Thursday, February 18, 2016

ወልቃይት ጠገዴ ማነው?


ወልቃይት ጠገዴ ማነው?
page1image936
መግቢያ
page1image1544
ወልቃይት ጠገዴ ማነው? የሚለው “ሊበሏት ያሰቧትን ....” አይነት ጥያቄ በተደጋጋሚ የሚነሳው ከማን በኩል እንደሆነ ማወቅ “ሊበላን” ያሰፈሰፈውን አስቀድሞ ለማወቅ ይረዳል የሚል እምነት አለን። ከዚህም በመነሳት ባደረግነው ጥናትና ክትትል ጥያቄው ተደጋግሞ የሚነሳው በትግራይ ነጻ አውጭ ቡድን በኩል ሲሆን ይህ ወራሪና ተስፋፊ ቡድን ለመጀመሪያ ጊዜ የወልቃይትን መሬት በረገጠ ወቅት በአቶ ስብሃት ነጋ አዛዥነትና በአቶ መኮንን ዘለለው አጥኝነት ጥያቄው ለወገናችን ቀርቦ ነበር። ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ደግሞ ለዚህ እኩይ ቡድን በተንበረከኩና ባደሩ፤ ይልቁንም የዚህን ወንጀለኛ ቡድን በህዝባችን ላይ የፈጸመውን የዘር የማጽዳት ወንጀልና በሃይል ወደ ትግራይ የከለላቸውን የጎንደር ታሪካዊ ለም መሬቶች ህጋዊ ሽፋን ለመስጠት በሚዋትቱ ጥቂት ተንበርካኪዎች በኩል ጥያቄው ዳግም ሲነሳ እየሰማን ነው።
በተለይም በቅርቡ አቶ ሃይሉ የሺወንድም የተባሉ የአካባቢው ተወላጅ በጃንዋሪ 6, 2016 “የወልቃይት ባህልና የማንነት ጥያቄ” በሚል በኢትዮሚዲያ ድረ-ገጽ ላይ ባሰራጩት ባለ 8 ገፅ ፅሁፍ ላይ ለአለፉት 37 ዓመታት ህወሃትን በወልቃይት ጠገዴና ጠለምት ማህበረሰብ ላይ ያደረሰውን የዘር ማፅዳትና በትግሪያዊነት የመተካት ወንጀል ለመግታት በታገሉና ለኢትዮጵያና ለመላው የዓለም ህዝብ ባጋለጡ በስደት በሚገኙ የአካባቢው ተወላጆችና በሃገር ውስጥ ሆነው “የወልቃይት ጠገዴ የአማራ ማንነት”ን ለማስከበር ለሚታገሉ ወገኖች ይህን የማንነት ጥያቄ ደጋግመው ሲጠይቁና እርስ በእርሳቸው የሚቃረኑ ሃሳቦችን በማንሳት አንባቢውን ግራ ለማጋባት ላይና ታች ሲዋትቱ ተመልክተናል።
ስለሆንም ይህን በጥቂት እውነትነት ያላቸው በሚመስሉና በፍፁም ክህደትና በህወሃታዊ ሴራ የተሞላ ፅሁፍ በአግባቡ መልስ መስጠትና እንደከዚህ ቀደሙ ሁሉ ህወሃትና ተላላኪዎቹ በታጋዩና ጀግናው ህዝባችን መካከል ሊዘራ ያሰበውን መርዛማ እንክርዳድ ነቅሶ በማውጣት ማጋለጥና ለወልቃይት ጠገዴ ማህበረሰብና ለመላው የኢትዮጵያ ህዝብ ትክክለኛውን ታሪካዊ መረጃ ከምንጩ ማቅረብ አስፈላጊነቱ ስለታመነበት ይህ ታሪካዊ ሰነድ እንደተለመደው በስደት በሚገኙ የወልቃይት ጠገዴ ተወላጆች አማካኝነት ተዘጋጅቶ ቀርቧል።
በቅድሚያ ግን ለጠቅላላ ግንዛቤ ይረዳ ዘንድ እነዚህ ለህወሃት ፍርፋሪ የተንበረከኩና የወልቃይት ጠገዴን ማህበረሰብ ህወሃትን ለመሰለ “የቀን ጅብ” አሳልፈው የሰጡ ግለሰቦች እነማን እንደሆኑ ለአንባቢ በመጠኑም ቢሆን ግልፅ ማድረጉ አይከፋምና እነሆ ። ይህ ባንዳነት የባህሪው የሆነው የሆድ-አደሮቹ ቡድን የሚመራው በወ/ሮ አዜብ መስፍን ሲሆን፣ በእርሷ ገንዘብና ስልጣን ሙሉ ድጋፍና እንክብካቤ የሚደረግለት የአንድ ቤተሰብ ስብስብ ነው። አቶ ኃይሉ የሺወንድም ደግሞ ለረጅም ዘመናት በአውሮፓ ኖርዌይ አገር ነዋሪ የነበሩና ካለፉት ሁለት አመታት ወዲህ ግን ነዋሪነታቸውን በኢትዮጵያ ያደረጉ ሲሆን በቅርቡ ሁለት ሰፋፊ የእርሻ መሬቶች በጋንቤላ ውስጥ እንደተሰጣቸውና አዲስ ባለሃብት ለመሆን እየተሯሯጡ የሚገኙ ናቸው።እኒህ ግለሰብ የወ/ሮ አዜብ መስፍን ወንድም (የወ/ሮ አዜብ ምስፍን እናትና የአቶ ኃይሉ እናት እህታማቾች) ሲሆኑ እንዲሁም የትግራይ ነጻ አውጭ ግንባር ባለስልጣን የሆነው የአቶ ፈረደ የሺወንድምና በካርቱም ሱዳን ውስጥ ስደተኞችን በመጠቆምና በማሳሰር በሰፊው የሚታማው የአቶ ተስፉ የሺወንድም ወንድም እንደሆኑ ይታወቃል።
አቶ ኃይሉ አገር ቤት ከመግባታቸው በፊት የትግራይ ነጻ አውጭ ግንባር እንደ ወራሪ ኃይል ይመለከቱ እንደነበርና ወልቃይት ወደ ነበረበት ግዛት ወደ ጎንደር ያለ ድርድር መመለስ እንዳለበትም እንደአቋም በመውሰድ ያስተጋቡ እንደነበር ይታወቃል። ሌላኛው ግብረ-በላ ደግሞ አቶ ፀጋዬ አስማማው የሚባል ሲሆን የፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ዳኛ በመሆን የሚያገለግልና የህወሃት ቀንደኛ አሽከርና ተላላኪ በመሆን ከአቶ ፈረደ ጋር ሰሜን አሜሪካ ድረስ በመምጣት የወልቃይት ተወላጆችን ሰብስበው የ“እራስ ገዝ” አስተዳደር እንዲጠይቁ ሲያግባባ የነበረና አሁንም በተሰጠው የዳኝነት ሙያ ሽፋን ታጋዩን ህዝባችንን በማስፈራራት ግንባር ቀደሙን ሚና የሚጫወት እርሱ ነው። በወልቃይት ጠገዴ ማህበረሰብ ላይና በተለይም “የወልቃይት ጠገዴ የአማራ ማንነት” አስከባሪ ኮሚቴ ላይ ለሚደርሰው ማንኛውም እንግልት፣ እስር፣ ስቃይና፣ አደጋ ግንባር ቀደም ጠያቂዎቹ እነዚህ አራት ሆድ-አደሮች መሆናቸውን ለማሳሰብ እንወዳለን።
መልካም ንባብ ከአዘጋጆቹ
1
ወልቃይት ጠገዴ ማነው?
“የወልቃይት ባህልና የማንነት ጥያቄ” የሚለው ፅሁፋ በገጽ 4, 2ኛው አንቀጽ ላይ “ስለዚህ የትግራይ ነጻ አውጭ ግንባር ወልቃይትን ከተቆጣጠረበት ጊዜ ጀምሮ እስከ አሁን ድረስ ያለውን ታሪክ በዜሮ ብናባዛው፤ የህዝበ-ውሳኔው ውጤት ከትግራይ ጋር መኖር የሚሹ ወልቃይቴዎች በሰፊ ልዩነት ሊያቸንፉ መቻላቸውን ያበስር ነበር” ይላል። ነገር ግን ይህ የአቶ ሃይሉ የሺወንድም ምኞትና ድምዳሜ ወይም ህወሃታዊ ተልዕኮ ከታሪክና ከተጨባጩ የወልቃይት ጠገዴ ማህበረሰብ አቋምና ምርጫ ፍጹም እንደሚቃረንና እንደሚጋጭ በሁለት ቀደምት የህወሃት አባላት የቀረቡ ምስክርነቶች አጥጋቢ መልስ ስለሚሰጡ እነርሱን እንመልከት።
ኢትዮጵያውያን እንደ ዛሬው ህወሃት በለጠፈብን የብሔር ታርጋ ምክንያት የጎሪጥ መተያየት ሳንጀምርና ሃገራችን ጎጥ ጎጥ ከመሽተቷ 37 ዓመታት በፊት በትግራይ ነጻ አውጭ ቡድን በኩል ለወልቃይት ጠገዴ ማህበረሰብ የቀረበው “ወልቃይት ጠገዴ ማነው?” ጥያቄ በወቅቱ የነበሩት ኩሩና በማንነታቸው ላይ ፍጹም ብዥታ ያልነበራቸው ወገኖቻችን የህወሃት ወኪል ለነበረውና ጥያቄውን ይዞ ለመጣው ለአቶ መኮንን ዘለለው በማያዳግም ሁኔታ መልሰውለት እንደነበር ታሪክ ህያው ምስክር ነው። በወቅቱ የነበረውን ሁኔታ የህወሃት ነባር አባልና የፋይናንስ ኋላፊ የነበሩት አቶ ገብረመድህን አርአያ በዲሴምበር 22, 2015 ኢትዮ-ሚዲያና ጎልጉል ድረ-ገፅ ላይ “በወልቃይት ጠገዴ፤ ጠለምት በአማራው ላይ ህወሃት የፈጸመው የዘር ማጽዳት ወንጀል” በሚል ባወጡት ጥልቅ ሰነድ በገጽ 2 ላይ፤
“በሪጅን 1 የህዝብ ግንኙነት ሃላፊ የነበረው፣ በአባቱ ወልቃይት ፀገዴ፣ በእናቱ ሽሬ የሆነው መኮንን ዘለለው፣ የተወጠነውን ትልእኮ ይዞ ወልቃይት ፀገዴ ፀለምት እየተዘዋወረ ህዝቡን በመሰብሰብ ይህ መሬት የትግራይ መሬት ስለሆነ እናንተ ከእንግዲህ ወዲህ የሰሜን ጎንደር ዜጎች አይደላችሁም፣ የትግራይ መሬት ስለሆነ እንኖራለን ካላችሁ ትግሬዎች መሆናችሁን አምናችሁ ተቀበሉ፤ የትግራይ ዜጎች አይደለንም፣ ሰሜን በጌምድር የትግራይ አይደለም ካላችሁ ደግሞ የድርጅቱን የህወሓትን ውሳኔ ተጠባባቁ፤ የምታምኑበትን አሁን ተናገሩ በማለት ሲያስጠነቅቅ፣ ከህዝቡ በኩል ያገኘው መልስ ግን አንድ ነበር። የቀረበውን ሃሳብ ከህፃን እስከ አዋቂ፣ የወልቃይት ፀገዴና የፀለምት ህዝብ፣ እኛ የሰሜን በጌምድር (ጎንደር) አማሮች እንጂ ትግሬዎች አይደለንም፣ የታሪካችን ስር መሰረቱ የበጌምድር አማሮች ነን። ይህ ቆመህ የምትናገርበት መሬት ሰሜን በጌምድር ይባላል። ከጥንቱ ታሪካችን 3 ብትነሳም ይህ መሬት ታሪካዊ ነው። ያለፉት የኢትዮጵያ ነገሥታት ከጥንት ጀምሮ እስከ አሁኗ ሰአት በመንግሥት እውቅና ያገኘ የጎንደር፣«”የበጌምድር” ጠቅላይ ግዛት እየተባለ የሚጠራ ነው። ዋና ከተማችን ደግሞ ጎንደር ነው። የእናንተም ትግራይ ጠቅላይ ግዛት ይባላል፣ ዋና ከተማው ደግሞ መቀሌ ነው። ስለዚህ ኣናንተ የተሓህት ታግዮች ጉዳዩን ብታሱብበት ጥሩ ነው። ወደ እርስ በርስ ግጭ ያመራል።በተጨማሪም ታሪካዊ የወሰን ክልል አለን፣ እሱም ተከዜ ወንዝ ነው። የትግራይና በጌምድር የድንበር ክልሉ ተከዜ ወንዝ ነው። ከጥንት ጀምሮ የሁለቱ ኢትዮጵያውያን የድንበር ወሰን መሆኑን ልናረጋግጥ እንፈልጋለን በማለት በአንድነት ድምፅ ህዝቡ ራሱ አረጋገጠ።” በማለት ገልፀውታል።
ይልቁንም በአቶ መኮንን ዘለለው በኩል ለቀረበላቸው የማንነት ጥያቄ “የበጌምድር አማሮች ነን” የሚለውን የማያወላዳ ምላሽ የሰጡ የማህበረሰቡ ታላላቅና የተከበሩ መሪዎች በአቶ ስዩም መስፍንና በአቶ ግደይ ዘራፅዮን መሪነት ታፍነው ወደ ትግራይ መወሰዳቸውንና በሳሞራ የኑስ ትእዛዝ እንደተረሸኑ እራሳቸው አቶ መኮንን ዘለለው ለኢሳት ቴሌቭዥን በሰጡት ቃለ-መጠይቅ ላይ በዝርዝር አጋልጠዋል። በዚህ “ወልቃይት ጠገዴ ማነው?” በሚለው የህወሃት ያልተቋረጠ ጥያቄ ዙሪያና ህዝባችን በሚሰጣቸው አንድ፤ ግልፅና ቀጥተኛ መልስ ምክንያት ወገናችን የጅምላ ግርፋቶች፤ መፈናቀሎች፤ እስራቶች፤ ግድያዎች፣ ስደቶች፣ ቅስም ሰባሪና፣ ፀያፍ በደሎች ተፈፅመውበታል።
ታዲያ ይህ ሁሉ ሰቆቃ አሁንም ሳያባራ የትግራዩ ነጻ አውጭ ቡድን እነሆ ዛሬም እንደገና በእነ አቶ ሃይሉ የሺወንድም በኩል “ወልቃይት ጠገዴ ማነው?” ይለናል። አስቀድሞ በአቶ መኮንን ዘለለው በኩል ቀርቦ ህዝባችንን ለእልቂት የዳረገው ህወሃታዊ ጥያቄ ዳግም ለወልቃይት ጠገዴ ማህበረሰብ መጠየቅ ማለት አንድም ወገኖቻችን በማንነታቸው ጸንተው በመቆማቸው ምክንያት የከፈሉትን መስዋእትነት እንደ “ውሻ ደም” በመቁጠር ለመሳለቅ ወይም በህዝባችን ላይ ለተደገሰው ቀጣይ ህወሃታዊ ፍጅት ሰበብ ለማዛጋጀትና የጥፋት መንገድ ለመጥረግ የታለመ ይመስላል።
የህወሃት ሆድ-አደሮች ምን እያሉን ነው?
ወልቃይት ጠገዴ ማነው? ለሚለው የህወሃት መላዘን ወልቃይት ጠገዴ ማህበረሰብ ምላሹ ከላይ በአይን እማኞችና በህያው ምስክሮች እንደተረጋገጠ አይተናል። ታዲያ ለምን የዛሬዎቹ ተላላኪዎች “ስለዚህ የትግራይ ነጻ አውጭ ግንባር ወልቃይትን ከተቆጣጠረበት ጊዜ ጀምሮ እስከ አሁን ድረስ ያለውን ታሪክ በዜሮ ብናባዛው፤ የህዝበ-ውሳኔው ውጤት ከትግራይ ጋር መኖር የሚሹ ወልቃይቴዎች በሰፊ ልዩነት ሊያቸንፉ መቻላቸውን ያበስር ነበር” እያሉ ሌላውን ህዝብ ለማደናገር ይሞክራሉ? ለምንስ በወልቃይት ጠገዴ ማህበረሰብ በደል ላይ ይዘባበታሉ? የሚል ጥያቄ መነሳቱ አይቀርም።
ከዚህ የሆድ አደሮች ዘመቻ የምንረዳው ነገር ቢኖር ተላላኪዎቹ ቀደም ሲል በተደጋጋሚ እንገልጸው እንደነበረው ሁሉ ከህወሃት የተሰጣቸውን “የወልቃይት ጠገዴ ማህበረሰብን በማዳከምና በመከፋፈል ትግሪያዊነትን አሜን ብሎ እንዲቀበል” የማስቻል ተልእኮ ለማሳካት በሚል በመላው ኢትዮጵያ በተለይም እንደ ጋምቤላ ባሉ አካባቢዎች በሚደረጉ የመሬት ዘረፋዎችና ቅርምቶች (ወልቃይት ጠገዴ ለትግራውያን ብቻ ነው) ቢንበሻበሹም ውጤቱ ግን “ጉም መዝገን” ሆኖባቸዋል። ይልቁንም በሃገር ውስጥ የሚገኘው የወልቃይት ጠገዴ ማህበረሰብ ከምንግዜውም በላይ ተደራጅቶና ከመላው የአማራ ህዝብ ጋር አንድ ሆኖ ማንነቱ ለማስከበር ቆርጦና አምርሮ ሲነሳ ከህወሃት ይልቅ የተጨነቁት በወልቃይት ጠገዴ ማህበረሰብ ስም ድርጎ ሲቀበሉ የከረሙት ናቸው።
page2image32328 page2image32488 page2image32648
2
ከህወሃት በኩል ልምጭ የተቆረጠበት የሚመስለው ሆድ-አደሩ ቡድን መላውን የኢትዮጵያ ህዝብ ያንገሸገሸውንና ህወሃትን እስከ አንገቱ ያነቀውን፤ ይልቁንም በህወሃት/ኢህአዴግ መንደር እውቅና አግኝቶ ከጠ/ሚ እስከ ተራ ካድሬ እየተቀባበለ የሚዘምርለትን “የመልካም አስተዳደር እጦት” በምትባል “የጦስ ዶሮ” በመታከክ የወልቃይት ጠገዴ ማህበረሰብ ያነሳውን ዘርንና ትውልድን ከጥፋት የመታደግና የአማራ ማንነቱን በትግሪያዊነት ከመተካት የማዳን ፈርጀ ብዙ ጥያቄ “የትግራይ ክልል ባለስልጣናት የአስተዳደር በደል ስለፈጸሙበት” ነው እያሉ ማፌዝ በወልቃይት ጠገዴ ማህበረሰብ ቁስል በእሳት የጋለ ብረት እንደመስደድ ይቆጠራል።ያስተዛዝባልም።
ይልቅስ አቶ ሃይሉና የጥቅም ተጋሪዎቻቸው በወልቃይት ጠገዴ ማህበረሰብ ላይ የደረሰው በደል የዘር ማፅዳትና በትግሪያዊነት የመተካት ዓለም-አቀፍ ወንጀል መሆኑን የምትስቱት አይመስለንም። ይህን በማንነታችን ላይ የተፈጸመና በዓለም-አቀፍ የፍርድ አደባባይ የሚያስጠይቅን ወንጀል በማኮሰስና “የትግራይ ክልል ባለስልጣናት የአስተዳደር በደል” አድርጎ በማቅረብ ከህወሃት ጋር የገጠማችሁን ኪሳራ ማወራረድ ወይም የሚቆረጥላችሁን ድርጎ ማሳደግ አትችሉም። ኪሳራችሁን ማወራረድም ሆነ ሌላም ማድረግ የምትችሉት ለጌቶቻችሁ እውነቱን በመናገር ብቻ ነው። ምክንያቱም የወልቃይት ጠገዴ ማህበረሰብ ጎንደሬ-አማራ መሆኑን በአንድ ድምጽ ያረጋገጠውና በማንነቱም ምክንያት ለሚመጣ ማንኛውም ነገር ዋጋ ለመክፈል ዝግጁነቱንና ቁርጠኝነቱን በተግባር ያሳየው ገና “የትግራይ” የሚባሉ ገዥዎችና አስተዳደራቸው ከመፈጠሩ እጅግ አስቀድሞ እንደነበር ከወልቃይት ጠገዴ ማህበረሰብ ባልተናነሰ እነ ስብሃት ነጋ ጠንቅቀው ያውቃሉና እራሳችሁን አታታልሉ። ትዝብት ላይም አትውደቁ።
በሌላ በኩል ምንም እንኳ ዛሬ ህወሃት እስከ አፍንጫው ቢታጠቅና የሃገሪቱን መንግስታዊ ስልጣንና ሃብት እንዳሻው ቢያዝና ቢናዘዝበትም የወልቃይት ጠገዴ ማህበረሰብ ዛሬም በማንነቱ ላይ ያለውን የቀደመ ጽኑ እምነትና የትውልዱን ምስክርነት ማስለወጥ አልተቻለውም። እንግዲህ ለህወሃትና ለእነ አቶ ሃይሉ የሺወንድም እውነታው እንደ እሬት መራራ ቢሆንባቸውም ታሪክ በደማቁ የመዘገበውና በእያንዳንዱ የወልቃይት ጠገዴ ተወላጅ ህሊና ተጽፎ የሚገኘውና ለትውልድ የምናስተላልፈው እውነታ ግን የወልቃይት ጠገዴ ማህበረሰብ ህወሃት ዕርስታችንን ከመርገጡ በፊትም ሆነ በወረራ በተቆጣጠረ ጊዜ በጎንደሬ-አማራነቱ ጸንቶ በመቆም መራር መስዋእትነት እንደከፈለ ሁሉ ወደፊትም በማንኛውም የከፋ ፈተና ውስጥ ቢያልፍም ከጎንደሬ-አማራነቱ ሊያናውጸው የሚችል ምንም አይነት ምድራዊ ሃይል ያለመኖሩን ነው። ምክንያቱም ወልቃይት ጠገዴ አይደለም ለማንነቱና ለዕርስቱ፤ አምነው ለተጠጉትም አንገት እንደማያስደፋ ትግራውያን ያውቃሉ!
ታዲያ ወልቃይት ጠገዴ ማህበረሰብ ማነው?
“በአፍ የመጣን በአፍ፣ በመጣፍ የመጣን በመጣፍ” መመለስ የቀደሙ አባቶቻችን ስርዓትና ብሂል በመሆኑና ታሪካዊ ጠላቶቻችንም እንደ አመጣጣቸው መመለስ ተገቢ በመሆኑ ህወሃት በተላላኪዎቹ በኩል በወልቃይት ጠገዴ ማህበረሰብ መካከል ሊዘራ የሞከረውን እንክርዳድና በኢትዮጵያ ህዝብና በታሪካችን ላይ ሊፈጠር የታሰብውን ብዥታ ለማጥራት ሲባልና ለታሪክም ምስክር ይሆን ዘንድ “የወልቃይት ጠገዴ ማህበረሰብ ማነው?” የሚለውን ጥያቄ በአጭሩ እንደሚከተለው ስንመልስ ጥልቁንና ተነግሮ የማይጠገበውን የወልቃይት ጠገዴና ጠለምት ታሪክ ለታሪክ ፀሃፊዎችና ለባለሙያዎች በመተው ነው።
 1. የወልቃይት ጠገዴ ማህበረሰብ እንደ ማንኛውም የሰሜኑ ኢትዮጵያ ማህበረሰብ ሁሉ የአካባቢውን ስያሜ በመውሰድ የእራሱ መጠሪያ አድርጎ ኖሯል። ለምሳሌ የጎንደሬ ዘሩ ምንድነው? የሚኖርበት አካባቢ ስያሜ ማን ይባላል? የጎጃሜውስ? የወሎዬው? የጋይንቴው? የምንጃሬው? የስሜንኛው? ... ወዘተ ለመሆኑ እነዚህ ወገኖቻችን እራሳቸውን ሲጥሩ “እኛ ማነን” ይላሉ? እኛስ እነርሱን እነማን ናቸው እንላለን? ጎንደሬውን - ጎንደሬ ፤ ጎጃሜውን - ጎጃሜ ፤ ወሎዬውን - ወሎዬ፣ ደብረታቦሬውን - ደብረታቦሬ፤ ጋይንቴውን - ጋይንቴ፤ ስሜንኛውን - ስሜንኛ፤ በለሴውን - በለሴ፣ ወግሬውን - ወገሬ፣ ቋረኛውን - ቋሬ .... ወዘተ እያልን ወልቃይቴውን - ወልቃይቴ፣ ጠገድቼውን - ጠገድቼ፣ ጠለምቴውን - ጠለምቴ አላልንምን? እንላለን እንጂ!
 2. ታዲያ የወልቃይት ጠገዴ ማህበረሰብ አባቱ ማነው? የዘር ሐረጉስ ከየት ይመዘዛል ቢሉ?
  ወልቃይት የሚለው ስም ከስር መሰረቱ የአማራ መስራች አባት የሚባለው የተጠቀሰበት አገር ነው። አማራው ከወልቃይት ወደ ጠለምት ከዚያም ወደ ላኮ መልዛ (የዛሬው ወሎ) እያለ ሌላውን አካባቢ እያስፋፋ እስከ ሞቃዲሾ ተጉዞ ሃገር ያቀና ታላቅ ነገድ ያረፈበት መሆኑ ታሪክ ሁሌም ይመሰክራል። ወልቃይት ጠገዴ አማራ የሆነው ዛሬ ትግሬ ሊያደርጉት እንደሚታትሩት በተዘዋዋሪ ሳይሆን የአማራ አባትና ግንድ በመሆን ነው። ለዚህ ፅሁፍ በሚስማማ መልኩ ታሪካዊ ማስረጃዎችን እንመልከት።
  አለቃ ታዬ ወልደማርያም የተባሉ ሊቅና የተመሰከረላቸው ታሪክ ፀሃፊ “የኢትዮጵያ ህዝብ ታሪክ” በተባለው ዝነኛ መፅሃፋቸው በገፅ 16 ላይ እንዲህ ፅፈዋል። “ከለው ከሳባ ወደ ምዕራብ ወደ ደቡብ ያለ ያማራ የወልቃይት የጠገዴ አባት ነው። ከእነዚህም የኢትዮጵስ ልጆች የወንድማማቾቹ ነገድ ህዝብ ሁሉ በመልካቸውና በቁርበታቸው ይመሳሰላሉ። እኒህም ህዝብ የያዙት አገር በጥቅሉ ባባታቸው ስም ኢትዮጵያ ተብሎ ይጠራል።” በመቀጠልም የአማራው አባት አስገዴ ግንዱ ከወልቃይት ጠገዴ አርማጭሆ ከዚያም እያደገና እየሰፋ አማራ ሳይንት ድረስ የደረስ መሆኑን ገልጸው ጽፈዋል።
  አቶ አማረ አፈለ “ደም አይፍሰስ በቃ የህወሃት ማኒፌስቶ ያብቃ!” በሚለው መፅሐፋቸው በገጽ 27 ታሪካዊ ምስክርነታቸውን እንደሚከተለው አስፍረዋል።
page3image29736 page3image29896
3
“ከተከዜ ጀምሮ ወደ ደቡብ እስከ ሸላሎ በተዘረጋው ምድር ላይ ያሉት ወረዳዎች ሕዝቡ አፍ መፍቻ ቋንቋው አማርኛ ነው። ከትግራይ ጋር በተከዜ ወንዝ ድልድይነት ጎረቤት ስለሆነ ወዲያና ወዲህ ማዶ ያለው የዐማራና የትግራይ ቋንቋ ቃላት ቢያንስ 80 በመቶ ተመሳሳይ በመሆናቸው መናገሩ አዳጋች አይሆንባቸውም። ይልቁንም የወልቃይት ጠገዴና ጠለምት መዘጋዎች ጥጥ ስለሚያመርት ብዙ የትግራይ ተወላጆች በጥጥ ለቀማ ወቅት በየዓመቱ ወደነዚህ መዘጋዎች ይመጣሉ። ዐማሮች ከእነርሱ ጋር ለመግባባት ሲሉ ትግርኛውን ይጠቀሙበታል። ከእንግዶች መካከል ሀገሬውን አግብተው የሚቀሩም አይጠፉም። ለዚህም ወደ ኋላ መለስ ብለን ታሪክ ስንመረምር ወልቃይት ጠገዴና ጠለምት በአክሱም፤ በላስታው በሽዋ ሆነ በጎንደር ዘመነ መንግሥት አንድም ግዜ የትግራይ ግዛት አካል ወይም ገባር የሆነበት የታሪክ ወቅት የለም። ይህን እውነት ለመረዳት ከጎንደር ዘመነ መንግሥት በፊት ጀምሮ 20ኛ ምዕተ ዓመት ሁለተኛ አጋማሽ ድረስ የታወቁ የውጭ ሀገር ጉብኝዎችና ታሪክ ፀሐፊዎች በተለያዩ ክፍለ ዘመናት ኢትዮጵያን እየተዘዋወሩ ካዩ በኋላ ስለ ብሔረስቦችና ስለ አስተዳደር ክፍሎች የተውልን ጹሑፎችና ካርታዎች ህያው የታሪክ ማስረጃዎች ናቸው።”
“ለአብነት ያህል ፍራንሲስኮ አልቫሬዝ፤ ጅምስ ብሩስ፤ ዶክተር ሚካኤል ረሥል፤ ማንስፊልድ ፓርኪንስ፤ ስቨንረንሰን ወዘተ.......የተባሉ ታዋቂ ተመራማሪዎች ለትውልድ ያበረከቷቸውን መጻሕፍት መመልከት ይቻላል። ይልቁስ የኢጣሊያን መንግሥት ኢትዮጵያን በ1928 /ም ከመውረሩ በፊት በጐንደር ከተማና በሌሎች ከተሞች በከፈታቸው የቆንስል ቢሮዎች አማካይነት ባካሄደው ሰፊ የኢትዮጵያ ብሔረሰቦች ጥናት ባወጣው አስተዳደር መዋቅር ትግራይ ከኤርትራ ጋር ሲደርብ ጠገዴንና ጠለምትን የአማራ ክልል በማድረግ ትግሬ አለመሆናቸውን አረጋግጧል።”
ወልቃይት ጠገዴ ፡ ትግሬ
የወልቃይት ጠገዴ ማህበረሰብ ለመላው ኢትዮጵያዊ ይልቁንም ለድንበርተኛ የትግራይ ህዝብ ያበረከታቸው ታሪካዊና ዘመን ተሻጋሪ ውለታዎች በትግራይ ህዝብ ሁሌም እንደሚታወሱና ከትውልድ ትውልድም እንደሚዘክራቸው በእርግጠኝነት መናገር ይቻላል፡፡ ለምን ቢሉ እነዛ የትግራይ ህዝብን ህልውና የተፈታተኑ ክፉ የረሃብና ዘመናትና በእነዛ የጭንቅና የስደት ዘመናት የታደገን ጎረቤት መርሳት የማይታሰብ ነውና፡፡
ይሁንና ወራሪውና ተስፋፊው የትግራይ ነፃ አውጭ ቡድን በወልቃይት ጠገዴ ማህበረሰብ ላይ እያደረሰ የሚገኘውን የዘር ማፅዳት ወንጀል የበቀል ሽፋን ለመሰጠትና የትግራይም ህዝብ የዚህ እኩይ ሴራ አካል በማስመሰል እጅግ የተዛቡና አኩሪ ታሪካችንን የሚያጎድፉ አሉባልታዎችና የፈጠራ ታሪኮች በህወሃት መንደር ከመወራት አልፈው ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ደግሞ ለህወሃት በተንበረከኩና ባደሩ የአንድ ቤተሰብ አባላት ፊታውራሪነት ወደ ህዝብ በነጻ ሚዲያዎች አማካኝነት በፅሁፍ ሲሰራጩ ለመመልከት ችለናል፡፡
አበው “ውሸት ሲደጋገም እውነት ይመስላል” እንዲሉ ይህን እኩይ ሴራ ከወዲሁ በማጋለጥ በህዝቦች መካከል ሊፈጠር የታሰበውን ውዥንብርና ህወሃታዊ ትርፍ ማኮላሸት አስፈላጊ ሆኖ አግኝተነዋል፡፡
ውንጀላ 1. “የወልቃይት ጠገዴ ማህበረሰብ የትግራይን ህዝብ ይንቃል (ዝቅ አድርጎ ይመለከታል)” ስለመባሉ፤
ምንም እንኳ እነ አቶ ሃይሉ የሺወንድም በፅሁፋቸው በገፅ 4 ላይ የትግራይን ህዝብ በወልቃይት ማህበረሰብ እንደተበደለና በደሉን “ህወሃቶች መች እረሱ?” እያሉ በማጠየቅ ለህወሃት የፈጠራ ውንጀላ ማረጋገጫ መሰል ሃሳብ ቢያዋጡም እኛ ግን ይህን ሃሰተኛ ክስ በሁለት ዋና ዋና አቅጣጫ በማየት ለከሳሾቻችንና ለአጫፋሪዎቻቸው ምላሽ ለመስጠት እንሻለን።
“ሊበሏት ያሰቧትን አሞራ፣ ይሏታል ጅግራ”
“የወልቃይት ጠገዴ ማህበረሰብ ትግሬ ነው” ለዚህም ነው ወደ ትግራይ የከለልነው እያሉ አይናቸውን በጨው አጥበው ከ25 ዓመታት በላይ የሚያደርቁን ህወሃቶች፤ በሌላ በኩል ደግሞ “የወልቃይት ጠገዴ ማህበረሰብ የትግራይን ህዝብ ይንቃል” በማለት ደጋግመው ይከሳሉ።
ለመሆኑ ከመቼ ጀምሮ ነው አንድ ህዝብ እራሱን የሚንቀው ወይም የእራሱን ዘር ዝቅ አድርጎ የሚመለከተው? እውነት የወልቃይት ጠገዴ ማህበረሰብና የትግራይ ህዝብ አንድ ዘር ነው ተብሎ ቢታመን ኖሮ ይንቀናል ወይም ዝቅ አድርጎ ይመለከተናል ሊባል ይቻል ነበርን? እውነታው ግን፦
 1. በትግራይ ነፃ አውጭ ቡድን የትግራይ ህዝብ ጠላት ተደርጎ በተቆጠረውና ሃገር አቀፍ የዘር ፍጅት የታወጀበት የአማራው ነገድ አካል በመሆኑና የዘር ማፅዳቱ ዘመቻ የወልቃይት ጠገዴ ማህበረሰብን የሚያካትት በመሆኑ ሲሆን፤
 2. በሌላ በኩል ደግሞ ለ“ታላቋ ትግራይ” መንግስትና ለ“ትግሪያዊው ወርቅ” ህዝብ የምግብ ዋስትና የሚያረጋግጥ ለም መሬትና ከቀሪው ዓለም ከሱዳን ጋር የሚገናኙበት የየብስ መውጫና መግቢያ መስመር ለማግኘት በመቋመጥ የተነደፈውን የ1968ቱን የህወሃት ማኒፌስቶ ስኬት ሊያደናቅፍ ይችላል በሚል እሳቤ ለፈጸሙት የወልቃይት ጠገዴን ዘር የማፅዳትና በትግሪያዊነት የመተካት ወንጃል ምክንያታዊ ለማስመሰል የተለጠፈ የበቀል ካባ ሆኖ እናገኘዋለን፡፡
 3. ይልቁንም ታሪክና ትውልድ ይቅር ለማይለውና ዓለም ለተፀየፈው የወልቃይት ጠገዴን ዘር የማፅዳትና በትግሪያዊነት የመተካት ወንጀላቸው በህዝባችን የተቀናጀ መራራ ትግል ሲከሽፍና ከተጠያቂነት እንደማያመለጡ ሲረዱት፤ በደሉን ለትግራይ ህዝብ ክብር ሲሉ የፈፀሙት ለማስመሰልና፣ የትግራይ ህዝብም የዚህ እኩይ ወንጀላቸው ተባባሪ እንደሆነ
page4image29440 page4image29600 page4image29760 page4image29920 page4image30080
4
የማስመሰል ሴራ አካል ስትሆን፤ በላዩም ላይ ተላላኪዎቻቸው “ህወሃቶች መች እረሱ?....” በማለት ልክ የወልቃይት ጠገዴ ማህበረሰብ የትግራይን ህዝብ ይንቅ እንደነበርና አሁን ህወሃቶች በደሉን መርሳት ሲገባቸው ነገር ግን እንዳልረሱት በማስመሰል ማረጋገጫ ይሁን ትዝብትነቱ ያለየለት ለህወሃት የፈጠራ ክስ የሃሰት ምስክርነታቸውን ይሰጣሉ፡፡
ውንጀላ 2. “የወልቃይት ጠገዴ ማህበረሰብ በ50/60ዎቹ ዓ.ም አካባቢ ወደ አካባቢው ለተለያዩ የጉልበትና የግብርና ስራዎች ይመጡ የነበሩትን የትግራይ ተወላጆች ያገለገሉበትን ገንዘብ ባለመክፈል ይበድላሉ” ስለመባሉ፤
ዛሬ በዚህ ጉዳይ ላይ መልስ መስጠት አላስፈላጊ እንደሆነ እናምናለን፡፡ ምክንያቱም ህዝባችን በፊውዳሉ ዘመን በአሰሪና ሰራተኛ መካከል ሊከሰቱ ከሚችሉ ከእንዲህ አይነቱ ተራና ታሳቢ ከሆኑ ክሶች በላይ እጅግ አንገብጋቢና አሳሳቢ በሆኑት የህወሃትና የተላላኪዎቹ ሴራዎች ላይ በናተኩርና በወገናችን መካከል በሚያሰራጯቸው በማር የተለወሱ መርዞች ላይ በማተኮር ከዘር ማፅዳቱ ወንጃል በብዙ መስዋዕትነት ያተረፈውን ትውልዱን ከብከላ እንድንከላከልለት ቅድሚያ እንደሚሰጥ ጠንቅቀን እናውቃለንና ነው፡፡
ነገር ግን ከ1969 .ም በኃላ ላለው አዲስና ለመጭው ትውልድ የአባቶቹንና የአያቶቹን አኩሪ ታሪክ እግረ መንገዱን እንዲያውቅና ከሁመራ የእርሻ ልማት ጋር ተያይዞ ለሚነሱ መጥፎም ይሁን ጥሩ ታሪኮች እውነተኛ ስንቅ ከምንጩ ማቀበል ተገቢ ነው በሚል በዚህ ውንጀላ ዙሪያ ትንሽ ለማለት ወደድን፡፡
የወልቃይት ጠገዴ አብዛኛው ህዝብ በግብርና ሙያ የሚተዳደር የነበረ ሲሆን የወባ በሽታን፣ ጊንጥና እባብን ...ወዘተ ተቋቁሞ መዘጋ ወልቃይትንና ሁመራን የመሰሉ ገናና የእርሻ ቦታዎችን አልምቷል። ያለማውን መሬትም “መውፈር ቀደም” ስርአት በመጠቀም ለሁሉም አራሽ ክፍት በማድረግ ከመላው ኢትዮጵያዊ ወገኑ በተለይም ደግሞ ከኤርትራና ከትግራይ ህዝብ ጋር ተካፍሎ ሲያርስ ኖራል። በወቅቱም በብዙ ሺ ለሚቆጠሩ የትግራይ ተወላጆች ጥጥ ለቀማና ማሽላ ቆርጣ ከመሳሰሉ ዝቅተኛ ደረጃ የስራ እድሎች እስከ ባለ መሬትነት ባሉ የልማት ዘርፎች ይሳተፍ ነበር።
በሌላ በኩል ደግሞ የወልቃይት ጠገዴ ማህበረሰብ ትግራይ ውስጥ በተደጋጋሚ ርሀብ በተከሰተባቸው በእነዛ ክፉ ዘመናት ነብሳቸውን ለማትረፍ በስደት ለሚመጡት በብዙ ሺዎች ለሚቆጠሩ የትግራይ ወገኖች ጊዚያዊ መጠለያና ምግብ በማቅረብ እንዲያገግሙ ካደረገ በኋላም ራሳቸውን መልሰው እንዲያቋቁሙ የስራ እድል በመስጠት ሲረዳ የቆዬ የወገን አለኝታ ነበር።
እንግዲህ በዚህ ወቅት በብዙ ሺ የሚቆጠሩ የትግራይ ተወላጆችና የአካባቢው ህዝብ በሚሳተፍበት የእርሻ ልማት በግለሰቦች ደረጃ ለሚፈጠሩ የአሰሪና ሰራተኛ ግንኙነቶች እንዴት የወልቃይት ጠገዴ ማህበረሰብ ተጠያቂ ሊሆን ይችላል?
እውነታው ግን እራሱን የትግራይ ነጻ አውጭ ብሎ የሰየመው ወራሪና ተስፋፊ ቡድን ለተዘፈቀባቸው የዘር ማፅዳት፣ የዝርፊያ፣ ኢትዮጵያን የማፈራረስና፣ አካባቢውን የማተራመስ ወንጀሎች በመላው የኢትዮጵያ ህዝብና በዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ከሚጠብቀው ፍርድ ለማምለጥ ከለላና ዋሻ በማድረግ የሚጠቀምበትን የትግራይ ህዝብ በመያዦነት ይዞ ለመቆየት በማለምና በተለይም አጎራባች ከሆኑት የጎንደርና የኤርትራ ህዝብ ጋር በጠላትነት እንዲተያይና በስጋት ውስጥ ሆኖ ህወሃትን ብቻ እያመለከና ለህወሃት ሹማምንት እየተገዛ እንዲኖር የተጠመደበት ወጥመድ አካል እንጂ ውንጀላው የወልቃይት ጠገዴ ማህበረሰብ ከትግራይ ህዝብ ጋር የነበረውን ግንኙነት በትክክል ያላገናዘበና የግንኙነቱንም ልክ አቆሽሾ የሚገልፅ የሃሰት ውንጀላ ነው።
ለትግራይ ሲቆርሱ አያሳንሱ
ይህ ለሆዱ ያደረ ቡድን የትግራይ ነፃ አውጭ ቡድን በወልቃይት ጠገዴ ማህበረሰብ ላይ በመፈፀም ላይ የሚገኘውን የዘር ማፅዳትና አካባቢውን በትግሪያዊነት የመተካት ወንጀል መቃወምና ማውገዝ ሲሳናችውና ይልቁንም አገር ያወቀውንና ፀሃይ የሞቀውን የህወሃት ወንጀል በትግራይ ህዝብ የተፈጸመ በማስመሰል “የወልቃይትን ህዝብ ሰብአዊ ክብር የሚያዋርዱ ጥሰቶችን በዚህ መድረክ ላይ መግለፁ በህዝቦች መካከል አላስፈላጊ ቁርሾ ስለሚፈጥር እዛው ተከድኖ ይብሰል ብለናል” በማለት ከትግራይ ህዝብ ይልቅ ለህወሃት ሹማምንት ያላቸውን ወገንተኝነትና ታዛዥነት ያረጋግጣሉ።
በሌላ በኩል ግን በትግራይ ህዝብና በወልቃይት ጠገዴ ማህበረሰብ መካከል ጠላትነት እንዳይፈጠርና ቁርሾ ለትውልድ ላለማስተላለፍ በሚል ያደረጉትን “ጥንቃቄ” እና “አስተዋይነት” በእጅጉ አድንቀናል። አንድም ትላንት የፊውዳሉ ስርዓት ፈጸመ ለሚባለው ግፍና በደል ዛሬ ተከሳሽና እዳ ከፋይ የተደረገው ጭቁኑ የአማራ ህዝብ ነውና ነገም የትግራይ ህዝብ የህወሃት ሹማምንት እዳ ከፋይ እንዳይሆን ቅድመ ጥንቃቄ መደረጉ ተገቢ ነው ።
ለወልቃይት አባት ፍለጋ፡ ከትግሪያዊነት ወደ ኤርትራዊነት መንሸራተት
የወልቃይት ጠገዴ ማህበረሠብ እንደ ማንኛውም የሰው ዘር መነሻዬ የሚለው አባት፣ የእኔ የሚለውና ቆጥሮ የሚደርስበት የዘር ሃረግ፣ ይልቁንም የእኔ የሚላቸውን ታሪኮቹንና ባህሎቹን የሚመዘግብበትና የሚጠብቅበት ብሎም ከትውልድ ወደ ትውልድ የሚያስተላልፍበት የእራሱ መንገድ ያለው ታላቅና አስተዋይ ህዝብ ነው። በአጭሩ ወልቃይት ጠገዴ አባቱን ያውቃል።
ነገር ግን እንደ አብዛኛው ኢትዮጵያዊ ማንነቱን ላይ ጥያቄ ውስጥ የሚያስገባና የከፋ አደጋ ላይ የሚጥል ተግዳሮት የገጠመው በታሪኩ ለመጀመሪያ ግዜ በትግራይ ነፃ አውጭ ቡድን በኩል ወረራ ከተፈፀመበት ግዜ ጀምሮ ነው። ይህን ታሪካዊ ፈተና ለማለፍና በድል ለመወጣት ይቻል ዘንድ ወገናችን እልህ አስጨራሽ የሆነ መስዋዕትነት ከፍሏል። በመክፈልም ላይ ይገኛል።
page5image30160 page5image30320 page5image30480
5
በእነዚህ የታሪካችን የጨለማ ዘመናት በዋናነት የተጋፈጥነው ተግዳሮት ትግሬነትን እንደ ማንነታችን በመቀበል ትግሬ መሆን እና ከህወሃት ጋር ተመሳስሎ በመኖር ትግሬነትን ለትውልድ ማውረስ ወይም በአማራ ማንነታችን ፀንተን በመቆም ያለልካችን በህወሃት የተሰፋልንን ትግሬነት ባለመቀበላችን ምክንያት በጠላት በኩል ሊመጣ ያለውን ሁሉ መከራና ችግር በመጋፈጥ በማንነታችን ላይ ያነጣጠረውን ጠላት ድል መንሳት ነበሩ።
ከዚህም በመነሳት እነሆ ወገናችን ለአለፉት 37 ዓመታት በህወሃት የጭካኔና የመከራ ወጀብ ውስጥ ለማለፍ ቢገደድም የህወሃት ትግሪያዊነት የአንድም ወልቃይቴ ወይም ጠገድቼ ልብ ማማለልና ትግሬያዊ ማድረግ አልተቻለውም። እንግዲህ ሁሉም ህወሃታዊ ሴራዎች ተጨፍልቀው በግለሠብ ደረጃ የአንድን ወልቃይቴ ወይም ጠገድቼ ቀልብ መማረክ ካልተቻለው እንዴትስ አድርጐ የዚህን ኩሩና ታላቅ ህዝብ ማንነት ማስለወጥ ይቻለዋል? እንዴትስ አድርጐ ወልቃይት ጠገዴ የትግራያዊነት ቀሚስ ማልበስ ይቻላል። ለዚህም ይመስላል ሆድ-አደሮቹ በፅሁፋቸው በገፅ 2/4 አንቀፅ 2 ላይ “ትግሪያዊነት በትግራይ ክልል ባለስልጣናት በኩል በወልቃይት ማህበረስብ የተጫነ...” መሆኑን በማለት ማስተባበያ አይሉት ማስተዛዘኛ ለመስጠት የሞከሩት። ይልቁንም አበው “የጨነቀው እርጉዝ ያገባል” እንዲሉ የትግራይ ጌቶቻቸውን ለማፅናናት በሚመስል ቃና የወልቃይት ጠገዴን ማንነት ከ“ትግራይ-ትግራያዊነት” ወደ “ኤርትራ-ትግሪያዊነት” ለማንሸራተት የተገደዱት። እንዲህም ይላሉ፦
“ከትግራይ ብሄረሰብ ጋር የሚመሳሰለው በቀጥታ ሳይሆን በተዘዋዋሪ መንገድ ነው። ይኅውም የወልቃይት ባህል የሚመሳሰለው ኤርትራ ነጻነቷን ስትቀዳጅ አብሮ ከተገነጠለው ትግርኛ ከተባለው የከበሳ አካባቢ ብሄረሰብ ባህል ጋር ነው። በቋንቋም ቢሆን የትግርኛ ዘዬ ወይም ዳያሌክት ተመሳሳይነቱ ከኤርትራ ትግርኛ ጋር ነው።”
እውነታው ግን ዛሬ ተከዜን አሻግረን አርቀን ወደ ኤርትራ-ትግሪያዊነት እንደ ወረወርናቸው ሁሉ በቀጣይ የህዝባችን ጠንካራና የተባበረ ብርቱ ክንድ ሲደቁሳቸውና አዲሲቷ ማንነታቸው ገዥ አጥታ እርቃኗን ስትቀር እንደ ሌሎቹ ቀይባህርን ተሻግረው “የወልቃይት ጠገዴ ዘር የመጣው ከማዳጋስካር ነው” እንደሚሉን አንጠራጠርም። ለምን ቢሉ እንደ ዛሬ አያድርገውና ታላላቅ የሚባሉት ብሄሮች ሳይቀር “ከማዳጋስካር ነው የመጣነው” የምትለውን የህወሃት የዘረኝነት ድርሳን እያነበነቡ ያደነቁሩን ነበር የቅርብ ጊዜ ትዝታ ነው።
ወልቃይት ጠገዴ ፡ አማራ
የወልቃይት ጠገዴ ማህበረሰብ ባሳለፋቸው መራር የትግል ዘመናት እንደ ማንኛውም ትግል በተለያዩ የእድገት ደረጃዎች ውስጥ ማለፉ የግድ ነበር። ምንም እንኳ ትግላችን ከፊት ለፊቱ ከፍተኛና ወሳኝ የታሪክ ምዕራፍ የሚጠብቀው ቢሆንም በአሁን ሰዓት የህዝባችን ትግል ከፍተኛ የስኬት ደረጃ ላይ ይገኛል። ይሃውም ፦
 1. ህዝባችን ለአለፉት 37 ዓመታት በትግራይ ነፃ አውጭ ቡድን ከደረሰበት ፈርጀ ብዙ የዘር ማፅዳትና አካባቢውን በትግሪያዊነት የመተካት የተቀነባበረ ወንጀል የተረፉትን ልጆቹን በማሰባሰብና ወጣት የልጅ ልጆቹን የትግሉ አካል በማድረግ ለህልውናውና ለማንነቱ መጠበቅ ተከታታይ የሞት ሽረት ትግል የሚያደርግበት ቀውጢ ሰአት በመሆኑ፣
 2. የትግራዩ ነፃ አውጭ ቡድን ለአለፉት 25 ዓመታት የሃገሪቱን መንግስታዊ ስልጣን በመጠቀም አካባቢውን ከጋዜጠኞችና መንግስታዊ ካልሆኑ ምግባረ-ሰናይ ድርጅቶች እይታና እንቅስቃሴ ዝግ በማድረግ በወልቃይት ጠገዴ ማህበረሰብ ላይ ይፈጽም የነበረው የተቀነባበረ የዘር ማጽዳት ወንጀል ለህወሃት ፍርፋሪ ባልተንበረከኩ ፅኑ ልጆቹ ያላስለሰ ትግልና በኢትዮጵያ የቁርጥ ልጆች ሁለገብ ድጋፍ በኢትዮጵያ ህዝብና በመላው ዓለም እውቅና ያገኘበትና የአብዛኛው ጋዜጠኞች፣ ዓለም አቀፍ ፍርድ ቤቶችና፣ የሰብአዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶች እንዲሁም ሌሎች በንቃት የሚከታተሉት ግንባር ቀደም ጉዳይ ለመሆን የቻለበት ወቅት በመሆኑ፣
 3. ኢትዮጵያ ሃገራችንና ህዝቧን እያሸበረና እየዘረፈ የሚገኘው የትግራዩን ነፃ አውጭ ቡድን ከስልጣን ለማስወገድ በሰላማዊም ሆነ ነፍጥ አንስተው የሚታገሉ ኢትዮጵያዊ የፖለቲካ ድርጅቶች በወልቃይት ጠገዴ ማህበረሰብ ላይ የደረሰበትን ፈርጀ ብዙ የዘር ማፅዳትና አካባቢውን በትግሪያዊነት የመተካት የተቀነባበረ ህወሃታዊ ወንጀል እውቅና የሰጡበትና ግንባር ቀደም የሚታገሉለት አጀንዳቸው በማድረግ በችግሩ አፈታትም ዙሪያ ግልጽ የሆነ አቋም የያዙበት ወቅት በመሆኑና፣
 4. በተለይም ከላይ የተዘረዘሩትንና በተለያዩ መድረኮች ያስመዘገባቸውን የተለያዩ ድሎች በማስጠበቅ መላውን የጎንደርና የአማራ ህዝብ ከጎኑ በማሰለፍ ለሚታገልለትና ለሚታገልበት የወልቃይት ጠገዴ የአማራ ማንነት ጥያቄ! መመለስ ከምንግዜውም በላይ ቆርጦ የተነሳበት ወሳኝ የትግል ወቅት ነው።
እንግዲህ በዚህ ወቅት ነው ሆድ-አደሩ ቡድን የህወሃት ጌቶቻቸውን ለማስደሰትና ከተቻላቸውም ጠራርጎ ሊወስዳቸው ከመጣው የህዝብ ቁጣ ለመታደግ መታተራቸውን በሚያሳብቅ መልኩ “ወልቃይት እና አማራ” በሚለው የመጣጥፋቸው 2ኛው አንቀጽ ላይ “ከቋንቋ ልዩነት ሌላ ወልቃይትን ከአማራ የሚያራርቅ ብዙ ግፍ ተፈጽሞል” በማለት ቀደም ሲል “ወልቃይት እና ትግራይ” በሚለው ክፍል “በህዝቦች መካከል ሰላም ለማውረድና አላስፈላጊ ቁርሾን ለትውልድ ላለማስተላለፍ” በማለት የተመፃደቁበትን ለህዝቦች ሰላም ያላቸው አርቆ አሳቢነታቸውንና ሚዛናዊ የሚመስለው ህሊናቸው ከመቅፅበት ከድቷቸው የጎንደር/አማራ ህዝብ በወልቃይት ላይ አደረሰ የሚሉትን ሁሉ በማተት የቆሙለትና ያደሩለትን ባንዳዊ አጀንዳ ምን ድረስ እንደሆነ ያሳዩናል፡፡
page6image28936 page6image29096
6
ይህ ሴራ የወልቃይት ጠገዴ የአማራ ማንነት ጥያቄ! አጀንዳን ከታጋዩ ህዝባችን በማስጣልና እርስ በእርሱ በመከፋፈል ለከፋው የህወሃት አፀፋዊ ጥቃት ያለ አጋርና ደጀን አጋልጦ ለመስጠት የተጠነሰሰ ህወሃታዊ ሴራ መሆኑን ለመረዳት ህወሃት ቀደም ሲል በህዝባችን መካከል ሰረጎ በመግባት የሄደባቸውን መሰሪ የከፋፍለህ-ግዛ መንገዶች ወደ ኃላ መለስ ብሎ ማየቱ በቂ ነው፡፡
ስለሆነም ከነበረን ልምድና ከቀደመው ታሪካችን በመነሳት ይህን በተንበርካኪው ቡድን በኩል የቀረበልንን ህወሃታዊ ሴራ ለህዝባችንና ከጎናችን ለተሰለፈው ለኢትዮጵያ ህዝብና በተለይም ለጎንደርና ለአማራ ህዝብ ጠለቅ ብሎ በማሳየት ህወሃትን በተባበረ የህዝብ ክንድ ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ለማስወገድ በሚደረገው ትግል የበኩላችንን ለማበርከት እንሻለን።
1ሴራ፡ የአማራን ህዝብ በፈጠራ ክስ መወንጀል የአማራ ማንነት ጥያቄ! አጃንዳን ማስጣል
 1. ፀሃፊው “ወልቃይትና አማራ” የሚለውን ርዕስ መጻፍ ሲጀምሩ “ሲጀመር ወልቃይት የጎንደር እንጂ የአማራ ሆና አታውቅም” በማለት ነበር። እኛም እውነት ነው ወልቃይት የጎንደር እንጂ የማንም ሆና አታውቅም!!!!
  ለአለፉት 25 ዓመታት ወልቃይት ጠገዴ የትግራይ አካል ነው እያለ ሲያደነቁረን የነበረው እርስዎ ዛሬ የተንበረከኩለት የትግራይ ነፃ አውጭ ቡድንና ከእርስዎ ቀደመው ለህወሃት ያደሩት ቤተሰቦችዎ ናቸው። ይልቁንም ታላቋን ኢትዮጵያ በቋንቋ ሸንሽኖ በአራቱም ማእዘን የዘር ግጭት የለኮሰው እርስዎ ያደሩለትና የተወዳጁት ህወሃት ነው። ጎንደርንም አማራ ብሎ የከለለው የእርስዎ ህወሃት እንጂ ሌላ ማንም አይደለምና ከሰማዎት እንደ ወዳጅነትዎ ለደንቆሮው ህወሃት “ወልቃይት ጠገዴ የጎንደር እንጂ ... ሆና አታውቅም” ብለዋል ይበሉልን።
 2. 2ኛው አንቀጽ ላይም “ከቋንቋ ልዩነት ሌላ ወልቃይትን ከአማራ የሚያራርቅ ብዙ ግፍ ተፈጽሞል” ይላሉ።
  ከዚህ ዓረፍተነገር ጀምሮ የተከተላችው አንባቢ ሁሉ በእርግጠኝነት አንድ እውነት ያስታውሳል። ይኅውም ህወሃት በአለፉት 25 ዓመታት የስልጣን ዘመኑ የአማራውን ህዝብ ከኤርትራው፣ ከኦሮሞው፣ ከሲዳሞው፣ ከወላይታው፣ ከትግሬው፣ ከጋምቤላው፣ ...ወዘተ ለማፋጀት የቀሰቀሰበትና ብዙ የአማራ ተወላጆች ለከፋ እልቂትና ስቃይ የተዳረጉበትን የህወሃት በአማራ ህዝብ ላይ የከፈተውን የዘር ማጥፋት ዘመቻ ቅስቀሳ ያስታውሳል።
  እንግዲህ ይህ በአቶ ሃይሉ የሺወንድም ፊታውራሪነት የቀረበው ደግሞ “የወልቃይት ጠገዴ ማህበረሰብ በአማራ ህዝብ ላይ ...” በሚል ወደፊት ህወሃት በጎንደር ህዝብ ላይ በተለይም አማራነን ባሉ የወልቃይት ጠገዴ ተወላጆች ላይ ለሚያካሂደው ጭፍጨፋ መንገድ እየተጠረገ መሆኑን እንረዳለን። ለዚህም ፍጅት ቅድመ ዝግጅት አቶ ሃይሉ በፅሁፋቸው የድርሻቸውን ተወጥተዋል።
 3. ጉደኛው ፀሃፊ “በሁመራ ዘመናዊ እርሻ ምክንያት ሲገኝ የነበረው ገቢ ለደብረታቦር ትምህርት ቤት መስሪያና ለሌሎች አካባቢዎች ጥቅም ይውል ነበር። አሁን እንደሚደረገው ማለት ነው” ይሉናል።
  የሁመራ እርሻ ልማት የተጀመረው በ1950ዎቹ መጀመሪያ ሲሆን አገልግሎቱ የተቋረጠው “ገስጥ” ይባል የነበረው የደርግ ጦር በ1969 .ም ሁመራንና አካባቢውን በሃይል በወረረበትና ህዝባችንን በጀምላ በጨረሰበት ጊዜ ነበር።
  በአንፃሩ ደግሞ ዛሬ በህወሃት የሚመራው የደብረታቦር ከተማ አስተዳደር በሚያወጣው አመታዊ መጽሄት በአስተዳደሩ ስር የሚገኙ ት
  /ቤቶችን አስመልክቶ ያውጣውን መረጃ ምን እንደሚል በከፊል እንመልከት።
  ከላይ በተጨባጭ መረጃ እንደምንመለከተው የሁመራ እርሻ ልማት ከተመሰረተበት ጊዜ አንስቶ እስከ ከሰመበት ጊዜ ድረስ በደብረታቦር አውራጃ ምንም አይነት ት/ቤት እንዳልተገነባ የተረጋገጠ እውነት ሆኖ እናገኘዋለን።
  ታዲያ የዚህ “ከሁመራ እርሻ በተሰበሰበ ግብር
  ... ደብረታቦር ላይ ት/ቤት ይሰራ ነበር... ።አሁን እንደሚደረገው ማለት ነው።” የሚለው የሆድ-አደሩ ቡድን ውንጀላ መነሻው መሰረተ ቢስ እንደሆነ በተጨባጭ የተረጋገጠ ሲሆን ታዲያ የዚህ ውንጀላ ዋና አላማ ምን ሊሆን ይችላል ብሎ መመርመር ተገቢ ነው። ከህወሃት ባህሪና እስከዛሬ ካለፍንባቸው ተሞክሮዎች በመነሳት በእርግጠኝነት መናገር የምንችለው፦
1. ህወሃት በአለፉት 25 ዓመታት የጎንደርን ህዝብ ሰሜንና ደቡብ ብሎ በመከፋፈል የማንወጣው የመጠላለፍና የመፋጠጥ አዙሪት ውስጥ ለመክተት አበክሮ ሰርቷል። አላማውም ይህ የታላቋ ኢትዮጵያ ጠባቂና ተቆርቋሪ የሆነውን ህዝባችን
page7image24168 page7image24328
የት/ቤቱ ስም
የተመሰረተበት ዓ.
አድቬንቲስት ሚሽን
1926
ዳግማዊ አፄ ቴዎድሮስ
1938
ህሩይ አባ አረጋይ 1ደረጃ
1971
ጋፋት 1ደረጃ
1973
ታቦር 1ደረጃ
1976
7
ከኢትዮጵያ ላይ አይኑን እንዲያነሳና ለህወሃት ዝርፊያና ኢትዮጵያን የማተራመስና የማፍረስ ሴራ እንቅፋት እንዳይሆን በማለም ነበር። ነገር ግን በህዝባችን አስተዋይነትና በታላላቆቻችን ብርቱ ጥረት ሴራው ለጊዜው ሊከሸፋና ውጤት ማምጣት ሳይችል ቀርቷል። እነሆ ይህ በሆድ-አደሩ ቡድን የሚቀርበው የፈጠራ ውንጀላ የሴራው ቀጣይ ክፍል ነው።
 1. የህወሃት የ37 ዓመታት የዘር ማፅዳትና በትግሪያዊነት የመተካት ወንጀል ያልተሳካውና ይልቁንም ህወሃትን እስከ አንገቱ ያነቀው የወልቃይት ጠገዴ ማህበረሰብ የአማራ ማንነት ትግል እዚህ ደረጃ ላይ የደረሰው በመላው የጎንደር ህዝብ ድጋፍና ተሳትፎ ጭምር ነው። ይህ እውነታ በህወሃት መንደር ግልፅ ከሆነ ሰነባብቷል። ስለዚህም ህወሃት በለመደው ከአያቶቹ በወረሰው የከፋፍለህ ግዛ ፈሊጡ ተላላኪዎቹን በመጠቀም የወልቃይት ጠገዴ ማህበረሰብን ከአማራ ህዝብና በተለይም ከጎንደር ህዝብ ለመነጠልና ለማጥቃት የተደረገ ሴራ አካል ነው።
 2. ...አሁን እንደሚደረገው ማለት ነው።” ይላሉ።
  ዛሬ ህወሃት የወልቃይት ጠገዴን መሬት በመውረር የሚፈፀመውን ለከት ያጣ ዝርፊያ ወንጃል በዘውዳዊው ስርዓት ወቅት እንደሚደረገው አይነት ነው ብሎ በንፅፅር ማቅረብ አንድም የወልቃይት ጠገዴ ማህበረሰብ በህወሃት አልጠግብ ባይነትና አይን ያወጣ ዝርፊያ ምክንያት ህዝባችን የገባበት የበይ ተመልካችነትና የድህነት አረንቋ ላይ መዘባበት ሲሆን ይህም እጅግ አሳፋሪም ነውረኛም ነው። ፍርዱንም የትግራዩ ነፃ አውጭ ቡድን ዕርስታቸውን በመውረርና ከግማሽ ሚሊዮን በላይ የትግራይ ሰፋሪዎችን የእርሻ መሬታቸው ላይ በማስፈር ለማያውቁት ረሃብና ልመና ለተዳረጉ የወልቃይት ጠገዴ ተወላጆች እንተዋለን።
 3. ፀሃፊው ውንጀላውን በመቀጠልም “በደጃዝማች አያሌው ብሩ ግዛት ዘመን በወገራ ደጋማና ቆላማ አካባቢ የሚኖሩ አማራዎች በወልቃይት ላይ ወረራዎችና ዝርፊያዎች እንዲያካሂዱ ተደርጓል።” ይሉናል።
  እንደሚታወቀው የፊውዳሉ ስራአት አንድን ለስርአቱ አልገዛ ወይም አልገብር ያለን ወረዳ ለመቅጣትና ለማስገበር ይጠቀምበት የነበረው አይነተኛ ዘዴ ሌላውን አጎራባች ወረዳ እንዲዘምትበትና እንዲወረው ብሎም እንዲያስገብረው በማድረግ ነበር። ይህም ድርጊት በተለያዩ የጎንደር አካባቢዎች ስለመፈጸማቸው በህይወት የሚገኙ አባቶቻችንና እናቶቻችን ህያው ምስክር ናቸው። ነገር ግን ይህን ዘርንም ሆነ ማንነትን መሰረት ሳያደርግ ይደረግ የነበረን መንግስታዊ ቅጣት “የጎንደር አማራዎች” በተለይ በወልቃይት ላይ ሆን ብለው የፈጸሙት አድርጎ ማቅረብ ህወሃት የጎንደርን ህዝብ እርስ በእርሱ ለማጋጨት ከጠነሰሰው ሴራ ሌላ ምን ሊሆን ይችላል?
  እዚህ ላይ አንድ የታሪክ ማስረጃን ጠቅሰን እንለፍ። በ1949 .ም አካባቢ አዲስ ዘመን/ይፋግ አካባቢ አቶ አግማሱ ወጤ የተባለ ግለሰብ ያምፃል (ይሸፍታል)። ከእለታት በአንዱ ቀን ሊይዙት ከመጡ ወታደሮች ጋር ይታኮሳሉ። በዚህ ጊዜ የወረዳው አስትዳዳሪ የነበሩት ፊታውራሪ (ደጃዝማች) በረደድ አስፋው አቶ አግማሱ ወጤ እንዲያዝ እርዳታ ስላልሰጡ እርሳቸው የሚያስተዳድሩት ወረዳ እንዲወረር ይደረጋል። እንዲወር የተላከውም የመናመቀጠዋ ወረዳ ነበር። ለወረራ የዘመተው ወታደር ቀለቡንም ሆነ ምኝታውን የሚያገኝው በወረራ ከያዘው ማህበረስብ ስለነበር ለዚህም ሲባል በየአለቃው እየሆነ በየመንደሩ ይሰማራል። በዚህም ወረራ የከምከም ቃሮዳ ህዝብ ክፉኛ መጎዳቱ የታወቃል።ይህም ፊውዳላዊ የማስገበሪያ ዘዴ በሁሉም አካባቢ ሲተገበር የኖረ እንጂ የህወሃት ተላላኪዎች እንደሚሉት የወልቃይትን ማህበረሰብ ሆን በሎ ለማጥቃት የተደረገ አንድም ወረራ አልነበረም።
  ይልቁንም ፀሃፊው ተወልደው ባደጉበት አካባቢ የልጅነትና የወጣትነት ዘመን ላይ የተፈጸመን ተመሳሳይ እውነተኛ ታሪክ ፍጹም አጣሞና አዛብቶ ለህወሃት ሴራ በሚመች መልኩ ማቅረብ፤ አንድም ህወሃት ማኒፌስቶ ቀርፆና አካባቢውን በሃይል ተቆጣጥሮ የወልቃይት ጠገዴን ዘር አፅድቶ በትግሪያዊነት ለመተካት ከግማሽ ሚሊዮን በላይ የትግራይ ሰፋሪዎች በማስፈር የተጓዘበትን ዘግናኝ የዘር ማፅዳት ወንጃል በስመ “ወረራ” ለማቃለልና ለማድበስበስ የታለመ ሲሆን በሌላ መልኩ ደግሞ ህወሃት በአማራ ህዝብ ላይ በቀጣይነት ለሚፈጽመው የዘር ማጽዳት ፍጅት መንገድ ጠራጊ ሆነው ለማገልገል ቆርጠው መነሳታቸውንና በአማራ ህዝብ ላይ ሊያካሂዱ ያቀዱትን ግጭት በፊታውራሪነት ለመምራት የሄዱበትን እርቀት ያመላክታል።
 4. አቶ ሃይሉ “ምዝበራው አልበቃ ብሎ አባወራውን አባርረው ሚስቲቱ አስገድዶ መድፈር የተለመደ ነበር” ይላሉ።
  “የበሰበሰ ዝናብ አይፈራም” እንዲሉ እዚህ ላይ እነ አቶ ሃይሉ የሺወንድም ቀስ በቀስ የገቡበት ህወሃታዊ የክህደትና የሸፍጥ ቁልቁልት ጥልቅና መውጫ ወደሌለው እንጦሮጦስነት ሲቀየር እናያለን።
  የወልቃይት ጠገዴ ማህበረሰብ እንኳንስ በሚስቱና በዕርስቱ ለመጣበት ይቅርና በዋዛ በፈዛዛ ክብሩን ለነካ ሁሉ ምላሹ ጥይት እንደሆነ ጠላታችን ህወሃት ሳይቀር ጠንቅቆ ያውቃል። ይህን በታሪካችን ተሰምቶም ሆነ ታይቶ የማያውቅ ፀያፍ
8
ምግባር በወልቃይት ጠገዴ ማህበረሰብ ላይ እንደተፈጸመ አድርጎ ማቅረብ በቅድሚያ ከሁሉም በላይ ይህ ለሆዱ ያደረ ተንበርካኪ ስብስብ ለወልቃይት ጠገዴ ማህበረሰብ ያላችውን ንቀት የሚያሳይ ሲሆን፤ በመቀጠልም ድርጊቱን ፈጽሟል ብለው በሚከሱት የጎንደር-አማራ ህዝብ ላይ ያላቸውን ከልክ ያለፈ ጥላቻ ምን ድረስ ሊጓዝ እንደሚችል በተጨባጭ ያረጋገጠ ነው።
ለመሆኑ የትኛው ወልቃይቴ ወይም ጠገድቼ ነው ከወራሪ ወታደር የተወለደና አባቱን የማያውቅ? የትኛውስ አባወራ ነው ሚስቱን አስደፍሮ በማህበረሰቡ ውስጥ ተዋርዶ የኖረው? ከዚህ ከተዋረደ ቤተሰብ ውስጥ የተወለዱ ልጆች እነማን ናቸው? የልጅ ለጆቹስ እነማን ይሆኑ? እንግዲህ መልሱን ለእነ አቶ ሃይሉ የሺወንድም እንተዋለን።
እኛ ግን እንዲህ እንላለን። ይህን በታሪካችን ተሰምቶም ሆነ ታይቶ የማያውቅ ፀያፍ ምግባር በወልቃይት ጠገዴ ማህበረሰብ ላይ እንደተፈጸመ አድርጎ ማቅረብና ማስተጋባት የማንም ሳይሆን ዕርስታችንን በወረራ ይዞ ዘራችንን እያጥፋና አካባቢያችንን በትግሪያዊነት እየተካ የሚገኘው ህወሃት በህዝባችን ላይ ያለውን ንቀትና ጥላቻ ያሳየበት ሲሆን እስከዛሬ በህዝባችን ላይ በዝግ ለፈፀማቸውና ነገ ታሪክ ለሚያወጣቸው ግፎችና ፀያፍ ድርጊቶች ፍንጭ የሰጠበት መንገድ ነው እንላለን።
እንዲህም እንመሰክራለን። ከህወሃት በፊት በነበሩ ስርዓቶች ሁሉ እንዲህ አይነት ፀያፍ ድርጊት በወልቃይት ጠገዴ ማህበረሰብ ላይ አይደለም ሊፈፀም ይቅርና በወሬ ደረጃ ተሰምቶም እንደማያውቅ ምስክሮች ነን። ይህ የፈጠራ ክስ ህወሃት የወልቃይት ጠገዴን ማህበረሰብ ክብር ለማዋረድና አኩሪ ታሪኩን ለማንቋሸሽ የሄደበት ፀያፍ መንገድ ነው።
2ሴራ፡ የወልቃይት ጠገዴን ከአማራዊነት መነጠል
 1. ውንጀላ እና የሃሰት ምስክርነት
  ፀሃፊው በመጣጥፋቸው እጅግ አደገኛ የሆኑ ሁለት የፈጠራ ውንጃላዎችን በማቅረብ የሃሰት ምስክርነታቸውን ይሰጣሉ።
  1. በስደት የሚገኙት የወልቃይት ጠገዴ ተወላጆች በአሁኑ ሰዓት በሀገር የተቀጣጠለውና የአማራ ምንነት እንቅስቃሴ የሚመሩ ወገኖችን አጀንዳውን ያገኙት የተሰጣቸው ከዲያስፖራው ነው የሚል ሲሆን፤
  2. “የወልቃይት አማራ ማንነት እንቅስቃሴ በአጭር ጊዜ ተደማጭነት ያገኘው ... የብአዴንን ቡራኬ ስላገኘ ” በማለት የወገናችንን የዘመናት ትግልና መስዋዕትነት ውጤት የሆነውን ይህን ታላቅ ድል እራሱን እንኳ ከህወሃት ቁንጥጫ ማዳን ለማይቻለው የብአዴን ባርኮት ያደርጉታል።
  እነዚህ ሁለት ውንጀላዎች ህወሃት ከመጀመሪያው ጀምሮ የሚያላዝንባቸውና አሁንም ወገኖቻችንን ለማሸማቀቅና እንደለመደው አፍኖ ለማጥፋት የሚያደርገው ቅድመ ሁኔታ ነው። በተለይም በአለፉት የእንቅስቃሴው የመጀመሪያ ወቅቶች የነበረው ህወሃት ሌላውን ተላላኪውን አቶ ፈረደ የሺወንድምን ወደ ጐንደር በመላክ የእንቅስቃሴውን የኮሚቴ አባላት ለማስፈራራት መሞከሩ የሚታውቅ ሲሆን በእንቅስቃሴው አመራር አባላት መካከል አንዳችም አይነት ጉዳት ቢደርስ ተጠያቂ የሚሆነው አቶ ፈረደ እና ግብረ አበሮቹ እንደሆኑ የኮሚቴው አባላት ለቤተሰቦቻቸው መናገራቸውን ልብ ይሏል።
  አሁንም ይህ ተመሳሳይ ውንጅላ በአቶ ኃይሉ የሺወንድም መደገሙ “አያ ጅቦ ሳታማኽኝ ብላኝ” ያለችው እንሰሳ ታሪክ ያስታውሰናል። ስለሆነም በኮሚቴው አባላት ላይና የወልቃይት ጠገዴ የአማራ ማንነት ጥያቄ! ፊርማ ማስባሰቢያ ሰነድ ላይ በፈረሙ የወልቃይት ጠገዴ ተወላጆች ላይ የሚደረሰው ማንኛውም ህወሃታዊ አፈና እና ጥቃት ግንባር ቀደም ተጠያቂ የሚሆኑት በመግቢያችን እንደገለፅነው በዋናነት ወ/ሮ አዜብ መስፍን፣ አቶ ፈረደ የሺወንድም፣ አቶ ሃይሉ የሺወንድም፣ አቶ ፀጋዬ አስማማው እና የጥቅም ታጋሪዎቻቸው መሆናቸውን ከወዲሁ ልናረጋግጥ እንወዳለን።
 2. ወልቃይትን ከጠገዴ መነጠል
  ቡድኑ በመጣጥፉ በገፅ 5, 2ኛው አንቀጽ ላይ “ወረራውና ዘመቻው እንደ ባህል ሆኖ፣ እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ በጠገዴው ተወላጅ በክቡር ቢትወደድ አዳነ መኮንን አስተዳደር ሳይቀር በየምክንያቱ ተመሳሳይ ዘመቻዎች ተካሂደዋል። የቢትወደድ ቀብቲያ ላይ በጥይት መቁሰልና የጀግናው ወጣት አርበኛ ወልቃይቴ የመኮነን በርሄ (ጎንደሬ በጋሻውን ያንብቡ) መገደል ከዚህ አይነቱ ዘመቻ ጋር የተያያዘ ነበር።” ይለናል።
  በክቡር ቢትወደድ አዳነ መኮንን የአስተዳደር ዘመን በወልቃይት ላይ የተፈጸመው ወረራ ከላይ በሰፊው እንደገለፅነው የፊውዳሉ ስርአት አንድን ለስርአቱ አልገዛ ወይም አልገብር ያለን ወረዳ ወይም አንገዛም ያሉ ግለሰቦች (ሽፍቶች) ለመቅጣትና ለማስገበር ይጠቀምበት የነበረው አይነተኛ ዘዴ ሌላውን አጎራባች ወረዳ እንዲዘምትበትና እንዲወረው ብሎም እንዲያስገብረው የማድረግ አንዱ አካል ነው። ከዚህም በመነሳት በዘመኑ በወልቃይት ማህበረሰብ እንደ ጀግና በፊውዳሉ
page9image25992
9
ስራአት ደግሞ እንደ አመፀኛ ይቆጠር የነበረው ወጣቱ አርበኛ መኮነን በርሄን ለመያዝና ለመንግስት ለማስረከብ የታዘዘው የክቡርነታቸው አስተዳደር ነበር።
ይሁን እንጂ ክቡር ቢትወደድ አዳነ መኮንን ምንም እንኳ በመንግስት መኮነን በርሄን ይዘው እንዲያቀርቡ ቢታዘዙም ወደ ወልቃይት ጦር አላዘመቱም። ይልቁንም እራሳችው ከጥቂት ወታደሮቻቸው ጋር ወደ አካባቢው በመሄድ የወልቃይትን ፊታውራሪዎች በማማከር በሽምግልና ምህረት ተደርጎለት እንዲገባ ይስማማሉ። መኮነን በርሄንም እኛ ዋስ እንሆንሃለን በማለት የእራሱ ዘመዶች ፊታውራሪዎቹ ክቡር ቢትወደድ አዳነ መኮንን ዘንድ ይዘውት ይቀርባሉ። እሳቸውም አባታዊ ምክራቸውን ለግሰው ዋስ እንዲጠራ ይጠይቁታል። እርሱም በሽምግልና ያመጡትን ፊታውራሪዎች ለዋስትና ቢጠይቅ ከወንድሞቹ አንድም የሚዋሰው ሰው ያጣል። በዚህም ጊዜ በሽምግልና ባመጡት ዘመዶቹ ክህደት የተናደደው ጀግና መታሰሬም ሆነ መሞቴ አይቅርልኝም በሚል ደብቆ በያዘው ሽጉጥ ክቡር ቢትወደድ አዳነ መኮንን ያቆስላል። በወቅቱም ቢትወደድ ከወደቁበት ሆነው እንዳትገሉት በማለት ያስጠነቀቁ እንደነበርና ነገር ግን እዛው የነበሩት ሁሉ ተረባርበው እንደገደሉት ታሪክ ህያው ምስክር ነው።
እውነታው ይህ ሆኖ እያለ ሆን ተብሎ ታሪክን በማጣመም በጠገዴ ተወላጆች አማካኝነት በወልቃይት ማህበረሰብ ላይ የተፈፀመ ወረራ አድርጎ ማቅረብ ይልቁም አንድ አካል አንድ አምሳል ከሆነው የጠገዴ ህዝብ የተገኙት ጀግናው አባታችን ክቡር ቢትወደድ አዳነ መኮንን ሆን ብለው ወልቃይትን ለመበቀል የዘመቱና በወልቃይት ጠገዴ ህዝብ ዘንድ እንደ ጠላት ወይም በዳይ እንደሚቆጠሩ ተደርጐ መቅረቡ እጅግ የተሳሰተና ከእውነታውም የወጣ ነው። እርግጥ ነው ክቡር ቢትወደድ አዳነ መኮንን ወደ ወልቃይት የዘመቱበት ጊዜ አለ። ይኸውም ለጣሊያን ባንዳ ሆነው አገር የከዱትን ደጃዝማች ለመያዝና ለመቅጣት እንደነበር ታሪክ በደማቁ ፅፎታል።
ከዚህም በመነሳት ቀደም ሲልም ፀሃፊው “በህዝቦች መካከል ሰላም ለማውረድና አላስፈላጊ ቁርሾን ለትውልድ ላለማስተላለፍ” በማለት ስለትግራይና ወልቃይት ህዝብ ፍቅርና ሰላም የተጨነቁትና የተጠነቀቁትን ያህል በዚህኛው የፅሁፋቸው ክፍል በጠገዴና በወልቃይት ማህበረሰብ መካከል ምን አይነት ፍቅርና አንድነት ለመገንባት እንዳሰቡና እንደጣሩ ከወዲሁ መመልከት ይቻላል።
በመጀመሪያ አንድ የታሪክ ማስረጃ እናቅርብ። ጣሊያን ኢትዮጵያን ለቆ በወጣ ማግስት የስሜን አውራጃ ህዝብ ጣሊያን ባደረሰበት ግፍና መከራ የተነሳ እጅግ በከፋ ድህነት ውስጥ እንደሚገኝና እንደሚሰቃይ፤ የዘመኑንም ግብር የመክፈል አቅም እንደሌለውና ምህረት እንዲደረግለት ለአፄ ኅይለስላሴ መንግስት ጥያቄ ያቀርባሉ። ነገር ግን ጥያቄውን ያልተቀበለው የአፄ ኅይለስላሴ መንግስት የስሜን አውራጃ በሰላም እንዲገብርና ፈቃደኛ ካልሆነ በሃይል እንዲገብር ትእዛዝ ይተላለፋል። ይህንም እንዲያስፈፅም ከመንግስት የታዘዘው የክቡር ቢትወደድ አዳነ መኮንን አስተዳደር ነበር። እንደተለመደው የክቡር ቢትወደድ አዳነ መኮንን ጦር ፊታውራሪ አጥናፉ መሸሻ የሚገኙበትን የስሜን አውራጃን ለመቅጣትና ለማስገበር ይዘምታል። በዚህም ጦርነት የቢትወደድ አዳነ መኮንን ጦር ይሸነፍና ቢትወደድ አዳነም ቆስለው ይማረካሉ። ይሁን እንጂ ፊታውራሪ አጥናፉ መሸሻ የዘመቱባቸውን ቢትወደድ አዳነን በክብር ተቀብለውና ይቅርታ ጠይቀው፣ የራሳቸውን በቅሎ በመስጠት ወደ መጡበት መልሰዋቸዋል።
ከዚህ ታሪካዊ እውነታ የምንረዳው ነገር ቢኖር ከላይ እንዳየነው ወደ ወልቃይት የዘመቱት አማራው የጠገዴው ተወላጅ ክቡር ቢትወደድ አዳነ መኮንንና ጦራቸው ወደ ሌላኛው አማራ ወደሆነው የእነ ፊታውራሪ አጥናፉ መሸሻ የስሜን አውራጃ ግዛት ለማስገበር በማእከላዊው መንግስት ትእዛዝ መዝመቱን እንረዳለን። ይህም ድርጊት በመላው ኢትዮጵያ ሲሰራበት የነበረ አሰራር ነበር።
ከእነዚህ የታሪክ እውነታዎች በመነሳትና “በህዝቦች መካከል ሰላም ለማውረድና አላስፈላጊ ቁርሾን ለትውልድ ላለማስተላለፍ” በማለት ስለትግራይና ወልቃይት ህዝብ ፍቅርና ሰላም የተጨነቁትና የተጠነቀቁትን በማየት የእነ አቶ ኃይሉ የሺወንድም በክቡር ቢትወደድ አዳነ መኮንን ጦርና በጠገዴ ላይ ያቀረቡት ውንጀላና ክስ ስንመለከት አላማው ግልፅ ይሆናል። ይኸውም ወልቃይትና ጠገዴ የማይነጣጠሉ የአንድ ሳንቲም ሁለት ገፅታ መሆናቸው አይደለም የወልቃይት ጠገዴ ማህበረሰብ ወራሪው ጣሊያንም ያውቀዋል።
ነገር ግን አንድ የጠገዴን ህዝብ ከሁለት በመክፈል ግማሹን ወደ ጎንደር/አማራ ሌላውን ግማሽ ደግሞ ወደ ትግራይ በመከለል ሁለት ጠገዴ የፈጠረው ተስፋፊውና ወራሪው የትግራይ ነፃ አውጭ ቡድን ከጠገዴ ማህበረሰብ በኩል የደረሰበትን “አንድ ጠገዴ እንጂ ሁለት ጠገዴ የለም!” የሚለውን የህዝብ ተቃውሞ ለማፈንና በወልቃይት ማህበረሰብ ከተቀጣጠለው የወልቃይት የአማራ ማንነት ጥያቄ! ጋር የተፈጠረው የትግል አንድነትና ትብብር ለማዳከምና ነጥሎ ለማጥቃት ሲል ህወሃት በተላላኪዎቹ በኩል የከፈተው የመከፋፈል ዘመቻ አካል መሆኑን ወገናችን ጠንቅቆ ይረዳል።
page10image26608
10
የሆድ - አደሮቹ አጀንዳ
 1. “የወልቃይት አማራ ማንነት ኮሚቴ አባላትና ደጋፊዎቻቸው ከተመደበላቸው ስራ ጎን ለጎን ለስታተስ ኮ አንቲ ቅድመ ሁኔታ መሳካት ትርጉም ያለው ጥረት ማድረግ ይጠበቅባቸዋል።” በማለት ከ 7 ገፅ በላይ በመፃፍ ለከሰሱትና ለወነጀሉት ታጋይ ህዝብና ኮሚቴ የራሳቸውን አጀንዳ ሊጭኑበት ይሞክራሉ።
  የዚህ አጀንዳ ምንጩና አላማው አንድና አንድ ነው። ይኸውም በወልቃይት ጠገዴ ማህበረሰብ ላይ ከ37 ዓመታት በላይ የተፈፀመው ዘርን የማፅዳትና አካባቢውን በትግሪያዊነት የመተካት ወንጀል በዓለም አደባባይ መጋለጡ፣ የኢትዮጵያ ህዝብ ከጎናችን መቆሙና፣ ይልቁንም ህዝባችን በጎንደርና በመላው የአማራ ህዝብ ደጋፍና ትብብር ታሪካዊ የተባለለትን ህዝባዊ ጥያቄ አንግቦ በአንድነት መነሳቱ ህወሃት በሃይል የወሰደውን የጎንደር ለም መሬት እንዲመልስ የሚይስገድድ ከሆነ፤ በስመ ምርጫ በሃይል የወረረውን ወልቃይት ጠገዴን ህጋዊ አድርጎ ለመጠቅለል የታለመ ቀጣይ ሴራ እንደሆነ እንረዳለን።
  እኛ የወልቃይት ጠገዴ ማህበረሰብ ማንነታችንን በሚመለከት “ህዝበ ውሳኔ” የምንሰጥበት መነሻም ሆነ መድረሻ ምክንያትና ግብ የለንም፡፡ ሊኖረንም አይችልም፡፡ መፍትሄውም እጅግ በጣም ቀላልና ግልፅ ነው፡፡ ይኸውም መሬታችንና ማንነታችን ከ1983 .ም በፊት ወደነበረበት ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ይመለስ፡፡ አራት ነጥብ!!!
 2. ህወሃት ዛሬ በተላላኪዎቹ በኩል “የትግራይ ሰፋሪዎችን ከወልቃይት ጠገዴ ማስወጣት” እያለ የሚያናፍሰው ወሬና የሚዘራው መርዝ፤ ትላንት በተመሳሳይ መልኩ ጠፍጥፎ በሰራቸው ተላላኪዎቹ አማካኝነት አባቶቻችን ውድ ህይወታቸውን ሰውተው በክብር ባቆዩልን ሃገራችን ውስጥ የሚኖሩ የአማራ ተወላጆችን ለዘመናት ከኖሩባቸውና ጎጆ መስርተው፣ ልጆች ወልደው አሳድገውና ድረው፣ ሃብትና፣ ንብረት አፍርተው በሰላም ከሚኖሩባቸው የኦሮሚያ፣ የቤንሻጉል፣ የጋምቤላና፣ የደቡብ ክልሎች በጀምላ እንዲባረሩና ሜዳ ላይ እንዲወድቁ የተደረገበትን በእጅጉ ያሳዘነንና ያስቆጣንን እኩይ ድርጊት በትግራይ ተወላጆች ላይ እንዲደገም የታለመ ሴራ እንደሆነ ጠንቅቀን እናውቃለን። ይልቁንም “በህዝቦች መካከል ሰላም ለማውረድና አላስፈላጊ ቁርሾን ለትውልድ ላለማስተላለፍ” በማለት የተመፃደቁበትና ለህዝቦች ሰላምና ለትውልድ አርቆ አሳቢ ለመምሰል የሞከሩበት ብዕራቸው ነጥፎ “የትግራይ ሰፋሪዎችን ከወልቃይት ማስወጣት” በማለት በህዝቦች መካከል የማይበርድ እሳት ሲጭሩ እንመለከታለን።
  እኛ ግን ከዚህ ቀደምም ባወጣናቸውና ለህዝብ ይፋ ባደረግናቸው ሰነዶችና የመፍትሄ ሃሳቦች ደጋግመን በግልፅ እንዳስቀመጥነው ሁሉ ዛሬም በድጋሚ አቋማችንን እንደሚከተለው አቅርበናል።
  ኢትዮጵያ ሃገራችን ሁሉም ኢትዮጵያውያን በሰላም፣ በፍቅር፣ በመከባበር፣ በእኩልነትና፣ በአንድነት የሚኖሩባት የጋራ ቤታችን ናት! መሆን አለባት የሚል ፅኑ እምነት አለን። ማንኛውም ኢትዮጵያዊ/ት በማንኛውም የኢትዮጵያ ክፍል በነፃነት ተንቀሳቅሶና የዜግነት መብቱ ያለአንዳች ገደብ ተከብሮለት፤ በሰላም ሰርቶ ሃብት የማፍራት፣ ጎጆ መስርቶ የመኖርና፣ ለጆች ወልዶ የማሳደግ ፍፁም እኩል መብት አለው፤ ሊኖረውም ይገባል የሚለው የቀደምት አባቶቻችን ኢትዮጵያዊ መርሆ ለወልቃይት ጠገዴ ማህበረሰብ ከትውልድ ትውልድ ሲተላለፍ የኖረና እኛም በተግባር የኖርንበት ኢትዮጵያዊ ማንነታችንና እንደ አንገት ማተባችን የምንጠብቅው ቃልኪዳናችን ነው። ለዚህም ተቀዳሚው ምስክራችን የትግራይ ህዝብ ነው።
  ስለሆነም ማንኛውም በህወሃት ሴራም ሆነ የሃሰት ፕሮፖጋንዳ ተወናብዶ ወይም ሰርቶ ለመኖርና ልጅ ወልዶ ለማሳደግ ወደ ወልቃይት ጠገዴ በህወሃት የሰፈራ ዕቅድ ምክንያት የሰፈረ ማንኛውም ኢትዮጵያዊ ዜጋ እንደ ቀድሞው ሁሉ የወልቃይት ጠገዴን የጎንደር-አማራ ብሄርተኝነትና አስተዳደር ተቀብሎ እስከኖረ ድረስ የዜግነት መብቱ ሙሉ በሙሉ ተከብሮለት ሊኖር ይገባል ይሚል ፅኑ እምነትና አቋም አለን። ለዚህም መብት መከበር አበክረን እንሰራለን።
ማጠቃለያ
እራሱን የትግራይ ነፃ አውጭ እያለ የሚጠራው ፀረ-ኢትዮጵያ፣ ፀረ-ሰላም ቡድን ከ1972 .ም ጀምሮ በወረራ በያዘቸው የጎንደር ታሪካዊ መሬቶች ላይ በሚኖሩ የወልቃይት ጠገዴና የጠለምት አማራ ተወላጆች ላይ ያደረሰው የዘር ማፅዳትና በትግሪያዊነት የመተካት ዓለም-አቀፍ ወንጀል በአስቸኳይ እንዲቆምና አፋጣኝ የመፍትሄ እርምጃዎች እንዲወሰዱ የሁሉንም ሰላም ወዳድ የሰው ዘር ድጋፍ
page11image23152 page11image23312
11
የምንሻበት ሁኔታ ውስጥ እንገኛለን። በተለይም ላለፉት 37 ዓመታት የህወሃትን ህገ-ወጥ መስፋፋትና ወረራ ለመግታት በሁሉም አቅጣጫ ሲታገል የኖረው ህዝባችን፤ ዛሬም ያለውን ሃይል በማሰባሰብና ትግሉን በወጣት ልጆቹ በማጠናከር ከፍተኛ መሰዋዕትነት እየከፈለ ይገኛል።
በአንፃሩ ህወሃት ዛሬም ቢሆን በስግብግብነት የያዝውን በአያት ቅድመ-አያቶቻችንን ክቡር አፅም የተዋጀችውን ዕርስታችንን በሰላማዊ መንገድ ላለመልቀቅ እንደቆረጠ የሚያሳዩ ተጨባጭ መረጃዎች ይታያሉ። በተለይም የህወሃት የ2ዜግነት ጥቅማጥቅም ያንበረከከው ቡድን አማካኝነት ታጋዩን ህዝባችን ለመከፋፈልና ለማዳከም ሲል ብቻ ጋምቤላውያንን ከመሬታቸው በሃይል በማፈናቀል ለነዚህ ሆዳሞች በገፍ እያከፋፈለና የሃገሪቷን ገንዘብ ሳይቀር እየረጨላቸው እንደሚገኝ በተጨባጭ መስረጃ ለማረጋገጥ ችለናል።
ይሁን እንጂ ይህ ከወራሪው የጣሊያን መንግስት የተቀዳ ህወሃታዊ ሴራ እጅግ ያረጀና ያፈጀ፣ የኢትዮጵያ ህዝብ በተለይም ወልቃይት ጠገዴና ጠለምት ጠንቅቆ የሚያውቀው በመሆኑ ህዝባችን አንድነቱንና ፅናቱን ጠብቆ፣ ለሆድ አደሮች የማደናገሪያ ጩኸትና፣ የማዘናጊያ ድርድሮች ጆሮውን ሳይሰጥ፤ ያነገበውን የወልቃይት ጠግዴና ጠለምት የአማራ ማንነት ጥያቄ! ከግቡ ሳያደርስና፣ የጀመረውን ዘሩን የማዳንና የአባቶቹን ዕርስት የማስመለስ ትግል በድል ሳያጠናቅቅ እንደማይመለስ ፅኑ እምነታችን ነው።
በመጨረሻም የወልቃይት ጠግዴና ጠለምት የአማራ ማንነት ጥያቄ! በውስጡ የሚከተሉትን ቅድመ ሁኔታዎችና የመዳረሻ መፍትሄዎች ያካትታል።
1. ወደ ቀደመው የጎንደር ግዛት መመለስ
ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ታሪካዊና መልክዓምድራዊ አካላችን ወደሆነው ጎንደር/የበጌምድር ግዛታችን መመለስ! ይህም ማለት ማንኛውንም መሰረታዊ የማንነታችን መገለጫዎች የሆኑትንና በተለይም ባህላችንና ቋንቋችን በነፃነትና ያለምንም ገደብ መጠቀም ወደምንችልበት ሁኔታ መመለስን ያካትታል፡፡ እነርሱም፡- በክልላችን ውስጥ በሚካተቱ በማንኛውም መንግስታዊም ሆኑ መንግስታዊ ያልሆኑ ተቋማት፤ እንዲሁም በትምህርት ቤቶች አማርኛ ቋንቋችን የመጠቀም መብታችን ያለምንም ቅድመ ሁኔታ መከበር፣ ታሪካዊ መጠሪያ ስማቸው ተቀይሮ በትግሪያዊ ስሞች የተተኩትን ት/ቤቶች፣ መንገዶችና፣ የአካባቢዎች ወደ ቀደመ ይዞታቸው መመለስና የመሳሰሉትን ጉዳዮች ያካትታል።
2. ዕርስት ለባለ ዕርስቱ
የተፈናቀሉትና የተሰደዱት የአካባቢው ተወላጆች ወደ ዕርስታቸውና ቀያቸው በመመለስ ያለምንም ቅድመ ሁኔታ የርስታቸው ባለቤት ማድረግ፡፡ ከስደት ተመላሹ ወገናችን ከዜሮ የሚጀምረውን ታሪካዊ ኑሮ ብዙ የሚባልላቸው ጉድለቶች እንደሚያጋጥሙትና በጊዜ ሂደት ሊሟሉ የሚችሉ የመሆናቸው ነገር እርግጥ ቢሆንም መሰረታዊ የሆኑት የማህበራዊ ህይዎት ግብአቶች እንዲሟሉለትና አካባቢው ሰላምና መረጋጋት ሰፍኖበት ኑዋሪዎቹም ያለስጋት ሰላማዊ የዕለት ከዕለት ቀጣይ ኑሮዋቸውን በአስተማማኝ ሁኔታ እንዲያከናውኑ ማስቻል ያስፈልጋል።
3. ወንጀለኞችን ለፍርድ ማቅረብ
አካባቢችን ከፍተኛ ወንጀል የሚፈፀምበትና እስከ አሁንም ድረስ ለማንኛውም ገለልተኛ አካላት ዝግ ነው። በተለይም መንግስታዊ ላልሆኑ የሃገር ውስጥና የውጭ ሃገር ድርጅቶች፣ ለጋዜጠኞች፣ ለሰብአዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶች በአካባቢው መንቀሳቀስ እንደማይችሉ ይታወቃል፡፡ በመሆኑም አካባቢው ለማንኛውም ገለልተኛ አካል ምርመራና እይታ ክፍት እንዲሆን በማድረግ የህወሃት አፈናና ወጥመዱ ተሰብሮ የወገናችን በደልና ስቃይ ለዓለም ሰላም ወዳድ ህዝቦች እንዲደርስ በማስቻል፣ የተፈፀመው ወንጀል በገለልኛና ነፃ አካላት እንዲጣራ በማድረግ ወንጀለኞቹን ለፍርድ ማቅረብ የግድ ይሆናል፡፡ በዚህም ለዘመናት የፈሰሰው የወገናችን እንባ ይታበሳል፤ ዓለማችንም ለወንጀለኞ ማምለጫ ቦታ እንደማይኖራት ይረጋገጣል።
4. የትግራይ ሰፋሪዎችን መልሶ ማቋቋም
በህወሃት የትግሪያናይዜሽን እኩይ ወጥመድ ተጠልፈው በወለቃይት ጠገዴና ጠለምት አካባቢዎች ሰላማዊና የተደላደለ ኑሮ መኖር የጀመሩትን የትግራይ ሰፋሪዎች ደህንነታቸውና ምቾታቸው ተጠብቆ ይኖሩ ዘንድ መርዳትና ማስቻል። ይኸውም እነዚህ ከ1972 .ም ጀምሮ ከትግራይ አካባቢዎች በተለያየ መንገድ መጥተው በዕርስታችን የሰፈሩት የትግራይ ሰፋሪዎች እንደፍላጎታቸው ወደ ትግራይ የመመለስ ድጋፍ ሊደረግላቸው ይገባል እንላለን፡፡
በመጨረሻም
ይህ ወቅታዊና ታሪካዊ ሰነድ እንዲዘጋጅ ከጅምሩ ግፊት ያደረጉ፣ በአዘጋጅነት ተመድበው የሰሩ፣ እጅግ ጠቃሚና አስፈላጊ የታሪክ ማስረጃዎችንና ሰነዶችን ያደረሱንና፣ በአጠቃላይ ሙሉ ድጋፋቸውን በመስጠት ከጎናችን ላልተለዩን በሃገር ውስጥና በውጭ የምትገኙ ወገኖቻችን ላቅ ያለ ምስጋናችን ይድረሳችሁ።
በሌላ በኩል በጉዳዩ ያገባናል ያሉ አያሌ ምሁራንና ድርጅቶች የህወሃትንና የተላላኪዎቹን ሴራ ለማጋለጥና ትክክለኛውን ታሪካዊ እውነታ ለኢትዮጵያውያን ለማድረስ ያዘጋጇቸውን ሰነዶች ለጊዜው እንዲያዘገዩልን በጠየቅናቸው መሰረት መልካም ፈቃዳቸውንና ቀና ትብብራቸውን ቸረውናልና ላቅ ያለ ምስጋናችን ይድረስልን።
page12image26056 page12image26216 page12image26376 page12image26536 page12image26696 page12image26856
12

ይልቁንም የህወሃትና ግፍና ጭካኔ ለወገንና ለዓለም ህብረተሰብ ለማጋለጥ በምናደርገው ትግል ከጎናችን ለተሰለፋችሁና መልእክቶቻችን በወቅቱ ለሚመለከተው ሁሉ ላደረሳችሁልን ድህረገጾች፣ ጋዜጣዎች፣ ሬዲዮኖችና ቴሌቪዥኖች ባጠቃላይ የህዝብ መገናኛ አውታሮች ሁሉ ከፍ ያለው ምስጋናችንና አክብሮታችን ይድረሳችሁ፡፡
ማንኛውንም አስትያየት፣ መርጃ፣ ወይም ጥያቄ በሚከተለው አድራሻ ለአዘጋጆቹ ሊያደርሱን ይችላሉ።
አባይ መንግስቱ፣ ቻላቸው ዓባይ፤ ጐሹ ገብሩና፣ አብዩ በለው
aamg50@yahoo.com
page13image3856
ኢትዮጵያ ለዘላለም በክብር ትኑር! ድል ለህዝባችን!
ጥር 192008 .
13 

No comments:

Post a Comment