Sunday, November 30, 2014

ግንባርህን አሳያቸው

The reading of Tsegaye Gebremedhin (Debteraw) poem, entitled GINBARHIN ASAYACHEW, at Quara before his forceful disappearance in 1991 by the regime of Meles Zenawi of Ethiopia. The video show is collection of few photos highlighting the EPRP struggle for a united democratic Ethiopia.


The reading of Tsegaye Gebremedhin (Debteraw) poem, entitled GINBARHIN ASAYACHEW, at Quara before his forceful disappearance in 1991 by the regime of Meles Zenawi of Ethiopia. The video show is collection of few photos highlighting the EPRP struggle for a united democratic Ethiopia.

የብሄር ነጻነት እስከ መጨፈር — ክንፉ አሰፋ (ጋዜጠኛ)

November 30,2014
ማስታወሻ፡ ይህች ጽሁፍ ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ከተከሰሰባቸው ሁለት መጣጥፎች አንደኛዋ ናት። በመጭው ወር በአሶሳ የሚደረገውን የብሄር ቀን ድራማ እሳቤ በማድረግ – በርካታ አንባብያን በጠየቁት መሰረት እነሆ በድጋሚ ለንባብ አቅርበናል።
— ክን
ፉ አሰፋ –
“እኛ ጭቁን ብሄረሰቦች ከዚህ ቀደም በየሰው ቤት ተቀጥረን የምንሰራ፣ አሽከሮች እየተባልን ነበር የኖርነው። አሁን ግን ይኸውና ህገ-መንግስታችን መብታችንን ሰጥቶናል… ኑሯችንም ተሻሽሎ ዛሬ ዘመናዊ ኑሮ እየኖርን ነው።”

እያለ የሚናገርን አንድ ጎልማሳ የቴሌቪዥኑ መስኮት ያሳያል። የደቡብ ቅላጼና ዘዬ ባለው አማርኛ ከደቡብ የመጣ ጎልማሳ ነው በቴሌቪዥን ቀርቦ መግለጫ እየሰጠ ያለው። ከአነጋገሩ በቀን ሶስቴ የሚበላ፣ የባቡር ሃዲድ እና የኤሌክትሪክ መስመር ገብቶለት፣ የስልክና የኢንተርኔት አገልግሎት ተጠቃሚም… ይመስላል።

  የዚህ ምስኪን ሰው ገጽታ እና አለባበሱ የሚነግረን ግን ሌላ ነው። በኢህአዴግ ዘመን መብቱ እንደተከበረና ኑሮው እንደተሻሻለ የሚነግረን ይህ ሰው፣ መሰረታዊ የሆነውን የሰው ልጆችን የኑሮ ፍላጎት እንኳን አላሟላም። ለእግሩ ጫማ የለውም።  በባዶ እግሩ ነው የቆመው። ሃፍረተ ስጋውን ከሸፈነለት ብጣቂ ጨርቅ በስተቀር ሰውነቱም እርቃኑን ነበር።

ለመገናኛ ብዙሃን ፍጆታ አነጋገሩ እንዲያሳምር ተነግሮት ሊሆን ይችላል – ንግግሩ ልክ መካከለኛ ገቢ ካላቸው የምዕራብ አውሮፓ ሃገሮች ተርታ የተሰለፈ ይመስላል። ይህ ደግሞ ገና የ’ትራንስፎርሜሽኑ’ ተስፋ እንጂ፤ ለውጡ በብሄር ብሄረሰቦቹ ላይ እንደማይታይ የቪድዮ ምስሎቹ ፍንትው አድርገው ነው የሚያሳዩት። ኢትዮጵያ በአምስት አመት ጊዜ ውስጥ መካከለኛ ገቢ ካላቸው ሃገሮች ተርታ ላይ እንደምትደርስ ኢህአዴግ ቃል ገብቷል። በአሁኑ ግዜ ሰባት በመቶ ብቻ የሆነው የኤሌክትሪክ ተጠቃሚ ብሄር ብሄረሰብ እና ሕዝብ በአምስት አመቱ እቅድ 80 በመቶ ይደርሳል ብለውናል። በእስር ያለው ጠንቋይ ታምራት ገለቴ ነግሯቸው ካልሆነ በስተቀር መቼም ይህንን ተረት ተረት በማህበራዊውም ሆነ በተፈጥሮ ሳይንስ ሊያረጋግጡልን እንደማይችሉ እርግጥ ነው። ከፈረሱ ጋሪው… እንዲሉ ከተግባሩ ወሬው፣ ከ’ህዳሴው ግድብ’ ስራም ሽልማቱ ቀድሞ መያዣ – መጨበጫው የጠፋ ነው የሚመስለው። ከገጠር እየታፈሱ ለሚመጡት ለነዚህ ምስኪን ወገኖች የ ‘ብሄር ብሄረሰቦች እና ህዝቦች’ መብት ማለት በአመት አንዴ በጎዳና ላይ እየወጡ መጨፈር እና ያለፈውን ስርዓት ማውገዝ ብቻ ነው የሚመስለው። ጭፈራውና ውግዘቱ እንደ ጥምቀት በዓል ስለተለመደ የግድ መደረግ እንዳለበት ያመኑበትም ይመስላል።
የደርግ ስርዓት ሰዎች በባህላቸውና በቋንቋቸው እንዳይዘፍኑ ከልክሎ እንደነበር የሚጠቁም መረጃ የለም። ደርግ አስራ ሰባት አመት ገዛ፣ 20 አመት ሙሉ በብሄር ጭቆናው ሲወገዝ ኖረ። በባንዲራ ቀን ውግዘት፣ በከተሞች ቀን ውግዘት፣ በብሄር ብሄረሰቦችና ህዝቦች ቀን ውግዘት፣ በግንቦት ሃያ ቀን ውግዘት…. በየሽልማቱ ስነ ስርዓት እና በየበዓላቱ ቀን ውግዘት….። የደርግ ሃጢያት መብዛት የነሱን ግፍ ይሸፍን ይመስል የኢህአዴግ በዓላት እና ውግዘቱ ከለት-ተለት ሲጨምር ብቻ ነው የምናየው – እንደ 11 በመቶው የኢትዮጵያ ኢኮኖሚያ እድገት።
የዚህ ሳምንት ወሬ ደግሞ በመቀሌ ስለተካሄደው ስድስተኛው የ ‘ብሄር – ብሄረሰቦች እና ህዝቦች ቀን’ ነው። የመከር ወቅት ስራቸውን እንዲያቆሙት ተደርገው፣ ከየክልሉ እየተጫኑ ለጭፈራ መቀሌ የገቡ አርሶአደሮች ቁጥር ቀላል አይደለም። በዲያጎን እየተፈለጉ የተለቀሙ ልማታዊ አርቲስቶች እና የመድረክ አስተዋዋቂዎችም በስፍራው ተገኝተዋል። የእውቁ ኪነጥበብ ሰው – የኪሮስ አለማየሁ ልጅ ዛፉ ኪሮስ ‘አንበሳ ገዳይ’ በሚለው የትግርኛ ዘፈንዋ መድረኩን ይዛዋለች። በርከት ያለ ሰው መድረኩን ከቦት ይጨፍራል። አዳራሹም በ ‘ብሄር – ብሄረሰቦች እና ህዝቦች’ ተሞልቷል። መቀሌ፣ ኅዳር 27 ቀን 2004 ዓ.ም.።
የእለቱ የመድረክ አስተዋዋቂ ‘አንበሳ ገዳይ’ የሚለው የዛፉ ኪሮስ ዘፈን የተስማማው አይመስልም፤ አልተዋጠለትም። አልያም ዘፈኑን እዚያው መድረክ ላይ እንዲያስተባብል ተነግሮታል። ተራውን ጠብቆ ማይክራፎኑን ያዘ። “ህገ መንግስታችን ለብሄር ብሄረሰቦች እና ህዝቦች ብቻ ሳይሆን ለዱር እንስሶችም…” ብሎ እየተናገረ እያለ እንደተለመደው መብራት ተቋረጠ።
  በዚህ ‘ታላቅ’ ቀን መብራት መቆራረጡ ቢያበሳጭም፣ በእንግድነት ወደ መቀሌ የተጓዙት ‘ብሄር ብሄረሰቦች እና ህዝቦች’ ኤሌክትሪክ ምን እንደሆነ ስለማያውቁ አልደነቃቸውም – የሚያውቁት ደግሞ የለመዱት ስለሆነ – ለእነሱ እንግዳ ነገር አይደለም።  ከቆይታ በኋላ ግን መብራት መጣ። ልማታዊው አርቲስትም ንግግሩን ቀጠለ።

“…ህገ መንግስታችን ለብሄር ብሄረሰቦች እና ህዝቦች ብቻ ሳይሆን የዱር አራዊቶችንም መብት ስላስከበረ አንበሶች አሁን አይገደሉም።…” በማለት የዘፈኑን መልእክት ለማስተባበል እና ጭብጡን ለብሄር ብሄረሰቦች እና ህዝቦች ለማስረዳት ሞከረ። እዚህ ላይ የመድረክ አስተዋዋቂው እና ዘፋኝዋ እንዳልተግባቡ መገመት ይቻላል። ዛፉ ኪሮስ ዘፈንዋን በዚህ መድረክ ታቅርበው እንጂ መልእክቱ ላሁኑ ትውልድ ሳይሆን ምናልባት ‘ተራራ ላንቀጠቀጠው’ ለዚያኛው ሊሆን ይችላል ብሎ ማሰብ የተሳነው ይመስላል። ያ ቡድን የትኛውን ተራራ እንዳንቀጠቀጠ ባይገለጽልንም አሁን ያጠለለበት የለውጥ ደመና ግን በተራው እያንቀጠቀጠው ለመሆኑ ከሚያደርጋቸው ግራ ገብ ድርጊቶቹ መረዳት ይቻላል።

የሆነው ሆኖ በአሉ ለመቀሌ ህዝብ ልዩ ስሜት እንደሰጠው ይታያል። ይህ ህዝብ ከሌላው ኢትዮጵያዊ ወገኑ ተለይቶ፣ በእነ መለስ እና በረከት ካድሬዎች ታጥሮና ታፍኖ የሚገኝ ህዝብ ስለመሆኑ በርካታ መረጃዎች ይመሰክራሉ። ከስፍራው የሚደርሱን መረጃዎች እንደሚተቁሙት ከመንግስት ራዲዮ እና ቴሌቪዥን ውጭ ያሉ የመገናኛ ብዙሃንን በዚያ ክልል መጠቀም ራሱ እስከ ስድስት ወር የሚያሳስር ወንጀል ነው። ለ20 አመታት የታፈነ ህዝብ ከሌላው ወገኑ ጋር ተቀላቅሎ ፣ አብሮ ሲጨፍር የሚፈጥርበትን ስሜት መገመት አያደግትም። የደርግ ስርዓት የአሜሪካ እና የጀርመን ድምጽ ራዲዮን የትግራይ ህዝብ እንዳይሰማ አልከለከለም ነበር። ወያኔ ግን የትግራይ ህዝብን የመናገር ብቻ ሳይሆን የመስማት መብቱንም ጭምር ነው የነፈገው።

የሳተላይት ዲሽ ቴሌቪዥን ክልክል በሆነበት በዚያ ክልል የኢቲቪ አኬልዳማ ድራማ ይደገምልን ብሎ የትግራይ ህዝብ ቢጠይቅ ሊደንቀን አይገባም። ጆሮ ካሰለቸው የ’ህዳሴው ግድብ’ ወሬ እና እጅ እጅ ካሉት ከነ ሰራዊት ፍቅሬ አኬልዳማ ትንሽም ቢሆን ዘና ሳያደርጋቸው አልቀረም። የቴሌቪዥኑ መግቢያ ላይ ታዲያ ‘እንደምን አመሻችሁ ዲሽ የሌላችሁ” ብሎ ነው የሚጀምረው እየተባለም ይቀለዳል። ይህ ህዝብ በስሙ ሲነገድበት እና ከሌላው ወገኑ ጋር እንዲቃቃር ሲደረግ የትግራይ ኢሊቶች ዝም ማለታቸው እጅግ የሚያሳዝን ጉዳይ ነው። ስለ ዱር አራዊት መብት እና ስለ አንበሳ መግደል ሲነሳ ትዝ ያለኝ የ1983ቱ የአምባሳደር ተስፋዬ ሃቢሶ ንግግር ነበር። ቻርተሩ ሲጸድቅ በነበረበት ጊዜ የከምባታና ሃድያን ጎሳ እወክላለሁ ብለው ወንበር ይዘው የነበሩት አቶ ተስፋዬ ሃቢሶ በወቅቱ ሲናገሩ። “እኛ አናሳ ብሄር ብሄረሰቦች ዲሞክራሲ ብቻ ሳይሆን የሚያስፈልገን፣ እንደብርቅዬ እንስሣ እንክብካቤም ይገባናል።” ብለው ነበር።

ኢህዴግም በወቅቱ ለእነኚህ ‘አናሳ ጎሳዎች’ ልዩ እንክብካቤ እንደሚያደርግ ነበር ቃል የገባው። አቶ ተስፋዬ ይህንን በተናገሩ ከአመታት በኋላ ታዲያ በሃዲያ እና ወላይታ ወገኖቻችን ላይ ጥይት እና ቦምብ እንደዝናብ ወረደባቸው። የ1993ቱ ብሄራዊ ምርጫ ተጭበርብሯል፣ ‘ድምጻችን ይከበር’ ብሎ የጮኸው የደቡብ ወገናችን በመለስ ወታደሮች ያለ ርህራሄ ነበር የተጨፈጨፈው። ልዩ እንክብካቤው እና ዴሞክራሲው ቀርቶ ይልቁንም የቆሙለት፣ በስሙም ስልጣን ያገኙበት፣ የራሳቸው ጎሳ በጥይት ሲቆላ አቶ ተስፋዬ ሃቢሶ ሹመታቸውን ላለማጣት ሲሉ ትንፍሽ አላሉም። እንዲያውም ዛሬም ስለ ‘ብሄር ብሄረሰቦች እና ህዝቦች’ መብት መከበር ከሚነግሩን እና የሌሎችን ጽሁፎች እየሰረቁ ከሚጽፉት ሰዎች አንዱ ናቸው።

  ማሌሊቶቹ የሃገሪቱ የዘመናት ችግር የብሄር ብሄረሰቦች እና ህዝቦች መብት መነፈግ ነው ሲሉ ሰበኩ። የዚህ ችግር መፍቻ ቁልፍም በእጃቸው እንዳለ ነገሩን። በለስ ቀንቷቸው ምኒሊክ ቤተ መንግስት ሲገቡም ጫካ ውስጥ የጻፉትን ያንን የስታሊን ፍልስፍና ወደ ህገ-መንግስትነት ቀየሩት። መፍትሄ ያሉት የጎሳ ፖለቲካም በጥላቻና በበቀል ተተካ። የማሌሊት ፍልስፍና ሲተገበር ታዲያ የመጀመርያ ሰለባ የሆነው አማራው ወገናችን ነበር። ለፖለቲካ ትርፍ ሲሉ እነ አቶ መለስ ዜናዊ ይዘውት የመጡት የጥላቻና የብቀላ ፖለቲካ እንደስካር ቶሎ በረደ እንጂ አካሄዱ እጅግ ዘግናኝ ነበር። በምስራቅ እና በምእራብ ኢትዮጵያ የአማራ ዘር ጨርሶ እንዲጠፋ ተዘምቶበት ነበር። የአማራን ዘር ጭካኔ በተሞላበት መንገድ ከተበቀሉት በኋላም ጽዋው ወደ አኙዋክ – ጋምቤላ ሄደ ፣ ከአኙዋክ ጭፍጨፋ በኋላ ደግሞ ዘመቻው በኦሮሞ ወገናችን ላይ ቀጠለ። በወላይታ ተከተለ፣ በኦጋዴን… ተዛመተ። የብሄር መብት እስከመገንጠልን ያስከበረው ህገ-መንግስት ጸድቆ በወረቀት ላይ ተቀምጧል። ይህንን መብት እየጠየቁ ያሉ ኢትዮጵያዊ ወገኖቻችንን ግን በዘራቸው ብቻ እየተመረጡ ማጥፋቱ ዛሬም በሚያሳዝን ሁኔታ እንደቀጠለ ነው።

እነ መለስ እነ በረከት ለዘመናት ተዋልዶና አብሮ ሲኖር የነበረን ህዝብ እንደ እንግሊዝ ከፋፍለህ ግዛው ቅኝ ስርዓት ለአገዛዝ እንዲያመቻቸው ህዝቡን እርስበርስ እያጋጩት ላለፉት 20 አመታት ለመቆየት ችለዋል። የዘር ፖለቲካው ምስጢር ይኸው ነው። ህንን ባያደርጉ ኖሮ እስካሁን እንደ ጉም ተበትነው በጠፉ ነበር።

  ወደመቀሌው በዓል እንመለስ። ብሄር ብሄረሰቦቹ በመቀሌ ከተማ በቡድን በቡድን እየዘፈኑና እየጨፈሩ ይጓዛሉ። በተለይ ከደቡብ የመጡት ብሄር ብሄረሰቦች መብታቸው ተከብሮላቸው ወደ እድገት ጎዳና ከተጓዙ ከሃያ አመት በኋላም – ጥንታዊው የጋርዮሽ ስርዓት ከሚመስለው አለባበሳቸው እንኳን አልተቀየሩም። መር ከሃያ አመት በፊት ቅጠል ለብሶ ይጨፍራል፣ ዛሬም ቅጠሉን አልቀየረም። ዳውሮ ድሮ ለእግሩ ጫማ አያደርግም ነበር አሁንም ጫማ የለውም። ከፊቾ ከ20 አመታት በፊት ከቀንድ የተሰራ የሙዚቃ መሳርያ ነበር የሚጠቀመው፣ አሁንም እሱኑ ይዞ ነው መቀሌ የመጣው…። ሁሉም አንዳች ለውጥ አይታይባቸውም። ታድያ የዚህ ሕዝብ ነጻነቱ፣ ለውጡ እና እድገቱ የቱ ላይ እንደሆነ ማን ይሆን የሚያስረዳን?

ህገ መንግስታዊ መብቴ ይከበርልኝ ባለ ብቻ ምላሹ የጥይት እና ቦንብ የሆነ ሕዝብ ቅጠል ለብሶ መጨፈሩ ምን ትርጉም ይሰጠናል? ይህ ነጻነቱን ያሳየናል እንዴ? ወይንስ ዛሬም የእግር ጫማ እንኳን አለማድረጉ እንደ ባህል ተቆጠረለት?  ጎንደሬው ሁመራ ላይ ለማረስ ፈቃድ ከመቀሌ መጠየቁ ነው የመብቱ መከበር? ወይንስ መቀሌ ላይ ሄዶ እስክስታ መምታት? አፋርና ኢሳ – ጉርጉራ ላይ ካላረሰ – አማራው ኦሮሞ ምድር ላይ እንዳይሰራ ከታገደ መብቱ ምኑ ላይ ነው?

ተረስቶ ይሆን ይሆናል እንጂ “የአክሱም ሃውልት ለወላይታው ምኑ ነው?…” ብለው ነበር አቶ መለስ። ታዲያ ዛሬ ምን አዲስ ነገር ተገኘ? በመቀሌ እየተደረገ ያለው የወላይታ ጭፈራስ ለአድዋው ምኑ ሊሆን ነው? ‘የኢትዮጵያ ጥንታዊ ስልጣኔ አንተን አይመለከትህም’ ተብሎ የነበረ የወላይታ ህዝብ ዛሬ የመለስን ፎቶ እና ‘ለልማት የተጋ ብቸኛው መሪ’ የሚል መፈክር ይዞ በመቀሌ እንዲሰለፍ ተደርጓል። ደቡቡ የየራሱን የአፍ መፍቻ ቋንቋ እርግፍ አድርጎ ትቶ ኢህአዴግ በፈጠረለት ‘ወጋ ጎዳ’ እንዲናገር አቶ መለስ፡ ሲያስገድዱት እነሱ ግን ልጆቻቸውን በአለም አቀፍ ቋንቋ ብቻ እንዲማሩ ነው ያደረጉዋቸው። ዛሬ አቶ መለስ የነዚህን ጎሳዎች መብት መከበር ነው በመቀሌ እያበሰሩ ያሉት።

ይህ ህዝብ እንዲሁ ‘ብሄር ብሄረሰቦች እና ህዝቦች እየተባለ ሲቀለድበት እንደዋዛ ሃያ አመታት አለፉ። በኢህአዴግ ዘመን ተወልዳ፣ ተምራ ዩኒቨርሲቲ የተመረቀች ወጣት አንድ አፍሪካ ሃገር አግኝቼ አወራኋት። ሜሮን ትባላለች። ስለ ብሄር ብሄረሰቦች እና ህዝቦች መብት እና ነጻነት ልትነግረኝ ሞከረች። ዩኒቨርሲቲ የሚያስገባ ውጤት ሳይኖራት ይልቁንም ኢህአዴግ በሰጣት እድል ዩኒቨርሲቲ ገብታ እንደተማረች ስለተነገራት የመለስ ዜናዊ አድናቂ ናት።

በወሬያችን መሃል በድንገት ‘ብሄር ብሄረሰቦች እና ህዝቦች ማለት ምን ማለት ነው?’ ብዬ ጠየቅኳት። ጥያቄዬ ዱብዳ ነገር ሆነባት። ለሚለኒየም ግብ ሲባል ከተከፈቱት ዩኒቨርሲቲዎች ለስታስቲክስ ማሟያ የተመረቀች ስለመሆንዋ አመለካከትዋ፣ አስተሳሰብዋ እና ንግግርዋ ይገልጸዋል። ጥያቄዬን ለመመለስ እንደከበዳት ተረዳሁ። ብሄር ብሄረሰቦች እና ህዝቦች የሚለውን ቃል የሜሮን ትውልድ ለሃያ አመታት ያለማቋረጥ ሲሰማው የነበረው ጉዳይ ነው። ለዚህ ትውልድ የብሄር መብት ማለት ግን በየአመቱ በጎዳና ላይ ከሚደረግ ጭፈራ ውጭ የሚሰጠው ሌላ ትርጉም ያለ አይመስለኝም። ማን ነው ብሄር? ብሄረሰሰቦችስ የትኞቹ ናቸው? ህዝቦች የሚባሉትስ? ለዚህ ጥያቄ እንኳንና ሜሮን – ወያኔም መልሱ እንደሚቸግረው ይገባኛል። ሜሮን ግን ኮስተር ብላ “ህገ መንግስቱ ነዋ!” አለችኝ።

ከዩኒቨርሲቲ ከተመረቀች ወጣት ቀርቶ ከአንደኛ ደረጃ ተማሪ እንኳን የማልጠብቀውን መልስ በማግኘቴ ባዝንም – በመልስዋ ግን ትንሽ ፈገግ ማለቴ አልቀረም። ከአፍታ ቆይታ በኋላ – ብሄር ብሄረሰቦች እና ህዝቦች ማለት ራሱ መለስ ዜናዊ ይመስለኛል ስትል ቀለደች ሜሮን። እዚህ ላይ ልብ በሉ! ‘የህዳሴው ግድብ’ ሽልማት ስነ ስርዓት እየተደረገ በነበረበት ግዜ የግድቡ “ወደር የሌለው ተሸላሚ”ን ሰራዊት ፍቅሬ በቴሌቭዥን ሲያስተዋውቅ የሆነው ነገር ታወስውኝ። ነገሩ ጤነኛ አእምሮ ላለው ሰው እንግዳ ነበር።
ሰራዊት እና ሙሉአለም እየተቀባበሉ – እየደጋገሙም ‘የህዳሴው ግድብ ወደር የሌለው ተሸላሚ’ ይላሉ። ከብዙ ደቀቃ በኋላም የህዳሴው ግድብ ወደር የሌለው ተሸላሚ ይፋ ሆነ።

“ብሄር ብሄረሰቦች እና ህዝቦች!” ሲል ሰራዊት ፍቅሬ በሚለኒየም አዳራሽ ለተሰበሰበው ህዝብ አበሰረ። ሸልማቱን የሚሰጠው አቶ መለስ ዜናዊ ፣ ሽልማቱን የሚቀበለው የኢህዴግ ተወካይ ሲሆን ፣ ይህም በተዘዋዋሪ አቶ መለስ ዜናዊ መሆኑ ነው። ሜሮን ይህንን ማለትዋ ከሆነ – ጥያቄዬን በትክክል እንደመለሰችልኝ ተረዳሁ። ሽልማቱ መጣም አልመጣ ለብሄር ብሄረሰቦቹ የሚፈይደው ነገር አይኖርም። በየአመቱ የሚደረገው የጎዳና ላይ ጭፈራ ግን የብሄረሰቦች መብት ብቻ ሳይሆን ግዴታቸውም ሆኗል ብለን እንደምድም።

የብሄር ነጻነት እስከ መጨፈር! ከዛ ካለፈ ግን የህይወት ዋጋም ያስከፍላል። ኦጋዴንን ያስተውሏል?

በኖርዌይ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን የአቶ አንዳርጋቸውን መታሰር በመቃወም ሰልፍ አደረጉ

ኀዳር ፲፱(አስራ ዘጠኝቀን ፳፻፯ / ኢሳት ዜና :- ኢትዮጵያውያኑ ኦስሎ በሚገኘው የእንግሊዝ ኢምባሲ ፊት ለፊት በመገኘት ገዢው ሃይል የወሰደውን እርምጃ ከማውገዝ በተጨማሪ የኢንግሊዝ መንግስት አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ስላሉበት ሁኔታ ወቅታዊ መረጃ እንዲሰጥ ጠይቀዋል።
የዲሞክራሲ ለውጥ በኢትዮጵያ ባዘጋጀው የተቃውሞ ሰልፍ ላይ አቶ አንዳርጋቸው የፍትህ ተምሳሌት፣ የነጻነት በር ከፋች ነው የሚሉ መፈክሮች ተሰምተዋል።
ኖርዌይ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን አቶ አንዳርጋቸው በግፍ የመን ውስጥ ተይዘው ወደ ኢትዮጵያ ከተላለፉበት ጊዜ ጀምሮ ተከታታይ የተቃውሞ ሰልፎችን አድርገዋል።

435 ኢትዮጵያዊያን ፍልሰተኞች ወደ ሃገር እየመለሰ እንደሆነ የኢትዮጵያ መንግሥት አስታውቋል

http://satenaw.com/amharic/?p=2747
በሕገወጥ መንገድ ተታልለው ከሃገር ከወጡ በኋላ በታንዛኒያ እሥር ቤቶች ውስጥ ቆይተው እንደነበር የገለፃቸውን 435 ኢትዮጵያዊያን ፍልሰተኞች ወደ ሃገር እየመለሰ እንደሆነ የኢትዮጵያ መንግሥት አስታውቋል፡፡
2698F4A2-7EE3-4D5F-B89A-0B5E7C92F767_w640_r1_s
ፎቶ ፋይል /ይህ ፎቶ የተገኘው ከአንድ የታንዛኒያ ዌብ ሣይት ነው፡፡ በሕገወጥ አሸሸጋጋሪዎች በብረት ኮንቴይነር ታጭቀው ሲወሰዱ የፀጥታ ኃይሎች የያዟቸውን “ኢትዮጵያዊያን” ነው የሚያሣየው፡፡ ከዚህ ታሪክ ጋር ግንኙነት ያለው ሰው በዚህ ፎቶ ግራፍ ውስጥ ለመኖሩ እርግጠኞች አይደለንም፡፡/
ናይሮቢ በሚገኘው በኬንያ የኢትዮጵያ ኤምባሲ የዳያስፖራ ጉዳዮች ሚኒስትር ካውንስለር አቶ መለስ ዓለም ለቪኦኤ በሰጡት መግለጫ መሠረት የመጀመሪያው ቡድን አባላት የሆኑት 253 ተመላሾች ዛሬ፤ ዓርብ ከቀትር በኋላ አዲስ አበባ ገብተዋል፡፡
ኢትዮጵያዊያኑ ወደሃገራቸው እየተመለሱ ያሉት የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር፣ የታንዛኒያ የሃገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስቴርና አዲስ አበባ የሚገኘው የዓለምአቀፉ የፍልሰት ጉዳዮች – አይኦኤም የኢትዮጵያ ቢሮ በጋራ ባደረጉት ጥረት መሆኑን የኤምባሲው ሪፖርት አስታውቋል፡፡
ኬንያ የሚገኘውና ታንዛኒያን ጨምሮ ሌሎችንም የአካባቢውን ሃገሮች የሚሸፍነው የኢትዮጵያ ኤምባሲ ባለሥልጣናት ታንዛኒያ ሄደው የዜግነት ማጣራት ማድረጋቸውንና ኢትዮጵያዊያኑ የአንድ ዓመት የእሥር ጊዜያቸውን የጨረሱ፣ በቁጥጥር ሥር ውለው ለፍርድ ያልቀረቡ፣ ገሚሶቹም የፍርድ ጊዜያቸውን ሳይጨርሱ በዲፕሎማሲያዊ መንገድ በተደረገ ጥረት በታንዛኒያ መንግሥት ምኅረት የተደረገላቸው መሆናቸውን መግለጫው ጠቁሟል፡፡
ዕድሜአቸው ከ15 እስከ 39 ዓመት የሆነና ከደቡብ ኢትዮጵያ ሃድያ እና ሆሣዕና አካባቢ የመጡት ኢትዮጵያዊያን እንደገለፁት ከእነርሱ ጋር ወደ ደቡብ አፍሪካ ለመሄድ በሚል ከተነሱ ውስጥ መንገድ ላይ ሕይወታቸው ያለፈና አካላቸው የጎደለ ብዙዎች እንዳሉ መናገራቸውን ኤምባሲው በዚሁ መግለጫው ላይ አስፍሯል፡፡
ኢትዮጵያዊያኑ ከሃገር ለመውጣት ከ50 ሺህ እስከ 70 ሺህ ብር ለሕገወጥ አሸጋጋሪዎቹ መክፈላቸውን እንደገለፁለት ኤምባሲው ጠቁሟል

ማን ያውራ የነበረ

Saturday, November 29, 2014

ፍርድ ቤት የሰጠውን ትእዛዝ የሚያስለውጥ በቂ እና አሳማኝ ምክንያት ባለመገኘቱ ወ/መ/ስ/ስ/ህ/ቁ 75 መሰረት ይግባኙን ባለመቀበል ወስነናል። መዝገቡ ተዘግቷል ይመለስ።

“በሽብር “ ተግባር ተጠርጥረው በማረሚያ ቤት ከሚገኘት 9 የዞን9 ጦማርያን እና ጋዜጠኞች መካከል ስምንቱ ተከሳሾች የዋስትና መብታቸው አንዲከበር ለጠቅላይ ፍርድ ቤት ያስገቡት ይግባኝ ውድቅ ተደረገ፡፡
ስድስቱ የዞን9 ጦማርያን እና ሁለቱ ወንዶች ጋዜጠኞች ጉዳያቸው በቋሚነት በሚታይበት ከፍተኛው ፍርድ ቤት ይግባኝ መብታቸው አንዲከበርላቸው ጠይቀው ውድቅ መደረጉን ተከትሎ ለጠቅላይ ፍርድ ቤት የይግባኝ አቅርበው ነበር፡፡ ጠቅላይ ፍርድ ቤቱ ጉዳዮን ከጠበቆች እና ከአቃቤ ህግ በመስማት ውሳኔ ለመስጠት አንድ ተጨማሪ ቀጠሮ የወሰደ ሲሆን በአጭር ጊዜ ውስጥ በሰጠው ውሳኔ ያለምንም ማብራሪያ በጸረ ሽብር ህጉ በመከሰሳቸው ዋስትና አይገባቸውም በሚል ምክንያት የስምንቱን ይግባኝ ባዮች አቤቱታ ውቅድ አድርጎታል፡፡
የፍርድ ቤቱ ውሳኔ ተያይዞ ይገኛል፡፡

Friday, November 28, 2014

የሕወሐት/ ኢህአዴግ ባለስልጣናት ፒ.ኤች.ዲዎችን ከተለያዩ የሀገር ውስጥና የውጭ ተቋማት እየገዙ እንዳሉ የቅርብ ምንጮች አስታወቁ።

November 28,2014

         እየሩሳሌም አርአያ
የሕወሐት/ ኢህአዴግ ባለስልጣናት ፒ.ኤች.ዲዎችን ከተለያዩ የሀገር ውስጥና የውጭ ተቋማት እየገዙ እንዳሉ የቅርብ ምንጮች አስታወቁ። የትግራይ ክልል ጤና ቢሮ ሃላፊ የሆኑት አቶ ሐጐስ ጐደፋይና ምክትላቸው አቶ አታክልቲ እንደሚገኙበት የጠቀሱት ምንጮቹ ለሁለቱ ባለስልጣናት በመቀሌ ሆስፒታል የሚሰራ የባዮስታቲክስ ባለሙያ በኩል የጥናት ፕሮፖዛላቸውን አሰርተው ፕሮፖዛሉ ፀድቆ ዋናውን ጥናት ይህ ባለሙያ ግለሰብ እየሰራላቸው እንደሚገኝ አያይዘው ገልፀዋል። ባለስልጣናቱ ስለጥናቱ አንዳችም የሚያውቁት ነገር እንደሌለ ምንጮቹ አጋልጠዋል።

 ሌሎች ስድስት የህወሀት ባለስልጣናትም የማስተርስና ፒ.ኤች.ዲ ጥናት እየፃፈላቸው እንደሚገኝ ምንጮቹ አክለው ገልፀዋል። ሌሎች የአገሪቱ ዩኒቨርሲቲዎችም የዚህ ህገወጥ ተግባር ተሳታፊዎች ናቸው ያሉት ምንጮቹ በተለይ ሪፍት ቫሊ የተባለውን የግል ዩኒቨርሲቲ ኮሌጅ የሚስተካከል የለም ብለዋል። የኦህዴድ ባለስልጥናት ባለድርሻ የሆኑበት ይህ ዩኒቨርሲቲ ገንዘብ ለከፈለ ሁሉ ሰነድ አዘጋጅቶ ዲግሪና ማስተርስ እንደሚሰጥ አስታውቀዋል።

የእስክንድር ነጋ ያገባኛል ባይነት!
በላይ ማናዬ

‹‹መብቴን አሳልፌ አልሰጥም፤ የትም ብሆን ስለመብቴና ሀገሬ ያገባኛል፡፡ እዚህ ከሚጠይቁኝ ሰዎች ጋር የፈለኩትን ማውራት እችላለሁ፡፡ እናንተ ከፈለጋችሁ በር ላይ መልሷቸው እንጂ እኔ ጋር ከመጡ በኋላ ስለሀገሬ ከእነሱ ጋር መነጋገር መብቴ ነው፡፡ አዎ የትም ቦታ ብሆን፣ መቼም ቢሆን ስለ ሀገሬ ያገባኛል!››

ይህን ያለው ትንታጉ ጋዜጠኛና የፖለቲካ ተንታኝ እስክንድር ነጋ ነው፡፡ እስክንድር ነጋን ካወኩት ወዲህ እንደዛሬ በኃይለ ቃል ሲናገር ሰምቼው አላውቅም፤ ወይም ትዝ አይለኝም፡፡ ዛሬ (ህዳር 19/2007 ዓ.ም) እኩለ ቀን ላይ እስክንድርን ልጠይቀው ቃሊቲ ተገኝቼ ነበር፡፡ ሆኖም ሁኔታው ሁሉ እንደማንኛውም ቀን አልነበረም፡፡ በር ላይ ስደርስ በርከት ያሉ የአንድነት ፓርቲ አባላት ሰሞኑን እያካሄዱት ያለውን የማህበራዊ ሚዲያ ዘመቻ በማስመልከት እስክንድር ነጋን፣ አንዱዓለም አራጌን እና ሌሎችንም ሊጠይቁ በቦታው ተገኝተው ነበር፡፡

በጠዋት ቂሊንጦ የሚገኙ ወዳጆቼን ጠይቄ አብረውኝ ከነበሩ የሰማያዊ ፓርቲ አባላት ጋር ነበር ወደ ቃሊቲ ያመራሁት፡፡ ቃሊቲ የተገኘው ሰው ሁሉ መጠየቅ የሚፈልገውን ሰው እና ሙሉ አድራሻውን እያስመዘገበ ሳለ በመሐል እኔም እስክንድርን መጠየቅ እንደምፈልግ ነግሬ ተመዘገብኩ፡፡ ከትንሽ ቆይታ በኋላ ግን ስማችሁ ከዚህ ቀደም ያልተመዘገባችሁ አሁን መግባት አትችሉም መባሉን መዝጋቢ ፖሊሱ አረዳን፡፡ እኔ እና ትንሽ ሰዎች መግባት ስንችል አብዛኛው ሰው ግን መግባት እንደማይችል ተነገረን፡፡

በዚህ ሁኔታ እስክንድር ጋር ደርሰን ሰላምታ ከተለዋወጥን በኋላ አንድ የአንድነት ፓርቲ አባል ሰሞኑን ፓርቲያቸው እስረኞችን በተመለከተ በማህበራዊ ድረ ገጽ ላይ እየተሰራ ያለውን ስራ ለእስክንድር ያብራራለት ጀመር፡፡ እስክንድር በተለመደ ጥሞናው ሲያዳምጠው ቆይቶ፣ በግሉ የተሰማውን እና መሆን ቢችል ያለውን ነጥብ ተናገረ፡፡ በመሐል ወጣቱ የአንድነት አባል ወደ እስክንድር ጠጋ ብሎ ሌሎች ተጨማሪ ጉዳዮችን ሲነግረው ድንገት አንድ የፖሊስ አዛዥ ጨዋታቸውን እንዲያቆሙና እስክንድር ወደ እስር ቤቱ እንዲገባ፣ ወጣቱ የአንድነት አባል ደግሞ ወደ ውጪ እንዲወጣ በትዕዛዝ ማጣደፍ ያዘ፡፡

ይህኔ እስክንድር ለስለስ ባለ አነጋገር ምንም እንዳላጠፋን በመግለጽ ፖሊሱ መረጋጋት እንዳለበት አስረዳ፡፡ የፖሊስ አዛዡ ግን ጭራሽ ብሶበት ወጣቱ በቶሎ እንዲወጣ አደረገ፡፡ ምክንያቱ ደግሞ ‹ፖለቲካ ማውራት አቁሙ› የሚል ሆነ፡፡ ይህን ተከትሎ እስክንድር ድንገት በኃይለ ቃል ተናገረ፡፡ ‹‹መብቴን አሳልፌ አልሰጥም፤ የትም ብሆን ስለመብቴና ሀገሬ ያገባኛል፡፡ እዚህ ከሚጠይቁኝ ሰዎች ጋር የፈለኩትን ማውራት እችላለሁ፡፡ እናንተ ከፈለጋችሁ በር ላይ መልሷቸው እንጂ እኔ ጋር ከመጡ በኋላ ስለሀገሬ ከእነሱ ጋር መነጋገር መብቴ ነው፡፡ አዎ የትም ቦታ ብሆን፣ መቼም ቢሆን ስለ ሀገሬ ያገባኛል! የማወራው ስለ ሰላማዊ ትግል፣ ስለህጋዊ ትግል ነው!›› አለ እስክንድር በስሜት ውስጥ ሆኖ፡፡

በግሌ እስክንድር እንዲረጋጋ፣ ሁኔታው ግን ያልተገባ እንደሆነ ገለጽኩ፡፡ ፖሊሱ ግን ሊረጋጋ አልቻለም፡፡ እስክንድርን ይዞት ሄደ፡፡ ‹‹በርቱ! እንቅስቃሴያችሁ ህጋዊና ሰላማዊ ይሁን እንጂ ትግላችሁን ቀጥሉ!›› ሲል እስክንድር ወደ እስር ቤቱ እየገባ ተናገረ፡፡ የፖሊስ አዛዡም ከእስክንድር ጋር የነበረንን ቆይታ ሰዓቱ ሳይደርስ ገታው፡፡ የእስክንድር ያገባኛል ባይነት አስደመመኝ፡፡ እስር ቤት ሆኖም፣ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ሆኖም እስክንድር ስለ ሀገሩ እንደሚያገባው በስሜት ተናገረ፡፡ መብቱን መቼም ቢሆን አሳልፎ እንደማይሰጥ አስረገጠ፡፡

ስለ ያገባኛል ባይነት ሳስብ በጠዋት ቂሊንጦ ያገኘኋቸውን የዞን 9 ጦማሪዎች አስታወስኩ፡፡ ‹ስለሚያገባን እንጦምራለን!› ይላሉ ወጣቶቹ ጦማሪያን፡፡ ከአብርሃ ደስታ ጋር አብረው ያገኘኋቸው እነ በፍቃዱ ኃይሉ እና አጥናፍ ብርሃኔ ብዙ ጉዳዮችን እያነሱ አወጉኝ፡፡ ‹‹ህወሓት አንድ ወይም ሁለት ነባር የህወሓት ባለስልጣናትን በሽብር ከከሰሰ ስርዓቱ እንዳበቃለት እቆጥራለሁ፡፡ ምክንያቱም ሽብር ማታለያ መሆኑ ይቀራል›› አለኝ በፍቃዱ ኃይሉ፡፡ አብርሃ ደስታ ቀበል አድርጎ ‹‹እናት አልጋነሽ በሽብር ስትከሰስ በጣም ብዙ ሰው ተቃውሞ ነበር›› አለ፡፡ አጥናፍ በበኩሉ ‹‹ቄስና ሸህ ሽብርተኛ እየተባለ አይደለም እንዴ›› በማለት ጠየቀ፡፡

አብርሃ ደስታ አንድ ነገር በኃይል እንደሚቆጨው ተናገረ፡፡ ምን እንደሆነ ጠየቅሁት፡፡ ‹‹ብዙ የሰላማዊ ትግል እንቅስቃሴ ሳላደርግ መታሰሬ ይቆጨኛል!›› አለ፡፡ በፍቃዱ በበኩሉ፣ ‹‹እኔም የገባኝ ነገር ያለውን የሰላማዊና ህጋዊ የመስሪያ ልክ አለመስራታችን ነው፡፡ አሁን ላይ ሆኜ ሳስበው እንዲህ ለሚያስሩን ስንት ህጋዊና ሰላማዊ እንቅስቃሴዎችን እንኳ ሳናደርግ በትንሽ ነገር በርግገው እዚህ ሲያስገቡን ይቆጨኛል›› በማለት ሀሳቡን ቀጠለ፡፡ ‹‹በእርግጥ አንድ ሰው አሁን መጠንቀቅ ያለበት የሚሰራው ስራ ህጋዊ መሆን አለመሆኑን እንጂ፣ ይህን ካደረኩማ ያስሩኛል የሚለውን መሆን የለበትም፡፡ እነሱ ከፈለጉ ያስሩሃል፤ ስለዚህ መብትህን ተጠቅመህ መታሰሩ ይሻላል እንዲሁ ምንም ሳይሰሩ ከመግባት›› ሲል አብርሃ ሀሳቡን አካፈለ፡፡

ቂሊንጦ ከእነ በፍቃዱ ጋር ስንጨዋወት ስለእስክንድር ነጋ ትሁትነት፣ አስተዋይነት፣ ሰላማዊነት እያነሱ ሰላምታ እንዳደርስላቸው ጠየቁኝ፡፡ እኔም እስክንድር ነጋን ሳውቀው በትሁትነቱ፣ በአስተዋይነቱና በሰላማዊነቱ ነው፡፡ ዛሬ በነበረው ሁኔታ ግን ክፉኛ ተበሳጭቶ ነበር የተመለከትኩት፡፡ ያ ፈገግታው ከፊቱ ብን ብሎ ጠፍቶ ‹‹ያገባኛል!›› ሲልበት የነበረውን ስሜት ግር አለኝ፡፡ ካልነኩት የማይነካ ሰው ሲነኩት ትንታግ ነው፡፡ እስክንድር እዛ ስሜት ውስጥ የገባው ተገድዶ ነበር፡፡ ሊጠይቁት የመጡትን ሰዎች አብዛኞቹን አላስገባም ማለታቸው ሳያንስ ከገቡትም መካከል የምታወራውን እኔ ልምረጥልህ በሚል ግብዝነት አባርረዋል፡፡ እስክንድር ይህን አይቶ ዝም ማለት አልቻለም፡፡ ስለሆነም እንዲህ አለ፤

‹‹…እዚህ ከሚጠይቁኝ ሰዎች ጋር የፈለኩትን ማውራት እችላለሁ፡፡ እናንተ ከፈለጋችሁ በር ላይ መልሷቸው እንጂ እኔ ጋር ከመጡ በኋላ ስለሀገሬ ከእነሱ ጋር መነጋገር መብቴ ነው፡፡ አዎ የትም ቦታ ብሆን፣ መቼም ቢሆን ስለ ሀገሬ ያገባኛል! የማወራው ስለ ሰላማዊ ትግል፣ ስለህጋዊ ትግል ነው! ስለሀገሬ ያገባኛል!››

ከ40 በላይ የአንድነት አባላትና አመራሮች በቃሊቲ እስር ቤት ታገቱ

የአንድነት ፓርቲ የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ አስራት አብርሃን ጨምሮ ከአርባ በላይ የሚሆኑ የፓርቲው አባላት ቃሊቲ እስር ቤት ውስጥ ታገቱ፡፡

አንድነት ፓርቲ የሚሊዮኖች ድምፅ ለህሊና እስረኞች በሚል መሪ ቃል ከህዳር 14 ጀምሮ እያካሄደያለው የማህበራዊ ሚዲያ ንቅናቄ አካል የሆነውን የህሊና እስረኞችን የመጎብኘት መርሀ-ግብር ለመሳተፍ ወደ ቃሊቲ እስር ቤት ያቀኑት የአንድነት ፓርቲ የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ አስራት አብርሃ እና የፓርቲው የአዲስ አበባ ሰብሳቢ አቶነገሰ ተፋረደኝን ጨምሮ 40 የአንድነት ፓርቲ አባላት ለግዜው ምክንያቱ ባልታወቀ ሰበብ በእስር ቤቱ ግዜያዊ ማቆያ እንዲገቡ መደረጋቸውን የፍኖተ ነፃነት ምንጮች ከስፍራው ዘግበዋል፡፡
አንድነት የሚሊዮኖች ድምፅ ለህሊና እስረኞች በሚል መሪቃል በዚህ ሳምንት እያካሄደ ያለው ንቅናቄ በብዙ ሺዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያዊያንን ትኩረት ማግኘቱ ገዢውን ቡድን ማስቆጣቱ መዘገቡ ይታወሳል፡፡ Thursday, November 27, 2014

ብዕሩም አንደበቱም እውነተኛ ሰው ያስብለዋል። አቶ በቀለ ገርቦ የሚሊዮኖች ድምፅ ቀጣይ መርሀ ግብሮች


ነሐሴ 21/2003 ዓ/ም ከምሠራበት ቦታ በስልክ ተጠርቼ በተለምዶ ማዕከላዊ ተብሎ ከሚጠራው የፌዴራል ወንጀል ምርመራ ዘርፍ ተወስጄ ከአንዲት ትንሽ ጨለማ ክፍል ውስጥ ከተወረወርኩ በኋላ በማግስቱ አራዳ ወረዳ ፍ/ቤት ቀርቤ የሃያ ስምንት ቀን የምርመራ የጊዜ ቀጠሮ ተጠይቆብኝ ተፈቅዶላቸው ያም ሲያልቅ እንደገና ሌላ ቀጠሮ ተጠይቆ ተፈቅዶላቸው፣ የማይመለከቱኝን ጥያቄዎች ስጠየቅና ስመልስ ቆይቼ ጥቅምት 3/2004 በፌዴራሉ ከፍተኛ ፍ/ ቤት 3ኛ ወንጀል ችሎት ቀርቤ የክስ ወረቀት ደርሶኝ ወደ ቃሊቲ ማረሚያ ቤት ተልኬ እነሆ እስከዛሬ ድረስ ዞን አንድ ቅጣት ቤት ተብላ በምትጠራው ቤት እገኛለሁ፡፡ 

የቀረበብኝ ክስ የኢ.ፌ.ዴ.ሪ የወንጀል ህግ አንቀጽ 241 የተመለከተውን በመተላለፍ የአገሪቱን የፖለቲካና የግዛት አንድነት በመንካት ወንጀል ሲሆን ዝርዝሩ፡- “የኦሮሞ ነፃነት ግንባር /ኦ.ነ.ግ/ አባል በመሆን ሶሎሎ ጐልቦ ሥልጠና ወስደሃል፤ በጥር ወር 2002 ዓ/ም በአምቦ ከተማ ኦ.ነ.ግ በቅርብ ወደ አገር ውስጥ አሸንፎ ይገባል፤ ከጐኑ ቆመን በሥልጣን ላይ ያለውን መንግስት መጣል አለብን ብለህ መመሪያ ሰጥተሀል፤ በሐምሌ 2003 ዓ/ም ተማሪዎችንና ህዝቡን ለአመጽና ለብጥብጥ እንዲነሳሱ ቅስቃሳ አካሂደሀል፤ እንዲሁም በ2004 ዓ/ም በመላው ኦሮሚያ አመጽና ብጥብጥ በማስነሳት በሥልጣን ላይ ያለውን መንግሥት መጣል አለብን በማለት ትዕዛዝ አስተላልፈሀል፤ በዚሁ ወር የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ መምህርነትህን ሽፋን በማድረግ ቢሮህ ተገኝተው የመመረቂያ ጽሁፍ ሊሰጡህ የመጡትን ተማሪዎች በሥልጣን ላይ ያለውን መንግስት በሃይል ከሥልጣን እናውርድ በማለት መመሪያ ሰጥተሀል” የሚል ነው፡፡ 

እነዚህ የቀረቡብኝ ክሶች ፈጽሞ የሀሰት ውንጀላዎች መሆናቸውን ለማስረዳት በመጀመሪያ ደረጃ ትጥቅ ትግልና ሰላማዊ ትግልን አስመልክቶ ያለኝን አቋምና እምነት ባጭሩ ከገለጽኩ በኋላ በቀረቡብኝ ምስክሮችና የሠነድ ማስረጃ ላይ ያሉትን እውነታዎች አቅርቤ በአጭሩ የማጠቃለያ ሀሳብ እደመድማለሁ፡፡ 

1.የትጥቅ ትግል በአንድ ወገን ድል አድራጊነት የሚጠናቀቅ እንደመሆኑ አሸናፊውን ወገን ክብርና የበላይነትን ሲያጐናጽፍ ተሸናፊውን ወገን ደግሞ የውርደትና የበታችነት ስሜት ይፈጥርበታል፡፡ በዚሁ የተነሳ ተሸናፊው ወገን ቂም አርግዞ ጊዜውን ጠብቆ አድፍጦ የሚያደባበት ስለሆነ እውነተኛ ያልሆነ አሉታዊ ሠላም የሰፈነበት ነው፡ ፡ ፖለቲካውም የምሬት፣ የጥላቻ የበቀልና የጠላትነት ስለሚሆን እስራት፣ ስደት፣ ከሥራ መፈናቀልና ሌሎች ምስቅልቅሎችን ያስከትላል፡፡ ይህን የትግል ዘዴ በታሪካችን ደጋግመን ሞክረነዋል፡፡ መዘዙንም ቀምሰነዋል፤ ለኋላ ቀርነታችን አንደኛው ምክንያት ሆኗልና፡፡ በአንፃሩ ግን ሠላማዊ ትግል አሸናፊና ተሸናፊ ስለሌለው መቋጫው እርቅ ወንድማማችነትና ዘላቂ ሰላም ነው፡፡ አውንታዊ ሠላም ፖለቲካውም ልዩነትና ብዙሀንነት ስለሚያስተናግድ የሚማረር ወገን አይኖርም፡፡ ስለዚህ ተመራጭ ብቻ ሳይሆን ብቸኛ የትግል ዘዴ መሆን አለበት የሚል እምነት ስላለኝ ህጋዊ በሆነ የፖለቲካ ድርጅት ውስጥ በመሳተፍ የድርሻዬን በማበርከት ላይ እገኛለሁ፡፡ 

2.የትጥቅ ትግል አሸናፊው ቡድን የአልበገር ባይነት ስሜት እንዲሰማውና እብሪተኛና ጨካኝ እንዲሆን ከማድረጉም በላይ ድሉን ለማግኘት ለከፈለው መስዋዕትነት ካሳ ፈላጊ እንዲሆን ያደርገዋል፡፡ በዚህ ምክንያት ሥልጣንንና የሀብት ምንጮችን ጨምድዶ በመያዝ በትግሉ ያልተሳተፉትን በማግለል ፍትሀዊ ክፍፍልን አዛብቶ የዜጐችን የእኩልነት መብት ወደ መርገጥ ያመራል፡፡ ውሎ ሲያድርም ይህን ስህተቱን ማረም ስለሚሳነው የሃሳብ ልዩነትን የማይቀበል አምባገነን ይሆናል፡፡ በዚህ ምክንያት መብታቸውን የሚጠይቁ ዜጐችን በጠላትነት ፈርጆ ሊያጠፋቸው ሕጋዊ የሚመስል ህገወጥ ድርጊቶችን በስውርና በግልጽ በመፈጸም ለሌላ ትጥቅ ትግል በር ይከፍታል፡፡ ይህን የትጥቅ ትግል ዑደት አንድ ቦታ ላይ ሰብሮ በማቆም አገሪቱን ከትርምስና የመገዳደል ባህል መታደግ የሚቻለው ራሳቸውን ለአደጋ አጋልጠው ሳይገድሉ እየሞቱ እየታሠሩና ከሥራ እየተፈናቀሉ በሠላማዊ መንገድ ብቻ በሚታገሉ ኃይሎች አማካኝነት ነው ብዬ አምናለሁ፡፡ መርጬ እየተጓዝኩበት ያለሁትም ይህን ነው፡፡ 

3.የትጥቅ ትግል ሰብዓዊና ቁሳዊ ሀብትን ከማውደሙም በላይ ጊዜያዊም ቢሆን ሥርዓተ አልበኝነትን ያስከትላል፡ ፡ በጣም ውስን በሆነች የሀገር ሀብት አንዱ የገነባውን ሌላው እያፈረሰ የሚሄድ ከሆነ መጨረሻችን የት ሊሆን እንደሚችል መገመት አያስቸግርም፡፡ የትጥቅ ትግል ለዜጎች ስንዴና ዘይት እንኳን ማቅረብ የማይቻል እንደኛ ያለ አገር ቀርቶ የሚዋጉበት በጦር መሳሪያ ለሚያመርቱ አገሮች እንኳን አዋጭ ስላልሆነ ዘለው አይገቡበትም፡፡ ብጥብጥና ሁከት በሚነሳባቸው አገሮች ዋነኞቹ ተጐጂዎች ተራ ዜጎች እንጂ እንደከሳሾቼ ያሉ ባለሥልጣናት ወይም የመንግሥት መሪዎች አይደሉም፡፡
በኛ አገርም ይህ ሁኔታ ቢከሰት ግንባር ቀደም ሰለባ መሆን ከሚችሉት ውስጥ እኔና ቤተሰቤ እንገኛለን፡፡ ምክንያቱም የምጓዘው በተራ ትራንስፖርት፤ የምኖረው በተራ መንደር በተራ ቤት፣ ልጆቼ የሚማሩት በተራ ትምህርት ቤት ሲሆን ከሳሾቼ ግን ይህ ሁሉ የማይመለከታቸውና የማያስጋቸው በመሆኑ ከነሱ የበለጠ ሠላም ለኔ ትልቅ ዋጋ አለው፡፡ ስለዚህ ነው ምንም ዓይነት ዜግነት፣ ቀለም ወይም ዘር ይኑርው ስብአዊና ቁሳዊ ውድመትን የሚያስከትል ጦርነትም ሆነ ብጥብጥ ከሚራምድ አካል ጋር የማልተባበረው 

4.በትጥቅ ትግል ወደ ሥልጣን የሚመጡ መንግስታት ከውይይትና ድርድር ይልቅ በኃይል መፍትሔ ስለሚያምኑ ዴሞክራሲያዊ አካሄድን ከማቀጨጭ አልፎ እስከነአካቴው ይፃረራሉ፡፡ ለይስሙላ በሚገኙባቸው የድርድር መድረኮችም ሌላም ወገን እንዲቀበል የሚፈልጉትን ለመንገር እንጂ ሰጥቶ ለመቀበል ስላልሆነ በድርድሩ ማግስት ወደ ቀድሞ የኃይል ተግባራቸው ይመለሳሉ፡፡ ህዝቡ የጦር ሜዳ ገድሎቻቸውን አይቶና ሰምቶ አይበገሬነታቸውን ተረድቶ በፍርሃት እንዲገዛላቸው ሚዲያውን በጦርነት ወሬ ያደምቃሉ፡፡ 

በሰላማዊ ትግል አግባብ ስልጣን የሚይዙት ግን የስልጣናቸው ምንጭ የሆነው ሕዝብ ጥቅሙና መብቱ ካልተጠበቀለት ነገ ደግሞ ለሌላ መስጠት እንደሚችል ስለሚገነዘቡ ዜጐቻቸውን ያከብራሉ፤ ከመፍራት ይልቅ መከበርን ይሻሉ ከመናገር ይልቅ ማዳመጥን ያስቀድማሉ፡ ፡ እውነተኛ ዴሞክራሲን በማስፈን ሕዝባቸውን ወደ ዘላቂ ሰላምና እድገት ይመራሉ፡፡ እንደዚህ ዓይነት ሰላማዊ ትግል ነው እንዲካሂድ የምሻውና ዋጋ እየከፈልኩበት ያለው፡፡ 

5.በእምነት ዝንባሌዬ ነፍስ የፈጣሪዋ ብቻ ስለሆነች የሰውን ልጅ ነፍስ ማጥፋት ከወንጀል አልፎ ኃጢአት መሆኑንና ይህን ክቡር ነገር በኃይል ከሰው የሚነጥቁ ሁሉ በተመሳሳይ መንገድ እንደሚነጠቁ በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ “ሠይፍ የሚመዙ በሠይፍ ይጠፋሉ” የሚለውን መለኮታዊ ቃል አምናለሁ፡፡ ስለዚህ የኃይል ተግባርን እንደአማራጭ ወስጄ አላውቅም፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘ ፈጣሪ እውነት ነው፤ በፈጣሪ የሚያምን ሁሉ እውነትን ያመነ ማለት ይገባዋል፡፡ “እውነትን ሲሻና ለፍትህ ሲከራከር በፍቅር ብቻ ማድረግ አለበት” የሚለውን የጋንዲ “ሳትያግራሀ” ፍልስፍና እቀበላለሁ፡፡ “ሳትያግራሀ” “የእውነት ኃይል፤ የፍቅር ኃይል” ማለት ሲሆን ጥቃት ለሚሰነዘር ሰው አፀፋ ሳይመልሱ በፍቅር ቀርቦ በውስጥ ያለውን መልካም ነገር በማንቀሳቀስ በህሊና ወቀስ ከክፉ ሥራው እንዲመለስ ማድረግ ይቻላል፡ ፡ የሚል ፍልስፍና ነው፡፡ ይህ የሰላማዊ ትግል የመጨረሻ ተሞክሮ በሰላማዊ ታጋዩ ወይም ሳትያግራሂው ላይ ከፍ ያለ ሥቃይን የማያስከትል እንደመሆነ በአስተሳሰቦች በሞራላዊነታቸውና በትዕግሥታቸው የላቀ ደረጃ ላይ የደረሱ ሰዎች ብቻ የሚተገብሩት ነው፡፡ ከሳትያግራሀ የሰላማዊ ትግል ስልቶች አንዱና ዋነኛው ከክፉ ሥራ ጋር ያለመተባበር ነው፡፡ እኔም አንድን ዓላማ ለማሳካት ኃይልን ከመጠቀም የበለጠ ክፉ ነገር አለ ብዬ ስለማሰብ ከእንዲህ አይነት ተግባር ጋር ተባብሬ አላውቅም፡፡ እንግዲህ ትጥቅ ትግል ውስጥ ያልተሳተፍኩት እላይ በጠቀስኳቸው ምክንያቶች እንጂ በማንምና በምንም ፍራቻ አሊያም አጋጣሚ አጥቼ አልነበረም፡፡ ከሳሾቼ እንደሚሉት ልጆች ሳላፈራና በትምህርት ሳልገፋ በአፍላ የወጣትነት ጊዜዬ ያላሰብኩትን ድንገት በሃምሳኛ ዓመት እድሜዬ ላይ በተራ የኦ.ነ.ግ ተዋጊነትና ካድሬነት ለመሠልጠን ኬንያና ሰሎሎ አልሄድኩም፡፡ 

ነፍስ ካወቅሁ ጊዜ ጀምሮ የሰው ልጆች መብት እንዲከበር ጽኑ ፍላጎና አቋም የነበረኝ ቢሆንም ሁሉም ሰው ፓለቲከኛ መሆን አለበት የሚል እምነት ስላለነበረኝ እስከ 2002 ዓ/ም ድረስ የማንኛውም ፖለቲካ ፓርቲ አባል ሆኜ አላውቅም፡፡ ተሰጥኦውና ዝናባሌው ያላቸው ጥቂቶች የፖለቲካ ማህበር መስርተው ለስልጣን ተወዳድረው ህዝባቸው በፍትሀዊነት ማስተዳደር ከቻሉ ሌሎች ዜጐች በተለያየ ሙያ ተሰማርተው አገራቸውን ማገልገል አለባቸው ብዬ ስለማምን እኔም በመምህርነት ሙያ ብቻ ተሰማርቼ ተግባሬን በትክክል ስወጣ ኖሬያለሁ፡፡ 

ይሁን እንጂ የፖለቲካ ድርጅቶች የሰዎች ስብሰብ እንደመሆናቸው መጠን ሁሉን ነገር ያለእንከን ይፈጽማሉ ብሎ ማመን ስለማይቻል ጊዜ ሊሰጣቸው እንደሚገባ በመረዳት ኢትዮጵያን እያስተዳደረ ያለው ፓርቲ የሚሰብከውን መተግበር እየተሳነው ሲሄድ ወይም በተፃራሪው ሲተገብር ሆን ብሎ አለመሆኑን ለራሴ ለማሳመን ሃያ አመታት ያህል ጥረት አድርጌያለሁ፡፡ በመጨረሻም በመላው የኢትዮጵያ ህዝብ ላይ በተለይ ደግሞ በኦሮሞ ሕዝብ ላይ የሚደርሰውን በደል ዝም ብሎ መመልከትን ህሊናዬ አልቀበል አለኝ፡፡ 

– ሦስት መቶ የዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ጥያቄ እንኳን ሳይቀርብላቸው በአንድ ቀን ሲባረሩ
– በየዩኒቨርስቲው ያሉ ሌሎች ደግሞ በየዓመቱ ሲደበደቡና ሲንገላቱ
– የፋብሪካ ዝቃጭ አተላዎች በማንአለብኝነት ህዝብ ወደሚጠጣቸው ወንዞች ሲለቀቁና አደጋ ሲያስከትሉ
– ለፌዴራሉ መንግስት ከፍተኛውን ገቢ የሚያስገባ ህዝብ በአንፃሩ ግን በነፍስ ወከፍ እጅግ ዝቅተኛው የፌዴራል በጀት ድጐማ ሲመደብለት
– መሬቱ በስበብ አስባቡ በግፍ እየተወሰደ ተቸብችቦ ሌሎችን ባለፀጋ ሲያደርግ፤ የሱ ቤተሰቦች ግን የትም ሲበተኑ
– ቋንቋው ቀድሞ ሲነገር ከነበረበት ቦታ እየጠፋ ሲሄድ
– ከኤኮኖሚው ዘርፍ ወጥቶ የበይ ተመልካች ሲሆን
– የዛሬ 120 ዓመት የኦሮሞ መንደር በነበረቸው ፊንፊኔ በቋንቋው የሚማርበት አንድ ት/ቤት ወይም አንድ የእምነት ሥፍራ እንኳ ሲነፈገው
– የፌዴራል ሠራተኞች ቅጥርና የመከላከያ ሠራዊቱ አመራር ብሔራዊ ተዋጽኦ አግባብ ባልሆነ መልኩ ሲከናወን
– ከሁሉም በላይ ደግሞ ገዥው ፓርቲ ሥልጣን ሲይዝ በእስር ቤት ከነበሩ ኦሮሞ፣ ዛሬ በብዙ እጥፍ የሚሆኑት በፌዴራል ወህኒ ቤቶች ሲማቅቁና ቤተሰቦቻቸው በረሃብ አለንጋ ሲገረፉ እያየሁ ዝም ማለት እንዴት ይቻለኛል?
እነዚህ ነገሮች እንዲሰተካከሉ ህገ መንግስቱ በሚፈቅደው መሰረት በሠላማዊ መንገድ አስተዋፅኦ ለማድረግ የአንድ ፓርቲ አባል መሆንን ሳውጠነጥን የኦሮሞ ፌዴራሊስት ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ /ኦ.ፌ.ዴ.ን/ ጥሪ አድርጐልኝ በ2002 ዓ/ም ለመጀመሪ ጊዜ አባል ሆንኩ፡፡ ከዚያም የድርጅቱ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባልና የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ አንድነት መድረክ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባል ሆንኩ፡፡ በ2002 ዓ/ም ለህዝብ ተወካዮች ም/ቤት ዕጩ ተወዳዳሪ ሆኜ መላው ሕዝባችን በሚያውቀው ሁኔታ ተሸነፍኩ፡፡ በምርጫ ዘመቻ ወቅትም በግልና በቡድን የተካሄዱብኝን ትንኮሳዎች ተቋቁሜ መንግሥት ባሰማራቸው ሁከት ፈጣሪዎች መካከል ቆሜ ለሠላማዊ ትግልና ለዴሞክራሲያዊ ሥርዓት እውን መሆን ያለኝን ቁርጠኝነት አስመስክሬያለሁ፡፡ ምርጫውን እንደማላሸንፍና መጨረሻዬም አሁን ያለሁበት እስር ቤት እንደሆነ እየተነገረኝ አንድ ሰላማዊ ታጋይ ማድረግ ያለበትን አድርጊያለሁ፡፡ 

በፖርቲዬ ውስጥ በተሰጠኝ የሕዝብ ግንኙነት የሥራ ድርሻ ምክንያት በእስር ላይ ስላሉ ኦሮሞዎች ሁለት ጊዜ ያህል ለውጪ ሚዲያዎች ቃለ መጠይቅ በመሰብሰብ ከሳሾቼን እንዳላስደስታቸው ከራሳቸው ተነግሮኝ ነበር፡፡ ነገር ግን የሰጠሁት መረጃ ሀሰትም፣ ምሥጢርም እንዳልሆነ ነግሬያቸው በተያየን በሃያ ቀናት ከቢሮዬ ተጠርቼ ታሰርኩ፡ ፡ ከመታሰሬ ጥቂት ቀናት በፊት ከአምነስቲ ኢንተርናሽናል የመጡ ሰዎች አነጋግረውኝ ነበር፡፡ የእነዚህ ነገሮች ድምር ነው “የአገርና የሕዝብን አንድነት በማፍረስ” ወንጀል አስከስሶ ለእስራት የዳረገኝ፡፡ 

በሕዝቦች መካከል ግልጽ ልዩነት እየፈጠረ አንዱ ሌላውን እንዲጠራጠር ኅብረቱ እንዲላላና አንድነቱ እንዲፈርስ እያደረገ ያለ ሥርዓቱ ነው ወይስ ይህ ሁኔታ እንዲሰተካከል በሰላማዊ መንገድ እያሳሰበ በመታገል ላይ ያለ ሰው ነው የአገሪቱን የግዛትና የፖለቲካ አንድነት በማፍረስ ወንጀል የሚጠረጠረው? ህገ መንግሥቱን በተግባር እየጣሰ ያለውስ መብቴ ይከበር የሚለው ነው ወይንስ መብቱን የገፈፈው ነው?
ድርጅታችን በኢ.ፌ.ዴ.ን ህዝቦች መብታቸው እስከተከበረላቸው ድረስ የመገንጠል ጥያቄ አያነሱም መለየትንም አይፈልጉም የሚል እምነት ስላለውና የአገር አንድና ቁልፍ እውነተኛ እኩልነት የሰፈነበት ሥርዓት ማስፈን መሆኑን ያምናል፡፡ 

ስለዚህ በኢ.ፌ.ዲ.ሪ ህገ መንግሥት አንቀጽ 39 ንዑስ አንቀጽ 1 ላይ ያለው እስከመገንጠል የሚለው ሀረግ ጠቃሚ አይደለም በሚል እምነት በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክረሲያዊ አንድነት መድረክ መለስተኛ የፖለቲካ ፕሮራም ውስጥ እንዲካተት ከፈረሙት አባል ድርጅቶች ውስጥ አንዱ ነው፡፡ እኔም የድርጅቱ አባልና አመራር ይህን ለማሳመን ጉንበስ ቀና በምልበት ሰዓት የአገር አንድነትን ለማፍረስ በመሞከር እንዴት ልከሰስ እችላለሁ?
ማንኛውም ኦሮሞ መብቱን የመጠየቅ አዝማሚያ ወይም ከሥርዓቱ ጋር ያለመተባበር ዝናበሌ ያሳየ እንደሆነ በኦነግነት ፈረጆ ማናቸውንም የግፍ ተግባር መፈፀም ከተጀመረ ሃያ አመታት ተቆጠሩ፡፡ ይህ አድራጎት በአፍሪካ ደረጃ እንኳን ሲታይ ወደር የለሽ ነው፡፡ ናይጄሪያ በየጊዜው ፍንዳታ እያደረሰ ኃላፊነት በሚወስደው የቦኮሃራሞ ድርጅት አግባብ ተመሳሳይ ቋንቋ የሚናገሩና ተመሳሳይ እምነት የሚከተሉ ዜጐቿን ቁም ስቅል አላሳየችም፡፡ የወደቀው የግብጽ መንግስት እንኳን ህገወጥ ነው ብሎ በፈረጀው የሙስሊም ወንድማማቼች ፓርቲ አመካኝቶ ተቀናቃኞችን ለማጥፋት ዘመቻ አልከፈተም፡ ፡ ከአንድ የዘር የተገኘ ሁሉ አንድ አይነት የፖለቲካ አመለካከት አለው ብሎ የሚገምት ቢኖር በሥልጣን ላይ
ያለው የኢትዮጵያ መንግስት ብቻ ይመስለኛል፡፡ አገር የሚያፈርሰው እንዲህ አይነት አመለካከት ነው፡፡ እኔ ግን ይህን በመርህም ተቀብዬ በተግባርም ሞክሬ አላውቅም፡፡
ነገር ግን ለሥርዓቱ ካለመመቸት ውጪ በሀገሬና በሕዝቤ ላይ አንዳች ጥፋት እንዳልፈፀምኩ ጠንቅቀው የሚያውቁት ከሳሾቼ በወህኒ ቤቶች አካባቢ “አዳፍኔ” በመባል የሚታወቁ የሀሰት ምስክሮችን አቅርበው አስመስክረውብኛል፡፡ በመጽሐፍ ቅዱስ 1ኛ ነገሥት ምዕራፍ 21 ላይ አጽመርስቴን አልለቅም ስላለ “ንጉሡንና እግዚአብሔርን ሰድቧል” ብለው የሀሰት ምስክሮችን አስመስክረው ናቡቴን በድንጋይ አስወግረው እንዳስገደሉት የአክአብ ባለሥልጣኖች የሰው ልጆች መብት ይከበር ባልኩ ኢትዮጵያዊው ናቡቴ ሆኜ ቀርቤያለሁ፡፡ ይህ ድርጊት ከዚህ መዘምር ከሳሾች እራሳቸው ሲኒማ ቤት ውስጥ የእጅ ቦምብ ወርውረው ብዙ ሰዎችን ካቆሰሉ በኋላ ይህን ያደረገው ማሞ ነው በማለት በሀሰት አስመስክረው ሞት ተፈርዶበት አለም በቃኝ እስር ቤት ውስጥ በስቃላት ተቀጥቷል፡፡
በኔ ላይ የቀረቡት የአቃቤ ህግ ምስክሮች በቁጥር አራት ሲሆኑ ሁለቱ ቤቴ ሲፈተሸ ታዛቢ የነበሩ ናቸው፡፡ ሁለቱም ያዩትን በመመስክራቸው በምስክርነት ቃላቸው ውስጥ ወንጀለኛ የሚያሰኘኝ ነገር ባለመኖሩ ሌሎች ሁለት ምስክሮች በሰጡት የሀሰት ምስክርነት ቃል ላይ አተኩራለሁ፡፡ የአቃቤ ሕግ ምስክር ሆኖ የቀረበብኝ አንደኛው ሰው በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ተማሪዬ ሆኖ የተመደበ የክረምት ተማሪ ኢዮስያስ አበራ ማሞ ከሌሎች ተማሪዎች ተነጥሎ ቢሮዬ መጥቶ የገዥው ፓርቲ አባል እንደሆነ ይህን ያደረገውም የደህንነት አባል የሆነውን አባቱን በመፍራት እንደሆነ አሁን ግን በፓርቲው ውስጥ የሰፈነውን ኢፍትሐዊነት በመፀየፍ የአንድ ተቃዋሚ ፓርቲ አባል መሆን እንደሚፈልግ በተለይም ደግሞ የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ አንድነት መድረክን እንደሚያደንቅ ነግሮኝ እንድመለምለው ጠይቆኝ ነበረ፡፡ እኔም እኔ ያለሁበት ፓርቲ የኦሮሞ ድርጅት እንደሆነና የመድረክ አባላት ከሆኑ ህብረብሔር ፓርቲዎች ውስጥ ወስኖ አንዱን መጠየቅ እንዲሚችል ነግሬው የአንድነት ለፍትህና ለዴሞክራሲ ፓርቲ አመራር አባል የሆነውን የአቶ አንዱአለም አራጌን ስልክ ቁጥር ሰጠሁት፡፡

ግለሰቡ ክቡር ፍ/ቤቱ ፊት ቀርቦ ቃሉን ሲሰጥ ተማሪዬ እንደሆነ ኮርስ ሰጥቼው እንደማላውቅ ለመጀመሪያ ጊዜ የተገናኘነው ሐምሌ ወር 2003 ዓ/ም የመመረቂያ ጽሁፉን ሊያስረክብ ቢሮዬ በተገኘበት ዕለት መሆኑን በዚሁ የመጀመሪያ ግኑኝነታችን “መንግሥት የኦሮሞንና የደቡብን ህዝብ ስለሚጠላ ይጨቁናቸዋል፣ ስለዚህ ተነሳስተን በአመጽ እናስወግደው” እንዳልኩት ተናግሯል፡፡ ሌሎችንም ተማሪዎች ጨምሮ እንደተወያየን አስመስሎ መስክሯል፡፡ 

ይህ ግን ፈጽሞ ሀሰት ነው፡ ፡ ግለሰቡ አግኝቶኝ የማያውቅ ከሆነ በሐምሌ 2003 ዓ/ም ሊያስረክበኝ የመጣው የመመረቂያ ጽሁፍ ማን ያማከረውን ነበር? ከአማካሪው ጋር አንዳች ግንኙነት ሳያደረግ ምንነቱ ያልታወቀ የመመረቂያ ጽሁፉን ይዞ ከመጣ ተማሪ ጋር ያውም በመጀመሪያው ግንኙነት ከአካዳሚ ነክ ጉዳዮች ወጥቶ ስለ መንግስት ግልበጣ ማውራት ይታሰባል ወይ? ለአንድ የዩኒቨርስቲ መምህር ተመካሪ ተማሪዎች የሚመደቡት በሚመለከተው ትምህርት ክፍል እንደመሆኑ የተለያየ ፖለቲካ ዝናባሌ እንዳላቸው እየታወቀ አንድን ወገን ብቻ በሚመለከት ፖለቲካ ውይይት መክፈት እንዴት ይታሰባል? የተከሰሰኩት በአሽባሪነት ከተፈረጀ የኦሮሞ ድርጅት ሆኖ ሳለ ግለሰቡ ደግሞ የዚህ ማህበረሰብ አባል አለመሆኑን በግልጽ እየተናገረ፤ ኦሮሞዎች ተበድለዋልና በመንግስት ግልበጣ ተባብረን ልል እንዴ እችላለሁ? ይህ ሰው ኦሮሞዎችን ከጭቆና ለመታደግ ከሰማየ ሰማያት የተላከ አዳኝ ነው ብዬ ልገምት አልችልም፡፡ ይልቅ እሱስ ፍትህን ሲገድል የተመደበ የአክአብ ምስክር ኖሯል፡፡
ሌላኛው ስሜን እንኳን በትክክል ያላስጠኑት የአቃቤ ሕግ ምስክር አመና አርኮ በክቡር ፍ/ቤቱ ፊት ቀርቦ ቃሉን ሲሰጥ “በጥር ወር 2002 ዓ/ም አቶ ጉቱ ሙሲሳ ቤት ተገናኝተን ለአመጽ አነሳስቶኛል” ሲል ተናግሯል፡፡ 

እኔ ይህን ግለሰብ ለመጀመሪያ ጊዜ ያየሁት ከዚሁ ፍ/ቤት ውስጥ ነው፡፡ ነገሩ የማይታመንና ዱብዕዳ ስለነበረ በዕለቱ ጥያቄም አላቀረብኩለትም፤ ስለማንነቱ ለማወቅ ባደረግሁት ጥረት በቂና ተጨባጭ መረጃዎችን ለማግኘት ችያለሁ፡፡ ግለሰቡ እውነተኛ ማንነቱ ኢመና ኢርኮ ሳይሆን ሺፈራው ኤቢዳ ሲሆን የትውልድ ሥፍራው በምዕራብ ሸዋ ዞን ሸነን ወረዳ ሆኖ አድራሻዬና የሥራ ቦታዬ ነው ያለውን ነቀምቴ ከተማ 01 ቀበሌን ረግጦ እንኳን አያውቅም፡፡ 

ይህ ግለሰብ የኦሮሞ ህዝብ ኮንግረስ /ኦ.ህ.ኮ /አባል የነበረ ሲሆን በ1997 ዓ/ም የምርጫ ታዛቢ ስነበር በ1998 ዓ.ም ታስሮ የተሠቃየ በ1999 ዓ.ም አጣሪ ኮሚሽን ፊት ቀርቦ ቃሉን የሠጠ በ2000 ዓ/ም ኦህኮን ወክሎ ለወረዳና ለቀበሌ ምርጫ የተወዳደረ፡ ፡ በ2003 ዓ/ም እንደገና ታስሮ የነበረ ሲሆን ይህን ሁሉ ያደረገው በእውነተኛ ስሙ ነበር፡ ፡ በመጨረሻም ከደረሰበት ስቃይ የተነሳ እንዲሁም የሚሉትን እሺ ካላለ መኖር እንደማይችል ስለተገለጸለት ያሉትን ሁሉ ለማድረግ ቃል ግብቶ በመፈታት በኔ ላይ በምስክርነት የቀረበ ነው፡፡ ይህንን የመከላከያ ምስክሮች ያስረዱልኛል፡፡
ከላይ እንደገለጽኩት ከግለሰቡ ጋር በአካልም ሆነ በማንኛውም የመገናኛ ዘዴ ተገናኝተን የማናውቅ ከመሆን አልፎ ቤቱ ተገናኘን ያለውን አቶ ጉታ ሙሊሳን እንኳን ለመጀመሪያ ጊዜ ያየሁት ማረሚያ ቤት ሁለታችንም እስረኞች ሆነን ነው፡፡ ይህንንም ምስክሮቼ ያረጋገጡልኛል ለመሆኑ በ2002 ዓ.ም ህገ መንግሥቱን አምኜና አክብሬ በምርጫ ለመሳተፍ ዝግጅት ላይ የነበርኩ ሰው እንዴት ሆኖ ለአመጽ ቅስቀሳ ማካሄድ የምችለው?
ከዚህ መረዳት እንደሚቻለው ግለሰቡ በኔ ላይ ስለመሰከረው ነገር ብቻ ሳይሆን ማንነቱንና አድራሻውን ጭምር እንዲዋሽ የተገደደ እንደመሆኑ መጠን ክቡር ፍ/ቤቱ ይህን ተመልክቶ የሰጠውን የምስክርነት ቃል ውድቅ እንዲያደርገልኝ እጠይቃለሁ፡፡
አቃቤ ህግ ወንጀለኛ ለመሆኔ እንደአስረጂነት ያቀረበው ሌላው የሠነድ ማስረጃ በ1989 ዓ/ም መጀመሪያ ላይ የተነሳሁት የኦነግ አርማ ተሰቅሎ የሚታይበት ፎቶ ግራፍ ነው፡፡ በ1983 ዓ.ም መጨረሻ ደረግ እሠራበት የነበረችውን ዓለም ተፈሪ ከተማ ለቆ ሲሄድ ብዙ ሰዎች አካባቢውን ለቀው ሲሰደዱ ሠላምና መረጋጋትን ለመፍጠር የተቋቋመውን ኮሚቴ እንድመራ በህዝብ ተመርጬ እስከ 1984 ዓ/ም መጨረሻ ድረስ ሰርቻለሁ፡፡ በዚህ ወቅት በከተማው ፍ/ቤት ከፍተው በይፋ ይንቀሳቀሱ ለነበሩ ሁለት የኦሮሞ ድርጅቶች ኦህዴድና ኦነግ ስብሰባዎችን እየጠራሁና እየመራሁ በገለልተኝነት ሥሰራ ቆይቻለሁ፡ ፡ በነዚህ ጊዜያት ውስጥ ለኦህዴድ በርካታ ስብሰባዎችን ለኦነግም ጥቂት ሰብሰባዎችን ከተማው መሃል በሚገኝ የወረዳው አስተዳደር ግቢ ሜዳ ላይ መጥራቴን አስታውሳለሁ፡ ፡ ከነዚህ ስብሰባዎች በአንዱ የተወሰደ ነው የተጠቀሰው ፎትግራፍ ያ ወቅት ሁለት ድርጅቶች እንኳን በመሰብሰቢያ ቦታዎች ቀርቶ በየምሶሶዎቹና ዛፎቹ አርማቻቸውን ይሰቅሉ የነበረ የትኩሳት ጊዜ ነበር፡፡
ኢፍትሐዊነትንና አድሎን …
ከ ገፅ 15 የዞረ….
በፎቶግራፍ ላይ እንደሚታየው ቁጥሩ ብዙ የሆነ ህዝብ ሜዳ ላይ ተሰብስቦ ይታያል፡፡ እንደሚታወቀው ኦነግ በ1984 ዓ/ም በመጨረሻ ሽግግር መንግሥቱን ለቆ ከወጣ በኋላ እንዲህ ዓይነት ስብሰባ በመሀል ከተማ አደባባይ ሊደረግ ይችላል ተብሎ አይታሰብም፡፡ በፎቶ ግራፉ ላይ የሚታዩ ሰዎች ብዙዎች በህይወት የሉም፡፡ በፎቶግራፉ ላይ የሚታየው የራሴ ገጽታም ከዛሬ ጋር ሲስተያይ የፎቶውን ዕድሜ ይናገራል፡፡ በፎቶግራፉ ላይ የሚታየው ቦታም ዓለምተፈሪ መሆኑ ተለይቶ ይታወቃል፡፡ እኔ ደግሞ በ1985 ዓ/ም ከዚያ ተዛውሬ ስለሄድኩ እና ወደዚያ ለመመለስ እድሉ ስላልነበረኝ፣ ቢኖረኝ ኖሮም ያንን ሰብሰባ ማካሄድ እንደማልችል ይታወቃል፡፡
በአጠቃላይ ከዛሬ ሃያ ዓመት በፊት በወቅቱ ህጋዊ የነበረና በሚኒስትሮች ም/ቤት አራት የካቢኔ ሚኒስተሮች የነበሩትና መዲናዋን (አዲስ አበባን) ጭምሮ በአርማዎቹ አጥለቅልቆት በነበረ ድርጅት አርማ ጋር የተነሳኸው ፎቶ ግራፍ የአገር ግዛትና ፖለቲካዊ አንድነት ለመንካትህ ማስረጃ ነው ተብሎ ሊቀርብብኝ ስለማይገባ ክቡር ፍ/ቤቱ ውድቅ እንዲደረግልኝ እጠይቃለሁ፡፡
ማጠቃለያ
ያለመተደል ሆኖ በአገራችን መልካም አስተዳደር አፈአዊ እንጂ ተግባራዊ ሆኖ ስለማያወቅ አንዱ የሠራውን ሌላው እያፈረሰ በዓለም ፊት በኩራት አንገታችንን ቀና የምናደርግበት ሳይሆን በሀፍረት የምንሸማቀቅበት፤ ለልጆቻችንም ተስፋን ሳሆን የስጋት ቅርስ እየተውንላቸው አበሳን እንደ ዱላ እየተቀባበልን ዛሬ ላይ ደርሰናል፡፡ ይህ እንዳይቀጥል የሳተው በጊዜ እንዲመለስ የተጣመመው እንዲቃና የተበላሸው እንዲስተካከል ጎረቤት ሳይሰማ፣ ፈረንጅ ገመናችንን ሳያውቀው አድብተን ሰንጠፋፋ ችግራችን ገለጥለጥ አድርገን ተወያይተን ተከራክረን ተወቃቅሰን መፍትሔ እናበጅለት፡፡ ይህንንም አንዱ ባንዱ ላይ ዱላ ሳይሰነዝር ቃታ ሳይስብ፣ ወደ እስር ቤት ሳይጎትተው በሠላማዊ መንገድና በፍቅር እናድርገው የሚል ጽኑ አቋም ነው፡፡ እኔና ድርጅቴ የምናራምደው፤ ይህ በኛ በጎ ጥረትና ፍላጎት ብቻ የሚሳካ ባይሆንም እኛ ግን በዚሁ መንገድ እንጓዛለን፤ ኢፍትሃዊነትንና አድልኦን አሜን ብሎ ውርደት ከመቀበል መከራና ስቃይን በክብር ማስተናገዳችንን እንቀጥላለን፡፡ በመጨረሻም ፍትህ ከጎናችን
ትቆማለች፡፡

Wednesday, November 26, 2014

ኢትዮጵያ ከአለማቀፍ የገንዘብ ገበያ ለመበደር ድርድር ጀመረች

 
ኀዳር ፲፯(አስራ ሰባትቀን ፳፻፯ / ኢሳት ዜና :- መንግስት የጀመራቸውን የሃይል፣ የመንገድ፣ የባቡርና የስኳር ፋብሪካዎችን ለመጨረስ የሚያስችለውን ገንዘብ ከአለማቀፍ አበዳሪ ድርጅቶች ለመበደር የሚያስችለውን ድርድር ከሁለት የአውሮፓ እና ከአንድ የአሜሪካ ባንክ ጋር ጀምሯል። መንግስት ገንዘቡን ለመበደር የሚያስችለውን ቦንድ ለገበያ የሚያቀርብ ሲሆን፣ አለማቀፍ አበዳሪ ተቋማትም የመንግስትን የመክፈል አቅም በማየት ብድሩን ይፈቅዳሉ።

መንግስት ከአለማቀፍ የግል አበዳሪ ድርጅቶች ገንዘብ ለመበደር ወደ አለማቀፍ የካፒታል ገበያ ሲገባ ይህ የመጀመሪያው ነው። ኢትዮጵያ እስካሁን ድረስ ከመንግስታት እንዲሁም ከአለማቀፉ የገንዘብ ተቋምና ከአለም ባንክ በአነስተኛ ወለድ ብድር ስታገኝ ቆይታለች። ይሁን እንጅ ከእነዚህ ተቋማትም ሆነ ከኤክስፖርት  የሚገኘው የውጭ ምንዛሬ  አነስተኛ መሆን የተጀመሩትን ፕሮጀክቶች ለማስፈጸም ባለማስቻሉ መንግስት ከአለማቀፍ የግል አበዳሪ ድርጅቶች ለመበደር በመወሰን ድርድር ጀምሯል።
መንግስት ወደ አለም የገንዘብ ገበያ ለመግባት መወሰኑን ተከትሎ የኢኮኖሚ ባለሙያዎች የተለያዩ አስተያየቶችን ይሰጣሉ። በአንድ በኩል መንግስት የጀመራቸውን ፕሮጀክቶች ለመጨረስ ብድሩ አስፈላጊ መሆኑን የሚከራከሩ ወገኖች ያሉትን ያክል፣ ብድሩ ኢትዮጵያን ልትወጣው በማትችል እዳ ውስጥ ይከታትና የሁላ ሁላ ችግር ያመጣባታል ብለው የሚሰጉም አሉ።
ታዋቂ የኢኮኖሚ ባለሙያ የሆኑት ፕ/ር ሰኢድ ሃሰን፣  ሚንጋ ነጋሽ፣ ተስፋየ ለማና አቡ ግርማ ሞገስ በጋራ ባወጡት ጥናታዊ ጽሁፍ የመንግስት ውሳኔ ችግሮችን ሊያመጣ እንደሚችል አስጠንቅቀዋል። የኢትዮጵያ እዳ በከፍተኛ ሁኔታ መጨመሩ አገሪቱ ወደ ውጭ ልካ ከምታገኘው ገቢ ጋር የማይጣጣም መሆኑ ሊያሳስብ እንደሚገባ የኢኮኖሚ ባለሙያዎቹ ገልጸዋል።መንግስት የሚወስደውን ገንዘብ ለየትኛው ፕሮጀክት በትክክል ማዋል እንዳለበት እንዲሁም ተጨባጭ የሆነ የፋይናንስ እቅድ ማዘጋጀት እንደሚኖርበት ባለሙያዎች ምክራቸውን ለግሰዋል።
ኢትዮጵያ ከ15 ቢሊዮን ዶላር በላይ የውጭ እዳ እንዳለባት መረጃዎች ያሳያሉ።

ኢትዮጵያን ለማጥፋት የሚደረግ ደባ፣ ከፕሮፌሰር አለማየሁ ገብረማርያም

ትርጉም በነጻነት ለሀገሬ

Nov 26, 2014
ለአራት አስርት ዓመታት እራሱን ህዝባዊ ወያኔ ሀርነት ትግራይ (ህወሀት) እያለ የሚጠራው እና በአሁኑ ጊዜ በኢትዮጵያ ህዝብ ጫንቃ ላይ ከህዝብ ፍላጎት ውጭ በኃይል በስልጣን ወንበር ላይ ተፈናጥጦ የሚገኘው የወሮበላ የማፊያ ቡድን ኢትዮጵያን ለማጥፋት ቀጣይነት ያለው እና የማያቋርጥ የፖለቲካ፣ የማህበራዊ እና የባህል ጦርነት በመክፈት ዕቅድ አውጥቶ በመንቀሳቀስ ላይ ይገኛል፡፡ የህወሀት ኢትዮጵያን የማጥፋት ተልዕኮው እና ፍልስፍናው የተመሰረተው በተወሰኑ የአፈጻጸም ስልቶች፣ ፖሊሲዎች፣ የድርጊት መርሀ ግብሮች እና ተሞክሮዎች ላይ ሲሆን በዋናነት የሚከተሉትን የአፈጻጸም ስልቶች ያካትታል፣ 1ኛ) የኢትዮጵያውያንን/ትን ብሄራዊ ማንነት በጠባብ እና በጎሳዊ አመላካከት ተክቶ በመከፋፈል ኢትዮጵያውያን/ት ያሏቸውን የማህበራዊ የጋራ ልምዶች፣ የህዝቡን የተከበሩ እሴቶች፣ እምነቶች እና ልማዶች ፍጹም በሆነ መልኩ እንዲወገዱ አበርትቶ መስራት፣ 2ኛ) የተለያዩ ዕኩይ የተግባር ስልቶችን እና ዕቅዶችን በማዘጋጀት ሀገሪቱን መከፋፈል፣ መሸጥ፣ መገንጠል እና መገነጣጠል፣ የወያኔ ኢትዮጵያን የማጥፋት ፍልስፍና እና ዕቅዶች ዓላማ አድርገው የተነሱት ኢትዮጵያ ተብላ የምትጠራዋን የአንጸባራቂ ታሪክ ባለቤት የሆነች ሀገር በማስወገድ ጭራቃዊነት በሆነ መልኩ በተጸነሱ፣ ለእኩይ ምግባር ፍጻሜው በጥንቃቄ በታቀዱ እና እነዚህን መሰሪ ዕቅዶች ስልታዊ በሆነ መልኩ ተግባራዊ በማድረግ በመጨረሻ በወያኔ ምናብ የተፈበረከች በጎሳ ተበጣጥሳ እና ተጣማ በተሰራች ደካማ ሀገር ለመተካት ነው፡፡ ወያኔ ኢትዮጵያን የማጥፋት ተልዕኮውን እ.ኤ.አ ከ1991 ጀምሮ በይፋ እና ግልጽ በሆነ መልኩ መተግበር ጀመረ፡፡   
የወያኔ ኢትዮጵያን የማጥፋት ፍልስፍና፣
ወያኔ ኢትዮጵያን ለማጥፋት የሚጠቀምበት ዋናው ፍልስፍናው ምንድን ነው?
ለዚህ ጥያቄ መልሱ ከቀድሞው የህወሀት የገንዘብ ኃላፊ እና ቁልፍ አመራር ሰጭ ከነበረው እና ድርጅቱን በመልቀቅ እራሱን በመለየት ከፍርሀት ነጻ ሆኖ ለድርድር የማይቀርበውን ኢትዮጵያዊ እውነት ተናጋሪ ከሆነው ገብረመድህን አርዓያ አንደበት ግልጽ በሆነ እና በማያሻማ መልኩ ቁልጭ ብሎ ይገኛል፡፡ በጣም ልዩ በሆነ የቪዲዮ ቃለመጠይቅ ተደርጎ እና በዩቱቤ ድረ ገጽ በተለቀቀው (ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ከአማርኛው ትርጉማቸው ወደ እንግሊዝኛ ቋንቋ የመለስኳቸውን) ጽሁፍ ላይ ገብረመድህን ህወሀት ስልታዊ በሆነ መልኩ የኢትዮጵያን የብሄራዊ ማንነት፣ ታሪክ እና እምነት ለማጥፋት የሚከተሉትን አራት የፍልስፍና ምሰሶዎች እየተቀመ እንዳለ ግልጽ አድርጓል፡፡ እነርሱም፣
1ኛ) ኤርትራ የኢትዮጵያ ቅኝ ግዛት ናት፡፡ ኤርትራ የበለጸገች ሀገር ናት፡፡ ኤርትራ ከኢትዮጵያ በፊት ቀድማ የነበረች ሀገር ናት፡፡ ኢትዮጵያ በንጉስ ምኒልክ የተፈጠረች ሀገር ናት፡፡ ኢትዮጵያ የሚለው ስም አይታወቅም፡፡ ኢትዮጵያ ታሪክ የላትም፣ ምንም፤
2ኛ) ትግራይ በዓጼ ምኒሊክ ተወርራ እና የአማራ ቅኝ ግዛት የነበረች እራሷን የቻለች ነጻ ሉዓላዊ ሀገር ናት፡፡ ትግራይ የአማራ ቅኝ ግዛት ናት፡፡ ይኸ ነው እንግዲህ በህወሀት መመሪያ በሆነው ማኒፌስቶ (ማኒፌስቶው በቪዲዮው እንደተመለከተው) በግልጽ ተቀምጦ የሚገኘው፡፡ (ዋናውን እና በፒዲኤፍ ፎርማት በእጅ የተጻፈውን የህወሀትን ማኒፌስቶ ለማንበብ እዚህ ጋ ይጫኑ፣ በመስመር ላይ ለማግኘት ደግሞ እዚህ ጋ ይጫኑ)፡፡ ስለሆነም ትግራይን ከአማራ ቅኝ ተገዥነት ነጻ ማውጣት አለብን፡፡ እናም የትግራይን ሬፐብሊክ መመስረት አለብን፡፡
3ኛ) አማራ የትግራይ ህዝብ ጠላት ነው፡፡ አማራ አንድ ጠላት ብቻ አይደለም፣ ሆኖም ግን ድርብ ጠላት ነው፡፡ ስለዚህ አማራን መደምሰስ አለብን፡፡ አማሮችን ልናጠፋቸው ይገባል፡፡ አማራ እስካልጠፋ፣ እስካልተሸነፈ እና ከመሬት ላይ እንዲጸዳ (የዘር ማጥፋት እርምጃ እስካልተወሰደበት ድረስ ለማለት መሆኑን ልብ ይሏል) እስካልተወሰደበት ጊዜ ድረስ ትግራይ በነጻነት ልትኖር አትችልም፡፡ እኛ አሁን እንዲፈጠር ለምንፈልገው መንግስት አማራ ዋና መሰናክል ነው፡፡
4ኛ) ኢትዮጵያ በሚኒልክ የተፈጠረች ሀገር በመሆኗ እና የተፈጠረችውም በምኒልክ ወረራ በመሆኑ ከዚህም ጋር ተያይዞ በምኒልክ የተወረሩ ብዙ ብሄር ብሄረሰቦች እና ህዝቦች ስላሉ እነዚህ ህዝቦች አሁን ኢትዮጵያ እየተባለች ከምትጠራዋ ሀገር ነጻነታቸውን ማግኘት አለባቸው፣ እናም የእራሳቸውን ነጻ ሉዓላዊ ሀገር መመስረት አለባቸው፡፡ (ጎሳዎችን ሁሉ ገነጣጥለው እራሳቸውን የቻሉ ነጻ ሉዓላዊ ሀገር ለማድረግ የሚያደርጉትን ጥረት ልብ ይሏል!) ኢትዮጵያ በመባል የምትታወቀው ሀገር አዲስ ናት፡፡ እንዲያውም ከ100 ዓመት በላይ እድሜ የላትም፡፡ ይህች ሀገር መደምሰስ አለባት፡፡ መጥፋት አለባት፡፡ ብሄሮች እና ብሄረሰቦች የእራሳችንን መንግስት ማቋቋም አለብን፡፡ ኤርትራ ነጻነቷን ማግኘት አለባት፡፡ የትግላችን ዋናው መሰረቱም ይኸው ነው ነው እያሉ ያሉት እነዚህ የዕኩይ ምግባር እና የሰይጣናዊ መንፈስ አራማጆች፡፡
ህወሀት እንደ ድርጅት ወይም ደግሞ በስልጣን ላይ ያሉት አመራሮቹ፣ ወይም ከስልጣናቸው ገለል የተደረጉት፣ ወይም ደግሞ ከስልጣናቸው በጡረታ ተገለሉት እስከ አሁን ድረስ ይህንን የህወሀት ማኒፌስቶ በመባል የሚታወቀውን ሰነድ በጋራ ወይም ደግሞ በተናጠል እየቀረቡ ስለሰነዱ ህጋዊነት ማስተባበያ ሳይሰጥ ወይም ደግሞ በይዘቱ ላይ ማሻሻያ ሳይደረግ ዝም ብሎ ተቀምጦ እንደሚገኝ ማስታወስ ተገቢ ነው፡፡ ማኒፌስቶው በአሁኑ ወቅትም የህወሀት መመሪያ እና የፍልስፍናው መሰረት ሆኖ በማገልገል ላይ ይገኛል፡፡
ኢትዮጵያን የማጥፋት ተልዕኮው እንዴት እንደሚሰራ፣
ለአስርት እና ከዚያ በላይ ዓመታት የዘለቀው የህወሀት ኢትዮጵያን የማጥፋት ተልዕኮ ዘርፈብዙ በሆኑ ስልታዊ ግንባሮች የተለያዩ አቀራረቦችን በመጠቀም በመተግበር ላይ ይገኛል፡፡ ኢትዮጵያን የማጥፋት ስልቱ በጣም ውስብስብ የሆነ እና የፖለቲካዊ ጦርነቱ ከባህል፣ ከማህበራዊ እና ከስነልቦናዊ ጦርነት ጋር ታዋህዶ በመተግበር ላይ ይገኛል፡፡ በዚህ በአሁኑ ትችቴ ላይ ሶስቱን ዋና ዋና የማስፈጸሚያ ስልቶች ብቻ (ሌሎች ተመሳሳይ ስልቶች በሚቀጥሉት ትችቶቼ የሚቀርቡ ይሆናል) የምንዳስስ ይሆናል፡፡ እነዚህም ስልቶች የሚከተሉት ናቸው፡፡ 1ኛ) የኢትዮጵያን ታሪክ እርባናየለሽ ማድረግ እና የኢትዮጵያን ባለታሪክ መሪዎች ስም ጥላሸት መቀባት፣ 2ኛ) “አማራን” እና “የአማራን” ህዝብ ስም ጥላሸት መቀባት፣ 3ኛ)  ኢትዮጵያን መከፋፈል፣ መገነጣጠል እና መሸጥ እንዲሁም የኢትዮጵያን የግዛት አንድነት እና ሉዓላዊነት መከፋፈል እና ማዳከም ዋና ዋናዎቹ ናቸው፡፡ እነዚህን የማስፈጸሚያ ስልቶች ከዚህ ቀጥሎ በዝርዝር እንመለክታለን፡፡
1የኢትዮጵያን ታሪክ እርባናየለሽ ማድረግ እና የኢትዮጵያን ባለታሪክ መሪዎች ስም ጥላሸትመቀባት፣
ከወያኔ ኢትዮጵያን የማጥፋት ተልዕኮ የመጀመሪያ መሳሪያ ማስፈጸሚያ ስልት ሆኖ የቀረበው ታሪካዊት ኢትዮጵያ የምትባል ሀገር እንደሌለች ሽምጥጥ አድርገው መካድ እና የቀድሞ የኢትዮጵያ መሪዎችን ስም ጥላሸት መቀባት እና የንቀት ትችትን ማቅረብ ነው፡፡ ለወያኔ ኢትዮጵያ ከመቶ ዓመታት የማይበልጥ ብቻ ታሪክ ያላት የፖለቲካ ህልው ናት፡፡ በወያኔ ተምኔታዊ ሀሳብ መሰረት ኢትዮጵያ በ19ኛው ክፍለ ዘመን መጨረሻ አካባቢ በዓጼ ሚኒልክ ተጠፍጥፋ የተፈጠረች የፖለቲካ መልካምድራዊ ህልው ናት፡፡ የወያኔ ትረካ ምኒልክ ጨካኝ ጦረኛ የነበሩ እና ጎረቤት የሆኑ ብሄሮችን እና ብሄረሰቦችን በጦር ኃይል ድል በማድረግ ለማስገበር እና የአማራን ግዛት ለመፍጠር በመንገዳቸው ላይ ያገኙትን ሁሉንም ነገር በመምታት እና በማቃጠል ላይ ትኩረት አድርገው የሰሩ እደነበሩ አድርገው ያስቀምጣሉ፡፡ ለወያኔ እና አሁን በህይወት የሌለው የወያኔ የክርስትና አባት የሆነው መለስ ዜናዊ “የሀበሻ ህዝቦች ሀገር” እየተባለች የምትጠራው ኢትዮጵያ (ወይም ደግሞ የአቢሲኒያ ህዝብ) የምትባለው ሀገር ወይም በግዛት ስፋቷ ኢትዮጵያ ተብላ የምትጠራው ሀገር አሁን ከሚኖረው ህዝብ ጋር ትንሽ ወይም ደግሞ ምንም ዓይነት ግንኙነት የሌላቸው ህዝቦች አድርጎ ያወራል፡፡
እንደዚህ ያለ የደናቁርት ታሪክን የመበረዝ እና የመከለስ እንዲሁም ታሪክን አዛብቶ የማቅረብ አባዜ የወያኔን ጭፍን አምባገነናዊነት ያመላክታል፡፡ እንደ ወያኔ ታሪክ ከሆነ በብሉይ ኪዳን በደርዘኖች የሚቆጠሩ እና በአዲስ ኪዳን ቢያንስ አንድ ዋቢ ማጣቀሻ ማስረጃዎች ኢትዮጵያ እና ኢትዮጵያውያን/ት መኖር አሁን በመኖር ላይ ላሉት ወይም ኢትዮጵያ ለምትባለው ምድር ምንም ነገር ማለት እንዳልሆነ ይገልጻል፡፡ በዘፍጥረት (2፡13) እንዲህ የሚል ቅዱስ ቃል ተጽፎ ይገኛል፣ “የሁለተኛውም ወንዝ ስም ጊዮን ነው፡ እርሱም የኢትዮጵያን ምድር ሁሉ ይከብባል፡፡“  በዘሁልቁ (12፡1) እንዲህ የሚል ቅዱስ ቃል ተካትቶ ይገኛል፣ “ሙሴም ኢትዮጵያይቱን  አግብቷልና፣ ባገባት በኢትዮጵያይቱ ምክንያት ማርያምና አሮን በእርሱ ላይ ተናገሩ፡፡”  እንደዚሁም በመዝሙረ ዳዊት (68፡31) እንዲህ የሚል ቅዱስ ቃል አለ፣ “ልዕልቶች ከግብጽ ይወጣሉ፣ ኢትዮጵያ እጆቿን ወደ እግዚአብሄር ትዘረጋለች፡፡“ እንደ ወያኔ ከሆነ ሁሉም የብሉይ ኪዳን ማስረጃዎች ሁሉ ተምኔታዊ (በእውን ተፈጥራ ላለች ሳይሆን በሀሳብ ተፈጥራ ላለች) ለሆነች ሌላ ኢትዮጵያ ነው፡፡ ሁሉምበመጽሐፍ ቅዱስ የተጠቀሱት ማስረጃዎች ሁሉ በወያኔ አመላካከት በአሁኑ ጊዜ ላለችውኢትዮጵያእየተባለች ለምትጠራ ሀገር ወይንም ደግሞ አሁንኢትዮጵያ እየተባለች በምትጠራ ሀገርለሚኖሩህዝቦች ቀደምት ትውልድ ምንም ዓይነት አስፈላጊነት የሌለው ነገር ነው፡፡      
በተመሳሳይ መልኩ ለወያኔ አሁን ያለችው ዘመናዊቷ ኢትዮጵያ ከጥንታዊ የአክሱም ግዛት (ከክርስቶስ ልደት በፊት ከ3ኛው-6ኛው ክፍለ ዘመን) ጋር ምንም ዓይነት ግንኙነት እና መስተጋብር የላትም፡፡ አክሱም ለኢትዮጵያ እና ለኢትዮጵያውያን/ት ሁሉ ልዩ የሆነ ጠቃሚነት ያለው የታሪክ አሻራ ቦታ ነው፡፡ አክሱም አሁን ላለችው ኢትዮጵያ የፖለቲካ መሰረት መሆኑ የሚያጠራጥር ጉዳይ አይደለም፡፡ አክሱም በብዙ ኢትዮያውያን/ት እና ኢትዮጵያዊ/ት ባልሆኑ ወገኖች በአፈታሪክ እንደሚነገረው ሁሉ የንግስተ ሳባ መናገሻ ከተማ ነበር ይባላል፡፡ የአክሱሙ ንጉስ ኢዛና ከክርስቶስ ልደት በኋላ በ4ኛው ክፍለ ዘመን የክርስትና ኃይማኖት የመንግስት ኃይማኖት እንዲሆን አድርገዋል፡፡ በአሁኑ ጊዜ በሀገሪቱ የሚገኙ በአስር ሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን/ት የክርስትና ኃይማኖት እምነት ተከታዮች አክሱምን ሁለተኛው ቅዱስ እየሩሳሌም አድርገው ይቆጥራሉ ምክንያቱም አስርቱ ትዕዛዛት የተጻፉበት ጥርብ ድንጋይ ያለው በአክሱም ጽዮን ውስጥ ነው ተብሎ ስለሚታመን ነው፡፡ በወያኔ ታሪክ መሰረትይኸ ሁሉ በሙሉ ልብወለድ ታሪክ ነው፡፡ ይህ ጉዳይ አሁንካለችው ኢትዮጵያ እናኢትዮጵያውያን/ ጋር ምንም ዓይነት ግንኙነት የለውም፡፡
ከክርስቶስ ልደት ከ615 በፊት በእስልምና እምነት ተከታዮች ላይ ይደርስ የነበረውን ማሰቃዬት ለመከላከል ሲባል በነብዩ መሀመድ ወደ አክሱም ጥገኝነትን እንዲያገኙ የተላኩትን የመጀመሪያውን የእስልምና ኃይማኖት እምነት ተከታይ ስደተኞች (የመጀመሪያ ስደት/First Hijira) ተቀብለው ያስተናገዱት እና ድጋፍም ያደረጉላቸው በወቅቱ የነበሩት የአክሱም ንጉስ ነበሩ፡፡ ነብዩ መሀመድ ያንን የጥሩ ተምሳሌት ጊዜ መዝግበው በመያዝ ለአክሱሙ ንጉስ እና ለሀበሻ ህዝቦች ከፍተኛ የሆነ ምስጋና አቅርበዋል፡፡ ይህንን በጎ ምግባር በአስተምህሮ ስብስባቸው ውስጥ በማስገባት ነብዩ መሀመድ እንዲህ ብለው ነበር፣ “እራሳቸው ጥቃት እስካልሰነዘሩ ድረስ ሀበሾችን ተዋቸው፣ እዳትነኳቸው!“ እንደወያኔ የወሮበላ ማፊያ ቡድን ከሆነ ይህ ሁሉ ተጨባጭ ታሪክ ልብወለድ ድርሰት ነው፡፡ ለወያኔ ነብዩመሀመድ ስለሀበሻ ህዝቦች የተናገሩት ሁሉ አሁን ካለችው ኢትዮጵያ እናኢትዮጵያውያን/ ጋርምንም ዓይነት ግንኙነትየለውም፡፡ 
የ18ኛው ክፍለ ዘመን የእንግሊዝ የታሪክ ምሁር የነበሩት ኤድዋርድ ጊቦን “የሮማውያን የግዛት ድክመት እና አወዳደቅ“ በሚል ርዕስ በጻፉት ታዋቂ የታሪክ ስራቸው እንዲህ ብለው ነበር፣ “በኃይማኖታቸው ምክንያት ኢትዮጵያውያን/ት በሁሉም አቅጣጫ በጠላት በመከበባቸው ለአንድ ሺህ ዓመታት ገደማ ያህል የረሳቸውን የዓለም ህዝብ እነርሱም እረስተውት ተኝተው ቆይተዋል፡፡“ እንደ ወያኔ ከሆነ ጊቦን ተራ አፈታሪክ ነው የጻፈው እና የተረከው፡፡ አሁን በህይወት የሌለው መለስ ዜናዊ እ.ኤ.አ በ1993 ኢትዮጵያ የ100 ዓመት እድሜ ነው ያላት ብሎ ተናግሮ ነበር ፡፡ ያለዚያ ከምንም ተነስተው ምንም ነገር ሳያገናዝቡ እራሳቸውን አዋቂ አድርገው የሚቆጥሩ ደናቁርት እብሪተኞች አፈታሪክ የሚያወሩ እንጅ የታሪክ ሰዎች አይደሉም፡፡
እ.ኤ.አ በ1896 ኢትዮጵያ በአድዋ ጦርነት ላይ በኢጣሊያን ወራሪ ኃይል ላይ የተቀዳጀችው አንጸባራቂ ድል በአፍሪካ ታሪክ ውስጥ እጅግ በጣም ጠቃሚ ወቅት ሆኖ ተመዝግቧል፡፡ የአድዋ ድል በአፍሪካ ታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ የአፍሪካ ጥቁር ወታደር ኃያል የሆነውን የአውሮፓን ነጭ ኃይል አንጸባራቂ በሆነ መልኩ ድል አድርጎ ከግዛቱ ያስወጣበት ድል ነው፡፡ ከሁሉም በላይ በጣም የሚያስደንቀው ነገር ደግሞ የአውሮፓ ኃያላን አገሮች አፍሪካን እንደ ቅርጫ ስጋ ለመቀራመት እና በ10 ዓመታት ጊዜ ውስጥ ሁሉንም የአፍሪካ አገሮች ሙሉ በሙሉ ለመቆጣጠር ደባ ለመሸረብ የበርሊን ጉባኤን ባከሄዱ ሁለት ዓመታት ጊዜ ውስጥ ኢትዮጵያ ኃያሉን የኢጣሊያ ወራሪ ኃይል አሳፋሪ የሆነ ሽንፈት በማከናነብ ከግዛቷ ጠራርጋ ማስወጣት መቻሏ ነው፡፡ ኢትዮጵያ ለበርካታ ዓመታት የግዛት ሉዓላዊነቷን እና አንድነቷን አስከብራ የቆየች እና ማንኛውንም ሀገር ቅኝ ግዛት ለማድረግ ሙከራ ሲያደርግ የነበረውን ኃያል ሀገር ሁሉ በተሳካ ሁኔታ ስትከላከል የቆየች የጀግኖች ሀገር ናት፡፡ እንደ ወያኔ ታሪክከሆነ ይህ ሁሉ አንጸባራቂ ኢትዮጵያን ብቻ ሳይሆን አፍሪካውያንን/ትንሁሉ ያኮራ አንጸባራቂ ታሪክ ዝም ብሎየተጻፈ ልብወለድ ድርሰት ነው፡፡ እንደ ወያኔ አስተሳሰብ እና እምነት በአውሮፓ ኃያላን ቅኝ ገዥዎች ላይ የተቀዳጀነው አንጸባራቂ ድል እና ታሪክ ሁሉ በአሁኑ ጊዜ ካለችው ኢትዮጵያ እና ኢትዮጵያውያን/ት ጋር ምንም ዓይነት ግንኙነት የለውም፡፡ እንደ ጎጠኛው የወያኔ ወሮበላ የማፊያ ቡድን እምነት ከሆነ የአድዋ አንጻባራቂ ድል የትግራውያን/ት ብቻ ነው፡፡ ወትሮስ “የአክሱም ሐውልት ለወላይታው ምኑ ነው “ከሚል ጎጠኛ የወሮበላ ስብስብ ምን ሊጠበቅ!?
ሁለተኛው የወያኔ የእርባና የለሽነት እና ጠላሸት የመቀባት ዘመቻ ሌላኛው ጫፍ ያነጣጠረው ለዘመናት እንደ ባህሉ እና ወጉ ሲያስተዳድሩ የኖሩትን የአትዮጵያን ነገስታት ስም እና ስብዕና ጥላሸት መቀባት ነው፡፡ ከዚህ አንጻር በ19ኛው ክፍለ ዘመን በአድዋ ጦርነት ኃያሉን እና ወራሪውን የኢጣሊያ ኃይል ድባቅ በመምታት ድል የተቀዳጁትን እና እ.ኢ.አ አቆጣጠር በዚህ በያዝነው ዓመት 100ኛ ዓመት ክብረ በዓል የሚከበርለትን ድል በተቀዳጁት ዓጼ ምኒልክ ላይ የወያኔ ስም የማጥፋት እና የማጠልሸት ተግባር የበረታ ሆኗል፡፡ የወያኔው ቡድን ዓጼ ምኒልክን የዘር ማጥፋት የጅምላ ገዳይ እንደነበሩ አድርገው ይስሏቸዋል፡፡ እ.ኤ.አ ጃንዋሪ 2014 “የኢትዮጵያን ታሪክ የማጠልሸት አባዜ“ በሚል ርዕስ ባወጣሁት ትችቴ ላይ ባቀረብኩት የመሞገቻ ጭብጥ መሰረት የወያኔው የወሮበላ ቡድን በዓጼ ሚኒልክ ላይ ከመጠን ያለፈ ግነትን በማራገብ፣ ክብርን በማሳነስ እና ስም የማጠልሸት ተግባራትን እንደ ዋና ስራው አድርጎ በመውሰድ ዕኩይ ምግባሩን ሲፈጽም ቆይቷል፡፡ ዓጼ መኒሊክ ካረፉ ከ100 ዓመታት በኋላ የወያኔው የወሮበላ ቡድን ከመቃብር በመቀስቀስ ሰይጣናዊ ሰው ለማድረግ ሙከራ አድርጓል፡፡  መለስ ዜናዊ ካረፈ ከሁለት ዓመታት ገደማ በኋላ መለስን ከመቃብር በማስነሳት እና ከፍተኛ ዘመቻ በማድረግ የኢትዮጵያ ብቸኛው አዳኝ መሲህ አድርገው ለማቅረብ ሞክረዋል፡፡ የወያኔ የወሮበላ ቡድን ምኒልክ የኦሮሞ ህዝብ ጠላት እንደሆኑ አድርጎ ታሪክ እንደገና ለመጻፍ ይፈልጋል፡፡ እውነተኛው ነገር ግን መለስ በህይወት ቢቆይ ኖሮ እርሱ እና ግብረ አበሮቹ እብሪተኞቹ የወያኔ ባለስልጣናት እና አባላት ያልተነገሩ እና ለመግለጽ እጅግ የሚዘገንኑ ወንጀሎችን በኦሮሞ ህዝብ ላይ የፈጸሙ ስለመሆናቸው ለህግ ለማቅረብ ከበቂ በላይ መስረጃዎች አሉ፡፡
አሁን በህይወት የሌለው መለስ ዜናዊ ግርማዊ ቀዳማዊ አጼ ኃይለ ስላሴ አሁን ምንም ዓይነት የአስተሳሰብ እና የድርጊት ለውጥ ሳይኖር ወደ የአፍሪካ ህብረትነት (ከአውሮፓ ህብረት ምግባር እና የአመራር ፍልስፍና ሳይሆን ስም ብቻ ተኮርጆ) የተለወጠውን እና ከዚያ በፊት ግን የአፍሪካ አንድነት ድርጅት ምስረታ ስላበረከቷቸው ጠቃሚ ነገሮች ሁሉ ሙልጭ አድርጎ በመካድ ጥላሸት በመቀባት ያለ የሌለ ጥረት ሲያደርግ ቆይቶ ነበር፡፡ በዚያን ወቅት በጥላቻ የተሞላው መለስ ዜናዊ ግርማዊ ቀዳሚ ዓጼ ኃይለ ስላሴ እንደ ጋናው የመጀመሪያ ፕሬዚዳንት እንደ ክዋሜ ንክሩማህ የፓን አፍሪካ አራማጅ አልነበሩም በማለት ተራ ቅጥፈትን በመከናነብ የድሁርነት አስተሳሰቡን ያለምንም ሀፍረት በማራመድ ለእነዚህ ባለውለታ ንጉሰ ነገስት በአፍሪካ ህብረት ቀጥር ግቢ ውስጥ ሀውልታቸው እንዳይቆም የሞት ሽረት ትገል አድርጎ ነበር፡፡ ታሪካዊ ማስረጃዎች ግን የተለዬ ታሪክ ይነግሩናል፡፡ የጋናው ፕሬዚዳንት ክዋሜ ንክሩማህ ግን ያለ ግርማዊ ቀዳማዊ ዓጼ ኃይለስላሴ ጥረት እና ትግል የአፍሪካ አንድነት ድርጅት እውን አይሆንም ነበር በማለት በተደጋጋሚ ይናገሩ ነበር፡፡ እ.ኤ.አ በ1972 በተካሄደው 9ኛው የአፍሪካ ርዕሰ ብሄሮች እና የአፍሪካ አንድነት ድርጅት መንግስታት እንዲሁም የመሪዎች ጉባኤ ላይ ግርማዊ ቀዳማዊ ዓጼ ኃይለ ስላሴ በአቻዎቻቸው የአፍሪካ አንድነት ድርጅት የአፍሪካአባት ተብለው ተመርጠው ነበር፡፡ እ.ኤ.አ በ1963 ግርማዊ ቀዳማዊ ዓጼ ኃይለ ስላሴ የመጀመሪያው የአፍሪካ አንድነት ድርጅት ሊቀመንበር ሆነው ተመርጠዋል፣ እንዲሁም እ.ኤ.አ በ1966 እንደገና ለሁለተኛ ዙር ያንኑ ተመሳሳይ የስልጣን ቦታ ማንም ሌላ የአፍሪካ መሪ ተመርጦ የማያውቀውን ድጋሜ ለሁለተኛ ጊዜ ተመርጠው አገልግለዋል፡፡
መለስ በህይወት ከተለዬ በኋላ አንድ የዜና ምንጭ ከድሮው “ፕሬዚዳንት” ግርማ ወልደጊዮርጊስ ጋር ባደረገው ቃለ መጠይቅ “ፕሬዚዳንት” ግርማ ወልደጊዮርጊስ ለ”ጠቅላይ ሚኒስትር” ኃይለማርያም ደሳለኝ እንዲህ የሚል ደብዳቤ ጽፈው እንደነበር ጠቁሟል፣ “ንጉሱን ለማስታወስ ሀውልት መገንባት አለበት… የአፍሪካ የመጀመሪያው መሪ ነበሩ፣ እናም ይህ ሀውልት የማቆም ሁኔታ ካበረከቱት አስተዋጽኦ አንጻር ይገባቸዋል ብዬ አስባለሁ፡፡“ ከመለስ አስመሳዮች እና አሽከሮች ግን በዚህ ጉዳይ ላይ ጥቂት ነገሮች ብቻ ሊከናወኑ ይችላሉ ተብሎ ይጠበቃል!
በግልጽ ለመናገር የኢትዮጵያን ታሪክ እርባናየለሽ የማድረግ እና በየዘመኑ የተነሱ ታሪካዊ መሪዎችን ስም ጥላሸት የመቀባት ሁኔታ አንድ ነገርን ለማሳካት የሚደረግ ግብ ነበር፡፡ ይኸውም የታሪክን ሰዓት ወደ መጀመሪያ ዓመት በመመለስ የሀገሪቱ አባት እና የወያኔ የሀገሪቱ የልምድ አዋላጅ በማድረግ የመለስ ዜናዊን ታሪክ አንድ ብሎ ለማስጀመር ነበር፡፡ ወያኔ እና የወያኔ አመራሮች ታሪካዊ መዛግብትን በማዛባት እና እውነተኛውን ታሪክ በመካድ ታሪክን እንደገና ለመጻፍ፣ አዛብቶ ለመጻፍ፣ አጋንኖ ለመጻፍ እና እውነተኛውን ታሪክ ያለመጻፍ እና በሌላ መልኩ በቅዱሱ የመለስ ዜናዊ ታሪክ ለመተካት የሚደረግ ከንቱ ሙከራ ነው፡፡ የዓጼ ምኒሊክ ታሪክ እንዲጻፍ አይፈልጉም፣ ይልቁንም የዘመናዊት አፍሪካ ታላቁ መሪ መለስ ዜናዊ እንደሆነ ተደርጎ እንዲጻፍ ይፈልጋሉ፡፡ የዓጼ ምኒልክን ስም እና ክብር በማጠልሸት መለስን አዲሱ የአፍሪካ ዝርያ መሪ፣ የልማታዊ መንግስት ፈጣሪ እና አምጭ፣ የዴሞክራሲ አራማጅ፣ የዓለም አቀፍ አየር ሙቀት የአፍሪካ መሪ፣ የአየር ለውጥ ባለሙያ እና ጅሀዲስቶችን እና አሸባሪዎችን ደምሳሽ እና ወዘተ ተብሎ እንዲመለክበት ይፈልጋሉ፡፡
2አማራን እና የአማራን ህዝብ ጥለሸት መቀባት፣
የወያኔ ጸረ አማራ ፍልስፍና እና በአማራ ላይ የሚደረግ ጥላሸት የመቀባት ዘመቻ መሰረተ ቢስ እና ምክንያታዊነት የሌለው ኢሞራላዊ ድርጊት ነው፡፡ የወያኔው ማኒፌስቶ እንዲህ በማለት ያውጃል፣ “አማራዎች የትግሬዎች ጠላቶች ናቸው፡፡ የወያኔ የገንዘብ ኃላፊ የነበሩት ገብረመድህን ዓርዓያ እንደገለጹት የወያኔ ፍልስፍና የመሰረት ድንጋይ አማራ የትግራይ ህዝቦች ጠላት ነው የሚል ነው፡፡ አማራዎች አንድ ጠላት ብቻ አይደሉም ሆኖም ግን ድርብ ጠላቶች ናቸው፡፡ ስለሆነም አማራን መደምሰስ አለብን፡፡ አማራዎችን ልናጠፋቸው ይገባል፡፡ አማራዎች እስካልጠፉ እና እስካልተሸነፉ ድረስ፣ እንዲሁም የዘር ማጥፋት እርምጃ እስካልተወሰደባቸው ድረስ ትግራይ በነጻነት ልትኖር አትችልም፡፡ የምናስበውን መንግስት ለመፍጠር እንዳንችል አማራ ዋና መሰናክል ይሆናል፡፡” አሁን በህይወት የሌለው መለስ እና ህወሀት አንዴ ስልጣን ከያዙ በኋላ የጥላቻ ፍልስፍናቸውን በአማራ እና በአማራ ህዝብ ላይ ሙሉ በሙሉ መተግበር ነበር፡፡ እናም አማራን ለመደምሰስ ሁሉንም ነገር አደረጉ፣ ሆኖም ግን…
ወያኔ በእብሪተኝነት የዘር ማጥፋት ወንጀል እየፈጸመበት ያለው አማራ እና የአማራ ህዝብ ለመሆኑ ማን ነው?
የወያኔ ወሮበላ የማፊያ ቡድን የአማራን ህዝብ ጭራቅ ነው በማለት ተከታታይነት ያለው የፕሮፓጋንዳ ዘመቻ ቢከፍትበትም እውነታው ግን አማራየሚባለው ህዝብ ከዓለም የመጨረሻ ደኃ እንደሆነመረጃዎችይጠቁማሉ፡፡ የአልጃዚራ ዘገባ በቅርቡ እንዲህ የሚል መደምደሚያ ላይ ደርሷል፣ “አማራ በኢትዮጵያ ብቻ አይደለም ደኃ ሆኖ የሚገኘው፣ ሆኖም ግን በአፍሪካም ጭምር እንጅ፡፡“
የአማራን ህዝብ ማሰቃዬት እና ማጥፋት የወያኔ ዋና ፍልስፍና እና ኃይል ሆኖ ቀጥሏል፡፡ አሁን በህይወት የሌለው መለስ በአማራ ህዝብ ላይ ጥልቅ የሆነ ጥላቻ የነበረው ሰው ነበር፡፡ ያለምንም ማጋነን የለየለት ጸረ አማራ ነበር ማለት ይቻላል፡፡ ለመለስ አማራን መጥላት አነደሚተነፍሰው አየር ለሂወቱ አስፈላጊው ነበር፡፡ መለስ በፖለቲካዊ ምክንያቱ አማራን አምርሮ ይጠላ ነበር! መለስም ሆነ ሌሎች የወያኔ መሪዎች አማራ የተባለውን ህዝብ ለምን እንደሚጠሉት ወይም ደግሞ ለምን የጥላቻ ስሜት እንደሚያንጸባርቁ በቂ የሆነ ምክንያት የላቸውም፡፡ የወያኔን እና አመራሮቹን በአማራ ህዝብ ላይ ያላቸውን ጥልቅ እና ስር የሰደደ ጥላቻ በማጥናት ምክንያቶቹን ለመገንዘብ የዓለም ታሪክን መመርመር የተሻለ ይሆናል፡፡
የመለስ እና የወያኔ በአማራ ላይ ያላቸው ፍጹም የሆነ ኢምክንያታዊ ጥላቻ እና የሂትለር እና የናዚ ሰው በላ ድርጅት በአይሁዶች ላይ የነበራቸው ጥላቻ ለንጽጽር በትይዩ የሚታይ ጉዳይ ነው፡፡ ሂትለር ለጀርመን ህዝብ ችግሮች እና ለሁሉም ሰይጣናዊ ድርጊቶች ተጠያቂዎቹ አይሁዶች ናቸው ብሎ ያምን ነበር፡፡ መለስም አሁን ላሉት እና ድሮ ለነበሩትም ለሁሉም የኢትዮጵያ ህዝብ ችግሮች እና ሰይጣናዊ ድርጊቶቸ ሁሉ ተጠያቂው የአማራ ህዝብ ነው ብሎ ያምን ነበር፡፡
ሂትለር እና ናዚዎች ህዝብን በጎሳ በመከፋፈል ያምኑ ነበር፡፡ በእነዚህ በተከፋፈሉ የተለያዩ ጎሳዎች መካከል ሁልጊዜ ቀጣይነት ያለው ትግል መኖር አለበት ብለው ያምኑ ነበር፡፡ እነዚህ ናዚዎች “አሪአን ሬስ” የተባለው ጎሳ ምርጥ እና ጠንካራ እንዲሁም ሌሎችን ጎሳዎች ለመግዛት የታደለ ነው ብለው ያምኑ ነበር፡፡ አይሁዶች እና ሌሎች የአሪአን ሬስ ጎሳ አባላት ያልሆኑ ህዝቦች እና ጎሳዎች የበታች ጎሳዎች (ከሰውነት የወረዱ ፍጡሮች) ናቸው ብለው ያምኑ ነበር፡፡
ለመለስ እና ለወያኔ ትግራውያን/ት ሌሎችን ጎሳዎች ለመግዛት ምርጦቹ እና ጠንካራዎቹ ናቸው ብለው ያምናሉ፣ ምክንያቱም ወያኔ በሽምቅ ውጊያ ታንክ፣ አውሮፕላን እና ሌሎች የተለያዩ የጦር መሳሪያዎችን ያከማቸውንጠንካራውን ወታደራዊ ኃይል ያሸነፈ ድርጅት ስለሆነ ነው ብለው ያምናሉ፡፡ በቀጣይነት የእድሜ ልክ ገዥዎች መሆን እንዳለባቸው እራሳቸውን አሳምነዋል፡፡ ወያኔ እና አመራሮቹ እራሳቸውን ከናዚዎች የአሪአን ሬስ አፋኝ ቡድን የዘር ጎሳ ጋር እኩል እድርገው ይቆጥራሉ፡፡ ሌሎቹ የኢትዮጵያ ብሄሮች እና ጎሳዎች አማራን ጨምሮ ትንሽ የጎሳ ፍጡሮች ናቸው ብለው ያምናሉ፡፡ ስለሆነም በኢትዮጵያ በአሁኑ ጊዜ የፖለቲካ አመራሩ፣ ቢሮክራሲው፣ የፖሊስ ኃይሉ፣ የደህንነት እና ወታደራዊ ተቋማት በሙሉ በወያኔ የበላይነት እና ቁጥጥር ስር ውለዋል፡፡ በአሁኑ ጊዜ የወያኔ አገዛዝ እና ሆድ አደር ደጋፊዎቹ በአጠቃላይ የኢኮኖሚ ዘርፎችን ባንኮችን፣ የግንባታ እና የስሚንቶ ምርቶችን፣ የማዕድን ዘርፉን፣ የትራንስፖርት፣ የኢንሹራንስ እና የአስመጭ እና ላኪ የስራ መስኮችን በሙሉ በእነርሱ ቁጥጥር ስር አውለዋል፡፡
አሁን በህይወት የሌለው መለስ ኢትዮጵያውያን/ት ፍጹም በሆነ መልኩ በጎሳ ማንነታቸው፣ በቋንቋ እና በባህል መሰተጋብራቸው መከፋፈል አለባቸው ብሎ የሚያምን ነበር፡፡ ይህም በጎሳ ቡድኖች መካከል ውድድር ይኖራል የሚል መሰሪ አስተሳሰብ ነበረው፡፡ መለስ የእራሱን የሸፍጥ “ፌዴራሊዝም” መሰረተ እና ክልል እያለ የሚጠራውን የአገዛዝ ስርዓት በመፍጠር የሸፍጥ ዕኩይ ተግባሩን ተግባራዊ ማድረግ ጀመረ፡፡ በኢትዮጵያ ህገመንግስት አንቀጽ 39 መለስ እንዲህ የሚል ነገር ጽፎ አስቀምጧል፣ “ብሄር፣ ዜግነት ወይም ደግሞ ህዝቦች ለዚህ ህገመንግስት የሰዎች ስብስቦች ወይም ደግሞ የጋራ ባህል ያላቸው ትልልቅ ጎሳዎች ወይም ደግሞ ተመሳሳይ ልማዶች፣ የጋራ ቋንቋዎች፣ እምነቶች ወይም ተመሳሳይ ማንነቶች እና የሚታወቁ የተፋፈጉ ግዛቶች ላይ የሚኖሩ ህዝቦችን ያካትታል፡፡”
ናዚዎች ሀዝቦችን በገፍ የማባረር እርምጃዎችን ወስደዋል፣ እናም አይሁዶችን ናዚዎች ከያዟቸው ግዛቶች ሁሉ በግዳጅ እንዲባረሩ አድርገዋል፡፡ እ.ኤ.አ በኤፕሪል 2012 “አረንጓዴ ፍትህ ወይም ደግሞ  የጎሳ ኢፍትሀዊነት “ በሚል ርዕስ ባወጣሁት ትችት አሁን በህይወት የሌለው መለስ ዜናዊ  በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ አማራዎችን ከደቡብ ኢትዮጵያ እንዲባረሩ ትዕዛዝ ሰጠ፡፡ ያደረገውን ዕኩይ ምግባር ለማስተባበል በማሰብ የምስራቅ ጎጃም ሰፋሪዎች እና ደኖችን እየመነጠሩ ያሉ መሬትን የወረሩ እና የተቀራመቱ ወንጀለኞች ናቸው በማለት የሚከተለውን አንጃ ግራንጃ ንግግር አሰምቶ ነበር፡፡
“…በታሪክ አጋጣሚ ባለፉት አስር ዓመታት ብዙ ሰዎች –30 ሺህ የሚሆኑ ሰፋሪዎች ከምስራቅ ጎጃም ፈልሰው በመምጣት በህገወጥ መልክ በደቡብ ኢትዮጵያ በቤንች ማጅ ዞን ሰፍረው ነበር፡፡ በጉራ ፈርዳ ወደ 24 ሺ የሚሆኑ ሰፋሪዎች ሰፍረው ይገኛሉ፡፡ አካባቢው ደን ያለበት በመሆኑ ምክንያት በርካታ ህዝብ አይኖርበትም፡፡ በሁሉም ዓይነት መለኪያ ቢታይ ጉራ ፈርዳ ትንሿ ምስራቅ ጎጃም በመሆን ህገወጥ በሆነ አሰፋፈር እና አመራር ላይ ትገኛለች…ሰፋሪዎች ወደ ጫካው አካባቢ በመሄድ ጫካውን ለመኖሪያነት በሚል ሰበብ መመንጠር እና ማውደም የለባቸውም፡፡ ይህ ህገወጥ ድርጊት ነው፡፡ ስለሆነም መቆም አለበት…በአማሮች ላይ ማሰቃየት እና ከሰፈሩበት ቦታ ማፈናቀል እየተባለ የሚደረገው ውንጀላ እና የአመጽ ቅስቀሳ ኃላፊነት የጎደለው እና ለማንም የማይጠቅም ጉዳይ ነው…”
እ.ኤ.አ በ1991 የመንግስት ስልጣንን ከወታደራዊው መንግስት ለወያኔ የወሮበላ ቡድን በዕርቅ ሰበብ ያስረከቡት የቀድሞው የዩናይትድ ስቴትስ የአፍሪካ ጉዳዮች ረዳት ጸሀፊ የነበሩት ኸርማን ኮኸን እ.ኤ.አ ጃኗሪ 2012 በሰጡት ቃለ መጠይቅ እንዲህ ብለው ነበር፣ “እናም እርሱን (መለስን መሆኑ ነው) ስለመሬት ይዞታ ጠይቄው ነበር፣ ገበሬዎች የመሬት ባለቤት እንዲሆኑ እንዲፈቀድላቸው የማግባባት ስራ ቅስቀሳ ሳደርግ ነበር፡፡ እርሱም ይህጥሩ አይደለምምክንያቱም አማሮች መጥተውይወስዱባቸዋል፣ እናም ገበሬዎቹ በንጉሱ ዘመን እንደነበሩት ሁሉ ተመልሰው ወደ ጭሰኝነት ይገባሉ፡፡“
ናዚዎች አይሁዶችን በጥላቻ የተሞሉ የሚል ስም በመስጠት እና የወረደ አስተሳሰብ ያላቸው እያሉ በመሳደብ ስማቸውን ጥላሸት ይቀቡ ነበር፡፡ የወያኔ የወሮበላ የማፊያ ቡድንም በተመሳሳይ መልኩ በአማራ ህዝብ ላይ የጥላቻ ሰይጣናዊ መንፈስን በማንገስ እና በጎሳዎች መካከል ጥላቻን እና ውጥረትን በመፍጠር ብሄርን ከብሄር በማጋጨት የአማራን ስም ጥላሸት በመቀባት ላይ ይገኛል፡፡ አማሮች ለወያኔ የወሮበላ የማፊያ ቡድን አባላት አንድ ጠላት ብቻ አይደሉም ሆኖም ግን ድርብ ጠላት ናቸው፡፡ ለወያኔ የወሮበላ እና የማፊያ ቡድን አባላት አማሮች ቅኝ ገዥዎች፣ እብሪተኞች፣ ትምክህተኞች፣ ጨቋኞች፣ በህገወጥ መልክ የሚሰፍሩ ወንጀለኞች፣ ጦረኞች፣ ነፍጠኞች (ጠብመንጃ ያዥዎች፣ መሬት ነጣቂ ሰፋሪዎች)፣ የባርነት ጌቶች፣ ወዘተ ናቸው፡፡ ማቋረጫ በሌለው መልኩ አማራን ጥላሸት የመቀባት የፕሮፓጋንዳ ስራ የተፈጠረው አማራን ጥላሸት ለመቀባት ብቻ አይደለም ሆኖም ግን አማራን የስቃይ ሰለባ፣ ከህግ አግባብ ውጭ የመያዝ፣ ስልጣንን ከህግ አግባብ ውጭ መጠቀሚያ፣ የማታለል ስራ የመስራት፣ ይፋ የመተው እና ደንታቢስ የሆነ ዓላማን በአማሮች ላይ ለመተግበር ታስቦ ጭምር  እንጅ፡፡
ቬይና ላይ አድጎ በህይወት ዘመኑ በአይሁዶች ላይ የተፈጠረውን የሂትለር ጭፍን ጥላቻ ለማወቅ እጅግ ከባድ እንደመሆኑ ሁሉ በተመሳሳይ መልኩ መለስ ይባል የነበረ ቀንዳም ሰይጣን፣ ስም እንኳ ሳይቀር የሰዎችን ስም ቀምቶ የእራሱ ያደረገ ቀማኛ በመናገሻ ከተማዋ በአዲስ አበባ አድጎ በህይወት ዘመኑ በአማሮች ላያ ሲያራምድ የነበረውን ጭፍን ጥላቻ መንስኤ ለማወቅ እጅግ በጣም አስቸጋሪ ነገር ነው፡፡ መለስ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርቱን የተከታተለው እዚሁ አዲስ አበባ ነው፣ እናም የዩኒቨርስቲ ትምህርት የመጀመር ዕድሉንም አግኝቶ የነበረው በዚህቸው ታሪካዊ ከተማ ነበር ማጠናቀቅ ባይችልም፡፡
3ኢትዮጵያን መከፋፈል፣ መገነጣጠል እና መሸጥ እንዲሁም የኢትዮጵያን የግዛት አንድነትእናሉዓላዊነት መከፋፈል እና ማዳከም
በአሁኑ ጊዜ መለስ እና የወያኔ የወሮበላ የማፊያ ቡድን ኢትዮጵያን በመከፋፈል፣ በመገነጣጠል እና በመሸጥ እንዲሁም ከዕውቀት እጦት የተነሳ የሀገሪቱን ጥቅም እና ሉዓላዊነት አሳልፎ በመስጠት እጅግ በጣም ረዥም ርቀት ተጉዘዋል፡፡ እ.ኤ.አ ፌብሯሪ 2014 “ኢትዮጵያን ከቅርጫ ማዳን” በሚል ርዕስ የኃይለማርይም ደሳለኝ (በእራሱ ነጻነት ምንም ሀሳብ የሌለው እና ምንም ማድረግ የማይችል በወያኔ የሚጦዝ አሻንጉሊት) የኢትዮጵያን ሉዓላዊ ግዛት ቆርሶ ለሱዳን ለመስጠት ያደረገውን እኩይ ምግባር ህጋዊ መሰረት እንደሌለው እና የኢትዮጵያን አንጡራ ሉዓላዊ ግዛት በማንአለብኝነት መስጠት እንደማይችሉ እና ህገመንግስት እየተባለ ከሚጮሁለት ሰነድም በላይ እንደሆነ ሞግቼ ነበር፡፡ ይህ ትችት እ.ኤ.አ በ2008 “በምዕራቡ ግንባር ሁሉም ነገር ጸጥታ የሰፈነበት አይደለም” በሚል ርዕስ መለስ በሚስጥር የኢትዮጵያን የግዛት መሬት ቆርሶ ለሱዳን ለመስጠት እያደረገ የነበረውን ሰይጣናዊ ተግባር በመሞገት አቅርቤው ለነበረው ትችቴ ተቀጥላ ነው፡፡
ኢትዮጵያን ማዳን በሚለው የክርክር ጭብጤ መለስ ወይም ማንም ቢሆን የኢትዮጵያን የግዛት መሬት ለሱዳን አሳልፎ ለመስጠት ምንም ዓይነት ህጋዊ ስልጣን የለውም የሚል ነበር፡፡ በአሁኑ ጊዜም ኃይለማርያም የኢትዮጵያን ሉዓላዊ ግዛት በማንአለብኝነት በመድፈር አንጡራ መሬቷን ለሱዳንም ሆነ ለሌላ የመስጠት መብትም ሆነ ስልጣን የለውም፡፡ ያንን የክርክር ጭብጥ ባቅርብም ቅሉ መለስ በንቀት እና በእብሪት ልቡ ተደፍኖ ጉዳዩን ከምንም ሳይቆጥር ከአማራ ክልል ብዛት ያለውን መሬት ቆርሶ ለሱዳን ለመስጠት ስምምነት ተፈራረመ፡፡ ኃይለማርያም እና አሻንጉሊት አለቆቹ በአሁኑ ጊዜ ይህንን ህገወጥ የመሬት ዝውውር “ስልታዊ የስምምነት ማዕቀፍ” በሚል ሌላ ማደናገሪያ በመሸንቀር እና በማታለል ነገሩን ውጠን ዝም እንድንል ለማድረግ ጥረት እያደረጉ ነው፡፡ እውነታው ግን በአሁኑ ጊዜ በስልጣን ላያ ያለው ገዥው አካል በኢትዮጵያ ህገመንግስት ወይም በዓለም አቀፍ ህግ ምንም ዓይነት ህጋዊ መሰረት ሳይኖረው ማንኛውንም የኢትዮጵያ የሆነውን የግዛት መሬት ለሱዳን ወይም ለሌላ ለማንኛውም ሀገር አሳልፎ መስጠት አይችልም፡፡
እ.ኤ.አ ማርች 2011 “ኢትዮጵያ፡ ለሽያጭ የቀረበች ሀገር” በሚል ርዕስ ሀገሪቱ ቀስ በቀስ በመዋለ ንዋይ አፍሳሽነት ስም ምንም ዓይነት የሞራል ስብዕና ለሌላቸው እምነተቢሶች በሚስጥር እየተሸጠች መሆኗን በመጥቀስ የተሰማኝን ቁጭት በመግለጽ ይህ እኩይ ድርጊት በአስቸኳይ እንዲቆም የሚያሳስብ ትችት አቅርቤ ነበር፡፡ ኢትዮጵያ ለሽያጭ ቀርባለች፡፡ እያንዳንዱ ሰው የእርሷን ቁርጥራጭ መሬት በእርካሽ ዋጋ እያገኘ ነው፡፡ የመሬት ተቀራማች ጆቢራዎች ከሁሉም የዓለም ክፍሎች በመምጣት ጋምቤላ ላይ እየወረዱ ነው፡፡ መለስ ዜናዊ ኩራት በተቀላቀለበት መልኩ ህንድን፣ ቻይናን፣ ፓኪስታንን እና ሳውዲ አረቢያን ጭምሮ 36 ሀገሮች የእርሻ መሬት በሊዝ እየወሰዱ መሆናቸውን ተናግሮ ነበር፡፡ በዚያው ወር (ማርች 2011) ስምምነቶች አደገኛ በሆነ ፍጥነት እየተደረጉ ትላልቅ ትራክተሮች እና ከባድ የዛፍ ማስወገጃ ማሽነሪዎችን በማሰማራት እረግረጋማ ቦታዎችን ማንጠፋጠፍ እና መሬቶችን ማረስ ተጀመረ…በዓለም ከሚገኙ 25 የእርሻ ስራን ከሚሰሩ ድርጅቶች መካከል አንዱ የሆነው ካሩቱሪ የተባለው ድርጅት ፓልም ዘይት፣ ስኳር፣ ሩዝ እና ሌሎች ምግብ ነክ ነገሮችን በማምረት ከጋምቤላ ክልል ወደ ዓለም አቀፍ ገበያዎች በማቅረብ መስራት እንደሚችል ዕቅድ አወጣ፡፡
እ.ኤ.አ ማርች 2013 “መሬት እና የኢትዮጵያ የሙስና ዘረፋ” በሚል ርዕስ የዓለም ባንክ “ሙስናን በኢትዮጵያ መመርመር“ በሚል ርዕስ አጥንቶ ያቀረበውን ባለ550 ገጽ በዋቢነት በመጥቀስ በኢትዮጵያ የመሬት ዘርፉ ላይ ሙስና በብዙ መልኮች እየተገለጸ እና እየተፈጸመ እንደሆነ ለማሳየት ሞክሪያለሁ፡፡ በመጀመሪያ ደረጃ “የተማሩ እና ነባር ባለስልጣኖች” በሀገሪቱ ውስጥ በጣም ተፈላጊ ናቸው የተባሉትን መሬቶች በመንጠቅ ለእራሳቸው አድርገዋል፡፡ እነዚህ ወፍራም ድመቶች ደካማ ፖሊሲዎችን እና የህግ ማዕቀፎችን እንዲሁም ያለውን ደካማ ስርዓት እና ያሉትን ፖሊሲዎች እና ህጎች ለእራሳቸው ጥቅም እያወሉ ለእራሳቸው ጥቅም ከፍተኛ የሆነ ሙስና እየሰሩ እንደሆኑ ገልጨ ነበር፡፡ መሬትን ከተማም ሆነ በገጠር፣ እንደዚሁም ከቤት ስራ ማህበራት እና ከከተማ አልሚዎች ጋር በሚኖራቸው የስራ ግንኙት እራሳቸውን ከሙስና እና ከማታለል ስራዎች ጋር በማዛመድ ሙስናን ይሰራሉ፡፡ እነዚህ ተጽዕኖ ፈጣሪዎች እና በጥሩ ሁኔታ ትስስር ያላቸው ግለሰቦች መሬት በሀገሪቱ ካለው ህግ እና ደንብ ውጭ ለእራሳቸው እንዲመደብላቸው ያደርጋሉ፡፡
ለሩብ ክፍለ ዘመን ያህል አሁን በህይወት የሌለው መለስ ዜናዊ እና ህወሀት የጎሳ ፌዴራሊዝም በሚል የጎሳ ፖሊተካ ዕቅድን ይዞ በማራመድ ላይ ይገኛል፡፡ የወያኔው ወሮበላ የማፊያ ቡድን የኢትዮጵያን ህዝብ በጎሳ ሸንሽኖ ክልል (በጥሬ ትርጉሙ የተገደበ፣ የጎሳ ቤቶች እንደዚሁም የእራስ የግል የሆነ ዞን ወይም አንድ የተወሰነ ቦታ የሚል ትርጉምን ይይዛል)    እየተባሉ በሚጠሩ ትላልቅ የአካባቢ የፖለቲካ ተቋማት በማዋቀር ዜጎችን እንደ ከብት በአንድ አካባቢ ብቻ በማጎር ተግባራዊ በማድረግ ጥረት ላይ ይገኛል፡፡
በወያኔ እየተራመደ ያለው የክልልነት ፍልስፍና የአፓርታይድን የባንቱስታን (የጥቁር አፍሪካውያን/ት ክልል) ብዙ መገለጫዎች ይጋራል፡፡ አፓርታይድ በደቡብ አፍሪካ የባንቱስታንስ (የጥቁር ክልሎች) እንደፈጠረ ሁሉ በኢትዮጵያ ህገመንግስት አንቀጽ 39ን በማስገባት መለስም የጎሳ ክልሎችን ፈጥሯል፡፡ የአፓርታይድ አንቀጽ 51 ባንቱስታንስን ፈጥሯል፡፡ የመለስ አንቀጽ 39 ደግሞ ለብሄር ብሄረሰቦች ወይም ደግሞ ተመሳሳይ ልማድ፣ የመግባቢያ ቋንቋ፣ እምነት ወይም ተመሳሳይ ማንነት እና በከፍተኛ ብዛት በአካባቢው የሚኖሩትን ህዝቦች፣ እንዲሁም ጎረቤት የሆኑ ተዛማጅ ህዝቦችን በአንድ ላይ በማጀል ሰውን እንደ ከብት በመገደብ ክልል የሚል የመጠርነፊያ አካባቢዎችን አዋቅሯል፡፡ የአፓርታይድ እና የወያኔ ሁለቱም ፍልስፍናዎች ዓላማዎች ያነጣጠሩት የተወሰኑትን የጎሳ ቡድኖች በመንደር በማሰባሰብ እና ቋንቋን መሰረት ያደረጉ ግዛቶችን በመፍጠር በመጨረሻም ራስ ገዝ የሆኑ ሀገሮችን እንፈጥራለን በማለት የበሽታ ፈውስ መድሀኒት በማለት ለህዝቡ ለመስጠት የሚል ሲሆን በሌላ በኩል ግን ህዝብ ገዳይ የሆነ መድሀኒት ያዝዛሉ፡፡
ፕሮፌሰር ቴድ ቬስታል “የሰብአዊ መብት ድፍጠጣ በዴሞክራሲያዊት ኢትዮጵያ፡ የመንግስት እገዛ የሚደረግለት የጎሳ ጥላቻ“ በሚል ርዕስ ባቀረቡት ጽሁፍ የህወሀትን የክልላዊ የጎሳ ምደባ ስልት ግልጽ ያደርጋል ብለው ነበር፡፡ እንደዚሁም ህወሀት የኢትዮጵያ ህዝቦች አብዮታዊ ዴሞክራሲያዊ ግንባር (ኢህአዴግ) በሚል ሸፍጥ በሀገሪቱ ውስጥ የብዙሀን ፓርቲ ስርዓት ያለ ለማስመሰል እና በጎሳ ላይ የተመሰረተ እና በብሄር ብሄረሰቦች ላይ ትኩረት ያደረገ የጎሳ ፌዴራል መንግስት መመስረት እንደሆነ ግልጽ አድርገዋል፡፡ ይኸ በጉልህነት የሚታይ ከሌኒን የተኮረጀ የአገዛዝ መርህ ከዊልሶኒያን የበለጠ ከማቼቬሌን የሸፍጥ አካሄድ መሳ ለመሳ ነው፡፡ ኢህአዴግን/ኢፌዴሪን የሚያጦዙት እና የሚፐውዙት ብዛት ያላቸው ትግራውያን ስለሆኑ ሌሎች የጎሳ ቡድኖች እንዲለያዩ እና የእየራሳቸውን ጎሳ ብቻ እንዲይዙ በማድረግ አንዱ ጎሳ የሌላኛውን ባህል እና ቋንቋ አንዲሁም ልማድ እየፈራ በፍርሀት ቆፈን በእራሱ አካባቢ ብቻ ተሸብቦ ሲኖር ትላልቅ ጉዳዮች ግን በአንድ ፓርቲ ገዥው የወያኔ ወሮበላ ማፊያ ቡድን የሚፈጸሙ ይሆናል፡፡ ስለሆነም አህአዴግ በውሸት እና በሸፍጥ ፍልስፍና ብሄር ብሄረሰቦች ለአንዲት ታላቅ ሀገር ኢትዮጵያ የሚለው በእርሱ ቁጥጥር ስር እየዋለች ሌሎች እርሱን የሚቃወሙት የበለጠ እየተከፋፈሉ እና እየተሸነፉ ይሄዳሉ፡፡
አሁን በህይወት የሌለው መለስ ዜናዊ ኢትዮጵያን የባህር መዉጫ በማሳጣት እና ሀገሪቱን ወደብ አልባ በማድረግ የሀገሪቱን ጥቅም በእጅጉ የጎዳ ዕኩይ ድርጊት ፈጽሟል፡፡ የቀድሞው የዩኤስ አሜሪካ ፕሬዚዳንት የነበሩት ጂሚ ካርተር እና የቀድሞው የዩኤስ አሜሪካ የአፍሪካ ጉዳዮች ረዳት ጸሐፊ ኸርማን ኮኾን መለስን በማስጠንቀቅ እና በመለመን ዓይነት አቀራረብ የአሰብን ወደብ ወደ ኢትዮጵያ በመመለስ የባህር በር እንዲኖራት የጠየቁት እና ያሳሰቡት ተመዝግቦ ተቀምጧል፡፡ ሆኖም ግን የእነዚህ አንጋፋ የዲፕሎማት ሰዎች ልመና እና ጥያቄ መለስ ጆሮ ዳባ ልበስ ብሎት ቀርቷል፡፡
እ..ኤ.አ በ2000 ከኤርትራ የሁለት ዓመታት ጦርነት እና ወደ 80 ሺ የኢትዮጵያ ወታደሮች ካለቁ በኋላ አሁን በህይወት የሌለው መለስ የኢትዮጵያ እና የኤርትራን ጦርነት ለማቆም የሚያስችለውን የአልጀርሱን ስምምነት ፈረመ፡፡ ያ ስምምነት በሁለቱ ሀገሮች መካከል የድንበር መስመሮችን የሚያካልል እና ሌሎች ጉዳዮችን የሚፈታ የድንበር ኮሚሽን እንዲቋቋም አደረገ፡፡ ስለስምምነቱ ሊታመን የማይችለው የሚያስገርመው ነገር እና ይቅርታ ሊደረግለት የማያገባው አሳዛኙ ነገር እ.ኤ.አ በ1998 ኤርትርራውያን/ት በሰሜን ኢትዮጵያ የምትገኘውን ባድሜን ከወረሩ በኋላ እና ኤርትራውያን/ትም በዚያ ጦርነት በተሸነፉ ጊዜ መለስ ከመቅጽበት እንደ ባህር ዓሳ በመገለባበጥ የባድሜን አንጸባራቂ የኢትዮጵያውያንን/ትን ድል በመቀልበስ ባድሜን በእርቅ ሰበብ ለወራሪዎቹ የሚሰጥ ስምምነትን በመፈረም አጠቃላይ የዲፕሎማሲ ሽንፈትን የመከናነቡ ጉዳይ ነው፡፡ ይህ ሁኔታ በዘመናዊው የዓለም ታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ አንድ ሀገር እጅግ ግዙፍ የሆነ የሰው ህይወት ገብሮ እና ለቁጥር የሚያታክት ንብረት እንዲወድም አድርጎ በኃይል አሸንፎ ከግዛቱ ወራሪውን ኃይል ካባረረ በኋላ እንደገና እንደ መዳብ ብረት ተለምጦ ያንኑ በአሸናፊነት የተቆጣጠረውን የእራሱን ግዛት ለዓለም አቀፍ ዕርቅ ተገዥነት በሚል የደካሞች አስተሳሰብ ወይም ደግሞ ለዕኩይ ዓላማው ሽፋን በመስጠት አሳልፎ ለጠላት የሚሰጥ በዓለም ላይ የመጀመሪያው ሳይሆን አይቀርም፡፡
(ይቀጥላል)
ኢትዮጵያ በክብር ለዘላለም ትኑር!
 ህዳር 16 ቀን 2007 .