Friday, December 19, 2014

ገረድ አትበለኝ (ለጠ/ር ሀይለማርያም ደሳለኝ)

ESAT_Radio_Thu_11_Dec_2014.mp3

Postby ሚጥሚጣ » 
***ገረድ አትበለኝ!!***

አልተገዛሁ እኔ ግርድናም የለብኝ፤
እድሜ ባንተ ዘመን ግዞት ተጥሎብኝ፤
በማያፍረው አፍህ እሰደባለሁኝ።
ሰድቦ አሰዳቢ ጥሎብኝ ቡችላ፤
ሌባ አሰራቂ ለጅብ የሚያስበላ፤
ማንነት አስጠቂ ያገር አሜኬላ፤
ገረድ ካንተ በላይ የት ይገኛል ሌላ።
--------------------/////-------------------
ባለጌ ስድ አደግ ላፋ ለከት የለው፤
ሀገሬን ለባዳ ለሰዳቢ ሰጠው።
ያ ጉልቱ ድንጋይ ይሻለኛል ካንተ፤
ሀገሩን ከሸጠ በቁም ከበከተ።
--------------////----------------
ሰብስበህ እየዋልክ ጭንቅላቱን ያጣ፤
ካንተ የደነዘ ለኑሮ ጐባጣ፤
ጀግንነቴን ገለህ ውርደት ከላይ ወጣ።
ካንተ በላይ ገረድ ለሆድ አዳሪ፤
እኮ የት ይገኛል የኢትዮጰያ መሪ።
---------------/////-------------------
ታሪክን የሚፈጭ ታሪኳን ሸራፊ፤
መሬቷን አየሸጥክ የሆንከው አትራፊ፤
ካንተ በላይ ገረድ ካንተ በላይ ለፊ፤
ለስደት አጋዡ ጡሩንባውን ነፊ።
እኮ የት ይገኛል አራስህ ንገረኝ፤
አንተ አውርሰኸኝ አንተ አታሰድበኝ፤
ስሙ የራስህ ነው ገረድ አትበለኝ።


#####


አቶ ሃይለማርያም ደሳለኝ በአሜሪካ፣ አውሮፓና አረብ አገራት ስለሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ከተናገሩት።
አንዳንድ ጊዜ አሜሪካ አገር ውስጥ የሆነ መርቸዲስ ምናምን መኪና ባለበት ተገትረው ፎቶ ይነሱና ከዚያ በሁዋላ ወደ ቤተሰባቸው ይልኩና ይሄ የእኔ መኪና ነው ይላሉ፤ ማንም እንደሚላቸው ግን አይደሉም"


ለልጆቼ ዶሮ ወጥ ይዘህ ሂድ አሉኝ። እሽ ብየ ተሸክሜ ሄድኩኝ ብደውል ብደውል ስልኩ እምቢ አለኝ። ምንድነው ሲባል ይሄ እማ ሃይም ውስጥ ነው አለኝ። ሃይም ምንድነው አልኳቸው? ሰው የሚሰቃይበት እስር ቤት ነው አሉኝ። ዶሮ ወጡን ይዤ ሃይም ውስጥ ሄድኩኝ። ስደርስ ኮንቴነር ውስጥ ነው ያሉት። ከዚያ ዱቄት ይሰጣል። ዱቄት ብቻ ነው የሚሰጠው። እቃውን አስረከብኩና ታዲያ ያ ሁሉ ፎቶግራፍ የላካችሁልን ከየት የመጣ ነው አልኩኝ። ብዙዎቻችን እናውቃለን ሰው እንዴት ውጭ አገር እንደሚኖር።"


ሳውዲ ሄደን እህቶቻችችንን ማየት አልቻልንም። ለምንድነው ማየት ማይፈቀድልኝ ? ብየ ጠየኩ ። ሃይማኖታዊ ስነስርዓት ሊሆን ይችላል። ከዚያ ደግሞ ወጣ ስንል መንገድ ላይ እንዳበደ ውሻ የሚኖሩ እህቶቻችንን አየን። ከዛ ደግሞ ወጣ ስንል ወደ አንድ ሺ የሚጠጉ እህቶቻችን ኢምባሲ ውስጥ ተኮልኩለው በዛ ሙቀት ውስጥ ኤር ኮንዲሸን በሌለበት ታጭቀው በዚያ ሲሰቃዩ አየን።"

No comments:

Post a Comment