Friday, January 1, 2016

የፍኖተ ዴሞክራሲ የኢትዮጵያ አንድነት ድምጽ ሀተታ. . . ሕዝባዊው አመጽ ሲገሰግስ ፤ ዘረውኛው አገዛዝ ሲደመሰስ !

የፍኖተ ዴሞክራሲ የኢትዮጵያ አንድነት ድምጽ ሀተታ ታኅሳስ ቀን 2008 .. የተላለፈ
ሕዝባዊው አመጽ ሲገሰግስ ፤ ዘረውኛው አገዛዝ ሲደመሰስ !
" አዕምሮ የሌለው ሕዝብ ሥርዓት የለውም ። የኃይል ምንጭ ሥርዓት እንጅ ፤ የሠራዊ ት ብዛት አይደለም ። ሥርዓት ከሌለው መንግሥት ይልቅ ፤ በህግ የምትኖር ትንሽ ከተማ ሞያ ትሰረላች ። "
ነግ አድራስ ገብረ ህይወት ባይከዳኝ ።
የሀገራችን ወቅታዊው ሁኔታ ፤ የ1966 ቱን ወርሃ የካቲት ሁኔታ በብዙ መልኩ ያንፀባርቃል ። ያስታውሳል ። ያመለክታል ። ተመሳሳይ የደወል ድምፅም ያሰማል ። ይህ ድምጽ ፤ የወየኔን ግብዐ -ተመሬት መርዶ ሲናገር ፤ በአንፃሩ ደግሞ ፤ የኢትዮጵያን ብሥራተ- ነፃነት ያውጃል ።
" ታሪክ ፤ በተለያየ ወቅትና ሁኔታ እራሱን ይደግማል ። " እንዲሉ፤ የ1966ቱ ዓም የካቲት ሕዝባዊ አመፀ ፤ በወቅቱ የነበረውን ኋላ - ቀር ሥርዓት እንደለወጠው ሁሉ ፤ የአሁኑም ሕዝባዊ አመፅ ፤ የወያኔን ዘረኛ አገዛዝ ፤ ወደ ግበዐ -ተመሬቱ እንደሚወስደው የታሪክ ሀቅ ነው ። ታሪክ የሚያመጣውን ሃቅ ደግሞ፤ ማንም ሊጠራጠር አይቻለውም ። አውቆ ካልተኛ በስተቀር !
በአንድ ትውልድ ዘመን የሚፈራረቁትን ታሪካዊ ኩነቶች ማነፃፀር ካለብን ፤ የስድሳ ስድስቱንና የአሁኑን የሀገራችንን ሁኔታ እያወዳደርን ማየት መቻል ይኖርብናል ።ይህ ተመክሯችን ደግሞ፤ ዕይታችንን በሀገራችን ሁኔታ ላይ እንድናተኩር ይረዳናል ። በመሆኑም፤ የባእዳንን ተመክሮ፤ እንደ ሸቀጥ ዕቃ (Imported Goods ) አግበስብሶ ለማምጣት አንገደድም ። አያስፈልገንምም !
የራሳችንን ተመክሮ በሚገባ ከተጠቀምንበት፤ ካወቅንበትና ከሰራንበት፤ ሞልቶ የተትረፈረፈ፤ ዕውቀትና የበለፀገ ልምድ፤ እናገኝበታለን ። ካለፈው ስህተትም እንማርበታለን ። ብልህ፤ ስህተቱን አይደግምም !
" ከታሪክ የማይማሩ ፤ራሳቸውን እየረገሙ ይኖራሉ።" ፤ እንጅ፤ እኛስ የታሪክ ክስተት ካመጣው ስህተት እየተማርን ስህተታችን እያረምን ወቅታዊውን ሁኔታ በሚገባ ተጠቅመን ሀገራችንን ከጥፋት ማዳን የመጀመሪያው ተግባራችን ከሆነ ቆይቷል ። ያ ደግሞ የይፈፀማል ! ይህ ሊሆን የሚችለው ግን፤ ኢትዮጵያ እንደ ሀገር፤ ሕዝቧም እንደ አንድ ሀገር ሕዝብ አብረው መኖራቸውን ሲቀጥሉ ነው ።
የሦስት ሺ ዓመት ታሪክ ያላት ሀገር መቅጠል ካለባት ፤ ከአድማስ ባሻገር ማስብን ይጠይቃል ። የፖለቲካ ሥልጣን ከመያዝ በላይ አርቆ ማስተዋልንም ግድ ይላል ። ሀገርን ሳያድኑ፤ ለፖለቲካ
page1image17840
ሥልጣን መራኮት ፤ ተያይዞ መጥፋትን ያስከትላል ። ሁላችንም ተያይዘን እንደንጠፋ ደግሞ ፤ ጠላቶቻችን ሌት -ተቀን ተግተው ይሰራሉ ።
1966 ዓም የካቲት ፤ ህዝባዊ አመፅ ፤ የዐፄ ኃይለ ሥላሴ መንግሥት ወደ እማይቀርለት ግበዐ - ተመሬቱ እንዲገባ የተደረገው በሚከተሉት ሳይንሳዊ ምክንያቶች ነበር ።
1. መሠረታዊ
. 1. የፊዳሉ ሥርዓት እንደ ወትሮው እየጨቆነ መግዛት ስለ አልሆነልት ።
2. የመጨቆኛ መሳሪያዎቹና መንግሥታዊ አውታሮቹ እየተፍረከረኩ መምጣታቸው ። 3. የገዥው መደብ ፤ ኃይሉ እየደከመ ፤ ክንዱ እየዛለ በመሄዱ ምክንያት ተስማምቶና
ተባብሮ ሥርዓቱን ማቆየት ስላልቻለ ።
. 1. መልዐተ- ሕዝቡ እንደቀድሞው እየተጨቆነ መገዛት ባለመፈለጉ ፤ አሻፈረኝ ብሎ በመነሳቱ፤
2. በገዥው መደብና በተገዥው ሕዝብ መካከል የነበረው ቅራኔ፤ እጅግ ሰልቶና ጎልቶ በመምጣቱ ።
3. ሥር ዓቱን አቅፈው ደግፈው የነበሩት ፤ የመንግሥት አገልጋዮች ሁሉ፤ የሕዝቡ አመጽ ባስከተለው የኃይል ሚዛን መለወጥ ምክንያት፤ ሲያገለግሉት የነበረውን ሥርዓት ከድተው ሰልፋቸውን ከሕዝብ ጎን ማድረጋቸው ።
2. ወቅታዊ / ነባራዊ ሁኔታዎች
. ድርቅ ያስከተለው ረሃብ በሕዝብ ላይ ያስከተለው አሰቃቂ ዕልቂት ፤ ለ. በየቦታው ሲካሄዱ የነበሩት ጦርነቶች፤
. የዓለም- አቅፍ ሁኔታ ባስከተለው ምክንያት፤ የቤንዚን /ነዳጅ ዋጋ መጨመር ባመጠው የኑሮ ውድነት መክንያት ፤ በዜጎች ላይ ያሳደረው ሮሮና ስቃይ። በድሃው ላይ ያመጣው የመኖር ተስፋ ማጣት ፤
. የተራማጅ ኃይሎች ለሕዝብ ወገንተኝነት ሲያደርጉት የነበረው ትግል ፤ ፈር እየያዘ መምጠቱ ፤ ዋና ዋና ምክንያቶች ነበሩ ።
የእነኝህ ሁሉ ድምር ውጤት፤ ሕዝባዊ አመፁን፤ የማይበገር ኃይል ስለአደረገው፤ ኋላ-ቀር ሥርዓቱን ሊለውጠው ችሏል ።
ዛሬም እንደ ትላንቱ ፤ የሀገራችን ተጨባጭ ሁኔታዎች ፤ ተመሳሳይ ኩነቶችን በማንፀባረቅ ላይ ናቸው ።
ይህ ዘረኛ አገዛዝ ባስከተለው ጭቆና ምክንያት፦----
በመላው ሀገሪቱ ክፍሎች ሕዝባዊ አመፆች በመካሄድ ላይ ናቸው ።
  •   በአርሲ፤ በጎንደር፤ በሐረር፤ በጅማ ፤ በወለጋ፤ በናዝሬት፤ በደብረ ብርሃን፤ በአዲስ አበባ፤ በባህር ዳርና በሌሎቹም ከተሞች ህዝባዊ አመጽ እየተቀጣጠለ የወያኔን አገዛዝ እየለበለበው ይገኛል ። ብዙ ቦታዎች ከወያኔ ቁጥጥር ውጭ በመሆን ላይ ናቸው።
  •   የኢትዮጵያ ተማሪዎችና የሕዝብ አመፅ፤ በግንባር ቀደም ፤ የህይወት መሥዋዕት የሚያስከፍል ትግል እያካሄዱ ናቸው።
  •   ሕዝባዊ አመፁን ለመግታት፤ ወያኔ በአልሞት ባይ- ተዳይነት ፤ ሕዝቡን በመጨፍጨፍ ላይ ይግኛል። ለዚህም፤ የወያኔው ዐጋዚ ጦር፤ የፍጥኖ ደራሽ ነፍሰ-ግዳይ ቡድን፤ የፖሊስ ጌስታፖ ሠራዊትንና በሽህ የሚቆጠሩትን የፀጥታ ሠራተኞችን ሁሉ አስልፎ በመርበትበት ላይ ይግኛል ።
  •   የዓለም -ዐቀፍ ሁኔታም ቢሆን፤ ወያኔን የሚስማማ ሊሆን አይችልም ። በመካከለኛው ምሥራቅ በተፈጠረው እስላማዊ ጽንፈኛ መንግሥት ( ኣይ ሲ ) በሚያካሂደው አሸባሪ የሰው ህይወትና የንብረት ጥፋት ምክንያት፤ ምዕራባውያን ሀገሮች፤ በከፈተኛ ውጥረትና ሁከት ውስጥ ይገኛሉ ። በመሆኑም፤ የወያኔ የጡት አባቶችና የበላይ ጠባቂዎቹ ፤ ከኢትዮጵያ ሕዝብ አመፅ ፤ ፈጥነው ሊደርሱለት በሚችሉበት ሁኔታ ላይ አይደሉም ። " የራሳቸው ቤት እያረረባቸው፤ የወያኔን እንኩሮ ሊያማስሉ የሚችሉ " አይሆኑም ። ሌላው ዓለም ፤ የየራሱ ውስብስብ ችግሮች ስለአሉት፤ ወያኔ ስለሚገጥመው ችግር ደንታ ሊኖረው የሚችል አይደለም።
  •   የመከላካያ ሠረዊት አባላት ሁኔታውን ለጊዜው በአርምሞ እየተካታተሉት ናቸው ለማለት ቢቻልም ፤ ሕዝባዊ አመፅ እየተፋፋመ በሚመጣበት ወቅት ፤ አመፁን ደግፈው ከሕዝብ ወገን በመቆም፤ታሪካዊ ተልዕኳቸውን እንደሚወጡ ይጠበቃባቸዋል ። ይህንን በማድረጋቸውም ፤ ከታሪክ ተወቃሽነትና ከህግ ተጠያቂነት ነፃ መውጣታቸውን ያረጋግጣሉ ።
    ይህ እንደለ ሆኖ ግን ፤ በዐፄ ኃይለ ሥላሴ መንግሥት አወዳደቅ ጊዜና በአሁኑ የሀገራችን ወቅታዊ ሁኔታ መካከል አንድ ዐብይ ልዩነት መኖሩን መገንዘብ ይገባል ። ይህ ልዩነት ደግሞ፤ በቀላሉ የሚታይ ሊሆን አይችልም ። ይህም ሀገሪቱ እንደ ሀገር መቀጠል ወይም አለመቀጠልና የኢትዮጵያ ኅልውና ጉዳይ ነው ። የየካቲት ሕዝባዊ አመፅ ባስከተለው ምክንያት፤ አብዛኛዎቹ ሀገራዊ ተቋማት በመፈራረሳችውም የተነሳ፤ በቀጣይነት ለማስቀጠል 
የሚያስችል አቅም የነበራቸው ተቋማት አልነበሩም ።ነበሩ ቢባሉም እንኳ፤ ሁለት የኢትዮጵያ ተቋማትን ብቻ መጥቀስ ይቻል ይሆን ይሆናል ። እነርሱም፦
1ኛ ቁጥሩ ከ ዓርባ ( 40) ሺ የማይበልጠው የሀገሪቱ መከላካያ ሠረዊትና 2. በሀገር አቅፍ ደረጃ የተደራጁት
. የኢትዮጵያ መምህራን ማህበር፤
ለ የኢትዮጵያ ተማሪዎች ማኅበር፤
. የኢትዮጵያ ሠርቶኞች ማህበር ኮንፈዴሬሽን ነበሩ።
የሀገሪቱ መምህራን ( ቁጥራችው 30 ሺ ነበር) ለሀገሪቱ እንደ ሀገር መቀጠል ተምሰሌ ብቻ ሳይሆኑ ዓይነተኛ ሚናም ተጫውተዋል ። የማኅበሩ መሪዎችም መሥዋዕት ከፍለዋል ።
በዚያን ጊዜ የነበረው የተማሪ ማኅበርም ቢሆን፤ በኢትዮጵያ ሀገራዊ ጥላ ስር እንጅ በጎሳና በሃይመኖት የልተደራጀ ስለነበረ፤ ኢትዮጵያ እንደ ሀገር ለመቀጠል አስተማማኝ ኃይል ነበር ። ለዚህም እውነታ፤ መሥዋዕት ከፍሎ አስመስክሯል ።
የሠራተኛው ማህበር ኮንፌደሬሽን ም ቢሆን የተደራጀው፤ በሀገር አቀፍ ደረጃ በኢትዮጵያ ጥላ ስር ስለነበረ ለሀገር አንድነት ተምሰሌት ነበር ማለት ይቻላል ። መሪዎቹም ተሰውተዋል።
ዛሬ ያ ሁኔታ የለም። የወታደሩም አደረጃጀትና ሥልጠና፤ ወያኔ ሥልጣን ለመቆየት ባቀደው መልክ የተቃኘ ሲሆን፤ ወታደራዊ ዶክትሪኑና አመለካከቱ፤ በዘርና በቋንቋ ላይ የተመሰረተ ነው። የጦር ሹማምንቱና አወቃቀር፤ የእዝ ሰንሰለትና የሥልጣን ተዋረድ፤ ስምሪትና አሰፋፈር ፤ የሀገር መከላካያ ባኅርይ ሳይሆን ፤ የጎጠኛና የዘረኛ ግብ አስፈጻሚ ሠራዊት ነው። የወያኔን ከፋፋይ " ህገመንግሥት" ለማስፈጸም ፤ አመች ሁኔታዎችን በጉጉት የሚጠባበቅ ያጥፋት ኃይል ነው። የዚህ ሁኔታ ደግሞ፤ ከኢትዮጵያ ለመገንጠል አድፍጠው ለሚጠባበቁ አፍራሽ ኃይሎች ተመችቷል።
በአሁኑ ጊዜ፤ የኢትዮጵያ ተማሪዎች ማኅበር የሚባል ነገር ደብዛውም የለ። ሆን ተብሎ ሁሉም በየ ጎሳውና ዘሩ፤ በየቋንቋውና ጎጡ እንዲደራጅ ተደርጓል ። በመሆኑም፤ ለኢትዮጵያ ሀገራዊ አንድነት የሚያስብ አይደለም ። ለዜጎቿ እኩለነትና አብሮነት ማሰብ እንደ ነውር የሚቆጠርበት ጊዜ ተደርሷል ።የአንድነት ኃይሉ እየመነመነ ፤ እየተዳከመና ወደ ዳር ጠርዝ እየተገፋ በመሄድ ላይ ነው። ይህንን ሃቅ አምኖ ለመቀበል እንኳን ገና አልተዘጋጀም ።
ለኢትዮጵያ አንድነት እናስባለን የሚለው ክፍልም፤ በየቤቱና በየመድረኩ፤ ህመሙንና ብሶቱን ከማስታመም አልፎ ትርፎ ፤ በድፍረት፤ አደባባይ በመውጣት ተደራጅቶ ፤ ለሀገሪቱ የቁርጥ

ቀን ልጅና ኃይል ሊሆን እንደሚገባው ማስመስከር አልቻለም ። ይህ ሁኔታ በበኩሉ ፤ ለተገንጣዮች የልብ ልብ ሰጥቷቸዋል ።
የሀገራችን ተጨባጭ ሁኔታዎች ፤ ከሞላ -ጎደል ይህንን ገፅታ፤ ሊያሳዩ ይችላሉ ቢባልም፤ ኢትዮጵያን ወደ ተባባሰ የጥፋት አቅጣጫ እያመራ ያለውን ለውጥ፤ መቆጣጠር አጣዳፊ ርምጃ መውሰድ አንገብጋቢ ሆኗል ። ከሁሉ አስቀድሞ፤
1. የአንድነት ኃይሉ፤ ያለምንም ውጣ- ወረድ በአስቸኳይ መሰባሰብ አለበት ! ኢትዮጵያን ከጥፋት ለማዳን ሀላፊነቱ ከእርሱ ራስ አይወርድም !!
2. " የገበያ ግርግር፤ ለሌቦች እንዳያመቻቸው " እንቅስቃሴያቸውን ማምከን ይገባል ። የወያኔን አንቅፅ 39 ለመጠቅም አድፍጠው የሚጠባበቁት ፀረ-ኢትዮጵያ ኃይሎች ፤ አመች ጊዜ መጣልን ብለው ለሚያደርጉት እንቅስቃሴ ተባባሪ ላለመሆን መጥንቀቅ ያስፈልጋል ።እኛ በበኩላችን ከአፍራሽ ኃይሎች ጋር ጉዳይ ሊኖረን አይችልም ። ይልቁንም፤ ሀገራችን እንዳትፈራርስ እንታገላለን እንጅ !
3. የኤርትርያው ሻኣቢያ ፤ " የኢትዮጵያን መከፋፈል አይፈልግም " የሚለውን ተጥቅ- አስፈች ፕሮፓጋንዳ ፤ የኢትዮጵያ ሕዝብ አይቀበለውም ። ኢትዮጵያን ከመፈከፋፈል የሚያድናት የአንድነት ኃይሉ ብቻ ነው ። የሀገራችን አንድነት ተከብሮ የኖረውም ፤ በሞግዚት ሳይሆን፤ በዐርበኞቿ ደምና አፅም ነበር ። አሁንም ያው እንዲሆን ግድ ነው ።
4. የወያኔ ነፍሰ-ገዳይ ቡድን በሕዝባችን ላይ የሚያካሄደውን ጦርነት ለማቆም የአንድነትና ዴምክራሲያዊ ኃይላት በፍጥነት ተባብረው እንዲነሱ አሁንም ደጋግመን፤ ጥሪያችንን አናስተላልፋለን ። እንጠባበቃለንም !
5. ዘረኛው ሥርዓት፤ በሕዝባዊ አመፅ እንደሚደመሰስ ፤ መጠራጠር አይቻልም ! ኢትዮጵያ ዘለዓለም ትኖራለች !

No comments:

Post a Comment