Friday, October 30, 2015

የህወሃት ባለስልጣናት በከፍተኛ ደረጃ ዶላር እያሸሹ ነው

October 30, 2015

በሰሜን አሜሪካ በህግ ወጥ የኮንትሮባንድ ንግድ ለአንድ ዶላር በ23 ብር እየቀየሩ ሃብታቸውን በማካበት ላይ እንደሚገኙ ታወቀ።
የኢህአደግ ስረአት ባለ ስልጣኖች ሃብታቸውን ከውስጥ ሃገር ለማውጣት እየተጠቀሙት ያለውን ስልት የኢትዮጵያ ባንኮዎች ከመጉዳት ባለፍ በአሁኑ ወቅት የአገሪቱን ኢኮኖሚ ከባድ ችግር ውስጥ አስገብተውት እንደሚገኙ የገለጸው መረጃ: በአሁን ጊዜ የኢህአዴግ ባለ ስልጣኖች በሙስና ያጠራቀሙት ሃብት ወደ ዉጭ በማጓጓዝ ላይ ተጠምደው ባሉበት ግዜ ከሰሜን አሜሪካ ወደ ኢትዮጵያ ከመጠን በላይ በኮትሮ ባንድ ንግድ ለአንድ ዶላር በ23 ብር እንመነዝርላችሓለን በማለት በህዝብ ሃብት በመጫወት ላይ ኣንደሚገኙ ለማወቅ ተችሏል።
TPLF Ethiopian Leaders
መረጃው አክለዉ እንዳመለከተው በአሁኑ ጊዜ፡ በዋሽንግተን፤ በዱሲ፤ ስያትል፤ ዴንቭር፤ ሚኒያፖሊስ፤ አትላንታ፥ ቺካጎ፤ በሂውስተን፤ ኦሃዮ፤ ፓርትላንድ፤ ላስቬጋስ፤ ካልፎርኒያ እንዲዚሁም በተለያዩ ከተሞች በአሪዞና በተዘረጉት መረቦች መረጃ ዶላር በኮትሮ ባንድ ንግድ በ23ብር እየተመነዘር መሆኑን መረጃው አስታውቀዋል።
በመጨረሻም አንድ የአሜሪካ ዶላር በህጋዊ መንገድ ብ20.85 ብር እየተመነዘር ቢሆንም በሌቦች የኢህአድግ የገዢው ስረአት ባለ ስልጣናት ግን ዶላር ያለ ህጋዊ መንገድ የኢትዮጵያ የውጪ ምንዛሬ ያለ አግባብበ በመቀየራቸው የተነሳ የሃገር ውስጥ መንዛሪ ከፋተኛ እጥርት እያጋጠመ እንዳለ የተለያዩ ህዝቦች በመግለፀ ላይ ይገኛሉ::

Andargachew Tsege ‘fears he will die in Ethiopia’

October 27,2015
A British man locked up for more than a year in Ethiopia fears he could die in prison.
Andargachew “Andy” Tsege, a father-of-three, has been detained in the country since he was removed from an airport in Yemen in June 2014.UK “stands shoulder to shoulder” with Ethiopia
Legal charity Reprieve said the 60-year-old asked the British Government to ensure that he is buried in England and told his children to “be brave” during a recent visit by the UK ambassador.
Mr Tsege, a prominent critic of Ethiopia’s ruling party, was sentenced to death in his absence in 2009 for allegedly plotting a coup – charges he and others deny.
The trial has been described as “lacking in basic elements of due process”.
He fled Ethiopia in the 1970s, seeking asylum in the UK in 1979.
Maya Foa, head of the death penalty team at Reprieve, said: “It is tragic that he now feels the only way he will return home to Britain is in a coffin.
“The Foreign Office must urgently push for his release, so he can return to his partner and children in London before it’s too late.”
Last week, Foreign Secretary Philip Hammond discussed the case with the Ethiopian Foreign minister.
Mr Hammond said: “I raised the case of Andargachew Tsege with the Ethiopian Foreign Minister during our meeting on October 21, and made it clear that the way he has been treated is unacceptable.
“I welcome the improvement in access to him, following the British Government’s intervention, but it must be more regular and it must include access to a lawyer.
“I am still not satisfied that Mr Tsege has been given an ability to challenge his detention through a legal process, and this is something we are continuing to pursue.
“The Foreign Office will continue to provide consular support to Mr Tsege and his family.”
Source: BT.com

Sunday, October 25, 2015

“ተመስገንን ማየት አትችሉም!” (ታሪኩ ደሳለኝ)

“ተመስገንን ማየት አትችሉም!” (ታሪኩ ደሳለኝ)

ታሪኩ ደሳለኝ – አዲስ አበባ
ወንድማችን ተመስገን ሀሳቡን በነጻነት ስለገለጸ እና ጽሁፎችን በጋዜጣ ስላተመ ብቻ ሶስት ዓመት ተፈርዶበት ወደ ዝዋይ እስር ቤት ከተላከ ዛሬ 374 ቀናት ሆነው፡፡ በተለያየ ጊዜ ተደጋጋሚ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች ቢደርስበትም ሁሉን ችሎ ዛሬ ላይ ደርሷል፡፡ ለሚያሰቃየው የወገብ እና የጆሮ ህመም ህክምና ሳያገኝ ዛሬም ህመሙን እየታገለ አለ፡፡ የታሰረበትን አንደኛ ዓመት በማስመልከት ይህንን ችግሩን እና የሚደርስበትን እንግልት አስመልከቶ እኛም፣ ወዳጆቹም ለመናገር ሞክረናል፡፡ አቤቱታችንን እና ጩኸታችንን ተከትሎ ችግሮቹ ይስተካከላሉ ብለን ብናስብም ይባስ ብሎ በገደብ የተፈቀደለት የቤተሰብ ጥየቃ እንዳያገኝ ከዚህ ሳምንት መጀመሪያ ጀምሮ ተከልክሏል፡፡Temesgen Desalegn "Fact" Ethiopian Amharic newspaper editor
ወንደሞቹ ወደ ዝዋይ እስር ቤት ተመላልሰን ያጋጠመንን ከዚህ በታች አንብቡት እና እናንተው ፍረዱ፡፡ አንዴ አይደለም ሁለት፣ ሶስት፣ አራት ጊዜ “አይቻልም” ተብለናል፡፡
ክልከላ 1፡- እሁድ ጥቅምት 7/ 2008 – ጠዋት ታላቅ ወንድማችን ዝዋይ ሰደርስ በአዋራና በፀሀይ ተቃጥሎ ነበር፡፡ የዝዋይ እስር ቤት መንገድን የቀመሰ ያውቀዋል፡፡ የእስር ቤቱ መግቢያ በር ላይ የተጠያቂ ስም ሲያስመዘግብ “ተመስገን ደሳለኝ” አለ፡፡
“እሱን መጠየቅ አይቻልም” አለ መዝጋቢው የእስር ቤት ወታደር፡፡
“ለምን?” ጠየቀ ወንድማችን፡፡
“ትላንት ማታ የደረስን ትዕዛዝ ነው”
“ማነው ያለው?”
“ከበላይ ነው”
“ምን ማለት ነው?”
“በማንም እንዳይጠየቅ ማለት ነው፡፡ አሁን ተመለስ” የእስር ቤቱ ወታደር ቆፍጠን ያለ ትዕዛዝ ሰጠ፡፡
“እሺ ምግቡን ላስገባ” ወንድማችን በመጨነቅ ጠየቀ፡፡
“አይቻልም” ቁርጥ ያለ ክልከላ፡፡
ክልከላ 2፡- ሰኞ ጥቅምት 8/2008 – ሌላኛው ወንድማችን ወደ ዝዋይ እስር ቤቱ አቅንቶ “የተመስገን ወንድም ነኝ” ሲል ፈጣኝ ምላሽ ተሰጠው፡፡
“የያዝከውን ምግብ ይዘህ ቀኝ ኋላ ዙር” ከጠባቂዎቹ ወታደሮች አንዱ የሰጠው መልስ ነበር፡፡
“በምን ምክንያት?” ወንድማችን ጠየቀ፡፡
“አይመለከትህም!”
“ወንድሜ እኮ ነው!”
“እናውቃለን፡፡ ትዕዛዝ ነው!”
“እሺ ምግቡን እንኳን ላስገባ”
“አይቻልም፡፡ ውጣ!”
ክልከላ እና ፍቃድ መሳይ 3፡- ማክሰኞ ጥቅምት 9/2008 – ከአዲስ አበባ በጠዋት ተነስቼ ረፋድ ላይ ዝዋይ እስር ቤት ደረስኩ፡፡
“ተመስገን ጋር ነው የምገባው” አልኩኝ ለተረኛ መዝጋቢ ወታደር፡፡
“ምኑ ነህ?”
“ወንድሙ”
“ግባ” አላምንኩም!
የያዝኩትን ምግብ አስፈትሼ ከሩጫ በማይተናነስ እርምጃ ተመስገን ወደሚጠየቅበት ታዛ ፈጠንኩ፡፡ ለወታደሮቹ እንዲጠሩልኝ ስሙን ሰጥቼ ተቀመጥኩኝ፡፡ ተሜ ሳይመጣ 40 ደቂቃ አለፈ፡፡ አንድ ወታደር በብስክሌት መጥቶ “ተነስና ውጣ፡፡ በስህተት ነው የገባኸው” አለኝ፡፡
ከተሜ በሜትሮች ርቀት ያህል ርቀት ተቀምጩ ሳላየው መውጣቴ ቢያስጨንቀኝም እኔም እንደወንድሞቼ ከመጠየቅ ወደኋላ አላልኩም፡፡
“ማነው አይጠየቅም ያለው?”
“ትዕዛዝ ነው” ባለፉት ሁለት ቀናት ስንሰማው የነበረው ተመሳሳይ መልስ ተሰጠኝ፡፡
“እሺ የያዝኩትን ምግብ ላቀብለው”
“አትሰጠውም”
“እሺ ከኃላፊ ካለ አገናኘኝ” አልኩት ወታደሩን
ወታደሩ አጠገቡ ካለው ወታደር ጋር በአይኑ ተነጋግሮ በምልክት ቢሮውን አሳየኝ፡፡ የያዝኩትን ስንቅ አስቀምጩ “አስተዳዳር” የሚል ጽሁፍ በሩ ላይ ከተለጠፈበት ክፍል አንኳኩቼ ስገባ ሰባት በኃላፊነት ደረጃ ላይ እንዳሉ ማዕረጎቻቸው የሚያሳብቁ ወታደሮች ተሰባስበው አገኘኋቸው፡፡
የሰብሳቢ ወንበር ላይ ፈንጠር ብሎ የተቀመጠው ወታደር “ምንድነው?” አለኝ
“ወንድሜን አትጠይቅም ተብዬ ነው” መለስኩ፡፡
“ማነው ስሙ?”
“ተመስገን ደሳለኝ”
የተማከሩ በሚመስል ሁኔታ አንድ ላይ “እሱን መጠየቅ አይቻልም” አሉኝ፡፡
“ለምን?”
ሰብሳቢው ወታደር “አያገባህም” ብሎኝ አጠገቡ ያለውን መገናኛ ሬድዬ አንስቶ “የጋዜጠኛ ተመስገን ወንድም ነኝ ባይ እንዴት እዚህ ድረስ መጣ” ሲል ጠየቀ፡፡
የሬድዮን መልስ ልሰማ ስል “ውጣ እና በር ላይ ጠብቀኝ” አለ ወጣሁ፡፡
እኔ ከወጣሁ ከ15 ደቂቃ በኋላ ሁለት ሬድዮ የያዙ ወታደሮች መጥተው ወደ መጠየቂያው ቦታ በድጋሚ ወሰዱኝ፡፡ ስደርስ ተሜ በስድስት ወታደሮች ተከቦ አገኘሁት፡፡ እኔን ካመጡኝ ወታደሮች ጋር ሲደመሩ ስምንት ሆኑ ማለት ነው፡፡ ከተሜ ጋር ሰላምታ ተለዋውጠን ማውራት ጀመርን፡፡
“ማዘር ምን ሆና ነው ያልመጣችሁት?” ጠየቀ ተሜ፡፡
“ኧረ! ምንም አልሆነችም፡፡ ከእሁድ ጀምሮ አትገቡም ብለውን ነው” አልኩት፡፡
ተሜ ወታደሮቹን እየተመለከተ “ለምንድነው የተከለከልኩት?” አለ፡፡
ሬድዮ የያዘው ወታደር ወደ እኔ እየተመለከተ “አሁን እሱን አናግረው” አለው፡፡
“ጉዳዩ ከእሱ ጋር አያይዝም” ተሜ መለሰ፡፡
ወታደሩ ወዲያውኑ “ተነስ” አለኝ
“ወዴት?” አልኩት
ተሜ ጣልቃ ገብቶ “ጉዳያችሁ ከእኔ ጋር መሰለኝ” አላቸው፡፡
መልስ አልመለሱትም፡፡ አንደኛው ወታደር ወደ እኔ ዞሮ “አንተ ሂድ” አለኝ፡፡
ሶስተ ደቂቃ በማይሞላ መተያየት ከሰላምታ የዘለለ ነገር እንኳ ሳናወራ ለመውጣት ተነሳሁ፡፡ የተሜን አይን አይን እያየሁ ሰወጣ ተሜ ስምንት ወታደሮች እንደከበቡት እያወራ ነበር፡፡ ምን እንደሚል መስማት አልቻልኩም፡፡ ከእስር ቤቱ ወጣሁ፡፡
ክልከላ 4፡- ሐሙስ ጥቅምት 11/ 2008 – ሰኞ ዕለት ተሜን ሳያይ እንዲመለስ የተደረገው ወንድማችን ዝዋይ እስር ቤት ሲደርስ ገና ከበር “ተመስገንን መጠየቅ አይቻልም” አሉት፡፡
“ማክሰኞ ወንድሜ ገብቶ ነበር”
“አልገባም፡፡ ገብቶም ከሆነ በስህተት ነው”
የሚለው ሲያጣ “እሺ ያመጣሁትን ስንቅ ላቀብለው”
“አይቻልም ተመለስ”
ከሰኞ እስከ ሐሙስ በተደጋጋሚ ተሜን ለማየት እና ስንቅ ለማቀበል ያደረግነው ሙከራ እንግዲህ ይህን ይመስላል፡፡ “ይህ ተመስገናችሁ የእኛ እስረኛ ነው፡፡ እኛ ደግሞ ህክምና እንደከለከልነው፣ መርጠን በሰው እንዳስጠየቅነው፤ ዛሬ ደግሞ ማንም እንዳይጎበኘው ማድረግ መብታችን ነው፡፡ ስለዚህ ከዚህ በኋላ ማንም እሱን መጠየቅ አይችልም” ብለዋል የዝዋይ እስር ቤት ሹሞች፡፡
ተሜ ህገመንግስታዊ መብቱ ተገፍፎ፣ ሰብዓዊ መብቱ ተጥሶ እና በህመም እየተሰቃየ እስከመቼ ነው የሚቀጥለው?

Tuesday, October 20, 2015

አገርንና ወገንን የሚያስቀድም ትውልድ ማነጽ የሁሉም ኃላፊነት ነው ። የፍኖተ ራዲዮ ዘገባ ( http://finote.org )ጥቅምት  2008 ዓም
አገርንና ወገንን የሚያስቀድም ትውልድ ማነጽ የሁሉም ኃላፊነት ነው
ከግማሽ   ምዕተ- ዓመት ያላነሰ ትግል ሲያካሂድ የቆየው ትውልድ፤ በተፈጥሮ ህግ ምክንያት፤ ቀስ በቀስ ሳያውቀው በሞት እየተለየ በመሄድ ላይ  ይገኛል ተኪውን ሳያዘጋጀ ቢያልፍ አገሪቱ ከባድ አደጋ ውስጥ ትወድቃለች። ይህ ትውልድ ሳይተካ ከሄደ ፤ ሀገሪቱ መፃዒ እድሏን  ሊረከብ   የሚችል  ትውልድ    እያጣች  ትሄዳለች ማለት ነው። ስለሆነም በዚህ በኩል መፍትሔ መፈለግ ይኖርበታል ለዚህ መፍትሄ ካልተገኘ ደግሞ፤ ሀገርን ማዳን ቀርቶ ራስንም እንኳን ቢሆን ከአደጋ መከላከል የሚቻል አይሆንም። የታጋዮች መዳከም   ወያኔ፤ ጠላቶቹን ለየብቻ እየነጣጠለ  ለመምታት ምቹ ሁኔታ የፈጠረለት ሲሆን  የወጣቱን ትውልድ አዕምሮ ለመስረቅ ዕድል ገጥሞታል  ። የተተኪውን ትውልድ  አዕምሮ ከመስረቅ የበለጠ፤ ሀገር የማጥፋት  ወንጀል ደግሞ  ሊኖር አይችልም  
አገርን የማያስቀድም ትውልድ ይዞ  ወደፊት  መራመድ ቀርቶ፤ መኖር እንኳን የሚቻል አይደለም።  የኢትዮጵያ ታሪክ፤ ብሎ  የጀመረው፤ ወያኔ እምኒልክ ግቢ ከገባ በኋላ ነው ብለው ለሚናገሩ ከንቱ ፍጡራን፤ ያሻቸውን እንዲዘላብዱ  ተመችቷቸዋል  ጋኖቹ አልቀው ምንቸቶች ጋን በሆነባት ሀገር፤ ይህ መሆኑ ደግሞ አያስገርምም። "ዛፍ በጠፋበት ሀገር፤ ቁጥቋጦ መሆኑ " የተለመደ ነው።  ዛፍ ለመሆን የተዘሩትን ቡቃያዎች፤ ደርግ  ስለጨፈጨፋቸው፤ ወያኔዎቹ ባድማ አገኙና ሰተት ብለው ገቡ። ከዚያ በኋላ የሆነውን በመዘረዘር ጊዜ ልናጠፋ አይገባንም   የሚያውቀው ያውቀዋልና ! ሊያውቅ  የማይፈልግ ደግሞ ራሱን እያተለለ ይኖራል መኖር አይበለውና !
አንድን ሀገር፤ ህያው ሆኖ ሊኖር የሚያስችለው፤ የዜጎቹ ህልውና ተከብሮና ተረጋግጦ ሲቀጥል ነው የዜጎች ነፃነትና የሀገር ኅልውና ተለያይተው ሊታዩ የሚችሉ አይደሉም   የኅልውና ትርጉሙ፤  ከነፃነት መከበር ጋር ካልታየ ትርጉም የለሽ ሆኖ ይቀራል። የሀገሪቱ ዜጎች ናቸው ተብለው  የሚቆጠሩት በወቅቱ የሚኖሩት ሰዎች ብቻ ሳይሆኑ፤  ያለፈውን  ዜጋና  የሚመጣውን ተተኪ  ትውልድ ሁሉ የሚያካትት መሆንኖርበታል።
ሦስቱንም ተከታታይ ዜጎች በአንድ ሀገር የታሪክ ምዕራፍ ውስጥ አስገብቶ ካልተነበበ፤ የሀገሪቱን  ታሪክ በተሟላ ዕይታ ለማየት ያስቸግራል  የልጅን፤ የአባትን፤ የአያትንና  የቅድመ-አያትን ታሪካዊ  ቅደም- ተከትል  ትስስርና  ተወራራሽነት  እያገናዘቡ  እያከበሩና  እያስከበሩ ካላስተላለፉት ኢትዮጵያዊነት  ባዶ ነበቢት ከመሆን አያልፍም ዛሬ የሚፈለገው ግን  ይሄ ሆኗል። አኩሪ ታሪክን እያጠፉ፤ በአሳፋሪ ታሪክ መተካት፤  የኢትዮጵያን መሠረታዊ ኅልውና ማጥፋት ነው። የሀገራችን ዋልታና ማገር ደብዛው እንዲጠፋ እየተደረገ ነው። ዐማርኛ ቋንቋንና ሃይማኖትን ማጥፋት፤ የሀገሪቱን ዋልታ ከማጥፋት ጋር የተየያዘ ነው።
 17 ዓመት የደርግ አምባገነን አገዛዝና የወያኔው 24+ ዓመታት ዘረኛ ሥርዓት ሲደመር፤ 41+ ዓመት መሆኑ ነው። በዚህ የዘመን ገደብ  እያደገ የመጣው  ትውልድ የሀገሪቱን ጠቅላላ ሕዝብ   (Demography  ) ቁጥር ከፍተኛውን  % እንደያዘ  ይገመታል    ይህም  ማለት፤   የሀገሪቱ ዜጋ በአመዛኙ በወጣት ትውልድ የተመላ ነው ማለት ያስችላል።
 ይህ ትውልድ የሁለት አምባገነን እኩይ ሥርዓቶች ሰለባ ሆኗል። በሰው -በላው የደርግ ጭካኔ፤  በፍርሃት  እየተሸማቀቀ ያደገውና፤ ዛሬ ደግሞ፤  በዘረኝነት የተበከለ ሥርዓት ውስጥ ገብቶ  በማደግ ላይ  ያለው ወጣት ዜጋ ነው የሁለት ሥርዓቶች  ሰለባ/ተጠቂ  የሆነው ትውልድ፤ ሁለት መሠረታዊ ችግሮች  እንዳሉበት ይገመታል 
ደርግ፤ የፍርሃትንና  የመሸማቀቅን ባኅርይ አውርሶ ሲሄድ፤  ወያኔም  በበኩሉ፤ በዘርና በጎሣ መርዝ  እየተበከለ እንዲያድግ  እያደረገው ይገኛል። ያንዲቱ ሀገር ኢትዮጵያዊ ዜጋ መሆኑ እየቀረ፤ ሁሉም፤ በየጎጡና በየአካባቢው አድማስወስኖ እንዲያምን  እየተደረገ ነው።  የቆየችዋን ጥንታዊ ሀገር እያፈራርሱ፤  በአያሌ ዘመናት ባንድ ላይ አብረው የኖሩትን ዜጎች በዘር እየከፋፈሉና እየበታተኑ፤ አዲሱን  ትውልድ፤  በኢትዮጵያዊነት ስሜት ሳይሆን፤ በየዘር- ማንዘሩ፤ በየጎጥ -ጎጥጎጡ፤  በየማጀቱና ስራ- ስሩ ተከልሎ የአስተሳሰብ ድሃ ሆኖ እንዲቀር እየተደረገ ነው። ይህ የዘረኞች ዕቅድ፤ የኋላ-ኋላ እንደሚከሽፍ የኢትዮጵያ ሕዝብ ባይጠራጠርም፤ክሎት የሚሄደው መርዝ ግን በቀላሉ የሚነቀል አይሆንም።
ከመሥዋዕት  የተረፈው  አብዮታዊ ትውልድ፤ የስድሳ ስድስቱ ሕዝባዊ  አመፅ ያነሳቸው መሠረታዊ ጥያቄዎች ባለመመለሳቸው በፅናት ትግሉን ቢቀጥልም፤ ተተኪውን ኢትዮጵያዊ ትውልድ የማዘጋጀት ኃላፊነት እንዳለበት በአንክሮ ይገነዘባል። ተተኪውን ትውልድ፤  ኃላፊነት እንዲሸክም  ማዘጋጀት ምን ያህል ብርቱ ጥረት እንደሚጠይቅም  ከልብ ያምናል። ሰፊ የትውልድ ክፍተት(Generation Gap  ) እንዳለም የሚስተው አይደለም የኢትዮጵያ  ብሄራዊ ስሜት  እየተሸረሸረ፤ ወጣቱ ትውልድ፤ ዘርንና ቋንቋን መስፈርት ባደረገ ፕሮፓጋንዳ አዕምሮው እየተበረዘ መሆኑንም በሚገባ ተረድቶታል የዚህ ሁሉ ድምር ወጤት ሁኔታዎቹን  ይበልጥ ውስብስብ  ሊያደርገው  እንደሚችል ጥርጥር አይኖርም። 
ውስብስብነቱን በጣጥሶ  ለማስወገድ የዚህ ሁሉ መርዝ ምከንያት የሆነውን ጠንቀኛውን ዘረኛ ሥርዓት መነጋግሎ መጣል አማራጭ የሌለው ጉዳይ ነው።  ዘረኛውን አምባገነን አገዛዝን ማስወገድ ቅድሚያ ሊሰጠው የሚገባ መሆኑ እንደተጠበቀ ሆኖ፤ ወጣቱን ትውልድ፤ በኢትዮጵያ ሀገራዊ ስሜት እንዲደራጅ ማድረግ ደግሞ ራሱን የቻለ ዐብይ ሥራ ነው። ይህ ዐብይ ተግባር ዐይኑን አፍጥቶ የሚጠብቀውም፤ በኅብረ- ብኄር ለተድራጁ  ድርጅቶችና ስብስቦች መሆኑ ግልፅ ሁኗል።
ይህ ግንዛቤ ካለ፤ ኅብረ- ብኄር ድርጅቶች፤ ሀገርን ለማዳን ብቻ ሳይሆን፤ ተተኪውንም ትውልድ  ከጥፋት ለመከላከል ሲባል እንኳ አብሮ መስራት ግዴታቸው እየሆነ መጥቷል። ተተኪውን ትውልድ፤ ለነገዋ ኢትዮጵያ ዛሬ ማዘጋጀት ካልተቻለ፤ ሀገር ማዳን የሚባል  ተስፋ ሁሉ ከምኞት በላይ  አያልፍም ባለ ራዕይ ሆኖ አስቀድሞ ሊመጣ የሚችለውን አደጋ ማስጠንቀቅ ካልተቻለ፤ አደጋው በሚከሰትበት ወቅት፤ የሚይዙትንና የሚጨብጡትን  ማጣት ይሆናል። ዕውር-ድንብሱን  የሚደረግ እንቅስቃሴ፤ የዳፍንት ጉዞ ከመሆን አያልፍም ጠላትንና ወዳጅን  እየለዩ ካልታገሉ፤ ወዳጅ ያሉት እየከዳ፤ ጠላት ያሉት እያበጠ ይሄዳል። ይህ ሁኔታ ደግሞ ሕዝቡን  ይበልጥ ተስፋ ማስቆረጡ አይቀርም የዚህ ሁሉ ሂደት ተጠቃሚ ሊሆን የሚችለው፤ ወያኔ ብቻ እንደሚሆን መገንዘብ ይገባል 
ትክክለኛ በመሆንና ጠላትን በማሸነፍ መካከል ያለውን ሚዛን  ጠብቆ ካልተሄደ " የሞራል  ልዕልና "   መያዙ ብቻውን ውጤት አያስመዘግብም  ውጤት ማስመዝገብ ካልተቻለ ደግሞ፤ የዘመንን ብዛት ማስቆጠሩ ብቻ የትም አላደረሰም። የሦስት ሺህ ዓመታት ትረካ፤ አሁን ካለንበት ደረጃ እልፍ ሊያደርገን አልቻለም    በኋላችን የነበሩ አያሌ ሀገሮች እየጣሉን መሄዳቸውን ተገንዝበን    ዕመርታ ለውጥ አምጥተን ማንነታችን በገቢር ካላስመስከርን፤ የተፈራራቂ አምባገነን ሥርዓቶች  ሰለባ ከመሆን  አንድንም
 ሁልጊዜ ሠላማዊ ሰልፍ በማድረግ፤  ለዓለም ኅብረተስብ የአቤቱታ ደብዳቤዎች መፃፋችን የቱን ያህል እንደተናቅን፤ እንደተዋረድንና  ትዝብት ላይ እንደወደቅን  ማውቅ አለብን። 
ሰሞኑን፤ በሊባኖስ ዋና ከተማ፤ ቤይሩት አይሮፕላን ማረፊያ ላይ  በመሰደድ ላይሉት በርካታ ኢትዮጵያውያት ወጣት እህቶቻችን  ምን ያኅል  የአደባባይ ውርደት እንደገጠማቸው ስንመለከት፤ የልብ ውጋት፤ እና የመንፈስ ስብራት  እንዳስከተልብን ከእኛ በቀር ሌላ ሊረዳልን አልቻለም አይችልምም 
 የሥርዓት ለውጥ አስፈላጊነት ታምኖበት የተሻለ ሁኔታ ይፈጠራል በሚል ተስፋ ከፍተኛ መሥዋዕት ቢከፈልም፤ በሀገራችን የተፈራረቁት ሦስት ሥርዓቶች፤ አፈራረቃቸው ከአንድ ጽንፍ ኋላ-ቀር ንጉሳዊ አገዛዝ፤ ወደ ሌላኛው ፅንፈኛ የወታደር አምባገነን ጨካኝ አገዛዝና ወደ ሦስተኛው ዘረኛ አምባገነን ሥርዓት ተገለባበጡ እንጅ፤ ሕዝባችን ከመከራ ኑሮ አልተላቀቀም ወደ አራተኛው አምባገነን  አጋዛዝ  ላለመሻገር ከተፈለገ፤ በሀገራችን፤ የዴሞክራሲ ሥርዓት መመስረት አማራጭ አይኖረውም   ዴሞክራሲ የሚለውን ቃል  ናላ እስኪዞር ድረስ ዘወትር ቢያነበንቡት፤ ራሱ ብቻውን  እስካሁን  መፍትሄ  አላመጣልንም። ሕገ መንግሥት በሚባለው ሰነድ መልካም የሚባሉ ነገር ግን በሕዝብ የለት ተለት ኑሮ የማይፈተኑ አንቀፆችን ማስገባትና ነጋ ጠባ ስለነሱ ፕሮፓጋንዳ መንዛትም ፈቅ አላደረገንም።
ዴሞክራሲ፤ ህልው  ሆኖ   በገቢር እንዲገለፅ በሕዝብ ልዕልና ቁጥጥር ስር እንዲሆን ያስፈልጋል ዴሞክራሲ በመፈክር ደረጃ ተወስኖ እንዳይቀር፤ ሁሉን ዜጋ የሚያሳትፍ ነፃ የፖለቲካ ምኅዳር ክፍት መሆን አንዳለበት የሚያከራክር አይሆንም  ይህንን ለማምጣት ደግሞ፤ የሀገሪቱን  የፖለቲካ  መልከዐ- ምድር፤  የነፃነት አየር እንዲነፍስበት ማድረግ ነው።  የነፃነት አየር ነፈሰ ማለት የሚቻለው ደግሞ፤ ነዋሪዎቹ፤ ያለ ስጋትና  ያለምንም ተፅዕኖ  ነጻ እንቅስቃሴ ማድረግ ሲችሉ ነው።  የዴሞክራሲ ባለቤቶች ሆነዋል የሚባለው፤ ከሁሉ አስቀድሞ፤  ራሳቸው ነፃ ሆነው፤ በነፃነት የሥልጣን  ልዕልናቸውን ሲያስከብሩ ብቻ ነው። የሥልጣናችውን  ልዕልና አስከብረዋል ማለት የሚቻለው፤ በነፃነታቸው ተማምነው ከማንኛውም ኃይል ነፃ ሆነው ነፃርጫ ሲያካሂዱ ብቻ ነው።
 የኢትዮጵያ ሕዝብ በታሪኩ ነፃ ምርጫ ለማካሄድ እድል አላገኘም። ወያኔርጫ አምጥቻለሁ ብሎ መቶ- በመቶ  100 %  አቸነፍኩ ብሎ እራሱን አታልሎ፤ በሕዝብ ላይ ቀልዶ ቀርቷል። ሲያሽቃብጡለት የነበሩት  ምዕራባውያን  የበላይ ጠባቂዎቹም ሳይቀሩ  ስቀውበታል የቅርብ ወዳጁ የሆኑት አሜሪካይቱ  ወይዘሮ  ሶስና እንኳን በቴሌቪዥን  ወሬውን ሲስሙ፤ ሳቁ አላስችል ብሏችው ሲንከተከቱ ታይተዋል            
የዛሪይቱ ኢትዮጵያ፤  የገደብና የሞግዚት ዴሞክራሲ  ( Guided Demoracy  ) አይስፈልጋትም   የዜጎቿ ንቃተ- ኅሊና  የላቀ፤ የመነጠቀና ከፍተኛ ደርጃ የደረሰ ሆኗል   ሕዝቡ፤ ከሦስት ፀረ- ዴሞክራሲ  መሪር አገዛዝ  በቂ  ተመክሮን አግኝቷል   ለዴሞክራሲ፤ ለፍትኅ-ርትዕ ለሕዝብ እኩልነትና ለሀገር  ሉዓላዊነት ሲባል የተከፈለውን  መሥዋዕትነትና  የወድቁለትን ሰማዕታት ልጆቹንም በከብር ያስታውሳል። " ዴሞክራሲ  ያለ ገደብ ! " ሲሉ የተዋደቁትን አርበኞች ዋጋ የሚከፍለውም፤ የነፃነት ሉዓላዊነቱን በተጨባጭ ሲያረጋግጥ ነው።  ደግሞ፤ የሚገኘው በአማላጅና በልመና ሳይሆን፤ በትግል መሆኑን፤ ከሠማዕታት ልጆቹ  ትምህርት ቀስሟል ጊዜውን እየጨረሰ ለሚሄድ አልፎ- ሂያጂ አምባገነን አይምበረከክም። በትግሉ ያንበረክከዋል እንጅ !
ለአለፉት አምሳ ዓመታት ፤በሦስት  የዘመን ክልል  የነበረውን/ ያለውን ትወልድ ኃይል አስተበብሮ፤ ለሀገር ግንባታ ለማሰለፍ የሚችል መንግሥት አልነበርም አሁንም የለም።  መሆኑ ቀርቶ እንዲያውም ትውልድን በመደብ፤ በዘርና ቋንቋ እየከፋፈሉ ማፋጀት ነበር ነውም። ትልቅ ጉዳትና ዕልቂት አስክትሎ ነበር። አሁንም ሁኔታው እንደቀጠለ ይገኛል   ይህ ሁኔታ ሊቀጥል አይገባውም። ሂደቱ አንድ ቦታ ሊሰበር ይገባዋል። ኢትዮጵያ የቅርስና -ውርስ ሀገር ነች ከተባለ፤ የቅርሱን ዓይነተኛ ቦታ ሊይዙ  የሚገባቸው፤  ዜጎቿ ናቸው። ይህንን አመለካከት የሚረዳ  ዜጋ ሁሉ፤ ትውልዱን በሙሉ የማክበርና የመንከባክብ ኃላፊነት እንዲሸከም ይጠበቅበታል።
ኃላፊነቱን በይበልጥ ለመሸከም  የሚጠበቅባቸው ደግሞ፤ በኅብረ ብኄር  ተዋቅረው  የተደራጁ ናቸው። ምክንያቱም፤ ኢትዮጵያን የሚመለከቷት  እንደ ኪራይ ቤት ሳይሆን፤ እንደ ዘለዓለማዊ ሀገራቸው አድርገው ስለሚያምኑባት ነው።  " ለእኛ ያልሆነች ኢትዮጵያ ትበጣጠስ!  "  ከሚሉት ክፍሎች ጋር ፤ በዕምነትም ይሆን በአመለካከት አይገናኙም  በዚህ ምክንያት፤ እስከዛሬ ድረስ በኅብረት ለመስራት ሳይቻል ቀርቷል  ይህ ልዩነት ካልተወገደ ወይም  ደግሞ  ካልጠበበ  አብሮ  የመስራቱ  እድል እንደጠበበ ይቆያል ዘለዓለማዊቷ  ኢትዮጵያ ህያው ሆና መቀጠል አለባት የሚለው የአንድነት ኃይል ጠንክሮ ከወጣ፤ ( መውጣትም አለበት ) ልዩነቱ ሊጠብ ይችላል ብለው የሚያምኑ ቁጥራቸው  በእጅጉ በርካታ ነው " ኢትዮጵያ መኖር አለባት " የሚለው ኃይል፤ የማታ ማታ አቸናፊ ሆኖ እንደሚወጣ ማንም ሊጠራጠር አይችልም።  የጊዜ ጉዳይ ነው  !  ጊዜው ሳይመሽ ሁሉም ሰልፉን  አሁኑኑ ማሳመር አለበት  !
የወጣቱን ትውልድ ኃይል ለማሰባሰብ፤ መጀመሪያ፤ የዚህን ትውልድ፤ አመለካከቱንና አስተሳሰቡን ቋንቋውንና አነጋገሩን፤ ፍላጎቱንና መስተጋብሩን፤ ራዕዩንና  ምኞቱን  ሁሉ በጥልቅ ጠንቅቆ ማወቅ ያስፈልጋል በአርባና አምሳ ዓመታት መካከል ያለው  የትውልድ ልዩነት፤ ስፋቱ ቀላል አይሆንም።  የስድሳ ስድስቱን  ( 1966 ) የካቲት ነባራዊ  ሁኔታዎች አሁን ስለሌሉ፤ ለሃያ አንደኛው ክፍለ-ዘመን የሚስማማውን  ዝግጅት አድርጎ መቅረብስኝ ነው። ኢትዮጵያ ሀገራችን በአርባና አምሳ ዓመታት ውስጥ ከሃያኛ ክፍለ-ዘመን ወደ ሃያ አንደኛው ክፍለ -ዘመን መሸጋገሯን ማጤን ይገባል    በዚያ በታገለው)  ትውልድና  በዚህ   (በወጣቱ ) ትውልድ  ሊኖር የሚችለውን ክፍተትና ልዩነት እያጠበቡ በአንድ ብሄራዊ ዓላማ ለማሰለፍ የሚቻለው፤ የተራቀቀ ( Sophisticated )  ዘዴንና ብልሃትን የያዘ ሀገራዊ ፖሊሲን ነድፎ በተግባር ለመተርጎም ሲቻል ነው። የወያኔ ረጋ-ሰራሽ (Artificial   ) ፖሊሲ ከፕሮፓጋንዳ ፍጆታና የውጭ ምፅዋዕት ከማግኘት የበለጠ ጥቅም የለውም። ያም ቢሆን ከጊዜያዊነት  አያልፍም
 የነገዋን ኢትዮጵያ የሚያስተዳድር መንግሥት ሆነ ሥርዓት፤ ከሁሉ አስቀድሞ የሀገሪቱን ብሄራዊ ጥቅምና፤ የሕዝቧንህንነትና ፍላጎት የሚያስጠብቅ እስካለሆነ ድረስ፤ አሮጊውን በአዲሱ መተካቱ ትርጉም የለሽ ሆኖ ይቀራል
 ዛሬ፤ በዘረኞች ፖሊሲ የምትገዛዋ ሀገራችን የሚከተሉት ገፅታዎች ይታዩባታል -------
1.   ደሙን አፍስሦ ጨርሶ፤ እምባውን እየተመገበ  የሚኖር ሰባት (7) ሚሊዮን በላይ ረሀብተኛ ሕዝብ አለባት
2.  በበርካታ ሚሊዮን የሚቆጠር ሕዝቧ ሀገሪቷን እየለቀቀ በመሰደድ ላይ ይገኛል   ከዚህ ቁጥር ውስጥ ከፍተኛውን ድርሻ የያዘው  ወጣቱ ትውልድ ሆኗል  የስደቱም ዓይነተኛ ምክንያቶች  ፤ የሰብዓዊ መብቶች አለመከበር፤  በሠላም ሰርቶ መኖር አለመቻል ዋናዎቹ ናቸው።
3.  በዕምነታቸው፤ በፖለቲካ  አመለካከታቸውና፤ በብሄር ልዩነታቸው ብቻ ወህኒ ወርደው የሚሰቃዩትን ዜጎች ቁጥር በትክክል ማወቅ የማይቻልበት ደረጃ ተደርሷል   የጅምላ ግድያና  ጭፍጨፋ  የዕለት ተዕለት የሥርዓቱ  ተግባርና ባኅርይ ሆኗል
4. የወያኔ ባለስልጣኖች፤ በሙስና፤ በዝርፊያ  የሀገሪቱን ሀብት ወደ ውጭ አሸሺተዋል። አሁንም የሚያሸሹበት ሰፊ ዕድል አላቸው።
5.  የሀገሪቱ ብሄራዊ ሀብት፤ ለውጭ ዜጎች መጠቀሚያ እየዋለ፤ የሀገሪቱ ዜጎች የበይ- ተመልካቾች ሆነው ቀርተዋል
6. ወጣቱ ትውልድ፤  ሆን ተብሎ፤  በአልባሌና አደገኛ ባኅል እየተበከለ እንዲያድግ  እየተደረገ ነው። በአድንዛዥ ዕፅ፤  አዕምሮው እንዲበከል ሆኗል 
7.  የሀገሪቱ የውጭ ፖሊሲ የተነደፈው፤ የምዕራቡን ጥቅም ለማስጠበቅ ነው።   ኢትዮጵያም፤ በአዲሱ የእጅ -አዙር ቅኝ አገዛዝ  ስር ወድቃለች። ሀገር-ወዳድ  መንግሥት እስካልተቋቋመ ድረስም፤  የሀገራችን ሉዓላዊነትናሄራዊ ክብሯ እንደተደፈረ ይቆያል 
ዝርዝሩ ብዙ ነው።   ታዲያ፤ ሁኔታውን ለመለወጥ ምን መደረገ አለበት?   ለሚለው ጥያቄ ሁሉም የበኩሉን መልስ እንዲያዘጋጅ ጥሪያችንን ማስተላለፋችንን እንቀጥላለን ፈቀደኛና ዝግጁ ሆኖ ከቀረበአንድነት ኃይል ጋርም እንተባበራለን ሀገራችንን ለአዲስ ዓይነት ቅርጫ ከሚያዘጋጇት ጋር ግን ግንኙነት አይኖረንም  ወጣቱን ትውልድ ለሀገራዊ ትግል እንዲሰለፍም ጥረታችንን እንቀጥልበታለን ሀገርን የማዳኑ ተግባር ከፍተኛ መሥዋዕትን የሚጠይቅ እንደሆነ በአንክሮ ስለምንገነዘብ፤  እስከመጨረሻው እስትንፋስ ድረስ  ከመቀጠል በቀር ሌላ አማራጭ አይኖረንም። በዚህ ቁርጠኝነት ከተዘጋጁት ጋር ለመተበባር ጥሪ እናስተላልፋለን !
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኖራለች !