Sunday, February 14, 2016

በምኞት የከበረ በአጓት የሰከረ የለም!... ከዳዊት ተመስገን (ኖርዌ ኦስሎ)

በምኞት የከበረ በአጓት የሰከረ የለም!
ከዳዊት ተመስገን (ኖርዌ ኦስሎ)
እኔ ቅን ነኝና ምን አለብኝ በማለት ከሃላፊነትህ በታች ሲፈጸም የሚታየውን ጠማማውን ተግባር ዝም ብሎ ማየት በቂ አይደለም: አገሩን ያፈረሰ (የካደ) ተመስጋኝነቱን አጠፋ ዓመፀኞችን ገዢዎች አድርጎ የሾመ እራሱም ቅን አይደለም አላዋቂዎችን (ሰነፎችን) አማካሪዎች ያደረገ ራሱም ቸር አይደለም መሪ ማውጣት ማለት ፕሬዚዳንት ወይም ጠቅላይ ሚኒስትር የሚሆን ሰው የማፈላለግ ጥረት ተደርጎ ሊወሰድ የሚገባው አይደለም። የሚመራን አጣን ማለት ሁላችንም ከኋላ ከኋላው የምንከተለው ሰው የለንም የሚል ባይሆን ደስ ይለኛል። ለምንድነው? ሁላችንም መሪዎች ለመሆን ጉጉት የሌለን መሪኮ ስንል አንድ ሰው ማለት አይደለም አይመስለኝም በአገር ትክክለኛና ድንቅ ራዕይ ያለው ሁሉ መሪ መሆን አለበት አገሪቱ ደግሞ ለአያሌ መሪዎች በቂ ቦታ አላት ወይስ የግለሰብ ሹሞችን ጭራ ይዘን የመከተል የአሽከርነት መንፈስ የሰፈረብን ነን:
በአንድ ወቅት አጼ ምኒልክ ከአዲስ አበባ እስከ አዲስ አለም ድረስ የመኪና መንገድ አስጠረጉና በአቶሞቢል ተጉዘው ሲመለሱ ከኋላ ከኋላቸው የሚከተላቸው አጀብ እዚያው ከአዲስ አበባ መሃል ከተማ እንደተሰበሰበ ይመለሳሉ ለወትሮው በቅሎቸውን እየተከተለ አዲስ አለም ድረስ ያጅባቸው የነበረው ህዝብ አኩርፎ ይጠብቃቸዋል ለምን የተከታይነትና የአሽከርነት ስሜት ስለ ቀረበት መሆኑ ይመስለኛል። ይኸ ስሜት ዛሬ በዚህ ትውልድ ዘንድ በቀጥታ የተንፀባረቀም ነው ይህን ስርዓት ጠግነውና ጠጋግነው የሚገኙትን አሳባቸውን ጥለው በዚህ በበሰበሰ ስርዓት ተማምነውና በአገር አጥፊነት ተጠልለው የሚኖሩትን አስቡ እንዲህ እንዲህ ያሉ ሁኔታዎች ሲታሰቡ የዚህ ትውልድ መልካም ፍሬ ወደ መሬቱ ማህፀን እንደተመልሰ ይቆጠራል።
ይህ ትውልድ ቀደምት ካሉ አባቶቻችን ከነበሩት ትውልድ ያነሰ የአገልግሎት ሰሜት ይኖረዋል ብዬ አልጠራጠርም ነገር ግን የኢትዮዽያዊነት የጋለ ስሜት የአገር ፍቅርና ያተኮሰ የአገልግሎት መንፈስ ቢኖረን ኖሮ ከጠላት ጋር ሆነን አገር ባላስገነጠልን ነበር። አሁንም አንዳንድ ጽንፈኛ ፖለቲካ የሚያራምዱ እንገንጠል የሚል መንፈስ ባላሉ ነበር። ለጠላት መንገድ መርተን በቤታችን አሳድረን ያለችንን ቀይ ሳንቲም ስጥተን እዚህ ደረጃ ባልደረሰን ነበር። አገር ለመምራት የምድር ጭቁኖችን ከረሃብና ከበሽታ ለመከላከል ያልቻለ እንበል የችግሩ እንብርት ደግሞ የኢትዮዽያዊነት ግንዛቤ አለመታወቅ ነው ይልቁንም እያንዳንዱ የዚህ ትውልድ አባል ልብ ከዚች አገር ጋር አለመገኘቱ ነው።
ምናልባትም ተንቀንና ተዋርደን የመኖራችን ሁኔታ በዚህ ዓይነት ሊገለጥ ይችላል በማለት ከተዋራጅነት ሰሜት አንፃርም ተፈልስፎ ይሆናል ኢትዮጵያዊነት ከግል ጠባብ ስሜት አኳያ ወይም ከልዩ ልዩ የተሳሳተ ግምት አንፃር ስናየው እንደ ቆየን አይጠረጠርም መቸም የወያኔ የይስሙላ የፍርድ ቤት በር ያልገጨው የለም ብል በልፋፍ ጽድቅ መልክ በብብት ኪስ ውስጥ ተጠፍሮ መያዝ የተጀመረበት በመሆኑ ተጠርጥራችሁና ተጠልታችሁ ልትታሰሩ ትችላላችሁ ኢትዮጵያ ውስጥ ደግሞ የማይገደደው አንድ ነገር ዘብጥያ መውረድ ነውና በቀን ውስጥ አምስት ስድስት ጊዜ ቃል ይሰጣል። ብሄር ብሄረሰብህ ምንድነው? ትባላለህ መቸም ሰባም ሰማኒያም ዓመት እርስዎ አያሰኝም ዘንድሮ ኢትዮዽዊ ነኝ ቁጣ አለበት ለምንኛውም ኢትዮዽዊ ነኝ ብሎ በኩራት የሚናገረውን አማራ የሚሉበት ምክኒያት አላቸው አንደኛው ሁሉም የተነሱት በኢትዮዽዊነት ላይ
page1image20072 page1image20232
እንደመሆኑ በዚህ የዜግነት መለዮ ላይ ከአማሮች ውጭ ያሉ ወገኖቻችን ዘመቻ ያደርጉ ዘንድ ነው። ዳግመኛ ደግሞ ወጣቱ የዚህ ትውልድ ዋነኛ አባል እንዲሆን ወያኔ የተከፋፈለ ዜጋ ሆኖ እንዲቀር ነው። እንደሚታወቀው ዓለሙ ሁሉ ለሁለት ነገሮች ይገዛል ይታዘዛል እነሱም አንድ ሰይፍ ነው አንዱም የቀለም ብዕር ነው እነዚህ ሁለት ኃያላን ነገሮች ለሚማሩ ተግሣጽና ምክር ናቸው። ለነጋዴዎችም የትርፍ(የወለድ)ገንዘባቸው ናቸው።
በሩቅና በቅርብ የሚገኙቱ ስዎች ሁሉ ምክርና ምስጢር በነሱ ይታወቃል ይገለጣል። ብሄርተኝነት ለምን የፋሺስት ደርግን ውድቀት ባቀረበበት ወቅት ራሱን ወደ ህብረ ብሄራዊነት ማሻገር ያልቻለው ህወሐት(ወያኔ)ትግራይ ብቻ ሳይሆን ሌሎችም ብሄሮች በአንድ ጨቋኝ ብሄር ስር ናቸው ከሚል ሙግት በዘመናዊ ኢትዮጵያ መንግስት አመሰራረት ሂደት ተጨቁነዋል የሚሉትን ብሄሮች ለማሰባሰብ መፈለጉ ለብሄር ፖለቲካው የመጀመሪያው ምክኒያት እንደሆነ የታወቀ ነው ኢሕአፓ ግን ራሱን ለህዝብ ሲያስተዋውቅ ከሚታገልባቸው በኢትዮዽያ ዴሞክራሲያዊ መብቶች ያለ ገደብ እንዲከበሩ የመንግስት ስልጣን ከህዝብ እንዲመነጭ በጾታና በእምነት ልዩነት እንዳይኖር የአገሪቱ ሉዓላዊነት እንዲከበር ማንኛውም ኢትዮዽያ በፈለገውና በነፃ ተዘዋውሮ መስራት እንዲችል የመሳሰሉት ይገኙበታል።
በአሁን ሰዓት ደግሞ ተጨባጭ ባልሆነ ትግል ወጣቱን እያጭበረበሩት ይገኛሉ ከአስመራ ወደ አሜራካ ለፌ ወለፌ እያሉ በቅርቡ ከአሜራካን አንዳንድ ጫጫታዎች ተሰምተዋል ሐሰትና ስንቅ እያደረ ይቀላል እንደሚባለው ሁሉ በእኔ እይታ ወጣቱ ማስተዋል ያለበት ሰው ተለዋዋጭ ፍጥረት ነው ይህ ሰው ሁሉ የሚጋራው ባህርይ ቢሆንም ምንጩ ግን ከሰው ወደ ሰው ሊለያይ ይችላል። አንዳንድ ሰዎች እንዲሁ የወረተኝነትና በአንድ ሃሳብ ያለመጽናትና ዝንባሌ እንዳላቸው ጥያቄ የለውም አንዳንዶቹ ግን ተለዋዋጭ የሚሆኑት ክፉና ወረተኛ ስለሆኑ ላይሆን ይችላል። የወቅቱ እዉነታ የሚለዋውጠው ሁኔታዎችና እይታዎች እንዲሁም ሌሎች ከቁጥጥራቸው ውጪ የሆኑ ጉዳዮች በላያቸው ላይ ስለሚለዋወጡ እነሱም ከመለወጥ ውጪ ምርጫ እንደሌላቸው ይገደዳሉ፡ ስለሆነም ዛሬ የደገፈህና አብሮህ የሆነ ሰው ነገ ከአቅሙ በላይ በሆነ ምክኒያት ሊለወጥ ስለሚችል ይህንን ሊለወጥ የሚችል የሰው ሁኔታ ተስፋ በማድረግ የማንነትህን ዋጋ ከዚያ ጋር ማያያዝ የስህተት ሁሉ ስህተት ነው።
በአሁኑ ሰዓት የአገራችን ችግር የጋራችን ከሆነ ወይም የእናት ኢትዮዽያ ችግር ማንንም ያካተተ ከሆነ መፍትሄ የእኔ ብቻ ነው። የዛችን ችግር የምናውቅላት እኛ ብቻ ነን ባዩስ ምን ማለቱ ነው ዛሬ ደግሞ ካለኛ አማራጭ የለህም ለማለት መቃጣቱስ የምንዮሽ ነው ፋሺስት ደርግ የሶሻሊዝም አመራር ይጠቅማል በማለት ሰብኮ እሱም በተራው የኢትዮዽያን ህዝብ አንጎል እንዲያጠብ ያስደረጉ ጠለቅ ያለ ጥናት ሳይደረግ ቤቶች እንዲወረሱ የእርሻ መሬት ሃብት እንዲቆረቁዝ የቀይ ሽብር በማለት በህዝባችን ላይ አምጥቶ በብዙ ሺ የሚቆጠሩ ወጣቶች እንዲያልቁ ምክኒያት ሆኑ ቀና ቢታጣ ይመለመላል ጎባጣ ሆነና ዛሬ ለኢትዮዽያ ህዝብ አለኝታ ሆነው አንተ ግባ አንተ ውጣ ባዮች መሆናቸው አሳዛኝ ትንግርት ነው። ችግሩ እራሱን ቢሸሽጉት እግሩ ይታያል በተጨማሪ ለኢትዮዽያ ህዝብ ፈተና የሆነበት ብዙሃኑን ወያኔ በገንዘብ አስሮታል በምፅዋትም ሆነ በብድር መልክ የተሰጠውን ከወሰድው በኃላ ደግሞ በለውጡ ነፃነቱን አሳልፎ መስጠት ግዴታ ሆኖበታል ስለዚህ በልጓም እንደሚገራ በቅሎ ወይም ፈረስ ወደተፈለገበት አቅጣጫ እየተሰገረ እንዲጋልብ ተደረጋጓል እናም የድህነት አንዱ ገፅታው በኢኮኖሚ ልጓም
ተይዞ ወደ ተፈለገበት ግብ እየተነዳ ነው ሞፈርን ጨነቀው ከኃላው እርፍ ከፊቱ ቀንበር አነቀው እንደሚባለው ነው ለምሳሌ:-የማንነት ጥራት ስኬት ያመጣል እንጂ ስኬት የማንነትን ጥራት አያመጣም። አንዳንድ ሰዎች ይህ እውነታ ይምታታባቸዋል። ስለዚህ ተሳክቶላቸዋል ብለው የሚያስቧቸውን ሰዎች ጨዋ ማንነትና አመለካከት ይመለከቱና እኔም በእውቀት በሃብትና በመሳሰሉት ሁኔታዎች እዚህ ደረጃ ብደርስ ኖሮ ጥራት ያለው ህይወትና ማንነት ይኖረኝ ነበር ብለው ያስባሉ።
ይህ ጉዞ የምኞት ጉዞ ነው እንጂ የእውነታ ጉዞ አይደለም። እነዚያ ሰዎች የጀመሩት ከማንነት ለውጥ መሆኑንና ሁኔታዎችን ከመለወጣቸው በፊት ማንነታቸውን ለመለወጥ ጥረት ማድረጋቸውን አልተገነዘቡም። ጊዜያዊ ስኬት ከዚህና ከዚያ ሊለቃቀምና በእጅ ሊገባ ይችላል። ዘላቂና ጥራት ያለው ስኬት ግን መነሻው ጥራት ያለው አስተሳሰብና ማንነት ነው። ግን ከቆየ ታሪካችን አንፃር ኢትዮዽያውያን የመረዳዳት የመተሳሰብና የሰብዓዊ ርህርሄ ባህላችን ነው በክፉና በደግ ቀን የህዝብ ተሳታፊነት ለችግር ቀን ተጋግዞ መቆም የኖረና መለያችንም ነው ለምሳሌ ባልሳሳት በክፉ ቀን ሰሜን ኢትዮዽያ በ1870 ዓ.ም ረሃብ ገባ ከብቶች አለቁ አዝማራ ነጠፈ ያን ጊዜ ታዲያ በሰሜን የተወሳውን ረሃብ ለመከላከል በመላው ኢትዮዽያ ያሉ በተለይ እዛው ሰሜን የእህል ጎተራዎች ሁሉ ተከፍተው ለረሃብተኞች እንዲታደል ተደርጓል ብዙዎች ደግሞ ከሰሜን ወደ ደቡብ መጥተው የተቋቋሙበት የታሪክ ክስተት ነበር በሰሜን ያለው ከብት በማለቁ አዝመራ ነጠፈ ያን ጊዜ ታዲያ በሰሜን የተነሳውን ረሃብ ለመከላከል በመላው ኢትዮዽያ ያሉ በተለይ እዛው ሰሜን የእህል ጎተራዎች ሁሉ ተከፍተው ለረሃብተኞች እንዲታደል ተደርጓል። ብዙዎች ደግሞ ከሰሜን ወደ ደቡብ መጥተው የተቋቋሙበት የታሪክ ክስተት ነበር በሰሜን ያለው ከብት በማለቁ ከደቡብና ከምዕራብ ኢትዮዽያ ከብቶች ወደ ሰሜን ተወስደው ከተረፉት ከብቶች ጋር በማቀላቀል እንዲበራከቱ መልካም ተግባር ተከናውኗል። ይህ የቆየ ደግ ተግባር በህዝባችን ውስጥ ያለ ነው ቅድሚያ ስንሰጠው የነበረ ሰብዓዊ ተግባርን ነው እኛ ኢትዮዽያን የክፉ ቀን ልምዳችን ተረዳድቶ ለመኖር ጥሩ የተግባር ምሳሌ ሆኖናል እንደዚሁ ሌላው ደግሞ ምንም እንኳን ታሪክ የጀመረው ከአንዳንድ ከተሞች ቢሆንም በዚያ ሂደት የተገኘው የስልጣኔ ሃቅ የመላው ኢትዮዽያዊን መሆኑም ላለን ታሪካዊና ባህላዊት ስር የተሻለ አስተዋጽኦ እያበረከተ መተጋገዝን ባህላችን እንዲሆን አግዟል ለምሳሌ አክሱም ላሊበላ በሽዋ ደብረ ብርሃን ዘግይቶ ደግሞ በጎንደር እነዚህ ሁሉ የማዕከላዊ መንግስት መቀመጫ ሆነው ያገለገሉ ናቸው በያንዳንዱ የመንግስት ማዕከሎች መካከል የ100 ዓመት ርቀትና ልዪነት አለ መንግስታቱ በችግር ጊዜ ማዕከላቸውን ይለውጣሉ። ህዝቡም ክፉ ቀን ሲመጣ እየተንቀሳቀስ በየቦታው አገር እያቀና የኖረ ነው እንዲውም በታሪክ ውስጥ አንድ ወጥ የሆነ ህዝብና በተመሳሳይ በአንድ ወጥ ኢኮኖሚ ተሳስረን የኖርን እኛ ብቻ ነን።
ዛሬ ልክ የወያኔን የጽንፈኛ ፖለቲካ የሚያራምዱትን የቁም ቅዠት እየሰማን እራሳችንን ማምታታት የለብንም ትግላችንን ማፋፋም እንጂ ትግል ደግሞ የሚመለከተው ኢትዮዽያዊነት ላይ ሲሆን ሁሉም ቁርጠኝነትን ታአማኒነትን ጽናትን ያደርጋል ያኔ ነው የኢትዮዽያ ህዝብ የድል ባለቤት የሚሆነው አለበለዚያ ትግሉ ትግል ሳይሆን የሞተ ተጎዳ ነው የሚሆነው ትግል በስልጣን ላይ የሚገኘውን አምባገነን አገዛዝ ለማኮላሸት አንፃር የፖለቲካ መሰረታቸውንና አቅማቸውን ሳይቋረጡ ሽቅብ ማሳደግ አለባቸው በውጤቱም የፖለቲካ ሃይል ደረጃው ቀስ በቀስ ከበታችነት

ወደ አቻነት ከዚያም ወደ በላይነት ደረጃ ይጓዛል። የበላይነት ደረጃ መያዝ ማለት የኢትዮዽያን ህዝብ የስልጣን ባለቤት ማድረግ ማለት ነው መንገዱ ደግሞ አሁን ባለንበት ሁናቴ ህዝባዊ አመጽ ብቻ ሊሆን የሚችለው የፖለቲካ ትግል ሌላ ቁልፍ የህብረ ብሄር ትግል ጽንሰ ሃሳብ ሲመራ ነው። አፈጻጸሙን በስፋት ማወቅ ጠቃሚ ነው የተሳካ ህዝባዊ አመጽ ለማድረግ ነገድ ጎሳ እያሉ ከተመረዙ የፖለቲካ ድሪቶዎች ወይም ከበካዮች መጠበቅ እውን ሲሆን ብቻ ነው ይህም የሚሆነው በምኞት አይደለም ምክኒያቱም በምኞት የከበረ በአጓት የሰከረ የለምና እኛ ምንጊዜም ትግላችን ከዘረኝነት የጸዳ ዲሞክራሲ እንዲሰፍን ነው ጎሳዎችን እስካሁን ካሉበት ሁኔታ በባሰ መልኩ ከሚያራርቅ ማናቸውም ድርጊት እንቃወማለን።
ጠጣሩ እውነታ ወይም ሀቅ ግን 25 ዓመት ሰላማዊ ትግል ለኢትዮዽውያን ያተረፈውና ያስገኘው ነገር ቢኖር እየበዛ የመጣው የመጨቆኛ ህግና እያነሰ የሄደ መብት ብቻ ነው ለዚህ ችሎት ይህን መረዳት ቀላል ላይሆን ይችላል ህዝቡ ለረጅም ዘመን ሃይል ስለታከለበት አመጽ ሲነጋገር መኖሩ እሙን ነው ከዘረኝነት የጸዳ መንግስት እንዲኖረን ለማድረግ የሰላማዊ ትግሉ ፖሊሲ ምንም ውጤት እንዳላመጣ መካድ አልተቻለም የሃይልን አመጽ እንደ ዋና አማራጭ በአዕምሮ ውስጥ ማጎልበት መጀመሩ ብቻ ሳይሆን አመጽ ውጤት ሲያሳይ ነው ነገር ካመለጠ፣ራስ ከተመለጠ፣ ወገብ ከጎበጠ መመለሻ እንደሌለው ሁሉ ትግል ከተጀመረም የትግሉ መጨረሻ የኢትዮዽያ ህዝብ የስልጣን ባለቤት እስከሚሆንበት ድረስ መሆን አለበት፡ ምክኒያቱም በምኞት የከበረ በአጓት የሰከረ የለምና ኢትዮዽያዊ የሚታወቀው በቁርጠኝነት በጽናት በጀግንነት በታአማኒነት ነው የመገፋትና ተቀባይነት የማጣት ስጋት ያለበት ሰው ውስጡ የተቆጣ ነው ይህ የውስጥ ስውር ቁጣ አንዳንድ ጊዜ እየገነፈለ ሊወጣና በግልፍተኝነት ሊገለጥ ይችላል።
የውስጥ ቁጣና ግልፍተኝነት ከመገፋት ስሜት ጋር የሚያያዝበት ምክንያት ሰውየው በሰዎች ተቀባይነትን እንዳላገኘ እንዲሁም እንደተገፋ ስላመነና በውስጡ ስለተቆጣ ሳያስበው በበቀል ስሜት ስለሚሞላ ነው እንደተገፋና ተቀባይነት እንዳጣ የተሰማው ሰው መራራ ሰው ነው እንደተገፋና ተቀባይነት እንዳጣ የተሰማው ሰው በጥያቄ የተሞላ ሰው ነው እንደተገፋና ተቀባይነት እንዳጣ የተሰማው ሰው ተቀባይነትን ለማግኘት ማድረግ የሚችለውን ካደረገ በኋላ ያንን የተቀባይነት ጥማቱን ለማርካት ካልቻለ በማንኛውም ሰዓት ሊገነፍል የሚችል ሰው ነው።
በዘርም የተቆራኘን በባህልም የተወራረስንና በመተጋገዝ የኖረ ነው ይህንንም ታሪክ እንዲህ ሲል ያሳምነናል የኩሽ የሴምና የናይሎቲክ ህዝቦች ዘራቸው ተዋህዶ ባህላቸውም ተወራርሶ በኢትዮዽያ ምድር ላይ መኖራቸው ተረጋግጧል ይለናል አሁን ግን ልዩ ልዩ ብሄራሰብ የሆንን ይመስል በልዩነት ማቆሙ የክፉዎች ስህተት እንጂ ታሪካዊ ዕውነት የለውም ስህተቱም ታሪክን ወደኋላ የጎተተ ያደርገዋል ሰው ፊት ለፊት እያየ ወደፊት ይራመዳል እንጂ የኃላውን እያየ ሲራመድ ገና ዛሬ ማየታችን ነው!!
የወያኔን አምባገነን አገዛዝ በተባበረ ትግል እናስወግዳለን !! 12.02.2016 

No comments:

Post a Comment