Saturday, July 4, 2015

የወያኔ ትኩረት ያልተሰጠው ጸረ ኢትዮጵያ ወንጀል


ፍኖተ ዴሞክራሲ የኢትዮጵያ አንድነት ድምጽ
Finote Democracy Voice of Ethiopian Unity
Efdpu@aol.com www.Finote.org
የፍኖተ ዴሞክራሲ የኢትዮጵያ አንድነት ድምጽ ሀተታ ሰኔ 4 ቀን 2007 .. የተላለፈ

ወያኔ ኢትዮጵያን ሊያጠፋ የመጣና እየጣረ ያለ ሀይል እንደመሆኑ መጠን ዘመቻው ፈርጀ ብዙ ሆኖ መቆየቱን ብዙ ሰዎች በሚገባ የተገነዘቡት አይመስልም ። ወያኔ ከግድያና ፍጅት፤ሕዝብን ከፋፍሎ ከማጫረስ አልፎ ሀሪቷን ምድረበዳ ለማድረግም ያልተቋረጠ ዘመቻ በማካሄድ ላይ ነው ። የአካባቢ ድህንነትና ማበላሸት የመጪውን ትውልድ ሀገር መጉዳት ማሽመደመድና ያለውንም ሕዝብ ለአደጋ ማጋለጡ የሚታወቅ ነው ።
ወያኔ የኢትዮጵያና የኢትዮጵያዊነትን ቅርስ ሊያጠፋ ሲጥር ቆይቷል ፡፤ ይህ በቅድሚያ ሀገራዊ/ብሔራዊ ቅርሶችን ማጥፋትን ቀጥሎበታል ። የሀይማኖት ተቋሞችን፤ ኢትዮጵያዊ ነን ብለው ጸንተዋል የተባሉ ሕዝቦችን፤ ቅርሶችንና ንብረቶችን በተቻለው መጠን ሊያጠቃ ሞክሯል፤አውድሟልም ። የትግራይ የባሕል ማዕከል የሚባል አቋቁሞ ሰነዶችን ቅርሶችን የትግራይ ናቸው ብሎ ወደ ትግራይ ማጓጓዙ ምስጢር አይደለም ። የሀገራችን ቅርስ ናቸው የሚባሉትን የዱር እንስሶች ሁሉ በአረብ አዳኝ ተብዬዎች ማስጨረሱ ምስጢር አይደለም ። ወያኔ ገና ጫካ በነበረበት ጊዜ ወደመተማ ሲዘልቅ ቀርቅሃና ዛፍ በሱዳን እንዲጨፈጨፍ ለንግድ አቅርቦ የደን ሀበታችንን የጎዳ መሆኑ ይታወቃል ። የጠገዴን ወዲምቢንም በገፍ ገድሎ ሲጠየቅ አማሮች ወደ ትግራይ ከአጼ ምኒሊክ ጋር ዘምተው ሰጎናችንን ሳይቀር ያጠፉ ናቸውና ሲያንሳቸው ነው ማለቱም የሚረሳ አይደለም ። ወያኔ ስልጣን እንደያዘ ለነጭ ሳር ፓርክ/ጫካ መቃጠል ዋና ተጠያቂ ነው ። ወያኔ ባላታወቀ ምክንያት ተነሳ በሚለው ቃጠሎ ከመርካቶ እስከ እቴጌ ሆተልና የደቅ እስጢፋ ገዳማትን አውድሟል ። በትግራይ ዛፍ ተከላን በሰፊው ሲያያዘው በሊሎች ቦታዎች ግን ደኖችን ጨፍጭፎ መሬቱን ምድረበዳ ሊያደርን ሞክሯል ። የኢትዮጵያ ደን መጨፍጨፉ ከኢትዮጵያ አልፎ የመካከለኛ አፍሪካን የአየር ሁኔታ ሁሉ ማዛባት መቻሉም በአዋቂዎች እየተነገረ ነው ። ይህ ዘረኛ ቡድንም ሀገርን ለማጥፋት በታሪክ ብረዛና ክለሳ መስክ እየሰራ ያለው ደግሞ ምስጢር አይደለም ። የሀገራችን ለም መሬት በባእድ ማዳበሪያ (ኖርዌይ ጉቦ ሰጥታ በምታራግፍብን) ና ባዕዳን እንዲተክሉ በተፈቀደላቸው
page1image15624 page1image15784
1
የአበባ ተክል እየተጎዳ ሲሄድ ወያኔ እስየው ነው ያለው ። ሁሉም የልማት ጥረት በቅድሚያ በትግራይ መሆን አለበት በሚልም ሊሎችን አካባቢዎች እንደጎዳ የሚታወቅ ነው ።
የአካባቢ ደህንነትን ጥበቃ ትኩረት የሚሰጠው ብሔራዊ ዘመቻ ነው ። ጫካውን፤ ዱር አራዊቱን፤ ቅርስና ተቋሙን ሁሉ በመንከባክብ ፈንታ ማጥፋቱ ተልዕኮ ከሆነ ሀገርን እያጫጩና እያዳከሙ እያበላሹ ነው ለመጪው ትውልድ የሚያሳልፉት ማለት ነው ። የሳውዲ አረቢያ ሀብታሞች በሀገራችን በወያኔ ተፈቅዶላቸው ዝሆንም አንበሳም መግደላቸው ሊደብቅ አልቻለም ። የቤተ ክርስቲያን ቅርሶች በወያኔና በሟቹ ጳጳስ ተብዬ ካድሬ ተዘርፈው ተሽጠዋል ። ካድሬው ጳጳስ ገና ለዚህ ቦታ ሳይበቁ በኢየሩሳሌም ገዳም ላይም ዝርፊያ አካሂደው ያደረሱት ጉዳት ተጋልጦ እንደነበር እናስታውሳለን ። ወያኔ በሙስሊሞች ጉዳይ ጣልቃ ገብቶና ሊያፈርሳቸው ጥሮ እነሆ እስከዛሬ ተቃውሞ መቀጠሉ የሚታይ ነው ። ቀደም ገና በ1983 ጀምሮ ትግራይ እንድትለማ ኢትዮጵያ ትድማ ሲባል የነበረው ሀቅ ሆኖ መቆየቱም ክርክርን የሚጋብዝ አይደለም ። ወያኔ ኢትዮጵያን እንደ ሀገር የማያይ በመሆኑ ጥፋቷን እንጂ ልማቷን አይመኝም ። የሚጎዳትን ነበር ሁሉ ይፈልገዋል ። ስሙና የሚያስጠሩት ባለታሪኮች ስማቸው እንዲነሳ አይፈለግም ። የአፍሪካ የእግር ኳስ ፌዴሬሽን አቶ ይደነቃቸውን ሊያከብር ሲል ያደረገውን ተቃውሞ ያስታዋሷል !
ትዮጵያን የሚያዋርድ ሁሉ ለወያኔ ደስታው ነው ።
ወያኔ ይሁነኝ ብሎ ኢትዮጵያን ምድረ በዳ ሊያደርግ ከተነሳ ጀምሮ በሁሉም መስክ በሀገራችን ላይ የደረሰውና እየደረሰ ያለው ጉዳት በቀላሉ የሚታይ አይደለም ። የነበረው ሰፊ ጫካ ዛሬ የለም ። ቅርስ የተባለው የጋምቤላ ጫካ እንኳን ለህንድ ተሰጥቶ ተመንጥሯል ። ለም መሬት ስለ ነገይቷ ኢትዮጵያ ደንታ ለሌላቸው ባዕዳን ከመሰጠቱ ባሻገር እየደረቀም መሆኑ ይታወቃል ። የወሎና ጎንደርን ለም መሬቶች ወያኔ በጉልበት ወደ ትግራይ መጠቅለሉም በዚህ የሚነሳና ወደፊትም ቢሆን ይህ ህገወጥ ድርጊት/እርምጃ ሳይውል ሳያድር የሚቀየር መሆኑን ወያኔ አለማወቁ ምንኛ እብሪት ያወረው ሀይል መሆኑን ያሳያል የሚለውም መጠቀስ ያለበት ነው ። የሀገራችን ብቻ የሆነው በባሌ የሚገኘው ቀይ ቀበሮ፤በስሜን ያለው ጭላዳ ዝንጀሮ፤ በልዩ ልዩ ቦታዎች ያለው የዝሆን፤የአንበሳ፤ የአጋዘን ወዘተ የዱር አውሬ ስብስብ ለጥቃት ተጋልጧል ። ወያኔ የሀገርን ቅርሶች እየሸጠ እንዳለው ሁሉ አውሬዎችንም ለገንዘብ ሲል ያሳድናል፤ይሸጣል ። የአካባቢ ደህንነትን ጥበቃ ለወያኔ ጉዳዩ አይደለም ። ይህም በሀገሪቷ የአየር ጠባይ ላይ እያደረሰ ያለውን ጉዳት ሁሉም ዜጋ ያውቀዋል ማለት ይቻላል ። ከትግራይ ውጪ የት ነው ሰፊ የዛፍ ተከላ የሚታየው ?
ዛፍ ተጨፍጭፎ ሕንጻ፤ ቡና ተነቅሎ ጫት፤ ጫካ ተመንጥሮ ህንጻ ነው የወያኔ ፖለቲካና እርምጃ። ለሀገር ክቶም የማይበጅና የነገን ኢትዮጵያ መድረ በዳ ሊያደርግ የተነሳ እርምጃ ማለት ነው።
ኢሕ አፓ በመጨረቫው መርህ ግብሩ የአካባቢ ደህንነትን ጥበቃ ዘመቻ ትኩረት ሰጥቶ አስፍሮታል ። አለምክንያት አይደለም ። ያለ ዕቅድና በተለይም ጎጂ በሆነ መንገድ የሚካሄድ የከተሞች መስፋፋት በሀሪቷ ኤኮኖሚ ላይ የሚያመጣው መዘዝ ቀላል አይሆንም ። በወያኔ እየተገነቡ ያሉ ሕንጻዎች ደረጃውን ባልጠበቀ ሲሚንቶ፤ አለበቂ ጥናት ወዘተ መሆኑ ሁሉም የሚያውቀው ጉዳይ ነው ። ለመሬት መንቀጥቀጥ ሰለባ ትሆናለች የተባለችው አዲስ አበባ ነገ ይህ አደጋ ቢመጣባት ሕንጻዎቹ ፈራሾች መሆናቸና ለአደጋ መከላከልም አንጻር በጥናት የተሰሩ ባለመሆናቸው ብዙ ጉዳት እንደሚያደርሱ ከወዲሁ ተነግሯል ። ሕንጻ በሕንጻ፤መዝናኛ መናፈሻ ቦታዎች አልባ የወያኔ ከተሞች የምድር ላይ ሲኦል ለመሆን በሽቅድድም ላይ ናቸው ። ጸሐዩ ገደለን፤አልቻልነውም መባሉ ምንኛ የአየር ጠባይ ለውጥ እንደመጣ የሚጠቁም ነው ። ወያኔ የኢትዮጵያና የመልካ ምድር የተፈጥሮ ይዘት እያበላሸ ነው መባሉ ተገቢ ነው ። ወያኔ ስልጣን ከመጣ በኋላ ሻዕቢያና ሱዳን የኢትዮጵያን ጫካዎች እየጨፈጨፉ ወደ ሀገራቸው ማጓጓዛችውን አልረሳንም ። ይባስ ብሎ ሰፊና ለም መሬት ለሱዳን ተሰጥቷል ። በከርሰ ምድሯ ያሉየኢትዮጵያ ንጥረ ሀብቶችም በነአላሙዲና ወያኔ በገፍ እየተበዘበዙ ሲሆን ሕዝብ ከወርቁም ከሌላውም እስካሁን ያገኘው ጥቅም የለም ። ዝርፊያው ቀጥሏል ። በሰው እጅ የተቀየሩ ዘሮች (ወይም ጄኔቲካሊ ሞዲፌድ ሲድስ) ለመሬቱም ለሰዉም ጎጂ ናቸው እየተባለ ወያኔ እነዚህንም ሆነ መሬት አጥፊ ማዳበሪያዎችን አስገብቶ በመሸጥላይ ነው ። አርሶ አደሩ ማዳበሪያ ከአገዛዙ እንዲገዛ ተገዶ በዕዳ እንደተያዘ አለ ።
ከሁሉም በላይ ድርቅ በሚል የሚገለጸውና ሚሊዮኖችን ለረሀብና ለሞት የሚዳርገው መነሻው በአብዛኛው ሰው መሆኑ የሚታወቅ ነው ። የወያኔ የጫካ ጭፍጨፋና የምድረ በዳ እርምጃ ድርቅን ያመጣል ። ለተፈጥሮ አደጋ መካላከያ አለመኖሩ ከዚሁ ይያያዝና ጉዳቱን ሰፊና አውዳሚ ያደርገዋል ። ለም መሬት እያለ ኢትዮጵያ ለድርቅና ለረሃብ የተጋለጠችው በ አገዛዞቹ የጥፋት እርምጃ መሆኑን መካድ የሚቻል አይደለም ። ድርቅ ሰው ሰራሽ ነው ሲባልም ይህን ሁሉ ያመላክታል ። አርሶ አደሩ ከመሬቱ መፈናቀሉ፤ በምርት መስክ በወያኔ ተፎካካሪነት መጎዳቱ፤ የአየር ጠባይ ወደ ድርቅ እንዲያዘነብል መደረጉ ወዘተ በበቂ ሊያመርትና ሊመቸው አልቻለም ። ከመሬቱም እየተፈናቀለ ወደ ከተማ በመግባት ለልመና ኑሮና ለከፋ ድህነት ተዳርጓልና በእርሻው መስክ የወያኔ ሁለገብ እርምጃ የሚያበለጽግ ሳይሆን ወያኔን የሚያከብር፤ መሬታችንን የሚጎዳና ሰፊውን ሕዝብ ወደ ርሃብና የችግር አዘቅት የሚወረውር ነው ። በአንጻራዊ ደረጃ
3

ያለው ልዩነት እንዳለ ሆኖ የትግራይም ይዞታ በመሰረቱና በዋና ደረጃ ወያኔን የሚጠቅም እንጂ የትግራይን ሰፊውንና ድሃውን አርሶ አደር ያበለጸገ አይደለም ።
ወያኔ መሬታችንን፤የተፈጥሮ ሀብታችንን፤ ቅርሶቻችንን፤ የዱር አውሬዎቻችንን ሁሉንም እያወደመ ያለ ጸረ ኢትዮጵያ ሀይል በመሆኑ ሀገርን ለማዳን ባስቸኳይ ይህንን ቡድን የማስወገድ እምርጃ መወሰድ ያለበት ነው ።

No comments:

Post a Comment