Thursday, February 11, 2016

የኢትዮጵያ ሕዝባዊ አብዮታዊ ፓርቲ ወጣት ክንፍ ድርጅት (ኢሕአፓ ወክንድ) Ethiopian Peoples Revolutionary Party Youth League (EPRP YL)

ፀረ- ወያኔው ትግል ይፋፋም!

የወያኔን ጸረ-ዴሞከረሲያዊንት ለማስረገጥ ሐቁ ሞልቶ መፍስስ ከጀመረ ብዙ ዓመታትን አስቆጠረ። ወያኔ ለህግ የበላይነት ይገዛል ብሎ ማስብ ከእባብ እንቁላል እርግብ እንደመመኘት ይሆናል ብንል ማጋነን አይሆነብንም። ወያኔ ክፍጥረቱ ጀምሮ እሰክዛሬ ድረስ ከሐቅ ተጣልቶ፣ ሀሰተን አንግሶ፣ ጥላቻን ተላብሶ በማደናገርና በማወናበድ ፓሊሲ የተመራ በመሆኑ አሁንም እድሜውን ጨርሶ በማብቂያው አዝማሚያ ያላደገበትን፣ ያልለመደውን ፍትህና ዴሞከርሲያዊ ባህሪ እንዲያሳይ ልንጥብቅ ከቶ አይግባም።
እኛ ወያኔ ከነግሳንግሱ ወደ ታሪክ ትቢያ እንዲወርድ ከመታገል ሌላ አማራጭ የለም ብለን በፅኑ የምናምንና በቀቢፀ ተሰፋ የተሞላን ሰላልሆን፣ ከወያኔ ነጻና ፍትሀዊ ምርጫን አንጠብቅም። ዱባና ቅል አበቃቀሉ ለየቅል እንዲሉ ወያኔና ሐቅ ሁሌም ለየቅል መሆናቸውን ጠንቅቀን እናውቃልንና ። ዴሞከሪሲ ስንል የህዝብ ልዕልና፣ ነጻ ዳኝነት፣ የህግ የበላይነት፣ የሰብዓዊ መበቶች መረጋገጥና የዜጎች እኩልነት እውን መሆን ማለት ነው። የወያኔ ዴሞክራሲ ጭንጋፍ ሳይሆን ጨርሶ የማይፀነስ ለመሆኑ የህክምና መዝገበ-ቃላትን መግለጥ ከቶም አያይሻም ።
ወያኔ ለዴሞክራሲ መካን መሆኑ ለተለጣፊዎችና ለታማኝ ተቃዋሚዎች አልከስት ያለ በሽታ ቢሆንም ለሀገርና ወገናቸው በሚታገሉ ዜጎቿ ግን ከታወቀ ዘመናትን አስቆጥሮአል። የዴሞከራሲ መገለጫው ህዝብ ወሳኝ ሆኖ በሀገሩ ጉዳዮች ፍላጎቱ ሲንጸባረቅና መብቶቹ ሲከበሩለት ነው።
ሀገራችን ኢትዮጵያ እንደህዳር በሽታ ለወያኔ ዘረኛ ወረርሽኝ ተጋልጣ ህልውናዋ በየቀኑ አየተሸረሸረ መሆኑ የአደባባይ ምስጢር ነው። ወያኔ ኢትዮጵያንና ኢትዮጵያዊነትን አላቅቆ፣ ገነጣጥሎና አሽመድምዶ ሊያጠፋት የቆመ ሀይል መሆኑን ማውቅና መገንዝብ ተገቢ ነው።
ራሱን ያወቀ ጠላትን ያወቀ ነው። ስለሆነም ለምን እንደሚታገል፤ ማንን እንደሚታግልና እንዴት መታገል እንዳለበት የተረዳ ብቻ ነው አሸናፊ ሊሆን የሚችለው። ስለትግል ስናወራ የወያኔን አፈጣጠርና ባሀሪ መረዳት ይኖረብናል። ተጨባጭ እውነታዎችን ሳያድበሰብሱ መመልከት፤ መመርመረና መገንዝብ ያሻል። ወያኔ ትናንት የደረሰበት ደረጃ ላይ የደረሰው ብቻውን ባደረገው ጥረት አይደለም። እስዛሬም እድሜው የረዘመው በውጭ ጠላት አጋዥነትም ሆነ በእነ ስብሃትና በረከት ተዋናይነት ብቻ ሳይሆን የአባትህ ቤት ሲዘረፍ አብረህ ዝረፍበሚሉ እበላ ባዮች፤ አገር አዋራጆችና አስምሳዮች በመብዛታቸው ነው ብንል ከሀቅ የራቅን አይመስለንም።
ዛሬም ከ24 ዓመት በዃላ በወያኔ ሙሉ ቁጥጥር ሥር በሚካሄድ ምርጫ ስለመሳተፍ የሚያላዝኑ ፖለቲክኞችመድረኩን ማጣበባችው ሳይገርመን፣ በምርጫ ሥም የዴሞከረሲያዊ ምርጫን መመዘኛ ማንሳት እርኩስ ለአሪዎስ እንደሆነ የሚስብኩና ለወያኔ ራሱን በራሱ የመምረጥ ቲያትር ተዋንያን የሆኑ ዛሬም አሉ። አንዳንዶቹ እንዲያውም የወያኔ አይነተኛ መርዝ የሆነውን ጎሰኝነት እንዳለ ገልብጠው እንደ አዲስ ራዕይ እያስፋፉ ወጣቱንም በዚሁ መረባችው ለማጥምድ
ሲወራጩ መታየታችው ገሀድ ነው። ሌሎች ደገሞ ትግልና ንግድ ተወራራሽ ሆኖባችው በትግል ሥም ለመከብር ደፋ ቀና ሲሉ የታያል።
በአሁኑ ጊዜ የኢትዮጰያ ህዘብ ክመቼውም ጊዜ በከፋ የኑሮና የፍትሀ እጦት እየተስቃይ መሆኑ ግልፅ ነው። ህዝቡ የኑሮ ውድነቱን መቋቋም አልቻለም። መላ ሀገራችንን ለጥፋት ለመዳረግ በሥልጣን ላየ የተሰየመው አገዛዝ በመሠረቱ ጸር-ህዝብ መሆኑ የሚጠበቅ ቢሆንም፣ በህዝብና በአገር ላይ የሚያደርሰውን በደል ማውገዝ፣ የህዝቡን ትግል ማገዝና እንደቀደምቶቹ የኢሕአወሊ ወጣቶቸ በትግሉ ወላፈን ውስጥ በግንባር ቀደምትነት መካፈል፣ የእኛ የወጣቶች ታሪካዊ ሃላፊነትና ግዴታም ጭምር መሆኑን ኢህወክንድ እንደገና መግለጥ ይወዳል ።
በኢህአወሊ ሰማዕታት ደም የተጻፈውን ታሪክ ወራሽ የሆነው ኢወክንድ ፀረ- ወያኔው ትግል በሁሉም ዘርፍ እንዲፋፋም ለአገር ወዳድ ኢትዮጵያዊ ወጣቶች እንስባስብ ብሎ የትግል ጥሪውን ያቀርባል። ትግሉን በቆራጥነት ለመግፋት የተነሱ፣ ከጥቅጥቅ ጨለማ ባሻገር የንጋት ጮራ እንደሚፈነጥቅ፣ ካንዣበበው የክረመት ደመና ፀደይ እንደሚወለድ የሚያውቁ በርካታ ወጣቶች ሀገራቸን ኢትዮጵያ ዛሬም አላት።
ፀረ-ወያኔው ትግል የፋፋም! ድል የሕዝብ ነው!! 

No comments:

Post a Comment