Sunday, February 28, 2016

ድርጅት ድርጅት ድርጅት በጋራ መታገል፤ ትብብር፤ ህብረት. Finote radio!!!

http://www.finote.org

ጊዜ ፈጅቶ፤የተጠራቀመውን  የሕዝብ ብሶት መሰረት አድርጎ ሕዝባዊ  አመጽ መነሳቱ የማይቀር ነው ። የሕዝብ አመጽ ሁሌም አሸናፊ ይሆናል ማለት ግን አይደለም ። የካቲት 66 ሕዝቡ በአመጹ ያገኘው ድል በደርግ ተነጥቋል። ከአመጽ ወደ ምርጫ ስንመጣም የ1997ኡ ድል በወያኔ በጉልበት ተወስዷል ። የግብጽ ሕዝብ አመጽ በወታደሮች ከሽፏል ። የባህሬንን ሕዝብ አመ ኡዲና አጋሮቿ አክሽፈውታል ። ይህ እንዳይሆን ምን ምን ጥንቃቄ መደረግ አለበት የሚለው ዛሬ ሊያሳስበን የሚገባ ጥያቄ ነው ።
የመጀመሪያው አስፈላጊው ሁኔ መደራጀት ነው ።ጠንካራ ማዕከል ያስልጋል። ይህ በአንድም ሆነ በርከት ባሉም ድርጅቶች ሊሟላ የሚገባው ቅድመ ሁኔታ ነው ። ማእከል-ድርጅት መኖሩ አመነጣጥለው እንዳይነጠቁና ተቀናጅተው ቀጣይነት እንዲኖራቸው ያደርጋል። ካልተዋቀረና ካልተቀናጀ በተናጠል ይመታል ። ዛ በሀገራችን ብቅ ብቅ ያለውን የተቃውሞ እንቅስቃሴ ስናይ ተሥፋፍቶና ሁሉም የህብረተሰብ ክፍል አቅፎ መካሄድ እያለበትና--ይህም እየተሞከረ እያለ--ሁሌም ትግልን ማደፍረስና ማምከን ልማዳቸው የሆኑ ክፍሎች የለም ይህ የሕዝብ መነሳሳት የእ ብቻ ነው ብለው መለፈፍ ጀምረዋል ። አማራን ማረድ ነው ባይ ጽንፈኞችም ገብተውበት ከነበረው የሃፍረት ጉድጓዳቸው ብቅ ብለው መድረክ ላይ እየጨፈሩ ናቸው ። ጸረ ኢትዮጵ መሆናቸውን ያረጋጋጡ ክፍሎችም የራዲዮየቴሌቪዥን ጊዜ ጥቷቸው እቧረቁ ነው ። የሚካሄደው ተቃውሞ የእኔ መሬት የእኔ መሬት ከሆነ ያው ከወያኔ አልሸሹም ዞር አሉ ሆኖ መገኘቱም መነገር ያለበት ነው ። በደልና ግፍ፤ ማፈናቀል መሬት ንጥቂያ በክልል አልተወሰነም ። አማራውም ፤አኝዋኩም፤ ቤኒሻንጉሊም ወዘተ ሁሉም ደርሶበታል ፡፤ በአጠቃላይም የወያኔ ዘረኛ አገዛዝ የማረው ሕዝብ ክፍል የም ማለትም ይቻላል ። ጸረ ወያኔ አመጽ የትግራይ ተወላጆችንም ሊያስነሳ ሊያቅፍ የሚችልበት ጊዜም ሩቅ አይደለም ። የግፉን ስአት ጎጥ ሳይለይ መታገል ሲገባ ትግሎችን በክልል አጥረውና  ያውም በዋናው ጠላይ ላይ ሳይሆን በፈረደበት አማራ ላይም ለመዝመት መጣር ሀላፊነት የጎደለው ጉዳይ ይሆናል ።አማራው ሲጠቃ ሌላው ይበው ካለ፤ኦሮሞው ሲነሳ ቀሪው ምን አገባኝ ካለ፤ ሙስሊሙ ሲቃወም ክርስቲያኑ ራሱን ካገለለ ወያ ነጥሎ  ለማጥቃትና ለማሸነፍ ምንም የሚያዳግተው ነገር አይኖርም ። ትግላችንም ብልጭ ድርግም ዕጣ ክፍሎ ሆኖ ይቀራል ማለት ነው ።

መደራጀት መተሳሰር፤ማበር  በአሁኑ ወቅት ወሳኝነት አለው ። ህብረትን የሚያላላና ትግልን ከአጋር የሚያርቅ አቅዋም ቅስቀሳ ጎጂ መሆኑን ደግመን ደጋመን ማሳየት ያለብን አይመስልም ። አምቦ ሲነሳ ሰሜን ሸዋ ካጀበው ፤ጎንደር ሲያምጽ  ሐረ ከተነሳ፤ ሁሉም ለኢትዮጵያ ብሎ በራ ሊታገል ከወሰነ አመጽ  የወያን መጨረየሚያበስሊሆን ይችላል ። አሊያ ግን በግርግር ያን ጊዜ ያለፈበትን ግንጠላ እውን እናደርጋለን ብሎ ማሰብ ለወያኔ ወፍጮ ባቄላ ማረብ እንጂ ጥቅም አይኖረውም ። ኢትዮጵያን ለመገነጣጠል ሲመኙ የቆዩ ሀይሎች እጃቸውን በሀገራችን ጉዳይ ሊያስገቡ ሴራቸውን ቢጀምሩም የሚሆንላቸው አይሆንም ። ወያኔ  ከመጣበት ጥፋት እንዲድን አጋሮቹ አሁንም ሸብረክ የሚሉ ሀይሎችና ክፍሎችን በአዲስ መጠጋትና ማባበልም ጀምረዋል ። ጠንካራ ኢትዮጵያዊ  ህብረት እንዳይመሰረት ደንቃራ እያዘጋጁ ናቸው ማለት ይቻላል ። ይህን ሁሉ ለመቁቋም መጋጀት አስፈላጊ ነው ። መስዋዕት የሆኑትን ወጣቶችና ሌሎችንም የምንዘክረው ትግሉን በማቀዝቀዝ ወይም አቅጣጫ አዛንፎ በማስጠቃት ሳይሆን  ሕዝባዊ አመጹ የወያኔን አገዛዝ እንዲያነደውና እንዲያነደው በማድረግና በዘረኛ አግዛዝ መቃብር ላይ ለጎቿ ሁሉ አኩነትና ዴሞክራሲን የምታጎናጽፍ ኢትዮጵያን በመመስረት ነው ። ወያኔ ይህ እንዳይሆን አጥብቆ እየታገለ ነው ። ሕዝብ ከሕዝብ የሚይጣላ፤ የሚይስፈራራ በራሪዎችንም እየበተነ ውዝንብርን እየነዛ ነው ። ነግ መስጊድ ቢያቃጥል፤ቤተክርስቲያን ቢያጋይ ፤ ቅጥረኞቹን ተጠቅሞ አማራውን ኦሮሞውን ቢጨፈጭፍና ሕዝብ እርስ በርሱ እንዲላኮስ ቢጠብቅ ማሳፈር ያስፈልጋል እንጂ ሰለባው መሆን የለብንም ማለት ነው ። በህብረት ጥረት ላይ እንቅፋት የሚሆኑትንም ማሸነፊያ ጊዜ አሁን ነው ። በጋራ ትግሉን ለመግፋትም ሆነ በድህረ ወያኔም ወቅት ለሚፈጠሩ የተልያዩ ሁኔታዎች በጋር መፍትሔ ለመሻት ሰፋ ያለና ጥልቀት ያለው ትብብር መፍጠር አስፈላጊና ወሳኝ ነው። የረባ፣ ጥርስ ጡንቻ ያለው ህብረት እንዳይመሰረት ደካማ ቡድንኖችን በማቋቋም ሆነ የይምሰል ስብስብን በመፍጠር  በዚያው በድነው የሚቀሩና ለሰፊው ሕብረት መፈጠር እንቅፋት የሚሆኑ አሉ ። የኢትዮጵያ ጠላቶች ለኢትዮጵያ ኃይሎች መከታና አለኝታ ሊሆኑ እንደማይችሉ ሁሉም ማመን መቀበል ይገባዋል ። የዚህ አጓጉል ምርጫ ትርፉ ራስን አታሎ ሀገርን እንደገና ማስቃት ነው ትርፉ ። አመጽ አመጽ ብለን በስሜት አዳንቀን መጨረሻችን መኮማሸሽ እንዳይሆን ድርጅት ህብረት በሚል  ያቀረብነው ምክር አዳማጭ ቢኖረው ጠቅማል ።ከሺህ በላይ ግብጾች ተሰውተው ድላቸውን ግን ተቀምተዋል ። ሊሎች ምሳሌዎችም ከራሳችን ጀምሮ ሞልተዋል ። ይታሰበበት፤እንደጅበት፤አናብር እንላለን ። ሌላው አማራጭ ውድቀት ነው
ይህ መልዕክት ጥሪንም አዘል ነው ።


No comments:

Post a Comment