Friday, July 31, 2015

ከኢትዮጵያ ሕዝባዊ አብዮታዊ ፓርቲ በሳተላይት የሚተላለፍ የራዲዮ ፕሮግራም (EPRP's Satellite Radio transmissions to Ethiopia and Horn of Africa.)


የሐምሌ 23 ቀን 2007 ዓ.ም. ወቅታዊ ዜናዎች (July 30, 2015 TOP News)
* የወያኔ የአማራ ክንፍ ብአዴን ስብሰባ ሊቀመጥ ነው
* የወያኔ ደህንነት እና ጸጥታ ሰራተኞች ግምገማ ላይ ተቀመጡ
* የጦማሪያን ጉዳይ አሁንም ሌላ ቀጥሮ ተሰጠበት
* በኬኒያ ሙስና አሳሳቢ ደረጃ ላይ መድረሱ ተገለጸ
* የናይጄሪያው ፕሬዚዳንት ወደ ካሜሩን ሄዱ፤ ጥምር ኃይሉን የሚመራ ጄኔራል ናይጄሪያ መደበች
* በየመን በፈንጅና በሰው አልባ መንኮራኩር ሰዎች ተገደሉ
* መዳረሻው የጠፋው የማሊዢያ አውሮፕላን ክፍል ነው ተብሎ የሚጠረጠር የአውሮፕላን ስብርባሪ አካል አንድ ደሴት ውስጥ ተገኘ
ለዝርዝር ዜናዎች > ከታች ይጫኑ (to read/listen detail news click below)
TO READ Click here http://www.finote.org/news.html
To LISTEN PART 1 http://finote.org/July30EVE_Hr1B.mp3
To LISTEN PART 2 http://finote.org/July30EVE_Hr2B.mp3

ወርቁ ቢጠፋ ፤ ሚዛኑ ጠፋ ?

ፍኖተ ዴሞክራሲ የኢትዮጵያ አንድነት ድምጽ
Finote Democracy Voice of Ethiopian Unity
Efdpu@aol.com www.Finote.org 
ወርቁ ቢጠፋ ፤ ሚዛኑ ጠፋ ?


ዛሬ፤ ሕዝብን በሀገር ፤ ገበሬን በዕርሻ፤ ስብልን በማሳ፤ እህልን በጎተራ ፤ እንስሳትን በሜዳ፤ ህፃናትን በትምህርት ቤት፤ ቀሳውስትን በቤተ-መቅደስ፤ ሸኹን በመስጊድ፤ ራባዩን በምኩራብ፤ ወታደሩን በጠረፍ፤ ማግኘት ከማይቻልበት ሁኔታ ተደርሷል ። ላወቃቸው፤ ሁሉም የሀገር ቅርሶች ነበሩ። ክብራ ቸውንና ጥቅማቸውን በሚገባ ለተረዳ ዜጋም ፤ ዋጋቸው ከወርቅ፤ ከአልማዝና ዕንቁ፤ ከከበረ ድንጋይም ይበልጥ ነበር ።
በዛሬይቱ ኢትዮጵያ ግን እነኝህ ሁሉ የተከበረ ቦታ አልተሰጣቸውም ። እንዲያውም ቅስማቸው እየተሰበረ እንዲከስሙ እየተደርጉ ናቸው ። ማር ለአህያ እንደማይጥመው ሁሉ ፤ የሀገርን ጥቅም ፤ የሕዝብንም ክብር ፤ የማያውቅ ሥር ዓት አራማጅም እንዲሁ ፤ ለታሪክና ባህል ዋጋ አይሰጣም ። የራስ ማንነት ገላጮች ስለሆኑ ለሀገር ቅርሶች ደንታ አይኖረውም ። ሁሉንም ያጠፋቸዋል። ለታሪክ ቅርስነት እንዳይቆዩ፤ ያፈልሳቸዋል። ለተተኪው ትውልድ ለማሰረጃ እንዳያገለግሉ ደብዛቸውን ያጠፋዋል ።
ይህንን የሚያደርገውም፤ ጥንታዊቷና ታሪካዊቷን ኢትዮጵያን አጥፍቶ፤ ቅርሷና መልኳ፤ ማንነቷናም ባልታወቀች ሌላ ሀገር ስም ለመተካት ታስቦ ነው። ነገር ግን፤ ይህ አጥፊ ቡድን ፤ አንድ ያልተገነዘበው ጉዳይ ቢኖር ፤ ወርቁ ቢጠፋም ፤ ሚዛኑ ያልጠፋና የማይጠፋም መሆኑን ነው ። እኛ ደግሞ፤ የተወለድነው፤ ያደግነውና እየታገልን የምንሰዋው፤ ለዚያች ታሪካዊትና ዘለዓለማዊት ለሆነችው ኢትዮጵያ ብቻ ነው። ይህ የኅልውናችን፤ የትግላችንና የመሥዋዕታችን አልፋ- ኦሜጋ ሆኖ፤ በደማችንና አጥንታችን ውስጥ ተዋኅዶ ይኖራል ። እስከ ዘለዓለሙ ! እስከ ምፅዐቱ ! እስኪያልፍ ያለፋል እንጅ፤ መከራው አልፎ ብሩኅ ቀን እንደሚመጣ ግን አንጠራጠርም !
ወያኔን ተፃርረን የምንታገለው መሠረታዊው ምክንያት ይህ ነው ። ይህንን መሰረታዊ ምክንያት አንግበን ለመታገል የማንንም ምክር፤ ፈቃድና ርዳታ አንጠይቅም ። ኢትዮጵያዊነታችን፤ ከምንምና ከማንም በላይ ስለሚበልጥብን፤ በሀገራችን ብሄራዊ ጥቅም ላይ አንደራደርም ። ያንዱ ኃያል መንግሥት መሄድና የሌላው መተካት፤ ይህንን ፅኑ እምነትና አቋም አይለውጠውም ። አንደ በተሃ (?) አፍለኝነት፤ እንደ እስስት ተለዋዋጭነት፤ እንደ እባላ- ባዮች ጥቅመኝነት፤ እንደ ፀሀፍ (?)- ፈሪሳዊ አስመሳይነት፤ ባህርይ የለንም። ለመኖር ብቻ ሲባል ለመኖር የትግላችን መርኅ አይፈቅድልንም ። ይኸው ባህርይና ሰብዕና የመላውን ሕዝብ አመኔታ አትርፎልናል ብለን አናምናለን ።
ምክንያቱም፤ ወርቁ ቢጠፋም ሚዛኑ ስለአልጠፋ ነው ። ሚዛኑ ደግሞ ፤ የኢትዮጵያ ሕዝብ ማለት ነው ። ሚዛንን ከሕዝቡ ጋር ለማዛመድና አንድም ሁሉትም ናቸው ብሎ ለመናገር የሚያስችለው፤ የበለፀገ ታሪክ፤ የዳበረ ባህል ያለው በመሆኑ፤ አባይ ያልሆነ ሚዛን አለው ። ሁሉ-አቀፍ መሥተጋብርና ትክክለኛ የኅሊና ፍርድ ስጭ ሕዝብ በመሆኑ የማይናጋ ሚዛን ባለቤት ሕዝቡ ነው ። እንደ በተሃ ጠጅ አፍለኛ ያልሆነ ፤ እንደ ብረድስት ሽሮ በቀላሉ የማይገነፍል፤ ለመጣው ሁሉ የማይሰግድ፤ ሥልጣን ለጨበጠ ሁሉ የማያጎበድድና አሜን ብሎ የማይገዛው ፤ በጥቅመኞች ስብከት የማይታለል ፤ በፍየል ወጠጤዎች ድንፋታ የማይደነብር ፤ በእበላ-ባዮች ወከባ የማይበገር መሆኑን አረጋግጧል
።በዚህ ምክንያት፤ ሚዛኑን አስከብሮ ይኖራል ። ወርቁ ቢጠፋበትም ሚዛኑን አላጣም ። ማንም ሊያሳጣው አልቻለም ። ሕዝቡ፤ ልዕልናውንና ስብዕናውን ከኅሌና ሚዛኑ ጋር አዋኅዶ ቆይቷል። ዛሬም በዚሁ ሁኔታ አለ። ሚዛኑንን ለማንም ሳያስነካ ወደ ፊት መኖሩን ይቀጥላል ። ወርቁን ቢያጣም፤ ሚዛኑን አላጣም ። " ወርቁ ቢጠፋ ሚዛኑ ጠፋ ? የተባለውም እኮ ለዚህ ነበር !
የኢትዮጵያ ሕዝብ፤ የደርግን ጭካኔ ተቋቁሞ የተሻለ አስተዳደር ለማምጣት ሲል ከፍተኛ መሥዋዕት ከፈለ። ግን ፤ ለባሰ አስከፊ ሥርዓት ተጋለጠ እንጅ፤ የከፈለውን መሥዋዕት የሚመጥን ነፃነት እንኳን አላገኘም ። ያም ሆኖ ግን፤ ሚዛኑን ሳያናጋ ክብሩን ጠብቆ ለነገው ብሩኅ ተስፋ ይታገላል ። የሀገር ውስጥ፤ የአካባቢና የዓለም አቀፍ ሁኔታዎች ተባብረው ኅልውናውን ለማጥፋት ቢጥሩም ፤ ሀገራዊና ሕዝባዊ ሚዛኑን ሊያናጉበት አልቻሉም ። ወደፊትም ቢሆን ይደክማሉ አንጅ፤ ኢትዮጵያዊ ሚዛኑን ለማናጋት፤ ችሎታ አይኖራቸውም ። ያም ስለተባለ ኢትዮጵያዊ ሚዛኗን ጠብቃ የምትቀጥለዋን ሀገር አድርጎ ለማቆየት የሚደረገው ጥረት ሁሉ ቀላል ይሆናል ማለት አይቻልም ። ለዚህም በቂ ምክንያቶች አሉ ። የሚከተሉትን እንደ ማስረጃ መጥቀስ ይኖርብናል ።

1. የሀገሪቱን ችግሮች በሚገባ አለመረዳት ዋነኛው እንደሆነ ይታመናል ።
2. ሀገሪቱ ችግር ያለባት መሆኗ ቢታወቅም፤ እንኳ ፤ ጥልቀቱ፤ ስፋቱና ክብደቱ እስካሁን በቅጡ አልታወቀም ።
3. ችግሩ በሚገባ ካልታወቀ ደግሞ መፍትሄውን ማግኘት አይቻልም ።
4. የሀገሪቱ ዋና ችግር ፈጣሪ የሆነው፤ የሀገሪቱ ተወላጅ በመሆኑ፤ የባዕዳንን ሙሉ ትብብርና ድጋፍ ማግኘቱ፤ ችግሩን ውስብስብና ይበልጥ አስቸጋሪ ማድረጉ ። የባዕዳን ወራሪ ኃይል ባለመሆኑ ምክንያት፤ የውጭ ዕርዳታ ለማግኘት ከባድ መሆኑ ።
5. መፍትሄ ፈላጊ ነኝ የሚለው ክፍል አለመተባበሩ። ይልንቁም፤ ዕርስ በዕርሱ በመከፋፈልና እንዲያውም ለመፍትሄው ፍለጋ ደንቃራ መሆኑ።
6." የጨነቀው ሙቅ አነቀው " እንዲሉ፤ የሀገሪቱ ዜጎች ራሳቸው መፍትሄ ከመፈለግ ይልቅ፤ ምዕራባውያን መፍትሄ ያማጡልናል ብለው ቀቢፀ -ተስፋን ተስፋ እያደረጉ መጨነቅ፤
7. የኢትዮጵያን ሕዝብ ዕውነተኛ ማንነት ፤ ባኅርይ፤ ጠባይና ሥነልቦና በሚጋባ ያለመረዳት ችግር፤ እንታገላለን ብለው በሚንቀሳቀሱ ድርጅቶች ወስጥ መኖሩን መካድ አይቻልም ። ለዚህም ይመስላል፤ ብዙዎቹ፤ ኅብረት ፈጠርን ካሉ በኋላ፤ የተፈራረሙበት ሰነድ ላይ ያስቀመጡት ፊርማ ሳይደርቅ ወደ መፈራረስና ወደ ጠብ የሚሄዱት ።
የኢትዮጵያን ሕዝብ በሚገባ ባለማወቃቸው፤ ሕዝብን ወደ ማታለልና እራሳቸውንም ወደ መደለል ተግባር ይሰማራሉ ። ይህ ደግሞ ሕዝቡን በሚገባ ያለማወቅ ችግር ወጤት ነው ። እኛ፤ የኢትዮጵያን ሕዝብ ጠባይና ባኅርይ በሚገባ እናውቃለን የሚል ግብዝነት ባይኖረንም ፤ ማወቅ የምንቸለውን ያህል ግን በመጠኑም ቢሆን እንረደዋለን ። ሕዝብን በሚገባ ያለማወቅ ችግር፤ ከባድ ቸግር እንደሆነ የትግል ተመክሯችን አስተምሮናል ።
ከብዙ በጥቂቱ፤ እነኝህ ዋና ዋና ምክንያቶች ናቸው ብለን እንገምታለን ። ችግሮቹ በቀላሉ እሳካሁን ሊቀረፈቱ ያልተቻሉት፤ የችግሩ ፈጣሪዎች አምባገነኖች ብቻ ሳይሆኑ፤ እነርሱን ለማሰወገድ የሚችል ኃይል ለመፍጠር አለመቻላችን ጭምር ሆኖብናል ። ይህንንም አውቆ በድፍረት አለመናገር ደግሞ ራሱን የቻለ ሌላ ተጨማሪ ችግር እየሆነብን ቆይቷል ። እያንዳንዱ ዜጋ የራሱን ስኅተት እያወቀ የችግሩ አካል መሆኑን በድፍረት ካላመነ በስተቀር፤ እናም ለመፍተሄው ፍለጋ የራሱን ድርሻ እስካልተወጣ ድረስ፤ የሀገራችንን ችግር ማንም ባዕድ መጥቶ ይፈታልናል ብሎ መጠበቅ ግብዝነት ነው። " እራሳችን ያቀለልነውን አሞሌ፤ ሌላ ባለ ዕዳ ሊሸከምልን አይችልም ። ስህተተን አምኖ መቀበልና ፈጥኖ ማረም ፤ ብሎም፤ ይቅርታ መጠየቅ የታላቅነት ምልክት እንጅ፤ የድክመት ነፀብራቅ አይደለም !
የማነኛውም ሀገር መሪ መጀመሪያ ተጠያቂነቱና ኃላፊነቱ ለራሱ ሀገርና ለመረጠው ሕዝብ መሆኑን ሳንገነዘብ ፤ ፕሬዝደንት እከሌ ዋይም ጠቅላይ ምኒስትር እከሌ ሊረዳን ይችላል ብሎ መተማመን፤ የዓለምን ፖለቲካ ጠባይና አካሄድ አለመረዳት ብቻ ሳይሆን፤ የዋህነትም ጭምር ይሆንብናል ። ፕሬዝደንት ኦፓማ በቆዳቸው ጠይምነት የተንሳ ኢትዮጵያን ይረዳሉ ብለው ያመኑ ብዙ የዋሆች እንደነበሩ የቅርብ ትዝታችን ነው:፡ የሰው ልጅ ለምኞት ባይከለከልም፤ ጠይሙ ፕሬዝዳንት ባራክ ኦባማ፤ የተመረጡት የአማሪካንን ብሄራዊ ጥቅም ለማስጠብቅ መሆኑን ቃለ መሃላ ወስደው ነው። የኣሚሪካ ህግ ተገዥ በመሆናቸውም የሚያገለግሉትም ለአሜሪካ ህግና ደንብ ነው። የአሜሪካ ወታደራዊ- የኢንዱስትሪና ሁል-አቀፍ ጥቅምን ( American- Military - Industrial- Financial Interest ) ለመጠበቅና ለማስጠበቅ መሆኑን ማጤን ይግባናል ። እራሱ ያረረበት የሌላውን የሚያማስል ሞኝ የለም ። ቢፈልጉትም አይገኝም ። እየባከኑ መኖር ብቻ ነው ትርፉ ።
የሰሞኑን የኦባማ ኢትዮጵያን መጎብኘት አስመልክቶ ብዙ ቲያትሮች ሲውጠነጠኑ ታዝበናል ። የእርሳቸው አዲስ አበባ መገኘት፤ የወያኔን ልብና አዕምሮ ይለውጠው ይመስል፤ እስረኛች ይፈታሉ፤ ወያኔ የዘጋውን በር ለተቃዋሚዎቹ ይከፍታል ። የዴሞክራሲ ጭላኝጭል በሀሪቱ የፖለቲካ መልከዐ- ምድር ላይ መንዣበብ ይጀምራል፤ ሠርግና ምላሽ ሆኖ ሕዝቡ በደስታና ሀሴት ይፈነድቃል ወዘተ ተብሏል ። የሀገሪቱን የፖለቲካ ሁኔታ በቅርብ የሚከታተሉ ተንታኞች ያላቸው ግንዛቤ ግን ከዚህ ምኞት የተለየ ሆኗል ። የሚከተሉት ግንዛቤዎች ያስቀምጣሉ ።
1. የኦባማ ጉብኝት የአሜሪካንን ጥቅም በበለጠ ከማስጠበቅ የተለየ ትኩረት አይኖረውም ።
2. ታማኝ አገልጋይነቱን በተግባር ያስመሰከረላቸውን ወያኔን አበጀህ በርታ ከማለት ያለፈ ለሕዝቡ የሚጠቅም ፋይዳ አያመጣም ።
3ኛ የወያኔ አገዛዝ የሚ ጠነክርበትንና በሥልጣኑ ተደላድሎ የሚቀጥልበትን በበለጠ ከማጠናከር በቀር፤ ለሕዝብ የሚጠቅም ያመጣል ተብሎ አይጥበቅም ። የጠበቀም ካለ እንደናቱ ጡት ርሳው።
4. ኢትዮጵያ፤ የአሜሪካ ሀረግ ሬሳ ሪፑብሊክ ( Banana Republic ) መሆኗን የሚያረጋግጥ ይሆናል ።
5. ምናልባት ከእንግዲህ በኋላ፤ ተቃዋሚው ሁሉ፤ አሜሪካ ይረዳናል የሚለውን ተስፋ ሁሉ አሟጥጦ አንድ ላይ ለመተባበር በር ይከፍትለት ይሆናል።\
ይህንን የሚሰማ ሁሉ፤ ( " እባካችሁ አታስጎምጁኝ ") ሊል ይችል ይሆናል፡ ፡

ያም ተባለ ይህ፤ የኢትዮጵያ ሕዝብ ግን ሁሉንም ታዝቦ ጨርሶታል ።
አንቱ ባራክ ኦባማ ያማሪካ ዕንግዳ፤
ጎራ ብለው ነበር በምኒሊክ ግቢ፤ በወያኔ ጓዳ፤
እኛስ መስሎን ነበር እስረኛ ሊያስፈቱ ፤
ፍትህ ከጠፋበት ከወህኒ ቤቱ
ፍዳውን ሊያስቆሙ ረሀብ ርዛቱ
አንቱ ባራክ ኦባማ ያማሪካ ዕንግዳ፤
ሌላ ጉዳይ ነበር ለካ ያመጣዎ ፤
ወያኔን መርቀው እኛን ለመርገምዎ፤
ጩኸታችን ንቀው ጥለው መሄድዎ ፤
መላው የጦቢያ ሕዝብ እንዴት ታዘበዎ ።
ይብላኝ ለርስዎ እንጂ፤ እኛስ አንጎዳም፤ ኢትዮጵያም አትጠፋም፤
ይህንን ለማየት ግን ይቆዩ በሠላም ።
ብሎ ተችኝቶባቸዋል ፤ ለአሚሪካው ፕረዝደንት !
ወትሮውንም ቢሆን በታሪክ፤ ከራሱ በቀር በማንም የማይተማምነው ሕዝብ፤ዛሬ እንደገና ያንን ዕምነቱን በድጋሜ የሚያጠነክርለት ዕድል አግኝቷል ። ሁሉም ነገር ግልፅ ሆኖለታል ። ይኽውም ፤እራሱ ታግሎ ራሱን ነፃ ካላደረገ ፤ ማንም መንግሥት ሆነ ፤ ሀገር ወይም ዓለም አቀፍ ድርጅት ወይም ሰብዓዊና ሃይማኖታዊ ድርጅቶች ነፃ የማያደርጉት መሆኑን እንደገና አረጋግጧ
። ሁሉንም አማራጮች ሞክሮ ሞክሮ ስላልተሳካለት፤ አንድ ምርጫ ብቻ ቀርቶታል ። ይኸውም፤ በሁሉን አቀፍ ትግል የታጀበ ሕዝባዊ ኣመፅ! አካሄዶ፤ የራሱ ድል መጎናፀፍ ይሆናል ። ይህ እንዴት ይሳካል ? ማንስ ያሳካዋል ? የሚባሉትን መሪ ጥያቄዎች መመለስ ግን ወሳኝ ነው ።፡
የፖለቲካ ትግል በድል እንዲጠናቀቅ ካስፈለገ፤ የኃይል ሚዛኑን በራስ እጅ ማስገባት አስፈላጊ ይሆናል ። የኃይል ሚዛኑን የሕዝባዊ ወገን ለማደረግ ፤ የፀረ - ሕዝብን አከርካሪ አጥንትና የኃይል ስበት ማዕከል ማስበር የመጀመሪያው ዒላማ ሊሆን ይገባል ። " ዝርዝር ኪስ ይቀዳል " እንዲሉ ፤ ዝርዝር አፈጻጸሙና አካሄዱ በሙያው የተካኑ ብቁዎች የተግባር ድርሻ ይሆናል ። ይህ በቃል እንደሚያወሩት ቀላል ስላይደለ ፤ ብርቱ ተግባርንና ከባድ መሥዋዕትን መጠየቁ አይቀሬ ነው ። ለዚህ ደግሞ ቁርጠኝነትን ቀጣይነትንና ቆራጥነትን የሚጠይቅ መሆኑን መገንዘብ አስፈላጊ ነው። ይህንን ሳያሟሉ በጥድፊያ የሚደረግ ሸተክ- በተክ፤ ሠላማዊውን ሕዝብ አስፈጅቶ -አስጨርሶ " ዘቅዝቆ ሮጠ ወደ ቦንጋ ወንዝ ! " የሚል ትችትንና ፌዝን ከማትረፍ በቀር ፋይዳ አያመጣም ። አስቀድሞ ማሰብ፤ ከታላቅ ጥፋት ያድናል !
ወቅታዊቷ ሀገራችን የሚከተሉትን መልክ ይዛለች ።
1. የዛሬይቱ ኢትዮጵያ፤ ሁሉ እያላት ሁሉንም እንድትጣ የተደረገች ሀገር ሆናለች ።
2. ይህ ሁኔታ የ ዓለም ተመፅዋዕች ሀገር አድርጓታል ።
3. መላው ሕዝቧም ፤ " የመጀመሪያው ምርጫህ ምን እንዲሆን ትፈልጋለህ ? " ተብሎ ቢጠየቅ፤ ያላንዳች ማመንታት ፤ሁሉ፤ ከሀገሩ መውጣትን ያስቀድማል ። ወያኔና ተባባሪዎች ግን፤ ለእነርሱ ብቻ ምድረ-ገነት የሆነችው ሀገር ሰለሆነችላቸው ፤ ሌላውን እያባረሩ እነርሱ ይኖሩባታል ።
4. ዛሬ፤ የሀገሪቱን ስታራተጂያዊ/ ዘላቂ ጥቅም የሚያስጥብቅ ኃይልም ሆነ ማዕከል አለመኖሩ ፤ መፃዒ- ዕድሏ ወዴት አቅጣጫ እንደሚያመራ መተንበይ አልታቻለም ። ሕዝቧ፤ በሜሶፖታሚያ ሀገር፤ በሀረግ ተንጠልጥሎ እንደነበረ የአትክልት ቦታ እየዋለለ ይገኛል ።
5. የተቃዋሚው ክፍልም ፤ መልኅቅ ስለሌለው ፤ በከንቱ ይንሳፈፋል ። በመሆኑም የጋራ ስትራተጅ ነድፎ ለመታገል አልቻለም ። ሕዝቡም መሪ አጥቷል ። ተስፋ ቆርጧል ። በተፈራረቁበት ሦስት ሥርዓት ባጋጠመው የጭቆና አገዛዝ ምክንያት ፤ መንግሥት የሚባለውን ተቋምም ሆነ የፖለቲካ ድርጅቶችን ሊያምን አልቻለም ። አይፈረድበት !
6. የሀገራችንን ያልተነካ ጥሬ ሀብት ለመዘረፍ ባዕዳኑ መልካም አጋጣሚ አግኝተዋል። ያላንዳች ቁጥጥር፤ ይዘርፉታል ። ያሸሹታል።
ኢትዮጵያ ሀገራችን ዛሬ አንድ መሠረት ብቻ ይዛ ቀርታለች። ሚዛኑ ያልተዛባ ጨገሬታዋ ብቻ ! በመሆኑ፤ " ወርቁ ቢጠፋ ሚዛኑ ጠፋ ? " እያለች ለመቆየት ተግድዳለች !


ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኖራለች !

Monday, July 20, 2015

የትግልን ስልት ወሳኝ ማን ነው?

የፍኖተ ዴሞክራሲ የኢትዮጵያ አንድነት ድምጽ ሀተታ ሐምሌ 10 ቀን 2007 .. የተላለፈ
የትግልን ስልት ወሳኝ ማን ነው?
አንዳንዶች የትግልን ስልት ሊወስኑ የሚችሉት ምሁሮች ወይም የዘመናችን ዶክተር ደጃዝማቾች ናቸው ብለው ያምናሉ። ይህ ስህተት ነው ። ምሁሮች ነን ባዮቹ ራሳቸው በዚህ ስህተት ተዘፍቀው በዘፈቀደ ሰላማዊ ትግል በስተቀር ሌላ አማራጭ የለም ብለው ቁርጥ ያለና የተሳሳተ አቅዋም ይዘው መቆየታቸውን አስተውለናል ። ምን ዓይነት ትግል ሕዝብን ለድል ያበቃል ብሎ ወሳኙ ግን በስልጣን ላይ ያለው ገዢ መደብ ወይም ቡድን ነው ።
የሰፈነው ስርዓት የመወገጃውንም መንገድ ያረጋግጣል ። ዴሞክራሲያዊ ስርዓት ከሰፈነና አፈና ከሌለ በሰላማዊ መንገድ፤ በምርጫ ወዘተ... ለውጥን ማጣት ይቻላል፤ ይለመዳልም ። የጭቆና አገዛዝ ከሰፈነና ሕዝብ ፍላጎቱን ሊሟላ ባልቻለበት፤ አገዛዙ አረመኔና ፋሺስታዊ ሆኖ በተሰየመበት ግን ሁኔታው የሚጠቁመውና የግድ የሚያደርገው አመጽን ነው ። ሁኔታው ግድ የሚለውን መገንዘብ ካቃተና ላም ባዋልበት ኩበት ለቀማ ከተገባ ጨቋኙ አገዛዝ ይበረክታል። መድፍ ሲገባው ጭቃ ይወረወርበታል ማለት ነው ። ገዢው ክፍል የሕዝብን መብት አክብሮ እስካልተገኘ፤ ለለውጥና መሻሻል ዝግ ሆኖ ክተገኘ፤ ደግሞ ደጋግሞ አፈና ሲያስፋፋ ምርጫን ሲያጭበረበር እየታየ ያለውን ሁኔታ አልረዳም በማለት በሰላማዊ ትግል ለውጥን መጠበቅ ጫንቃን ለባርነት ቀምበር ማመቻቸት ነው ።
ወያኔ ስልጣን እንደያዘ ተሯርጦ ሊያሰፍን የጣረው ሀሳብና አቅዋም ከእንግዲህ አመጽና እብረት ትግል አከተመ የሚለውን ነበር ። ይህን አደናጋሪና ትጥቅ አስፈቺ አቅዋም ዶክተር ደጃዝማቾች ደግፈው መላ ነው እንጂ ዱላ ተዉ ብለው ሲሰብኩና ሕዝብንም ሲያዘናጐለት ከረሙ ። የሕዝብ መብት ባልተከበረበት ግን ሰላም ሰላም የሚባልበት አልነበረም ። ስልጣን ሲይዝ ወያኔ ለዝቦና ለስልሶ ሳይሆን ዘረኛነቱንና አፋኘቱን አጠናክሮ እንደነበርም የሚታይ ነበር ። እስር ቤቶች እንዲሞሉ አድርጎ፤ በእጁ የወደቁትን ሁሉ መዳረሻቸውን አጥቶና ረሽኖ ፤ የተቹትንና የተቃወሙትን ለስየል ዳርጎ፤ ለብዙዎች ስደትን ሳይወዱ በግድ እንደአማራጭ አንዲይዙ አድርጎ ነበር ። በዚህ ወቅት የወያኔ ቅጥረኞችን አደናጋሪ ሰበካ አንሰማም ብለው ብረት አንስተው ወደ ትግል የገቡትን ቡድኖች ግን ወያኔ ብቻ ሳይሆን ዶክተር ደጃዝማቾች በአመጸኛነትና ጸረ ስላምነት በማወገዝና ትግሉን በማምከን ለወያኔ የተመቸ ሁኔታ ፈጥረውለት የነበረ መሆኑ የሚታወስ ነው። የሰላሙ ሙከራ ይኸው እስከዛሬ ወያኔ ምርጫ በሚሉት አዙሪት ከቶ በከንቱ እያሽከረከረ ባዶ አስቀርቷል ።ገዢው ክፍል ራሱ በሰላም እየቀለደ፤ በትግል ክሆነም ሞክሩኝ ብሎ እየደነፋ፤ ታግለን ያገኝነውን በትግል ንጠቁን የሚል መፈክር እያሰማ የቆየ በመሆኑ አቋሙ ድብቅ አልነበረም ። ስልጣን ነጠቃው በአመጽ እንደሚሆን ጠቁሞናል ማለት ይቻላል ። በመሆኑም ሁለገብ ትግል ማካሄድ፤ ይህን መሰል የትግል ስልትን ማስቀደም ባለው ተጨባጭ ሁኔታ የተወሰን ነው ማለት ትክክል ይሆናል ።
ፍየል ወዲህ ቅዝምዝም ወዲያ እንዲሉ ወያኔን በሰላማዊ ትግል ብቻ መጋተር ይቻላል፤ይገባል ብሎ መቆሙ ስህተት መሆኑ የ1997 ኡ ግድያ ሳይሆን 24 ዓመታት ሙሉ ሲካሄድ የባጀው ግፍና ፍጅት የሚያረጋግጠው ነው ። ወያኔና ዴሞክራሲ፤
page1image21216 page1image21376 page1image21536
1

ወያኔና ሰላም፤ ወያኔና ፍትህ ተዋውቀው የማያውቁ በመሆናቸው ፤ዱባና ቅል ለየቅል በመሆናቸው ወያኔን በማይገባው የሰላም ቋንቋ ማነጋገሩ ፋይዳ ቢስ ነው ። 24 ዓመታት ሙሉም አይተነዋል ምንም--ከቶም ቅንጣትም--ለሕዝብ እንደማይጠቅም ። ከተመክሮ መማር ጊዜ በመፍጀቱ እነሆ ኢትዮጵያ ትደማለች፤ህዝቧም መከራና ግፍን ተቀባይ ሆኖ ይገኛል። በየአምስት ዓመቱ ምርጫ የሚባለውን የሞኝ ጨዋታ መጠበቁ አላከትም ብሎ ሕዝብን ከሚፈለገው ትግል አርቆ መገኘቱ ሀገርን ጎድቷል ። ወያኔ ሊቃወሙ ሊታገሉ የሚፈልጉትን በጸረ ሰላምነት ፈርጆ የሚያጠቃውም አለምክንያት አይደለም ።የሚያሳዝነው ይህን ማደናገሪያ ተቀብለው በሰላም ብቻ እንጂ በወያኔ ላይ ማመጹ ጎጂ ነው ብለው የሚለፍፉ ተቃዋሚ በሉን ባዮች ትምህርት አለመውሰዳቸው ነው ። በብረትና በአመጽ የመጣ በግድ ጨቋኝ ይሆናል የሚለውን መሰረተ ቢስ መደምደሚያ ማስተጋባታቸው አልቀረም ። የአሜሪካ ነጻነት የተረጋገጠው በአመጽና በአብዮት ነው ። በአያሌ ሀገሮች ዴሞክራሲ የተገኘችው ሕዝብ በአመጽ ተነስቶ፤ብረት አንግቦ ታግሎ ነው ። ይህ ነው ሀቁ ። በአንጻሩ ተለምኖ፤ አዝኖ ወይም የሕዝብን ጩኸት ሰምቶ ስልጣን የለቀቀ ጨቋኝ ሀይል ግን ተፈልጎ የሚገኝ አይደለም ። ሁለገብ ትግል አማራጭ የለሽ የትግል ጎዳና ነው ማለት ተገቢ ነው ። በሌላ ስምሪት ጊዜንም ህይወትንም ማባከን የሚመረጥ አይደለም ። ያለፉት 24 ዓመታት የወያኔ ጨቋኝ አገዛዝ አምጹ ተነሱ በሁሉም መስክ ወያኔን ተዋጉ የሚል ነው እንጂ ሌላ መልዕክት የለውም ። 

Sunday, July 19, 2015

ህወሓት/ወያነና የትግራይ ሕዝብ (ክፍል 2)

ከነቢዩ ያሬድ
ባለፈው ያቀረብኩት ክፍል 1 ጽሑፌ “ተሓህት/ወያነ የትግራይ ሕዝብ ነፃ አውጭና ጥቅም አስከባሪ ነውን? የትግራይ ሕዝብ ከመሰረቱ ጀምሮ የተሓህት/ወያነን ዓላማ ደግፎና በእርሱ ተመርቶ ተንቀሳቅሷልን?” የሚሉትን ጥያቄዎች ነበር የተመለከተው:: የተጠቀሱትን ጥያቄዎች ስንወያይ ያቀረብኳቸው ታሪካዊ ማሳያዎች የሚያደርሱን ሀቅም የትግራይ ሕዝብ ተሓህት/ወያነን ይቃወምና ይፋለመውም እንደነበር፣ አሁንም እግር ከወርች ታፍኖ እንዳለ በመሆኑ “እንዴት ሆኖ ታዲያ ተሓህት/ወያነ አሸነፈ?” በማለት አንባቢያንን መሰናበቴ ይታወሳል:: ከዚያው ልቀጥል::
የትግራይ ሕዝብ ተሓህት/ወያነን ይቃወም ነበር እንጂ አልደገፈም ሲባል ይህንን በተመለከተ ተዘውትረው የሚደመጡና የሚነሱ ጥያቄዎች አሉ። ሕዝቡ ተሓህትን የሚቃወም ከነበረ እንዴት ሆኖ ታዲያ ተሓህት/ወያነ አሸነፈ? ለምንስ አይቃወመውም ወይም ሲቃወመው አይታይም? በማንስ ተደግፎ ነው አገሪቱን አምቆ እየገዛ ያለው? የሚሉትና የመሳሰሉት:: አንዳንድ ወገኖች የፋሺስቱ መንደርተኛ ድርጅት የተሓህት/ወያነንና የትግራይ ሕዝብን አንድነት ለማስረገጥ እንደ መከራከሪያ የሚያቀርቡት ነጥብ ታዲያ ለምን አይታገላቸውም የሚል ነው። ግራ የሚያጋባው ግን ለምን ይህ ጥያቄ ሌላውን የአገራችንን ሕዝብንም አስመልክቶ እንደማይቀርብ ነው። እንኳንስ በልጅ ፣ በቤተ-ሰብ፣ በሥራ ቦታ፣ በአካባቢ ሚሊሻ፣ በካድሬ፣ በ”ሕዝባዊ” ማኅበራት፣ … የስለላ ድር ተጠፍንጐና በግል ንብረትነት ደረጃ ታግቶ ያለው የትግራይ ሕዝብ ቀርቶ በንጽጽር ሲታይ፤ በፈራ ተባም ቢሆን፤ ድምጹ የሚያሰማለት ወገን ያለው የሌሎች ክፍለ-ሀገራት ሕዝብም ቢሆን በእመቃው ብዛት ምክንያት ሆኖ መገኘት የሚገባውን ሆኖ ሲገኝ አይታይም።
ያም ተባለ ይህ የትግራይ ሕዝብ በርግጥ ተሓህት/ወያነን ይቃወም ነበር፤ ተዋግቶታልም። ይህ ማለት ግን ድርጅቱ አመጹን ሲጀምርም ሆነ በቀጠሉት ዓመታት በትግራይ ውስጥ ወይም የትግራይ ተወላጅ የሆነ ምንም ደጋፊ አልነበረውም ወይም የለውም ማለት አይደለም። ነበረው። ለምሳሌ፥ ከጅምሩ ጀምሮ ጥላው ባጠላበት አካባቢ ነዋሪ በነበረውና በተለያየ ምክንያት ከትግራይ ውጭ ይኖር በነበረው የክፍለ ሀገሩ ተወላጅ ውስጥ በጭፍን የትግራዋይነት ስሜት የተመሠረተ ውሱን ድጋፍ ነበረው። ጠባብ አመለካከት ያጠቃቸው፣ በአማራው ጐሳ ጥላቻ የሰከሩ (የመጀመሪያው “ውፈር ተበገስ ተጋዳልይ ትግራይ፣ ሲሕብካ በሎ ነዙ ዓሻ አምሓራይ”፤ ዘፈናቸውን ልብ ይለዋል። ትርጉሙ “ዝመት ተነስ የትግራይ ታጋይ፣ ሳብ አርገህ ግጨው ያንን ጅል አማራ” ማለት ነው)፣ በትግራይ ኪሳራ ኤርትራን የማስገንጠል አጀንዳ ያነገቡ፣ የፊውዳላዊው ሥርዓት ተንኮታኩቶ የአባቶቻቸው መሬት በመወረሱ ያኰረፉ ቀለም ቀመሶችና ጭፍን ተከታዮቻቸው፣ ወዘተ … የዚሁ ድርጅት የድጋፍ እምብርት ነበሩ። በዚህ ጽሑፍ ለማመልከት የተፈለገው አብዛኛው የትግራይ ሕዝብ፤ በተለይ ደግሞ ከምዕራብ እና ከፊል መሃል ትግራይ ውጭ የነበረው የክፍለ-ሀገሩ ሕዝብ ተሓህት/ወያነን የማይደግፍ እንደነበረ ነው። ያም ሆነ ይህ ግን የትግራይ ሕዝብ ፀረ-ተሓህት/ወያነ አቋም በረጅም ሂደት ውስጥ በተለያዩ ምክንያቶች እየተዳከመ መጥቷል። ከምክንያቶቹ ጥቂቱን መጥቀስ አስፈላጊ ነው።
ለ14 ዓመታት ያህል ተሓህት ወያነ ትግራይን ሙሉ በሙሉ መቆጣጠር ሳይችል ቆይቷል። በተለይ እስከ 1976/77 ድረስ እንደሽምቅ ተዋጊነቱ ድንገተኛ አደጋ እየጣለ በአንዳንድ ከተሞች በነበሩ ወታደራዊ ሠፈሮችና በመጓጓዣ አጀባ ወቅት ጉዳት እያደረሰ ሲያፈገፍግ የነበረ ቢሆንም አብዛኛው እንቅስቃሴው በከፊል መሃልና በምዕራባዊው ክፍል ተገድቦ ቆይቷል። በሰሜን፣ ምስራቅ፣ ደቡብና ከፊል መሃል ትግራይ የነበረው ተቀባይነትም የጐላ ሳይሆን ቆይቷል፤ በፋሺስታዊ ተግባሩ ከመፈራቱ በቀር። ከ1976/77 ዓ.ም. ጀምሮ ግን የአገርና የሕዝብ ደኅንነት መ/ቤት በፈጸመው አሳዝኝ በክህደትም ይሁን የሙያ ብቃቱን ደካማነት ባጋለጠ ስህተት ወይም፤ በሌላ የተሻለ አገላለጽ፤ በአገር አንድነትና ደኅንነት ላይ የፈጸመው ወንጀል ምክንያት ሁኔታው በፍጥነት መቀየር ጀመረ። እጅግ በርካታ የክፍለ-ሀገሩ ተወላጆች ባልዋሉበትና ባልሆኑት የተገንጣይ ቡድኖች አባላት ሆነው ተገኙ በማለት ለእስራት፣ ለግርፋት፣ ለአካል መጉደልና ለሞት ዳረጋቸው። የእነዚህ የአንድነት ኃይሉ ግምባር ቀደም ተዋናዮች ቤተሰብ ፈረሰ፤ ልጆቻቸውና የሚጦሩት ሁሉ ለችጋር ተዳርገ፤ ለመሳቀቅና አንገት ለመድፋት ተገደደ። እነዚህ ሰዎች በትግራይ ውስጥ ከክፍለ-ሀገር እስከ ወረዳና ቀበሌ ድረስ በመንግሥትና በማኅበራት መዋቅር ውስጥ ተመድበውና ተመርጠው ሲሰሩ የነበሩ ጉልህና ጽኑ ፀረ-ተሓህት አቋም የነበራቸው ሰዎች ናቸው። በትጥቅ ትግሉም ጭምር ተሓህት/ወያነን እያሳደዱ ሲቀጡና መግቢያ መውጫ ሲያሳጡ የነበሩ ጽኑ ኢትዮጵያዊ አቋም የነበራቸው ሰዎች ናቸው። እነዚህ ሰዎች ናቸው እንግዲህ በተሓህት/ወያነ ሥውር ደባና በዋናነት ግን በአገርና የሕዝብ ደኅንነት ጥበቃ መሥርያ-ቤቱ የሀገር ክህደትም ይሁን ንዝህላልነትና ብቃት ማነስ ”የወያነ አባለት” ተሰኝተው ከውጭ አገር ሳይቀር በወረንጦ ተለቅመው ለተባለው እስርና መከራ የተዳረጉት። ይህንን ጉዳይ አቶ ገብሩ አሥራትም በመጽሓፋቸው ጠቅሰዉታል (ገብሩ፣ 2006፣ ገፅ 159-161)። ከነዚህ ሰዎች መካከል ጥቂቱ በተለያየ ምክንያት ሕይወታቸውን በእስር-ቤት አጥተዋል። ገሚሱ በጀ/ል ታሪኩ ላይኔ የትግራይ ጦር አዛዥነት ወቅት ተሓህት/ወያነ የመቀሌ ወኅኒ-ቤትን በወረረበት ጊዜ አስፈትቶ ወስዷቸው ከፊሉ ድርጅቱን ሲቀላቀሉ ከፊሉ ደግሞ በሱዳን በኩል ወደ ምዕራብ አገራትና ጥቂቱ ደግሞ ወደ ኢትዮጵያ ተመልሰዋል። አብዛኛዎቹ ደግሞ ከ1976 ዓ.ም. ጀምሮ በእስር ቆይተው ወያነ የተረከባቸው ሲሆን ከፊሉን ፈቶ ከፊሉን ደግሞ አባሎቹ ናችሁ በተባሉለት በወያነ ዘመንም እስራታቸው ቀጥሎ እስካሁንም ድረስ ያልተፈቱ አሉ፤ ጥቂቱ ደግሞ በግርግሩ አምልጠው በስደት ይኖራሉ። ይህ መከራ ከደረሰባቸው ሰዎች ውስጥ የተወሰኑት በተሓህት/ወያነ ውስጥ ታቅፈው ለበርካታ ዓመታት የሠሩና እየሠሩ ያሉ ሲሆን፤ ጥቂቶቹ በደረሰባቸው የኅሊና ቁስል በበቀል ስሜት ተነሳስተው ከልብና በፈቃደኝነት ያገለገሉትን የደርግን ሥርዓት “ትግራዮችን ለማጥፋት የተነሳ” ብለው እስከ መክሰስ ድረስ ሄደዋል።
በኰ/ል ተስፋዬ ወልደ-ሥላሴ የአገርና የሕዝብ ደኅንነት ሠራዊት በተሓህት/ወያነ አባልነት ተወንጅለው በአፈሳ ለእስር፣ ለስየልና ለሞት ከተዳረጉት የትግራይ ተወላጆች መካከል፣ የራሳቸው ድርጅት ተንኰል ጠልፎ የጣላቸው በጣት የሚቆጠሩ የወያነ አባላት የነበሩ ቢሆንም አብላጫዎቹ ግን ለወያነ ህልውና አደጋ የጋረጡ ፀረ-ወያነ ታጋዮች ነበሩ። በጣም የሚገርመው በአገር ጉዳይ ቀርቶ በራሳቸው ህይወትም የረባ ዓላማ ያልነበራቸውም አብረው መታፈሳቸው ነው። ከእነዚህ በወቅቱ ወያነ ተብለው በኰ/ል ተስፋዬ የጅብ ሠራዊት የታፈሱ ዜጎች መካከል አብዛኛዎቹ በወያነ ዘመንም በፀረ-ትግራዋይነት ለበርካታ ዓመታት ታስረው የተፈቱና በእስር በመማቀቅ ላይ ያሉም ይገኙባቸውል። ዕድሉ የገጠማቸው ደግሞ ለማምለጥ በቅተው ኑሮኣቸውን በስደት ዓለም እየገፉ ናቸው። የተሓት/ወያነን ፀረ ኢትዮጵያ አቋም አንደግፍም ያሉና ምንም ፖለቲካዊ ተሳትፎ የሌላቸው፣ የሌሎች ኀብረብሄር እና አፍቃሪ የኢትዮጵያ አንድነት የፖለቲካ ድርጅቶች አባላት የሆኑ የትግራይ ተወላጆች አይደሉም፣ በኢሠፓ መንግሥትም ውስጥ ፖለቲካዊ ተሳትፎ የነበራቸው እንኳ ተገድለዋል፣ ተሠቃይተዋል፣ ከትግል ታግተዋል:: በወያነ ተከል የመንግሥት አካላት:: ባለኝ ትንሽ ቆየት ያለ መረጃ መሠረት ከነዚህ በሺዎች ከሚቆጠሩት ግፉአን መካከል ለምሳሌ ያህል የሚከተሉትን ማየት ይቻላል።
  • አቶ በላይ በርሄ (በቅደም ተከተል፥ የተምቤን አውራጃ የሕዝብ ድርጅት ኃላፊ፣ የትግራይ ክፍለ-ሀገር የሕዝብ ድርጅት ኃላፊ፣ ሲታሰር የጎንደር ክፍለ-ሀገር የኢሠፓአኰ ሥራ-አስፈጻሚ ኰሚቴ አባልና የኅብረት ሥራ ማህበራት ጉዳይ ኃላፊ፤ ታስሮ ደብዛው የጠፋ)፣
  • አቶ ኃይለ-ኪሮስ አሰግድ (የግምባር ገድሊ ሓርነት ትግራይ አመራር አባል፣ የራያና አዘቦና የእንደርታ አውራጃዎች አስተዳዳሪ እና የዘንዶ ሠራዊት መስራችና አዛዥ የነበረ፤ በኢሠፓአኰ/ኢሠፓ ዘመን ለስድስት ዓመታት ያህል ታስሮ የቆየና ተሓህት/ወያነም እስራቱን ቀጥሎበት እስከ ቅርብ ጊዜ በእስር የማቀቀ።)፣
  • መምህር ታደሰ ገብረ እግዚአብሔር (መጀመሪያ የየካቲት 66 ፖለቲካ ትምህርት-ቤት አስተዳዳሪ፤ ሲታሰር የኢሠፓኰ ማዕከላዊ ኰሚቴ አባልና የሸዋ ክፍለ-ሀገር/የአዲስ አበባ የርዕዮተ-ዓለም ጉዳይ ኃላፊ፤ ታስሮ ደብዛው የጠፋ)፣
  • አቶ ኅሩይ አስገዶም (በቅደም ተከተል የትግራይ ክፍለ-ሀገር ትምህርት ቤቶች ጽህፈት ቤት ምክትል ሥራ-አስኪያጅ፣ የዓጋመ አውራጃ አስተዳዳሪ፣ የትግራይ ክፍለ-ሀገር ተቀዳሚ ምክትል አስተዳዳሪ፤ በቁጥጥር የማዋል ሙከራ ወቅት እጄን አልሰጥም ብሎ ተታኩሶ የሞተ)፣
  • አቶ አብራሃ በላቸው (የሽሬ አስተዳዳሪ የነበረ፤ የተሓህት/ወያነ የሌሊት ቅዠት፣ እያሳደደ ይቀጣቸው የነበረ እና በጣም ይፈሩት የነበረ፤ በኢሠፓአኰ/ኢሠፓ ዘመን ለስድስት ዓመታት ያህል ታስሮ የቆየና ተሓህት/ወያነም እስራቱን ቀጥሎበት በእስር እየማቀቀ ያለ። የቅርብ ጊዜ መረጃ የለኝም።)፣
  • አቶ ተስፋሁን አወቀ (የዓድዋ አውራጃ የሕዝብ ድርጅት ኃላፊ፤ በኢሠፓአኰ/ኢሠፓ ዘመን ለስድስት ዓመታት ያህል ታስሮ የቆየና ተሓህት/ወያነም እስራቱን ቀጥሎበት በእስር እየማቀቀ ያለ። የቅርብ ጊዜ መረጃ የለኝም።)፣
  • አቶ አብረሃ ውበት (የገርዓልታ እና የሳምሬ ወረዳ አስተዳዳሪ፤ በታሰረበት ወቅት አሁን የተረሳኝ የአንድ የትግራይ አውራጃ የኢሠፓአኰ ቁጥጥር ኰሚሽን ሰብሳቢ የነበረ፤ በኢሠፓአኰ/ኢሠፓ ዘመን ለስድስት ዓመታት ያህል ታስሮ የቆየና ተሓህት/ወያነም እስራቱን ቀጥሎበት በእስር እየማቀቀ ያለ። የቅርብ ጊዜ መረጃ የለኝም።)
  • መምህር ብርሃኑ ማሞ (በደርግ ዘመን የመቀሌ ከተማ የመጀመሪያ ከንቲባ፤ በኢሠፓአኰ/ኢሠፓ ዘመን ለስድስት ዓመታት ያህል ታስሮ የቆየና ተሓህት/ወያነም እስራቱን ቀጥሎበት እስከ ቅርብ ጊዜ በእስር የማቀቀ። በዚህ ወቅት የደርጉ ቀዳሚ ዘመቻ መምሪያ መቀሌ ሰፍሮ ነበር)፣
  • መምህር አሰፋ እሸቱ (በደርግ ዘመን የመቀሌ ከተማ የመጀመሪያ ምክትል ከንቲባ፤ በኢሠፓአኰ/ኢሠፓ ዘመን ለስድስት ዓመታት ያህል ታስሮ የቆየና ተሓህት/ወያነም እስራቱን ቀጥሎበት እስከ ቅርብ ጊዜ በእስር የማቀቀ።)፣
  • አቶ ጉግሳ ተኽለ (የሕዝብ ድርጅት ካድሬ፣ ሲታሰር የመናገሻ አውራጃ የኢሠፓአኰ 1ኛ ፀሓፊ)፣
እነዚህ በመቶዎች ከሚቆጠሩት ተሓህት/ወያነን ቀጥ አድርገው ከመከቱትና ድርጅቱ ይፈጥረው የነበረውን ችግርንም ለዘለቄታው ለመፍታት ጥረት ካደረጉት የክፍለ-ሀገሩ ግንባር ቀደም ፀረ-ተሓህት/ወያነ ሰዎች ውስጥ ተቆንጥረው ለአብነት የተገለጹ ናቸው።
ይህን ከፍ ብሎ የተገለፀው በኢሠፓ ሥርዓት ውስጥ ሲያገለግሉ የነበሩትንና የተሓህት/ወያነ ዓላማን ሳይቀበሉ ከፖለቲካው ዓለም ውጭ ሆነው በመንግሥትም ይሁን በግል የሥራ ዓለም ተሰማርተው ይገኙ የነበሩትን ለኢሠፓ መንግሥት የደኅንነት ቢሮ የጥቃት ኢላማ እንዲሆኑ ያበቃ ሴራ ተሓህት/ወያነ የሰራው ሴራ ነው። ድርጅቱ እነዚህ ሰዎች አባሎቹ እንደነበሩ የሚያስመስል መረጃ የኢሠፓ መንግሥት የደኅንነት ቢሮ ጆሮ ዘንድ እንዲደርስ በማድረጉ ነው የጅምላ እስሩ የተፈፀመው። ይህ ዕውነታ ከያኔ ጀምሮ ሲነገር የኖረና በስተመጨረሻም ኢሠፓ ራሱም ነቅቶበት ያቆመው አሳዛኝ ተግባር ሲሆን አሁን አቶ ገብሩ በጽሑፋቸው አረጋግጠዉታል።
ይህ ተግባር ለተሓህት/ወያነ የመንግሥት ሥልጣን መቆጣጠርና ኤርትራን የማስገንጠል ድርጊት በር የከፈተ አስዛኝ ስህተት/ወንጀል ሲፈፀም ክፍለ-ሀገሩ በነሻለቃ ሙሉጌታ ሓጐስ (የኢሠፓኣኰ/ኢሠፓ 1ኛ ፀሓፊ)፣ ጀነራል ከፈለኝ ይብዛ (የክፍለ-ሀገሩና የጦሩ የበላይ አስተዳዳሪ)፣ ኰ/ል ፈቃደ ዋኬኒ (የክፍለ-ሀገሩ ዋና አስተዳዳሪ)፣ ጀነራል ታሪኩ ላይኔ (የትግራይ ዕዝ አዛዥ)፣ ሻለቃ ደስታ መሸሻ (የክፍለ-ሀገሩ ምክትል አስተዳዳሪ)፣ አቶ አምባቸው ደምሴ (የክፍለ-ሀገሩ የኢሠፓኣኰ/ኢሠፓ የሥራ-አስፈጻሚ ኰሚቴ አባልና የድርጅት ጉዳይ ኃላፊ)፣ አቶ ሳሙኤል ሃብቴ (አቶ አምባቸው ደምሴን ተክቶ የኢሠፓኣኰ/ኢሠፓ የሥራ-አስፈጻሚ ኰሚቴ አባልና የድርጅት ጉዳይ ኃላፊ)፣ አቶ አፈ-ወርቅ (የክፍለ-ሀገሩ የኢሠፓኣኰ/ኢሠፓ የሥራ-አስፈጻሚ ኰሚቴ አባልና የርዕዮተ-ዓለም ኃላፊ)፣ ሻለቃ ሰሙ-ንጉስ (የክፍለ-ሀገሩ የኢሠፓኣኰ/ኢሠፓ የሥራ-አስፈጻሚ ኰሚቴ አባልና የቁጥጥር ኰሚቴ ሰብሳቢ)፣ ኰ/ል ገብረመድህን (የክፍለ-ሀገሩ ፖሊስ አዛዥ፣ በኋላ በጀነራል ማዕርግ የኤርትራ ፖሊስ አዛዥ [?])፣ አቶ ውብሸት (የክፍለ-ሀገሩ የሕዝብ ደህንነት መ/ቤት ኃላፊ) ወዘተ… ይተዳደር ነበር።
እነዚህ ባለሥልጣኖች ተሓህት/ወያነ በትግራይ ውስጥ የበላይነት ለማግኘት ስለቻለበት ሁኔታ ተጠያቂነት ያላቸው ሰዎች ናቸው። ዋነኛ ተጠያቂዎቹ ግን ሻለቃ ሙሉጌታ ሓጐስ፣ ሜ/ጀነራል (?) ከፈለኝ ይብዛ፣ ጀነራል ታሪኩ ላይኔ፣ አቶ ውብሸት (?) እና ማዕርጋቸውና ሥማቸው የተዘነጋኝ የትግራይ ወታደራዊ ዕዝ የፖለቲካና የወታደራዊ ደኅንነት ኃላፊዎች ናቸው። በዋናነት የእነዚህ ሰዎች አደራን ያለመወጣት ተግባር ነው ኢትዮጵያ አሁን ለደረሰችበት መታመስ በር የከፈተው። በተለይ ሻለቃ ሙሉጌታ ሓጐስ፣ ሜ/ጀነራል (?) ከፈለኝ ይብዛ፣ አቶ ሳሙኤል ሀብቴ፣ ብ/ጀነራል ታሪኩ ላይኔ፣ አቶ ውብሸት የትግራይ ሕዝብን የትግል ስሜት ያላሸቁ፤ የአንድነት ታጋዮችን ያዳከሙና አብዛኛው ክፍለ-ሀገሩ በሙስና ተግባር እንዲዘፈቅ ምክንያት የሆኑ አደራ-በሎች ናቸው። የእነዚህ ሰዎችና መሰሎቻቸው በሥልጣን መማገጥና በግል ጥቅም ማሳደድ ላይ አትኩረው መደበኛ ዕለታዊ የስምንት ሰዓት የሥራ ኃላፊነታቸውን ያለመወጣት ተግባር ነው ኢትዮጵያ አሁን ለደረሰችበት መታመስ በር የከፈተው። የእነዚህ ሰዎች አደራ-በይነትና የፈጠሩት ሁለንተናዊ ንቅዘት ለተሓህት/ወያነ አሁን የደረሰበት ደረጃ ላይ መድረስ በር የከፈተ ግዙፍ የአገር ክዳት ስለሆነ በሚገባ ሊገለጽ የሚገባው የአገሪቱ የፈተና ወቅቶች ታሪክ አካል ነው። ወደፊት ተነጥሎ ሰፋ ባለ መልኩ ይታያል።
ሌላኛው እስካሁን ድረስ ምስጢሩ በቅጡ ያልተገለጠው ሕዝቡን ያስቆጣ ተግባር በሓውዜን ላይ የተደረገው የአየር ድብደባ ነው። በዚህ ድብደባ እጅግ በርካታ የከተማውና የአካባቢው ነዋሪ የሆኑ ሰላማዊ ወገኖቻችን በአሰቃቂና አሳዛኝ ሁኔታ ሕይወታቸውን አጥተዋል። ድብደባው የተካሄደው በብርጌዶች የሚቆጠር የተሓህት/ወያነ ጦር በከተማው ሰፍሮ መቀሌን ለማጥቃት ዝግጅት እያደረገ ነው የሚል መርጃ በክቶ ለነበረው የኢሠፓ መንግሥት የደህንነት መሥሪያ-ቤት በመድረሱ ነው። ይህንን አቶ ገብሩና ሌሎቹም የወያነ መሪዎች አሌ ያሉት ቢሆንም የዓጋመና የኽልተ-አውላዕሎ ሕዝብ ቁጣ ለመቀስቀስ ሆን ተብሎ የተቀነባበረ ሴራ ነው። ይህ ተግባር እንደ ብዙ ሌሎች ነገሮች የስብሓት/መለስ ቡድን ከሌሎቹ የድርጅቱ የአመራር አባላት ጀርባ የፈፀመው ሊሆን ቢችልም ዕውነቱ ግን ይኸው ነው።
ልቦናቸውን ጨፍነው አገዛዙን የሚደግፉ ደካሞችና ጠባብ ጐሰኞች ይህንን ተሓህት/ወያነ የፈጸመውን በርካታ የክፍለ-ሀገሩ ልጆችን ለእስራት፣ ለአስቃቂ ግርፋት፣ ለአካል መጉደልና ለሞት የዳረገበትን አረመኔያዊ ደባም ሆነ ሌላው ሁሉ የሕዝብንና የአገርን ደኅንነትና ጥቅምን የጐዳ ተግባር መፈጸሙ “ለትግሉ መጐልበት ጠቃሚ ስለነበረ ተግቢ ነው” የሚል ነፈዝ መከላከያ ያቀርቡለታል። ለነዚህ ነፈዞች ተሓህት/ወያነ ሙሉእ በኵሌሁ የሆነ ምንም ዓይነት ጥፋት የማይፈፅም ድርጅት ነው። በእነዚህ አዕምሮ-ስውራን እይታ ኤርትራን መገንጠሉና (ኤርትራን የገነጠለው እሱ ነውና) አገሪቱን የባሕር በር አልባ ማድረጉ፣ የአገሪቱ ታሪካዊና መተክላዊ ጠላቶች በሆኑት በግብጽና በሱዳን እና በሶማሊ እየተረዳና ከርነሱ ጋር አብሮ የአገር አንድነትን አደጋ ላይ መጣሉ፣ መሬት እየቆረሰ ለሱዳን መስጠቱ፣ የድርጅቱ አቋም የተፃረሩትንና በድርጅቱም ውስጥ ሆነው ከአመራሩ ጋር ልዩነት ያሳዩትን ማስገደሉና መግደሉ፣ ወዘተ … ሁሉ ተገቢም አስፈላጊም ልክም ነበር፤ ነውም። ሌላው ወገን የሕዝብና የአገር ሉዓላዊነትን ለድርድር ሳያቀርብ ተሓህት/ወያነን ከማይወዱ ኃይሎች ድጋፍና ትብብር ሲጠየቅ ግን አገራዊ ክህደት፣ ፀረ-ሉዓላዊነት፣ አሸባሪነት፣ ወዘተ ወዘተ ነው። ደርግ ወይም ሻዕቢያ የትግራይ ተወላጆችን ያሰረ፣ የገደለ እንደሆነ ዘር ማጥፋት ነው፤ ተሓህት ወያነ ከዚያ በበለጠ ይህንን ያደረገ እንደሆነ ግን ለትግሉ መስመር አስፈላጊ ነው። ወይም ተራ ስህተት ነው። ደርግ እንደ መንግሥት፤ በዋናነት ደግሞ የሕዝብ ደኅንነት መሥሪያ ቤትና በክፍለ-ሀገሩ የነበሩ የሲቭልና ወታደራዊ ባለሥልጣኖች ተጠያቂ ለመሆናቸው አጠያያቂ ባይሆንም ይህንን ሴራ በመዶለቱ ተሓህት/ወያነም ቢያንስ እኩል ተጠያቂ መሆኑን ግን ዘንግተዋል።
ሌላው የተሓህት/ወያነ ደጋፊ ኃይል ደግሞ በጠባብ የጐሳ/መንደር ስሜት የሰከረው ጨለምተኛ ክፍል ነው። መለስ ጠቅላይ ሚኒስቴር፣ በርካታ የዓድዋ ልጆች ”ጄነራል”፣ ሚኒስቴር፣ ቱጃር (ዋልጌውን ሼክ ልብ ይለዋል)፣ ወዘተ … ስለሆኑ ዓድዋ በመላ፤ እንዲያም ሲል ትግራይ በመላ የሆነ የሚመስላቸው በህልም ዓለም የሚዋዥቁ የዋኅን እና መንፈሰ-ደካሞች ቁጥራቸው ቀላል አይደለም።
ሌላው እዚህ ውስጥ የሚመደበው ቡድን ደግሞ ከኤርትራ ተባርረው የመጡ እዚያው ተወልደው ያደጉና ትግራይ ተወልደው ኤርትራ ያደጉ ያቀፈው ነው። ለነዚህ ሰዎች የኢትዮጵያ ታሪክ ከግንቦት 20፣ 1983 ዓ.ም. ነው የሚጀምረው። ስለ ትግራይ የገዘፈ የኢትዮጵያ ታሪክ ባለድርሻነት፣ ከዚያ በፊት የትግራይ ሕዝብ ለኢትዮጵያ አገሩ አንድነትና ህልውና እውን መሆንና መከበር የከፈለው መስዋዕትነትና ያደረገው ገድል ያላቸው እውቀት መሬት የወረደ ነው። እዚያው ተወልደው ያደጉ በመሆናቸው አርቲፊሻል ትግራዋይነት የሚሰማቸውና ትግራይም ሆነች ኢትዮጵያ የስደት መጠጊያ ከመሆን ያለፈ ብዙ ትርጉም የሚሰጣቸው አይደለም።
በርካታ ኤርትራ ውስጥ ሰርተው ሃብት አፍርተውና ከብረው የኖሩ በሻዕቢያ ተዋርደውና ንብረታቸው ተዘርፈው የተባረሩትም የተሓህት/ወያነ ስሜታዊ ደጋፊዎች ናቸው። እነዚህ ወገኖች ጫጉላው አልቆ ተሓህት/ወያነና ሻዕቢያ/ህግደፍ ሲራገጡ ተሓህት/ወያነ በደላቸውን የተበቀለላቸው መስሏቸው በስሜታዊነት ሰክረው አድረዉለታል። የተሓህት/ወያነና ሻዕቢያ መራገጥ የሌላ ጐሳ ተወላጆችም ተሓህት/ወያነ ኢትዮጵያዊ የሆነ መስሏቸው እንዲደናበሩ ያደረጋቸው ሲሆን፤ ራስ አሞኝ ”ብልጣ-ብልጦቹ” ደግሞ ሰበብዋን ተጠቅመው ወደ አገዛዙ ጠጋ እንዲሉ ሰበብ ፈጥሮላቸው ግብር ለመስፈር ሲጣደፉ ተስተውለዋል።
በአጠቃላይ ከዚህ በላይ እንደተጠቀሰው የደርግ መንግሥት የፀጥታው ቢሮ ባሳየው የዘቀጠ የሙያ ድክመትና በፈጸመው በጣም አሳዛኝ ክህደት በክፍለ-ሀገሩ ቁልፍ ቦታዎችና በግምባርም ጭምር የነበሩ ፀረ-ተሓህት/ወያነና ሻዕቢያ ባለሥልጣናትና ታጋዮች አፍሶ ዘብጥያ አውርዶ ክፍተት በመፍጠሩ ፀረ-አንድነት አማጽያኑ የፖለቲካና ወታደራዊ ምህዳሩ ያለ ከልካይ እንዳሻቸው እንዲፈነጩበት ዕድል አገኙ። ሕዝቡም ተስፋ መቁረጥ ዳምኖበት ደርግን ያመነና ውኃ የዘገነ ብሎ አረፈው። ከዚህ ውጭ ግን የትግራይ ሕዝብ በመላ ወይም አብላጫው ክፍል የተሓህት/ወያነ ደጋፊና ተከታይ ሆኖ የታየበት ጊዜ አልነበረም። ድርጅቱም ደግሞ የሕዝቡ ጋሻና መከታ አልነበረም። አሁንም፤ እላይ ለማብራራት እንደተሞከረው፤ የሕዝቡን ስትራቴጂያዊ ጥቅሞች እየጐዳ የትግራይ ሕዝብ ጥቅም አስከባሪ ሊሆን አይችልም።
የትግራይ ሕዝብ በነፃነት የኖረና ነፃም ሕዝብ ስለሆነ ነፃ አውጭ አልሻውም፣ አያሻውምም። መብቱና ክብሩ ተጠብቆና በልፅጐ ለመገኘት እንዲችል ግን እንደ 1930ዎቹ አሁንም ለፍትሃዊ ሥርዓት መስፈን ይታገላል። ይህ ግን የብተና ፊተውራሪና የባዕዳን ተልዕኰ ፈጻሚ በሆኑት በተሓህት/ወያነ እና በሻቢያ መሪነት እውን ሊሆን አይችለም። ይህ እውን ሊሆን የሚችለው እነሱን በማስወገድ ወይም እነዚህ ቡድኖች በሆነ ተአምር የያዙት አጥፊ ፀረ-ሕዝብና ፀረ-አገር ዓላማ ሲተዉ ብቻ ነው።
• ተሓህት/ወያነ ሁሉንም የትግራይ አካባቢዎችንና ተወላጆችንስ በእኩል ዓይን ይመለከታል? የታገለውና የሚታገለውስ ታላቅ ትግራይን ለመመስረት ነው?
የትግራይ ሕዝብ ኢትዮጵያዊነትና የአገር ፍቅር ማንኛውም እዚያ ክፍለ-ሀገር የኖረና ተዘዋውሮ ያየ ሰው ሊመሰክረው የሚችል ግልጽ ጉዳይ ነው። ይህንን እንደነ አቶ ተክሌ የሻው የመሳሰሉ በክፍለ-ሀገሩ ቁልፍ ቦታ ላይ ተመድበው የሠሩ ሰዎችም ያዩት ኃቅ በመሆኑ ሊመሰክሩለት ይገባ ዘንድ ኢትዮጵያዊ አደራና ሰብኣዊ ግብረ-ገብነት ግድ ይላቸዋል። ዛሬ ሌላ ጊዜ ላይ ነው ያለነው። በዛሬው ወቅት የትግራይ ሁኔታ በአያሌ ውስብስብ ምክንያቶች ሳቢያ ሌላ መልክ ይዟል። ቢሆንም ግን ስለ ትግራይም ሆነ ስለ ሌላው አካባቢ አስተያየት ሲሰጥ የትላንቱን በትላንት የዛሬውን በዛሬ እየተለካና እየተቀመጠ ነው መሆን ያለበት። የትግራይ ሕዝብ ዛሬ ያለ ጠበቃና እውነተኛ ወኪል ቀርቶ፣ የተሓህት/ወያነ የግል ንብረት እስኪመስል ድረስ በጠባብ መንደርተኛ ነፍጠኞች፣ ባዕድ ነን ባይ ከሃዲዎችና የባንዳ ተተኪዎች ታግቶ መጫወቻ ሆኖ ያለ ሕዝብ ነው። ሌሎች ስለ አካባቢው ምንም ዕውቀት የሌላቸው፤ ወይም በጣም የደከመ የአሉ ተባለ መረጃ ያላቸው፤ ወይም በአገዛዙ ፕሮፓጋንዳ ግዳይ የተጣሉ፤ አለያም ለሆነ ጠባብ ዓላማ ሲሉ እውነታውን መካድ የመረጡ ሕዝቡን ከአገዛዙ ጋር አዳብለው ስለሚመለከቱት አለኝታ አልባነት እየተሰማው የሚኖር ሕዝብ ሆኗል። ከዚህ በላይ ደግሞ አንዳንድ ያልተገሩ ደካማና ለአገዛዙ ያደሩ ፍርፋሪ ለቃሚዎች እምር እያሉ በሚያሰሙት ቀረርቶ ቀረሽ ዛቻ (ሌላ ቃል የተሻለ አይገልጸውም) የበለጠ ጥርጣሬ እንዲያድርበትና ’እኛ ከሌለን አለቀልህ’ የሚለውን የፋሺስቱ መንደርተኛ ቡድን አርቲ ቡርቲ ሰበካ ለመቀበል እንዲያቅማማ እየተገደደ ያለ ሕዝብ ነው።
እውነቱ ይነገር ከተባለ ይህ መንደርተኛ ፋሺስታዊ ድርጅት በሥሙ ይነግዳል እንጂ ወኪሉም፣ ነፃ-አውጪውም አይደለም፤ ያደረገለትም ነገር የለም። በርግጥ አገዛዙም ሆነ ደጋፊዎቻቸው ፋብሪካ ተሰራ፣ ቤት ተሰራ፣ ቪላ በቪላ ሆነ፤ በየወረዳው ትምህርት-ቤትና የጤና ተቋምት ፈሉ፣ ወረዳዎቹ በመንገድ ተገናኙ፣ ወዘተ … ይሉናል። አዎ፤ ግን ማን የሠራው ፋብሪካ፣ ባለቤትነቱ ማን የሆነ? የነማን ቤትና ቪላ? የዘመነኛ ነፍጠኞች፣ የአገዛዙ ሹሞችና የአገዛዙ አጨብጫቢ አረመኔ ከበርቴዎችና የአየር ባየር ሞጭላፎች ቪላና ህንፃ ለሕዝቡ ምኑ ነው? ለነገሩማ መንግሥት የሚባል ነገር’ኰ እንዲህ ዓይነት ተግባራት ሊያከናውን እንጅማ የማን ጐፈሬ ሊያበጥር ነው ሕዝቡ የሚቀጥረው?! የተሓህት/ወያነዎች ይህን ቢያደርጉ ኖሮስ ነን ብለው ከሚቦተሉክት አንፃር ደጋፊዎቻቸው ለምን ይደነቃሉ?! ለመሆኑ ይህ ሁሉ በዚያ ኋላ በቀረ የኢኰኖሚ አቅምም ሳይገደቡ ልዑል ራስ መንገሻ ሥዩምም ሕዝቡን እያስተባበሩ የፈጸሙት ተግባር እንደሆነ የተሓህት/ወያነ ጀሌዎች ያውቃሉ? በርግጥ ልዑሉ በዘመናቸው ያሠሩት ሁሉ ጠላት እንዳይጠቀምበት በሚል ፈሊጥ ተሓህት አፍርሶና ነቃቅሎ አጥፍቶታል፣ በፈንጅ ደረማምሶታል። ዛሬ ይህ መንደርተኛ ፋሺስት ቡድን ይህንን ትላንት ያወደመውን ቢተካ ምን ይገርማል?
እላይ ቆንጠር ተደርጐ ለመግለጽ እንደተሞከረው የአብላጫው የትግራይ ሕዝብ ዓላማና የፋሺስቱ መንደርተኛ ቡድን ተሓህት/ወያነ ዓላማ ፈጽሞ ተቃራኒ ነው። ለማብራራት እንደተሞከረው የዚህ ፋሺስታዊ ቡድን ዋነኛው የተፅእኖ አካባቢ ምዕራባዊው እና ከፊል መሃል የትግራይ ክፍል ሲሆን በሌላው ክፍል እኩል የሆነ ተቀባይነትና ድጋፍ ለማግኘት ሳይችል እስከ የኢሠፓ ሥርዓት መፈረካከስ ዋዜማ ድረስ ለመቆየት ተገድዷል። በተጨማሪም እላይ ጠቆም እንደተደረገው የድርጅቱ አመራር በአብላጫው በአሽዓ (አክሱም፣ ሽሬ፣ ዓድዋ) ተወላጆችና በኤርትራዊያን የተሞላ ነበር፣ ነውም። ከእነዚህም አብዛኛዎቹ አፍቃሪዬ-ኤርትራ የሆኑ ለኢትዮጵያ አንድነት በጐ አመለካከት ያልነበራቸው (አሁንም የሌላቸው) ስለነበሩ ይህንን ዓላማ ይፃረሩ የነበሩትን እጅግ አብላጫው ከሌሎቹ የትግራይ ክፍሎች የሆኑትን አባሎቻቸውን ገና ከማለዳው በግልጽም በሥውርም አጥፍተዋቸዋል። ይህ ደግሞ በአብዛኛዎቹ የደቡብ፣ ምሥራቅ፣ ሰሜንና ከፊል መሃል ትግራይ ተወላጆች ዘንድ ቅሬታ ፈጥሮ የኖረ በመሆኑ ድርጅቱ በአካባቢው ሚዛን የሚደፋ ተቀባይነት እንዳይኖረው ጋሬጣ ሆኖበት ዘልቋል፤ ምንም እንኳን በተለያዩ ምክንያቶች በተነጻጻሪ አነስተኛ የሆኑት የአካባቢው ተወላጆች ድርጅቱን የተቀላቀሉ ቢሆንም። ምክንያቶቹ በዋናነት የኢኰኖሚ ችግር፣ እላይ እንደተጠቀሰው ዓይነት የደህንነቱ መሥሪያ-ቤት የሠራው ዓይነት ጥፋት፣ በጦርነቱ መራዘም ምክንያት የወደፊት ሕይወት አስመልክቶ ተስፋ መቁረጥ፣ ዛሬም እንደሚታየው የምዕራቡ ዓለም የተሻለ ሕይወት ፍለጋ ወደ ስደት ሲያመሩ ድርጅቱ በሚቆጣጠረው ክልል ሲያልፉ ለጠባብ ብሄረኛ ፕሮፓጋንዳ ተጋልጠው ግዳይ በመሆን፣ ወዘተ … ናቸው።
የእነዚህ አካባቢዎች ሕዝብ እንደ ምዕራቡ እና ከፊል መሃሉ ድርጅቱን ሙሉ በሙሉ ባለመደገፉ በድርጅቱ ግምባር ቀደም መሪዎች ዘንድ ጥርስ ተንክሶበት ኖሮዋል። የድርጅቱ አመራር በአብዛኛው የምዕራብ ልጆች በመሆናቸው የበለጠ መደጋገፍና ግልጽ አድልዎም ይፈፅሙ ነበር። ለዚህም እንደ የጐላ ምሳሌ መለስ ዜናዊ ከግዳጅ ሲፈረጥጥ የተሰጠው ድርጅቱ በወቅቱ ይከተለው ከነበረው ደንብ ጋር የማይመጣጠን ቅጣት መጥቀስ ይቻላል። እንዲህ ዓይነቱ ተግባር የድርጅቱ አባሎች በሆኑት የሌሎች አካባቢዎች ተወላጆች ዘንድ የፈጠረው ቅሬታ በድርጅቱ ዘንድ ህንፍሽፍሽ በመባል ለሚታወቀው የውስጥ መታመስና ለገሚሶቹም ድርጁትን ጥለው ለመኮብለል ምክንያት እስከ መሆን በቅቷል። ዛሬም ቢሆን ይህ ሁኔታ ቀጥሎ ያለ ሲሆን ይህንን ለመረዳት የድርጅቱ ወታደራዊና የሲቭል መሪዎች የትውልድ አካባቢ መፈተሽ ይበቃል።
ድርጅቱ በውስጠ-ድርጅት ሕይወቱ ብቻ ሳይሆን በአደባባይም በግልጽ የሚታይ አድልዎ እየፈፀመ ይገኛል። አድልዎው ጊዜያዊ ሳይሆን ከምዕራቡ ክፍል ውጭ ያለውን ሕዝብ ማንነት መለያ የሆኑ ጉዳዮችንም እስከነአካቴው ለመቀየር ያለመ ነው።
ሌላኛው እንደ ምሳሌ መመልከት የሚቻለው በቋንቋ ረገድ እየተደረገ ያለው ዘመቻ ነው። በትግራይ ውስጥ የተለያዩ የትግርኛ ዘዬዎች (dialects) አሉ። ዓድዋ፣ አክሱምና ሽሬ አካባቢ የሚነገረው ትግርኛ አንድ ዓይነት ወይም በጣም ተቀራራቢ ሲሆን፤ የኽልተ-ኣውላዕሎና የዓጋመ አውራጃዎች ደግሞ አንድ ዓይነት ወይም በጣም ተቀራራቢ ነው። የእንደርታና የተምቤን ትግርኛ የተለየ ሲሆን ትንሽ ተቀራራቢነት አለው። የራያ ትግርኛ ደግሞ ራሱን የቻለ ነው። በእርግጥ በኩታ ገጠም አውራጃዎች ወይም አካባቢዎች የሚነገረው ትግርኛ ተቀራራቢነት ሊኖረው ይችላል። የሆነ ሆኖ ዓድዋ፣ አክሱምና ሽሬ አካባቢ የሚነገረው ትግርኛ ራያና እንደርታ ከሚነገረው ትግርኛ ይልቅ አንድ ዓይነት ነው ለማለት በሚያስደፍር ደርጃ ኤርትራ ውስጥ ከሚነገረው ትግርኛ ጋር ይመሳሰላል።
እላይ ለመጥቀስ እንደተሞከረው ዛሬም አብላጫው የመንደርተኛው ፋሺስታዊ ቡድን ተሓህት/ወያነ መሪዎች የምዕራቡ ክፍል ተወላጆች፣ የኤርትራ ተወላጆች እና የትውልድ ሃረጋቸው ከዚያው የሚመዘዙ ናቸው፤ እንደነ ዶ/ር አዲስ-ዓለም ባሌማ፣ ወ/ሮ ሮማን ገብረ-ሥላሴ (አቶ መለስ ደንቆሮ ብለው የሰየሙዋቸው መንፈሰ-ስንኩል)፣ … የመሳሰሉ እፍኝ የማይሞሉ ማፈሪያዎች ቢያስኰለኩሉም።
ዛሬ የድርጅቱ መሪዎች ባላቸው የሌሎቹን አካባቢዎች ማንነት የመጥላት፣ የመናቅ፣ የማኰሰስና የማጥፋት ዓላማ መሠረት የሁሉም አካባቢ ልጆች በአስገዳጅ ከኤርትራ ጋር የሚመሳሰለውን የዓድዋ፣ አክሱምና ሽሬ ትግርኛ ዘዬ እንዲማሩ እያደረጉ ነው። ይህንን ደፍረው የሚቃወሙ የእነዚህ አካባቢ ተወላጆች በርክተውና ጐልተው አለመታየታቸው ደግሞ የበለጠ አስዛኝና አሳሳቢ ነው። ነገረ ግርምቢጥ ሆኖ አንዳንድ አወቅን መጠቅን የሚሉ የእነዚህ አካባቢ ተወላጆች ግለሰቦችም በነሱ ብሶ ይህንን ሲፈጽሙና ሲያስፈጽሙ ነው የሚታየው። እሩቅ ሳንሄድ የአቶ አበበ ተክለ-ኃይማኖትን (ጆቤ) የአቶ ገብሩ አሥራትን መጽሓፍ የተቹበት ጽሑፍ ላይ የተጠቀሙት የትግርኛ ዓይነት መጥቀስ ይቻላል። አቶ አበበ ተክለ-ኃይማኖት ከርዕሱ አንስቶ የተጠቀሙበት ቋንቋ እራሳቸው የተወለዱበት አካባቢና የአፍመፍቻቸው የሆነውን፤ ያደጉበትን ዓይነት ትግርኛ ሳይሆን የአማቾቻቸው አካባቢ ዘዬን ነው (የአቶ አበበ ተክለ-ኃይማኖት ሚስት ወ/ሮ አስካለ የዓድዋ ተወላጅ መሆናቸው ልብ ይለዋል)። የተሓህት/ወያነ አፈቀላጤዎች ይህንን ማለት መከፋፈልና ዘር-ቆጠራ ነው ብለው ሊመፃደቁ የችላሉ። መልሱ አጭር ነው። እንዲህ ማለት በናንተ ቋንቋ ለመናገር ያህል ሳይሆን ዕውነቱን ለመግለጥ ነው። ሁሉም ባህሉና ቋንቋው ይከበርለት ከተባለ ኽልተ-ኣውላዕሎም፣ ራያና አዘቦም፣ እንደርታም፣ ተምቤንም፣ … የራሱ ቋንቋ ዘዬ፣ ልምድና ወግ፣ ወዘተ… ስላለው አክብሩለት ለማለት ነው።
አንዳንድ የዞረባቸውና ማንነታቸው የሚያሳፍራቸው፣ የእነዚህ ማንነታቸው እንዲከስም እየተደረጉ ያሉት አካባቢዎች ተወላጆችና የትውልድ ሃረጋቸው እንደምንም ከኤርትራ ጋር ለማቆራኘት ፍዳቸውን የሚቆጥሩ እንጭጮች ይህንን ተሓህት/ወያነ የሌሎቹን እየተጫነ እያስፋፋው ያለውን የኤርትራ መሰል የምዕራብ ትግራይ ልሳን የውድብ ቋንቋ በማለት ሊያድበሰብሱትና ሊኳኩሉት ሲዳዳቸው ይታያል። የውድብ (የድርጅት) የሚባል ቋንቋ የለም። እንዲያሸንፍና ሌላውን እንዲያጠፋ እየተደገፈ ያለው ቋንቋ የኤርትራ-መሰሉ የምዕራብ ትግራይ ትግርኛ ነው። የነ አቶ መለስ፣ አቶ ስብሓት ነጋ፣ የአቶ ብርሃኔ ገብረ-ክርስቶስ፣ የአቶ በረከት ስምዖን፣ የአቶ ሳሞራ የኑስ፣ የአቶ ቴድሮስ ሓጐስ፣ ወዘተ ወላጆች ወይም ከወላጆቻቸው የአንዱ አገር ልሳን ነው። ኃቁ ይህ ነው። የኤርትራው ትግርኛ የበላይነት የማቀዳጀቱ ዘመቻ ተሓህት/ወያነ ብቻ ሳይሆን የአሜሪካ ድምጽ ሬድዮም ሥራ ሆኖ ነው የሚገኘው።
• እውን የተሓህት/ወያነ ታላቅ ትግራይን ለመመስረት ነው የታገለው?
ሌላኛው የተሓህት/ወያነ መንደርተኝነት፣ ለምዕራቡ የትግራይ ክፍልና ለኤርትራ የሚያደላና የበለጠ የሚቆረቆር መሆን፣ መላው ትግራይን በዕኩል ዓይን እንደማይመለከት አስረጅ የሆነ አብይ ጉዳይ ሥልጣን ላይ ከወጣ ጀምሮ እንዴት የክፍለ-ሀገሩን ካርታ (Map) እንደለዋወጠው ነው። ይህ ጉዳይ ከተሓህት/ወያነ የትግራይ ነፃ አውጭ ነኝ ባይነት ጋር ተያይዞ የሚነሳ ጉዳይ በመሆኑ፤ አንዳንድ ወገኖችም ከተሳሳተ መነሻ በመንደርደር ድርጅቱ መላ ትግራይን ዕኩል የሚያፈቅርና ታላቅ ትግራይን የመመስረት አጀንዳ ያለው አድርገው ስለሚቆጥሩ በሚገባ ሊብራራ የሚገባ ታላቅ ጥያቄ ነው።
እላይ ለመግለጽ እንደተሞከረው የትግራይ ሕዝብና የተሓህት/ወያነ ዓላማዎች ለየቅል ናቸው። ድርጅቱም የትግራይን ሕዝብ በመላ በእኩልነት ዓይን እንደማይመለከት እላይ ለመግለጽ ተሞክሯል። ተሓህት/ወያነ ለምዕራባዊው ክፍል የሚያደላ፣ ለሚወደው ለሚሳሳለት አካባቢ ጨምሮለትና (ይህ ራያን አይመለከትም፤ የተወሰደበት መሬት ከተጨመረለት ያነሰ ነው።) የሚጠላውንና ቂም የቋጠረበትን ግን ጐምዶ ጐማምዶ ያስቀረውን ትግራይን የመገንጠል አጀንዳው (ከኢትዮጵያ ገንጥሎ ከኤርትራ ጋር ለማዋሃድ) ያልቀየረ፣ የትግራይ ሕዝብ ስትራቴጂያዊ ጥቅሙ የሚያስከብርለትንና በዘመናት መስዋዕትነት የገነባውን ኢትዮጵያዊነቱን የሚገድል ድርጅት እንጂ ለትግራይ ጥቅምና ታላቅነት የሚጥር ድርጅት አይደለም። የተሓህት/ወያነ የትግራይ መውደድና ተቆርቋሪነት የሚገለጸውና እውን የሚሆነው በነባራዊው ዓለም ሳይሆን እውነቱን ማየት በተሳናቸው ተቃዋሚዎችና በያዘው ልቀቀው ዘፈንና በወርቅ ዘር አፍዝዝዝ አደንዝዝ ፕሮፓጋንዳ በታወሩ የዋኅን የክፍለ-ሀገሩ ተወላጆች ምናብ ውስጥ ነው። በነባራዊው ዓለም የምናየው እውነታ ግን የዚህ ተቃራኒ ነው።
በመሠረቱ የተሓህት/ወያነ አመራር የትግራይን ሁሉንም አካባቢዎች እኩል ወይም በተመዛዛኝ ሁኔታ ያልወከለ፣ የክፍለ-ሀገሩን ሕዝብን በእኩል ዓይን የማያይ፣ ከብቅለቱም ጀምሮ በምዕራብ ትግራይ ተወላጆች የተሞላና ለዚያ የሚያደላ ሆኖ የተፈጠረ ስለሆነ ታላቅ ትግራይን የመፍጠር ዓላማ አልነበረውም፤ የለውምም። በርግጥ ግምባር ገድሊ ሓርነት ትግራይ (ግ.ገ.ሓ.ት. = TLF) የተባለው ተሓህት/ወያነ ያጠፋው ድርጅት እንዲህ ዓይነቱን ዓላማ ይዞ ተንቀሳቅሶ የነበረ በመሆኑ የተጫረውን ስሜት ለመሳብ አልሞ ሊሆን በሚችል ምክንያት ተሓህት/ወያነም እንዲያ የመሰለ ግን ጠበብ ያለ ካርታ ይዞ የተወሰነ መንገድ ተጉዟል። እውነተኛው አጀንዳውና ዓላማው ግን ሥልጣን በጨበጠ ጊዜ አሳይቷል። በእርግጥ ተሓህት/ወያነ ገና የቀረው ያልቋጨው ቁልፍ አጀንዳ አለ። ይህም ቢቻል እሱ የፈጠራትን የአሁንዋን ትግራይ በመላ ካልሆነ ደግሞ ምዕራባዊና ሰሜናዊ ክፍሏን ገንጥሎ ከኤርትራ ጋር የማጠቃለል አጀንዳ ነው። ከቅርብ ጊዜ ወዲህ እነ አቶ ስብሓት ነጋ ትግራይና የቀሩት የክፍለ-ሀገሩ ክፍሎች ታሪክና ግንኙነት አስመልክቶና ኤርትራን አስመልክቶ ፍንትው እያደረጉልን ያሉት አመለካከት ልብ ላለው ሰው ይህንን ጠቋሚ ነው። ’’የራስዋ እያረረባት የሰው ታማስላለች’’ አንዲሉ ለዜጐችዋ በቂ የትምህርት ተቋማትና ጥራት ያለው ትምህርት ማቅረብ ያልቻለችው ኢትዮጵያ ጠላታችን ነሽ ብለው ጡቷን ለነከስዋትና መገንጠልን መርጠው ለጠነጠንዋት የኤርትራው ክፍል ተወላጆች ሲሆን ጊዜ በርዋን በርግዳ ማምበሽበሽዋ አቶ መለስ የደሰኮሩልንም ሌላ ነገር አይደለም የሚያሳየን። አቶ መለስ ይህንን ሲነግሩን በብሽቅ ቀመር እርር-ድብን በሉ ለማለት ፈልገው ይሁን ወይም እንደ ድል ቆጥረዉት፤ ወይም ለእናታቸው የትውልድ አካባቢ ሰዎች ያላቸው የተለየ ፍቅር ሊያሳዩን ፈልገው ይሁን እምብዛም ሳይገደን ዓላማው ግን በኢትዮጵያዊያን ሃብት ኤርትራን በተማረ የሰው ኃይል (Human Capital) ለማጠናከር መሆኑን ማወቅ ይገባል። ከፍ ሲል ደግሞ ለመጪው የትግራይ-ትግርኚ ምሥረታ ቅድመ ዝግጅት ሊሆን እንደሚችል አለመጠርጠር የአእምሮ ስንኩልነት ነው።
በአጭሩ ተሓህት/ወያነ ታላቅ ትግራይ የመመስረት ዓላማ የለውም። ተሓህት/ወያነ ለኤርትራ ካለው ፍቅር በቀር ይዞት የዘለቀ መሠረታዊ አስተሳሰብ የሌለው፣ ከግራ ጫፍ ወደ ቀኝ ጫፍ የሚንከላወስ፣ በየወንዙ ዳር አቋሙን የሚለዋውጥ የአየር-ባየር ፖለቲካ አራማጅ ስለሆነ እንዲህ ወይም እንዲያ አያደርግም ወይም ያደርጋል ማለት ቀላል ባይሆነም ቢያንስ እስካሁን እንዲህ ዓይነት ዓላማ የለውም። ተሓህት/ወያነ ታላቅ ትግራይን የመመሥረት ዓላማ ቢኖረው ኖሮ ሂሳብ ሳያወራርድ ተሯሩጦ ኤርትራን ባላስገነጠለ፣ በረጅም ዕቅዱና ህልሙ መሠረት ወደፊት ኢትዮጵያ ብትንትኗ ወጥቶ በትናንሽ መንግሥታት ስትተካ ትግራይ ወደ ባሕር ቅርበት እንዳይኖራት በማቀድና (ባሕሩ ያለው በምሥራቅ በኩል ስለሆነ!) በትግርኛ ተናጋሪው ሕዝብና በአፋር ሕዝብ መካከል የግጭት ጥንስስ እንዲሆን በማሰብ የቀድሞዋ ትግራይ ግማሽ ያህል የሆነውን የክፍለ-ሀገሩን ምሥራቃዊ፣ ሰሜናዊ-ምስራቅና ደቡባዊ-ምሥራቅ ክፍልን ቆርጦ ወደ አፋር ክልል ባላካተተ ነበር (ካርታ ቁ. 4, 5 እና 6 ይመልከቱ)።
የተሓህት/ወያነ መሪዎች በምሥራቃዊ ትግራይ ሕዝብ ላይ ከፍተኛ ጥላቻ፣ ፍርሃትና ንቀት የተደበላለቀበት ስሜትና አጀንዳ ይዘው ነው የሚጓዙት። የአቶ ስብሓት “እንደርታዎች ትልቅ ዳቦ እንጂ ትልቅ ሰው የላቸውም፣ እንደርታዎች ሙያተኛ ለማኞች ናቸው፣” ዓይነት ብልግና የተመላበት አነጋገር፤ የምዕራቡ ክፍል ተወላጅ የሆኑና የነሱ አሽከሮች እንደሚያላዝኑት እንደርታዎች፣ ዓጋመዎች፣ ራያዎች ምንም አልተዋጉምና የጠላት መሣሪያ ነበሩ፤ “ትግርኛ ዓድዋ ተወለደች፣ አክሱምና ሽሬ አደገች፣ ዓጋመና ተምቤን ታመመች፣ መቐለ ሞታ ራያ ተቀበረች፤” ወዘተ … የመሳሰሉ ብልግና የተመላባቸው የንቀት አነጋገሮች የተራው ዜጋ መረን የለቀቁ የመሸታ ቤት ቀልዶች ወይም መዘራጠጦች አይደሉም፤ የቱባ ቱባ የድርጅቱ መሪዎች እምነቶችና አመለካከቶች ናቸው። ድርጅቱ ደግሞ የሚመራው እንዲህ ዓይነት የዘቀጠ አሳፋሪና ኋላ ቀር አመለካከት የሚያመነጭ አእምሮ በተሸከሙና እንዲህ ዓይነት አቋም በሚያራምዱ ፋሺስቶች ነው።
የተሓህት/ወያነ መሪዎች እንዲህ ዓይነት አመለካከት አንግበው ደግሞ እንዲህ ከሚንቁትና ከሚጠሉት ሕዝብ ጋር የሚያቆራኛቸውን ታላቅ ትግራይ ለመመስረት የሚነሱበት አሳማኝ ምክንያት የለም፤ እስስትን የሚያስንቀው ተለዋዋጭ ባህሪያቸው እንዳለ ሆኖ።
map4
ካርታ ቁጥር 4 ተሓህት/ወያነ ሥልጣን ከመቆጣጠሩ በፊት የነበረው የትግራይ እና ተጐራባች ክፍለ-ሀገሮች ክልል የሚያመለክት ሲሆን ከዚህ በታች የሚታየው ካርታ ቁጥር 5 ደግሞ ድርጅቱ የመንግሥትን ሥልጣን ወሮ ከያዘ በኋላ ያወጣው ነው። ካርታ ቁጥር 5 ድርጅቱ መጀመሪያ ቀርፆዓቸው ከነበሩት ሁለት ካርታዎች ፈጽሞ የተለየ ነው (በክፍል 1 ውስጥ እና ወረድ ብሎም በአባሪነት ከቀረቡት ካርታ ቁጥር 1 እና ቁጥር 2 ጋር ያነጻጽሩ)። እንዲህ ዓይነቱ መገለባበጥ አንድም የድርጅቱን የመነሻና የመድረሻ አቋምና አምክንዮ አልባነት፣ አለያም ወንዝ በተሻገረ ቁጥር የሚጠቀምበት ተራ የማጭበርበር ዘዴ ከመሆን አልፎ ሌላ ምንም ነገር ሊሆን አይችልም። ተሓህት/ወያነ ሲመሠረት ፀረ-አማራ ጠባብ ብሄርተኛ ድርጅት፣ ሰንበት ብሎ ደግሞ የብሄር-ብሄረሰቦች መብት የተከበረባት ኢትዮጵያ እውን ለማድርግ የሚታገል አገራዊ ኃይል፤ አንዴ በማርክሳዊ-ሌኒናው ርዕዮተ-ዓለም የሚመራና ዓለም-አቀፋዊ ራዕይ ያለው (እሱ ነኝ እንደሚለው የትግራይ ብሄረተኘቱን ሳይለቅ) የዓለም የላብ አደሮች ትግል አካል፣ ከረምረም ብሎ ደግሞ የካፒታሊስት ሥርዓት አራማጅና የሥርዓቱ አፍሪካዊ ደቀ-መዝሙር፣ ሌላም ሌላም መሆኑን ላስተዋለ ይህ ድርጅት ከአየር ባየር ተራ የፖለቲካ አጭበርባሪነትና አቋም የለሽነት በቀር ሌላ ባህርይ ሊያይበት አይችልም። ተወደደም ተጠላም ተሓህት/ወያነ ከውልደቱ ጀምሮ ያልቀየረው አላማ ቢኖር ኤርትራ የተባለችን አገር መፍጠርና ጥቅሟን ማስጠበቅ ብቻ ነው።
Map5
ተሓህት/ወያነ አገሪቱን ከመቆጣጠሩ በፊትና ከተቆጣጠረ በኋላ ያሉት ካርታዎች (ካርታ ቁጥር 4 እና 5) አንድ ላይ ተጣምረው ሲነጻጸሩ ተሓህት/ወያነ ምንን ከማንና ከየት ወስዶ ለማንና በየት በኩልስ እንደጨመረ በግልጽ ለመረዳት ይቻላል። ድርጅቱ በከበሮ አሳጅቦ የሚለፍፈውን ሳይሆን የሚያደርገውን ለማየትና ለማወቅ ለሚፍልጉ ይህ ተግባሩ ቢያንስ ቢያንስ የድርጅቱ አድላዊነት ለማን እንደሆነ ለመገንዘብና ዓላማውን ለማወቅ የሚያስችል መነጸር ነው (ካርታ ቁጥር 6 ይመልከቱ)።
ከዚህ በታች በካርታ ቁጥር 6 ለማመልከት እንደተሞከረው በቁጥርና ፊደል ከተመለከቱት የትግራይ አውራጃዎች ቆርጦ ወደ አፋር ክልል ያካተተው በካርታው ላይ የተመለከቱት አውራጃዎች የቆዳ ስፋት አሁን ቀርቶ ካለው በእጅጉ የበለጠ ነው፤ ከዓጋም አውራጃ በቀር።
Map6
ትክክለኛ ግምቱን ለካርታ ባለሞያዎች ትቶ የዓይን ግምት ቢሰጥ ከድሮዋ ትግራይ ግማሽ (50 %) ያህሉን ነው ተሓህት/ወያነ ወደ አፋር ክልል የሰደደው። ይህ የተደረገው ደግሞ ከዓድዋ፣ አክሱምና ሽሬ ሳይሆን ከዓጋመ፣ ከኽልተ-ኣውላዕሎ፣ ከእንደርታና ከራያና አዘቦ ነው። ከፊል ተምቤንን ጨምር እነዚህ አውራጃዎች ደግሞ ድርጅቱ በኢድኅ፣ በኢሕኣፓና በደርግ ደጋፊነት፤ ለትግሉ ምንም ወይም የረባ አስተዋፅዖ ባለማድረግ፣ በፀረ-ኤርትራነትና በመሳሰሉት ሌሎች የተለያዩ ምክንያቶች ቂም ቋጥሮባቸው የኖሩ አካባቢዎች ናቸው።
ማጠቃለያ
እላይ ለማመልከት እንደተሞከረው የትሓህት/ወያነና የትግራይ ሕዝብ ዓላማ ሆድና ጀርባ ነው። የትግራይ ሕዝብ በአሁኑ ወቅት ጐልቶ በሚታይ ደርጃ ይህንን ፋሺስታዊ መንደርተኛ ቡድንን ሲቃወም አለመታየቱ በገሃድ የሚታይ ነገር ነው። ይህ ግን የትግራይን ሕዝብ ብቻ የሚመለከት ጉዳይ አይደለም። አፋሩን፣ ጉራጌውን፣ ኦሮሞውን፣ ሶማሌውን፣ አማራውን፣ ቤንሻንጉሉን፣ … በአጠቃላይ መላውን የአገሪቱን ሕዝብ የሚመለክት ነው። ከዚህ በላይ ደግሞ ይህ ጐሳ-በቀል ፋሺስታዊ አገዛዝ (Ethno-fascist regime) ትግራይን ነጥሎና ከርችሞ ዘግቶ ከሌሎች ክፍሎች በተለያ ሁኔታ የሚገዛበት ሥርዓት ፈጥሯል።
የትግራይ ሕዝብ በተሓህት/ወያነ፣ በሕዝብ ደኅንነት፣ በገበሬዎች ማኅበር፣ በወጣቶች ማኅበር፣ በሴቶች ማኅበር፣ በአካባቢ ህዝባዊ ሠራዊቶች፣ ከድርጅቱ ጦር በተቀነሱ ታጋይ-ነበሮችና በሌሎች መሰል መዋቅሮች እጅ-ተወርች ተቀፍድዶ ያለ ሕዝብ ነው። አገዛዙ ኢትዮጵያን በእስካሁን ታሪክዋ ዓይታው በማታውቅ የደኅንነት መዋቅርና (አንድ ለአምስትን አደረጃጀትን ልብ ይሉዋል) የመረጃ ሠራዊት ተብትቦ በመንፈሳዊ ሽብር አሸማቅቆ እየገዛ ያለ ለመሆኑ እሙን ቢሆንም የትግራይ ሁኔታ ግን ከዚህ እጅግ በጣም የከፋና የጠጠረ ነው። እንኳንስ በአገር ውስጥ በውጭ አገርም በተለያዩ ስብስቦች ለመተብተብ ድርጅቱ የሚሠራው ሥራና የዘረጋው መዋቅር ቀላል አይደለም።
የትግራይ ተወላጆች እንደሌላው በንግድ ፈቃድ፣ በቤት ምሪትና በኮንደምንየም ዕደላ እየተሸነገሉ ሳይሆን አንድም ከሀዲ ትግሬ ተሰኝቶ ላለመነጠል ብለው ነው በድርጅቱ ዙርያ የተኰለኰሉት። ከዚያ ካለፈ ደግሞ እኛ ከሌለንና ከእኛ ጋር ካልወገንክ አማሮችና ነፍጠኞች ያጠፉሃል በሚል መንፈሳዊ ሽብር ተቀፍድደው ነው ከድርጅቱ ጐን የሚኰለኰሉት። ከዚህ በላይ ደግሞ የድርጅቱ የግል ንብረት ተደርጐ ስለ ተሸነሸነ ማንም የክልሉ ተወላጅ ተሓህት/ወያነ እንዲያስብ ከሚፈልገው ውጭ እንዲያስብ እንኳን አይፈቀድለትም። ትግራይ ውስጥ የክፍለ-ሀገሩ ተወላጅም ቢሆን ከድርጅቱ ሌላ ዝር እንዳይል ተደርጐ የተሸነሸነ በመሆኑ ትላንት አብርዋቸው በቆሰሉና በደሙ የትላንት ጓዶቻቸው የተለየ አመለካከት ስለያዙ ብቻ የሚፈጽሙባቸው አረመኔያዊ ተግባር መመልከቱ ይበቃል። ይህ ማመን የሚከብዳቸው ካሉ የችግሩን ሀሁ መገንዘብ እንዳልቻሉ መረዳት ይገባቸዋል።
ምንም እንኳን አብላጫው የየትኛውም የትግራይ ክፍል ሕዝብ የተሓህት/ወያነን ዓላማ የማይደግፍ ቢሆንም አገዛዙ በሚያካሂድበት የስነ-ልቦና ዘመቻ ወዳጁንና ጠላቱን በመለየት ረገድ ብዥታ የለበትም ማለት ግን አይደለም። አገዛዙ ጐሳን ማእከል ባደረገ የግዛት ክፍፍልና ከፋፍለህ ግዛ ዘዴ በመጠቀም በሕዝቡ መካካል የመፈራራትን ንቃቃት ለመፍጠር ያደረገው ጥረት ቀላል አይደለም። እኛ ከሌለን አማሮች፣ ነፍጠኞች፣ የድሮው ሥርዓት ናፋቂዎች፣ የደርግ ርዝራዦች፣ ሻዕቢያ፣ ኦነግ፣ ወዘተ … ያጠፉሃል የሚለው ፕሮፓጋንዳ ዝም ብሎ አሸዋ ላይ እየፈሰሰ ነው ብሎ ማሰብ አስፈሪ ድንቁርና ነው። ይህ ጥረት ደግሞ የፈጠረው አደጋ የለም ማለት አይቻለም። በዝቅተኛ ደረጃም ቢሆን ጐሳዊ አመለካከት እንዲነሳሳና አጥንትና ሥጋ እንዲለብስ እየበቃ ነው። በተቃዋሚው ጐራ ውስጥ የተሰገሰጉ አንዳንድ ዋልጌዎችና የአገዛዙ ስውር መለእክተኞች የሚያሰሙት በትግራይ ሕዝብ ላይ ያነጣጠረ ዛቻና ማቅራራትም በአገዛዙ አፈቀላጤዎችና በየአዋቂ አጥፊ ድርጐኞቻቸው እየተጋነነ ለዚህ ማረጋጋጫና አቀጣጣይ ነዳጅ ሆኖ እያገለገለ ነው። የተቃዋሚው ጐራ ከእንደዚህ ዓይነት መተክላዊና ስልታዊ (strategic and tactical) ስህተት የጸዳ መሆን ይገባዋል።
እላይ ለማብራራት እንደተሞከረው የትግራይ ሕዝብ ወዲህ፤ ተሓህት/ወያነና ሻዕቢያ ከነግሳንግስ ኹርኹሮቻቸው ደግሞ ወዲያ መሆናቸው ተገቢው ግንዛቤ አግኝቶ ሕዝቡን በዕኩልነት የተመለከተና በሙሉ ቅንነትና ኢትዮጵያዊ ፍቅር የሚያይ፣ ታጋሽነት የተመላበት አቋምና የትግል ስልት መከተል የዴሞክራሲያዊ ኃይሉ ይዋል ይደር የማይባል ሥራ ነው። ይህ ደግሞ የዴሞክራሲያዊ ትግሉ ዓቢይ ጥያቄ እንጂ የትግራይንም ሆነ የሌላውን የአገራችን ሕዝብ በተናጠል የሚመለከት ጉዳይ አይደለም። ስለዚህም ነው ዴሞክራሲያዊ የተቃዋሚ ኃይሉ ቆምና ሰከን ብሎ ወዳጅና ጠላትን በቅጡ መለዬት ዋነኛውና ቀዳሚው ግዴታው የሚሆነው። መላውን የአገሪቱ ሕዝብም ይህንን ጉዳይ በሚገባ ማየት እንዲችል ለማብቃት በብቃት መሥራት ያለበት። የሚሰምር ትግል ለማካሄድ ከማን ጋር ተጎዳኝቶ ማንን መታገል እንደሚገባ፤ ማን ጊዜያዊ ወዳጅ፣ ማንስ የዘለቄታ አጋር እንደሆነ መለየት የትግሉ ሀሁ ነው። ወዳጅንና ጠላትን አብጠርጥሮ ማወቅ ለትግሉ ስኬት ወሳኝ አስተዋጾ አለው። እነ ክህደቱን የመሳሰሉ ለወያነ ያደሩ ወይም፤ ቢያንስ ቢያንስ የማይጎረብጡት መጫኛዎች፤ መገለል ያለባቸው መዥገሮች ናቸው ሲባሉ አልሰማ ያሉት የከፈሉት ዋጋና በትግሉ ያደረሱት ጉዳት ለአፍታም ቢሆን ሊዘነጋ አይገባም።
ከዚህ እሳቤ በመነሳት የሚከተሉትን ጥቂት ጥያቄዎች አንስቶ ተገቢ መልስ መስጠት ያስፈልጋል ብዬ አምናለሁ። የትግሉ ዓላማ ምንድነው? ጠላት ማን ነው፣ ለምንስ በጠላትነት ተፈረጀ? በትግሉ ውስጥ ተሳታፊ ነን የሚሉት ወገኖች እነማን ናቸው? ታጋይ ነን ከሚሉቱ ውስጥ ከጠላት ዓላማ ጋር የሚቃረን ግልጽ ዓላማ ያላቸው እነማን ናቸው? የፖለቲካ ሥራ-አጦችና ቀላዋጮች፣ የግል ዝና አስዳጆች? ጠጠር ያለ ነገር ሲያጋጥም ሸብረክ የሚሉ ልፍስፍሶች የሆኑትስ እነማን ናቸው? የሕዝቡ ዝግጁነትስ ምን ያህል ነው? ለምንስ ነው ሕዝቡ ታጋይ ነኝ ላለ ሁሉ ልቡን የሚሰጠው? እንደነዚህ የመሳሰሉ መሠረታዊ ጥያቄዎች ተገቢው መልስ ባላገኙበት ሁኔታ ውስጥ ሆኖ ወደፊት ለመጓዝ መጣር አውድማ ማስኬድ ነው። የአውድማ በሬ መንዳት ነው።
ከትግል ስልትና ወዳጅና ጠላት ከመለየቱ ሥራ ጋር ተዛምዶ ሊነሳ የሚችል ሌላ አንድ በጣም ወቅታዊ የሆነ ጥያቄ አለ፤ ለምንድን ነው የሆነ የፖለቲካ አጀንዳ ይዞ የሚታገል ድርጅት እያለ የተቀዳ እስኪመስል ድረስ ተመሳሳይ የሆነ መርሃ-ግብር ነድፎ ብቅ የሚል አዲስ ድርጅት የሚያስፈልገው? ከመብት ጥያቄ አኳያ ይህንን ማድረግ በመሠረቱ ስህተት ባይሆንም አገራችን በምትገኝበት የክፍፍል አደጋ ውስጥ ተሆኖ ግን ቅንጦት ብቻ ሳይሆን በእሳት መጫወት ነው። እየዬ ሲደላ ነውና ቢቆየንስ?!
የአንድነት ትግሉ በርትቶ አገራችንን ከብተና እንድንታደግና ፍትሃዊ ሥርዓት እንዲነግሥ ግቢያችንን አጽድተን ተቃቅፈን እንራመድ።
አባሪ ካርታዎች (ከክፍል 1)
map1map 2
ዋቢ
ገብሩ አሥራት (2006)፣ ሉዓላዊነትና ዴምክራሲ በኢትዮጵያ፣ Gaithersburg [Maryland]: Signature Book Printing.
Aregawi Berhe (2009). A Political History Of The Tigray People’s Liberation Front (1975-1991). Los Angeles [CA]: Tsehai Publishers.
Gebru Tareke (2009). The Ethiopian revolution: war in the Horn of Africa. New Haven, [Conn.]: Yale University Press.
Jenny Hammond (1999). Fire from the Ashes: A Chronicle of the Revolution in Tigray, Ethiopia, 1975-1991. Asmara: The Red Sea Press, Inc.
ክፍል 3 ይቀጥላል በተዛማጅ ጉዳዮች ላይ::

ህወሓት/ወያነ እና የትግራይ ሕዝብ (ክፍል1)

 ከነብዩ ያሬድ
መግቢያ 

ህወሓት/ወያነ እና የትግራይ ሕዝብ (ክፍል1) የዚህ ጽሁፍ ዋነኛ ዓላማ የትግራይ ሕዝብና የተሓህት/ህወሓትን የግኑኝነት ታሪክና ወቅታዊ ሁኔታ እጅግ በጣም በአጭሩ መግለጽ ነው። የዚህ ፅሁፍ ፀሓፊ የተቃዋሚው ጐራ ውስጥ ወዳጅና ጠላትን የመለየት ብዥታ ሰፍኖ ይገኛል ብሎ ያምናል። ይህንን ብዥታ ማጥራት ደግሞ የአገራዊው ዴሞክራሲያዊ የአንድነት ትግሉ ሀሁ ነው ብሎ ያምናል። ስለዚህ ይህ ጽሁፍ የትግራይ ሕዝብና የተሓህት/ህወሓትን ታሪካዊና ወቅታዊ ግኑኝነት እጅግ አጭር በሆነ መንገድ በመግለጽ ወዳጅና ጠላትን በመለየት ረገድ አስተዋፅዖ ለማድረግ ታስቦ የቀረበ ነው። ይህ ጉዳይ በጣም ሰፊ ከመሆኑ የተነሳ በርካታ ጦማሮች ሊወጣው የሚችል በመሆኑ በዚህ አጭር፣ አጠቃላይና ቀላል አቀራረብ ይሸፈናል የሚል ግምት በዚህ ጽሑፍ አቅራቢ ዘንድ የለም።
ተሓህት/ወያነ የአገሪቱን በትረ-መንግሥት ወሮ ከያዘ ሩብ ምእተ-ዓመት ሊደፍን ነው። በነዚህ ሁሉ ዓመታት ሲለው በዴሞክራሲ ሥም እያላገጠ፤ ሲያሰኘው ደግሞ በፌዴራል ፖሊስና በጦር ኃይል እየደፈጠጠ ሲገዛ ኖሩዋል። የአገዛዙን ኢ-ዴሞክራሲያዊነት ለመገንዘብና እርሱ የሚመርጠው የፖለቲካ ቧልት ሳይሆን ዴሞክራሲያዊ ሥርዓቱን እውን ለማድረግ የሚበጅ ሁነኛ የትግል ስልት መርጦ ለመገኘት የታለፈው ጊዜ እጅግ በጣም ከበቂ በላይ ነው። አለመታደል ሆኖ ግን አብዛኛዎቹ ተቃዋሚ ነን ባይ ድርጅቶች ከመጃጃል ለመላቀቅ ብቃት ሳያገኙ ቀርተው ይሁን ወይም አውቆ የተኛ ቢቀሰቅሱት አይሰማም እንዲሉ ሆኖ የገዢው ቡድን የምርጫ ድራማ አዳማቂና ማላገጫ ከመሆን የዘለለ እርባና ያለው ነገር ሳይሰሩ ዘልቀዉታል። በዚህ ሳቢያ ጐሳ-በቀሉ ፋሺስታዊ አገዛዝ በራሱ ጥንካሬ ሳይሆን በተቃዋሚው ድክመት ሳቢያ ካሰበው በላይ በሥልጣን ኳርቻ ላይ ፍጢጥ እንዳለ ለመክረም የታደለበት ሁኔታ ውስጥ ገብቶ ነው የሚገኘው።
ስለ ተሓህት/ወያነ ማንነትና ምንነት ገና ድርጅቱ ጫካ ሳለ የተነገረና የታወቀ ጉዳይ ነው። ድርጅቱ ሥልጣን ከያዘ በኋላም በወታደር ኃይል እየደፈጠጠ፣ በግፍ የንፁሃንን ሕይወት እየቀጠፈና ለመብታቸው የሚታገሉ ዜጐችን እንበለ ፍትህ ዘብጢያ እያወረደ እውነተኛ ባህርዩ በገቢር አሳውቆናል። በተለያየ ደረጃ የሥርዓቱ አገልጋይ ሆነው አብረው ሲወቅጡን የከረሙትም በሆነ ምክንያት ሥርዓቱን ሲለዩ ስለ ሥርዓቱ ግምነት መስክረውልናል። የሥርዓቱ ቁንጮ የነበሩት ሟቹ ሰውዬም ጣታችን፣ እጃችን ወዘተ … እንደሚቆርጡን እኝኝ እስኪለን ድረስ እየዛቱና በገቢርም እያሳዩን ለአገሪቱና ለሕዝቧ ያላቸውን ንቀትና ጥላቻ አሳይተውናል። ይህ ሁሉ ግን የሚገባንም የሚሰማንም አንመስልም። አገዛዙ እራሱ ‘እኔ ግም ሥርዓት ስለሆንኩኝ መወገድ ይገባኛልና ይኸው እራሴን በራሴ መነገልኩላችሁ’ እስኪለን የምንጠብቅ ነው የምንመስል። ይህ ደግሞ ሲያምረን ይቀራል እንጂ መቼም ቢሆን የሚፈጸም አይደለም።
ካለፈው የቅርብ ጊዜ የአገራችን ታሪክ ልንማር እንደምንችለው አገዛዞች በሕዝብ ቢጠሉም፣ ባይፈለጉም ራሳቸውን በራሳቸው ሲፈነግሉ ወይም ተነው ሲጠፉ አልታዩም። ለምሳሌ በየካቲት 1966 ዓ.ም. ሕዝባዊ አብዮት የተገረሰሰው ዐፄያዊው ሥርዓት ተዳክሞና አብቅቶለት ሳለ ገፊ አሻ እንጂ ራሱን በራሱ አልፈነገለም። ተሓህት/ወያነ ገረሰስኩት፣ አሸነፍኩት፣ ቅብርትስ እያለ የሚመጻደቅብን የኢሠፓ/ኢህዴሪ ሥርዓትም ቢሆን ሕዝቡ ፊት ነስቶት፣ ድጋፍ ነጥፎበት፣ ውስጡ ተቦርቡሮና በቁሙ ደርቆ እያለ ራሱን በራሱ አልመነገለም፤ ሎተሪ በወጣለት ተሓህት/ወያነ እስኪተካ ጠበቀ እንጂ። የተሓህት/ወያነ ፋሺስታዊ መንደርተኛ ቡድንም ከእርሱ በፊት እንደነበሩቱ አስወጋጅ ኃይል እስኪያገኝ ድረስ ቀርንቶም ቢሆን ባለበት መገኘቱ የማይቀር ነው። ሁኔታው የሚጠይቀው ይህንን ሆኖ ሳለ ተቃዋሚ ነን ባዮች ግን አሁንም ጊዜአቸውንና ጉልበታቸውን የሚያባክኑት ከምጽአተ-ተሓህት/ወያነ ዋዜማ አንስቶ ታውቆ ያደረውን የአገዛዙን ፀረ-ኢትዮጵያዊነት፣ ኢ-ዴሞክራሲያዊነት፣ ቤተ-ሰባዊነትና መንደርተኛነት፣ ሙሰኛነት፣ ወዘተረፈ … በመደስኮር ላይ ነው። ብዙ ተቃዋሚ ነን ባይ ወገኖች የድግምት ነገር እስኪያስመስልባቸው ድረስ ቆርጦላቸው ከእንደዚህ ዓይነት አባዜ ለመውጣትና ከአገዛዙ ጋር የሚያደርጉትን ድሪያ ለማቆም በቅተው አይታዩም።
እርግጥ ነው የተቃዋሚው ጐራ ውስጥ ጥራት ጐድሎ፣ የእንክርዳዱም የስንዴውም አንድላይ መርመስመስ አብዝቶ የሚታይ በመሆኑ ተቃዋሚውን ኃይል በአንድ የወል ሥም በጥቅሉ በተቃዋሚነት ብቻ ፈርጆ ማየት አይቻልም። አይገባምም። ለከፊሉ የተቃዋሚው ጐራ ዴሞክራሲያዊ ሥርዓትን ማምጣት፣ አገርን ከጥፋት መታደግ፣ ሕዝብን ከአረመኔአዊ ጐሰኛ አገዛዝና ከድኅነት አረንቋ ነፃ ማውጣት የትግሉ ማዕከል ነው። ለሥራ-አጥ ፖለቲከኞች ደግሞ የአሠሪና ሠራተኛ መገናኛ ማዕከል ነው። ለሌሎቹ ደግሞ የጡረታ ዘመን ጊዜ ማሳለፊያና ዝና መሸመቻ ገበያ ነው። በእርግጥ ፀረ-አገዛዙ ትግል ለአንዳንዶቹ የጡረታ ጊዜ ማሳለፊያ ነው ሲባል፤ ትግሉ የወጣቶችና የጎልማሶች ብቻ ነው የሚለውን ደካማና ከፋፋይ ቅኝት ለማቀንቀን ወይም ለመደገፍ አይደለም። የሕዝባቸው መከራና የአገራቸው ህልውና አደጋ ላይ ወድቆ መገኘቱ ሠላም ነስቷቸው፤ በማረፊያ ጊዜአቸው ለሕዝባቸውና ለአገራቸው ከልብ ተቆርቁረው ሲታገሉ መከራ የተቀበሉ፣ ለፋሺስታዊ ሥርዓት ጥቃት የተዳረጉና አሁንም በእንደዚህ ዓይነት ሁኔታ ውስጥ ሆነው የሚታገሉ አዛውንቶች መኖራቸው የአደባባይ ምስጢር ነው። መጥቀስ የተፈለጋው እንዲህ ያልሆኑትን ነው። ነገር ጠጠር ሲልና የሚያስጠጋ ሲገኝ ሸብረክ ብለው ከሞሰቢቱ ስር የሚነጠፉ፤ አገዛዞቹ ደክመው ሲታዩዋቸውና አስጠጊ ሲታጣ ደግሞ የሕዝብ መብት አስከባሪ ፊታውራሪዎች ሆነው የሚያደናግሩትን ነው። ያም ሆነ ይህ ግን የተቃዋሚው ጐራ ጥራት ነጥፎበታል። እውነተኛ ለሕዝብ መብት የሚታገሉ ኃይሎች፣ የምርጫ ሰሞን አውደልዳዮችና ፍርፋሪ ለቃሚ የፖለቲካ ሥራ-አጦች አንድ ላይ የሚርመሰመሱበት ዝብርቅርቁ የወጣ የገበያ ቦታ ሆኖ ነው የሚታየው። ድክመት ጠርንቆ ይዞትና ጨለምተኛነት አጥልሎበትም ተስፋን አምካኝ ሆኗል። በዚሁ ጐራ ውስጥ የሚርመሰመሱት አብዛኛዎቹ ተቃዋሚ ነን ባይ ስብስቦች ገዢ ቡድኑ ሲያጉረጠርጥባቸው ጭራቸውን ቆልፈው የሚሸመጥጡና ላላጠፉት ጥፋት ምህረትን የሚማጸኑ የአገዛዙ አሻንጉሊቶችና ተስፋ አስቆርጭ የሕዝብ ማፈሪያዎች ሆነው ነው የሚታዩት። የተሻለ ነው ከተባለም ከድምፅ መስጠቱ በፊት ድምፁ ተቆጥሮ ባለቀለት፣ ቢሸነፍም ባይሸነፍም አሸናፊው ገዢ ቡድኑ በሆነበት ምርጫ ለመሳተፍ እየተሽቀዳደሙ ከምርጫው በፊት ተሸንፈው ለውድድር የሚቀርቡ ለአገዛዙ የምርጫ ቧልት ሽፋን ሰጪ ከመሆን አያልፉም። ጥቂት የጸና አቋም ይዘው የሚታገሉ ግለሰቦች በየድርጅቶቹ ሊገኙ መቻላቸው አሌ የማይባል ቢሆንም የአብላጫው የህገ-ደደቢት አክባሪ ተቃዋሚዎች ባህርይ ግን ከዚህ ብዙ ርቆ የሚታይ አይደለም። የትግሉ በእንደዚህ ሁኔታ ውስጥ እየዳኸ መገኘት የብዙዎችን ስሜት መጉዳቱ የማይቀር ጉዳይ ነው። ከዚህ ጋር በተያያዘ ምክንያትም የተለያዩ አመለካከቶች ሲሰነዘሩ ይስተዋላል። አንዳንዴ ሰዎች ተቃዋሚ ድርጅቶችን ‘መተባበር የማይችሉ፣ ደካሞች፣ ወዘተ …’ እያሉ ሲያብጠለጥሉና ሲተቹ ይሰማል። ‘ምን የረባ ተቃዋሚ አለ፣ ዝም ብሎ የራስን ሕይወት መኖር ይሻላል’ ዓይነት ምክንያትም ሲሰጥ ይደመጣል። የአባባሎቹ እድምታ በደፈናውና በጥቅል ሳይሆን ከባዩ ማንነት ጋር ተቆራኝቶ ሊፈተሽ ይገባል። ለትግሉ አቅማቸው የፈቀደውን ያህል አስትዋጽዖ እያበረከቱ የሚጠብቁት ውጤት ወይም መሆን ያለበት ነገር ሆኖ ሳያዩ ሲቀሩ እንዲያ የሚሉ ወገኖች አሉ፤ አይፈረድባቸውም። ለአስረሽ ምችውና ለግል ጥቅም ሲሆን ከተፎዎች፤ ለሕዝብና ለአገር ጉዳይ ሲሆን ደግሞ የውኃ ሽታ ሆነው የሚገኙትም ወሬ ለመጠረቅና የሞራል ንቅዘታቸውን ለመሸፈን ሲሉ እንዲያ ይላሉ። የዓላማ ጉዳይ ሆኖባቸው የአገዛዙ ስውር መልዕክተኞችም ሕዝቡን ተስፋ ለማስቆረጥና የተቃዋሚ ጐራውን ለማዳከም እንዲያ ይላሉ። በርግጥ ዕውነተኛ ያልሆኑ አላጋጭ ግለሰቦችና ስብስቦች በተቃዋሚው ሠፈር እንዳሉ፣ እያውደለደሉና ለመናኛ ጥቅም ሲሉ ትግሉን እንደሚያዳክሙ መካድ አይቻልም። ያም ተባለ ይህ ግን የተቃዋሚ ድርጅቶች ድክመትም ሆነ ጥንካሬ የሕዝቡ ድክመትና ጥንካሬ መገለጫ ከመሆን አያልፍም። ወዳጅና ጠላቱን አነጥሮ፤ የማንም ሰሞነኛ አውደልዳይ ማላገጫ ከመሆን ራሱን ታድጐ፤ እውነተኛ ተቃዋሚዎችን አቅፎና ደግፎ ማጠናከር የሕዝቡ ድርሻ ነው። እንዲያ ሲሆን ብቻ ነው የተቃዋሚዎች ክንድ ፈርጥሞ የሕዝቡን ትግል በአግባቡ ለመምራት አቅምና ብቃት የሚኖረውና ይህንን ጐሳ-በቀል ፋሺስታዊ ቡድን ጨርሶ እንዲወገድ ለማድረግ የሚችለው።
ሕዝቡ ለመጣው ሁሉ ልቡንና ኪሱን በርግዶና የጉዳዩ ባለቤትነቱንም አሳልፎ ሰጥቶ መጠቀሚያና መቀለጃ ሆኖ ከተገኘ ግን እውነተኛ ተቃዋሚዎች ሊዳከሙና ትግሉ ሊራዘም፣ እንዲያም ሲል ሊመነምን የግድ ነው። ልብ እንበል! ሕዝባዊው የትግል ጐራ ስንቶቹን አለሌዎችን ነው ያስተናገደው? ለስንቶቹ ነው ድርጐ የተሰፈረው? ስንቶቹ ናቸው ጦራችን አዲስ አበባን ከቧል ብለው ያላገጡብን? እነ ክህደቱ፣ እነ ምህረት ተመጽዋች ተንበርካኪዎች፣ እነ ሲያቃጥል በማንኪያ ሲቀዘቅዝ በእጅ መንታፊዎች፣ ስንትና ስንቱ ነው በሕዝቡ የቀለደው?!
በመሠረቱ በትግሉ ውስጥ ወሳኙ ጥያቄ የሕዝቡ ወዳጅና ጠላቱን ለይቶ፣ አላጋጩና የምር ታጋዩን አንጓሎ፣ ጥንካሬና ድክመቱን መዝኖ ጉዞውን እስከመጨረሻው ለመጓዝና ትግሉ የሚጠይቀውን ዋጋ ለመክፈል ተዘጋጅቶ መነሳት ነው። የወጣቱ ትውልድም ራሱን በዕውቀት አንፆ፣ የአገሩን እውነተኛ ታሪክ አውቆና ታሪኩ የተሠራበትን ወቅትና ሁኔታ ተገንዝቦ፣ ከጠባብ መንደርተኛ አስተሳሰብና ጨለምተኛነት ራሱን አፅድቶ፣ የቀደምት ትውልድን አገራዊ ተጋድሎና ጀግነነትን ወርሶና አድሶ መገኘትም ሌላኛው ለዴሞክራሲያዊ ትግሉ መስመር ወሳኝነት አለው። በዚህ ረገድ መረጃ ያለው ድርሻ ከፍተኛ ነው። የሕዝብን ሁለንተናዊ መብት ለማስከበርና የአገር አንድነትን ከጐሳ-በቀሉ ፋሽስታዊ ቡድኑና ጋሻ ጃግሬዎቹ ጥቃት ለማዳን የሚታገሉ ቁርጠኛ ታጋዮች ካሉባቸው ግዙፍ ሥራዎች መካከል አንዱ እውነተኛው ታሪክና ተረት-ተረቱ ነጥሮ እንዳይታይ የጋረደውን ጉም መግለጥ ነው።
በዛሬ ወቅት በተሓህት/ወያነ የአገዛዝ ዘመን ተፈጥረው ጉልቻ ለመመስረት ለበቁ ዜጎች ታሪክ ተብሎ የሚነገራቸው መርዘኛ ተረት-ተረትና የውሸት ታሪክ ነው። በኢትዮጵያዊያን መካከል ያለውን ለዘመናት የተገነባውን አብሮነት ለማዳከምና የተለያየ ማንነት ለመፍጠር በዚህ ጐሳ-በቀል ፋሺስታዊ ቡድን እየተፈፀመ ያለው መርዘኛ ተግባር በጣም አደገኛ ነው። ስለዚህም፤ የእንደነ አቶ መለስ ዜናዊ የመሳሰሉት የባንዳ ቤተሰቦች ባያደርጉትም፤ ትላንት የየቤተሰቡ ተግባር የነበረው የኢትዮጵያ ምንንነትና ማንነት የማስረዳትና ህቡር ታሪኳን የማስተማር ተግባር የፖለቲካ አጀንዳ ሆኖ ለማየት የተገደድንበት ሁኔታ ላይ ደርሰናል። ይህ ፀረ-አገር አገዛዝ ዓላማው እየሰመረለት ታሪክ ሁሉ፤ ያውም የጐጥ ታሪኮች ከሱ የጀመሩ እስኪመስሉ ድረስ እየተበጁ ነው። ይህ ስሌት ደግሞ ከመቶ ዓመትም በጣም፣ በጣም ያነሰ ነው። በተለያየ አጋጣሚ ቁጥራቸው ቀላል ያልሆነ የትግራይ ክፍለ-ሀገር ተወላጅ ወጣቶችና ጐልማሶች በየዋህነት የዚህ ጐሳ-በቀል ፋሺስታዊ ቡድን አፍዝዝ አደንዝዝ ፕሮፓጋንዳ ግዳይ ሆነው የተሳሳተ ተረት-ተረት ሲያስተጋቡ ይስተዋላል። እነዚህ ወጣቶችና ጐልማሶች ከወያነ በፊት አማራ የሚባል ብሔር ገዥ እንደነበረና በተሓህት/ወያነ እንደተወገደ ያምናሉ። የደርግና የኢሠፓ/ኢህዴሪ መንግሥት ትግርኛ ተናጋሪውን ሕዝብ ብቻ ለይቶ ለማጥፋት ዘምቶ እንደነበርና የተሓህት/ወያነ እንደመከተው ያምናሉ፤ ይህንንም ደግፈው ይሞግታሉ። እስከ ምጽአተ-ተሓህት/ወያነ ድረስ ከሁሉም የኢትዮጵያ ክልሎች ተነጥሎና ሆን ተብሎ ትግራይ ብቻ የፖለቲካ፣ የኢኰኖሚና የማኅበራዊ መብቶቹ እንዲገፈፍ ተደርጎ ነበር ብለው ያምናሉ። ይህ በጣም የተሳሳተ አመለካከትና ድምዳሜ ቢሆንም በአገዛዙ እመቃ ምክንያት ሌሎች ወገኖች እውነተኛውን ታሪክ ማቅረብ በማይችሉባትና እውነተኛውን ታሪክ ለማወቅ ዕድሉ በማይገኝበት ትግራይ ውስጥ ሆነው የሚያርሙት አይሆንም።
በተቃዋሚው ጐራ ውስጥ አገዛዙ የተከላቸው አማኬላዎችም የባንዳ ተልዕኰአቸውን ለመወጣት የእብድ ገላጋይ ድንጋይ ያቀብላል እንዲሉ በትግራይ ሕዝብ ስነ-ልቦና ውስጥ ጥርጣሬ የሚፈጠር አርቲ ቡርቲ በመንዛት የሕዝቡን አንድነት ለማዳከምና የኅብረት ትግሉን ለማሰናከል ምክንያት ሆነዋል። የኤርትራና የሌሎች የብዙ አካባቢዎች ሁኔታም ከዚህ ብዙ የተለየ አይደለም። በዚህ ምክንያት ነው እውነተኛ ታሪክን ማሳወቅ፣ ሕዝቡ ወዳጅና ጠላቱን እንዲለይ ትክክለኛ ዕውቀት መስጨበጥና ትክክለኛ መረጃ ማሰነቅ የማንኛውም የሕዝብ ወገን የሆነ ሁሉ ዋነኛ ተልዕኰና ከግዳኞቹ አንደኛው የሚሆነው።
ወዳጅና ጠላትን በመለየቱ ሥራ ውስጥ የአገዛዙ እስትንፋስ የሆነው ፋሺስቱ ተሓህት/ወያነ ከትግራይ ሕዝብ ጋር የነበረውን፣ ያለውንና ሊኖረው የሚችለውን ግንኙነት በሚገባ መፈተሽ ቀዳሚው ሥፍራ መያዝ ያለበት ጥያቄ ነው። ይህንንም ሁኔታ በሚገባ ለመረዳት “የተሓህት/ወያነ የትግራይ ሕዝብ ነፃ አውጭና ተቆርቋሪ ነውን? የትግራይ ሕዝብ ከመሰረቱ ጀምሮ የተሓህት/ወያነን ዓላማ ደግፎና በእርሱ ተመርቶ ተንቀሳቅሷልን? እውን የተሓህት/ወያነ ታላቅ ትግራይን ለመመስረት ነው የታገለው? ሁሉንም የትግራይ አካባቢዎችንና ተወላጆችንስ በዕኩል ዓይን ይመለከታልን?” የመሳሰሉ ጥያቄዎችን አንስቶ መወያየት ያስፈልጋል። በዚህ ረገድ የቀድሞ የተሓህት/ወያነና የኢህኣዴግ ፖሊት-ቢሮ አባልና የተሓህት/ወያነ ትግራይ ክልል አስተዳዳሪ የነበሩት አቶ ገብሩ አሥራት የጻፉት መጽሓፍ ከፍተኛ አስተዋጽዖ አለው።
የአቶ ገብሩ መጽሓፍ የተሓህት/ወያነን ክንብንብ በከፊል ገልጦ እውነተኛ ማንነቱና ተግባሩ ያሳየ የውስጥ አዋቂ ምስክርነት ነው። የድርጅቱና የትግራይ ሕዝብ ግንኙነት ባህሪይንም ያሳየ ነው። ድርጅቱና የአመራሩ አባላት በሕዝቡ ላይ የፈጸሙት ወንጀልና ክህደትንም በተወሰነ ደረጃ እርቃን ያወጣ ነው። ለዚህም ነው አቶ አበበ ተክለ-ኃይማኖትን (ጆቤን)፣ ዶ/ር አዲስ-ዓልም ባሌማን፣ አቶ ስብሓት ነጋን ጨምሮ ብዙ የድርጅቱ አመራር አባላት፣ አመራር-ነበር ግለሰቦች፣ አባላትና ጋሻ ጃግሬዎችን ያንጨረጨረው። እንደ የዚህ ጽሑፍ አቅራቢ ዕምነት የአቶ ገብሩ ሥራ የዚህን መሰሪ ፀረ-ሕዝብና ፀረ-አገር ድርጅት ወንጀሎችንና የአገር ክዳትን ተግባራት በማጋለጥ ረገድ ያበረከተው አስተውጽዖ እጅግ ከፍተኛ ነው። ያም ሆኖ ግን ገና ብዙ መገለጥ የሚገባቸው ያልተጋለጡ ድርጅቱን የሚመለከቱ ጉዳዮች አሉ። ስለዚህ አቶ ገብሩ ገና የሚያስነብቡን የሚያሳውቁን ምስጢርና ቁም ነገር ይኖራል ብየ አምናለሁ። ይህ ማለት ግን ይህንን ማድረግ የአቶ ገብሩ አሥራት ብቻ ኃላፊነትና ሥራ ነው ማለት አይደለም። ይልቁንስ እንደ አቶ ገብሩ ያለ እውነቱን የመረጠና ቁርጠኛ አቋም ያያዘ ሰው ሊያደርገው የሚገባ ጉዳይ ነው። አፋችሁ ተለጉሞ ያለው ካፈርኩ አይመልሰኝን የመረጣችሁት የድርጅቱ አመራር ነበሮችም የአቶ ገብሩን ፈለግ ተከትላችሁ ከእውነት ጋር እንድትታረቁና እውነቱን እንድትገልጡ ይጠበቅባችኋል።
በመግቢያው እንደተገለጸው የዚህ ጽሑፍ ዋነኛ ዓላማ በተቃዋሚው ጐራ ውስጥ የሚታዬውን ወዳጅና ጠላት የመለየት ብዥታን ለማጥራት ለሚደረገው ጥረት አስተዋፅዖ ለማድረግ ነው። ስለዚህ ከዚህ በላይ በጥያቄ መልክ በተነሱት ነጥቦች ዙርያ በውሱን ደረጃ በመወያዬት የትግራይ ሕዝብና የተሓህት/ወያነ ግንኙነትን ለማሳየት ይሞክራል።
• ተሓህት/ወያነ የትግራይ ሕዝብ ነፃ አውጭና ጥቅም አስከባሪ ነውን? የትግራይ ሕዝብ ከመሰረቱ ጀምሮ የተሓህት/ወያነን ዓላማ ደግፎና በእርሱ ተመርቶ ተንቀሳቅሷልን?
ታሪክ አበክሮ እንደሚመሰክረው የክልሉ መስፋትና መጥበብ ጉዳይ እንዳለ ሆኖ ትግራይ የጥንታዊት ኢትዮጵያ መንግሥትነት ማዕከል የነበረው ክልል ውስጥ የሚገኝ ክፍለ-ሀገር ነው። የክፍለ-ሀገሩ ህዝቡ ከሌሎች ወገኖቹ ጋር ሆኖ ለኢትዮጵያውነቱና ለአገሩ ሉዓላዊነት የከፈለው ዋጋም ታሪክ የመዘገበው ነው። የትግራይ ሕዝብ በአለፈው ታሪኩ የኢትዮጵያዊነት ማዕከል እንደሆነ የሚያምን፣ ከጥንት ጀምሮ ለአገሪቱ የግዛት አንድነትና ሉዓላዊነት መከበር የላቀ ዋጋ እየከፈለ የኖረና ምን ጊዜ ቢሆን ኢትዮጵያዊነቱን ጥያቄ ውስጥ አስገብቶ የማያውቅ ሕዝብ ነው። ከዚህ በላይ ደግሞ የትግራይ ሕዝብ ኢትዮጵያ ሲል እስከ የኢሠፓ/ኢህዴሪ ውድቀት ድረስ የነበረችዋን ኢትዮጵያን ነው፤ ከአክሱም ዘመን ጀምሮ የግዛት ክልልዋ አንዳንዴ እየሰፋና ሌላ ጊዜ ደግሞ ሰብሰብ እያለ የዘለቀችውን ኢትዮጵያን ነው (የአሁኑ የመን ደቡባዊ አርቢያን እስከማጠቃለል የደረሰበት ወቅት ልብ ይለዋል)፤ እስከ ጣልያን ወረራ ጊዜና በኋላም በተሓህት/ወያነ አለቃ በአቶ መለስ ዜናዊ ፊርማ እስከተገነጠለ ድረስ ፈፅሞ ከእጇ ወጥቶ የማያቀውን የኤርትራ አብላአጫ ክፍልና የቀይ ባህር በሮችዋን የምታጠቅልለው ኢትዮጵያን ነው። አሁን በጐሳ-በቀሉ ፋሺስታዊ ቡድን እየተሸራረፈች ያለችውን ማለቱ ሆኖ አያውቅም።
ተሓህት/ወያነ በተቃራኒው ከመነሻው ጀምሮ የኢትዮጵያን ታሪክ የካደና የአማራው ገዢ መደብ ምሁራን ተረት-ትረት ብሎ የደመደመ ነው። የዘመናት ታሪኳንና የግዛት አንድነትዋን የመቶ ዓመት ታሪክና ክስተት አድርጐ የፈረጀ ነው። የግዛት ሉዓላዊነትዋን ተፃርሮ ከዋነኛ ታሪካዊ ክፍሎችዋ ውስጥ አንዱ የሆነውን የኤርትራን ክልል ለማስገንጠል ከማንኛውም ኤርትራዊ ነኝ ባይ ተገንጣይ ኃይል በላይ የጣረና የተገበረ ነው። በዓለም ታሪክ ታይቶና ተሰምቶ በማያውቅ የራስን አገር የመጥላት ስሜትና የመጉዳት ተግባር ተሰማርቶ አገሪቱን የባህር በሮችዋን ያሳጣ ከሀዲ ቡድን ነው። ይህ የተሓህት/ወያነ ተግባር የብዙዎች የትግራይ-ትግርኚ ተወላጅ የሆኑ እንደነ አፄ ዮሓንስ፣ ራስ አሉላ አባ-ነጋ፣ ዘርዓይ ደረስ፣ ራስ መንገሻ ዮሓንስ፤ በኋላም እነ ደጃዝማች በየነ ባራኺ፣ ቢትወደድ አስፋሓ ወልደ-ሚካኤል፣ መልአከ-ሠላም ዲሜጥሮስ ገብረ-ማርያም፣ ብ/ጄነራል ተድላ ዕቁቢት፣ ሼኽ ሱሌማን ኤልዲን፣ ወዘተ ወዘተ … የመሳሰሉት ጀግኖች ኢትዮጵያዊያን መስዋእትነትና ገድል ያረከሰ፣ ታሪካቸውንም የፋቀ የክህደት ተግባር ነው። ይህ ድርጅት የካደው፣ ያጐደፈውና የቀለበሰው የቀደምቶቹ ኢትዮጵያዊያን የክልሉ ተወላጆች የተጋድሎ ታሪክና ሥራ ብቻ አይደለም። እርሱ ዓላማዬ ነው ብሎ እንደሚወሸክተው ሳይሆን በእውነተኛ መንፈስ የመላ ሕዝቧ ዴሞክራሲያዊ መብት የተከበርባት፣ ፍትህና ርትዕ የሰፈኑባትና አንድነትዋ የተከበረች ኢትዮጵያን ዕውን ለማድረግ ብለው የታገሉ፤ እንደርሱው ሁሉ ወታደራዊውን አገዛዝ ሲፋለሙ የነበሩትንም የክልሉ ተወላጆችን ያካተቱ ድርጅቶችንም በስውር ለደርግ ያጋለጠ፣ የወጋና ቀን ጐድሎባቸው በእጁ የወደቁትንም ሕይወት በግፍ የቀጠፈ ነው። በኢሕኣፓና በኢድኅ ላይ የፈጸመው አረመኔአዊ የወንጀል ተግባር ለአብነት መጥቀስ ይቻላል።
ስለዚህ የትግራይ ሕዝብ እምነትና የተሓህት/ወያነ እምነት በፍጹም የማይታረቁ መሰረታዊ ልዩነት ያላቸው እምነቶች ናቸው። የትግራይ ሕዝብ ቀርቶ በመጀመሪያዎቹ ዓመታት የድርጅቱ አባላት የነበሩት በኢትዮጵያዊነታቸው ጥርጥር ያልነበራቸው ቁጥራቸው የማይናቅ አባላቱም ቢሆኑ የድርጅቱን ፀረ-ኢትዮጵያ አቋምን አክርረው ታቃውመዋል። እነዚህ በአብዛኛው map1የምዕራብ ትግራይ ተወላጅ ያልሆኑ የድርጅቱ አባላት ዓላማቸው የብሔር ዕኩልነትን ማረጋገጥ እንጂ አገራቸውን መገነጣጠል አልነበረም። ስለዚህም የኤርትራ ጥያቄ የቅኝ ግዛት ጥያቄ ነው የሚለውና ትግራይን ገንጥሎ የትግራይ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ማቋቋም የሚለውን በነ አቶ ስብሓት ነጋ፣ አቶ መለስ ዜናዊ ፣ አቶ አባይ ፀሓዬ፣ አቶ ስዩም መስፍንና መስሎቻቸው ሲቀነቀን የነበረውን ዓላማ አውግዘው ታግለዋል። ሕዝቡና ኢትዮጵያዊ አቋም የነበራቸው በርካታ ከመላው ትግራይ የሚወለዱ የድርጅቱ አባላት የነበሩት እነ አቶ ስብሓት፣ አቶ አባይና አቶ መለስ በነደፉላቸው የትልቅ ትግራይ ህልምም አልተደለሉም (ካርታ ቁ. 1)። እንደነ አቶ ግደይ ዘርአ-ጽዮን የመሰሉቱ ኤርትራዊ የትውልድ ሀረግ ያላቸውም ይህንን ትግራይንና ኤርትራን የመገንጠል ዓላማ ተቃውመዋል።
ተሓህት/ወያነ ከውስጥና ከውጭ፤ ከሰፊው የትግራይ ሕዝብና ከአባሎች በደረሰበት ተቃውሞ ትግራይን ገንጥሎ ሪፑብሊክ የመመስረት አቋሙን አለዝቦ ቀጥሏል። ከጡት አባቱ ከኤርትራው ገንጣይ ቡድን ሻዕቢያ በደረሰበት ጫና ሳቢያ እንደሆነ በሚታመን ምክንያትም የመጀመሪያ ካርታውን ለውጦ፤ ከመርሳ ፋጡማ እስከ ጁቡቲ ጠረፍ ያለውን የአፋር ክልል የሆነውን የኤርትራ ከፍለ-ሀገር አውራጃ (በሻዕቢያ ደቡባዊ ቀይ ባህር የተሰኘው ክፍል) አስቀርቶ አዲስ ካርታ ነድፎ ሥልጣን እስከያዘበት ወቅት ድረስ ዘልቋል (ካርታ ቁ. 2)። የሆነ ሆኖ ግን ሁሉም ይህንንን ፀረ-ኢትዮጵያ አንድነት ዓላማን የተቃወሙ የድርጅቱ አባላት በተለያዩ ሰበቦችና መንገዶች ለነ ስብሓት-መለስ እርድ ተዳርገዋል።
map 2
ሌሎች የድርጅቱ አባል ያልሆኑ የትግራይ ተወላጆችም ከዚህ የድርጅቱ ፀረ-ኢትዮጵያ ፋሺስታዊ ጥቃት አላመለጡም። ድርጅቱ የመንግሥት ሥልጣንን ከተቆጣጠረ በኋላ እንኳን ይህንን ፋሺስታዊ የውንብድና ተግባሩን አላቋረጠም። ለዚህም ባዶ ስድስት የተባለ እስር-ቤቱን ከመሃል ትግራይ ከወርዒ አካባቢ (?) ወደ መቀሌ ሲያዛውር የረሸናቸው ከአምስት መቶ በላይ በአብዛኛው የክፍለ-ሀገሩ ተወላጆች የሆኑ ኢትዮጵያዊያንንን እንደ አብነት መጥቀስ ይቻላል። ይህ ውሳኔ በአቶ መለስ ዜናዊና በአቶ ስብሓት ተፅዕኖ የተፈፀመ ሲሆን የአብዛኛዎቹን የድርጅቱ አመራር አባላት ይሁንታ ያገኘ ነው። ይህ ጭፍጨፋ ከተካሄደባቸው ወገኖቻችን ጋር ታስረው የነብሩ አንዳንድ ወገኖች ዛሬም በሕይወት አሉ። እነዚህ በዚህ ሁኔታ በግፍ የተገደሉ ሰዎች በየአውደ-ውጊያውና ሌሎች ተያያዥ ሁኔታዎች በዚህ ፋሺስት ድርጅት እጅ የወደቁት ሰዎች ፍርድ-ቤት አቅርቦ ከፍተኛ ቅጣት ለማስወሰን በቂ ምክንያት ያልተገኘባቸው የድርጅቱ ጠንካራ የፖለቲካ ተቃዋሚዎችና ነበር አባላት ይገኙባቸዋል። ድርጊቱ የተፈፀመበት ወቅት ድርጅቱ ተሓህት/ወያነ አገሪቱን ከመግዛት የሚያግደውና የሚያሰጋው ነገር እንደሌለ ግልጽ የሆነበት ወቅት ነበር። ድርጊቱ የጥቂት የድርጅቱ መሪዎች የቂም በቀል ጥማት ከማርካት በቀር ሌላ አመክንዮ ሊሰጠው የሚችል አይደለም።
የትግራይ ሕዝብ የተሓህትን/ወያነ አረመኔአዊ ተግባር ገና ከማለዳው ጀምሮ ያውቀዋል፤ የድርጅቱን ፀረ-ኢትዮጵያ መሰሪ ዓላማ በመቃወሙ ሳቢያ የዚህ ፋሺስታዊ ስብስብ ጥቃት ማሟሻ የሆነው እሱ ነበርና። የትግራይ ሕዝብ ተቃውሞ ወደ ትጥቅ ትግል አድጎም በተለያዩ የአካባቢ ሕዝባዊ ሠራዊቶችና ፀረ-ጉሬላ ስብስቦች ታቅፎም ይህንን የባዕድ ተልዕኰ ፈጻሚና አስፈጻሚ ፀረ-አንድነት ጐሳ-በቀል ድርጅትን ወግቷል፤ አሳድዷል። ለአብነት ያህል በእንደርታ የዘንዶ፣ በራያና አዘቦ አዞ ”ሀ”፣ በተምቤን ተኩላ፣ በኽልተ-አውላዕሎ ሽላ [?]፣ በሚል ስያሜ ይጠሩ የነበሩትን ከሁሉም የብረተሰብ ክፍል የተውጣጡትን ፀረ-ሸማቂ ህዝባዊ ኃይሎች መጥቀስ ይቻላል። ይህንን እውነታ በተሳሳተና አሉታዊ ወይም አጥቋሪ አቀራረብ ቢሆንም የተለያዩ ፀሓፊዎችም ነካክተዉታል (ለምሳሌ፥ Aregawi, 2009; Gebru Tareke, 2009)። ከእነዚህ ኃይሎች ሌላ በሁሉም ከገበሬው ክፍል ተውጣጥተው የታጠቁ ህዝባዊ ሠራዊት በመባል የሚታወቁ ኃይሎች ከሚሊሻውና ከመደበኛው የአገሪቱ ሠራዊት ጐን በቋሚነት ተሰልፈው የሚያኰራ ተግባር ፈጽመዋል። በተለይ ደግሞ እስከ 1979/80 ድረስ ተሓህት/ወያነ የረባ ፖለቲካዊና ወታደራዊ ተፅእኖ (influence) ባላሳደርባቸው በእንደርታ፣ በራያና አዘቦ፣ በኽልተ አውላዕሎ፣ በዓጋመና በተምቤን ደጋው ክፍል አውራጃዎች የነበሩ ህዝባዊ ሠራዊቶች ይፈጽሙት የነበረው አስተዋፅዖ እጅግ የጐላና የገዘፈ ነበር። በወረዳ ደረጃ ተፈናቃይ የነበሩት የገርዓልታ ወረዳ፣ የዋዕረብና ሰሓርቲ አካባቢ ወረዳዎች፤ በአብዛኛው ጊዜ በመንግስት ቁጥጥር ሥር የነበሩ የህንጣሎ፣ የድድባና-ደርጋዓጀን፣ የዋጅራት፣ የእንዳ-መኾኒ፣ የሓውዜን፣ የአጽቢ፣ የስንቃጣ፣ የእንትጮ፣ የሰለኽለኻ [?] እና ሌሎች የዘነጋኋቸው ወረዳዎች ሕዝባዊ ሠራዊቶች ያደረጉት ገድልና እንዴት ተሓህት/ወያነን ያንቆራጥጡ እንደነበር በአካባቢው የነበሩ የቀድሞው የኢትዮጵያ ሠራዊት አባላት የሚመሰክሩለትና ሃቅ ነው። ይህ የአገሪቱ ታሪክ ከቀበሌ ጀምሮ እንዲጠና በተደረገው ሙከራ መሠረት የትግራይ ታሪክ ሲጠና ተካትቶ ተጠንቷል። የጥናቱ ቅጅ ያላችሁ ለብርሃን ብታበቁት የሚስመሰግን ተግባር ነው።
እስከ 1970ዎቹ ሁለተኛው አጋማሽ ድረስ ተሓህት/ወያነ በአብዛኛው ከምዕራባዊው የትግራይ ክልልና ከተምቤን ቆላማ አካባቢዎች ያለፈ የጐላ ተቀባይነትም ሆነ ተፅዕኖ ሳይኖረው ቆይቷል። እንዲህ ሊሆን የቻለው በዋናነት ድርጅቱ ይዞ በተነሳው ትግራይን የመገንጠል ዓላማና ኤርትራ ቅኝ ግዛት እንጂ የኢትዮጵያ አካል አይደለችም የሚለው አቋሙ ምክንያት ነበር። ይህ የድርጅቱ የኢትዮጵያ አንድነትን የሚፃረር አቋም በሁሉም የትግራይ ክፍሎች ተቀባይነት ያልነበረው ቢሆንም በበለጠ ደግሞ በራያ፣ በዓጋመ፣ በእንደርታ፣ በኽልተ-ኣውላዕሎና በተምቤን አካባቢዎች ከፍተኛ ተቃውሞ ፈጥሮበታል።
አቶ ገብሩ በመጽሓፋቸው በትግራይ ውስጥ የነበረውን የተሓህት/ወያነ ተቃዋሚ ”ደርግ በሹመትና በጥቅም አባብሎ ያገኘውን የተወሰነ ድጋፍ” በማለት ገልጸዉታል (ገብሩ፣ 2006፣ ገፅ 161)። እውነቱ ግን በከተሞችና አነስ ባለ ደረጃም ቢሆን በገጠርም በተካሄደው የፖለቲካ ሥራ የተሓህት ፀረ-ኢትዮጵያዊነት አጀንዳና እውነተኛ ማንነት በመጋለጡ ምክንያት የተፈጠረ ነው። በወቅቱ ተሓህትን ይቃወም የነበረው ወገን ድርጅቱን የተቃወመበት ዋነኛ ምክንያት ይህ እንደነበረ አንድ ተሓህት ሊመለምለው ሞክሮ የነበረ ሰው የሰጠው መልስ ብለው እራሳቸው አቶ ገብሩ በጠቀሱት ውስጥም ተመልክቷል (ገብሩ፣ 2006፣ ገፅ 158)። የወቅቱን የድርጅቱ ዓቋም የተቃወሙት በሜዳ የነበሩ የድርጅቱ አባላትም ጭምር ነበሩ። ለዚህም ነበር በወቅቱ በርካታ አባሎቹ ድርጅቱን እየኰነኑ ጥለዉት የወጡት፣ ከመንግሥት ጐን የተሰለፉት፣ ወደ ውጭ የኰበለሉት፤ መጥፎ ዕድል ገጥሟቸው ድርጅቱ ከረሸናቸው በቀር። አቶ ገብሩ የደርግን እና የኢሠፓአኰ/ኢሠፓ መንግሥትና ባለሥልጣኖቹ እንዲሁም በሥርዓቱ ያገለገሉ ሰዎችን፣ በወቅቱ የነበረው የኃይል አሰላለፍን፣ የኢሠፓ ሥርዓት ሊፈርስ ስለቻለበት ምክንያት አስመልክቶ ያላቸው አመለካከት ስሜታዊነት ያጠላበት ሆኖ አግኝቸዋለሁ። ይህ ጉዳይ ራሱ የቻለ የመወያያ ርዕስና የታሪክ ኩነት ስለሆነና የዚህ ጽሑፍ ዓላማም የአቶ ገብሩን መጽሓፍ መገምገም ወይም መተቸት ባለመሆኑ በሌላ ጊዜ እመለስበታለሁ።
የመጀመሪያው ፀረ-ዐፄ ኃይለ-ሥላሴ መንግሥት አቋም የነበረው የ1934 ዓ.ም. የወያነ አመጽ የተቀሰቀሰው በእንደርታ አውራጃ ውስጥ ድድባና-ደርጋ ዓጀንና ዋጀራት ወረዳዎች ውስጥ ሆኖ የመላው እንደርታ፣ የራያና የከፊል ኽልተ-ኣውላዕሎ ገበሬዎች ያካሄዱት አመፅ ነበር። እያደር የተምቤን ገበሬዎችም በከፊል ተቀላቅለዉታል። የዚህ አመፅ ዓላማ በኢትዮጵያዊነት ማዕቀፍ ውስጥ በራሱ ደንብና ራሱ በመረጣቸው መተዳደርና የፊውዳላዊው ሥርዓት ገዢ መደብ አባላትንና ሹሞችን ማስወገድ ነበር። የአመፁ ዋነኛ መነስኤ ከጣሊያን ሙሉ ሽንፈት በኋላ በሕዝቡ ላይ የተጣለው ፈጽሞ ከአቅሙ በላይ የሆነና ሊሸከመው የማይችል የግብር ክፍያ ነበር። ሕዝቡ በሠላማዊ መንገድ ቅሬታውን ቢገልጽም ሰሚ በማጣቱና ለአስገዳጅ የመንግሥት እርምጃ በመዳረጉ መፍትሄው ኢ-ፍትሃዊ አስተዳደሩን በትጥቅ መክቶ ራሱን በራሱ ማስተዳደር አድርጐ ወሰደ። ከጅምሩ ኢኰኖሚያዊ ይዘት የነበረው እንቅስቃሴ መልኩን ለውጦ የፖለቲካ መልክ ይዞ፤ ነገድ ሳይለይ ፀረ-መሳፍንታዊው አገዛዝ ትግል ሆኖ አረፈው። የፊውዳሉ መንግሥት ለዚህ የሕዝብ አመጽ ፖለቲካዊና ሠላማዊ መፍትሄ በመስጠት ፈንታ በእንግሊዝ ወታደራዊ ኃይል ጭምር በመታገዝ በጦር ኃይል ደፈጠጠው። የ1933ቱ የከፊል ትግራይ ወያነ (አመጽ) በኋላ ተሓህት/ወያነ ይዞት ከተነሳው ዓላማ ጋር ፍጹም ተጻራሪ ነው። መሠረታዊ ልዩነታቸውን እንደሚከተለው ማነጻጸር ይቻላል፥
1933 .የትግራይ ገበሬዎችወያነ        የተጋድሎ ሓርነት ህዝቢ ትግራይ (ተሓህትበኋላ   ህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ህወሓትአብዮት
በኢትዮጵያዊነት ያምናል።       በኢትዮጵያዊነት አያምንም።
ፍትህን ለማግኘት አልሞ የተነሳ፣ በኢትዮጵያዊነት ማእቀፍ ውስጥ ራሱ በመረጣቸው ሰዎች ለመተዳደር ያቀደ ነበር።
       ትግራይን ከኢትዮጵያ በመገንጠል ራስዋን የቻለች መንግሥት ለማድረግ አልሞ የተነሳ ነው። ከዚህም በላይ ኤርትራንም በማስገንጠል (በመገንጠል ማለቱ የተሻለ ይገልጸዋል) ኢትዮጵያን የባህር በሮቿን ለማሳጣት ቆርጦ የተነሳና የተገበረም ነው።
አርማው የኢትዮጵያ ሰንደቅ ዓላማ ነበር።          የራሱ የሆነ ከትግራይ ሕዝብ ጋር ምንም ግኑኝነት የሌለው አርማ አለው። የኢትዮጵያን ሰንደቅ ዓላማ ተራ ጨርቅ ነው ብሎ ያንቋሸሸና ጥላቻውን የገለጠ ድርጅት ነው።
ከ1970ዎቹ የመጀመሪያው አጋማሽ ጀምሮ እነዚህ ሁለት በትግራይ ውስጥ የተካሄዱ አመጾች ቐዳማይ ወያነ እና ኻልኣይ ወያነ (የመጀመሪያው ወያነ እና ሁለተኛው ወያነ) የሚል መጠሪያ ተሰጥቷቸው ይገኛል፤ ወይም ተሰኝተዋል። የዚህ ስያሜ ምንጩ ተሓህት/ወያነ ቢሆንም ይሁነኝ ተብሎ በፖለቲካ ዓላማና በየዋኅ-ልምድ ተዘውትሮ በመነገሩ ሥር የሰደደ ስያሜ ለመሆን በቅቷል። ዳሩ ግን የ1930ዎቹ የትግራይ ገበሬዎች አመጽና የተሓህት አመጽ ታሪካዊም ሆነ ፖለቲካዊ ይዘቱ ሲመዘን ባለው መሠረታዊ ተቃርኖ ምክንያት ተሓህትን “ወያነ” ብሎ መጥራት ስህተት ነው። ወያነ ማለት የግዕዝ ውርስ ቃል እርባታ ሆኖ አመጽ ወይም አብዮት ማለት ነው። እንዲያ በመሆኑም ማንም አብዮታዊ ነኝ ያለ ሁሉ ሊጠራበት ካማረው የሚከለክለው ነገር አይኖርም። ተሓህት ግን ወያነ ሲል የመጀመሪያ ወያነ እና ሁለተኛው ወያነ (ቐዳምይ ወያነ፣ ኻልኣይ ወያነ) በሚል መንፈስና አጠራር ሲሆን የመጀመሪያው ወያነ ትግል ወራሽ ለማለት ነው፤ ይህንን አስተጋብታ Jenny Hamond “Fair From The Ashes” እንዳለችው ዓይነት (Hammond, 1999)። ስለዚህ ይህንን ጐሳ-በቀል ፋሺስታዊ ስብስብን ወያነ ብሎ መጥራት የሌለበትን ተፈጥሮ ሰጥቶ ለፍትህና ርትዕ የቆመ ኢትዮጵያዊ ኃይል ማድረግ ነው የሚሆነው።
በመሰረቱ ድርጅቱ ሲነሳ ራሱን ወያነ ብሎ አልሰየመም። የተደላደለ የድርጅት መልክ ይዞ ሲወጣ ለራሱ የሰጠው የትግርኛ መጠሪያ ተጋድሎ ሓርነት ህዝቢ ትግራይ (ተ.ሓ.ህ.ት.) የሚል ነው። በእንግሊዝኛው ስያሜው EPLF (Eritrean People’s Liberation Front) የሚለውን መጠርያ ገልብጦና ’E’ን በ’T’ ተክቶ TPLF (Tigray People’s Liberation Front፣ የትግራይ ሕዝብ ነፃ አውጪ ድርጅት/ግንባር) የሚል ነበር። ”የትግራይ” የሚለው ስያሜ ደግሞ ቀደም ብሎ በነበረው አመለካካከትና ልምድ ትግራይ ማለት ከወርዒ ወንዝ ማለትም ምዕራባዊው የትግራይ ክፍል አድርጐ ይመለከት በነበረው የመሃል፣ ደቡብና ሰሜናዊ የትግራይ ክፍል ሕዝብ፤ በዋናነት ደግሞ ተሓህት/ወያነ አቶኩሮበት በነበረው የገጠሩ የኅብረተሰብ ክፍል ዘንድ በየእኛነት እንዲታይ አላስቻለውም። ከዚህ በላይ ደግሞ ድርጅቱ በአብላጫው በአክሱም፣ ሽሬ እና ዓድዋ ተወላጆች የተሞላና የሚመራ ከመሆኑም በላይ ይበልጥ ያተኰረውም በነዚህ ሦስት አውራጃዎች ስለነበር ከሌላው የክፍለ-ሀገሩ ክልል ጋር እዚህ ግባ የሚባል ትስስር አልነበረውም። አሁንም በግልጽ እንደሚታየው የአክሱም፣ ሽሬና ዓድዋ (አሽዓ) እና የኤርትራ ተወላጆች (ግማሽ ወይም ሙሉ) የበላይነት እንዳለ ቀጥሎ እና ይበልጥ ጠቦ እስከዛሬ ዘልቋል። ሌላው አድርባይ አጃቢ ነው። አሽዓ ማለት በድርጅቱ የገነነ አውራጃዊ ክፍፍል ተከስቶ በነበረበት ድርጅቱ ሕንፍሽፍሽ እያለ በሚጠራው ወቅት የሦስቱ አውራጃዎች ተወላጆች መለያ ተደርጐ ተወስዶ የነበረ ነው።
በመጀመሪያ የድርጅቱ ዓመታት አብላጫና ቁልፍ መሪዎቹ የነበሩት የአሽዓ ተወላጆችና ኤርትራዊያን የድርጅቱን ኢ-ዴሞክራሲያዊ ባህርይ፣ የኤርትራ ግንጠላ አጀንዳ አራማጅነት እና ጠባብ-ብሄረኛነቱን የኰነኑትን የሌላ አውራጃዎች ተወላጆችንንና ተመሳሳይ አመለካከት ያንጸባረቁትን ጥቂት የአሽዓ ተወላጆችንም በግፍ የፈጁ ለመሆናቸው የአደባባይ ምስጢርና ድርጅቱም ስህተቱን አምኖ ይቅርታ ያልጠየቀበት አስቀያሚ ጠባሳው ነው። ከዚህም በላይ የድርጁትን አቋም ጥያቄ ውስጥ ያስገቡና የተቃወሙ፤ እንዲደግፉት ተጠይቀው ፈቃደኛ ያልሆኑ፣ የሌላ ድርጅት አባል ወይም ደጋፊ ናቸው ብሎ የፈረጃቸው፣ በአገሬው ባህል መሠረት በአዛውንትነታቸውና በጐልማሳነታቸው መክረው የሚያሰሙ የመሰላቸው፣ … ወዘተ የክፍለ-ሀገሩ ተወላጆችንም ያለ ርህራሄ አጥፍቷል።
ድርጅቱ ተጋድሎ ሓርነት ህዝቢ ትግራይ (ተ.ሓ.ህ.ት.) የሚለውን መጠሪያውን አውልቆ ህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ህ.ወ.ሓ.ት.) የሚል ጭምብል ያጠለቀው ከተመሰረተ ከበርካታ ዓመታት በኋላ በ1970ዎቹ ነበር። ይህ ያደረገበት መሠረታዊ ምክንያትም ከ1933ቱ ወያነ ማለትም የመሃልና የደቡብ ትግራይ ሕዝብ ፍትሃዊ ትግል ጋር ትስስር ለመፍጠርና እራሱን የዚሁ ትግል ወራሽ አድርጐ ለማቅረብ ነው (ካርታ ቁ. 3)። ተሓህት ሥሙን ቀይሮ ወያነ ሲሰኝ መሰረታዊ ፀረ-እትዮጵያ አንድነት እምነቱን ግን ፈፅሞ አልቀየረም። ይህንንም ኤርትራን በማስገንጠል (በመገንጠል!) በወሰደው አቋምና ወደፊት ኢትዮጵያ ተበጣጥሳ በጥቃቅን የጐሳ መንግሥታት ትትካ ዘንድ የክልል ሰንደቅ ዓላማ፣ የመንግሥትነት ቅርጽ የያዙ አካባቢያዊ ጐሳና ነገድ መሰረት ያደረጉ አስተዳደራዊ መዋቅሮች፣ ወዘተ በመፍጠርና በማደራጀት በሚፈጽመው ደባ እያረጋገጠ ነው። ኤርትራ ራስዋን የቻለች አገር ነበረች ለሚለው ክርክር ከሚቀርቡት መሟገቻ ውስጥ የራስዋ ፓርላማ ነበራት፣ የራስዋ ሰንደቅ ዓላማ ነበራት የሚለው በዋናነት መቅረቡ ትምህርት ሰጭ ሊሆን ይገባው ነበር።
አንዳንድ የዋኅን አቶ መለስ ዜናዊ ማለም ትችላላችሁ ብለው በፈቀዱላቸው መሠረት ”ተሓህት/ወያነ አሁን አቋሙን ለውጦ ለኢትዮጵያ ትንሳኤ እየሰራ ነው፣ ዓባይን እየገደበ ነው፣ ምንትስ፣ ምንትስ” እያሉ ህልማቸውን ቢቀጩም ”ድመት መንኩሳ፤ ያባትዋን አትረሳ” ነውና ቢሂሉ፤ ተሓህት/ወያነ ግን ሥራውን አይተውም። እነዚህ ወገኖች ነገ ዓባይ ተገድቦ ሲያበቃ ”ዓባይ ለሶማሊ፣ ለአፋር፣ ለአማራ፣ ለጉራጌ፣ … ወዘተ ምኑ ነው” እንደማይባል ሊያረጋግጡልን የሚችሉበት አስረጅና መላምት የለም።
map 3
የተሓህት/ወያነ ከምዕራባዊው የትግራይ ክልልና ከተምቤን ቆላማ አካባቢዎች ያለፈ የጐላ ተቀባይነትም ሆነ ተፅዕኖ ሳይኖረው እስከ 1970ቹ አጋማሽ ድረስ ለመዝለቁ ሌላም ተጨማሪ ምክንያት ነበረው። የኢህኣፓ (EPRP) ሠፈሩን በዓጋመ መቆርቆርና በዓጋመና በተምቤን አካባቢ ፈጥሮት የነበረው ተቀባይነትና በልዑል ራስ መንገሻ ሥዩም ይመራ የነበረው የኢትዮጵያ ዴሞክራሲያዊ ኅብረትም (EDU) በመካከለኛው ሰሜናውና ደቡባዊ ትግራይ የነበረውም ፖለቲካዊ ተጽዕኖም ለተሓህት/ወያነ በካባቢው እምብዛም ተቀባይነት ያለማግኘት ከፍተኛ አስተዋፅዖ ነበረው።
በአጠቃላይ እላይ በተዘረዘሩት የተለያዩ ምክንያቶች ሳቢያ ተሓህት/ወያነ በአብዛኛው ከምዕራባዊው የትግራይ ክልልና ከተምቤን ቆላማ አካባቢዎች ያለፈ እምብዛም የጐላ ተቀባይነትም ሆነ ተፅዕኖ ሳይኖረው እንዲቆይ ተገዷል። ለዚህም ዋነኛ ምክንያቱ ከዚህ በላይ ለመግለጽ እንደተሞከረው የትግራይ ሕዝብ የማንነት እምነትና የተሓህት/ወያነ እምነት ፈጽሞ የተለያዩ ወይም ተቃራኒ ነበሩ። በዚህ ሳቢያ የትግራይ ሕዝብ የወያነን ዓላማ ተቃውሞ ሲታገል ቆይቷል። የወያነ ዓላማ ተሳክቶ ኤርትራ እንዳትገነጠል ከሌላው የኢትዮጵያ ክፍለ-ሃገራት ሕዝብ የበለጠ፤ ቢያንስ ደግሞ እኩል የሆነ ዋጋ ሲከፍል ኖሯል። በወጣት ዘማቾች፣ በፀረ-ሸማቂ ኃይሎች፣ በሕዝባዊ ሠራዊቶች፣ ወዘተ … እየተደራጀ የሕይወት፣ የንዋይና የጉልበት መስዋዕትነት ከፍሏል። ትግራይ ከሌሎች የአገራችን ክፍል ጋር ሲነጻጸር በኢኰኖሚ ደከም ብሎ ይታይ የነበረ ክፍለ-ሀገር ቢሆንም በሶማሊያ ወረራ ወቅት ክፍለ-ሀገሮች ያደርጉት በነበረው የእናት አገር ጥሪ የኢኰኖሚ ድጋፍ መሠረት ወደ ስምንት ሚልዮን ብር በማዋጣት ከአገሪቱ ክፍለ-ሀገሮች የሁለተኛነት ሥፍራ ይዞ እንደነበር በወቅቱ በይፋ የተገለጠ ጉዳይ ነው (የበለጠው አዲስ አበባ ብቻ ይመስለኛል)። ይህንን ሁሉ የዚህ ጽሑፍ አቅራቢ በሥራ ምክንያት በተዘዋወረባቸው የትግራይ ክፍለ-ሀገር አውራጃዎችና በኤርትራ፤ ለአብነት ያህል፤ የታዘበው እውነታ ነው።
የትግራይ ሕዝብ አቋም ፀረ-የተሓህት/ወያነ ዓቋም ከነበረ ደግሞ ይህ ድርጅት የዚህ አገሩን አፍቃሪ፣ ለአንድነቱና ለነፃነቱ ሟች ጀግና ሕዝብ ወኪልና ጥቅም አስከባሪ ሊሆን የሚችልበት ቀመር ፈጽሞ የለም። ትግራይ እኰ ሰሜን አሜሪካ ወይም ኤሺያ ወይም ሌላ ቦታ ላይ ያለ ሌላ ራሱን የቻለ አገር አይደለም፤ የኢትዮጵያ አንድ ክፍል ነው። ታዲያ በምን መለኪያ ነው ተሓህት የኢትዮጵያን ብሔራዊ ጥቅም እየጐዳ፣ የአብዛኛው ሕዝቧን መብት እየረገጠና እያፈነ የትግራይ ሕዝብ ጥቅም አስከባሪ ሊሆን የሚችለው? እንዴት ሆኖ ነው አገሩ ያለ ባሕር በር እንዲቀር መደረጉ፣ በኢትዮጵያዊነቱ እንደልቡ ተዘዋውሮ ሠርቶ እንዳይኖር በዘር ተሸንሽኖ መገደቡ፣ በስሙ በሚቀጥፍ ዋልጌ መንደርተኛ ቡድንና የሥርዓቱ ተጠቃሚ በሆኑ ነብሰ-በላ ባለሃብቶች ዳፋ ጥርስ መግባቱ፣ … ወዘተ ጥቅሙ መከበር የሚሆነው?
የትግራይ ሕዝብ ጥቅም የሚከበረው የመላ አገሩ ጥቅም ሲከበር ነው። አገዛዙም በአንድ ወቅት ፍትሃዊም አፋኝም የሆነ የአንድ ሳንቲም ሁለት ገጽታ ዓይነት ተፈጥሮ ሊኖረው ፈፅሞ አይችልም። በአንድ የጊዜ ቅጽበት ውስጥ ከሁለቱ አንዱ ብቻ ነው መሆን የሚችለው። በቀሪቱ የአገሪቱ ክፍል ውስጥ አፋኝና አረመኔአዊ የሆነው አገዛዝ እዚያው በዚያው ከመቅጽበት ለትግራይ ሕዝብ ሲሆን ፍትሃዊና የሕዝብ መብት አስጠባቂ ሊሆን አትችልም። አሜሪካዊው የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ማርቲን ሉተር በወቅቱ በአገራቸው የነበረው ሁኔታ አስመልክተው “… Injustice anywhere is a threat to justice everywhere.” ያሉት ይህንን ነው የሚያሳየን። በርግጥ አገዛዙ ጃስ የሚላቸው ውሾች በትግራይ ሕዝብ ሥም እያጭበረበሩ የትግራይ ሕዝብ የአገዛዙ ጭፍን ደጋፊና የሥርዓቱ ተጠቃሚ እንደሆነ አድርገው ሊያላዝኑ ይችላሉ፤ አገዛዙም እንዲያ ሊያደርግ ይችላል፤ አገዛዙ ድርጐ እየሰፈረና ፍርፋሪ እየወረወረ ያሰማራቸው ባንዳዎችም በተቃዋሚው ጐራ ውስጥ መሽገው ይህንን ሊያስተጋቡ ይችላሉ። ይህ ሁሉ ግን፤ ”አባ በበሉ፣ አማሆይ አገሱ” በሚል ስሌት ካልተሰላ በቀር፤ ውሸት ነው። ወይም የትግራይ ሕዝብ ማለት ላይ መግባባት የለም ማለት ነው፤ ብዥታ አለ ማለት ነው። የተሓህት/ወያነዎች ጀግኖች አባቶቻችን ሲሉ እንደነ ባንዳው የአቶ መለስ ቀድመ-አያት ባሻይ አስረስ፣ እንደነ ደጃዝማች ኃይለ-ሥላሴ ጉግሳ፣ … ወዘተ ማለታቸው፤ የነሱ ተቃዋሚ የሆኑት ደግሞ እንደነ ዐፄ ዮሐንስ፣ አሉላ አባ-ነጋ፣ ወዘተ … ማለታቸው ሆኖ እንድሚለያዩት ማለት ነው።
ሌላኛው አስገራሚ ነገር ተሓህት/ወያነ የትግራይ ሕዝብ ነፃ አውጭ ማለቱ ሳይሆን የዴሞክራሲያው ሥርዓት ምንነት ገብቶናል የሚሉ ኃይሎችና የዚህ ድርጅት ግትልትሎችም ጭምር እንዲያ ነው ብለው ማመናቸው ወይም መቀበላቸው፣ ወይንም ድርጅቱን መጥራታቸው ነው። ነፃ መውጣት ማለት ምንድን ማለት ነው እንዴ?! የትግራይ ሕዝብ ነፃ ሆኖ የኖረ ብቻ ሳይሆን የሌሎችንም ነፃነት ለማስከበር ሲታገል የኖረ ሕዝብ ነው። ታዲያ ከማን ነው ነፃ የሚወጣው?! ያውም ነፃነት በማይሰማቸው የባንዳ ልጆችና የራሳቸውን ክፍለ-ሀገር አስገንጥለው ተጣብቀዉን በቀሩ መዥገሮች! ይህ በጣም አሳዛኝ አላዋቂነትና ብሽቅ ቀልድ ነው። በእርግጥ የትግራይ ሕዝብ እንደ ማንኛውም የአገሪቱ ሕዝብ በአገሪቱ የመንግሥት ሥልጣን በጨበጡ ገዥ መደቦችና አገዛዞች ሲጨቆንና ሲመዘበር የኖረ ሕዝብ ነው። ስለዚህ ከእንደዚህ ዓይነት ሥርዓት ተላቆ ኢኰኖሚያዊና ማኅበራዊ መብቱ በተከበረበት ፍትሃዊና ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት መተዳደር አለበት። ለዚህም መታገል አለበት። ይህ ደግሞ በመደባዊ ትግል እንጂ በጐሳ ፖለቲካ ሳቢያ ገዥና ተገዢን፣ በይና ተበይን በአንድነት አጉሮ በሚያንተከትክ፤ አረመኔያዊ አገዛዝን ለማስቀረት ሳይሆን በራስ ጐሳ ጅቦች ለመበላት በሚዳርግ የጐሳዎች ወይም ብሄረ-ሰቦች መገንጠል እዉን የሚሆን አይደለም። የኤርትራ ነባራዊ ሁኔታ ይህንን ኃቅ ነው የሚያሳየን።
የትግራይ ሕዝብ ገና ከጥዋቱ ይህንን በተገነዘቡ የክፍለ-ሀገሩ ተወላጆች እውነታው እንዲያውቅ በመደረጉ የተሓህት/ወያነን ዓላማ ደግፎና በእርሱ ተመርቶ አልተንቀሳቀስም። ዛሬም ቢሆን እንደማንኛውም ቀሪው የአገሪቱ ክፍል ሳይሆን በባሰ ሁኔታ ተቀፍድዶና ተሸብቦ እንጅ የዚህ መንደርተኛ ድርጅት ተከታይ ያለመሆኑ ሊታወቅ ይገባል። ለዚህም በምርጫ 97 የወሰደው አቋም ጉልህ አስረጅ ነው።
ከዚያ በላይ ደግሞ የዐፄው አገዛዝ ገዢ መደብን በዐፄው አገዛዝ የገዢ መደብ መሳፍንትና የማኅበረ-ኢኰኖሚያዊ ሊህቃን ልጆች መተካት እና አዲስ ነፍጠኛ ገዢ መደብ መፍጠር የትግራይን ሕዝብ ጥቅም አያስጠብቅም። ለአብነት ያህል የተምቤኑ ፊውዳል የግራዝማች አብራሃ ልጅ አቶ ስዬ አብራሃ፣ የሽሬው ፊውዳል የደጃዝማች አርኣያ ልጅ አቶ ሓየሎም አርኣያ፣ በዐፄው ዘመን የትግራይ ልማት ድርጅት ሥር-አስኪያጅና የልዑል ራስ መንገሻ ሥዩም ባለሟል የነበሩት የትግራይ ሕዝብን ደም የመጠጡት የሠራዬው (ኤርትራ) ተወላጅ የአቶ ገብረ-ክርስቶስ ገብረ-እግዚአብሄር (የመቀሌው Green Hotel ባለቤት) ልጆች እነ አቶ ብርሃነ ገብረ-ክርስቶስ፣ የመቀሌው ፊውዳል ነጋዴ የባላምባራስ ተክለ-ኃይማኖት ካሕሳይ ልጆች እነ አቶ አበበ ተክለ-ኃይማኖት፣ የዓድዋ መሬት ከበርቴ ፊታውራሪ ልጅ አቶ ስብሓት ነጋ፣ ወዘተረፈ … መጥቀስ ይቻላል። ትላንት አባቶቻቸው ጋጡት፤ ዛሬ ደግሞ ልጆቻቸው እየጋጡት ብቻ ሳይሆን እየቀለዱበትም ነው።
የትግራይ ሕዝብ ተሓህት/ወያነን ይቃወም ከነበረ እንዴት ሆኖ ታዲያ ተሓህት/ወያነ አሸነፈ?
በክፍል ሁለት ይቀጥላል።
yane.07.2006@gmail.comn