Monday, February 15, 2016

ሳምንታዊው የፍኖተ ፍካሬ ዜና ። የካቲት 6 ቀን 2008 ዓ.ም


ፍካሬ ዜና
page1image1384
የካቲት 6 ቀን 2008 .
page1image2152
  •   ከመጽሃፍት ዓለም ያለው ሁኔታ ግልጽ አድርጎ የሚሳየው ወያኔ በተጧጧፈ ደረጃ የኢትዮጵያን ታሪክ በሀሰት ትረካ ለማጨናነቅ ያለውን ትኩረት የሚያረጋጋጥ ነው ሲሉ ታዛቢዎች ትችታቸውን አቅርበዋል። በዓመት ቢያንስ አራት አምስት ጸረ-ኢሕአፓ መጽሐፍ ተብዬዎች በወያኔ ተባባሪነት ይወጣሉ በተባለው መሠረት ሐረግ ሬሳ ሆነው በድርጅቱ ላይ ከፍተኛ ጉዳት/አደጋ ያደረሱትን የደርግ ጊዜ አንጃዎች ዛፍ ብሎ የሚያቆላጵስና የሚያዳንቅ ጽሁፍ ለገበያ በአዲስ አበባ ቀርቧል። በተጨማሪ በአረመኔው መንግስቱ የተጻፈውና የገደላቸውን ጄኔራሎች ታሪክ የሚያንቋሽሽ ሁለተኛው ቅጽም በአዲስ አበባ እየታተመ ነው። ወያኔ ታሪክን ለማርከስ የማይጠቀመው መንገድ የለም።
  •   ኃይሌ ገብረ ሥላሴ የሚባል ታዋቂ ሯጭ ኢትዮጵያ ማፍራቷ የሚታወቅ ሲሆን ይህ ግለሰብ ግን በፖለቲካው መስክ ቀባጣሪና መሀይም መሆኑ መጋለጥ የጀመረው ትንሽ ቆየት ብሏል ሲሉ ታዛቢዎች ዘግበዋል። አጼ ኃይለሥላሴ ከእግሩ ሲፈጥን ከወደ ጭንቅላቱ ደከም ይላልብለዋል አሉ በሚል ሲወቀሱ ቢቆይም ለዚህ ሯጭ ግን ንግግራቸው ትክክል ነው ቢባል ስህተት አይሆንም። ይህ ሯጭ በአሸናፊነት ብዙ መቶ ሚሊዮን ዶላር ስላገኘ፤ ስለከበረ፤ ከድህነት ወደ ሀብት ስለተሸጋገረ በአላዋቂ ዕብሪት ተወጥሮ አንዴም ለኢትዮጵያ ፕሬዚዳንት ልሁን ሲል ሌላም ጊዜ ደግሞ የኢትዮጵያ ሕዝብ ሰነፍ ነው ሲል የተደመጠ ሲሆን አሁን ደግሞ አወቅሽ አወቅሽ ቢሏት ቅዱስ መጽሃፍ አጠበች ሆኖበት ለአፍሪካ ዴሞክራሲ አያስፈልጋትም ሲል በይፋ ቀባጥሯል። በፖለቲካ ዘው ማለት የማይገባው ይህ አላዋቂ ሯጭ ለሀገር የሚያስፈልገው ጎበዝ መሪ እንጂ ዴሞክራሲ አይደለም በሚል አላዋቂነቱንም አጋልጧል። ሀፍረተ ቢሱ የሆነው ኃይሌ የወያኔና በተለይም የመለስ ዜናዊ አድናቂና ተማሪ መሆኑን ያጋለጠ ስለሆነ ይህ የሰሞኑ ልፈፋው የሚገርም አይደለም ያሉ ታዛቢዎች በኃይሌ የንግድ ተቋሞች ላይ ዜጎች ማዕቀብ ማድረጋቸው ጊዜው ነው ብለዋል።
  •   ሳውዲ አረቢያ አሁንም መካን እንዲሆኑ የተደረጉ ባርያዎችን እንደምትሸጥ ተጋለጠ። የዓለም አቀፍ መከራ ዋና ምንጭ የሆነችው ሳውዲ አረቢያ ባርያ የምትላቸውን ወደ መካከለኛው ምሥራቅ ሀገሮች ትሸጣለች በሚል ክስ እየቀረበባት ነው። በሳውዲ አረቢያ ብዙ ሺ ኢትዮጵያውያን በዘመናዊ ባርነት ደረጃ ግፍ እየደረሳባችው መሆኑ ይታወቃል።
  •   ጉድ አይሰማ ጆሮ የጭቆናና መጥፎ አገዛዝ ምሳሌ የሆነቸው የተባበሩት የአረብ ኤሚሬት የደስታ ሚኒስትር በሚል ሾማለች፤ ሚኒስቴርም አቋቁማለች። የተሰጠው ሥራ ሕዝብ ደስተኛ መሆኑን ማረጋጋጥ ሲሆን ሕዝብን ደስተኛ የሚያደርግ እርምጃ ለመስወድ ግን የተሰጠው ሥልጣን የለም።
  •   በይፋ በወያኔና በምዕራቦች በምስጢር የምትደገፈው ሶማሊላንድ በሰሞኑ 13 ኢትዮጵያውያን ስደተኞችን ለወያኔ ማስረከቧን ማወቅ ተችሏል። ወደ ወያኔ ከተሰጡት ስደተኞች መሀል ዘጠኙ ወንዶች ሲሆኑ አራቱ ሴቶች መሆናቸውን የገለጡት ምንጮች ሁሉም ከ35 ዓመት ዕድሜ በላይ አለመሆናቸውን ገልጠዋል ።
ርሀቡ ተገቢውን ትኩረት እንዳላገኘ ተነገረ፡፡
ወያኔ ርሀቡን ለፖለቲካ ተረፌታ ለማዋል ደፋ ቀና ቢልም ርሀቡ እየገሰገሰ በመሆኑ ለኪሳራ እንደዳረገው ይታወቃል፡፡ ወያኔ የዛሬ አራት ወር አካባቢ በድርቁ ሳቢያ ከብቶች በየመንገዱ ተፈንግለው እንደሚታዩና ርሀቡ አስከፊና አስፈሪ እንደሆነ የዓይን እማኞች ሲገልጹ፤ የወያኔ ጠቅላይ ሚንስትር ተብዬውን ጨምሮ ቱባ ቱባ ካ ድ ሬ ዎ ቹ የዘረኛ ፖለቲካቸውን ጭምብል ለማስጠበቅ ርሀብ እንደሌለና የተከሰተው የዝናብ እጥረትም ከቁጥጥራቸው ሊወጣ እንደማይችል በገለጹ ማግስት የዓለም አቀፍ ለጋሾች ላይ ምሬታቸውን መግለጽ ጀመሩ፡፡ በየአስራ አምስት ቀናት ስንዴ ከውጪ ለመግዛት እያሉ የሚያሰራጩት ባዶ ወሬ እንደሆነና ምንም የተጨበጠ ነገር እንደሌለ ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው ወገኖች ይገልጻሉ፡፡ ወያኔዎች በየአመቱ የሀገር ውስጥ የስንዴ ምርት በእጅጉ ከሕዝቡ ፍላጎት በታች በመሆኑ ከውጪ በተለይ ከደቡብ አፍሪካ እየሸመቱ እንደሚያመጡ እየታወቀ ከክምችት ለተረጂው ሕዝብ እንዳቀረቡ አድርገው የሚለፍፉት ሁሉ ከእውነት የራቀ መሆኑ ሊሳት አይገባውም፡፡ ወያኔ አስቀድሞ እርዳታ እንዳቀረበ አድርጎ የሚያወራው ለመንታ ጥቅም እንሆነ ጉዳዩን በቅርብ የሚያውቁ ያስረዳሉ፡፡ በየጊዜው ርሀቡ አድማሱን እያሰፋ መሄድ ላይ መሆኑ እየተገለጸ መሆኑ የሚታወቅ ነው፡፡ በጥር ወር ወትሮውንም ተገቢ ትኩረት የተነፈገው የሰሜን ሸዋ የቀወት፣ የአንኮበር፣ የገምዛና የፉርሲ ርሀብ እያገጠጠ መጥቶ ከብቶች መፍጀት እንደጀመረ ከሚደርሱን ዘገባዎች መረዳት ተችሏል፡፡ ሕዝቡ ቢቸግረው የተረፉ ከብቶቹን እየነዳ ከተማ በመውሰድ የወያኔ ሹሞች እንዲታደጉት ቢማጠንም ያገኘው ምላሽ የ15 ኪሎ ግራም ስንዴ እርዳታ ብቻ ነው፡፡ ይህችን ገበሬው ባለው ጊዜ በቀን ሁለቴ ንፍሮ ተቀቅላ የምታልቅ እንደሆነ አካባቢውን በውል የሚያውቁ ይገልጻሉ፡፡
ጋምቤላ በአጋዓዚ ጦር ስር ወደቀች፡፡
ብዙ የፖለቲካ ተንታኞች እንደሚሉት ጋምቤላ የትግራይ አዋሳኝ ብትሆን ኖሮ ወያኔ እስካሁን የትግራይ ግዛት ያደርጋት እንደነበር ነው፡፡ በአሁኑ ሰዓት ጋምቤላ ሙሉ በሙሉ በአጋዓዚና በፌደራል ፖሊስ ቁጥጥር ስር ወድቃለች፡፡ ይህ በይፋ የተነገረ ሲሆን ቀደም ብሎም በሞግዚትነት ስም ጋምቤላን በቁጥጥሩ አድርጎ የነበረው ወያኔ ህወሀት እንደሆነ የታወቀ ነው፡፡ አኝዋክና ኑዌርን እርስ በእርስ የሚያጋጨው ወያኔ መሆኑን የጋምቤላ ኗሪዎች ያስረዳሉ፡፡ በጋምቤላ የብዙ ንጹሀን ደምን በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ የወያኔው አጋዓዚ ጦር አፍስሷል፡፡ በዚህ ግጭት ከጥር 19 ቀን አንስቶ እስካሁን የሞቱ ሰዎች ቁጥር በትክክል ባይታወቅም ከመቶ በላይ ሊሆን እንደሚችል የሚስረዱ አሉ፡፡ በአሁኑ ሰዓት ጋምቤላ ባልታወጀ የጦርነት ቀጠና ውስጥ ትገኛለች፡፡ እስካሁን ትምህርት ቤቶችና የመንግሥት መሥሪያ ቤቶች እንደተዘጉ ነው፡፡ ይህ ወያኔ እያደረሰ ያለው ግፍ የነጮች አገዛዝ በደቡብ አፍሪካ ያደርሰው ከነበረው ጋር ግጥም ያለ ተመሳሳይነት እንዳለው የሚያስረዱ የፖለቲካ ተንታኞች ቁጥር ጥቂት አይደለም፡፡ የጋምቤላን ሕዝብ ትጥቅ የማስፈታት ዘመቻን ብዙዎች እንደሚሉት አሳን ከባሕር እንደመልቀም ከባድና አዳጋች መሆኑን ያስረዳሉ፡፡ ወያኔ እራሱ ለጋምቤላ ልዩ የጸጥታ ኃይል ያስታጠቀውን እንኳ መሰብሰብ አስቸጋሪ ሆኗል፡፡ አብዛኛው መሣሪያ ከደቡብ ሱዳን በገፍ ስለሚገባ በአካባቢው መሣሪያ እንደ ዱላ ከሆነ መክረሙ የታወቀ ነው፡፡ ይህ በእንዲህ እንዳለ ከአካባቢው ምንጮች በተገኘው መረጃ በጋምቤላ ከተማ ከፍተኛ የደቡብ ሱዳን መኮንኖች መያዛቸው ታውቋል፡፡ ከተያዙት የደቡብ ሱዳን ከፍተኛ መኮንኖች ሌተናል ጄነራል ቶማስ ማቦር ዶል፣ ሌተናል ጄነራል ዶ/ር ማንጁር ጋንትሉክና ሌሎች በርካታ የበታች ሹሞችና ተራ ወታደሮች እንደሚገኙበት ለማወቅ ተችሏል፡፡
page2image20616 page2image20776
ወያኔ መኢአድንና ሰማያዊፓርቲን እያመሰ እንደሆነ ተገለጸ፡፡
ወያኔ የሰማያዊ ፓርቲንና የመኢአድን እየበጠበጠ መሆኑን ከሚወጡ መረጃዎች መገንዘብ ተችሏል፡፡ የሰማያዊ ፓርቲ ከውጪ ከደጋፊዎች የሚላከው ገንዘብ የአመራር አባላቱ ለየግላቸው እንዳዋሉት ውስጥ ውስጡን ሲብላላ በመጣ አለመተማመን በፈጠሩት ሁለት ጎራ ላይ ተከፋፍለው መነዛነዝ ከጀመሩ ከወር በላይ እየሆነ ነው፡፡ በዚህ ሳቢያ ዋናው ጉዳይ ሕዝባዊ ትግሉ ውሀ ሊቸለስበት ችሏል፡፡ በተመሳሳይም መኢአድ በፕሬዚደንቱና በምክትል ፕሬዚደንቱ በሚመሩ ሁለት አንጃዎች ተከፍሎ እየተነታረኩ መሆኑን ከሚወጡ መረጃዎች ተገንዝበናል፡፡ በርካታ የፖለቲካ ተንታኞች እንደሚያስረዱት በቅርቡ ወያኔ አዳዲስ ፓርቲዎች እንዲቋቋሙ ያደርግና እንደ ልማዱ የህዝቡን የትግል ስሜት ወደ ተቋቋሙት ድርጅቶች ይወስድና ህዝባዊ ትግሉን ያሽመደምደዋል፡፡ ወያኔ ለእንዲህ ዓይነቱ እኩይ ተግባር ድርጅቶች ውስጥ ሰርጎ በመግባት ህልውና የሚያናጉ በከፍተኛ ወጪ የሰለጠኑ የደህንነት ሠራተኞቹንና ካድሬዎቹን እንደሚያሰማራ የታወቀ ነው፡፡
ወያኔ አንዳንድ ዳኛዎችን ከኃላፊነታቸው ማሰናበቱን ቀጠለ፡፡
የወያኔ ፓርላማ ጥር 28 ቀን 2008 .. 2006 .ም ጀምሮ በፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት እንዲያገለግሉ በዳኝነት በፓርላማው ተሹመው ሲያገለግሉ የነበሩት ዳኛ አቶ ግዛቸው ምትኩ ለወያኔ ህገ-መንግሥት ታማኝ አልሆኑም ተብለው መሻራቸው ታወቀ፡፡ ዳኛ ግዛቸው ከተወነጀሉባቸው ጉዳዮች ውስጥ ዳኛ ህገ-መንግሥቱ ላይ ልዩነት ቢኖረውም በዳኝነቱ ግን መቀጠል እንደሚችልና የወያኔ ህገ-መንግሥትም በርካታ ሳንካዎች እንዳሉትና መስተካከል እንደሚገባቸው በተለያዩ ወቅቶች ሀሳባቸውን ይሰነዝሩ እንደነበር ተጠቅሷል፡፡ በተጨማሪም ወያኔ ሆን ብሎ ኢትዮጵያ የዓለም አቀፍ የወንጀል ፍርድ ቤት አባል እንዳትሆን ያደረገው የወያኔ ከፍተኛ ባለሥልጣናት ውሎ አድሮ ተከሳሽ ስለሚሆኑ እንደሆነ በቀጥታና በተዘዋዋሪ ሁኔታ እገለጹ እንደሆነ ለመረዳት ተችሏል፡፡ ወያኔ በየጊዜው የተማሩ ሰዎችን ከተጠቀመባቸው በኋላ በፈጠራ ውንጀላ እንደሚሽራቸውና ከሥራ እንደሚያሰናብታቸው የታወቀ ነው፡፡
የፖለቲካ እስረኞች በህይወታቸው ላይ የሞት አደጋ እያንዣበበ እንደሆነ ታወቀ፡፡
ወያኔ የፖለቲካ ተቃዋሚዎቹን እያደነ በማሰርና በማሰቃየት ከቻይና ቀጥሎ ከሚገኙት አረመኔ መንግሥታት አንዱ መሆኑ በተለያዩ ጊዜያት በዓለም አቀፍ የሰብዓዊ ተቋማት የተገለጸ ነው፡፡ ወያኔ ለይስሙላ የፖለቲካ እስረኞችን ፍርድ ቤት ቢያቀርብም ሕግ ማለት ወያኔ ህወሓት በመሆኑ ሁሌም የሚሰጠው ውሳኔ የፖለቲካ እንጂ የሕግ አለመሆኑ በአደባባይ የታየና የታወቀ ነው፡፡ የፖለቲካ እስረኞችን ከማዕከላዊ ምርመራ በተጨማሪ በቃሊቲና በቅሊንጦ እስር ቤቶች ከባድ ስቃይ ይፈጸምባቸዋል፡፡ ወያኔ ከከሰሳቸው የፈጠራ የሽብር ክስ ምንም መከራከር ሳይስፈልጋቸው የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በነጻ ቢያሰናብታቸውም የወያኔ የፖለቲካ ውሳኔ በይግባኝ ስም እንዲታሰሩ ማድረጉ የሚታወስ ነው። እነዚህ የፖለቲካ አመራሮች በህይወታቸው ላይ የሞት አደጋ እያዣበበ መሆኑን ለፍርድ ቤት አቤቱታቸውን አሰሙ፡፡ በግፍ ከታሰሩት የአንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ አመራር አባል የነበሩት አቶ ዳንኤል ሺበሺ፣ የአረና ፓርቲ አመራር አባል የነበሩት አቶ አብርሀ ደስታ፣ የሰማያዊ ፓርቲ አመራር አባል የነበሩት አቶ የሺዋስ አሰፋ የካቲት 1 ቀን 2008 .. ለቀረቡበት ችሎት የታሰሩት ብቻ ብቻቸውን በኮንቴይነር ውስጥ እንደሆነና ግለቱና ቅዝቃዜው ጤናቸውን እዳወከ የገለጹ ሲሆን፣ ከቤተሰብ ምግብ እንዳይገባለቸውና ከዘመድ
page3image19144 page3image19304 page3image19464
ወዳጆቻቸው ጋርም መገናኘት እንዳይችሉ መደረጋቸውን በመጥቀስ ለፍርድ ቤቱ አቤቱታቸውን አቅርበዋል፡፡ ከዚህ በተጨማሪም የኢትዮጵያ ብሔራዊ አንድነት ፓርቲ ሊቀ-መንበር አቶ ዘሪሁን ገ/እግዚአብሔርና ሌሎች ስማቸው ያልታወቀ ሙስሊሞች ቀዝቃዛና ጨለማ ኮንቴይነር ውስጥ ታስረው እንደሚገኙ ከቃሊቲ እስር ቤት ከሚገኙ ምንጮች ተረድተናል፡፡ በተያያዘ ዜናም የነገረ-ኢትዮጵያዋና አዘጋጅ ጋዜጠኛ ጌታቸው ሽፈራው ከጠበቃ ጋር እንዳይገናኝ መከልከሉን ለማወቅ ተችሏል፡፡ በቅርቡ ከአዲስ አበባ የቆዳ ስፋት ጋር በተያያዘ በተቀሰቀሰው ሕዝባዊ አመጽ ሳቢያ ከተለያዩ አካባቢዎች ተይዘውና ታፍነው የመጡ እስረኞች በማእከላዊ የማሰቃያ እስር ቤትና በስውር እስር ቤቶች እጅግ ዘግናኝ የሆነ ስየል እየተፈጸመባቸው እንደሆነ ከፖሊሶች የተገኘው መረጃ ያስረዳል፡፡
በአዲስ አበባ የታክሲ ታሪፍ ጭማሪ ሊደረግ መሆኑ ታወቀ፡፡
የዓለም የነዳጅ ዋጋ እየወረደ ባለበት የአዲስ አበባ የሚኒ ባስ ባለ ንብረቶች ማህበር የታሪፍ የጭማሪ ማስተካከያ እንዲደረግ የአዲስ አበባ የትራንስፖርት ዘርፍን እያሳሰበ እንደሚገኝ ታወቀ፡፡ የታክሲ ባለንብረቶች ማህበር አመራሮች እንደሚያስረዱት የመኪናዎቹ መለዋወጫዎች፣ ጎማና ቅባቶች ከመቶ እጅ በላይ በመጨመራቸው አሁን ባለው ታሪፍ ለመሥራት እንደማይቻል ይገልጻሉ፡፡ ከአዲስ አበባ ትራስፖርት ቢሮ ውስጥ አዋቂዎች መረዳት እንደተቻለው የተጠየቀው አግባብ ያለው በመሆኑ ተገቢ የሆነ የታሪፍ ማስተካከያ ማለትም የታሪፍ ጭማሪ በቅርቡ ይፋ እንደሚደረግ ለማወቅ ተችሏል፡፡ ሕዝቡ ከእጅ ወደ አፍ ከሆነ ኑሮ ባነሰ በነፍስ ውጪ በነፍስ ግቢ ስቃይ ውስጥ እያለ ይህ የታክሲ ታሪፍ ጭማሪ በቁስል ላይ እንጨት እንደ መሰቅሰቅ ይቆጠራል የሚሉ ብዙ ናቸው፡
የወልቃይት ጠገዴ ሕዝብ ተወካዮች የሕዝቡን ጥያቄ ለወያኔ ፓርላማ አቀረቡ፡፡
ወደ አዲስ አበባ እንዳይገቡ ጫንጮ ከተማ ላይ ታግተው የቆዩት የወልቃይት፣ የቃፍታ፣ የሁመራና የዳንሻ ሕዝብ ሰማንያ ተወካዮች ለፓርላማ የማንነት ጥያቄያቸውን ባቀረቡበት ወቅት ለግማሽ ቀን በማእከላዊ እስር ቤት መታሰራቸው ታወቀ፡፡ የተወሰኑ ወኪሎች ጥያቄያቸውን ለማቅረብ ወደ ፓርላማ እንደገቡ ቀሪዎቹን ትግሬ የሆኑ የፌደራል ፖሊስ አባላት በአሸባሪነት እንደሚጠረጥሯቸው በመንገር እንዳሰሯቸው ያስረዳሉ፡፡ ወደ ውስጥ ገብተው የነበሩትም ሲወጡ እንደታሰሩ ለማወቅ ተችሏል፡፡ ምንም ወያኔ እንደፈለገው ቢያስፈራራቸውም የሕዝቡን ጥያቄ ከማቅረብ ወደ ኋላ እንዳላሉና እስከመጨረሻውም እንደሚገፉ በምሬት ያስረዳሉ፡፡
የጉጂ ሕዝብ አመጽ ወያኔንና ሸሪኮቹን አሸበረ፡፡
አላሙዲን ከወያኔ ከፍተኛ ባለሥልጣናት ጋር በመሆን የሀገሪቱን ማእድን እየመዘበረ ይገኛል፡፡ እስከዛሬ በሕግ የተደነገገውን ለብሔራዊ ባንክ ማስገባት ያለበትን አርባ ከመቶ ሮያሊቲ እያስገባ አለመሆኑ የታወቀ ነው፡፡ በዚህ አረመኔ ሰው ድርጅቶች ላይ በየቦታው ሠራተኞቹ በተለይና ሕዝቡ በአጠቃላይ ጥርስ እየነከሰበት እንደሆነ የሚታወቅ ነው፡፡ በዚህ ሳምንት፣ ውስጥ ውስጡን ተዳፍኖ ሲጤስ የነበረውን ብሶቱን የጉጂ ሕዝብ የሚዘረፍ ሀብቱን ለማስከበር ማመጽ ጀምሯል፡፡ ጉጂ እየተመዘበረ አላሙዲና ወያኔዎች እየከበሩ ነው፡፡ ይህን በመቃወም ሕዝቡ በአንድ ላይ ተነስቶ እያመጸ ነው፡፡ በዚህ ሳቢያ ወያኔ በርካታ ሰዎችን እያሰረ መሆኑን ተረድተናል፡፡ ይህ ሁኔታ በወለጋ ደንቢና በሌሎችም የሕዝብ አመጽ ሊቀሰቀስ እንደሚችል ብዙዎች ያስረዳሉ፡፡
page4image18688 page4image18848 page4image19008
ኢሕአፓ ለፍኖተ ዴሞክራሲ ባስተላለፈው መልዕክት የመታወቂያ ሰነዱን ችግር አሳሰበ
page5image1168
ወያኔ ሕዝብን ለመከፋፈልና ለማጫረስ ባለው የቆየ ዕቅድ መሰረት የመታወቂያ ሰነድ በሚለው ላይ የእያንዳንዱ ዜጋ ኢትዮጵያዊ ሳይሆን ብሄረሰብ ምንጩ (አማራ፣ ኦሮሞ፣ ክልል 1፣ ትግሬ፣.ጉራጌ፣ ሶማሌ፣ ... ወዘተ) በሚል መመዝገቡ
በራሱ ለነዚሀ የሞት፣ ዕልቂትና ፍጅት መሰረት የሚሆን ነው ተባለ። ቀደም በሩዋንዳ የነበረው አገዛዝ ይህን ዓይነት ምዝገባ ሁቱ ቱትሲ በሚል የመታወቂያ ሰነድ ሰጥቶ ፍጅት ሲጀምር መታወቂያ እየጠየቀ ቱትሲ ያለውን እንደፈጀ የሚታወቅ ነው ያሉ ታዛቢዎች ወያኔ ነገ ወደ ፍጅት ሲያመራ ይህን መታወቂያ እንደ ሞት ፍርድ ሰነድ የሚጠቀምበት ነው ብለዋል። በዚሁም መሰረት ሁኔታው ከተለወጠ ክልል አንድ ትግሬ ወይም ሐራሪ የሚለውም መታወቂያ ለራስ ዕልቂት ጠሪ ይሆናል ብለው አሳስበዋል ። ይህን ሁሉ በማጤንና በተመለከተ ኢሕአፓ ባስተላላፈው መልዕክት ከሕዝባዊ አመጽ ጋር በተያያዘ መንፈስ ዜጎች በጋራ ይህን መታወቂያ የማቃጠል እርምጃ እንዲወስዱ ጠርቷል፡፡ በሌሎች ሀገሮች እንደታየው ሁሉ ይህን የአመጽ እርምጃ አስፈላጊ ነው የሚሉ ሌሎች ክፍሎችም ኢትዮጵያዊ የሚለው ቀርቶ በብሔረሰብ መፈረጁ ዜጎችን ለይተውና አውቀው ለፍጅት ሊያዘጋጁ እንጂ ለሀገር ቅንጣትም ጥቅም የለውም ያሉት ታዛቢዎች ያቀረቡቱን ማሳስቢያ ኢሕአፓ ቦታ ሰጥቶ የወያኔን መታወቂያ ሰነድ ተቃውሞ ማመጽ ያስፈልጋል የሚለውን ጥሪ አስተላልፏል።
ሴቭ ዘቺልደረን 245 ሚሊዮን ዶላር እርዳታ ያስፈልጋል አለ
በተባበሩት መንግስታት ድርጅት ስር የሚገኘውና ህጻናትን እናድን (ሴቭ ዘ ቺልድረን) የተባለው ተቋም ትናንት የካቲት 1 ቀን 2008 ዓም በሰጠው መግለጫ በሚቀጥሉት ሶስት ሳምንታት በኢትዮጵያ ለገባው ድርቅና ረሃብ 245 ሚሊዮን ዶላር እርዳታ ካልተገኘ ከሚያዚያ ወር ጀምሮ የረሃቡ ሁኔታ አደገኛ ሁኔታ ውስጥ ሊወድቅ እንደሚችል አስታውቋል። በአሁኑ ወቅት በምግብ እጥረት የተጠቁ ከ400 ሺ በላይ የሆኑ ህጻናት ተጨማሪ አልሚ ምግቦች የሚያስፈልጋቸው መሆኑንና ባጠቃላይ 1.7 ሚሊዮን የሚሆኑ ሴቶችና ህጻናት በከፍተኛ የምግብ እጥረት ሊጠቁ እንደሚችሉ ገልጿል። የድርጅቱ የኢትዮጵያ ቅርጫፍ ዋና ዳይሬክተር በጉዳዩ ላይ ተጨማሪ ማብራሪያ ሲሰጡ ከረጅዎች የተባለው እርዳታ ካልመጣ አሁን ያለው የምግብ ክምችት በሚቀጥለው ሚያዚያ ወር ላይ ሊገባደድ የሚችል መሆኑን ገልጸው ከግንቦት በኋላ ባሉት ወራት ከፍተኛ ችግር ሊከሰት እንደሚችል ተናግረዋል። እህሉ ከውጭ ተሸምቶ ወደ አገር ውስጥ እስኪገባ ድረስ የሶስትና የአራት ወራት ጊዜ ስለሚያስፈልግ በሚቀጥሉት ሶስት ሳምንታት የተጠቀሰውን እርዳታ ማግኘት ወሳኝ ነው ብለዋል። በደቡብ ኢትዮጵያ ብቻ ወደ 20 ሚሊዮን የሚጠጉ ኢትዮጵያውያን በረሃቡ የተጠቁ መሆናቸውን አንዳንድ ምንጮች የገለጹ ሲሆን በአሁኑ ጊዜ አስቸኳይ እርዳታ እየተሰጣችው የሚገኙት ዜጎች ብዛት 10.2 ሚሊዮን ደርሷል ተብሏል። ባጠቃላይ በዚህ ዓመት የድርቁና የረሃቡን ችግር ለመቋቋም 1.4 ቢሊዮን ዶላር ያስፈልጋል የተባለ ሲሆን እስካሁን በእርዳታ ሰጭ ድርጅቶች የተሰበበው 680 ዶላር ብቻ መሆኑ ተዘግቧል።

በተለያዩ ቦታዎች በደረሰው የትራንስፖርት መኪና አደጋ በርካታ ዜጎችተጎዱ
በዚህ ሳምንት በአርሲና በወሎ በሕዝብ ማመላለሻ መኪኖች ላይ በደረሰው አደጋ በርከታ ሰዎች መሞታቸውና መጎዳታቸው ታውቋል። ጥር 30 ቀን 2008 ዓም በአርሲ ጎለልቻ በተባለው አካባቢ አንድ አይሱዙ የህዝብ ትራንስፖርት መኪና ሁለት መቶ ሜትር ጥልቀት ባለው ገደል ገብቶ የተሳፋሪዎች ህይወት ማለፉን ከስፍራው የመጣ ዘገባ ገለጠ:: ተሽከርካሪው 55 ሰዎችን አሳፍሮ ይጓዝ የነበረ ሲሆን በግሎልቻና በጮሌ ወረዳዎች መካከል የሚገኘውን ዳገት በመውጣት እንዳለ ተንሸራቶ ገደል ውስጥ የገባ መሆኑ ተዘግቧል። በአደጋው 22 ሰዎች መሞታቸው የተነገረ ሲሆን የአካል ጉዳት ደርሶባቸው በህይወት የተረፉትን ከገደል ለማውጣት የተቻለ መሆኑ
page5image23000 page5image23160
ታውቋል። ጥር 3 ቀን 2008 ዓም ከደሴ ወደ አዲስ አበባ ይጓዝ የነበረ አገር አቋራጭ አውቶብስ ከማጀቴ ወደ ከሚሴ ይጓዝ ከነበረው አይስዙ ቅጥቅጥ የህዝብ ማመላለሻ መኪና በመጋጨቱ የ10 ሰዎች ህይወት ወዲያውኑ ያለፈ መሆኑና በሌሎች ተሳፋሪዎች ላይ ቀላልና ከባድ ጉዳት የደረሰ መሆኑ ተዘግቧል፡፡
  •   ካርቱም ሱዳን ላይ ተሰብሰበው የነበሩት የግብጽ የሱዳንና የወያኔ የቴክኒክ ኮሚቴ አባላት የአባይ ግድብን አስመልክቶ የፈረንሳዩ አጥኝ ኩባንያ ባቀረበው የጥናት ሀሳብ ላይ ያላቸውን አቋሞች ተለዋውጠው ማክሰኞ የካቲት 1 ቀን 2008 ዓም በመሰረታዊ ጉዳዮች ላይ ስምምነት ላይ ደርሰዋል ቢባልም ሙሉ በሙሉ ባለመስማማታቸው ድርድሩን በአጭር ጊዜ ውስጥ አዲስ አበባ ላይ ለመቀጠል መስማማታችው ተገልጿል። በአርቲሊያ እና ቢ አር ኤል የተባሉት የፈረንሳይ አጥኝ ተቋሞች የሚያጠኗቸው ጥናቶች የሚያተኩሩት ግድቡ ወደ ሱዳንና ወደ ግብጽ በሚፈሰው የውሃ መጠን ላይ የሚያስከትለውን ጉዳትና እንዲሁም በግድቡ ምክንያት በአካባቢው የእጽዋት ሁኔታ ሊያስከትል የሚችለውን አሉታዊ ሁኔታ ነው። የግብጽና የሱዳን ፕሬዚዳንቶች እና የወያኔው ጠቅላይ ሚኒስትር በየካቲት ወር መጨረሻ ላይ ሻርም ኤል ሼክ በተባለው በግብጽ የመዝናኚያ ከተማ ተገናኝተው ስለአባይ ግድብ ሁኔታ እንደሚወያዩ ተገልጿል።
  •   ሰኞ ጥር 30 ቀን 2008 ዓም በዋሽንግተን ዲሲ በሚገኘው ከአሜሪካው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር መስርያ ቤት ጀምሮ እስከ አሜሪካው ምክር ቤት ድረስ በርካታ ኢትዮጵያውያን የተገኙበት ታላቅና ደማቅ ሰልፍ ተደርጓል። 21 የሚሆኑ የሃይማኖት የፖሊቲካ የሲቪክ ማህበራት የሴቶች ድርጅቶች በተውጣጣ የጋራ ኮሚቴ የተዘጋጀው ሰልፍ ላይ ከዋሽንግተን፣ ከቦስተን፣ ከፍሎሪዳ፣ ከአትላንታ፣ ከቺካጎ፣ ከኖርዝ ካሮላይና፣ ከፔንሴልቪኒያ እና ከኒውዮርክ የመጡ በርካታ ኢትዮጵያውያን ተሳትፈዋል። ሰልፈኞቹ ወያኔ የመሬት ነጠቃውን በተቃወሙ ዜጎች ላይ ያካሄደውን የግፍ ጭፍጨፋ አውግዘዋል፤ በዘርና በሃይማኖት የሚያደርገውን ክፍፍልና ከዚህ ጋር ተያይዞ እየተካሄደ ያለውን ጭፍጨፋ ኮንነዋል፤ ወያኔ መሬታችንን ለሱዳን አሳልፎ መስጠቱንበብርቱ ተቃውመዋል። የተለያዩ መፈክሮችም በአማርኛና በኦሮምኛ ተሰምተዋል። የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ህጋዊ ሲኖዶስ ጳጳሳትና የኢትዮጵያ ሙስሊም አባቶች በሰልፉ ላይ ተገኝተዋል። በተመሳሳይ ቀናት በኒውዮርክ ከተማ ከተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና መሥርያ ቤት ፊት ለፊት የዳግ ሃመርሾልድ አደባበይ በሚባለው ቦታ ላይ በአካባቢው የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን በወያኔ እየተካሄደ ያለውን ጸረ-ሕዝብ ድርጊት በማውገዝ የተቃውሞ ሰልፍ አድርገዋል። በሰልፉ ላይ የወያኔን ድርጊት የሚያጋልጡና የሚያወግዙ መፈክሮች ተሰምተዋል።
    በሶማሊያ አውሮፓላን ላይ ጉዳት ያደረሰው አልሸባብ መሆኑ ተነገረ፤ በአገሪቱ የተከሰተው ድርቅ ከፍትኛ ችግር አለከተለ
ከጥቂት ቀናት በፊት ከሶማሊያ ዋና ከተማ ወደ ጅቡቲ ይበር በነበረው የዳዓሎ አየር መንገድ ንብረት በሆነው አውሮፕላን ላይ የደረሰው ጉዳት በላፕ ቶፕ ላይ በተጠመደ ፈንጅ ምክንያት መሆኑን የሚያሳይ የቪዲዮ መረጃ ከሲሲቲቪ ላይ ያገኙ መሆናቸውን የሶማሊያ የጸጥታ ኃይሎች በዚህ ሳምንት ገልጸዋል። የተገኘው የቪዲዮ መረጃ አንድ ተሳፋሪ ላፕ ቶፕ የሚመስል ዕቃ ከአውሮፕላን ማረፊያው ሰራተኛ ሲቀበል የሚያሳይ ሲሆን ተሳፋሪው አውሮፕላኑ አደጋ ሲደርስበት በተፈጠረው ክፍተት ተስፈንጥሮ ወጥቶ የሞተ መሆኑ ተነግሯል። ቦምቡን ያፈነዳው ተሳፋሪ ቀደም ብሎ ሊሄድ የነበረው በቱርክ አየር መንገድ ሲሆን የቱርክ አውሮፕላን በመሰረዙ ምክንያት የዳአሎ አየር መንገድ ተሳፋሪውን ተቀብሎ ያሳፈረው መሆኑ ታውቋል። በሴራው እጃቸው አለበት በሚል የሱማሊያ የጸጥታ ኃይሎች ወደ 20 የሚጠጉ ሰዎችን በቁጥጥር ስር ያደረጉ መሆናቸው ታውቋል። የካቲት 5 ቀን 2008 ዓም አልሸባብ በአውሮፕላኑ ላይ ለተፈጸመው ጥቃት ኃይላፊነቱን ወስዷል።
ሱማሊያው ውስጥ በተከሰተው ድርቅ ምክንያት ወደ 58 ሺ የሚደረሱ ህጻናት በቂ እርዳታ ካልተሰጣቸው ህይወታቸውን ሊያጡ እንደሚችሉ የተመድ ባለሥልጥጣናት ሰኞ ጥር 30 ቀን 2008 ዓም ገልጸዋል። ቢያንስ 305 ሺ የሚሆኑ ህጻናት በምግብ እጥረት የሚሰቃዩ መሆናቸው የተገለጸ ሲሆን ከእነዚህ ውስጥ58 ሺ የሚደርሱት በሞት አፋፍ ላይ መሆናቸው ተነግሯል። ለአራት ተከታታይ ዓመታት በሱማሊያ በአንዳንድ ቦታዎች ድርቅ፤ በሌሎች ቦታዎች የጎርፍ አደጋ በመድረሱ የብዙ ዜጎች ህይወት የተቃወሰ ሲሆን የአገሪቱ አርባ ከመቶ የሚሆነው 4.7 ሚሊዮን ሕዝብ እርዳታ የሚያስፈልገው መሆኑን ታውቋል።
በተመሳሳይ ዜና በደቡብ ሱዳን በጦርነት ቀጠና ውስጥ ያሉ ቢያንስ 40 ሺ ሰዎች እየተራቡ መሆናቸውን የተባበሩት መንግስታት ሰኞ ጥር 10 ቀን 2008 ዓም በሰጠውም መግለጫ አስታውቋል። የአገሪቱ 25 ከመቶ የሚሆነው 2.8 የሚሊዮን የሚሆነው ሕዝብ እርዳታ የሚፈልግ ሲሆን በግጭቶች በመስፋፋታቸው ምክንያት እርዳታውን ለማድረስ ያልተቻለ መሆኑ ተነግሯል። እርዳታውን በወቅቱ ከሚፈለገው ቦታ ለማድረስ የጸጥታው ሁኔታ አስተማማኝ መሆኑ አስፈላጊ በመሆኑ ጦርነት በሚያካሄዱባቸው ክፍሎች ትብብር ካልተገኘ በርካታ ዜጎች በምግብ እጥረት ሊሞቱ እንደሚችሉ ይኸው የተመደ ዘገባ አስታውቋል።
የሁቲ አማጽያን የሳኡዲን ግዛት ተቆጣጠርን አሉ
በየመን በሁቲ አማጽያን የሚደገፈው የየመን ጦር በሳኡዲ አረቢያ ደቡብ ምዕራብ በአሲር ክፍለ ሀገር ውስጥ ከሳኡዲ ወታደሮች ጋር ከባድ ውጊያ አካሄዶ አልራቦህ የተባለውን የሳኡዲ አረቢያ ከተማ እና በአካባቢው ያሉትን መንደሮች በቁጥጥሩ ስር ማድረጉን ገልጿል። የሳኡዲ ጦር በአውሮፕላንና በሌሎች ከባድ መሳሪያዎች ቢረዳም በጦርነት ከባድ ጉዳት ደርሶበት መሳሪውያውን እየጣለ የሸሸ መሆኑን ቢገልጽም ዘገባው በሌላ በሶስተኛ ወገን ማረጋገጫ አላገኘም።

ሰሜን ኮርያ አንድ ተመዘግዛጊ መሣሪይ ወደ ኅዋ አመጠቅኩ አለች
እሁድ ጥር 29 ቀን 2008 ዓም ሰሜን ኮሪያ አንድ የጠፈር ተምዘግዛጊ መሳሪያ ማምጠቋ ታውቋል። የሰሜን ኮሪያ ባለስልጣናት ተምዘግዛጊው መሣሪያ (ሮኬቱ) የተተኮሰው በኅዋ ላይ የሳተላይት ጣቢያ ለማስቀመጥ ነው የሚል ምክንያት ቢሰጡም ሌሎች አገሮች ግን ሰሜን ኮሪያ የባለስቲክ ሚሳየል ተክኖሎጂን ለመሞከር ያደረገቸው ነው ይላሉ። ሰሜን ኮሪያ ይህንን ሮኬት ያመጠቀችው አራተኛውን የኑክሌር ሙከራ ባደረገች በሳምንታት ጊዜ ውስጥ መሆኑ ተዘግቧል። ጃፓንና ደቡብ ኮሪያ እንዲሁም የምዕራብ አገሮች ጉዳዩን በጣም አሳሳቢ ነው ያሉት ሲሆን የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የጸጥታው ምክር ቤት ባስቸኳይ ተሰብስቦ የሰሜን ኮሪያን ድርጊት አውግዞ ተጨማሪ የማዕቀብ እርምጃ ለመውሰድ መዘጋጀቱ ተገልጿል። ከዚህ በፊት በሰሜን ኮሪያ ላይ በተከታታይ የተደረጉት ማዕቀቦች በአገሪቱ የኑክለር ፍላግትና ተግባር ላይ ያመጡት ተጽእኖ አነስተኛ ሲሆን ወደፊት የሚወሰደውም ማዕቀብ ምን ውጤት ሊያስከትል እንደሚችል ግልጽ አይደለም። በተጨማሪም ቻይና የሰሜን ኮሪያ አገዛዝ ቢፈነገል የሚከተለው ቀውስ ወደ አገሯ እንዳይዛመት ስለምተሰጋ ከበድ ያለ ማዕቀብ በሰሜን ኮሪያ ላይ እንዳይወሰድ ታደርጋለች የሚል ግምት አለ።
የቢን አሊ ንብረት ወደ መንግስት ካዝና ገባ
የቀድሞ የቱኒዚያ ፕሬዚዳንት ቢን አሊ የአገሪቱን ንብረት በመዝረፍ በግል አከማችተውት ከነበረው ንብረት ውስጥ 500 ሚሊዮን ዶላር የሚሆን ገንዘብ ወደ መንግሥት ካዝና የገባ መሆኑን አንድ የቱኒዚያ ሚኒስትር ረቡዕ የካቲት 03 ቀን 2008
page8image20560 page8image20720 page8image20880

ዓም የተናገሩ መሆኑ ታውቋል። የዛሬ አመስት አመት በቱኒዚያ በተነሳው ሕዝባዊ አመጽ ምክንያት ፕሬዚዳንት ቢን አሊ አገር ጥለው ወደ ሳኡዲ አረቢያ ሲሰደዱ የቢን አሊና የተባባሪዎቻቸው ንብረት የሆኑ የንግድ ተቋማት፣ ህንጻዎች፣ የቅንጦት መኪናዎች፣ ወርቅና አልማዝ እንዲሁም ሌሎች ጌጣጌጦች የተወረሱ መሆናቸው ይታወቃል። ባለፉት አምስት አመታት አብዛኞች ንብረቶች ተሸጠው ከግማሽ ቢሊዮን ዶላር በላይ ወደ መንግሥት ካዝና የገባ መሆኑን ሚኒስትሩ አስታውቀዋል። በአሁኑ ወቅት ያልተሸጡ በርካታ ንብረቶች ያሉ መሆናችውን ሚኒስትሩ ገልጸው ባጭር ጊዜ ውስጥ ለመሸጥ ጥረት የሚደረግ መሆኑን ተናግረዋል።
አርብ የካቲት 4 ቀን 2008 ዓም የሮማው ካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ሊቀ ጳጳስ እና የሩሲያው የኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ፓትሪያርክ በኩባ ዋና ከተማ በሃቫና አውሮፕላን ማረፊያ ለሁለት ሰዓታት ተገናኝተው ባደረጉት ታሪካዊ ስብሰባ በሁለቱ ቤተ ክርስቲያናት መካከል አንድነት እንዲፈጠር ጥሪ አስተላልፈዋል። ከዚህ በተጨማሪም በተለይ በመካከለኛው ምሥራቅ በክርስቲያኖች ላይ እየደረሰ ያለውን ግድያ ሁሉም እንዲከላከል ጥሪ አድርገዋል። ከ1000 ሺ ዓመት በፊት በአስራንደኛው ክፍለ ዘመን የካቶሊክና እና የኦሮቶዶክስ እምነት ተከተያዮች ከተለያዩ በኋላ በሁለቱ ቤተ ክርስቲያናት መሪዎች መካከል ግንኙነት ተፈጥሮ ውይይት ሲካሄድ ይህ የመጀመሪያው በመሆኑ ታሪካዊ ነው ተብሏል። ከስብሰባው በኋላ ሁለቱም ወገኖች በሰጡት መግለጫ ስብሰባው በቅንነትና በግልጽ የተካሄደ የወንድማማቾች ስብሰባ ነበር ብለውታል። 

No comments:

Post a Comment