Sunday, July 19, 2015

"መሬት ላይ ላለ ሥጋ ፤ በሰማይ ያለአሞራ ተጣላ !" የኦሮሞ ተረትና ምሳሌ

የፍኖተ ዴሞክራሲ የኢትዮጵያ አንድነት ድምጽ ሀተታ ሐምሌ 10 ቀን 2007 .. የተላለፈ

"መሬት ላይ ላለ ሥጋ ፤ በሰማይ ያለአሞራ ተጣላ !" 
የኦሮሞ ተረትና ምሳሌ
በአንድ በተወሰነ ገፀ-ምድር ላይ የሚገኝን ቦታ ፤ በባለቤትነት የሚቀመጡበት ዜጎችን ያቀፈ መሬት ካለ ፤በዕውነትም ሀገር አለ ማለት ይቻል ይሆናል ፡፡፤ የሀገር ትርጉም፤ በበለጠ ተሟልቷል ለማለት የሚቻለው ግን በዚህ ምድር ላይ ያሉ ነዋሪዎች ተስማምተውና ፈቅደው የራሳቸውን መንግሥት ሲመሰርቱ ይሆናል። ይህ አገላለፅ፤ ሀገር ብሎ ለመጥራት ካስፈለገ፤ እንግዲህ ሦስቱንም አሟልቶ እንዲገኝ ይጠበቃል ማለት ነው። ይኸውም፡------
1. ዳርና ድንበሩ በቋሚነት በህግ አሳውቆ፤ ጠረፉና ወሰኑንም አስከብሮ፤ የተገኘ መልከዐ-ምድር ፤ 2. በዚህ ምድር ላይ በአንድ ላይ የሚኖር ሕዝብ ፤
3. ሕዝብ ፈቅዶ-ተስማምቶ የሚመሰርተውን መንግሥት ያጠቃልላል ።
ባጭሩ፤ ሀገር የሚያሰኘው፤
. መሬት
. ሕዝብ
. መንግሥት፤ በአንድ ላይ ተሟልተው ሲገኙ ማለት ነው።
ሦስቱም አንድ ላይ ተሟልተው ሲገኙ፤ ያን ገፀ- ምድር ሀገር ነው ማለት ይቻላል ። ዛሬ ኢትዮጵያ፤ በስም ብቻ ካልሆነ በስተቀር ፤ ሦስቱንም መስፈርቶች አሟልታ እንደ ሀገር ትኖራለችም፤ ትቆያለችም ማለት አልተቻለም። አይቻልምም ። ምክንያቱም፡ ------
1. ዳር ድንበሯ፤ በቋሚነት ተረጋግጦ አልሰከነም። አካሏ የነበረው፤ ከሰሜን ምዕራብ ጀምሮ እስከ ደቡብ ያለው መሬት በየጊዜው ወደ የሚሄድበት እየሄደ ይገኛል ። የሰሜኑ ግዛቷ፤ እስከ ባኅር ዳርቻዋ ተገንጥሏል ። የግዛቷ ልዕልና፤ ወዴት አቅጣጫ እንድሚሄድና የትስ እንደሚቆም ገና ስክኖ አልተረጋጋም፤ አልታወቀም ። አልተረጋገጠም ። በየወቅቱ ጃርት አንደሚግጠው ዱባ በመፍረክረክ ላይ ይገኛል።
page1image13784 page1image13944 page1image14104
1
2. በአንድ ምልከዐ - ምድራዊ የግዛት ልዕልና፤ አንድነቱን አስከብሮ የሚኖር ሕዝብ አለ ለማለት ከማይቻልበት ጊዜ ተደርሷል። እንደ አንድ ሀገር ሕዝብ ፤ ምሉዕነቱን ጠብቆና አስከብሮ ለመኖር የሚያስቸለው ዋስትና የለውም ። ሀገር- ከሕዝብና ከመንግሥት ጋር ተመስርተው፤ ተቆራኝተውና በአንድ ላይ ሊኖሩ የሚችሉበትን ዕድል እንዳይኖራቸው ተደርጓል ።
እዚህ ላይ መተኮር የሚገባው፤ ኢትዮጵያ እንደ ሀገር፤ ነዋሪዎቿም እንደ አንድ ሕዝብና ዜጋ አንድ ላይ ተቆጥረው፤ የመኖር/ ያለመኖር ጉዳይ ነው ። መኖር ሳይኖርና ሳይረጋገጥ ፤ የወደፊቱም የመኖር ምኞት ተስፋው ሳይገኝ፤ ስለ ዴሞክራሲ- ነፃነትና ህገመንግሥት ፤ ስለ ዕድገትና ብልፅግና፤ ማውራት አይቻልም። ይህንን ሀቅ ያልተገነዘበ ፤ እራሱን እየደለለ መኖሩን ሊያውቀው ይገባል ።
3. ዛሬ፤ የኢትዮጵያን የግዛት አንድነትና የፖለቲካ ልዕልና ፤ የዜግቿንም ነፃነትና አንድነት ጠብቆና አክብሮ የሚያስከብር መንግሥት የለም። በተፃራሪው ግን፤ የአንድን ብሄር ጥቅም ለማስጠበቅ ተብሎ የተፃፈ የድርጅት ህግ እንደ " ህገመንግሥት" ተቆጥሮ፤ ሀገሪቱን ለማፈራረስና ሕዝቧን ለመበታተን መሳሪያ በመሆን፤ ጥንታዊቷ ኢትዮጵያንና ዘለዓለማዊው ሕዝቧ እንዳልነበሩ ለማድረግ ይጠቀሙብታል ። ሀገር አፍራሽና ሕዝብ በታኝ ቡድን በትረ- ሥልጣን ጨብጦና ፤ ገደብ የለሽ ኃይል እየተጠቀመ ያሻውን በመስራት ላይ ነው ። የአንድ ጎሳ መሪዎች መላዋን ኢትዮጵያ እያፈራረሷት ናቸው ። ይህ ሀቅ ያልተዋጠላችው ዜጎች ይኖራሉ ተብሎ አይታሰብም ።
በመሆኑም ፤ ዛሬ ፤ በሀገሪቱ መጥፋትና በዜጎቿ መበታተን ፤ ማን ተጠያቂ ፤ ማን ጠያቂ ፤ ማንስ የሀገርንና የሕዝብ ወኪል ሆኖ፤ የቆመ ኃይል አለ ማለት አይቻልም ። ኢትዮጵያን በሚያፈርሰው አፍራሽ ኃይልና፤ ኢትዮጵያ መፍረስ የለባትም ብሎ በቆመው ተቆርቋሪ ወገን መካከል ያለው የኃይል ሚዛን፤ ያልተመጣጠነ በመሆኑ፤ ኢትዮጵያን እያፈራረሰ ያለው ቡድን የበላይነቱን ይዞ የጥፋት ዓላማውን አንግቦ እየተራመደ ነው ። ይህ በሆነበት ሁኔታ፤ሀገር አፍራሹን ኃይል ለመግታት፤ ፈርጥሞና ጠንክሮ መገኘት ባስፈለገ ነበር ። ተቃዋሚው ክፍል፤ ግን በዚህ ላይ ማተኮር ሲገባው፤ ልክ፤ " በሰማይ ላይ እንዳለ አሞራ፤ በመሬት ላይ በወደቀ ስጋ ላይ መጣላቱን መርጦል ። " " ወጡ ሳይወጠወጥ ወስከምቢያው ጥልቅ " እንዲሉ፤ ሀገርና ሕዝብ ሳይኖሩ፤ ለሥልጣን ሺሚያ መረባረብ ሥራየ ተብሎ ተይዟል ። " መጀመሪያ መቀመጫየን " ያለችውን እንስሳ እንኳን ያህል ማሰብ አልተቻለም ! ኢትዮጵያን ከወደቀችበት አዘቅት የማውጣቱ ተግባር ቅድሚያ ሳይሰጠው፤ የፖለቲካ ሥልጣን ለመያዝ ተብሎ የሚደረገው ጠብና ፍጅት፤ ልክ በመስመጥ ላይ ባለች መርከብ ውስጥ እንደሚጣሉ መርከበኞች መሆን ነው። መርከቧ ስትጠልቅ ባህረኞቹም አብረዋት እንደሚጠፉ አልተገነዘቡትም። " ሀገር ከሌለ፤ ሁሉ ነገር አይኖርም የሚለውን እሳቢ ለመገንዘብ የጠረፍ ምርመራ ጠበብት መሆንን ባልጠየቀም ነበር ።
4. ሀገር ሲባል፤ የትኛው ሀገር ? ሕዝብ ሲባል፤ ማነኛው ሕዝብ ? መንግሥት ሲባል ፤ የማን መንግሥት ? ተብሎ ሲጠየቅ፤ ምልዕው(?) መልስ የሚመልስ ስካልተገኘ ድረስ፤ እንደ ገበታ ውሃ ከመዋለሉ ያለፈ ፋይዳ አያመጣም። መላው ዜጋ ፤ መልኅቁን አጥቶ በውቅያኖስ ላይ እንደሚንሳፈፍ መርከብ ፤ እየዋዠቀ የሚኖረው በዚህ ምክንያት ነው ቢባል፤
page2image19360 page2image19520
2
ከዕውነት የራቀ ነው አይባልም ። ይህንን ለማለትም የሚያስችል በቂ ምክንያት አለ። ይኽውም፤ ሁሉም ዜጋ፤ ኢትዮጵያ ተብላ ስትጠራ የኖረችው ጥንታዊቷ ሀገር፤ እርሱ እየኖረባት የቆየችው ምድርና ፤ አብሮ የኖረው ኢትዮጵያዊው ዜጋ ከተፍጥሯዊ ሰብዕናው ወደ ሰው-ሰራሽና ወደ ባዶነት እየተለወጠ መሄዱን መገንዘቡ ነው ። ይህ ደግሞ እያንዳንዱን ዜጋ ወደ ባዶነት/ ከንቱነት፤ የሚለውጥ ክፉ ክስተት ነው ። የአብሮነት ኅልውንም ቀስ በቀስ እየተሸረሸረ መሄዱ የማይቀር
መሆኑ እየተመቻቸ ነው ። የባዶነት ስሜት፤ ኅልውናን እየሸረሸረ የሚሄድ አጥፊ ሥነልቦናዊ ይገባል ።
ሂደት መሆኑን መገንዘብ
"
መሬቱም ይሄዳል እግር አውጥቶ እንደ ሰው ፤ ወሰኑም ይከስማል ፤ ጠላት ካፈለሰው ፤ ዜጋ ተረባርቦ ፈጥኖ ካልመለሰው ፤ የባላንጣን ግፊት ቆሞ ካላቆመው ።
ሕዝቡም ይበተናል፤ይጠፋል፤ሟምቶእንደጨውዘር፤
ሁሉም ተባብሮ ካልቆመ በአንድ ልብ ለሀገር ። "
መጀመሪያ መደረግ የሚገባው ፤ መጀመሪያ ሊሆን የሚገበው ነው ተብሎ እስከታመነበት ድረስ፤ የሁሉም ትኩረት ሊያነጣጥር የሚገበው ፤ ሕዝብን ከመበታተንና ሀገርን ከመከፋፈል ማዳን በሆነ ነበር ። ይህ እስካሁን በብዙ የታሰበበት መስሎ አልታየም ። እንዲያውም፤ ይህ ዐብይ ጉዳይ ወደ ጎን እየተገፋ፤ብዙዎች ያተኮሩት በሥልጣን ኮርቻ በመፈናጠጥ ላይ ብቻ ሆኖ ቀርቷል። ተቃዋሚ ነን ብለው የተሰለፉትም ፤ የአብዛኛዎቹ ትኩረት ፤ ከወያኔ ጋር የመንግሥት ሥልጣን ሽርክና አግኝቶ በሰላም የመቆየቱን ሁኔታ ማመቻቸት ሆኗል ። ሀገርና ሕዝብ በአንድ ላይ ሳይቆዩ/ ሳይኖሩ፤ በምን ላይ ለመቆሞና ማንንስ ለመግዛት ተፈልጎ ነው ? ለሚለው መሠረታዊ ጥያቄ እንኳን መልስ ለመስጠት ድፈረት የላቸውም ። ወያኔ ደግሞ፤ የሥልጣን ሽርክና ሊያካፍላቸው ቀርቶ፤ በፖለቲካው መድረክ አካባቢ ሊያንዣብቡ እንኳን አልፈቀደላቸው ። ከኢትዮጵያ የወርቅ ማዕደን የተዘፈቀ የትግራይ የገዥ ቡድን የመንግሥት ሥልጣን ማካፈል ቀርቶ፤ ከድግሱ የተረፈውን ትርፍራፊ እንኳን ቢሆን የሚቸራቸው አይደለም ።
የማይገኘውን ሥልጣን ለማግኘት ከመቋመጥ ይልቅ ሀገሪቱን ከመከፋፈል ለማዳን በሚደረገው ትግል ላይ ማተኮሩ በተገባ ነበር። ኢትዮጵያን ለማዳን የመጀመሪያው በር ከፋች ፤ ወያኔን ከሥልጣን ማወረድ መሆኑን አውቆ-ተረድቶ፤ በዚያ ላይ መተኮሩ የወቅቱ አንገብጋቢ ጥያቄና የምልዐተ- ሕዝቡ ፍላጎት ነው።
በጭቁን ብሄራት ስም፤ ወያኔ ኢትዮጵያን ለማጥፋት የጀመረውን ሴራ፤ ዛሬ ከሁሉም በላይ የተረዱት፤ በስማቸው ወያኔ የሚነግድባቸው እራሳቸው ጭቁን ብሄሮች ሆነዋል ። ይህ ደግሞ፤ ኢትዮጵያን ለማዳን በሚደረግው ትግል ዓይነተኛ ሚና
3
ለመጫወት የበኩሉን ኃላፊነት ይሸከማል ተብሎ ይታመናል ። ወትሮውንም ቢሆን፤ በልዩ ልዩ ስሞች በዓለም ውስጥ ብዙ ወንጀሎች እንደተፈፀሙ እንገነዝባለን ።
በዓለም የታሪክ ሂደት ፤ በሥልጣኔ ፤ በሃይማኖት ፤ በግዛት ማስፋፋት ፤ በብሄርና በመደብ ትግል ፤ በነፃነት ፤ በዴሞክራሲና በሶሻሊዝም ወዘተ.. ስም ፤ የተለያዩ በደሎችና ወንጀሎች እንደተፈፀሙ ፤ በርካታ መዛግብት አስፈረው አቆይተውታል ። ቤኒቶ ሙሶሊኒ ኢትዮጵያን ለመወረር ከተጠቀመባቸው ምክንያቶች አንዱ፤ " ድንጋዮቹን ወደ ሰው ለመለወጥ" ( Humanizing The Stone ) መሆኑን በሮማ ከተማ ባደረገው ንግግር ውስጥ ተናግሮታል ። ዛሬም ወያኔ በአቅሙ፤ በኢትዮጵያ ላይ ለሚፈፀው ወንጀል ምክንያት ካደረጋቸው ሰበቦች መካከል ፤ ለጭቆን ብሄሮች ጥብቅና የቆምኩት እኔ ነኝ የሚል ሽፋን ሰጥቷል ። በድርጊት የሚፈፀው ግን ተቃራኒውን ሆኗል ። የጋራ የሆነቸውን ሀገር ሁሉም በጋራ አብሮ እየኖረ፤ ሃብቷንና ፀጋዋንም፤ በጋራ የመጠቀም ዕድሉ ሁሉ እየተዘጋ፤ የጋራ የሆነችው ሀገር እንዳትኖርና ፤ ለአያሌ ዘመናት በጋራ አብረው የኖሩት ዜጎቿም በጋራ አብረው እንዳይቆዩ እየተደረገ ነው። የዘረኞች የአፍራሽ ፖለቲካ ፤ " የቆየችውን ሀገር አፍራርሶ " ኅልውናዋን ማጥፋት ሆኗል ። ይህን ያፍራሽች ፖለቲካ ተባብሮ ማስወገድ ይሁሉንም ዜጋ ትብብር ማስፈለጉ ደጋግመን የምንለው ስለሆነ፤ ወያኔን ተፃርረው የቆሙ ኃይሎች እስኪተባበሩ ድረስ ጥሪያችንንና ጥያቄያችንን ማሰማቱን እንቀጥልበታለን ።
ዛሬ፤ የኢትዮጵያ ሕዝብ የቅድሚያ ብሄራዊ መርሓ ግብር ሆነ ጥያቄ ፤ ማን ሥልጣን ይያዝ ? የትኛውስ ድርጅት የሀገሪቱ መሪ ይሁን ? የሚለው ሳይሆን፤ በዕርግጥ ሀገሪቱን ከጥፋት ለማዳን የሚችል ኃይል ያለው ማን ነው ? ኢትዮጵያንስ ከወያኔ መንጋጋ ለማላቀቅ የሚችል ብርታትና ችሎታ ያለው ማን ሊሆን ይችላል ? የሚለው ነው ። በነኝህ መሠረታዊ ጥያቄዎች ሁሉም የሚስማማበት መሆኑ ቢታወቅም፤ እኔስ የድርሻየን ለመወጣት ምን እያደረግሁ ነው ? የዜግነት ግዴታየን ለመወጣት፤ የበኩሌን ሚና ለመጫወት ከእኔ ምን ይጠበቅብኛል? የሚሉትንና ተዛማጅ ጥያቄዎችን ጠይቆ ከራሱ ድምዳሜ እየደረሰ፤ ሁሉም ድርሻውን እንዲወጣ ይጠበቅበታል ። ቀስ በቀስ በመጥፋት ላይ ያለችውን ሀገር ለማዳን የሚቻለው፤ በሁሉ ዜጋ ርብርቦሽ እንጅ በተወሰኑ ድርጅቶች ብቻ እንዳልሆነ ሁሉም ሊገነዘበው ያስፈልጋል ። ማንም ድርጅት ለሌላው ዜጋ ፤ ቤዛ- መድኅን እየሆነ ሊታገል አይጠበቅበትም ። ይህንን ሀቅ፤ ባለቅኔው በሚከተለው ስንኝ ቋጥሮታል ።
የሰው እንጀራ አውጭ እንደ ሰብስጥራ ፤
እኛ እየተቃጠልን ሌላ ስም ሊጠራ
?
ትግሉን መሥዋዕቱን አብረን ካልከፈልነ ፤
የኋላ የኋላ ውጤቱ እና ድሉ እንዲያው ከንቱ ሆነ ። ድሉ ከንቱ እንዳይሆን፤ ፍሬውም ገለባ

ሁሉም እንደየ አቅሙ ወደ ትግሉ ይግባ ።
4
ይህ መልዕክት፤ ሀገርን ከጥፋት ለማዳን ሆነ፤ የተረጋጋ ሠላምና ዋስትናን በመፍጠር፤ ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ገንብቶ ወደ ልማትና እድገት ለመሸጋጋር ፤ የሁሉንም ዜጋ ትብብርና ተሳትፎ ወሳኝ መሆኑን ያመለክታል ። የዜጎች ትብብርና ህብረት መኖር ያለጥርጥር አንገብጋቢና ወሳኝ ነው። ይህንን ማምጣት ደግሞ ለጊዜ ቀጠሮ የሚተላለፍ ሊሆን አይገባውም ። ለዚህ መሠረታዊ ጉዳይ፤ አፅንኦት ተሰጥቶ ሁሉም ሊያስብበት ግድ ይላል ። ሀገሪቱ ከጥፋት ልትድን የምትችለው በሁሉ ዜጎች መሥዋዕት ብቻ ነው:
ታላቂቷ ኢትዮጵያ የሚገባት ታላቅ መንግሥት እንጅ፤ የጎጠኞች ዳስና የክልለኞች ሽርፍራፊ " መንግሥታት" አይመጥኗትም። ታሪክ ያለው ሕዝብ ታሪክ እየሰራ መቀጠል ካለበት፤ ታሪክ አጥፊዎቹን እያስወገደ፤ ታሪኩን እያስከበረ መኖር ይኖርበታል ። ሀገራችን እንደ ሀገር መኖር አለባት ከተባለ፤ ለሁሉ ዜጎቿ የምትስማማ ኢትዮጵያ እንድትኖር ያስፈልጋል ። እኛ በበኩላችን ፤ ትልቋ / ዐባይ ኢትዮጵያ ስንል የሚከተሉትን ዕውነታዎች ተመርኩዘን ነው።
1. የበለፀገ ታሪክ፤ የዳበረ ባኅል፤ የሦስት ታላላቅ ሃይማኖቶች ምዕመናንና ጉራማይሌ ውበት ያላቸው ዜጎች ለዘመናት የኖሩባት ምድር መሆኗ፤ በነፃነቷ ታፍራና ተከብራ መኖሯ፤ ለነፃነታቸው ቀናዒ የሆኑ ዜጎች ያሏት በመሆኗ ፤
2. ከሰማይ በታች፤ በድሯ በላይና በከርሰ- ምድሯ ያለው የተፈጥሮ ሀብቷ፤ መጥንና ዓይነት ግዙፍ መሆኑ ። እስከ ዛሬ ደረስ ግን ለዜጎቿ ጥቅም ያልዋለ መሆኑ፤
3. የመልከዐ - ምድር አቀማመጧ፤ ለአካባቢው ፖለቲካ እጅግ ወሳኝና ተፈላጊ ያደረጋት መሆኑ፤
4. የሦስት አየር ንብረቶችን ማስተናግዷ፤ ለሰው ህይወት ተስማሚ፤ ለአዝርዕት- ለአትክልት ፤ ለአዝመራ- ለሰብል፤ ለእንስሣት፤ ለአራዊት፤ ለአዕውፋት፤ተስማሚ መሆናቸው፤
5. ታላላቅና ንኡሳን ዥረቶችና ወንዞቿ፤ ከሀገር ውስጥ አለፈው- ተርፈው ፤ ደንበር ዘለል መሆናቸው፤
6. ወደ አንድ መቶ ሚሊዮን የሚጠጋ የሰው ኃይልና ሀብት ያላት መሆኗ ፤
7. በሦስተኛው ዓለም ከተመደቡት ሀገሮች ጋር ሲነፃፀር ቁጥሩ የማይናቅ የተማረ የሰው ኃይል ያላት መሆኗ ፤
ከላይ ከቁጥር አንድ እስከ ሰባት የተጠቀሱት አካትታ የያዘች ኢትዮጵያን ፤ ታላቅ ሀገራችን ነች ብለን አፋችንን ሞልተን ለመናገር የምንደፍረው በነኝህ ምክንያቶች ነው። ይህች ታላቅ ሀገርና ዜጎቿ አንድ ላይ መኖር እንጅ፤ በጎሳና በቋንቋ ተከፋፍለው በጥቃቅን ተውሳክ መንግሥታት ስር ሊሆን አይገባቸው ብለን በፅኑ ዕናምናለን።
እዚህ ላይ ግን ፤ አንድ ሊካድ የማይቻል ሌላ ሀቅን ጠቁመን ማለፍ እንሻለን። ሀገራችን ሁሉንም ሀብትና ፀጋ ሳታጣ፤ ምንም ነገር የሌላት ሀገር ሆና እንደምትኖር መገንዘባችን ነው። ይህንን ዕውነታ እያንገፈገፍንም ቢሆን መቀበል ያለብን መሆናችንን እናምናለን።
5

ይህንን አንገት ሰባሪ ሀቅ ለመለውጥ ያለንን ምርጫ ደግሞ፤አንድ ብቻ ሆኖ አግኝተነዋል ። ወያኔን አስወግዶ ዴምክራሲያዊ ሥርዓትን መመስረት ብቻ ነው !
መጀመሪያ ሀገርንና ሕዝብን ከመፍረስና ከመበታተን ማዳን ይቀድማል እንጅ፤ " በመሬት ላይ ላለ ሥጋ ፤በሰማይ ላይ ያለ አሞራ እንደሚጣላ" ዓይነት፤ እርስ በእርስ እየተፋጁ ኅብረት መፍጠር አለመቻል፤ በታሪክም ሆነ በትውልድ ያስጠይቃል ። ኢትዮጵያ በታሪኳ ብዙ ፈተናዎችን ማለፏን ስለምናውቅ፤ አሁን የተጋረጠባትን ፈተና እንደምትወጣው አንጠረጠርም ። በመሆኑም፤ የችግሯና የፈተናዋ ተከፋዮች ሆነን ትግላችንን እንቀጥላለን !!
ኢትዮጵያም ለዘለዓለም ትኖራለች

No comments:

Post a Comment