Tuesday, January 26, 2016

የወያኔን ብሎን ለማወላለቅ ( Finote Democracy: The Voice of Ethiopian Unity! )

ብሎኖቹ ሁሉ የወላለቁ፤ የተበላሹ፤ ቤንዚን አልባ የሆነ መኪና ሊንቀሳቀስ አይችልም ነው። ወያኔም እንደዚያው ነው። የአፈና መሳሪያዎች ስላሉት ብቻ በሰላም ሊገዛ አይችልም። የአፈና መሳሪያዎቹን ራሳቸውን ማበለሻሸት፤ ከጥቅም ውጪ ማድረግ ይቻላል። የደርግን ግዙፍ ጦር ውድቀት ያጤኗል!
ወያኔ መንግስት ሆኛለሁ ብሎ ሲውገረገር ከመቀሌ እስክ ሞያሌ፤ ከጅማ እስከ አሳይታ መዋቅር ዘርግቻለሁ ባይ ነው። ለዚህ ስራው በመለስተኛ ቡችላነት፤ ባርነት የሚያገለግሉትና ሕዝብን በጎሳና በሀይማኖት ከፍለውለት የሚሰሩለት አሉ። ተለጣፊና ቅጥረኛ የምንላቸው እነ አዲሱ-ብአዴን፤ እነ ሀይለማርያምና አባዱላ ዓይነቶቹን ማለት ነው።

 የወያኔ መዋቅር ወልገድ ወልገድገድ ካለ ቆይቷል። ሙስናና ዘረኝነት እንደ ምስጥ በልቶታል። አውራጃዊነት ምርጥ ዜጋ የተባሉትንም እያመሳቸው ነው። ሙስሊም ኢትዮጵያውያን መብታችን እምነታችን ይከበር ብለው ትግል ከጀመሩ ዓመቶችን እያስቆጠሩ ነው። ሕዝብ እንደ ህዝብ ቅሬታ ይዟል፤ ከባድ ቂም ቋጥሯል። ሂሳብ ማወራረጃ ቀንን እየጠበቀ እንዳለም ግልጽ አድርጓል ማለት ይቻላል። የሚጠበቀው የጋለ ትግል ግን ገና መሆኑ ይታያል። የአመጽ መከሰቻው ዘግይቷል። ስለ ትግል የሚያወሳው በዝቶ ተጨባጭ ትግል ግን ኮስሶ እንዳለ ዜጋ ሁሉ የሚያውቀው ነው። በ 6 ወር ነጻ እናወጣችኋለን ገንዘብ አምጡ ብቻ ያሉንም ኪሳቸውን ሞሉ እንጂ በስድስት ዓመትም አልቻሉም። ነውናም ሕዝብ ነጻ አውጪን ሳይጠበቅ የራሱንና የሀገሩን ጉዳይ የራሱ አድርጎ መነሳትና ወያኔን በሁሉም መስክ እያጠቃ ማዳከምና ለማሸነፍም መጣር አለበት።
ወያኔ ሰፊ መዋቅር አለውና ስስ ብልቶቹ ብዙ ናቸው። እነዚህን ለይቶ ማወቅና ማጥቃት ብዙ ጉዳትን ያመጣበታል። ወያኔ ሰላማዊ ሰልፍን በጥይት ይበትናል ሲባል የሙት ከተማ አድማን መጠቀም ያዋጣል የተባከውን አንዘነጋም። የአይሲስ ነፍሰ ገዳዮች ኢትዮጵያውያን በሊቢያ ያረዱ ወቅት የተደረጉትን ሰልፎችንም መጥቀስ ይቻላል። ዝግጅትና የይቻላል መንፈስ ካለ በጋራ ተቃውሞ ብዙ ማድረግ ይቻላል። ሰፊ ድርጅትን ሳይጠይቁ በግለሰብና በጥቂት የሚተማመኑ ዜጎችም ብዙ መስራት ይቻላል። ክብሪትን ከወያኔ ንብረቶች ማስተዋወቁ አንዱ ስምሪት ነው። የወያኔን ምስጢር የአደባባይ ማድረግም ይጎዳዋል። ችሎታ ያላቸው ደግሞ የወያኔን የኮምፕዩተር መዋቅር ጥሰው ገብተው ሊያበላሹትና የምስጢር ሰነዶቹንም ይፋ ሊያደርጉበት ይችላሉ። የወያኔን የመስሪያ ቤት ኮምፕዩተሮችንም ማበላሸት ትግል ነው። የወያኔን፤ የአፋኝ ተቅዋሞቹን መኪናዎችንም ሆነ ሌሎች ተንቀሳቃሾችን ማበላሸት ይቻላል። በወያኔ የፖሊስና ወታደራዊ ተቋሞች ውስጥ ያሉ ሀገር ወዳድ ዜጎች ብዙ ይጠበቅባቸዋል። የወያኔ ቀንደኛ አገልጋዮችንና
በተለይም ሰላዮችን ስማቸውንና አድራሻቸውንም ይፋ ማድረግ ጉዳቱ ቀላል አይደለም። በዚህ ስምሪት የውስጡና የውጩ ጥረት ሊቀናጅ ይችላል።
ቀደም ማዕቀብ ያልነውም በዚሁ ሊነሳ የሚገባው ነው። በተለይም በውጭ ሀገር ያሉት ዜጎች በወያኔና በቀንደኛ ደጋፊዎቹ ንግድና ምርት ላይ ሙሉ ማዕቀብ ሊያደርጉ ይችላሉ። የወያኔ የጤፍ እንጀራ፤ ቢራ፤ የገንዘብ መለወጫ ቢሮዎች፤ የወያኔ ቪኖ፤ የወያኔ ጋዜጦችና ድረ ገጾች፤ አየር መንገዱ፤ ወያኔዎች ሁሉም ላይ ማዕቀብ ማረግ ይቻላል። በሀገር ቤት ወደ ወያኔ ሱቅና ሆቴል አለመግባት፤ ወያኔ ከሆኑ ባለሱቆች አለመሸመት፤ በወያኔ አውቶቡሶች አለመጓዝ--ዝርዝሩ ብዙ ነው ግን መደረግ ያለበት ስውር አይደለም። ወያኔን ገንዘብ አለመስጠት፤ ከሕዝብ መነጠል ማለትም ነው። በወያኔ ላይ ጎጂ ቅስቀሳ ማካሄድም መፋፋም አለበት። በውስጣቸው ክፍፍልን ማባባስ ይጠቅማል። ታምራት ላይኔን ከወያኔ ለማጣላት በስልት በኢሕአፓ የተፈጸመው ሻጥር ምሳሌ ሊሆንም ይችላል። አሁንም እየተካሄዱ ያሉ ጸረ ወያኔ ከፋፋይና ጎጂ ሻጥሮች እንዳሉ መገመትም ከባድ አይደለም። ወያኔን (ፖሊስ፤ ጸጥታና ወታደራዊ ተቋሞቹን ወዘተ) ሰርጎ መግባት ደግሞ በግለሰብ ደረጃም ሊሰራ የሚችል ነው። ወያኔ ጠላት ነውና በውስጡ ሰርገው ገብተው የሚጎዱት ካሉ ለጥቃት በሚገባ ይጋለጣል። የሰርጎ ገብ ስምሪት በግልም በተደራጀ መልክም ሊካሄድ የሚችል ነው። ባለፈው አገዛዝ የኢሕአፓ ሰርጎ ገቦች በልዩ ልዩ ደረጃ ደርግን ሊጎዱና ድርጅቱን ሊከላከሉ ችለዋል። የዚህን ዝርዝር ማቅረቡ ያለው ሁኔታ ባይፈቅድም ታሪክ ግን ዘግቦት የሚያቆየው መሆኑ አያጠራጥርም። ባለፉት ጥቂት ዓመታት ወያኔ በበኩሉ ባጀት መድቦና ሰርጎ ገቦችን አሰናድቶና አሰልጥኖ ወደ ኢሕአፓ የላካቸውን ማክሸፍ ተችሏል። ድርጅቶችና ዜጎችም ጥንቃቄ ካደረጉ፤ ሙያተኛ ስምሪትን ከተጠቀሙ ሰርገው የሚገቡ ወይም ህብረተሰቡን ተመሳስለው ሊሰልሉ የሚሞክሩት ውጤት አልባ ይሆናል። ወያኔና ደጋፊዎቹን ከሕዝብ ማራቅ አንዱ ጥንቃቄ ነው። አንዳንዶች ሻጥር ሲባል ቀፈፍ የሚላቸውና አግባባ ያጣም ነው የሚሉ አሉ። በመሰረታዊው ጉዳይ ላይ ግልጽነት ካላቸው ግን ይህ ጥርጣሬ አይመጣባቸውም። መሰረታዊው ጉዳይ ወያኔ የኢትዮጵያና የሕዝብ ጠላት ነው የሚለው ነው። ካራቢንዬሪውን/ሶልዳቶውን ከባንዳው መለየት አይገባምና ጠላት ሲባል ጠላትን የሚጎዳ፤ የሚያደናቅፍ እርምጃን ሁሉ መውሰድ አስፈላጊ ነው ማለት ነው። የኢትዮጵያ አየር መንገድ ላይ ማዕቀብ አድርጉ ሲባል ይህ ተቋም የሚያገኘው ምርት ለወያኔ መጠቀሚያ በመዋሉ ብቻ ሳይሆን አብዛኛው ሰራተኞቹም ተመርጠው ከወያኔ መንደር የተወለዱ በመሆናቸውም ነው። የወያኔ ዕቅዶች በሞላ ለወያኔ እንጂ ለኢትዮጵያ አይጠቅሙምና ቢደናቀፉ ተገቢ ነው። መደናቀፍም አለባቸው። ወያኔዎችን ማራቅ መጥላት ስንልም መነሻው ይኸው ነው--ጠላትን ማራቅ መጉዳት እርስ በርሱ እንዲናቆር ሻጥር መስራት፤ ሴራዎችን መጎንጎን ማለት ነው። በዚህ ላይ ጠንክሮ መግፋት ሲፈለግ ይህን የሚቃወሙት ጉዶች ማፈሪያ
የሆኑት ለዚህ ነው። አይ አይገባም፤ ላንፋታ ተጋብተናል ወዘተ ዓይነት አቅዋሞችና ንግግሮች የሚጠቅሙ አይደሉም።
የወያኔን የትራንስፖርት አቅምም መዳከም ያለበት ነው። የጦሩን የመንቀሳቀስ ችሎታም ማዳከም ከድንበር ጥበቃ ሳይሆን ከአጋዚና ፌዴራልን ማደናቀፍ ጋር የሚያያዝ ነው። የወያኔ ጦር የኢትዮጵያ ሳይሆን የወያኔ ነው። ወያኔ ከሻዕቢያ ቅራኔ የገባው ለኢትዮጵያ ብሎ አይደለም። ሆኖም ግን ስምሪታችን ለሀገር ጠላቶች ምንም ቀዳዳ የማይከፍት መሆን እንዳለበት ማስታወስ ይገባል፡፡ ዚያድ ባሬ ኢትዮጵያን ሲወር በ ጦሩ የነበሩ የኢሕአፓ አባላት ተዋግተው ተሰዉ እንጂ ድርጅቱ ሚሊሺያውን ሆነ ወታደሩን ለማደናቀፍ የሰራው አንድም ነገር እንደሌለ ህዝብ ያውቃል፤ አናምንም የሚሉ ዋሾ ደርጎችና ርዝራዦቹ መሆናቸውም ተጋልጧል። ወያኔም ኢሕአዴግ አይደለም-- ነጻ ድርጅቶች ሳይሆኑ ተለጣፊዎችን ያቀፈ ነውና አገዛዙ ወያኔ ተብሎ መጠራቱ አግባብ ያለው ነው። ሕወሀት/ኢሕአዴግ ብለው ከጫማው የሚደፉት ማፈሪያ የተባሉት ለዚህ ነው። ወያኔ መንግስት አይደለም--በሕዝብ ላይ የተጫነ ጨቋኝና ዘረኛ አገዛዝ እንጂ። ወያኔ ኢትዮጵያዊ አይደለም--ትግራይ ትግራይ የሚል ጎጠኛና ጠባብ ብሄረተኛ ቡድን እንጂ። እነዚህን ከተገነዘብንና ወያኔ ጠላት መሆኑ ላይ ምንም ዓይነት ብዥታ ላለማስተናገድ ከወሰንን ምን እርምጃ መውሰድ እንዳለብን ግልጽ ይሆንልናል። ገደብም የሚያስፈልገው አይመስለንም።
ሀገርና ወያኔ ለየቅል ናቸው። ይህ ዘረኛ ቡድን ሀገርን የጎዳው ዘረኝነትን ጎጠኝነትን በማስፋፋትና በተለይም የወጣቱን የአንድነት/አብሮነት ስሜት በመስለብ በማጫጫት ነው። ይህም ወጣቶችን በሀገር ፍቅር ስሜት፤ በአርበኞችና ጀግና ትውልድ መንፈስ መቃኘት ትኩረት ተሰጥቶት መሰራት ያለበት ነው። ወጣቱ ከዳነ ሀገር ትድናለች። ትውልዱን ታሪክ አልባ ለማድረግና ሀገሪቷ ጀግናም አፍርታ አታውቅ በሚል ለማናውዝ እየጣሩ ያሉ ምሁሮች የወጣቱን አንጎል እንዳይሰርቁም መታገል ወሳኝ ነው። ወያኔ በሕዝብ ዘንድ በአጠቃላይ በወጣቱ በተለይ ቀቢጸ ተስፋን ማስፈን ይፈልጋልና በዚህ ጨለምተኝነት ዘመቻ የሚያጅቡትን ምሁሮች ለአንዴም ለሁሌም ወግዱ ማለትም አስፈላጊ ነው። የትግል መንፈስን ማስጨበጥ የቤተሰቦችም የህብረተሰቡም ተግባርና ግዳጅ መሆኑም መዘንጋት የለበትም። ሞራል ግንባታ፤ ሰብዕናን ማስከበር፤ ሕይወቴ ለኢትዮጵያ ማለት፤ በገቢር ወደ ትግል መሰማራትና መሰል መንፈሶችን የራስ ማድረግ የሚጠበቅ ነው ማለት ነው። አይናችን እያየ ወጣቶቻችንን ወኔ ቀምቶና ወደ ጎጠኛነት ነክሮ ሀገረ የሚል ትውልድ እንዳያሳጣን የሞት የሽረት ትግል ማካሄድ አለብን። አማራጭ የለንም። ሀገርን ለማዳን ትውልድን ወደ ቀና ሀገር ወዳድ ጎዳና እነመልስ።
በሁሉም አጋጣሚና ባለን አቅም ሁሉ ወያኔን እናጥቃ፤እናዳክም፤ ወደ ውድቀቱም እንግፋው

No comments:

Post a Comment