Sunday, August 30, 2015

ከፍኖተ ዴሞክራሲ በ አማራ ሕዝብ ስም ሌሎችን መዝለፍ የሚወገዝ ነው


ከፍኖተ ዴሞክራሲ
በ አማራ ሕዝብ ስም ሌሎችን መዝለፍ የሚወገዝ ነው
ይህን አቅዋም ማስተጋባቱ የግድ የሆነብን አማራው ህዝብ ተበደለ በሚል ጸያፍ ዘመቻዎች በሌሎች ህዝባችን ላይ መካሄዱ ስለቀጠለ ነው ። ዝምታ ሕዝብን ለጥቃት አሳልፎ መስጠት በመሆኑ ግዳጅና ሀላፊነትን መካድ ይሆንብናል ። በሰሞኑ አማራው ህዝብ ከቤኒ ሻንጉል ተፈናቀለ በሚል ለዚህ ዋናውን ተጠያቂ ወያኔን በማውገዝ ፈንታ በጉምዝ ሕዝብ ላይ የተከፈተው ጸያፍ ዘመቻ የአማራን ሕዝብ ተገን አድርጎ በመሆኑ ሊወገዝ የሚገባው ነው።
በመጀመሪያ ደረጃ አማራው ክጉምዝና ቤኒ ሻንጉል አካባቢዎች መፈናቀል የጀመረው ወያኔ ኢሕአፓን አጥቅቶ ቦታውን ከተቆጣጣውረ ከ1983 .. ጀምሮ ነው ። ደርግ በጣና በለስ አካባቢ አስፍሯቸው የንበሩ ዜጎች የዚህ ወያኔያዊ ዘመቻ ሰለባ ነበሩ ፡፡ ቀደም ደርግ ያደረሰባቸው በደልና ይህንንም በመቃወም ድርጅቱ ያደረጋቸውን ጥረቶች ለታሪክ ትተን ወያኔ ስልጣን ሲይዝ በቦታው በነበሩ የአማራ ተውላጆች ላይ እርምጃ ሲወስድ ያኔ ከኢሕአፓ ሌላ በጉዳዩ ቁጭትም ያሰማ ትችትም ያቀረበ አልነበረም ። አሌ ከተባለ በመረጃ መርታት ይቻላል ። ከቤኒ ሻንጉልም፤ ከምስራቅ ወለጋም፤ ከደቡብ ኢትዮጵያም ወዘተ አማሮች ላይ የማፈናቀሉ ዘመቻ ምንጩ ወያኔ ነው ። የወያኔ ተለጣፊዎች ናቸው ፡፤ በ አሶሳ፤በደኖ፤ አርባጉጉ ከወያኔ ያበሩ የኦሮሞ ድርጅቶች ለደረሰው ወንጀል ተጠያቂነታቸው የሚካድ አይደለም ። የነሺፈራው ሽጉጤና ሃይለ ማርያም ደሳለኝም ወንጀል ወያኔ በሚል የሚሸፈን አይደለም ። ይህ እንዳለ ሆኖ ግን ንጹህ ሕዝብን በጸያፉ መወንጀልና መክሰስ ብልግና ነው ።
የጉምዝ ሕዝብ/ቤኒ ሻንጉሎች አማራውን ገድለው ጉበቱን፤ኩላሊቱን፤ የታፋ ስጋውን በሉ ብሎ ዓይንን በጨው አጥቦ ሕዝብን መዝለፍ አፍሪካን ከሚጠሉ ነጮች የሚጠበቅ እንጂ ለአማራው ተቆረቆርን ባዮች ሊሰማ የሚገባው አይደለም ። ያሳፍራል ይህ ሲደመጥ ። ሊደመጥ የማይገባውን ትምክህትንም አንጸባራቂ ነው ። ሕዝባችን የትም ቢሆን የት ሰው አይበላም ፡፤ ይህን ውሸት ማሰራጨት ኢትዮጵያ ላይ መዝመት ነው ። የሚከሰሱት አህዛብ ናቸው ፤ሀይማኖት የላቸውም ስለዚህም ሰው የሚበሉ አረመኔዎች ናቸው ብሎ ልፈፋም አማራ ነን ባዮቹ ምንኛ ኋላ ቀርና የሀገርን ስምና የአንድነት መሰረት አውዳሚ እንደሆኑ ያሳያል ። ሁሉም ሕዝብ የራሱ እምነት አለውና መከበር ይገባዋል ከማለታችን በተጨማሪ ሰው ብላ የሚል እምነት በኢትዮጵያ አለ ብሎ መነሳት ሀገራችንን ማዋረድ ነው ። ኢትዮጵያዊያን ግፍ አይፈጹምም ስንል ቆይተን የደርግ አረመኔዎች (አሁን ሰው ተበላ ባዮች አንዳንዶቹ እነዚሁ ናቸው ) የኢሕአፓን አባላት ስጋ እየቆረጡ ብሉ ሲሉ ታዝበናል ። እነዚህ ከይሲዎች ዛሬ በየተቃዋሚው ድርጅት ተሰግስገው እንዳሉም እናውቃለን ። በየ ፓል ቶኩ የሚባልጉት እነዚሁ ናቸው ። ይህ የአማራው ስጋ ተበላ የሚል መረጃ አልባ ልፈፋ ተወደደም ተጠላም ወያኔን የሚጠቅምና ተከሳሹን ሕዝብ ብቻ ሳይሆን መላ ኢትዮጵያን ሕዝብ መብትና ክብር የሚጥስም የሚያክቸለችልም ነው ፡፡ የጉምዝ ቤኒሻንጉልን ሕዝብ በጸያፍ ውንጀላ የከሰሱት ሁል ህዝብን ይቅርታ መጠየቅ ይገባቸዋል። አፍሪካኖች አረመኔዎች ናቸው ብለው ሊያጣጥሉን ለሚጥሩ ባዕዳንም ወፍጮ እህል በማቅረባችው የሚወገዙ ናቸው ። ኢትዮጵያን ሲጎዳ የቆየውን ትምክህት በማናፈሳቸውም በህዝብ መከፋፈል ልክ እንደ ወያኔም ሊከሰሱ ይገባቸዋል ። እውነቱ ተነግሮ ሳያልቅ ወደ ሀሰቱ መጓዝስ ለምን አስፈለገ?
ወያኔ አማራውን ከየቦታው ያፈናቅላል? እውነት ።
page1image20520 page1image20680

ከቤኒ ሻንጉልና ሌሎች ቦታዎች አማራው ተፈናቅሏል ? እውነት።
መፈናቀሉ በደልንም አዘል ነበር
? አዎ
የተገደሉ አማራዎች አሉ
? ትክክል ።
ሬሳቸው ቅርጫ ገብቶ ተበልቷል
? አሳፋሪና ጸያፍ ውሸት ።
ይህን ውሸት ማራገቡ ጠቃሚ ነው ብለው የተነሱ ክፍሎች ፖለቲካዊ መሃይምነታቸውን ተገንዝበው እንዲያቆሙ ሊደረጉ ይገባል ። የጉምዝና ቤኒ ሻንጉል ሕዝብ ኢትዮጵያዊነትን በጥያቄ ማስገባት ራሱ አሳዛኝ ከመሆኑ ባሻገር ግን ሬሳ በላ ብሎ መወንጀሉ አሳፋሪ፤ትምክህተኛና የኢትዮጳያን የአንድነት መሰረት ጎጂ ነው ። የተወነጀለው ሕዝብ አያሌ መሀይሞችና ትምክህተኞች አሁንም እንዳሉ ተገንዝቦ ቅሬታ እንዳይኖረው ጥሪ ማድረግን እንፈልጋለን ። 

Thursday, August 27, 2015

እምቢኝ በል ወያኔን ! (ዳዊት ከበደ)


እምቢኝ በል ወያኔን !
(ዳዊት ከበደ)
ተጨፈኑና ላሞኛችሁ የሚለውን የወያኔን ደባ ለመቃወም አለበለዚያም የጎሳና የሃይማኖት ፖለቲካን ለማራመድ በወያኔና ሻዕቢያ አጋፋሪነት አብረው አሸሸ ገዳሜ መቼ ነው ቅዳሜ እያሉ የኢትዮዽያን ህዝብ ሲገሉና ሲያስገድሉ የነበሩ አሁን ደግሞ በውጭ በመሆን ስማቸውን በመቀያየር የሻዕቢያ ተለጣፊ በመሆን እንደ ሸማኔ ዕቃ ወዲያና ወዲህ እያሉ በሌላ በኩል ትላንት የኢትዮዽያን ህዝብ ሲገልና ሲያስገድል ሲዘርፍና ሲያዘርፍ የነበረው፣ የኢትዮዽያን ወጣት ለስደት የዳረገውና በሞት የቀጣውን መለስ ዜናዊ በማጀብ ኢትዮዽያን ሲዘርፉ የነበሩና ዛሬ ከሞት ተርፈው በውጭ ያሉ የሀገራችንን ልጆች የአበሳና የመከራ ጊዜ ለማራዘም ተንኳሽ ፖለቲካን የሚያራምዱትን ካንተ የኔ ይበልጣል አንተ በኔ ስር ዕደር በኔ ጥላ ተጠለል በማለት ከኢትዮዽያ ህዝብ ሊለያየን እየሞከረ ያለውን ይህን የወያኔ እና የሻዕቢያ ቅጥረኛ እንቢ እንበለው። በተሻለ መልኩ ኢትዮዽያዊና የኢትዮዽያ ህዝብ ዓይኑን የጣለበትን አንጋፋ የፖለቲካ ድርጅትን በየምክኒያቱ እያራከሱና ስም እያጠፉ የማድቤት ፖለቲካን በመጀመራቸው ለተጠናከረ ድጋፍ ማጣት ምክኒያቶች እየሆኑ ያሉትን እንቢኝ አሻፈረኝ እንበላቸው። በትውልዴ ነብይ ወይም የነብይ ልጅ አይደለሁም ጆሮዬ ካዳመጠው ዓይኔን ካፈዘዘው የግፍና የጣር ማስታወሻ ጨልፌ ሀገር ወዳድ ለሆኑ ኢትዮዽያዉያን ወገኖቼ የሚከተለውን ለማሳሰብ እወዳለሁ።
ህይወት ተሻጋሪ ናት ለአፍታ ደስታ ትሰጠና ሳይታሰብ ደግሞ ሀዘንን ከመከራ ለቅሶ ጋር ታላብሰናለች በዚህ ዓለም የምናሳልፈው ዘመንም እጅግ ጥቂት ነው። ትላንት በሀገራችን አውራ ጎዳናዎች ክፉኛ የኢትዮዽያ ህዝብን ሲያሰቃይና ሲገድል የነበረ የወያኔ አለቃ የነበረው ዛሬ በህይወት የለም፡ አውራው ቢሞትም በሀገራችን በኢትዮዽያ ታይቶ ተሰምቶ የማይታወቅ የመከፋፈልና የማፈራረስ ዘመቻውን ወያኔ አሁንም ተያይዞታል። ህዝባችን በአንድነትና በህብረት እንዳይኖር የተቃጣበትን ጥቃት በጋራ እንዳይመክት በዘር በቋንቋ በሃይማኖት በተሰመረ የአስረሽ ምችው የፖለቲካ ዘይቤ አለቅጥ ይታመሳል።
ታዲያ አንባቢ እንዲረዳልኝ የምሻው የዚህ ሁሉ ሴራ መሠሪ እራሱ የወያኔው ዘረኛ ቡድንና አሽከር ሆድ አደሮቹ በኢትዮዽያ ህዝብ ውስጥ ተሰግስገው ያሉትን ሲሆን ግብራቸው ሰይጣናዊ ስለሆነ ወያኔን በሁለገብ ትግል እንቢኝ አሻፈረኝ ልንለው ይገባል። ወያኔና ሻዕቢያ የኢትዮዽያ የውስጥ መዥገር ናቸው። አሁንም በስልጣን ላይ አለሁ የሚለውም ወያኔ የኢትዮዽያ ህዝብን ሊወክል አይችልም!! እንደሚታወቀው በምንሊክ ቤተመንግሥት ተወሽቆ ኢትዮዽያንና ኢትዮዽያዊነትን ከህዝባችን ልብ ለመፋቅና በምትኩ የጎጥንና የጎሳን ፖለቲካ የሚያራምድ ድርጅት ነው። ነገር ግን የትግራይ ህዝብ ወኔና ኢትዮዽያዊነትም በዚህ ስንኩል ድርጅት ሴራ

አይለካም። የትግራይ ህዝብ ወያኔ ከደገነበት አፈሙዝ ውጭ በራሱ የሚያስብ የሀገር ፍቅር የሚያንገበግበው ቆራጥና አስተዋይ ህዝብ ነው። ለዚህም ነው የዚህ ኩሩ ህዝብ ብርታትና ኢትዮዽያዊነት በወያኔ ነኝ ባዩ ዘረኛ ድርጅት ልንለካው የማይገባን። አንዳንድ በወያኔ ጠረጴዛ ስር ፍርፋሪ ለመልቀም ጎንበስ ቀና በሚሉ ከዚህ ብሔር መካከል ወጥተው ብሎም የራሳቸውን ህሊና የሸጡና ለወያኔ ጊዜያዊ መገልገያ በሆኑ ሰዎች ምክኒያት የትግራይ ህዝብ ተወቃሽ አይሆንም። ወያኔንና የእሱ ተላጣፊዎች የሆኑትን አንተ የትግራይ ህዝብ እንቢ ልትላቸው ይገባል። እኛ የትግራይ ህዝብ ከኢትዮዽያ ህዝብ ጋር ነን በማለት የወያኔ ምፀት ልታወግዝ ይገባል።
ይህን ህዝብ የፈጠራ ፕሮፓጋንዳ ለጊዜው ቢያደናግረውም ኢትዮዽያዊነቱንና አሁን በወያኔ የተያዘው አፍራሽ የፖለቲካ ዘይቤ ልክ አለመሆኑን እውነት ራሷ ትመሰክርለታለች። ከዚህም ባሻገር ሀገር በጎሳና በቋንቋ ስትከፋፈል የሚያስከትለውን መዘዝ የአካባቢ ክስተቶች ይመሰክራሉ። ጥቃት ደግሞ አመፅን ይወልዳል ግፍ በቀልን ያመጣል መከፋፈል ለውጭ ጠላት አጋልጦ ይሰጣል። አንዱ በሌላው ላይ የሚያደርሰው በደል ምንም ጊዜ ቢቆጥርም መመለሱ አይቀርም። ለጥቃት አሜን ብሎ የሚኖር ሰው አንዴ ሳይሆን በየዕለቱ ነው የሚሞተው በሌላ አባባል ህይወት የባለቤቷን ቆራጥነት ትፈታተናለች። ስለዚህ እንቢኝ በል አንበሳ ፀጉሩን ዝንብ አያስነካም።
የኢትዮዽያ አንድነትን ለማስከበር ሆነ የህዝባችንን ውህደት ለማፋጠን በቅድሚያ የወያኔን ሴራ የምናከሽፈው እንቢ ስንልና ብሎም ለህዝባዊ አመፅ ስንነሳሳ ብቻ ነው። ተራ በተራ እጅና እግርህ እየታሰረ ቤትህ ተዘርፎ ሀገርህ ፈርሳ ዓይንህ እያየ ዳግመኛ ሞትን ከመሞት የሁሉንም ዘር ሃይማኖትና ቋንቋ ባቀፈ የፖለቲካ መርህ በመመራት ህዝባዊ በሆነ ድርጅት ታቅፈን ስንታገል ብቻ ነው የምናቸንፈው።
በአገር ውስጥም ሆነ በየዓለማቱ ተበትነን የምንገኝ ኢትዮዽያዊ/ት የጎሳንና የቋንቋን ክልል በተሻገረ አመለካከት በመሰለፍ የኢትዮጵያ ህዝብ ስልጣን ባለቤት ለማድረግ የሚበጀን ሐዋርያው እንደመከረን እንቢ ለጋኔን እንዳለው እኛም ደግሞ እምቢኝ አሻፈረኝ ብለን ጸረ ወያኔ ትግላችንን እናፋፍም ስል ጹሑፌን በዚሁ እቋጫለሁ። ይዋል ይደር እንጂ በህዝብ ደም እና እንባ የሚሳለቁ አምባገነኖች ሁሉ በህዝብ አመፅ ተገርስሰው ህዝባዊ ፍርድ የሚቀበሉበት ጊዜ ፀሐይ በምስራቅ እንደ መውጣቷ ያለና አይቀሬ የተፈጥሮ ህግ ነው። የወያኔን አምባገነን አገዛዝ በተባበረ ትግላችን እናስወግዳለን። የኢትዮዽያ ህዝብ የስልጣን ባለቤት እስከሚሆን ድረስ ትግላችን ይቀጥላል
እናቸንፋለን!! 

Wednesday, August 26, 2015

አቶ አርከበ እቁባይ መለስ ዜናዊን መግደል ጀምረዋል (ሪፖርታዥ)

በአንድ የቅርብ ስብሰባ ላይ አቶ አዲሱ ለገሠ አቶ አርከበን ሲነቅፉ “ ቆይ ቆይ አርከበ እኔ እዚህችጋር አንድ ጥያቄ አለችኝ። እስኪ ይሄ ያዘጋጀኸው ዶክመንት ከመለስ አስተምህሮ ጋር እንዴት እንደሚሄድ አስረዳኝ……” አቶ አዲሱ በኢህአዴግ ድርጅታዊ መዋቅር ውስጥ እንጂ በመንግሥት መዋቅር ውስጥ የሉም። አቶ አርከበ ደግሞ በመንግሥት እንጂ በድርጅቱ መዋቅር ውስጥ የሉም። መዋቅር የማያገናኛውቸው ከሆነ ሁለቱን ከአንድ ስብሰባ ምን አስቀመጣቸው? የመከራከሪያቸው ፍሬ ነገርስ ስለምን የመለስ አስተምህሮ ሆነ? የመለስ አስተምህሮ ራዕይና ሌጋሲ የአገሪቱ አቅጣጫ መመሪያ ማስፈራሪያ እየሆነ ዋነኞቹን ባለሥልጣናት ሳይቀር እያከራከረ ይመስላል። ወደታች ወረድ ብለን እንመለከተዋለን። ለማናኛውም አቶ መለስ ዜናዊ ሞልተውን ለሄዱት የውድቀትም ሆነ የእድገት ሰሌዳ፣ ከአንዳቸው እንደርስ ዘንድ ምን ያህል ጊዜ ይቀረናል? በራዕይ የተገለጠላቸውን የኢትዮጵያ የወደፊት እጣ ምልክቱን እናይ ዘንድ ምን ያህል መጓዝ ይኖርብናል? ወይስ ደርሰናል ? ወይስ አቅጣጫውን ስተን ሌላ መንገድ ይዘናል? ከእድገቱ ወይስ ከቁልቁልቱ አፋፍ ላይ ነን? በፈጣኑ እድገታችን ፋፍተን እንደ ጽጌረዳ ፈንድተን እንፈካለን ወይስ እንደ ፈንጂው እንጠፋለን? ወዴት እየሄድን ነው? በወቅቱ እንደተዘገበው 8ኛው የኢህ አዴግ ጉባዔ የተካሄደው ከመስከረም 5-7/2003 ዓ.ም አዳማ የኦሮምያ የመሰብሰቢያ አዳራሽ ነበር። ጉባዔውን በመምራት ላይ የነበሩት አቶ መለስ፣ የአምስት- ዓመት የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ ላይ የተደረገው ውይይት በቂ እንደሆነ ገልፀው፣ ‹‹የቀረበውን ሪፖርት መፅደቁን የምትደግፉ፣ ያደረጋችሁትን ባጅ ከፍ አድርጋችሁ አሳዩ›› ሲሉ ጠየቁ። ጉባዔተኛው በሙሉ አንገታቸው ላይ ያንጠለጠሉትን ሰማያዊ የጉባዔ ተሳታፊነት መለያ ወደ ሰማይ ቀሰሩ። 
‹‹እቅዱን የምትቃወሙና ድምፅ የማትሰጡ?›› 
ማንም የለም። “የአምስት- ዓመት የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ ጸድቋል።” አሉ።
 አዳራሹ በጭብጨባ ተሞላ።

 የአቶ መለስ በዚህ ጉባኤ ባሰሙት ንግግር እንዲህ አሉ አቶ መለስ ዜናዊ ከሞቱ በኋላ ግን ድርጅታቸው ዛሬ ላይ ቆሞ ሲያየው የአቶ መለስ እቅድ ያለቅጥ የተለጠጠ ነበር። ምክንያቱም አልተሳካም። የማይሳካው ነገርም የታቀደው ሆን ተብሎ ነው። አቶ መለስን ልክ አልነበሩም በማለትና እሳቸውን በማምለክ መካከል በመንገላታት ላይ የሚገኘው ድርጅታቸው በጣም የሚያስቅ መግለጫ ይዞ ወጥቷል። የአቶ መለስን ስህተት እንኳ እንድ ራዕይ አይቶት ከሰማይ ከዋክብትን ከማርገፍ ጋር አመሳስሎታል። በሌላ በኩል ደግሞ አቶ መለስ ከላይ በንግግራቸው  እ ያሉትን አደጋ ዛሬ መልሶ የሚያመጣ ወይም ድላቸውን የሚቀለብስ አደጋ በገዛ ጓዶቻቸው መጥቶባቸዋል። በቦንድ ሽያጩ ትላልቅ ኢንደስትሪ ዞኖችን በማቋቋም ስም ትላልቅ የውጭ ኢንቨስተሮችን ጓዶቻቸው ወደ አገር ውስጥ እየጋበዙላቸው ነው። ምክንያቱም አቶ መለስ ያሉት እድገት አልመጣም። አገሪቷ በኢኮኖሚ ቀውስ ተዘፍቃ ከሌሎች ችግሮቿ ጋር አብጣ ልትፈነዳ ሰከንድ የምትቆጥር መስላለች…. በኢህአዲግ አመራሮች መካከል ይቅር እንጂ አቶ መለስም ድርጅታቸውንና አገሪቱን ከማይሆን ነገር ውስጥ ዘፍቀዋት ሄደዋል…. መወቃቀስ መያዛቸው ይሰማል። ቀጣዩ አቅጣጫ ይህ ሊሆን ይገባል አይገባም መባባላቸው እየተሰማ ነው። ክርክሩ ንትርክ ከንትርክም አልፎ የተካረረ መስመር እየያዘ መምጣቱ ይሰማል። ይህ ወደ ፖለቲካው ሽኩቻ አድጎ ወይም ሰበብ ሆኖ እንደ ኤርትራው ጦርነት ክፍፍል ዘመን ኢህአዴጎችን ለሁለት እንዳይከፍላቸው አስግቷል። ወይም አስጎምዥቷል። በሌላ አነጋገር አቶ መለስ ልክ ነበሩ ወይስ አልነበሩም ይከለሱ ወይስ አይከለሱ የሚል ትርጓሜ እየፈጠረ ይመስላል። የመለስ ራዕይ ወይም አስተምህሮ አራማጆችና አስጠባቂዎች ባንድ በኩል ከላሾችና ምንትስሊብራሎችየተባሉትደግሞ በሌላ በኩል ሆነው ለመወጋገዝ በተጠንቀቅ ሆነዋል። የክፍፍል ዓይነቱ ብዙ ነው። ፓርቲ ውስጥ ያሉትን የመንግሥት ሰዎች በአንድ በኩል መንግሥት ውስጥ የሌሉ የፓርቲ ሰዎችን ደግሞ በሌላ በኩል ማሰለፉም እየተሰማ ነው። ለዚህ ሁሉ የልማትና የትንራንስፎርሜሽን እቅዱ ዋነኛው መነጋገሪያ ወይም የመዋጊያ ሜዳ መስሏል። ሰበብ ሆኖ የሚያነጋግረው ይሄ የ 5 ዓመት እቅዱ ዋነኛው ይሁን እንጂ ከአቶ መለስ ሞት በኋላ እያደገ የመጣው መናናቅና ዓይን የሚሞላ ሰው በድርጅቱ አመራር ውስጥ አለመገኘት መሆኑም ይወራል። ሥልጣን የባለ ራዕዮች ስለሆነ የነበረውን ማስቀጠል ወይም አዲስ ራዕይ መውለድ ወቅቱ የጠየቀው ጥያቄ መስሏል። ይህ ሁሉ ተደማምሮ የመጀመሪያውን እቅድ አፈጻጸምን በመገምገምና በሁለተኛው ትራንስፎርሜሽን አስተቃቀድ ላይ አለመግባባት ደንቅሯል። በዚህ ጽሑፍ የምናየው እነዚህን ይሆናል። የገዢው ፓርቲ የኢህአዴግ ሥራ አስፈጻሚ አባላት በየዓመቱ የአገሪቱን አጠቃላይ የፖለቲካና ኢኮኖሚ አቅጣጫና ግብ አስመልክቶ ግምገማ ያደርጋሉ። በተለይ የአምስት ዓመቱን የልማትና የትራንስፎርሜሽን አፈጻጸም ይቃኛሉ። አሁን የአምስት ዓመቱ እቅድ ሰኔ ላይ አልቆ ሁለተኛው የአምስት ዓመት የልማትና የትራንስፎርሜሽን እቅድ ይፋ መደረግ ይጀምራል። በዚህም መሠረት ከወራት በፊት በጥቅምት 2007/ ኖቨምበር 2014 ላይ የኢህአዴግ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ መደበኛ ስብሰባውን አካሂዷል። በዚሁ ስብሰባ የመጀመሪያውን እቅድ ጉድለቶችና ችግሮች ገምግሞ በሁለተኛው የአምስት አመት የእድገትና ትራንስፎርሜሽን እቅድ መነሻ ማዕቀፍ ላይ ተወያይቶ የኢኮኖሚ መዋቅራዊ ለውጥ እንዲመጣ አዟል፡፡ የእቅዱ ዋናው ማጠንጠኛ አቅጣጫ የኢንዱስትሪያላዜሽን ትራንስፎርሜሽን ማረጋገጥ እንደሚሆን አስምሮበታል፡፡ ይሄ የኢንደስትሪያላዜሽን ትራንስፎርሜሽን ወይም የኢኮኖሚ መዋቅራዊ ለውጥ ጉዳይ “ዋነኛ” ሆኖ መውጣቱ በአቶ መለስ ብዙም የማይደገፍ አካሄድ መሆኑና አፈጻጸሙም ላይ ልዩነት መኖሩ ይታወቃል። የትራንስፎርሜሽኑ ምሶሶ ኢንደስትሪ መሆኑ በመርህ ደረጃ ተቀባይነት ቢኖረውም በኢንደስትሪ ዞን አመሠራረት ፖሊሲ ዙሪያ አሁን ያለው የኢህአዴግ አመራር ለሁለት ተከፍሏል። የኢንዱስትሪ ዞኖቹ የት የት አካባቢ ነው መቋቋም ያለባቸው መጠናቸውና አገልግሎታቸው እንዴት ይሆናል የፋይናንስ ድጋፉንስ ከየት ያገኛሉ በየትኞቹ የምርት ዓይነቶች ላይ ማተኮር አለባቸው እነዚህ ሁሉ ኢህአዴጎቹን ያስማሙ አልሆኑም። ለምሳሌ አንዳንዶቹ ኢንደስትሪያል ዞን (ፓርክ) ላይ ማተኮር አለብን ባዮች ናቸው። የሆነ አካባቢ ትልቅ ቦታ ተከልሎ የተንጣለለ መሬት ይሰጣል። ገንዘብ ይቀርባል። ባንኩ ታክሱ ሁሉ ነገር እዚያው ይጠናቀቃል። ልክ ሞጆ ላይ ለቻይኖቹ እንደሆነው ትልቅ ኢንደስትሪ ዞን ማለት ነው። እዚህኛው ላይ ጥያቄ የሚያነሱት አመራሮች እንደዚያ ያለ ትልቅ ዞን ሲቋቋም የአገር ባለሀብቶች አቅሙ አይኖራቸውም። እንደዚያ ያለ ካፒታል የሚኖራቸው የውጭ ኩባንያዎች ስለሆኑ አገር ቤት ያለው ባለሀብት እየቀነሰ ይመጣል። ያ ደግሞ እንደ ኬንያና መሰል አገሮች ኢንቨስትመንቱን የሚቆጣጠሩት የውጭ ኢንቨስተሮች ይሆናሉ። ይህ አገሪቱን አሳልፎ ለውጭ ባለሀብቶች የመክፈት ስለሆነ የኒዮ ሊብራሎች አስተሳሰብ ነው። ይህ ከኢህአዴግ መርህ፣ ከመለስ አስተምህሮ ጋር ይቃረናል። ስለዚህ እናንተ ካላሾች በራዦች (ሪቪዥኒስት) ናችሁ…. ባዮች ናቸው። ከሱ ይልቅ በትንናሽ መንደሮች (ሳተላይት) መካከለኛ ኢንደስትሪ ማቋቋም እንደሚሻል ይከራከራሉ። በየተወሰነው ትናንሽ ከተማ ትናንሽ የጎጆ ኢንደስትሪዎችን ብንቋቁም ይሻላል። ያቺ ለአካባቢው ነዋሪ የሥራ እድል ትፈጥራለች። አካባቢውም ለኢንደስትሪው የሚሆን ግብአት (ጥሬ እቃና የሰው ኃይል) በመስጠት ይደግፋል። ስለዚህ መደጋገፍ ይኖራል፡ ፡ ለትንንሽ መንደሮችና ከተሞች እንዲሁም ለገበሬዎች ትንሽ ትንሽ እየሰጡ ከተሠራ እነሱ እያደጉ ይመጡና በረጅም ጊዜ ሂደት ውስጥ ራሳቸውን ወደ ትላልቅ ኢንደስትሪዎች ማሳደግ ይችላሉ ባዮች ናቸው። ትራንስፎርሜሽን አብይ ዓላማው ገጠሬን ወደ ከተማ መለወጥ ግብርናን ወደ ኢንደስትሪ መቀየር ኤክስፖርት ላይ የተመሠረተ ምርት በማፍራት የአገሪቱን ገቢና የህዝቡን የኑሮ ደረጃ ማሻሻል የሚለው ሲናገሩት ቢጣፍጥም አብረው ሊሄዱ የሚችሉ የአመራርና የአስተዳደር ብቃት በቦታው አልተገኘም። የግል ባለሀብቱም ሚናው በግልጽ አልተመለከተም። አንደኛ ይህንን ህልም ሊደግፍ የሚችለው የግል ባለሀብቱ የፋይናንስ ድጋፍ ሊያገኝ የሚችልበት የብድርም ሆነ የፋይናንስ ምንጭ የለም። የአገር ውስጥ ባንኮች እንዳይበድሩ በመመሪያ ታስረዋል። እያንዳንዱ ባንክ የሚያበድረውን ብድር 27% ቦንድ እንዲገዛ ይገደዳል። ይህ ማለት ለግል ባለሀብቱ ሊያበድር ከሚችለው ገንዘብ ለቦንዱ ይከፍላል ማለት ነው። ስለዚህ ባንኮች ብዙ ባበደሩ ቁጥር ክፍያቸው እየመጨረ ይሄዳል፡፡ በመካከሉ ባለሀብቱ ገንዘብ አያገኝም። ለዚሁ ተብለው የተቋቋሙት እንደ ልማት ባንክ ያሉት የመንግሥት አበዳሪዎችም ቢሆኑ የባንኩ ኃላፊ ሰሞኑን እንደገለጹት ከሆነ መስፈርቱ ቀላል አይደለም። ለተመረጡ ዘርፎች ያውም ተበዳሪዎች ቢያንስ 30 ከመቶ የማዋጣት ኃላፊነት ይኖርባቸዋል። ከውጭ ባለሀብቶች ይልቅ የአገር ውስጥ ባለሀብቶች ጋር ሲስተያይ የአገር ውስጥ ባለሀብቶች ከባንኩ ብድር የማግኘት ተጠቃሚነታቸው ከመቶ ፐርሰንት ወደ 75 በመቶ እየወረደ መምጣቱም ተገልጿል። ይህም እያደገ ሄዶ ወደፊት አብዛኛውን የባንኩን ብድር የውጭ ባለሀብቶች ጠቅልለው ሊወስዱ የሚችሉበት አቅጣጫ ይታያል። ሌሎቹ ደግሞ ሲከራከሩ የፋይናንስ ምንጫችንን ከውጭ ቢሆን አፈላልገን እናገኛለን። ለዚህም መፍትሔ የተለያዩ የፋይናንስ ምንጮችን አፈላልጎ ማግኘት ነው እንጂ እንዲሁ በር ዘግቶ መቀመጥ አያዋጣንም ባዮች ናቸው። የቦንድ ሽያጩ ነገር የመጣው እዚህጋ ይመስላል።

መለስ ቢኖሩ ቦንዱ አይኖርም! መለስ እየሞቱ ነው! 
የመለስ ሌጋሲ አስጠባቂዎቹ አመራሮች እነ አቶ በረከት እና አባይ ፀሐዬ ቦንዱን በጥብቅ ተቃውመውታል። የቦንዱ ሽያጭ የፓርቲው ዶክመንት ከሚፈቅደው ውጭ አገሪቱን ለውጭ ኃይሎች በርግዶ መስጠት ነው። ለትላልቅ ፕሮጀክቶቻችን የአገር ውስጥ የፋይናንስ አማራጮችን ገና ተጠቅመንና ፈልገን አልጨረስንም። በኒዮ ሊብራሎች ኃይልና ግፊት ነው እዚህ ውስጥ የገባነው ብለው ያምናሉ። ቦንዱ ከኢህአዴግ እምነት ውጭ የተደረገ ፣ ሁሉንም ነገር ከፍቶ የመስጠት ኢኮኖሚውን ለውጭ ኃይላት የመክፈት የመጀመሪያው ዝንባሌና ምዕራፍ ነው። ነገ መለስ ተሟግቶ ያቆየውን ቴሌ ይሸጥ፣ ባንኮች ለውጭ ባለሀብቶች ባለቤትነት ክፍት ይሆኑ…የሚለው ክርክር ጅማሬ ነው ባዮች ናቸው። የእነዚህ ከፍተኛ አመራሮች ምሬት ስናይ ምናልባትም ወደፊት “ቦንድና ሉአላዊነት በኢትዮጵያ” የሚል መጽሐፍ በክፍፍል አፈንግጦ በሚወጣ ሌላ ባለሥልጣን እናነብ ይሆናል። ምክንያቱም ጨዋታውና መወነጃጀሉ ሁሉ እንደ ኢትዮ ኤርትራ ወቅት ክፍፍል ከላሽና ተቸካይ መባባልን እያመጣ ነው። ሌሎች ተንበርካኪ ይሏቸው የነበሩ ባለሥልጣናት አሁን ደግሞ በተራቸው ተንበርካኪ የሚባሉበት ሁኔታ የተፈጠረ ይመስላል። የክፍፍሉን ደረጃ አስገራሚ የሚያደርገው ሌላው ነገር ደግሞ የቦንዱ ሽያጭ ውሳኔ የተወሰነበትና ለህዝብ ይፋ የተደረገበት መንገድ ነው። ጠቅላይ ሚንስትር አቶ ኃ/ማርያም (ከአማካሪያቸው አቶ አርከበ ጋር) ቦንድ ሽያጭ የመግባቱን ውሳኔ ሲወስኑ የኢህአዴግን ሥራ አስፈጻሚ አልተነጋገረበትም። በመጀመሪያ በሚኒስትሮች ም/ቤት ተወሰነ። ከዚያ ወደ ፓርላማ ሄደ። ከፓርላማውም በፓርላማው ጠቅላላ (በአዳራሹ) ሳይሆን በኢኮኖሚ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ብቻ ነው የታየው። ይህን የሰሙት የፓርቲው የኢህአዴግ ሥራ አስፈጻሚ አባላት ተቆጡ። እነ ኃ/ማርያም ሥራ አስፈጻሚውን ሳታስፈቅዱ ለምን ገባችሁበት ተብለው ሲጠየቁ ፍርጥም ያለ ምላሽ ሰጡ። 1ኛ የኢህአዴግ ጽ/ቤት ሊነጋገር የሚገባበት ጉዳይ አይደለም። ሁለተኛ የመንግሥት ሚኒስትሮችና ፓርላማው ተነጋግሮበት ወስኗል። 3ኛ በዚያ ላይ የሚኒስትር ም/ቤት አባላትም ውስጥ ቢሆን የፓርቲው ሥራ አስፈጻሚ አባላት አሉ። ሁሉም የኢህአዴግ ሥራ አስፈጻሚዎች የሚኒስትሮች ም/ቤት አባል ባይሆኑም ከሞላ ጎደል ሁሉም ሚኒስትሮች ግን የፓርቲው ሥራ አስፈጻሚ አባላት ናቸው። የኢህአዴግ ሥራ አስፈጻሚ አባላት 60 ሲሆኑ የሚንስትሮች ም/ቤት አባላት ደግሞ 30 ናቸው። እዚህ ላይ አቶ ኃ/ማርያም ሥር የተጠለሉ የፓርቲው አንጃዎች (ከአቶ መለስ የተማሩትን) ጨዋታውን በሚገባ አውቀውታል። እንዲያውም ይባስ ብለው እንዴ ምን ማለት ነው? ምንስ ቢሆን እኛን እንዴት አታምኑንም? እዚያ ቦታ ስታስቀምጡን ከድርጅታችን ውጭ እንዴት ልንወስን እንችላለን በማለት ተቆጡ። ሆድ ሲያውቅ ዶሮ ማታ ሆነና እነዚያም እንዲሁ ይተዋወቃሉና ውስጣቸው እያረረ በሉ ላሁኑ ይሁን አሉ። እንደዚህ ዓይነት ነገር ግን ለወደፊቱ መደገም የለበትም ይህ ቀላል ውሳኔ አይደለም የድርጅቱን መርሆ የታላቁ መሪያችንን አስተምህሮ የሚቃቀረን ነው አባሎቻችንን ማረጋጋት ይኖርብናል ዓይነት ነገር ብለው ሂስ አስውጠው እንዳይደገም ማስጠንቃቂያ ሰጡ። ለዚህም ይመስላል አቶ ሱፍያን ወዲያው አደባባይ ወጡና ስለቦንዱ ስለሶቭሪን ቦንዱ መግለጫ ሰጡ። “ሶቭሪን ቦንድ መሸጥ ማለት የኢኮኖሚ ፖሊሲያችንን ቀይረናል ማለት አይደለም። ለሚቀጥለው ሶስትና አራት ዓመት ሌላ የቦንድ ሽያጭ አናወጣም” ብለው ተናገሩ። እዚህ ላይ ፖሊሲ ስለመቀየር አለመቀየር መናገርን ምን አመጣው? ቦንዱንስ የማይሸጡት ለምንድነው? ያቀርብነው ቦንድ የ1 ቢሊዮን ቢሆንም ያገኘነው ግን 2.5 ቢሊዮን ለመግዛት ፈቃደኛ የሆነ ገበያ ነው። ያህን ያህል ገበያ ካገኙ፣ ቦንዱም ያን ያህል ተፈላጊ ከሆነ፣ ለሚቀጥሉት ዓመታት አንሸጥም ማለትን ምን አመጣው? አይለመደንም እንደማለት ይመስላል። ይህ ዓይነት ልዩነትና መቀበጣጠር የኖረው ሁሉም መሪያችን ነው ብለው የሚያከበሩት ሰው ባለመኖሩ ነው። ሁሉም የሚያከበሩት መሪ (ግለሰብና) ድርጅት የሌለበት ሁኔታ ነው የሚታየው። አንዱ ላንዱ ያለው አክብሮት ጤነኛ አይመስልም። መጥፎ ስሜትም እያሳደሩ ነው። ይህ ከኢኮኖሚ ወጥቶ የፖለቲካ ጉዳይ የማይሆንበት ምክንያት የለም። እነዚህ ሰዎች ልዩነታቸውን ምን ያህል በሰለጠነ መንገድ ይፈታሉ? ከዚህ ገፍተው የሞትና የሽረት ትንቅንቅ (የሰርቫይቫል) ቢያደርጉና ቢሞክሩ ሁሉም ነገር ሌላ መልክ ይኖረዋል። እነ አርከበ/ኃይለማይርም የቦንዱን ውሳኔ ለብቻቸው ሲወስኑ ምክንያት ነበራቸው። ለምሳሌ ከአቶ መለስ ራዕይ የተለየው የኢንደስትሪያል ዞኑ ፖሊሲ ጉዳይ ሁለቴ ተጥሏል። ቦንዱን በራሳቸው ከወሰኑ በኋላ ለፓርቲው ማስረዳት የመረጡት በዚህ ምክንያት ነው። ይህንም ብናቀርብ ይጥሉብናል። ሰለዚህ ለራሳችን ለምን አናደርገውም የሚል ብልጠት መኖሩ ተነግሯል። በሌላ በኩል ከአቶ መለስ ራዕይ ጋር በተቸከሉትና በቻልነው ፍጥነት ተጠዳድፈን ካፈጠጠብን ቀውስ እውንጣ በሚሉት አባላት መካከል ፍትጊያ ቢርኖም ችግሩ በአንድና በሁለት የመከፈል ሳይሆን ቢያንስ ወደ ሶስት የሚጠጋ ቡድን መፈጠሩም ይሰማል። በረከት አዲሱ አባይ ፀሐዬ የመለስ ሌጋሲ እናስጠብቅ ባዮች ሆነው አንድ ቡድን ናቸው። አርከበ ዋነኛው ሆኖ ኃይለማርያም ሱፍያን ተክለወልድና ደብረፅዮን ደግሞ ሌላኛው ቡድን ሲሆኑ የማሻሻያ ለውጥ ያስፈልጋል ባዮች ናቸው። ጄኔራል የተባሉት እነ ሳሞራ የመለስ ራዕይ ከሚለው ውጭ ጉዳዩ ብዙም ስለማይገባቸው አገሪቱን በሥልጣን እያሳደረ ነው የሚባለው ሠራዊታቸው ከማንኛቸው ጋር እንደሚቆም ለመገመት ሳያዳግት አልቀረም። ገና እጅ ያልሰጡት እነወይዘሮ አዜብና ቀሪዎቹ የህወሓት ሥራ አስፈጻሚዎች ከሠራዊቱ ጋር ማንዣበባቸው ይሰማል። ይህ ጽሑፍ በዘኢትትዮጵያ ጋዜጣ ላይ ታትሞ ወጥቷል; ርዕሱን ግን እኛ ቀይረነዋል:: - See more at: http://www.zehabesha.com/amharic/archives/38861#sthash.G47tQsUP.dpuf

Sunday, August 23, 2015

አሸባሪነት ሲሉ – ያኔ እሰከ ዛሬ ታሪኩ አባዳማ

ላለፉት ሁለት አሰርት ዓመታት በላይ በወያኔ አገዛዝ ስር የጭካኔ በትር ሰለባ የሆኑ ሰላማዊ ዜጎች ቁጥር በቀላሉ የሚሰላ ባይሆንም እንበለ-ሕግ ሰብአዊ መብት ማዋረዱ መርገጡ ግን እነሆ እስከ ዛሬ አላባራም። በአዲስ አበባ የሚፈፀመውን ግፍ እና በደል ሳይውል ሳያድር በትኩሱ ለማወቅ ዕድል ቢኖርም በሌሎች የአገሪቱ ክልሎች በምስጢር እስር ቤቶች እየታጎሩ ፣ በየጉድባዎች እየተረሸኑ የሚገኙ ሰለማዊ ዜጎች እሪታቸው የገደል ማሚቶ መሆኑ ቀጥሏል። ዛሬም እሪሪሪሪ ተገፋሁ… የሚለው ኢትዮጵያዊ ድምፅ ከመቸውም ግዜ የበለጠ ጎልቶ እያስተጋባ ነው። ወያኔ ሆነ ብሎ በሚቀሰቅሰው የሀይማኖት እና የጎሳ አምባጓሮ ውድ ህይወታቸውን ያጡ ፣ ቤት ንብረታቸው የወደመ ፣ የተፈናቀሉ ምስኪን ዜጎች ቁጥር እያሻቀበ ነው። 
አሸብር ዜናዊ አስታቅፎን በሄደው ‘የሽብር ህግ’ መሰረት ፍፁም ሰላማዊ የሆኑ የእስልምና ሀይማኖት መሪዎች እስከ ሀያ ሁለት ዓመት በሚደርስ እስራት ፍርደኛ ተብለው የወህኒ ኑሯቸው መራዘሙ ለዚህ አንዱ ማሳያ ነው። ባለ ‘ራዕዩ መሪ’ ለገሰ ዜናዊ ያወረሰን የተወልን ሌገሲ። 
ትናንት ሆነ ዛሬ ትልቁ ወንጀል ‘ነፍጠኛ ፣ ትምክህተኛ ፣ ጠባብ ፣ አክራሪ’ ቢሆንም – እነ ፕሮፌሰር አስራት ወልደየስ ስማቸው ግን ጎልቶ ከማይታወቅ በሺህዎች ሚቆጠሩ ተከታዮቻቸው ጋር ውድ ዋጋ ከፍለውበት ሳያበቃ ዛሬም በየጉድባው አማሮች ፣ ኦሮሞዎች ፣ የጋምቤላ ክልል ዜጎች…ወዘተ እየታደኑ ነው። ከዚህ ጋር ተያይዞ ‘ህገ መንግስቱን በሀይል ለመናድ’ የተነሱ ተብለው የታሰሩ ፣ የተደበደቡ ፣ የተገደሉ እና ቤት ንብረታቸው የወደመ ዜጎች ቁጥር አሁንም በአሀዝ የሚገለፅ አይደለም። 
‘ፀረ-አሸባሪነት’ እንደ ‘ነፍጠኛ’ነት ሁሉ ለወያኔ ጎጣዊ እና ኢ-ሰብአዊ አገዛዝ አልመችም ያሉ ሰላማዊ ዜጎች የሚታደኑበት እና የሚመቱበት ከህጎች ሁሉ የበላይ ‘ህግ’ ሆኗል። ኢትዮጵያ የምትተዳደረው ደግሞ ህወሐት ራሱ ህግ በሆነባት አገር በመሆኑ ድርጅቱ አሸባሪ ወይንም ‘ነጭ ለባሽ’… ያለው ዜጋ ለምን እና እንዴት ተብሎ እንኳ ሳይጠየቅ በታማኝ ካድሬዎች ይመታል። 
በአገሪቱ ያለው አንድ ህግ ነው – እሱም መለስ ዜናዊ ፅፎት የሄደው የህወሐት ፕሮግራም ነው። ህግ ተብሎ የታወጀ ማናቸውም ደንብ ከህወሐት ፈቃድ እና ፍላጎት ውጭ ከሆነ ተፈፃሚ አይሆንም። የህወሐት ፕሮግራም ህግ በሆነበት ሌላ ህግ የለም። የይስሙላው ሰነድ እንደ ህገ መንግሰት ለህወሐት ፕሮግራም እና አላማ ጭንብል ከመሆን የዘለለ ፋይዳ የለውም። 
ለምሳሌ ይፋ በተፃፈው ህግ መሠረት “አንድ ተጠርጣሪ ወንጀለኛ መሆኑ በህጋዊ ፍርድ ቤት እስካልተረጋገጠ ድረስ ነፃ ነው” ቢልም ቅሉ በዚህ ስርዓት ህወሐቶች የጠረጠሩት ሁሉ ነፃ መሆኑ እስካልተረጋገጠ ደረስ ወንጀለኛ ነው። ህወሀት የጠረጠረውን ‘ነፃ’ ነህ ብሎ የሚያሰናብት ፍርድ ቤት ይኖራል ብሎ መጠበቅ ደግሞ ህወሐትን ጠንቅቆ ካለመገንዘብ የሚመነጭ የዋህ ግምት ከመሆን አይዘልም። ፍረድ ቤት ይፈታ ሲል ህወሐት በበኩሉ አልፈታም ማለት እንደሚችል ደጋግሞ አሳይቶናል። ከፍርድ ቤት ደጃፍ ዳግም እያዳፉ ይወስዱሀል። 
አንቀፅ 39 በግልፅ እንደሚደግገው ‘ብሔር ብሔረሰቦች የራሳቸውን ዕድል በራሳቸው የመወሰን መብት እስከ መገንጠል’ ይችላሉ ይላል። በዚህ አንቀፅ መሰረት የመገንጠል ጥያቄ ማንሳት በጣም ህጋዊ ነው። ይሁንና በተገንጣይነት የሚከሰሰው ኦነግ ዛሬ ‘አሸባሪ’ ተብሎ አባላቱ እና የተጠረጠሩ ኦሮሞዎች በሙሉ እየተጋዙ ፣ እተገደሉ ነው – ምክንያቱም የህጎች ሁሉ የበላይ የሆነው የህወሐት ፖሊሲ ኦነግ ‘አሸባሪ’ ነው ብሎ ስለፈረጀ 
ወያኔ አሸባሪዎች ብሎ ሲነሳ አንድ የሚገርመኝን ነገር ልጥቀስና ወደ ተነሳሁበት ልመልሳችሁ – በወያኔ መገናኛ አውታሮች ተደጋግሞ እንደሰማነው ሻ’ኣቢያ/ኤርትራ በኢትዮጵያ ውስጥ የማያቋርጥ ሁከት ለመቀስቀስ የአሸባሪነት ተግባር ይፈፅማል እየተባለ ነው። ይሁንና የወያኔ ፓርላማ አልቃይዳን እና አልሽባብን ጨምሮ ኦነግ ፣ ግንቦት 7 እና ኦብነግን ‘አሸባሪ’ ብሎ ‘ሲፈርጃቸው’ ሻ’ኣቢያን ግን ከቶ ስሙ በዚህ ዝርዝር ተራ እንዲጠቀስ አልፈለገም። ምክንያቱ ምን እንደሆነ ለመገንዘብ ካስፈለገ ህጉ ማለትም ህወሐት (እነ ስብሀት ነጋ) ስለ ሻአቢያ/ኤርትራ የሚሉትን መስማት ጠቃሚ ነው። ይህ ሀቅ ከፍ ሲል የተጠቀሰውን ህወሀት በኢትዮጵያ የፖለቲካ ህይወት ውስጥ የሚጫወተውን የፈላጭ ቆራጭነት ሚና በጉልህ የሚያመለክት ነው ብዬ አምናለሁ። 
በወያኔ ዘንድ ‘አሸባሪ’ የሚለውን መስፈርት ለማሟላት እንደ ሻ’ኣቢያ በግልፅ የጠላትነት ተግባር መፈፀም ብቻ በቂ አይደለም – ይልቁንም በአገሪቱ ውስጥ የህግ በላይነት ለዘለቄታው መስፈን ይገበዋል የሚሉ ሀይሎች ሁሉ ቀንደኛ አሸባሪ ናቸው። ምክንያቱም አካሄዳቸው በቀጥታ የወያኔን ተፈጥሮ የሚፃረር ነውና!!
ስለሆነም ወያኔ አሸባሪ ብሎ ዛሬ እንደ አውሬ የሚያሳድዳቸው ንፁሀን ዜጎች አብላጫውን ለሰብአዊ መብት መረጋገጥ በፅናት የቆሙ ጀግኖች ናቸው የምንለውም ለዚህ ነው። 
የወያኔ ካድሬ በ’ተጠረነፈው’ ፓርላማ ፊት ወይንም መገናኛ ብዙሀን ዘንድ ቀርቦ የተነፈሰው የጥላቻ ወገዛ ሁሉ እንደ ሕግ አንቀፅ ያገለግላል – በዚህም የተነሳ የወያኔ ’ፀረ-ሽብር’ ሰነድ ትርጉሙ እና አፈፃፀሙ አንዳች ወጥነት የሌለው – ይልቁንም የወያኔ ሹሞች በእጀ መናኛ ያሻቸውን የሚመትሩበት ፣ ባሻቸው ጊዜ የሚመዙት የበቀል በትር ነው። 
ጋዜጠኛ ውብሸት አሸባሪ ነው ፤ መምህር በቀለ ገርባ አሸባሪ ነበር ፤ አርቲስት ደበበ እሸቱም አሸባሪ ነበር ፤ ርዕዮት አለሙ ፣ እስክንድር ነጋም አሸባሪ ናቸው… በቃ። ‘ፀረ-አሸባሪ’ ህግ በመደንገጉ ብቻ የመብት ጥያቄ አንግቦ በፅናት መቆም በወያኔ አይን ከአሸባሪነት ተነጥሎ የሚታይበት ነገር የለም – መብት ረጋጩን ወያኔ እምቢ ለመብቴ ብሎ መሟገት አሸባሪነት ነው። የወያኔን ህግ አልባ የስልጣን ዘመን ለማሳጠር የሚደረግ ማናቸውም እርምጃ ‘አሸባሪነት’ ነው። 
ከፍ ሲል እንዳመለከትኩት ተቃዋሚ ፓርቲ በሙሉ በፀረ-አሸባሪ መነፅር እይታ radar ውስጥ ነው – ማለትም ተጠርጣሪ ነው… ስለዚህ ወንጀለኛ ነው። ነፃ ፕሬስ አሸባሪ ነው ፣ በነፃ መደራጀት አሸባሪነት ነው፣ ቦንድ አለመግዛት አሸባሪነት ነው ፣ ግንቦት ሰባት አሸባሪ ነው ፣ ኦነግ አሸባሪ ነው – እነኝህን ድርጅቶች የሚመለከት ዜና መዘገብ አሸባሪነት ነው ፣ የድርጅቶቹንም ሆነ የመሪዎቹን ስም ተሳስቶ እንኳ መጥራት አሸባሪነት ነው… በወያኔ ራዳር እይታ ይሄ ሁሉ ተጠርጣሪ በፍርድ ቤት ‘ነፃ’ መሆኑ እስኪረጋገጥ ወንጀለኛ ነው።
ነፃ ምርጫ ‘ሽብር’ ስለሚያስከትል ‘በጥርነፋ’ ቁጥጥር ስር ብቻ ይደረጋል – እናም 100% ድል አድርጎ ‘ከአሸባሪዎች’ የፀዳ ፣ ከተጠርጣሪ (ማለትም ወንጀለኛ) ‘የጠራ’ ፓርላማ ተመስርቷል። 
ወያኔ የኢትዮጵያን ህዝብ የመብት እና ነፃነት ጥያቄ ለማፈን ያዋጣኛል ብሎ የቀየሰው ስልት ‘በፀረ-አሸባሪ’ አዋጅ እንዲታጀብ የተደረገው ግን አለምክንያት እንዳልሆነ ብዙዎች ይረዳሉ ብዬ ገምታለሁ። በዲሞክረሲ ካባ ተከናንቦ ለመታየት የዞትር ምኞቱ በመሆኑ ‘ሽርክ’ ካደረገችው አሜሪካ ጋር ለመመሳሰል ብዙ ይመኛል። የአሜሪካ መንግስት ወያኔን ‘ሽርክ’ ያደረገው ለአሜሪካ ብሔራዊ ጥቅም ብሎ ሳይሆን ወያኔ ዲሞክራሲያዊ ስለሆነ እንዲመስል ለማመልከት ይታክታል – እንደ አሜሪካ ሁሉ ‘ፀረ-አሸባሪ’ ህግ በማውጣት ፣ አሸባሪዎችን በማሳደድ ፣ በማሰር ተባባሪ እና ዘላቂ ወዳጅ መሆኑን ለማስመስከር ይታክታል… ።
አሜሪካ ከአሸባሪዎች ሴራ ለመከላከል ስትል ሶስት ሺህ ዜጎቿን ከቀጠፈው የሴፕተምበር 11 አሸባሪዎች ጥቃት ማግስት ‘ፀረ-አሸባሪ’ ህግ አውጃለች። የህጉ አቢይ አላማ የመላውን ዓለም አገር ዜጎች ወይም ዕምነት ተከታዮች በማስጠጋት የምትታወቀው አሜሪካ በዚህ አጋጣሚ ሰርገው ሊያጠቋት የሚሹ ድርጅቶችን ሆነ ግለሰቦችን ለመከታተል የሚያግዝ ህጋዊ መሣሪያ አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ ነው። ህጉ የዜጎችን ደህንነት ለማረጋገጥ ሲባል በልዩ ሁኔታ እና የወንጀል ድርጊት ላይ ተፈፃሚ ከመሆን በስተቀር የአገሪቱን ህጎች ተክቶ የሚሰራ አይደለም። ያም ሆኖ አሻሚ ነው በሚል ብዙ ትችት የቀረበበት ሰነድ በመሆኑ አፈፃፀሙ እጅግ ብርቱ ጥንቃቄ ይደረግበታል -። 
በዚህ መካከል የምዕራቡ ዓለም በተለይም ደግሞ አሜሪካ ለፀጥታ አስጊ ናቸው ብላ የመዘገበቻቸውን አክራሪ እስላሞች እንቅስቃሴ ለመቆጣጠር ተባባሪ ትሻለች – ወያኔ ይህን የምዕራባውያን ስጋት ተንተርሶ የቅርብ ተባባሪ ሆኖ ቀርቧል። ተባባሪነቱን አንተርሶ ያወጣው ‘ፀረ-አሸባሪ’ ህግ ግን ላም ባልዋለበት ኩበት ለቀማ አይነት መሆኑን ድፍን አለም ያውቀዋል። 
እሩቅ ሳንሄድ አልቃይዳ አሜሪካ ላይ ጥቃት ማድረግ ሲጅምር ቦምብ ያፈነዳው ኬንያ እና ታንዛኒያ ርዕሰ ከተሞች ላይ በ1998 ኦገስት ነበር። ያ አሸባሪ ጥቃት በተፈፀመበት ቀን የዚህ ፅሁፍ አቅራቢ ናይሮቢ ነበርኩ። ሰሞኑን ደግሞ አንድ የወያኔ ተላላኪ እንደ ትኩስ ዜና ያንን ከአስራ ሰባት ዓመታት በፊት የደረሰ ጥቃት ሲዘግብ አስተውዬ ገረሞኛል። የፈራረሰ ግንብ እና በፊንጂ የቆሳሰሉ ሰዎችን በማሳየት ዜጎችን ለማስፈራራት የሚደረግ የሙያ ብቃት የነጠፈበት ሙከራ ነው። 
በመሰረቱ ኬኔያ እና ታንዛኒያ ላይ የተፈፀመው አሸባሪ ጥቃት የሚሰጠን ትምህርት አለ ከተባለ አንድ ነገር ብቻ ነው። እሱም ቢን ላደን ናይሮቢ ላይ ጥቃት ሲሰነዝር ኬንያ በውስጥ የፖለቲካ ውጥረት ስትታመስ መሆኑ። ተቀዋሚዎች ገዢውን ካኑ ፓርቲ ከስልጣን ለማውረድ ጠንካራ እንቅስቃሴ የሚያደርጉበት ወቅት ነበር። ይሁንና ገዢው ፓርቲ አጋጣሚውን ተጠቅሞ ተቃዋሚን ለማዳከም ሲል ‘ፀረ-አሸባሪ’ ቅብጥርሴ የሚባል ህግ አላወጣም። አሸባሪዎች በአገር ጥቅም ላይ የሚነሱ እንደመሆናቸው ሁሉም ዜጋ አገሩን ለመከላከል እኩል ሀላፊነት እንዳለበት በማመልከት ጉዳዩ በጥንቃቄ እንዲያዝ ተደረገ። 
በወቅቱ ስልጣን ላይ የነበሩት ዳንኤል አራፕ ሞይ ተቀናቃኞቻቸውን ፀጥ ለማሰኘት መልካም አጋጠሚ ነው ብለው አዋጅ ለማውጣት አልተጣደፉም። ይህ ከቶ ሊሆን ያልቻለበት አቢይ ምክንያት ደግሞ አገሪቱ በማይናቅ ደረጃ የህግ የበላይነት ያለበት በመሆኑ ነው። ጦር ሀይሉ እና የፍትህ ስርዓቱ ከፖለቲካ ፓርቲ ታማኝነት የላቀ ነፃና ብሔራዊ ቅርፅ የያዘ በመሆኑ ነው። የቢን ላደን አሸባሪ ቀጥተኛ ጥቃት ሰለባ የሆኑት ኬንያ እና ታንዛንያ ብዙ ዜጎቻቸው በጠራራ ፀሀይ ሲያልቁ እንኳ ነባር ህጋቸውን መሰረት ያደረገ ይፋዊ ክትትል እና እርምጃ ከመውሰድ በስተቀር ‘ፀረ-አሸባሪ’ የሚል አዋጅ በማርቀቅ ድብቅ እና በቀል የተላበሰ እንቅስቃሴ ለማድረግ አልዳዳቸውም – ለዜጎች ደህንነት በፅናት መቆም ይሏል ያ ነው። 
አርብ ኤፕሪል 10 2015 Mwaura Samora የተባለ ታዋቂ ኬንያዊ ጋዜጠኛ. Kenya can’t, won’t be Ethiopia በሚል ርዕስ ፅፎ እንዳነበብነው “አልሽባብ ኢትዮጵያ ውስጥ ጥቃት ማድረስ ያልፈለገው አገሪቱ ከላይ እስከታች ባንድ የፖለቲካ ድርጅት ስር በስለላ ሰንሰለት ተቆልፋ መፈናፈኛ ስላጣች ነው” ብሏል። በተዘዋዋሪ ማውራ የሚለው – ኢትዮጵያውያን ቀድሞውኑ በአሸባሪ መንግስት መዳፍ እና ቁጥጥር ስር ስለሚገኙ ሌላ ተቀናቃኝ አሸባሪ አያነጣጥርባቸውም ነው። ዝርዝሩን ለማየት www.standardmedia.co.ke/article/…/kenya-can-t-won-t-be-ethiopia እዚህ ይጫኑ። ብዙ ወያኔዎችን ያንጫጫ ዘገባ ነበር። በነገራችሁ ላይ ማውራ በናይሮቢ ዩንቨርሲቲ ድህረ-ምረቃ ህንጻ ጎረቤቴ ሆኖ ለሁለት ዓመታት ያህል በቅርብ የማውቀው ጠንካራ ሰው ነው። ማውራ ሙያህን በሀላፊነት ስለምትወጣ thank you, I have a T-shirt that says this. As a journalist, I know it is true 
አሜሪካ አሸባሪ ብላ የምትከታተላቸው ግለሰቦች የሚኖሩት አንድም በቶራቦራ ተራራ አለበለዚያም በየመን ብሎም በፓኪስታንና ሶማሊያ አሸምቀው ወይንም በተለያዩ አገሮች ስማቸውን ቀይረው ፣ የውሸት ፓስፖርት ይዘው በስጋት እና በጥንቃቄ ነው። አክራሪዋች የሚከተሉት ፀረ-አሜሪካ ጥላቻ አለም አቀፋዊ ባህሪ ቅርፅ እንዲይዝ እና ምዕራባውያን ዲሞክራሲያዊ አገሮች ሁሉ የጥላቻው እና የጥቃት ኢላማ እንዲሆኑ ይፈልጋሉ። የነኝህ አገሮች ቡችሎች ናቸው የሚሏቸውን ድሀ አገሮችም ከማጥቃት እንደማይመለሱ አሳይተዋል። 
ቢንላደን ፓኪስታን ተሸሽጎ ይኖርበት ከነበረው የተንጣለለ ቪላ ድረስ በማሳደድ እንዲወገድ መደረጉን እናውቃለን። የሚኖርበትን ስፍራ ለማወቅ ዘጠኝ ዓመታት የፈጀ ጥብቅ ክትትል ተደርጓል። ይሁንና ቢንላደን እንደ ጠላት ጦር መሪነቱ አገዳደሉ ፍትሀዊ ነበር ወይ ብለው የሚጠይቁ እና የሚሟገቱ የህግ ባለሙያዎች አሜሪካ ውስጥ አሉ። የህግ የበላይነት አለመጣሱን እየመረመሩ ነው። 
አንድ የጠላት ጦር መሪ እጁ ላይ የጦር መሳሪያ ሳይኖር እና በወገን ላይ ተኩሶ አደጋ ለማድረስ ማነጣጠሩ ሳይረጋገጥ እንዲገደል ማድረግ በአሜሪካ ሆነ በአለም አቀፍ ህግ ያስጠይቃል በሚል የቢንላደንን አገዳደል የሚያጣይቁ ብዙ ናቸው። ከዚህ በመነሳት ለመሆኑ ቢንላደን ላይ ለመተኮስ የሚያበቃ በቂ አስገዳጅ ሁኔታ ነበር ወይ – ማርኮ ወይንም በቁጥጥር ስር አውሎ ለፍርድ ማቅረብ ለምን አልተሞከረም ይላሉ። እንግዲህ አስቡት ቢንላደን ለምን በህጋዊ ፍርድ ቤት ቀርቦ ይፋ በተጠራ ችሎት ጉዳዩ አልታየም ብለው የሚንገበገቡ ለህግ የበላይነት ያለማወላወል የተሰለፉ አሉ… አሜሪካ ለዚህ አይነቱ አቋም መኖር ዋስትና የሚሰጥ ህግ ያለበት አገር ነው። ታዲያ ሰሞኑን ብርሀኑ ነጋ አሜሪካ ተመልሶ እንዳይገባ ለማስወሰን ውጪ ጉዳይ ቢሮ ደጅ የሚጠኑ ታጋዮች መኖራቸውን ስሰማ በሳቅ ፈንድቼ ነበር። 
በዳበረው የምዕራብ ዲሞክራሲ ዜጎች ካለ አንዳች ስጋት በነፃ ሀሳባቸውን የሚገልፁበት ፣ የሚፅፉበት ፣ የሚደራጁበት ፣ የፖለቲካ ዕምነታቸውን አለ አንዳች መሸማቀቅ የሚያራምዱበት ነው። በአጭሩ ሰብአዊ ክብር በህግ የበላይነት በማያሻማ መንገድ የተረጋገጠበት ሥርዓት ነው። ሀይማኖት ፣ ዘር ፣ የቆዳ ቀለም ፣ ፆታ ወይንም ፆታዊ ዝንባሌ ሌላውን የማግለያ መሣሪያ የማይደረግበት ህግ አለ። ህግ ሲጣስ ይፋዊ ተጠያቂነት አለ። ስለሆነም አሜሪካ እና ምዕራባውያን ላይ ያነጣጠረው አሸባሪነት በዲሞክረሲ እና በነፃ አኗኗር ላይ የታወጀ የሀይማኖት አክራሪዎች ጥቃት ነው የሚባለው ለዚሁ ይመስለኛል።
ለአሜሪካ መንግስት አሸባሪ ማለት የአሜሪካንን ህልውና ፣ ዲሞክራሲያዊ ተቋማት እና አኗኗር ለማደፍረስ በሰላማዊ ህዝብ ኢላማ ላይ ጥቃት ለመፈፀም የተሰለፈ ሀይል ነው። አሜሪካንን ለመምሰል የሚንደፋደፈው ወያኔ አሸባሪ ብሎ የሚያሳድዳቸው ዜጎች… እነ ብርሀኑ ነጋ የሚያነሱት መሰረታዊ ጥያቄ የአሜሪካ መንግስትና የመንግስታቱ ድርጅት የቆሙለትን የሰብአዊ መብት ድንጋጌ የሚያንፀባርቅ ነው። 
አሜሪካ እና ወያኔ በፀረ ሽብር አቋም ተባባሪ ናቸው ይባል እንጂ ስለ አሸባሪ እና ሽብር እንዲሁም ሽብረተኞች ያላቸው ትርጉም የሰማይ እና ምድር ያህል ልዩነት አለው። በመሠረቱ ትብብሩ አሜሪካ ስጋት አለ ብላ በምትገምተው የሶማልያ እና መካከለኛው ምሥራቅ አካባቢ ቅርብ ክትትል ለማድረግ እንድትችል ነዳጅ እና ስንቅ ማከማቻ ለመሻት እንጂ ለዋሽንግተን ከዚያ የዘለለ ትርጉም የለውም – ትብብሩ በተመሳሳይ አመለካከት እና አቻ ግንኙነት ላይ የተመሠረተ ቢሆን ኖሮ ወያኔ አሸባሪ ያለውን አሜሪካ አክብሮ ማስተናገድ ባልቻለ ነበር። ወያኔ ይህን ትብብር በአገር ውስጥ የሚነሱ ፍትሀዊ እና ሰብአዊ መብት ጥያቄዎች ለመጨፍለቅ ሲል የሚጠቀምበት መሆኑ ለአሜሪካ ሚስጥር አይደለም። 
ግልፅነት እና ተጠያቂነት የማዕዘን ድንጋይ በሆነባት አሜሪካ የፖለቲካ መስመሬን አልተቀበለም ተብሎ በአሸባሪነት የሚፈረጅ ድርጅት ወይም ዜጋ የለም – ‘ቲ ፓርቲ’ የተሰኘው አክራሪ የሪፐብሊካን አንጃ የኦባማን አስተዳደር ጥላሸት በመቀባት እና ዘረኛ ቅስቀሳ በማድረግ ላይ መሆኑን ሁላችንም እናውቃለን። ህገ መንግስታዊ መብታቸው ነው ተብሎ በፈለጉት ቦታ ስብሰባ ጠርተው ያሻቸውን ቅስቀሳ ያደርጋሉ። በድርጅትነት አልተመዘገቡም ፣ አሸባሪ ናቸው ብሎ የጠየቃቸው የለም – ይሄ ነው ሰፊው ልዩነት። 
ወያኔ አሸባሪ ብሎ የሚያስራቸው ወይም የሚያሳድዳቸው ኢትዮጵያውያን በአገራቸው ለመኖር ወስነው ነገር ግን ሰብአዊ ክብራቸው በህግ የበላይነት እንዲረጋገጥ ብሎም በትግል የተሻለ የፖለቲካ አመራር እናመጣለን ብለው የቆሙ ናቸው። ወያኔ ‘አሸባሪ’ ብሎ የፈረጃቸው በውጭ የሚንቀሳቀሱ ድርጅቶች ደግሞ በምዕራብ አገሮች ይፋ በከፈቱት ፅ/ቤት እና አድራሻ መሆኑን እናውቃለን። እነ ብርሀኑ ነጋ አሜሪካ ውስጥ አንቱ ተብለው ክብር እና ሞገስ ያለው የጥበብ ሥራ መስክ ላይ ተሰማርተው ህጋዊ እና ይፋ የሆነ ህይወት ይኖራሉ። ብርሀኑ ነጋ አሜሪካ ብቻ ሳይሆን ወደ ፈለገው የዓለም ክፍል በፈለገ ግዜ በይፋ መንቀሳቀስ የሚችል ‘አሸባሪ’ በሚል ክስ ግን ወያኔ ሞት የፈረደበት ወይም የፈረጀው ኢትዮጵያዊ ነው። ብርሀኑ ነጋ – ቶራቦራ አልተደበቀም ወይም እንደ አሸባሪ ሸሽጉኝ ፣ መታወቂያዬን ደልዙ ሲል አልታየም። 
እስቲ ገምቱት ወያኔ እና አሜሪካ በፀረ-ሽብር ሽርክና መስርተዋል። አሜሪካ አሸባሪ ያለችው ግለሰብ ወይንም ድርጅት በየትኛውም የአለም ክፍል ቢሸሸግ (ኢትዮጵያን ጨምሮ) መኖሩ ሲደረስበት ፈጣን እርምጃ ይወሰድበታል። ወያኔ አሸባሪ ያለው ግለሰብ/ቦች እና ድርጅት/ቶች ግን ዋና ፅህፈት ቤታቸው ሳይቀር በይፋ አሜሪካ እና በተለያዩ አውሮፓ አገሮች ነው። የድርጅቶቹ መሪዎች በአሜሪካ እና አውሮፓ በነፃ እና ህጋዊ በሆነ ሰነድ ይንቀሳቀሳሉ ፣ ሰርተው ማደር ብቻ ሳይሆን ለድርጅቶቻቸው ድጋፍ ለማሰባሰብ ቅስቀሳ ያካሂዳሉ ፣ ስብሰባ ይጠራሉ ፣ አላማቸውን በይፋ ያስተዋውቃሉ ፣ ድጋፍ ያሰባስባሉ። ወያኔ የሚያላግጥበትን ‘ህገ-መንግስት’ በሀይል መናድ አስፈላጊ መሆኑን ፣ ጭምብሉን ከስክሶ መጣል ተገቢ መሆኑን ጭምር በይፋ ያስተምራሉ – ፍትሀዊ ጥያቄ መሆኑንም ይሰብካሉ። 
በዓለም ውስጥ ተፎካካሪ የፖለቲካ ሀይል አሸባሪ የሆነባት ብቸኛዋ አገር የወያኔይቱ ኢትዮጵያ ናት። ትናንት ሆነ ዛሬ የዜጎች ትልቁ ወንጀል በህግ የበላይነት ካልሆነ በግለሰቦች እና በቡድኖች ፈቃድ አንገዛም ማለታቸው ነው። የህግ በላይነት ደግሞ በፎቆች ርዝመት ፣ በባቡር መስመሮች ስርጭት ፣ በግድቦች ስፋት የሚለካ የሚተካም አይደለም። የህግ በላይነት እስኪረጋገጥ ፣ ህዝብ የፈቀደው የፖለቲካ ሀይል ስልጣን የሚይዝበት እና የሚወርድበት አግባብ እስኪሰፍን እስከ መጨረሻዋ ደቂቃ ድረስ ለመታገል ቆርጠው ለተሰለፉ ክብር ይሁን። 
As a journalist, I know it is true.

ቄሱም ዝም መጽሐፉም ዝም (ፍኖተ ዴሞክራሲ) Efdpu@aol.com www.Finote.org

ፍኖተ ዴሞክራሲ የኢትዮጵያ አንድነት ድምጽ
Finote Democracy Voice of Ethiopian Unity
Efdpu@aol.com www.Finote.org
የፍኖተ ዴሞክራሲ የኢትዮጵያ አንድነት ድምጽ ሀተታ ነሐሴ 12 ቀን 2007 .. የተላለፈ
ቄሱም ዝም መጽሐፉም ዝም
ነሐሴ 2007 ዓም
page1image4440 page1image4600 page1image4760
አዳዲስ ኃስብ ማመንጨት የተሳነው ኅብረተስብ፤ ሁል ጊዜ በቆየውና ባሮጌው ጉዳይ ላይ ሲያመነዥግ ጊዜውን ያሳልፋል። ያንኑ በመደጋግም ፤ እያዘዋወረ፤ እያፍተለተለና እያውጠነጠነ ከመኖር የተሻለ አዲስ
ኃሳብ ለማምጣት አልታደለም ። አሮጌውን በመቀባበል ብቻ የሚረካ ኅብረተሰብ፤ " እልፍ ሲሉ ዕልፍ
እንደሚገኝ " እንኳን አይገነዘብም ። በልተውና ጠጥተው ከተገለገሉበት በኋላ እንደገና ለመገልገል
የሚፈልጉትን የወረቀት ሳህንና ዋንጫ ( Recicle/ ሪሳይክል ) እያዟዟሩ መኖር፤ የፈጠራ ክኅሎትን አያበረታታም ።
አባቶችና እናቶች ባስመዘገቡት ታሪክ ብቻ እየተኮራሩ መኖር ፤ የትም እንዳላደረሰን፤ አሁን የወደቅንበት ሁኔታ በቂ ማስረጃ ሆኖብናል ። ይህ ትውልድ፤ የራሱን ችግር አስወግዶ፤ መፃዒ ዕድሉን የሚያመቻች ተግባር መፈፀም ካልቻለ፤ የአምባገነኖች ሰለባ መሆን ብቻ ሳይሆን፤ በድኅነት አረንቋ ውስጥ ተዘፍቆም ይኖራል። የዓለም ኅብረተስብ መሳቂያ መሳለቂያ ከመሆንም አይድንም። የሀገራችንም ዕድል፤ ተስፋው ብርሃን አይገኝም። ዝም አይነቅስም በመሆኑ፤ ሁሉን በዝምታ ማሳለፍ ተመርጧል ።
ሻዓቢያ ፤ በሠላም የተደላደለ ኑሮ ሲኖር የነበረውን ሕዝብ ለአመፅ እንዲነሳ የቀሰቀሰበት መፍክር ፤
" ባህላይ አይትኹን ነዐይ ይጥዐመኒ ! " እኔን ይጣመኝ ባይ አትሁን ። የሚል እንደነበር እናውቃለን ።
በሀገራችን ዛሬ ስንቱ የጣመ ኑሮ እንደሚኖር ግን አናውቅም ። በመሆኑም፤ " ኑሮ፤ ጥሞኛል አትበል " ማለት አንችልም። ደስተኛ እንዳልሆነ ግን እንገነዘባለን ።
ሀገራችን ዛሬ ፤ በአስቸጋሪ ሥነልቦና ውስጥ ስለምትኖር፤ ሰው ማፍራት፤ መሪ ማውጣት፤ ሀገር ወዳድ ዜጋ መፍጠር ፤ ሕዝብ አፍቃሪ ዐርበኛ ማብቀል፤ አልተቻላትም ። አዳዲስ ሰው ማውጣቱ ቀርቶ፤ ያሉንን
አዋቂዎችና ሀገር ወዳድ ታጋዮችንን እንኳ በተገቢው መንገድ ይዘን- አቅፈን -ደግፈን ልንጠቀምባቸው አልቻልንም። ይህንን ሃቅ እያንገፈገፈንም ቢሆን ልንቀበለው ይገባናል ። ምናልባት ይህንን መራራ ዕውነት መቀበል ብንችል፤ ፈጣን የአስተሳሰብ ለውጥ አምጥተን የሀገራችንን ሁኔታ ለመቀየር የሚያስችለንን
ተዐምር ሥራ መስራት በቻልን ነበር። ሁሉም ነገር፤ ነበር ሆኖ እንዳይቀር ከፈልግን ፤ ይቻላል ! ይሆናል ! 1
ይሳካል ! በሚለው ላይ ማተኮሩ ይሻለናል ። ያለዚያ፤ ላለፈው ክረምት ቤት መስራት ይሆንብናል ። ይህ ደግሞ፤
" የነበር ሲወጋ ይመስላል ያልነበር ፤ ያባታችን ጋሻ ጦር ይመክት ነበር። "
የሚል ባህላዊ ስንኝ ከመስማት የተሻለ ርባን አያስገኝም ! አዲስ ራዕይ አያመጣም ! ተስፋ መቁረጥ፤ ዙሪያ- ገደሉ የጨለመበት ኅብረ-ተስብ ነፀብራቅ ነው ለማለት ቢቻልም እንኳ፤ እንደ ከዋክብት ብሩኅ ተስፋን
የሚፈነጥቁ ባለ ራዕይ ዜጎች ብቅ ብቅ ማለታቸው ግን አይቀርም ። ሀገሪቱ፤ ምንጊዜም ቢሆን፤ የወላድ መካን ሆና አታውቅም ! ወደፊትም አትሆንም !
በዛሬይቱ ኢትዮጵያ ፤ በርካታ አዳዲስ ጽሀፍት በቅ ብቅ እያሉ በመውጣት ላይ ናቸው እየተባለ ይነገራል ። የአንዳንዶቹ ድርሰትም፤ ድንቅ ወደሚያሰኛቸው ተረተር እየወጣ እንደሀነ ከአንባባያን ከሚሰጡት አስተያየት መገንዝብ ተችሏል ። ይህ ተስፋ ሰጭና አበርታች ዜና ሆኗል ። ደራሲያኑን በበለጠ ሊያበረታቱ ከሚችሉት አንዱ፤ የአንባብያን መበርከት እንደሆነ ቢታሰብም፤ የዴሞክራሲ መብቶች ያለገደብ መከበር ግን ዓይነተኛውና መሠረታዊ ነው። ዴሞክራሲን፤ የወያኔ ዳፍንት አገዛዝ ባዳፈነበት ሀገር፤ ሃሳብን በነፃ የመግለጽ ዕድል የሚታሰብ ባይሆንም ቅሉ፤ ማናኛውንም አደጋ በመቋቋም የተቻላቸውን ያህል የሚሞክሩትን ደራሲያን ማበረታታትና መደገፍ የነፃነት ትግሉን ያጎለብተዋል ። ነፃነትን የቀመሰ ደግሞ በቅምሻ ብቻ
አይረካም ። ለበለጠ ነፃነት ይታገላል !
ነፃ ኃሳብን የመግለጽና የማካፈል ነፃነት በታፈነበት ሀገር፤ ደራሲያንም ሆኑ አንባብያን ሊኖሩ አይችሉም ። ደራሲያኑ በኅቡዕ ( በቀድሞ ምስራቅ አውሮፓ፤ በአፍሪካ፤ በአስያና በላቲን አሜሪካ ሀገራት እንደታየው)
ሊጽፉ ቢችሉም እንኳን፤ አንባባቢያን ከሌሉ፤ ዕውቀት ተድፍኖ ይቀራል። የሥነ ፅሁፍ መምህራን እንደሚያስተምሩት ደግሞ፤ መስማትንና ማንበብን፤ መናገርንና መጻፍን አቻ ለአቻ አድርገው ያስቀምጡታል ። ካልሰማህ አትናገርም፤ ካላነብብክ አትጽፍም የሚል መልዕክት ለማስተላለፍ ይመስላል ።
አዲሱ ትውልድ ማነኛውንም ችግር ሁሉ እየተቋቋመ አዕምሮውን በንባብ ፤ ማጎልበትና ማበልፀግ ይጠበቅበታል። ሀገር የምትገነባው በበለፀገ አዕምሮ ብርታትና ጉልበት መሆኑ፤ ዋቤ ጥቀሱ
የሚባለበት አይደለም ። " ያላነበበ አይፅፍም ፤ ያላዳመጠ አይናገርም " ነውና ፤ አዲሱ ትውልድ፤ የመጽሐፍ ቀበኛ የድንቁርና መጋኛና ደመኛ ከሆነ፤ የነገዋ ኢትዮጵያ፤ ባለ ራዕይ ዜጎች የሞሉባት ሀገር ትሆናለች።
ራዕይን አንግቦ የሚራመድ ትውልድ ለሀገር/ ለወገን የተስፋ ብርሃን ሰጭ ይሆናል ። ባለ ራዕይ መሪዎችንም
ለማፍራት ዕድል ያገኛል ። የሠለጠነ የሰው ኃይል ምንጮች፤ ትምትህርት/ንባብ/ መፃህፍት ናቸው። ደራሲያንን የሚያበረታታና የሚያበረክት የአንባቢ ብዛትና ትጋት እንደመሆኑ፤ ደራሲያንና አንባብያን አቅኝና ሸማች በመሆን ከተባበሩ ፤ ሀገሪቱ የሊህቃን- የምሁራን- የጠቢባን- ማዕከል ትሆናለች ።
2
በአንፃሩ፤ ኢትዮጵያ፤ ደናቁርት መሪዎች ፤ በላዒ-ስብ ጉግማንጉጎች፤ ፍርደ- ገምድል ጲላጦሶችና ከሃዲያን ይሁዳዎች ፤ የሚጫወቱባት ሀገር ልትሆን አትችልም ።
የራሷ ፊደላት- ልሣናት፤ ስንክሳር- መዛግብት፤ መፃፍት- ሊቃውንት ፤ ዜማና ሙዚቃ፤ ለደስታው
እስክስታ፤ ለሀዘኑ እርግዶ፤ ለሰርጉ ዳንኪራ ፤ ለውጊያው ቀረርቶ፤ ለጦርነቱ ፤ ነጋሪት- ዕምቢልታ ፤ የሀገራችን ጠበብና ሥልጣኔ ቅርስ ሆነው ቆይተዋል ። ሁሉም ሲጠቃለሉ፤ የሀገራችን ሥልጣኔ ድምር ውጤት ነበሩ፡፡ አሁንም ናቸው ። የዚህ ታሪክና ሥልጣኔ ባለቤት የሆነ ሕዝብ ራዕይ ያለው መሪ፤ ሊያወጣ
ይገባው ነበር ። ያ ግን አልሆነም ። እየመጣ የሚሄደው " መሪ" ሁሉ ፤ ለነገ ራዕይ ስላልነበረው፤ "የኋላ ልጅ ይጨነቅበት ! " ብሎ ይጠፋል ። እዳው ለተተኪው ትውልድ ይተርፋል ።
" የወለዱትን የማይስሙለት፤ የጻፉትን የማያነቡለት፤ የደገሱትን የማይበሉለት " ኅብረተሰብ፤ እንደ ዉለታ ቢስ ይቆጠራል ። የደራሲያን መኖር አንባብያንን ካላፈራ፤ አንባቢውም፤ የደራሲያኑን ዋጋና ጥቅም ካልተረዳ ፤ ዕውቀትና ጥበብ ተለያይተው ይቀራሉ። የሁሉም ቆልፍ ጥያቄ ግን ፤ የዴሞክራሲ ሥርዓት መስፈን መሆኑ የሚያከራክር አይደለም ። የዴሞክራሲ አስተዳደር ከሌለ ደግሞ ምኞቱና ተስፋው ሁሉ፤
የበረሃ ንብልብሊት ( The Desert Mirage ) ሆኖ ይቀራል ።
ዛሬ በሀገራችን የዴሞክራሲ መብት ቀርቶ፤ ጭላንጭሉ እንዃን ደብዛው ጠፍቷል። በቅርቡ ኢትዮጵያን የጎበኙ አንድ የውጭ ሀገር መሪ፤ ወያኔ የቀለደበትን ምርጫ ፤ " ዴሚክራሲያዊ ነው " ማለታቸው፤ እኛን ኢትዮጵያውያንን ቀርቶ፤ መላውን ዓለም አስገርሞታል ። እኝህ ሰው፤ ያሻቸውን ለመናገር የራሳቸው ጉዳይ ቢሆንም፤ የሕዝባችንን የማሰብ ችሎታ፤ ( Intelligence ) መናቃቸው ግን አናድዶናል ። በማያውቁትና ባልተረዱት የሀገራችን ጉዳይ መግባታቸው ትዝብት ላይ ጥሏቸዋል ።
የፕሬዝደንቱን ምፀት ፤ " የዐይጥ ምስክር ድንቢጥ " ነች ከሚለው ብሂል በላይ አሻግረን ልናስብበት
ይገባናል ። በሀገራችን ዛሬ፤ የመጻፍና ሃሳብንም በአደባባይ በነፃ የመግለፅ መብት እንደሌለ እያወቅን፤
ማንም አልፎ- ሃጅ መጥቶ ሊያታልለን መሞከሩ ባልተገባው ነበር ። ኢትዮጵያውያን " ብኩርናቸውን
በጭብጥ ምስር መለወጥ " ልምድ ስለሌላቸው፤ ነፃነታቸውን የሚግፍፍ ርዳታ፤ በአፍንጫችን ይውጣ
ባዮች ናቸው። ኩራት ራት ነውና፤ አዋርዶ ከሚመጣ ርዳታ፤ ሽህ ጊዜ ነፃነትን ከድህነት ጋር መምረጥ ይበልጣል ።
ማንም ባዕድ ኢትዮጵያን እንዲወድ ባይጠበቅም፤ የህዝቡን የማሰብ ችሎታ ግን ሊፈታተን አይገባውም ። አይፈቀድለትምም ! ባዕዳኑ ባይወዱንም እንኳ ሊጠሉን ባልተገባቸውም ነበር ። " እንኳን ሲሸጡኝ ሲስማሙብኝ " አውቃለሁ እንዲሉ፤ ማንም ሲያስነጥሰው፤ ጉንፋን ከማያዙ በፊት የምንረዳ ሕዝቦች ነን ።
3
በባኅላዊ ልምድ ላይ የተመሰረተ ህይወት መምራት በራሱ ፤ አዲስ ኃሳብን ለማፍለቅ እንቅፋት ሊሆን እንዳማይችል፤ ታሪካቸውን አክብረውና ባኅላቸውን ጠብቀው በሥልጣኔ የተራመዱ በርካታ ህዝቦች እንደ አርዓያ ይጠቀሳሉ ። በአካባቢያቸው የዴሞክራሲ ተምሰሌት ናቸው ተብሎ የሚነገርላቸው፤ ሕንድና ጃፓን እንደ ማስረጃ ይቀርባሉ ። ሁለቱም በዕድገት ደረጃ፤ የት እንደ ደረሱ ሁሉም የሚያውቀው ሃቅ ነው ።
የጃፓንን የሥልጣኔ ዕድገትና ርምጃ ቀደም ብለው የተገነዘቡ ኢትዮጵያውያን ምሁራን ከጃፓኖች ተመክሮ፤ ብዙ ጠቃሚ ብልሃቶች እንደሚገኙ መናገራቸው ተደጋግሞ ሲነገር እንደነበር ይታወቃል። ጃፓንን እንደ ሞዴል ለማየት አስፈላጊ የነበረው፤ ባህሏንና ታሪኳን ጠብቃ ፤ ነፃነቷንና ሀገራዊ ሉዓላዊነቷንም አስከብራ በሥልጣኔ የተራመደች ሀገር በመሆኗ እንድሆነ ይጠቀሳል ።ሀገራችንም ቢሆን፤ ይህንን ርምጃ ለማድረግ
የሚሳናት እንዳልነበረች፤ በፀፀት እየተናገሩ ያለፉ በርካታ ሀገር-ወዳድ ዜጎች ነበሩ ። ይህንን በመገንዘብ፤ ከአምሳ ዓመት በፊት አንድ ድምፃዊ ተጫዋች ፦
" ለምሳሌ ጃፓን በጣም ሥልጡን ናቸው ፤ አልተቀላቀለምከሌላባኅላቸው። "
እያለ ሲያቀነቅን እንደነበረ፤ የዚያ ሀገር- ወዳድ ትውልድ የተስፋ ትዝታው ነበር። ተስፋው ወደ ዕውን መለወጡ ቀርቶ፤ እንዲያውም ዛሬ ይባስ ተብሎ ፤ በኢትዮጵያ መኖር / አለመኖር ላይ ዋይታና ጩኸት
ማሰማት ሆኖ ቀርቷል ።
ዛሬ፤ ሁሉም ፤ ተስፋው እየጨለመ፤ ምኞቱ እየተነነ ፤ ራዕዩ እየበነነ፤ ደብዛው ሳይቀር እየጠፋ ነው ።

በዚህ ምክንያት፤ ሀገርና ሕዝብ አሳቢና - ሰብሳቢ አጥተው ቀርተዋል። ኅልውናው በጥያቄ ውስጥ የሚዋልል ሕዝብ ፤ ራሱ ምን እንደሚገጥመው እንኳ ማወቅ አይችልም። በደህናው ጊዜ ያላፈሩት ሰው ደግሞ በጭንቅ ቀን ተፈልጎ የሚያገኘቱ አይሆንም ። እኔ አለሁ ብሎ ብቅ ቢልም እንኳ ፤ ከመንግሥቱ
ሃይለማርያም የተሻለ ስብዕና ያለው ሊሆን አይችልም ። " የገበያን ግርግር ሌባ እንደሚጠቅምበት " ሁሉ፤ ማኅበራዊ ቀውስ በሚፈጠርበት ጊዜ፤ ለሥልጣን ያቆበቆበው ሁሉ፤ በየጎጡና ማጀቱ፤ ብቅ ብቅ ማለቱ አይቀርም ። "የቁርጥ ቀን ልጅ ! የታሪክ አደራ የጣለብኝ ! " የሚል አታላይ መፈክር እያሽጎደጎደ ቲያትሩን ይሰራል ።
ደርግ፤ በዐብዮት ስም ፤ " የፖለቲካ ርምጃና ውሳኔ " በሚል ፈሊጥ፤ ሀገሪቱን እምን ላይ ጥሏት እንደሄደ
ማን ይዘነገዋል ? ወያኔም በበኩሉ፤ በትግራይ ሕዝብ ነፃነት ስም ፤ ምን ዓይነት ወንጀል እንደሰራ/ እንደሚሰራ፤ ሕዝብ ያወቀው ታሪክ የመዘገበው ሀቅ ሆኗል ። ታዲያ ይህንን ሁሉ የታዘበ ሕዝብ፤ አዲስ የሚመጣውን ቢጠራጠር ማን ይፈርድበታል ? ለነገሩማ፤ እንደ ይሁዳ ከሃዲ ከመሆን ፤ እንደ ቶማስ ተጠራጣሪ መሆን አይሻልም እንዴ ?
ለትዝብት ያልታከተው የኢትዮጵያ ሕዝብም ፦
4
"ዐይኔጉድዐዬ፤ዕድሜየምረዝሞ፤ ያዘመኔ በዝቶ፤ ጉግማንጉሄዶ፤ ጭራቁሲተካ፤ ደህናሰውም ጠፍቶ!"
እያለ ማልቀሱን ይቀጥላል። እምባውን እንደ ጎርፍ ቢያጎርፈውም፤ ጩኸቱንም ላንቃው እስኪሰነጠቅ ቢለቀውም ሰሚ አላገኘም። " እርስ በርሳቸው የተከፋፈሉ አባላትን ያቀፈ ሀገርና መንግሥት አይፀናም " እንደተባለው፤ የተከፋፈለ ኅብረተ-ሰብም እንዲሁ ሊፀና አይችልም ። ሊፀናም ከቶ አይታደለም ።
የራሳችንን ኃይል አሰባስበን፤ የራሳችንን ትግል መርተን / አካሂደን፤ የራሳችንን ነፃነት ማስበከር አቅቶን፤ ባዕድ መጥቶ እንዲረዳን እንጠብቃለን። ይህ እንዳማይሆን ግን አሁንም የተረዳን አይመስልም። ኢትዮጵያን ያጠፋ ጠላት፤ ይረዳናል ብሎ መጎናበስ፤ የውርደት ውርድት መሆኑን፤ ማወቅ በተገባ ነበር። ይህንን ማወቅ ካልተቻለ ደግሞ፤ ቢያንስ፤ የኢትዮጵያን ሕዝብ የማሰብ ችሎታና የፍርድ ሚዛን ማክበር ግዴታ ነው ።
" ኦባማ መጥቶ ችግራችን አይቷል፤ እንደተመለሰ ቶሎ ይፈታልናል "
እያልን ራሳችንን ማተታለል ይቅርብን። ይልቁንስ፤
" ወያኔና ኦባማ፤ እንዴት ተቀናጡ፤ ምንኛስ ቀለዱ፤
በምኒልክ ግቢ ዳንኪራ ጨፍረው፤ እስክስታ ወረዱ፤
በሀገራችን ችግር መመፃደቃቸው፤ በሕዝባችን እምባ መዘባበታቸው፤

እነርሱ ምን ያርጉ ጥፋቱ ከኛው ነው፤ ቤታችንን ክፍተን ስንተውላቸው ! " ለካ ትንቢት ኖሯል ቀድሞ መነገሩ፤ ጥንትም መበሰሩ፤
" ከፍት ይዋል ክፍት ይደር ብለው ሲመርቁ ፤ ቤቱም ክፍቱን ቀረ ሰዎቹምአለቁ ! "
ብለን በመቆጨት፤ ኢትዮጵያዊ ማንነታችንን በተግባር ማስመስከር ይጠበቅብናል ። ይህ ካልሆነ ግን፤ የአዞ እምባ ከማፍሰስ አያልፍም ! የአዞ እምባ የሚያለቅስልን ግን አናጣም ፤ የሚጠቅም ከሆነ ?
1933 ዓም ዐፄ ኃይለ ሥላሴ ልክ ከስደት እንደተመለሱ ፤ በአርበኞች በኩል ፤ አንድ የምፀት ስንኝ ተነግሮ ነበር የይባላል ። ይኸውም
" እንግሊዝ እናቱ አማሪካ አባቱ ፤
5

ደጋግፈው አስገቡት ከቤተ መንግሥቱ "
ልብያለህ ልብብል! ልብየሌለህልብግዛ !እንደጲላጦስ እጅን ቢታጠቡት፤ እንደይሁዳ የክኅደት
አሳሳም ቢስሙት፤ እንደ ባንዳ ጥብቆ ቢቀያይሩት ፤ ከደሙ ንፁህ ነኝ ማለት አይቻልም። ከወንጀልም ክስ ነፃአያወጣም !
" የፖለቲካ ሳይንስ አጥንቶ የመጣ፤
ሀገሩንያወጣልከነአጼውጣጣ
" ሲልየነበረውሁሉ፤በ11ኛውስዓትወደዘሩ፤ነገዱናወደብሄሩ
እያፈተለከ መሄዱን ታዝበናል ። መቆየት መልካም ነው ብዙ ያስተዛዝባል! በዚህ ምክንያት ፦ " እዚህ መጥተሽ በላሽ፤ እዚያም ሄደሽ በላሽ ፤
ሰው ታዘበሽ እንጅ ሆድሽን መቼ ሞላሽ ? "
ለማለት በቅተናል ። የቆየ ሰው መልካም !
ኢትዮጵያ ከ 1933 እስከ 1966 ዓም ድረስ በምን ሁኔታ ላይ እንደነበረች የቅርብ ትዝታ ስለሆነ፤ በዚያ ላይ ማተኩርን አንመርጥም። ህይወት ዘወተር በማያቋርጥ የለውጥ እንቅስቃሴ ሂደት መገኘቷን የማይረዱ ራዕይ-ቢስ መሪዎች፤ እራሳቸው ጠፍተው፤ ሀገሪቱንም ለጥፋት ዳርገዋት ይሄዳሉ። መከራውና ፍዳው ግን ለትውልድ ይተላለፋል ።
ይህ ተደጋጋሚ ችግር እንዳይከሰት ከተፈለገ፤ ራዕይ ያላቸው ዜጎች ስትራተጂያዊ ዓላማቸውን
አስተባብረው መስራት ይጠበቅባቸዋል ። አሁን እንደሚታየው ከሆነ ግን፤ እንኳንስ በስትራተጅ ( ወደ
ግባችን በሚወስደን ረጅም መንገድ ) ላይ መስማማት ይቅርና በታክቲክ (በስልት) ላይም ቢሆን መስማማት የሚቻል አልሆነም ።
በአሁን ዘመን ፤ ማንም ሀገር፤ የሌላውን ሀገር ችግር ሊፈታ ቀርቶ ፤ ሊቀርፍ እንኳን አይችልም። ደንታም አይሰጠውም ። ይልቁንም፤ የራሱን ጥቅም ለማስጠበቅ ሲል፤ ከአምበገነኖች ጋር ተመሳጥሮ፤ ሕዝብ የሚጎዳ ተግባር ለመፈፀም ወደ ኋላ አይልም። ይህንን ሃቅ አበክሮ የተገነዘበ ሕዝብ፤ ሊኖረው የሚችለው ምርጫ አንድ ብቻ ይሆናል። እራሱን አደራጅቶ፤ እራሱ ታግሎ፤ ራሱን ከችግር ማውጣት እንዳለበት ለአፍታም
ቢሆንከኅሊናውሊፍቀውአይገባም።ያለዚያ፤ሁሉምነገር፤"ቄሱምዝም መጽሐፉዝም"ሆኖ ይቀራል ! የኢትዮጵያ ሕዝብ ሆይ ፤ ዕርምህን እያወጣህ ትግልህን ቀጥል !
ኢትዮጵያ በነፃነቷ ለዘለዓለም ትኖራለች

አለቃዎ ሳይሆን ቅን ህሊናዎ የሚያዝዎትን በመፈፀም መልካም ዜጋ ይሁኑ!

አለቃዎ ሳይሆን ቅን ህሊናዎ የሚያዝዎትን በመፈፀም መልካም ዜጋ ይሁኑ!

August 12, 2015
def-thumbመልካም ዜጋ ማለት ምን ማለት ነው?
ይህን ጥያቄ ለመመለስ በርካታ መጻሕፍት መፃፍ ይቻላል፤ መሠረተ ሀሳቡን ግን በጥቂት ዓረፍተ ነገሮች ማቅረብ ይቻላል።
መልካም ዜጋ ኢፍትሃዊ ተግባር ሲፈፀም “እኔ ምናገባኝ?” አይልም። መልካም ዜጋ “ያባትህ ቤት ሲዘረፍ አብረህ ዝረፍ”፤ “እኔ ከሞትኩ ሰርዶም አይብቀል”፤ “እያለህ ካልሆነ ከሌለህ የለህም” እና በርካታ መሰል ምሳሌዎችን አይሰማም። መልካም ዜጋ በማናቸውም ሁኔታ ውስጥ ቢሆን ከነፃና ቅን ህሊናው ጋር ታርቆ ይኖራል።
የህወሓት አገዛዝ፣ መልካም ዜጋ ማለት የመንግሥት ሥልጣን የያዘን ማንኛውም አካል ማክበርና በታማኝነት ማገልገል ተደርጎ እንዲተረጎምለት ይሻል። ፍትህ የሚያዛባ መንግሥትን መቃወም የመልካም ዜጋ አቢይ ተግባር መሆኑ የዘመናችን ወጣት እንዳይገነዘብ ያደርጋል። በተለይ ባለሙያዎች የሚያገለግሉትን አገዛዝ ባህርይ እግምት ውስጥ ሳያስገቡ የተቀጠሩበትን ሥርዓት በታማኝነት ማገልገል የዜግነት ግዴታቸው አድርገው እንዲወስዱት ይወተውታል።
ኦስካር ግሮኒንግ ( Oskar Groening)የዘጠና አራት ዓመት ሽማግሌ ጀርመናዊ ነው። በጀርመን የሂትለር አገዛዝ ወቅት በሚሊዮን የሚቆጠሩ ንፁሃን የተፈጁበት አሽዊትስ ካምፕ ውስጥ የሂሳብና ጽህፈት ሠራተኛ ነበር። ኦስካር ግሮኒንግ አንድም ሰው አልገደለም፤ አንድም ሰው አልገረፈም። እሱ ሂሳብ ነው የሠራው። ሆኖም በደል ሲፈፀም አይቶ “ምናገባኝ” ብሎ አልፏልና ከብዙ ዓመታት በኋላ ተከሶ በቅርቡ የ4 ዓመታት እስር ተፈርዶበት በሁለት እግሮቹ መቆም በማይችልበት በ 94 ዓመቱ በእርጅናውና በመጦሪያው ዘመን ቤተሰቦቹና ጓደኞቹ ፊት ተዋርዶ እስር ቤት ወርዷል።
በአንፃሩ ኦስካር ሽንድለር (Oskar Schindler) በጀርመን ናዚ ወቅት ሂትለር ይመራው የነበረው የናዚ ፓርቲ አባልና ሰላይ ነበር። ሆኖም ግን የሥርዓቱን ኢሰብዓዊነት ሲረዳ እዚያው የናዚ ፓርቲ ውስጥ ሆኖ አለቆቹ ያዘዙትን ሳይሆን ቅን ህሊናው ያዘዘውን በምስጢር መሥራት ጀመረ፤ በዚህም የ 1200 ሰዎችን ሕይወት ታደገ። ከጦርነቱ በኋላ ኦስካር ተከብሮ የኖረ በርካታ የክብር ስሞችና ሽልማቶች የተሰጠው በመልካም አርዓያነቱ የሚጠቀስ ሰው ሆነ።
በአገራችንም በአምስት ዓመታቱ የፋሽስት ወረራ ወቅት ስመ ጥር የውስጥ አርበኞች ነበሩ። ከነፃነት በኋላ ባንዶች እንኳን በውስጥ አርበኝነት ለመጠራት ያደርጉት የነበረውን እሽቅድድም ልብ በሉ።
በህወሓት፣ ብአዴን፣ ኦህዴግ፣ ደህዴግ እንዲሁም አብዴፓ፣ ቤጉህዴፓ፣ ጋህአዴን፣ ሀብሊና ኢሶዴፓ ያላችሁ ወገኞች ኦስካር ግሮኒንግን ወይንስ ኦስካር ሽንድለርን መምሰል ትፈልጋላችሁ? በህወሓት ፋሽስታዊ አገዛዝ የጦርና የፓሊስ ሠራዊት ውስጥ ያላችሁ ወገኖቻችን ነገ የምትዋረዱበትን ሥራ መሥራት ነው የሚበጃችሁ ወይስ ዛሬ ከህሊናችሁ ጋር ታርቃችሁ እየኖራችሁ ነገ ደግሞ ልጆቻችሁና የልጅ ልጆቻችሁ የሚኮሩበትን ተግባር መፈፀም ትፈልጋላችሁ? በአገዛዙ የስለላ ድርጅቶች ውስጥ ያላችሁ ወገኖች ስማችሁን በመልካም ማስጠራት አትሹምን?
ልቦና ያላችሁ ወገኖቻችን ሆይ! መልካም ዜግነት ሎሌነት አይደለም። መልካም ዜግነት ለቅን ህሊና ታማኝ መሆን ነው። መልካም ዜግነት ሲመች በገሀድ፤ ሳይመች በምስጢር ኢፍትሃዊነትን መዋጋት ነው።
አርበኞች ግንቦት 7 የአንድነትና ዲሞክራሲ ንቅናቄ በማናቸውም መንገድ በአገዛዙ የፓለቲካ፣ የጦርና የፓሊስ ተቋማት፤ በስለላም ይሁን በሌላ የሲቪል ሙያ የተሰማራችሁ ወገኖቻችን የታዘዛችሁትን ሳይሆን ቅን ህሊናችሁ የሚጠይቃችሁን በመሥራት ኢፍትሃዊ፣ ፋሽስታዊና ዘረኛ የሆነውን የህወሓት አገዛዝን እንድታዳክሙ ጥሪ ያቀርብላችኋል። በአገዛዙ ውስጥ ሆናችሁ እያለም የምትሠሩት ለሀገርና ለትውልድ የሚጠቅም በርካታ ሥራ አለ። የአገዛዙን ምስጢራዊ ሰነዶች ለአርበኞች ግንቦት 7 እንዲደርስ ማድረግ፤ አሊያም በማኅበራዊ ሚዲያዎች (ለምሳሌ ፌስ ቡክና ቱተር) ማሰራጨት ትልቅ ዋጋ ያለ ሥራ ነው። የህወሓት ፀረ-አገር እና ፀረ-ሕዝብ ፕሮጀክቶችን ማሰናከል ሌላ ትልቅ ሥራ ነው። በነፃነት ታጋዮች ላይ የሚደረጉ ዱለታዎችን ማክሸፍ ሕይወት አድን ሥራ ነው። ድርጅቶቹ ውስጥ ሆኖ ድርጅቶቹን ማዳከም የመልካም ዜግነት ግዴታ መወጣት ነው።
በሥርዓቱ ውስጥ ሆነው ኢፍትሃዊነትን ለማጋለጥ እና ሥርዓቱን ለማዳከም ለሚጥሩ ወገኞች አርበኞች ግንቦት 7 ከፍተኛ ክብር አለው፤ ደህንነታቸው እንዲጠበቅም የተቻለውን ሁሉ ያደርጋል። ፀረ ኢትዮጵያ እና ፀረ ሰው የሆነውን የህወሓትን ሥርዓት ለመጣል እና በምትኩ ፍትህ፣ ነፃነት፣ ዲሞክራሲ፣ እኩልነትና የሀገር አንድነት የተረጋገጠባት ኢትዮጵያን ለማጽናት ከሥርዓቱ ውስጥም ውጭም የሚደረገውን ትግል እናፋፍም።
ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ!!!

የኤልያስ ገብሩ ቆይታ ከጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ጋር (ዝዋይ እስር ቤት)

የኤልያስ ገብሩ ቆይታ ከጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ጋር (ዝዋይ እስር ቤት)

August 13, 2015
በኤልያስ ገብሩ
  • ታገሉ! ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ (ከዝዋይ እስር ቤት)
  • ተመስገን ደሳለኝ ስለሙስሊም መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ አባላት ፍርድም ሀሳቡን ሰንዝሯል
Temesgen Desalegn Fteh newspaper editor
ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ
ቦሌ አካባቢ ብርዱ ጠንከር ያለ ነበር፡፡ ከቦሌ ብራስ ወደሚሊኒየም አዳራሽ በሚወስደው ቀጭን መንገድ ላይ ወንዱም ሴቱም በፍጥነት ይራመዳል፡፡ ከታክሲ በሁለቱም አቅጣጫዎች የወረዱ ሰዎች ወደመደበኛ ሥራቸው ለመግባት ብሎም የግል ጉዳያቸውን ለመፈጸም ሲንቀሳቀሱ ነበር – ከትናንት በስትያ ሰኞ (ነሐሴ 04 ቀን 2007 ዓ.ም) ጥዋት 1፡45 ሰዓት፡፡
እኔ እና ወዳጄ አቤል ዓለማየሁ ወደከአዲስ አበባ 160 ኪሎ ሜትር ርቀት ወደሚገኘው ዝዋይ እስር ቤት አምርተን ጋዜጠኛ ውብሸት ታዬን እና ተመስገን ደሳለኝን ለመጠየቅ በዚህ ቀን ቀጠሮ ይዘን ነበር፡፡ አቤል ከቀጠሯችን 20 ደቂቃ ዘግይቶ፣ ቦሌ ጫፍ ደረሰና ወደቃሊቲ መናሃሪያ ሁለት ታክሲዎችን በመጠቀም ደረስን፡፡ ወደዝዋይ የሚጭኑ ሚኒባስ ታክሲዎች እና ‹‹አባዱላ/ዶልፊን›› የሚል መጠሪያ የተቸራቸው የህዝብ ማመላለሻ መኪኖች ቢኖሩም በተለምዶ ‹‹ቅጥቅጥ›› የሚባለውን መካከለኛ አውቶቡስ ምርጫችን አደረግን – የትራፊክ አደጋን በመስጋት፡፡
የተሳፈርንበት አውቶቡስ፣ ከቃሊቲ ትንሽ ወጣ ካለ በኋላ፤ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም፣ በእስር ላይ የሚገኙትን የግንቦት 7 ዋና ፀሐፊ አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ “ልማቱን አሳዩኝ” ሲለን ከከተማ ወጣ እያደረግን የምነሳየው… [እውነት ግን፣ በከባድ እስር ላይ መሆናቸው የሚገመተው አቶ አንዳርጋቸው ‹ልማቱን አሳዩኝ› ይሏቸዋልን?!]›› ሲሉ ለቪኦኤዋ ጋዜጠኛ ትዝታ በላቸው የገለጹትን፣ የአዲስ አበባ አዳማ አዲሱ የፍጥነት መንገድ (Express way)ን ተቀላቀለ፡፡ በዚህ መንገድ ሁለታችንም ሄደን አናውቅም ነበር፡፡ ሆኖም እስከዛሬ ካየኋቸው የመኪና መንገዶች በደረጃው ከፍ ያለ ይመስላል፡፡ [በሀገራችን አምረው የተሰሩ የመኪና መንገዶች በጥቂት ዓመታት ውስጥ በከፍተኛ ሁኔታ የመቦርቦር፣ የመፈረካከስ፣ ውሃ የማቆር ችግሮች ገጥሟቸው እንዲሁም ከመንገዱ ዳር እና ዳር የሚገኙ የብረት አጥሮች ተሰርቀው፣ ተገጭተው፣ ተጨረማምተው፣ ተነቃቅለው … አደጋ ሲያደርሱና የተለመደ የሬንጅ የመለጠፍ ሥራ ሲሰራላቸው በገሃድ የምናየው ሀቅ መሆኑን ማስታወስ ግን የግድ ይላል] ይሄኛው መንገድ ከጠቀስኳቸውና ካልጠቀስኳቸው ችግሮች ምን ያህለ ነጻ ነው? ለሚለው ትክክለኛ መስክርነት መስጠት ያለበት ለእውነት የቆመ የዘርፉ ባለሙያ ቢሆንም በኢህአዴግ ‹ልማት› ላይ የጥራት መተማመኛ ማግኘት እጅግ ከባድ መሆኑን ግን አምናለሁ፡፡ አስፋልቱ ለፍጥነት አመቺ መሆኑን ግን በቀላሉ መረዳት ይቻላል፡፡
በሶስት ሰዓታት ጉዞ ዝዋይ በመድረስ ምሳ ከበላን በኋላ ወደእስር ቤቱ የፈረስ ጋሪ መጠቀም ግዴታችን ነበር፡፡ አቧራማው አስቸጋሪ መንገድ፣ ከፊሉ ደቃቅ አሸዋ መልበስ ጀምሯል፡፡ የእስር ቤቱ የማስፋፊያ ግንባታ ሥራ፣ በፊት ውብሸትን ለመየጠቅ ስመጣ ከማውቀው ተፋጥኗል፡፡ አንዱ የሥርዓቱ “የልማት ውጤት” እስረኛ ማብዛት አይደለ ታዲያ?!
ከቀኑ 7፡30 ሰዓት ላይ የምንጠይቀውን እስረኛ በማስመዝገብ ተፈትሸን ገባን፡፡ ሁለት እስረኛ በአንዴ መጠየቅ ስለማንችል እኔ ተመስገን ጋር፣ አቤል ደግሞ ውብሸትን ለመጠየቅ ተስማምተን ነበር፡፡ አቤል ውብሸትን ከጠየቀ በኋላ እንደምንም ብሎ ተመስገንን ለመጠየቅ ጥረት እንደሚያደርግ ግን ቀድሞ ነገረኝ፡፡
ተመስገን እና ውብሸት የታሰሩበት ዞን ስለሚለያይ እኔ እና አቤል ሌላ የውስጥ ፍተሻ ካደረግን በኋላ መለያየታችን ግድ ነበር፡፡ የእስር ቤቱ ፖሊሶች የሚኖሩበትን ጉስቁልና ያጠቃቸው፣ መኖሪያ ቤቶችን አልፌ መጠየቂያው ጋር ደርሼ የታሳሪው ስም ያለባትንና በፖሊሶች የምትጻፈዋን ቁራጭ ወረቀት እስረኛን ለሚጠራው ፖሊስ ሰጠሁትና በአጣና እንጨት ርብራብ በተሰራው መጠየቂያው አግዳሚ ላይ ተቀመጥኩ፡፡ ከቅርብ ርቀት የፖሊሶች ማማ ይታያል፡፡ መሳሪያ የታጠቁ ፖሊሶች ማማው ላይና ከማማው ሥር በዛ ብለው ተቀምጠው ያወጋሉ፡፡ አብዛኞቹ ፖሊሶች ከላይ የለበሷት እና “Federal prison” የሚል የታተመባት አረንጓዴ ዩኒፎርምም በፀሃይ ብዛት ነጣ ወደማለት ደርሳለች፡፡ አንዱ ፖሊስ መጣና ከእኔ በትንሽ ሜትር ራቅ ብሎ ተቀመጠ፡፡ ‹‹አዳማጭ ነው›› አልኩ በልቤ፡፡ ወደፊት ለፊቴ ወደሚታየኝ የእስር ቤት ግቢ አማተርኩ፡፡ ለእይታ የሚጋብዝ አንዳች ነገር አጣሁ፡፡ የተበታተኑ ዛፎች፣ ቅርጽ አልባ ሳሮች፣ አስታዋሽ ያጡ አረሞች፣ ግድግዳ እና ጣራቸው በቆርቆሮ የተሰሩ የእስረኛ መኖሪያዎች፣ …ብቻ ጭርታ እና ድብታ የወረረው የግዞት መንደር ይመስላል፡፡
ከአንደኛው የእስረኛ ቆርቆሮ ቤት ጣሪያ ላይ ሁለት ተለቅ ተለቅ ያሉ ሙቀት ማቀዝቀዣዎች ይሽከረከራሉ፡፡ ወደፖሊሱ ዞሬ ‹‹ለሙቀት ነው?›› አልኩት ወደ ጣራው በመጠቀም፡፡ ‹‹አዎ፣ ወባ አደገኛ ነው›› አለኝ፡፡ ‹‹እስረኞች ሲታመሙ እንዴት ይሆናሉ?›› ስል ጥያቄ ሰነዘርኩ፡፡ ‹‹ያው እዚሁ ይታከማሉ›› አለኝ ድምጹን ቀሰስ አድርጎ፡፡ የእኔም ሆነ የእሱ ልብ፣ በማረሚያ ቤቱ (በእነሱ አጠራር) በቂ ህክምና እንደማይሰጥ ግን ያውቃል ብዬ አሰብኩ፡፡ ቀጭኑ ፖሊስ፣ ‹‹ለወባ ህመም ምግብ ወሳኝ ነው›› አለኝ አስከትሎ፡፡ ‹‹በቂ ምግብ የለም ማለት ነው?›› ስል ድጋሚ ጠየኩት፡፡ ‹‹በፊት በፊት አቀራረቡ ዝም ብሎ ነበር፤ ሙያ ባሌላቸው ሴቶች ነበር የሚሰራው፡፡ አሁን ግን ለውጥ አለ›› አለኝ፡፡ ‹‹ምን አይነት ለውጥ? ጥቂትም ቢሆን ታስሬ፣ ለእስረኞች የሚቀርበውን በጣም ደረጃውን ያልጠበቀ ምግብ አይቻለሁ›› አልኩት፡፡ ‹‹በፊት ጥቁር ጤፍ ነበር የሚቀርበው፤ አሁን የነጭ ጤፍ እንጀራ ነው የሚበሉት፤ እስረኞች ችግር የለባቸውም፤ ባለሙያ ሴቶችም ናቸው የተቀጠሩት …›› ‹‹(ውስጤ አላመነምና) ለእስረኛ የነጭ ጤፍ እንጀራ እያቀረባችሁ ነው?!›› …‹‹አዎ›› ብሎ ሊያብራራልኝ እያለ ከታች ከርቀት ‹‹አረንጓዴ ኮፊያ፣ ቲ-ሸርትና ስካርፍ ያደረገ ሰው አየሁ፡፡ ትኩረቴን ከፖሊሱ አዙሬ ቁልቁል ተመለከትኩ – ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ነበር፡፡ ተሜም፣ ረጋ ብሎ በራስ በመተማመን መንፈስ ወደመጠየቂያው ሥፍራ ቀረብ ብሎ ጠያቂውን ለማወቅ ጥረት አደረገ፡፡ ሳየው አንዳች የሀዘን ስሜት ውስጤ ገባ፡፡ ቆሜ ጠበኩት፡፡ ፈገግ እያለ መጣና ተጨባብጠን አራት አምስቴ ያህል ተቃቀፍን፡፡ ‹‹በዚህ በጸሐይ ለምን መጣህ?›› ሲል ጠየቀኝ፡፡ ከአቤል ጋር መምጣታችንን፣ እሱ ውብሸትን ሊጠይቀው መሄዱን ነገር ግን ከቂሊንጦ በኋላ እስከአሁን ዝዋይ ድረስ መጥቼ ባለመጠየቄ የጸጸት ስሜት ውስጤ እንዳለ ገለጽኩለት፡፡ ‹‹መንገዱ ረዥም ነው፣ ባትመጡም እረዳለሁ›› ካለ በኋላ፤ ‹‹ምን አዲስ ነገር አለ?›› በማለት ፊት ለፊት በእንጨት አጥር ተከልለን በመቀመጥ ጨዋታችንን ቀጠልን፡፡
‹‹አሁን ምን እየሰራችሁ ነው?››፣ ‹‹ክስህስ እንዴት ሆነ?››፣ ‹‹አዲስ ጋዜጣ ለማቋቋም ለምን ጥረት አታደርጉም?›› ከተመስገን በተከታታይ የተነሱ ጥያቄዎች ነበሩ፡፡ አጠር አጠር አድርጌ መለስኩለት፡፡ የጋዜጣ /የመጽሔት ህትመትን ድጋሚ መጀመር የግድ አስፈላጊ መሆኑን ግን ተመስገን አጽንኦት የሰጠበት ጉዳይ ነበር፡፡ …ስለተወሰኑ ጋዜጠኞችና የዞን 9 ጦማሪያን ከእስር መፈታት፣ ስለኦባማ የአዲስ አበባ ጎብኝት፣ በቂሊንጦ ዞን አንድ ከእነአብበከር አህመድ፣ ጦማሪ አቤል ዋበላና ዘላለም ክብርት ጋር ስለነበረው ቆይታ፣ እሱ ወደዝዋይ ከወረደ በኋላ እኔም በዚያ ዞን ገብቼ በነበረበት ጊዜ እነአቡበከር፣ አቤልና ዘላለም እሱን በተመለከተ ስለነገሩኝ ነገሮች ሳቅ እያልን አወጋን፡፡
ሰፊ ውይይት ያደረግነው በሙስሊም መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ አባላት ላይ በቅርቡ ከ7 እስከ 22 ዓመት የሚደርስ ጽኑ እስራት ፍርድን በተመለከተ ነበር፡፡ ‹‹እኛ ከሙያ ጋር በተያያዘ ነው የታሰርነው፡፡ ታስረንም እንወጣለን፡፡ ከባዱ የሙስሊሞቹ እስር ነው፡፡ ኢህአዴግ እውነተኛ ሰላም ከፈለገ እነአቡበከርን በነጻ መፍታት አለበት፡፡ እኔ የእነሱ መከላከያ ምስክር ሆኜ ምስክርነቴን ሰጥቻለሁ፡፡ በወቅቱ ዘንግቼው ያልተናገርኩት አንድ ነገር ነበር፤ አሁን ሳስበው ትንሽ ይቆጨኛል – በተናገርኩ ብዬ፡፡ ያኔ (በምስክርነት ጊዜ)፣ ‹የኮሚቴዎቹ እንቅስቃሴ ሰላማዊ ነበር ወይስ አልነበረም?› የሚለው ጥያቄ በራሱ መነሳት አልነበረበትም፡፡ እንቅስቃሴያቸው፣ ሰላማዊ ባይሆን ኖሮ እንዴት ሶስት ዓመት ሙሉ በክስ ሂደት ይቀጥላል?! ሰላማዊ ስለሆኑ እኮ ነው፣ ባለፉት ሶስት ዓመታት ምንም ያልተፈጠረው፡፡ እስኪ በእነሱ አንድ የተሰበረ መስታወት አለ?! ቅንጣት የወደመ ንብረት አለ?! የማንንስ ሕይወት አጠፉ?! በእነሱ የተፈጠረ አንድም ነገር የለም፡፡ ጥያቄያቸው ኃይማኖታዊ እንጂ ፖለቲካዊ አይደለም፡፡ ፖለቲካዊ ቢሆን ኖሮ ትግሉ አቅጣጫውን ይቀይር ነበር፡፡ ‹የመጅሊስ አመራሮችን ካለመንግሥት ጣልቃ ገብነት እንምረጥ!› ነው አንዱ ሰላማዊ ጥያቄያቸው፡፡ ያው ምስክር ስትሆን ከዚህም ከዚያ ጥያቄ ሲነሳ ስለምትዘናጋ መመስከር ያሰብከውን ነው ቅድሚያ የምትሰጠው እንጂ አሁን የምልህን ያኔ ብገልጸው በጣም ደስ ይለኝ ነበር …›› በማለት በኢትዮጵያ ውስጥ ከታሪክ አኳያ፣ በሁለቱ ትልልቅ ሃይማኖት ተከታዮች መካከል ስለነበረው ግንኙነት በዝርዝር የራሱን ምልከታ እና ሀሳብ ደጋግሞ አወጋኝ፡፡ ኃይማኖታዊ መቻቻል ነበር ወይስ አልነበረም? የሁለቱም እምነት ተከታዮች ጉርብትና ነበራቸው ወይስ አልነበረባቸውም በሚሉት አንኳር ጉዳዮችም የራሱን አቋም አንጸባረቀልኝ፡፡
ኡስታዝ አቡበከር አሕመድን አስመልክቶም አንድ ጥሩ ምሳሌም አንስቶልኝ ነበር ተመስገን፡፡
‹‹አሁን ባለሁበት ዞን፣ በአንድ የወንጀል ክስ ግብረ-አበር ተብለው አምስት ዓመት የተፈረደባቸው አንድ ቄስ አሉ፡፡ እኚህ ቄስ ለጠበቃ የሚከፍሉት አጥተው የጠበቃ ክፍያ የፈጸመላቸው አቡበከር እንደሆነ ነግረውኛል››
እኔም ፣ በህዳር ወር ቂሊንጦ ዞን አንድ በነበርኩበት ጊዜ ከዚህ ጋር ተመሳሳይ የሆነ ነገር፣ ስለአቡበከር ሰምቼ ነበር፡፡ ታሪኩ እንዲህ ነው፡- አንዱ እነአቡበከር ይገኙ በነበረበት ዞን 1 8ኛ ቤት ውስጥ የቀጠሮ እስረኛ ነበር፡፡ ዋስትና ይጠየቅና በዚህ ክፍል ውስጥ በሙስና ወንጀል ተጠርጥረው የታሰሩ አንድ የናጠጡ ሀብታም (ልጃቸው 22 አካባቢ እጅግ ዘመናዊ ሆቴል አለው) ጋር ጠጋ ብሎ ለዋስትና የሚሆን ብር ተጨንቆ በአክብሮት ይጠይቃቸዋል፡፡ እሳቸውም ‹‹እኔም እንደአንተው እስረኛ እኮ ነኝ!›› በማለት ይመልሱለታል፤፡፡ ልጁም ያዝናል፡፡ ይህ ጉዳይ አቡበከር ጆሮ ይገባና ለልጁ የሚስፈልገውን የዋስትና ብር ከፍሎ ልጁን ከእስር እንዲወጣ አድርጎታል፡፡ እንግዲህ፣ ከሁለቱ እውነተኛ ምሳሌዎች በመነሳት፣ አቡበከር ለወገኖቹ ሃይማኖትን መሰረት ሳያደርግ፣ በሰብዓዊነት ደግ መሆኑን እንማራለን፡፡
ከተመስገን ጋር በነበረን ሰፋ ባለ የጨዋታ ጊዜ፣ ከጎኔ የነበረው ፖሊስ በተመስጦ ቢያዳምጥም፣ አንዴም አላቋረጠንም ነበር፡፡ …ስለ 100% ቱ የዘንድሮ ምርጫ ፍጻሜ፣ በሰሞኑ በአፋር ክልል ስለደረሰው የድርቅ አደጋ፣ በአይ ኤስ አሸባሪ ቡድን ስለተቀሉና ስለተገደሉት ኢትዮጵያኖች፣ ድርጊቱን በማውገዝ በመስቀል አደባባይ በተጠራው ሰልፍ ላይ ስለተፈጠረው ረብሻ፣ ጉዳትና እስር ተመስገን የራሱን አተያይ በስሜት ተውጦ የግሉን ሀሳብ አብራራልኝ፡፡ በተጨማሪም፣ አይ ኤስ ያንን ድርጊት፣ ያንን ጊዜ መርጦ አደረገ ያለበትን የራሱን የተለየ (ከማንም ያላደመጥኩትን፣ ተጽፎም ያላነበብኩትን) ሀሳብ አጋራኝ፡፡ የተለየ ሃሳብ በመሆኑም ‹‹አሃ!›› ብያለሁ፡፡
ከተመስገን በጣም የገረመኝ፣ የማስታወስ ችሎታው ነበር፡፡ በጥቅምት ወር፣ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ‹‹ጥፋተኛ›› በተባለበት ማግስት ጥዋት አምስተኛ ፖሊስ ጣቢያ ልጠይወቅ ሄጄ በማያመች ሁኔታ ውስጥ ሆነን አብዮትን አስመልክቶ የተለዋወጥናቸውን ሃሳቦችን፣ እንዲሁም ከአቤል ጋር ቂሊንጦ ስንጠይቀው ያነሳናቸውን ሀሳቦች ድጋሚ በማስታወስ በዚህ ቀን ለተነሱት ርዕሰ ጉዳዮች የውይይት ማጠናከሪያ ሀሳብ ሲያደርጋቸው አስተውያለሁ፡፡
ለተመስገን አሁን ስለሚገኝበት ዞን ሁኔታ ጥያቄ አቀረብኩለት፡፡ ቀደም ሲል ከእነውብሸት ጋር አብሮ እንደነበረ ጠቅሶ፣ ‹‹የኢትዮጵያ ገመና›› በሚል ርዕስ በእስር ቤት ውስጥ ስላወቀው ነገር ሁለት ተከታታይ ጽሑፎችን ካወጣ በኋላ ወደዚህ ዞን መዘዋወሩን ይገልጻል፡፡ አሁን ባለበት ክፍል 80 የሚሆኑ እስረኞች አብረውት አሉ፡፡ ብዙዎቹ ከደቡብ ክልል የመጡ ናቸው፡፡ ከእሱ ጋር አንድም የፖለቲካ እስረኛም ሆነ ጋዜጠኛ አብሮት የለም፡፡ [አቶ በቀለ ገርባ ከወራቶች በፊት የ3 ዓመት ከ7 ወር የእስር ጊዜያቸውን አጠናቅቀው ከዝዋይ እስር ቤት በተፈቱ ማግስት ተመስገን ከባድ ወደሆነው ወደዚህ ዞን መሸጋገሩን ነግረውኝ ነበር] አሁን ባለበት ዞንም ከእሱ ጋር እስረኞች እንዳያወሩ እና እንዲያገልሉት በዘዴ ተደርጓል፡፡ ከእሱ ጋር በቅርበት ሆነው የሚያወሩ ካሉ፣ እንደትልቅ ተስፋ በሚጠብቁት አመክሯቸው ላይ እንደመፍረድ ይቆጠራል እንደተመስገን አባባል፡፡ ‹‹በዚህ ጉዳይ ማናቸውም ላይ አልፈርድም፤ ከእኔ ጋር አውርተው የአመክሮ ጊዜያቸውን እንዲያጡ አልሻም፡፡ ግን እንዲህ ያደረጉት ሌሎች የፖለቲካ እስረኞች ቢሆኑ ኖሮ ይሰማኝ ነበር፡፡›› ሲል ያለበትን ከባድ ሁኔታ ያስረዳል፡፡
‹‹ማንበብ፣ ማጸፍስ ትችላለህ?›› ሌላኛው ጥያቄዬ ነበር፡፡ ‹‹መጽሐፍ አይገባም ተልክሏል፤ ያነበብኳቸው ጥቂት ልብወለድ መጽሐፍቶች አሉ፡፡ መጻፍ ትንሽ ጀምሬ በእስረኞች በኩል ተጠቁሞ የጻፍኩት ተወሰደ፡፡ ሁለት ሶስቴ ለመጻፍ ሞክሬ ነበር፡፡ ግን ተመሳሳይ እርምጃ በመወሰዱ ተውኩት፡፡›› ይላል ተመስገን፡፡ ‹‹ቀኑን እንዴት ነው የምታልፈው?›› የሚለው የመጨረሻ ጥያቄዬ ነበር፡፡ ‹‹ሁለት የማውቃቸው የአዲስ አበባ ልጆች አሉ፤ ጫናውን ችለው ያናግሩኛል፡፡ ከእነሱ ጋር ቼዝ እጫወታለሁ፡፡ የእግር ኳስ ፕሮግራም የሚተላለፍባቸው ቻናሎች ቢኖሩም መገለሉን አስበውና ደስ ስለማይለኝ ወደክፍሌ እገባለሁ›› የሚለው የተመስገን መልስ ነበር፡፡
ተመስገን አቤልን ከርቀት አይቶት ‹‹ያ አቤል ነው አይደለ?›› አለኝ፡፡ ዞሬ አየሁት፣ አቤል ውብሸትን ጠይቆት ከርቀት ወደመውጪያው በር እየሄደ ነበር፡፡ ‹‹ግን እንዴት አስገቧችሁ?፤ ይመልሱ ነበር እኮ›› አለኝ፡፡ አቤልም ተመስገንን ተመስገንም አቤልን ማግኘት ፈልገው ነበር፡፡ ብዙም ሳይቆይ አቤል አንዱን ፖሊስ እንደምንም አናግሮ ተመስገንን ሊጠይቅ መጣ፡፡ ተቃቅፈው ተሳሳሙ፡፡ የሶስትዮሽ ጨዋታችንን ለግማሽ ሰዓት ያህል አደራነው፡፡ ተመስገን ከታሰረ በኋላ የግራ ጆሮው እንደማይሰማለት እና ወገቡም ሕክምና በማጣቱ አሁንም ድረስ እንደሚያመው አልሸሸገንም – ‹‹እዚህ ያለው መድኃኒት ፓናዶል ብቻ ነው›› በማለት፡፡ አያይዞም ‹‹ሰው መጥቶ ሲጠይቅህ ደስ ይላል፤ ጥሩ እንቅልፍ ትተኛለህ፤ግን የመንገዱን ርቀት ሳስበው ሰው ባይመጣ እላለሁ›› አለን በድጋሚ፡፡
የእስረኛ መጠየቂያ ጊዜ መጠናቀቁን ፖሊሶች ነገሩንና ተቃቅፎ መለያት ግድ ሆነ፡፡ ‹‹አይዞህ የምትባል አይደለህምና ሰላም ሁን›› አልኩት፡፡ ‹‹ምን መልዕክት አለህ?›› ስል የመጨረሻ ጥያቄዬን ሰነዘርኩለት፡፡ ተመስገንም ‹‹ታገሉ!›› ሲል መለሰና በመጣበት መንገድ ቻው ብሎን እርምጃውን ቀጠለ፡፡ ሲሄድ አራት እና አምስት ጊዜ ያህል ዞረን አየነው፡፡ ስለገኘነው ደስ ቢለንም በሳሮች መካከል ባለው መንገድ ወደታሰረበት ክፍል ሲያመራ ማየት ዳግመኛ የመረበሽ እና የማዘን ስሜት በውስጤ ፈጥሮብኝ ነበር፡፡ ስሜቱ በጣም የሚገባው በቦታው ላይ ሲገኙ ነው!
ተመስገን፣ ያመነበትን ሀሳብ በድፍረት ስለጻፈ ነበር በኢ-ፍትሃዊነት ሶስት ዓመት እስር የተፈረደበት፡፡ ሰው መታሰሩ ሳያንስ፤ ከቤተሰቡ፣ ከወዳጁ፣ ከዘመዱ፣ ከጓዳኞቹ እርቆ እንዲታሰር ማድረግ ሌላ ቅጣት ነው! ሰው መታሰሩ ሳያንስ፣ ህክምና መከልከሉ፣ በሌሎች እስረኞች እንዲገለል መደረጉ፣ መጽሐፍ ማንበብ እና የግል ማስታወሻዎቹን እንዳይጽፍ መከልከሉ ይሄም ሌላ ቅጣት ነው! ሰው ግን በስንቱ ይቀጣል?! እንዲህም ሆኖ፣ ትናንት የምናውቀው ጋዜጠኛ ተመስገን፣ አሁንም ድረስ ያ ያመነበትን የመናገር ድፍረቱ፣ መንፈሳዊ ብርታትና ጥንካሬው አብሮት አለ!!! አካል ቢታሰር ህሊና መቼም አይታሰር!!!
ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር!!!

የመከላከያ ሰራዊት ከፍተኛ አዛዦች በከፍተኛ ስብሰባ ተጠምደዋል::

የመከላከያ ሰራዊት ከፍተኛ አዛዦች በከፍተኛ ስብሰባ ተጠምደዋል::

August14,2015

sirag fergesa and samora
የመከላከያ ሰራዊት ከፍተኛ አዛዦች በአዲስ አበባ ከተማ ውስጥ በከፍተኛ ስብሰባ ላይ መጠመዳቸውን ከቦታው ያገኘነው መረጃ አስታወቀ:: በአዲስ አበባ ከተማ ከሃምሌ 25 ቀን 2007 ዓ/ም ጀምሮ በከፍተኛ የመከላከያ ሰራዊት አዛዦች ሳሞራ የኑስና ሲራጅ ፈርጌሳ ስብሰባ መካሄዱና በስብሰባው እንደመወያያ ርእስ ሁኖ የቀረበውም አዲስ ሰራዊት ቢጨመርም አብዛኛው የሚፈርስና የሚበታተን በመሆኑ አሁንም የሰራዊቱ ይዘት አነስተኛ ነው። እናንተ ምን እያደረጋችሁ ነው? ለምንድነው የማትቆጣጠሩት የሚል እንደነበር መረጃው አስረድቷል።
የክፍለ-ጦሮች አመራሮች የቀረበላቸውን ጥያቄ መመለስ እንዳልቻሉ የገለጸው መረጃው ስብሰባው ወደ ታች በመስመራዊ መኮነን ደረጃ ወርዶ በተለይ ከሻንበል በላይ በተደረገው ስብሰባ ላይ የሰራዊቱ መፍረስ ምክንያት በከፍተኛ የሰራዊቱ አዛዦች ውስጥ ብልሹ አሰራር፤ ወገናዊነትና አድልዎ በመኖሩ ነው ብለው መናገራቸው ተገልጿል።
መረጃው በማከልም- የበላይ የሰራዊቱ አዛዦች ከተራ ወታደሮችና የበታች የሰራዊቱ አዛዦች የነጠቁትን ገንዘብ የግል ኑሮአቸውን እያመቻቹበት ነው ተብሎ በስብሰባው በተነገረበት ግዜና የተሰጠውን ሃሳብ ተከትሎ የድጋፍ ድምፅ በተሰማበት ወቅት የመድረኩ መሪዎቹ ድንጋጤና ፍርሃት እንደተሰማቸውና በከባድ ስጋት ላይ በመውደቃቸው ምክንያት አመራሮቹ ስብሰባውን ለማካሄድ መቸገራቸውን መረጃው አክሎ አስረድቷል።

የማለዳ ወግ…ለአሚራና ቤተሰቦቿ የጎደለው ፍትህ … !

የማለዳ ወግ…ለአሚራና ቤተሰቦቿ የጎደለው ፍትህ … !

Augest 14,2015
Amira
Amira
==================================
* ህጻን የደፋረን የ4 ወር እስር መቅጣት ምን ይሉታል ?
* ፍርዱ ቅጣት ነው?  ወይስ ማበረታታት ?
* ህግ አውጭና አስፈጻሚ አካላት ወዴት ናችሁ?
* ወላጆቿ " ወላጅ ይፍረደን፣ህዝብና ሀገር ይፍረደን!"ይላሉ
የኢፊድሬ ህገ መንግሰት ሴቶች  ልክ  እንደ  ወንዶች  በሕገ-መንግሥቱ  እኩል  መብትና  ጥበቃ  እንዲሰጣቸው ይደነግጋል ትግበራውን መከታተልና ማስፈጸም ያለባቸው ህግ እውጭና አስፈጻሚ አካላት የሴቶችን መደፈር ለመከላከል የከበደ ኃላፊነት እንዳለባቸው ይህው የፈረደበት ህገ መንግስት ያስረዳል  ! ዳሩ ግና አልፎ አልፎ የሚሰማ የሚታየው የነገር ጭብጥ ውጤት ህግ አውጭና የሚያወጡት ህግ ደንብና መመሪያ ከወንጀል ፈጻሚው ባልተናነሰ በህግ አስከባሪና አስፈጻሚዎች ህጉ ይጣሳል ። ህግ ተጥሶ የዜጎች ሰብአዊ መብት መዳጡ  በአደባባይ እየተሰማና እየታየ ህግ አውጭ አካላት የሚወስዱት እርምት እርምጃ አያስደስትም ። የሴት ጠለፋ በተለይም በህጻናትና ታዳጊዎች ላይ የሚፈጸም አስገድዶ  መድፈር ዝርዝሩ ሰፋ ያለ ይሆናል ። ዳሩ ግን የህግ እውቀት ኖሮኝ ያንን ለመተንተን ባይዳዳኝም በህግ አስከባሪዎች ፍትህ እየጎደለ በዜጎች ላይ የሚፈጸመው በደል ዘልቆ ቢያመኝ እንደ ዜጋ በጎደለው ፍትህ ተቃውሞና በቅሬታየ ዙሪያ የዜጋ ድምጼን ማሰማት ግድ ብሎኛል ...
ዛሬ ዛሬ የምንሰማው ሰው በሰው ላይ ቀርቶ በእንስሳ ላይ መፈጸም የሌለበትን ርክሰት የተጠናወተው ወንጀል ጀሯችን ሆኗል ። በተለይ በአቅመ ደካማ ህጻናት ታዳጊዎችና በሴቶች ላይ የሚፈጸመው ወንጀል እያደር መክፋቱ  ጸሀይ የሞቀው እውነት ሆኗል። በዚህ ረገድ እየተኬደ ያለውን የከፋ ወንጀል ሳስበው " ወደ የት እየሄድን ይሆን?  " እያልኩ ያስፈራኛል  ! የአጉራ ዘለል አስገድዶ የመድፈር ወንጀለኞች መስፋፋት ፣ እያደር ውሎ አዳራችንና አብሮነታችን እንዳያጎድፈውም በአስፈሪ የታሪክ ምዕራፍ ላይ እንገኛለን  !  ሴሰኛ ወንጀለኛ ሽምጥ ጋልቦ  እዚህ ሲደርስ ወንጀሉን በጥብቅ ተከታትሎ የማያዳግም ቅጣት አርአያነት ያለው ውሳኔ ቢሰጥ ዛሬ እዚህ ባልተደረሰ ነበር ፣ ይህ አይፈጸምምና ፣ ይህ አልተደረገምና ዛሬ ውርደትን መከናነብ ግድ ብሎናል ።  የተከናነብነው ውርደት ምክንያት የሆነን ወንጀልም ሊሰሙት ከሚችሉት በላይ ሰቅጣጭና የከበደ እየሆነ ለመምጣቱ ብዙ ማሳያዎችን ማቅረብ አይገድም  !
ይህን ሁሉ የምለው በአንዲት የ4 ዓመት ከ6 ወር ብላቴና ተዳጊ ላይ የተፈጸመው ወንጀልና ተመጣጣኝ ያልሆነውን የፍርድ ውሳኔ ወደምቃዎምበት የማለዳ ወጌ የመረጃ ግብአት ለመዝለቅ ነው   ! እንደኔ የፍትህ መዛባት ዘልቆ ያመማችሁ ተከተሉኝና ፍርዱን ስጡ ... !
በያዝነው ሳምንት ማህበራዊ መገናኛ ድህረ ገጾችን ቀልብ የሳበው ጉዳይ መካከል የ4 ዓመት ከ6 ወሯ ታዳጊ  መደፈርን ተከትሎ የተላለፈው ዜና የብዙዎቻችን ቀልብ ስቧል ። ለዚህ መሰሉ ዜና አዲስ ባይንሆንም ብላቴናዋ  መደፈሯ ሳይሰማ ባሳለፍነው ሳምንት ሀሙስ  በመጨረሻ ው የፍርድ ውሳኔ ጋር ሰማን ፣ በውሳኔውም ደፋሪው የ4 ወር እስራት ቅጣት ፍርድ መሰጠቱን በአንድ ላይ ሲነገረን ማመን ከተቸገሩት መካከል አንዱ ነበርኩ።  የጉዳዩን ጭብጥ ለማጣራት ባደረግኩት ሙከራ ያገኘሁት መረጃ ይዠ የዜጋ ተቃውሞ ድምጼን በማለዳ ወጌ ላሰዳ ስውተረተር በድሬ ትዩብ ስሟን በመጥቀስ በጉዳዩ ዙሪያ የቀረበ አንድ ዘገባ ለወጌ መረጃ ግብአትነት ተጠቅሜበታለሁ ። ትክክለኛ ስሟ ስለመሆኑ ግን ማረጋገጫ አላገኘሁም ። ስሟ ቢታወቅም መግለጹ አስፈላጊ ባለመሆኑ የድሬ ትዮብን ስም ተቀብየ እዘልቃለሁ ።  ከዚሁ በተጨማሪ ሌላም ሌላ መረጃዎችን ለማሰባሰብና ለማጣራት ሞክሬ በእርግጥም ወንጀሉ ለመሰራቱና ፍርደ ገምድል ብይን የመሰጠቱ ሁነኛነት አረጋግጫለሁ  !
የተሰራጩ መረጃዎች እንደሚስረዱት ታዳጊዋን የ4 ዓመት ከ6 ወር ተዳጊዋን አሚራ ትባላለች ።  ኑሮዋም አዲስ አበባ አቃቂ ክፍለ ከተማ እንደሆነ ተጠቁሟል። ደፈረ የተባለው አስነዋሪ ወንጀል ፈጻሚ የ25 ዓመት ጎረምሳ ነው። በችርቻሮ ንግድ የሚተዳደሩት የአሚራ ቤተሰቦቿ ቤት ጎን ተከራቶ ነበር አሉ ።
ከውሳኔው አስቀድሞ ተከሳሽ አሚራን ስለመድፈሩ ክስ ቀርቦበት ፣ ጉዳዩ በፖሊስ ቀርቦና ተጣርቶ ተከሳሽ ተይዞ በፊዴራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት የአቃቂ ቃሊቲ ፍርድ ቤት ችሎት የቀረበ ሲሆን በ30 ሽህ ብር ዋስትና ተለቀቀ።  ክሱን በዋስ ወጥቶ እንዲከላከል በፊዴራድ  ከፍተኛ ፍርድ ቤት የአቃቂ ቃሊቲ ፍርድ ቤት ወሰነ ። ያ ከሆነ በኋላ ባሳለፍነው ሳምንት ተከሳሽ  ለብይን ቀረበ ። ፍርድ ቤቱ በፖሊስ የቀረበለትም ምርመራ ተመልክቶ በሰጠው ውሳኔ " ተከሳሽ ድንግልናዋን ባይገስም በእጆቹ የማህጸኗ ግድግዳ የመሰንጠቅና የመላላጥ  ጉዳትና ማድረሱና በማህጸኗ የመቅላት ምልክት በመታየቱ  !" በሚል ማስረጃ  ፍርድ ቤተ ተከሳሽን " ሞከርክ " በሚል ወንጀለኛ ሲል የ4 ወር እስራትን አስተላልፎበታል ። ይህው ፍርድ ቤት ገና የትምህርት ገበታ ያልቀመጠችን ታዳጊ ብላቴና አመራን  የደፈረበትን የጨካኝ ድርጊት ከደፈረ ሞከረ ቀይሮ በቀረበ ማስረጃ በፍትሀ ብሔር ህግ 6264 ሀ መሰረት ውሳኔ መሰጠቱ ተነግሮናል ። አስገራሚ ፣ አስደንጋጭና አሳዛኝ የፍርድ ውሳኔ !
ክሱን አቀለለ ወደተባለው ምክንያት ስንሄድ ደግሞ ይበልጡኑ እንታመማለን ... ወንጀለኛው  " የሳንባ ነቀርሳ በሽተኛና በቀጣዩ አመት ተመራቂ !" መሆኑን በቅጣት ማቅለያነት አቅርቦ በፍርድ ቤቶ ተቀባይነት ማግኘቱ አገኘ ብለውናል  ። ለእኔ  የክስ ማቅለያ የቀረበው ሀሳብ የተማረ የተመራመረው " የዩኒቨርሲቲ ተማሪ " ነኝ ባይ ወንጀለኛ ነው ፣  ምንም የማታውቅን እምቦቃቅላ ታዳጊ ገላን በአሻው መንገድ አድርጎ ገፎታል ፣ ገፈፋውም የተፈጸመው በአንድ አዋቂ መሆኑ ብቻ ወንጀሉን ሊያከብድ እንጅ ሊያቀል ባልተገባ ነበር ባይ ነኝ ። ይህ ያቀረበው የክስ ማቅለያ ይልቁንም በሰነድ ተረጋግጦ ክሱን ማጠንከር ሲገባው ክሱን ማቅለያ ሆኖ መቅረቡና ከምን ወደ ምን እንደቀለለ ያልተገለጸው ማቅለያ ተቀባይነት ማግኘቱ በራሱ  በምንም ሚዛን ፍትሃዊነት የለውም  ! ይህን ለመናገር ሰብእናና የራስን ፍርድ መስጠት እንጅ ግዴታ ህግ ማጥናት አያስፈልገውም ...
የህዝብን መብት ለማስጠበቅ የተሰየሙትን የፍትህ አካላት የሙያ ብቃት ጥያቄ  ውስጥ የጣለው ይህ መሰሉ አሳዛኙ የፍትህ ውሳኔ ማህበረሰቡ በፍትህ እንዳይተማመን ከማድ ረግ ባሻገር በህግ ጥላ ስር መጠበቁን በጥርጣሬና እንዲ ያይ እንደሚያደርገው ጥርጥር የለኝም ። ከዚህም አልፎ ተርፎ በአሚራ ደፋሪ ላይ የተላለፈው ውሳኔ ሀገሬው  ፍትህ አጥቶ የሚንገዋለል እንዲሆን አድርጎታል ወደሚል መደምደሚያ አድርሶኛል ... የአስገድዶ መድፈር ወንጀለኞ ች ጉዳይ መስፋፋትና ገደብ ማጣት በተደጋጋሚ በመንግ ስት ላይ የሰላ ወቀሳ ይቀርባል ። በተለይም የህግ ጥበቃ ውንና ቅጣቱን ከማጠንከሩ በተጓዳኝ ተማኝነት እንጅ የሙያ ብቃት ሚዛን ሆኖ ቅጥር ስለማይፈጸም ተደጋጋሚ ችግሮች ተስተውለዋል ። የፍትህ አካላት ብዛት እንጅ ጥራት የጎደላቸው መሆኑ ከዚሁ ጋር ይጠቀሳል ።  የተባለውን ወቀሳ እውነታነት እንዳለው ለመረዳት የአሚራን አይነት በደል ተሰርቶ የተሰጠውን ውሳኔ መመልከት ብቻ  ማየት ከበቂ በላይ ይመስለኛል  ።
በአሚራ ውሳኔ አሰጣጥ  እንዳየነው ከምንም በላይ የፍትህ ስርአቱ በወንጀለኛውም ሆነ በጠበቆች የቀረበውን የተውተፈተፈ መከላከያና ቅጣት ማቅለያ መቀበላቸው ለፍትህ አካላት የደረሱበትን ደረጃ ያሳይ ከሆነ መልካም ነው ። የአሚራን ጉዳይ በግርድፉ ላየ ለተመለከተው   ጥፋታቸውን በአዞ እንባ ለመሸፋፈን ከተጉ ወንጀለኞች ጎን ለገንዘብ ብለው ጥፋቱን ለማቅለል ሚሞግቱት ጠበቆች ሰብዕና ያማል ፣  የዳኞቹ ውሳኔ አሰጣጥና ውሳኔ ማቅለያ አቀባበል ደግሞ  ይገርማል ፣ ይደንቃል ... !  ይህ መሰል ከእውነታው ጋር የሚጋጭ የተፋለሰ ፍርድ  በአደባባይ ሲሰጥ ህጉን ማስከበር ያለባቸው አቃቤ ህግ ተወካዮች የታሉ  ? ፍትህ ወዴት ነህ  ?  ያስብላል ...
በሰብዕና ላይ ወንጀል ሲሰራ በቸልተኝነት መመልከት ሊቆም ይገባል ።  የሴቶችን መብት ለማስከበር ተብሎ የወጡት ሕጎች  ተፈጻሚ  ይሆኑ ዘንድ  የኢትዮጵያ  ሰብአዊ  መብት  ኮሚሽን  አካል  የሆነ  የሴቶችና ሕጻናት  ጉዳዮች  ብሔራዊ  ኮሚሽንን  በ2005  ዓም መቋቋሙን ከሰማን አመታት ተቆጥረዋል ።  ኮሚሽኑ በሴቶችና  በሕጻናት ለሚፈጸሙ የሰብአዊ  መብት  ጥሰት  ተገን እንደሚሆን ቢጠቀስም ለአሚና የጎደለ ፍትህ ድምጹን ሲያሰማ አለመታየቱ ግር ያለው እኔን ብቻ ከሆነ መልካም ነው ፣ ግን አይመስለኝም ። " መብቷ ይከበር ፣ ፍትህ ጎድሎባታል፣  ፍትህ ታግኝ " የምንላት  ታዳጊዋ አሚራ ያለ ፈቃዷ አይደለም ገላዋ የጸጉር መጠምጠሚያ "ሂጃቧ " ሊነካ አይገባም ፣ ከተነካ ህግ ተጥሷል ! አሚና ድንግልናዋ አልተገሰሰም ፣ ማህጸኗ ግን ተነካክቷል ብሎ ወንጀለኛን ከአስገድዶ መድፈር ወንጀል ማራቅ ፣ ማሸሸት ፍትህን ማረጋገጥ ሳይሆን ፍትህን ማርከስ አድርጌ ነው የምቆጥረው ።  ወንጀለኛው " አስገድዶ የደፈረ " ለመባል አሚራ በጭካኔ ተደፍራ እንደተገደለችው እንደ ሀና ኦላንጎ መሆን አልነበረባትም  ! አሚራም ሀና እንደሆነችው ባትሆንም በአሚራም ማህጸን ዙሪያ ክብረ ነክ የመድፈር ሙከራ አድርጓል ። የቀረበው ማስረጃ የሚየስረዳው አርቆ አሳቢው የተማረ ጎልማሳ ምንም በማታውቀው የ4 ዓመት ከ6 ወር ታዳጊ ህጻን ላይ ወንጀል አስገድዶ መድፈር ለመሆኑ ሌላ ከበቂ በላይ ማስረጃ  አለ ብየ አላምንም!
የሴቶችና ሕጻናት  ጉዳዮች  ብሔራዊ  ኮሚሽንን  ሴቶች  ሥርዓተ-ፆታን  መሠረት  ያደረገ  ጥቃት ደርሶባቸው እንዲህ ሲመለከት አብሮ ከተጎጅ ወገኖች ጎን  መቆም ፣ የሕግ  ጥበቃ  ማቆም ፣ የህግ ጠበቃ የማቆም አቅም ከሌለው  የህግ ጥሰቱን በአደባባይ ተቀውሞ ስታዳጊዋ ብላቴና ስለአሚራ ፍትህ ማግኘት ድምጹን ሊያሰማ ይገባል !
በፍርድ ገምድሉ ውሳኔ ያዘኑ ቤተሰቦች  ወላጆቿ ፍትህ ጎድሎባቸው " ወላጅ ይፍረደን፣ህዝብና ሀገር ይፍረደን!" ማለታቸው ስሰማ የእነሱም ጩኸትና አቤቱታ የእኔም ለአሚራና ቤተሰቦቿ ፍትህ ርትዕ ይከበርላቸው የሚል ጥያቄ እንዳነሳ አድርጎኛል  ! ከምንም በላይ የሴት ልጅ በረከት የታደልኩ አባት እንደመሆኔ የሴት ልጅን ወሰን የሌለው ፍቅር አውቀዋለሁና ከአሚራ ቤተሰቦች ጋር ልቤ በሀዘን ተሰብሯል ፣ በጎለው ፍትህ አምርሬም አዝኛለሁ ... !
ፍትህ ለህጻን አሚራና ቤተሰቦቿ ስል እጠይቃለሁ  !
ነቢዩ ሲራክ
ነሀሴ 5 ቀን 2007 ዓም