Saturday, January 31, 2015

የሕወሃት ታጥቂዎች የአንድነት ፓርቲን ጽ/ቤት በኋይል ተቆጣጥረዉታል። ወደ ፓርቲዉ ፅህፈት ቤት መዉጣትም ሆነ መግባት አይቻልም!!

Jan 31st, 2015 · 0 Comment

0
10943889_1541649606105436_297487080983844425_n
Current government of Ethiopia forcefully invaded “Unity Party”: No Entry and coming out from the officeየሕወሃት ታጥቂዎች የአንድነት ፓርቲን ጽ/ቤት በኋይል ተቆጣጥረዉታል። ወደ ፓርቲዉ ፅህፈት ቤት መዉጣትም ሆነ መግባት አይቻልም!!
ዛሬ ጠዋት የተሰበሰበው የስራ አስፈጻሚው ባደረገው ጥሪ መሰረት የአንድነት ፓርቲ ብሄራዊ ምክር ቤት አባላት እነ ከ 43 የአንድነት ቅርንጫፍ ቢሮዎች የተወከሉ አመራሮች ስብሰባ ተቀምጠዋል የሚሉ መረጃዎች እየተሰሙ ነው::በተመሳሳይ የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት (መኢአድ) ቢሮው በፖሊስና በደህንነቶች በመከበቡ ወደ ፓርቲዉ ፅህፈት ቤት መዉጣትም ሆነ መግባት አይቻልም!!
የሕወሃት ታጥቂዎች የአንድነት ፓርቲን ጽ/ቤት በኋይል ተቆጣጥረዉታል። ጥዋት ሥራ አስፈጻሚው ስብሰባ አደረጎ የነበረ ሲሆን፣ ከሰዓት በኋላ ምክር ቤት ሊሰበሰብ ታስቦ የነበረ ቢሆን፣ ደህንነቶች ጽ/ቤቱን ከበው ማስገባትና ማስወጣት ስላልተችለ፣ የምክር ቤቱ ስብሰባ ሳይደረግ ቀርቷል። ሆኖም የሥራ አስፈጻሚው ጠዋት ባደረገው ዉስኔዎችን አስተላልፏል። የመጀመሪያ ዉሳኔ በአገሪቷ ክፍል ያሉ የአንድነት አባላትና ደግፊዎች በሕወሃት ለተቋቋመው ተለጣፊ ቡድን ምንም ኣይነት እውቅና እንዳይሰጡና እንዳይደገፉ ጥሪ አቀርበዋል።
የሥራ አስፈጻሚው በአዲስ ስም መንቀሳቀሱ፣ ሕወሃት ተመሳሳይ እርምጃ እንዳይወሰድ የማያከላክለው በመሆኑ፣ መሰረታዊ የዲሞክራሲ ተቋማት ለዉጥ በሌለበት መልኩ አዲስ ስም አወጥቶ እንደገና መንቀሳቀስ ዋጋ እንደሌለው ገልጸዋል። ሌሎች ድርጅቶችን መቀላቀሉ በተመለከተ ያ የአባላት የግል ዉሳኔ እንደሆነ አስረድተው፣ ነገር ግን እንደ አንድነት ሥራ አስፈጻሚ ወደ ሌል ድርጅት ቢቀላቀሉም፣ አገዝዙ ተመሣሳይ እርምጃ በተቀላቀሉት ድርጅት ላይ ሊወስድ እንደሚችል አስረድተዋል
- See more at: http://satenaw.com/amharic/archives/4262#sthash.G12YPuKI.dpuf

ከአንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ (አንድነት) የተሰጠ መግለጫ

Jan 31st, 2015 · 0 Comment

የገዢውን ፓርቲና መንግስትን ሽፍትነት ያጋለጠው አንድነትን የማፍረስ የምርጫ ቦርድ ውሳኔ በኢትዮጵያዊን ዘንድ ተቀባይነት አይኖረውም!!!
ጥር 21/2007 ዓ.ም በኢትዮጵያ ታሪክ የምርጫ ቦርድ የሚባል ተቋም ያለበትን ደረጃ ይፋ ያደረገ ሲሆን፤ በዚህ ደረጃ እንዲዋራድ ከጀርባ ሆኖ አመራር የሚሰጠው ገዢ ፓርቲም ሆነ መንግሰት በዚያው ልክ የሚገባቸውን የተዋረደ ደረጃ የያዙበት ዕለት ነው ብለን እናምናለን፡፡ አንድነት ፓርቲ አንድም የህግ ጥሰት ሳይፈፅም የሚያደርጋቸውን ሁሉ በፓርቲው መተዳደሪያ ደንብና በሀገሪቱ ህግ እየፈፀመ ባለበት ሁኔታ በህግ ሽፋን የገዢው ፓርቲ ልሳን የሆነው ፋና ሬዲዮ፣ የመንግሰት ሬዲዮና ቴሌቪዥን ከምርጫ ቦርድ ጋር በመተባበር የከፈቱት ዘመቻ የመጨረሻ የሆነውን አንድም ህጋዊ መሰረት የሌለውን ህገወጥ ውሳኔ በአንድነት ፓርቲ እና አባላት ላይ አሰተላልፈዋል፡፡
ገዢው ፓርቲና መንግሰት በምርጫ ቦርድ በኩል እንዲነበብ ያደረጉት የፖለቲካ ውሳኔ በኢትዮጵያ ሀገራችን የመድበለ ፓርቲ ስርዓት ከወረቀት አልፎ በተግባር እንዳይታይ ግብዓት መሬቱን ፈፅመዋል፡፡ በዚህ ፀያፍ ተግባር ከፊትም ሆነ ከጀርባ ሆነው የተሳተፉ ግለሰቦችም ሆኖ ተቋማት በታሪክ ተገቢው የውርደት ቦታ እንደሚይዙ እምነታችን ነው፡፡ ይህ ህገወጥ አካሄድ ህጋዊ መሰመር እንዲከተል የበኩላቸሁን ድርሻ የተወጣችሁ የአንድነት አባላትና ደጋፊዎች በሀገር ውሰጥም ሆነ በውጭ የምትገኙ ሁሉ በተለይ በገዢው ፓርቲ እኩይ ሴራ በሀስት ተወንጅላችሁ በወህኒ ቤት ለምትማቅቁ ታጋዮች ታሪካችሁ በወርቅ ቀለም ተፅፎዋል፡፡ በቀጣይም ያለምንም መዘናጋት እና ተሰፋ መቁረጥ በምናደርገው ሰላማዊ ትግል በሀገራችን ኢትዮጵያ የመድበለ ፓርቲ ሰርዓት ትንሳኤ እንደሚሆን ምንም ጥርጥር የለንም፡፡
የምርጫ ቦርድ ተብዬው ተቋም በህገወጥ መንገድ ለሆዳቸው ባደሩ ጥቂት አንድነት ፓርቲ አባላት እና በአንድነት አባልነት በማይታወቁ የገዢው ፓርቲ ጥርቅሞች ለተደረገ ጠቅላላ ጉባዔ  ዕውቅና ሰጥቻለሁ ማለቱን በምንም መመዘኛ ተቀባይነት የሌለው ሲሆን፣ የአንድነት ፓርቲ አባላት ያነገብነው የነፃነት መንፈስ በምርጫ ቦርድ በሚሰጥ ሰርተፊኬትና ዕውቅና ማዕቀፍ ውስጥ የሚገኝ ስለአልሆነ ለነፃነት የምናደርገውን እልህ አስጨራሽ ትግል የምንቀጥል ሲሆን፤ በሁሉም ደረጃ የሚገኙ የአንድነት መዋቅሮች እና የአንድነት አባላት ለዚህ ህገወጥ ቡድን በግልፅ እውቅና እንዲነሱ እንጠይቃለን፡፡
ፓርቲያችን በመጨረሻ ሰዓት እንኳን ተፈትነው ለወደቁ ተቋማት እድል ለመስጠት ወደ ፍርድ ቤት ለመሄድ ወሰኖ እንቅሰቃሴ በማድረግ ላይ ቢሆንም፤ በዛሬው ዕለት ጥር 22/ 2007 ከቀኑ ሰባት ሰዓት ጀምሮ የፓርቲያቸን ፅ/ቤት በፖሊስ ተወሮ የፓርቲው ንብረት ያለምን ህጋው ርክክብ በቁጥጥር ስር እንዲውል ተደርጎዋል፡፡ በአሰተዳደር የተሰጠን ውሳኔ በፍርድ ቤት የማሰለወጥ ህጋዊ ሰርዓት እንዳለ ቢታወቅም ህገወጥ አስተዳደራዊ ውሳኔን በፖሊስ ወረራ ለማሰፈፀም የተሄደበት መስመር ገዢው ፓርቲና መንግሰት አሁንም ከጫካ አሰተሳሰብ ያለመውጣቸውን እና የአውራ ፓርቲ ፍልስፍናቸውን በማናለብኝነት ለመተግበር መቁረጣቸውን የሚያሳይ ነው፡፡ በዚህ ህገወጥ ድርጊት ተጠያቂው ትእዛዙን ያስተላለፈው ክፍል መሆኑ መታወቅ ይኖርበታል፡፡
ሰለሆነም በሀገር ውስጥ እና በውጭ የምትኖሩ ኢትዮጵያዊያን፣የሰብዓዊ መብት ተማጋች ድርጅቶች፣ የዓለም አቀፍ ማህበረሰብ እንዲሁም በኢትዮጵያ ሀገራችን የመድበለ ፓርቲ ሰርዓት እንዲጎለብት ፍላጎት ያለችሁ ሁሉ ይህን እኩይ ተግባር በማውገዝ ተጨባጭ እርምጃ እንድትወሰዱ ጥሪያችንን እናቀርባለን፡፡
ድል የህዝብ ነው!!!
ጥር 22/ 2007 ዓ.ም
- See more at: http://satenaw.com/amharic/archives/4265#sthash.qmthOR71.dpuf

የአንድነትና የመኢአድ ቢሮ በፖሊስ ተከቧል
የአንድነት ለፍትሕና ዴሞክራሲ ፓርቲ (አንድነት) ቢሮ በፖሊስና በደህንነት መከበቡን አቶ አስራት አብርሃ ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጸዋል፡፡ ቢሮው በደህንነትና በፖሊስ በመከበቡ አባላት መውጣትና መግባት እንደማይችሉ የገለጹት አቶ አስራት ‹‹ውጭ ያለነው ወደ ውስጥ እንዳንገባ ተከልክለናል፡፡ ውስጥ ያሉትም መውጣት አይችሉም፡፡›› ብለዋል፡፡ የአንድነት አመራሮችና አባላት እንዳይወጡና እንዳይገቡ የከለከሉት ደህንነትና ፖሊሶች የከበባውን ምክንያት እንደማይናገሩ አቶ አስራት ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጸዋል፡፡ በተመሳሳይ የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት (መኢአድ) ቢሮው በፖሊስና በደህንነቶች በመከበቡ አመራሮችና አባላቱ ወደ ውስጥ መግባትም ሆነ ወደ ውጭ መውጣት እንደማይችሉ ተግልጾአል፡፡
 - See more at: http://www.zehabesha.com/amharic/archives/38595#sthash.8B9B7lVi.dpuf

Friday, January 30, 2015

በቅንጅት ለአንድነትና ለዲሞክራሲ (ቅንጅት) ፓርቲ የሬሣ ሳጥን ላይ የመጨረሻ የሚባለውን ሚስማር መትቷል፡፡

አንድነትን “እናኝከዋለን፤ እንገድለዋለን” – ምርጫ ቦርድ

January 30,2015
ትዕግስቱ አወሉ እንደ አየለ ጫሚሶ
tplfs election board

የዛሬ አስር ዓመት “የሕዝብ ሱናሚ” እያለ ሲምል ሲገዘት የነበረው ህወሃት ሱናሚው ወደ እርሱ እየጎረፈ ሲመጣ በረገገ፡፡ መፍትሔ በጠብመንጃ አፈሙዝና በብረት ብቻ እንደሆነ የሚያምነው ህወሃት በረሃ የለመደውን በትሩን አነሳ፤ ንጹሃንን ጨፈጨፈ፤ ደም አፈሰሰ፤ ኢትዮጵያን ወደ እስርቤትነት ቀየራት፡፡ ትዕዛዙን በቀጥታ የሰጡት “ባለራዕዩ” ለፍርድ ሳይቀርቡ “እንደጀመርን እንጨርሰዋለን” ያሉትን ሰፊውን ሕዝብ ሳይጨርሱት እንደ ክዳን ቆርኪ ተስፈነጠሩት፤ ላይመለሱ ሄዱ፡፡
የዛሬ አስር ዓመት የቅንጅት አካሄድ ያስፈራው ህወሃት ጉዳዩን ለራሱ ለፓርቲውና ለሕዝብ ከመስጠት ይልቅ ደም መቃባት ውስጥ ገባ፡፡ ፓርቲው የነበረበት የውስጥ ችግር እንዳለ ሆኖ የፈሪ በትር የዘረጋው ህወሃት የገደለውን ገድሎ ከጨረሰ እና የኢትዮጵያን መሬት በደምና በእናቶች እምባ እንደገና ካጨቀየ በኋላ ቅንጅትን የማፍረስ ተግባሩን በዕቅድ ይዞ በይፋ መንቀሳቀስ ጀመረ፡፡ ግምባር ቀደም ተሰላፊው የተቋም ባንዳ “ምርጫ ቦርድን”፤ በግለሰብ ደረጃ ደግሞ በተለይ ሁለት ግለሰቦችን አሰለፈ፡፡ ዘመቻ “ቅንጅትን መግደል” ተጀመረ፡፡
በወቅቱ የነበረውን ሁኔታ ምንም በማያሻማ ሁኔታ በኢትዮጵያ የቀድሞ የአሜሪካ አምባሳደር የነበሩት ዶናልድ ያማሞቶ በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር (ስቴት ዲፓርትመንት) ለሚገኙት አለቆቻቸው THE ETHIOPIAN GOVERNMENT CHEWS THE CUD” (የኢትዮጵያ መንግሥት ቅንጅትን አኘከው) በሚል ርዕስ የጻፉት እንዲህ ይነበባል፤
Over the course of the week of January 7, the National Electoral Board of Ethiopia (NEB) hammered what appear to be the final nails in the coffin of the opposition Coalition for Unity and Democracy (CUD) party. Since their surprise showing in the 2005 elections, gaining enough seats to become the second largest political party in Ethiopia, the CUD has virtually disintegrated as a result of internal power struggles and interference from the Ethiopian Government (GoE). In the latest setback, the NEB awarded the famous victory sign — the CUD symbol widely recognized by voters — to former ally turned foe, Lidetu Ayalew of the United Ethiopian Democratic Party-Medhin (UEDP-Medhin).  The NEB followed this later in the week by finally awarding registration of the reformed Coalition for Unity and Democracy Party (CUDP) party name to yet another former CUD ally turned foe Addis Ababa city council member-elect Ayele Chamisso.  Though Ayele, who is broadly viewed as having been co-opt by the GoE, has invited all faction of the former CUD to join his party, few will likely take his offer.
In a meeting with Ambassador on January 11, NEB board chairman Dr. Merga Bekana and vice-chairman Dr. Addisu Gebre-Egziabhier said that the Board still had not decided on the CUDP’s registration and would continue to consider the matter in coming weeks. Almost immediately following the meeting, however, the NEB publicly announced that it had decided that morning to award the party license to Ayele. This followed their controversial decision earlier in the week to give the CUD’s famous victory symbol to the CUD’s despised adversary Lidetu Ayalew (another person believed to have been co-opted by the GoE during the CUD’s post-2005 election struggles), and his UEDP-Medhin party.
The opposition fiercely accused the NEB of being under the influence of the GoE and of delivering votes to the ruling Ethiopian Peoples Revolutionary Democratic Forces (EPRDF) party after the opposition’s surprisingly strong showing. Since then, a new Board has been put in place, but the opposition have not altered their criticism. The NEB’s recent decisions to award the CUD party symbol and name to politicians, who are at best undeserved and at worst proxies of the GoE, has done much to reignite lingering suspicions regarding the NEB’s independence. As if to prove these suspicions, NEB vice-chairman Dr. Addisu (a Tigrayan political scientist widely believed to be the “enforcer” at the NEB) recently commented to USAID’s Senior Democracy Advisor — a former Stanford University Political Science Professor ) (strictly protect) that the NEB had decided to “kill the CUD.” The NEB decisions of the last week have effectively done exactly that.
በጃኑዋሪ 7 ሳምንት ወቅት የኢትዮጵያ ብሔራዊ የምርጫ ቦርድ በቅንጅት ለአንድነትና ለዲሞክራሲ (ቅንጅት) ፓርቲ የሬሣ ሳጥን ላይ የመጨረሻ የሚባለውን ሚስማር መትቷል፡፡ በ2005 (1997) ምርጫ በአገሪቱ ሁለተኛው ትልቁ የተቃዋሚ ፓርቲ ለመሆን የሚያስችለውን አስደናቂ ድልና በቂ መቀመጫ ካገኘ በኋላ ቅንጅት በውስጡ በነበረው የኃይል (የሥልጣን) ሽኩቻና ከኢትዮጵያ መንግሥት በኩል ይደርስበት በነበረው ጣልቃ ገብነት ምክንያት አለሁ ቢልም እየተፈረካከሰ ነበር፡፡ በቅርቡ በተደቀነበት ሌላ ደንቃራ ደግሞ ምርጫ ቦርድ ዝነኛውንና በብዙሃን መራጭ ዘንድ ዕውቅና የነበረውን የቅንጅትን (V) ምልክት ቀድሞ (የቅንጅት) ወዳጅ በኋላ ጠላት ለሆነው የኢትዮጵያ ዴሞክራቲክ ፓርቲ – ኢዴፓ-መድህን ልደቱ አያሌው ሸልሞታል፡፡ በመቀጠልም ምርጫ ቦርድ ይህንን ተከትሎ የቅንጅት ለአንድነትና ለዴሞክራሲ ፓርቲ የስም ምዝገባ ቀድሞ የቅንጅት ወዳጅ በኋላ ጠላት ለሆነው የአዲስ አበባ ምክርቤት እጩ ተመራጭ አየለ ጫሚሶ ሸልሞታል፡፡ የኢትዮጵያ መንግሥት ቅጥረኛ እንደሆነ በሰፊው የሚታመነው አየለ ጫሚሶ ከቀድሞው ቅንጅት ተሸራርፈው ለወጡት ሁሉ የእርሱን ፓርቲ እንዲቀላቀሉ ጥሪ ቢደርግም ጥቂቶች ብቻ ጥሪውን ይቀበላሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡ . . .
addisu  g of neb
አዲሱ ገብረእግዚአብሔር
የምርጫ ቦርድ ሊቀመንበር ዶ/ር መርጋ በቃና እና ምክትል ሊቀመንበሩ ዶ/ር አዲሱ ገብረእግዚአብሔርከአምባሳደሩ (ያማሞቶ) ጋር ጃኑዋሪ 11 ቀን ባደረጉት ስብሰባ የቅንጅትን ምዝገባ በተመለከተ ገና ውሳኔ ላይ እንዳልደረሱ እና በመጪዎቹ ሳምንታት ጉዳዩን እንደሚመለከቱት ነበር የተናገሩት፡፡ ነገር ግን ወዲያውኑ ስብሰባው እንዳበቃ ማለት ይቻላል የዚያኑ ቀን ጠዋት የቅንጅትን የስም ምዝገባ ለአየለ ለመስጠት መወሰኑን ምርጫ ቦርድ ለሕዝብ ይፋ አደረገ፡፡ ይህ የቦርዱ ውሳኔ በሳምንቱ መጀመሪያ አካባቢ የቅንጅትን ዝነኛ (V) ምልክት በቅንጅቶች ለተናቀውና የፓርቲው ጠላት ለሆነው ልደቱ አያሌውና ለኢዴፓ-መድህን ፓርቲው ለመሸለም የተደረገውን አከራካሪ ውሳኔ ተከትሎ ነው፡፡ (ልደቱ አያሌው ከምርጫ 1997 በኋላ ቅንጅት ውስጥ በነበረው ትግል ውስጥ በኢትዮጵያ መንግሥት የተመደበ ሌላው ቅጥረኛ እንደሆነ ይታመናል)፡፡ . . .
ምርጫ ቦርድ በኢትዮጵያ መንግሥት ሥር እንደሆነ እና ተቃዋሚዎች አስገራሚ ውጤት በምርጫው ላይ ካሳዩ በኋላ (የመራጮችን) ድምጽ ለኢትዮጵያ ሕዝቦች አብዮታዊ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (ኢህአዴግ) እንዳስረከበ ተቃዋሚ (ፓርቲዎች) አጥብቀው ይከስሳሉ፡፡ ከዚያ ወዲህ አዲስ ቦርድ የተሰየመ ቢሆንም ተቃዋሚዎች ግን አሁንም ትችታቸውን አላቆሙም፡፡ የቅንጅትን ስም እና ምልክት ፍጹም ለማይገባቸውና ለኢትዮጵያ መንግሥት የቅርብ ወዳጆች ለሆኑት ፖለቲከኞች ማስረከቡ ምርጫ ቦርድ ከአድልዎ የነጻ አለመሆኑ ላይ ያሉትን ጥርጣሬዎች እንደገና እንዲቀጣጠል አድርጓል፡፡ የምርጫ ቦርድ ምክትል ሊቀመንበር ዶ/ር አዲሱ በቅርቡ ለዩኤስኤይድ ከፍተኛ የዴሞክራሲ አማካሪና የቀድሞ የስታንፎርድ ዩኒቨርሲቲ የፖለቲካ ሳይንስ ፕሮፌሰር (ስሙ እንዳይወጣ በጥብቅ የተከለከለ) ምርጫ ቦርድ “ቅንጅትን ለመግደል” ወስኖ እንደነበር መናገሩ እነዚህን ጥርጣሬዎች እርግጠኛ ያደርጋቸዋል፡፡ (የአዲግራት ተወላጅ የሆነው) (ዶ/ር አዲሱ የትግሬ የፖለቲካ ሳይቲስት ሲሆን የምርጫ ቦርድ “ፈጣሪና አድራጊ” እንደሆነ በሰፊው ይታመናል)፡፡ ባለፈው ሳምንት ምርጫ ቦርድ የወሰደው ውሳኔ (የቅንጅትን ስምና ምልክት ለቅጥረኞቹ መስጠቱ) ይህንኑ (ቅንጅትን የመግደሉን ዕቅድ) የሚያረጋግጥ ነው፡፡ . . . (ሹልክዓምድ (ዊኪሊክስ) ላይ የወጣውን ሙሉ መረጃ ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ)
አሁንስ ማነው ባለሳምንት? በዚህኛው የምርጫ ድራማ አየለ ጫሚሶን የሚጫወተው ትዕግስቱ አወል እንደሆነ ይፋ ሆኗል፤ ልደቱንስ ማን ይተውነዋል?
ከዚህ በፊት በሰማያዊና በሌሎች ፓርቲዎች ላይ የደረሰውና አሁንም እየደረሰ ያለው እንዲሁም ሰሞኑን በአንድነት ፓርቲ አመራሮች፣ አባላትና ደጋፊዎች ላይ የደረሰው ሰቆቃ የዘንድሮውን ሁኔታ የተለየ እያደረገው እንደሆነ ጎልጉል ከተለያዩ ምንጮች የሚደርሱት መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡ ስለዚህም ነው “ምርጫ ቦርድ” ቅንጅትን በዕቅድ እንደገደለው አሁንም አንድነትንና ሌሎቹን ተቀናቃኞች “አኝኮ ለመግደል” ውሳኔው የሆነው፡፡
ከሕዝብ በኩል የሚሰማው የሰላማዊ ትግል ቁርጠኝነት ግን የህወሃትን የልመና ኮሮጆ በሚሞሉት ምዕራባውያንም ዘንድ ትልቅ ትኩረት የተሰጠው እንደሆነ ጎልጉል የደረሰው መረጃ ያመለክታል፡፡ የአንድነት ፓርቲ ሰልፍ በተካሄደበት ወቅት በተለያዩ የማኅበራዊ ገጾች ላይ ተሰራጭቶ ያገኘነውን መረጃ መጥቀሱ የቁርጠኝነቱን መጠን በተወሰነ መልኩ የሚያመለክት ነው፡፡ “በዕለቱ የደረሰበትን ጉዳት አስመልክቶ ለቢቢኤን ሬዲዮ የተናገረው የአዲስ አበባ ወጣቶች ጉዳይ አንድነት ፓርቲ ኃላፊ ስንታየሁ ቁስሉ ሳይደርቅ በወኔ እንዲህ ነበር ያለው “ወያኔ ላጠፋው ጥፋት የሚያወራርደው ሒሳብ እንዳለ ማወቅ አለበት፡፡ ለትግላችን እንሰዋለን፤ በዋዛ አንላቀቅም”፡፡

Wednesday, January 28, 2015

አንዳንዶቹ በግዳጅ ከመኖሪያ ቀያቸው ተፈናቅለዋል

ኢትዮጵያ

ሕግጋቱን ይጥሳል የተባለው የዓለም ባንክ

የዓለም ባንክ ለኢትዮጵያ የልማት ስራዎች በሚያደርገው ድጋፍ የራሱን ህግጋት እና መርሆዎች በተደጋጋሚ መጣሱ ተነገረ።የኢትዮጵያ መንግስት ከዓለም ባንክ ያገኘውን የገንዘብ ድጋፍ በጋምቤላ ክልል ለሚያደርገው የግዳጅ የሰፈራ መርሐ-ግብር ሲጠቀምበት ቆይቷል የሚል ወቀሳም ይሰነዘርበታል።
Landverpachtung an ausländische Investoren in Äthiopien
የኢትዮጵያ መንግስት በጋምቤላ ክልል እንደ ጎርጎሮሳውያኑ አቆጣጠር ከ2010 እስከ 2013 ዓ.ም. ድረስ የሰፈራ መርሐ-ግብር ሲያካሂድ መቆየቱን የዓለም ባንክ አጣሪ ቡድን ዘገባ ያትታል።በዘገባዉ መሠረት የሰፈራ መርሐ-ግብሩ 45,000 ነዋሪዎችን መሰረታዊ አገልግሎቶች በሚያገኙበት መንገድ ለማስፈር የታቀደ ነበር። በዓለም አቀፍ የምርመራ ጋዜጠኞች ጥምረት (The International Consortium of Investigative Journalists) ይፋ የተደረገው እና ከባንኩ ሾልኮ ወጥቷል የተባለዉ የአጣሪ ቡድን ዘገባ የዓለም ባንክ ለጤና፤ትምህርት፤የገጠር መንገድ፤ግብርና፤የመጠጥ ውሃ አቅርቦት እና ንጽህና አገልግሎቶችን ለማሳደግ ለኢትዮጵያ መንግስት ያደረገውን የ2 ቢሊዮን ዶላር ድጋፍ እና የሰፈራ ፕሮግራም ያላቸውን ግንኙነት የፈተሸ ነው። ‘ከመኖሪያ ቀያችን በግዳጅ ተፈናቅለናል’ በማለት የኢትዮጵያ መንግስትን በከሰሱ 26 የአኙዋክ ተወላጆች ጥያቄ የተቋቋመው አጣሪ ቡድን ያዘጋጀው ሰነድ የሰፈራ መርሐ-ግብሩ በግዳጅ መከናወኑን፤ ከዓለም ባንክ ለመሰረታዊ አገልግሎት ተብሎ የተመደበው ገንዘብም ነዋሪዎችን አስገድዶ ለማስፈር መዋሉን ይጠቁማል። ሰዎችን በማፈናቀልና ሌላ ሥፍራ በማስፈሩ ሒደት በአኝዋክ ተወላጆች ላይ ድብደባ፤አስገድዶ መድፈር እና ግድያ መፈጸሙን ዘግቧል።እንደ ጎርጎሮሳውያኑ አቆጣጠር ከ1996-99 ዓ.ም. በኢትዮጵያ የአሜሪካ አምባሳደር የነበሩት ዴቪድ ሺን አሁን የዓለም አቀፍ ጉዳዮች ፕሮፌሰር ናቸው።
Landverpachtung an ausländische Investoren in Äthiopien Flash-Galerie
«በኢትዮጵያ የጋምቤላ ክልል የተካሄደውና በ2013 የተጠናቀቀው የሰፈራ መርሐ-ግብር ለሰፊ የእርሻ መዋዕለ-ንዋይ የአኙዋክ ተወላጆችን ወደ ሌሎች የሃገሪቱ አካባቢዎች ለማዘዋወር ያቀደ ነበር።በዚህም አንዳንዶቹ በግዳጅ ከመኖሪያ ቀያቸው ተፈናቅለዋል የሚል ትችት ይቀርባል። ይህንን የግዳጅ ሰፈራ የሚያረጋግጡ ማስረጃዎችም አሉ።የዓለም ባንክ የሰፈራ ፕሮግራሙ በግዳጅ እንደሚካሄድ እያወቀ ድጋፍ ማድረጉ ነው አሁን ክርክር የፈጠረው።»
ከመኖሪያ ቀያቸው በግዳጅ ተፈናቅለዋል ከተባሉት የአኙዋክ ተወላጆች መካከል ወደ ኬንያ እና ደቡብ ሱዳን ለመሰደድ የተገደዱ እንዳሉ የዓለም ባንክ አጣሪ ቡድን ዘገባ ይገልጻል። ቡድኑ የዓለም ባንክ በግዳጅ ሰፈራው በቀጥታ ተሳትፎ ባይኖረውም የገንዘብ ድጋፉ ለመርሕ-ግብሩ ማስፈፀሚያ መዋሉን ባንኩ መቆጣጠር አለመቻሉንና የተፈናቃዮቹን ደህንነት በቸልታ በማለፍ የራሱን ህግጋት እና መርሆዎች መቃረኑን ያትታል።የሰፈራ መርሐ-ግብሩን በበላይነት የሚያስፈጽሙ የኢትዮጵያ መንግስት ባለስልጣናትም ከዓለም ባንክ የገንዘብ ድጎማ ደሞዝ ይከፈላቸው እንደነበር ይኸው ዘገባ ይፋ አድርጓል።
ከመኖሪያ ቀያቸው በግዳጅ ተፈናቅለው ለስደት ለተዳረጉ 26 የአኙዋክ ተወላጆች የሚከራከረው ኢንክሉሲቭ ዴቨሎፕመንት ኢንተርናሽናል (Inclusive Development International) ሃላፊ ዴቪድ ፕሬድ ስለጉዳዩ ጠይቀናቸው «የዓለም ባንክ የጋምቤላ ህዝቦችን ቀርቦ በማማከር ከፍርሃት እና ከሰቆቃ ነጻ በሆነ መንገድ ፍላጎታቸውን መሰረት ያደረገ እና በማህበረሰቡ የሚመራ የመልሶ ማቋቋም ስራ መሰራት ይኖርበታል።» ሲሉ በኢ-ሜይል መልሰውልናል።
Flash-Galerie Äthiopien Land Grab
አምባሳደር ዴቪድ ሺን በበኩላቸው የአጣሪ ቡድኑ ዘገባ የዓለም ባንክ ከኢትዮጵያ ጋር በሚኖረው ቀጣይ ግንኙነት ላይ ሊያሳድር የሚችለው ተጽዕኖ ለመኖሩ እርግጠኛ አይደሉም።
«የዓለም ባንክ ከኢትዮጵያ ጋር ለረጅም ጊዜ የዘለቀ መልካም ግንኙነት አለው።ኢትዮጵያ የዓለም ባንክን ድጋፍ በመጠቀም ጥሩ ምሳሌ እንደሆነችም ያምናል። በኢትዮጵያ የሰፈራ መርሐ-ግብር መካሄድ ከጀመረ ብዙ ጊዜ ሆኖታል። አንዳንዶቹ በግዳጅ የተካሄዱ ነበሩ። ችግሩ አዲስ ሳይሆን የቆየ ነው። ስለዚህ ባንኩ ችግሩ አንዳች ውሳኔ ወይም እርምጃ ያስፈልገው እንደሆነ መወሰን ይኖርበታል። ለጊዜው ምን ሊያደርጉ እንደሚችሉ የማውቀው ነገር የለም።»
የዓለም ባንክ የስራ አስፈጻሚ የአጣሪ ቡድኑን ዘገባ ከመገምገሙ በፊት ምንም አስተያየት እንደማይሰጥ የባንኩ የአፍሪቃ ጉዳዮች ቃል አቀባይ ፊል ሄይ መናገራቸውን ዓለም አቀፍ የምርመራ ጋዜጠኞች ጥምረት ዘግቧል።
እንደ ጎርጎሮሳውያኑ አቆጣጠር በ2013 ዓ.ም. በተጠናቀቀው የሰፈራ መርሐ-ግብር 37,883 ቤተሰቦች ከመኖሪያቸው ወደ ሌላ አካባቢዎች መዘዋወራቸውን የዓለም ባንክ አጣሪ ቡድን ዘገባ ያትታል። በግዳጅ ሌላ አካባቢ የተዘዋወሩት የአኙዋክ ተወላጆች ከለም የመኖሪያ አካባቢያቸው ለመልቀቅ ባይፈልጉም በፖሊሶችና ወታደሮች መገደዳቸውን በዚህም የሰብዓዊ መብት ጥሰት መፈጸሙን ዘገባው ገልጿል።
እሸቴ በቀለ
ነጋሽ መሐመድ

Police Brutally Attack Peaceful Protesters in Addis Ababa ahead of National Election


By Betre Yacob
Ethio-police2
Police brutally attacked and dispersed peaceful demonstrators in the capital Addis Ababa on Sunday as they try to protest against the ongoing government repression on opposition political parties and dissents in run-up to the countries general election..
Political activists say the Sunday’s attack against the peaceful demonstrators is further evidence of the authorities’ determination to clamp down the activities of opposition political parties ahead the election.
In this latest brutal attack against peaceful protesters, dozens of members and supporters of Unity for Democracy and Justice Party (UDJ) were seriously injured. The incident is the most blatant and massive case of lethal police brutality in Ethiopia.
According to reports, demonstrators were brutally beaten with baton, stick and iron rod in the head, face, hands, and legs. One of the victims is said to have been a pregnant woman. Reports show the victims were taken to hospital right away, and some of them are still receiving medical treatment.
Among seriously injured was Sileshi Hagose, the member of the general assembly of the party and editor in chief of a weekly newspaper. Recently released photographs show that he was wounded in the face and head, and his both hands were seriously broken.
UDJ is the main opposition political party struggling in the narrowing political landscape in Ethiopia and is one of the few parties working at national level with an inclusive structure by bringing different ethnic groups all together.
Reports show in the past few weeks the party has been struggling with the National Election Board of Ethiopia (NEBE) over the case of an internal faction that is accusing the party of violating its laws.
The party claims that the faction is consisted of double agents working for the ruling party, and accuses the NEBE of fuelling the problem and using the allegation of the faction as a tactic to tackle the party in favor of the government. And one of the objectives of Sunday’s demonstration was to protest against this what the party calls “government plot.”

The Sunday’s brutal attack is the latest in a serious of similar measures against peaceful demonstrators in Ethiopia. For instance, on 6 December 2014 several people were beaten during attempts to stage a demonstration called by a coalition of nine opposition political parties.
Amnesty international reported that the demonstration had been part of a series of activities of nine-party coalition calling for a free and fair election.”
Reports show holding an election rally or demonstration is now totally impossible in Ethiopia as government continue to reject applications for such events and keep its brutal attack against those trying to held.
Escalating Crackdown
According to the National Election Board of Ethiopia (NEBE), the election will be held on May 23 across the country. Yet, as the election approaches, the ruling party is intensifying its crackdown on opposition political parties and dissents.
In 2014 only, several opposition leaders, Journalists, bloggers, and Human Right activists were arrested with numerous publications of the free press closed. More than 30 journalists were also forced to flee the country. The arrest is part of a long trend of arrests and harassment of political opponents, human rights defenders, and journalists.
Activists said at least 12 key and outspoken opposition political leaders, 6 journalists, 6 bloggers, and 2 political activists had been jailed in the capital Addis Ababa only under fabricated terrorism charges.
The ongoing crackdown has included independent civic associations that could play an important role in the upcoming election. Reports shows in 2014 two civic associations were targeted in orchestrated false accusations.
This wide array of measure, which is getting increasingly worrying, is said by oppositions to be calculated to deter challenges and eliminate the scope for the mildest expressions of opposition.
The Ethiopian People Revolutionary Democratic Front (EPRDF) has been on power since 1991, and 4 general elections have been held in the past 23 years. Yet, all those elections were abused, and failed to meet the international standards.

በኢትዮጵያ መንግስት በጥብቅ የሚፈለጉ 3 አርቲስቶች


ከሮቤል ሔኖክ
እንዳለመታደል ሆኖ ኢትዮጵያ ውስጥ ሃሳብን በነፃነት ያለመግለጽ መብት አለመከበሩ ያጠቃው ጋዜጠኞችን ብቻ አይደለም። አርቲስቶችም ጋዜጠኞች ከሚከፍሉት መስዋእትነት ያልተናነሰ ትግል እያደረጉ ይገኛሉ። ኢትዮጵያ ውስጥ እንዳለመታደል ሆኖ የሃሳብን የመግለጽ ነጻነት በመገደቡ ዛሬ እንደ ታላቁ ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ፣ ርዕዮት ዓለሙና ተመስገን ደሳለን ያሉ ጋዜጠኞች ያልሆነ ክስ ተልጠፎባቸው በእስር ላይ ይገኛሉ። የእነዚ ታላላቅ ጋዜጠኞች ‘ወንጀል’ መንግስት እንደሚለው ሳይሆን የሕዝብን በደልና ብሶት ማሰማታቸው ብቻ ነው።
ዛሬ ዛሬ ደግሞ ላለፉት 23 ዓመታት ሃሳባቸውን በነጻነት ከሚገልጹት ጋዜጠኞች ባልተናነሰ በመንግስት ጥርስ እየተነከሰባቸው የሚገኙት የጥበብ ባለሙያዎች እየሆኑ ነው።
እንደሚታወቀው በስደት ዓለም ከ150 በላይ ጋዜጠኞች እንዳሉ ሁሉ ዛሬ ቁጥራቸው በዛ ያሉ አርቲስቶችም በስደት ይህንን ስርዓት በመሸሽ በስደት ላይ ይገኛሉ። ከነዚህ መካከልም የኢትዮጵያ መንግስት እንደታላቁ እስክንድር ነጋ አስሮ ለማሰቃየት ከሚፈልጋቸው ታላላቅ አርቲስቶች መካከል 3ቱ ዋነኞቹ ሲሆኑ ሌሎቹ ሁለቱ ደግሞ ገና መንግስት እያጎበጎበባቸው በመሆኑ የ3ቱን ገድል አሳይቻችሁ የሁለቱን እንስት አርቲስቶችን ማንነት አስተዋውቃችኋለሁ።
1ኛ. ታማኝ በየነ
ብዙዎች እንደስሙ ነው ይሉታል። አክቲቪስት ሆኗል ከአርቲስትነቱ በተጨማሪ። አላሙዲ ካደረገለት በላይ የኢትዮጵያ ሕዝብ ያደረገልኝ ይበልጣል በሚል ዛሬም ድረስ የያዘውን አቋም ባለማዋዠቅ ይህን ተራ መንግስት ማንነቱን በማጋለጥ ላይ ይገኛል። በብዙ ኢትዮጵያውያን ዘንድ “የሕዝብ ልጅ” የሚል ስያሜ የተሰጠው ታማኝ በየነ አሁን በስልጣን ላይ ያለው አንባገነን ስርዓት ከዚህ አርቲስት ጎን ፎቶ የተነሳ፣ የታየ፣ ሻይ የጠጣ አሸባሪ ነው የሚል ክስ እንደሚመሰርት አስታውቋል። ታማኝ በየነ በኢትዮጵያውያን ዘንድ ክብርን ያገኘ በመሆኑና ክብሩንም ለገንዘብም ይሁን ለታይታ ያልቀየረ በመሆኑ ብዙዎች የሚያከብሩት ሲሆን የሕወሓት መንግስት ይህን ታላቅ አርቲስት በቁጥጥሩ ስር ለማዋል የማፈነቅለው ድንጋይ የለም።
ታማኝ የማንኛውም የፖለቲካ ፓርቲ አባል ሳይሆን በግሉ በሕዝብ ላይ እየተፈጸመ ያለውን ግፍ በነፃነት እያጋለጠ ዘረኛውን ስርዓት እርቃኑን እያስቀረው ሲሆን በተለይም መንግስትን የሚያጋልጠው ራሳቸው የመንግስት ባለስልጣናት በሚሰጡት እርስ በእርሱ በሚጣረስ በቪድዮ የታጀበ ቃለምልል መሆኑ በብዙሃን ዘንድ ተወዳጅነትን በሥርዓቱ ዘንድ ደግሞ ለመታሰር ከሚፈለጉ 3ቱ አርቲስቶች መካከል አንዱ ሆኗል።
2ኛ. ፋሲል ደመወዝ
አርቲስት ፋሲል ደመወዝን የማውቀው አዲስ አበባ ስድስት ኪሎ የሚባል ሰፈር በተለምዶው ሸለቆ የሚባል አካባቢ ነው። በሸለቆ አካባቢ ሲራመዱ ፋሲል ሙዚቃ በመለማመድ ላይ እያለ የሚያሰማውን እንጉርጉሮ ማድመጥ የተለመደ ነው። ይህ ታላቅ ድምፃዊ የጎንደር መሬት ለሱዳን ተላልፎ በሕወሃት/ኢሕአዴግ መንግስት በተሰጠበት ወቅት “አረሱት” የሚል ዘፈን ካወጣ በኋላ በስር ዓቱ ሰዎች ወፌ ላላ ተገርፏል። ፋሲል ታዝሎ እስኪሄድ ድረስ በዚህ ፋሽስት መንግስት የተገረፈ ከመሆኑም በላይ የዳነው በህክምና ብቻ ሳይሆን በጸበልም ጭምር ነው።
ፋሲል ደመወዝ አሁን ሰሜን አሜሪካ ከመጣ በኋላ ‘እንቆልሽ” በሚለው አልበሙ ‘ያውላችሁ’ የሚል ዘፈን ያወጣ ሲሆን በዚህም ዘፈኑ ሃገሪቱን ካለምንም ተቀናቃኝ በአፓርታይድ ስርዓት ለሚመሩት ሰዎች “ሰው አስተዳደራችሁን እና በደላችሁን ጥሎ ጥሏችሁ እየሄደ ነው” ሲል ነግሯቸዋል። ፋሲል ደሞዝ በአሁኑ ሰዓት በሕወሓት አስተዳደር ከሚፈለጉ ዋና አርቲስቶች መካከል አንዱ ነው።
3ኛ. ክበበው ገዳ
ኮሜዲያን ነው። በጣም ይወደዳል። በተለያዩ ጉዳዮች ዙሪያም ይቀልዳል – ክበበው ገዳ። በአሁኑ ወቅት በኢትዮጵያ ውስጥ እሱን የሚያል ኮሜዲያን አለ ብሎ ለመናገርም ይከብዳል ይላሉ በሙያው ውስጥ ያሉ ሰዎች እና ባለሙያዎች። ክበበው ገዳ በማንኛውም ማህበራዊ ሕይወት ዙሪያ በመቀልድ ይታውቃል። ይህ ኮሜዲያን ከኢትዮጵያ ወደ አሜሪካ በመመላለስ የተለያዩ የኮሜዲ ሥራዎችን አቅርቦ ተመልሷል። የዘንድሮው ግን ለጉድ ነው። የሥርዓቱን ሰዎች በእጅጉ እስቆትቷል።
ባለፈው ኦገስት 2014 ላይ ክበበው ገዳ በዳላስ የኢትዮጵያ ኮሚዩኒቲ በዓል አስተናጋጅነት ትልቅ በዓል ላይ ተገኝቶ ነበር። ይህ ኮሜዲያን አሁን ባለው የኢትዮጵያውያን ነባራዊ ሁኔታ ዙሪያ በርካታ ቀልዶችን አቀረበ። በተለይም አሁን ባለው ስርዓት ዙሪያ ልክ እዚህ ሰሜን አሜሪካ ኮሜዲያን በመሪዎቻቸው እንደሚቀልዱት ሁሉ ቀለደ። የሕዝቡን ብሶትም በቀልዱ አሰማ። ስለሟቹ ጠ/ሚ/ር፣ ስለሟቹ ፓትሪያሪክ፣ አሁን ስላለው የመንግስት አካሄድ በቀልድ አዋዝቶ አቀረበ። ለዚህ ኮሜዲያን ከሕዝብ የቀረበለት አድናቆትን ቢሆንም ከ ስርዓቱ ግን የቀረበለት ማስፈራሪያና ዛቻ ነው። እንደውም ‘ሃገርህ ትገባታለህ” የሚሉ ዛቻዎች ከስርዓቱ ደርሶታል። ክበበው ሙያውን ተጠቅሞ ባስተላለፈው መልዕክት ከኢትዮጵያ መንግስት ተላላኪዎች የሚደርስበት ማስፈራሪያ ሃገርህ ብትገባ አለቀልህ የሚል ብቻ ሳይሆን አሁን ባለበት ሃገር ሳይቀር እንደማይለቁት የሚገልጹ ናቸው።
ማነህ ባለሳምንት?
ሜሮን ጌትነትና አስቴር በዳኔ።

ሁለቱም ሴት አርቲስቶች ናቸው። በኢትዮጵያ ውስጥ የሚደርሰውን የሴት ልጅ ተጽ ዕኖ ተቋቁመው አደባባይ የወጡ ሴቶች። ሁለቱም ያመኑመትን ይናገራሉ። ሁለቱም በተለይ ሃገር ቤት ካሉ አርርቲስቶች የሚለዩበት ነገር አላቸው። እነዚህ አርቲስቶች ስለ እውነት እውነትን ስለመሰከሩ ዛሬ በ ሥ ር ዓቱ ሰዎች እየተነከሰባቸው ያለውን ነገር አብረን እያየነው ነው።

Tuesday, January 27, 2015

ታኅሣሥና ሰማዕታቱ ሲዘከሩ !


 ከቅርቡ የሀገራችን ታሪክ ስንነሳ፤ ታኅሣሥና ሰማዕታት የተቆራኙ አንፀባራቂ ከዋክብት እንደሆኑ እንገነዘባለን። ከዋክብት ሰማዕታቱም የጀግንነት አሻራቸውን አሳርፈው ሄደዋል ። ይህም፣ ኢትዮጵያውያን ኩራታችንን የበለጠ ያጎለዋል። ተተኪው ትውልድም፤ አዳዲስ ሰማዕታት ማፍራቱን ይቀጥላል። የታኅሣሥ ጀግና ትውልድ የሚከበረው፤ በአይበገሬነቱና ቆራጥነቱ ብቻ ሳይሆን፤ እንከን በማይገኝለት ሀገር ወዳድነቱና በሕዝብ አፍቃሪነቱም ጭምር ነው። ይህንንም፤ በለገሰው ክቡር ደሙና በከሰከሰው ዕፁብ -ድንቅ አፅሙ አስመስክሮ ያለፈ በመሆኑ ነው። ከመሥዋዕት የተረፈው ኃይልም ፤ ያልደረቀ ደሙን እያከበረ፤ በማይቀረው መሥዋዕትነት ትግሉን ይቀጥላል። በመሆኑም ፤ የታኅሣሱ ዓላማና ራዕይ ግቡን መምታቱ አይቀርም። ከአምሳዎቹ መጀመሪያ አንስቶ እስከ ስድሳ ስድስቱ አብዮታዊ ማዕበልና እስከ አሁንም ድረስ፤ በተካሄደው የለውጥ ፈላጊዎች ትግል፤ አያሌ ኢትዮጵያውያን በግንባር ቀደም መሥዋዕት ከፍለዋል። የ1953ቱ የመኮንንኖች የለውጥ እንቅስቃሴ፤ በወርሃ ታኅሣሥ እንደነበረ መጥቀሱም አግባብነት አለው። ከዚያ ታኅሣሥ ጀምሮ በተከታታይ፤ ለዴሞክራሲ ለውጥ ሲባል፤ ተማሪዎች፤ ወጣት ምሁራንና ሀገር-ወዳድ ዜጎች የህይወት ዋጋ ከፍለዋል። ሁሉም የታኅሣሥ ጀግና ሰማዕታት ናቸው። በዚህ ያላሰለሰ ትግል፤ ሕዝቡን በማንቃትና የዘውድ ሥርዓቱን ምንነት በማጋለጥ፤ ከፍተኛ ዋጋ የተከፈለበት ትግል ተካሂዷል። ያ ትውልድ፤ በለውጥ ፋና-ዊጊነት፤ ጉልኅ ሚና ተጫውቷል። 
https://articles2u.files.wordpress.com/2015/01/democracia_tahsas_2007-1.pdf

Sunday, January 25, 2015

የህወሓት/ኢህአዴግ ፖሊሶች ቆርጠው በመግባት ከባድ ድብደባ አድርሰዋል፡፡

የወያኔ ቅልብ ወታደሮች ዳግም የሰላማዊ ሰልፈኞችን ደም አፈሰሱ * ነብሰ ጡር ሳይቀር በቆመጥ ቀጠቀጡ (ፎቶዎች ይዘናል)ቀበና ከሚገኘው የአንድነት ፓርቲ ጽ/ቤት የተነሳው ከ 150 በላይ የሚሆን ሰልፈኛ ከጽ/ቤቱ 100 ሜ/ር ርቀት ላይ ከሚጠብቁ ከ500 በላይ ሰልፈኞች ጋር ከመቀላቀላቀላቸው አስቀድሞ የህወሓት/ኢህአዴግ ፖሊሶች ቆርጠው በመግባት ከባድ ድብደባ አድርሰዋል፡፡ አራት ኪሎ፣ በፒያሳና የሰልፉ ማጠናቀቂያ በሆነው ኢቲዮ ኩባ አደባባይ ይጠባበቅ የነረው ሰልፈኛ ሊበተን ችሏል፡፡ ጉዳት የደረሰባችው 24 ሰልፈኞች ህክምና በመከታተል ላይ ይገኛሉ፡፡ ፖሊሶች ያደረሱትን ጉዳት በቅርብ ሲከታተሉ የነበሩት የተለያዩ ሀገራት ዲፕሎማቶች የአንድነት አመራሮችን እና ጉዳት ደርሶባቸው በየሆስፒታሉ የሚገኙ የአንድነት አባላትና ደጋፊዎችን አነጋግረዋል፡፡ የፓርቲው አመራሮች ከአባላትና ከደጋፊዎች ጋር ውይይት ያደረጉ ሲሆን አንድነት በአዲስ አበባ ተከታታይ የተቃውሞ ሰልፎችን እንደሚያደርግ ይፋ ተደርጓል፡፡ አንድነት ፓርቲ ያወጣውን መግለጫ ከዚህ በታች ይመልከቱ፡፡ 
የፍትህና የነፃነት ጥያቄያችን ደም በማፍሰስ አይቀለበስም!!!
ከአንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ የተሰጠ መግለጫ
ፓርቲያችን አንድነት ገዥው ፓርቲ፣ ምርጫ ቦርድና የገዥው ፓርቲ ልሳን በመሆን እያገለገሉ ያሉ ሚዲያዎች በመተባበር ከምርጫ ለማስወጣትና ተለጣፊ አንድነት ለመፍጠር የሚደረገውን ጥረት በመቃወም የተቃውሞ ሰልፍ መጥራቱ የሚታወቅ ነው፡፡
የተቃውሞ ሰልፉን ጥር 17 ቀን 2007 ዓ.ም እንደምናከናውን ለአዲስ አበባ መስተዳድር ብናሳውቅም መስተዳድሩ በ12 ሰዓት ውስጥ በፅሁፍ ምላሽ መስጠት ባለመቻሉ ሰልፉ እውቅና አለው፡፡ መስተዳድሩ ግን የተጣለበትን ሃላፊነት ከመወጣት ይልቅ ወደ ጎን በመግፋት የተወሰኑና የማይታወቁ ግለሰቦች ፔቲሽን ተፈራርመው አምጥተዋል በማለት ብዥታ ለመፍጠር ሞክሯል፡፡ ፓርቲያችን ህጉን ጠብቆ ህጋዊ የሆነ ሰልፍ ለማካሄድ ቢሞክርም አሁንም ሃላፊነት በጎደለው ሁኔታ የፓርቲያችን ከፍተኛ አመራሮች፣ አባላትና ደጋፊዎች ጭካኔ በተመላበት ሁኔታ ከፍተኛ ድብደባ ተፈፅሞባቸዋል፡፡ በተደጋጋሚ እንዳየነው ፖሊስ ደንብ ማስከበር ሲገባው አድሎ ለፈፀመው አካል በመወገን ድብደባ መፈፀሙ ከወገንተኝነት ያልፀዳ መሆኑን እንድናረጋግጥ አድርጎናል፡፡
ጥያቄያችን አሁንም የፍትህ፣ የእኩልነትና ህግ እንዲጠበቅ የማድረግ ነው፡፡ ገዥው ፓርቲ የመንግስትነት ስልጣኑን በመጠቀም የስልጣን ዘመኑን ለማስረዘም እየከወነ ያለውን ሴራ ማስቆም ነው፡፡ ጥያቄያችን የነፃነትና ያልተሸራረፈ ዴሞክራሲ ይረጋገጥ የሚል ነው፡፡
ጥቄያችን ምርጫ ቦርድ የገዥው ፓርቲ አጋር መሆኑ ቀርቶ ገለልተኛ ሚናውን ይወጣ የሚል ነው፡፡ እነዚህ ጥያቄዎቻችን ደግሞ ደም በማሰስ፤ በድብደባም ሆነ በእስር ፈፅሞ አይቆሙም፡፡ ትግላችን የአንድ ፓርቲ የበላይነት አገዛዝ እስከሚያበቃ ድረስ የሚቀጥል ይሆናል፡፡
በሚቀጥለው ሳምንትም በተለያዩ ከተሞችና በአዲስ አበባ የሰላማዊ ተቃውሞ ድምፃችንን ከፍ አድርገን እናሰማለን፡፡ ትግሉ ይቀጥላል፡፡
ድል የህዝብ ነው!!


“እኛ አገር ደግሞ ሰውን በቁሙ ነው እንጂ ሲሞት አናቃጥልም!“

የደደቢት ጉዞ መዘዝ፤ ከሰራዊት ፍቅሬ እስከ ታገል ሰይፉ

ክንፉ አሰፋ (ጋዜጠኛ)
በመጀመርያ ዶክተር ደብረ ጽዮን ገብረ ሚካኤል የህዝባዊ ወያኔ ሃርነት ትግራይ (ህወሃት) ደጋፊና ተደጋፊ የኪነጥበብ ባለሙያዎችን በሙሉ ጠሯቸው። ሰበሰቧቸው። እንዲህም አሏቸው። “ወደ ደደቢት አብራችሁን ትሄዳላችሁ፤ እዛ እንደደረሳችሁም አመጣጣችንንና አካሄዳችንን በደንብ አድርጋችሁ ታጤናላችሁ። ከዚያ ስትመለሱ ሁሉንም ነገር ለህዝቡ ትናገራላችሁ።…”       
በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ማዕረግ የሃገር መሪ ሆነው የሚሰሩት እኝህ ሰው መልዕክታቸውን በዚህ አላበቁም። አይናቸውን ፈጠጥ፤ ጉሮሯቸውንም ጠረግ-ጠረግ አደረጉና ንግግራቸውን ቀጠሉ “ስለረጅሙና መራራው ትግላችን፤ ከጅምራችን እስከ አያያዛችን የታዘባችሁትን ሁሉ ንገሩን። ጥሩውንም ይሁን መጥፎውን ነገር ሳትደብቁ ተናገሩ።…”
serawit fikre
ድምጻዊው በዝማሬ፣ ጸሃፊው በድርሰት፣ ተዋንያኑ በተውኔት ስለ ህወሃት የአርባ አመት ጉዞ እንዲመሰክሩ የተሰጠች ትእዛዝ መሆንዋ ነው። አጭር፣ ግልጽ እና ቀጭን መልዕክት ነበረች።
       የስርዓቱ ደጋፊ ሳይሆን ይልቁንም ተደጋፊ የሆኑት ሁሉ የዘመቻውን ጥሪ በደስታ ተቀበሉ። ወደ ደደቢትም አመሩ። የታዘቡትንም ነገር ሲናገሩ ሰማን።
ልብ እንበል! እነዚህ የጥበብ ሰዎች ናቸው። ጥበብ ደግሞ የሕዝብ አገልጋይ ናት። ጥበብ ለእውነት የምትቆም ዘብ ናት። ጥበብ አንድን ህብረተሰብ የመቅረጽ እና የመለወጥ ሃይል አላት።
በአለማችን የጥበብ ሰዎች ሚና ጎልቶ የሚታየው ተፈጥሮ ባደላቸው የጥበብ ስራ ብቻ ሳይሆን፤ እነዚህ ሰዎች በጥበብ ስራቸው ውስጥ ለህዝብ በሚያስተላልፉት እውነተኛ መልእክትም ጭምር ነው። 
አርቲስቶች አክቲቪስቶች መሆን አለባቸው ብሎ መከራከር አይቻልም። ይህ የራሳቸው ምርጫ ነው። መሆን ካለባቸው ግን የህዝብን እንባ ማበስ ነው የሚገባቸው። ወቅቱን ጠብቆ እንደሚቀየር ድሪቶ መንግስት ሳይሆን ከህዝብ ጎን መቆም ያስከብራቸዋል።
ጥበብ ቆራጥነትን ትጠይቃለች። መስዋዕትነትን ልታስከፍልም ትችላለች። ፍሬዋ ግን ሁል ጊዜ ጣፋጭ ነው። እውቁ ቻይናዊ አርቲስት አይ ዌዊ እዚህ ላይ ይጠቀሳል። አሜሪካዊቷ ጁዲ ችካጎም እንዲሁ። ጃማይካዊው ቦብ ማርሌይ እና የናይጄርው ፌላ ኩቲ በአለማችን ላይ ለውጥ ያመጡ የጥበብ ጀግኖች ናቸው። የኛዋ አርቲስት አስቴር በዳኔም ለዚህ ዋቢ ነች። ማህበራዊ ድረ-ገጾች ይህንን አስረግጠውልናል።
  “ህዝቡ አጎብዳጆች ይለናል።” አለች አርቲስት አስቴር በዳኔ ከዚያ ሁሉ መንጋ ተነጥላ። ‘እውነት ነጻ ያወጣችኋል!’  የሚለው ክርስቶሳዊ አባባል የተዋሃዳት ወጣት። እውነትን ተናግራ ራስዋን ነጻ አወጣች። እርግጥም የህሊና ነጻነትዋን ለማወጅ መድፈር ነበረባት። ማማጥም ነበረባት። አርቲስትዋ እንደጦር የፈራችው ከፊትዋ ተደርድረው የነበሩ ጉምቱ ባለግዜዎች አልነበሩም። ምክንያቱም ጉዳዩን ለነሱ አስቀድማ ተናግራ ነበርና። ይልቁንም ከአጠገብዋ የነበሩ የስራ ባልደረቦችዋ እና የሙያ አጋሮችዋ እንደጦር ያስፈራሉ። እንደ ይሁዳ አሳልፈው ሊሰጧትም ይችላሉ። ደደቢት ላይ ሲደርሱ ሁሉም በአንድ ማሰብ ጀመሩ። ደደቡ… አንድ ግዜ ተኑሮ ለሚሞትበት አለም ሁሉም ከራሱ ተጣላ። ሁሉም ከህሊናው ሸሸ። ሁሉም ለማደር አጎብዳጅ ሆነ። በመጨረሻም ሁሉም አስቴርን በአርባ ክንድ ራቁዋት። ግና እስዋ ጣርያ ስትነካ እነሱ ደግሞ ሲዘቅጡ አየን።
የኪነ-ትበብ ሰዎቻችንን መፈተኛ ግዜ ብቅ አለ። ግን ይህ ሁሉ ወጪ እና ሽርጉድ ለምን አስፈለገ?
ጉዞውን ከመጪው ምርጫ ጋር የሚያያይዙ ወገኖች አሉ። ጉዞውን እንደምርጫ ዘመቻነት ለመጠቀም…። ይህ የዋህነት ይመስላል። ምክንያቱም ህወሃት አንድም ግዜ በምርጫ ዘመቻና ግልጽ በሆነ ውድድር ምርጫ አሸንፎ አያውቅም። ነብሳቸውን ይማርና አቶ መለስ ከነ ስዬ ቡድን ጋር በተለያዩ ግዜ ተናግረውታል። “ህወሃት በስብሷል!” ነበር ያሉት። ላለፉት ፪፫ አመታት ይህ የበሰበሰ ስርዓት ነው ሃገሪቱን እየገዛ ያለው። ይህ የበሰበሰ ስርዓት በምርጫ ሳይሆን የህዝብን ድምጽ በመስረቅ ነው እስካሁን ያለው።
ከምናከብራቸውና ከየምናደንቃቸው የኪነጥበብ ስዎች ውዳሴዎች ሰማን። ነዋይ ደበበም እጅግ አድርጎ ሲረግመው በነበረው ደደቢት ላይ ዘፈነ። እንዲያውም በስሜት ዘፈነ። “የሃገር ነቀርሳዎች” ሲላቸው የነበሩትን እነ ሳሞራን፣ እነ አባዱላን፣ … እያቀፈ … አልረሳም እያለ አቀነቀነ።
tagel
በዚያ የቀውጢ ወቅት ከሰለሞን ተካልኝ ከተቃዋሚ ወገን ወጥቶ ህወሃትን ሲቀላቀል ድምጻዊው ነዋይ ደበበ እንደ እብድ ነበር ያደረገው። ያዙኝ፤ ልቀቁኝ አለ። የንዴት ቃላትን ሁሉ በዘፋኙ ላይ አዥጎደጎደው። “ማሰብ የማይችል ደደብ ሰው!” አለ ነዋይ። ቀጠለናም “ሰለሞን ተካልኝ ስጋ የሚበላ በሬ ነው።” ሲል ድምጻዊውን ከሰብአዊ ፍጡርነት ወደ እንስሣነት ጎራ መድቦት ነበር።
ዛሬ በዚያው መድረክ ላይ አዲስ ትእይንት እያየን ነው። የግዜ ሃዲድ ላይ ሆኖ የሚመለከተው ሁሉ በትዝብት የሚያስቆዝም አሳዛኝ ድራማ፤ አርቲስት ብለን የምንጠራቸው ወገኖቻችን የሚፈጽሙት የፖለቲካ ዝሙት። ነዋይ ደበበ በግዙፉ የሰለሞን ተካልኝን ትከሻው ላይ ለመጠምጠም እጆቹ በጣም ሲረዝሙ በመገናኛ ብዙሃን ተመለከትን። … አጃኢብ አለ ያገሬ ሰው!
አዕምሮ ማሰብ ሲያቆም፣ አንገታቸው አዙሮ ማየት ሲሳነው፣ ልቦናችን የቅርቡን ክስተት ሲዘነጋ፣ የስነ-ልቦና ችግር ነው ከማለት ውጭ ምን ይባላል? 
የሰራዊት ፍቅሬ ማጎብደድ ደግሞ ተወዳዳሪ አልተገኘለትም። ይህ ሰው በ ፩፱፹ዎቹ በነበረው የርስ በርስ ውግያ ወታደር ሆኖ ከደርግ ወገን ነበር የተሰለፈው። ዛሬ በሽሬ ሽንፈቱ ላይ ጥሎት የሸሸው የጦር ታንክ ላይ ቆሞ በኢትዮጵያ ህዝብ ላይ እጆቹን እያወጣ ደግም ቀለደ። ለካስ ደርግ እንደዚህም አይነት ወታደር ይዞ ነበር ህወሃትን ይፋለም የነበረ? ሰራዊት ፍቅሬ ዛሬ ዝናው ሳይሆን ሃብቱ ጣርያ ነክቷል። አሰልቺ ድምጹና ምስሉ እጅ-እጅ እስኪል በቴለቭዥን እንዲቀርብ በገዢው ፓርቲ ተፈቅዶለታል። ለፕሮፓጋንዳ ፍጆታ የሚውሉ የስርዓቱ በዓላት ቁጥር እጅግ በዝተዋል። የብሄር ብሄረሰቦች ቀን፣ የከተሞች ቀን፣ የአርሶ አደሮች ቀን፣ የአርብቶ አደሮች ቀን፣… ባዛር ለልማት ወዘተ። የማስታወቂያ ወጪው ከዝግጅቱ ወጪ አይተናነስም። ሁሉንም የማስታወቂያ ስራ ለሰራዊት ፍቅሬ ሰጥተውታል። ታዲያ እሱም ገሚሱን ለባለስልጣናቱ ማካፈሉ የግድ ነው። የዚህ ሰው መንቀልቀል ምስጢር ይህ ብቻ ነው። ሰራዊት ፍቅሬ በዚህ ሁኔታ የማስታወቂያ ስራውን በሙስና መስመር ውስጥ አዝልቆታል።
  አንደኛው ተደጋፊም ተነስቶ  “ይህ ነገር በአፍሪካ አንድነት ድርጅት ፊት ለፊት ሃውልት ሊሰራለት ይገባል።” ሲል ተደመጠ። ሰውዬው ይህንን አምኖበት እንዳልተናገረ ሰዎቹም ይገምታሉ። መቼም ለእለት ጉርስ ሲባል እንደዚህ አይነት ለህሊና የሚጎረብጥ ነገር እያደረጉ ከመኖር፤ በልመና መተዳደር ክብር ነው።  
        ከጅምሩ የስርዓቱን አዎንታዊም ሆነ አሉታዊ ሂደት ለመገምገም ወደ ደደቢት በረሃ መሄድም አያስፈልግም። ኢትዮጵያ ዛሬ ከገባችበት መከራ ለማውጣት የህወሃት አነሳስን ማጥናት ምንም ፋይዳ የለውም። መነሻው ጥሩም ይሁን መጥፎ፣ መድረሻው ግን አላማረም። ይህ ስርዓት ሃገሪቱን ባህር አልባ አገር አድርጓታል። የባህር በር የአንድ ሃገር ምስጢርም ነው። ኢትዮጵያ እንደ ማንኛውም ሉአላዊ ሃገር ምስጢር እንኳን የላትም። 
ህዝቧም ከአፈናው ሰንሰለት ገና አልወጣም።
       በአመለካከት ልዩነታቸው ብቻ ወገኖቻችን እንደ ጥጃ ሲታሰሩ የደደቢት ተጓዦቹ ይመለከታሉ። ሃሳባቸውን በነጻ የገለጹ ዜጎች የሽብርተኛነት ታርጋ ተለጥፎላቸው በግፍ ሲፈረድባቸው ይሰማሉ።  ኢትዮጵያውያን እንደ ምጽዓት ሲሰደዱ በአይናቸው ይመለከታሉ።  ለነጻነትና ለእኩልነት ታግለን መጣን የሚሉን ደግሞ በአንዲት ጀንበር ሚሊየነር ሲሆኑ ይታዘባሉ። ይህ ሁሉ ሲሆን ታዲያ እንደሙያቸው አንዲት ቃል እንኳን ተንፍሰው አያውቁም። ወደ በረሃው መጓዙ እንደ ሲሲሊው የማፍያ ቡድን ከደደቢት ምሽግ ውስጥ ቃል-ኪዳን ለመግባባት ካልሆነ በቀር ፋይዳው አይታይም።
        “ህዝቧ አጎብዳጆች ይለናል።” አለች አስቴር በዳኔ። ህዝብ ምን እንደሚላቸው የምትሰማው እስዋ ብቻ አይደለችም። ጆሮ ያለው ሁሉ ይሰማዋል።  ይህን እያወቁ ግን አጎብዳጅ ምሆናቸውን ጭራሽ በብሄራዊ ቴሌቭዥን ወጥተው አሳዩን።  
ህዝቡ ብቻ አይደለም። በእርግጠኝነት ለመናገር እነዚያ ባለ-ስልጣናትም አድርባዮቹን ይንቋቸዋል። በባህር ዳሩ የኢህአዴግ ጉባኤ “የኢህአዴግ አባል ለመሆን አንዱና ዋናው መስፈርት አድርባይነት ነው” በማለት አድርባይነትን የፈጠረውና ያስፋፋው ራሱ ህወሃት እንደሆነ ተናግረው ነበር። “አድርባይነት” ስርዓቱን በሚፈታተን ደረጃ መስፋፋቱን ከመግለጻቸውም በላይ አድርባዮቹን እንዴት እንደሚበቀሏቸውም ባህርዳር ላይ መክረዋል።
        ደብረጽዮን ትእዛዙን ሲሰጡ ትንሽም ቢሆን ዲፕሎማት ነበሩ። ከትእዛዞቻቸው መሃል እንዲት እንዲህ የምትል መልእክት ነበረች። “…ችግሮቻችንንም ንገሩን።”
ይህች ሃረግ የኪነ-ጥበብ ሰዎቹ የህዝብን ብሶት በአደባባይ እንዲናገሩ በር ከፋች ነበረች። እነ አበበ ባልቻ ይህችን እድል ተጠቅመው ስለ-ኪነጥበብ መውደቅ እንኳን ትንሽ መልእክት ከማስተላለፍ ይልቅ ልወደድ ባይነትን መረጡ።   ይህን ጥሬ ሃቅ የመናገር ድፍረት ያለው አንድ ሰው ጠፋ። ሁሉም ምስጋናና ውዳሴውን አበዛ። ለማደር የሚደረግ ካንገት በላይ ውዳሴ… መቼም ያሳዝናል።
  በጭምጭምታም እንደሰማነው፤ በደደቢት አንዳች የተለወጠ ነገር የለም። ደደቢት ድሮም በረሃ – አሁንም በረሃ ነው። የአካባቢው ህዝብ ላይም ምንም የሚታይ ለውጥ የለም። ይህ ህዝብ ከሃያ አመታት በፊት የመናገር በብት አልነበረውም።  ይህ መብት አሁን ብሶበት ሕዝቡ የመናገር ብቻ ሳይሆን የውጭ ራዲዮ እንኳን የመስማት መብቱን ተነፍጓል።  
ይህችን ሃቅ የጎበኘ አንድ የኪነ-ጥበብ ባለሞያ እንዴት አስችሎት ዝም ይላል? ይህ የብዙዎች ጥያቄ ነበር። “ስለ እውነት የቆመ አንድ ሰው ይጥፋ?” የሚለው ጥያቄ በህዝብ ዘንድ እየተብላላ እያለ ነበር አስቴር በዳኔ ብቅ ያለችው። ይህች አርቲስት የህዝቡን ጥያቄ ይዛ በድፍረት ወረወረችው። መገናኛ ብዙሃንና ማህበራዊ ገጾችም በዚሁ ጉዳይ ተጨናንቀው ከረሙ። 
ለድቅድቅ ጨለማ ትንሽ የብርሃን ፍንጣቂ ትበቃለች እንዲሉ የዚያን ሁሉ የውሸት ክምር አንድ እውነት አፈራረሰው። ህዝብ ያከብራቸው የነበሩ የኪነጥበብ ባለሞያዎች ሁሉ ወረዱ። የማያልፈውን የህዝብ ፍቅር በሚያልፍ ነገር ቀየሩት።
ጥሪ የተደረገላቸው አርቲስቶች ሁለት አማረጮች ነበራቸው። ጥሪውን ተቀብሎ ሄዶ እውነትን መመስከር አሊያም እንደ ገጠሚ ታገል ሰይፉ ጥሪውን አለመቀበል። ገጣሚ ታገል ሰይፉ በኤፍ ኤም ፱፯ ራዲዮ ሲናገር እንዲህ ነበር ያለው።
“ባለፈው የመቀሌ ጉዞ ላይ እኔ አልሄድኩም። አርቲስቶች ሲሄዱ ጥሪ ተደርጎልኛል። ነገር ግን የደደቢቱን ጉዞ ስላላመንኩበት ቀርቻለሁ። ስለማልፈልገው ማለት ነው። …ለነሱም የምለው ነው። በተለይ ባለፉት 15 አመታት ብዙ ነገር አልተሰራም። ለስነ ጽሁፍ የሚመች ግዜ አይደለም። ስነጽሁፍን ትኩረት አልሰጡትም። እያየን ነው።”
ታገል ሰይፉ ቀደም ሲልም በመንግስት መገናኛ ብዙሃን ሃሳቡን ተቆርጦ እንዳስቀረበት ተናግሯል። ደደቢት ድረስ ሄዶ ሃሳቡን የማያስተላልፉለት ከሆነ መቅረቱ አይነተኛ አማራጭ ነው። አበበ ባልቻን፤ ሙሉ አለምን፣ ነዋይ ደበበን፣ … አርቲስቶች እና የኪነጥበብ ሰዎች ብለን ጠርተን፤ አስቴርንና ታገል ሰይፉን ምን ልንላቸው ይሆን?… ማህበራዊ ፍርዱን ከህዝቡ ያገኙታል።
ህወሃት ግን አንድ መልዕክት ለማስተላለፍ ነበር አርቲስቶቹን ወደ ደደቢት የወሰዳቸው። አዚህ ተነስተን፣ አፈር ለብሰን፣ አፈር በልተን፣ የፈረስ ሽንት ጠጥተን የያዝናት ስልጣን ናት። ይህችን ስልጣን በምርጫ እንደማናስረክብ እናንተም አረጋግጡልን… እንዲሁ ተቃጥላችሁ ታልቃላችሁ እንጂ በሰላማዊ መንገድ ለውጥ አታስቡ… የሚል መልዕክት። 
እኔም በዚህች ቀልድ ጽሁፌን ልቋጭ። አንድ የህንድ ኢንቨስተር አዲስ አበባ ዬሴፍ ቤተ ክርስቲያንን የቀብር ስፍራ አይቶ በሊዝ ሊገዛ ፈለገ። የአዲስ አበባ ባለስልጣናትን ጠርቶ እንዲሸጡለት ጠየቀ። ባለስልጣናቱም መልሰው ሌሎች ቦታዎች ሳያልቁ የቀብር ስፍራ ለግዜው እንደማይሸጡለት ነገሩት። ህንዱ መለሰና መከራቸው። “እኛ አገር ሰው ሲሞት እናቃጥላለን እንጂ አንቀብርም። ለምን ይህን ለም ቦታ ታባክናላችሁ?”
ባለስልጣናቱ መለሱ፣ “እኛ አገር ደግሞ ሰውን በቁሙ ነው እንጂ ሲሞት አናቃጥልም!“

በዛሬው ዕለት በሕወሓት ወታደሮች ጉዳት የደረሰባቸው 26 የአንድነት አመራሮች ስም ዝርዝር

(የሚሊዮኖች ድምጽ) በዛሬው ዕለት በህወሃት/ኢህአዴግ ፖሊሶች አንድነት ፓርቲ የጠራውን ሰልፍ ለመበተን ከፍተኛ ድብደባ ተፈፀመ፡፡ ድብደባው የአካል ማጉደልንም ያካተተ ነው፡፡ ጋዜጠኛ ስለሺ ሐጎስና አቶ ዳግማዊ ተሰማ ራሳቸውን ስተዋል፡፡ ዳግማዊ አይኑ ማየት አልቻለም፡፡ በአንባገነኑ ስርዓት ከፍተኛ ድብደባ ከተፈፀመባቸው አመራር አባላትና አባላት መካከል፡-


1. አቶ አስራት አብርሃም (የህዝብ ግንኙነት ተጠባባቂ ሃላፊ)
2. አቶ ዳንኤል ተፈራ (የውጭ ጉዳይ ሃላፊ)
3. አቶ ብሩ ብርመጅ (የፖለቲካ ጉዳይ ሃላፊ)
4. አቶ ፀጋየ አላምረው (ምክትል አፈ-ጉባኤ)
5. አቶ አሻግሬ መሸሻ (የሰሜን ቀጠና ሃላፊ)
6. አቶ ሰለሞን ስዩም (የኤዲቶሪያል ቦርድ ሰብሳቢ)
7. ወ/ት ልዕልና ጉግሳ (የም/ቤት አባል)
8. አቶ ዳግማዊ ተሰማ (የም/ቤት አባል)
9. ጋዜጠኛ ስለሺ ሀጎስ (የም/ቤት አባል)
10. አቶ ስንታየሁ ቸኮል (የአዲስ አበባ የወጣቶች ጉዳይ ሃላፊ)
11. አቶ አሸናፊ አሳምረው (የወረዳ አመራር)
12. አቶ ኢሳያስ ቱሉ (አባል)
13. ወ/ት መስከረም ያረጋል (አባል)
14. አቶ ሃይሉ ግዛው (የወረዳ ሰብሳቢ)
15. አቶ አዲሱ መኮንን (የወረዳ ሰብሳቢ)
16. አቶ ሲሳይ ካሴ (አባል)
17. አቶ ወጋየሁ አድማሴ (አባል)
18. አቶ ክብረት ሃይሉ (የም/ቤት አባል)
19. አቶ ስለሺ ደቻሳ (አባል)
20. አቶ ማሩ አካሉ (አባል)
21. አቶ ክፍሉ በዳኔ (አባል)
22. አቶ ፋሲካ አዱኛ (የወረዳ አመራር)
23. ወ/ሮ ገነት ሞገስ (የወረዳ አመራር)
24. ተስፋየ ብዙነህ (አባል)
25. ሙሉጌታ ተፈራ
26.ኤፍሬም ሰለሞን(የአዲስ አበባ ስራ አስፈፃሚ)
ሲሆኑ በርካቶች የደረሱበት አልታወቀም፡፡

Saturday, January 24, 2015

እንኳን ደህና መጡ ወደ ወያኔ 2007 የምርጫ ጨዋታ!

የኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ እኔ ዳኛ ነኝ እያለ ቢለፍፍም አብዛኛው ኢትዮጵያዊ የምርጫ ቦርድ የወያኔ/ኢህአዴግ የመሃል ተጫዋች እንደሆነ ይገነዘባል። ይህ የዳኝነት ካባ ለብሶ የወያኔን የአጥቂ መስመር የሚመራ አካል በአሁኑ ሰዓት ዋነኛው ስራው የዳኝነት ካባውን ተጠቅሞ ጨዋታው ሲጀመር ለቡድኑ ወያኔ የሚያሰጉትን ጠንካራ ተቃዋሚዎች እና ፖለቲከኞች ሰበብ አስባብ እየፈለገ (Disqualify) እያለ ምርጫው ውስጥ እንዳይገቡ መከላከል ነው። በመኢሕአድ እና አንድነት ፓርቲ ላይ እያደረገ ያለውን ልብ ይበሉ።Ethiopian election 2015
የወያኔው ቋሚ ተሰላፊ ምርጫ ቦርድ ተቃዋሚዎቹን ሁሉ ምርጫ ውስጥ እንዳይገቡ ቢከለክል ምርጫ ተብዬው ጨዋታ ሊኖር አይችልም፣ ስለዚህ ወያኔን በምርጫው ወቅት የሚያጫውቱት ቡድኖች ስለሚያስፈልጉ አንዳንዶችን ያሳትፋል።
የምርጫው ቦርድ ጨዋታው በሚካሄድበት ወቅት ቡድኑ ወያኔ ሲጠቃ የዳኝነት ካባውን ደርቦ ከች ይልና ባሰማራቸው የምርጫ ድምጽ ቆጣሪዎች እና ታዛቢዎች (ሁሉም የወያኔ ካድሬዎች ናቸው) አማካኝነት ኮሮጆ ዘቅዝቆና ቀመሩን አስተካክሎ ቡድኑ ወያኔ 99.6% ድምጽ በማግኘት እንዳሸነፈ ያውጃል።
እንኳን ደህና መጡ ወደ ወያኔ 2007 የምርጫ ጨዋታ!
አንድነት ፓርቲ የምርጫ ቦርድ የሸረበበትን ሴራ ለመቃወም እሁድ ጥር 17 – 2007 ዓ.ም አዲስ አበባን ጨምሮ በተለያዩ ከተሞች ህዝባዊ ሰልፎችን ጠርቷል። ለዚህም አባላቱ የሰልፉን ጥሪ ለህዝብ ለማድረስ ከወያኔ ደህንነቶች ጋር እየተናነቁ ቅስቀሳውን ተያይዘውታል። መንግስት ተብዬው የወሮ በላ ቡድን አንድነት ፓርቲ በድንገት የጠራውን ሰልፍ እንዲተው ወይንም ቀኑን እንዲቀይረው ማስፈራራትንና መለማመጥን እያቀያየረ ለማግባባት ጥረት በማድረግ ላይ ይገኛል።
እስርና ወከባም ተጧጡፏል!
ነብዩ ሃይሉ እስርን በተመለከተ እንዲህ ብሏል
“ቀደም ሲል በደህንነት ሃይሎች በቅስቀሳ ላይ ሳሉ በቁጥጥር ስር የዋሉትን የአንድነት ፓርቲ የብሄራዊ ምክር ቤት አባላት አቶ ያሬድ አለማሁ እና አቶ ሲሳይ ጌትነት ለመጠየቅ ባልደራስ አካባቢ ወደሚገኘው ፖሊስ ጣቢያ ያመሩት የአዲስ አበባ ምክር ቤት ሰብሳቢ አቶ ለገሰ ተፋረደኝ ለእስረኞቹ እራት ለመግዛት በእቅራቢያው ወደሚገኝ ምግብ ቤት በማምራት ላይ ሳሉ ሲቢል በለበሱ ደህንነቶች አማካይነት ከዛንቺስ አካባቢ ወደሚገኘው ፖሊስ ጣቢያ መወሰዳቸው ታውቋል፡፡”
እሁድ ጥር 17 – 2007 ዓ.ም የተጠራው ህዝባዊ ተቃውሞ አይታጠፍም! (አንድነት ፓርቲ)
ይህ በዚህ እንዳለ አንድነት ፓርቲ እሁድ ጥር 17 – 2007 ዓ.ም የተጠራው ህዝባዊ ተቃውሞ እንደማይታጠፍ አሁን ባወጣው መግለጫው አሳውቋል።
“የአንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ አንድነት በምርጫው ለመወዳደር መወሰኑን ተከትሎ የኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ እና ኢህአዴግ እያደረጉት ያለውን ስውር ደባ እንዲያቆሙ በተደጋጋሚ ሲጠይቅ ቢቆይም መፍትሄ የሚሰጥ አካል ባለመገኘቱ ምክንያት ‹‹መብታችንን ለማስከበር አንለምንም›› በማለት በነገው እለት ማለትም ጥር 17/2007 ዓ.ም በ5 ከተሞች የጠራውን ህዝባዊ ሰላማዊ ሰልፍ ተከትሎ በመንግስትና በተለያዩ የዲፕሎማሲ ማህበረሰብ አካላት ፓርቲው የጠራውን ሰላማዊ ሰልፍ ቀን እንዲቀይርና ከመንግስት አካላት ጋር ድርድር እንዳያደርግ ጥረት ቢደረግም የፓርቲው ብሔራዊ ምክር ቤት በዛሬው እለት ባደረገው ልዩ አስቸኳይ የምክር ቤት ስብሰባ ሰልፉ በአዲስ አበባም ሆነ በሌሎች ከተሞች እንደሚደረግና ለዚህም የሚያስፈልገውን ክፍያ ለመክፈል መዘጋጀታቸውን በማረጋገጥ ስብሰባውን አጠናቀዋል።
ጥሪ ለተቃዋሚ ፓርቲዎችና አባላት ከአንድነት ፓርቲ
“የሰልፍ ትብብር ጥሪ ለእውነተኛ ተቃዋሚዎች በሙሉ!
አንድነት እሁድ ጥር 17 በአዲስ አበባ እና በሌሎች ከተሞች የሚያካሄደው ሰላማዊ ስልፍ ላይ እውነተኛ ተቀዋሚዎች ሁሉ በፈለጉት መልኩ በሰልፉ ላይ ትሳተፉ ዘንድ ጥሪያችንን በአክብሮት እናስተላልፋለን። በተለይ ደግሞ በአዲስ አበባ በሚካሄደው ታላቅ ሰላማዊ ስልፍ ላይ የሰማያዊ፣ የመኢአድ፣ የመድረክ እና የዘጠኙ ፓርቲዎች አመራሮች እንድትሳተፉ በዚህ አስቸጋሪና ታሪካዊ ወቅት ከጎናችን እንደምትሆኑ እምነታቸን ነው።”

Friday, January 23, 2015

ካልደፈረሰ አይጠራም!!

የደቡብ ምስራቅ እዝ የመከላከያ ሰራዊት ካልደፈረሰ አይጠራም እያለ ነው

ምኒልክ ሳልሳዊ እንደዘገበው:-
ጨፍጫፊው ሌ/ጄነራል አብረሃ ወልደ ማርያም (ኩዋተር) የሚመራው ለሶማሌ ክልል ሰላም በሚል በአከባቢው የሰፈረው የደቡብ ምስራቅ እዝ የሕወሃት የጦር አዛዦች በራሳቸው የሚወሥዱት ውሳኔ የመከላከያ ሰራዊት ላይ የሚያደርሱት ጫና እና እንዲሁም ሰራዊቱ ያቀረበውን ሕገ መንግስታዊ ጥያቄ ወደ አመጽ ማምራቱ ተሰምቷል::በጎዴ ከሚገኙ የመከላከያ ደህንነት ምንጮች የተገኘው መረጃ እንደሚያመለክተው ካልደፈረሰ አይጠራም በሚል የተነሳውን አመጽ የተመለከቱ የሕወሓት የጦር አዛዦች የመከላከያ ሰራዊት ጥያቄ እና አመጻ ተከትሎ አነሳስተዋል የተባሉ አራት ወታደራዊ መኮንኖች መታሰራቸው ታውቋል::
በዚህም መሰረት
ሌተናት ኮሎኔል ተክለአረጋይ ዳኘው
ሻለቃ አበባየሁ አቡኑ
ሻለቃ ደምወዜ የኔአለም
የም/መቶ አለቃ ላቀው ልኬየለህ በጎዴ ወታደራዊ እስር ቤት መታሰራቸው ታውቋል::
በጅጅጋ ከተማ በተከታታይ የሚሰበሰበው የሕወሓት ጄኔራሎች ቡድን በደቡብ ምስራቅ እዝ ውስጥ የተነሳውን አለመተማመን እና ግርግር መቅረፍ እንዳልተቻለ እና አመጾች ሳይስፋፉ እና ስር ሳይሰዱ መወሰድ ያለባቸው እርምጃዎች ሁሉ እንዲወሰዱ ሲል ተስማምቷል::በሶማሊ ክልል የሚገኘው የሕወሓት ጀሌዎች የሆኑ መኮንኖች በኦጋዴን ክልል ማህበረሰብ ላይ ይህ ነው የማይባል ከባድ ግፍ እና ግድያ እስር ሰቆቃ የሚፈጽሙ ሲሆን በሕገወጥ ንግድ ላይ በመሰማራት የሃገሪቷን አንጡረ ሓብት በመዝረፍ እና በማሳጣት ስራ ላይ መሰማራታቸው የአደባባይ ሃቅ ነው::ከዚህ ቀደም እንደተገለጸው የሕወሓት የጦር መኮንኖች እንዲሁም በፖለቲካ ጣልቃ ገብነት ሴቶችን በመድፈር በዘረፋ ከአከባቢው ሲቭል ባለስልጣናት ጋር የተመሳጠረ ሙስና በመስራት የሚከሰሱ ሲሆን ስርኣቱ በስልጣን እንዲቆይ ከፍተኛ የሆነ ገንዘብ በአከባቢው እንደሚፈስ ምንጮቹ የተናገሩ ሲሆን የዚህ ገንዘብ ፍሰት የሙስና ተግባራት በሕወሓት የጦር መኮንኖች ይፈጸማል ሲሉ ይናገራል::

Thursday, January 22, 2015

Ethiopia media being decimated.


(Nairobi) – The Ethiopian government’s systematic repression of independent media has created a bleak landscape for free expression ahead of the May 2015 general elections, Human Rights Watch said in a report released today. In the past year, six privately owned publications closed after government harassment; at least 22 journalists, bloggers, and publishers were criminally charged, and more than 30 journalists fled the country in fear of being arrested under repressive laws. 


The 76-page report, “‘Journalism is Not a Crime’: Violations of Media Freedom in Ethiopia,” details how the Ethiopian government has curtailed independent reporting since 2010. Human Rights Watch interviewed more than 70 current and exiled journalists between May 2013 and December 2014, and found patterns of government abuses against journalists that resulted in 19 being imprisoned for exercising their right to free expression, and that have forced at least 60 others into exile since 2010.

Ethiopia’s government has systematically assaulted the country’s independent voices, treating the media as a threat rather than a valued source of information and analysis,” said Leslie Lefkow, deputy Africa director. “Ethiopia’s media should be playing a crucial role in the May elections, but instead many journalists fear that their next article could get them thrown in jail.”

Most of Ethiopia’s print, television, and radio outlets are state-controlled, and the few private print media often self-censor their coverage of politically sensitive issues for fear of being shut down.

The six independent print publications that closed in 2014 did so after a lengthy campaign of intimidation that included documentaries on state-run television that alleged the publications were linked to terrorist groups. The intimidation also included harassment and threats against staff, pressure on printers and distributors, regulatory delays, and eventually criminal charges against the editors. Dozens of staff members went into exile. Three of the owners were convicted under the criminal code and sentenced in absentia to more than three years in prison. The evidence the prosecution presented against them consisted of articles that criticized government policies.


While the plight of a few high-profile Ethiopian journalists has become widely known, dozens more in Addis Ababa and in rural regions have suffered systematic abuses at the hands of security officials.

The threats against journalists often take a similar course. Journalists who publish a critical article might receive threatening telephone calls, text messages, and visits from security officials and ruling party cadres. Some said they received hundreds of these threats. If this does not silence them or intimidate them into self-censorship, then the threats intensify and arrests often follow. The courts have shown little or no independence in criminal cases against journalists who have been convicted after unfair trials and sentenced to lengthy prison terms, often on terrorism-related charges.

“Muzzling independent voices through trumped-up criminal charges and harassment is making Ethiopia one of the world’s biggest jailers of journalists,” Lefkow said. “The government should immediately release those wrongly imprisoned and reform laws to protect media freedom.”

Most radio and television stations in Ethiopia are government-affiliated, rarely stray from the government position, and tend to promote government policies and tout development successes. Control of radio is crucial politically given that more than 80 percent of Ethiopia’s population lives in rural areas, where the radio is still the main medium for news and information. The few private radio stations that cover political events are subjected to editing and approval requirements by local government officials. Broadcasters who deviate from approved content have been harassed, detained, and in many cases forced into exile.

The government has also frequently jammed broadcasts and blocked the websites of foreign and diaspora-based radio and television stations. Staff working for broadcasters face repeated threats and harassment, as well as intimidation of their sources or people interviewed on international media outlets. Even people watching or listening to these services have been arrested.

The government has also used a variety of more subtle but effective administrative and regulatory restrictions such as hampering efforts to form journalist associations, delaying permits and renewals of private publications, putting pressure on the few printing presses and distributors, and linking employment in state media to ruling party membership.

Social media are also heavily restricted, and many blog sites and websites run by Ethiopians in the diaspora are blocked inside Ethiopia. In April, the authorities arrested six people from Zone 9, a blogging collective that provides commentary on social, political, and other events of interest to young Ethiopians, and charged them under the country’s counterterrorism law and criminal code. Their trial, along with other media figures, has been fraught with various due process concerns. On January 14, 2015, it was adjourned for the 16th time and they have now been jailed for over 260 days. The arrest and prosecution of the Zone 9 bloggers has had a wider chilling effect on freedom of expression in Ethiopia, especially among critically minded bloggers and online activists.

The increased media repression will clearly affect the media landscape for the May elections,.

“The government still has time to make significant reforms that would improve media freedoms before the May elections,” Lefkow said. “Amending oppressive laws and freeing jailed journalists do not require significant time or resources, but only the political will for reform.”