Friday, January 15, 2016

የአሲምባ ውይይት መድረክ ፕሮግራም ቅዳሜ ጥር 7 ቀን 2008 ዓ.ም. ከኢሕአፓ አመራር አባላት ጋር ቆይታ ያደርጋልየአሲምባ ውይይት መድረክ ፕሮግራም
ቅዳሜ ጥር 7 ቀን 2008 .. ከኢሕአፓ አመራር አባላት ጋር ቆይታ ያደርጋል
January 16, 2016)
የፊታችን ቅዳሜ ጥር 7 ቀን 2008 .. በአሲምባ የውይይት መድረክ የኢሕአፓ አመራር አባላት በመካከላችን በመገኘት ከየአቅጣጫው እየተቀጣጠለ ስላለው ሕዝባዊ አምጽና የፖለቲካ ሁናቴ ያወያዩናል።
በዚሁ ዕለት
 •   ኢሕአፓ በአሁኑ ጊዜ እየተቀጣጠለ ስላለው ሕዝባዊ አመጽ ምን ይላል
 •   ከየአቅጣጫው ስለሚሰማው የተባበሩ ጥሪ ኢሕአፓ ምን አስተያየት አለው
 •   ኢሕአፓ ምን መደረግ አለበት ብሎ ያምናል
 •   ኢሕአፓ የሕዝቡን አመጻ መሪነት ሰጥቶ አቅጣጫ ለማስያዝ ዝግጁ ነው ወይ
  እና የመሳሰሉትን ጥያቄዎች በማንሳ የምንወያይበት ቀን ስለሆነ ሀገር ወዳድ ኢትዮጵያውያን በአሲምባ የውይይት መድረክ በመገኘት በአሁኑ ወቅት የሚሰማቸውን ጥያቄም ሆነ ለድርጅቱ መደረግ አለበት ብለው የሚያምኑበትን መልዕክት እንዲሰጡ ለሁሉም ጥሪ እናደርጋለን።
  በአጠቃላይ በሀገራችን እየተጧጧፈ ስላለው ሕዝባዊ አምጽና በዕለቱ የኢሕአፓ አመራር አባላት መደረግ አለበት ብለው በሚያቀርቧቸው ሀሳቦች ላይ ግልጽ ውይይት የምናደርግበት ቀን ስለሆነ ጥያቄዎቻችሁንና አስተያየታችሁን ይዛችሁ እንድትመጡ ጥሪ እናደርጋለን።
  የአሲምባ ውይይት መድረክ ዘወትር ቅዳሜ በዋሺንግተን ዲሲ ሰዓት አቆጣጠር ከቀኑ 2 ሰዓት ጀምሮ ሀገር ወዳድ ኢትዮጵያውያን ተሰባስበው ስለሀገራቸው ኢትዮጵያ የሚወያዩበትና ገንቢ ሀሳቦችን የሚያዳብሩበት ዴሞክራሲያዊና ነፃ የውይይት መድረክ ነው።
  የአሲምባ ውይይት መድረክ 

No comments:

Post a Comment