Tuesday, January 5, 2016

ህግ ያልገዛውን ወያኔ ህዝባዊ አመፅ ያንበረክከዋል ! Finote Radio

ህግ ያልገዛውን ወያኔ
ህዝባዊ አመፅ ያንበረክከዋል !


በአገራችን ውስጥ የተለያዩ መንግሥታት ተፈራርቀዋል። ነባሩ ወደ ቀጣዩ አገዛዝ የሚተላለፈው ተቀመጥ በወንበሬ፤ ተናገር በከንፈሬ ተብሎ በአብዣኛው ህዝብ  ተመረጦ ሳይሆን  በፖለቲካ መመሳጠርና በነፍጥ ተመርኩዞ  ነው። በስልጣን ሽግግር ወቅት ሕዝብ የአስተዳደሩን ሥልጣንና ሃላፊነት ለሚያምንባቸው መሪዎች የሰጠበት ሁኔታ አልነበረም።
በአገራችን  ታሪክ መንግሥት ማለት በሕዝብ ላይ የተጫነ፤ የሥልጣን ልጓምን ጨብጦ ከቤተመንግሥት ተሰይሞ እንዳፈተተው የሚሠራ፤ ሲሻው የሚገድል፤ ሲያሰኘው የሚያሥርና የሚያግዝ፤ ከህዝብ ተነጥሎ የቆመ፤ የማይደፈረና የማይገሰሥ መለኮታዊ ሃይል ሆኖ ቆይቷል። እያንዳንዱ የአገዛዝ ሥርዓት የራሱ መለያ ጠባይ ያለው ቢሆንም በበትረ-ሥልጣን አያያዝና አጨባበጥ ላይ ግን ሁሉም ተመሳሳይነት አላቸው።
 በህዝብና በመንግሥት መሀል ያለው ግኑኝነት የጌታና የሎሌ ወይም የገዥና የተገዥ ነው ተብሎ በህግ የተደነገገ ይመሥል በአገራችን መንግሥትና ሕዝብ ለየቅል ሆነው በመቆየታችው ሀገሪቱ ዛሬም ከመከራና ማጥ፤ ከድቀትና ከችግር መላቀቅ አቅቷታል። የባስ እንጂ የተለወጠ ነገር የለም።
 የወያኔ አገዛዝ ከውልደቱ በዓቢይነት ወታደራዊ ሃይል ለሕዝብ የሚያስብና ለሕዝብ ጥቅም የቆመ ድርጀት ባለመሆኑ ህዝቡን በጠብ-መንጃና በጡንቻ ረገጦና ደፈጥጦ ለመግዛት ካለው በህሪ የተነሳ፤ የሀዝብን ለእልና ተቀብሎ፤ በህዝብ ወሳኝነትና የበላይነት አምኖ፤ የህዝብን ጥያቄ አስቀድሞ፤ ህዝብን በማግባባት ፤በማወያየትና በማስማማት ውሳኔ ከመሻት ይልቅ ጠብ-መንጃውን በመወዝወዝና ቃታን በመሳብ የህዝብን ዴሞክራሲያዊ መብቶች በማምከንና በመደምሰስ የሥልጣን እደሜውን ሲያራዝም የቆየ አሁንም በዚሁ የጥፋት ጎዳና እየነጎደ ያለ ጎጠኛ ቡድን ነው።
የኢትዮጵያ ሕዝብ ከባህሉ፤ ከልምዱ ፤ከሀይማኖቱ በመነሳት የእለተ ተእለት ኑሮውን በሠላም ለማካሄድና የሀሪቱን የኢኮኖሚ፤ የባህል፤ የፖለቲካ፤ ወዘተ… እድገት ሊያፋጥን የሚችል የግኑኝነት ዘይቤን ለመፍጥርና የራሱን መብቶችና የአስተዳደሩን ሥልጣን ለመወሰን የሚያስችሉ መብቶቹ  ተገፈዋል።
ወያኔ ለአገዛዙ የሚስማማውን እንዳሻው ትርጉም የሚሰጠውን ሕዝብ ያለመከረበትንና ያልተወያየበትን ሕገ-መንገሥት ተብየውን (የራሱን የፖቲካ ፐሮግራም) በአገሪቱ ላይ ደንግጓል።
ለአገዛዜ ይጠቅሙኛል ያላቸውን ሕጎችና ደንቦች አውጥቶ ነጋሪት አስደልቋል። በየጊዜው የሚነሳበትን የህዝብ ጥያቄና እመቢተኝነት ለማፈንና ለመጨፍለቅ ሲፈልግ በየጊዜው አዳዲስ ህጎችንና አዋጆችን እየፈበረከ፤   የሀገሪቱን ሉዓላዊነት አስደፍሮና የህዝብን የሥልጣን ባለቤትነት አልቀበል ብሎ ህዝቡን ለረሀብ፤ ለድንቁርና ለበሽታ ዳርጓል።
የወያኔን ያለፉ ታሪኮች ከደደቢት ወደአዲስ አባባ የተጓዘበትን አካሄድ ለጊዜው ብናልፈው እንኳን፤ አዲስ አበባ በገቡ እለት በተቃዋሚ ሠልፈኞች ላይ ያዘነቡትን የጥይት ሩምታ ምንጊዜም ሊረሳ የማይችል ፤የወያኔን ጭምብል ለኢትዮጵያ ህዝብ ፍንትው አድርጎ በአደባባይ ያሳየ መጥፎ ትዝታ ነው። በማከታተል በተደረጉ ሠላማዊ የተቃውሞ ሰልፎችም  አያሌ ኢትዮጵያዊያን በአሰቃቂ ሁኔታ ተገድለዋል፤ ታስረዋል፤ የሚወዷትን አገራቸውንና ቤተሰባቸውን ጥለው እንዲሰደዱ ተደርገዋል።  የኢትዮጵያ ሕዝብ ወያኔን መቃውም የጀመረው ዛሬ ሳይሆን ፤ ከዛሬ ሃያ አምስት (25) ዓምት በፊት የሚንሊክ ቤተመንግስትን ሳይቆጣጠር ለመሆኑ የህዝብ ትግል ታሪክ መዝግቦት ያለ ሀቅ ነው።
 በየጊዜው ከቤታችው በግድ በወያኔ የፅጥታ ሠራተኞችና ቅልብ ወታደሮች እየታፈኑ መሞታቸው ወይንም በህይወት መኖራችው  የማይታውቅ የንጹህን ዜጎች ወላጆችና ዘመዶች ምስክር ናቸው። በተቀረ ሌላውን ቤት ይቁጠረው  ከማለት በስተቀር በአሀዝ ማስቀመጥ አስችጋሪ ሆኗል። በግልጽ የሚታወቁ ፤ የፖለቲካና የህሊና እስረኞች እንዲፈቱ በሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶች በኩል በተደጋጋሚ ጥያቄ ቢቀርብም ወያኔ  “ዓይኔን ግንባር ያርገው “ “አንድም የፖለቲካ እሥረኛ በእጄ የለም ”  በማላት አብሮት የተወለደ ቅጥፈቱን ያዥጎደጎዳል።፡ዛሬም እንደትናትናው የሲቪክና የሙያ ማህበራት፤ የፖለቲካ ድርጀቶች አባላትና መሪዎች፤ ተማሪዎች፤አርሦአደሮችና ጋዜጤኞች እንዲሁም ግለስብ ተቃዋሚዎች ይታሰራሉ ፤ይገደላሉ ይታፈናሉ።  የወያኔ ባለሥልጣናትና ካድሬዎች ኪሳቸውን ያሳበጡበትንና ህዝቡን ያፈናቅሉበትን  የአዲስ አበባ ከተማን ማስተር ፕላን አስመልክቶ ከታህሳስ ወር 2008 ዓ.ም. መጀመሪያ ጀምሮ በተቀሰቀስው አሁንም ባላባራው  የህዝብ ተቃውሞ በመቶዎች የሚቆጠሩ ንፁሀን ዜጎችን ሲገድሉ ቁጥራችው በውል ያልታወቀ ዜጎች ለእስር ተዳርገዋል።
 በአዲሳበባ ዙሪያ የተቀሰቀሰውን የህዝብ እቢተኝነት በመደገፍ  የመብት ረገጣ ይቁም፤ የታሰሩ የፖለቲካና የህሊና እስረኞች ይፈቱ፤ ፍትህ ይሥፈን፤ አርሶአደሩ የመሬት ባለቤትነቱ ይረጋጋጥ በማለት  በአደባባይ በመሰለፍ ህዝባዊ ጥያቄ ያቀረቡትን የህብረተስብ ክፍሎች በአሰቃቂ ሁኔታ አጋዚ በተባለው ልዩ ሀይል በግፍ እንዲጭፈጭፉ አድርጓል። በየቦታውም የሰልፉ አስተባባሪዎች ናችው የሚላችውን ለይቶ በመልቀም እያስራበ፤እያስጠማ፤ አስቃቀ ስየል እየፈጸመባቸው ይገኛል። ነባር አስርቤቶች አልበቃ ብለውት አገዛዙ አዳዲስ የማሰቃያና ያማጎሪያ  ሥፍራዎችን በብዛት እየከፈተ ነው።
ወያኔ ከመቼውም  ይበልጥ በህዝብ በመጠላቱና ገበናው በመጋለጡ  የተነሳ የሚቃወመውንና የሚታገለውን ኢትዮጵያዊ ሁሉ ከማንገላታት አልፎ ከውልደቱ ጀምሮ የተካናበት ተቀናቃኞችን በአካል የማጽዳት እርምጃውን በሥውርና በአደባባይ ተግባራዊ አያደረግ ነው። የዚህ ሁሉ ሚስጥሩ ወያኔ ልዩነትን የማስተናገድ ባሀሪ የሌለው ጎጠኛ ድርጅት ከመሆኑም ሌላ ከላይ ለመጥቀስ እነደሞከረነው ከፖለቲካ ደርጀተነቱ ይልቅ በወታደራዊ ሃይሉ /በጡንቻው የሚተማማን ስብስብ በመሆኑ ጭምር ነው ።
ኢሕ አፓ ከትግል ታሪኩና ከተመክሮው በመነሳት ሥላልፉትም ሆነ ስለዛሬዎቹ አምባገነኖች ባሀሪ ሲያብራራ   “አምባገነኖች ለውስን ወቅት በተለየም በሥልጣን ኮርቻቸው ላይ እስኪደላደሉ ድረስ ዴሞክራሲያዊ መስለው መቅረባቸው ያዋጣል ብለው ፈራ ተባ እያሉ የሚሞክሩት ቢሆንም ዘለቂታ የለውም። ዋነኛው ባህሪያችው አፋኝነታችው በአጭር ጊዜ ፈጦና አግጦ ይመጣል። ልዋጥ ልሰልቅጥ ይላል። ነፃ መድርክ፤ ነፃ ውይይት፤ ሠላማዊ ተቃውሞ፤ ወዘተ… የሚባሉት ይከስማሉ። የተቹ ይታደናሉ። የተጋለጡ የታፈናሉ። የተቃወሙ ይመታሉ በደርጉም ታይቷል በወያኔም እየተደገም ነው” ሲል አስቀድሞ ያስጠነቀቀው።
የአምባገነኖችን በሥልጣን የመደላደል እቅድ በአጭር መቅጨት የሚቻለው ሕዝብ ሉዓላዊነቱን በገቢር ተረድቶ የሥልጣን ምንጭ እሱና እሱ ብቻ መሆኑን አውቆ እኔ ህጋዊነት ያልሰጥሁት መንግስት ሕገ-ወጥና  ፅረ- ሕዝብ ነው ብሎ አለማወላውል እስከቆመና መብቱን ለማስከበር እስከመጨረሻው ሲታግል ብቻ ነው።
የጎረቤት መብት ሲደፈር ያልተቃወመ ፤ የራሱ መብት ሲደፈር ጯሂም ድጋፊም እንደማያገኝ ግልፅ በመሆኑ  አምባገነኖችንና ጎጠኞችን መታገል የሚገባው ገና ከጥዋቱና ሁሉም በጋራ ነው። ነጥለው ሊመቱ ሲነሱ ተነጣጥሎ ላላመጥፋት በአንድነት መቋቋም ያሻል። የሕዝብ ሀያልነት ከህብረቱ የሚሰርፅ እንጂ ቁጥሩ በዝቶ ተነጣጥሎ በመቆሙ አይደለም። የብዙ ዓመታት የኢትዮጵያ ተማሪዎች ትግል ጨቋኞችን ሊያናጋ የቻለው ሕዝቡ ከዳር እሰከዳር አሻፈረኝ ብሎ በየካቲት በአንድነት ለመብቱ መከበር በመነሳቱ ነው። ይህ የተባበረና የጽኑ ትግል መንፈሥ ከየካቲት በሁላ በአስፈላጊው ስፋትና ጥንካሬ  ባለመቀጠሉ ደርግ ተቃዋሚዎቹን ሊጨፈጭፍና በመላው ህዝብ ላይ ፈላጭ ቆራጭ አገዛዙን ለማስፈን ቻለ። ሀገር አቀፍ ተቃውሞ በወቅቱ ተቀናብሮና ተጥናክሮ ባለመከሰቱ የነቁ የሕዝብ ወገኖች አታጋዮችና ቆራጥ ታጋዮች በድፍረት አገዛዙን ተጋፍጠው ተዋደቁ ። ትግሉም ከፍተኛ ጉዳት ደረሰበት። የዛሬዎቹም ጎጠኞች ሂደት ከምርጦቹ የተለይ አይደለም። የወያኔ ዋና ተልኮ ሀገርን መከፋፍል- መበታተን፤ ህዝብን ከህዝብ ማጋጨት ፤መዋሽት ወዘተ…  በመሆኑም የከፋፍለህ አጥፋ ፖሊሲው መረን የለቀቀ ነው።  ወያኔ ሕዝብን ርስ በርስ በብሔር፤ በሃይማኖት አላኩሷል። ድርጅቶች ቀፍቅፎ ድርጅቶችን ርስበርስ አጋጭቷል። ወያኔ ተጠያቂነቱ ለሕዝብ ሳይሆን ለባእዳን መሆኑ አያከራክርም።
የኢተዮጵያ ሕዝብ  ለዘመናት የታገለላቸው ሕይውቱን የገበረላችው መሰረታዊ ጥያቂዎች ዛሬም ምላሽን አላገኙም። ወያኔና የወያኔ የጡት አባቶቹ “በኢትዮጵያ ሰላምና ዴሞክራሲ ሰፍኗል፤ አገሪቱም በእድገትና ትራንስፎርሜሽን ጎዳና  እየተመዘገዝገች ነው”  ሲሉ ያሾፉብናል። እውነታውን ግን ከዚህ የተለይ ነው ። “ግመል ሰርቆ አጎንብሶ አንዲሉ “ ወያኔም  ሆነ ባእዳኑ  ሊደበቁት የማይቸሉበት ደረጃ ላይ በመድረሱ በአጋራችን ዛሬ  በችጋር/በረሀብ የሚጠበሰው ህዝብ ብዛት ከሃያ ሚሊዮን በላይ ከመደረሱም ሌላ፤  በአገራችን አራቱም መእዘናት የህዝብ እርቢትኝነት ከአጥናፍ እስከአጥናፍ ተስተጋብቷል ።  ሰላም ጠፍቷል። ሽበር ነግሷል። የተጭቆነና መብቱ የተረገጠ ሕዝብ ይዋል ይደር እንጂ  እንቢኝ ማለቱ አይቅሬ ነው። ከተማሪው እንቅስቃሴ ጀምሮ እሰከ ፖለቲካ ፓርቲዎች ድረስ በአብይነት የተስትጋባው የመሬት ላራሹ መፈከር ዛሬም መላሽና ምላሽ አላገኘም።
መሬት ላራሹ በሚል የተጠቃለልው መፈክር በዋናነት የአርሶ-አደሩን ከብዝበዛ መውጣት ባለሙሉ መብት መሆንን፤ በሀገሪቱ የፖቲካ ማሀበራዊና ኢኮኖሚያዊ ድርሻ መጎናፅፉንና ሚና መጫወቱን የሚመለከት ነው። ዛሬም እንደትናቱ የኢትዮጵያ አርሶአደር የአምባገነኖችና የጎጠኞች መጫወቻ እነደሆነ አለ። ይበዘበዛል ፤  ከመሬቱ ይፈናቀላል። በክልል ፖለቲካም የታመሳል።በወያኔ ካድሬዎች ይረገጣል ። “ለአርሶአደሩ ተዋጉለት አትሽሹ” የሚለው የቀደሞ የኢትዮጵያ ወጣቶች የትል መፈክር ዛሬም ወቅታዊንውቱን እንደተላበስ ይገኛል።
ላብ አደሩ የምርቱ ተጠቃሚ ይሁን ፤አይበዝበዝ ፤አይዋረድ፤ አይሰቃይ በነጻ የመደራጀትና የመታገል መብቱ ይከበርለት፤ የሚለው ጥያቄ ዛሬም የትግሉ አብይ ጥያቄ ነው። የኢትዮጵያ ላብ አደሮች ወያኔና ባላሀብት ባእዳን በሚወስኑበት ጋጠ-ወጥ የኢኮኖሚ ፖሊስ የተነሳ ለመከራና ለሥራ አጥነት ተዳርጓል። ሲሻቸው እንደ አረጀ ቁና ያለምንም ካሳ ከሥራ ገበታው ላይ ያባርሩታል።
ዛሬ የኢትዮጵያ መምህራኖችም ሆኑ የመንግሥት ሠራተኞች እጣ ፍንታ  ከላብ አደሩ ሁኔት ብዙም የተለ አይደለም ። በማሀበር የመደረጀት፤ የኑሮ ዋሰትናን የደሞዝ ጭማሪን መጠየቅ አይችሉም።   እነዚህ የህበረትስብ ክፍሎች በነጻ የመደራጀት መበታችው ተገፎ በባርነት ቀንበር ሥረ ወድቀዋል ።
 የአማኞች የእመነት ነፃናትና መብት አልተከበረም። ወያኔ በሃይማኖት ተቋማት ውስጥ ካድሬዎቹን በማሰረግ ያተራምሳል፤ በሃይማኖች መካካል ቅራኔና ግጭት በማስፋት መከባብር እንዳይኖር ጥላቻና ፍራቻን ሆን ብሎ ያሰጭራል። ሲያሰኘው ምአእመኑና ጁማው በተሰበስብስብት አብያተከርስቲያትና መስጊዶች ወታደሮቹን  ባማሳማራት  በህዝብ ላይ ጉዳት ያደርሳል።
በአጭሩ ወያኔ የኢትዮጵያን ሕዝብ መከራና ሥቃይ አባባስ፤ አፋፋመ፤ አጠናክረ አንጂ አልቀነስም ። የኢትዮጵያንና የሕዝቧን መብት ለማስከበር ከተፈለገተደራጀቶ መታገል የግድ መሆኑን ኢሕአፓ አሁንም በአጽናኦት ለመግለጽ ይወዳል ።
ትናትና ለሀገርና ለወገን ሲሉ ሰማእታት የሆኑት ዜጎች ደም  ይጣራል ። ደማችን የፈሰሰላችው የሕዝብ ጥያቄዎች ገና ምላሽ አላገኙም ይላል።ትግሉ መቀጠል ያለበትም ለዚህ ነው። ዛሬ ከትላንት አልተሻለም። አለተለወጠም። የሕዝብ እንባ ተበራከተ እንጂ አላቆመም። አገራችን ለባእዳን ተገዥ ሆነች እንጂ፤ ለውርደት ተጋለጥች አንጂ፤ ሉዓላዊነቷ ተደፈር እንጂ፤ አልተከበረም።

በአጭሩ የሕዝብ ጥያቄዎች ዛሬም አልተመለሱም ብዝበዛውና ጭቆናው ተጠናክሮ ቀጥሏል። ዛሬም  እንድትናትናው ጨቋኞችን፤ ጎጠኞችንና አምባገነኖችን  በሁሉም መንገድ አምርረን መታገል እንዳለብን ይታያል። ትግላችን ለምን ለሚለው መልሱ ግልጥ ነው። ትግላችን እንዴት? ለሚለው ምላሹ ምስጢር አይደለም።ዛሬ ከትናት አልተለወጠም። ቢከፋ እንጂ ።

No comments:

Post a Comment