Saturday, February 28, 2015

የሆሳህና ደብረ ገነት ቅድስት ማርያም ቤ/ክ በእሳት ነደደች

ቤተክርስቲያኗ ከመቃጠሏ በፊት
ቤተክርስቲያኗ ከመቃጠሏ በፊት
ከተቃጠለች በኋላ
ከተቃጠለች በኋላ
ከተቃጠለች በኋላ
ከተቃጠለች በኋላ

(ዘ-ሐበሻ) እኔ የዘ-ሐበሻ ሪፖርተር ነኝ ያሉ በአካባቢው የሚገኙ ነዋሪዎች በፎቶግራፍ እና በቭዲዮ አስደግፈው በላኩት መረጃ የካቲት 21/2007 ዓ.ም በሀዲያና ስልጤ ሀ/ስብከት የሆሳዕና ደብረ ገነት ቅድስት ማርያም ቤ/ክ በእሳት መንደዷን አስታወቁ፡ 

የቃጠሎው መነሻ እስካሁን ያልታወቀ ሲሆን ጉዳዩን ለማድበስበስ የሚደረገው ጥረት ም ዕመናኑን እያስቆጣ መሆኑንም ለዘ-ሐበሻ የደረሰው መረጃ ያመለክታል::
የካቲት 21 ቀን ከቀኑ 10 ሰዓት ጀምሮ ህዝበ ክርስቲያኑን ለማጽናናት እንዲሁም የገቢ ማሰባሰብ መርሐግብር የሀ/ስብከቱ ሊቀጻጻስ ብጹዕ አቡነ ቀሌምንጦስ በተገኙበት ከአ.አ በመጡ መምህራን እና ዘማሪያን መርሐ ግብር የተዘረጋ ማንኛውም ም እመን የሚቻለውን ስፍራው ድረስ በመገኘት ድጋፍ እንዲደርግ ያልተቻለም በጸሎት እንዲያስቡ በእግዚአብሔር ስም ቅድስት ቤተክርስቲያን ጥሪዋን አስተላልፋለች ሲሉ እኔ የዘ-ሐበሻ ሪፖርተር ነኝ ያሉ ከስፍራው ዘግበዋል::
ለዘ-ሐበሻ የደረሰው መረጃ እንደሚያመለክተው በዚሁ ቤተክርስቲያኒቱ በምትገኝበት ከተማ ከሳምንት በፊት በተመሳሳይ እሳት አደጋ አጠና ተራ ወድሟል::
- See more at: http://www.zehabesha.com/amharic/archives/39410#sthash.6vrzdl3Z.dpuf

Friday, February 27, 2015

Top 10 infamous Meles Zenawi quotes


With Ethiopian Prime Minister Meles Zenawi just a few years away from joining an elite club of despots who have ruled their country for a quarter of a century or more, it would only be fitting to take a trip down memory lane at some of his most infamous quotes, as well as his memorable fatuous statements.

10) In 1991, during the London conference, Meles said to British and American officials that the umbrella EPRDF coalition will be subordinate to his TPLF party. When British officials objected, a visibly angry Meles said:

"Let me make something clear. After the conference we are not going to have an EPRDF government."

9) In 1993, during the conclusion of his interview, a reporter asked Meles on his views of Ethiopian history, to which Meles responded with:
"Ethiopia is only 100 years old. Those who claim otherwise are indulging themselves in fairy tales."

8) During a 1994 interview with foreign journalists in Asmara, Meles was quoted to have said the following about Eritrean President Isaias Afwerki:

"Spending one hour with Isaias is far more worthwhile, rewarding and enlightening than reading ten books"

7) In 1997, while holding a discussion with Professor Donald Levine, an intellectual who has studied Ethiopia's history for five decades, Meles stated that Ethiopia had never been a single country prior to Menelik's conquest. In trying to emphasis this point, Meles said:

"The Tigreans had Axum, but what could that mean to the Gurague? The Agew had Lalibela, but what could that mean to the Oromo? The Gonderes had castles, but what could that mean to the Wolaitai?"

6) In an an interview with state media, Meles said the Ethiopian flag is nothing more than a "piece of rag"

"The flag is just a piece of rag."

5) In 1999, after inhumanly deporting over 80,000 Ethiopians of Eritrean origins and robbing them of their property, Meles said to his rubber-stamp parliament:

"If we don't like the color of their eyes, we have the right to chase them away!"

4) In early 2001, a concerned Ethiopian woman asked Meles as to the whereabouts of her son who did not  return from his war with Eritrea. Irritated by the tone of her question, he responded with:

"Lady, if your son does not return in six months time, then you'll have your answer!"

3) During the 2005 election demonstrations, to which Meles ordered the deaths of 193 unarmed Ethiopian civilians in Addis Ababa, the premier is said to have referred to Amharas as "donkeys" to his trusted Tigrayan General Samora:

"These Amhara donkeys need to be taught a lesson. They only become peaceful and religious when a kalashnikov is pointed at them."

2) During the disastrous failed invasion and subsequent occupation of Somalia by Ethiopia in 2006, Meles said to the New York Times that his goal was not to topple the ICU but to go after non-existent Eritrean soldiers in Somalia.

“The only forces we are pursuing are Eritreans who are hiding behind the skirts of Somali women.”

1) In 2010, while discussing bilateral relations with the former Libyan dictator Moammar Gadhafi in Addis Ababa, Meles said:

"I am Yemeni. I know myself to be a Yemeni. We are Yemenis. Apart from the royal family, Ethiopians are Arabs."

ሼክ አላሙዲን የህወሃትን 40 ኛ አመት በአል በአዲስ አበባ ስፖንሰር አደረጉ

ህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) በትግራይ ክልል በብዙ መቶ ሚሊዮኖች የሚቆጠር ብር በማውጣት ከአንድ ወር በላይ ሲያከብር የቆየውን የ40ኛ ኣመት የምስረታ በዓሉን የፊታችን እሁድ በአዲስአበባ ሚሌኒየም አዳራሽ በሚያካሂደው ድግስ ለማጠቃለል መዘጋጀቱ ታውቋል፡፡
በዚህ ዝግጅት ላይ ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት፣ አምባሳደሮችና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች የሚገኙ ሲሆን የዕለቱን የፌሽታ በዓል ወጪ ሚሊየነሩ ሼህ አልአሙዲ እንደሚሸፍኑት ምንጮች ገልጸዋል። ህወሓት 40ኛ ዓመት በዓሉን አስታኮ ያለእሱ ሀገሪትዋ ምንም አማራጭ እንደሌላት በመስበክ አጋጣሚውን በመንግስት ሐብት፣ ንብረትና ገንዘብ ለምርጫ ቅስቀሳ እየተጠቀመበት ነው በሚል አንዳንድ የተቃዋሚ ፓርቲዎች ድርጊቱን ማውገዛቸው የሚታወስ ነው፡፡
አርቲስቶችና ጋዜጠኞችን የትግራይ ክልል የሚገኘውን የደደቢት በርሃ ከአንድ ወር በፊት በማስጎብኘት የተጀመረው የህወሃት 40ኛ ዓመት የምስረታ በዓል እጅግ በተጋነነ መልኩ ከፍተኛ ወጪ ወጥቶበት ከመንግስት ካዝና ወጪ ሆኖ በፌሽታ ሲከበር መሰንበቱ ይታወሳል፡
በዚህ በዓሉ ላይ የህወሓት መመስረት ለሀገሪቱ ትንሳዔ እንዳስገኘ ፣ ልማት፣ ዴሞክራሲ፣ የህግ የበላይነት እንደተገኘ ተደርጎ በመንግስት ቁጥጥር ስር ባሉ መገናኛ ብዙሃን የአንድ ፓርቲ ፕሮፖጋንዳ ሲሰራጭ ይሰንብት እንጂ በተቃራኒው የትግራይ ሕዝብን ጨምሮ መላው ሕዝብ በህወሓት መራሹ መንግስት ሙስና፣ የመልካም አስተዳደር እጦት፣ የዴሞክራሲና የፍትሕ መጓደል እንዳንገሸገሸው ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው ወገኖች ጠቅሰው ይህ ሁኔታ ህወሓቶች ከሕዝቡ የቱን ያህል እንደራቁ ትንሽ ማሳያ ነው ብሎአል፡፡
- See more at: http://satenaw.com/amharic/archives/4946#sthash.5iqIIKiX.dpuf

Tuesday, February 24, 2015

የባቡር ሃዲድ መስመር በሙስና ምክንያት ከደረጃ ውጭ እንዲሆን በመደረጉ የ124 ሚሊዮን ብር ኪሳራ ደርሷል።

የጦፈ ሙስና ከመንገድ ሥራ፣ ከባቡር መስመር ዝርጋታና ከቤቶች ልማት

በቢሊዮኖች የሚቆጠር ገንዘብ እየተዘረፈ ነው – ሚኒስትሩ

* ከ30 እስከ 40% የግንባታ ወጭ ይዘረፋል!!

የኮንስትራክሽንና ኢንዱስትሪ ልማት ሚኒስትሩ አቶ መኩሪያ ሃይሌ ከስነ ምግባር እና ፀረ ሙስና ኮሚሺን አጣሪ ቡድን ጋር ባደረጉት ውይይት ከመንገድ ስራ፣ ከባቡር መስመር ዝርጋታና፣ ከቤቶች ልማት ፕሮጀክቶች ጋር በተያያዘ በቢሊዮኖች የሚቆጠር ገንዘብ እየተዘረፈ መሆኑን አምነዋል።
የፀረ ሙስና ኮሚሽን ባካሄደው ጥናት በባቡር መስመር ግንባታ 2.3 ኪሜ የባቡር ሃዲድ መስመር በሙስና ምክንያት ከደረጃ ውጭ እንዲሆን በመደረጉ የ124 ሚሊዮን ብር ኪሳራ ደርሷል። የአደጋ መከላከያ ብረቶች የተሰሩት ከወጣላቸው የጥራት ደረጃ በሶስት እጅ ያነሱ ሆነው በመገኘታቸው ጉዳዩ ለቦርድ ሰብሳቢው አርከበ እቁባይ ቢቀርብም ምላሽ ሳይሰጠው በመቅረቱ በቢሊዮን የሚቆጠር ገንዘብ የት እንደገባ ማወቅ አለመቻሉን ገልጿል።
የስነ ምግባር እና ፀረ ሙስና ኮሚሺን ያቀረበውን ሪፖርት ተከትሎ ምላሽ የሰጡት ሚኒስትር መኩሪያ ሃይሌ፣ ችግሩ የተፈጠረው ለምርጫው ሲባል የባቡሩ ግንባታ እንደ ትልቅ የምርጫ ማሳመኛ በመያዙ ነው ።
የግንባታ ኢንዱስትሪው ከሚያወጣው ወጪ ከ30 እስከ 60 በመቶ የሚሆነው በሙስና ይባክናል ሲሉም ሚኒስትሩ አክለዋል።
እንደዚያም ሆኖ በቅርቡ የተመረቀ የአዲስ አበባ መለስተኛ የባቡር ግንባታ፣ አገልግሎት ከመጀመሩ ከወዲሁ በርካታ የመፈራረስ ችግሮች እያጋጠሙት ነው። ለፖለቲካ ፍጆታና ለፕሮፓጋንዳ ሲባል ቶሎ ቶሎ እንዲሰራ ከማድረግ ዉጭ እነ አቶ አርከበ እቁባይ የሕዝቡን ፍላጎት ከግምት ያላስገቡ ሲሆን፣ አስፈላጊ የጥንቃቄ እርምጃዎች አልተወሰዱም። በዋናነት የባቡ ሃዲዱ ከተማዋን ለሁለት የከፈለ ሲሆን ከሃዲዱ በስተቀኝ እና በስተግራ ያሉ ነዋሪዎች ለመገናኘት እጅግ በጣም ብዙ ርቀት ለመጓዝ ተገደዋል። 

Monday, February 23, 2015

Seven children perish as several fires break out in Hawassa

HAWASSA, Ethiopia - Several fires broke out Sunday night in an emerging, traditional-like market place in the tourist-hub city of Hawassa, 270km south of Addis Ababa.
The raging fires killed atleast seven street children, and largely destroyed the area called 'Addis Gebeya,' whose English equivalent is "New Market."
Awassa fire fighters couldn't put out the wind-swept flames alone, and were joined by their colleagues from Shashemene, 25 km away from the lake-side city. At dawn, several bulldozers cleared the area of ashes and debris.
Observers said fire fighters, known for their sluggish efforts, were this time on alert, making sure the blames do not go beyond the targetted 'Addisu Gebeya' and wipe out residential quarters.
The public believes the fires are the work of the ruling party TPLF/EPRDF, which, under the cover of "modernizing urban towns" is dubiously known for destroying private businesses or emerging markets by setting them on fires.
"When bulldozers appear in the morning and clear the area of ashes and debris, it is evident it was the work of the government," one observer said.
TPLF, which in reality practices Marxist-like economics, has a voracious appetite to own the entire economy by way of decimating private businesses - even if they are budding.
Even as recent as in January, a privately-owned and historic Taitu Hotel was burned down, with the public squarely pointing its accusatory finger at the ruling party or government.

State-employed fire fighters spent one hour haggling over how much the owner of the hotel should pay them to spare his property. By the time the firefighters agreed , much of the historic site was gone.
http://www.ethiomedia.com/10parts/4273.html

ህወሃት ምንድን ነው? - ገለታው ዘለቀ


በቅርቡ የህወሃት ኣርባኛ ዓመት ለየት ባለ መንገድ መከበሩ ገርሞኛል። በየዓመቱ እንደሚከበር ሁላችን እናውቃለን። ይሁን እንጂ የዓርባኛ ዓመቱ በዓል እንዲህ ለምን እንደተወራለት ለምን የሌላ ኣገር መሪ ሳይቀር እንደተጋበዘበት ኣልገባኝም። ብዙ ጊዜ እንዲህ ዓይነት ለየት ያለ ድግስ የሚደረገው የኢዮቤልዩ በዓል ሲከበር ነው። የሆነው ሆኖ የመነሻ ኣሳቤ ይሄ ኣይደለም። ህወሃት ኣርባኛ ዓመት በዓሉን ሲያከብር እኔ በህወሃት ተፈጥሮ ስደመም ነበር።
በርግጥ ኢትዮጵያ ኣሁን ላለችበት የተመሰቃቀለ ህይወት ሲንከባለሉ የመጡ ኣንዳንድ ችግሮች ኣስተዋጾ ቢያደርጉም የችግሩ ከፍተኛ ኣስተዋጾ ኣድራጊ ግን ህወሃት ነው። በየክልሉ የህወሃት ተከታዮች ኣስተዋጾኣቸው እንዳለ ሆኖ የህወሃት ድርሻ ግን በጣም ገዝፎ ይታያል። ግን …ግን ለምንድነው በህወሃት መራሹ መንግስት ጊዜ ኢትዮጵያ እንዲህ ዓይነት ኣስከፊ ችግር ውስጥ የገባችው? ብለን መጠየቅ ካማረን የህወሃትን ተፈጥሮና ኣነሳስ በሚገባ መረዳትን ይጠይቀናል። ብዙ ሰው ህወሃትን የሚገልጸው ዘረኛ…ኣምባገነን በሚል ነው። እውነት ነው ህወሃት ጎጠኛና ኣምባገነን ነው። ከዚህ በተሻለና በጠራ ሁኔታ የህወሃትን ስርና መሰረት መመርመሩ የበለጠ የህወሃትን ተፈጥሮ እንድንረዳው ያደርገናል። ኢትዮጵያ በየጊዜው የሚገጥማት ችግር በርግጥ እንዴት ከዚህ ከህወሃት ተፈጥሮ ጋር እንደሚመጋገብ አብርቶ ያሳየናል። ከዚህም በተጨማሪ የሃገሪቱን ፖለቲካዊ እንቅስቃሴዎች ጉዳይ የበለጠ እንድንረዳው ያደርጋል።
ህወሃት ምንድን ነው? ምን ዓይነት ጉዳይ ኣንገብግቦት ነው የዛሬ ኣርባ ዓመት ወደ በረሃ የገባው? ብለን ከጠየቅን የህወሃት ኣባላት እንደሚሉት የነጻነት (Liberty) ጥያቄ ጉዳይ ኣይደለም። የነጻነት ጥያቄ ስል ትግራይንም ማለቴ ነው። ህወሃት የታገለው ለትግራይ ነጻነትም ኣይደለም ማለቴ ነው።
ህወሃት ወደ ጫካ ሲገባ በርግጥ በወቅቱ የነበረው የፖለቲካ ድባብ ማለትም “የብሄር ብሄረሰብ ጥያቄ” የሚባለው ነገር ኣስተዋጾ ቢያደርግም ዋናው የዚህ ቡድን ጥያቄ የነጻነት ጥያቄ፣ የእኩልነት ጥያቄ፣ ወይም የዴሞክራሲ ጥያቄ ሳይሆን በወቅቱ ያበሸቀውና ወደ ጫካ የሰደደው ጉዳይ የኢኮኖሚ ጉዳይ፣ የከፋ ድህነት ጉዳይ ነው። የህወሃት መስራቾች በወቅቱ ስርዓት ኣኩርፈው ወደ ጫካ ሲገቡ በነበራቸው ግምገማ መሰረት ትግራይ በጣም የተጎዳች፣ ረሃብ ያጠቃት ናት። ሌላው የኢትዮጵያ ህዝብ ህይወት ከትግራይ የማይለይ፣ የሃብት ክፍፍሉ በኣጠቃላይ ህዝብ ደረጃ ኣብዛኛውን የጎዳ መሆኑን ለማወቅም ሆነ ይህንን ለመመርመር ኣልፈቀዱም። በጠባቡ የትግራይን የኢኮኖሚ ህይወት፣ የገበሬውን ህይወት ኣይተው የትግራይ ሃርነት ትግል ጀመሩ። የዚህ ህዝብ ችግር በሃገር ጥላ ስር ኣብሮ ይፈታል የሚለው ነገር ያበሽቃቸው ነበር። የኣንድነትን ሃይሎች እንደነ ኢህዓፓ ኣይነቶችን እንደጠላት ያዩትም ለዚህ ነው። ትግራይን ነጥለው ሲያዩ ችግሩን ለመረዳት በጣም የቀለላቸው ይመስላል። ለመጡበት ቀየ የራራው ልባቸው ለኦሮሞው ለኣማራው ለሌላው ድሃ ህዝብ ኣልራራም ኣላቸው። እንዴውም ይህንን ስሜት ሳይንሳዊ ይዘት እንዲኖረው ለማድረግ ሲጥሩ ታዩ። በመጀምሪያ ኣካባቢህን ከዚያ ሃገር ምናምን… እያሉ በዚያ ስሜታቸው ከማፈር ይልቅ ለማስተማመን (justify ለማድረግ) ብዙ ጣሩ።
ከፍ ሲል እንዳልነው ህወሃቶች “ትግራይ ሃርነት” ይበሉት እንጂ መራራው ጥያቄ ትግራይን ከሆነ ጨቋኝ ስርዓት ኣላቅቆ ኣንድ ነጻ ኣገር ለማድረግ ኣልነበረም። ጥያቄው የፖለቲካና የኣስተዳደር ነክ የነጻነት ጥያቄ ስላልሆነ በትግላቸው የመጀመሪያ ወራት ኣንዳንድ ኣባላት የመገንጠል ጥያቄ ኣንስተው የነበረ ቢሆንም ገና በማለዳ ይህ ኣሳብ ተቀጨ። ከፍ ሲል እንዳልኩት መራራው ጥያቄ የኢኮኖሚ ኦፖርቹኒቲ እንዴት ለኛ ሰፈር ይሰፋል? የሚል በመሆኑ ለዚህ ጥያቄ ብዙ መስዋእትነት ተከፈለ። ሌላው ኢትዮጵያዊ በደርግ ስርዓት ተጨቁኖ ስለነበረና ለውጥ ሽቶ ስለነበር የህወሃትን ተፈጥሮ መመራመር ኣልፈለገም። የኣንድ ኣካባቢ ኣርማ ለጥፈው ቢመጡም በኣንድያ የሃገር ስሜት ስር ያደገው ሰፊ ህዝብ ይህ ኣስተዳደጉ ስለ ህወሃት እንዳይመራመር ትኩረቱን ጋረደው። ኣንዳንዱ ሰው ደግሞ ከጅምሩ ብሄርተኞች መሆናቸው ባይዋጥለትም እስቲ ይሁን፣ ወንድሞቻችን ናቸው፣ ማእከላዊውን ስልጣን ሲይዙት፣ ኢትዮጵያ የምትባለውን ኣገር ሲያዩ፣ የሌላውን ህዝብ የከፋ ችግር ጠጋ ብለው ሲያዩ፣ ኣለማቀፋዊ መጋለጥ ሲኖራቸው ይተውታል ብሎ በልበ ሰፊነት ሲጠብቅ እነሆ ህወሃት ኣርባ ኣመቱን ትናንትና ሲያከብር ወይ ፍንክች ኣልተለወጠም።
ወያኔ የዛሬ ሃያ ሶስት ዓመት የኢኮኖሚ ጥያቄ ዋና ጥያቄው ኣድርጎ ስልጣን ላይ ሲወጣ የኦፖርቹኒስቲክ ባህርይ (Opportunistic behavior) በሃገሪቱ ፖለቲካ ኣካባቢ በሰፊው ሰፈነ። ይህ ባህርይ የፖለቲካውን ጨዋታ ሁሉ እንዳይሆን እንዳይሆን ኣድርጎ ኣበላሸው:: ማህበራዊ ሃብታችንን በተለይም የመተማመን (የ trust) ሀብታችንን በጣም ጎዳብን።
ህወሃት ትግራይ ትግራይ ይበል እንጂ በትግሉ ጊዜ ለትግራይ የገባውን ቃል መፈጸም ኣልቻለም። ከሁሉ በላይ የትግራይ ህዝብም በወያኔ ጎጠኛ ስሜት ተከፋ። ኣብዛኛውን የትግራይን ህዝብ ወደማይፈልገው ስሜት ውስጥ ከተተው። ስለዚህም ህወሃት ከትግራይም ሌላ ክብ ሰርቶ የዚያን ክብ እርሻ ለወጠ። የዚያን ጠባብ ክብ ኣባላት ነጋዴዎች ኪስ በገንዘብ ጠቀጠቀ። ስልጣኑን ለማቆየት ይረዳኛል በሚል በየክልሉ ጥቂት ጥቂት ክቦችን እየሰራ እነሱን የከፍተኛ የኢኮኖሚ ኦፖርቹኒቲ ተጠቃሚ እያደረገ እልፉን ህዝብ ሜዳ ላይ ጣለው።
ቶሎ እንድናድግ ሃብት በኣንድ ኣካባቢ ይደልብልን በሚል ማታለያ ኣንዳንዴም የልማታዊ መንግስትን ስም ለጠፍ እያደረገ የኢኮኖሚውን ኦፖርቹኒቲ ሁሉ በጣም በጠበበ የህብረተሰብ ክብ ውስጥ ጠቀጠቀው። ይህ ቡድን መነሻው የኢኮኖሚ ችግር በመሆኑና የታገለውም ለዚህ በመሆኑ ነው ይህን የሚያደርገው። ይህ ቡድን ለኢኮኖሚ ጉዳቱ ማገገሚያ ኣድርጎ የወሰደው የፖለቲካ ስልጣንን መሳሪያ በማድረግ በመሆኑ በሃገሪቱ ፍትህ ኣድሮ ሲቀጭጭ ይታይ ጀመር። ያሳዝናል።
ህወሃት ገና ከመነሻው የዚህ የኢኮኖሚ ጥቅም ጉዳይ ኣናዶት ጫካ መግባቱ ብቻ ሳይሆን የጎዳን ይህንን ጠባብ የሆነ የኢኮኖሚ እድል ለማስፋት ኢትዮጵያ የምትከፍለው ዋጋ እጅግ ከፍተኛ መሆኑ ነው። የጥቂት የህወሃት ደጋፊዎችን እርሻ ለመለወጥ፣ የጥቂት የሰርዓቱ ደጋፊ ነጋዴዎችን ኪስ ለመሙላት ኢትዮጵያ የባህር በር እስክታጣ፣ ኢትዮጵያ ድንበሩዋ ተቆርጦ እስክታንስ፣ በዘር ፖለቲካ ማህበራዊ ሃብታችን እስኪፈርስ ድረስ ዋጋ ትከፍላለች።እስከዚህ ጥግ የሄደ መስዋእትነት ይከፈላል። ይሄ ነው እጅግ ኣሳዛኙ ነገር። እነዚህን ኣላፊ ወይም ኣነስተኛ የኢኮኖሚ ድጋፎችን ለማድረግ ስለምን ኢትዮጵያ ሉዓላዊነቱዋ እስኪደፈር ዋጋ ትከፍላለች? ብለን ስናስብ እስከ ሃቹ ያስደምመናል። ህወሃት ቢገነዘብ ኖሮ ይህን በዙሪያው የኮለኮለውን ጠባብ ቡድን ኣሁን የጠቀመውን ያህል ለመጥቀም ኢትዮጵያ ይሄን ያህል ዋጋ መክፈል ኣልነበረባትም። በኣምባ ገነን ኣገሮች ሙስና እንዳለ ሁሉ በሙስና የተለያዩ ጥቅሞችን ማደረግ ቢቻል የህወሃት ክፋት እስከዚህ ጥግ ይባል ነበር። ይህ ግን ኣልሆነም። ስርዓቱን ለመጠበቅ ሲባል፣ የነዚህን ጠባብ ቡድኖች ጥቅም ለመጠበቅ ሲባል በሱዳን በኩል ተቃዋሚ እንዳይነሳ የጠገበ መሬት ቆርሶ እስከ መስጠት መድረሱ በጣም ያስገርማል። ኢትዮጵያን የሚያህል ትልቅ ኣገር የባህር በር ጥያቄን ኣምርራ ከመጠየቅ ይልቅ ዝምታን መርጣ የነዚህን ጠባብ ጉጅሌዎች ኪስ መሙላት ይሻላል ለወያኔ።
ይህ ስርዓት ከቀደሙት የሚለየው በዚህ ነው። የቀደሙት ስርዓቶች ኣምባገነን ሆነው የሆነ ክብን እየጠቀሙ ብዙውን ኣግልለው ይኖሩ ነበር። እነዚህ መንግስታት ይህን ቡድናቸውን ወይም ጉጅሌዎቻቸውን የሚጠቅሙት ግን የድሃውን ጉልበት እስከመበዝበዝ በሚደርስ ጭካኔ ነው። ህወሃት ግን ድሃውን ከመበዝበዝ ኣልፎ ኢትዮጵያን ራሱዋን ሉዓላዊነቱዋን ታሪካዊ ማንነቷን ሁሉ ሸጦ ነው ቡድኑን የሚጠቅመው።
ደርግ ለዚህ ምሳሌ ነው። ሁሉ እንደሚያስታውሰው ጨካኝ በመሆኑ ኢትዮጵያ ብዙ ዋጋ ከፈለች። ነገር ግን ለስልጣኑ ሲል የሃገሩን ሉዓላዊነት ኣላስደፈረም። ደርግ ለስልጣኑ ሲል በሉዓላዊነት ላይ ቢነሳ ኤርትራን እንድትገነጠል ማድረግ ብቻ ይበቃው ነበር። ኤርትራን በሰላማዊ መንገድ እንድትገነጠል ቢስማማ ወይም ቀደም ብሎ በኮንፌደሬሽን ኣስተዳደር ችግሩን ቢፈታ ሃይሉን ኣሰባስቦ ወያኔን ያጠፋ ነበር። ህወሃት ወደ ስልጣን እንዲመጣ የሻእቢያ ኣስተዋጾ እጅግ የጎላ እንደነበር ይታወቃል። በመሆኑም ያለፉት መንግስታት በስልጣን ለመቆየትና ለግል ጥቅም ልክ የነበራቸው ሲሆን ያሁኑ መንግስት ግን ኢትዮጵያን መስዋእት እያደረገ ኣላፊ የሆነ ጥቅማጥቅም የሚቃርም በመሆኑ በታሪካችን ኣይነተው የማናውቀው ጉደኛ መንግስት ያደረዋል።
በቅርቡ ኣርባ ኣመቱን ያከበረው ህወሃት በኣርባ ኣመት ቆይታው ምንም ኣልተማረም። ከጥፋት ወደ ጥፋት ሲያዘግም ነው የምናየው። መሪዎቹ የዛሬ ሃያ ኣመት ካሳዩት ትህትና ያሁኑ ያንሳል፣ የዛሬ ሃያ ኣመት ካሳዩት የፕሬስ ነጻነት የዛሬው ያንሳል። ወያኔ ኣንዱ እንዳይማር ያደረገው ነገር ከመነሻው ትግሉ የኢኮኖሚ እድልን መጠቀም በመሆኑ እንዲሁ ሃብቱን እንደነከሰ መኖርን ስለሚመርጥ ነው። የህወሃት ተፈጥሮ እንደዚህ ነው። ይህ ስርዓት ካልተለወጠ ኢትዮጵያን ብቻ ሳይሆን ኣጠቃላይ የኣካባቢውን ኣገራት ጂኦ ፖለቲክስ በመቀየር በኣፍሪካ ቀንድ ችግር ሊፈጥር እንደሚችል መገመት ኣያዳግትም። የዘር ፖለቲካውና የመሬት ነጠቃው የኣካባቢውን ጂዖ ፖለቲክስ ወደ ኣልተፈለገ ኣቅጣጫ ሊወስዱ የሚችሉ እምቅ ችግሮች ናቸው። የመሬት ነጠቃ በኢትዮጵያ የኢኮኖሚና የኦፖርቹኒቲ ጥያቄ ብቻ ሳይሆን ፖለቲካዊ እንድምታውና ተጽእኖው በሚገባ መታወቅ ኣለበት። እንደሚታወቀው ኢትዮጵያ በኣፍሪካ ቀንድ ካላት ግዝፈት የተነሳ ኣለመረጋጋት ቢፈጠር በጅቡቲ፣ በሶማሊያና በኤርትራ ላይ የሚፈጥረው ተጽእኖ እጅግ ጉልህ ነው። የኣፍሪካ ቀንድ ሰላም ሲታሰብ ከኢትዮጵያ ሰላምነት ውጭ ማሰብ ኣይቻልም። ወያኔ ትልቅ ውስጣዊ ችግር በውስጡ ደብቆ ይዞ በኣካባቢው ኣገራት ዘንድና በኣለም ኣቀፍ ተቋማት ዘንድ ሰላም እንደሆነ፣ ሃላፊነት ሊሸከም እንደሚችል ለማሳየት ይሞክራል። ይህ ግን እውነት ሳይሆን በርግጥ ኢትዮጵያ በኣሁኑ ሰዓት ማህበራዊ ሃብቱዋ ያለ ልክ ተጎድቶ በከፍተኛ ውጥረት ላይ ያለች ኣገር ናት። ለኣፍሪካ ቀንድ ዋና ስጋት የሆነው የኣክራሪነት ችግር በህወሃት ኣይፈታም ብቻ ሳይሆን ራሱ የኢትዮጵያ ፖለቲካ ድባብ ኣክራሪነት የሚታይበት በመሆኑ እምቅ ኣሸባሪነት በህወሃት ኣገዛዝ ውስጥ ተቀብሮ ይኖራል።ህወሃት በተፈጥሮው የኣሸባሪነት ጠላትም ሊሆን የሚያስችል ነገር የለውም። ኣክራሪነት የሚገለጸው ከሃይማኖት ጋር በተያያዘ ብቻ ሳይሆን ከማንነት ፖለቲካ ጋር የተያያዘ በመሆኑ ኢትዮጵያ በኣህኑ ሰዓት ይህን ችግር በውስጡዋ ይዛ ያለች ኣገር ናት። በየትኛውም ጊዜ ሊፈነዳ የሚችል የጎሳ ኣመጽን እያፈራች ያለች ኣገር ናት። ከፍ ሲል እንዳልነው የህወሃትን ተፈጥሮ ተከትሎ የመጣው የኦፖርቹኒስቲክ ጸባይ ብዙዎችን ኣብሽቆ ይታያል። እኛ ኢትዮጵያዊያን የወያኔን ተፈጥሮ ተረድተን የጋራ የሆነችውን ኣገራችንን በጋራ እንደገና ለማነጽ ሳንከፋፈል በጋራ ታግለን ይህን ስርዓት መለወጥ ይኖርብናል። በኣንድም በሌላም መንገድ ለወያኔ የጎሳ ፖለቲካ ሰለባ ሳንሆን ኣንድነትን ኣጥብቀን ልንይዝ በፍቅር ላይ የተመሰረተ የለውጥ እንቅስቃሴ ልናደርግ ይገባናል።
እግዚኣብሔር ኢትዮጵያን ይባርክ

Saturday, February 21, 2015

ዓለም አቀፍ የጦር ወንጀል ተመልካች ፍርድ ቤት ጠ/ሚ አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝን ወቀሰ -

0,,16786511_303,00
ዘ ሄግ ኔዘርላንድስ የሚገኘው ዓለም አቀፍ የጦር ወንጀል ተመልካች ፍርድ ቤት የአፍሪቃ ህብረት አባል ሀገራት መሪዎች በአዲስ አበባ ባለፈው ሰኞ ጉባኤአቸውን ባጠናቀቀበት ጊዜ የሰነዘሩበትን ወቀሳ ውድቅ አደረገ።
ፍርድ ቤቱ ከትናንት በስቲያ ባወጣው መግለጫ የአፍሪቃ ህብረት ፍርድ ቤቱ የተነሳበትን ዓላማ በመሳት እና በዘረኝነት በመገፋፋት፣ ሆን ብሎ አፍሪቃውያንን ብቻ ዒላማ አድርጓል ሲል ያሰማውን ወቀሳ በማጣጣል የፍርድ ቤቱን ገለለተኛነት አስታውቋል። ህብረቱ ይህንን ወቀሳ የሰነዘረው ከኬንያ የ 2007 ዓም ፕሬዚደንታዊ ምርጫ በኋላ በሀገሪቱ በሰብዓዊነት ላይ ተፈፀሙ ባላቸው ወንጀሎች ምክንያት በአራት  የኬንያ ባለሥልጣናት ላይ በ ዘ ሄግ የተመሠረተው ክስ በኬንያ  ፍርድ ቤቶች እንዲታይ ለጉባዔው የቀረበውን ረቂቅ ሀሳብ ባፀደቀበት ጊዜ የወቅቱ የአፍሪቃ ህብረት ፕሬዚደንት የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚንስትር አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ ባሰሙት ንግግር ወቅት ነበር።
« ዘ ሄግ ኔዘርላንድስ የሚገኘው ዓለም አቀፍ የጦር ወንጀል ተመልካች ፍርድ ቤት በአሁኑ ጊዜ በአፍሪቃ የጀመረው ሂደት ስህተት አለበት። የፍርድ ቤቱ ዓላማ ወንጀል እና መጥፎ አገዛዝ ካለቅጣት እንደማይታለፉ ማሳየት ነበር። ነገር ግን ሂደቱ አሁን በዘረኝነት ወደ ማደኑ አሰራር አዘንብሎዋል። »
በናይሮቢ የሚገኙት የሕግ ባለሙያ እና የፖለቲካ ተንታኝ ኦጂና ኦሽዋንግ ይህንኑ የህብረቱን ክስ የሚደገፍ ማስረጃ እንደሌለ እና ዓለም አቀፉ ፍርድ ቤት አፍሪቃዉያንን ሲከስ አፍሪቃዉያኑ ራሳቸዉ ተባባሪዎች ነበሩ ሲሉ  ነው ለዶይቸ ቬለ የገለጹት።
« ፍርድ ቤቱ በአሁኑ ጊዜ እየተመለከታቸው ካሉት ስምንት አፍሪቃ ጉዳዮች መካከል አምሥቱ በራሳቸው አፍሪቃውያኑ መንግሥታት ወደ ፍርድ ቤቱ የተመሩ ናቸው።  የሊቢያ፣ ኮት ዲ ቯር እና የሱዳን ጉዳዮች ብቻ ናቸው በተመድ የፀጥታ ጥበቃ ምክር ቤት ጥያቄ ወደ ፍርድ ቤቱ የተመሩት። በዚያን ጊዜ አንድም አፍሪቃዊ መሪ በዚሁ የፀጥታ ጥበቃ ምክር ቤት ጥያቄ አንፃር ድምፁን አላሰማም።  ሁለተኛ፣ በፍርድ ቤቱ እየታዩ ያሉት ወንጀሎች ጭፍጨፋን፣ ክብረ ንፅሕና መድፈርን እና አፍሪቃውያንን ስብዕና የነፈገበትን ወንጀል ይመለከታል። አንድ አፍሪቃዊ የሀገር መሪ ይህንኑ ሥልጣን እንደ ዕድሜ ልክ ሥልጣን ማየትም ሆነ፣ የሕዝብን ስብዕና ለመግፈፊያ ወይም ክብረ ንፅሕና ለመድፈሪያ ወይም ጭፍጨፋ ለማካሄጃ ሊጠቀምበት እንደማይችል ሊያውቅ ይገባል።  ይህን በማድረጉ ቢከሰስ ግን ሂደቱ ዘረኝነት ነው ይላል። ይህ  ፍፁም ስህተት ነው።»
አይ ሲ ሲ የኬንያን  ጉዳይ መከታተል የጀመረው ኬንያ ለ 2007 ቱ ድህረ ምርጫ ሁከት ተጠያቂ ተብለው የተጠረጠሩትን  ጉዳይ የሚመለከት ልዩ ፍርድ ቤት ለማቋቋም ፈቃደኛ ባለመሆንዋ ነበር። በኬንያ ምርጫ ወጤት ሰበብ የተወ,ዛገቡትን ተቀናቃኝ ወገኖች  የሸመገሉት የቀድሞው የተመድ ዋና ፀሐፊ ኮፊ አናን በወንጀል ተጠረጥረዋል የተባሉ ኬንያውያን ፖለቲከኞችን ስም ዝርዝር  ለአይ ሲ ሲ ማስረከባቸው የሚታወስ ሲሆን፣ ዝርዝሩን ያገኙት ከኬንያ መንግሥት አካላት እንደነበር  የሕግ ባለሙያው እና የፖለቲካ ተንታኙ ኦጂና ኦሽዋንግ አመልክተዋል።
የቀድሞው የኮት ዲቯር ፕሬዚደንት በአይ ሲ ሲ
« ኮፊ አናን ለአይ ሲ ሲ ያስረከቡትን ዝርዝር ያዘጋጀው በዚያን ጊዜ የከፍተኛው የኬንያ ይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤት ዳኛ የመሩት ብሔራዊ ኮሚሽን ነበር። ኮሚሽኑ ከኬንያ ስለላ ድርጅት እና ፖሊስ መኮንኖች፣ እንዲሁም፣ ሌሎች ግለሰቦች ነው ማስረጃውን  ያገኘው። ምርመራውን ያካሄዱት እና ዝርዝሩን ያሰረከቡት አውሮጳውያን ወይም አይ ሲ ሲ አልነበሩም። ምክር ቤቱ ልዩ ፍርድ ቤት አላቋቁምም ከማለቱ ጎንም፣ ምንም እንኳን እነዚህ ወንጀሎች በኬንያም እንደ ወንጀል ቢታዩም፣ በሀገሪቱ ያሉት ፍርድ ቤቶች እና የዓቃቤ ሕግ ጽሕፈት ቤት ጭምር አንዳችም ርምጃ አልወሰዱም። የዘር ማጥፋት፣ ክብረ ንፅሕና መድፈር፣ መኖሪያ ቤቶችን እና ሰዎችን ማቃጠል፣ እነዚህ ሁሉ ኬንያ ውስጥ እንደ ወንጀል ነው የሚቆጠሩት። እና ልዩ ፍርድ ቤት ማቋቋም አያስፈልግም ነበር፤ ዓቃብያነ ሕግ ራሳቸው ጉዳዩን ሊከታተሉት ይችሉ ነበር። »
ኦሽዋንግ እንደሚሉት፣  አይ ሲ ሲ የምስክሮችን ደህንነት ለመከላከል እና የሁከቱ ሰላባዎች ፍትሕ ይኖራል ብለው እምነት እንዲያድርባቸው ሲል የተጠርጣሪዎቹ ኬንያውያን ስም ዝርዝር እንደቀረበለት ተጠርጣሪዎቹን በዚያን ወቅት ወዲያውኑ በቁጥጥር ሥር ማዋል ነበረበት። ይህን አለማድረጉን ስህተት ነው ያሉት ኦሽዋንግ አሁን ተጠርጣሪዎቹ ወይም የተከሰሱት ሰዎች በአነፃራቸው የምስክርነት ቃል የሚሰጡት ሰዎች ተከላካዮች ሆነው መቅረባቸው የምስክሮች መካላከያ አውታርን ትርጉም አልባ ከማድረጉ ጎን የኬንያ ድህረ ምርጫ ሰለባዎች በፍትሑ ላይ  እምነታቸው  በየቀኑ እየቀነሰ እንዲሄድ ምክንያት ሆኖዋል ሲሉ ኦሽዋንግ ወቅሰዋል።
አርያም ተክሌ
መሥፍን መኮንን
- See more at: http://satenaw.com/amharic/archives/4817#sthash.XPx0OcwJ.dpuf

Friday, February 20, 2015

ከፍትፍቱ አጉሩሱኝ ከመረቁ ፆመኛ ነኝ – Biniam Gizaw ( Norway Oslo)                   

        
የብዙሀኑ  የጣት ሽታ  እንደገደፈ ያሳብቃል። በጥቂትም ሆነ በብዙ ያልተነካካ ቢፈለግ በግራም ሆነ በቀኝ ቢነፍስሙን ያላፈረሰ ማግኘት አልተቻለም።ከፍትፍቱ አጉሩሡኝ ከመረቁ መኛ ነኝ ብሎ እንክት አድርጎ ከሰለቀጠ ወዲያምንም  እንዳልገደፈ አፉን ጠረግ ጠረግ አድርጎ ባላየ ባልሰማ የሚጓዘው ተበራክቷል።  በዕንዶድም የማይነፃ ጣትከምን አይነት መረቅ ውስጥ ቢዘፈቅ ይሆን ? . . . ጠቢቡ ሠሎሞን በምሳሌው . . .  ስጦታ በስውር ቍጣን ታጠፋለች፥የብብትም ውስጥ ጉቦ ጽኑ ቍጣን ታበርዳለች ያለው ትዝ አለኝ በተለይ ደግሞ የኢትዮጵያን የባለስልጣን ቢሮዎችንሳስባቸው ምን ቢያምራቸው እንኳን  ምራቃቸውን ገርገጭ አርገው ውጥው ስርዓቱ እና ህጉን በማክበር ፆሙ ምንአለ?  ሁሉም ቢሮ ስጋ ስጋ ደም ደም ነው የሚሸተው። !
  
            ትምህርት ሚኒስቴር፣ ጤና ጥበቃ ሚኒስቴር  ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር  ፍትህ ሚኒስቴር፣ ፌዴራል ፖሊስ  ወህኒ ቤት፣ ሆስፒታል፣ ባንክ ቤቶች፣   . . . መጥቀስ እስኪታክት ድረስ ሁሉም በዋና ዋና  የሀጢያት አበጋዞች ተዘፍቀዋል። በተለይም በወያኔ ዘመን ያለቅጥ ተንሰራፍቶ የሚገኘው  ብዙ በደለኞችን ፃድቅአድርጎ ፍርድን እና ፍትህን በማጣመም አይን የሚያስውረው በሽታ   ምድሪቷን ጠፍንጎ ከመግቢያው የግሙሩክ መስሪያቤት ጀምሮ እስከመውጫው ኢሚግሬሽንድረስ በጉቦኝነት ጠፍንጓታል። በኢትዮጵያ ውስጥ ወያኔ እስካለ ድረስ ሀቀኛ ነኝ አልነካካም  ብትል እንኳን ብዙም ሳትሔድ በቀላሉ በጥንቃቄ እያሽከረከርክበምትነዳበት መንገድህ ላይ የሸሚዙ ቁልፍ እስኪፈናጠር በላይ በላይ የሚበላው ትራፊክ ፖሊሱ እቁብ ስለደረሰበት ብቻ ፊሽካውን ነፍቶ ሲያስቆምህ ከመንጃ ፈቃድህይልቅ የመቶ ብር ኖቶችን ማዘጋጀቱ ብቻ ነው መገላገያ መንገዱ።በቃ ፃምህን ያስገድፉሐል።  በዚህ ውስጥ ያልተነከረ እና ያልተዘፈቀ  እጁን ያሳይ? . . . የተነከረበትከሩቅ የሚሰነፍጠው መረቁ ምስክር ነው  በጉቦ መረቅና  በሙስና የተዋዛ ጣት !

                       እጅ የሚስቆረጥም የፍትፍት ጉርሻ ፅኑ ቁጣን እንደምታበርድ  የንፁሐንን ቃል እና ፍርድ በጉቦ ተጣሞ  ለማይገባቸው ሲፈረድላቸው ማየት አዲስነገር አይደለም። በተለይም ድንገት አዲስ እንደተወለደ ህፃን ከዚህ በፊት ሳይታዩ ከባዶ ካፒታል ላይ ተንደርድረው ከናጠጠ ሀብት ጋር ብቅ የሚሉት ቱጃሮችየሀብታቸው ምንጭ ከየት እንደፈለቀ ለማወቅ ግልፅ ሆኖ ሳለ ከባለስልጣናቱ ጋር በመሞሳመስ የሚያደራጁያቸው የተለያዩ የንግድ ሂደቶችም በፌደራሉ ስነ ምግባር እናፀረ ሙስና ኮሚሽን ምንም አይነት ክትትል  ሊደረግባቸው የማይችልበት  ዋናው ምክንያት ባለስልጣናቱ ከላይ እስከታች እያንዳንዱን ተጠያቂ ስለሚያደርጋቸው እናክትትል አድራጊውም ሆነ ድርጊቱን ፈፃሚው ከአንድ ወንዝ የተቀዱ ስለሆኑ ነው። ቢሆንም የኢትዮጵያ ህዝብ የስልጣኑ ባለቤት ሆኖ ይህ አገዛዝ ለፍርድእስከሚቀርብበት ጊዜ  ድረስ  አንድነትን በመጠበቅ በፅናት እና  በትዕግስት ለሐገሪቷ ነፃነት እየታገሉ መቆየት የእያንዳዳችን ድርሻ ሊሆን የተገባ ግዳጃችም ነው።

                      እያልኩ ያለሁት ለምን ሰው ባለጠጋ ሆነ አይደለም። ይልቁንም የፖለቲካን የበላይነት እና ባለስልጣን መሆንን ተገን አድርጎ የሚደረግ  የሀገርን  ሀብትየመዝረፍ ወንጀል ከአውራነቱ የተነሳ  በምድሩም ሆነ በሰማይ  በሚሰየመው ችሎት እንደሚያስጠይቅም ለማሳሰብ ጭምር እንጂ። በተጨማሪም በኢትዮጵያ ከተከሰቱትታላላቅ መፍትሔያቸው የራቁ የኑሮ ቀውሶች መካከል ለሰው ልጅ መኖር መሰረታዊ  የሆኑትን ብቻ    ለመገብየት ከዋጋው ግሽበት የተነሳ የሀገሪቱ የገንዘብ ጉልበት  እጅግ ደቃቃ  ሆኖ አቅም የለሽ በሆነበት፣ ስራ አጥነት ተበራክቶ ብዙሀን የወጣቱ ክፍል ህይወቱን ያጣበት የበረሀ ጉዞ እና በባህር ሰጥሞ አስከመቅረት  ዋጋየሚይስከፍሉ የስደት አይነቶች ህዝብ እንዲጋለጥ፣ ወላጅ እየተጦረ እፎይ ብሎ በሚያርፍበት የሽምግልና ዘመኑ ለልመና ሰው ፊት የቆመበት እንዲሁም በብዙ ምሬትውስጥ በመሆን ለተጎነበሰበት እና በምድሪቷ ላይ ከሊቅ እስከ ደቂቅ ሙስና ባህል እስኪመስል ድረስ በእጅጉ ተንሰራፍቶ ጥላውን እንዲያጠላ እና እንዲባባስ ገዢውድን ከፍተኛ ሚና ተጫውቷል። እየተጫወተም ይገኛል። አምባገነናዊነት፤ እብሪት፤ግትረኛነትና ትምክህተኛነት በከባድ የተጠናወተው ቡድንተኛ መሪ የሃገሪቱንምሆነ የህብረተሰቡን አንጋፋ ችግሮች በጋራ ተመካክሮ፤ የፖለቲካ ስልጣንን በመካፈል  የሕዝቡን ድምጽ አክብሮ፤ በተለይ ሀገር ተረካቢውን ወጣቱን ትውልድ ፍላጎትለማሟላት በሁሉምየሀገሪቱ አቅጣጫ  በእኩልነት ለመስራት የተዘጋጀ አይደለም። አቅሙም ልቡም የለውም። ይልቁንም የአብዛኛው ህብረተሰብ የኑሮ ሁኔታ ወደማጡ አባብሶታል። ይህ የአንድ ብሔር ብቻ ወገንተኛ  የፖለቲካ ብድን  የኢትዮጵያን ህብረተሰብ እና የተለያዩ ብሔሮችን ግልፅ በሆነ አሰራር ሳያካትት የሀገሪቷንአንድነት  ባልጠበቀ ዘመቻው በአደገኛ ሁኔታ በሙስና እና በተለያዩ ጤናማ ባልሆኑ አካሄዶቹ የህዝቡን ኑሮ ከስሩ አናግቶታል። የጉቦኛነት ተስቦ ሳያንሰው ከሁሉምበላይ አዲሱ ትውልድ በኢትዮጵያዊነት ሳይሆን በጠባብ ጎሰኛነት  እንዲያምን በሚያደርገው ርብርብ ኢትዮጵያዊነት ከቶውንም ተሽሮ ብሔርተኝነት እንዲያብብ  የማያቋርጥ ተጋድሎ እያደረገም ጭምር ነው። የሙስናው እንቅስቃሴ እና  ተግዳሮት  ለሀገርና ለህዝብ ጠንቅ መሆኑ አለም ሁሉ የሚስማማበት ስለሆነም በተለይም ደግሞ ሰላም በሰፈነባቸው  ሀገሮች ይህ ድርጊትእንደ ትልቅ ውርደት የሚታይ እና በአንዳንዶች ዘንድ ፈፅሞ የማይታወቅ ተልካሻ ስርዓት ነው። ዛሬ የስቃይ ኑሮ ገፈት ቀማሽ ያደረገን ወያኔ ከፅንሰቱ ጀምሮ እጁከሙስና ሳይፆም የረከሰ በመሆኑ ምክንያት አባላቱን እንኳን ሲመለምል ቀድሞውንም ስለ ኢትዮጵያ በመቆም ለትግሉ በእውነተኛነት አሳምኖ ሳይሆን በፍቅረ ንዋይየተቃጠሉትን በማማለል ከድል ማግስት የሚገኘውን ሀብት በማለም ብቻ እንደሆነ ግልፅ ነው፡፡ ለዚህም ነው ዛሬ በሀገራችን የተማረው  ክፍል በሙያቸው፣በዲግሪያቸውም ሆነ በልምድ እውቀታቸው ሰርተው ሀገር የሚያለሙበት  መንገዱ ሁሉ ቢዘጋጋባቸው ለመኖር ሲሉ የግዳቸውን ከባለስልጣናቱ ጋር የተለያየ አይነትየሙስና መንገዶችን ለማጠቀም የሚገደዱት።

                      በኢትዮጵያ ከኖርክ በብዙም ሆነ በጥቂቱ ለመኖር ስትል ጉቦ ትሰጣለ ወይም ታበላለህ። በዕጅ ማለት ብርቅ አይደለም። ከዘበኛው ጀምረህ ባለስልጣኑንእስክታገኘው ድረስ ሁሉን እያጉረስክ ማለፍ የግድ ነው። ለምሳሌ የገንዘብ ተመን ከወጣላቸው ጉቦኝነት መሀከል የመኪና መንጃ ፈቃድ ለማውጣት የሚከፈለው ክፍያነው። ካልሰጠህ መንጃፍቃድ የምይታሰብ ጉዳይ ነው  ሊያውም ዳጎስ ያለ እንደሆነ ደግሞ ያሉበት ድረስ ይመጣልዎታል። ይህም ሂደት ሀገሪቷን ለከፍተኛ የመኪናአደጋ አጋልጦ ሰጥቷታል። በመሬት ንግዱ ዙሪያ እና የፃድቁን ውሳኔ ለማጣመም በፍርድ ቤቶች   የሚከፈሉት የዳጎሱ ጉርሻዎች ሐገር ሁሉ የሚያውቀው ራቁትነትነው። የተማረው፥ፊደል የቆጠረው በደጅ ሆና ተስፋ ቆርጦ ሲማረር እና ፀሀይ ሲበላው ሌላው ዘሩን ጠርቶ የግንባሩን ምልክት አሳይቶ ለምሁሩ የተዘጋበትን በርአስከፍቶ ዘው ይልበታል። ለዚህ ሁሉ ውድቀት ዋናው  ምክንያቱ  ባለቤት እና እውነተኛ መሪ በሌላት ሀገር ላይ  የመንግስት ተቋማት ከፍትፍቱ አጉሩሱኝ ከመረቁ መኛ ነኝ በማለት ሳይነክሱ መኖር አቅቷቸው ለሙስና በመዘፈቃቸው ብቻ ነው፡፡
      
                ጉቦኝነት ሁሉን ዳሶታል  ፈተናውን ሁሉ ለመለፍ ወይ ገንዘብ አሊያም እንደ ባለስልጣናቱ  ጥያቄ መሰረት ፍላጎታቸውን ማርካት የተለመደ ቢሆንም ይህንሀገርን ወደኋላ የሚጎትት አሰራር ከስሩ ለማድረቅ ኢትዮጵያውያን የሆንን ሁሉ ለሀገራችን ነፃ መውጣት የምንከፍለው ሌላ ክፍያ አለ። በሁሉ አቅጣጫ አንድነታችንንበማጉልበት ለወያኔ አገዛዝ በእንቢተኛነት መጋፈጥብሔር ከሀገር አይበልጥምና  የጎሰኝነትን እና የብሔርተኝነትን የመለያየት መርዝ አርክሰን በአንድነት መቆም!

  ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር።  
  ቢንያም ግዛው (ከኖርዌይ ኦስሎ)