Saturday, December 20, 2014

የኢትዮጵያ ዕድል በባዕዳ ሲወሰን
 ፍኖተ ዴሞክራሲ የኢትዮጵያ አንድነት ድምጽ 
Finote Democracy Voice of Ethiopian Unity 
Efdpu@aol.com www.Finote.org 
ፕሮግራም፡ ረቡዕ እሁድ ከምሽቱ ሁለት ሰአት እስከ ሶስት ሰአት በ 25 ሜትር ባንድ 
Programm. Wednesday and Sunday 8.00 PM – 9.00PM on 25 meter band 
የፍኖተ ዴሞክራሲ የኢትዮጵያ አንድነት ድምጽ ሀተታ 
ታህሳስ 8 ቀን 2007 ዓ.ም. የተላለፈ 
የኢትዮጵያ ዕድል በባዕዳ ሲወስን 
ምዕራባውያን ፤ ከሁሉም በላይ የሚጠሉትና የሚፈሩት፤ ከየትኞቹም ሀገራት የሚመጡትን ሀገር- ወዳድ መሪዎችን ነው ። ሀገሩን አፍቃሪና አርበኛ የሆነ መሪ ወደ ሥልጣን እንዲመጣ ቀርቶ፤ በሀገሬው ሕዝብ ፈቅድና ውሳኔ የተመረጥን መሪ እንኳን ቢሆን ከሥልጣኑ እንዲወገድና እንዲገደል ከማድረግ አይመለሱም ። ይህ አባባል ባዕዳንን ከመጥላትና ከመፍራት የሚሰነዘር ጭፍን ምክንያት አይደለም ። ምክንያታዊ -አልባ/ ቢስ ላለመሆኑ፤ በታሪክ የተደገፈ ማስረጃ እየጠቀሱ ማቅረብ ይቻላል። በሌሎቹ አህጉራት የተፈፀሙትን ወንጀሎች ለጊዜው አቆይተን፤ በአፍሪካ የተፈጸሙትን የሦስት ሀገራት ሀገር ወዳድ መሪዎች፤ ከመሪነት ሥልጣናቸው ማስውገድና ማስገድል ፤ እንደ አብነት መጥቀስ ብቻ ይበቃናል ። የጋናውን ኩዋሚ- ንኩርማኅ ፤ የኮንጎውን ፓትሪስ ሉሙባን፤ የሞዛምብኪውን ሳሞራ ማሸልንና የአልጀርያውን አህመድ ቤንቤላን ጠቅሶ መመዝገብ በቂያችን ነው ። እነኝህ የ4 ሀገራት መሪዎች፤ ሀገሮቻቸውን ከቅኝ ግዛት ቀምበር ታግለው ነጻ ከማውጣታቸውም ባሻገር ፤ ሕዝቦቻቸውን ከድህነት፤ ከማይምነትና ከበሽታ ለማላልቀቅ ብሩህ ራዕይና ስትራተጃዊ ዕቅድ የነበራቸው ምሁራን መሪዎች ነበሩ ። ይህንን የማይወዱ ምዕራባውያን ሁሉንም፤ በየተራ እያደኑ አጠፏቸው ። በምትካቸው ደግሞ፤ ለራሳቸው ጥቅም አስፈጻሚ የሚሆኑትን ታማኝ አገልጋዮቻቸውን ወደ ሥልጣን በማምጣት ፤ የአፍሪካን ሀብት ለመበዝበዝ የሚያስችላቸውን ዋስትና ለያረጋግጡ ችለዋል ። አሁንም ይህንኑ በመፈጸም ላይ ናቸው። 
ሀገርችን ኢትዮጵያም ፤ ከሁለተኛው ዓለም ጦርነት ፍጻሜ ጀምሮ፤ከባዕዳን ተጽዕኖና ቁጥጥር አልተላቀቀችም ። በሦስት ከተሞች በሚፈራረቁ የባዕድን መሰሪ ፖሊሲዎች ሰለባ እየሆነች ቆይታለች ። በዚህ ተጠቃሽ ዘመን፤ አንድ ጊዜ ሎንዶን፤ ሌላ ጊዜ ሞስኮና ዋሽንግቶን ላይ በሚጠነሰሱ ፖሊሲዎች ስትሽከረከር ነበረች ። አሁንም ይህ ሁኔታ እንዳለ ነው። በአንድ ወይም በሌላ ወቅት በሚደረጉ የባዕዳኑ ዲፕሎማሲ ገበጣ ጨዋታ ስትጎዳ ኖራለች። ይህ ሁኔታ፤ ዛሬም ቢሆን በከፋ መልኩ ቀጥሎባታል ። የሀገሪቱን ህልውና አደጋ ላይ እስከመጣል ድረስ ! 

ደርግ፤ በሚያሳፍርና በሚያዋርድ መልኩ የሞስኮ መሪዎችን ሙዚቃ ሲደንስ ቆይቶ ሀገርን አጥፍቶ፤ ሕዝብን ጨርሶ፤ ደብዛው ጠፍቶ ቀረ። የማታ-ማታ ግን አለቆቹ አላዳኑትም ። ይህች ጉደኛ ሀገራችን፤ ዛሬም ቢሆን፤ የመከራ ገመዷ ስለአልተበጠሰላት፤ ከሞስኮ ወደ ዋሽንግቶን በተሸጋገረው የባዕዳን ገበጣ ጨዋታ በሚደንሱ ወያኔዎች ስር ወድቃ ትማቅቃለች። " ለድህነት ያደለው፤ ቢነግድ አይተርፈው " እንደሚባለው፤ የዓመታት መቀያየር፤ የክፍለ-ዘመናት ወለዋወጥና የመሪዎች መፈራረቅ ፤ በኢትዮጵያና በሕዝቦቿ ዕጣ-ፋንታ ላይ ያመጣው ፋይዳ የለም ። ዜጎቿም፤ የራሳቸውን ነጻነትና ህይወት፤ ኑሮም ይሁን የወደፊት ዕድላቸውን ለመወሰን የማይችሉ እየሆኑ ቆይተዋል ። ይህ ሁኔታ እስከመቸ ይቀጥላል ? እንዲቀጥልስ ሊፈቀድለት ይገባል ዋይ ? አርበኛና ሀገር -ወዳድ መሪዎችን መቸ ነው ኢትዮጵያ ለታገኝ2 
የምትችለው? ነጻነት ማለት ሰንደቅ ዓላማ ማውለብለብ ብቻ ነውን ? እነኝህንና መስል ጥያቄዎችን እየጠየቁ ተገቢውን መልስ ማግኘት ከያንዳንዱ ዜጋ የሚጠበቅ ተግባር ነው። 
በባዕዳን እየተጠፈጠፉና ለባዕዳን ጥቅም የቆሙ፤ ሳይሆኑ፤ ለሀገራቸው ነጻነት ቀናዒ፤ ለህዝባቸው ጥቅም ተቆርቋሪ፤ ለሀገራዊ ኩራት ተንሰፍሳፊና ለወገን ፍቅር ሟች፤ ለህግ ተገዥ፤ ለዴሞክራሲ ሥርዓት የቆሙ መሪዎችን ማፍራት፤ የነጻነት ዋስትና ይሆናል። ይኅንን ማደረግ የሚችለው ደግሞ ራሱ የኢትዮጵያ ሕዝብ ብቻ መሆኑን አምኖ መቀበል ያስፈልጋል ። ይህ እስካልሆነ ድረስ፤ ሀገራችን ከባዕዳን ተጽዕኖ ነጻ ተወጣለች ብሎ ማሰብ የኅልም እንጀራ ሆኖ ይቀራል። 
በቀጥታም ይሁን በተዛዋሪ መንገድ፤ ባዕዳን ሀገራችንን ፈጽሞ፤ በቀላሉ ሊለቋት አይፈልጉም በማለት በርካታ የፖለቲካ ጠበብቶችና የታሪክ ምሁራን ስጋታቸውን ይገልጻሉ ። ይህ ስጋት፤ ከዕውነት የራቀ ነው ማለት አይቻልም ።ይህንን ለማስረግጥ ደግሞ ካለፈው ታሪክ ማስረጃ መጥቀስ ብቻ ሳይሆን፤ የወቅቱን የሀገሪቱን ነባራዊ ሁኔታንና በመሬት ላይ የሚታዩትን ተጨባጭ ኩነቶች በማገናዘብ፤ አሳማኝ መሆናቸውን ማረጋገጥ ይችላል ። ኃያልን - ባዕዳን መንግሥታት ኢትዮጵያን በብርቱ የሚፈልጓትና ጠቃሚነቷንም በቀላሉ የማያዩበት በርካታ ምክንያቶች አሏቸው ።አንኳር- አንኳር የሆኑትን እንጠቅሳለን፡ ---- 
1ኛ. ስትራተጂያዊ መልከዐ -ምድር አቀማመጧ የ ( ጂኦ-ፖልቲክስ ) ይዞታዋ በአንደኛ ደረጃ አስቀምጧታል ። በአፍሪካ-ቀንድ አካባቢ ታላቅና ታሪካዊ ሀገር ነች። የመካከለኛ ምሥራቅን፤ የቀይ ባህርን- በብዔል-መንደብን፤ አፍሪካንና አስያን፤ ለመቆጣጠርና ለማዝዝ የምታስችል ሀገር መሆኗን ማንም አይክደውም ።ለህንድ ውቅያኖስም ያላት ቅርብት ፤ ጠቃሚነቷን ያጎላዋል ። ምዕራብያኑ፤በተፈላጊነታቸው በእጅጉ ካተኮሩባቸው የአፍሪካ ሀገሮች መካከል፤ ሴኔጋልን ናይጀሪያንና ኢትዮጵያን በግምባር ቀደም እንደ ፈርጇቸው የታወቀ ነው ። 
ሀገራችን፤ የአፍሪካ ዓይነተኛ መዲና በመሆኗ፤የአፍሪካ ኅብረት ፤ የአፍሪካ ኢኮኖሚ ኮሚሲዮንና ሌሎችም ዓላም አቀፍ ተቋማት- አድባራት መቀመጫ መሆኗ ለሳፈላጊነቷ ጥርጥር የለውም ። የዓለም የንግድ፤ የባኅል፤ የሳይትፊክ፤ የፊናንስ፤ ባንኮችና -ንግድ መናሃሪ ነች። ይህ ሁሉ ተጠራቅሞ፤ የአፍሪካ ዕንቁ ( ጅዌል ኦፍ አፍሪካ ) የሚል የቁልምጫ ስም አትርፎላት። ይህንን ሁሉ ግምት ውስጥ ያስገቡት ባዕዳን ኅይሎች ኢትዮጵያን እንዲሁ በቀላሉ የሚተዋት ሀገር አልሆንችላቸውም ። አለመታደል ሆኖ ነው መስል፤ እኛ ዜጎቿ ግን፤ " በእጅ የያዙትን ወርቅ እንደ መዳብ ይቆጥሩታል " የሚል ተረት ተተርቶብናል ። ሀገራችንን አስመልክቶ፤ ከአድማስ -ባሻገር ለማየት የሚያስችል ራዕይ አጥተናል ። ይህ ደግሞ በመሪዎች ዘንድ ጎልቶ ይታያል ። ባጋጣሚ የሚመጡ መሪዎቿ ሁሉ እንደ ቤት -ኪራይ መቆያና መበዝበዣ እንጅ እንደ ቋሚ ምድርና ለትውልድ ትውልድ ለትተላለፍ የሚግባት ሀገር መሆኗን አያስቡም ። 
2ኛ. የመሬት ስፋቷ ትልቅ መሆን፤ የሕዝቧ ቁጥር ከፍተኛ መሆኑ፤ ከአፍሪካ ሀገሮች በሕዝብ ብዛት ሦስተኛ ያደርጋታል። ይህ ደግሞ፤ ለኢዱስትሪ ዕቃቸው መሸጫ ሰፊ ገበያ ስለምትሆንላቸው ፤የሸቀጥ - ዕቃ ማራገፊያ አመች ሆና አግኝተዋታል ። ያልተነካውን- ያልተዳሰሰውን ጥሬ ሃብቷን ለመዝረፍም3 
ተመችቷቸዋል ። የሕዝብ ቁጥር ብዛት፤ ለአንድ ሀገር ስትራተጃዊ ሀብት ብቻ ሳይሆን የማይነጥፍ ንብረትና የሚንከባከቡት የከበረ- ዕንቁ ( ትሬዠር ) ነው ። ኢትዮጵያንና የሕዝቧንም ማንነት የሚያደንቅና የሚያከብር መሪ እስካልተከሰተ ድረስ ፤ ሀገሪቱ አልባሌ ሆና መቆየቷ ይቀጥላል ። ይህ ሁኔታ በበኩሉ፤ ሀገራችን የባዕዳን መፈንጫ ሆና ቀርታለች ። ? 
3ኛ. ምናልባትም ፤ በተፈጥሮ ሀብት፤ ከአፍሪካ ሀገሮች መካከል ተወዳዳሪ የሌላት ሀገር መሆኗ ፤ የዐየር ጠባይዋ ተስማሚነት፤ለም አፈሯ ፤ እስካሁን በጥቅም ላይ ያልዋሉ የታላላቅ ወንዞቿ፤ የባዕዳንን ቀልብ ሲስብ ኖሯል። ብዛት ብቻ ሳይሆን፤ ድንበር-ዘለል በሆኑት ወንዞቿ ምክንያት፤ ወደፊት በዓለም አቅፍ የውሃ ዲፕሎማሲም ሆነ፤ " የውሀ- ጦርነት " ምክንያት ልትጫወተው የምትችለውን ሚና ግምት ውስጥ ማስገባት በዕንዝህላልነት የሚታለፍ አይደለም። ወደፊት፤ የዓለም አቀፍ ፖለቲካ ትክረት ከሚሰጣቸው ዐበይት የመነጋገሪያ ነጥቦች ( አጀንዳዎች ) መካከል፤ የውሀ ጉዳይ መሆኑ፤ ስትራተጂያዊ አመለካከት ያላቸው ጠበብቶች ይተነብያሉ ። ይህ ራሱ፤ ሀገራችንን በጉዳዩ ላይ ግንባር -ቀደም ተዋናይ ያደርጋታል ። ይህ በበኩሉ ደግሞ ፤ ኢትዮጵያን የበለጠ በመካከለኛው ምሥራቅ በሚገኙ ሀገሮችና በምዕራባያኑ ዘንድ የማትናቅ ፤ ግን ፤ ተፈላጊ ሀገር አድርጓታል ። ይህንን የተገነዘቡ መሪዎች እስካላገኘች ድረስ ግን ፤ ምፀትና እንቆቅልሽ የሚፈራረቁባት ሀገር ሆኗ ትቆያለች። እየጠሏት የሚፈልጓት፤ እየናቋት የሚፈሯት፤ እየገፈተሩ የሚስቧት ሀገር መሆኗን የማይገነዘብ ዜጋ አለ ብሎ ለማምን ያስቸግረናል ። የኢትዮጵያን ተፈላጊነት፤ ለሀገራዊ ጥቅሟና ለብሄራዊ ጸጥታዋ፤ ለሕዝቧ ነጻነትና በልጽግና ለመለወጥ መቻል አለበት ። ይህ ደግሞ ወያኔ እያለ የሚሳካ አይደለም ። ይህንን ዘረኛ ሥርዓት መለወጥ የሚያስፈልገው በዚህ ዐብይ ምክንያት ነው ። 
4ኛ. በአካባቢዋ ሰር የሰደደው የሃይማኖት አክራሪነት- ጽንፈኝነት ወደ አደገኛ አሸባሪነት በመሸጋገሩ ምክንያት፤ ያፍሪካ ቀንድም ሆነ የመካከኛው ምሥራቅ የአደጋ ቀጠና ከሆነ ቆይቷል ። ኢትዮጵያም በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ መንገድ ፤የአደጋው ገፈት-ቀማሽ ከመሆን የምትድን አይመስልም ። በእስራዔሎችና ፍልስጤማውያን ግጭት ምክንያት፤ በአካባቢው ልትከተል የምትፈልገውን ዲፕሎማሲ፤ ገላዋን ሰድዳ/እንደልቧ እንድታካሂድ አላስቻላትም። ( ፕሪካሪየስ ሁኔታ ላይ ልትሆን የምትችልበት ግፊት ይኖራል ተብሎ የታሰባል ) ። የሁለቱ ታላላቅ ሃይማኖቶች መዲና በመሆኗ ዜጎቿ፤ የክርስቲያንና የእስልምና ምዕመናን ናቸው ። በሁለቱ ምዕመናን መካከል፤ እነርሱን የሚያኮራ፤ ዓለምን የሚያስደንቅ ትብብርና ክብብር ሰፍኖ ይኖራል ። 
በመሆኑም፤ ኢትዮጵያ ወደፊት ለምትከተለው በገለልተኝነት መርኅ ላይ ለሚመሰረተው ፖሊሲዋ አውንታዊ አስተጋቦኦ ይኖረዋል ተብሎ ቢገመትም፤ ይህ ግምት ተጨባጭ ሊሆን የሚችለው፤ ሀገራችን በአካባቢው፤ የፈረጠመ ፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ኀይል ሲኖራት መሆኑ አያከራክርም ። በኢኮኖሚ ደርጅታ፤ የፖለቲካ ግዝፈቷን ካረጋገጠች ፤ በአካባቢው ልታሳድር የምትችለው ተጽዕኖ ፤ የራሷን ጸጥታ ከምታስከብርበት ደረጃ መድርሷ አይቀርም ። ተፈላጊነቷም፤ በአውንታዊ መልኩ የሚቀጥል ይሆናል ።ለአካባቢው ጸጥታና መረጋጋት ልትጫወተው የሚያስችላትን ሚና ተከባሪ ሊያደርግላት ይችላል ተብሎ ይገመታል ።አሁን በወደቀችበት የጎሳ ክፍፍል አገዛዝ ግን፤ ይህ የሚታስብ አይሆንም ። የዚህ ሥርዓት መለወጥ አንግብጋቢ የሚሆነውም፤ ከዚህ አኳያ ነው ። 
5ኛ. በሦስተኛውና አራተኛው ተራ ቁጥሮች እንደተገለጸው፤ ምዕራባውያኑ፤ ከምን ጊዜውም በበለጠ፤ ዛሬ በወያኔ አገዛዝ ያለችውን ኢትዮጵያ ኣጥብቀው የሚፍልጓት፤ የጠነከረ ምክንያት አላቸው። ጥቅማቸውን ለማስጠብቅ የሚችል ቡድን ወያኔ በመሆኑ ነው ።ያላንዳች ማመንታት፤ ትእዛዛቸውን ሊፈጽምላቸው የሚችል ታማኝ አገልጋይ፤ ከወያኔ የተሻለ እንደማያገኙ አረጋግጠዋል ። ምዕራባውያኑ፤ ከወያኔ ጋር ፈላጊና ተፈላላጊ ናቸው። ወይኔ ውኅዳን በመሆኑ በምልዐተ- ሕዝቡ ዘንድ ተቀባይነት እንደሌለው አሳምሮ ያውቃል ። 
በመሆኑም፤ በሥልጣኑ ለመቆየት፤ጥንድ ፖሊስ ማራመድ አለበት ። አንደኛው ሕዝቡን እየከፋፍሉ እርስ-በእርስ እንዲናከስ ማድረግ ሲሆን፤ ሁለተኛ፤ የውጭ ረዳትና ተባባሪ ማግኘትን መረጋገጥ ነው። ጊዚያዊም ቢሁን ሁለቱ ዘዴዎች አልተሳኩለትም ማለት አይቻልም ። ሰኔና - ሰኞ ተገጣጥመውለት ጊዚያዊ ስኬት አግኝቷል ። ይህ ግን ዘለቄታ እንድማይኖረው በዕርግጠኝነት መናገር ይቻላል ። ይኅን ለማለት የሚያስችሉ ሁለት ምክንያቶች አሉ ። አንደኛው፤ የዲፕሎማሲው ይትበሃል እከክልኝ- ልከከልህ በሚል (ሪፕሮሲቲ ) ፖሊሲ ዙሪያ የሚሽገረገር በመሆኑ፤ አንደኛው ወገን፤ ጥቅሜ አልተጠበቀልኝ ከሚል ደርጃ ከደረሰ፤ ሽርከኛውን ጥሎት እንደሚሄድ ግልጥ በመሆኑ ነው ። ጊዚያው ጥቅምና ጊዚያዊ ወዳጅ እንጅ ዘላቂ ጥቅምና ዘላቂ ወዳጅ የሚምባል ነገር ስለሌለ ፤ አንድ ቀን ወያኔን አፍንጫህን ላስ ብለው እንደሚጥሉት ያውቃል ። ዛሬ ከቻይናዎች ጋር የሚያደርገው መሞዳሞድም፤ መገልበጫ አልጣም ከሚል ራስን ከመደለለል እሳቤ እንደሆነ አይሳትም ። ሁለተኛው ምክንያት፤ የወያኔ፤ ሕዝብን፤ በዘር፤ በቋንቋና በሃይማኖት የመከፋፈሉ አሰራር፤ ከጊዜ ወደ ጊዜ ስሩ እየተመነገለ በመሄዱ ነው ። ይህ የዘረኛ ፖሊስ መርዘኛና አጥፊ መሆኑን ሕዝቡ በሚገባ ተረድቱት አንድነቱን ከምን ጊዜውም በበለጠ እያጠነከረ በመሄድ ላይ ነው ።የሕዝቡን አንድነትና ትብብር ከተረዱ፤ ምዕራባውያኑ፤ ለጥቅማቸው ሲሉ፤ ሌላ አገልጋይ ለመፈልግ እንደሚሯሯጡ የቀርብ ክስተቶች አረጋግጠዋል ። የልብ አገልጋይ በመሆን ጥቅማቸውን ሲያስጠብቅላቸው የኖረውን የግብፁን መሪ ሁስኒ ሙባረክን ሕዝቡ ሲያምጽበት አይተው፤ እንዴት አጋልጠው እንደሰጡት የትላንት ትዝታ ሆኗል ። 
6ኛ. ከላይ የተዘረዘሩት ምክንያቶች፤ ከሞላ ጎደልም ቢሆን ፤የኢትዮጵያን ተፈላጊነት- አስፈላጊነት ለመገንዘብ ቢያስችሉም፤ የሀገራችንን አስከፊ ሁኔታ ለመለወጥ ግን በርቱ ሥራ እንደሚጠብቅ ሁሉም ሊረዳው ይገባል ። ምዕራባውያን ሌላ ታማኝ አሽከር የሚሆንላቸውን ቡድን ለመለወጥ እንደማይቦዝኑ ቢታወቅም፤ የኢትዮጵያ ሕዝብ አዲስ የባእዳን አሽገር እንዲመጣበት አይፈልግም ። የሕዝቡ ዓላማና ግብ፤ ቅን አገልጋይ የሚሆንለትን መሪ መምረጥ ብቻ ነው ። ይህንን መሪ የሚያገኘ ደግሞ በራሱ መንገድና በዴሞክራሲ ሂደት መርጫ ሲያከሂድ ብቻ ነው። ይህ ግን እስካሁን አልተሳካለትም ።እስካሁን ሲደረግ የቆየው፤ በባዕዳን እየተቦካ የሚጠፈጠፍ ወያኔን በሥልጣን የማቆየት ቲያትር ነው ።የሚቀጥለውም የግንቦቱ የወያኔ ምርጫ የተለየ አይሆንም ።ይህንን ተግባራዊ ለማድረግ፤ ምዕራባውያኑ የቤት ሥራቸውን ሰርተው ጨርሰዋል ። ወያኔም በበኩሉ ሥርውን እየሰራ ይገኛል። ይህም ያልተጠበቀ አልነበረም ። 
7ኛ. በመጭው ግንቦት የወያኔ የምርጫ ድራማ ጨዋታ ፦---- 
ሀ) ምዕራባውያኑ፤ ወያኔን እንደገና በሥልጣን እንዲቆይ ማረጋገጣቸው ብቻ ሳይሆን፤ በጠቅላይ ምኒስትር ደረጃ ማን መሆን እንዳለበት መርጠው አስቀምጠዋል ። ከአንድ አሻንጉሊት ግለስብ፤ ወደ ሌላ አዲስ አሻንጉሊት አገልጋይ በማዛዋወር፤ የራሳቸውን ጥቅም የማስጠበቁን ሁኔታ አረጋግጠዋል ። 
ለ ) በወያኔም በኩል፤ ታማኝነታችውን በብቃት ለመውጣት አስፍስፈው የሚጠባበቁ ዕሳት የበሉ ካሃዲዎች ተሰልፈዋል ። 
ሐ) " ሎሌ በአፍላው የአህያ መዥገር ይከላላል " እንደተባለው፤ አዲሱቹ አገልጋዮችም አሮጊዎቹን በሚያስንቅ ደረጃ ኢትዮጵያን የመጥፋቱን ተልዕኳቸውን በትጋት የቀጥሉበታል ። 
መ) የዓለም አቅፉን ኅበረተሰብ ለማታለል፤ " ነጻና መልካም ምርጫ " ( ፍሪ- ኤንድ ፌር ኤሌክሽን ) ምርጫ ተካሄዷል ለማሰኘት የተቀነባበረ ፕሮፓጋንዳ ያካሂዳሉ ። ጥቂት የፓርላማቸውን መቀመጫዎች ለምርጫው ላሰፈሰፉ ግለስቦች የመጸውታሉ። ጥቂት እስረኞችንም ያስፈታሉ ። 
ሰ) ለቲያትራቸው ይበልጥ ፈገግታ ለመስጠት እንዲቻልና የሕዝቡንም የትኩረት አቅጣጫ ለማሳት በሚያደርጉት ጥረት፤ በምርጫው ሂድት መካከል፤ ገለስቦችን የማሰርና የመፍታት ድራማ ያካሂዳሉ ። ወያኔዎቹ፤ በሚያስሩ- በሚፈቷቸውና በነርሱ መከከል፤ ቅድመ- ስምምነት ይኖራል ። ይኸውም ፤ ተስማምተን - እስሩንና ፈርመን ለቀቁን ( ፍቱን ) የሚል አስቂኝ ቀልድ ይካሄዳል ። ይህም ቲያትር ቀደም ባሉት ጊዚያት ተከናውኗል ። ተጎንብሰው - እጅ ነስተው - ይቅርታ ጠይቀው - ፈርመው- ጠፈጥመው የተለቀቁት ማን ማን እንደነበሩ ሕዝቡ በሚገባ ስለሚያውቃቸው ስም መዘርዘር አስፍላጊ አልመሰለንም ። 
8ኛ. ሀገራችን ኢትዮጵያ ከውጭ ባዕዳንና ከሀገር- በቀል ጠላቶቿ ለመላቀቅ ከፈላገች፤ ዜጎቿን አስተባብራ ሕዝባዊ የነጻነት ትግል ከማድረግ የተለየ ሌላ አማራጭ የላትም !ይህንን ማደረግ ደግሞ ያማይቻል አይደለም ። እራሱን ነጻ ለማውጣት ግን መሥዋዕታዊ ትግል ወሳኝ ነው ። ነጻነትን በወርቅ ቆለምሽሽ የሚሰጥ የለም ። 
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኖራለች ! 

No comments:

Post a Comment