ሀገርን የማፍረስ ታሪክ ነው” ቢባል ከእውነት የራቀ አይደለም። ይህን በሚመለከት ዝርዝሩን ለታሪክ ፃፊዎች ትቼ አንድ ሁለት አብነቶችን ብቻ ልጥቀስ። ህወሓት ከትጥቁ ትግል ዘመን ጀምሮ እስካሁን ድረስ ለ40 ዓመታት ያህል የዘለቀው አንድ ገዢ መፈክር ነበረው። እሱም “ የቻለ ይሩጥ!! ያልቻለ ያዝግም!! ያበቃለት ይለይለት!!? በትግርኛ (ዝኻኣለ ይጉየ! ዘይካኣለ ይሳለ! ዘብቀዐ ይታኣለ) የሚል ነው። ከመፈክሩም ጎን ለጎን በድርጅቱ የኪነት ቡድን የተሰራ ከአቶ መለስ መልክ ጋር የሚመሳሰል ፊት ለፊቱ ደግሞ ጣቱን ወደ ሰዎች ቀስሮ የሚያስፈራራ ሥዕል በየስብሰባውና ታጋዮች ባሉበት ሁሉ የሚለጠፍ ነበር።
ስዕሉ በጋሃድ በአደባባይ መውጣት የጀመረው ደግሞ ልክ እነ ዶ/ር አረጋዊ በርሄና አቶ ግደይ ዘርኣፅዮን ከድርጅቱ ተለይተው ከወጡ በኋላና “ማርክሰ ሌኒስት ሊግ ትግራይ (ማሌሊት)” ከተመሰረተ አንድ ዓመት ባልሞላ ውስጥ ነበር። ስዕሉ ያልተለመደ ነገር ስለነበረ ብዙ ታጋዮችን በተለይም ያልተማሩ የገበሬ ልጆች የሆኑትን ታጋዮች ግራ አጋብቷል። አንዳንድ ቦታም ሌሊት በሳንጃ እየቀደዱ ይጥሉት ነበር። ከጊዜ በኋላ ግን ስዕሉ ተለመደ። የሚገርመው ግን በወቅቱ የድርጅቱን የኪነ ጥበብ አባል ሆኖ ስዕሉን ያቀነባበረ ሳኣሊውንም ጭምር ከጥቂት ወራት በኋላ ድርጅቱን ለቆ በመውጣት ዛሬ በስደት ዓለም በህወይት ይገኛል። ስሙን ያልጠቀስኩበት ምክንያት ደግሞ የሱ ፍቃደኝነት መጠየቅ ስላለብኝ ነው። የመፈክሩ ዋና አላማና ስትራተጂም የሚከተሉትን ሶስት ዋና ዋና ነገሮችን ያቀፈ ነው፡-
1. አንደኛ የአቶ መለስ ዜናዊና የአቶ ስብሓት ነጋ ቡድን ተቀናቃኝ ወይሞ ሞጎደኛ ተብለው የሚጠረጠሩትን ያመራር አባላት፣ ምሁራንና የጦሩ አለቆችን (ይህችን ባቄላ ካደረች አትቆረጠምም) በማለት ቀስ በቀስ የማፅዳት ስልትና ስትራተጂ ነው። ይህንንም ሰሞኑን በኢትዮ- ሚዲያ ድሕረ ገፅ የወጣውን የነ ሙሴ፣ ዶ/ር አታክልት፣ ገሰሰው አየለን ጨምሮ ተኩሉ ሃዋዝ፣ መለስ ካሕሳይ፣ ዶ/ር አረጋዊ በርሄ፣ ግደይ ዘርኣፅዮንና ሌሎች በሽዎች የሚቆጠሩት የድርጅቱን ከፍተኛና መካከለኛ የአመራር አባላትን ያካትታል።
2. ሁለተኛው የመፈክሩ አላማና ስትራተጂ የትግራይ ብሄረተኝነትንና ብሎም የኢትዮጵያዊነት ስሜትን ከትግራይ ምድርና ከህዝቡ አስተሳሰብ ከስረ መሰረቱ በመፋቅና በማጥፋት በምትኩ በትግራይ ብሎም በሀገራችን የኤርትራ ሻዕቢያዊ አመለካከት የበላይነት እንዲይዝ ማረጋገጥ ነው። በዚሁ ዙሪያ በቅድሚያ የተመቱት የድሮ አስተሳሰብ፣ ሀገራዊ ስሜትና እንዲሁም በኤርትራ ጉዳይና በአገር አንድነት ጉዳይ ላይ የከረረ አመለካከት አላቸው ተብለው የሚገመቱትን ባላባቶችንና የሀገር አዛውንቶችን ናቸው። ቀጥሎም የተመቱት የትግራይ መሁራኖች ናቸው። በኤርትራና በሀገር ጉዳይ ዙሪያ የሚከራከሩና ጥያቄ የሚያነሱ ምሁራን እንደ ኤለክትሪክ ይፈሩዋቸው ነበር። በዚህ መሰረት “ሽዋውያን ተጋሩ” የሚል የቅፅል ስም መለጥፍ ብቻ ሳይሆን በዘፈንም ሳይቀር ቅስማቸው እንዲሰበርና አንገታቸው እንዲደፉ ተደርጓል። በዚህ ምክንያት የቻሉትን ከድርጅቱ ሸሽተው እንዲያመልጡ ያልቻሉት ደግሞ ለእስርና ለግድያ ተዳርጓል። በዚህ ምክንያት በሀገር ውስጥም ሆነ በውጭ የሚኖሩ የትግራይ ምሁራን ዛሬም ስለህዝባቸውና ሀገራቸው ጉዳይ ደፍረው ጥያቄ እንዳያነሱ ፍርሃት እንደ ወባ
በሽታ በደማቸው ውስጥ ገብቶ እያዩ እንዳላዩ ዝም እንዲሉ ትልቅ ምክንያት የሆነውን ጠባሳ እስካሁን ድረስ አልሻረም።
ዛሬ በአረና ትግራይ አባላትና ደጋፊዎቻቸው እየደረሰ ያለው ዱላም ከዚሁ የተለየ አይደለም። ለአንድ የአረና አባል ከአምስት በላይ ሰላዮች በመመደብ ኮቲያቸውን እየተከተሉ መውጫና መግቢያ ያሳጧቸዋል። ዛሬ ትግራይ ለነ ስብሓት ነጋና ሌሎች መሪዎች ታማኝ የሆኑትን የኤርትራ ተቃዋሚ ነን የሚሉ ድርጅቶች በነፃነትና በልበ ሙሉነት የሚንቀሳቀሱባት በአንፃሩ ከህዝቡ አብራክ የተፈጠሩ ለነ አረና ትግራይና ሌሎች ሀገር በቀል ድርጅቶች ግን በገዛ ሀገራቸው ተሸማቅቀውና በአደባባይ በዱላ እየተመቱ የሚኖሩባት ምድራዊ ሲኦል ሆና ትገኛለች።
በመሆኑም ዛሬ ሰፊው የትግራይ ህዝብ ባንድ በኩል የትግራይ ሻዕቢያ በሌላ በኩል ደግሞ የኤርትራ ሻዕቢያ አጣብቅኝ ውስጥ ገብቶ በሁለት አለንጋ እየተገረፈ የሚገኝ ህዝብ ሆኗል። ታዲያ!! ለዘህ ሚስኪን ህዝብ አለሁልህ የሚል ወገን ማን ይሆን?
3. ሶስተኛው የመፈክሩ አላማና ስትራተጂ በህዝቡ የስነ ልቦናና የአካል ጥቃት በማድረስ በተለይም በትግራይ ምድር ፍርሃት፣ ሽብር፣ ጥርጣሬና ህወከት በማንገስና የህዝቡን ሁለንትናዊ አስተሳሰብ በመቆጣጠርና በማደንዘዝ ፀጥ ረጭ ብሎ እንዲገዛና ለጥቂት መሪዎች ዘላለማዊ ስልጣን አገልጋይ ሆኖ እንዲኖር ለማድረግ ነው። በሌላ አነጋገር ትግራይ ወፍ እንኳን ዞር የማይልባት፣ ሌላው ኢትዮጵያዊ በትግራይ ህዝብ ጉዳይ ላይ እንደማያገባው ተደርጎ መፈናፈኛ በማሳጣት በስመ ልማት እንደፈለጉ የሚግጥዋት የህወሓት የጓሮ አትክልት ሆና እንድትኖር ለማድረግ ነው።
ልበ በሉ!! የትግራይ ህዝብ በጦርነት የደቀቀ ህዝብ ነው። ትግራይ ደርግ፣ ኢዲዩ፣ ጀብሃ፣ ሻዕቢያ፣ ኢሕአፓ፣ ህወሓትና ሌሎች ብረት ያነገቡ ሀይሎች የሚንቀሳቀሱባት ለአስራ ሰባት ዓመታት ያህል የጦርነት አውድማ ሆና ቆይታለች። ዛሬም ህዝቡ ከጥይት ጭኾት አልተላቀቀም። በኤርትራና በኢትዮጵያ በሁለቱም ሀገሮች ድንበር ከሩብ ሚሊዮን በላይ ሰራዊት በመሸገበትና በተፋጠጠበት የጦርነት ደመና ስር ሆኖ ዛሬ ነገ ውጊያ ይጀመራል እያለ በፍርሃት ተውጦ የሚገኝ ህዝብ ነው። በዚህም ላይ በየጊዜው ከያሉበት በታጣቂዎች እየታፈኑ ወደ ኤርትራ ተወስደው ደብዛቸው የማይታወቁ ንፁኃን ዜጎች ቁጥራቸው ቀላል አይደለም። በዚሁ ፍርሃት ቀያቸውንና ቤታቸውን እየለቀቁ ወደ ዓረብ ዓለም የሚሻገሩና ወደ ማሀል ሀገር በመሸሽ የኢትዮጵያ ዋና ዋና ከተሞችን በልመና ያጥለቀለቁት የየተኛው አካባቢ እንደሆኑ ማንም ኢትዮጵያዊ ያውቃል። እነዚህ ግጭቶችም እንደ ፓለቲካ መሳሪያና ማስፈራሪያ እየተጠቀሙ “እኛ ከሌለን ያ ሁሉ
ጠላት ይመለሳል፣ ሻዕቢያ ተመልሶ ይውጥሃል፣ ኦነግና ትምክሕተኞች ቂማቸው ይወጡቡሃል፣ የሽብርተኞች ዒላማ ትሆናለህ፣ በትግራይ የተተከሉ ፋብሪካዎች ተነቅለው ወደ ማሃል ሀገር ይወሰዳሉ፣ በትግልህ የቀበርካቸው ጠላቶች ከመቃብር ተነስተው ይመጣሉ፣ ወዘተ እያሉ ነጋ ጠባ ህዝቡን ማሸበርና ማደንቆር የተካኑበት ዋነኛ የአገዛዝ ጥበባቸው ሆኖ ይገኛል።
ወንድሞቼ ሆይ!! ታዲያ እንዲህ ዓይነቱ የቆሸሸ ታሪክ ያለው ድርጅት ዛሬ በትግራይ ህዝብና በተለይም በአረና አባላትና ደጋፊዎቻቸው ላይ የአራዊት ስራ ቢሰራ የሚያስገርም አይደለም። ህዝብን ሁሉ ጊዜ ማታለል የማይቻል መሆኑን ያልገባቸውና ጊዜውም ጥሏቸው እየሄደ መሆኑንም የማይቀበሉ እንደ ሾላ ፍሬ ውስጣቸው የበሰበሱ መሪዎች እስከ ህልፈተ ቀናቸው ድረስ “የደንቆ ልቅሶ መልሶ መላልሶ” እንዲሉ ዛሬም የሚናገሩት ቋንቋና የሚሰሩት ስራ ያው በጫካ የለመዱት ዓይነት ነው። ከላይ የተጠቀሰው የመፈክራቸው አላማና ስትራተጂም በትክክል ሲተረጎም “እምቢ ያለ ሰው ጥይት አጉርሰው” ከሚለው የደርግ ስርዓት መፈክርና ተግባር ጋር አንድ ዓይነት መሆኑን የኢትዮጵያ ህዝብ ይስቷል ብዬ አልገምትም።
የሚያሳዝነውና የሚያስገርመው ነገር ግን ትግራይን የጥፋትና የመከራ ሞዴል በማድረግ የሚፈፅሙትን ጉድ እንደ ኤይድስ ወረርሽኝ በሽታ ወደ ሌሎቹ ክፍላተ ሀገራትም እየተዛመተ መምጣቱ ነው። በዚሁ ነጥብ ዙሪያ በቀጣዩ ፅሑፌ ተመልሼ እመጣለሁ። ቸር ሰንብቱ።

ኦሞት ኦባንግ – የታዳኝ አዳኝ ድራማ * ኢህአዴግም በበኩሉ እያደናቸው ነው

“ሁሉም ከህግ አያመልጡምና ዜጎች መረጃ በመሰብሰብ የቤት ስራችሁን ስሩ” ኦባንግ ሜቶ

ኦሞት ኦባንግ በዓለም ዓቀፍ ተቋማት ለፍርድ እንዲቀርቡ እየታደኑ ነው
Feb.3/2014
ሰሞኑን አገር ጥለው መኮብለላቸው የተደመጠው የቀድሞው የጋምቤላ ክልል ርዕሰ መስተዳደር አቶ ኦሞት ኦባንግ በተለያዩ የዓለም ዓቀፍ ተቋማት ክትትል እየተደረገባቸው እንደሆነ ታወቀ። የአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ /አኢጋን/ ዋና ዳይሬክተር አቶ ኦባንግ ሜቶ ፍትህ የተዛባባቸው ዜጎች ሁሉ መረጃ በማሰባሰብና ለድርጅታቸው በመላክ የዜግነት የቤት ስራቸውን እንዲሰሩ ጥሪ አቅርበዋል። አቶ ኦሞትን ፍትህ ደጅ ለማቆም ከ19 ዓለም አቀፍ ተቋማት ጋር በኅብረት እየሰሩ መሆናቸውም አመልክተዋል። በሌላም በኩል ኢህአዴግም “ነገር ሳይበላሽ” እያደናቸው እንደሆነ ተሰምቷል፡፡

በ2003 በጅምላ ለተጨፈጨፉና በሺህ ለሚቆጠሩ የአኙዋክ ተወላጆች መሰደድ ከመለስ ቀጥሎ ግንባር ቀደም ተጠያቂ የሚባሉት አቶ ኦሞት፤ ሳምንት በፈጀ ግምገማ ከክልሉ ሊቀመንበርነታቸው መነሳታቸውና የፌዴራል ጉዳዮች ሚኒስትር ዲኤታ ሆነው መመደባቸው ይታወሳል። “እውነተኛው ወያኔ” እየተባሉ የሚጠሩት አቶ ኦሞት ምንም እንኳ በሚኒስትርነት ደረጃ ቢመደቡም በሙስና ተወንጅለው እንደሚታሰሩ ጎልጉል ምንጮቹን ጠቅሶ መዘገቡ አይዘነጋም።

በሰኔ 10፤2005 ዓም (June 17, 2013) የጎልጉል ዘገባ ላይ እንደተጠቀሰው ከ83 ሚሊዮን ብር በላይ አላግባብ ለግል ጥቅማቸው ማዋላቸውን፣ እንዲሁም በክልሉ የሚፈጸሙትን የተጭበረበሩ የበጀት አፈጻጸሞችንና ምዝበራዎችን የሚያጋልጡ ሰነዶችን በሚስጥር ተደራጅቶ ለኢህአዴግ የድርጅት ቢሮ ቀርቦ ነበር። የክልሉ የፋይናንስ ቢሮ ሃላፊ የነበሩት አቶ ተስፋዬ ኢሬሳ ከፍተኛ ምስጢር ያላቸውን ሰነዶች በመያዝ ከመታሰራቸው በፊት መሰወራቸውን የጠቆመው ዘገባ “የቢሮ ሃላፊው ይዘው የተሰወሩት መረጃ አቶ ኦሞት የፈረሙባቸው ከፍተኛ የገንዘብ ሰነዶችና ሙስና የተከናወነባቸው የኮንስትራክሽንና የተለያዩ መረጃዎች ይፋ የሚያደርጉ ነበሩ። በወቅቱ “መረጃዎቹ አንድ ቀን ህዝብ ፍርዱን ይሰጥ ዘንድ ይፋ ይሆናሉ” ተብሎም ነበር። የመረጃ ምንጫቸውን ባይጠቅሱም አቶ ኦባንግ “ኦሞትን በተመለከተ ከበቂ በላይ መረጃ አለን፤ ህግ ፊት እናቀርበዋለን፤ በንጹን ደም ተጨማልቆና ህዝብ ላይ ግፍ ፈጽሞ መሰወር አይቻልም” በማለት በስልክ ለጎልጉል ተናግረዋል። አቶ ተስፋዬ ኢሬሳ በድንገት ምሳ እየተመገቡ ከመርዝ ጋር በተያያዘ ህይወታቸው በድንገት ማለፉ ይታወሳል።

ከታህሳስ 23 ቀን 2004 ዓ ም ጀምሮ ሟቹ አቶ መለስ በላኳቸው አስገምጋሚዎች ለሳምንት በተካሄደ አውጫጪኝ አቶ ኦሞት “የአኙዋክ ተወላጆችን አስጨፍጭፈሃል” የሚል መነሻውና ዓላማው ግልጽ ያልሆነ ጥያቄ ቀርቦላቸው ነበር። በወቅቱ ግምገማው ላይ የነበሩ እንዳሉት አቶ ኦሞት “እኔ በዚህ ጉዳይ ተጠያቂ ከሆንኩ መሳሪያና ወታደር የሰጠኝ መለስም ይታሰራል” በማለት መልስ ሰጥተው ነበር።

በወቅቱ አቶ ኦባንግ ሜቶ የሚመሩት ድርጅት /አኢጋን/ አቶ መለስን በዓለም አቀፉ የወንጀለኞች ችሎት ተጠያቂ ለማድረግ ያቀረበው ማመልከቻ ተቀባይነት ያገኘበትና አቶ መለስ ላይ ክስ እንዲመሰረት ውሳኔ የተደረሰበት ዜና የተሰማበት ነበር። ለጉዳዩ ቅርብ የሆኑ የጋምቤላ ምንጮች “አቶ መለስ አቶ ኦሞትን በጭፍጨፋው ተጠያቂ በማድረግና ርምጃ በመውሰድ ራሳቸውን ጲላጦስ ለማድረግ የወጠኑት አካሄድ እንደሆነ የፌዴራል ሰዎች ነግረውናል። ኦሞትም በሙስና በዘረጋው መዋቅር እስከላይ ድረስ ዘመድና ተቆርቋሪ ስላበጀ መረጃው ደርሶት ነበር” ብለዋል። /በዓለም አቀፉ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት የተመሰረተው ክስ መለስ ቢሞቱም እስካሁን ክፍት ነው/

በሌላም በኩል ወቅቱ በክልሉ ኢህአዴግ ለልማት በሚሰጠው ርዳታ ዜጎችን ለማፈንና ረግጦ ለመግዛት የሚያስችለውን ሃይል ያደራጅበታል በሚል ተቆርቋሪዎች መረጃ አስደግፈው ባቀረቡት ክስ ዓለም ባንክ አጣሪ የላከበት ነበር። ከዚሁ ጋር ተያይዞ መሬታቸውን፣ የትውልድ ቀያቸውን በአንጋቾች የተነጠቁ ምስኪን ዜጎች ድምጽ ዓለም አቀፍ ትኩረት አግኝቶ ኢህአዴግን ክፉኛ የተፈታተነበት ነበር። ለዚህ ይመስላል ኢህአዴግ በግምገማ በርካታ የክልሉን ሃላፊዎች ወረዳ ድረስ በመዝለቅ በሙስና ሰበብ ሲያባርርና ሲያስር፣ አቶ ኦሞትን ወደ ፌዴራል በማዛወር በቅርብ ይከታተላቸው ነበር። አቶ ኦሞት ወደ ፌዴራል ሲዛወሩ “የቤንሻንጉል ጉምዝ ፕሬዚዳንት በነበሩት አቶ ያረጋል አይሸሹ ላይ የተደረገው ይፈጸምባቸዋል” ተብሎ አስቀድሞ ተተንብዮ ነበር።

ለአብነት ከላይ በተዘረዘሩት መነሻዎችና በሌሎች ተያያዥ ምክንያቶች ሳቢያ የአቶ ኦሞትና የህወሃት ግንኙነት ማክተሙን የሚናገሩት ለጉዳዩ ቅርብ የሆኑ ክፍሎች፣ “ቀደም ሲል ህወሃትን ሲያገለግሉ ኖረው መጨረሻቸው እስር እንደሆነው አራት የቀድሞ የክልሉ መሪዎች፣ ወይም እንደ አምስተኛው ፕሬዚዳንት አቶ ኦኬሎ አኳይ ስደት እጣ ፈንታቸው ይሆናል” የሚል ቅድመ ትንበያ ነበር።

አቶ ኦኬሎ አኳይ በአኙዋክ ተወላጆች ላይ የተፈጸመውን የጅምላ ጭፍጨፋ አስመልክቶ ለዓለም አቀፍ የሰብአዊ መብት ድርጅቶች ክልሉን ወክለው የተዛባ መረጃ እንዲሰጡ ታዘው ነበር። በአቶ አባይ ጸሃዬና ገብረአብ በርናባስ መመሪያ መሰረት ግጭቱ በጎሳ ላይ የተመረኮዘ የርስ በርስ እንደሆነ፣ በግጭቱ 59 ሰዎች ብቻ ሲሞቱ አንድ ቤት መቃጠሉን እንዲናገሩ የተሰጣቸውን መመሪያ ያልተቀበሉት አቶ ኦኬሎ ህይወታቸው አደጋ ላይ በመውደቁ አገር ጥለው መሰደዳቸው ለጉዳዩ ቅርብ የሆኑ በተደጋጋሚ ገልጸው ነበር። ይሁን እንጂ አቶ ኦኬሎ አኳይ በስደት ሆነው በይፋ በዚህ ጉዳይ መግለጫ ለመስጠት አለመድፈራቸው ብዙዎችን ግራ ያጋባ ጉዳይ ሆኗል።

ኦሞት የት ናቸው?

አቶ ኦሞት የክልሉ የደህንነት ሃላፊና ፖሊስ ኮሚሽነር ሆነው ባገለገሉበት ወቅት ፍጹም ታማኝ ስለነበሩ በ2005 የተሰጣቸው የክልል መሪነት ስልጣን ለህወሃት ለሰሩት ውለታ የተከፈለ ወሮታ እንደሆነ ተደርጎ ነው የሚወሰደው። በዚሁ መነሻ ይመስላል አብዛኛው የጋምቤላ ተወላጆች ለአቶ ኦሞት የከፋ ጥላቻ እንደነበራቸው የሚናገሩ ክልሉ ተወላጆች፣ ኦሞት ከአገር ኮበለሉ መባሉ አያስገርማቸውም።
አሁን ጥያቄው ኦሞት ከኢህአዴግ አፍንጫ ስር እንዴት አመለጡ? አሁን የት ናቸው? መጪው እጣ ፈንታቸውስ? የሚለው ነው። አዲስ አድማስ ባለፈው ቅዳሜ እትሙ አቶ ኦሞትን የግምባር ዜና አድርጎ ሲያቀርብ አገር ጥለው መኮብለላቸውን የፌዴራል ጉዳዮች ሚኒስትር ዶ/ር ሽፈራው ማረጋገጣቸውን አስነብቧል። አቶ ኦባንግ ሜቶ ለጎልጉል እንደገለጹት አቶ ኦሞት ከሁለት ወር በፊት ለስልጠና አውሮፓ ሲመጡ በነበራቸው ቪዛ ከሁለት ሳምንት በፊት ዓርብ ቀን አገር ጥለው እንደወጡ መረጃው አላቸው።

ለአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ /አኢጋን/ ከ19 የተለያዩ ዓለም አቀፍ ተቋማትና ከፍተኛ ባለስልጣናት ጋር በጉዳዩ ዙሪያ እየሰሩ መሆናቸውን ያመለከቱት አቶ ኦባንግ ሜቶ “ኦሞት መለስ በህይወት እያለ ቢኮበልል መልካም ነበር። አሁን ከኦሞት የምንፈልገው ችሎት ፊት በወገኖቹ ላይና በኢትዮጵያ ህዝብ ላይ የተፈጸመውን ጭፍጨፋ፣ ቶርቸር፣ እስር፣ ዝርፊያ፣ የመሬት ንጥቂያ፣ ወዘተ አስመልክቶ እንዲናዘዝ ነው” ብለዋል። ኮብላዩ አቶ ኦሞት የት እንደሚገኙ ተጠይቀው “አሁን እዚህ ነው የሚባልበት ደረጃ ላይ አይደለንም። ግን መሰወር የሚችል አይመስለኝም። በደም ተጨማልቆ በስደት ተበዳይ መስሎ መኖር አይቻልም። የዓለም አቀፉ ፍርድ ቤት ከመለስ ጋር በተመሰረተው ክስ ላይ ኦሞት የተካተተ መሆኑ መዘንጋት የለበትም። እኛ እንኳ ዝም ብንል ፍትህ በርዋን አትዘጋም” ሲሉ ምላሽ ሰጥተዋል።

ጎልጉል ባሰባሰበው መረጃ አቶ ኦሞት አገር ጥለው የወጡት ከሁለት ሳምንት በፊት ሲሆን አንድ ሳምንት ቢዘገዩ ኖሮ እስር ቤት ይገቡ ነበር። አስቀድሞ በደረሳቸው መረጃ መሰረት አቶ ኦሞትን እስር ቤት እንዲወረወሩ የሚያዘው የአስር ማዘዣ የሚቆረጥበት ግምገማ ተዘጋጅቶ ነበር። እሳቸው አስቀድመው አገር ጥለው በመውጣታቸው ግምገማው ተስተጓጉሏል። ግምገማው የዓለም ባንክ አጣሪ ቡድን በትላንትናው ዕለት ኢትዮጵያ ሲገባ በሙስናና በሰብዓዊ ጉዳዮች ላይ ኢህአዴግ ርምጃ በመውሰድ ዝግጅት አጠናቆ ለመጠበቅ የሚረዳው ነበር። ግን አልሆነም።
በጋምቤላ በኢቨስትመንት ስም መሬት ወስደው ከሚሰሩት መካከል 70 ከመቶ የሚሆኑት የቀድሞ የህወሃት ታጋዮችና የትግራይ ተወላጆች መሆናቸው አቶ ኦሞት የሚደረግባቸውን ክትትል አልፈው አገር ሊወጡ እንደቻሉ ግምት አለ። አሁን “ባለሃብት” የሚባሉት እነዚህ ክፍሎች ባላቸው መዋቅር ሳቢያ አቶ ኦሞትን ሊታደጓቸው እንደሚችሉ ከግምት በላይ የሚናገሩ አሉ።

አቶ ኦሞት ሆላንድ ገብተዋል የሚሉም አሉ። በሌላ በኩል ደግሞ አውሮፓ ሊገቡ አይችሉም በማለት ግምቱን የሚያጣጥሉ አሉ። እነዚህ ክፍሎች ወደ ማሌዢያ ሄደዋል የሚለውን ምንጭ ይደግፋሉ። በስፋት እንደሚነገረው ከሆነ አቶ ኦሞት ኤዢያ እንደሚሄዱ የሚያጠናክሩ ምልክቶች አሉ። አብዛኛው የኢህአዴግ ባለስልጣኖች በማሌዢያ ባንኮች ገንዘብ አላቸው። አቶ ኦሞትም በተመሳሳይ የማሌዢያ ባንክ ተጠቃሚ ናቸው ተብሎ እንደሚገመት የሚቀርቧቸው ይናገራሉ። በተመሳሳይ በኢንቨስትመንት ስም የተወዳጇቸው ባለሃብቶች በኤዢያ ከለላ ሊሆኗቸው ስለሚችሉ የመጀመሪያ ምርጫቸው ኤዢያ እንደሚሆን ይስማማሉ።

ለጎልጉል ማንነታቸውን ሳይገልጹ መረጃ የሰጡ የኢህአዴግ ሰው እንዳሉት “ኦሞት ርቆ አልሄደም ይያዝል” በማለት ግምታቸውን ሰጥተዋል። ጉዳዩን በቅርብ እንደሚከታተሉ የገለጹት እኚህ ሰው “ኦሞት ብዙ ጉዳዮችን እንዳያበለሽ ጥንቃቄ ሲደረግ ነበር። እንዴት ለጊዜውም ቢሆን ተሰወረ?” የሚለው መነጋገሪያ መሆኑን ግን አልሸሸጉም። ኦሞት በወቅቱ የፈጸሙትን ከ400 በላይ የአኙዋኮችን ጭፍጨፋ፣ የተሳተፉበትን ሙስና፣ የመሬት ነጠቃ፣ ግድያ፣ ወዘተ የወንጀል ምስጢር በማውጣት ኢህአዴግን አሳጥተው ፍርድ እንዲቀልላቸው መደራደሪያ ከማድረጋቸው በፊት ኢህአዴግ የራሱ አደን አጠናክሮ እንደሚገኝ ተጨማሪ ዘገባዎች አሉ፡፡

አቶ ኦባንግ ሜቶ የኦሞት መሰወር አያስጨንቅም ባይ ናቸው። ኦሞትን ፍትህ አሳድዳ ትይዘዋለች የሚሉት አቶ ኦባንግ ትኩረታቸው ወንጀል የተፈጸመባቸው በሙሉ መረጃ በመሰብሰብና ወደ ጋራ ንቅናቄው በመላክ እንዲተባበሩ የመነሳሳታቸው ጉዳይ ላይ ነው። ህወሃቶች ወንጀል አሰርተው፣ መጨረሻ ላይ ፍትህ ወዳድ ለመምሰል በወንጀል ያጨማለቋቸውን ሰዎች ህግ ፊት አቅርበው እንደሚያስፈርዱባቸው ያመለከቱት አቶ ኦባንግ “ሌሎች ከዚህና ከቀድሞው ተሞክሮ ተማሩ። ኦሞትን ፍትህ አደባባይ ለማውጣት የሚሰራው ስራ ወንጀለኞችን ለመፋረድ የምናደርገውን ትግል አንድ ርምጃ ያሳድገዋል። እንደ ኦሞት ያሉት ወንጀለኞች ካሉበት ይለቀማሉ። ይህንን ማድረግ አቅም አለን። በደም ተጨማልቆ በስደት መኖር አይቻልም። ሌሎችም ካሁኑ ንስሃ ግቡ፤ ህብረተሰባችሁን አስቀድሙ” ሲሉ ጥሪ አስተላልፈዋል።

ህወሃትም ሆነ ኢህአዴግ በራቸውን መክፈታቸው ወይም ለውጥ እንዲመጣ እንዲፈቅዱ የሚገደዱበት ዘመን መቃረቡን ያመለከቱት አቶ ኦባንግ “ነጻ ውጡና ህዝባችሁን ነጻ አውጡ፣ አዲሲቷ ኢትዮጵያ ለወንጀለኞች ቦታ የላትም፣ ትፋረዳቸዋለች” ሲሉ በድጋሚ ህዝብ በወንጀለኞች ላይ መረጃ በማሰባሰብ የቤት ስራውን በወጉ እንዲሰራ ጠይቀዋል።

Please click the link to read the entire report http://www.goolgule.com/the-hunt-for-omot-obang-olum-continues

I am appealing to each of you to forward it to all your friends. If you do, you will not just be giving a voice to our beautiful people, but you would be doing justice to our humanity. Knowing the truth is overcoming the first obstacle to freedom!

Thanks so much for your never-ending support. Don’t give up. Keep your focus on the bigger picture and reach out to others and listen! Care about those who are suffering. Think about our family of Ethiopians and humanity throughout the world—they are YOU! There is no “us” or “them.” This is at the heart of the SMNE.


For media enquiries, more information including interview requests, contact Mr. Obang Metho, Executive Director of the SMNE. Email: Obang@solidaritymovement.org. SMNE ( www.solidaritymovement.org ), is a non-political and non-violent social justice movement of diverse people that advocates for freedom, justice, good governance and upholding the civil, human and economic rights of the people of Ethiopia, without regard to ethnicity, religion, political affiliation or other differences. The SMNE believes a more open, transparent and competitive market economy, supported by viable institutions and reasonable protections, which provides equal opportunity, will result in greater prosperity to the people rather than keeping it in the hands of a few political elites.

Sunday, February 2, 2014

ሌንጮ ለታ – ታሪክ ሊሰሩ ወይንስ ታሪክ ሊጽፉ…?

ሌንጮ ለታ – ታሪክ ሊሰሩ ወይንስ ታሪክ ሊጽፉ…?

February 2, 2014
ክንፉ አሰፋ
Former OLF chairman Lencho Leta
ኦቦ ሌንጮ ለታ
ኢትዮጵያዊው ቱጃር ለለውጥ ብለው በኮንትራት ታክሲ በመሄድ ላይ ናቸው። እሳቸውን የጫነው ታክሲ መስቀል አደባባይ ላይ ሲደርስ በድንገት ቀጥ ብሎ ቆመ። ሾፌሩ ተደናጋጠ። መኪናውን እንደገና ለማስንሳት ብዙ ሞከረ። ከብዙ ሙከራ በኋላ ጥረቱ ስላልተሳካለት ቱጃሩን ለትብብር ጠየቃቸው። እንዲህ ሲል። “ወጣ ብለው ይግፉ።”  ቱጃሩ በመገረም ሾፌሩን አዩት።  ”ይግዙ” ማለትህ ነው ሲሉም መለሱለት። እኚህ ሰው መኪናውን ከመግፋት ይልቅ አዲስ መኪና መግዛት ይቀላቸዋል።  የቤቶች ድራማ ላይ እከ ደከ አስር ጊዜ “እኔን ነው?” የሚለው ወዶ አይደለም። ማመን የሚቸግሩንን ነገሮች ማጣራት ስንፈልግ እንደጋግማለን።
በዚያን ሰሞን በኦቦ ሌንጮ ለታ የወጣው ዜና ብዙዎችን አስገርሟል።
“ሃገር ቤት ገብተን በመታገል አዲስ ታሪክ እንሰራለን።” የሚል ነበር የዜና እወጃው ርዕስ። ይህን ርዕስ እንዳየሁ አይኔን በደንብ ጠረግ ጠረግ አደረግኩና እንደገና አነበብኩት።
“ታሪክ እንሰራለን” የሚለው ሃረግ በስህተት የሰፈረ ነበር የመሰለኝ።  ሌንጮ ለማለት የፈለጉት “ታሪክ እናነባለን” ይሆናል በሚል ጥርጣሬ ደጋግሜ ያየሁት።  ያነበብኩት ነገር ትክክል ነው። ይህንኑ ቃል ከራሳቸው አንደበትም ሠማሁ።  በስህተት የሰፈረ ዜና አልነበረም።  ታሪክን ማንበቡም ሆነ መስራቱ ቀርቶ “ሃገር ቤት ገብተን አዲስ ታሪክ እንጽፋለን።” የሚል ቢሆን እንኳን ግርታውን ይቀንሰው ነበር።
በፍትህ ሳይሆን ይልቁንም በአዋጅ በምትተዳደር ኢትዮጵያ፤ እጅና እግራቸውን ብቻ ይዘው በመግባት ታሪክ መስራት የሚችሉ ከሆነ በምትሃት አልያም በመለኮታዊ ሃይል ብቻ መሆን አለበት። ሌንጮ ሃገር ቤት ገብተው ሰላማዊ ትግል ለማድረግ መወሰናቸው ላይ ምንም ችግር የለብኝም። የዚህ ውሳኔ ትክክለኝነት የሚዳኘው አስቀድመው በሚተቹ እና በሚተነብዩ የፖለቲካ ነብያት አይደለም። ፍርድ የሚሰጠው ሂደቱ በተግባር ሲፈተን ብቻ ይሆናል። ይህን ለማየት ደግሞ ብዙም ሩቅ አይሆንም።  በጎረበጠ የፖለቲካ መንገድ ላይ ጉዞ ለማድረግ ወደ ሃገር ቤት ለመግባት መወሰናቸው ግን አስመራ ላይ፤ በሻእቢያ ከታገቱት የኦነግ መሪዎች የተሻለ ውሳኔ ይመስላል።  ታሪክ ለመስራት አስመራ የመሸጉት እነ ዳውድ ኢብሳ ታሪክ ሆነው ቀርተዋል።
ችግሩ ያለው “ታሪክ እንሰራለን” ማለቱ ላይ ነው። እንደዚህ አይነት የፖለቲካ ትግል ውሳኔ ላይ መድረስ ቀላል ነገር አይደለም። ከመቅጽበት የመጣው ይህ ውሳኔ ልክ እንደ ኦሎምፒክ ውድድር ዝግጅቱን እንዳጠናቀቀ አትሌት ይመስላል። አትሌቲክስም ቢሆን የአካል ብቃትና በቂ ዝግጅትን ይጠይቃል።  ፖለቲካ ደግሞ ዘው ብለው ገብተው ታሪክ የሚሰሩበት በኦሎምፒክ የውድድር መድረክ አይደለም። እነ ሌንጮ እየነገሩን ያሉት አዲስ አበባ ገብተው በባላገሩ አይደል ላይ ለመወዳደር አይደለም። በባላገሩ የጫወታ ደንብ ጥሩ ስራ የሰራም፤ አስቀያሚ ስራ የሰራም ይሸለማል። ሌንጮ ታሪክ እንሰራለን የሚሉት “ስልጣን ወይንም ሞት!” የሚል መፈክር አንግቦ እስካፍንጫው የታጠቀ ሃይልን በመጋፈጥ ነው።
ታሪክን ለመስራት ብቃት ያላቸው ድርጅቶች በኢትዮጵያ የፖለቲካ መድረክ ጠፍተው አያውቁም። ከኦሮሞ ድርጅቶችም ቢሆን እነ ኦቦ ቡልቻ ደመቅሳ እና ፕ/ር መረራ ጉዲና አሉ።  የኦሮሞን ህዝብ አደራጅተው በምርጫም፣ በፓርላማም፣ በሰልፍም፣ በእርግማንም፣ በጸሎትና ምልጃም፣  በወረቀትም … ብዙ ተጉዘዋል። የእነዚህ ድርጅቶች አባላት እንደጥጃ እየተለቀሙ እስር ቤቱን ከማጨናነቃቸው በቀር ታሪክ ሲሰሩ አላየንም። አንድ እርምጃ ወደፊት፤ አስር እርምጃ ወደኋላ እየተጓዙ ሄደው…ሄደው በመጨረሻ ራሳቸውም ታሪክ ከመሆን አላለፉም። ይህ ለአቶ ሌንጮ ለታ እንግዳ ነገር አይደለም። አቶ ሌንጮ በኢትዮጵያ የፖለቲካ መድረክ በከባድ ሚዛን ደረጃ የሚመደቡ ናቸው።
በዛሬይቱ ኢትዮጵያ በፖለቲካ ታግሎ ታሪክ ከመስራት ይልቅ ነድጅ ቆፍሮ ታሪክ መስራት እንደሚቀል ለሌንጮም አዲስ ነገር አይደለም። እርግጥ ነው።  የታሪክ ትርጉም አሰጣጣችን ላይ እንለያይ ይሆናል። የገዥው ፓርቲ የታሪክ ትርጉምም ከልማት ጋር ይያያዛል። በዘመናችን ብዙ ታሪኮችን እየሰማን ነው። ልማታዊ አስተሳሰብ ያለው ሰው ሁሉ ዛሬ ታሪክ ሰሪ ይባላል። ታሪክ ሰርተው የሚሸለሙ የልማት አርበኞችን በቴሌቭዥን እናያለን።  በአነስተኛና ጥቃቅን እየተደራጁ የኮብል-ስቶን ድንጋይን እያናገሩ ያሉ ወጣት ምሁራንም በታሪክ መዝገብ ላይ እየሰፈሩ ይገኛል።
ኦቦ ሌንጮ ታሪክ የሚሉን እንዲህ አይነቱን ድራማ እንደማይሆን እርግጠኞች አይደለንም።  እኝህ የፖለቲካ መሪ ታሪክ መስራት ከነበረባቸው ግዜው አሁን አይደለም። በሽግግሩ ዘመን 20 ሺህ ጦር እና 20 መቀመጫ ይዘው በነበሩበት ጊዜ ለዚህ እድሉ ነበራቸው። ያንን እድል ይዘው ታሪክ ከመስራት ይልቅ ድርጅታቸው ጥቁር ነጥብ ጥሎ ነበር ያለፈው።  አቶ ሌንጮ ታሪክ መስራት ከነበረባቸው በሽግግሩ መንግስት የኢትዮጵያ መሪ ሆነው በተመረጡ ግዜ ነበር። በወቅቱ ምን ነበር ያሉት?  “በዚህ ላይ አልተዘጋጀሁበትም።” ሲሉ የእድሉን በር ራሳቸው ዘጉት። በርግጥ ያን ጊዜ ከኦሮሚያ የመገንጠል አዙሪት ውስጥ አልወጡም ነበር። ትልቅ ህዝብን ይዘናል እያሉ፤ የመገንጠል ጥያቄን ሲያነሱ በአለም ላይ የመጀመሪያዎቹ ብቻ አይደሉም። የኦሮሞን ህዝብ በፖለቲካ አናሳ ማድረጋቸው የታያቸውም ከ40 አመታት በኋላ መሆኑ ነው።  በዚያን ወቅት ኢትዮጵያን መምራት እንችላለን ለማለት በራስ መተማመን አልነበራቸውም።  አንድ ሰው አንድ ድምጽ በሚል መርህ ምርጫ አድርገው ከመጓዝ ይልቅ፤ እንደ አናሳ ጎሳ “መገንጠል አለብን” የሚል ያታሪክ ስህተት ውስጥ ነበሩ።
ከኦሮሞ ነጻ አውጭ ግንባር ወጥተው የኦሮሞ ዲሞክራቲክ ግንባርን መመስረታቸው ከታሪክ ተወቃጭሽነት ሊያድናቸው ይችላል ። ይህንን በማድረጋቸው የሰማይና የምድርን ያህል ርቆ የነበረውን የፖለቲካ መስመር ሊያጠበው እንደሚችል ግልጽ ነው። ዛሬ የመገንጠልን ጥያቄውን ውድቅ አድርገው ለዲሞክራሲና ለፍትህ መታገል መምረጣቸው ታሪክ ሰሪ ሊያደርጋቸው አይችልም። ይህ ሊሆን የሚችለው ለውጥ አምጥተው ፍትሃዊ ስርዓት ማስፈን ሲችሉ ብቻ ነው።
ሌንጮ ለታ አዲስ አበባ በመግባት ታሪክ እሰራለሁ ሲሉ ይህ የመጀመርያቸውም አይደለም። እ.ኤ.አ. 1993 የስራ ባልደረባቸውን ከከርቸሌ ለማስፈታት አዲስ አበባ ዘው ብለው ገብተው ነበር። እኝህ ሰው ሲገቡ ቦሌ ላይ ልዩ አቀባበል ተደረገላቸው። በብረት ተጠፍረውም ከርችሌ ተወረወሩ። በወቅቱ አዲስ አበባ ላይ ተካሂዶ በነበረው የግዮኑ የሰላም እና እርቅ ጉባዔ ላይ ለመሳተፍ ሲገቡ የታሰሩ ልኡካንን እዚያው ተቀላቀሉ።
ሌንጮ በዚያ ሰዓት ታሪክ ይሰራሉ ብለን ጠብቀን ነበር። ግን ይቅርታ ጠይቀው ከእስር ለመውጣት አንድ ሳምንትም አልፈጀባቸውም።  በወቅቱ ከአቶ ሌንጮ ለታ ጋር ረጅም ቃለ-መጠይቅ አድርጌ ይህንን ታሪክ በማሳትመው ጋዜጣ ላይ ለህዝብ ይፋ አድርጌዋለሁ። እርግጥ ነው። የሌንጮ ለታ ፖለቲካ እውቀት የሚደነቅ ነው። በፖለቲካ ብስለታቸውና ትንተናቸው ከማደንቃቸው የፖለቲካ ሰዎች አንዱ ናቸው።  ፖለቲካ ማወቅ እና ህዝብን መምራት ግን በጣም የተለያዩ ነገሮች ናቸው። ብዙውን ግዜ የሰዎችን የፖለቲካ ብቃት የምንለካው በንግግር ችሎታው ብቻ ነው። ጥሩ የፖለቲካ መሪ አስተዋይም መሆን አለበት። የመሪ አስተዋይ አለመሆን ደግሞ ችግር የመፍታት ብቃታ ማጣቱን ነው የሚያሳየን።  ኦነግ ከ40 አመታት በላይ በትግል ላይ እንደሆነ ይነገረን እንጂ ድርጅቱ ድል አድርጎ አይተን አናውቅም። የሽግግሩን መንግስት ላይም ቢሆን የተገኘው በድል አድራጊነት ሳይሆን ከህወሃት እና ከሻእቢያ ጥሪ ተደርጎለት ነበር።
በአሁኑ የአዲስ አበባ ጉዞ ሌንጮ እንደቀድሞው ልዩ አቀባበል ላይገጥማቸው ይችላል። በእርግጠኝነት ለመናገር ከጉዞው በፊት አንዳች ቅድመ ሁኔታዎች ወይንም ስምምነቶች ይኖራሉ።  ይህ ካልሆነ ግን እኝህን ሰው በቀይ መስመር ላይ ማስቆም ወይንም ደግሞ ማኖ ማስነካቱ አይቀሬ ነው። እሳቸውን ቀይ መስመር ላይ ለማቆስም በጣም ቀላል ነው። የበደኖው፣ የዋተሩና የአርባጉጉ ፋይሎች እየተመዘዙ ማውጣት ብቻ ይበቃል። አልያም ቦሌ ላይ እነ ዋልታ ብቅ ብለው በካሜራ ይቀበሏቸዋል። ልማቱን እንዲያደንቁ ይጠየቃሉ። በእስር ያሉ ወገኖችና “ሽብርተኞች”ን ማውገዛቸውም የግድ ነው። በዚህ መስመር ላይ ከሄዱ  ”አባ ጸበል ይርጩን” ብለው እንደገቡት እንደነ ስም አይጠሬ ተዋርደው ይመለሱና የፖለቲካ ሞትን ዳግም ይቀምሷታል።
ለእንደዚህ አይነቱ “ልማታዊ” የተቃውሞ አስተሳሰብ ሳይገዙ ታሪክ መስራት ከተቻለ ግን ተአምር ይሆናል።  ለማንኛውም መልካም ጉዞ…

Saturday, February 1, 2014

“ታሪክ ለባለ ታሪኩ”

Feb, 1, 2014
ገብረመድህን አርአያ፣ አውስትራሊያ
Ato Gebremedhin Araya is one of former Tigray People Liberation Front (TPLF) leaders
አቶ ገብረመድህን አርአያ የቀድሞ የሀወሀት ገንዘብ ያዥ
ኢትዮጵያ ሃገራችን ትልቁ እድሏ ከጥንት ዘመን ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ ብዙ የታሪክ ሊቃውንትና ጸሓፍት ያፈራች ሃገር መሆኗ ነው።
በጥንቱ ዘመን በኢትዮጵያ መቀመጫቸውን አክሱም ያደረጉት ነገሥታት ታሪካቸውን እና ጥበባቸውን በሳብኛና በግእዝ እያጻፉ አዘጋጀተዋል። በመቀጠልም መቀመጫቸውን ወደ ዛጔ፣ ላስታ ላሊበላ፣ ወሎ ሲተላለፍ በዚያ የነገሡ ነገሥታትም ታሪካቸውን እና ጥበባቸውን በግእዝና በአማርኛ እያዘጋጁ አልፈዋል። የነገሥታቱ መቀመጫ ከወሎ ወደ ሸዋ፤ ከዛም ወደ ጎንደር ሲሸጋገር፣ የነበረው ታሪክ፣ ጥበብና የነገሥታቱ ዝርዝር ሁኔታ ተዘጋጅተው ተመዝግበዋል።
የታሪክ ሊቃውንት የነጋሥታቱን ብርቱና ደካማ ጎኖቻቸውን እና የሰሩትን ታሪክና ገድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ በማሳወቅ፣ ሕዝቡም በተራው ያለፉት ነገሥታት የጣሉበትን የጀግንነት አደራ እንዲጠብቅ አድርጎታል። የኢትዮጵያን ሉአላዊነት፣ ዝና እና ክብር እንዲሁም ታሪክና የታሪክ ቅርሶቿ በክብር እንዲንከባከባቸው በሰጡት አደራ መሰረት ኢትዮጵያ ለማንም ቅኝ ገዢ ሳትንበረከክ በዓለም ደረጃ ዝነኛ ሆና የወጣች ሃገር እንድትሆን አድርገዋታል።
የታሪክ ሊቃውንት በ845 በኢትዮጵያ አክሱም ዘመነ መንግሥት በኢትዮጵያ ንጉሥ አንበሳ ውድም ልታወድም የተነሳችው ዮዲት ጉዲት ዙፋኑን ገልብጣ፣ አብያተ ክርስቲያናቱን በማቃጠል፣ ሃውልቶችን እያፈረሰች ታሪካዊ ቅርሶችን በማውደም፣ ክርስቲያኖችን በመጨፍጨፍ ብዙ ከባድ ግፎችን ፈጽማለች። ቀጥሎም በ1515 በአፄ ልብነ ድንግል ዘመን መንግሥት ግራኝ አህመድ የተባለ ጠላት ተነስቶ ብዙ አብያተ ክርስቲያናትን፣ ታሪካዊ ገዳማትን እና ታሪካዊ መዛግብትን ከማውደሙም በላይ፣ ክርስቲያኖችንም አንገታቸውን በሰይፍ እየቀላ ሕዝብ ጨርሷል። ታሪክ ጸሐፊዎችም በዮዲት ጉዲትና በግራኝ አህመድ የተፈጸመውን ግፍ በጥቁር ታሪክነቱ ከትበው ለትውልደ ኢትዮጵያውያን አስተላልፈዋል።
አሁን ባለንበት ዘመን ከሰሜን ኢትዮጵያ ትግራይ የመጣው ገዢ፣ ህዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) ኢትዮጵያን እና ሕዝቧን ከላይ ከተጠቀሱት የኢትዮጵያ ጠላቶች እጅግ በጣም ተወዳዳሪ የማይገኝለት፣ በክፉ መልኩ ኢትዮጵያን እና ሕዝቧን ያወደመ፣ የሃገር ሉአላዊነትን ያፈረሰ፣ ሃገር የሸጠ፣ ወጣት ሴቶችን እና ወንዶችን ለባርነትና ለስደት የዳረገ ነው። ከየት መጣ ሳይባል ኢትዮጵያን በቅኝ ግዛት በመቆጣጠር ሃገር በማፍረስ፣ ሕዝብን ከተወለደበት በማፈናቀል የሚፈጽመውን ፋሽስታዊ ተግባራቱን የታሪክ ጸሐፊዎችና የኢኮኖሚ ሊቃውንት ኢትዮጵያውያን እየጻፉት ነው።
በህዳር 2006 መጨረሻ አስደንጋጭ ዜና በዓለም ሚዲያዎች ተነገረ። የደቡብ አፍሪካው የነፃነት አባት ኔልሰን ማንዴላ ከዚች ዓለም በሞት እንደተለየ ተገለጸ። የዓለም ሕዝብና መሪዎቹ የተሰማቸውን ጥልቅ ሃዘን በማስተላለፍ የኔልሰን ማንዴላን አንጸባራቂ ታሪክና ኤ.ኤን.ሲን በመምራት የከፈሉትን መስዋእትነት፣ በተካሄደው መራራ ትግል ደቡብ አፍሪካን ከአፓርታይድ ስርዓት አላቀው ሃገሪቷን እና ሕዝቧን ነፃ ምውጣታቸውን፣ እስከ ግባተ መሬታቸው ድረስ በትግል የፈጸሙትን አኩሪ ታሪካቸውን እና ገድላቸውን ካለምንም ማቋረጥ በዓለም ዙሪያ ነግሮላቸዋል፣ የሰላምና የእርቅ አባትም ተብለዋል።
በቀብራቸው እለትም ከ100 በላይ የዓለም መሪዎች ደቡብ አፍሪካ ድረስ በመጓዝ ለመጀመሪያ ጊዜ በዓለም ያልታየ እጅግ የደመቀ የቀብር ስነስርዓት ተፈጽሞላቸዋል። የዚህ ሁሉ ድምር ውጤት ማንዴላ የፈጸሙት የትግል ድልና ታሪክ ነው። ስለሆነም ታሪክ ለባለ ታሪኩ እንደሆነና እንደሚገባ በኔልሰን ማንዴላ ታይቷል። ጥቁር ታሪክ የተሸከመው ወያኔ ህወሓት ደግሞ ከትወልድ ወደ ትውልድ እየተላለፈ፣ እየተረገመና እየተወገዘ ልክ እንደ ዮዲት ጉዲት በሳጥናኤል ምስል እየታወሰ ይኖራል።
የኔልሰን ማንዴላን ህልፈት ተከትሎ የዓለም መሪዎች የተሰማቸውን ሃዘን ሲገልጹ፣ የዓለም ብዙሃን መገናኛዎችም ለሶስት ሳማንታት የቆየ ሰፊ ሽፋን ሰጥተውታል። በዚህም የተነሳ ለህወሓት አመራርና ካድሬዎቹ፣ እንዲሁም የፋሽስቱ ስርዓት መሳሪያ በመሆን የሚያገለግሉት ብአዴን፣ ኦህዴድ፣ ደቡብ ህዝቦች ተብለው በሚታወቁት የገዢው አጎብዳጆች ላይ የራስ ምታት ለቆባቸው ሰንብቷል። ምክንያቱም የህወሓት መሪ ከዚህ ዓለም በሞት ሲቀጠፍ ማንም የዓለም መሪም ሆነ ሕዝብ ከግምት ውስጥ ስለአላስገባው። ሚዲያውን በተመለከተ አልጀዚራና ቢቢሲ ከ2 ደቂቃ ባነሰ ጊዜ መለስ ዜናዊ የኢትዮጵያው አምባገነን መሪ ሞተ ብለው ከመናገር የዘለለ ምንም አልጨመሩም።
በ24/12/2013 በአይጋ ፎረም ርእሰ አንቀጽ “ማንዴላን በማሳበጥ የመለስ ራእይ አይሟሽሽም”!! በሚል ርእስ ስር የተጻፈውን አንኳር አንኳሩን ልዳስስ፤
ከመነሻው ጀምሮ ኔልሰን ማንዴላን በመጥፎ ስምና ተግባር እያብጠለጠለ የመለስ ራይእይን እና ጀግንነት፤ ሀገር ወዳድነት ወዘተ. እያለ ሙግስናውን ይቀጥላል፤
- ጀግናው መለስ ዜናዊ ጦርነት ሳይንስ እንጂ በእድል የሚገኝ አይደለም ብሎ የተነተነ ምሁር ሲሆን፣ ፋሽስት በሆነው ደርግ ላይ ያረጋገጠ ጀግናና የብዙ ጀግኖች ፈጣሪ ነው ይላል፤
በመሰረቱ የዚህ ርእሰ አንቀጽ ጸሐፊ የመለስ ዜናዊን ማንነት የማያውቅ፣ ለጥቅሙ ብሎ በአየር ላይ የሚንሳፈፍ ፊኛ ፍጡር ነው። መለስ ዜናዊ ከተሓህት/ህወሓት ለትግል ከተደባለቀበት ጊዜ አንስቶ በጦርነት ተሳተፍ ተብሎ በግዴታ በተሰለፈባቸው ጦርነቶች ገና የመጀመሪያዋ ጥይት ስትተኮስ ፈርቶ የሸሸ ለመሆኑ በጊዜው የነበሩ የተሓህት ታጋዮች በሚገባ እናውቃለን። በተሓህት ህግና ስነሥርአት መሰረት ከጦርነት ያፈገፈገ ሞት ይፈረድበታል። መለስ ዜናዊ በአደዋ፣ ፈረሰማይ፣ አዲደእሮ፣ ማይቅንጣል፣ ሃገረሰላም፣ አዲ-ኮኸብ፣ ገለበዳ ወዘተ. በተደረጉት ጦርነቶች ፈርቶ የሸሸና ያፈገፈገ ግለሰብ ነው። ለምን እንደሌሎቹ አፈገፈጋችሁ ተብለው እንደተገደሉት መለስ ዜናዊ ስላልተገደለበት ምክንያት በቀዳሚነት የሚጠየቅበትና መልስ የሚሰጠው አረጋዊ በርሄ ነው። ጀግኖች የፈጠረ ማለት ቀልድና ቧልት ነው። ሌቦችን እና ዘራፊዎችን የፈጠረና ራሱም ቀንደኛ ዘራፊ የሆነ ሰው ጀግኖች ሊፈጥር አይችልም። መለስ ዜናዊ ምንም የጦርነት ሳይንስም ሆነ ወታደራዊ ጥበብ የለውም።
- የባለ ራእይነትና አርባኝነት ትልቁ ዓላማው ኢትዮጵያን በአጭር ጊዜ ከበለጽጉት ሃገሮች ጋር እንድትቀላቀል ማድረግ ነው። የትራንስፎርሜሽን እቅዱም የዚሁ ራእይ አካል ነው ይላል። ቀጠል በማድረግም፣ የታላቁ መሪ ራእይ ስኬታማ እየሆኑ መምጣታቸውን እየተመለከትን ነው። የኢትዮጵያን ሕዝብ ከጭቆና በማላቀቅ የኢኮኖሚ ባለቤትነቱን ያረጋገጠ ጀግና ነው ብሎም ያትታል።
ባለርእሰ አንቀጹ ይህን ሲጽፍ ከጠባብ አስተሳሰብ በመነሳት ነው። ህወሓት ኢትዮጵያን በቅኝ ግዛት ከተቆጣጠረበት ከግንቦት 1983 እስከ አሁን ድረስ በሃገሪቱና በሕዝቧ የወረደው ፋሽስታዊ አገዛዝ ረሃብ፣ በሽታ፣ እንክርት፣ መፈናቀል፣ እስራት፣ የሃገር መሬትና ድነበር ለባእዳን መሸጥ፣ ሰቆቃ፣ አፍኖ ማጥፋት ወዘተ. እየተፈጸሙ ያሉት የመለስ ዜናዊ ራእይና የህወሓት አመራሮች እቅድ መሆኑን ማወቅና መገንዘብ መቻል ያለበት ይመስለኛል። በመሰረቱ የርእሰ አንቀጹ ጸሐፊ ህወሓት ማነው? ሲፈጥርስ ዲሞክራሲያዊ ድርጅት ሆኖ የተፈጠረ ነው ወይ? የሕዝብ ፍቅርና ስሜት መስፈርቱ ነበር ወይ? በኢትዮጵያ ሉአላዊነት ያምን ነበር ወይ? የሚሉትን ጥያቄዎች ያላገናዘበ ከጠባብ ዘርኝነት ስሜት የመነጨ ነው። ውሸት በመደርደር መለስንም ሆነ የህወሓት አመራርን ለልማት የቆሙ አስመስሎ መጻፍ የጸሐፊው አባላት ሳይቀሩ ይታዘቡታል፣ ይንቁታል። ለምን ቢባል፣ ጸረ-ሕዝብና ጸረ-ሃገር የሆነውን የህወሓትን ጥቁር ታሪክ በወርቃማ ቀለም መለወጥ አይቻልምና። ኢትዮጵያን ለማፍረስ ትልእኮው አድርጎ የተነሳ ድርጅት ነው። ከላይ የተጠቀሱትን ኢትዮጵያን ወሮ ከተቆጣጠረ ጀምሮ በተግባር ታይተዋል። ስለሆነም የመለስ ራእይ ለእድገትና ትራንስፎርሜሽን የሚበጅ ሊሆን አይችለም። የመለስና ግብረአበሮቹ ባህሪና የፖሊሲ አቋመቸው ጸረ-ዲሞክራሲ፣ ጸረ-ሃገርና ሕዝብ ነው። በቅጽበት ተለውጠው ለሕዝብና ለሃገር ተቆርቋሪ ሊሆኑ አይችሉም። ዲሞክራሲ ገና ከጅምሩ አንድ ድርጅት ሲፈጠር መሰረታዊ የዲሞክራሲ መሰሶዎች አበጅቶ የሚዳሰስ፣ የሚታይ ጠንካራ የህንጻ ብረት መሳሪያ መሰረቱን የጣለ ከሆነ ነው። ህወሓት ግን ከዚህ ያፈነገጠ ጠባብና ዘረኛ ፋሽስት ድርጅት የዲሞክራሲ መድረኩ አይፈቅድለትም። ስለዚህ፣ የኢኮኖሚ ባለቤትነትን ያረጋገጠ የመለስ ዜናዊ የጀግንነት መግለጫ ነው የሚለው አባባል ከእውነት የራቀ የጠባብ ዘረኝነት አስተሳሰብ ነው። ውሃ የማይቋጥር ቀዳዳ ጣሳ እንበለው።
- መለስ ዜናዊ ከድህነት በላይ አዋራጅ ከድህነት በላይ ክፉ ጠላት የለም የሚለው ራእይ በወሰደው ቆራጥ አመራር የከተማና የገጠር ልማት ፖሊሲዎችና የአፈጻጸም ስልቶች የመለስን የልማት አርበኝነትና ጀግንነት በትክክል የሚያሳይና የሚያርጋግጡ ናቸው ይላል።
የመለስ ዜናዊ የልማት፣ የእድገት አርበኝነት እያሉ በየቀኑ ሕዝብን የሚያደነቁሩ የህወሓት ካድሬዎች ብአዴን፣ ኦህዴድ፣ ደቡብ ህዝቦች ናቸው። ህወሓት የፈጠራቸው ቅጥረኛ ድርጅቶች ሃገር እያፈረሱ፣ ሕዝብን እየጨፈጨፉ ሲሆን፣ መሪያቸው የህወሓት አመራር ድህነትን የተዋጋ፣ ሰፊ የልማት አውታር በመዘርጋት ኢትዮጵያን የለወጠ ብሎ መናገር ከሃዲነት ነው። ወያኔ ህወሓት በ1983 ሃገር ወሮ በቅኝ ግዘቱ ስር ባደረጋት ማግስት የኢትዮጵያ ሁኔታ ሙሉ በሙሉ ተለዋወጠ። ሕዝቡ በርካሽ እየገዛ የሚጠቀምባቸው የምግብ አይነቶች ጤፍ፣ ስንዴ፣ ቅቤ፣ ሥጋ ወዘተ. ዋጋ የሰማይ ጣራ ነካ። እስከ ደርግ ዘመን ፍጻሜ ድረስ ጤፍ በኩንታል ብር 45-60 ይሸጥ ነበር። ቅቤ፣ ዘይት፣ ስጋ ወዘተ. በተመጣጣኝ ዋጋ ይገበይ ነበር። በወያኔ ህወሓት አገዛዝ ቅቤ፣ ዘይት ወዘተ. ከገበያ ጠፍቷል። ጤፍ በኩንታል ብር 1500-1800 ደርሷል። ከአፄ ኃ/ሥላሴ እስከ ደርግ ዘመን ማንኛውም ኢትዮጵያዊ በቀን ሶስት ጊዜ መብላት ይችል ነበር። በአሁኑ ስርዓት ግን በቀን አንድ ጊዜ ለመብላት የሚታገለው ሕዝብ ቁጥሩ በርካታ ሆኗል። የኢትዮጵያ ሕዝብ በታሪክ አይቶት ለማያውቀው ድህነት ከተዳረገ 23 ዓመት አስቆጥሯል። መራሹ ገዢ ህወሓት የኢትዮጵያን ሕዝብ ለከፋ ረሃብ፣ በሽታና ስደት ዳርጓል። “እንኳንስ ዘንቦብሽ ዱሮውንም ጤዛ ነሽ” እንደሚባለው፣ ከትግሉ መነሻ ጀምሮ እስከ መጨረሻው ወያኔ ህወሓት ለኢትዮጵያና ህዝቧ ጠላት ሆኖ የተፈጠረ ድርጅት ነው። ከ1967 ጀምሮ ሕዝቧን በጎሳና በዘር ከፋፍዬ አጠፋታለሁ ብሎ የተነሳ ድርጅት ነው። ይህንን ከመጠን ያለፈ ጥላቻ ከትግሉ መነሻ ጀምሮ ሲያራምደው የመጣና ዛሬ በተግባር እያሳየው ነው። ምክንያቱ፣ ህወሓት ኢትዮጵያዊ አይደለምና።
የህወሓት ካድሬዎችና ደጋፊዎች የምትናገሩትና የምትጽፉት ገደብ የለሽ ውሸት፣ በሙስና እና በዝርፊያ ባገኛችሁት ንብረት ከነቤተሰባችሁ እየተንደላቀቃችሁ ጠግባችሁ ብታድሩም፣ ለኢትዮጵያ ሕዝብ የምትነግሩትና የምትጎስሙትን የውሸት ነጋሪት ውድቅ ካደረገው ዓመታት አልፈዋል። ህወሓት፣ ብአዴን፣ ኦህዴድ፣ ደቡብ ህዝቦች በሕዝብ ፊት ቀርባችሁ ፍርዳችሁን የምታገኙበት ጊዜ ተቃርባለች።
ህወሓት ኢትዮጵያን ሲቆጣጠር ተሸክሞት የመጣውን በቀል አማራው፣ ኦሮሞው፣ ጋምቤላው፣ አፋሩ፣ ኦጋዴኑ ወዘተ. ዘር የማጥፋት ተግባሩን ፈጽሞታል። አሁንም እያጠፋ፣ እየገደለ በየወህኒ ቤቶቹ እየማገደው ነው። ይዞት የመጣው ድህነትና በሽታን ብቻ ነው። ፖሊሲው የኢትዮጵያን ሕዝብ ከዓለም ሃገሮች በድህነት ከወለል በታች ያደረገ ስርዓት ነው። የኢትዮጵያ ገበሬ የመሬቱ ባለቤት በነበረበት ወቅት እራሱን እና ቤተሰቡን አብልቶ ቀሪውን ለገበያ በማቅረብ ሕዝቧ እንደአቅሙ በልቶና ጠጥቶ ያድር ነበር። የህወሓት አስተዳደር መሬት የመንግሥት ነው ብሎ በማወጁ የኢትዮጵያ ሕዝብ በገጠሩም በከተማም መሬት አልባ ሆኗል። የኢትዮጵያ ሕዝብ በገዛ ሃገሩ ሁለተኛ ዜጋ ከመሆኑ የተነሳ ሲሞት እንኳን የሚቀበርበት ቦታ ያጣ ሕዝብ ሆኗል። የመለስ ራእይ እድገትና ልማት ነው ተብሎ የተጻፈው፣ የኢትዮጵያ ሕዝብ በዚህ ሁኔታ ይቀጥላል የሚል አመለካከት ካለው ፈጽሞ ተሳስቷል። የኢትዮጵያ ሕዝብ ለገዢው ስርዓት መቃብር ቆፍሮ እየጠበቃቸው ነው። የሚተርፋቸው ጥቁር ታሪካቸው ከትውልድ ትውልድ መተለለፉ ብቻ ይሆናል።
ይህንን በዚሁ ላብቃ። በሌላ መልኩ ደግሞ መልስ ልስጥህ። “ማንዴላን በማሳበጥ የመለስ ዜናዊ ራእይ አይሟሽሽም” ያልከው ጸሐፊ ይህንን አንብብ።
ለመለስ ዜናዊ ከድህነት በላይ ክፉ ጠላት የለውም ብሎ መጻፉ ትክክል ነው፣ እስማማበታለሁ። መለስ ዜናዊ የድሃ ቤተስብ ልጅ መሆኑ እንዳይታወቅበት ብዙ ጊዜ ሲከላከል እንደነበር የምናውቀ ሃቅ ነው። መለስ ዜናዊ የሹምባሽ አስረስ ተሰማ የልጅ ልጅ ነው። የሴት አያቱም ወ/ሮ ዘውዲቱ መንገሻ ይባላሉ። አድዋ አውራጃ የተወለደው አስረስ ተሰማ ደግሞ ኤርትራዊ ሲሆን፣ መለስ ዜናዊ በትግራይ ያለው ትውልድ በሴት አያቱ ብቻ ነው። ወራሪው ጣልያን ለሁለተኛ ጊዜ በአፄ ኃ/ሥላሴ ዘመነ መንግሥት በተሸነፈበት ጊዜ የጣልያን ባንዳው ሹምባሽ አስረስ ተሰማ በግዞት አድዋ ውስጥ ነበር። በ6 ወራት ጣልያን ሙሉ በሙሉ ተሸንፎ ኢትዮጵያ ነጻነቷን ስትቀዳጅ አስራስ ተሰማ በደረሰበት ድንጋጤ ታሞ ሞተ። ዜናዊ አስረስም ከአድዋ ከተማ ወደ ኤርትራ አልተመለሰም። ቀደም ብሎ በጣሊያን ጊዜ ያገባቺው ሚስቱም አንዴ አድዋ፣ ሌላ ጊዜ ደግሞ አዲኳላ እየተመላለሱ ኖረዋል። ዜናዊ አስረስ ከወ/ሮ አለማሽ ወ/ልኡል መለስ ዜናዊን ጨምሮ 5 ልጆች ወልደዋል። ሌሎች ሁለት ኤርትራውያን ሴቶች ስለነበሩት በጠቅላላው 13 ልጆች አሉት። ዜናዊ አስረስ ጣልያንኛ በመጠኑ ይናገራል፣ ግን አይጽፍም። ዜናዊ አስረስ ሥራ ያልነበረው ድሃ ስለነበር ማመልከቻ ጸሐፊ በመሆን ኑሮውን ይገፋ ነበር። በኤርትራዊነቱ ስለሚታወቅ በአድዋ አውራጃ ውስጥ የእርሻ መሬት አልነበረውም። አባቱ ሹምባሽ አስረስ ተሰማ በሕዝብ ላይ ብዙ ግፍ የፈጸመና በጣሊያን ባንደነቱ የተነሳ አድዋ ውስጥ በጣም የተጠላና የተገለለ ነበር። ይህንን ሁሉም የአድዋ ሰው የሚያውቀው ሃቅ ነው። ድህነት የሚያሳፍርና የሚያሸማቅቅ አይደለም። የዚህ ጽሑፍ አቅራቢ የድሃ ልጅ ነኝ፣ ስለሆነም አላፍርበትም። በድህነቴ እኮራለሁ እንጂ የሌለኝን አለኝ ብዬ አልመጻደቅም።
መለስ ዜናዊ ግን ይህን አይቀበልም፣ ቤተሰቦቹም ይህን አይቀበሉም። ወንድሞቹ በክፉ ድህነት ያደጉ፣ እህቶቹ እነ ገርግስ ዜናዊ በአሁኑ ጊዜ ሚሊየነር ብትሆንም እንጀራ እየሸጠች ያደገች፣ ኒቆዲሞስ ዜናዊም እንቁላል እየቀቀለና እንጀራ በየጠላ ቤቱ ማታ ማታ እየሸጠ ያደገ ነው። ይህ ሁሉም ሥራ ነው፣ የሚያስከብር እንጂ የሚያሳፈር አይደለም። ዜናዊ አስረስ በአፄ ኃ/ሥላሴ ዘመን የአድዋ አውራጃ ገዢ ነበር ብሎ ዋሸ። የተናገረውን ሁሉ ረስቶ ለሞቱ በተቃረበ ጊዜ አፄ ኃ/ሥላሴ አዲስ አበባ ድረስ አስጠርተው የአባትህን ሥራ ልስጥህ፣ በአታሼ ድረጃ ሥራ ልመድብህ ሲሉኝ አልቀበልም አልኩ በማለት ተናግሯል። የወላጅ አባቴን ሃብትና ንብረት ጠብቄ ለልጆቼ አወርሳለሁ ብዬ ወደ አድዋ ተመልስኩ ብሎ የተናግረውን በድረ ገጾች አይቸዋልሁ። ይህ ሁሉ ደረቅ ውሸት ነው። የሚኖረው ተወልደን ባደግንበት አድዋ ከተማ ነው። እስከምናውቅ ድረስ ምንም አይነት ሃብት የሌለው፣ በማመልከቻ ጸሐፊነት የሚተዳደር ደሃ መሆኑን የወቅቱ የአድዋ ከተማ ሕዝብ ያውቀዋል። መለስም ሥልጣን እንደጨበጠ የደሃ ልጅ እንዳይባል በተክለ ሰውነቱ እንዳትጠጋው አደረጋት። ድህነት አያሳፍርም። በዚህ ዓለም አሳፋሪ ነገር ውሸት፣ ዝርፊያ፣ ሙስና፤ የንጹሃን ደም ማፈሰስ፣ ባጠቃላይ ወንጀል ናቸው። መለስ ዜናዊ የዚህ ሁሉ ቀንደኛ ተዋናይ ነው።
አንድ እውነተኛ ታሪክ ላቅርብ። የታሪኩ ባለቤት የአድዋ ሰው ሲሆኑ አሁን ግን አልፈዋል። ታሪኩን በጊዜው የነበሩ የአድዋ ከተማ ኗሪ የሚያውቁት ትክክለኛ የታሪክ ሃቅ ነው። አባቶቻችን ለኛ ለልጆቻቸው ነግረውና አስተምረው አልፈዋል።
አስረስ ተሰማ የታወቀ የጣሊያን ባንዳ ነበር። ጣሊያን ኢትዮጵያን እንደወረረ አስረስ ተሰማ የጣሊያኖች ታማኝ አሽከር ነበር። በጣሊያኖች የተሰጠው ማእረግ መጀመሪያ ኮማንዳቶሪ ሲሆን፣ ቀጥሎም ካባሌሪ ሆነ። ትንሽ እንደቆየም ሹምባሽ አስረስ ተብሎ ይጠራ ነበር። በአድዋ፣ አዲግራትና አክሱም በርካታ ግፎችን ፈጽሟል። ግለሰቦችን ሁለት እግራቸውን፤ እጆቻቸውን እና ጆሯቸውን በመቁረጥ እስከግድያ በሚደርስ ድርጊት አስቃይቷል። በገበያ ቀን ኢትዮጵያውያንን ሰላይ እያለ ሴት ከወንድ ሳይለይ ለገበያ በወጣው ሕዝብ ፊት አርባ አርባ ጅራፍ በመግረፍ ስፍር ቁጥር በሌለው ሕዝብ ላይ ስቃይ አድርሷል። በዚህ መጥፎ ተግባሩ የታወቀው ሹምባሽ አስረስ ተሰማ ለዓመታት በዚህ አይነት ሲቀጥል፣ የሕዝቡ አቤቱታ ለራስ ስዩም መንገሻ ይደርስ ነበር። ጣልያን ውድቀቱ በተቃረበበት ወቅት፣ ራስ ሥዩም ደጃዝማች ገ/ህይወት መሸሻን ይህንን ሰው እንደምንም ብለህ ይዘህ አምጣልኝ የሚል ትእዛዝ ሰጥተዋቸው ነበር። ደጃዝማቹ አካባቢውን ስለሚያውቁት በሶስት ሳምንት ክትትል አዲኳላ በምትገኘው ማይጫአት፣ ልዩ ስሟ አዲአዝማቲ ከምትባል ቦታ በሌሊት ተከታትለው ሹምባሽ አስረስ ተሰማን ከልጃቸው ዜናዊ አስረስ ጋር ማርከው ያዟቸው። በሌሊት ወደ አድዋ አሸጋግረው ለፊታውራሪ ገ/አምላክ ከነልጁ በግዞት እንዲቆይና ለፍርድ እንዲቀርብ አደረጉ። ፊታውራሪ ገ/አምላክ ማለት የወያኔ ህወሓት መሪ የነበረው በ1993 ከነስየ አብርሃ ጋር የተባረረው የአለምሰገድ ገ/አምላክ ወላጅ አባት ናቸው። አስረስ ተሰማ ለጥቂት ወራት በግዞት ላይ እንዳለ ኢትዮጵያ ጣልያንን አሸንፋ ነጻነቷን ተቀዳጀች። አስረስ ተሳማና ዜናዊ አስረስን የራስ ሥዩም አሽከሮች ይኖሩበት ወደነበረው አድዋ እንዳሥላሴ አዘዋወሯቸው። የጣልያንን ሽንፈት በሰማ ጊዜ ታሞ ከትንሽ ጊዜ በኋላ ሞተ። ሹምባሽ አስረስ በሞተ ጊዜ የሚቀበርበት ቦታ ታጥቶለት ነበር። ጥቂት የሆኑት ቀባሪዎቹ እንዳሥላሴ ቤተ ክርስቲያን በመሄድ በቦታው እንዲቀበር ቢማጸኑም፣ ንብሰ ገዳይና የጣልያን አሽከር በቤተ ክርስቲያናችን አናስቀብርም ብለው ከለከሉ። አስረስ ተሰማ ከቆየባት ቤቱ በግመት 300 ሜትር ርቀት ላይ በምትገኘው እንዳጽዮን ቤተ ክርስቲያን ሂደው ሲጠይቁ፣ ለምን እንዳሥላሴ አትቀብሩትም፣ የቤተ ክርስቲያኑ አለቃ አስረስ ተሰማ በዚች ቅድስት ማርያም ቦታ፣ ገዳይና ከሃዲ የጣልያን አሽከር አናስቀብርም የሚል መልስ ሰጥተው አሰናበቷቸው። በቀሪዎቹ ቤተ ክርስቲያናት እንደ እንዳ መድሃኔዓለም፣ እንዳ ገብርኤል፣ እንዳ ሚካኤል ፈጽሞ የማይታሰብ ሆነ። ያላቸው አማራጭ በረሃ ውስጥ ጉድጓድ ቆፍረው ምቅበር ብቻ ነበር። ማይ ምድማር ውሰዱ ተባሉ። ይህ ቦታ ደግሞ የወንድሞቻችን እስላሞች መካነ መቃብር ነው። በአጥር የተከለለ በጣም ሰፊ ሜዳ ነው። ቦታው በክብር የሚጠበቅ ስለሆነ ማንም ዝር አይልበትም። ስለሆነም እዛም አልተቻለም። እንደ አማራጭ ብለው ያሰቡት ማይ ምድማርን ተሻግሮ በሚገኝ ቦታ ላይ ሆነ። ማይ ምድማር ማለት፣ ከሰሜን በኩል ማይጓጓ ወንዝ፤ በፀሃይ መውጫ በኩል አሰብ ወንዝ የአድዋን ከተማ ለሁለት ሰንጥቆ የሚያልፍ ሲሆን፣ ሁለቱ የሚገናኙበት ቦታ ማይምድማር ተብሎ ይጠራል። አንዳንድ ጊዜም ጉራንጉር ተብሎ ይጠራል። ከማይምድማር ተሻግሮ የሚገኘው ቦታ ደግሞ የእንዳ ጊዮርጊስ መሬት ነው። ብዙ የመስኖ እርሻ ስላለበት ቀባሪዎቹ እዚያ ማድረግ እንደማይችሉ ስለተገነዘቡ፣ ሬሳውን ተሸክመው ወደ ተምቤን በሚያቀና መንገድ ተጉዘው አንድ በማይታወቅ ቦታ ቀበሩት። ከቀባሪዎቹ ከማስታውሳቸው መካከል አቶ ግብረቱ፣ አቶ ገብሩ፤ ልጃቸው ዜናዊ አስረስ ሲሆኑ ቀሪዎቹን ማስታውስ አልቻልኩም። የሹምባሽ አስረስ ተሰማ ሬሳ በረሃ እንደተጣለ አባቶቻን ነግረውናል። ይህንንም በወቅቱ የነበረው የአድዋ ሕዝብ በግልጽ የሚያውቀው ነው። ዜናዊ አስረስ ከሕዝብ የተገለለ፣ ልጆቹም ከሰው ተገልለው ማደጋቸው ሁሉም የሚያውቀው ሃቅ ነው።
መለስ ዜናዊ በቤልጂየም ሆስፒታል መሞቱን ለኢትዮጵያ ሕዝብ ያበሰረው ኢሳት ነበር። ሕይወቱ ያለፈችው ከብዙ ስቃይ ብኋላ ነው። ነብስ ይማር ያለው ኢትዮጵያዊ አልነበረም፣ እሰይ አምላክ ፍርድህን ሰጠህ ከማለት በስተቀር። ሬሳው ኢትዮጵያ ውስጥ ይቀበር አይቀበር አይታወቅም። የአያቱ ሹምባሽ አስረስ ተሰማ ሬሳ የገጠመው አይነት እድል እንደገጠመው እገምታለሁ። የማይቀረው ጊዜ ሲደርስ ስላሴ የተቀበረው ባዶ ሳጥን የአያቱን አይነት እድል እንዲሚያገኝ አልጠራጠርም። መለስ ዜናዊና ግብረ አበሮቹ ኢትዮጵያን ሲቆጣጠሩ በእናቱም በአባቱም የደጃዝማች ልጅ ነው ብለው በድረ ገጽ ተጽፎ አንብቤአለሁ። ከላይ እንደዘረዘርኩት ከእውነት የራቀ ነው። ባንዳዎቹ ኢትዮጵያ ወደ ነፃነቷ እያመራች በነበረችበት ጊዜ አስመራ ለነበረው ጄነራል ደቦኖ አቤቱታ አቅርበው ነበር። የኢትዮጵያ መንግሥት ለራሱ ሰዎች ራስ፣ ደጃዝማች፣ ፊታውራሪ ወዘተ. እያለ ማእረግ ሰጥቷቸዋል። እኛ የጣሊያን አሽከሮች ግን ምንም አይነት ማእረግ አልተሰጠንም። እኛም ልክ እንደ ኢትዮጵያውያኖቹ አይነት ማእረግ እንዲሰጠን እንፈልጋለን ብለው አቤት ብለው ነበር። አቤቱታቸውን ግራዚያኒ ወደ ሮም መንግሥት በማስተላለፍ ሹመቱን እንዲሰጥ ተፈቀደለት። በዚያም መሰረት የጣሊያኑ ባለሥልጣን ለባንዳዎቹ ደጃዝማች፣ ፊታውራሪ ወዘተ. እያለ አምበሸበሻቸው። ለአጭር ጊዜም ቢሆን፣ የዚህ ተጠቃሚ የሆኑት፣ የዜናዊ አስረስ ባለቤት የነበረች አለማሽ ገ/ልኡል፣ አባቷ ደጃዝማች ገ/ልኡል ሲሆኑ፣ ሹምባሽ አስረስም ደጃዝማችነት ተችሮት ነበር። ይሁንና ሳይጠራበት በኢትዮጵያ ጀግኖች ተይዞ ግዞት ገባ። ሌላው የዚህ ተጠቃሚ የነበሩት የስብሃት ነጋ አባት ፍታውራሪ ነጋ ነበሩ። ማእረጉን ባገኙ በጥቂት ወራት ጣልያን ተሸንፎ ሲወጣ፣ እስከ እለተ ሞታቸው ድረስ የአድዋ ሕዝብ በጣልያን የተሰጠውን ፊታውራሪነት አልተቀበለላቸውም። አብዛኛው ኗሪ አቶ ነጋ ሲላቸው፣ ጥቂት የቅርብ ጓደኞቻቸውና ዘመዶቻቸው በጣልያኑ ሹመት ፊታውራሪ ነጋ እያሉ ሲጠሯቸው አውቃለሁ።

ይድረስ ለህወሓት አመራር አባላት፣ ለብአዴን እና የደቡብ ኢትዮጵያ ብሔር ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች ዲሞክራሲይዊ ንቅናቄ

የደቡብ አፍሪካው መሪ ኔልሰን ማንዴላ በሞቱ ጊዜ የዓለም ሕዝብና መሪዎቻቸው መራራ ሃዘናቸውን ገልጸዋል። የዓለም ብዙሃን መገናኛዎችም ሶስት ሳምንታት ሙሉ የኔልሰን ማንዴላን አርበኝነት፣ የንፃነት መሪነታቸውን፣ የሰላምና የፍቅር አባትነታቸውን እና አንጸባራቂ ታሪካቸውን በስፋት ዘግበዋል። ይህ ነው እንግዲህ ታሪክ ለሰሪው፣ ታሪክ ለባለታሪኩ የሚባለው።
መለስ በሞተበት ጊዜ ሕዝብ በቀበሌ ተገዶና ብር 100 የውሎ አበል እየተሰጠው ነው ለቀብር የወጣው። ከዓለም መሪዎች መካከል የተገኙትም ጥቂቶች ናቸው። አብዛኛዎቹም ከነአካቴው የሃዘን መግለጫ እንኳን አልላኩም። ሚዲያውም ቢሆን፣ በጣም ጥቂቶቹ፣ አምባገነኑ መሪ መለስ ዜናዊ ሞተ ብለው ከመዘብ ያለፈ አላደረጉም። የኢትዮጵያ ገዢው መደብ ግን በዚህ ተናዷል። በዚህ የተነሳ፣ “ማንዴላን በማሳበጥ የመለስ ራእይ አይሟሽሽም” ብለው ጽፈዋል። እናንተ በየጊዜው የነበራችሁ የህወሓት አመራር አብሎችና አባላት ሆይ፣ መሪዎቻችሁ የፈጸሙት ግፍና ግድያ ለናንተ ደስታ ይሰጣችኋል። በትግልና በአመራር ዘመናቸው ዘርፈዋል፣ በሙስና ተጨማልቀዋል፣ የኢትዮጵያን ሕዝብ ለስደት፣ ለረሃብና ለሰቆቃ ዳርገዋል። እናንተም የዚህ ሁሉ ግፍ ተሳታፊዎች ናችሁ። ድርጊታችሁና ታሪካችሁ በደም የተጨማለቀ መሆኑን ዘንግታችሁ መለስ ዜናዊን ከኔልሰን ማንዴላ ጋር ማወዳደራችሁ በጣም አሳፋሪ ነው። በሁለቱ መካከል ያለው ልዩነት የሰማይና የምድርን ያክል ነው። ባለፉት ጽሑፎቼ እንደገለጽኩት፣ አጠር ባለ መልኩ፣ ሕወሓት ኢትዮጵያን ተቆጣጥሮ ያለ ድርጅት ነው። ስርዓቱም ፋሽስት፣ አምባገነን፣ ጠባብ ዘረኛ፣ ሽብርተኛ፣ ጸረ-ኢትዮጵያ ሉዓላዊነት፣ ጸረ-ኢትዮጵያ ሕዝብና የባእዳን ቅጥረኛ ነው።
ከ1969 መጀመሪያ ጀምሮ በትግራይ ሰላማዊ ዜጋ ላይ ግድያውን አቀጣጠለው። ግድያው ሳያንሰው ሃብትና ንብረቱም ተወረሰ። ከደደቢት በረሃ የጀመረውን አማራ የትግራይ ሕዝብ ጠላት ነው በማለት በተለያዩ ጊዜያትና ቦታዎች አማራውን በመጨፍጨፍ የዘር ማጥፋት ወንጀል ፈጽመዋል። ለሴቶች በግዳጅ የማምከኛ መድሃኒት በመስጠት የአማራው ቁጥር እንዳይጨመር አድርገዋል። ከኖርበት ቀየውና መሬቱ በግዳጅ እንዲፈናቀል አድርገዋል።
ህወሓት ኢትዮጵያን እንደተቆጣጠረ ከ1985 መጀመሪያ ጀምሮ በኦሮሞ ሕዝብ ላይ ሰፊ የጥቃት ዘመቻ በመክፈት የግድያ፣ የቤት ማቃጠል፣ ንብረቱን መዝረፍና ከፍ ያለ ሰቆቃ አድርሶባቸዋል። እንደ አማራው ሁሉ ከመኖሪያ ቦታውና ከመሬቱ ላይ ተፈናቅሏል። የኦነግ አባል ናችሁ እየተባሉ በሺዎች የሚቆጠሩ ያለምንም የፍርድ ውሳኔ ወደ ወህኒ ወርደዋል። በየቦታው በከፍተኛ ትምህርት ተቋሟት የሚማሩት የኦሮም ልጆች ከትምህርታቸው ተባረዋል። የተባረሩትም፣ መባረራቸው አልበቃ ብሎ ለእስር ተዳርገዋል። ደጉና ሩህሩሁ የኦሮሞ ሕዝብ ከእርሻው ተፈናቅሎ የረሃብና የበሽታ ሰለባ ሆኗል።
ህወሃት በጋምቤላ አኝዋኮች ላይ በፈጸመው የዘር ማጥፋት ወንጀል ተጠያቂ ነው። ሕዝቡ ከመሬቱ ተፈናቅሎ አብዛኛው በጎረቤት ሃገሮች ስደተኛ ሆነው በየሃገሩ እየተንከራተተ በችግር ላይ ነው።
የኦጋዴን ሕዝብም የዘር ማጥፋት ወንጀል ተፈጽሞበታል። ቤት ንብረቱ በህወሓት ወታደሮች ተቃጥሎበታል። ሴት ልጆቹና ሚስቶቹ ተደፍረውበታል። በተጨማሪም ከመሬቱ ላይ ተፈናቅሎ ለስደት ተዳርጓል።
የአፋር ሕዝብም በሌሎቹ የኢትዮጵያ ጎሳዎች የደረሰው ደርሶበታል፣ እየደረሰበትም ነው። የኢትዮጵያን ሕዝብ ከማሰቃየት ባለፈ ደግሞ የኢትዮጵያን ዳር ድንበር ለሱዳን መንግሥት ሸጠዋል። ሃገሪቱን ካለባህር በር አስቀርተዋል። የሃገር ሃብትና ታሪካዊ ቅርሶችን አውደመዋል፣ ሸጠዋል። ጊዜው ሲደርስ በኢትዮጵያ ሕዝብና በሃገሪቱ ላይ ለፈጸማችሁት ወንጀል ለፍርድ ያቀርባችኋል።

ይድረስ ለትግራይ ሕዝብ

ውድ የትግራይ ሕዝብ ሆይ!! ተሓህት ደደቢት በረሃ እንደወረደ በየሰበብ አስባቡ በየቤተ ክርስቲያናት እየመጡ፣ የትግራይ ሕዝብ በደመኛ ጠላትህ በአማራው የተጠቃህ ነህ። ነፃ የነበረችው ትግራይ ሃገርህ ወድቃልችና ተነስ። ከመሪ ድርጅተህ ተሓህት ጎን ተሰልፈህ አማራው ጠላትህን ደምስስ፣ ሲሉህ የሰጠኸው መልስ፣ አማራ የትግራይ ሕዝብ ጠላት አይደለም፣ ሆኖም አያውቅም፤ አብረን ተባብረን እና ጎን ለጎን ተሰልፈን፣ በአድዋና በማይጨው ጦርነት ጠላት የደመሰስን እና በደማችን አንድ የሆንን ኢትዮጵያውያን ነን። የአማራ ጠላት የሚባል አናውቅም። ትግራይ ኢትዮጵያ፣ ኢትዮጵያም ትግራይ ናት፣ የቅኝ ግዛት አይደለችም። ስለዚህ ኢትዮጵያዊነታችንን የሚነፍገን ምንም ሃይል አይኖርም። ድርጅታችሁ ትሓህት የምትሉትንም አናውቀውም፣ አንቀበለውም ብለህ መልሰሃል።
ይህንን ዓላማቸውን ለማዛመት በየቦታው የተንቀሳቀሱት የተሓህት መሪዎች በሁሉም ቦታ ተመሳሳይ ተቃውሞ ገጠማቸው። ተቃውሞው በሁሉም ከተሞች ሲበዛባቸው በብስራት አማረ የሚመራው የፈዳያን ቡድን በጠራራ ፀሃይ ሕዝቡን ፈጀው። ከየከተማው ሰዎችን እያጋዙ በየእስር ቤቱ እያጎሩ ገደሉት። የገጠሩን ሕዝብ ደግሞ ‘ትግራዋይ ሸዋዊ’ (የትግራይ ሸዋ)፣ ፊውዳል፣ ጸረ-ትሓህት፣ ጸረ-ኤርትራ ትግል ወዘተ. በማለት በውሽት በመወንጀል በቀንና በሌሊት በአፋኝ ቡድን እየተያዘ፤ ሃብት ንብረቱ እየተወረሰ ሃለዋ 06 ተወረወረ። እዚያም ገብቶ በብዙ ሺህ የሚቆጠሩት እንደተገደሉ አንተው እራስህ የምታውቀው ሃቅ ስለሆነ ምስክር አያስፈልግህም። ልጆችህ በተሓህት እየታፈኑ ወደ ሜዳ ወጥታችሁ ታገሉ እየተባሉ ብዙ ሺዎች ወንድና ሴት ልጆችህን ለሻእቢያ አሻግሮ ሸጠብህ። በቀይ ኮከብና በተለያዩ ዘመቻዎች ለሻእቢያ ተሰልፈው በማያውቁት የኤርትራ በረሃ ማለትም በሳህል፣ አቁርደት፣ ከርከበት፣ ናቅፋ፣ ሰሎሞና ወድቀው ቀሩብህ። በወቅቱ አንተው የትግራይ ሕዝብ ተሓህት/ህወሓትን በግለጽ የተቃወምከውና ያወገዝከው ስለነበረ መስካሪ አያሻህም። ኢትዮጵያዊነትህን እና ለሰንደቅዓላማዋ ያለህን ፍቅር አስመስክረሃል፣ ታሪክም ዘግቦታል።
ውድ የትግራይ ሕዝብ ሆይ፤ የህወሓት አመራሮችን ማንነት ጠንቅቀህ ታውቃለህ። ዛሬ ኢትዮጵያ ሃገራችን በሰቆቃና በችግር ውቅያኖስ ውስጥ ሰምጣለች። ይህ የሆነበት ምክንያት የህወሓት መሪዎች ኤርትራውያን እና የትግራይ ባናዳዎች ተሰባስበው በህወሓት ስም ሃገር አውድመዋል። ባንተ ስም ብዙ ሸቅጠዋል። በስምህ የመጣውን ሰፊ እርዳታ የህወሓት መሪዎች ዘርፈው ሸጠዋል። ይህም ካንተ የተደበቀ አይደለም። ወያኔ በጠነሰሰው ተንኮል በጠራራ ፀሃይ ያለረህራሄ በቦምብ ተደብድበሃል፣ ይህ ነው የማይባል የሰውና የንብረት ውድመት ደርሶብሃል። ከኢትዮጵያውያን ወገኖችህ ጋር ቅራኔ ውስጥ ሊከቱህም ብዙ ጥረዋል። በቆራጥ ኢትዮጵያዊነትህ ቁጣህን በማሳየት የወያኔ መሪዎችን አሳፍረሃቸዋል፣ አሁንም በርታበት፣ ቀጥልበት። የህወሓት መሪዎች 40 ዓመት ሙሉ አሰቃይተውሃል፣ አሁን በቃኝ በል። ከኢትዮጵያዊ ወገነህ ጎን ተሰልፈህ ግንባር ቀደም በመሆን ይህንን የህወሓት ገዳይና ሽብርተኛ ቅጥረኛ ፋሽስት ስርዓት በተበባረው ሕዝባዊ አመጽ መቃብር አስገብተን የኢትዮጵያን ሉአላዊነት፣ አንድነታችንን እና ነፃነታችንን እንጎናጸፍ።
የተከበርክ የኢትዮጵያ ሕዝብ ሆይ፤ ሰላማዊ ትግል እያልን ጊዜ አንስጠው። የተጀመረውን ሕዝባዊ ቁጣ በማቀጣጠል እጅ ለእጅ ተያይዘን በሕዝባዊ ማእበል ወያኔን ደምስሰን ሃገራችን ኢትዮጵያን ነፃ እናውጣት።
የተቃዋሚ ፓርቲ መሪዎች ለመስዋእትነት ቁርጠኛ ሁናችሁ ውጡ፣ ሕዝቡን ምሩት። በውጭ ሃገር ያለህ ኢትዮጵያዊም የትግሉ የጀርባ አጥንት ስለሆንክ አስፈላጊውን ሁሉ ለማቅረብ ተዘጋጅ።
በበረሃ ያላችሁ የትጥቅ ታጋዮችም ውጡ፣ የፋሽስቱን የወያኔ ሰራዊት በምታውቁት የውጊያ ስልት አጥቁት። የኢትዮጵያ ሕዝብ ያልተቆጠበ ድጋፉን ይሰጣችኋል። ጊዜው አሁን ነው፣ ሕዝቡም የናንተው ነው።
ድል ሊትዮጵያ እናታችን!!
ጥር 2006