Tuesday, December 29, 2015

አመጽ ህዝባዊነትን ያማከለ ይሁን! (ከዳዊት ተመስገንOslo,Norway)


ነጻነትን ከመናፈቅና የባርነትን ቀንበር ከማራገፍ ምኞት ባሻገር የባለ አገርነትን የአንድነት መንፈስ ሊኖረን ይገባል ኢትዮጵያዊነት ህዝብነታችንንና ስልጣኔነታችንን በዓለም ላይ ያሳወቀ በአፍሪካውያን መካከል የክብር ቦታችንን ያስጠበቀ የጀግንነትንና የእምነት ጽናት የሚያንጸባርቅ ነው ኢትዮጵያዊነት የረዥም ዘመናት የነጻነት ታሪክና የበለጸገ ባህላችን የሚታወቅበት ከሁሉም በላይ የአንድነት ስማችን ነው አሁን ካለንበት ህይወት ላይ የተፈጠረው ሰቆቃ ሁሉ መሰረታዊ ምንጩ የጎሳ ፖለቲካ ላይ ያጠነጠነ ስለሆነ ብቻ ነው እንደሚታወቀው አብዛኛዎቹ ተቃዋሚ ፓርቲዎች ነን ብለው የሚንቀሳቀሱት ከኢትዮጵያዊነት ይልቅ ጎሳን ያተኮረ ወይም የሚያውጠነጥን በመሆኑ ትግሉ ህዝባዊነት የሌለው አመጽ ስላልሆነ ለመስረቅ እድል ያላገኘ ሌባ ሰው ታማኝ ነኝ ብሎ ያስባል እንደሚባለው ሆኖ ይቀራል:: ኢትዮጵያዊነትንና ህዝባዊነትን ያማከለ አመጽ ሲሆን በእርግጠኝነት መናገር የሚቻለው ይፍጠንም ወይም ይዘግይ እንጂ የሚፈለገው ፍትህና ነጻነት እውን ይሆናል።
እስካሁን ድረስ ዘላለማዊት ኢትዮጵያን እድሜው በዛሬና በነገ መካከል የተወሰነውን ወያኔን እንደ መዥገር ተጣብቆ ከሚያራምደው ቡቱቶ ስርዓት ለመለየት አለመቻላችን ልብን የሚያቆስል ህመም ነው፡ እያለቁ ያሉትን የኢትዮጵያ ንጹሀን ዜጎች የሚፈርሰውና የሚቃጠለው በዚች አገር ዜጎች ደምና ላብ የተገነባ ሀብት መሆኑን የምናምን ቢሆን በየወቅቱ ከጎናችን አንዳንድ ኪሎ ስጋ በወደቀ ነበር ችግሩ ምናልባት ኢትዮጵያዊነትን ባለፉት 40 ዓመታት ተንገላቷል ለአፍ አመል የምናነሳው እንጂ የልብ እምነትና ትልቅ መርህ አላደረግነውም በጎሳና በሃይማኖት አናሳ ክፍል መሆን ትልቅ ችግር አለበት የእኔ አመለካከት ዞሮ ዞሮ ሁሉም ኢትዮጵያዊ ያቺ አገር የጋራ አገር መሆንዋን እንዲረዳና ኢትዮጵያዊነት በተባለ ጥልቅ የአገር እሴት ዙሪያ ብሎም ማንም ዜጋ ማንም ከዚያች አፈር ተቆንጥሮ የተሰራ ሰው ሌላ ነኝ እንዳይል ነው በኢትዮጵያዊነት ላይ ትልቅ ዘመቻ ግንባር የተከፈተው በንኡስና በክፍልፋይ እንድንወሰን የጎሳ ፖለቲካ ወያኔ መስበክ ከያዘበት ወዲህ መሆኑ ይታወቃል።
አንዳንድ ዘመናት አግበስብሰው የሚያመጡአቸው ችግሮች የህዝብን ነፍስ ምንኛ እንደሚፈታተኑ ይታወቃል በወቅት አንጻር ሲታዩ እንደ ችግሮች የሚገመቱ ክስተቶች የታሪክ ጉርድፎችይባላሉ ለእነዚህ ፈሳሽና አላፊ ተጓዥ ክስተቶች የኢትዮጵያ ወጣቶች ትክክለኛውን የትግል ፈለግ የማሰናዳት ወይም ልዩ ቦይ የመቅደድ ሃላፊነት አለባቸው ጠንካራ ዜጎች ከያሉበት የወጡበትና ህዝብንም የሚያስተባብሩበት ወይም የሚያነሳሱበት ወቅትም ይህ ሰዓት ነው።በነፍስ መፈተኛነት በተጠቀሰው የህይወት ነውጥ የጊዜ ክፍል ችግሩን ለመጋፈጥ ወይም እንዲሁ ለችግሩ ለመንበርከክ የምንቆምበት መድረክ ከራሳችን አልፎ የአገርን ህልውና ይመለከታል። የአነጋገር ወግ ሆነና አንዳንድ አባቶችና እናቶች ያለፈውን ዘመን ሁሉ ደጉ ዘመን የማለት ሰብአዊ አነጋገር አላቸው በመሰረቱ ግን ደጉ ዘመን እየተባለ የሚጠቀስ የታሪክ ወቅት እንዳለፈና
page1image17008 page1image17432 page1image17856 page1image18280 page1image18440
እንደሚያልፍም ሁሉ ክፉ ወቅትም አሻራውን ትቶ በትውልድ ግንባር ላይ ጠባሳውን ለጥፎ ያልፋል ምን አልባትም ለአዲስ የፖለቲካ መልክአ ምድርም መፈጠር አንድ አይነት ግፊት ፈጥሮ ማን ያውቃል ብዙ ብዙ ኮተት ኩርንችትና ግሳንግስ ከምሮብን ይሄዳል አዎን እንደሚባለው ሁሉ ትውልዶች እንዳለፉና እንደሚያልፉ ሁሉ የእነሱ ዘመነ ጉድ የሆኑ ደግ ቀኖችና ክፉ ዘመናትም ያልፋሉ ዘላለማዊነት የላቸውም ዘላለማዊነትስ ያለው አገር ነው ዘላለማዊነትስ ያለው የታሪክ ትዝብትና የእውነት ምስክርነት ብቻ ነው ለመሆኑ የመጣውን ብሄራዊ ግፍና መከራ እንዴት አየነው የሚመጣውንስ እናውቃለን ወይ? ካወቅንው እንዴት ልናስቀረው እንችላለን`?ከመጣስ ከባድና የማንወጣው አደጋ ሳይጥልብን እንዴት ልናስተናግደው ይገባናል? በፈታኙ ሰአት እንደ ሶቭየቱ ሚኮያን ከኢሊች ሌኒን እስከ ኢሊች ብሪዥኔቭ ድረስ ተመሳስሎና መስሎ ለየተረኛው የአየር ጠባይ የሚሆን ልብስ አዘጋጅቶ ክፉ ቀን ማሳለፍ ይቻል ይሆን?
በዚህ መጣጥፍ ችግርን መሸሽን ትቶ ከውስጡ ዋኝቶ ስለ መውጣት ማንሳቱን እንጅ ስለ የኋሊት ሩጫው ላለማንሳት እሻለሁ ለምሳሌ ከሁለት አመት በኋላ 7 ሚሊዮን ኢትዮጵያዊ ይራባል ቢባል ደፍሮ የሚያስተባብር አለ ጭራቅ ሊበላን እንደሚችል እያወቅንና እያመንን ኢትዮጵያውያን ሁሉ ሲመጣ እናየዋለን ከማለት ባሻገር አውሬው ወዳለበት ስፍራ ሂደን የምንገድል አይደለንም የሚል ትችት በየደረታችን ላይ ለጥፈን የምንሄድ ነን በራሳችን የተፈጥሮ ቸልተኝነት ላይ እና በዋናነት በወያኔ ጭካኔ አመለካከትና ልበ ደንዳናነት ተጨምሮ ደግሞ ተይያይዞ ወደ ገደል የመግባት ያህል ነው አሁን ያለንበት ወቅት ይህን ይመስላል ጅብ በቀደደበት ውሻ እንደሚባለው ሁሉ ወያኔያዊ አመለካከትና ወያኔያዊ አመሰራረት ማራመድ ትግሉን ጥግ ያደርሰዋል ብየ አላምንም በብሔረሰብ ማንነት ላይ ብቻ ያተኮረ ተቃውሞ ውጤት አልባ ነው። ተማሪዎቹ ፖለቲካ ያልተገለጸላቸው የ24 ዓመታት የጎሳ ፖለቲካ ውጤት ናቸው። ወያኔ የዚህ ክልል የዚያ ክልል እያለ ተማሪዎቹን የበሰበሰውን የጎሳ ጭቃ ፖለቲካን አብዛኛው ተለውሰዋል።በወያኔ የዘር ፖለቲካ ጭንቅላታቸው ተመርዞአል።እንደሚታየኝ የፖለቲካ ምህዳር መጥበብና መስፋት እንዲሁም ተቃዋሚዎች ያሉበትን ሁኔታ በትክክለኛው ፖለቲካዊ ይዞታን ይዞ መሄድ ሲገባው ነገር ግን ሁኔታዎች ተጣምመው ተንጋደውና ጎብጠው ቀርበዋል።ብዙውን ጊዜ ትግሉ ወደ ኋላ የሚጎተተው ህዝባዊነትን ያላማከለ ስለሆነ ብቻ ነው ወጣቱ የብሄርተኛና የጎሳ ፖለቲከኞች መጠቀሚያና ሰለባ ሊሆን አይገባም።
ኦሮሞ እንዴት እንደሚገነጠል ጋምቢላ ወዘተ.....እየተባለ ትግሉን ያኮላሸዋል እንጂ ትግሉን ወዴትም አያደርሰውም ኢትዮጵያን ያላማከለ ትግል ብሎም ሕዝባዊነት ያላማከለ አመጽ የሳምንት ብቻ ነው የሚሆነው በሌላም በኩል የውሃው ሙላት ሲመጣ አካፋና ዶማ ይዘን መውጣት እንጂ የጅረቱን ቁጣ እዚያው በወቅቱ የማስቀረት ስነ ልቦናዊ ባህርይ ስለሌለን ይኽው ችግሩን በስጋና በደም አየነው ማለት ብቻ ነው የተባለው ሁሉና ሌላ ሌላውም አብሮ መጣ በችግሮቹ ውቅያኖስ ውስጥ ከገባን በኋላ ነው ችግሩ ሲደፍቀው በስነ ተፈጥሮአችን ውስጥ ጎልቶ የሚታየው ባህሪ ችግር ሲመጣ መጋፈጥ እንጂ የማስቀረት ግንዛቤ ማጣት በእቅድ የመስራትና የመኖር ባህል አለማዳበር ጠላትን መናቅና በወገን ጉልበት ከሚገባው በላይ የመተማመን ስህተት ነው ትግሉን በምን አይነት ሁኔታ እየሄደ እንዳለ አትኩሮት ስጥቶ አለማየት ነው ወያኔም የተሰራው በዚህ አይነት ክር ሲሆን አረመኔያዊ አገዛዝ የዚህ የስነ ህይወት ፍሬዎች

ናቸው ስለዚህ የሰለጠነ ስርአት ተከታይ አገር የሚያተኩርበት ነገን እያዩ የማቀድ የዛሬ ችግሮችን ትናንት ለመፍታት መሞከርና ምንም አይነት መከራ በውዝፍ ለሚቀጥለው ትውልድ ማውረስ ትክክል ያለመሆኑን ሀቅ አልተቀበልንም በአጭሩ የወደፊት ተመልካችነት ሊኖረን አልቻለም ስለዚህ ዘወትር ከራሳችን ይልቅ ወደኋላ ተመልካችና አወዳሽ ነን የወደፊት በጉጉት የምንመለከት የወደፊቱ ብርሃን እንዳይጠፋ የምንደክመው አይደለንም የኢትዮጵያን ህዝብ ንብረት ባለፉት 30 አመታት ከፊሉም መነሻውን ድልድዩን መንገዱን ፋብሪካውን እያቃጠለ ኖሮአል ገሚሱ ደግሞ ያንን ተግባር እንደማይከፍልበት ተውኔት ሲመለከት ቆይቶአል ቢባል ማጋነን አይመስለኝም ታዲያ ወያኔ በለስ ቀንቶት መዲናውን ከያዘ ጅምሮ ከተማይቱን ከማቃጠል አልፎ ኢትዮጵያንና ህዝቦቾን ዘርፈ ብዙ በሆነ ችግሮች እያመከነ ይገኛል::
ከወያኔ ጋር በፊት ጋብቻ ፈጽመው በጋብቻ ላይ ጋብቻ እየፈጸሙ የፖለቲካ ጽንፈኛነትን የሚያራምዱ ስልጣን ከያዘ በኋላ እንኳ በሚያወጧቸው የኢኮኖሚና ማህበራዊ እቅድ አማካኝነት አገር የማፈራረሱንና የማቀጨጩን ተግባር እየገፉበት እንደመቀጠሉ ቡችሎቻቸውም የዚህ ስርዓት ጥገኛ ናቸው ይህን ስርዓት ደመኛ ላደረገ ኢትዮጵያዊ በትህትና ልገልጥ የምወደው ወያኔ የያዘው ሃብትና ንብረት የኢትዮጵያ ህዝብ ንብረት እንደሆነ መላልሰው እንዲያስቡ ነው፡፡ይህን የበሰበሰውን ስርዓት አፈራርሶ በይዘትና በቅርጽ አዲስ በሆነ ስርዓት በፍራሹ(በመቃብሩ) ላይ መተካትና መገንባት እንዴት ነው የሚሆነው ብለን ማሰብ መቼም ይጠበቅብናል ያ ትውልድ የአንድ ትውልድ አብዮትዊ ገድል የታሪክ ማስረጃዎች በጥልቀትና በገፍ ቀርበው ምእራፎችን ከምእራፎች በማገናዘብ ትእይንቶችን ከትእይንቶች በማነጻጸር ሂደትን ከሂደት በማመሳከር ሀቅ ሊነጠርበትና ሊናጥበት የሚችል በዋዛ ሊታይ የማይገባ የዘመናችን አንዱ ታላቅ የታሪክ ስንክሳር ነው ማንኛችንም ቢሆን የምንፈልገውን ለማግኘት ደረጃ ይለያይ ይሆን እንጂ ዋጋ መክፈል ይኖርብናል ልክ ፈረንጆች ነጻ ምሳ የለም እንደሚሉት ማለት ነው በአሁን ሰአት ለውጥ ለማምጣት እየተንቀሳቀሰ ላለው ትምህርት እንዲሆነው ያ ትውልድ ከጊዜ ብዛት በብዥታ የታወከውን አይነ ህሊናን የብርሃን ብልጭታ በመስጠት 40ና ከዚያም በላይ ዓመታት ወደኋላ በመመለስ በወቅቱ የተከናወኑትን የትግል ተውኔቶች ማስተማር ይገባል ወጣቱ ትውልድ የብሄረሰብ ወርቀ ዘቦ በሆነች ኢትዮጵያ የህብረ ብሄርን የፖለቲካ የትግል ስልት ይዞ የተነሳውን ፈለግ ሊያራምድ ግድ ይላል ኢትዮጵያዊ ወጣት የቱን ያህል የብሄርተኛና የጎሳ ፖለቲከኞች መጠቀሚያና ሰለባ ሊሆን አይገባም::
የወያኔን አምባገነን አገዛዝ በተባበረ ትግል እናስወግዳለን!! 28 December 2015 

No comments:

Post a Comment