Sunday, January 31, 2016

ወተት ይሸፍታል እንኳን ሰው ሲበደል....ዴሞክራሲያ ቅፅ41 ቁ. 3 ታኅሣስ 2008 ዓ.ም ወርሃ ታኅሣሥ--


ዴሞክራሲያ ቅፅ41 . 3 ታኅሣስ 2008 .
ወርሃ ታኅሣሥ-- ወተት ይሸፍታል እንኳን ሰው ሲበደል
በኢትዮጵያ ሕዝብ ታሪክ ውስጥ የታኅሣሥ ወር የአመጽና ለውጥን አብሳሪ የሆኑ ትግሎች ሲከሰቱባት መቆየቷ የሚታወስ ነው። ዛሬም ቢሆን ታኅሣሥ፣ ሕዝባዊ አመጽን አስተናግዳለች። ዞር ብለን ግን ለአገራቸው ራሳቸውን የሰጡትን ሰማዕታትን ስንዘክር ገዝፎና ሚዛን ደፍቶ የምናገኘው የኢትዮጵያ ተማሪዎች እንቅስቃሴ መሆኑ የሚረሳ አይደለም - ታኅሣሥ 20 የተማሪዎች እንቃስቃሴ ሰማዕትን መዘከሪያ ቀን መሆኑን ያስታውሷል።
page1image4536
የታኅሣሥ ቅርስ ግን በቅድሚያ የንዋይ ልጆችን--መንግሥቱና ገርማሜን--እና የሌሎችንም የመፈንቅለ መንግሥት ሙከራ ያስታውሰናል፡፡ አንዳንዶች የዚህን ክስተት ክብደት መረዳት ተስኗቸው የታኅሣሥ ግርግር ብለው ሊያንኳስሱት ቢሞክሩም የመንግሥቱና የገርማሜ ንዋይ እንዲሁም የጓደኞቻቸው ጥረትና እርምጃ አዲስ የትግል ምዕራፍ የከፈተ ለሕዝባዊ ትግሉ ጭላንጭል ብርሃን የፈነጠቀ አቢይ እርምጃ ነው። ከዛሬው ጋር ስናስተያየው ለምሳሌ፡ ለወያኔ ካደሩ መኮንኖችና ባለስልጣናቱ አንጻር በሥርዓቱ ከፍተኛ ቦታ የነበራቸው መኮንኖችና ምሁሮች የሕዝቡን ብሶትና እሮሮ ተገንዝበውና ሰምተው ለውጥ ብለው ሲነሱ የሚደርስባቸውን ጉዳት ሳያውቁ ሳይሆን ለሀገር ሲሉ ሞትን ደፍረው ነው። ሞተዋልም። ራሳቸውን የገደሉት ብቻ ሳይሆን ተይዘው የተፈረደባቸውም እነ መንግሥቱ በየአደባባዩ ተሰቅለዋል ፤ ለእስርም ተዳርገዋል፡፡ ለምን ታገላችሁ፤ ለውጥን ለምን ፈለጋችሁ፤ ... ወዘተ ያላቸው አልነበረም - መስዋዕትነታቸው ተከበረ እንጂ፤ ምሳሌ ሆነ እንጂ። የታኅሣሡ የመፈንቅል ሙከራ ዋናው አንደምታው በተማሪዎች እንቅሳቃሴ ላይ ያደረገው ተጽዕኖ ነው ቢባልም ስህተት አይደለም። ቀደም ብሎ ተማሪዎች የጥገና ለውጥ አቀንቃኝ ነበሩና ለአጼው መንግሥት የምለላ ደብዳቤ እየጻፉና እየተማጸኑ አንዳንድ ለውጦች እንዲደረጉ ሲጠይቁ እንደነበሩ የሚታወቅ ነው። ለውጥ ከገዢዎች በጎ ፈቃድ የሚጠበቅ ነበር። ታኅሣሥ 1953 ግን ይህን ሁሉ ቀየረውና የአጼው ሥርዓትና ተማሪዎች ተቆራረጡ። ሥር ነቀል ለውጥም ተፈላጊና ተቀንቃኝ ሆነ።
ከዚያን ጊዜ እስከ የካቲት የተደረገው ጉዞ ውጣ ውረድ የሞላበት እንደነበር ሊረሳ የሚገባውም አልነበረም። ከተማሪዎች በፊት የኢትዮጵያ ሠራተኞችም ታግለዋል። ልዩ ልዩ የአርሶ አደሮች አመጾችም ተካሂደዋል። በሕግ የተደነገገ ጪሰኝነትን የሚያጸድቅና የአርሶ አደሩን ምርት ከሦስት ሁለት እጅ (ሁለት ሶስተኛ ምርት) ለባለመሬቶች የሚሰጥ የገባርነት/ጪሰኝንት ሥርዓት ነበርና የተጠቃው አርሶ አደር ከጊዜ ወደ ጊዜ አምጾ ተሰውቷል። ትግሎቹ ግን የተቀናጁና ስልታዊ ስላልነበሩና የአጼው አገዛዝ የአፈና ተቋሞች ዘመናዊና ጨካኝ ስለነበሩ አመጾቹ መቸነፋቸው የሚጠበቅ ነበር። በንጉሡ የበላይነት የሰፈነው ሥርዓት ፊውዳል ወይም ይባል እንደነበረው ባላባታዊ ስለነበር መሠረታዊ ቅራኔው አገዛዙ ከሠፊው አርሶ አደር ሕዝብ ጋር ቢሆንም ከጅቡቲ ኢትዮጵያ (ቀደም ፍራንኮ ኦትዮጵያ ይባል የነበረው) ባቡር ሃዲድ መዘርጋት ጋር ተያይዞ ላባደሮች ብቅ ብለው ነበር። ከብዙ ችግርና ትግል በኋላ በመጋቢት 5/1947 የኢትዮጵያ የምድር ባቡር ሠራተኞች ማኅበር (ሲንዲካ ደ ሼሚኖት ኢትዮጵያ) በሚል ስም ተመሠረተ። ይህ በዚህ እንዳለና ማኅበራቸውንም አለፍቃድ የመሠረቱ ቢሆንም ብዝበዛን በመቃወም በዚያ ዓመት ያደረጉት የሥራ ማቆም አድማ የተሳካ መሆኑ ለሌሎችም ምሳሌ ሆኗል። በ19051908 ዓመታት ባዕዳን ባንኮችን በመክፈታቸው የቢሮ ሠራተኞች ቁጥር ተበራከተ። የፋብሪካዎች መቋቋምም እንዲሁ የላባአደሩን ቁጥር እያሳደገው መጣ። ኤርትራ በፈደሬሽን ስትደዳድር በነበረበት ጊዜም የሠራተኛ ማኅበር ማቋቋም የተፈቀደ ስለነበር መንግሥት ሲያስፈልገው የሠራተኛ ማኅበራትን ሊያፈርስ/ሊሰርዝ ይችላል የሚል አንቀጽ በወጣው አዋጅ ውስጥ በመካተቱ የኤርትራ ሠራተኞች ይህን በመቃወም ያደረጉት ጠቅላላ የሥራ ማቆም አድማ የተሳካ ሆኖ ሠራተኞቹም ከቀሪው የኢትዮጵያ ሠራተኞች ጋር በማኅበር ሊያያዙ መቻላቸው ትግላቸውን በቁጥርም በተመክሮም አዳበረው። ሠራተኛው ለመብት--በተለይም አታጋይ ማኅበርን በጋራ ለመመሥረት ያደረገውን ትግል ታሪክ በዚህ ለመዘርዘር ባንቃጣም በ1950ዎች መጀመሪያ ላይ በእነ አቶ አበራ ገሙ (ቃጫ ፋብሪካ)ና የሞዝቮልዱ የእንጨት ሥራ ድርጅትና ሌሎች (ዲያባኮ ጥጥ ፋብሪካ፣ የኢትዮጵያ ተሽከርካሪ አግልግሎት፣ ቫስኪንና ዳርግስታድ) በምስጢር ግንቦት 20 ቀን 1953 .ም ደጃዝማች ባልቻ ሜዳ ተሰብስበው የጋራ ድርጅት ለማቋቋም መስማማታቸው መጠቀስ ያለበት ነው። መጋቢት 3 ቀን 1954 .. በቃጫ ፋብሪካ ሠራተኞች ሊቀመንበር(ነት) የተካሄደው ስብሰባም አንድ ቋሚ የኢትዮጵያ ሠራተኞች ማኅበር እንዲቋቋምና በኮንፌዴሬሽን መልክም ኢንዱስትሪዎችን፣ ፋብሪካዎችንና የኅብረት እርሻዎችን ሁሉ እንዲያቅፍ ተወስኖ በመቀጠልም በሰኔ 1954 ዓም 3ኛው የተወካዮች ስብሰባ ሲደረግ የምድር ባቡር ፣ የድሬዳዋ ሲሚንቶ ፋብሪካዎች፣ በዘረኛ ሆላንዶች ሥር ይሰቃዩ የነበሩት የወንጂና ሸዋ ስኳር ፋብሪካ ሠራተኞችና ሌሎችም ሊሰባሰቡ ቻሉ። ሚያዝያ 1 ቀን 1955 ም የኢትዮጵያ ሠራተኞች አንድነት ማኅበር ሊቋቋም ቻለ። በሕዝባዊ ኑሮ ዕድገት ሚኒስቴር ሥር ማኅበራት መመዝገብ አለባቸው በሚል ሥርዓቱ ማኅበሩን ሊቆጣጠር ሲጥር አጋሩ አሜሪካም በራሷ የሠራተኞች ድርጅት አማካይነት ወጥመዷን ዘረጋች። በሠራተኛው ማኅበር ላይ ከባድ ተጽዕኖ ተደርጎ የክብር ፕሬዚዳንቱ አቶ አበራ ገሙ ራሱን ገደለ ተብሎ ቢለይም ማኅበሩ ለብዙ ሥራ ማቆም አድማዎች አደራጅና አዋላጅ ሆኖ ቀጥሏል - ከተቋቋመ በአራት ወሩ የጠራው አድማ በተደረገው አፈና የተነሳ ባይሳካም።
እይታችንን ወደ ሠራተኞች ማኅበር ዞር ያደረግነው ቀደምም ትግል ማካሄዳቸውን ለመጥቀስና ቀጥሎም ከተማሪዎቹና ከአስተማሪዎቹ እንቅስቃሴ ጋርም በመቀናጀት ለየካቲት 66 ስፋትና ጉልበት የሰጡ መሆናቸውን (የእንዳልካቸው መኮንን ካቢኔ ከሥልጣን እንዲወርድ ጠቅላላ የሥራ ማቆም አድማ ያደረገው አስተዋጽኦ
እንደምሳሌ ሊጠቀስ ይችላል) ለማስታወስም ነው። የኢትዮጵያ ተማሪዎች እንቅስቃሴም ሲጀምር የተማሪውን ሁሉ ድጋፍና ተሳትፎ ያገኘ አልነበረም። ጃንሆይ ምን አጠፉየሚሉ ጥቂቶች ካለመሆናቸው በተጨማሪም የተማሪው የንቃት ደረጃም በጣም ደካማ ነበር ቢባል ስህተት አይሆንም። ከዩኒቨርሲቲው አስተማሪዎች የነበሩት ባዕዳንም -- በተለይም የሰላም ጓድ ተብለው የተሰማሩት አሜሪካውያንና ሚሲዮናውያን -- ተማሪው በፖለቲካ እንዳይነቃና እንዳይደራጅ፤ እንዲከፋፈልም ከፍተኛ ሚና ተጫውተዋል። ጥቂቶች ቢሆኑም ጊዜው የደረሰን ወይም የመጣለትን ጽንሰ ሀሳብና አቅዋም ይዘው ከተነሱ ብዙሃኑን ሊሰበስቡ ይችላሉ በተባለው መሠረት ጥቂት የነቁ የዩኒቨርስቲ ተማሪዎች በምስጢር ተሰባስበው፤ ንቃታቸውን እያዳበሩ፤ በተለያዩ መንገዶች የአብዛኛውን ተማሪ የአስተሳሰብ አድማስ ለማስፋትና ለማበልጸግ ቻሉ። የእነኃይሉ ገሞራውና የእነጸገየ ወይን (ደብተራው) ግጥሞች (በረከተ መርገም፣ ናስተማስለኪ፣ . . . )፤ በተለያዩ ጉዳዮች ላይ በግልጽ የሚደረጉ ውይይቶች በተማሪው ማኅበር ጋዜጦችና በተባራሪ ወረቀቶች በሚደረጉ ጽሁፎች ተማሪዎች ስለአገራቸውና ስለዓለም አቀፍ ሁኔታ ያላቸውን ግንዛቤ አሳደጉ። በአመለካከትና በአስተሳሰብ ግልጽነትም አስፈላጊ እየሆነ የመጣውንና መሠረታዊ የሆነውን ጥያቄ -መሬት ለአራሹን- እንዲሁም ሌሎች አገራዊ ጥያቄዎችን በማንሳት ተከታታይ ሰልፎችን አካሄዱ። ጥያቄው ሥርዓቱን የሚያናጋ በመሆኑ አገዛዙ ለተማሪዎቹ የሰጠው ምላሽ የኃይል እርምጃ ሆነ። በሰልፋቸው ከአገዛዙ ጋር ተጋጩ ። በቅድሚያ ተነስቶ የነበረው የመሬት ጥያቄ የአጼውን አገዛዝ ምሰሶ የሚነቀንቅ በመሆኑ አገዛዙ በሰልፈኞቹ ላይ የኃይል እርምጃ ወሰደ፤ መሪዎች ናቸው ያላቸውን ዘጠኝ ተማሪዎች (ሟቹ ኃይሉ ገበረዮሐንስ- ገሞራውን- ጨምሮ) ከዩኒቨርስቲው አባረረ። ቀንዲሉ፣ እሳቱ ተለኩሷልና አልጠፋ ማለቱ የሚጠበቅ ነበርና በተከታታይ ዓመታት ተቃውሞውና ሰልፉ ቀጠለ።
የኋላ መብራት ፈዘዝ፤ ወደ ኋላ ዕይታ ጨንበስ የሚል አይደለምና በዚያን ጊዜ ድርጅቶች የነበራቸው ድክመት፣ ጥንካሬ፣ ትግልና መስዋዕትነት፣ ምርጫ፣ ስልትና መፈክሮችንም በተመለከተ የሚሰጠው ፍርድና ትችት አስፈላጊ የሆነውን ግምገማን ከጊዜው ተጨባጭ ሁኔታ ጋር ማቆራኘትን የሚቀበል አይመስልም። ስለዚህም ትችቱ የሐቅ ደኻ እና ገለባ ሆኖ ቆይቷል። ለጨለማ መብራት፤ ለወገንም ኩራት ሆኖ ያለፈውን ትውልድ መዝለፉ አወቅን ባዮች ሥራዬ ብለው ተያይዘውት ቆይተዋል። ለካፒታሊዝም ከመሰዋት ለሠርቶ አደሩ ሕዝብ ሥልጣንና ዴሞክራሲ መሰዋት ይበልጥ የተከበረ መሆኑን የሚስቱት ምሁራን ተብየዎች የተማሪዎች እንቅስቃሴ ግራ ክንፍ ነበር ብለው በደፈናው ሊያወግዙ ይነሳሉ። ሐቁ ይነገር ከተባለ ደግሞ፣ ለሰው በላና ለበዝባዥ ሥርዓት ከመሞት ለሠርቶ አደሩ ሕዝብ ሥልጣንና ለዲሞክራሲ መሰዋት ይበልጥ የተከበረ ነው። ተማሪዎችና ምሁሮች ወደ ግራና ወደ ሶሻሊዝም ያዘነበሉበትም ምክንያት የነበረውን ጨቋኝ አገዛዝ በሁሉም መስክ ሊፋለሙ ሲነሱ የርዕዮት ትጥቅ ሊሆናቸው የሚችለው ይህ ብቻ ስለነበር ነው። የካፒታሊዝም አገዛዝ ቁንጮ የሆነችው አሜሪካ የአጼው አጋር ሆና የተሞከረውን መፈንቅል ያከሸፈች ከመሆኗ በላይ በዓለም አቀፍ ደረጃም ኢምፔሪያሊስት ተብላ ሕዝባዊ ትግል ያነጣጠረባት፤ የደቡብ አፍሪካን አፓርቴይድ የምትደግፍና ዘረኛ ሀገር ነበረች። ለማንም አርዓያ የማትሆን የግፍ ሀገር። ተማሪዎችና ምሁሮች ዕይታቸውን ወደ ሌላ አቅጣጫ ማድረጋቸው አንድም በዚህ ምክንያት ሲሆን በሌላም በኩል ሥር ነቀል ለውጥ ፈላጊውና አሜሪካ ሆድና ጀርባ በመሆናቸው ነው። ለነገሩ ዛሬም ይህ ሐቅ ሆኖ ያለ ነው።
ጊዜውን መመርመር ባልነው መሠረት ደግሞ የተማሪው እንቅስቃሴ ደምቆና አምርሮ በተነሳበት ወቅት በዓለም አቀፍ ደረጃ ጸረ ኢምፔሪያሊስትና ጸረ-ቅኝ ገዢዎች ትግል በአፍሪካ፣ እስያና ደቡብ /ላቲን አሜሪካ ተፋፍሞ ነበር። በሀገራት ደረጃ ቪየትናም፣ ላኦስ፣ ካምቦዲያ፣ ሞዛምቢክ፣ አንጎላ፣ ጊኒ ቢሳው፤ በታጋዮች ደረጃ ቼ ጉቬራ፣ ካብራል፣ ሞንድሌን፣ ማሼል፣ ሆቺ ሚንህ፣ ማንዴላ፣ ሉሙምባ፣ ቤን ቤላ፣ ... ወዘተ የሚባልበት ጊዜ ከመሆኑ ሌላ የትግሎቹ አጋሮች ደግሞ የሶሻሊስቶቹ ጎራ (ሶቭየት ህብረት፣ ቻይና ፣ ኩባ፣ ... ወዘተ ) ነበሩ። በ1966 ኢሕአፓ መሆን ከወጣቱ የሚጠበቅ ሆኖ እንደተገኘው ሁሉ ከዚያ ቀደም ባለው ጊዜ ግራ ክንፍ አለመሆን ኋላ ቀር ያሰኝ ነበር ብንል ትክክል ነው - የነበረ የወቅቱ ዕውነታ ነው።
ስለዚህም ያ ትውልድ ግራ ክንፍ የሆነው ለኢትዮጵያ ችግሮች በዚህ መልክና መንገድ መፍትሔ አገኛለሁ በሚል ነው እንጂ የሀገሩን ባህልና ወግ በደፈናው ሰርዞና ለባዕድ አድሮ አልነበረም። እውነቱ ሲነገር እንቅስቃሴውም ሆነ ኋላ የተቋቋመው ኢሕአፓ ለማንም ባዕድ አንገዛም፣ አንጎነበስም በማለታቸው ጉዳት ደረሰባቸው እንጂ ከሀዲዎቹ እንደሆኑት እንደነ ወያኔ አልተጠቀሙም። ያን ትውልድ ወደ ግራና ወደ ስር ነቀል ለውጥ ፍለጋም የገፋፋው ራሱ ሥርዓቱ ነው። ጉድ ይሰማል ጆሮ፣ ሆኖ ዛሬ የአጼውን ዘመን ጭፍን ጭቆና ሲክዱ የሚሰሙ ያሉ ቢሆንም ያ አገዛዝ ለሚሊዮኖች እስር ቤት፣ የመከራ፣ የስቃይና የፍዳ፣ የልዩነትና የበደል አገዛዝ እንደነበር የሚካድ አይደለም። ደከም ያለ ለውጥ እንኳን ለማድረግ አጼውም ተከታዮቻቸውም ዝግጁ አልነበሩም። ሕዝብን ንቀውና ቀጥቅጥው መግዛት የለመዱ ነበሩና፤ እኩልነትን ነፍገው፤ ዴሞክራሲያዊ መብቶችን ሁሉ አፍነው፤ ስዩመ መለኮት ነን በሚል ዘለዓለማዊነትን ከጅለው (የዛሬውን የትግራይ ወያኔዎች፣ ጠባቦች በሚመስል ደረጃ) ነበርና ለተማሪው መልስ ምላሻቸው አፈናና ግድያ በመሆኑ ሁኔታው እየተባባሰ መሄዱ የማይቀር ሆነ።
በልዩ ልዩ ቦታዎች አመጾች መቀጠላቸው ፤ ሠርቶ አደሩ ማመጹ፤ አስተማሪዎችና የቢሮ ሠራተኞች መነሳታችው፤ የእነ ደጃዝማች ታከለ መገደልና፤ መፈንቅሎች መሞከራቸው፤ የተማሪውም ትግል ማየሉና አልቋረጥ ማለቱ ውሎ አድሮ ለየካቲት 66 መከሰት በሩን ከፈተ፤ ድልዳል ሆነ። የካቲት የግብታዊነት ውጤት ነው ፤ የሕዝብ አመጽ ድርጅትና ትግልን አይጠይቅም የሚሉት ይህን ሐቅ መረዳት የተሳናቸው መሆኑም በግልጽ ያታያል። ችግሮቹንም የነበሩት ሥርዓቶች ፈጠሯቸው እንጂ ተማሪዎች የሌለውን ችግር አለ ብለው ለተቃውሞ እልተሰለፉም። ይህን መሠረታዊ ሐቅ የዘነጉ ክፍሎች ችግር ፈጣሪውን ሥርዓት ትተው ተማሪዎች በጠበጡ፤ ሀገር አስገነጠሉ፤ . . .ወዘተ ሲሉም ይደመጣሉ።
በተጨባጭ ታኅሣሥ 20 የተማሪ ሰማዕት መዘከሪያ ቀን የተባለውም በዚህ ቀን በርካታ ተማሪዎች በመገደላቸው ነው። የተማሪው እንቅስቃሴን የሚከሱ ክፍሎች መረዳት ወይም መቀበል የተሳናቸው ከአንድ አፈና ደረጃ ወደ ከፍተኛ ጥቃት የተሸጋገረው ሥርዓቱ መሆኑን ነው። የተማሪው እንቅስቃሴ መፈክሮች ሲመረመሩና በተለይም ከዛሬው የተሰበጣጠረ መፈክር ጋር ሲነጻጸሩ በዚያን ጊዜ ተማሪዎች ሲያነሷቸው የነበሩ መፈክሮች ለሀገሪቷ ችግሮች መፍትሔን ጠቋሚ ነበሩ። ከመፈክሮች ውስጥ አንደኛው መሬት ለአራሹየሚለው ነው። የዚህ መፈክር ጥፋቱና ጎጂነቱ በተለይም ለጭሰኛውና ገባሩ ምንድ ነው የሚል ጥያቄ ሊነሳ ይችላል? የኢትዮጵያ ሕዝብ ዴሞክራሲያዊ መብት ይከበር የሚለው እስከዛሬ ያልተመለሰ የሕዝብ ጥያቄ ነው። መብት ለሠርቶ አደሩ ሕዝብድህነት ወንጀል አይደለምየሀገራችን ሉዓላዊንት ይከበርእና መሰል መፈክሮች ያኔ የቀረቡና ያታገሉም ናቸው። ሕዝባዊ መንግሥት ይቁቋምደግሞ ዛሬም ሊስተጋባ የሚገባውና የሕዝብን መሠረታዊ ፍላጎትም የሚያንጸባርቅ ነው። የሃይማኖት ልዩነቶች ተወግደው ነጻነታቸው ይጠበቅ፤ የሴቶች መብት ይከበር የሚሉት ጥያቄዎች ዛሬም መሠረታዊ ናቸው። ተማሪዎችና ተራማጁ የኤርትራም ጥያቄ በሰላማዊና ዴሞክራሲያ መንገድ ይፈታ በማለት ሲያሰሙ የነበሩት ጩኸት አድማጭ አግኝቶ ቢሆን ኖሮ አሁን የተከሰተው ችግር በአጭር በተቀጨም ነበር። የኢትዮጵያ ትግል ላይ አሉታዊ ተጽዕኖ ማድረጉ፣ ባከተመ ነበር። በወቅቱ የተደረጉት ሰልፎች በአገሪቱ ውስጥ ተከስተው የነበሩትን ሕዝባዊ መፈክሮች ይዘው መሆኑን ማንም ሊክድ አይችልም።
ጥላሁን ግዛው ተገደለ። በቀጣዩ ሰልፍና ተቃውሞም በደብረ ብርሃን እነ ሺፈራው ከበደና ሊሎችም ተረሸኑ። መኮንን ሀጎስና ሊሎችም በሐረር ፣ እንዲሁ። በጥላሁን ቀብር ላይ እነጀማል፣ ስብሓት፣ አበበና ብዙዎች በግፍና በገፍ ተገደሉ ፤ ታኅሣሥ 20 የሰማዕት ቀን የተባለውም በዚህ ነው። ያ እንቅስቃሴና ትውልድ ለሀገራችን ችግር ያቀረበውን መፍትሔ የሚመጣጠን እስካሁን ካለመቅረቡ ሌላ አሁንም ሰማህ አልሰማሁም፤ አየህ አላየሁም ባዮች ያን የከሰረውን ሥርዓት ሂደት መፍትሔ ብለው ያን ትውልድ እያወገዙ ማላዘኑን መርጠው ይገኛሉ። የቀድሞ ሰማዕትን ስንዘክርና የየካቲትንም ክስተት መሠረቱን ለመግለጽ ስንጥር በተለይም ዛሬ የሕዝብ ትግል ከሚያሳየው ድክመትና ስህተት አንጻር ከተመክሮ መማር ይቻል ነበር፤ አሁንም ይገባል ለማለት ነው ። ማለትም፡
 •   የተማሪው እንቅስቃሴ ግቡን የሚያውቅ ነበር - ዴሞክራሲና እኩልነት ለኢትዮጵያ።
 •   የተማሪው እንቅስቃሴ ብቁ አመራር የሚሰጡት የነቁ አባላት/መሪዎች ነበሩት።
 •   ያነሳቸው መፈክሮች በሞላ የሕዝብና በሕዝብ የተደገፉ ነበሩ።
 •   በጎጥ ወይም ብሔረሰብ ፣ በሃይማኖት የተከፋፈለ አልነበረም። ምንም እንኳን የተወሰኑ የኤርትራን ግንጠላ ይደግፉ የነበሩ (በኤርትራ የተወለዱ ተማሪዎች) የተማሪው ትግል አይመለከተንም ብለው ራሳቸውን ከእንቅስቃሴው ቢያገልሉም ብዙዎቹ ግን በእንቅስቃሴው ተካፍለው በዚያም ጊዜ ሆነ በየካቲት መስዋዕትነትን ከፍለዋል።
 •   የተማሪው እንቅስቃሴ በስልት ከሌሎች የኅብረተሰቡ ክፍሎች ጋር ሊቀናጅና ትግሉን ሀገር አቀፍ ሊያደርገውም መቻሉ ውጤቱ በየካቲት 66 ሊታይ ችሏል ዛሬ ያለውን ተጨባጭ ሁኔታ በጥሞና ስናየው ያኔ የነበረው ሁኔታ እንደሌለ መቀበል እንገደዳለን። ወያኔ ለሥልጣን የበቃው በወደቀው ፀረ-ሕዝብና ቀይ ሽብርተኛ አገዛዝ የተነሳ መሆኑን ማንም የሚክደው ወይም የሚዘነጋው አይደለም። እብሪተኛውና ፈርጣጩ ኮሎኔልና የወንጀሉ ተባባሪዎች የሆኑት ጓደኞቹ ሀገር ወዳድ ትውልድን ጨፍጭፈው ለገንጣይ ኃይሎች ድል መሠረት መጣላቸው ይታወቃል። ፀረ-ኢትዮጵያ ኃይሎችም ሊረባረቡ የሚችሉበት ሁኔታ ተፈጥሮ የደርግ ከፍተኛ ባልሥልጣን ከነበሩት የባዕዳን ሰላዮችና ሠራተኞች የነበሩባቸው መሆኑም ተጋልጧል። የቀጠለውን ሁኔታ ሕዝብ ያውቀዋልና ሀተታን ባይጠይቅም፤ ሀገራችንን ለቅርጫ ወያኔ ሲያቀርብ ተባባሪዎች ከየጎራቸው ብቅ ብለው አጫፋሪ ሆነውታል። ተማሪዎች ለአንዴም ለመጨረሻም ሊባል በሚችል ሁኔታ ወያኔን ተቃውመው ቢሰለፉና ቢሰዉም በጋራ እንዳይሰለፉና እንዳይቃወሙ ወያኔና ጠባቦች የተንኮል ሴራቸውን ጠንስሰው ተግባራዊ አደረጉ። ሕዝቡንም ወጣቱንም በጎጥ፣ በክልል፣ በብሔር፣ በቋንቋ፣ ...ከፋፈሉ። ይህ ሁኔታ በስፋት ሰፍኖ የሕዝብ አመጽንና ትግል አደናቅፎ እስካሁን ቆይቷል። የታኅሣሥ መንፈስና የሰማዕቱ ቅርስ ተኗል ለማለት ባንችልም ችግሩ ግን ግልጽ ነው ለሁላችንም።
ለጋራ ሀገር ለኢትዮጵያ መታገል ቀርቶ ለክልልና ለጠባብ ግብ መቆሙና ይባስ ብሎ ኢትዮጵያዊነትን መካዱም ያለ ሆኗል። የተሰው ተማሪዎችና ወጣቶች ጀግኖች፣ ተራማጆች አጥንታቸው ይገላበጥብናል። ተማሪዎችና ወጣቶች የለውጥ አንቀሳቃሾች መሆን ሲገባቸው ተከፋፍለው መቆማቸው ምስጢርም አይደለም። የሚነሱት መፈክሮች ሀገራዊ ሳይሆን ጠባብና ውሱን ናቸው። ድርጅቶቹ የኢትዮጵያን ነጻነትና የሕዝቧን ዴሞክራሲ የሚሹ ሳይሆኑ ግንጠላን የሚያቀነቅኑ ስለሆኑ ሕዝባዊ ትግልንም ሊመሩ የሚችሉ አይደሉም--አያምኑበትምና። ትግል ተብሎ የምናየው አንድ ግብ ያለው ባለመሆኑ በመከፋፈሉም ገዢውን ክፍል በጋራ ሊያጠቃ አልቻለም። ገዢው ክፍል ላይም፣ አንድ ወጥና ለአገዛዙ ተጻራሪ የሆነ አቅዋም አልከሰት ብሎ ከርሟል። ግማሹ በሰላም እንደራደር ሲል፤ ሌላው አብዮት ቃሉን እንኳን መጠቀም ስህተት ነው ብሎ ራሱን ለትዝብት ሲዳርግ፤ ቀሪው የግንጠላ አንቀጽን ይዟል በሚል የወያኔን ሕግ ሕገ-መንግሥታችን ነውና ይከበርልን በማለት ጥያቄ ሲያቀርብ፤ በዚህ ውጥንቅጥና ውዥንብር የተነሳ ወያኔ ከውድቀት እየዳነ መቀጠሉን ሁሉም በምጸት እየተገነዘበው ነው ማለት የሚቻል አልሆነም። ያን ትውልድና ያን ሀገራዊ ቁርጥ አቅዋም የምንናፍቅበት ጊዜ መምጣቱ በራሱ ምንኛ አሳሳቢ ደረጃ ላይ እንዳለን የሚጠቁም ነው። ካለፈው መማር ሲቻል ያለፈውን የሕዝብ ደምና መራራ ተመክሮ ማክቸልቸል ፤ ለሕዝብና ለሀገር ጠላቶች ሰለባ መሆን መጨረሻው ጎጂ ለመሆኑ አስተማሪ አያሻውም። መደራጀት ወሳኝ ነው፤ ትግሉ ለኢትዮጵያ መቆምና የጋራም መሆን አለበት፤ ክፍፍል ማክተሙ አስፈላጊ ይሆናል፤ በሕዝብ ላይ ሳይሆን በባዕድ ላይ መተማመኑ ማብቃት ይገባዋል። እንዲሁም ወያኔ በወደደው ቦይ መፍሰሱ ኢትዮጵያን የሚጎዳ መሆኑ መቀበል የተገባ ሲሆን ለትምክህተኞችም ሆነ ለጠባቦች መድረኩን መልቀቅ ደግሞ ሊታሰብ አይገባውም። ከራሳችን ተመክሮ ከተነሳን ለራሳችን የጋራ ታሪክ ክብር ከሰጠን ወደሚፈለገው ጎህ ለመድረስ እንችላለን። የታኅሣሥ ሰማዕትም በከንቱ አልሞቱም ማለት የምንችልበት ሁኔታ ይከሰታል ማለት ነው።
ያኔ ትግሉ ለኢትዮጵያ ነበር። የጋራ ነበር። በሥርዓቱ ላይ ሕዝብ በጋራ የተነሳበት ነበር። ዛሬ አፍን ሞልቶ ይህን ማለት አይቻልም። ያኔ የነበሩት ድርጅቶች፣ በዴሞክራሲና በእኩልነት፤ በሀገርም አንድነት ጉዳይ ላይ ልዩነቶች አልነበሯቸውም። እነ ወያኔ የጋራውን ሰልፍ ሊበታትኑ ሲነሱም አድማጭ አልነበራቸውም። ትግሎች ቀስ በቀስ የተቀነበባሩ ነበሩ እንጂ በየፊናቸው አልነጎዱም። ከሁሉም በላይ ተማሪዎችና ወጣቶች በአንድነት ተደራጅተው ቆዩ እንጂ በየብሔራችን ብለው አልተለያዩም። ምሁሮችም በአጠቃላይ ሀገራዊ ተልዕኮ እንጂ ሕዝብን በጎጥና በሃይማኖት የሚከፋፍሉ አልነበሩም። የጊዜ ጎማ ግን ያን ድንቅ ቅርስ ረጋግጦ ቀይ ሽብርተኞችና ፤ ጠባብ ነፍሰ ገዳዮች ሰው የሚባሉበትን ጊዜ ስላመጣብን ከገባንበት ረግረግ ለመውጣት ወደ ኋላ መለስ ብለን ሀገርን የዴሞክራሲና የመብት ባለቤት ለማድረግ የተደረገውን የጋራ ተጋድሎ ማስታወሱ የግድ ይሆናል። እያንዳንዱ ትውልድ የራሱን ግዳጅ መቀበልና መስቀሉንም መሸከም እንዳለበት ሲታወቅ ባለፈው ታጋይ ትውልድ ላይ በአሉታዊ መረባረብ የራስን ግዳጅ ያለመቀበልን ጥፋት የሚሸፍን አይሆንም። ካለፈው ተመክሮ ጠቃሚውን ሁሉ ቅርስ አድርጎ አሁንና ዛሬ በሚጠይቀው መንገድ መታገሉ ነው ዋናው። ስለ ትግል ወሬው ደርቶ ትግል ደብዛው ከጠፋ፤ ያው ለተቀማጭ ሰማይ ቅርቡን ያመጣል እንጂ የሚፈይደው ነገር አይኖርም። በኢትዮጵያ ተማሪዎች እንቅስቃሴ ላይና አከታትሎም በኢሕአፓና በዚያ ጀግና ትውልድ ላይ ዛሬ የሚደመጠው መረን የለቀቀ አሉታዊ ትችት የሕዝብ ትግል ጠላት በሆነው ወያኔና መሰሎቹ የሚራገብ፤ ያሁኑ ወጣት ትውልድ ካለፈው እንዳይማር ለማድረግ መሆኑን የምንስተው አይደለም። በመሆኑም ነው ቅርሳችንን በተደጋጋሚ ለማሳወቅና የአሁኑ ባለፈው የኅብረትና የዕኩልነት፣ የኢትዮጵያዊነት ጎዳና እንዲጓዝ ለመጥራት እየሞከርን ያለነው።
ጊዜ ተለውጧልና በጨቋኞች ላይ ብረት ማንሳቱ ጊዜው አልፎበታል የሚሉም እንዳሉ የምናውቀው ነው። በዚያው ልክ ግን ለውጥ በአመጽና በብረት ትግልም እንደሚመጣ በዓለም ደረጃ እያየነው ከመሆኑ ሌላ ሕዝብም ደምቶና ታግሎ ድሉን በታጠቁ እንዳይቀማ (የካቲትን ያስታውሷል! ግብጽን ይመለከቷል!) ድርጅትና ኃይል ያስፈልገዋል። ሁሉን ኃይሎች ያቀፈ የሽግግር ሂደት ይኑር በሚል የቀረበውን አብዮት አድን አማራጭ ያኔም ሥልጣን ቀሚዎቹና ዛሬም እርዝራዦቻቸው በአሉታዊ ቢተቹትም ይህን ሕዝባዊ አማራጭን ዕውን ለማድረግ መንገዱ ምለላ ወይም ባዕዳንን ልመና እንዳልሆነ ግልጽ ሊሆንልን ይገባል። የድርጅቶቹንም ይዘትና ተመክሮ በሚገባ መመርመሩ የሚታለፍ ወይም ቸል የሚባል ግዳጅ አይደለም - ነጋ ጠባ የፖለቲካ ቁማርተኞች ሰለባ እያደረጉን ወደ ክስረትና ቀቢጸ ተስፋ እንዳይከቱን ማለት ነው። ደግሞ ደጋግሞ የሚታለል ሰው የሚታዘንለት ሊሆን አይችልም ተብሏልና እየተስተዋለ እንላለን። ጥላሁን ተባለ ጀማል፤ ደመቀ ተባለ አበበ፤ ጀሚላ ተባለች አስቴር ፤ አበራ ገሙ ተባለ ገ/እግዚአብሔር ... ወዘተ ከአንድ ብሔር የተወለዱ ሳይሆኑ ለኢትዮጵያ ብለው የታገሉና የሞት ጽዋንም የጠጡ ጀግኖች ናቸው። አርዓያዎች። ከደርግ ሽብርተኞችና ከወያኔ ዘረኞች የተለዩ፤ የተቃረኑ። ተባብረው የታገሉ፤ ፍርሃትን አሽንፈው ሞትን የተጋፈጡ፤ የአፍ ሳይሆን የተግባር ታጋዮች፤ ኢትዮጵያንም መውደዳቸውን ውድ ህይወታቸውን ሰጥተው ያስመሰከሩ። የታኅሣሥን ሰማዕት፤ የተማሪውና የሠራተኛውን፣ የአርሶ አደሩና የወታደሩን፣ የአስተማሪውን የሴቱን፣ ...ወዘተ ትግል ስንዘክር ያ ኢትዮጵያዊነት፤ ያ ቆራጥነት፤ ያ ኅብረት ህያውነቱ ይታደስ ዘንድ በመፈለግ ነው።
ለሕዝብና ለሀገር የተሰዉ ሁሉ በትግላችን ህያው ይሁኑ ! ኢትዮጵያዊነት ያቸንፋል !!

Thursday, January 28, 2016

Statssekretær til Etiopia

http://www.utviklingsfondet.no/nyheter/statssekretaer_til_etiopia


Det er gledelig at norske myndigheter viser at det tørkerammede Etiopia er en prioritet.

Statssekretær i Utenriksdepartementet Tone Skogen ankommer i dag Etiopia.
Landet opplever nå en alvorlig tørke. Det fryktes at så mange som 15 millioner kan rammes at matmangel i løpet av de kommende månedene. Derfor er det gledelig at norske myndigheter med dette besøket signaliserer at Etiopia er en prioritet, sier daglig leder i Utviklingsfondet Kari Helene Partapuoli.
Etiopia har krevende klimatiske forhold og har vært rammet av tørke mange ganger tidligere. Klimaendringer vil gjøre landet enda mer utsatt for tørke, sviktende avlinger og sult i fremtiden.
Gjennom vårt arbeid har vi erfart at bønder står mye sterkere i tørkeperioder dersom de får litt hjelp til å skaffe vann, bytte til vekster som tåler tørke bedre og dyrke på måter som gir større avlinger i tørre perioder.
- For å forebygge fremtidige kriser burde Norge støtte langsiktige tiltak for å fremme klimasmart landbruk i Etiopia og andre land med krevende dyrkingsforhold, fortsetter Partapuoli.

Tuesday, January 26, 2016

የወያኔን ብሎን ለማወላለቅ ( Finote Democracy: The Voice of Ethiopian Unity! )

http://ethfreedomfighter.blogspot.no
ብሎኖቹ ሁሉ የወላለቁ፤ የተበላሹ፤ ቤንዚን አልባ የሆነ መኪና ሊንቀሳቀስ አይችልም ነው። ወያኔም እንደዚያው ነው። የአፈና መሳሪያዎች ስላሉት ብቻ በሰላም ሊገዛ አይችልም። የአፈና መሳሪያዎቹን ራሳቸውን ማበለሻሸት፤ ከጥቅም ውጪ ማድረግ ይቻላል። የደርግን ግዙፍ ጦር ውድቀት ያጤኗል!
ወያኔ መንግስት ሆኛለሁ ብሎ ሲውገረገር ከመቀሌ እስክ ሞያሌ፤ ከጅማ እስከ አሳይታ መዋቅር ዘርግቻለሁ ባይ ነው። ለዚህ ስራው በመለስተኛ ቡችላነት፤ ባርነትየሚያገለግሉትና ሕዝብን በጎሳና በሀይማኖት ከፍለውለት የሚሰሩለት አሉ። ተለጣፊና ቅጥረኛ የምንላቸው እነ አዲሱ-ብአዴን፤ እነ ሀይለማርያምና አባዱላ ዓይነቶቹን ማለት ነው።

 የወያኔ መዋቅር ወልገድ ወልገድገድ ካለ ቆይቷል። ሙስናና ዘረኝነት እንደ ምስጥ በልቶታል። አውራጃዊነት ምርጥ ዜጋ የተባሉትንም እያመሳቸው ነው። ሙስሊም ኢትዮጵያውያን መብታችን እምነታችን ይከበር ብለው ትግል ከጀመሩ ዓመቶችን እያስቆጠሩ ነው። ሕዝብ እንደ ህዝብ ቅሬታ ይዟል፤ ከባድ ቂም ቋጥሯል። ሂሳብ ማወራረጃ ቀንን እየጠበቀ እንዳለም ግልጽ አድርጓል ማለት ይቻላል። የሚጠበቀው የጋለ ትግል ግን ገና መሆኑ ይታያል። የአመጽ መከሰቻው ዘግይቷል። ስለ ትግል የሚያወሳው በዝቶ ተጨባጭ ትግል ግን ኮስሶ እንዳለ ዜጋ ሁሉ የሚያውቀው ነው። በ 6 ወር ነጻ እናወጣችኋለን ገንዘብ አምጡ ብቻ ያሉንም ኪሳቸውን ሞሉ እንጂ በስድስት ዓመትም አልቻሉም። ነውናም ሕዝብ ነጻ አውጪን ሳይጠበቅ የራሱንና የሀገሩን ጉዳይ የራሱ አድርጎ መነሳትና ወያኔን በሁሉም መስክ እያጠቃ ማዳከምና ለማሸነፍም መጣር አለበት። 
ወያኔ ሰፊ መዋቅር አለውና ስስ ብልቶቹ ብዙ ናቸው። እነዚህን ለይቶ ማወቅና ማጥቃት ብዙ ጉዳትን ያመጣበታል። ወያኔ ሰላማዊ ሰልፍን በጥይት ይበትናል ሲባል የሙት ከተማ አድማን መጠቀም ያዋጣል የተባከውን አንዘነጋም። የአይሲስ ነፍሰ ገዳዮች ኢትዮጵያውያን በሊቢያ ያረዱ ወቅት የተደረጉትን ሰልፎችንም መጥቀስ ይቻላል። ዝግጅትና የይቻላል መንፈስ ካለ በጋራ ተቃውሞ ብዙ ማድረግ ይቻላል። ሰፊ ድርጅትን ሳይጠይቁ በግለሰብና በጥቂት የሚተማመኑ ዜጎችም ብዙ መስራት ይቻላል። ክብሪትን ከወያኔ ንብረቶች ማስተዋወቁ አንዱ ስምሪት ነው። የወያኔን ምስጢር የአደባባይ ማድረግም ይጎዳዋል። ችሎታ ያላቸው ደግሞ የወያኔን የኮምፕዩተር መዋቅር ጥሰው ገብተው ሊያበላሹትና የምስጢር ሰነዶቹንም ይፋ ሊያደርጉበት ይችላሉ። የወያኔን የመስሪያ ቤት ኮምፕዩተሮችንም ማበላሸት ትግል ነው። የወያኔን፤ የአፋኝ ተቅዋሞቹን መኪናዎችንም ሆነ ሌሎች ተንቀሳቃሾችን ማበላሸት ይቻላል። በወያኔ የፖሊስና ወታደራዊ ተቋሞች ውስጥ ያሉ ሀገር ወዳድ ዜጎች ብዙ ይጠበቅባቸዋል። የወያኔ ቀንደኛ አገልጋዮችንና
በተለይም ሰላዮችን ስማቸውንና አድራሻቸውንም ይፋ ማድረግ ጉዳቱ ቀላል አይደለም። በዚህ ስምሪት የውስጡና የውጩ ጥረት ሊቀናጅ ይችላል።
ቀደም ማዕቀብ ያልነውም በዚሁ ሊነሳ የሚገባው ነው። በተለይም በውጭ ሀገር ያሉት ዜጎች በወያኔና በቀንደኛ ደጋፊዎቹ ንግድና ምርት ላይ ሙሉ ማዕቀብ ሊያደርጉ ይችላሉ። የወያኔ የጤፍ እንጀራ፤ ቢራ፤ የገንዘብ መለወጫ ቢሮዎች፤ የወያኔ ቪኖ፤ የወያኔ ጋዜጦችና ድረ ገጾች፤ አየር መንገዱ፤ ወያኔዎች ሁሉም ላይ ማዕቀብ ማረግ ይቻላል። በሀገር ቤት ወደ ወያኔ ሱቅና ሆቴል አለመግባት፤ ወያኔ ከሆኑ ባለሱቆች አለመሸመት፤ በወያኔ አውቶቡሶች አለመጓዝ--ዝርዝሩ ብዙ ነው ግን መደረግ ያለበት ስውር አይደለም። ወያኔን ገንዘብ አለመስጠት፤ ከሕዝብ መነጠል ማለትም ነው። በወያኔ ላይ ጎጂ ቅስቀሳ ማካሄድም መፋፋም አለበት። በውስጣቸው ክፍፍልን ማባባስ ይጠቅማል። ታምራት ላይኔን ከወያኔ ለማጣላት በስልት በኢሕአፓ የተፈጸመው ሻጥር ምሳሌ ሊሆንም ይችላል። አሁንም እየተካሄዱ ያሉ ጸረ ወያኔ ከፋፋይና ጎጂ ሻጥሮች እንዳሉ መገመትም ከባድ አይደለም። ወያኔን (ፖሊስ፤ ጸጥታና ወታደራዊ ተቋሞቹን ወዘተ) ሰርጎ መግባት ደግሞ በግለሰብ ደረጃም ሊሰራ የሚችል ነው። ወያኔ ጠላት ነውና በውስጡ ሰርገው ገብተው የሚጎዱት ካሉ ለጥቃት በሚገባ ይጋለጣል። የሰርጎ ገብ ስምሪት በግልም በተደራጀ መልክም ሊካሄድ የሚችል ነው። ባለፈው አገዛዝ የኢሕአፓ ሰርጎ ገቦች በልዩ ልዩ ደረጃ ደርግን ሊጎዱና ድርጅቱን ሊከላከሉ ችለዋል። የዚህን ዝርዝር ማቅረቡ ያለው ሁኔታ ባይፈቅድም ታሪክ ግን ዘግቦት የሚያቆየው መሆኑ አያጠራጥርም። ባለፉት ጥቂት ዓመታት ወያኔ በበኩሉ ባጀት መድቦና ሰርጎ ገቦችን አሰናድቶና አሰልጥኖ ወደ ኢሕአፓ የላካቸውን ማክሸፍ ተችሏል። ድርጅቶችና ዜጎችም ጥንቃቄ ካደረጉ፤ ሙያተኛ ስምሪትን ከተጠቀሙ ሰርገው የሚገቡ ወይም ህብረተሰቡን ተመሳስለው ሊሰልሉ የሚሞክሩት ውጤት አልባ ይሆናል። ወያኔና ደጋፊዎቹን ከሕዝብ ማራቅ አንዱ ጥንቃቄ ነው። አንዳንዶች ሻጥር ሲባል ቀፈፍ የሚላቸውና አግባባ ያጣም ነው የሚሉ አሉ። በመሰረታዊው ጉዳይ ላይ ግልጽነት ካላቸው ግን ይህ ጥርጣሬ አይመጣባቸውም። መሰረታዊው ጉዳይ ወያኔ የኢትዮጵያና የሕዝብ ጠላት ነው የሚለው ነው። ካራቢንዬሪውን/ሶልዳቶውን ከባንዳው መለየት አይገባምና ጠላት ሲባል ጠላትን የሚጎዳ፤ የሚያደናቅፍ እርምጃን ሁሉ መውሰድ አስፈላጊ ነው ማለት ነው። የኢትዮጵያ አየር መንገድ ላይ ማዕቀብ አድርጉ ሲባል ይህ ተቋም የሚያገኘው ምርት ለወያኔ መጠቀሚያ በመዋሉ ብቻ ሳይሆን አብዛኛው ሰራተኞቹም ተመርጠው ከወያኔ መንደር የተወለዱ በመሆናቸውም ነው። የወያኔ ዕቅዶች በሞላ ለወያኔ እንጂ ለኢትዮጵያ አይጠቅሙምና ቢደናቀፉ ተገቢ ነው። መደናቀፍም አለባቸው። ወያኔዎችን ማራቅ መጥላት ስንልም መነሻው ይኸው ነው--ጠላትን ማራቅ መጉዳት እርስ በርሱ እንዲናቆር ሻጥር መስራት፤ ሴራዎችን መጎንጎን ማለት ነው። በዚህ ላይ ጠንክሮ መግፋት ሲፈለግ ይህን የሚቃወሙት ጉዶች ማፈሪያ
የሆኑት ለዚህ ነው። አይ አይገባም፤ ላንፋታ ተጋብተናል ወዘተ ዓይነት አቅዋሞችና ንግግሮች የሚጠቅሙ አይደሉም።
የወያኔን የትራንስፖርት አቅምም መዳከም ያለበት ነው። የጦሩን የመንቀሳቀስ ችሎታም ማዳከም ከድንበር ጥበቃ ሳይሆን ከአጋዚና ፌዴራልን ማደናቀፍ ጋር የሚያያዝ ነው። የወያኔ ጦር የኢትዮጵያ ሳይሆን የወያኔ ነው። ወያኔ ከሻዕቢያ ቅራኔ የገባው ለኢትዮጵያ ብሎ አይደለም። ሆኖም ግን ስምሪታችን ለሀገር ጠላቶች ምንም ቀዳዳ የማይከፍት መሆን እንዳለበት ማስታወስ ይገባል፡፡ ዚያድ ባሬ ኢትዮጵያን ሲወር በ ጦሩ የነበሩ የኢሕአፓ አባላት ተዋግተው ተሰዉ እንጂ ድርጅቱ ሚሊሺያውን ሆነ ወታደሩን ለማደናቀፍ የሰራው አንድም ነገር እንደሌለ ህዝብ ያውቃል፤ አናምንም የሚሉ ዋሾ ደርጎችና ርዝራዦቹ መሆናቸውም ተጋልጧል። ወያኔም ኢሕአዴግ አይደለም-- ነጻ ድርጅቶች ሳይሆኑ ተለጣፊዎችን ያቀፈ ነውና አገዛዙ ወያኔ ተብሎ መጠራቱ አግባብ ያለው ነው። ሕወሀት/ኢሕአዴግ ብለው ከጫማው የሚደፉት ማፈሪያ የተባሉት ለዚህ ነው። ወያኔ መንግስት አይደለም--በሕዝብ ላይ የተጫነ ጨቋኝና ዘረኛ አገዛዝ እንጂ። ወያኔ ኢትዮጵያዊ አይደለም--ትግራይ ትግራይ የሚል ጎጠኛና ጠባብ ብሄረተኛ ቡድን እንጂ። እነዚህን ከተገነዘብንና ወያኔ ጠላት መሆኑ ላይ ምንም ዓይነት ብዥታ ላለማስተናገድ ከወሰንን ምን እርምጃ መውሰድ እንዳለብን ግልጽ ይሆንልናል። ገደብም የሚያስፈልገው አይመስለንም። 
ሀገርና ወያኔ ለየቅል ናቸው። ይህ ዘረኛ ቡድን ሀገርን የጎዳው ዘረኝነትን ጎጠኝነትን በማስፋፋትና በተለይም የወጣቱን የአንድነት/አብሮነት ስሜት በመስለብ በማጫጫት ነው። ይህም ወጣቶችን በሀገር ፍቅር ስሜት፤ በአርበኞችና ጀግና ትውልድ መንፈስ መቃኘት ትኩረት ተሰጥቶት መሰራት ያለበት ነው። ወጣቱ ከዳነ ሀገር ትድናለች። ትውልዱን ታሪክ አልባ ለማድረግና ሀገሪቷ ጀግናም አፍርታ አታውቅ በሚል ለማናውዝ እየጣሩ ያሉ ምሁሮች የወጣቱን አንጎል እንዳይሰርቁም መታገል ወሳኝ ነው። ወያኔ በሕዝብ ዘንድ በአጠቃላይ በወጣቱ በተለይ ቀቢጸ ተስፋን ማስፈን ይፈልጋልና በዚህ ጨለምተኝነት ዘመቻ የሚያጅቡትን ምሁሮች ለአንዴም ለሁሌም ወግዱ ማለትም አስፈላጊ ነው። የትግል መንፈስን ማስጨበጥ የቤተሰቦችም የህብረተሰቡም ተግባርና ግዳጅ መሆኑም መዘንጋት የለበትም። ሞራል ግንባታ፤ ሰብዕናን ማስከበር፤ ሕይወቴ ለኢትዮጵያ ማለት፤ በገቢር ወደ ትግል መሰማራትና መሰል መንፈሶችን የራስ ማድረግ የሚጠበቅ ነው ማለት ነው። አይናችን እያየ ወጣቶቻችንን ወኔ ቀምቶና ወደ ጎጠኛነት ነክሮ ሀገረ የሚል ትውልድ እንዳያሳጣን የሞት የሽረት ትግል ማካሄድ አለብን። አማራጭ የለንም። ሀገርን ለማዳን ትውልድን ወደ ቀና ሀገር ወዳድ ጎዳና እነመልስ። 
በሁሉም አጋጣሚና ባለን አቅም ሁሉ ወያኔን እናጥቃ፤እናዳክም፤ ወደ ውድቀቱም እንግፋው

የወያኔን ብሎን ለማወላለቅ ( Finote Democracy: The Voice of Ethiopian Unity! )

ብሎኖቹ ሁሉ የወላለቁ፤ የተበላሹ፤ ቤንዚን አልባ የሆነ መኪና ሊንቀሳቀስ አይችልም ነው። ወያኔም እንደዚያው ነው። የአፈና መሳሪያዎች ስላሉት ብቻ በሰላም ሊገዛ አይችልም። የአፈና መሳሪያዎቹን ራሳቸውን ማበለሻሸት፤ ከጥቅም ውጪ ማድረግ ይቻላል። የደርግን ግዙፍ ጦር ውድቀት ያጤኗል!
ወያኔ መንግስት ሆኛለሁ ብሎ ሲውገረገር ከመቀሌ እስክ ሞያሌ፤ ከጅማ እስከ አሳይታ መዋቅር ዘርግቻለሁ ባይ ነው። ለዚህ ስራው በመለስተኛ ቡችላነት፤ ባርነት የሚያገለግሉትና ሕዝብን በጎሳና በሀይማኖት ከፍለውለት የሚሰሩለት አሉ። ተለጣፊና ቅጥረኛ የምንላቸው እነ አዲሱ-ብአዴን፤ እነ ሀይለማርያምና አባዱላ ዓይነቶቹን ማለት ነው።

 የወያኔ መዋቅር ወልገድ ወልገድገድ ካለ ቆይቷል። ሙስናና ዘረኝነት እንደ ምስጥ በልቶታል። አውራጃዊነት ምርጥ ዜጋ የተባሉትንም እያመሳቸው ነው። ሙስሊም ኢትዮጵያውያን መብታችን እምነታችን ይከበር ብለው ትግል ከጀመሩ ዓመቶችን እያስቆጠሩ ነው። ሕዝብ እንደ ህዝብ ቅሬታ ይዟል፤ ከባድ ቂም ቋጥሯል። ሂሳብ ማወራረጃ ቀንን እየጠበቀ እንዳለም ግልጽ አድርጓል ማለት ይቻላል። የሚጠበቀው የጋለ ትግል ግን ገና መሆኑ ይታያል። የአመጽ መከሰቻው ዘግይቷል። ስለ ትግል የሚያወሳው በዝቶ ተጨባጭ ትግል ግን ኮስሶ እንዳለ ዜጋ ሁሉ የሚያውቀው ነው። በ 6 ወር ነጻ እናወጣችኋለን ገንዘብ አምጡ ብቻ ያሉንም ኪሳቸውን ሞሉ እንጂ በስድስት ዓመትም አልቻሉም። ነውናም ሕዝብ ነጻ አውጪን ሳይጠበቅ የራሱንና የሀገሩን ጉዳይ የራሱ አድርጎ መነሳትና ወያኔን በሁሉም መስክ እያጠቃ ማዳከምና ለማሸነፍም መጣር አለበት።
ወያኔ ሰፊ መዋቅር አለውና ስስ ብልቶቹ ብዙ ናቸው። እነዚህን ለይቶ ማወቅና ማጥቃት ብዙ ጉዳትን ያመጣበታል። ወያኔ ሰላማዊ ሰልፍን በጥይት ይበትናል ሲባል የሙት ከተማ አድማን መጠቀም ያዋጣል የተባከውን አንዘነጋም። የአይሲስ ነፍሰ ገዳዮች ኢትዮጵያውያን በሊቢያ ያረዱ ወቅት የተደረጉትን ሰልፎችንም መጥቀስ ይቻላል። ዝግጅትና የይቻላል መንፈስ ካለ በጋራ ተቃውሞ ብዙ ማድረግ ይቻላል። ሰፊ ድርጅትን ሳይጠይቁ በግለሰብና በጥቂት የሚተማመኑ ዜጎችም ብዙ መስራት ይቻላል። ክብሪትን ከወያኔ ንብረቶች ማስተዋወቁ አንዱ ስምሪት ነው። የወያኔን ምስጢር የአደባባይ ማድረግም ይጎዳዋል። ችሎታ ያላቸው ደግሞ የወያኔን የኮምፕዩተር መዋቅር ጥሰው ገብተው ሊያበላሹትና የምስጢር ሰነዶቹንም ይፋ ሊያደርጉበት ይችላሉ። የወያኔን የመስሪያ ቤት ኮምፕዩተሮችንም ማበላሸት ትግል ነው። የወያኔን፤ የአፋኝ ተቅዋሞቹን መኪናዎችንም ሆነ ሌሎች ተንቀሳቃሾችን ማበላሸት ይቻላል። በወያኔ የፖሊስና ወታደራዊ ተቋሞች ውስጥ ያሉ ሀገር ወዳድ ዜጎች ብዙ ይጠበቅባቸዋል። የወያኔ ቀንደኛ አገልጋዮችንና
በተለይም ሰላዮችን ስማቸውንና አድራሻቸውንም ይፋ ማድረግ ጉዳቱ ቀላል አይደለም። በዚህ ስምሪት የውስጡና የውጩ ጥረት ሊቀናጅ ይችላል።
ቀደም ማዕቀብ ያልነውም በዚሁ ሊነሳ የሚገባው ነው። በተለይም በውጭ ሀገር ያሉት ዜጎች በወያኔና በቀንደኛ ደጋፊዎቹ ንግድና ምርት ላይ ሙሉ ማዕቀብ ሊያደርጉ ይችላሉ። የወያኔ የጤፍ እንጀራ፤ ቢራ፤ የገንዘብ መለወጫ ቢሮዎች፤ የወያኔ ቪኖ፤ የወያኔ ጋዜጦችና ድረ ገጾች፤ አየር መንገዱ፤ ወያኔዎች ሁሉም ላይ ማዕቀብ ማረግ ይቻላል። በሀገር ቤት ወደ ወያኔ ሱቅና ሆቴል አለመግባት፤ ወያኔ ከሆኑ ባለሱቆች አለመሸመት፤ በወያኔ አውቶቡሶች አለመጓዝ--ዝርዝሩ ብዙ ነው ግን መደረግ ያለበት ስውር አይደለም። ወያኔን ገንዘብ አለመስጠት፤ ከሕዝብ መነጠል ማለትም ነው። በወያኔ ላይ ጎጂ ቅስቀሳ ማካሄድም መፋፋም አለበት። በውስጣቸው ክፍፍልን ማባባስ ይጠቅማል። ታምራት ላይኔን ከወያኔ ለማጣላት በስልት በኢሕአፓ የተፈጸመው ሻጥር ምሳሌ ሊሆንም ይችላል። አሁንም እየተካሄዱ ያሉ ጸረ ወያኔ ከፋፋይና ጎጂ ሻጥሮች እንዳሉ መገመትም ከባድ አይደለም። ወያኔን (ፖሊስ፤ ጸጥታና ወታደራዊ ተቋሞቹን ወዘተ) ሰርጎ መግባት ደግሞ በግለሰብ ደረጃም ሊሰራ የሚችል ነው። ወያኔ ጠላት ነውና በውስጡ ሰርገው ገብተው የሚጎዱት ካሉ ለጥቃት በሚገባ ይጋለጣል። የሰርጎ ገብ ስምሪት በግልም በተደራጀ መልክም ሊካሄድ የሚችል ነው። ባለፈው አገዛዝ የኢሕአፓ ሰርጎ ገቦች በልዩ ልዩ ደረጃ ደርግን ሊጎዱና ድርጅቱን ሊከላከሉ ችለዋል። የዚህን ዝርዝር ማቅረቡ ያለው ሁኔታ ባይፈቅድም ታሪክ ግን ዘግቦት የሚያቆየው መሆኑ አያጠራጥርም። ባለፉት ጥቂት ዓመታት ወያኔ በበኩሉ ባጀት መድቦና ሰርጎ ገቦችን አሰናድቶና አሰልጥኖ ወደ ኢሕአፓ የላካቸውን ማክሸፍ ተችሏል። ድርጅቶችና ዜጎችም ጥንቃቄ ካደረጉ፤ ሙያተኛ ስምሪትን ከተጠቀሙ ሰርገው የሚገቡ ወይም ህብረተሰቡን ተመሳስለው ሊሰልሉ የሚሞክሩት ውጤት አልባ ይሆናል። ወያኔና ደጋፊዎቹን ከሕዝብ ማራቅ አንዱ ጥንቃቄ ነው። አንዳንዶች ሻጥር ሲባል ቀፈፍ የሚላቸውና አግባባ ያጣም ነው የሚሉ አሉ። በመሰረታዊው ጉዳይ ላይ ግልጽነት ካላቸው ግን ይህ ጥርጣሬ አይመጣባቸውም። መሰረታዊው ጉዳይ ወያኔ የኢትዮጵያና የሕዝብ ጠላት ነው የሚለው ነው። ካራቢንዬሪውን/ሶልዳቶውን ከባንዳው መለየት አይገባምና ጠላት ሲባል ጠላትን የሚጎዳ፤ የሚያደናቅፍ እርምጃን ሁሉ መውሰድ አስፈላጊ ነው ማለት ነው። የኢትዮጵያ አየር መንገድ ላይ ማዕቀብ አድርጉ ሲባል ይህ ተቋም የሚያገኘው ምርት ለወያኔ መጠቀሚያ በመዋሉ ብቻ ሳይሆን አብዛኛው ሰራተኞቹም ተመርጠው ከወያኔ መንደር የተወለዱ በመሆናቸውም ነው። የወያኔ ዕቅዶች በሞላ ለወያኔ እንጂ ለኢትዮጵያ አይጠቅሙምና ቢደናቀፉ ተገቢ ነው። መደናቀፍም አለባቸው። ወያኔዎችን ማራቅ መጥላት ስንልም መነሻው ይኸው ነው--ጠላትን ማራቅ መጉዳት እርስ በርሱ እንዲናቆር ሻጥር መስራት፤ ሴራዎችን መጎንጎን ማለት ነው። በዚህ ላይ ጠንክሮ መግፋት ሲፈለግ ይህን የሚቃወሙት ጉዶች ማፈሪያ
የሆኑት ለዚህ ነው። አይ አይገባም፤ ላንፋታ ተጋብተናል ወዘተ ዓይነት አቅዋሞችና ንግግሮች የሚጠቅሙ አይደሉም።
የወያኔን የትራንስፖርት አቅምም መዳከም ያለበት ነው። የጦሩን የመንቀሳቀስ ችሎታም ማዳከም ከድንበር ጥበቃ ሳይሆን ከአጋዚና ፌዴራልን ማደናቀፍ ጋር የሚያያዝ ነው። የወያኔ ጦር የኢትዮጵያ ሳይሆን የወያኔ ነው። ወያኔ ከሻዕቢያ ቅራኔ የገባው ለኢትዮጵያ ብሎ አይደለም። ሆኖም ግን ስምሪታችን ለሀገር ጠላቶች ምንም ቀዳዳ የማይከፍት መሆን እንዳለበት ማስታወስ ይገባል፡፡ ዚያድ ባሬ ኢትዮጵያን ሲወር በ ጦሩ የነበሩ የኢሕአፓ አባላት ተዋግተው ተሰዉ እንጂ ድርጅቱ ሚሊሺያውን ሆነ ወታደሩን ለማደናቀፍ የሰራው አንድም ነገር እንደሌለ ህዝብ ያውቃል፤ አናምንም የሚሉ ዋሾ ደርጎችና ርዝራዦቹ መሆናቸውም ተጋልጧል። ወያኔም ኢሕአዴግ አይደለም-- ነጻ ድርጅቶች ሳይሆኑ ተለጣፊዎችን ያቀፈ ነውና አገዛዙ ወያኔ ተብሎ መጠራቱ አግባብ ያለው ነው። ሕወሀት/ኢሕአዴግ ብለው ከጫማው የሚደፉት ማፈሪያ የተባሉት ለዚህ ነው። ወያኔ መንግስት አይደለም--በሕዝብ ላይ የተጫነ ጨቋኝና ዘረኛ አገዛዝ እንጂ። ወያኔ ኢትዮጵያዊ አይደለም--ትግራይ ትግራይ የሚል ጎጠኛና ጠባብ ብሄረተኛ ቡድን እንጂ። እነዚህን ከተገነዘብንና ወያኔ ጠላት መሆኑ ላይ ምንም ዓይነት ብዥታ ላለማስተናገድ ከወሰንን ምን እርምጃ መውሰድ እንዳለብን ግልጽ ይሆንልናል። ገደብም የሚያስፈልገው አይመስለንም።
ሀገርና ወያኔ ለየቅል ናቸው። ይህ ዘረኛ ቡድን ሀገርን የጎዳው ዘረኝነትን ጎጠኝነትን በማስፋፋትና በተለይም የወጣቱን የአንድነት/አብሮነት ስሜት በመስለብ በማጫጫት ነው። ይህም ወጣቶችን በሀገር ፍቅር ስሜት፤ በአርበኞችና ጀግና ትውልድ መንፈስ መቃኘት ትኩረት ተሰጥቶት መሰራት ያለበት ነው። ወጣቱ ከዳነ ሀገር ትድናለች። ትውልዱን ታሪክ አልባ ለማድረግና ሀገሪቷ ጀግናም አፍርታ አታውቅ በሚል ለማናውዝ እየጣሩ ያሉ ምሁሮች የወጣቱን አንጎል እንዳይሰርቁም መታገል ወሳኝ ነው። ወያኔ በሕዝብ ዘንድ በአጠቃላይ በወጣቱ በተለይ ቀቢጸ ተስፋን ማስፈን ይፈልጋልና በዚህ ጨለምተኝነት ዘመቻ የሚያጅቡትን ምሁሮች ለአንዴም ለሁሌም ወግዱ ማለትም አስፈላጊ ነው። የትግል መንፈስን ማስጨበጥ የቤተሰቦችም የህብረተሰቡም ተግባርና ግዳጅ መሆኑም መዘንጋት የለበትም። ሞራል ግንባታ፤ ሰብዕናን ማስከበር፤ ሕይወቴ ለኢትዮጵያ ማለት፤ በገቢር ወደ ትግል መሰማራትና መሰል መንፈሶችን የራስ ማድረግ የሚጠበቅ ነው ማለት ነው። አይናችን እያየ ወጣቶቻችንን ወኔ ቀምቶና ወደ ጎጠኛነት ነክሮ ሀገረ የሚል ትውልድ እንዳያሳጣን የሞት የሽረት ትግል ማካሄድ አለብን። አማራጭ የለንም። ሀገርን ለማዳን ትውልድን ወደ ቀና ሀገር ወዳድ ጎዳና እነመልስ።
በሁሉም አጋጣሚና ባለን አቅም ሁሉ ወያኔን እናጥቃ፤እናዳክም፤ ወደ ውድቀቱም እንግፋው

FINOTE RADIO


oፍኖተ ዴሞክራሲ ራድዮ  አጫጭር ዜናዎች
o ረሀቡ ህፃናትን እየፈጀ ነው፡፡
o በተለያዩ አካባቢዎች ሕዝባዊ አመጽ እንደቀጠለ ነው፡፡
o ባሳለፍነው ሳምንት የግል ባንኮች ድንገተኛ የብር እጥረት ውስጥ እንደገቡ ታወቀ፡፡
o የድንበር ማካለሉ በዚህ በያዝነው አመት እንደሚጠናቀቅ በሱዳን እየተነገረ ነው፡
o ከሙስሊሞች እንቅስቃሴ ጋር በተያያዘ የታሰሩት ተፈረደባቸው
o ወያኔ በአሜሪካ የሚኖሩ ተቃዋሚዎች ተላልፈው እንዲሰጡት ለአሜሪካ ሰነድ እንዳዘጋጀ ተወቀ፡፡ o የወያኔ የመዋጮ ወረርሽኝ ሠራተኞችን እያማረረ ነው
o የአውሮፓው ፓርላማ ውሳኔዎችን አሳለፈ
o የቀድሞ የናይጄሪያ ባለስልጣኖች 9 ቢሊዮን የአገሪቷን ሀብት መዝረፋቸው ተነገረ
o የደቡብ ሱዳን የአንድነት መንግስት እንዲመሰረት የተያዘለት ቀነ ቀጠሮ ሳይከበር ቀረ
 •   ባሳለፍነው ሳምንት በሐዲያ ወደ ሆሳዕና እና ወደ ተለያዩ ከተሞች የሚደረጉ የትራንስፖርት እንቅስቃሴዎች ለአንድ ቀን ዝግ ሆነው መዋላቸውንና በኋላም መጀመራቸውን ከአካባቢው ከተገኘው መረጃ ለማወቅ ተችሏል። ትራንስፖርት ሊቋረጥ የቻለው የአካባቢው ባለስልጣኖች የጣሉትን ተጨማሪ የቅጣት መመሪያ በመቃወም አሽከርካሪዎች አድማ በመምታታቸው ሲሆን መመሪያው የተነሳ መሆኑ ሲገለጽ የትራንስፖርት አገልግሎቱ የጀመረ መሆኑ ታውቋል። ከዚህ ጋር በተያያዘ በሃዲያ ዞን ከሚገኘው ከዎቻሞ ዪኒቨርስቲ ተይዘው የተወሰዱት 8 ተማሪዎች የት እና በምን ሁኔታ ላይ መሆናችው ስላልታወቀ ቤተሰቦቻቸው በከፍተኛ ሀሳብና ጭንቀት ላይ የወደቁ መሆናቸውን ከአካባቢው የተገኙ ዜናዎች ገልጸዋል። በዲላም ዩኒቨርስቲ ውስጥ ከተማሪዎቹ እኩል ቁጥር ያለው የአግአዚ ጦር ተሰማርቶ ጥበቃ እያካሄደ ሲሆን በተማሪዎቹ ላይ ከፍተኛ በደል ከመፈጸሙ ባሻገር የእጅ ስልኮቻቸውንም የቀማ መሆኑ ታውቋል።
 •   ጥር 11 ቀን 2008 ዓም በመላው ኢትዮጵያ በሚገኙ የክርስትና እምነት ተከታዮች የጥምቀት በዓል በደመቀ ሁኔታ የተከበረ ሲሆን የአዲስ አበባ በዓል አከባበር ላይ በወያኔ የደኅነነት ኃይሎች ተጥለቅሎ እንደንበር ከስፍራው የመጣው ዘገባ ገልጿል። ቁጥራቸው ከፍተኛ የሆነና የሲቪል ልብስ የለበሱ የወያኔ የደህንነት ተቀጣሪዎች አስተናባሪ የሚል ባጅ ደረታቸው ላይ ለጥፈው ታቦቱን አጅቦ ወደ መንበሩ ለማስገባት ከሚንቀሳቀሰው ሕዝበ
ጥር 15 ቀን 2008 ዓ.ም
dollar
ክርስትያን ጋር በመቀላቀል ሲያስፈራሩ የነበሩ መሆናቸውን ለማወቅ ተችሏል። በአዲስ አበባ እና በአካባቢዎ ባሉ አንዳንድ ቦታዎች ተቃውሞ የሚያሰሙ ወጣቶች የተደበደቡና ተይዘው የታሰሩ መሆናቸው የታወቀ ሲሆን በተለያዩ ከተሞችም የጥምቀት በዓሉን አስታኮ በወያኔ አገዛዝ ላይ ተቃውሞ ሲሰማ መዋሉ ተነግሯል። በማግስቱ ጥር 12 ቀን 2008 ዓ/ም በአዲስ አበባ ተከብሮ በዋለው የቃና ዘገለሊላ በዓል ላይ የበዓሉ ታዳሚ በነበሩት ምዕመናንና በፖሊስ መካከል ግጭት ተነስቶ ለግዜው ቁጥራቸው ያልታወቁ ሰዎች በአካላቸው ላይ ጉዳት እንደደረሰባቸውና በፖሊስ ታፍነው የተወሰዱ መሆናቸውንም ከስፍራው የደረው ዘገባ ገልጿል። በተለምዶ ሾላ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ የሚገኘውን የየካ ቅዱስ ሚካኤል ታቦትን በማጀብ ወደ መንበሩ ለማስገባት ተሰባስበው የነበሩ ምዕመናን ባህላዊ ዘፈኖችና ጭፈራዎች እያደረጉ በሚጓዙበት ወቅት ለጭፈራ ማድመቂያ የያዙትን ዱላ በተለያዩ ስፍራዎች ቆሞ ይጠብቅ የነበረው የወያኔ የፖሊስ ኃይል ለመንጠቅ ሙከራ ሲያደረግ ከፍተኛ ግብግብ መከሰቱና ዱላቸውን የተቀሙት ወጣቶች እንደጀመራችሁ ጨርሱን በማለት ፖሊሶችን ማጥቃት በመጀመራቸው ግጭት ተፈጥሮ በርካታዎች የመፈንከት አደጋ እንደደረሰባቸውና አንዳንዶቹ ሲሮጡ የእግር ወለምታ አጋጥሟቸው ጉዳት እንደደረሰባችው ተያይዞ የመጣው ዜና ይገልጻል። ብዙዎች ታስረው በመኪና ተጭነው ወደ አልታወቀ ቦታ የተወሰዱ ሲሆን ከፖሊስ አባላት መካከልም ጉዳት የደረሰባችው እንደነበሩ ለማወቅ ተችሏል።
ከቅርብ ጊዜ ወዲህ አሳሳቢነቱ እየጨመረ የሄደው ሊምፎማ በመባል የሚታወቀው በሰውነት ውስጥ የሚገኙ የሊምፍ አካላትን የሚያጠቃና የደም መበከልንና መመረዝን የሚያስከትለው በሽታ አርሶ አደር ገበሬዎችን በወረርሽኝ መልክ እያጠቃ መሆኑን ከሀኪሞችና በጤና ላይ ምርምር ከሚያካሄዱ ወገኖች መረዳት ተችሏል፡፡ ከጥቁር አንበሳና ከቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታሎች ከሀገሪቱ የተለያዩ አካባዎች ለህክምና የሚመጡ አብዛኛዎቹ ገበሬዎች ሊምፎማ በተባው በሽታ የተጠቁና የበርካቶቹም ሁኔታ ወደ የደም ነቀርሳነት ያደገ መሆኑን መገንዘብ ተችሏል፡፡ ይህ በሽታ ሊከሰት የሚቸው በዘር፣ ከቀዶ ህክምና በኋላ እንደ ጡት ነቀርሳ የመሰለው፣ ጡቱ በቀዶ ህክምና ከተወገደ በኋላ የተለመደ ሲሆን በአረም ማጥፊያ አሲድም ሊከሰት እንደሚችል ይታወቃል፡፡ እንዲህ ያለውን በሽታ ሊያስከትሉ የሚችሉ የአረም ማጥፊያ አሲዶችን ከይዘታቸው መለየትና እንዳይገቡ እግድ ማውጣት ሲገባ ወደ አገር ውስጥ በወያኔ የንግድ ድርጅቶች አማካይነት እንዲገቡ መደረጋቸውና ገበሬው በግዴታ እንዲገዛና እንዲጠቀም መደረጉ ለዚህ ለገዳዩ ሊምፎማ በሽታ እንዳጋለጣቸው ማወቅ ተችሏል፡፡ ይህ ደግሞ ለተቃውሞ የወጡ ዜጎችን ከመረሸን በላይም የከፋ መሆኑን ከፍተኛ የህክምና ባለሙያዎች በመቆጨት ያስረዳሉ፡፡
ከገሙ ላይቀር ብስብስ ነው እንዲሉ ወያኔን እንደ ጋማ ከብት እያገለገለ ያለው ኃይለማርያም ጥር 1 ቀን 2008 ዓ.ም. ከመንግስት ተብየው ካዝና ከአንድ ሚሊዮን ብር በላይ በማውጣት ልጁ ሀናን በቤተ መንግስት መዳሩ ታወቀ፡፡ ይህን ወጪ የሰርጉ እድምተኛ የነበረው የሳዑዲው ደላላ አላሙዲ ወጪውን ሙሉውን የሸፈነ መሆኑን ከቅርብ ምንጮች ተረድተናል፡፡ አስቀድሞ ከወያኔው ገንዘብ ሚንስትር የወጣውን ገንዘብ የወያኔ ቁንጮዎች ለመቀራመት እንዲያመቻቸው ወደ “መለስ ፋውዴሽን” የዘረፋ ቋት እንደሚገባ መወሰኑ ታውቋል፡፡ ይህ ሁኔታ በ1997 ዓ.ም. ሟቹ መለስ ዜናዊ የጋጠ ወጥ ልጁ የሰመሀልን 12ኛ ክፍል ማጠናቀቅ አስመልክቶ በሸራተን ሆቴል የነበረውን የውስኪ ግብዣ ያስታውሳል፡፡ የመለስ ልጅንም ወጪ የሸፈነው አላሙዲ መሆኑ በወቅቱ ይነገር እንደነበር ማስታወሱ ተገቢ ነው፡፡ ዘረኛ አምባ-ገነኖች በመጠሪያ ስማቸው ቢለያዩ እንጂ በምግባራቸው ያው እንድ ናቸው።

File Photo
File Photo
 በወያኔ መገናኛ ብዙሀን እስከ ዛሬ ድርቁን የዝናብ እጥረት፣ እርሀቡን የምግብ እጥረት በማለት በሕዝብ ስቃይና ሞት ላይ ለፖለቲካ ትርፍ ብቻ በማሰብ የቃላት ጨዋታ እያደረገ መሆኑ ይታወቃል፡፡ እስካሁን ባለው መረጃ ከአምስት መቶ ሺ በላይ የተለያዩ ከብቶች በድርቁ ምክንያት እረግፈዋል፡፡ ህፃናት እርሀቡና ጥሙ ጠንቶባቸው ዋይ ዋይ እያሉ እንደዋዛ፣ እንደ ቅጠል እየረገፉ ነው፡፡ ወያኔ ነጋ ጠባ እያሰላ ያለው ከርሀቡ የሚገኘውን ትርፍ ነው፡፡ ባሳለፍነው ሳምንት ከተለያዩ አገራት የተውጣጣ የህፃናት አድን ድርጅቶች ቡድን እርሀቡ ህፃናትን፣ ነፍሰጡርና የሚያጠቡ እናቶችን በከፍተኛ ሁኔታ እያጠቃ መሆኑን መገንዘብ ችለዋል፡፡ ህፃናትና ነፍሰጡር እናቶች በርሀቡና በጠኔው እየረገፉ ነው፡፡ የርሀቡን አስከፊነትን የታዘበው የህፃናት አድን ድርጅቶች ቡድን በመጨረሻ ያሰማው 1.4 ቢሊዮን ዶላር በአስቸኳይ ከለጋሽ አገራትና ከግብረ-ሰናይ ድርጅቶች ማግኘት ካልተቻለ የርሀቡ ግድያ ከመልቀም ወደ ማጨድ ሊሸጋገር እንደሚችል ስጋታቸውን ሰንዝረዋል፡፡ ከዚህ ከተጠየቀው የገንዘብ መጠን መገንዘብ የሚቻለው እርሀቡ እጅግ ዘግናኝና ከግምት በላይ እንደሆነ ነው፡፡ በርሀብ አለጋ እየተገረፉ ያሉትን ገበሬዎች የወያኔ የንግድ ድርጅቶች የማዳበሪያ እዳ ከርሀቡ የተረፉ ከብቶቻቸውን ሽጠው እንዲከፍሉ እያስገደዷቸውና እያንገላቷቸው መሆኑን አውቀናል፡፡ በአንዳንድ አካባቢዎች የማዳሪያ እዳ ያልከፈለ አባወራ እርዳታ እንዳይሰጠው መታገዱ ይታወቃል፡፡ በንጉሡ ዘመን ድርቅ ሰብሉን ክው አድርጎ አድቆት ያዘረዘረው እንኳ ከአፈር ተደባልቆ እየታየ ባለ እርስቶቹ ገበሬው የግድ እንዲገብር ያስገድዱት እንደነበር የሚታወስ ነው፡፡ ይህንን ግፍ ወያኔ ደገመው፡፡ እርሀቡ አድማሱንና መከራውን እያሰፋ ነው፡፡ ወያኔ ደግሞ ከረሀቡ የፖለቲካና የገንዘብ ትርፉ ለማካበት እየማሰነ ነው፡፡
በተያያዘ ዜና ካሪታስ ኢንተርናሽናል የተባለው የካቶሊክ የአርዳታ ሰጭ ድርጅት ባለስልጣኖችን በወቅቱ እርዳታ ካልተኘ በኢትዮጵያ በዚህ ዓመት መጨረሻ ላይ ከፍተኛ የሆነ እልቂት ሊከተል እንደሚችል አስጠንቅቀዋል። ድርቁ ባጠቃቸው አካባቢዎች ከ90 ከመቶ በላይ በመቀነሱ ምክንያት በብዙ ሚሊዮን የሚቆጠር ሕዝብ በድርቅና ረሃብ እየተጠቃ መሆኑን ባለስልጣኖቹ ገልጸው ካሁኑ ጀምሮ በእርዳታው ላይ መረባረብ ካልተቻለ የዛሬ ሰላሳ አመት ተፈጥሮ የነበረው ዓይነት የእልቂት ሁኔታ ሊደገም እንደሚችል አስጠንቅቀዋል።
በሌላ በኩል ለእርዳታ የመጣውን እህል በተለያየ መንገድ በመዝረፍ ላይ ያሉት የወያኔ ባለስልጣኖች ሕዝቡን እያስመረሩት መሆኑ እየተስተዋለ ነው። በዚህ ሳምንት ባገኘነው ዜና መሰረት በመቂና በሞጆ ከተሞች መካከል በሚገኝ የህብረት ስራ ማህበር መጋዘን ውስጥ ተከማችቶ የነበረ ስንዴ ጨለማን ተገን በማድረግ አስራ አምስት በሚሆኑ በበቅሎ በሚጎተቱ ጋሪዎች ተጭኖ ወደ ጥቁር ገበያ ለሽያጭ ሲወጣ የተመለከቱ መሆናቸውን በአካባቢው የነበሩ የአይን እማኞች የገለጹ ሲሆን የስንዴው ብዛት እስከ ሁለት ሺህ ኩንታል ሊጠጋ እንደሚችል ተናገረዋል። ድርቅና ረሃብ ያጠቃቸው ወገኖች እርዳታ በማጣታችው ወደ አዲስ አበባ እየፈለሱ መሆናችውም እየታየ ነው። ሰሞኑኑ ዘጋቢያችን በመርካቶ ራጉኤል ቤተክርስትያን አካባቢ ያነጋገራቸው ወገኖች ከትግራይና ከወሎ ቦረና የመጡ መሆናቸውን የገለጸሉት ሲሆን የእርዳታ ስንዴ እንሰጣችኋለን ከሚል ተስፋ በስተቀር የተሰፈረልን እህል ባለመኖሩ ልጆቻችን ሲሞቱ ከማየታችን በፊት በራችንን ዘግተን መምጣቱን መርጠናል ብለውታል።
 •   ወያኔ በማን አለብኝነት የደነገገውን የአዲስ አበባን የቆዳ ስፋት እሰከ አንድ መቶ ሃያ ኪሎ ሜትር ድረስ ለመለጠጥ መደንገጉን በመቃወም በተለያዩ የሀገሪቱ አካባቢዎችና ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ያለ ማቋረጥ በተካሄዱ አመጾች ወያኔ ለይስሙላ ድንጋጌው መነሳቱን ቢለፍፍም የተጀመረው አመጽን ሊገታው እንዳልቻለ የታወቀ ነው፡፡ ወያኔ በርካታ ህጻናትን፣ ወጣቶችን፣ ገበሬዎችን፣ ሴቶችን ገድሎ ሲያበቃ የማስተር ፕላኑ መሰረዙን ማውራቱ ለሕዝብ ያለውን ንቀት ሚያሳይ መሆኑን የፖለቲካ ተንታኞች ያስረዳሉ፡፡ ወደ አምስት ሺ የሚጠጉ ሰዎች በየእስር ቤቶች በግፍ እየማቀቁ ባለበት የማስተር ፕላኑ መሰረዝ ከፖለቲካ ቧልትነት አይዘልም የሚል አስተያየት እየተሰማ ነው፡፡ አሁን እየተካሄደ ያለው እንቅስቃሴ ወያኔ እራሱን እንጂ ሕዝብን አያታልልም የሚል መንፈስ የተላበሰ መሆኑን መገንዘብ ችለናል፡ ፡ የማስተር ፕላን መሰረዝ በግብር መገለጽ ይገባዋል የሚሉ ወገኖች እንደሚሉት የንፁሀንን ደም ያፈሰሱ የአጋዚ ጦር አባላት ለፍርድ ሲቀርቡና ቤተሰቦቻቸው ለተገደሉባቸው ቤተሰቦች ተገቢ የህይወት ካሣ ሲከፈል፣ የታሰሩት በአጠቃላይ ሲፈቱና ተገቢ ካሣ ሲከፈላቸው መሆኑን አበክረው ያስረዳሉ፡፡ ለዚህ ነው ሰሞኑን በተለያዩ የሀገሪቱ አካባቢዎች ሕዝባዊ አመጹ እየቀጠለ ያለው፡፡
 •   በዚህ በዘረኛው ወያኔ ዘመን አብዛኛው ሥራ የሚከናወነው ጥናት ላይ ተመርኩዞ ሳይሆን እንዲሁ በደፈናው ነው፡፡ አንዳንዶች በጥናት ላይ እንደተመሰረቱ የሚነገርላቸው ቢሆኑም ዝም ብለው አረጋ ሰራሽ በመሆናቸው ጥናቱን አካሄደ የሚባለው ክፍል እራሱ መጠናት እንዳለበት የሚናገሩ ጥቂቶች አይደሉም፡፡ ባለፈው ሳምንት ምንጩ ከዓለም የገንዘብ ድረጅት የተገኘ ብድር እንደሆነ የሚነገር የውጪ ምንዛሪ በመገኘቱ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በድንገት በፋብሪካ ሥራ ለተሰማሩ ድርጅቶች ምንዛሪ እንደሚሰጥ በማሳወቁ የግል ብንኮች ላይ ከፍተኛ ቀውስ እንደፈጠረ ለማወቅ ተችሏል፡፡ የባንክ ባለሙያዎች እንደሚሉት እንዲህ ዓይነቱ የግድየለሽነት አሰራር ከበስተጀርባው ተንኮል ያዘለ እንደሆነ ያስረዳሉ፡፡ የባንኮችን በነፃነት የመፎካከር ሁኔታን በእጅጉ ያውካል፡፡ ለምሳሌ ከአንድ የግል ባንክ ብቻ በአንድ ቀን 1.3 ቢሊዮን ብር እንዲወጣ መደረጉ ለግል ባንኮች ከፍተኛ ፈተና መሆኑን ባለሙዎቹ ያስረዳሉ፡፡ በአንድ ቀን ከተለያዩ ባንኮች ወጪ ተደርጎ ወደ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እንዲገባ የተደረገው ገንዘብ 4.5 ቢሊዮን ብር ሲሆን ይህን ያህል ገንዘብ በአንድ ጊዜ ማውጣት የባንኮቹን እንቅስቃሴ በከፍተኛ ሁኔታ እንዳወከው ተውቋል፡፡
ethiopia sudan Boarder
 •   ወያኔ በተደጋጋሚ ከሱዳን ጋር ምንም ዓይነት ድንበርን ለማካለል የተካሄደ ድርድር መኖሩን ቢክድም በሱዳን በኩል ግን በማስረጃ እየቀረበ መሆኑን መረዳት ተችሏል፡፡ ሱዳን ከኢትዮጵያ ጋር 725 ኪሎ ሜትር እርዝመት ያለው ድንበርተኛ መሆኗ ታወቃል፡፡ ወያኔና የአል በሺር መንግስት በሟቹ በመለስ ዜናዊ ትዕዛዝ ከሁለቱ አገራት የተውጣጣ ጉዳዩን የሚያጠና የቴክኒክ ቡድን ተመስርቶ አንደነበር የሱዳኑ ጋዜጣ “ሱዳን ትሪቡን” የተሰኘው ዘግቧል፡፡ ይህ የተጀመረው ጥናት እንዲቀጥል አል በሺር 2014 ዓ.ም. የወያኔ የይስሙላውን መሪ ኃይለ ማርያምን ማሳሰቡን አስታውሷል፡፡ ሱዳን ከኢትዮጵያ ይገባኛል የምትለው መሬት ሰቲት፣ አትባራ እና ባላሳም የተባሉ ወንዞች የሚፈሱበት 600 ሺ ሄክታር ስፋት
ያለው፣ እየታረሰ ያለ ለም መሬትን አንደሆነ ጋዜጣው አትቷል፡፡ ይህ ቦታም ለገደሀሪፍ አዋሳኝ የሆነ ሲሆን አል-ፋሻጋ በመባል የሚታወቅ እንደሆነም ሱዳን ትሪቡን ጠቁሟል፡፡ ይህ የተጠቀሰው ስፋት የአዲስ አበባን ስፋት ከአስር እጅ በላይ እንደሚያጥፍ የስነ-ምህዳር አዋቂዎች ያስረዳሉ፡፡ ወያኔ አገር አጥፊ ነው ሲባል አገርን ይሸጣል ማለት ነው፡
 •   “ድምጻችን ያሰማ” የሚሉ ሕዝበ ሙስሊሙ በወያኔ ላይ በአንድነት እንዲነሳ የሚቀሰቅሱ ጽሑፎችን በትነዋል፣ የታሰሩትን የሙስሊም መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ አባላትን ለማስፈታት ተንቀሳቅሰዋል የተባሉ 16 የእስልምና እምነት ተከታዮች ተፈረደባቸው፡፡ ማክሰኞ ጥር 10 ቀን 2008 ዓ.ም. የወያኔ ከፍተኛ ፍርድ ቤት 14ኛ ወንወጀል ችሎት በተከሳሾቹ ላይ እጃቸው ከተያዘበት አንስቶ የሚታሰብ 7 አመት ጽኑ እስራት ፈረደባቸው፡፡ ተከሳሾቹ 15 ወንዶችና አንዲት ሴት ሲሆኑ እነሱም ኤልያስ ከድር፣ ሙባረክ ከድር፣ ቶፊቅ መሐመድ፣ ፌይሰል አርጋው፣ አብዱልመጂድ አብዱልከሪም፣ እስማኤል ሙስጠፋ፣ ሬድዋን አብደላ፣ አንዋር ሱልጣን፣ አብዱላዚዝ ፈቱዲን፣ ጃፋር ደጋ፣ ፋሩቅ ሰይድ፣ መሪም ሀያት፣ መሐመድ አሊ፣ መሐመድ አይለየን፣ አክበር ስልጣን እና ሙአዝ ሙደሲር ናቸው፡፡ የወያኔው አቃቤ ህግ ያተተባቸው በአዲስ አበባና በወልቂጤ፣ የታሰሩትን የሙስሊሙ ህብተሰብ ችግሮችን ለመፍታት የተቋቋመው ኮሚቴ አባላት፣ በወያኔ በመታሰራቸው እነሱን ተክቶ ለመሥራት በህቡዕ በመንቀሳቀሳቸው እንደሆነና በየመስጂዱ ውስጥ ውስጡን ሕዝበ ሙስሊሙ በወያኔ ላይ እንዲያምጽ በመቀስቀሳቸው በመሆኑን አትቷል፡፡ ወያኔ በየጊዜው ሙስሊሞችን ያስራል ትግላቸው ግን እንደቀጠለ ነው፡፡ ይህ የሙስሊም ኢትዮጵያውያንን ትግል ሕዝበ ክርስቲያኑም እንደሚደግፈው የታወቀ ነው፡፡
muslim addis
 •   ወያኔ በአሜሪካ የሚኖሩ ተቃዋሚዎችን አድኖ ወደ ሀገር ቤት የአሜሪካ መንግስት እንዲልክለት እረቂቅ ሰነድ አዘጋጅቶ ማጠናቀቁን ከውስጥ አወቆች መረዳት ተችሏል፡፡ ከዚህ ቀደም በሌሉበት እስራት የፈረደባቸውና በ”ሽብርተኝነት” የወነጀላቸውን ሁሉ አሜሪካ እያሰረች እንድትልክለት መሆኑን ከሰነዱ መረዳት እንደሚቻል እነዚሁ ምንጮች ያስረዳሉ፡፡ ይህ ድርጊት አወቅሽ አወቅሽ ሲሏት መጽሐፍ አጠበች እንደሚባለው ያለ መሆኑን የሚገልጹ የዓለም አቀፍ ህግ አዋቂዎች ቁጥር ቀላል አይደለም፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘ ከወያኔ የደህንነት ምንጮች የተገኘው ጉዳዩ የሚያነጣጥረው በተለይ በኢሕአፓ አባላት ላይ እንደሆነና በተለያዩ ጊዜያት የተቃውሞ ሰልፎችንና ስብሰባዎችን በመምራትና በመስተባበር የሚታወቁትንም ያካትታል፡፡ በተለይ በአሜሪካ በወያኔ ኤምባሲ የወያኔን ባንዲራ አውርደው የኢትዮጵያ ባንዲራን የሰቀሉትን፣ በስብሀት ነጋና በሬድዋን ላይ የተቃውሞ ድምጽ ያሰሙት ተላልፈው እንዲሰጧቸው ከሚጠየቁት በመጀመሪያው እረድፍ እንደሚገኙ ለማወቅ ተችሏል፡፡
 •   ደርግን በመዋጮ ብዛት ይኮንነው የነበረው ወያኔ መዋጮ በግዳጅ የሠራተኛውን ጉሮሮ እያነቀ በመውሰድ ተወዳዳሪ አልተገኘለትም፡፡ የዓባይ ግድብ መዋጮ አላቆም በማለቱ ለኢትዮጵያ ሕዝብ በመርገምነቱ እንጂ በሲሳይነቱ መታየት አቁሟል፡፡ ከዚህ ከጥር ወር ጀምሮ የሚቀቆረጠው የጤና
መድንም እዬዬ እያሰኘ ነው፡፡ ህክምና ወደ ሸቀጥነት በወረደበት አገር በገንዘብ ያልተገኘ ህክምና በመድንማ ዘበት እንደሚሆን የተፈታ ህልም ነው፡፡ አብዛኛው ሰው እንደሚለው ወያኔ በመድን ስምም የሚሰበስበው ለዛው ለመከረኛው ዓባይ ገድብ እንደሆነ ነው፡፡ የዛሬ አስር ወር ግድም ወያኔ ምርጫ ተብዬውን አስታኮ የደሞዝ ጭማሪ እንደሚያደር ቀለምዶ ሲያበቃ እንኳን ጭማሪው ወሬውም የለም፡፡ ሠራተኛው እንዳይተፍስ በስብሰባ ስም አበል እየፈለ አፉን ማስያዝ የሚል ዘመቻ ተይዟል፡፡ የወያኔ አባላትም በተጣለባቸው የግዴታ የአባልነት መዋጮ እየተማረሩ መሆናቸው ታውቋል፡፡ ከዚህ ቀደም በፈቃደኝነት ከ50 እስከ መቶ ብር ይከፍሉ የነበረው ቀርቶ በደሞዝ መክፈያው ላይ በመትከል አራት ከመቶ ከደሞዛቸው እንዲቆረጥ በመወሰኑ ቅሬታቸውን በማልጎምጎም እየገለጹ መሆኑንም ተረድተናል፡፡ የውሀ፣ የመብራት ታሪፍ በቅርቡ ጨምሯል፡፡ በተመሳሳይ መልኩም የዕለት ተዕለት የምግብ ሸቀጦች ዋጋ እየናረ ይገኛል፡፡
 ባለፈው ሳምንት የአውሮፓው ህብረት ምክር ቤት (ፓርላማ) ሰሞኑን በኢትዮጵያ እየተካሄደ ያለውን የሕዝብ አመጽ አንተርሶ ጠንካራ ውሳኔዎች ማስተላለፉ ተገለጿል። የአውሮፓው ሕብረት ምክር ቤት ባለፉት ሁለት ወራት የአዲስ አበባ ማስተር ፕላንን በመቃወም ተካሄዱትን ሕዝባዊ አመጾች ለመግታት ወታደሮች ከ140 ሰዎች በላይ መግደላቸውን፤ የአዲስ አበባ መስፋፋት ብዙ አርሶ አደሮችን ያፈናቀለ መሆኑን፣ በአካባቢው የሰብአዊ መብት ጥሰት መኖሩን፤ የወያኔ የጸጥታ ኃይሎች አሸባሪዎች ናቸው በሚል በርካታ ሰልፈኞችን ማሰሩን፤ የፖለቲካ ድርጅቶች መሪዎችን ጋዜጠኞችንና ጦማሪያንና ይዞ እያሰቃየ መሆኑና አንዳንዶቹንም በሽብረተኞች ክስ በማፈረድ በእስር ቤት ማሰቃየቱንና በአንዳንድ አካባቢዎች የሚያካሄደው ጦርነትና ጭፍጨፋ አስከፊ መሆኑን የተረዳ መሆኑን ገልጿል። በተጨማሪ የወያኔ አገዛዝ ባለፈው አመት ግንቦት ወር ላይ ያካሄደው ምርጫ በአፈናና በማስፈራራት የተካሄደ መሆኑና አርሶ አደሮች ለም ከሆነው መሬታቸው ላይ ተነቅለው መሬታቸው ለባዕዳን መሰጠቱን ምክር ቤቱ መረጃ የደረሰው መሆኑን በመጠቆም ጉዳዩ ያሳሰበው መሆኑ አብራርቷል። ወያኔ በሕዝብ ላይ ከፍተኛ የሆነ የሰብአዊ መብት ረገጣና አፈና እያካሄደ በየአመቱ 3 ቢሊዮን ዶላር የሚገመት ገንዘብ ማግኘቱ አግባብ አለመሆኑን ምክር ቤቱ ገልጾ በርካታ ውሳኔዎችን አስተላልፏል።፡ በውሳኔውም ኦሮሚኛ ተናጋሪዎች በሚኖሩበትና በሌሎች የኢትዮጵያ ግዛቶች የወያኔ ወታደሮች በዜጎች ላይ ያካሄዱትን ገደብ የለሽ ግድያ፤ የሰብአዊ መብት ረገጣ፤ ህገ ወጥ እስራትንና ሰቆቃዊ ድርጊቶች፤ የመናገርና የመጻፍ መብት መታገዳቸውን እንዲሁም ወንጀለኞች ለፍርድ ሳይቀርቡ በነጻ መለቀቃቸውን አውግዟል። በመንግስት የጸጥታ ወታደሮች እየተደረጉ ያሉት የአፍናና የግድያ ተግባሮች ባስቸኳይ እንዲቆሙና መብታቸውን በመጠቀም ድምጻቸውን በማሰማታቸው ብቻ የታሰሩ ተማሪዎች፤ አርሶ አደሮች የፖለቲካ ተቃዋሚዎች፣ ምሁራን ጋዜጠኞችና ጦማራውያን በሙሉ ባስቸኳይ እንዲፈቱ ጠይቋል። በተደረጉት ግድያዎች ላይ ነጻና ገለልተኛ በሆነ መንገድ ምርመራና ማጣራት እንዲካሄድና ጥፋተኞች ለፍርድ እንዲቀርቡ ጥሪ አስተላልፏል። ወያኔ የዓለም አቀፉንና የአፍሪካ ህብረትን የሰብአዊ መብት ቻርተርና ድንጋጌን ማክበር ያለበት መሆኑን ገልጾ በሚዲያ ላይ እያካሄደ ያለውን የሞገድ አፈናና እንዲያነሳና ነጻ የሆኑ ሚዲያዎች ስራቸውን በነጻ የሚሰሩበት ሁኔታ እንዲፈጠር ጠይቋል። አልአግባብ እየተካሄደ ያለው የሰፈራ
ፕሮግራም ምክር ቤቱን ያሳሰበው መሆኑን ገልጾ በአካባቢዎቹ የሚደረጉት የልማት ስራዎች ሕዝብ ጋር ተመካክሮና ተስማምቶ መሆን እንደሚገባው አሳስቧል። የአውሮፓ አገሮች ለልማት ስራዎች ለወያኔ የሚሰጡት እርዳታና ብድር ከአገሪቱ የሰብአዊ መብት ሁኔታ ጋር መመጣጠን ያለበት መሆኑን ገልጾ የአውሮፓው ኅባረትና አባል አገሮች በንጹሐን ዜጎች ላይ እየተወሰደ ያለውን ርምጃ ኮንነው ድርጊቱን ለማስቆም አስፈላጊውን ተጽእኖ እንዲያደርጉ ጥሪ አድርገዋል።
 •   የናይጄሪያ የማስታወቂያ ሚኒስትር ትናንት ሰኞ ጥር 9 ቀን 2008 ዓም ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ በሰባት ዓመት ጊዜ ውስጥ ብቻ የናይጄሪያ አገረ ገዠዎች፤ ሚንስትሮች የንግድ ተቋም ባለቤቶች ፤ የባንክ እና የመንግስት ባለሥልጣኖች 9 ቢሊዮን ዶላር የአገሪቷን ገንዘብ አለአግባብ የዘረፉ መሆናቸውን ገልጸዋል። የተሰረቀው ገንዘብ 1.35 ትሪሊዮን የናይጄሪያ ናይራ መሆኑን ሚኒስትሩ ገልጸው ይህም 36 ሆስፒታሎች ለመስራት ወይም 4000 ተማሪዎችን እስከዩነቨርስቲ ድረስ ለማስተማር የሚያስችል ገንዘብ እንደነበር ገልጸዋል። ሁኔታው አሳሳቢ መሆኑን ገልጸው ባሁኑ ወቅት አስፈላጊው ርምጃ መወሰድ አለበት ብለዋል። ሚኒስትሩ የተዘረፈውን ገንዘብ ዝርዝር መረጃም አቅርበዋል። ገንዘቡ ተዘርፏል የተባለው እንደ አውሮፓ አቆጣጠር ከ2006 እስከ 2013 በአብዛኛው የቀድሞ ፕሬዚዳንት ጉድላክ ጆናታን በስልጣን ላይ በነበሩበት ወቅት ሲሆን የቀድሞ የጸጥታ አማካሪ የነበሩት ሚስተር ዳሱኪ 2 ቢሊዮን ዶላር ዘርፈዋል ተብለው መወንጀላቸው ይታወሳል። በአሁኑ ወቅት የናይጄሪያ ተቃዋሚ ፓርቲ የሆነው ፒፕልስ ዴሞክራቲ ፓርቲ የአሁኑ እርምጃ የፓርቲውን አባላት ለማጥቃት ሆን ተብሎ በስልጣን ላይ ባለው ኦል ፕሮግሬሲቭ ኮንግሬስ በተባለው ፓርቲ የተጠነሰሰ ሴራ የሚል ውንጀላ ሲያቀርብ ባለስልጣኖቹ ደግሞ የአገሪቱን ገንዘብ የሰረቀ የማንኛውም ፓርቲ አባል ለፍርድ ይቀርባል ብለዋል።
 •   በደቡብ ሱዳን ከሁለቱም ተጻራሪ ወገኖች በተውጣጡ ወኪሎች እንዲመሰረት ስምምነት ተደርሶበት የነበረው ጊዜያዊ የአንድነት መንግስት በተግባር እንዲውል የተሰጠውን ቀነ ቀጠሮ ያሳለፈ መሆኑ ተገለጸ። የአንድነት መንግስቱ እንዳይመሰረት እንቅፋት ከሆኑት አቢይ ምክንያቶች ውስጥ አንዱ የስልቫኬር መንግስት ከስምምነት ውጭ የአካባቢ አስተዳደሮችን ከ10 ወደ 28 ከፍ ማደረጉንና 28 አስተዳዳሪዎች መሾሙን በሪክ ማቻር የሚመራው የአማጽያን ኃይል በመቃወሙና ባለመቀበሉ መሆኑ ታውቋል። በዕቅዱ መሰረት ከሁለቱም ተጻራሪ ኃይሎች የተውጣጣ የአንድነት መንግስት ከጥር 13 ቀን 2008 ዓም በፊት መመስረት ነበረበት። ለስምምነቱ መፍረስ ሁለቱም ወገኖች እርስ በርሳቸው የተወነጃጀሉ ሲሆን የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ሰሞኑን ባወጣው ዘገባ ሁለቱም ተጻራሪ ኃይሎች ጦርነቱን በማስፋፋት እንዲሁም በጦር ሜዳዎች የጅምላ ርሸና በማካሄድ፤ የያዟቸውን ዜጎች ዱካ በማጥፋት፤ በቡድን ሴቶችን በመድፈር፤ ለወሲብ አገልግሎት ሴቶች አግቶ በመያዝ ፤ አስገድዶ ጽንስን በማስወረድና የመሳሰሉ ወንጀሎችን በመፈጸም በኩል ሁለቱም ወገኖች ተጠያቂዎች ናቸው ብሏል።
 ባለፈው ሳምንት በምዕራብ ፓኪስታን በቻርሳዳ ከተማ በሚገኘው ባቻ ከሃን ዩንቨርስቲ ላይ ታጣቂዎች ባካሄዱት የቦምብ ጥቃት 19 ሰዎች መገደላቸውና ከ50 በላይ መቁሰላችወን የፓኪስታን ፖሊስ ገልጿል። አጥቂዎቹ ከጠዋቱ 3 ሰዓት ተኩል ሲሆን የዩኒቨርስቲውን የጀርባ አጥር በመዝለል ጥቃቱን መሳሪያ በመተኮስና ቦምብ በማፈንዳት መፈጸማቸው የተገለጸ ሲሆን ከዩኒቨርስቲው የጸጥታ አባላት ጋር በተደረገ የተኩስ ልውውጥ ተደርጓል። አንድ የታሊባን ወታደራዊ ኮማንደር ጥቃቱ የተወሰደው በታሊባን መሆኑን ጠቅሶ እርምጃውም በቅርቡ የፓኪስታን ወትደራዊ ኃይል ለወሰደው ጥቃት የአጸፋ እርምጃ ነው ብሏል። በሌላ በኩል የታሊባን ቃል አቀባይ የሆነው ለቢቢሲ የዜና ወኪል በሰጠው ቃል ድርጊቱ ከሙስሊም ሃይማኖት ትእዛዝ ውጭ የተደረገ የሚወገዝ ድርጊት በማለት ታሊባን እንዳልፈጸመው አስተባብሏል።

Sunday, January 24, 2016

በሕወሓቱ ድረገጽ ወጥተው ስለግንቦት 7 ከተናገሩት መካከል ” በንቅናቄው ጦር ካምፕ ሴት በማስገባት በዲሲፕሊን የተባረሩ ናቸው”

ህወሓት/ኢህአዴግ ላንድ አራተኛ ምእተ ዓመት በኢትዮጵያ ህዝብ ላይ ተደጋጋሚ የጅምላና የተናጠል ፋሽስታዊ ጭፍጨፋዎች እያካሄደ፣እያሰረ፣ እየደበደበ፣ የህዝባችንን ሰብኣዊ መብትና ነፃነት ረግጦ፤ በቋንቋ እየከፋፈለ፣ በሃይማኖት ጣልቃ እየገባ፣ የህዝብ ሃብት እየዘረፈና በሙስና ተዘፍቆ ህዝባችንን አፍኖ በመግዛት ላይ ይገኛል፡፡
abebe Gelaw
“ህወሓት/ኢህአዴግ” የሚል መጠሪያ ስንጠቀም፣ ከህወሓት በስተቀር ሌሎቹ የኢህአዴግ አባል ድርጅቶች ከህወሓት ነፃ የሆነ ድርጅታዊ ህልውና ኖሯቸው እንደማያውቅ፤ ህወሓት ሌሎቹን ድርጅቶች የኢትዮጵያ ህዝብን ተቆጣጥሮ ለመግዛትና ለመበዝበዝ የጠፈጠፋቸው ድርጅቶች መሆናቸውን ለመግለፅ አስፈላጊ ስለሆነ ነው፡፡
ይህ የኢህአዴግ ኣባል ድርጅቶች በወታደራዊ የሃይል ልዩነት ላይ የተገነባ የይምሰል ጥምረት በስልጣን ክፍፍል ላይ የህወሓት የበላይነት አረጋግጧል፡፡ ህወሓት በሰራዊት፣ በደህንነት፣ በውጭ ጉዳይ፣ በኦርቶዶክስ ሃይማኖት የበላይነት ስልጣን፣ በመገናኛ ብዙሃን፣ በኢኮኖሚና በቻይና የኢትዮጵያ የአምባሳደርነት ቦታ ሳይቀር ያለ ማቋረጥ መቆጣጠሩ፣ ህወሓትን ባለ ርስት እንዲመስል አድርጎታል፡፡
በኢትዮጵያ ህዝብ ላይ ለሚፈፀሙ ግፎች የህወሓት ባለስልጣኖች እንደ ስልጣናቸው ከፍተኛ ተጠያቂነት አለባቸው፡፡ ይሁን እንጂ የሌሎቹ የኢህአዴግ ኣባል ድርጅቶች ባለስልጣኖችም ከመጠየቅ ሊድኑ አይችሉም፡፡
ህወሓት ባንድ በኩል የደርግ ኣገዛዝን ለማስወገድ ባስር ሺዎች የሚቆጠሩ የትግራይ ወጣቶች
ህይወታቸውን የሰዉበት ድርጅት ነው፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ ህወሓት ሲመሰረት ጀምሮ የተቆጣጠሩት ግለሰቦች ፀረ ኢትዮጵያ ስለሆኑ ሌሎች አባላትን አግልለው የድርጅቱ ዓላማ የትግራይ ሬፐብሊክ መመስረት እንደሆነ በማኒፌስቶ ገልፀው ነበር፡፡ እነዚህ ግለ ሰቦች የመገንጠል ዓላማቸው ለመተው ቢገደዱም በኢትዮጵያ ደረጃ ስልጣን ከያዙ በሁዋላም በሉአላዊነትና በኢትዮጵያ ህዝብ አንድነት ጥያቄዎች ላይ የማይታመኑ መሆናቸውን ደጋግመው አሳይተዋል፡፡ በዚህ መሰረት በኢትዮጵያ ታሪክ እንደ ህወሓት ብሄራዊ ጥቅምን አሳልፎ የሰጠ አገዛዝ የለም። አሁንም ህወሓት/ኢህአዴግ ግልፅነት በጎደለው አሰራር የኢትዮጵያን መሬት ለሱዳን የመስጠቱ አደጋ ስላለ የኢትዮጵያ ህዝብ ለያውቀውና ሊቃወመው ይገባል፡፡
እነዚህ ግለ ሰቦች በትጥቅ ትግሉ ጊዜ በትግራይ ውስጥ ከጦርነት ውጭ ደርግ ከገደላቸው በቁጥር የሚበዙ ሰላማዊና ራሳቸውን ሊከላከሉ የማይችሉ ዜጎችን አስረሽነዋል፡፡ ስለዚህም ነፍሰ ገዳዮቹ ከ40 ዓመት በፊት ጀምረው የንፁሃን ዜጎችን ህይወት በመቅጨት ላይ ይገኛሉ፡፡ ይህ ግፍ በይፋ እንዳይገለፅ ቢታፈንም የትግራይ ህዝብ በየቤተሰብና በየጎረቤት ደረጃ ያውቀዋል፡፡ ስለዚህ የህወሓት ባለስልጣኖች በትግራይ ውስጥ የጀመሯቸውና የለመዷቸው የግድያና አፈና ድርጊቶች ለሁሉም የኢትዮጵያ ህዝብ አዳርሰዋል፤
ምክንያቱም ወንጀለኞቹ በወቅቱ ከስልጣን አልተወገዱም፡፡
ባለፈው ህዳር በኦሮሞ ተማሪዎች የተጀመረውና የህዝብ ድጋፍ ኣግኝቶ የተቀጣጠለው ህዝባዊ እንቅስቃሴ ለመግታትና ለመደፍጠጥ የህወሓት/ኢህአዴግ መሪዎች ብዙ የኦሮሞ ተወላጆችን ገድለዋል፣ በብዙ ሺ የሚቆጠሩ አስረዋል። በኦሮሞ ህዝባችን ላይ የሚፈጸመው ግፍ በእጅጉ አሳዝኖናል፣ አስቆጥቶናል።
እንዲሁም በጎንደር አካባቢ የሚፈፀመው ወንጀል በእጅጉ አሳዝኖናል፣ አስቆጥቶናል።
የኦሮሞ ተማሪዎችና አርሶ አደሮች ሰላማዊ ተቃውሞ በማሰተር ፕላኑ ምክንያት ቢቀጣጠልም በ25
ዓመት የህወሓት/ኢህአዴግ ጭቆና ከተጠራቀመ ብሶት ጋር የተያያዘ ነው፡፡ ጭፍጨፋውም
የህወሓት/ኢህአዴግ አገዛዝ ሁሉ ጊዜ ለሰላማዊ ተቃውሞ የሚሰጠው መልስ ነው፡፡
የህወሓት/ኢህአዴግ መሪዎች የሚፈጽሟቸው አረመኔያዊ የጅምላ ግድያዎች ከዚህ በፊትም በአዲስ አበባ በተደጋጋሚ በ1985፣ በ1993፣ በሰኔ በ1997፣ በጥቅምት 1998፣ በጋምቤላ በታህሳስ 1996 ወዘተ..
ተፈፅሟል፡፡ ስለዚህ እነዚህ ጭፍጨፋዎች የሚቆሙት አስጨፍጫፊዎቹ ወንጀለኞች ከስልጣን ሲወገዱ ብቻ ነው፡፡
በበኩላችን የነዚህ ወንጀለኞች አገዛዝን በሚመለከት ያሉን አቋሞች የሚከተሉት ናቸው፦
1. የህወሓት/ኢህአዴግ መሪዎች ማንንም ብሄር/ብሄረሰብ የማይወክሉ፣ ለይስሙላ የህዝብን ጥያቄ
አንግበው ብዙ ወጣቶችን አስገድለው ለሰልጣን የበቁ ተራ አጭበርባሪዎችና ወንበዴዎች ናቸው፤
2. ለነዚህ ወንጀለኞች አቤቱታ ማቅረብ (ግድያቸውን እንዲያቆሙ፣ ህገ መንግስታቸውን እንዲያከብሩ መጠየቅ ወዘተ)ፋይዳ የለውም፤ ወንጀል ያልፈፀሙ የኢህአዴግ አባላት ወንጀለኞቹን በይፋ በማጋለጥ የህዝብ ወገንነታቸውን ማሳየት አለባቸው፡፡
3. የህወሓት/ኢህአዴግ አገዛዝ የሚደመሰሰውና ዴሞክራሲያዊ ስርዓት የሚገነባው በተናጠል ሳይሆን መላው የኢትዮጵያ ህዝብ ኣብሮ ሲታገል ነው፤ በህዝብ መካከል መሰረታዊ ቅራኔና ጠላትነት የለም፤
4. በኢትዮጵያ ህዝብ ላይ ለሚፈጸመው ወንጀል ተጠያቂዎች በዋናነት የህወሓት መሪዎች ቢሆኑም ፣ ግብረ-አበሮቻቸውም (የኦህዴድ፣ ብአዴን፣ ደኢህዴግ መሪዎችም) ተጠያቂዎች ናቸው፡፡
በመጨረሻም ማስገንዘብ የምንፈልገው የትግራይ ህዝብ የህወሓት ሰለባ እንጂ ለህወሓት ወንጀል ተጠያቂ አለመሆኑን ነው። በዚህ አጋጣሚ ግን በዲያስፖራ የሚኖሩ ትግራዎት ከሌላው ኢትዮጵያዊ ወገናቸው ጋር አብረው ለዴሞክራሲና ለአገር አንድነት እንዲታገሉ ጥሪያችንን እናቀርባለን።
እኛም ኦሮሞች ነን፤ ከኦሮሞ ህዝባችን ጎን ቆመን ፋሽስታዊውን የህወሓት/ኢህአዴግ መንግስታዊ የሽብር ድርጊት እናወግዛለን፡፡ በቅርቡ ሰላማዊ ተቃውሞ ምክንያት የታሰሩ ኦሮሞዎችና ሁሉም የፖለቲካ እስረኞችን ካለ ምንም ቅድመ ሁኔታ ለመፍታትና የተገደሉ ዜጎች ቤተሰቦችን ለመካስ አሸባሪው አገዛዝ እንዲገደድ ለኢትዮጵያ ህዝብ እናሳስባለን፡፡
በኢትዮጵያ ህዝብ (በትግራይ ከ40 ዓመታት በላይ፣ በመላ ኢትዮጵያ ለ25 ዓመታት) የሚፈፀሙት ተዳጋጋሚ ጭፍጨፋዎች (serial massacres) የሚቆሙት አስጨፍጫፊዎቹ ወንጀለኞች ከስልጣን ሲወገዱ ብቻ ነው፡፡
ከትግራይ ተወላጆች ኢትዮጵያውያን የተሰጠ መግለጫ
አብራሃ በላይ
አረጋዊ በርሀ (ዶር)
በላይነሽ ተክለሃይማኖት
ገብረመድህን ኣርኣያ
ግደይ አሰፋ (ዶር)
ግርማይ ገዛኸኝ
ካሕሳይ በርሀ
ነጋሲ በየነ
ተስፋይ ኣፅብሃ

Saturday, January 23, 2016

ሕዝባዊው አመጽ ሲገሰግስ ፤ ዘረውኛው አገዛዝ ሲደመሰስ ! ፍኖተ ዴሞክራሲ የኢትዮጵያ አንድነት ድምጽ ሀተታ

 

ፍኖተ ዴሞክራሲ የኢትዮጵያ አንድነት ድምጽ ሀተታ
ሕዝባዊው አመጽ ሲገሰግስ ፤ ዘረውኛው አገዛዝ ሲደመሰስ 
አዕምሮ የሌለው ሕዝብ ሥርዓት የለውም ። የኃይል ምንጭ ሥርዓት እንጅ ፤ የሠራዊ ት ብዛት አይደለም ። ሥርዓት ከሌለው መንግሥት ይልቅ ፤ በህግ የምትኖር ትንሽ ከተማ ሞያ ትሰረላች ። 
ነግ አድራስ ገብረ ህይወት ባይከዳኝ ። 
የሀገራችን ወቅታዊው ሁኔታ ፤ የ1966 ቱን ወርሃ የካቲት ሁኔታ በብዙ መልኩ ያንፀባርቃል ። ያስታውሳል ። ያመለክታል ። ተመሳሳይ የደወል ድምፅም ያሰማል ። ይህ ድምጽ ፤ የወየኔን ግብዐ -ተመሬት መርዶ ሲናገር ፤ በአንፃሩ ደግሞ ፤ የኢትዮጵያን ብሥራተነፃነት ያውጃል ። 
ታሪክ ፤ በተለያየ ወቅትና ሁኔታ እራሱን ይደግማል ። እንዲሉ፤ የ1966ቱ ዓም የካቲት ሕዝባዊ አመፀ ፤ በወቅቱ የነበረውን ኋላ ቀር ሥርዓት እንደለወጠው ሁሉ ፤ የአሁኑም ሕዝባዊ አመፅ ፤ የወያኔን ዘረኛ አገዛዝ ፤ ወደ ግበዐ -ተመሬቱ እንደሚወስደው የታሪክ ሀቅ ነው ። ታሪክ የሚያመጣውን ሃቅ ደግሞ፤ ማንም ሊጠራጠር አይቻለውም ። አውቆ ካልተኛ በስተቀር 
በአንድ ትውልድ ዘመን የሚፈራረቁትን ታሪካዊ ኩነቶች ማነፃፀር ካለብን ፤ የስድሳ ስድስቱንና የአሁኑን የሀገራችንን ሁኔታ እያወዳደርን ማየት መቻል ይኖርብናል ።ይህ ተመክሯችን ደግሞ፤ ዕይታችንን በሀገራችን ሁኔታ ላይ እንድናተኩር ይረዳናል ። በመሆኑም፤ የባእዳንን ተመክሮ፤ እንደ ሸቀጥ ዕቃ (Imported Goods ) አግበስብሶ ለማምጣት አንገደድም ። አያስፈልገንምም 
የራሳችንን ተመክሮ በሚገባ ከተጠቀምንበት፤ ካወቅንበትና ከሰራንበት፤ ሞልቶ የተትረፈረፈ፤ ዕውቀትና የበለፀገ ልምድ፤ እናገኝበታለን ። ካለፈው ስህተትም እንማርበታለን ። ብልህ፤ ስህተቱን አይደግምም 
ከታሪክ የማይማሩ ፤ራሳቸውን እየረገሙ ይኖራሉ።፤ እንጅ፤ እኛስ የታሪክ ክስተት ካመጣው ስህተት እየተማርን ስህተታችን እያረምን ወቅታዊውን ሁኔታ በሚገባ ተጠቅመን ሀገራችንን ከጥፋት ማዳን የመጀመሪያው ተግባራችን ከሆነ ቆይቷል ። ያ ደግሞ የይፈፀማል ይህ ሊሆን የሚችለው ግን፤ ኢትዮጵያ እንደ ሀገር፤ ሕዝቧም እንደ አንድ ሀገር ሕዝብ አብረው መኖራቸውን ሲቀጥሉ ነው ። 
የሦስት ሺ ዓመት ታሪክ ያላት ሀገር መቅጠል ካለባት ፤ ከአድማስ ባሻገር ማስብን ይጠይቃል ። የፖለቲካ ሥልጣን ከመያዝ በላይ አርቆ ማስተዋልንም ግድ ይላል ። ሀገርን ሳያድኑ፤ ለፖለቲካ 
page1image17840
ሥልጣን መራኮት ፤ ተያይዞ መጥፋትን ያስከትላል ። ሁላችንም ተያይዘን እንደንጠፋ ደግሞ ፤ ጠላቶቻችን ሌት -ተቀን ተግተው ይሰራሉ ። 
1966 ዓም የካቲት ፤ ህዝባዊ አመፅ ፤ የዐፄ ኃይለ ሥላሴ መንግሥት ወደ እማይቀርለት ግበዐ ተመሬቱ እንዲገባ የተደረገው በሚከተሉት ሳይንሳዊ ምክንያቶች ነበር ። 
1መሠረታዊ
. 1. የፊዳሉ ሥርዓት እንደ ወትሮው እየጨቆነ መግዛት ስለ አልሆነልት ። 
2. የመጨቆኛ መሳሪያዎቹና መንግሥታዊ አውታሮቹ እየተፍረከረኩ መምጣታቸው ። 3. የገዥው መደብ ፤ ኃይሉ እየደከመ ፤ ክንዱ እየዛለ በመሄዱ ምክንያት ተስማምቶና 
ተባብሮ ሥርዓቱን ማቆየት ስላልቻለ ።
. 1. መልዐተሕዝቡ እንደቀድሞው እየተጨቆነ መገዛት ባለመፈለጉ ፤ አሻፈረኝ ብሎ በመነሳቱ፤ 
2. በገዥው መደብና በተገዥው ሕዝብ መካከል የነበረው ቅራኔ፤ እጅግ ሰልቶና ጎልቶ በመምጣቱ ። 
3. ሥር ዓቱን አቅፈው ደግፈው የነበሩት ፤ የመንግሥት አገልጋዮች ሁሉ፤ የሕዝቡ አመጽ ባስከተለው የኃይል ሚዛን መለወጥ ምክንያት፤ ሲያገለግሉት የነበረውን ሥርዓት ከድተው ሰልፋቸውን ከሕዝብ ጎን ማድረጋቸው ። 
2ወቅታዊ ነባራዊ ሁኔታዎች
ሀ 
ድርቅ ያስከተለው ረሃብ በሕዝብ ላይ ያስከተለው አሰቃቂ ዕልቂት ፤ ለበየቦታው ሲካሄዱ የነበሩት ጦርነቶች፤ 
የዓለምአቅፍ ሁኔታ ባስከተለው ምክንያት፤ የቤንዚን /ነዳጅ ዋጋ መጨመር ባመጠው የኑሮ ውድነት መክንያት ፤ በዜጎች ላይ ያሳደረው ሮሮና ስቃይ። በድሃው ላይ ያመጣው የመኖር ተስፋ ማጣት ፤ 
የተራማጅ ኃይሎች ለሕዝብ ወገንተኝነት ሲያደርጉት የነበረው ትግል ፤ ፈር እየያዘ መምጠቱ ፤ ዋና ዋና ምክንያቶች ነበሩ ። 
የእነኝህ ሁሉ ድምር ውጤት፤ ሕዝባዊ አመፁን፤ የማይበገር ኃይል ስለአደረገው፤ ኋላ-ቀር ሥርዓቱን ሊለውጠው ችሏል ።
ዛሬም እንደ ትላንቱ ፤ የሀገራችን ተጨባጭ ሁኔታዎች ፤ ተመሳሳይ ኩነቶችን በማንፀባረቅ ላይ ናቸው ።
ይህ ዘረኛ አገዛዝ ባስከተለው ጭቆና ምክንያት፦----በመላው ሀገሪቱ ክፍሎች ሕዝባዊ አመፆች በመካሄድ ላይ ናቸው ። 
 •   በአርሲ፤ በጎንደር፤ በሐረር፤ በጅማ ፤ በወለጋ፤ በናዝሬት፤ በደብረ ብርሃን፤ በአዲስ አበባ፤ በባህር ዳርና በሌሎቹም ከተሞች ህዝባዊ አመጽ እየተቀጣጠለ የወያኔን አገዛዝ እየለበለበው ይገኛል ። ብዙ ቦታዎች ከወያኔ ቁጥጥር ውጭ በመሆን ላይ ናቸው። 
 •   የኢትዮጵያ ተማሪዎችና የሕዝብ አመፅ፤ በግንባር ቀደም ፤ የህይወት መሥዋዕት የሚያስከፍል ትግል እያካሄዱ ናቸው። 
 •   ሕዝባዊ አመፁን ለመግታት፤ ወያኔ በአልሞት ባይተዳይነት ፤ ሕዝቡን በመጨፍጨፍ ላይ ይግኛል። ለዚህም፤ የወያኔው ዐጋዚ ጦር፤ የፍጥኖ ደራሽ ነፍሰ-ግዳይ ቡድን፤ የፖሊስ ጌስታፖ ሠራዊትንና በሽህ የሚቆጠሩትን የፀጥታ ሠራተኞችን ሁሉ አስልፎ በመርበትበት ላይ ይግኛል ። 
 •   የዓለም -ዐቀፍ ሁኔታም ቢሆን፤ ወያኔን የሚስማማ ሊሆን አይችልም ። በመካከለኛው ምሥራቅ በተፈጠረው እስላማዊ ጽንፈኛ መንግሥት ኣይ ሲ በሚያካሂደው አሸባሪ የሰው ህይወትና የንብረት ጥፋት ምክንያት፤ ምዕራባውያን ሀገሮች፤ በከፈተኛ ውጥረትና ሁከት ውስጥ ይገኛሉ ። በመሆኑም፤ የወያኔ የጡት አባቶችና የበላይ ጠባቂዎቹ ፤ ከኢትዮጵያ ሕዝብ አመፅ ፤ ፈጥነው ሊደርሱለት በሚችሉበት ሁኔታ ላይ አይደሉም ። የራሳቸው ቤት እያረረባቸው፤ የወያኔን እንኩሮ ሊያማስሉ የሚችሉ አይሆኑም ። ሌላው ዓለም ፤ የየራሱ ውስብስብ ችግሮች ስለአሉት፤ ወያኔ ስለሚገጥመው ችግር ደንታ ሊኖረው የሚችል አይደለም። 
 •   የመከላካያ ሠረዊት አባላት ሁኔታውን ለጊዜው በአርምሞ እየተካታተሉት ናቸው ለማለት ቢቻልም ፤ ሕዝባዊ አመፅ እየተፋፋመ በሚመጣበት ወቅት ፤ አመፁን ደግፈው ከሕዝብ ወገን በመቆም፤ታሪካዊ ተልዕኳቸውን እንደሚወጡ ይጠበቃባቸዋል ። ይህንን በማድረጋቸውም ፤ ከታሪክ ተወቃሽነትና ከህግ ተጠያቂነት ነፃ መውጣታቸውን ያረጋግጣሉ ። 
  ይህ እንደለ ሆኖ ግን ፤ በዐፄ ኃይለ ሥላሴ መንግሥት አወዳደቅ ጊዜና በአሁኑ የሀገራችን ወቅታዊ ሁኔታ መካከል አንድ ዐብይ ልዩነት መኖሩን መገንዘብ ይገባል ። ይህ ልዩነት ደግሞ፤ በቀላሉ የሚታይ ሊሆን አይችልም ። ይህም ሀገሪቱ እንደ ሀገር መቀጠል ወይም አለመቀጠልና የኢትዮጵያ ኅልውና ጉዳይ ነው ። የየካቲት ሕዝባዊ አመፅ ባስከተለው ምክንያት፤ አብዛኛዎቹ ሀገራዊ ተቋማት በመፈራረሳችውም የተነሳ፤ በቀጣይነት ለማስቀጠል 
የሚያስችል አቅም የነበራቸው ተቋማት አልነበሩም ።ነበሩ ቢባሉም እንኳ፤ ሁለት የኢትዮጵያ ተቋማትን ብቻ መጥቀስ ይቻል ይሆን ይሆናል ። እነርሱም፦ 
1ኛ ቁጥሩ ከ ዓርባ ( 40) ሺ የማይበልጠው የሀገሪቱ መከላካያ ሠረዊትና 2በሀገር አቅፍ ደረጃ የተደራጁት 
የኢትዮጵያ መምህራን ማህበር፤
ለ የኢትዮጵያ ተማሪዎች ማኅበር፤
የኢትዮጵያ ሠርቶኞች ማህበር ኮንፈዴሬሽን ነበሩ። 
የሀገሪቱ መምህራን ቁጥራችው 30 ሺ ነበርለሀገሪቱ እንደ ሀገር መቀጠል ተምሰሌ ብቻ ሳይሆኑ ዓይነተኛ ሚናም ተጫውተዋል ። የማኅበሩ መሪዎችም መሥዋዕት ከፍለዋል ። 
በዚያን ጊዜ የነበረው የተማሪ ማኅበርም ቢሆን፤ በኢትዮጵያ ሀገራዊ ጥላ ስር እንጅ በጎሳና በሃይመኖት የልተደራጀ ስለነበረ፤ ኢትዮጵያ እንደ ሀገር ለመቀጠል አስተማማኝ ኃይል ነበር ። ለዚህም እውነታ፤ መሥዋዕት ከፍሎ አስመስክሯል ። 
የሠራተኛው ማህበር ኮንፌደሬሽን ም ቢሆን የተደራጀው፤ በሀገር አቀፍ ደረጃ በኢትዮጵያ ጥላ ስር ስለነበረ ለሀገር አንድነት ተምሰሌት ነበር ማለት ይቻላል ። መሪዎቹም ተሰውተዋል። 
ዛሬ ያ ሁኔታ የለም። የወታደሩም አደረጃጀትና ሥልጠና፤ ወያኔ ሥልጣን ለመቆየት ባቀደው መልክ የተቃኘ ሲሆን፤ ወታደራዊ ዶክትሪኑና አመለካከቱ፤ በዘርና በቋንቋ ላይ የተመሰረተ ነው። የጦር ሹማምንቱና አወቃቀር፤ የእዝ ሰንሰለትና የሥልጣን ተዋረድ፤ ስምሪትና አሰፋፈር ፤ የሀገር መከላካያ ባኅርይ ሳይሆን ፤ የጎጠኛና የዘረኛ ግብ አስፈጻሚ ሠራዊት ነው። የወያኔን ከፋፋይ ህገመንግሥትለማስፈጸም ፤ አመች ሁኔታዎችን በጉጉት የሚጠባበቅ ያጥፋት ኃይል ነው። የዚህ ሁኔታ ደግሞ፤ ከኢትዮጵያ ለመገንጠል አድፍጠው ለሚጠባበቁ አፍራሽ ኃይሎች ተመችቷል። 
በአሁኑ ጊዜ፤ የኢትዮጵያ ተማሪዎች ማኅበር የሚባል ነገር ደብዛውም የለ። ሆን ተብሎ ሁሉም በየ ጎሳውና ዘሩ፤ በየቋንቋውና ጎጡ እንዲደራጅ ተደርጓል ። በመሆኑም፤ ለኢትዮጵያ ሀገራዊ አንድነት የሚያስብ አይደለም ። ለዜጎቿ እኩለነትና አብሮነት ማሰብ እንደ ነውር የሚቆጠርበት ጊዜ ተደርሷል ።የአንድነት ኃይሉ እየመነመነ ፤ እየተዳከመና ወደ ዳር ጠርዝ እየተገፋ በመሄድ ላይ ነው። ይህንን ሃቅ አምኖ ለመቀበል እንኳን ገና አልተዘጋጀም ። 
ለኢትዮጵያ አንድነት እናስባለን የሚለው ክፍልም፤ በየቤቱና በየመድረኩ፤ ህመሙንና ብሶቱን ከማስታመም አልፎ ትርፎ ፤ በድፍረት፤ አደባባይ በመውጣት ተደራጅቶ ፤ ለሀገሪቱ የቁርጥ

ቀን ልጅና ኃይል ሊሆን እንደሚገባው ማስመስከር አልቻለም ። ይህ ሁኔታ በበኩሉ ፤ ለተገንጣዮች የልብ ልብ ሰጥቷቸዋል ። 
የሀገራችን ተጨባጭ ሁኔታዎች ፤ ከሞላ -ጎደል ይህንን ገፅታ፤ ሊያሳዩ ይችላሉ ቢባልም፤ ኢትዮጵያን ወደ ተባባሰ የጥፋት አቅጣጫ እያመራ ያለውን ለውጥ፤ መቆጣጠር አጣዳፊ ርምጃ መውሰድ አንገብጋቢ ሆኗል ። ከሁሉ አስቀድሞ፤ 
1የአንድነት ኃይሉ፤ ያለምንም ውጣወረድ በአስቸኳይ መሰባሰብ አለበት ኢትዮጵያን ከጥፋት ለማዳን ሀላፊነቱ ከእርሱ ራስ አይወርድም !! 
2. " የገበያ ግርግር፤ ለሌቦች እንዳያመቻቸው እንቅስቃሴያቸውን ማምከን ይገባል ። የወያኔን አንቅፅ 39 ለመጠቅም አድፍጠው የሚጠባበቁት ፀረ-ኢትዮጵያ ኃይሎች ፤ አመች ጊዜ መጣልን ብለው ለሚያደርጉት እንቅስቃሴ ተባባሪ ላለመሆን መጥንቀቅ ያስፈልጋል ።እኛ በበኩላችን ከአፍራሽ ኃይሎች ጋር ጉዳይ ሊኖረን አይችልም ። ይልቁንም፤ ሀገራችን እንዳትፈራርስ እንታገላለን እንጅ 
3የኤርትርያው ሻኣቢያ ፤ የኢትዮጵያን መከፋፈል አይፈልግም የሚለውን ተጥቅአስፈች ፕሮፓጋንዳ ፤ የኢትዮጵያ ሕዝብ አይቀበለውም ። ኢትዮጵያን ከመፈከፋፈል የሚያድናት የአንድነት ኃይሉ ብቻ ነው ። የሀገራችን አንድነት ተከብሮ የኖረውም ፤ በሞግዚት ሳይሆን፤ በዐርበኞቿ ደምና አፅም ነበር ። አሁንም ያው እንዲሆን ግድ ነው ። 
4የወያኔ ነፍሰ-ገዳይ ቡድን በሕዝባችን ላይ የሚያካሄደውን ጦርነት ለማቆም የአንድነትና ዴምክራሲያዊ ኃይላት በፍጥነት ተባብረው እንዲነሱ አሁንም ደጋግመን፤ ጥሪያችንን አናስተላልፋለን ። እንጠባበቃለንም 
5ዘረኛው ሥርዓት፤ በሕዝባዊ አመፅ እንደሚደመሰስ ፤ መጠራጠር አይቻልም ኢትዮጵያ ዘለዓለም ትኖራለች