Sunday, January 24, 2016

በሕወሓቱ ድረገጽ ወጥተው ስለግንቦት 7 ከተናገሩት መካከል ” በንቅናቄው ጦር ካምፕ ሴት በማስገባት በዲሲፕሊን የተባረሩ ናቸው”

ህወሓት/ኢህአዴግ ላንድ አራተኛ ምእተ ዓመት በኢትዮጵያ ህዝብ ላይ ተደጋጋሚ የጅምላና የተናጠል ፋሽስታዊ ጭፍጨፋዎች እያካሄደ፣እያሰረ፣ እየደበደበ፣ የህዝባችንን ሰብኣዊ መብትና ነፃነት ረግጦ፤ በቋንቋ እየከፋፈለ፣ በሃይማኖት ጣልቃ እየገባ፣ የህዝብ ሃብት እየዘረፈና በሙስና ተዘፍቆ ህዝባችንን አፍኖ በመግዛት ላይ ይገኛል፡፡
abebe Gelaw
“ህወሓት/ኢህአዴግ” የሚል መጠሪያ ስንጠቀም፣ ከህወሓት በስተቀር ሌሎቹ የኢህአዴግ አባል ድርጅቶች ከህወሓት ነፃ የሆነ ድርጅታዊ ህልውና ኖሯቸው እንደማያውቅ፤ ህወሓት ሌሎቹን ድርጅቶች የኢትዮጵያ ህዝብን ተቆጣጥሮ ለመግዛትና ለመበዝበዝ የጠፈጠፋቸው ድርጅቶች መሆናቸውን ለመግለፅ አስፈላጊ ስለሆነ ነው፡፡
ይህ የኢህአዴግ ኣባል ድርጅቶች በወታደራዊ የሃይል ልዩነት ላይ የተገነባ የይምሰል ጥምረት በስልጣን ክፍፍል ላይ የህወሓት የበላይነት አረጋግጧል፡፡ ህወሓት በሰራዊት፣ በደህንነት፣ በውጭ ጉዳይ፣ በኦርቶዶክስ ሃይማኖት የበላይነት ስልጣን፣ በመገናኛ ብዙሃን፣ በኢኮኖሚና በቻይና የኢትዮጵያ የአምባሳደርነት ቦታ ሳይቀር ያለ ማቋረጥ መቆጣጠሩ፣ ህወሓትን ባለ ርስት እንዲመስል አድርጎታል፡፡
በኢትዮጵያ ህዝብ ላይ ለሚፈፀሙ ግፎች የህወሓት ባለስልጣኖች እንደ ስልጣናቸው ከፍተኛ ተጠያቂነት አለባቸው፡፡ ይሁን እንጂ የሌሎቹ የኢህአዴግ ኣባል ድርጅቶች ባለስልጣኖችም ከመጠየቅ ሊድኑ አይችሉም፡፡
ህወሓት ባንድ በኩል የደርግ ኣገዛዝን ለማስወገድ ባስር ሺዎች የሚቆጠሩ የትግራይ ወጣቶች
ህይወታቸውን የሰዉበት ድርጅት ነው፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ ህወሓት ሲመሰረት ጀምሮ የተቆጣጠሩት ግለሰቦች ፀረ ኢትዮጵያ ስለሆኑ ሌሎች አባላትን አግልለው የድርጅቱ ዓላማ የትግራይ ሬፐብሊክ መመስረት እንደሆነ በማኒፌስቶ ገልፀው ነበር፡፡ እነዚህ ግለ ሰቦች የመገንጠል ዓላማቸው ለመተው ቢገደዱም በኢትዮጵያ ደረጃ ስልጣን ከያዙ በሁዋላም በሉአላዊነትና በኢትዮጵያ ህዝብ አንድነት ጥያቄዎች ላይ የማይታመኑ መሆናቸውን ደጋግመው አሳይተዋል፡፡ በዚህ መሰረት በኢትዮጵያ ታሪክ እንደ ህወሓት ብሄራዊ ጥቅምን አሳልፎ የሰጠ አገዛዝ የለም። አሁንም ህወሓት/ኢህአዴግ ግልፅነት በጎደለው አሰራር የኢትዮጵያን መሬት ለሱዳን የመስጠቱ አደጋ ስላለ የኢትዮጵያ ህዝብ ለያውቀውና ሊቃወመው ይገባል፡፡
እነዚህ ግለ ሰቦች በትጥቅ ትግሉ ጊዜ በትግራይ ውስጥ ከጦርነት ውጭ ደርግ ከገደላቸው በቁጥር የሚበዙ ሰላማዊና ራሳቸውን ሊከላከሉ የማይችሉ ዜጎችን አስረሽነዋል፡፡ ስለዚህም ነፍሰ ገዳዮቹ ከ40 ዓመት በፊት ጀምረው የንፁሃን ዜጎችን ህይወት በመቅጨት ላይ ይገኛሉ፡፡ ይህ ግፍ በይፋ እንዳይገለፅ ቢታፈንም የትግራይ ህዝብ በየቤተሰብና በየጎረቤት ደረጃ ያውቀዋል፡፡ ስለዚህ የህወሓት ባለስልጣኖች በትግራይ ውስጥ የጀመሯቸውና የለመዷቸው የግድያና አፈና ድርጊቶች ለሁሉም የኢትዮጵያ ህዝብ አዳርሰዋል፤
ምክንያቱም ወንጀለኞቹ በወቅቱ ከስልጣን አልተወገዱም፡፡
ባለፈው ህዳር በኦሮሞ ተማሪዎች የተጀመረውና የህዝብ ድጋፍ ኣግኝቶ የተቀጣጠለው ህዝባዊ እንቅስቃሴ ለመግታትና ለመደፍጠጥ የህወሓት/ኢህአዴግ መሪዎች ብዙ የኦሮሞ ተወላጆችን ገድለዋል፣ በብዙ ሺ የሚቆጠሩ አስረዋል። በኦሮሞ ህዝባችን ላይ የሚፈጸመው ግፍ በእጅጉ አሳዝኖናል፣ አስቆጥቶናል።
እንዲሁም በጎንደር አካባቢ የሚፈፀመው ወንጀል በእጅጉ አሳዝኖናል፣ አስቆጥቶናል።
የኦሮሞ ተማሪዎችና አርሶ አደሮች ሰላማዊ ተቃውሞ በማሰተር ፕላኑ ምክንያት ቢቀጣጠልም በ25
ዓመት የህወሓት/ኢህአዴግ ጭቆና ከተጠራቀመ ብሶት ጋር የተያያዘ ነው፡፡ ጭፍጨፋውም
የህወሓት/ኢህአዴግ አገዛዝ ሁሉ ጊዜ ለሰላማዊ ተቃውሞ የሚሰጠው መልስ ነው፡፡
የህወሓት/ኢህአዴግ መሪዎች የሚፈጽሟቸው አረመኔያዊ የጅምላ ግድያዎች ከዚህ በፊትም በአዲስ አበባ በተደጋጋሚ በ1985፣ በ1993፣ በሰኔ በ1997፣ በጥቅምት 1998፣ በጋምቤላ በታህሳስ 1996 ወዘተ..
ተፈፅሟል፡፡ ስለዚህ እነዚህ ጭፍጨፋዎች የሚቆሙት አስጨፍጫፊዎቹ ወንጀለኞች ከስልጣን ሲወገዱ ብቻ ነው፡፡
በበኩላችን የነዚህ ወንጀለኞች አገዛዝን በሚመለከት ያሉን አቋሞች የሚከተሉት ናቸው፦
1. የህወሓት/ኢህአዴግ መሪዎች ማንንም ብሄር/ብሄረሰብ የማይወክሉ፣ ለይስሙላ የህዝብን ጥያቄ
አንግበው ብዙ ወጣቶችን አስገድለው ለሰልጣን የበቁ ተራ አጭበርባሪዎችና ወንበዴዎች ናቸው፤
2. ለነዚህ ወንጀለኞች አቤቱታ ማቅረብ (ግድያቸውን እንዲያቆሙ፣ ህገ መንግስታቸውን እንዲያከብሩ መጠየቅ ወዘተ)ፋይዳ የለውም፤ ወንጀል ያልፈፀሙ የኢህአዴግ አባላት ወንጀለኞቹን በይፋ በማጋለጥ የህዝብ ወገንነታቸውን ማሳየት አለባቸው፡፡
3. የህወሓት/ኢህአዴግ አገዛዝ የሚደመሰሰውና ዴሞክራሲያዊ ስርዓት የሚገነባው በተናጠል ሳይሆን መላው የኢትዮጵያ ህዝብ ኣብሮ ሲታገል ነው፤ በህዝብ መካከል መሰረታዊ ቅራኔና ጠላትነት የለም፤
4. በኢትዮጵያ ህዝብ ላይ ለሚፈጸመው ወንጀል ተጠያቂዎች በዋናነት የህወሓት መሪዎች ቢሆኑም ፣ ግብረ-አበሮቻቸውም (የኦህዴድ፣ ብአዴን፣ ደኢህዴግ መሪዎችም) ተጠያቂዎች ናቸው፡፡
በመጨረሻም ማስገንዘብ የምንፈልገው የትግራይ ህዝብ የህወሓት ሰለባ እንጂ ለህወሓት ወንጀል ተጠያቂ አለመሆኑን ነው። በዚህ አጋጣሚ ግን በዲያስፖራ የሚኖሩ ትግራዎት ከሌላው ኢትዮጵያዊ ወገናቸው ጋር አብረው ለዴሞክራሲና ለአገር አንድነት እንዲታገሉ ጥሪያችንን እናቀርባለን።
እኛም ኦሮሞች ነን፤ ከኦሮሞ ህዝባችን ጎን ቆመን ፋሽስታዊውን የህወሓት/ኢህአዴግ መንግስታዊ የሽብር ድርጊት እናወግዛለን፡፡ በቅርቡ ሰላማዊ ተቃውሞ ምክንያት የታሰሩ ኦሮሞዎችና ሁሉም የፖለቲካ እስረኞችን ካለ ምንም ቅድመ ሁኔታ ለመፍታትና የተገደሉ ዜጎች ቤተሰቦችን ለመካስ አሸባሪው አገዛዝ እንዲገደድ ለኢትዮጵያ ህዝብ እናሳስባለን፡፡
በኢትዮጵያ ህዝብ (በትግራይ ከ40 ዓመታት በላይ፣ በመላ ኢትዮጵያ ለ25 ዓመታት) የሚፈፀሙት ተዳጋጋሚ ጭፍጨፋዎች (serial massacres) የሚቆሙት አስጨፍጫፊዎቹ ወንጀለኞች ከስልጣን ሲወገዱ ብቻ ነው፡፡
ከትግራይ ተወላጆች ኢትዮጵያውያን የተሰጠ መግለጫ
አብራሃ በላይ
አረጋዊ በርሀ (ዶር)
በላይነሽ ተክለሃይማኖት
ገብረመድህን ኣርኣያ
ግደይ አሰፋ (ዶር)
ግርማይ ገዛኸኝ
ካሕሳይ በርሀ
ነጋሲ በየነ
ተስፋይ ኣፅብሃ

No comments:

Post a Comment