Sunday, May 31, 2015

FINOTE DEMOCRACY VOICE OF ETHIOPIAN UNITY RADIO  ርዕሰ ዜናዎች


  • የወያኔ የምርጫ ድራማ ውጤትን ተቃዋሚዎች አንቀበልም እያሉ ነው
  • ወያኔ በጦሩ ውስጥ ስነልቦናዊ ማጭበርበር እያደረገ ነው፤
  • ተቃዋሚዎችን ማስፈራራትና ማሳደድ የወያኔ ግብ ሊሆን ነው
  • እስራኤል የኤርትራና የሱዳን ስደተኞችን ወደ ሶስተኛ አገር ልታባራር ነው
  • በሳዑዲ የሚመራው የኅብረት ኃይል በየመን እያካሄደ ያለውን የአየር ድብደባ ቀጥሏል
  • በማእከላዊ አፍሪካ ሪፐብሊክ ወታደሮቻቸውን ያሰማሩ አገሮች ሰላማዊ ሰዎችን በወሲብ ማስገደዳ ግድያ ማካሄድ የሚለውን ክስ ለማጣራት ርምጃ እንዲወስዱ የተመድ የሰብአዊ መብት መሪ ገለጹ
  • በሰሜናዊ ማሊ የታጠቁ ኃይሎች እርስ በርሳቸው ባካዱት ጦርነት በብዙ ሺ የሚቆጠር ሕዝብ ተፈናቀለ


  • በሳኡዲ የሚመራው የህብረት ኃይል በየመን ላይ እያካሄደ ያለውን የአየር ድብደባ የቀጠለ ሲሆን ዛሬ ቅዳሜ ጠዋት በዋናው ከተማ በሳናዕ የሚገኘውን የቀድሞውን ፕሬዚዳንት የሳላህ አብዱላህ ሳላህን መኖሪያ ቤት በመደብደብ ከጥቅም ውጭ ያደረገው መሆኑ ታውቋል። የአየሩ ድብደባ በቀድሞ ፕዚዳንቱ ቤት ላይ የተካሄደበት ምክንያት የቀድሞው ፕሬዚዳንት ሁቲዎችን መተባበርና መደገፍ ካቆሙና ሁቲዎችን ከተቃወሙ ብዙ ሚሊዮን የሚቆጠር ዶላር በመስጠት የሳኡዲ ባለስልጣኖች ለመሸንገል የሞከሩ መሆናቸውንና እሳቸውም እምቢ ማለታቸውን በትናንትናው ምሽት ለአንድ የቢይሩት ቴሌቪዥን በሰጡት ቃለ ምልልስ በይፋ በማጋለጣቸው ነው የሚል ግምት አለ። የቀድሞ ፕሬዚዳንት ቤታቸው ውስጥ ባለመኖራቸው በህይወት የተረፉ ሲሆን በመጨረሻ የተካሄደው የአየር ድብደባ አማጽያኑ በሚቆጣጠሩት የመንግስት መስርያ ቤቶች ላይና እንዲሁም መሳሪያና ጥይት ማከማቻ ዴፖዎች ላይ የተካሄደ መሆኑ ታውቋል። የነዳጅ ዘይት በሚገኝበት ማሪብ በተባለው በምስራቃዊ ግዛትም የአየሩ ድብደባ ቀጥሎ ውሏል። የአየሩ ድብደባ የተካሄደው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሰላም ልዑካን በስናዕ የሚገኙ ባለስልጣኖችን ለማነጋገር ከተማ ውስጥ በገቡ በሰዓታት ውስጥ መሆኑን የዜና ምንጮች ተናግረዋል። በየመን የእርስ በርስ ግጭት ከተፈጠረ ጀምሮ ከ2000 በላይ በግጭቱ እንደሞቱ ሲነገር በርካታዎች መቁሰላቸውና በብዙ ሺ የሚቆጠሩ ደግሞ የተሰደዱ መሆናቸው ተዘግቧል።
  • የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሰብአዊ መብት ጉዳይ ኃላፊ በማእከላዊ አፍሪካ ሪፐብሊክ ወታደሮቻቸውን አሰማርተው የሚገኙ አገሮች ወታደሮቻቸው በአገሬው ዜጋ ላይ አስገድደው የወሲብ ድርጊት ይፈጽማሉ ግድያም ያካሄዳሉ የሚሉ በሰፊው እየቀረቡ ያሉ ክሶችን መመርመርና ጥፋተኞችን ለፍርድ ማቅረብ አለባቸው የሚል ጥያቄ አቅርበዋል። ባለፈው ጊዜ በማዕከላዊ አፍሪካ የሚገኙ የፈረንሳይ ወታደሮች እነዚህን ወንጀሎች ፈጽመዋል ተብለው ከተወነጀሉ በኋላ ተመሳሳይ ክሶች በአገሪቷ ውስጥ በተሰማሩ የሌሎች አገሮች ወታደሮች ላይም ቀርቧል። 14 የሚሆኑ የፈረንሳይ ወታደሮች በወንጀሉ ተጠርጥረው ምርመራ እየተካሄደባቸው ሲሆን የሌሎች አገሮች ወታደሮችም ተመሳሳይ ድርጊት መፈጸማቸውን የሚያጋልጥ ዘገባ የደረሳቸው መሆኑን የተመድ የሰብአዊ መብት ጉዳይ ኃላፊ ገልጸዋል። 
  • በሰሜናዊ ማሊ የሚገኙ የታጠቁ ሃይሎች ባካሄዱት የርስ በርስ ውጊያ በ10ሺዎች የሚቀጠሩ ነዋሪዎች ቀያቸውን ጥለው የሸሹ መሆናቸው ታወቀ። የተባበሩት መንግስታት የስደተኞች ጉዳይ አርብ ለት እንዳስታወቀው በሰሜን ማሊ በታጠቁ ቡድኖች መካካከል በተፈጠረው ግጭት 60 ሺህ የሚሆኑ ነዋሪዎችን ከቦታቸው እንዲሸሹ ማድረጉንና እየተባባሰ የሄደው ቀውስ በተባበሩት መንግስታት ድርጅት አነሳሺነት የተጀመረውን የሰላም ጥረት ሊያበላሸው ይችላል የሚል ስጋት አለ ብሏል። ባለፈው ዓመት በመንግስት እና በሰሜናዊ ማሊ በሚንቀሳቀሱ ተገንጣይ ሃይሎች መካከል የተኩስ ማቆም ስምምነት መደረጉ የሚታወስ ሲሆን የመንግስቱ ደጋፊ ሃይሎች ሚናካ የተባለውን አውቅ ከተማ ባለፈው ወር መያዛቸው ቀውሱን አንዳባበሰው ምንጮች ዘግበዋል።
  • የሴቶች ግርዛትን በመከልከል ናይጀሪያ ያወጣችውን አዲስ ህግ ጎጂው ባህል እንዲቀር ትግልና እንቅስቃሴ ሲያደርጉ የነበሩ በርካታ ዜጎች የደገፉት ሲሆን ህግ ማውጣት በራሱ በቂ እንደማይሆንና ድርጊቱን እንደማያስወግደው ግን ማስጠንቀቂያ የሰጡ መሆኑ ታውቋል። የናይጄሪያው የጉድለክ ጆናታን መንግስት ስልጣኑን ለአዲሱ ፕሬዚዳንት ከማስረከቡ በፊት ካከናውናቸው መሰረታዊ ተግባሮች መካከል ይህን መጥፎ ባህል በህግ ማገድ ነው። በ2014.ም የተባበሩት መንግስታት የጥናት መረጃ ከናይጀሪያ ሴቶች መካከል ሩብ የሚሆኑት የብልታቸው የውጭ ክፍል መቆረጡን ጠቅሶ በዚህ ምክንያት እነዚህ ሴቶች ለአካልና ለስነልቦና ችግር ሊጋለጡ የቻሉ መሆናቸውን አስታውቋል። በዓለም ላይ 125 ሚሊዮን የሚሆኑ ሴቶች በተመሳሳይ መልክ ከሚመጣ በሽታ የሚሰቃዩ መሆናቸውን ዘገባው ገልጿል።፡ከዚህ ጋር በማያያዝ ቻሪቲ ኢኳሊቲ (Charity Equality) የተባለው ግብረሰናይ ድርጅት ተወካይ ግሬስ ኡዊዚ፣ ህጉ ማህበረሰቡን ከድርጊቱ ወዲያውኑ እንደማያስቆመው ተናግረው አዲሱ ህግ ተግባራዊ እንዲሆን ለማድረግ በጠንካራ ህግ አስፈፃሚ እርምጃ መደገፍ ይኖርበታል በማለት አሳስበዋል።

የአዉሮጳ ኅብረትና የስደተኞች ጉዳይ

የአዉሮጳ ኅብረትና የስደተኞች ጉዳይ

የአዉሮጳ ኅብረት ጣሊያንና ግሪክ የገቡ ስደተኞችን ወደተለያዩ አባል ሃገራት የማስፈር እቅድ ነድፏል። ወደአዉሮጳ ለመግባት የሚያልሙ ስደተኞች የሚሸጋገሩባቸዉ ግሪክና ጣሊያን ችግሩ ከአቅማቸዉ በላይ መሆኑን መናገር ከጀመሩ ሰንብተዋል።የአዉሮጳ ኅብረት በስደተኞች የተጥለቀለቁትን ሁለቱን ሃገራት ባስቸኳይ መተባበሩ ጊዜ ሊሰጠዉ እንደማይገባ ያሳስባል። የኅብረቱ ሀሳብ ግን የሁሉንም አባል ሃገራት ስምምነት ያገኘ አይመስልም።
ወደአዉሮጳ የገባ ተሰዳጆች ጠያቂ በኅብረቱ ዉል መሠረት መጀመሪያ እግሩ በረገጠበት ሀገር ነዉ ጥገኝነት መጠየቅ የሚችለዉ። በሜዲትራኒያን ባህር ላይ እስካሁን የቀጠለዉ የስደተኞች ፍሰት አሁን ኅብረቱ የቀድሞ መመሪያዉን እንዲያሻሽል ያስገደደዉ ይመስላል። የአዉሮጳ ኅብረት ለመጀመሪያ ጊዜ መሆኑ ነዉ በኅብረቱ ስምምነት ዉስጥ አዲስ አንቀጽ ለመጨመር ሲወስን። አዲሱ አንቀጽም የአስቸኳይ ጊዜን ይመለከታል። ይህም ወደአዉሮጳ የገቡ ስደተኞችን ወደተለያዩ የኅብረቱ አባል ሃገራት ተከፋፍለዉ ጥገኝነት እንዲያገኙ የሚፈቅድ ነዉ። በአሁኑ ጊዜ ጣሊያንና ግሪክ ወደአዉሮጳ ለመግባት ባላባራዉ የስደተኞች ጎርፍ ተጥለቅልቀዋል። 
Belgien EU-Kommission beschliesst Quotenplan für Flüchtlinge
የኅብረቱ ኮሚሽነር ዲሚትሪስ አቭራምፖሎስ
ማልታም ለረዥም ጊዜያት የስደተኞች መዳረሻ በመሆኗ ስትቸገር ቆይታለች። አዲሱ የኅብረቱ አንቀጽ አሁን ትኩረቱ ጣልያንና ግሪክን ያስጨነቁትን ጥገኝነት ጠያቂዎች ወደተለያዩ የኅብረቱ ሃገራት አከፋፍሎ የሁለቱን ሃገራት ችግር ለማቃለል ያለመ ነዉ። የኅብረቱ ኮሚሽነር ዲሚትሪስ አቭራምፖሎስ ይዘረዝራሉ፤
«40,000 ጥገኝነት ፈላጊዎችን ወደሌሎች ሃገራት ለማስፈር የሚያስችል የአስቸኳይ ጊዜ እቅድ አለን። በሁለት ዓመታት ዉስጥም ሶርያዉያንና ኤርትራዉያን ከጣሊያንና ግሪክ በተለያዩ የአዉሮጳ ሃገራት እንዲሰፍሩ ይደረጋል።»
ሆኖም ሃሳቡን እንደማርቀቁ ተግባራዊነቱ ቀላል አይደለም። የኅብረቱ ባለስልጣናት አባል ሃገራቱ ሃሳቡን እንዲቀበሉት ለማግባባት ብዙ ሥራ ይጠብቃቸዋል። ብሪታንያ፤ ዴንማርክ፣ እንዲሁም አየርላንድ በኅብረቱ ዉስጥ ያላቸዉን ልዩ መብት ተጠቅመዉ ከአስቸኳይ ጊዜ እቅዱ ራሳቸዉን ማግለል ይችላሉ። ፈረንሳይ፤ ስፔን፣ ሀንገሪ፣ ፖርቱጋል፣ ቼክ ሪፑብሊክ፣ የባልካን ሃገራት እና ስሎቫኪያ ተገን ጠያቂዎቹን በዉስን ኮታ መቀበል እንደማይፈልጉ ይፋ አድርገዋል። ኮሚሽነር አቭራምፖሎስ ግን ለስደተኞች ጥገኝነት የመስጠቱ ዉሳኔ ከኮታ ጋ ግንኙነት እንደሌለዉ ያስረዳሉ፤
Libyen Migranten im Abu Salim Zentrum
«አንዳንድ በትክክል ያለመረዳት ወይም የአተረጓጎም ስህተቶች አሉ። በሕገወጥ መንገድ የመጡ ስደተኞችን በመላዉ የአዉሮጳ ኅብረት የማስፈር ሃሳብ የለም። የተወሰነ ኮታ ስለመኖሩም ሃሳብ አላቀረብንም። የማንወደዉና በፍፁም ያልተጠቀምነዉ ቃል ነዉ። ይህ ሁሉ አጋርነትን የማረጋገጥ ጉዳይ ነዉ። ያም ቢሆን ግን ለስንት ስደተኞች የጥገኝነት ማረጋገጫ መስጠት እንደሚችል መወሰን የሚችለዉ እያንዳንዱ አባል ሀገር ነዉ።»
ያም ሆኖ ሁሉም የኅብረቱ አባል ሃገራት የአዉሮጳ ኅብረት ኮሚሽን ባቀረበዉ ሃሳብ መሠረት ጥገኝነት ፈላጊዎቹን ለመቀበል አልተዘጋጁም። የአዉሮጳ ኅብረት ኮሚሽን በተቻለዉ አባላቱን ለማግባባት እየጣረ ነዉ። ጥገኝነት ጠያቂዎቹን ለሚቀበሉ ሃገራትም ከ6000 ዩሮ አንስቶ ጉርሻ እንደሚሰጥ ገልጿል። ቀደም ሲል ግን የኮሚሽነሩ ሠራተኞች አባል ሃገራት ባላቸዉ ስፋትና የኤኮኖሚ ጥንካሬ መሠረት ጥገኝነት ጠያቂዎቹን በኮታ እንደሚቀበሉ አመልክተዉ ነበር። እንዲህ ከሆነ ደግሞ ጀርመን በሁለት ዓመት ዉስጥ እስከ 8000 ስደተኞች መቀበል ይኖርባታል። የአረንጓዴ ፓርቲ የአዉሮጳ ምክር ቤት አባል ስካ ካለር ስደተኞቹን ለመቀበል ለረዥም ጊዜ የቆየዉ የኅብረቱ ዉል መስተካከል ይኖርበታል ይላሉ፤ 
Schweigeminute beim EU-Sondergipfel zur Flüchtlingspolitik
ሊቢያ ዉስጥ ለተገደሉት ስደተኞች የሕሊና ጸሎት 
«ጥገኝነት ጠያቂዎቹን ማከፋፈሉ የመጀመሪያዉ ርምጃ ነዉ። ሆኖም ጥገኝነት ጠያቂዎች የት መጠየቅ እንዳለባቸዉ የሚደነግገዉ የደብሊኑን መመሪያ ከመሠረቱ መለወጥ ይኖርበታል። ይህም እግራቸዉ በገባበት የመጀመሪያ የአዉሮጳ ግዛት የሚለዉ ማለት ነዉ። ይህ ደግሞ አሁን አይሰራም። ለረዥም ጊዜ ያየነዉ ጉዳይ ነዉ።»
እሳቸዉ እንደሚሉትም በተለይም የስደተኞቹ መዳረሻ የሆኑት የመጀመሪያዎቹ የአዉሮጳ ኅብረት ሃገራት በዚህ ረገድ ኃላፊነታቸዉም አልተወጡም። ለምሳሌ ሜዲትራኒያን ባህርን እያቋረጡ ወደጣሊያን ደሴቶች የሚመጡትን ተገቢዉን ምዝገባ ሳታካሂድ ወደሰሜን ታሳልፋቸዋለች በሚል ጀርመን ጣሊያንን ትወቅሳለች። የአዉሮጳ ኅብረት በ2ዓመት ዉስጥ ወደየአባል ሃገራቱ በማከፋፈል ጥገኝነት እንዲያገኙ ለማድረግ ካለመዉ ጣሊያንና ግሪክ ዉስጥ ከሚገኙት 40,000 ተሰዳጆች በተጨማሪ 20,000 ሶርያዉያንንም ከአዉሮጳ ዉጭ ከየሚገኙባቸዉ መጠለያ ጣቢያዎች እንደሚያመጣ ተገልጿል። ዉሳኔዉም እነኚህ ስደተኞች አዉሮጳ ለመግባት ሲሉ በሕገወጥ ሰዉ አሸጋጋሪዎች እጅ ወድቀዉ በአደገኛ መንገድ ሜድትራኒያን ባህርን ከማቋረጥ ለማዳን ነዉ። ኅብረቱ ከሀገር ሀገር ሰዉን በ ሕገወጥ መንገድ አሸጋጋሪዎቹን ለመቆጣጠር የባህር ላይ ጥበቃና ቅኝቱን ማጠናከሩን አስታዉቋል። 
በርን ሪገርት/ሸዋዬ ለገሠ
ኂሩት መለሰ

Saturday, May 30, 2015

እንጻፍ ካልንማ (4 )ከ ኢያሱ ዓለማየሁ

እንጻፍ ካልንማ (4)
"ስፈልግ ነኝ የሚል ኮርቶ የሚያኮራ  ልቤን አቆሰለው የነበርን ጫጫታ" ።
ከ ኢያሱ ዓለማየሁ
ታሪክ ቅርስ ነው። ያለፈውን በምጸት ወይም በመኩራራት ለማስታወስ ብቻ ሳይሆን ለብሩህና የተሻለ ነገን እውን ለማድረግ ለሚደረገው ትግል መሳሪያ ነው። አልያማ ትኩሱ ሬሳ ደረቁን አስረሳ ዓይነት ይሆንና አጼን ሙገሳ፤ ውድቁን ፋሺስት መናፈቅና ሊወገር የሚገባው ዘረኛና ነፍሰ ገዳይ ሲሞት ደረት ድለቃ ሊከተል ይችላል። ከወያኔ ጋር ተጣምሮ የመጣና የህዝብን ትግል የጎዳው አንዱ ክስተት ወይም ጽንሰ ሀሳብ ስልጡን ፖለቲካ የሚባለው ነው። ይህ አምርሮ መታገልን የሚተች አቅዋም በለሆሳስና በጩኸትም ሊያሰፍን የጣረው ፍርሃትን፤ ለጠላት መልፈስፍን፤ በባዕድ መተማመንን፤ እጅ መስጠትንና በአጠቃላይ ቀቢጸ ተስፋን ብልጠት ብልህነት አስመስሎ ማቅረቡ ነው። ወያኔ ስልጡን ፖለቲካን አፍቅሮ ቢገኝ የሚያስገርም አይደለም። ትግል አልበገር ያለውን የገዢዎች ምሽግ እናፈርሳለን የሚል መንፈስን ያቀፈና ሁሉም ጭራቆች ይወገዳሉ ባይ ሊሆን ሲገባው የሚቻል ፖለቲካ--ገና ሳይነሳ ራሱን የወሰነና ያሽመደመደ-- ስልጡን ተብሎ በመቅረቡ ትግላችንን ጎድቷል። ጣሊያን ኢትዮጵያን ሲወር ብዙ ነጮች በጦርና ጋሻ፤ በምኒሺር ደረጃ ታጥቀው የተሰለፉት አርበኞች ላይ ሞኞች ብለው እንደተሳለቁት ሁሉ ማለት ነው። ዛሬም ሆነ ዘገየ፤ ተፈለገም ተጠላም ግን የድል አብሳሪ ትግል ወያኔን በሀይል በአመጽ የሚያጠቃና እግረ መንገዱንም ስልጡን መሆን ሳይሆን ቆራጥነትና መስዋዕትነትን የሚጠይቅ መሆኑ አይቀሬ ነው። ጨዋነትና ባርነትን መቻል ተወራራሽ አይደሉም።
በአሁኑ ጊዜ በተለይም ከወያኔ ጋር የተደላደለ ኑሮና ይዞታ ያላቸው ክፍሎች ያለውን ትውልድ በመተቸትና በማውገዙ ላይ ማተኮራችው ይደመጣል። ሰዉ ሁሉ--ድሀው ከበርቴው-- የራሱን ኑሮ ለማሻሻል ነው የሚሯራጠው፤ ለሀገር ደግ ቢመኝም ጊዜ የለውም ይሉናል። ለራሳቸው መፋዘዝ ሕዝብን ተጠያቂ ሊያረጉ ይጥራሉ ማለት ይቻላል። እንደ ዱሮው አይደለም ሰዉም ሁኔታውም የሚል ማሳሰቢያም ሲሰጠን ቆይቷል። ይህን በተመለከተ ታሪክን እናንሳ ካልን የያኔው የተማሪ እንቅስቃሴ በመጀመሪያ የብዙሃን እንቅስቃሴ አልነበረም። የተወሰኑ ጽኑ መሪዎችና ታጋዮች ናቸው እንቅስቃሴውን ሊያጠናክሩትና ተደማጭነት/ተቀባይነት ሊያሰጡት የቻሉት። ግንባር ቀደም የነበሩት ዘጠኝ የተማሪው እንቅስቃሴ መሪዎች-- ሀይሉ ገብረዮሓንስ/ገሞራው/፤ ብርሃነ መስቀል ረዳ፤ ዘሩ ክህሸን፤ ሚካኤል አበበና ሊሎችም ከዩኒቨርስቲ ሲባረሩ እነሱ ካልተመለሱ ትምህርት አንገባም የሚል ተቃውሞ ተማሪው አላሰማም።
page1image14952 
በቀጣዩም ሰልፍ ሲደረግና ዩኒቨርስቲው ሲዘጋም ትምህምርት ለመቀጠልና ከተቃውሞው ለመራቅ የጣሩት ጥቂቶች አልነበሩም። ያ የጥቂቶች--የቆራጦች-- እንቅስቃሴም በጊዜ ሂደት ብዙዎችን ሊያሰባስብና ሊያቅፍ ችሏል። አንዳንዶች የያኔ ወጣቶችን የባዕድ ርዕዮት ተከታይ አድርገው በመፈረጅ ሊያወግዙ ብዙ ጥረዋል። በአንጻሩ ግን ሊበራሊዝም ወይም ካፒታሊዝምን እናፈቅራለን ሲሉ ይህ ርዕዮት በዋልድባ እንዳልተፈለሰፈ የምናውቅ አይመስላቸውም። ዛሬ ያ የፈረደበትን ዋለልኝ ኢትዮጵያዊነቱን ሊቀሙት፤ ሀገር ብሎ አፍቅሮና ቆርጦ የሞተላትን ሀገር ከዳ ሊሉ የሚከጅሉት ሁሉ ጥያቄው እናንተስ ያኔ የት ነበራችሁ ቢባሉ የሚያኮራ መልስ የሚሰጡ እለመሆናቸውን የምናውቀው ነው። ወደ ቁም ነገሩ ለመመለስ ግን ዛሬም ወጣቱ ትውልድ አርአያ የሚሆነውና የሚያታግለው ካለ ለሀገሩና ለወገኑ የሚታገልና የሚሰዋ መሆኑን በየጊዜው አሳይቷል። የሚያሳዝነው ትግሉን እንመራለን የሚሉት ብቁ አታጋይ ሊሆኑ አለመቻላቸው ነው። የታገለውን ትውልድ ታሪክ የሚከልሱና የሚያቆሽሹ መብዛታቸው ነው ብንል ስህተት አይሆንም።
ትግል ስለተባለ ብዙሃኑ ሆ ብለው በሰልፍ አይገኙም። ብዙ ጥረትን ይጠይቃል፤ ሰውን ማደራጀት ማሰባሰብ፤ ያ ግዙፍ ሊሆን የቻለው የተማሪዎች የወጣቶች እንቅስቃሴ በመጀመሪያ ሰሞኑ የጥቂቶች እንቅስቃሴ ነበር። ከታጋዩ ዝምተኛውና ተቃዋሚውም ይበዛ ነበር። ዩኒቨርስቲው አስተዳደር/ለአሜሪካ ያደሩና የተደራጀውን ሊያፈርሱም አምርረው የታገሉ ነበሩ። እዚህ ላይ ነው የጽናትና የመደራጀት ጉዳይ ብቅ የሚለው። ጽናት በመኖሩም፤ የመደራጀትን ተግባር በቀላሉ ስላልተያዘ ትግሉ የሚጠይቀውን ዋጋ ሊከፍሉ ዝግጁ የሆኑ ወጣቶ በመኖራቸውም እንቅስቃሴው ሊስፋፋምና ሊጠናከር ቻለ። ዛሬም አርአያ የሚሆኑ መሪዎችና ድርጅቶች ከተገኙ ወጣቱ እናት ሀገሩን ሊታደግ ና ሊሰዋላት ዝግጁ መሆኑ የሚያጠራጥር አይደለም። ወያኔ አዲስ አበባ ሲገባም፤ ግንጠላን ሲያጅብም፤ በ1997 ምርጫና ከዚያም በኋላ ወጣቱ ቁርጠኛነቱን አሳይቷል። በ ጸረ ወያኔ ትግል ተካፍሏል። ሸብረክ ያለው ወጣቱ ሳይሆን የተቃዋሚ ድርጅት መሪዎች ነን ያሉት ግለሰቦች ናቸው። በአሁኑ ጊዜ ድርጅት ከቶም አያስፈልግ የሚሉና በዚያው አፋቸው ደግሞ የትግሉ መሪ ሊሆኑ ሲከጅሉ የሚሰሙ እንዳሉ መዘንጋት የለብንም። ከሕዝብ ትግል ተመክሮ መማር ያቃታቸው ብንል ትክክል ነው።
        የነበረ ሁሉ ስለነበረው የሚያወሳው ሙሉ በሙሉ ሀቅ ነው ብሎ መደምደም ባይቻልም ቢያንስ በቦታው የተገኘውንና በስማ በለው ደረጃ የሰማውን ሀቅ ብሎ የሚያቀርበውን በአንድ ማየት አይቻልም። ኢሕአፓን በተመለከተ ሊያጠቁት ፈላጊዎች ጥቂት ስላልሆኑ ታሪኩ ብለው ሲያቀርቡ ብዙዎቹ ስለምን እንደሚጽፉ ማወቅ አይቻልም። ከበሬ ወለደ ባሻገር የሚፈጥሩትም ትረካ ሀሰተኛ ምስክር ጉልበት ይሰብር የሚያሰኝባቸው ነው። የኢሕአፓን የፖለቲካ መርሃ ግብር መጀመሪያ ያየው ሳዳም ሑሴን ነው ሲል አንዱ ምሁር በይፋ ከሶ ነበር -- አሜሪካን ያሳስብ ካልሆነ ከሀቅ ግንኙነት የለውም። የኢሕአፓ የፖለቲካ ፕሮግራም በ1967 በ አማርኛና ሌሎች የሀገር ቋንቋዎችና በእንግሊዝኛ ወዘተ የተሰራጨው በቅድሚያ በመላ ኢትዮጵያ ነው። የድርጅቱ መርሃ ግብር በአረቦች ተጻፈ ያለም ሀፍረተ ቢስ ነበር። ከዋሹ አይቀር ይቀደዱ ነው ነገሩ። ተነግሮ የማያልቅ ውሸት ተዋሽቷል -- ደካማና አላዋቂዎችንም አታሏል። ወያኔም ይጠቅመኝ ብሎ አራግቦታል፤ መድረክንም ለግሷል። ማማት የለመደ አፍ ሲዶልት ያድራል ብለዋል አዛውንት። ለገበያ የሚያመች ስለሆነም ኢሕአፓ ብለው ሶምሶማ መርገጥ ሳይሆን ላጥ ብለው ሲሮጡ ይሉኝታ የሚባል ልጓም ያዝ አያደርጋቸውም። ምስክር የጠፋም ይመስል የማይዋሹት የለም። መሰከርን፤ ምስጢሩን አሰጣነው፤ ዕንቆቅልሹን ፈታነው፤ ሲሉና ይህንንም ወያኔና ሌሎችም በአታሚነት ሲረዷቸው አይተናል፤ እያየንም ነው። ያቺም ጣሊያን እንደበተነው እንደረጨው የባንዳ ፊታውራሪነትና ደጃዝማች ዓይነት ዶክተር የምትል ከየጉራንጉሩ የምትገኝ ወይም የምትገዛም ታፔላ የተጻፈውን ሀቅነት የምትሰጥ ናት፤ የምታስመስል ናት ተብላ መለጣጠፏም አልቀረም። ከንቱ ልፋት፤ መማር ለመደንቆር !
" እየነገርናቸው እያረጉት ዋዛ
ከተለበለበው የተላጠው በዛ
" እንደተባለው ሁሉ "ስንቴ ብነግራቸው እያሉን አልሰማ
መወናበድ በዛ በዋሾዎች መንጋ
" ማለትም ተገደን አለን።
የዋሾ አፉ ምላጭ እንበልና ይህ ሁሉ ጸረ ኢሕአፓ ዘመቻ ትኩረቱ በወጣቱ ወይም በአዲሱ ትውልድ ላይ ነው። እኛና ታላቆቻችንማ ታግለን ኖረነዋልና የድርጅቱን ታሪክ ጠንቅቀን እናውቀዋለን። ወጣቱን ግን 17 ዓመት ፋሺስቶቹ ሲዋሹበት ከርመው ወያኔ ደግሞ 24 ዓመት ሲቀልድብን አዲስ ጎልማሶችን የሀሰት ታሪክ እያድበለበለ ጣፋጭ ጥኽሎ ብሎ ሊያጎርስ ሲሞክር ቆይቷል። ኢሕአፓ ወያኔን ገና ከናቅፋ ደደቢት ውልደቱ ጊዜ ጀምሮ ነቅቶበት አምርሮ የታገለው ነውና ድርጅቱን ለማጥፋት የሁሌም ምኞቱና ፍላጎቱ ነው። በፊትም በቅርብም ፍኖተ ዴሞክራሲ ራዲዮን ለማፈን መጣሩ ለዚህ አንድ ምስክር ነው። ኢሕአፓን ይፈራል፤ ሊፈራም ይገባዋል። ወያኔን ሊያጠፋ እንጂ ሊያቅፍና ሊለማመጥ የቆመ ድርጅት ባለመሆኑ። የወያኔ የባዕድ ረዳቶች ደግሞ የኢሕአፓን ታሪክ ሳያውቁት ቀርተው አይደለም የሚቀባጥሩት። ኢሕአፓ የባዕዳንን ጣልቃ ገብነት አውግዞ፤ የኢትዮጵያ ሉአላዊነት ይከበር ብሎ ብቻ ሳይሆን በአፍሪካና በዓለም አቀፍ ደረጃም ከጭቁን ሕዝቦች ጎን በመቆሙ በጠላትነት ፈርጀውታል። አሜሪካም፤ ምዕራቡም፤ ሶቪየትና ጭፍሮቹ ሁሉ ሰርገው ሊገቡት፤ ሊጎዱት በየጊዜው ሲሞክሩ እንደነበር
page3image14880
የምናውቀው ነው። ጥረታቸው በአብዛኛው ቢከሽፍም ሰርገውን የገቡ ጥቂቶች እንደነበሩ የሚካድ አይደለም። ሶማሊያም ወያኔም ሻዕቢያም ሊሰርጉን መሞከራቸው የጠበቅነው ነበርና ከጥቅም ውጪ ማድረጋችንን እነሱም የሚያውቁት ነው። የባዕድ ጋዜጠኞች እነ ወያኔን ሲያሞግሱ ና ሲደግፉ ኢሕአፓን ግን ያጥላሉና ትምክህተኛ አማራ ብለው ሲያወግዙ እንደነበርም የምንረሳው አይደለም። ዳን ኮኔል፤ ጌይል ስሚዝ፤ ዴቪድ ኦቶዌይ፤ ፒተር ኒግሊ፤ ፒተር ያንግ፤ አሌክስ ደ ቫል ወዘተ ሲጽፉ የነበረውን ዝቃጭ ሁሉ ያስታውሷል። የአምኔስቲ ኢንተርናሽናሉ ሟቹ ማርቲን ሂል ለዓመታት የገንጣዮች አፈ ቀላጤ ሆኖ ሲቆይ በወያኔ ደብዛቸው የጠፋውን የኢሕአፓ መሪዎችና አባላት ስም ሳያነሳ ህይወቱ አልፋለች።
ታሪክን መቀማትና መበረዝ የሕዝብን ህልውናና ሀገርን ከመቀማት ዘመቻ ጋር የተቆራኘ ነው። በርማ ብቻ አይደለችም ዛሬ ሙስሊም ሮሂንግያ የሚባል ሕዝቤ የለም፣ አይደለም ብላ የምትክደው። ቱርክ አርመኖችን አልፈጀሁም ሲል ቆይቷል። ሶርያ ለኩርዶች ዜግነትን ሳይሰጥ ዘመን አልፏል:: እስራኤል የምስረታ በዓሌ የምትለው ለፍልስጤሞች የመርገም የሀዘን ቀን (አል ናቅባ ) ነው። በኤርትራ ታሪክ ተቀምሞ ኢትዮጵያ ቅኝ ገዢ ሆነች። ኦነግም እስከዛሬ የቅኝ ገዢን አቅዋም እሹሩሩ እያለ ድል አልባ ሆኖ ቀርቷል። ወያኔም መገንጠልን አቀንቅኖ አልሆን ሲለው ዘዴ ቀይሮ ብቅ አለ እንጂ ሀቀኛ የትግራይ የጭቆና ታሪክ በሚል ያላወራው ተረት አልነበረም። አርበኞችን ቦታ ለማሳጣት ባንዳዎች--የባንዳ ጨዋ የለውምና-- ለራሳቸው አዲስና ሀሰት የሆነ ታሪክ ይሰጣሉ። ዛሬ በኢሕአፓ ይህን አድርገን ነበር፤ ይህን ሰርተን ነበርን፣ መስራች ነን፤ ወዘተ በሚል አንዳንዶች ስደት ለወሬ ያመቻል በተባለው ዓይነት የሚዋሹትን መስማት ብቻ ይበቃል።
አሜሪካ የሚደግፈው ይህ ወጣቶችን የማደናገርና ከሀቀኛው የኢትዮጵያ ታሪክ ጋር የማጣላት ዘመቻ በወሬ ብቻ ወይም በቃል ደረጃ ብቻ ታቅቦ የቆየ ሳይሆን በአፍራሽና አጥፊ እርምጃዎችም የታጀበ ነበር። ደርግን አፍርሶ ወያኔን በቦታው ለመተካት አሜሪካ--በጎርባቾቭም እርዳታ--በኢትዮጵያ ህልውናና ሉዓላዊነት ላይ የፈጸመችው ወንጀል የቅርብ ጊዜ ትውስታ ነው። ወያኔና ሻዕቢያን ብሎም ኦነግን ለመርዳት አሜሪካ ይሁነኝ ብሎ የመረጠው ጸረ ኢትዮጵያ ፖሊሲ ቀደም ብሎ የተጠነሰሰ ለመሆኑ ታሪክን የሚያውቁና በትግል አካባቢ የነበሩ ሁሉ ተችተውታል። ኢትዮጵያ መዳከም አለባት የሚለው አቅዋም መሰረታዊ የአሜሪካ አቃዋም ነበር። አንዳንዶች የአሜሪካ ሰርጎች ገቦች እጅ አለበት ብለው በሚጠረጥሩት የኢሕ አፓ ሰራዊት ብተና ሂደት ሳቢያ የተበተኑት ተመልሰው በድርጅቱ እንዳይሰባሰቡ ማራቅ የሚል ዕቅድ ተጠንሶና ለሱዳንም ቀርቦ ብዙዎቹን ወዲያውኑ ወደ አሜሪካ ማጓጓዝ--ማስፈር መካሄዱን እናውቃለን። ኢሕአፓም ብተናው ያደረሰበትን ችግርና ቀውስ ተቆጣጥሮ እንደገና ትግሉን ሲቀጥልም በጭልጋ ቋራ ጥቃት ሊያደርስበት በቀጥታ በሲአይ ኤ፤ ሻዕቢያና የሱዳን የሚሊቴሪ የስለላ ተቋም የተደራጀ ና አዳዲስ
page4image16824
የቻይና መሳሪያ የታጠቀ ሀይል ኢሕአሠን ሊያጠቃ ሞክሮ ድባቅ ተመቶ ሴራው ከሽፏል። ግቡ የነበረው ኢሕአፓ/ሠ ን አጥፍቶ የነደረጀ ዴሬሳ ኢሕዴአ/ኢፒዲኤ ለመትከልና ሻዕቢያ በሚሰጣቸው የጦር አስረኞች ለማጠናከርና የኢፒዲኤንም ሱዳን የተተከለ ራዲዮ ወደ ሀገር ለማስገባት ነበር። ሻዕቢያና ሲአይ ኤ የደርግን ጦር ለነሻዕቢያ በሚያመች ደረጃ ለመከፋፈል ሳይጀመር ያለቀለት መፈንቅለ መንግስት አስሞክረው እንደነበር ሲታወቅ ለዚህም ተባባሪ የሆናቸው አረመኔው ኮለኔል አንጋፋ የጦር ጄኔራሎችን ገድሎ ያደረሰው ጉዳት ታሪክ ገና ዝርዝሩ የተነገረ አይደለም። በመፈንቅሉ ተሳትፈው ወደ አሜሪካ የሮጡ ጄኔራሎችም ዝርዝር መረጃና ዘገባ ለአሜሪካ እንጂ ለሚመለክተው ለኢትዮጵያ ሕዝብ አልሰጡም። ይህ ሁሉ ታሪክ አስተማሪና አልፎም አስጠንቃቂ ሆኖ እያለ ዛሬም አሜሪካን እንደ ወዳጅ መማጸን፤ አሜሪካ ቅጥረኛ ያደረገቻቸውን ታጋይ ብሎ በትከሻ መጫንና ሀገር ጎጂ መጃጃልን ማቀፍ ሰፍኖ ይታያል።
ከታሪክ አንጻርም ማንን መሪ፤ ማንን ጀግና፤ ማንን ታጋይ ብሎ መመዘን እንደሚገባ ያለው ውዥንብር ከታሪክ ብረዛው ጋር የተያያዘ ነው። ባንዳ አርበኛ፤ ገንጣይ ታጋይ፤ ቀይ ሽብርተኛ ሀገር ወዳድ ጓድ፤ አንጃ አብዮተኛ ሲባል ትውልድ ማን ቢወልድ ማ ቢጠፋውና ቢደናገር የሚያስገርም አይሆንም። 20 ሺ አባላትን ለወያኔ አስረክቦ በመውጫ ቪዛ ፍቃድ መለስን ተሰናብተው ሀገርን የሚለቁ ማፈሪያ ሊባሉ ሲገባ መሪ ሲባሉ የተዛባ ነገር እንዳለ ግልጽ ነው። ግለሰቦች በታሪክ ያልነበራቸውን ቦታ ሊይዙ ሲጥሩ አዲስ ታሪክ ማሰራጨታቸው የግድ ይሆንባቸዋል። በቅርቡ፤ ያውም ያኮራ ይመስል፤ ያውም በሀሰት፤ የሻዕቢያውን መሪ እናውቀው ነበር፤ አግኝተነው ነበር ብለው መለፈፍ የመረጡትን መታዘብ እንችላለን። አንዳንዶች አንጃ ብለው ሌሎችን ያወገዙና ያጠቋቸውን ዛሬ መለስ ብለው ከደሙ ንጹህ ነን ዓይነት "ልክ ነበሩ እነሱ" ሲሉም አድምጠን አፍረንባቸዋል። ዘመናዊ ጴጥሮሶች! ሕዝብን ክደን ለፋሺስት መስገዱና ለሹመት መዋረዱ የማይሆንልን ሆኖ በመታገላችን መቸም ሆነ ማንንም ይቅርታ የምንጠይቅ ባለመሆናችን ደግሞ ለወንጀል ድበቃ ከወያኔ ጎን የቆሙትን ሆነ ታሪክን ከልሰው ሊያወግዙን ለተነሱትም ምላሻችንም የተለወጠ አይደለም። ያ ትውልድ ግን ሊኮራበት የሚገባና ታሪክም መቸም የማትረሳው መሆኑን ማንም ሊሰርዝ አይችልም። መሪ ያልናቸውም ወኔ ቢሶችና የስልጣን ጥመኞች ሳይሆኑ ለሕዝብ የተሰው፤ አንበገርም ያሉ፤ ያልካዱ፤ ሌሎችን እንዳያጋልጡ መሰዋትን የመረጡ፤ መርዝ ክኒን የሚውጡ፤ እናቸንፋለን ብለው ሞትን የሚጋፈጡ ነበሩ። የሰው ሰዎች፤ ሀገር ወዳድና ፍርሃትን ያሸነፉ፣ ያኮሩንና አሁንም የሚያኮሩን ብዙዎች። እንደ እንክርዳድ ብቅ ያሉት፤ ለግል ስልጣን የባከኑት፤ ጠቋሚና ከሀዲ የሆኑትንም ድርጅቱ ባለው አቅም ታግሏል፤ አስወግዷል (አንጃዎች ያደረሱትን ከፍተኛ ጉዳት ያጤኗል!)። የድርጅቱ ዋናው መለያው ግን “በትግል መሞት ሕይወት/ ዳግም ትንሳኤ ልደት” ብሎ ለዲሞክራሲ፤ ለሕዝብ መብትና ለኢትዮጵያ ሉዓላዊንት መታገሉ ነው። ጓዶቻቸውን ከገደለው ፋሺስትና ዘረኛ ወያኔ ተገልብጠው የሰመሩና የተቃቃፉ እንደነበሩና እንዳሉም ረስተን አንገኝም። ኢሕአፓ ወደ ራስ መከላከልና የከተማ ተኩስ የተገፋው በገዢዎችና ጭፍሮቻቸው መሆኑን ታሪክ የመዘገበው ነው። የታገለን ትውልድና ያታገለን ድርጅት ማውገዙ ከሰፈነና ለሀገር መሰዋት ሞኝነት ተብሎ ለስላቅ ከተዳረገ ተኪ ጀግና፤ ትግልን አፍቃሪ አርበኛ ቢጠፋ የሚያስገርም አይሆንም። ልቡ የሽበተን ትውልድ ወያኔም የኢትዮጵያ ጠላቶችም ይፈልጋሉ። ትግል ደግሞ እውን ከተደረገ መራራ ነውና ፈሪ ተለይ እንጂ ፈሪና ደካማው ይምራን የሚባልበት አይደለም።
ማንኛውም ትግል ሆነ ክስተት ብቅ ባለበትና በተካሄደበት ሁኔታ ውስጥ ነው መመርመር መገምገም ያለበት። የጀግናው ትውልድም ትግል ዛሬ በኋላ በሚወጣለት አቃቂር የጊዜ ክልል ሳይሆን የተካሄደው ያኔ በ 66ና ሰባዎች መጀመሪያ ነው። ርዕዮቱ፤ መፈክሮቹ፤ አደረጃጀቱና ህቡዕነቱ፤ ወዳጅ ጠላት አፈረጃጀቱ፤ ስምሪቱ ሁሉ የነበረበትን ሁኒታና ጊዜ አጣቅሶና ይዞ መታየት ያለበት ነው። ጸረ ኢምፔሪያሊስት ትግሉ ደግሞ የግድ ነበር። የአሜሪካንን ሰው በላ ስርዓትም አልፈልግም ማለት የሚያስመሰግነው ነው። ዛሬም ቢሆን የህብረሰቡን መሰረታዊ መብት ለሚያስከብር ዲሞክራሲያዊና ሕዝባዊ ስርዓት ይታገላል እንጂ ለሰው በላ ካፒታሊዝም መስዋዕት የሚሆን አይደለም። ሊበራል ካፒታሊዝም ወይም የአሜሪካ ስርዓት በሚል የሚጮሁት ሆኑ ወይም አብዮታዊ ዴሞክራሲ ብለው የሚያሾፉትን አምባገነኖች አልተቀበላቸውም፤ የሚቀበላቸውም አይሆንም። የያኔው እንቅስቃሴ ግራ ክንፍነት ደግሞ የሚመለጥም አልነበር። አሌ ብሎ ወደ ቀኝ ሊያዘም የሚፈልግ ሀይልና እንቅስቃሴ ካለመታየቱ ሌላ ለባዕድ ተገዢ ከሆነው ከአቀባባይ ከበርቴው ሌላ የጥገና ለውጥን ሊያቀነቅን የሚችልም ይህ ነው የሚባል ከበርቴ መደብ አልነበረም። በዓለም አቀፍ ደረጃም የምዕራቡ ጎራ የቅኝ ገዢዎች፤ የአፓርታይድ ደጋፊዎች፣ የጭፍን በዝባዦችና የዘረኞች ሰፈር ነበር፡፡ ሳንቶ ዶሚንጎ፤ ኩባ፤ ቪየትናም ላኦስ ካምቦዲያ፤ አንጎላ ሞዛምቢክ፤ ጊኒ ቢሳው ናሚቢያ፤ አልጄሪያ የመን፤ሌባኖን ፓለስታይን፤ኬንያ ... ስንቱ ሰቆቃ ተነስቶስ ያልቃል? ለሕዝብ መታገል ከተባለ ከተራማጅነትና ግራ ክንፍ ከመሆን በመለስ ሌላ አማራጭ አልነበረም።
ከዚህ በተያያዘ መነሳትና ጫና ሊሰጠው የሚገባው የአደረጃጀትና የትግልም ስልት ጉዳይ ነው። በዚህ መስክ ብዙ ተመክሮ አለ። የዛሬ ስልጡን ፖለቲከኞች ግን ይህን ተመክሮ ከቁም ነገር ባለመቁጠራችው የተነሳ የብዙ ዜጋ ሕይወት አልፏል፤ ብዙዎች ለስየልና እስር ተዳርገዋል። ይህ ሁኔታ ካልተቀየረ አሁንም ትግል ለአደጋ መጋለጡ አይቀሬ ነው። ታሪክ ይታወስ ስንል ያለፈውን ለማስታወስ ብቻ ሳይሆን የዛሬና ነገን ትግል አቅጣጫ ለማስያዝም ነው። ኢሕአፓ ራሱ ለጥቃት የተጋለጠው በዚህ መስክ ዘረክረክና ላላ ሲል ነው። ማዕከላዊነትና ህቡዓዊነት--ትግሉ የግድ የሚላቸው መርሆች-- በተገቢው መንገድ በስራ ላይ መዋል ሲያቅታቸው ክሩ እየተፈታ ጉዳት ይከተላል። ጠበቅና ሙያተኛ የሆነ ደርጅት/አደረጃጀት መኖሩ አስፈላጊ ሆኖ ሳለ በጥቂት የአመራር አባሎች ዲሞክራሲያው ግንባር (ዲኤፍ) በሚል አባልና ደጋፊን የሚያደባልቅ አወቃቀር መምጣቱ፤ ህቡዕነት መዳከሙ፤ ሁሉም አካላት/ተቋማት የየራሳቸው ስኳድ ማቆማቸውና፤ ማወቅ ካለበት በላይ ማወቅ አይገባም የተባለው ዋና መርህ በመሻሩ አንድ ሲያዝ ወይ ሲከዳ ብዙ ጓዶችና መዋቅሮች የሚመቱበት ሁኔታ ተፈጠረ ። ይህ አንዱ ገጽታ ሲሆን በሌላ ደረጃ ደግሞ ካለው አገዛዝ ጋር የሚያብሩ ለሹመትም ሆነ ሌላ የአባላቸውን ስም ለጊዜያዊ ወዳጃቸው እየሰጡ ለመጪው እርድ ራሳቸውን ያመቻቻሉ። ያየነው ነው በደርግም በወያኔም ጊዜ። ዓለም ሰለጠነ፤ ፖለቲካም ክፍት ሆነ፤ በሰላምና በግልጽ መታገል ነው እንጂ የምን ህቡዕነት በሚባልበት በዘመናችን፤ በአሁኑ ጊዜ ደግሞ የየሀገሩን ተጨባጭ ሁኔታ መርምሮ ተገቢውን ስልትና አደረጃጀት አሰራር መቀየስ ሲገባ ይህ ተብሏልና ማለትም ሰላምን ግልጽነት ተሰብኳልና በረቱን ክፍት አድርገን ለሁሉም ተኩላና ቀበሮ እንተውለት ማለት ጉዳት እያደረሰ ነው። ህጋዊነትን አገኘን፤ የምንታገለው በሰላም ነው ቢባልም ሀይልን ሁሉ አለማጋለጥ የፖለቲካ ሀ ሁ መሆን ነበረበት። ይህ ግን አልሆነም። የድርጅቶች ገበና በየአደባባዩ ይሰጣል፤ ምስጢራቸው ይዝረከረካል፤ በድርጅቶች ላይ ከፋፋይና የወያኔ ተገዢ ሆነው የሚነሱት ክፍሎች ምን ያህል ወያኔን እንደጠቀሙት የምናውቀው ነው። የምዕራቡ የፖለቲካ ሁኔታ በኢትዮጵያ የሚሰፍን መስሏችው፤ ወያኔንም ካለውና ከማይለቀው አውሬነት ነጥለው ሊያዩ የቃጡ ከወያኔ የሚገባቸውን ቅጣት ሲቀበሉ የሕዝብን ትግልንም በዚያው ጎድተዋል። የኢሕአፓ የቀድሞውና የዛሬው ህቡዕነት ለየቅል ቢሆንም የድርጅትን አወቃቀር በምስጢር መያዝ፤ ሁሉንም አመራርና አባላት አለማጋለጥ (ለምሳሌ በኢትዮጵያ ያሉ ቀርቶ በውጭም ያሉ የከፍተኛ አመራር ኮሚቴ ሁሉም በአባሎች አለመታወቅ ድርጅቱን ከጥቃት ጠብቆት መቆየቱ የሚታወቅ ነው)። በግልጽነት እንታገል ብለው አቅዋም የያዙም የዚህን ገደብ ማወቅና መጠንቀቅ ይኖርባቸዋል። በዲሞክራሲ ስር ሊኖር የሚችል ሰፊ ሕዝባዊ ፓርቲ ይዘትና አደረጃጀት አምባገነኖች በስልጣን ባሉበት አደገኛ ሁኔታ ሊኖር ሊገኝ ሊታሰብና ሊያዝም የሚችል አለመሆኑን የኢሕአፓ ተመክሮ ያስረዳል ።
እንጻፍ ካልንማ በሚል አቢይ ጉዳዮችን በተመለከተ መጻፉ ግድ ሆኖ የመጣው ያ በሁሉም አባላት ተሳትፎና የጋራ ጥረት የሚጻፈው ታሪክ ለህትመት እስኪበቃ የዋሾዎች ወሮበላ ቡድንና ወያኔ የወጣቱ አንጎል ላይ የእንዶድም የኦሞም አጠባ እንዳያካሂዱ ለማድረግ ነው። በታሪክ ስም ሀቀኛ ታሪክን ሊያጠፉና እግረ መንገዳቸውንም ወደዱም ጠሉም ወያኔን ሊጠቅሙ የተነሱትን ከነውሸታቸው ማጋለጥና መከላከል የግድ በመሆኑ ነው። ይህን ስናደርግ ያው ቀደሞም እንደተባለውም ዶሴን ከፍቶ የመዘርገፉ ጊዜ ገና ነውና አሁንም ቢሆን መቆጠብ የግድ ሆኗል። ድርጅቱ ዛሬም በትግል ላይ ያለ ነውና፤ በሚናገረውና በሚያወጣው ምስጢርም አሁንም ሊጎዳ የሚችልበት ሁኔታ አለና እንደ ግለሰቦች ሀላፊነት የጎደለውን የጽሁፍ መፉለል ሊያስተናግድ አይችልም። የአንዳንዶቹን ገበና--ያውም አላርፍ ያለች ጣት ሲሆኑ ሳይቀር-- አፍኖ የሚይዘውም ለዚህ ነው። ሌሎችንም በተመለከተ ይህ ተደርጎ፤ ተወስኖ ነበር ማለቱ ጊዜው ገና ሆኖ ያስቸግራል። ባለውና በሚታወቀው ቢሆንም ኢሕአፓ ለኢትዮጵያና ለህዝቧ የታገለና የደም ዋጋ የከፈለ፤ አሁንም ቢሆን ለማንም ባዕድ ሳይሰግድ፤ ሀገርና ሕዝብን ሳይከዳ እየታገለ መቀጠሉን ማንም ጮሌ ሆነ መደዴ ዋሾ ሊሰርዘው የሚችል አይደለም። አሁንም ቢሆን ከወያኔ ጋር እንተቃቀፍ፤ ሰላም በሚል ሰበብ ወያኔን አምርረን መታገሉን እንተው፤ ሁለገብ ትግል ማለት ጊዜው አልፎበታል ከሚሉት ጋር ኢሕአፓ የሚግባባ አይደለም። ውሻ ወደ ትፋቱን ድርጅቱ አያውቅም። ጊዜው ያለፈበት ትግል ሳይሆን ጭቆናን ተሽክሞ መኖር ነው። ወያኔና መሰሎቹ እንደሆነ የሌባ ዓይነደረቅ መልሶ ልብ ያደርቅ ናቸው። የወያኔ ውድቀት ደግሞ በምርጫ ድምጽ ሳይሆን በአመጽና ጥይት መሆኑን ለካዱት አሁን የተጠናቀቀው የምርጫ ጨዋታም ውጤት አሳይቷቸዋል። የአመጽን ዋናነት በኢትዮጵያ ኢሕአፓ የተረዳው ከ43 ዓመት በፊት ነው። ይህ ነው ታሪክ-- እንጻፍ እንናገር እንዘክር ከተባለ። የሰማዕትን ደምና መስዋዕትነትም የምናከብረው ከገድላቸው ትሁት ሆነን በመማር ነው።
ይቀጥላል.........
page8image7288
 እንፃፍ ካልንማ (4) ከኢያሱ ዓለማየሁ 

Friday, May 29, 2015

ነጻነት በሌለባት ኢትዮጵያ ሕዝባዊ አስተዳደር መትከል ዘበት ነው!!! ከሰማያዊ ፓርቲ

ከሰማያዊ ፓርቲ የተሰጠ መግለጫ
Blueሰማያዊ ፓርቲ በ2007 ዓ.ም ጠቅላላ ምርጫ ለመሳተፍ ሲወስን በዚህች ሐገር ገለልተኛና ብቃት ያላቸው ተቋማት እንደሌሉና ገዥው ቡድንም እውነተኛ ምርጫ እንደማይፈቅድ እያወቀ መሆኑን ከዚህ በፊት በሰጣቸው የአቋም መግለጫዎች ግልፅ አድርጓል፡፡ በሒደቱም እንደታየው ገና ከመጀመሪያው ምርጫ ቦርድ የሰማያዊ እጩዎችን ከምዝገባ ሰርዟል፡፡ ገዥው ቡድን ስልጣኑን ላለማጣት የአፈና መዋቅር በመዘርጋት የዜጎች በነፃነት የመምረጥ መብትን በእጅጉ አፍኗል፡፡ የገዥው ቡድን ካድሬዎችና የፀጥታ ኃይሎች የተቃዋሚ ፓርቲዎች ተዋዳዳሪዎችን፣ ታዛቢዎችንና አባላትን በማን አለብኝነት ደብድበዋል፣ አስረዋል፣ አለፍ ሲልም ገድለዋል፡፡ ዜጎች ያላቸውን አማራጮች ሊያውቁባቸው የሚችሉ የመገናኛ ብዙሃንና የሲቪክ ማሕበራት በሐገሪቱ እንዳይኖሩ ተደርገዋል፡፡ በህገ መንግስቱ በግልፅ የተከለከለውን ቅድመ ምርመራ በመተላላፍ የፓርቲያችን የቅስቀሳ መልዕክቶች ለህዝብ እንዳይደርሱ የመንግስት የመገናኛ ብዙኃን ከፍተኛ ደባ ፈፅመዋል፡፡ ሃሳባቸውን በነፃነት የገለፁ አባሎቻችን ከየቤታቸውና ከሚሰሩባቸው ቦታዎች እየታደኑ ታስረዋል፣ አሁንም በእስር እየማቀቁ ይገኛሉ፡፡
በእነዚህና በሌሎችም ህገ ወጥ አሰራሮች ታጅቦ የተካሔደው ምርጫ በምንም መመዘኛ ፍትሃዊ፣ ነፃና ተአማኒ ሊሆን እንደማይችል ሒደቱ በግልፅ አመላካች ነው፡፡ በውጤቱም በሐገራችን የዲሞክራሲና የመድብለ ፓርቲ ስርዓት መኖርን ወደ መቃብር የከተተና ኢትዮጵያ የአንድ ፓርቲ ስርዓት ሐገር መሆኗን ያረጋገጠ በውጤቱም የገዥውን ቡድን 100% አሸናፊነት አከናንቦታል፡፡ ይህ ውጤት ለኢትዮጵያ ዴሞክራሲ የጨለማ ዘመን መምጣቱን ከማሳየቱ ባሻገር ኢህአዲግ በፍርሃት ተውጦ ሁሉንም ለመቆጣጠር ባደረገው ሩጫ ለመግለፅ እስኪያፍር ድረስ የሚያሸማቅቅ ውጤት እንዲከናነብ ሆኗል፡፡
በርካታ ኢትዮጵያውያን በምርጫው ሂደት ተስፋ በማጣት የመራጭነት ካርድ እንዳልወሰዱ የታወቀ ቢሆንም በአፈና ስርዓቱ ኢህአዲግን እንዲመርጡ በከፍተኛ ጫና የመራጭነት ካርድ የወሰዱ ዜጎች ሰማያዊ ፓርቲ ያቀረባቸውን የፖሊሲ አማራጮችና ለሐገራችን ያለውን ቀናኢ አመለካከት በመገንዘብ ሳይገደዱ፣ በጥቅም ሳይታለሉ ወይም ሌላ ማንኛውንም ስጦታ ሳይጠብቁ ለሰማያዊ ፓርቲ የሰጡት ድምፅ እጅግ የሚያስደምም ሆኖ አግኝተነዋል፡፡ ፓርቲያችን በዚህ አፈናና ጭቆና ውስጥ ከሕዝብ የተሰጠውን ክብርም ያከብራል፣ ያመሰግናል፡፡ በምርጫ ሂደቱ የተደበደባችሁ፣ የተሳደዳችሁ፣ የታሰራችሁ እና የተንገላታችሁ የፓርቲያችን አባላትና ደጋፊዎች ፓርቲያችን ዛሬ በኢትዮጵያ ሕዝብ ተዓማኒ፣ ተወዳጅና ተስፋ የተጣለበት እንዲሆን እናንተ ላይ የደረሰው መከራና በደል ትልቁን ድርሻ ይወስዳልና ክብርና ምስጋና ይገባችኋል፡፡
በመጨረሻም ከላይ በተዘረዘሩት ሕገወጥና የአፈና ስርዓት የተካሔደው የ2007 ዓ.ም ጠቅላላ ምርጫ የሚያመላክተው ኢትዮጵያ አሁንም ነፃና ፍትኃዊ ምርጫ ልታካሂድ ቀርቶ በኢትዮጵያ ከዚህ ቀደም ከተካሔዱት ምርጫዎች ጋር እንኳ ሊወዳደር የማይችል እጅግ ኢፍትኃዊ፣ ወገንተኛና ተዓማኒነት የሌለው በመሆኑ ሰማያዊ ፓርቲ ሂደቱንም ሆነ ውጤቱን አይቀበለውም፡፡ በኃይል በተቀማ ድምፅ የሚመሰረት መንግስትም በሕዝብ ተቀባይነት የለውም፡፡ የዜጎች ነፃነት ሳይከበር ነጻና ፍትኃዊ ምርጫ ሊደረግ ስለማይችል አሁንም ሰብአዊና ዲሞክራሲያዊ መብቶቻችን እስከሚከበሩ ድረስ ሰማያዊ ፓርቲ በሚያካሂደው የነጻነት ትግል ኢትዮጵያውያን ከጎኑ እንዲቆሙ እየጠየቀ ለነፃነት የሚደረገው ትግል ተጠናክሮ የሚቀጥል መሆኑን ያሳውቃል፡፡
ግንቦት 21 ቀን 2007 ዓ.ም
አዲስ አበባ
11392881_715789008546760_7142204330075555507_n

- See more at: http://satenaw.com/amharic/archives/7385#sthash.jTlRGgn5.dpuf

Thursday, May 28, 2015

FINOTE DEMOCRACY RADIO • የቀድሞ የአንድነት ፓርቲ ብሔራዊ ምክር ቤት አባልና የፋይናንስ ግዳይ ምክትል ኃላፊ የነበሩት አቶ አዲሱ ካሳሁን የወያኔ አገዛዝ በእሳቸውና በቤተሰባቸው ላይ ባደረገባቸው ከፍተኛ ወከባና አፈና ምክንያት አገር ጥለው የተሰደዱ መሆናቸው ተሰምቷል። አቶ አዲሱ የወያኔ ግድያ አፈናና እንግልት በማምለጥ ወደ ውጭ ከተሰደዱት በብዙ ሺ የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውን መካከል አንዱ ሲሆኑ መቼ ከአገር እንደወጡና ወዴትኛው አገር እንደተሰደዱ የተገለጸ ነገር የለም።
 • ከሉሲ እድሜ የሚበልጥና ከ3.3 እስከ 3.5 ሚሊዮን ዓመት የሚገመት እድሜ ያለው የሰው የላይ መንጋጋና ጥርስ በኢትዮጵያ አፋር ግዛት በወራንሶ ሚሌ አካባቢ የተገኘ መሆኑን የአርኪዎሎጂ ጥናት ተመራማሪዎች አስታውቀዋል። ኖራማ በሆነው በሃ ድንጋይ ውስጥ የተገኘውና ኦውስትራሎፒተከስ ደይሪሜዳ የሚል ስያሜ ያገኘው ይህ የሰውና የዝንጀሮ መሰል አስከሬን ክፍል ከዚህ በፊት ተማራማሪዎች ካገኟዋቸው የተለየ ሲሆን የጥርሱና የመንጋጋው መጠንም ከሉሲ ከፍ ያለ መሆኑ ተረጋጧል። ይህ የሰው ዘር ግንድ ነው ተብሎ የታመነው ፍጡር የኖረበት ዘመን ከሉሲ እድሜ ጋር ተመሳሳይ ግምት የተሰጠው በመሆኑ ለሰው ዘር ግንድ ናቸው የተባሉት ፍጡሮች የተለያዩ እየሆኑ የመጡበት ሁኔታ እንዳለ ተስተውሏል።
 • በርካታ የዓለም እግር ኳስ ፌዴሬሽን (FIFA) ባለስልጣኖች ጉቦ ተቀብላችኋል የተለያዩ ሙስና ውስጥ ተዘፍቃችኋል የሚል ክስ በአሜሪካና በስዊዝ መንግስት የቀረበባቸው መሆኑ በትናንትናው ዕለት ተዘግቧል። በተለያዩ ደረጃ ኃላፊነት ላይ ከነበሩና ካሉ ክስ ከቀረበባቸው 14 የድርጅቱ ባለስልጣኖች መካከል ሰባቱ በትናንትናው ዕለት በሲዊዝ መንግስት ባለስልጣኖች የተያዙ ሲሆን ሌሎቹ በተለያዩ ባሉበት ቦታ እጃቸውን የሰጡ መሆናቸው ታውቋል። ባጠቃላይ ለ24አመታት 150 ሚሊዮን ዶላር ግምት ገንዘብ በሙስና መልክ ለራሳቸው ጥቅም አውለዋል የሚል ክስ የቀረበባቸው ሲሆን በስዊዝ የተያዙት ሰባቱ የካሬቢያንና የደቡብ አሜሪካ ተወላጆች ወደ ዩናይትድ ስቴትስ ይላካሉ ተብሏል። የ79ዓመት በሆኑት በፊፋው ፕሬዚዳንት በሚስተር ብላተር ላይ እስካሁን ክስ ያልቀረበ ሲሆን ሚስተር ብላተር ለአምስተኛ ጊዜ ለፊፋ ፕሬዚዳንትነት ውድደር በዚህ ሳምንት ውስጥ የሚቀርቡ መሆናቸው ቀደም ብሎ መገለጹ ይታወሳል። የቀደሞ የፊፋ ምክትል ፕሬዚዳንት የትሪኒዳዱ ጃክ ዋርነር የዓለም ዋንጫ ውድደሩ በደቡብ አፍሪካ ለማካሄድ የ10 ሚሊዮን ዶላር ጉቡ ተቀብለሃል ተብለው ክስ የተመሰረተባቸው ሲሆን በ1918 ሩሲያ ውስጥ በ 1924 ..ም ደግሞ ካታር ውስጥ ሊካሄድ የታቀደው የዓለም ዋንጫ ጨዋታ በጉቦ የተደረገ ነው በማለት የስዊዝ ባለስልጣኖች ምርመራ እያካሄዱ መሆናቸውም ተገልጿል። ደቡብ አፍሪካ ሂሳባችንን ቀደም ብለን ኦዲት ያስደረግን ስለሆነ ምንም ዓይነት ጉቦ አልከፍልንም የሚል መግልጫ የሰጠ ሲሆን ሩሲያም ለማንኛችውም ምርመራ ዝግጁ ነን ብሏል። በፊፋ ባለስልጣኖች ላይ የተደረገው እስራትና ክስ በርካታ ወገኖችን ያስደነገጠና ያስገረመ ሲሆን አንዳንድ ድምጾችም መሰማት ጀምረዋል። የፈረንሳይና የእንግሊዝ ባለስልጣኖች አርብ ሊካሄድ የታቀደው የፊፋ ፕሬዚዳንትነት ምርጫ መራዘም አለበት የሚል ድምጽ ሲያሰሙ የ79 ዓመቱ ፕሬዚዳንት ደጋፊ የሆኑ አገሮች ሩሲያና የእሲያ እግር ኳስ ኮንፌዴረሽን ምርጫው መራዘም የለበትም የሚል ጠንካራ ሀሳብ ሰንዘረዋል። በርካታ የምእራብ አገሮች በአሜሪካና በስዊዝ ባለስልጣኖች የተወሰደውን ርምጃ ሲደግፉ የሩሲያው ፑቲን አሜርካ በማያገባት ገብታ ይህን እርምጃ የወሰደችው አለምን ለመቆጣጠርና የራሷን ጥቅም ለማስጠበቅ ነው የሚል ተቃውሞ አሰምተዋል። 
 • በብሩንዲ ውስጥ ከፍተኛ ተሰሚነትና ተጽእኖ ያላት የካቶሊክ ቤተከርስቲያን በስልጣን ላይ ባለው የብሩንዲ መንግስት የታቀደውን ሀገራዊ ምርጫ እንደማትደግፍ በመግለጽ መግለጫ ያወጣች መሆኑ ታወቀ። መግለጫው “ የታቀደው ምርጫ የሚካሄድበትን መንግደ በጥሞና ካጠናንና ትክክለኛ አለመሆኑን ካረጋገጥን በኋላ በአገሪቱ የተለያዩ የምርጫ ኮሚሽን ውስጥ ተመድበው የሚሰሩ ቄሶች ራሳቸውን እንዲያገልሉ ወስነናል” ብሏል። ይህ የካቶሊክ ቤተክርስያን መግለጫ የተሰጠው ተቃዋሚ ፓርቲዎች አሁን ባለው ሁኔታ በብሩንዲው ውስጥ ነጻና ፍትሃዊ ምርጫ ሊካሄድ አይችልም ከተካሄደም ውጤት በሕዝብ ተቀባይነት ሊኖረው አይገባም የሚል ውሳኔ ባሳለፉ በሁለተኛው ቀን ነው። በካቶሊክ ቤተክርስቲያን ራዲዮ ተነቦ የተሰማው የቤተክርስቲያኗ መግለጫ ምርጫው ብዙ ውስብስብ ችግሮች የተበተቡት መሆኑን እያየን ዝም ልንል አንችልም፤ ማንም ሰው በወከባና በማስፈረሪያ ወደ ምርጫ ጣቢያ ሊሄድ አይገባም፤ በእግዚአብሄር ፊት ይህንን ማድረግ ከስይጣን ተግባርና ከባርያ ፍንገላ ተለይቶ አይታይም” ብሏል። ህግና ስርዓት ሲጣስ፤ በሕዝብ ላይ ግፍ ሲበዛ ቤተ ክርስቲያን ተቃውሞ ለማሰማት የሞራል ግዴታ ያለባት መሆኑን የቡሩንዲው ካቶሊክ ቤተክርስቲያን በሚገባ ያሳየች ስትሆን በኢትዮጵያ ግን በህገ ወጡ ሲኖዶስ የሚመራው ቤተክርስቲያን በተገላቢጦሽ የአምባገንኖችንና የአሸባሪዎችን ድርጊት እየደገፈና እየመረቀ መጓዙ የሚያሳዝን ነው በማለት ታዛቢዎች አስተያየታቸውን ይሰጣሉ።
የሱዳን የነጻ ጋዜጠኞች ማህበር የተባለው ተቋሞ የበሽር መንግስት በጋዜጠኞች ላይ የሚያደርገውን አፈና በመቃወም የስራ ማቆም አድማ እንዲያደርጉ የጠየቀ መሆኑ ታውቋል። በሱዳን በህግ ተመዝገበው ከሚሰሩ 1200 ጋዜጠኞች መካከል 400 የሚሆነትን በአባልነት የያዘው ይኸው የጋዜጠኞች ማህበር በትናነትናው እለት የፕሬስና የፕፕሊኬሽን ምክር ቤት ሕንጻ ፊት ለፊት የተቃውሞ ስልፍ ያደረገ ሲሆን ተቃውሞ የተደረገውም የ 10 የጋዜጣ ተቋሞች ያወጧቸው ጋዜጦች በመወረሱና አራት የሚሆኑት የጋዜጣ ተቋሞች ላልተወሰነ ጊዜ በመታገዳቸው ነው ተብሏል። ጋዜጦቹ ላይ የበሽር መንግስት ይህንን እርምጃ የወሰደው የመንግስቱን ድርጊት እየተከታተሉ በማጋለጣቸው መሆኑ ተነግሯል። 
 

Ethiopia's May 24 Parliamentary and Regional Elections
Press Statement
Marie Harf
Deputy Department SpokespersonOffice of the Spokesperson
Washington, DC
May 27, 2015

The United States commends the people of Ethiopia for their civic participation in generally peaceful parliamentary and regional elections on May 24. We acknowledge the National Electoral Board’s organizational efforts and the African Union’s role as the only international observer mission on the ground. We also note the importance of the nine televised party debates as progress in fostering open public discussion of the challenges facing the country. We encourage all candidates, political parties and their supporters to resolve any outstanding differences or concerns peacefully in accordance with Ethiopia’s constitution and laws.
The United States remains deeply concerned by continued restrictions on civil society, media, opposition parties, and independent voices and views. We regret that U.S. diplomats were denied accreditation as election observers and prohibited from formally observing Ethiopia’s electoral process. Apart from the election observation mission fielded by the African Union, there were no international observer missions on the ground in Ethiopia. We are also troubled that opposition party observers were reportedly prevented from observing the electoral process in some locations.
A free and vibrant media, space for civil society organizations to work on democracy and human rights concerns, opposition parties able to operate without impediment, and a diversity of international and domestic election observers are essential components for free and fair elections. The imprisonment and intimidation of journalists, restrictions on NGO activities, interference with peaceful opposition party activities, and government actions to restrict political space in the lead-up to election day are inconsistent with these democratic processes and norms.
The United States has a broad and strong partnership with Ethiopia and its people. We remain committed to working with the Ethiopian Government and its people to strengthen Ethiopia’s democratic institutions, improve press freedom, and promote a more open political environment consistent with Ethiopia’s international human rights obligations.

ሌላ የመሬት ነጠቃ ዘመን! ሌላ የስደት ዘመን!

አምስተኛው ዙር የድምጽ ዘረፋ… (ክንፉ አሰፋ)


የ”ምርጫው” ድራማ እየተተወነ ሳለ፤ የቦርዱ ሊቀመንበር ዶ/ር መርጋ በቃና እና ምክትል ሊቀመንበሩ ዶ/ር አዲሱ ገብረእግዚአብሔር ለአቦይ ስብሃት ስልክ ደወሉ።
 “ሃሎ?” 
“ሃሎ፣ አቦይ ስብሃት ኖት?” 
“ነኝ፣ ምን ፈለግክ?” 
“ዶ/ር መርጋ በቃና እና ዶ/ር አዲሱ ገብረእግዚአብሔር ነን።”
 “ችግር መስማት አልፈልግም። የታዘዛችሁትን አደረጋችሁ?”
 “99.8% ህዝብ አልመረጠንም። 
ግን በታዘዝነው መሰረት ውጤቱን ገልብጠነዋል!”
 “0.2% ብቻ ነው የመረጠን ማለት ነው?”
 “አዎን ጌታዬ። ሌላ ምን እንታዘዝ?”
 “99.8% ህዝብ የስም ዝርዝሩን አንብብልኝ።” አሉ አቦይ ስብሃት እየተባለ ይወራል። 
              
           አንድ ወዳጄ ስለ አቦይ ስብሃት የነገረኝ ታወሰኝ። ሰውዬው ከግመል እንኳን የማይሻል እንስሳ ብጤ ነው። ግመል ሳትጠጣ ለቀናት ትሰራለች አቦይ ስብሃት ደግሞ ሳይሰራ ቀኑን ሙሉ ይጠጣል። አብዛኞቹ የህወሃት አባላት እድሜያቸው እንደ አስተሳሰባቸው ስላረጀ ጨዋታቸው ከውሃ ጋር ነው። ከውድ ውሃ ጋር! ድንጋይን ውሀ ያስጮኸዋል! ሜዳው የኢህአዴግ፣ ዳኛው ኢህአዴግ፣ ታዛቢው ኢህአዴግ፣ ድምጽ ቆጣሪው ኢህአዴግ እንዲሆን ተደርጎ የተዘጋጀው “ምርጫ” እነሆ ተጠናቀቀ። በአፈና የታጀበው ምርጫ ጸጥ-እረጭ ባለ ድባብ ተጠናቅቋል። ልክ አስገድደው እንደሚደፍሩ ወሮበሎች፤ በሃይል ጠልፈው ያላቻ ትዳር እንደሚመሰርቱ ጉልበተኞች፣ የኢትዮጵያ ሕዝብ ያለፍቃዱ እንደገና የአምስት አመት የትዳር ቁርኝት ውስጥ ገብቷል። ሌላ አምስት አመት። ሌላ የህወሀት ዘመን። ሌላ የጥርነፋ ዘመን! ሌላ የቁምራ ዘመን! ሌላ የመፈናቀል ዘመን! ሌላ የመሬት ነጠቃ ዘመን! ሌላ የስደት ዘመን!… የህወሃት ሰዎች አሁን የጭንቀቱ ምእራፍ ሁለት ላይ ናቸው። በዛሬው እና በትላንቱ እለት የህወሃት ባለስልጣናት ተሰባስበው በፐርሰንቱ ምደባ ላይ ውይይት ይዘዋል። ዘረፋው ላይ ሁሉም በ 100% ይስማማሉ። ምደባው ላይ ግን ችግር አለ። አንዳንዶቹ ይህ ጉዳይ ተአማኝነት እንዲኖረው ለተቃዋሚዎቹ ትንሽ መልቀቅ ይኖርብናል ሲሉ ለሎች ደግሞ ይህንን ሃሳብ ይቃወማሉ። ጥቂት ተቃዋሚዎችን ፓርላማ እንዲገቡ መፍቀድ አለብን የሚሉ ተከራካሪዎች “ሌባ ከሰረቀው ጥቂቱን ቢሰጥ” እንደማይጎዳው ይናገራሉ። ይህንን የማይቀበሉት ግን የተቃዋሚዎች በፓርላማ መግባት ራስ ምታት እንደሚሆንባቸው በስፋት መክረዋል። 547 መቀመጫ የነበረው የቀድሞው ፓርላማ ውስጥ እውነትን የያዘ አንድ ተቃዋሚ ብቻ ጭንቅላታቸውን በጥብጦት እንደነበር ሁሉም አይዘነጉትም። ይህንን በድጋሚ መፍቀድ አልያም ውግዘቱን በመቀበል መሃል ባለ አጣብቂኝ ውስጥ ከርመዋል። ውጤቱን ከሰሞኑ ይፋ ያደርገዋል ዶ/ር መርጋ። የዘንድሮው ዝርፍያ ጤናማ አይደለም። ልክ እንደ ቦራት ዘ-ዲክታተር ፊልም ተወዳዳሪዎችን እግር እግራቸውን እየመቱ ለብቻ ሮጦ፤ በራስ ዳኛ የድል ዋንጫ መረከብ? ይህ በእውነት በዚህ በ21ኛው ዘመን እጅግ የሚያሳፍር ተግባር ነው። ተቃዋሚ ሃይሎች በምርጫው ክርክር እና በትውልድ ስፍራቸው ላይ የነበራቸው የሕዝብ ድጋፍ ምን ያህል እንደሆነ በግልጽ በታየበት ሁኔታ ህወሃቶች 100% አሸንፈናል ሲሉ ከሌብነታቸው ይልቅ ንቀታቸው ጥርስ የሚያስነክስ መሆኑን ለአፍታ እንኳ አላስተዋሉትም። እጅግ ትንሽ ጭል ብላ የነበረችውን ዲሞክራሲ በምድረ ኢትዮጵያ ገድለው፣ ከፍነው ቀበሩት። አዲዮስ ዲሞክራሲ… ፈረንጆች የሚሉት አባባል አለ። “ለነብሰ-ገዳዮች ትክክለኛ ዲሞክራሲ ማለት ፍጹም አንባገነን መሆን ነው።” “በ100% ድምጽ ተመርጠናል!” አሉ። የመረጣቸው ህዝብ የቱ ይሆን? በአዲስ አበባ በነቂስ ወጥቶ “ወያኔ በቃን! መንግስቱ ይግደለን” ያለው ህዝብ ነው ወይንስ ለም መሬቱን ተነጥቆ ለባእድ የተሰጠበት የገጠር ህዝብ? በጋምቤላ፣ በቤንሻንጉል፣ በሁመራ…ወዘተ የተፈናቀለው ህዝብ ነው የመረጣቸው? ወይንስ አምቦ – ጉደርን እንደ ሱናሚ ያጥለቀለቀው ህዝብ ? የቱ ነው ወያኔን የመረጠው? ከስርአቱ ጋር ሆድና ጀርባ የሆነው ሙስሊሙ እምነት ተከታይ ነው ወይንስ በእምነቱ ጣልቃ እየገቡ ካድሬ ጳጳስ የሚሾሙለት ክርስቲያኑ ህብረተሰብ? ማን ነው ህወሃትን የመረጠው? እንደ ምጽዓት ለስደት እያኮበኮበ ያለው ስራ-አጥ ወጣት ነው ወይንስ በአነስተኛና ጥቃቅን ተደራጅቶ ድንጋይ የሚፈልጠው ወጣት ምሁር? መብራት እና ውሃ በፈረቃ ያደረጉበት ህዝብ ነው የመረጣቸው?… ለመሆኑ ስንት አመት ነው ህዝቡ ላይ እንዲህ የሚቀልዱት? እነሱ ልባቸው በትእቢት ስለተወጠረ፤ ሌላው ህዝብ የማይመለከትና የማይሰማ ይመስላቸው ይሆናል። ትእቢት ደግሞ የውድቀት ምልክት ናት። በመጀመርያ የውጭ ታዛቢዎች እንዳይገቡ ተደረገ። ዝም! በምርጫው ወቅት ደግሞ የተቃዋሚ ፓርቲ ታዛቢዎችን አሰሯቸው። አሁንም ዝም ተባለ። ከዚያ ኮሮጆ እየተሞላ ቀረበና በቁም ያሰሯቸው ታዛቢዎችን ምሽት ላይ ፈትተው እንዲፈርሙ አዘዝዋቸው። የተያያዙት አስገድዶ መድፈር ነውና አንዳንዱን አስገድደው በተሰረቀ የድምጽ ሳጥን ላይ አስፈረሟቸው። ምርጫ 2007 በዚህ ሁኔታ “ሰላማዊ፣ ፍትሃዊ፤ ዲሞክራሲያዊና የህዝብ ተዓማኒነትን አግኝቶ” ተጠናቅቋል ሲሉ ፕ/ር መርጋ በቃና አበሰሩ። እኚህ ፕሮፌሰር ግን ህሊና ይኖራቸው ይሆን? ካላቸው በምን ለወጡት? በገንዘብ? ህሊና ስንት ያወጣል? አለም አቀፍ መገናኛ ብዙሃን ከምርጫው በኋላ ስላለው ነገር ብዙም አላሉም። ማን እንደሚያሸንፍ እና በምን ያህል ድምጽ እንደሚያሸንፍ አስቀድመው ዘግበው ስለነበር ውጤቱን መድገም የፈለጉ አይመስልም። አስቀድሞ ውጤቱ የታወቀበት ምርጫ መሆኑን አለም አቀፍ መገናኛ ብዙሃን ብቻ ሳይሆኑ፣ ራሱ የምርጫው ቦርድ በድረ-ገጹ ላይ በግልጽ አስቀምጦት ነበር። የምርጫው ቦርድ በድረ-ገጹ እንዳስቀመጠው የኢሕአዴግ 501 ተወዳዳሪዎች የተመዘገበለት ሲሆን መድረክ 270፣ የሰማያዊ ፓርቲ 139 እጩዎች ብቻ እንዲኖራቸው ተደረገ። የሰማያዊ ፓርቲ 200 እጩዎች በምርጫ ቦርዱ ተሰርዘውበታል። 108 እጩዎች አስመዝግቦ የነበረው አንድነት ፓርቲም ስልታዊ በሆነ ዘዴ በቦርዱ እንዳይሳተፍ ታግዷል። ይህ እንግዲህ በሎተሪ ሰበብ የተገለሉትን ሳይጨምር ነው። መቼም ይታገሉታል እንጂ አይታደሉትምና ቀኑ እስኪደርስ የኢትዮጵያ ሕዝብ ባልፈለገው ሊገዛ፤ ባላመነበት ሊዳኝ፣ ባልመረጠው ሊተዳደር ነው። አሁንም ዝምታን መርጧል። ዝምታ ራሱን የቻለ መልስ ነው። በዝምታ የተዋጠች እያንዳንድዋ ሰከንድ ቁርሾ ይዛ ማለፍዋም ግልጽ ነው። ማሰብ ላልተሳነው ሁሉ ዝምታ ያስፈራል። ምጥና ውሃ ሙላት በድንገት እንዲሉ ዝም ያለ ወራጅ ሲወስድ አይታወቅም። ጽዋም ሲሞላ ይፈስሳል… አለም-አቀፉ ህብረተሰብም ዝርፊያውን ስለለመደው ችላ ብሎታል። የእንግሊዙ “ዘ ጋርዲያን” ጋዜጣ “ምርጫውን ለአብዛኛው ኢትዮጵያዊ እንደ አንድ ክስተትም አይቆጥረውም።” ሲል፣ ሂዉማን ራይትስ ዎች፤ አምነስቲ ኢንተርናሽናል፣ ፍሪደም ሃውስ፣ ሲፒጄ፣ የመሳሰሉት አለም አቀፍ የመብት ተከራካሪ ተቋማት አፈና የሰፈነበት እና ነጻ ሜድያ በሌለበት ሁኔታ የሚካሄደው ይህ ምርጫው ፍሱም ኢ-ፍትሃዊ እንደነ ገልጸዋል። አልጃዚራ፣ ዋሽንግተን ፖስት፣ ኒውዮርክ ታይምስ የመሳሰሉ ታላላቅ ሜድያ ውጤቱ አስቀድሞ የታወቀ ምርጫ ሲሉ ሂደቱን በክፉ ኮንነውል። ነገሩ ግልጽ ነው። ነጻ ሜድያ በሌለበት፣ ገለልተኛ ታዛቢዎች ባልተፈቀዱበት፣ ነጻ ዳኛ በልተመደበበት ነጻ ምርጫ አይታሰብ። የዘንድሮው ክስተት ህወሃት የዘረፋ ደረጃውን ያወረደበት ምርጫ ነው። ከረቀቀ የዘረፋ ስልት ወደ ግልጽ የውንብድና ተግባር። የጀርመን ድምጽ እንግሊዝኛው ክፍል ከምርጫው በኋላ ምንጮችን ጠቅሶ ሲዘግብ “ታዛቢዎ የቁም እስር ላይ ስለነበሩ ወደ ውጭ ወጥተው ምርጫውን መታዘብ አልቻሉም” ብሏል። የሰራዊት እና የሚሊሽያ አባላት በየምርጫ ጣብያው እየተገኙ መራጮችን እያስፈራሩ የተካሄደ ምርጫ በአለም ላይ ይህ ብቻ ነው። የምርጫ ዘመቻም በታጠቁ ሃይሎች ወታደራዊ ትእይንት የተካሄደው በኢትዮጵያ ብቻ ነው። 30 አመት ሙሉ ያል ህዝብ ፍቃድ በስልጣን መቆየት ይሰለቻል። እነዚህ ሰዎች የምእተ አመቱን አንድ አራተኛ የሃገሪትዋን ሃብት ብቻ ሳይሆን የህዝብን ድምጽም እየዘረፉ ተቀመጡ። ባለፉት 24 አመታት በአሜሪካ አምስት ግዜ መንግስት ተቀይሯል። በሆላንድ 7 ግዜ መንግስት ወርዶ በህዝብ ድምጽ ሲቀየር አይተናል። አፍሪካዊቷ ጋና አምስት ግዜ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ፣ ሶስት ግዜ ፓርላሜንታዊ ምርጫ አድርጋለች።… ያልታደልን ወይንም ያልታገልን እኛ ግን ለ30 አመታት በአንድ አንባገነን ተይዘናል። ህወሃቶች በሩን ሁሉ ዘግተው ህዝቡን ወደማይፈለገው አመጽ እየገፉት ነው። ያልተረዱት ቢኖር አንደኛው በር ሲዘጋ ሌላኛው በር መከፈት መቻሉን ነው። የ90 ሚሊዮን ህዝብን ድምጽ ሰርቀው፣ አንደበቱን ለጉመው ምን ያህል እንደሚዘልቁ የምናየው ይሆናል። መቶ አመት የዘለቀ አንባገነን በታሪክ አልተከሰተም። ከዚህ ቀደም ባስነበብኳችሁ ቀልድ ጽሁፌን ልቋጭ። አንድ የህንድ ኢንቨስተር አዲስ አበባ ዮሴፍ ቤተ ክርስቲያንን የቀብር ስፍራ አይቶ በሊዝ ሊገዛ ፈለገ። የአዲስ አበባ ባለስልጣናትን ጠርቶ እንዲሸጡለት ጠየቀ። ባለስልጣናቱም መልሰው ሌሎች ቦታዎች ሳያልቁ የቀብር ስፍራ ለግዜው እንደማይሸጡለት ነገሩት። ህንዱ መለሰና መከራቸው። “እኛ አገር ሰው ሲሞት እናቃጥላለን እንጂ አንቀብርም። ለምን ይህን ለም ቦታ ታባክናላችሁ?” አላቸው። ባለስልጣናቱም መለሱ፣ “እኛ አገር ደግሞ ሰውን በቁሙ እንጂ ሲሞት አናቃጥልም!”

Wednesday, May 27, 2015

የወያኔ/ኢህአዴግ ተግባር ፍየል ወዲህ ቅዝምዝም ወዲያ። በስብሰባ ጋጋታና በባዶ ፕርፖጋንዳ እንዳንፈታ ትግሉ ይፋፋም!


                                                                  የተሰጠ መግለጫ
የወያኔ/ኢህአዴግ ተግባር ፍየል ወዲህ ቅዝምዝም ወዲያ። በስብሰባ ጋጋታና በባዶ ፕርፖጋንዳ እንዳንፈታ ትግሉ ይፋፋም!
ግንቦት 14 ቀን 2007ዓ.ም
page1image2376 page1image2536
የችግራችን ቀጣይ ክስተቶች ለትምህርተ ሥርዓቱ ከጊዜ ወደ ጊዜ ማሽቆልቆልና የውድቀት ጠርዝ መድረስ አስተዋጽኦ ማድረጋቸው ባይካድም ያለፉትን መንግሥታት በመኮነን ከምንም በላይ ራሱን የለውጥ ሐዋሪያና የዕደገት ተምሳሌት አድርጎ የሚቆጥረው ወያኔ/ኢህአዴግ በዕውቀት ላይ የተመሰረተ የትምህርት አመራር ከመስጠትና ችግሮችን ከመፍታት ይልቅ ይበልጥ ውስብስብና ሊፈቱ ከማይችሉበት ደረጃ አድርሷቸዋል።
በሚሊዮን የሚቆጠሩ ተማሪዎች በመምህራን እጥረት፣በመማሪያ ክፍሎች፣ በማስተማሪያ መጻሕፍትና በሌሎችም የትምህርት ግብአቶች እጥረት የተነሳ የተሟላ ትምህርት የማያገኙበት፣ ተማሪዎች ከመቼውም ጊዜ በላይ ተስፋ የቆረጡበት ፣ ፈተና በአንድና በሁለት ደቂቃዎች ሰርተው የሚያጠናቅቁበት፣ ጭራሹን ትምህርታቸውን ለማቋረጥ የሚገደዱበት ወቅት ስለሆነ ትምህርት ቀውስ ውስጥ ገብቷል።
የዚህ ቀውስ አንዱ ማሳያ ሊሆን የሚችለው ወያኔ/ኢህአዴግ በሶስት ምድብ አመቻችቶ የማደናገሪያ /የማጭበርበሪያ አጃንዳዎቹን ለማስፈጸም የሚሞክርበትን አካሄድ ቀጥሎ እንመልከት፡-
ከመምህራን ጋር ፡-በአንዳንድ አካባቢዎች በህዳር ወር 2007ዓ.ም መጀመሪያ ሳምንት በተደረገ የመምህራን ስብሰባ ከ2006ዓ.ም በፊት በነበሩት አመታት ትምህርታቸውን ያቋረጡ ተማሪዎች እስከ ህዳር ወር መጨረሻ 2007ዓ.ም ድረስ ትምህርት ቤት እንዲገቡ የሚል ሐሳብ በወያኔ ካድሬዎች ይቀርባል።ለዚህ የተሰጠው ምክንያት የምዕተ ዓመቱ ( የሚሊኒየሙ) የልማት ግብ በዚህ በያዝነው አመት ስለሚጠናቀቅ አሁን በመማር ላይ ያሉት መማር ከሚገባቸው ተማሪዎች ቁጥር ያነሰ በመሀኑ ያቋረጡትን “በቅስቀሳ “ በማምጣት ከመስከረም 2007ዓ.ም ጀምሮ እየተማሩ ካሉት ጋር እኩል ማድረስና የምዕተ ዓመቱን “ ትምህርት ለሁሉም” የሚለውን ግብ ማሳካት በሚል የቀረበ አጀንዳ ነበር። በዚህ አጀንዳ ላይ የመማር ተግባራቸውን አቁመው ለዓመታት ከትምህርት ገበታቸው ተለይተው የቆዩ ተማሪዎችን የትምህርት መጀመሪያ ዓመት ካለፈ ከወራት በኋላ መቀበል ማለትም እስከ ሀዳር ወር 2007ዓ.ም ያልተማሩትን በምን ተአምር ትምህርት እንዲያገኙ ይደረጋል? ከትምህርት ተለይተው የቆዩት ተማሪዎች ለተለያዩ ደባል ሱሶች የተጋለጡ ሊኖሩ ስለሚችሉ በነባሮቹ ላይ ተጽዕኖ ስለሚያሳድር የትምህርት ቤቶችን ድሲፕሊን ይጎዳል በሚል መምህራን ተቃውመውታል።ሥርዓቱ ፊቱ ላይ የሚታየው የአፈጻጸም ሂደት የውጭ ርዳታ ማግኘትን ትኩረት ሰጥቶ ንዋይ መሰብሰብ ዋናው ዓላማ ሆኖ ትምህርቱና ትውልዱ እንዲሞቱ ተፈርዶባቸዋል በማለት አስተያየት እየሰጡ ስብሰባውን ረግጠው እሰከመውጣት ደርሰዋል።
ከዚህ በመቀጠል በታህሣሥ ወር መጨረሻ 2007ዓ.ም በአማራ ክልል የሁለተኛ ደረጃ ት/ቤቶች መምህራንና ተማሪዎች ለ3 ቀናት የሚቆይ
 •   የተሀድሶ መስመርና የኢትዮጵያ ህዳሴ
 •   የልማታዊ ዴሞክራሲያዊ ሥርዓትና በትግሉ የተገኙ ውጤቶችና ተግዳሮቶች
 •   2007.ም የትምህርት ንቅናቄ ሰነድ በሚሉ አጀንዳዎች ስልጠና የሚል ስያሜ ተሰጥቶት የስልጠናው ዓላማ መምህራንና ተማሪዎች በተጀመረው የልማትና የመልካም አስተዳደር ላይ ግልጽነት እንዲኖር ለማድረግ የሚል ሆኖ ቀጥሎ ያሉት ንዑስ ዝርዝሮች ተካተዋል።
 1. የተጀመሩትን ኢክኖሚያዊ፣ ማህበራዊና ፖለቲካዊ ለውጦች ከዳር ለማድረስና የአጋጠሙ ተግዳሮቶችን ፈትሾ የአገራችንን የተሀድሶ ጉዞ ከትምህርት ማህበረሰብ ጋር ያለውን ፋይዳ ለመመዘን፣
 2. ልማታዊ አስተሳሰብ የተሀድሶው መነሻ በመሆኑ ሁላችንም ልማታዊ አስተሳሰብ እንድንይዝ ለማስቻል፣
 3. የህዳሴው የጉዞ ደረጃና መድረሻ ምን እንደሆነ ለማስገንዘብ፣
page1image21704
 1. ችግሮችን መለየትና ለውጡን በጠራ አቅጣጫ ለመምራት የሚያስችሉ ግብአቶች ለማግኘት፣
 2. የተደራጀ የትምህርት የልማት ሠራዊት ግንባታ ለትምህርት ጥራት የማይተካ ዓላማ አለው፣ስለሆነም በተበታተነ
  አደረጃጀት ጥራት ማምጣት ካለው ፋይዳ ጋር ለመገምገም፣
 3. 2007 .ም የትምህርት በጀት የዕድገትና የልማት ዕቅዱ ማጠቃለያ ስለሆነ የቀሩንን ለይተን ርብርብ ለማድረግ
  ሰላማዊ የመማር ማስተማር ሂደት ወሳኝ ስለሆነ ፣
 4. የአገራችን የተሀድሶና የህዳሴ ጉዞ የሚያጋጥሙትን ተግዳሮቶች አውቆ ርብርብ ለማድረግ እንዲያስችል ታስቦ
  የተዘጋጃ መሆኑ በካድሬዎች ተነግሮ አስፈላጊ ነው ወይስ አይደለም የሚል ጥያቄና የአስተያየት ሀሳብ ከራሳቸው ከካድሬዎች ይነሳል።
ለነዚህ ከላይ ለተዘረዘሩት በትምህርት ስልጠና ስም በወያኔ ለቀረበው የፖለቲካ አጀንዳ የመምህራን መልስ ይህ አቀራረብ በየቀኑ ከምንሰማው ፕሮፖጋንዳ የተለየ አይደለም፣ ሰነዱ የስልጠና ይዘት የለውም፣ለስልጠናም የሚያግዝ የማቴርያል ( የቁሳቁስ) አቅርቦት የለም፣ እንዲያውም በትምህርቱ የንፍቀ ዓመት ( የሴምስተሩ አጋማሽ ወቅት) መዘጋጀቱ የትምህርትን ሂደት የሚጎዳ ስለሆነ አስፈላጊ አይደለም የሚል በመሆኑ ውዝግብ ተፈጥሮ ስልጠና ተብዬው ለግማሽ ቀን ያህል ተቋርጦ ከቆየ በኋላ ከመምህራን ፍላጎት ውጪ በካድሬዎች ጫና ሊቀጥል ችሏል።
ከዚሁ ጋር ተያይዞ ከትምህርቱ ጉዳይ ጋራ በማጣመር የቀረቡት አንዳንድ ትምህርት ነክ አጀንዳዎች ዓላማቸው የወያኔን የተሳሳተ የፖለቲካ መሰመር ጥሩ ገጽታ ለማላበስ የቀረቡ ናቸው። ሐሳብን በነፃነት የመግለጽና የመደራጀት መብት ፣ የብሔርና የሃይማኖት እኩልነት ተረጋግጧል በማለት የውሸት ድስኩሩን በሰብሰባዎቹ ወቅት አቅርበዋል።እንዲሁም ከአማራ ክልል የተወሰደ መሬት የለም፣የድሮዋን ኢትዮጵያ የተሻለች አድርጎ ማቅረብ፣ የአማራ ሕዝብ እንደተዋረደና ዝቅ ተደርጎ እንደሚታይ ማቀንቀን፣ ፌዴራሊዝም ኢትዮጵያን ለማፈራረስ የታቀደ ነው ማለት ፣ የአንድ ብሔር የበላይነት እንዳለ አድርጎ መቀስቀስ የትምክህትና የጠባብነት መግለጫዎች ናቸው በማለት የወያኔ ካድሬዎች በሕዝብ ላይ የፈጸሙትንና እየፈጸሙ ያሉትን እውነት ክደዋል። መቼ ወያኔና እውነት ይታዋወቃሉ? በሀይማኖት ስም የፖለቲካ አጀንዳ ይዞ ወደ ሕዝብ መግባትና ሕገመንሥቱን መቃወምና ኢትዮጵያ የክርስቲያን ደሴት ናት አንድ አገር፣ አንድ ሀይማኖት፣ በመጅሊሶቻችን መሪዎቻችንን እንዳንመርጥ መንግሥት ጣልቃ እየገባ ነው ፤የሸሪአ ሕግ መመስረት አለበት ፤ የእስላም መንግሥት እናቋቁማለን ፤ በትምህርት ቤቶች መስገጃ ቦታ ይፈቀድልን የመሳሰሉት በክርስትናና በእስልምና እምነት ተከታዮች የሚንፀባረቁ የአክራሪነት መገለጫዎች ስለሆኑ በትግል መፍታት ይገባል ተብሎ በካድሬዎች በኩል ለቀረቡት አስተያየቶች የመምህራኑ መልስ ለካድሬዎች የቀና አልነበረም። ቀድሞውንም በስልጠናው ይዘትና አካሄድ ደስተኛ ያልነበሩት መምህራን ባንድ ድምፅ ተቃውሞቸውን በማሰተጋባት እኛ አንድ ነን፣ አትከፋፍሉን፣አንከፋፈልም በማለት በጩኸት፣ በፉጨት፣ በሞባይል ወኔ ቀስቃሽ የሆኑ የቀረርቶና የሽለላ ዜማዎችን በማሰማት የካድሬዎችን የውሸትና የተንኮል ፕሮፖጋንዳ ጆሮ ሳይሰጡ በወቅቱ መምህራን ያሳዩት ተቃውሞና የትግል ተነሳሽነት የሰርዓቱን ውድቀት አይቀሬነት አመላካች ነበር።
እንዲሁም በሌሎች የአገሪቱ ክፍሎች በትምህርትና በመምህራን ላይ የሚፈጸመው በደል ዘርፈ ብዙ ነው። በደቡቡ የአገራችን ክፍል የእርከን ጭማሪ ለርዕሳነ መምህራንና ለሱፐርባይዘሮች ተፈቅዶ ለመምህራን የተከለከለ መሆኑን ለተለያዩ የዞን ት/ቤቶች አሰተዳደር ከደቡብ የትምህርት ቢሮ የተለከው ደብዳቤ ያሳያል። ወያኔ ለይስሙላው ምርጫ መጠቀሚያ ለማድረግ የድርጅቱ አባል የሆኑትን መምህራን በትምህርት ቤት ቅጥር ግቢ በትምህርት ሰዓት ስብሰባ በማካሄድ በትምህርት ላይ በደል እየፈጸመ ይገኛል። በ11/07/2007 በሀድያ ዞን ውስጥ በዋቸሞ መሰናዶ ት/ቤት ለወያኔ የምርጫ ድራማ ለ25 የወያኔ/ኢህአዴግ አባል መምህራንና ሰራተኞች ስልጠና በሚል የትምህርት ፕሮግራም ተቋርጦ ስብሰባ እንዲገቡ በመደረጉ የቀሩት የድርጅቱ አባል ያልሆኑ 75 መምህራን በድርጊቱ በመናደድ ፣ በትምህርት ቤት የትምሀርትን ክፍለ ጊዜ በማቃወስ የፖለቲካ ስብሰባ መካሄዱን ተቃውመው ወደ ቤታቸው ሄደዋል። ተማሪዎቹም አስተማሪ ስላጡ ወደየቤታቸው ለመሄድ ተገደዋል። በዚህም ሁኔታ የትምህርት ስራ ለሁለት ቀናት ተቋርጧል።ይህን ሁኔታ በመከተል በአካባቢው በሚገኙ ት/ቤቶች የሚያስተምሩ የወያኔ ደጋፊ ያልሆኑ መምህራን ተመሳሳይ እርምጃ በመውሰድ ተቃውሟቸውን አየገለጹ መሆናቸው ተረጋግጧል። መቀጠል ያለበት የትግል ስልት ነው።
ከተማሪዎች ጋር በተደረገው ስብሰባም ከተነሱ ጥያቄዎች መካከል በሌሎች አገሮች የስልጣን ዘመን የተገደበ ነው።እናንተ ግን ወደ ስልጣን ከወጣችሁ 23 ዓመታት ሆናችሁ። ስልጣናችሁን ልቀቁ፣ እናንተን አንመርጥም፣ በቃችሁ። የሕግ የበላይነት አለ ትላለችሁ አቶ አንዳርጋቸው ጽጌን ከ6 ወራት በላይ እንዲሁም ሌሎችን ፍ/ቤት ሳታቀርቡ በእስር ማቆያታችሁ የተያዙ ሰዎች በአርባ ስምንት ሰአታት ውስጥ ፍ/ቤት የመቅረብ መብት አላቸው የሚለውን ሕገ መንግሥታዊ ድንጋጌ አይጻረርምዎይ? በትምህርት ቤት ተማሪዎችን በኢህአዴግ አባልነት ትመለምላለችሁ ፣ በህዋስ በአንድ ላምስት ታደራጃላችሁ፣ ትምህርት ቤት በማናቸውም ረገድ ከሃይማኖት ፣ ከፖለቲካ አመለካከቶችና ከባሕላዊ ተጽዕኖዎች ነፃ መሆን አለበት ከሚለው ሕገ መንግሥታዊ ድንጋጌ አይጻረርምዎይ? ተቃዋሚዎች ይህን በት/ቤቶች እንዲያደርጉ ተፈቅዳላችሁዎይ?-----የመሳሰሉትን ጥያቄዎች በማንሳትና ኢህአዴግ ይውደም!ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር! የሚል መፈክር በማሰማት ስብሰባው ያለምንም መግባባት በልዩነትከመጠናቀቁም በሻገር ተማሪዎች ለነሷቸው ጥያቄዎች የወያኔ/ኢህአዴግ ካድሬዎች መልስ መስጠት ተስኗቸው እንደነበር ለመራዳት ተችሏል።
ወያኔ/ኢህአዴግ ከአባላቱ ጋር በጥር ወር 2007ዓ.ም መጨራሻ ባካሄደው ስብሰባ ከአባላቱ በርከታ ጥያቄዎችና አስተያየቶች ቀርበዋል። ከነዚህም ለተቃዋሚዎች መፈራረስ የኢህአዴግ እጅ አለበት ፣ ኢህአዴግ ዲሞክራሲ አለ ይላል ግን ያስራል፣ ይገርፋል፣ ይገድላል። ይህን እየፈጸማችሁ ከደርግ በምን ትሻላለችሁ? የአማራ ወጣቶች በሌሎች ክልሎች ተቀጥረው አይሰሩም? የሌሎች ክልሎች ወጣቶች ግን በአማራው ክልል እስከ መሾም ይደርሳሉ። የእኛ አገር የሕዝብ ተወካዮችና ሌሎችም ምርጫዎች ከሌሎች አገሮች ምርጫዎች ጋር እንዴት ይነጻጸራል? ለመንግሥት ሠራተኞች የተሰጠው የደመወዝ ጭማሪ ፍትሐዊ አይደለም። አርሶአደሩ ከይዞታ መሬቱ ያለበቂ ካሣ እየተፈናቀለ ነው ለዘለቄታው ምን ታስቦበታል? የድርጅት አባላት ድርጅቶቻቸውን ያማርራሉ ችግሩ ምንድነው? አየለ ጫሚሶና መሰሎቹ የኢህአዴግ ሽርጥ ለባሾች እንጂ ተቃዋሚ አይደሉም ---ወዘተ የመሳሰሉ ጥያቄዎችና አስተያየቶች ተሰጥተው ከመድረክ መሪዎች የተሰጡ ምላሾች ቁጣን በመቀስቀሳቸው ስብሰባው ያለምንም መግባባት ተጠናቋል።
በሌላ በኩል በመንግሥት መስሪያ ቤቶችም ሆነ በትምህርት ቤቶች በበጀት እጥረት የተነሳ ስራ ወደ መቆም የተቃረበበት ፣ ካድሬዎች ከምርጫ ጋር በተያያዘ በስብሰባ የተጠመዱበትና ፍርሃታቸው ከምንጊዜውም በላይ ገዝፎ እርስ በርስ አለመተማመን ደረጃ ላይ የደረሱበት ፣ ሰራተኛው ፊት ለፊት ስርአቱን እየሞገተ ጥላቻውን በግልጽ እያሳየና ለስርዓት ለውጥ ለሕዝባዊ እምቢተኝነት ራሱን እያዘጋጀ እንደሆነ ይታያል።
የኑሮ ውድነቱ፣ የስራ ዋስትና ማጣት ፣ የመብት ረገጣው፣ የመልካም አስተዳደር እጦት -----ያስመረራቸው መምህራን የተለያዩ የመብት ጥያቄዎችን በማንሳት ላይ ይገኛሉ።ከእነዚህ ውስጥ የሚጠቀሱ በደሴ ከተማ የሚገኙ የአንዳንድ ት/ቤቶች መምህራን ለተመሳሳይ ስራ ተመሳሳይ ክፍያ ይደረግ፣የመምህራን የዕድገት መሰላል ( Career Structure) በአንዳንድ ክልሎች ተሻሽሎ ተግባራዊ ሲሆን በሌሎች ክልሎች ለምን አይተገበርም ? የቤት አበል ( Housing allowance) ለምን ተግባራዊ አይሆንም? የቤት መስሪያ ቦታ ያለምንም ክፍያ በነፃ ልናገኝ ይገባል። የትምህርት ጥራትን እናረጋግጣለን እየተባለ በይድረስ ይድረስ በዘፈቀደ በለብለብ ለመህራንና ለሌሎች ባለሙያዎች ስልጠና እየተሰጠ ነው፣ ይህ በአስቸኳይ እንዲቆም እንጠይቃለን። የተሰጠው የደመወዝ ጭማሪ የኑሮ ውድነቱን ያላገናዘበ ስለሆነ እንደገና ማስተካከያ እንዲደረግበት የሚሉ ጥያቄዎችን በማንሳት በየካቲት ወር 2007ዓ.ም መጀመሪያ ፒቴሽን ተፈራርመው ለሚመለከታቸው አካላት በማቅረብ ጥያቄዎቹ አስቸኳይ መልስ ካልተሰጣቸው የስራ ማቆም አድማ እንደሚያደርጉ አስታውቀዋል። ይህ በደሴ ከተማ መምህራን የተነሳው ጥያቄ በአገሪቱ የሁሉም መምህራን ጥያቄ፣ ከዚያም ባለፈ ባጠቃላይ የሠራተኞች ጥያቄ ስለሆነ ለተግባራዊነታቸው ዜጎች ሁሉ እንዲተባበሩና ትግሉን እንዲያግዙ በሰደት የኢትዮጵያ መምህራን ማህበር አባላት አስተባባሪ ኮሚቴ ጥሪውን ያቀርባል።
በዚህ ጽሑፍ ወያኔ/ኢህአዴግ መምህራንን ፣ ተማሪዎችንና የራሱንም አባላት በተለያዩ ጊዜያት ሰብስቦ ለማወያየት መሞከሩን አይተናል። በተለይ በመግቢያው ላይ በተመለከቱት የመወያያ አጀንዳዎች ላይ በነቂስ ለመተቸት አንድ መድበል የሚወጣው ስራ ይጠይቃል። በጥቂቱ ቀንጨብ አድርገን ለማሳየት እንገደዳለን። ልማታዊ አስተሳሰብ ምንጩ ጥሩ የኢኮኖሚ ፖሊሲ ነው። የፖሊሲው ቅኝት በአንድ ዘረኛ ፓርቲ ቁጥጥር በዋሉና ንብረትነታቸው የፓርቲው የሆኑ ኩባንያዎች ያለገደብ ያለውድድርም ተጠቃሚዎች በሆኑበት ስርአት ፣ ሌሎች የግል ባለሐብቶች ወደዳር በሚገፉበት ሁኔታ አባባሉ ጉንጭ አልፋ ከመሆን አይዘልም። የህዳሴው መነሻና መድረሻ ሕዝብ በወጉ እንዲያውቀውና እንዲቀበለው ያልተደረገ በሂደቱም የጠራ አቋም ይዞ በፍላጎት ላይ በተመሰረተ ስሜት የማይሳተፍበት ፣ የጉልበት፣ የዕውቀት፣ የማቴርያል፣ የገንዘብ እገዛ እንዲያደርግ የሚያዘጋጁ ስነልብናዊ ሁኔታዎች ባልተመቻቹበት ዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ከየት ወዴት የሚለውን ጥያቄ ያስነሳል።በዚሁ ላይ ዕድገት በተመጽዋችነት ፣ በርዳታና በብድር ውጤታማ የሆነበት አገር በ50 እና 60 አመታት አልታየም። በተለይ ኢትዮጵያን በመሰሉ የአፍሪካ አገሮች ያተረፈው ነገር ቢኖር የአምባገነኖችን ኪስ ማሳበጥና የአገዛዝ ጡንቻቸውን ማጠንከር ሆኗል። ስለዚህ በአገዛዝ ስር ያለ ሕዝብ የዕድገትና ሽግግር መለኪያው የአገዛዙን ከንቱ ውዳሴ ከማጉላት ውጪ የሚታይ አይሆንም።
ስለትምህርት ፖሊሲው ሰንካላነት፣ ስለካርኩሉም፣ ስለመምህራን ምልመላና ስልጠና ስለትምህርት ግብአቶች ጥራትና ተደራሽነት ችግር----በተለያዩ መግለጫዎች ለሕዝብ ለማሳወቅ ሞክረናል። ብዙ አገር ወዳድ ምሁራንም በተለያዩ ጊዜያት ስለትምህርቱ ውድቀትና ትውልድ ገዳይነት ትችት አቅርበውበታል።ሌላው ቀርቶ መምህራን በነፃነት በሙያቸው ተደራጅተው ስለትምሀርቱ ሂደት በተለይና ስለአገራቸው ጉዳይ ባጠቃላይ የበኩላቸውን አስተዋጽዖ እንዳያደርጉና ብሔራዊ ግዴታቸውን እንዳይወጡ በሚያግድ ፣በሚያደናቅፍና ማህበራትን በአንድ ፓርቲ ዕዝ በሚያስገባ ስርዓት “የተምህርት ሠራዊት ግንባታ” የሚል ርዕስ የተካተተበት አጀንዳ መምህራንን ለማደናገር ማቅረብ ቧልት በመሆኑ የወያኔ ስብሰባ ውሉ ጠፍቶበት መጠናቀቁ ታይቷል። ትምህርቱንና ትውልዱን የመግደል የወያኔ ስልት ገና ከመነሻው 42 የዩኒቨርሲቲ ዕውቅ መምህራንን በማባረር አሳይቷል።አሁን በቅርቡም ሁሉቱን ብርቱ የዩኒቨርሲቲ መምህራን አባሯል። ስለትምህርቱ ጥራትና ውድቀት ከተባራሪዎቹ አንዱ ዶ/ር ዳኛቸው አሰፋ ያለበቂ ዝግጅት፣ ብቃት ያላቸው መምህራን ሳይኖሩ፣ የትምህርት ግብአቶች በሚፈለገው ደረጃ ሳይመቻቹ በየጨካው ዩኒቨርሲቲ መክፈት ምርታማ ዜጎችን የማያወጣና የአገሪቱን አንጡራ ሀብት እንደማባከን እንደሚቆጠር አመላክተዋል።ማን ያርዳ የቀበረ ፣ ማን ይንገር የነበረ እንዲሉ። ይህ ሕዝብን የማደንቆር ፖሊሲ አንድ ቦታ ካልቆመ

የትውልድ ግድያው ይቀጥላል። የትምህርት አፓርታይድ የተከለው ወያኔ ሕዝብን አደንቁሮ የመግዛት ኃይሉ እየጎለበተ ከመሔዱ በፊት ወላጆች፣ተማሪዎች ፣ ሌሎች የሕብረተሰቡ አካላት ለአሁኑና ለተተኪው ትውልድ ዕጣ ፋንታ መቆም ይጠበቅባቸዋል።
ለዚህ ነው መምህራን በየወቅቱ ፣ በየቦታው የተቃውሞ ድምጻቸውን እያሰሙ ያሉት። በራሳቸው ላይ ቤንዚን በማርከፍክፍ መስዋዕት የሆኑት። ጩኸታቸውን ኢትዮጵያውያን በያሉበት አስተጋበተው ትውልዱን ከድንቁርናና ከሞት እንዲታደጉ በሰደት የኢትዮጵያ መምህራን ማህበር አባላት አስተባባሪ ኮሚቴ ጥሪውን በድጋሚ ያቀርባል።

ለስርዓት ለውጥ ትግሉ ይፋፋም!! በትምህርትና በባለሙያዎች ላይ መቀለድ ያብቃ!! ትምህርት የዕድገት መሰላል ነው! መወጣጫው አይፋለስ!! 

Monday, May 25, 2015

የኢትዮጵያ ምርጫና ዉዝግቡ

ኢትዮጵያን ለአስራ-አራት ዓመት የመራዉ የቀድሞዉ አማፂ ቡድን ኢሕአዴግ ጠመጃ-መትረየሱን አስቀምጦ (ባንዳዶች አገላለጥ ደብቆ) የምርጫ ካርድ የጨበጠበት፤ ተቃዋሚ ፖለቲከኞች ክፍፍል ንትርካቸዉን ሸፍነዉ ባንድ የቆሙበት፤ ጋዜጠኞች፤ የመብት ተሟጋቾች፤የሲቢል ማሕበራት ድንከመታቸዉን በጥንካሬ-የከደኑበት-ታሪክ።ያኔም ታዲያ ግንቦት ነበር።

ኢትዮጵያዉያን መረጡ።አልመረጡምም።ትናንት።ታሪክ ለሞላባት፤ ከታሪክ ብዙም ለማትጠቀመዉ፤ ምንም ለማትማረዉ ግን ታሪክ ለማትጠግበዉ ሐገር ሌላ-ታሪክ።
እነሱ ድምፅ ሰጡ።መረጡ።እነዚሕኞቹም ድምፅ ሰጥተዋል።ግን አንድም አልመረጡም።ሁለትም መራጭ፤አስመራጩ ፈጣሪ ነዉ ባይ ናቸዉ።
እነሱ አልመረጡም።ግን ተመረጠላቸዉ።
Wahltag in Äthiopien
እሷ በርግጥ መርጣለች። ሌሎቹንም ታሳስባለች። በእንግሊዝኛ-አማርኛ ቅይጥ ቋንቋዋ። ማሳሰቢያዉ ለነሱ ነዉ።ለ ወጣቶቹ።
እሳቸዉ ፖለቲከኛ ናቸዉ። የምክር ቤት እንደራሴ። ኢትዮጵያ መረጠች፤ አልመረጠችም። ወይስ ተመረጠላት።ከትናንት የተረፈን ጥያቄ። ግንቦት 1983 እስከ ዛሬ ላልተመለሰ ጥያቄ-የዳረገ ታሪክ ተፈፅሞባት ነበር።የአስራ-አራተኛ ክፍለ-ግዛትዋ ነፃነት ከአዲስ አበባ የተፈቀደበት፤ወደብ አልባነቷ የተረጋገጠበት-ታሪክ።
አስራ-ሰባት ዘመን የፀናዉ ወታደራዊ፤ ሶሻሊስታዊ መንግሥት በእስከያኔዉ አማፂ ቡድን የተተካበት፤ የሠላም፤የዴሞክራሲ፤ የፍትሕ ተስፋ የተንዠቀዥቀበት-ታሪክ።በርግጥም የተስፋዉን ያክል አይሁን እንጂ ኢትዮጵያ ከቀድሞ አካሏ-ከአዲስ ጎረቤትዋ ጋር መቶ ሺዎችን ካረገፈዉ ጦርነት እስከተዘፈቀችበት ድረስ አንፃራዊ ሠላም ሰፍኖባታል።ያኔም ግንቦት ነበር።1990
ከጦርነቱ በፊት ብቅ ያለዉ የመድብለ ፓርቲ ሥርዓት፤ የፕረስ ነፃነት፤የፍትሕ ዴሞክራሲያ መርሕ በጦርነቱ መሐልም፤ በጦርነቱ ማግሥትም ብልጭ ድርግም እያለ አዝግሞ ታሪካዊቱን ሐገር ለሌላ ታሪክ አቀበለ።ለ1997ቱ።
ኢትዮጵያን ለአስራ-አራት ዓመት የመራዉ የቀድሞዉ አማፂ ቡድን ወያኔ ጠመጃ-መትረየሱን አስቀምጦ (ባንዳዶች አገላለጥ ደብቆ) የምርጫ ካርድ የጨበጠበት፤ ተቃዋሚ ፖለቲከኞች ክፍፍል ንትርካቸዉን ሸፍነዉ ባንድ የቆሙበት፤ ጋዜጠኞች፤ የመብት ተሟጋቾች፤የሲቢል ማሕበራት ድክመታቸዉን በጥንካሬ-የከደኑበት-ታሪክ።ያኔም ታዲያ ግንቦት ነበር።1997።የሠላም፤ የዴሞክራሲ፤ የፍትሁ ተስፋ-ከተስፋ አልፎ በገቢር ብልጭ ያለበት ምርጫ።ግን-በ1983ቱ ግንቦት የሠፈረባት ዛር-ምሥ- ግብሩ ደም ሆነና-1997ቱን ምርጫ ያጀበዉ ቦረንትቻም ዉል ስቶ-በዉዝግብ፤ ግጭት፤ግድያ፤ እስራት እመቃ፤ ክፍፍል አሳረገ።
በአምስተኛ ዓመቱ፤ በ2002 ሌላ ምርጫ ሲደረግ በ1997 እንደ ተወርዋሪ ኮኮብ ተግ-ቦግ፤ብሎ ባፍታ ጥፍት-ድርግም ያለዉ ተስፋ በርግጥ ትዝታ ነበር።ግን እንደገና ግንቦት።እንደገና ምርጫ።እንደገና አዲስ ታሪክ።ምናልባትም የሉሲን በመሠለ ቅርሷ፤ ቀይ ቀበሮን በመሰሉ አራዊቶችዋ፤ የአዉሮጳ ቅኝ ገዢዎችን ድል በመንሳት ጀግንነቷ፤ በዓለም የምትደነቀዉ ሐገር።በ2002ትም ነፃ ምርጫ አስተናገደች ተብላ ለገዢ ፓርቲዋ ወያኔ የ99,6 በመቶ ድል አስመዝግባ ዓለምን አስደነቀች።
በያኔዉ ምርጫ-ለምክር ቤት እንደራሴነት የበቁት ብቸኛዉ የተቃዋሚ ፓርቲ አባል አቶ ግርማ ሠይፉን ሥለ ትናንቱ ምርጫ እንዲነግሩን «ሐሎ» አልናቸዉ ዛሬ።
የመረጠም፤የተመረጠለትም፤ ምርጫ የለም ብሎ ተስፋ የቆረጠዉም ኢትዮጵያዊ ተቃራኒ ስሜት የተንፀባረቀበት የትናንቱ ምርጫ ሌላ ዕዉነትም ታይቶበታል።ዕዉነት አንድ፤- የቀድሞዉ የኢትዮጵያ ጠንካራ መሪ ጠቅላይ ሚንስትር መለስ ዜናዊ ከሞቱ ወዲሕ ለመጀመሪያ ጊዜ የተደረገ ነዉ።ዕዉነት ሁለት፤ ከዚሕ ቀደም የተደረጉ ምርጫዎችን በተለይም የ1997ቱን እና 2002ቱን በቅርብ የተከታተሉት የአሜሪካዉ የካርተር ማዕከል እና የአዉሮጳ ሕብረት ታዛቢዎች ሒደቱን አልተከታተሉትም።
የካርተር ማዕከል የዘንድሮዉን ምርጫ ያልታዘበበትን ምክንያትን በግልፅ እናዉቅም።የአዉሮጳ ሕብረት ግን ታዛቢዎቹን ላለመላኩ-የኢትዮጵያዉ ጠቅላይ ሚንስትር አቶ ሐይለማርያም ደሳለኝ የሰጡት ምክንያት የሐብታሙ ማሕበር «የገንዘብ፤ በጀት እጥረት» ሥላለበት የሚል ነበር።የአዉሮጳ ሕብረት ባለሥልጣናት ግን በሰወስት ወር ዉስጥ ሰወስት ምክንያቶችን ተናግረዋል።የብራስልሱ ወኪላችን ገበያዉ ንጉሴ-ያስታዉሰዋል።
በትናንቱ ምርጫ ድምፁን ለመስጠት 37 ሚሊዮን ሕዝብ ተመዝግቦ ነበር።ከተመዘገበዉ ድምፁን የሠጠዉን ሕዝብ ቁጥር ለማወቅ ትንሽ ጊዜ ይጠይቃል።የምርጫዉ ዉጤም እንዲሁ።አቶ ግርማ ግን መራጩንም-ዉጤትንሙ መገመቱ አይገድም ባይ ናቸዉ።
የትናንቱን የድምፅ አሰጣጥ ሒደት የተከታተሉት ፖለቲካ ተንታኝ ሳንዴ ኦኬሎ እንደሚሉት ከምርጫዉ ዘመቻ ጀምሮ ደከማ የነበሩት ተቃዋሚ ፓርቲዎች ከትናንቱ ምርጫ «ተዓምር ሊጠብቁ አይገባም» ባይ ናቸዉ።
«በምርጫ ዘመቻዉ ወቅት ገዢዉን ፓርቲ በቅጡ የፈተኑ፤ ጠንካራ ተቃዋሚዎች በእዉነቱ አላየሁም።ይሁንና አንዳዶቹ ተቃዋሚዎች ሐሳቦቻቸዉን በግልፅ ለማሳየት የሞከሩ ነበሩ።ብዙ ቁጥር ያለዉ ድምፅ በማግኘት ግን ገዢዉን ፓርቲ የሚያሰጉ አይደሉም።»
ቁጥር-የመቶኛ ሥሌቱ ባናዉቀዉም ወያኔ ማሸነፉ እርግጥ ነዉ።እና ኢትዮጵያን መምራቱን ቢያንስ ለአምስት ይቀጥላል።ኢትዮጵያ ከዉጪ በተለይም ከምዕራባዉያን ጋር የሚኖራት ግንኙነትም በነበረበት መቀጠሉ የማይቀር ነዉ።ገበያዉ ወደፊት ይታያል።ነጋሽ መሐመድ ነኝ ቸር ያሰማን።

Saturday, May 23, 2015

የተበላ ዋንጫ- ቢንያም ግዛው


የመስመር ዳኞቹ እና የመሀል ዳኛው የአንድ ሀገር ዜጋ ናቸው። ቋንቋቸው ፥ የለበሱት ማልያ እና ጠባቃይቱ ቁምጣ ፥ በልካቸው ተጥፈዋል። ከግራ ከቀኝ በሚያራግቡት አንድ አይነት ባንዲራ እና ከእግር አጣጣላቸው እንዲሁ በጨረፍታ ላያቸው በአንድ ካምፕ ውስጥ የሰለጠኑ እና የብዙ አመት አራጋቢዎች እንደሆኑ በቀላሉ ማወቅ ይቻላል። የመሀል ዳኛው ከእሱ ፍላጎት ውጪ የሆነውን እንቅስቃሴ በማስቆሚያ እና በማስቀጠያ ፊሽካ አፉ ታፍኖ ባፍንጭው ብቻ በመተንፈሱ ምክንያት አይኑ ስለሚጉረጠረጥ ቶሎ ተናዳጅ ሰዎች ከሚባሉት ወገን እንደተወለደ ለማወቅ ዘር መቁጠር አያስፈልግም ።ሰሜናዊ ነው።
ከተጋጣሚዎቹ አንደኛው ቡድን ከዚህ በፊት እንደተለመደው የተሰጠውን ገፀ ባህሪ ሊተውን ነው የሚጫወተው። ለመሸነፍ ብቻ ሰልጥኗል። የሚገርም ግጥሚያ!!! የዋንጫው ባለቤት የሚሆነው ተጋጣሚ ኳስዋን ሳይነካ፥ ሜዳው ውስጥ ሳይገባ አሸንፏል። ሌላ ሜዳ ላይ ጥለዛውን እና ፍልሚያውን አጠናቅቆታል ።የይስሙላው ጨዋታ ግን ተሰይሟል ። ጨዋታውን ለማየት የከበቡት ምስኪን የሆኑ የዋሀን ከልባቸው በቲቮዞነት ተቀምጠዋል ። ጨዋታው ውድድሩ ምርጫው ድራማ አልመሰላቸውም።
24 ዐመታት ውስጥ ለ አራት ጊዜ የተደረጉትን ግጥሚያዎች በአንባ ገነነት የዋንጫው ባለቤት የሆነው ወያኔ አዳዲስ የማታለያ ስልቱ እና ጥለዛዎቹን በማጠናከር እንዲሁም ምስጢራዊና ዒሰብዐዊ ማደናገሪያዎቹ እንዳይቀሰሙ ልምምዱን በቅጠረ ቤተ መንግስቱ በአራት ነጥብ ዘግቶት ነው የሚመጣው ።
በግጥሚያው ወቅት እንዴት ከጫፍ እስከ ጫፍ እንደሚለጉ ሀገሬው ሁሉ ጥለዛቸውን ያውቀዋል። በጣም ይጠልዛሉ። የተለዩ ጠላዥ አካላት አሏቸው።እንዲህ ያለርህራሔ ጠልዘው እንዴት ዋንጫውን አይበሉ። ሹታቸው ሀይለኛ ነው። በያቅጣጫው ነው የሚሾቱት። መሾት ለምደዋል። ወደ ውድድሩ ለመግባት በኢትዮጵያውያን አቆጣጠር ከየካቲት 11/ 1967 ጀምሮ በየክልሉ ባደረጉት ልምምዶች ሁሉ ጎል አግቢ ነበሩ። ፍርድ የተገመደለላቸው ጎሎች። ኡኡኡ የሚያስብለው ቴስታውና ረገጣውን ሁሉም ያስታውሷል።
በኢትዮጵያ ምድር ላይ የ40አመት የጥለዛ እና የሹት ልምምድ ቀላል ነው ብሎ ማሰብ ይከብዳል ማለቴ በመሾት፥ በመጠለዝ እና በማጎን አቅጣጫ ። ከርግጫቸው የተነሳ ብዙ የተነፈሱ እና ድጋሚ ግልጋሎት የማይሰጡ ኳሶች ጭርምት ጭርምት ብለው የነጻነት አየር አጥሯቸው በየማጎሪያው ተጠራቅመዋል እየተጠራቀሙ ነው ገና ይጠራቀማሉ። ኢህአዴግ የተባለው አምባገነን እና ጫካ በቀል ቡድን ተገዳዳሪዎቹን ሁሉ ያለ ርህራሄ እንደ ትንኝ እሽሽሽ እያለ ሊያውም ሰውን እንደ ትንኝ ሊያውም ዳር ድንበሩን ጠብቆ አንድ ሆኖ የኖረን ጥቁር ህዝብ። ሊያውም ታሪካዊውን የኢትዮጵያ ህዝብ ። ደጉን ህዝብ ።
ይህ ነው አምባገነን ወያኔ ። ለእውነተኛ ተወዳዳሪዎች ነጻ ፍትህ የተሞላበት እድል ሳይሰጥ ብቻውን እየተወዳደረ ዋንጫውን የሚበላው ቡድን ተገዳዳሪዎቹን በጠረን ያውቃቸዋል። እውነተኛ፥ ሰላማዊ ፥ ህዝብን ሀይማኖትን ጎሳን የሚወደውን ሁሉን ኢትዮጵያዊ ከጨዋታ ውጪ ማድረግ እና ማኖ ማስነካት ክህሎቱ ነው። ቅጣት ምቱ እና ቆረጣ ስልቱ ሹሌ ተደምሮብት ደግሞ ማንም አይችለው። በእውነተኛነት የተጉትን፥ ሀገር ስትደማ፥ ስትራብ፥ ስትራቆት፥ ስትመዘበር፥ ከልጅነት እስከ እውቀት ብዕር የጨበጡ በወንድ ወኔያቸው እንባቸው በጉንጫቸው ላይ እንዳይወርድ ጥርሳቸውን ነክሰው ያቆረዘዘ አይናቸውን የማይጨምቁ ጸሀፍት እና ጋዜጠኞችን ድጋሚ እንዳያንሰራሩ ማድረግ ፈጣሪ ያልዘጋውን አንደበት መለጎም ለ40 አመታት የዳበረበት ጡንቻውን የቀረጸበት ለማፈን ለማረድ አገርን ለመቆራረስ የጠበደለበት ነው።
እናም በዚህ ጨቃኝ አገዛዝ የህዝብ እጅ ሳይጠመዘዝ የምርጫ ኮሮጆዎች ሳይመዘበሩ የምርጫን ነገር ማሰብ ላም አለኝ በሰማይ ይሆናል። የኢትዮጵያ ህዝብ ዋንጫውን ከሩቅ ያየዋል እንጂ እንዲሁ በወያነ ዘመን በሰላማዊ ግጥሚያ መሸናነፍ ይህ በህልም አለም ሙቅ ማኘክ ይሏል። ወያኔ ዋንጫው የግሉ እንደሆነ ያውቃልና የብዙ ገና የብዙ አመት ራዕይ አለው የመስረቅ ፥የመክፈል፥ በጎሳ የመሸንሸን፥ የማቃረን፥ በኢትዮጵያውያን ልብ የእርስ በእርስ በቀልን የመጠንሰስ፥ ሌላም ሀገሪቷን የመስበር ጎዞ።
ይህን የኢትዮጵያን ጠላት ታሪክ አብጠርጥሮ የሚያውቀው ኢህአፓ የወያኔ ነውር ገላጭ እና ራስ ምታት ስለሆነ በኢትዮጵያ ምድር ባይተዋር ለማድረግ ተሞክሯል ነገር ግን በኢትዮጵያዊያን ልብ ላይ ታሪኩ እና ገድሉ ስለታተመ ከህዝብ ሊለየው መቼውንም ቢሆን አይችልም። አሁንም ቢሆንም ባሀገሪቷ ውስጥ ባሰለጠናቸው ወጣት ታጋዮቹ አማካይነት በህቡዕ ትግሉ እንደቀጠለ ይገኛል። ስለዚህም ከከተመበት አቅጣጫ ላይ ሆኖ የኢትዮጵያ ህዝብ የድሉ ባለቤት እስከሚሆን ድረስ በአንድ መንፈስ ይጋደላል ።
ለብዙ የፖለቲካ ፓርቲዎች እና ቡድኖች አባት፥ መምህር እና ምሳሌ ሆኖ የረዥም ዐመት የትግል ስልት ያለው የኢትዮጵያ ህዝባዊ አብዮታዊ ፓርቲ /ኢ ህ አ ፓ/ በብዙ ዲምክራሲያዊነት በተሞሉት መድረኮቹ እና ልሳኑ የወያኔን ሰው በላነት ከተጨባጭ ማስረጃ ጋር አጎልቶ እያሳየ ወያኔን በትግል ጥረት በህዝባዊ አመጽ እናስወግድ የሚለው። የዚህ ጽሁፍ መነሻም ወያኔ በግፍ ከገደላቸው
የኢ ህ አ ፓ ጓዶቼና መሪዎቼ መንፈስ ጋር ስወያይ ያገኘሁት ብልጭታ ነው።የኔ የሚሉት ነገራቸው ኢትዮጵያ እና ኢትዮጵያዊነት እንጂ ሌላ የሌላቸው ጀግኖቻችን ፀጋዬ ገ/መድኅን (ፀጋዬ ደብተራው) ፤ ይስኃቅ ደብረ ጽዮን ስጦታው ሁሴን ፥ በለጠ አምሃ ፥ አበራሽ በርታ ፥ ደሳለኝ አምሳሉ እና ሌሎችም የሞቱለት የተዋደቁለት አላማ የኢትዮጵያ አንድነት እና ሎአላዊነት የጸና ለማድረግ ነው። አሁንም እኛ ወጣቶች የእነርሱን ፈለግ ተከትለን ትግሉን ለማፋፋም ቃል እንገባለን ።
ኑ ለአንድነት! ኑ ለትግል! በሀገራዊ አመጻችን ወያኔን ከኢትዮጵያ ጫንቃ ለይ እናውርደው! ፀረ ወያኔ ትግል በየአቅጣጫው ይፋፋም!!!
ታዲያ ማነው ያባቶቹ ወኔ የሚቀሰቅሰው ? ለነጻነቱ የሚታገል? ከሀገር ውጪም በሀገር ውስጥም አውነተኛ ኢትዮጵያዊ? በበረታ አንድነት ወያኔን የሚገጥመው ? ለኢትዮጵያዊ ጥሪ ባለበት ስፍራ አቤት የሚል ምላሽ ያለው? ማነው የጀግና መንፈሱ ወኔው በመከራ ያልተሰለበበት? በቃ!በሚል መፈክር ጨቋኙን የኢትዮጵያ ጠላት የሚያስውግድ?
መፍትሔው ህዝባዊ አመፅ ብቻ ነው። ስለሆነም ለአንድነት እንነሳ ፥ እንታገል ፥ የኢትዮጵያን ጠላት ከስር ከመሰረቱ ወያኔን እናድክመው። በአንድነት መንፈስ እንቁም።
ድል ለኢ ት ዮ ጵ ያ ህዝብ !!!!
እናቸንፋለን!!!
ቢንያም ግዛው

ከኖርዌይ

Friday, May 22, 2015

ከእንግዲህ ቀልድ የሆኑ ምርጫዎችን አብረን ማፅደቅ የለብንም ብለን ስለወሰንን ነዉ። Ana Gomes ( አና ጎሜስ ) European Parliament


የእሁዱ ምርጫና ታዛቢዎች

ኢትዮጵያ የፊታችን እሁድ ግንቦት 16 ቀን 2007ዓ,ም አምስተኛዉን ብሔራዊ ምርጫ ታካሂዳለች። ከአፍሪቃ በሕዝብ ብዛት ሁለተኛ ደረጃ ላይ በምትገኘዉ ሀገር በዘንድሮዉ ምርጫ ከ50 በላይ ፓርቲዎች ይሳተፋሉ።
በምርጫዉ ድምፁን ለመስጠትም ከ36,8 ሚሊዮን ሕዝብ በላይ መመዝገቡን የሀገሪቱን የምርጫ አስፈፃሚ አካል የጠቀሱ ዘገባዎች ያመለክታሉ። ምርጫዉን ለመታዘብ ከሀገር ዉስጥ ምርጫ ቦርድ ከሚያሰማራቸዉ ሌላ ከዉጭ የአፍሪቃ ኅብረት ታዛቢዎች ብቻ እንደሚገኙ ተገልጿል። ከዚህ ቀደም በኢትዮጵያ የተካሄዱ ምርጫዎችን የታዘቡ የአዉሮጳ ኅብረትም ሆነ የአሜሪካዉ ካርተር ማዕከል ታዛቢዎች አይገኙም። የ1997ቱን ምርጫ የታዘቡት የአዉሮጳ ኅብረት ልዑካን መሪ ታዛቢ መላክ አስፈላጊ አይደለም ይላሉ። 
የዘንድሮዉ ምርጫ ከ1983 እስከ 2004,ም ድረስ በመንግሥት ስልጣን ላይ ከነበሩት ከቀድሞዉ ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ሕልፈተ ሕይወት በኋላ የሚካሄድ የመጀመሪያዉ ምርጫ ነዉ። ዓለም አቀፉ ኅብረተሰብ ድምፁን ለመስጠት የተመዘገበዉ ሕዝብ ብዛት በሀገሪቱ የተሻለ ዴሞክራሲ ሰፍኖ እንደሁ የሚፈትንበት አጋጣሚ እንደሆነ መጠቆሙን የዜና ዘገባዎች ያመለክታሉ
የሰብዓዊ መብቶች ተሟጋቾች ገዢዉ ፓርቲ የተቃዋሚዎችን ደጋፊዎች እና ጋዜጠኞችን ይጫናል፤ እንዲሁም ፀረ ሽብር ሕጉን በመጠቀም የዜጎችን ድምፅ ያፍናል ተቺዎቹንም ያስራል ሲሉ ይከሳሉ። ከሁለት አስርት ዓመታት በላይ ስልጣን ጨብጦ የሚገኘዉ ገዢዉ ፓርቲ በበኩሉ በምርጫዉ ስኬት ለማግኘት ያከናወናቸዉ የልማት ተግባራት በቂ እንደሆኑ እንደሚገልፅ አዣንስ ፍራንስ ፕረስ ከአዲስ አበባ ዘግቧል። 
የቀድሞዉ ጠቅላይ ሚኒስትር በጎርጎሪዮሳዊዉ 2012,ም ከዚህ ዓለም በሞት በመለየታቸዉ በመንበራቸዉ የተተኩት ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ የሀገሪቱን የፖለቲካ ስርዓት ለቀቅ በማድረግ ለተቃዋሚ ፓርቲዎች የተሻለ ስፍራ ለመስጠት ቁርጠኛ መሆናቸዉን መግለፃቸዉም እንዲሁ ተሰምቷል። ባለፈዉ ዓመት ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያ በሰጡት መግለጫ «ትክክለኛ የመድበለ ፓርቲ ዴሞክራሲ በዚህች ሀገር ካልኖረ ሀገሪቱ እንደሶማሊያ ልትሆን ትችላለች» ማለታቸዉን የፈረንሳይ የዜና ወኪል ጠቅሷል። ተቃዋሚዎች ግን መንግሥት በምርጫዉ ድሉን ለማረጋገጥ የፈላጭ ቆራጭነት ስልት ይጠቀማል ሲሉ ይከሳሉ። ፓርቲና መንግሥት አለመለየታቸዉ፤ መገናኛ ብዙሃን፤ የፀጥታ ኃይሎችና ገንዘብ በመንግሥት ቁጥጥር ሥር መሆናቸዉንም እንደዋና ችግር ይጠቅሳሉ። በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች የሚንቀሳቀሱ እጩዎቻቸዉም መጠነሰፊ ወከባ እየደረሰባቸዉ ነዉ ሲሉም ተቃዋሚ ፓርቲዎች አቤቱታቸዉን ያሰማሉ። 


የምርጫዉ አስፈፃሚ አካል ግን እነዚህን አቤቱታዎች ሁሉ መሠረተ ቢስ ሲል ያጣጥላል። የብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ፕሬዝደንት ፕሮፌሰር መርጋ በቃና የዘንድሮዉ ካለፉት ዓመታት እጅግ የተሻለ ነዉ፤ ለተቃዋሚ ፓርቲዎች የተመቻቸዉ ምህዳርም ልዩ ነዉ ማለታቸዉን አዣንስ ፍራንስ ፕረስ ዘግቧል። 
ለእሁዱ ምርጫ የምርጫ ኮሚሽኑ 40 ሺህ የሚሆኑ የሀገር ዉስጥ ታዛቢዎችን በ45 ሺህ 795 የምርጫ ጣቢያዎች ያሰማራል። ዘንድሮ ብቸኛዉ የዉጭ የምርጫ ታዛቢ አካል የአፍሪቃ ኅብረት ነዉ። ኅብረቱ 59 ታዛቢዎችን ያሰማራል። የ1997ቱንና የ2002ቱን ምርጫ የታዘቡት የአዉሮጳ ኅብረትና የአሜሪካዉ የካርተር ማዕከል ግን ዘንድሮ አይገኙም። የዶቼ ቬለ የአማርኛዉ ክፍል ኃላፊ ሉድገር ሻዶምስኪ ያነጋገራቸዉ በ1997,ም የአዉሮጳ ኅብረት የምርጫ ታዛቢ ልዑካን መሪ የነበሩት አና ጎሜዥ ምርጫዉን ለመታዘብ መሄድ እንደማያስፈልግ መወሰኑን ይናገራሉ።
«ላለመሄድ በትክክል የወሰንነዉ የሀሰት ምርጫ እንደሚካድ እያወቅን ያንን ለማረጋገጥ ታዛቢ መላክ እንደሌለብን ስላመንን ነዉ። ቀልድ ነዉ የሚሆነዉ፤ ምክንያቱም ፍፃሜዉ ልክ በ2002 እና በ1997 እንደነበረዉ ነዉ የሚሆነዉ። ሕዝቡ በብዛት ድምፁን ሊሰጥ ወጣ በቆጠራዉ ላይ አጭበረበሩ።» ፓርቱጋላዊቱ የአዉሮጳ ኅብረት አባል አና ጎሜዥ አያይዘዉም ኅብረቱ የምርጫ ታዛቢ ወደኢትዮጵያ ያልላከበትን ምክንያት እንዲህ ያስረዳሉ። 
«በዚህ የተነሳ ምክር ቤቱ ለሚስ ሙጌሪኒ ኢትዮጵያ ዉስጥ ምርጫ የሚታዘብ ተልዕኮ ሊኖር እንደማይገባ በማስታወቅ ደብዳቤ ጽፏል። የቲየስ በርመን እና የእኔ የ1997 የምርጫ ትዝብት ዘገባዎች በመንግሥት ተቀባይነት አላገኙም። ተግባራዊ ማድረግ ይቅርና እዚያዉ ተመልሰን እንኳን ዘገባችንን እንድናቀርብም አልፈቀደም። ምክንያቱን የሰሉ አስተያየቶችን በመያዛቸዉ። የኢትዮጵያ መንግሥት በአሁኑ ጊዜ የአዉሮጳ ኅብረት ለምርጫ መታዘብ ያልመጣዉ በገንዘብ እጥረት ነዉ ማለቱን አዉቃለሁ። ሆኖም ይህ ፍፁም እዉነት አይደለም። እኔ ራሴ ከአዉሮጳ ኅብረት የናይጀሪያን ምርጫ ለመታዘብ ሄጄ ገና መመለሴ ነዉ፤ በተለያዩ የአፍሪቃ ሆነ ከአፍሪቃ ዉጭ ሃገራትም የምርጫ ታዛቢ ልዑካን አሉን። ወደኢትዮጵያ የማንሄደዉ በበጀት ጉዳይ ሳይሆን በፖለቲካዊ ምክንያት ነዉ። ይህም ማለት ከእንግዲህ ቀልድ የሆኑ ምርጫዎችን አብረን ማፅደቅ የለብንም ብለን ስለወሰንን ነዉ።»