Sunday, March 27, 2016

ታሪካዊ ግዴታ --እስኪ ስለ እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ ሰብአዊ መብት መነጋገር እንጀምር-- አክሎግ ቢራራ (ዶር)

ታሪካዊ ግዴታ
--እስኪ ስለ እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ ሰብአዊ መብት መነጋገር እንጀምር--
አክሎግ ቢራራ (ዶር)
እኛ ኢትዮጵያዊያን የፖለቲካ ልሂቃን ከአብዛኛው የኢትዮጵያ ሕዝብ አስተሳሰብና ፍላጎት የተለየ ኋላቀር የፖለቲካ ባህል ስንከተል ቆይተናል። ከፍተኛ ትምህርት ኖሮን መደማመጥ አንችልም፤ ለመናበብ አንችልም። ይኼ ችግር ብሄራዊ አደጋዎችን ፈጥሯል። በአገር ደረጃ የሚነጋገረው ልሂቃንና ምሁራን ቁጥር በጣም ዝቅተኛ ነው። ሁኔታውን ያባባሰው ስርዓቱ መሆኑ የሚያከራክር አይመስለኝም። ባለፉት ሃያ አምስት ዓመታት በጭቁን ሕዝቦች ስም በመነገድ በኢትዮጵያ ሕዝብ ላይ የተጫነው የቋንቋና የጎሳ መለያ ሕገመንግሥትና የክልል አስተዳደር ለሁሉም ኢትዮጵያዊያን ማፈኛና ለጥቂት የህወሓት ኪራይ ሰብሳቢዎች ሚሊየኔርነት መሳሪያ መሆኑ በሂደት እየታየ ነው። ይህ ኪራይ ሰብሳቢ ቡድን ሌሎችም ኪራይ ሰብሳቦዎች እንዲሆኑ አድርጓል። ኪራይ ሰብሳቢ በሞላበት አገር ድህነት፤ ረሃብ፤ ስደትና ውርደት እየባሰ ብሄድ አያስገርምም። ተቃዋሚውን ሽባ ያደረገውም ፍርሃት ከስርዓቱ ጋር የተያያዘ ነው። ስርዓቱ ለፖለቲካና ለኢኮኖሚ ፍጹም የሆነ የበላይነት (Absolute minority ethnic elite hegemony) ያገለገለው በትግራይ ሕዝብ ስም ለሚንቀሳቀሰው፤ ሆኖም የአብዛኛውን የትግራይ ሕዝብ አዘቅት ላስገባው ለህወሓት አባላት ነው።
ባለፈው ሃተታየ እንዳቀርብኩት፤ የዘውግ ወይንም የጎሳ ፌደራሊዝም ከጅምሩ የጀርባ ምስጢር ነበረው። ይኼውም በጭቁን ህዝቦች ነጻነት፤ መብትና ራስን ችሎ ማስተዳደር ስም፤ የህወሓትን የበላይነት ሕገመንግሥታዊ ሽፋን ስጥቶ የበላይነትን ተቋማዊ ማድረጉ ነው። የዚህ ሃተታ መሰረት ለዚህ ስርዓት ወለድ ተግዳሮት መፍትሄው በብሄራዊ ደረጃ መሰብሰብ፤ መደራጀትና አብሮ መታገል አስፈላጊ ሆኗል የሚል ነው። የህወሓት የበላይነት ሽፋን ኢህአዴግ የሚለው የብሄረሰብ ልሂቃን ስብስብና አገዛዝ ነው። ኢህአዴግ ሲባል አቻ ለአቻ የሆኑ ድርጅቶች ስብስብ አለመሆኑ በተደጋጋሚ ታይቷል። ውጤቱ ምንንድን ነው? ብለን ብንጠይቅ የሚከተሉትን እናያለን፤
አንድ፤ የኢትዮጵያ አንድነትና ሉዐላዊነት አደገኛ በሆነ ደረጃ መድከሙ። አንድ ኢትዮጱያዊ ከክልሉ ወጥቶ ወደሌላ ክልል ሲሄድ ልክ ከጎረቤት አገር እንደመጣ እንግዳ “ከየት መጣህ” ተብሎ ይጠየቃል። ይህ በአገር “እንግዳ” መሆን በአፄ ኃይለ ሥላሴና በደርግ መንግሥታት ፍጹም የማይታሰብ ነበር። አንድ የታወቀ ኢትዮጵያዊ ምሁር፤ ፕሮፌሰር ዳኛቸው አሰፋ በድህረ ገጾች እንዳስቀመጠው፤ “ለመሆኑ ኢትዮጵያ አለች ወይ” ተብሎ ከሚጠየቅበት ደራጃ የገባነው በህወሓት ዘመን መሆኑ ነው።
ሁለት፤ የጎሳ ልሂቃን ባይፈቅዱ ኖሮ የማንነት ጥያቄ የኢትዮጵያን ሕዝብ ሊለያየውና ሊበታትነው አይችልም ነበር። ሕዝቡ ይኼን በሚገባ ያውቃል። ሕዝቡን የምንለያየው የፖለቲካ ልሂቃኖቹና ምሁራኖቹ ነን። ከማንኛውም አገር በበለጠ ደረጃ የኢትዮጵያ ሕዝብ ጠባብ ጎሰኛና ብሄርተኛ ሆኖ አያውቅም። ጎሠኛ ቢሆን ኖሮ ብዙ እልቂት ይካሄድ ነበር። ሕዝቡ ተጋብቷል፤ ተዋልዷል፤ ተቻችሎ ይኖራል። የአድዋን የመቶ ሃያኛ ዓመት በዓል ስናከብር ማስታወስ ያለብን ድሉ የሁሉም ኢትዮጵያዊያን ድል መሆኑን ነው። ማንም ሳይስገድደው ገበሬው፤ ነጋዴው፤ የቢሮ ሰራተኛው፤ ወታደሩና ሌላው ከሁሉም የኢትዮጵያ ክፍሎችና ጎሳዎች ስንቁን ተሸክሞ ጣልያንን ተባብሮ አሸንፎ ወደመጣበት የመለሰው ከጎሰኛነትና ከጎጠኛነት ባሻገር ለአገሩ ነጻነት፤ ሉዐላዊነትና ለሕዝቡ ክብር ስለቆመ ነው። ዛሬ ማንነት መነገጃ ሆኗል፤ ትርጉም አጥቷል። የማንነት ጥያቄ ተቀዳሚ ሆኗል ሲባል አሁንም የሕዝቡን ልዩነት የሚያሳይ አይደለም። አንድ ግለሰብ በሞያው ገበሬ ወይንም ነጋዴ፤ በኃይማኖቱ ክርስቲያን ወይንም ሙስለም፤ በጾታው ወንድ ወይንም ሴት ወዘተ ሊሆን መብቱ ነው። ይኼን መብት ማንም ሊነፍገውና ሊከለክለው አይችልም። ከዚያ ባሻገር ግን በአገር ደረጃ “ጋናዊው እኔ ጋናዊ ነኝ” እንደሚለው ሁሉ ኢትዮጵያዊው “እኔ ኢትዮጵያዊ ነኝ” የማለት ግዴታችን ግልጽ ነው። በዜግነታችን መለያ ኢትዮጵይዊ ነን ካልን መኖሪያችን በጎሳዊ ክልል ምሽግ፤ ግንብና ድንበር ሊወሰን አይችልም። በእያንዳዱ ክልል የእያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ መብት ካልተከበረ የማንም መብት ሊከበር አይችልም። ይኼን ካልተቀበልን ከህወሓትና ሌሎች የጎሳ ስብስቦች ከሚሉት ምን ይለየናል?
በነገራችን ላይ፤ በጎሳ መለያየት በተመጣጠነ፤ በዘላቂና ፍትሃዊ የኢኮኖሚና የማህበረሰባዊ እድገት ላይ ከፍተኛ ተጽኖ አለው። ለምሳሌ፤ የኦሞ ሸለቆ፤ የቤኒ-ሻንጉል ጉሙዝ፤ የአፋር፤ የጋምቤላ፤ የኦጋዴን ሕዝብ በዜግነቱ ምን ያገኘው ጥቅም አለ?
ሶስት፤ የህወሓት ደጋፊዎችና ወፍ ዘራሽ ተጠቃሚዎች እንደሚሉት ሳይሆን የጎሳ ፖለቲካ ለሃያ አምስት ዓመታት ሊሰራ የቻለው የኢትዮጵያ ሕዝብ ስለተቀበለው አይደለም። ህወሓት ለብዙ ሽህ ዓመታት በወንድማማችነት፤ በእህትማማችነት ሲኖር የቆየውን ሕዝብ፤ በተለይ የአማራውንና የኦሮሞውን ሕዝብ እንዲጋጭ በማድረጉ ነው። ይኼን መከፋፈል ድብቅ አጀንዳቸው የሚጠቀሙ ከፋፋዮች ቢኖሩም ሁኔታውን የፈጠረው የህወሓትና ተባባሪው የኢህአዴግ አመራር ነው። ለምሳሌ፤ ከጅምሩ ህወሓት ህብረብሄር የሆኑ የፖለቲካ ፓርቲዎችን፤ አገር ወዳዶችን፤ ምሁራንን፤ የሞያና ሌሎች ተቋሞችን በማፈራረሱ። በምትካቸው ልክ በፋብሪካ እንደሚመረቱ አድርጎ ለራሱ የሚጠቅሙትን መተኪያዎች አገር አቀፍ በሆነ ደረጃ ዘርግቷል። ፓርላማውን ለራሱ መገልገያ አድርጎታል። ሕግ አዉጭው፤ ሕግ ተርጓሚው፤ ሕግ አስፈጻሚው ህወሓት ነው። ፊት ለፊት ለይስሙላ የሚያስቀምጣቸው ግለሰቦች ከሌሎች ብሄረሰቦች የተወጣጡ ናቸው ተብሎ እንዲታመን ያደርጋል። ይህን ሽፋን (Camouflage) ሕዝቡ ያውቀዋል። ፊት ለፊትና በጀርባ ሆነው ፖሊሲ የሚያወጡትና የሚተገብሩት የህወሓት አባላት ናቸው። የሚጠቀሙባቸው አባባሎች ብዙ ናቸው፤ “ሕገመንግሥቱን ለማስከበር፤ ለመደጋገፍ፤ እድገቱን ለመቀጠል፤ ሽብርተኞችን ለመቆጣጠር” ወዘተ። እናንተን ማን ይቆጣጠራል የሚል ተቋም ወይንም ግለሰብ የለም፤ አይታሰብም። በአንድ ትንተና ላይ ጋርዲያን የተባለው የእንግሊዝ ጋዜጣ በትክክል እንዳስቀመጠው፤ ይህ አገዛዝ ኦርዌልያን (Orwellian) ወይንም የፖሊስ መንግሥት (Police State) ከሆነ ሃያ አምስት ዓመታት ሆኖታል። ከህወሓት ውጭ ያሉት የኢህአዴግ አባል ድርጅቶች ቢቀበሉትም ባይቀበሉትም የበላዩ ወይንም አለቃው ህወሓት ነው። የህወሓትን የበላይነት የማይቀበል የኢህአዴግ አባል ፈልጎ ለማግኘት አይቻልም። “ኢህአደጎች ራሳችሁን ከአምባገነኑ ህወሓት ነጻ አውጡ” ያለ ግለሰብ ትዝ ይለኛል።
አራት፤ ህወሓት ቀላል ድርጅት አይደለም፤ ምስጢር ይጠብቃል። ጠንካራ ስለሆነ ከፋፍሎናል። ህወሓት ይደጋገፋል፤ ይጠቃቀማል። ሌሎቹን አባል ድርጅቶች የማሳመን ችሎታው የሚደነቅ ነው። ያስፈራራል ወይንም ያባብላል፤ ይገዛል፤ ያከብራል፤ ይደልላል፤ ያደኸያል ወይንም በስውር ያሸሻል፤ ያባርራል ወዘተ። አጭበርብሮም ሆነ አስፈራርቶ ምርጫዎችን ለበላይነት ይጠቀማል። ቅንጅትና ህብረት የዘጠና ሰባቱን ምርጫ አሸነፉ። ህወሓት ማሸነፋቸውን አልተቀበለም። የራሳቸው የአመራር ድክመት መኖሩ ባይካድም፤ የሕዝብን ድምጽ የሰረቀው ህወሓት ነው። የፖለቲካ ሙስና በጭካኔ! ተሸንፎ ያሸነፉትን ይቅርታ የሚጠይቅ አገዛዝ ስኬታማ የሆነው በራሱ ጥንካሬ ሳይሆን ተቃዋሚው የተከፋፈለ በመሆኑ፤ የውጭ ድጋፍ ስላለው፤ ህብረብሄር ድርጅቶችን በማፈኑ፤ በማፈራረሱና ቆራጥ የሆኑ አገር ወዳድ ድርጅቶችና መሪዎች ባለመኖራቸውና እንዳይኖሩ በመደረጋቸው ነው። በተደጋጋሚ የታየውና አሁንም የሚደገመው ክስተት አንድ ነው። በጎሳ ተከፋፍሎ ራስን ማጋለጥ የፖለቲካ ክስረት አስከትሏል። የተከፋፈለ ህብረተሰብና ተቃዋሚ ሁሌም የሚያገልግለው ህወሓትን ነው።
እንደገና በ2010 ተወዳዳሪዎችን አፍኖ፤ ከፋፍሎና አስሮ ምርጫውን 99.6 በመቶ አሸነፍኩ አለ። አምስት ዓመት ቆይቶ በለመደው የፖለቲካ ጮሌነት በ2015 ይባስ ብሎ 100 በመቶ “አሸነፍኩ” አለ። ምርጫን መሳቂያና መሳለቂያ አደረገ። ሕዝብን ፍጹም በሆነ ደረጃ ተስፋ አስቆረጠ። የብሄረሰብ እኩልነት ተብሎ ይጠራ የነበረው ስርዓት የኦሮሞ ተወላጅ የሆኑ ኢትዮጵያዊያን ሲታፈኑ፤ ሲገደሉ፤ ሲሰወሩና ሲሰደዱ የጎሳ ፖለቲካ አስተዳደር የማያዋጣ መሆኑን አስመሰከረ። አንዳንድ ተመልካቾች አዲስ ምርጫ “በኦሮሚያ ክልል ቢካሄድ ይመረጣል” ይላሉ። ስር ዓቱ ነጻና ፍትሃዊ ምርጫ የማይፈቅድ መሆኑ እየታወቀ አዲስ ምርጫ ዋጋ ቢስ ነው። የሚያዋጣው ስርዓቱን መለወጥ እንጅ የይስሙላ ምርጫ አይደለም። እንዲያውም የኢትዮጵያን ሕዝብ በተከታታይ ማታለል ነው።
አምስት፤ “ታዲያ ምን አለበት፤ ተቃዋሚው ደካማና የተከፋፈለ ከሆነ፤ ኢህአዴግ ለምን አያሸንፍም? ጠንካራ ፓርቲና መንግሥት ከሌለ ኢትዮጵያ እንደ ሶማሊያና ኬንያ ትሆናለች፤ በአመጸኞች፤ ተገንጣዮችና ሽብርተኞች ትጠቃለች። እድገቷ ያቆማል። የመበታተን አድሏ ይባባሳል። የትኛው ተቃዋሚ ነው ከገዢው ፓርቲ ጋር ሊነጻጸር የሚችል?” የሚሉ ጥያቄዎችና ትችቶች ይሰነዘራሉ። አግባብ አላቸው። በአንድ አገር ሁለት ወይንም ከዚያ በላይ መንግሥታት ሊኖሩ አይችልም። በአንድ ፌደረላዊ አገር የተለያዩ፤ ራሳቸውን እንደ ጎረቤት አገር የሚለዩ አገሮች ሊኖሩ አይችልም። ሁለት ወይንም ከዚያ በላይ የሚሆኑ ራሳቸውን እንደ ነጻ አገር የሚቆጥሩ አገሮች አሉ ከተባለ ኢትዮጵያ የምትባል አገር የለችም ማለት ነው። ቁም ነገሩ ወደዚህ ችግር ያሸጋገረን ማነው? ብለን ብንጠይቅ የክልሎች ሕገመንግሥት ያወጡት የጎሳ ስብስቦች ናቸው፤ ህወሓት፤ ሻቢያና ኦነግ። ይኼን በሚቀጥለው ሃተታየ አቀርባለሁ።
የዚህን የተሳሳተ የጎሳ ፖለቲካ ሂደትና ውጤት እያወቅን፤ አንዳንዶቻችን አውቀንም ይሁን ሳናውቅ እነዚህን መሰረታዊ ችግሮች የፈጠረውን ገዢ ፓርቲና የብሄር ተቃዋሚዎችን በቀላሉ እየሸነገልን ነው። ህወሓት፤ ኢህአዴግን መቃወም አግባብ አለው። ሆኖም፤ ለመቃወም ብቻ ሲባል ብሄርተኞችን፤ ሽብርተኞችን፤ አመፀኞችን፤ ተገንጣዮችን፤ የውጭ ጠላቶችን ወዘተ መደገፍ እንዴት ሊያዋጣ ይችላል? ከአብዛኛው ሕዝብ እኩልነት፤ ፍትህና ዲሞክራሲ ምኞት ጋር ምን ግንኙነት አለው? የአገሪቱን በክልል መከፋፈል ተቀብሎ ኢትዮጵያና ኢትዮጵያዊያን የሚሉትን እሴት የተመረኮዙ ስያሜዎች ለመጠቀም አለመቻል፤ ወይንም አለመፍቀድ የማንን ዘላቂ ግብ ያጠንክራል፤ ያገልግላል? ሕዝብን ከሕዝብ-- ኦሮሞውን ከአማራው፤ ሁለቱን ከትግራዩና ከሌላው ሕዝብ--ጋር በማገናኘት፤ በማስታረቅና በማስማማት ፋንታ እንዲጋጭ የምናደርግበት ምክንያት ምንድን ነው? ከጥንት ጀምሮ ዛሬ ኦሮምያ በሚባለው ክልል ብዙ ሚሊየኖች የኦሮሞ ብሄረሰብ ያልሆኑ ኢትዮጵያዊያን ይኖራሉ። የኦሮሞ ሕዝብ በጎንደር፤ በጎጃም፤ በወሎ፤ በሸዋና ሌሎች ቦታዎች ይኖራል። እነለያይ ብንል ማን ከማን ይለያያል። በመፈቃቀድና ተፈቃቅዶ ችግሮችን በጋራ ከመፍታት የበለጠ አማራጭ የለም። አለያ፤ ከአንድ ችግር ወጥተን ወደሌላ ችግር መግባታችን አይቀርም። ያም ሆነ ይህ፤ የጎሳ ጥላቻና መከፋፈል ህይወትና ቆይታ የሚሰጠው እንቃወመዋለን ለምንለው ገዢ ፓርቲ ነው።
ለእውነተኛ ፍትህ ቆመናል ካልን መቀበል የሚኖርብን ተራው የኢትዮጵያ ሕዝብ የጎሳ ግጭት የማይፈልግ መሆኑን ነው። በሌላ በኩል ህወሓት ውስጥ ለውስጥ ኦሮሞ ያልሆነውን የሕብረተሰብ ክፍል የሌለ ጠላት ፈጥሮ “እኔን ካልደገፍክ ህልውናህ አስተማማኝ አይሆንም” የሚለውን የከፋፍለህ ግዛው ዘዴ መከላከል አለብን። አንዴ አኟኩን፤ ሌላ ጊዜ አማራውን፤ ሌላ ጊዜ የኦጋዴን ሶማሌውን፤ ሌላ ጊዜ የኦሞ ሸለቆ ኢትዮጵያዊውን፤ ሌላ ጊዜ የኦሮሞ ተወላጁን ወዘተ እያሰሩ፤ እያሳደዱ፤ እየወነጀሉ፤ እያፈራረሱ፤ ዜጎች በድብቅ እንዲሰወሩ እያደረጉ፤ ከደርግ በተለየ ጥበብ በማይታወቁ መንገዶች ተቃዋዋሚውን “እየሰወሩ” ተቃዋሚ ፓርቲ፤ ዲሞክራትና አገር ወዳድ የለም ማለት፤ ወይንም እየጨፈጨፉ አልጨፈጨፍኩም ማለት የፖለቲካ ጮሌነት ነው። ፈረንጆች ማኬቬሊያን የሆነ የፖለቲላ አመራር ይሉታል። የህወሓት አለቃዎችና ወራሾች ከዲሞክራቶችና አገር ወዳዶች ይልቅ ከአምባገነኖች ፈላስፋዎች የተማሩት ይልቃል።
ማኬአቬሊ (Machiavelli) 1513 The Prince በተባለው የፖለቲካ ፍልስፍና መጽሃፉ አንድ ቡድን ሌሎችን ፍጹም በሆነ ደረጃ የበላይ ሆኖ እንዴት እንደሚገዛ ትምህርት ያቀርባል። አራት የተለያዩ አምባገነን የሆኑ የመንግሥት ስርዓቶችን አጥንቶና መሰረት አድርጎ እያንዳንዳቸው እንዴት የበላይነታቸውን እንደሚያጠናክሩ ዘዴዎችን ይጠቁማል። ከእነዚህ መካከል ከፍተኛ ሚና ያለው የስለላና የወታደር ኃይል ተቋም ወሳኝ መሆኑን ይናገራል። ኃይል ያለው ይገዛል፤ ኃይል የሌለው ይገዛል የሚል መሆኑ ነው። ህወሓት ይኼን ጥበብ ሙሉ በሙሉ ተጠቅሞበታል፤ የአሜሪካ እርዳታ ለጥንካሬው መሰረት ሆኗል። ማኬያቬሊ እንዳለው የመሳሪያ የበላይነት በአንድ በኩል፤ በሌላ በኩል ግብረገብነት፤ ፍትህ፤ ሰብአዊነት አብረው አይሄዱም። የህወሓት ህልውናና አምባገነናዊው አገዛዝ እንዲቀጥል ከተፈለገ ህወሓት ጭካኔ ያለበት (Evil Political Actions) እርምጃ መውሰዱ የማይቀር ነው። ፈላስፋው ሁኔታዎች ሲለወጡ አምባገነን አገዛዝም እንደሚለወጥ ይናገራል። ሕዝብ በአንድ ድምጽ ተያይዞና ተባብሮ ከተነሳ የሚያቆመው ኃይል እንደሌለ ይታወቃል። በጎሳ መከፋፈላችን ይብቃ የምልበት መሰረታዊ ሃሳብ ይኼ ነው።
እርስ በርሳችን ከመጋጨት በላይ መጠየቅ ያለብን የሕዝብ ዐመጽ ተደጋጋሚ ሲሆንስ ህወሓት ራሱን ለመለወጥ ፍላጎት አለው ወይንስ የማኬያቬሊን ፍልስፍና ይከተላል? አላውቅም። የማውቀው የጭካኔ አገዛዝ ለጊዜው እርጋታ ቢፈጥርም መሰረታዊ የሆኑ ችግሮችን አይፈታም። መሰረታዊ ችግሮች የሚፈቱት የኢትዮጵያ ሕዝብ ለመብቱ በአንድ ድምጽ ሲነሳ ነው። በኦሮምያ፤ በጋምቤላ፤ በቤኒ ሻንጉል ጉሙዝ፤ በኦጋዴንና በሰሜን ጎንደር በተከታታይ የሚታየው የሕዝብ ዐመጽ ለገዢው ፓርቲ ስጋት እንደፈጠረ ይታያል። ሆኖም፤ ይህ ስጋት ወደ ለውጥ ሊሸጋገር የሚችለው የጎሳና ሌሎች ልሂቃን የእርስ በርስ ትችቱን ትተው ወደ አንድነትም ባይሆን ወደ እውነተኛ መተባበር ሲሸጋገሩ ነው። አንድነት ስል፤ ማንም ክፍል በተናጠል የአንድነት ጠበቃና ሃላፊ እንዳልሆነ ለማሳሰብ እፈልጋለሁ። የኢትዮጵያ ብሄራዊ አንድነትና ሉዐላዊነት የአንድ ወይንም የሁለት ብሄረሰብ ጉዳይ ብቻ አይደለም። የኢትዮጵያ ሕዝብ አንድነት ስል የሁሉም ሕዝቦች አንድነት ማለቴ ነው። ብሄራዊ አንድነት አስተማማኝ የሚሆነው የፌደራሉ መንግሥት መሪዎች የአገሪቱን ስብጥር ሕዝብ ሲወክሉ ነው። የአገርም ሆነ የሕዝብ ጥንካሬ መሰረት ኢትዮጵያዊያን “የእኔ መንግሥት ነው” ለማለት ሲችሉ ነው። የህወሓት ድክመት መሰረት የአንድ አናሳ ብሄረሰብ ፍጹም የበላይነት ነው።
ስድስት፤ በተከታታይ ጽሁፎቸ በማስረጃ እንዳሳየሁት፤ በሁሉም ወሳኝ በሆኑ የስለላና መረጃ፤ የመከላከያ፤ የፌደራል ፖሊስ፤ ቁልፍ የሆኑ ሚኒስትሪዎችና የአገር ንብረት ተቋሞች (State owned enterprises such as Ethiopian Airlines, Telecommunication etc.) ባለፉት ሃያ አምስት ዓመታት ፖሊሲና ውሳኔ ለማድረግ የሚችሉት ግለሰቦች ትግራዮች ናቸው። ይህ የአንድ ብሄረሰብ ፍጹም የሆነ የበላይነት በኢትዮጵያ ታሪክ ታይቶ የማይታወቅ ነው። ኢትዮጵያዊያን ብቻ ሳይሆኑ የውጭ ተመልካቾች ይኼ ሁኔታ አደገኛ መሆኑን በተደጋጋሚ አሳስበዋል። የኢትዮጵያን የመከላከያን ኃይል ተቋም ብቻ ብናይ ከኮሎኔል በላይ የበላይ እዙ አባላት ከሆኑት መካከል 97 በመቶ የሚሆኑት የህወሓት አብላት ወይንም ደጋፊዎች ናቸው፤ ከአንድ ብሄረሰብ የተወጣጡ ማለት ነው። (See on line “Ethiopia promotes 37 Senior Officers to the rank of general). ከአገሪቱ ዘላቂ ደህንነትና ከሕዝቧ አንድነት አንጻር ብናየው ይኼ ለትግራይ ሕዝብም አደገኛ ነው። ግልጽ ለማድረግ የምፈልገው የትግራይ ተወላጆች በእዙ ሚና አይኑራቸው ለማለት አይደለም። የእዙ ስብጥር የኢትዮጵያን ሕዝብ የሚወክል ይሁን ማለቴ ነው። ይህ ለኢትዮጵያ ደህንነት ወሳኝ ነው።
ሌሎቻችን፤ የህወሓት አባላትንና ደጋፊ ትግራዮችን ጨምሮ፤ መተቸት ያለብን “ለብሄረሰቦች እኩልነት” ቆምኩ የሚለው ህወሓት ይኼን የሚያስወቅስ ጎሳዊ አድልዎ በተደጋጋሚ መርህ ሲያደርግ አለመተማመንን እንደፈጠረና ይኼ አለመተማመን ወደ አደገኛ ሁኔታ እንደሚያመራ ማሳየትና መፍትሄ መፈለግ ነው። መተቸቱ ብቻ በቂ አይደለም። የእዙ ስብጥር ወሳኝ ነው ስል፤ የጋምቤላ ወይንም የጎንደር ወይንም የኦጋዴን ወይንም የኦሮምያ ወዘተ ሕዝብ የትግራይ አዛዦችን፤ ልዩ ኃይሉን አጋዚን በሚያዩበት ጊዜ ምን እንደሚሰማቸው ለማጤን ይቻላል። የተጎዱት “እኛና እነሱ” እያሉ ቢናገሩ እንዴት ይፈረድባቸዋል። “እኛና እነሱ” የሚለው እጅግ በጣም አደገኛ መሆኑን ሁላችንም መገንዘብ አለብን።
በኢኮኖሚውም ያለው ሁኔታ ተመሳሳይ ነው። የዘመናዊውን ኢኮኖሚ የበላይነት ጥልቀት ባለው መልኩ ብናየው የበላይነቱን የያዙት የህወሓት አባላት፤ ታማኞችና ደጋፊዎች ናቸው። እዚህ ላይ ጥንቃቄ ማድረግ አግባብ አለው። አንድ፤ የወፍ ዘራሽ ተጠቃሚዎች መኖራቸውን መካድ አንችልም። የኢኮኖሚው የበላይነት በአብዛኛው የህወሓት ልሂቃን ይሁን እንጅ ከሌሎች ጎሳዎች የተወጣጡ አዲስ ሃብታሞች እንዳሉ መካድ አይቻልም። ስርጭቱ የመደብ መልክ እየያዘ ነው---አማራም፤ ጉራጌም፤ ኦሮሞም፤ ወላይታም፤ ሶማሌም፤ ክርስቲያንም፤ ሙስለምም ወዘተ ተሳታፊ ነኝ የሚል የመደብ መልክ የያዘበት ሁኔታ ተፈጥሯል። በአጭሩ፤ የህወሓት የኢኮኖሚ የበላይነት ባይካድም፤ ኪራይ ሰብሳቢ ሲባል የህወሓት አባላት ብቻ ናቸው ከሚል የተሳሳተ ድምዳሜ ላይ እንዳንደርስ ማለቴ ነው። ሁለት፤ አብዛኛው የትግራይ ሕዝብ የኪራይ ሰብሳቢው ክበብ ወይንም ቡድን አባል አይደለም። በእኔ ግምት አብዛኛው የትግራይ ሕዝብ ድሃ ነው፤ ሰርቶ አደር ነው፤ አገር ወዳድ ነው፤ የታፈነና ነጻነት የሌለው ነው፤ ባህሉን የሚያከብር መንፈሳዊ ሕዝብ ነው። ባጭሩ፤ የህወሓትን የበላይነት ከትግራይ ሕዝብ ሁኔታ እንለየው።
በቅርቡ ጠቅላይ ሚንስትር ኃይለማሪያም ደሳለኝ ስለ አገሪቱ ሁኔታ፤ በተለይ በኦሮምያና ሌሎች አካባቢዎች ስለተከሰተው ሕዝባዊ አመጽ ሲናገሩ ችግሩን የፈጠረው ስርዓቱ፤ መንግሥቱና አመራሩ መሆኑን አስምረውበታል። እሳቸው ያሉት ህዝብን ለመሸንገል ካልሆነ በከፊልም ቢሆን ያሉትን እጋራለሁ። ለምስታወስ፤ ስለመጥፎ አስተዳደርና ስለ ኪራይ ሰብሳቢነት ባህልም ተመሳሳይ ትችት አድርገው ነበር። ትዝ እንደሚለኝ ከሆነ “እኛ ከዚህ ስንወጣ ልክ እንዳልሰማንሆነንወደራሳችንቡድኖችእንገባለን፤ለውጥአንዳናካሂድማነቆእንሆናለን”በለዋል። ምንምየረባለውጥ አልታየም። አሁንም ያሉት የችግሩ መንስኤ “እኛው ኢህአዴጎች ነን (We in EPRDF are to blame)” ነው። ይኼን በመለስ ዜናዊ አገዛዝ የማይታሰብ መናገር ቀላል አይደለም። አሁንም በህወሓት ውስጥ የሚገኙ ግትሮች የችግሩን ጥልቀትና ስፋት የተረዱት አይመስልም። ጠቅላይ ሚንስትር ተሹሞ አገሪቱን ያለምንም ጫና ለመምራትና መፍትሄዎችን ለመፈለገ ካልቻለ “ጉልቻ” መሆኑ ነው፤ ሰው ጉልቻ አይደለም። ሌላው ቢቀር ለህሊናው ተገዢ መሆን ግዴታው ነው። እሳቸእ ስለተናገሩ የገዢው ፓርቲ የበላይ ህወሓት ይለወጣል ብሎ ማሰብ ራስን ማታለል ነው።
የማይካደው የፖለቲካ ክስተት አንድ ነው። ቀደም ሲል በጎንደር፤ በጋምቤላ፤ በኦጋዴን፤ ባለፉት አምስት ወራት በኦሮምያና በአዲስ አበባ የተካሄደውና የሚካሄደው የሕዝብ እምቢተኛነት መሰረታዊ የሆኑ የፖሊሲ፤ የመዋቅር፤ የአስተዳደርና የኪራይ ሰብሳቢነት ውጤቶች ናቸው። ሕዝብ እንዲሁ በራሱ ላይ ፈርዶ ልደብደብ፤ ልታሰር፤ ልሰወር፤ ልገደል፤ ልሰደድ ወዘተ አይልም። ሕዝብን ወደ እምቢተኛነት የሚወስዱት የሚከተሉት ናቸው፤
 •   የፍትህ መጓደል፤ የሰብአዊ መብቶች መታፈን፤ የነጻነት አለመኖር
 •   ጭፍን የሆነ ጎሳዊ አድልዎ፤ ጉቦ፤ ሙስናና ከሕግ ውጭ ከአገር የሚወጣ ግዙፍ ኃብት
 •   የኑሮ ውድነት፤ የአቅርቦት ጉድለት
 •   የሰብአዊ ክብር መውደም፤ ስደት፤ በወጣት ሴቶች መነገድ
 •   የመልካም አስተዳደር መጉደል
 •   ችግሮችን በግድያ፤ በአፈና፤ ዜጎችን በመሰወር፤ በመደብደብ ለመፍታት መሞከር
 •   የመሬት ነጠቃና የዜጎች ከቀያቸው በተከታታይ መባረር፤ መገለል፤ መኖሪያ ማጣት
  በአጠቃላይ ስመለከተው የኢትዮጵያና የኢትዮጵያ ሕዝብ መሰረታዊ ችግር ስርዓቱ ነው። በኢትዮጵያ ሕዝብ መካከል ያለውን ጥቃቅን የተለመደ የባህል፤ የልምድ፤ የቋንቋ ወዘተ ልዩነት ወደማይታረቅ ልዩነት እንዲሸጋገር የምንጎተጉተው የፖለቲካ ልሂቃንና ምሁራን ጭምር ነን። በአገዛዝና በአመራር ደረጃ ሲታይ፤ ተቃርኖው በአንድ በኩል ህወሓት በበላይነት በሚመራው ኢህአዴግ እና በሌላ በኩል በሕዝብ መካከል ነው። ችግሩ ሊፈታ የሚችለው ሕዝብ የስልጣኑ ባለቤት ሲሆን ነው።
  ጠቅላይ ሚንስትሩ እንዳሉት ኢህአዴግ የፈጠረውን ችግር በእልክ፤ በጭካኔ፤ በማስፈራራት፤ በማሰር፤ በማቁሰል፤ በመሰወር ሊፈታው አይችልም። ሰውን ለመሰወር ቢቻልም ችግሩን ለመሰወር አይቻልም። ሊፈታ የሚችለው በፍትህ፤ በሕግ የበላይነትና በእውነተኛ ዲሞክራሳዊ አማራጭ ብቻ ነው።
  በቅርቡ ክራይስስ ግሩፕ የተባለው ተቋም እንዲህ ብሎ ነበር፤
page4image25728 
“ልክ እንደጎረቤት አገሮች፤ ኢትዮጵያን የገጠማት የፖሊሲ አማራጭ ጉዳይ ነው። የውስጥ ችግሮችን ለመፍታት ስርዓት ወለድ ጉዳዮች መፈታት አለባቸው”። ጠቅላይ ሚንስትሩ በቅንነትም ሆነ ሌላ ችግሩን “የፈጠርነው እኛው ነን” ካሉ የሚመሩት ፓርቲ ደፍሮ ለሕዝብ የፖለቲካ የበላይነት ማጎብደድና መገዛት አለበት።
Ethiopia, like its immediate neighbours, is faced with difficult policy choices
involved in guarding against internal radicalisation through systematic (constitutionally questionable) interventions...The government, and donors keen to support global efforts against violent extremism, should always consider first, the risk of such interventions to the state’s neutrality as mediator..Above all, those backing interventions should always seek better understanding of what faith (ለምሳሌ) means to multi-ethnic, religiously diverse societies like (but not limited to) Ethiopia, in which the distinction between group and individual identity is often not well defined, and rival local actors are apt to make use of religious disputes where social and governmental constraints inhibit open political competition.” See Ethiopia: Governing
the Faithful. Crisis Group Africa Briefing N°117. Nairobi/Brussels, 22 February 2016 

Saturday, March 26, 2016

Finote Democracy Voice of Ethiopian Unity Satellite Radio News

Finote Democracy Voice of Ethiopian Unity Satellite Radio News
መጋቢት 16 ቀን 2008 ዓ.ም.ዜና (March 25, 2016 NEWS)
‪#‎የወልቃይት‬ ጠገዴ ሕዝብ ያነሳውን የማንነትና የመብት ጥያቄ የወያኔ መሪዎች ሚሊሺውንና የፖሊስ ኃይሉን ከትግራይ በማስመጣትና ወታደሩን በማስፈር ምላሽ በመስጠት አስፈራርተውና አሸብረው የታላቋ ትግራይን ህልውና እውን ለማድረግ የጀመሩት ሙከራ አሁንም ከሕዝብ ከፍተኛ ተቃውሞ እንደገጠመውና ውጥረቱ እየከፋና ግጭቶችም እየበረከቱ መምጣታቸው ከአካባቢው የሚመጡ መረጃዎች ያመለክታሉ። 
‪#‎በምዕራብ‬ ወለጋ በመንዲ ከተማ አንድ የገበያ ማዕከል በእሳት አደጋ እንዲወድም ከተደረገ ወዲህ ሕዝባዊ ተቃውሞ በማገርሸቱ የወያኔ ፖሊሶች የመንዲ ከተማ ተማሪዎችንና መምህራንን አስረው ወደ አልታወቀ ሰፈራ እንደወስዷቸው ታውቋል።
‪#‎በመቀሌ‬ የጀመረው የባጃጁ የሥራ ማቆም አድማ አሁንም እንደቀጠለ ሲሆን የወያኔ አገዛዝ በርካታ የታጠቁ ፖሊሶቹንና ወታደሮችን በከተማ ውስጥ በማስፈር ሕዝብን እያስፈራራና የባጃጅ ሹፌርና ባለንብረቶችንም እያዋካበ እንደሚገኝ ታውቋል።
‪#‎ከአስር‬ ሚሊዮን በላይ ኢትዮጵያውያን በድርቅና በረሃብ አደጋ መጠቃታቸው እየተነገረ ባለበትና ከፍተኛ የሆነ የሰዎች ሞትና ዕልቂት እንዳይከሰት የዓለም አቀፉ ኅብረተሰብ በፊት ርብርብ በሚያደርግበት ሰዓትና በሀገር ውስጥ ያለው የእርዳታ እህል መጠን ከሁለት ወር በላይ አያራምድም በሚባልበት ጊዜ በጂቡቲ ወደብ የእርዳታ ስንዴ ማራገፊያ ማጣቱ ተገለጸ።
‪#‎በልዩልዮ‬ ሰበብና ምክንያት የሕዝብ ገንዘብ መሰብሰብና መዝረፍ መለያ የሆነው ወያኔ በባለተሽከርካሪዎች ላይ ተጨማሪ የግዳጅ ገንዘብ መሰብሰቢያ ዘዴ ጀምሯል።
‪#‎ማኅበረ‬ ቅዱሳን ከመጋቢት 15 ቀን እስከ መጋቢት 21 ቀን 2008 ዓም ድረስ በአዲስ አበባ ከተማ በኢግዚብሽን ማዕከል ኦርቶዶክሳዊ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያንን አስተምህሮዋን እንጠንቀቅ ድርሻችንን እንወቅ በመሪ ርዕስ ያዘጋጀውን ዐውደ ርዕዩትን በመጨረሻ ሰዓት ላይ በወያኔ ባለሥላጣናት መከልከሉ ታወቀ።
‪#‎በብራስልስና‬ በፓሪስና በጀርመን ተጨማሪ አሸባሪዎች ተያዙ
‪#‎በግብጽ‬ ጣሊያናዊውን ተመራማሪ የገደሉት የተያዙ መሆናቸውን የግብጽ መንግስት አስታወቀ
‪#‎በናይጄሪያ‬ 300 የሚሆኑ የንግድ ኩባንያዎችና ግለሰቦች በሙስና ለፍርድ ይቀርባሉ ተባለ
‪#‎የቀደሞ‬ የቦዚኒያ ስርብ መሪ ተፈረደበት
ለዝርዝር ዜናዎች > ከታች ይጫኑ (to /read/listen detail news click below)
To Read: http://www.finote.org/news.html
To Listen PART 1: http://www.finote.org/March25EVE_Hr1.mp3
To Listen PART 2: http://www.finote.org/March25EVE_Hr2.mp3

Friday, March 25, 2016

Finote Democracy Voice of Ethiopian Unity Satellite Radio News

Finote Democracy Voice of Ethiopian Unity Satellite Radio News
መጋቢት 15 ቀን 2008 ዓ.ም.ዜና (March 24, 2016 NEWS)
‪#‎በወልቃይት‬ ጠገዴ የአገር ሽማግሌዎችና የሃይማኖት አባቶች ህዝቡ አመጹን እንዲተው ከፍተኛ ግፊት እያደረጉ ነው
‪#‎የወያኔ‬ የፍትህ ሚኒስትር በአዲስ አቃቤ ህግ ተቋም ሊተካ ነው ተባለ
‪#‎የአረና‬ ድርጅት መሪዎች ታሰሩ
‪#‎በሞዛምቢክ‬ ወደብ የተገኙት የአውሮፕላን ስብርባሪዎች የጠፋው የማሊዚያ አውሮፕላን አካል ነው ተባለ
‪#‎በምዕራብ‬ ሳሃራ ያለው የተመድ ቢሮ ሊዘጋ ይችላል በማለት አንድ ባለሥልጣን ተናገሩ
‪#‎በሴኒጋል‬ የፕሬዚዳንቱን የሥልጣን ዘመን ከሰባት ወደ አምስት አመት ዝቅ እንዲል ሕዝቡ ወሰነ
‪#‎የአረብና‬ የአፍሪካ አገሮች የመከላከያ ሚኒስትሮች ግብጽ ውስጥ ተሰበሰቡ
ለዝርዝር ዜናዎች > ከታች ይጫኑ (to /read/listen detail news click below)
To Read: http://www.finote.org/news.html
To Listen PART 1: http://www.finote.org/March24EVE_Hr1.mp3
To Listen PART 2: http://www.finote.org/March24EVE_Hr2.mp3

Wednesday, March 23, 2016

ግፍ በገፍ የሞላበት አገር! ( ያሬድ ኃይለማርያም ከቤልጂየም )ግፍ በገፍ የሞላበት አገር!
ከደቡብ ኦሞ እስከ መተማ፤ ከጅጅጋ እስከ ጋምቤላ፤ ከመቀሌ እስከ ባሌ፤ ከወልቃይት እስከ ኮንሶ 
ያሬድ ኃይለማርያም
ከቤልጂየም፤ መጋቢት 142016 ..
በአንድ ማህበረሰብ ውስጥ ቅድመ-አያቶች፣ አያቶች፣ ወላጆችና ልጆች፤ ሦስትና ከዛም በላይ የሆነ ትውልድ ተመሳሳይ በሆኑ ማህበራዊ፣ ፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ችግሮች መሃል ተተብትቦ የሚማቅቅ ከሆነ የዛ ማህበረሰብ ጉዞ ጤናማነትና አቅጣጫ ጥያቄ ውስጥ ይወድቃል፡፡ በእንዲህ አይነት ማህበረሰብ ውስጥ መሰረታዊ የሆኑና የጎሉ ለውጦች ብዙም አይስተዋሉም፡፡ አንዳንዶቹም ለውጦች የቁልቁለት ጉዞ ውጤቶች ይሆኑና በራሱ ብቻ ሳይሆን በአያቶቹም ቁስል የሚማቅቅ፣ መቃብር ቆፋሪና ሸክሙ የከበደው ትውልድ ይፈጠራል፡፡ ይህ አይነቱ ትውልድ የተጫነውን ሸክሙን አራግፎ በነገ ህይወቱና ጥቅሞቹ ዙሪያ ላይ በማተኮር ለፈጠራና ለምርምር ሊያውለው የሚችለውን አቅሙንና ጊዜውን ያልኖረበትን ትላንትን እያመነዠከና የወረሰውን ቁስል እየጎደፈረ ይቆዝማል፣ ያቄማል፣ እርስ በእርሱ ይጎነታተላል፤ ሲከፋም ወደ እልቂት ያመራል፡፡ እንዲህ አይነቱ አዙሪትም ከመስመር በወጣ ጊዜ በሌላው አለም እንደተስተዋለው ለአገራት መበታተንና ውድቀት፤ በሚሊዮኖችም ለሚቆጠሩ ሰዎችም እልቂት መንስዔ ይሆናል፡፡
ግፍ በገፍ የሆነባት አገራችን፤ በዚህ አይነቱ የመከራ አዙሪት ውስጥ ከሚሽከረከሩ ጥቂት አገራት አንዷ ነች፡፡ በእርግጥ እርሃብ፣ የፖለቲካ አለመረጋጋት፣ ጭቆና እና አፈና፣ የጎሣ ግጭቶችና ሌሎች መሰል አደጋዎች ለኢትዮጵያ አዲስ ነገሮች አይደሉም፡፡ ባለፉት 50 እና 60 አመታት ውስጥ እንኳ እነዚህ አደጋዎች ተደጋገመው፤ አንዳንዶቹም ያለማቋረጥ ተከስተዋል፡፡ እነዚህ አደጋዎች ኢትዮጵያን አራቁተዋታል፣ አዋርደዋታል፣ ከሥልጣኔና እድገት ጎዳናም አሽሽተዋታል፡፡ በእነዚህ አደጋዎችም ዜጎቿ አንገቸውን ደፍተዋል፣ ለስደት፣ ለግዞት፣ ለእርሃብና እርዛትም ተዳርገዋል፤ የብዙዎችም ሕይወት ተቀጥፏል፡፡
ግፍ በገፍ የሆነባት አገራችን፤ እኩይ በሆኑ ልጆቿ እጅግ ሰቅጣጭና አስነዋሪ የሆኑ ድርጊቶችንም በተደጋጋሚ ጊዜያት አስተናግዳለች፡፡ ግፈኛን በግፈኛ የሚተካው የፖለቲካ አዙሪታችንም የግፉአን ልጆች ግፈኛ፤ የግፈኛም ልጆች ግፉአን እየሆኑ ዛሬ ላይ ደርሰናል፡፡ ብዙም ሳንርቅ አንባገነንነትን፣ አፈናን እና ጭቆናን ላንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ከኢትዮጵያ ምድር ለማጥፋትና ነፃነት፣ እኩልነትና ፍትሕ የሰፈነባት ኢትዮጵያን ለመፍጠር ቆርጦ የተነሳውን እና በብሶት ተጸንሶ፣ በብሶት ተወልዶ፣ በብሶት ያደገውን የ60ዎቹን ትውልድ ጉዞ በቅጡ ማጤንም ይቻላል፡፡ ከዛ ትውልድ ውስጥ አብዛኛው ከብሶቱ ጋር አብሮ ያረጀ ሲሆን ብዙዎቹም ካለሙበት ሳይደርሱና የአገራቸውንም ትንሳዔ ሳያዩ አልፈዋል፡፡ ጥቂቶቹም በለስ እየቀናቸው ሆድ አስባሽ እየሆኑ አዙሪቱን የአንድ ጎልማሳ ሰው እድሜን እንዲያስቆጥር አድርገውታል፡፡
ግፍ በገፍ የሆነባት አገራችን፤ ዛሬም በከፋ የርሃብ አደጋ እየተለበለበችና በአስር ሚሊዮን የሚጠጉ ዜጎቿ በሞት አፋፍ ላይ ሆነው ችጋር እያሰቃያቸው ይገኛል፡፡ አሥር አመታትን እያሰለሰ ይከሰት የነበረው ችጋርም በየሁለት እና ሦስት አመታቱ እየተከሰተ በአለም አቀፉ ማህበረሰቡ ዘንድ የተሰጠንን የእርሃብተኝነት መለያ እያደሰልንና የምጽዋት ጠባቂውንው ቁጥር በብዙ እጥፍ እያሳደገ ከእኛነታችን ጋር ተጣብቶ ብዙ ዘመናትን አብሮን እየተሻገረ እዚህ ደርሰናል፡፡ የወያኔ ‘የልማት’ ፕሮፓጋንዳ ሊጋርደው ያልቻለው ይህ የችጋር አደጋ የስንት ወገኖቻችንን ሕይወት እንደቀጠፈ ቤት ይቁጠረው፡፡
ግፍ በገፍ የሆነባት አገራችን፤ በሁሉም አቅጣጫ የአገዛዝ ሥርዓቱ ጭቆና እና አፈና ባንገሸገሻቸው ብሶተኞች አመጽ እየተናወጠች ትገኛለች፡፡ ሦስት አመታትን ያስቆጠረው የሙስሊሙ ማህበረሰብ የመብት እንቅስቃሴ፣ ከአራት ወራት በላይ ያስቆጠረውና የበርካታ ንጹሃን ወገኖቻችንን ደም ያፈሰሰውና ሕይወት የቀጠፈው በኦሮሚያ ክልል ውስጥ እየተካሄደ ያለው ሕዝባዊ ቁጣና የነጻነት ጥያቄ፤ እንዲሁም የማንነት ጥያቄን መሰረት ያደረገው የወልቃይት ሕዝብ ንቅናቄና በሌሎች የአገሪቱ ክፍሎች የሚታዩት የፖለቲካ ኃይሎች መነቃቃት ሥርአቱን ብቻ ሳይሆን ሕዝቡንም ስጋት ውስጥ ከተውታል፡፡ ከዚያም ባለፈ አገሪቱ ውስጥ የፖለቲካ አለመረጋጋት አለመኖሩን እና ችግሩ በዚሁም ከቀጠለ አስፈሪ የሆነ አቅጣጫን ሊይዝ እንደሚቻል የሚያመላክቱ በርካታ ነገሮች ከወዲሁ እየተስተዋሉ ነው፡፡
ግፍ በገፍ የሆነባት አገራችን፤ የብሄር ብሔረሰቦች መብትና እኩልነት ተረጋግጧል እየተባለ ለ25 አመታት ሲደሰኮርና ሲጨፈርባት እንዳልኖረ ዛሬም ማንነታችን ይታወቅልን፣ እንደ ሕዝብም እንደሰውም እየተቆጠርን አይደለም የሚሉ ወገኖች ጥያቄ አንስተው መልስ የተነፈጉባት አገር ሆናለች፡፡ የወልቃይትና የኮንሶ ሕዝብ ጥያቄ ከብዙዎቹ በጥቂቱ የሚጠቀሱ ናቸው፡፡ የመብት ጥያቄዎቹን ያነሱ የሕዝብ ተወካዮችም ለእስርና እንግልት ተዳርገዋል፡፡ ለብሔረሰቦች መብት ቆሜያለው የሚለው ወያኔ የድል በዓሉ ሲደርስ በአመት አንዴ የሚያስታውሳቸውና ከያሉበት በውሎ አበል እያባበለ በየአደባባዩ የሚያስጨፍራቸውና የበዓሉ ማድመቂ ያደረጋቸው ህዳጣኖች በምን ሁኔታ ውስጥ እንደሚገኙ በቅርቡ በማህበራዊ ድረ-ገጾች የተሰራጨውና የብዙዎችን ቀልብ የሳበው የሱርማ ብሔረሰብ አባላት ላይ የደረሰው ዘግናኝ ሁኔታ የበደላቸውን መጠን በግልጽ የሚያሳይ ነው፡፡ ምስሉ ለሰው ልጅ ክብር ከሚገባው አያያዝ ውጭ እጅና አንገታቸውን አቆራኝተው በሲባጎ እያሰሩ ድብደባ የፈጸሙባቸው መሆኑንና የአድራጊዎቹንም

ማንነት በግልጽ ያሳያል፡፡ በአገዛዙ የጎሣ ፖለቲካ ሳቢያም ኢትዮጵያውያን በዘር ተቧድነው ወደ ግጭት እያመሩ ያሉበትና እርስ በእርስም በጥርጣሬ የሚተያዩባት አገር ሆናለች፡፡
የወያኔ ሥርዓት በሂደት ይለወጣል፣ ለሕግና ለሥርዓትም ተገዢ ይሆናለ፣ ያጠበበውንም የፖለቲካ ምህዳር በሂደት የእያሰፋና የሕዝቡን የፖለቲካ ተሳትፎ እያበረታታ አገሪቱ ወደ ዲሞከራሲያዊ ጎዳና እንድታቀና ያደርጋል የሚለው የብዙዎች ተስፋ የተሟጠጠበት ደረጃ ላይ የደረስን ይመስለኛል፡፡ የመብት ጥያቄ ለሚያቀረቡ ሕፃናት ተማሪዎችም ሆነ ሥርዓቱን በአደባባይ በሃሳብ ለሚሞግቱ ጎምቱ ፖለቲከኞች የሥርዓቱ ምላሽ ጡንቻና ጠመንጃ ነው፡፡ ወያኔ ስልጣን ከያዘበት ጊዜ አንስቶ ዘር፣ ጽኦታ፣ ኃይማኖት፣ እድሜ፣ የፖለቲካ ምልከታ ወይም ሌሎች ልዩነቶች ሳይገድቡት በጠላትነት የፈረጃቸውን ሁሉ ሲያስር፣ አስሮም ሲያሰቃይ፣ ሲገድልና ሲያስገድል፣ ሲያሳድድና ሲያፈናቅል፣ ሲዘርፍና ሲያዘርፍ፣ በሃሰት ሲከስና በሃሰት ሲያስፈርድ ቆይቷል፡፡ የሥርዓቱ ጡንቻ የሕግም ሆነ የሞራል ልጓም እንደሌለው ተደጋግሞ ተስተውሏል፡፡
ይህ አይነቱ ሁኔታ ግን ሊቀጥል እንደማይችል ባለፉት ጥቂት ወራት ውስጥ በአገሪቱ የተለያዩ ክፍሎች እየታዩ ያሉት ሕዝባዊ ቁጣዎችና የለውጥ መነቃቃቶች ጠሩ ምልክቶች ናቸው፡፡ ቀደም ሲል በሙስሊሙ ማህበረሰብ የተጀመረው የሰከነ የተቃውሞ ንቅናቄ ተገቢውን ምላሽ ሳያገን እጅግ ከፍተኛ ቁጣ በተቀላቀለበት የኦሮሚያ ክልል ሕዝባዊ አመጽ ታጅቦ ሥርዓቱን ሊወጣ ወደማይችለው አጣብቂኝ ውስጥ ከቶታል፡፡ በወልቃይት፣ በኮንሶ እና በጋምቤላም የተቀሰቀሱት እሳቶችም ተደማምረው የአገዛዙን እድሜ ብቻ ሳይሆን የአገሪቱንም ዘላቂ ሰላምና ደህንነት አደጋ ውስጥ ሊጥሉ እንደሚችሉ አደጋዎች አንጃበዋል፡፡
የአገዛዝ ሥርዓቱ ላለፉት 25 ዓመታት የገነባው አጥርና ያሰመረው ቀይ መስመር ዛሬ ግፍ ባሰከራቸው ግፉዋን እየተጣሰና እየተደረመሰ ነው፡፡ ባደባባይ በሰለጠነ መንገድ የተቃወሙትን፣ የሃሳብ ልዩነት ያላቸውን፣ የተቹትንም ይሁን ለሥርዓቱ አገልጋይ ሆነው የቆዩትንና በጥርጣሬ ያያቸውን ሁሉ በፈረጠመ ጡንቻው እየደቆሰ እዚህ የደረሰው ወያኔ ፈተና ላይ የወደቀ ይመስለኛል፡፡ ጡንቻ ልብን ቢያደነድንም፣ ማናለብኝነትን ቢያነግስም፣ አእምሮን አዶልዱሞና የማሰብ ችሎታን አቀጭጮ ለሌላው የሰው ዘር እንዳንራራ ቢያደፋፍርም መሰረቱ ግን ጥልቅ ፍርሃት ነው፡፡ በፍርሃት ውስጥ የሚኖር የፖለቲካ ሥርዓት ብቻ ነው ጡንቻውን በሕዝብ ሃብት እያሳበጠ መልሶ ቀለቡን የሚሰፍርለትን ሕዝብ እየጨፈለቀና እያስፈራራ መኖር የሚፈልገው፡፡
አገሪቷ ላይ ያንጃበቡት እነዚህ አደጋዎች የኢትዮጵያን ቀጣይ ጉዞ የሚወስኑ ይመስለኛል፡፡ ከዚህ ትርምስና አስፈሪ ሁኔታ በቀላሉ አገግመንና በድል አድራጊነት ልንወጣ የምንችለው እንደ እኔ እምነት ከዚህ በሚከተሉት ሃሳቦች ዙሪያ መግባባትና አብሮ መስራት ሲቻል ይመስለኛል፡፡
1. ከአፋኝና ታፋኝ የፖለቲካ አዙሪት ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ልንላቀቅና ጭቆናን ታሪክ አድርገን ወደ ዲሞክራሲያዊ ጎዳና ለንሸጋገር የምንችለው ግፉአን ብቻ ሳይሆኑ ግፍ ፈጻሚዎቹም አብረው ነጻ ሲወጡ ብቻ ነው፡፡ ስለዚህም አገርን የማዳን ትግሉ ለአገዛዝ ሥርዓቱ የመጨቆኛ መሳሪያ በመሆን እያገለገሉ ያሉ አጋር ድርጅቶችን እና ግለሰቦችን ከወያኔ ጉያ ማውጣትና የሕዝብ ወገንተኛ እንዲሆኑ ማድረግን ዋና ግቡ ማድረግ አለበት፡፡ ለዚህም በመሳሪያ አቅም፣ በፖለቲካ አደረጃጀት፣ በገንዘብም አቅም ይሁን ሰፊውን የአገሪቱን ክፍል በማስተዳደር ዕረገድ የማይናቅ ድርሻ ያላቸውን ኦህዴድ (የኦሮሞ ህዝብ ዴሞክራሲያዊ ድርጅት)፣ ብአዴን (የብሔራዊ አማራ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ) እና ሌሎች አጋር ድርጅቶችን የትግሉ አካል እንዲሆኑ ሁኔታዎችን ከወዲሁ ማመቻቸት ትግሉን ከማፋጠን ባለፈም ሊደርስ የሚችለውን የጥፋትና እልቂት አደጋም የመቀነስ ኃይል ይኖረዋል፡፡ የህዝብ እሮሮዎችና ትያቄዎች ሆኖ በማያውቅ ምልኩ በእነዚህ ሁለት ድርጅቶች ውስጥ በይፋ እየተንጸባረቀ እንደሆነ በየጊዜው ከድርጅቶቹ እያፈተለኩ የሚወጡት መረጃዎች በግልጽ ያሳያሉ፡፡ በምን መልኩ እነዚህን ድርጅቶች ከወያኔ ጉያ ማላቀቅና ነጻ ማውጣት እንደሚቻል ዝርዝሩን በጉዳዩ ላይ ለመስራት ፍላጎቱና አቅሙ ላላቸው አካላት እተወዋለሁ፡፡
2. ኢትዮጵያንና ሕዝቧን ከተሰነቀሩበት ቅርቃር ለማማቀቅና ዴሞክራሲ፣ ፍትህ፣ እኩልነትና ሰላም የተረጋገጠባት እና የሁሉም የሆነች ኢትዮጵያን ለማምጣት የተደራጁ የፖለቲካ ኃይሎች መቀናጀት ባለመቻላቸው የተነሳ ለለውጥ አመቺ የሆኑ በርካታ አጋጣሚዎች እየተፈጠሩ ሊጠቀምባቸው የሚችል ኃይል ባለመፈጠሩ እልም እየሆኑ አልፈዋል፡፡ ዛሬ ግን ከመቼውም ጊዜ የተሻለ ሁኔታ የተፈጠረ ይመስለኛል፡፡ በመላ አገሪቷ ሰፊ የሆነ ሕዝባዊ መነቃቃት እየተስተዋለ ነው፡፡ በመሆኑም የፖለቲካ አመራር ኃይሎች በተለይም በውጭ የሚገኙ ድርጅቶች በየመድረኩና በየመገናኛ ብዙሃኑ ከመነታረክ፣ አሰልቺ የሆኑና የተለመዱ የፖለቲካ ትንታኔያቸውን ከመስጠት፣ እርስ በእርስ ከመናቆርና አንዳንዴም በባዶ ሜዳ ‘ወሬ የፈታው’ አይነት ፉከራና ቀረርቶ ከማሰማት ተቆጥበው ለጋራና የተቀናጀ ትግል ቢሰሩ እና ያለመሪ በተበታተነ መልኩ በየቦታው የተቀጣጠለውን ሕዝባዊ ንቅናቄና የለውጥ ጥያቄም አቅጣጫ ቢያሲዙት ለውጡም ይፋጠናል፤ ያንጃበቡትም አደጋዎች ብዙ የህይወት ዋጋ ሳያስከፍሉ የኢትዮጵያ ትንሳዔ እውን ይሆናል፡፡
ለመብታቸውና ለነጻነታቸው ሲታገሉ የተሰዉትን ሰማዕታት ነፍሳቸውን ይማር! በቸር እንሰንበት!
ያሬድ ኃይለማርያም ፡ yhailema@gmail.com 

Monday, March 21, 2016

እስኪ ስለ እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ ሰብአዊ መብት መነጋገር እንጀምር-- አክሎግ ቢራራ (ዶር)

ታሪካዊ ግዴታ
--እስኪ ስለ እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ ሰብአዊ መብት መነጋገር እንጀምር--
አክሎግ ቢራራ (ዶር)
እኛ ኢትዮጵያዊያን የፖለቲካ ልሂቃን ከአብዛኛው የኢትዮጵያ ሕዝብ አስተሳሰብና ፍላጎት የተለየ ኋላቀር የፖለቲካ ባህል ስንከተል ቆይተናል። ከፍተኛ ትምህርት ኖሮን መደማመጥ አንችልም፤ ለመናበብ አንችልም። ይኼ ችግር ብሄራዊ አደጋዎችን ፈጥሯል። በአገር ደረጃ የሚነጋገረው ልሂቃንና ምሁራን ቁጥር በጣም ዝቅተኛ ነው። ሁኔታውን ያባባሰው ስርዓቱ መሆኑ የሚያከራክር አይመስለኝም። ባለፉት ሃያ አምስት ዓመታት በጭቁን ሕዝቦች ስም በመነገድ በኢትዮጵያ ሕዝብ ላይ የተጫነው የቋንቋና የጎሳ መለያ ሕገመንግሥትና የክልል አስተዳደር ለሁሉም ኢትዮጵያዊያን ማፈኛና ለጥቂት የህወሓት ኪራይ ሰብሳቢዎች ሚሊየኔርነት መሳሪያ መሆኑ በሂደት እየታየ ነው። ይህ ኪራይ ሰብሳቢ ቡድን ሌሎችም ኪራይ ሰብሳቦዎች እንዲሆኑ አድርጓል። ኪራይ ሰብሳቢ በሞላበት አገር ድህነት፤ ረሃብ፤ ስደትና ውርደት እየባሰ ብሄድ አያስገርምም። ተቃዋሚውን ሽባ ያደረገውም ፍርሃት ከስርዓቱ ጋር የተያያዘ ነው። ስርዓቱ ለፖለቲካና ለኢኮኖሚ ፍጹም የሆነ የበላይነት (Absolute minority ethnic elite hegemony) ያገለገለው በትግራይ ሕዝብ ስም ለሚንቀሳቀሰው፤ ሆኖም የአብዛኛውን የትግራይ ሕዝብ አዘቅት ላስገባው ለህወሓት አባላት ነው።
ባለፈው ሃተታየ እንዳቀርብኩት፤ የዘውግ ወይንም የጎሳ ፌደራሊዝም ከጅምሩ የጀርባ ምስጢር ነበረው። ይኼውም በጭቁን ህዝቦች ነጻነት፤ መብትና ራስን ችሎ ማስተዳደር ስም፤ የህወሓትን የበላይነት ሕገመንግሥታዊ ሽፋን ስጥቶ የበላይነትን ተቋማዊ ማድረጉ ነው። የዚህ ሃተታ መሰረት ለዚህ ስርዓት ወለድ ተግዳሮት መፍትሄው በብሄራዊ ደረጃ መሰብሰብ፤ መደራጀትና አብሮ መታገል አስፈላጊ ሆኗል የሚል ነው። የህወሓት የበላይነት ሽፋን ኢህአዴግ የሚለው የብሄረሰብ ልሂቃን ስብስብና አገዛዝ ነው። ኢህአዴግ ሲባል አቻ ለአቻ የሆኑ ድርጅቶች ስብስብ አለመሆኑ በተደጋጋሚ ታይቷል። ውጤቱ ምንንድን ነው? ብለን ብንጠይቅ የሚከተሉትን እናያለን፤
አንድ፤ የኢትዮጵያ አንድነትና ሉዐላዊነት አደገኛ በሆነ ደረጃ መድከሙ። አንድ ኢትዮጱያዊ ከክልሉ ወጥቶ ወደሌላ ክልል ሲሄድ ልክ ከጎረቤት አገር እንደመጣ እንግዳ “ከየት መጣህ” ተብሎ ይጠየቃል። ይህ በአገር “እንግዳ” መሆን በአፄ ኃይለ ሥላሴና በደርግ መንግሥታት ፍጹም የማይታሰብ ነበር። አንድ የታወቀ ኢትዮጵያዊ ምሁር፤ ፕሮፌሰር ዳኛቸው አሰፋ በድህረ ገጾች እንዳስቀመጠው፤ “ለመሆኑ ኢትዮጵያ አለች ወይ” ተብሎ ከሚጠየቅበት ደራጃ የገባነው በህወሓት ዘመን መሆኑ ነው።
ሁለት፤ የጎሳ ልሂቃን ባይፈቅዱ ኖሮ የማንነት ጥያቄ የኢትዮጵያን ሕዝብ ሊለያየውና ሊበታትነው አይችልም ነበር። ሕዝቡ ይኼን በሚገባ ያውቃል። ሕዝቡን የምንለያየው የፖለቲካ ልሂቃኖቹና ምሁራኖቹ ነን። ከማንኛውም አገር በበለጠ ደረጃ የኢትዮጵያ ሕዝብ ጠባብ ጎሰኛና ብሄርተኛ ሆኖ አያውቅም። ጎሠኛ ቢሆን ኖሮ ብዙ እልቂት ይካሄድ ነበር። ሕዝቡ ተጋብቷል፤ ተዋልዷል፤ ተቻችሎ ይኖራል። የአድዋን የመቶ ሃያኛ ዓመት በዓል ስናከብር ማስታወስ ያለብን ድሉ የሁሉም ኢትዮጵያዊያን ድል መሆኑን ነው። ማንም ሳይስገድደው ገበሬው፤ ነጋዴው፤ የቢሮ ሰራተኛው፤ ወታደሩና ሌላው ከሁሉም የኢትዮጵያ ክፍሎችና ጎሳዎች ስንቁን ተሸክሞ ጣልያንን ተባብሮ አሸንፎ ወደመጣበት የመለሰው ከጎሰኛነትና ከጎጠኛነት ባሻገር ለአገሩ ነጻነት፤ ሉዐላዊነትና ለሕዝቡ ክብር ስለቆመ ነው። ዛሬ ማንነት መነገጃ ሆኗል፤ ትርጉም አጥቷል። የማንነት ጥያቄ ተቀዳሚ ሆኗል ሲባል አሁንም የሕዝቡን ልዩነት የሚያሳይ አይደለም። አንድ ግለሰብ በሞያው ገበሬ ወይንም ነጋዴ፤ በኃይማኖቱ ክርስቲያን ወይንም ሙስለም፤ በጾታው ወንድ ወይንም ሴት ወዘተ ሊሆን መብቱ ነው። ይኼን መብት ማንም ሊነፍገውና ሊከለክለው አይችልም። ከዚያ ባሻገር ግን በአገር ደረጃ “ጋናዊው እኔ ጋናዊ ነኝ” እንደሚለው ሁሉ ኢትዮጵያዊው “እኔ ኢትዮጵያዊ ነኝ” የማለት ግዴታችን ግልጽ ነው። በዜግነታችን መለያ ኢትዮጵይዊ ነን ካልን መኖሪያችን በጎሳዊ ክልል ምሽግ፤ ግንብና ድንበር ሊወሰን አይችልም። በእያንዳዱ ክልል የእያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ መብት ካልተከበረ የማንም መብት ሊከበር አይችልም። ይኼን ካልተቀበልን ከህወሓትና ሌሎች የጎሳ ስብስቦች ከሚሉት ምን ይለየናል?
በነገራችን ላይ፤ በጎሳ መለያየት በተመጣጠነ፤ በዘላቂና ፍትሃዊ የኢኮኖሚና የማህበረሰባዊ እድገት ላይ ከፍተኛ ተጽኖ አለው። ለምሳሌ፤ የኦሞ ሸለቆ፤ የቤኒ-ሻንጉል ጉሙዝ፤ የአፋር፤ የጋምቤላ፤ የኦጋዴን ሕዝብ በዜግነቱ ምን ያገኘው ጥቅም አለ?
ሶስት፤ የህወሓት ደጋፊዎችና ወፍ ዘራሽ ተጠቃሚዎች እንደሚሉት ሳይሆን የጎሳ ፖለቲካ ለሃያ አምስት ዓመታት ሊሰራ የቻለው የኢትዮጵያ ሕዝብ ስለተቀበለው አይደለም። ህወሓት ለብዙ ሽህ ዓመታት በወንድማማችነት፤ በእህትማማችነት ሲኖር የቆየውን ሕዝብ፤ በተለይ የአማራውንና የኦሮሞውን ሕዝብ እንዲጋጭ በማድረጉ ነው። ይኼን መከፋፈል ድብቅ አጀንዳቸው የሚጠቀሙ ከፋፋዮች ቢኖሩም ሁኔታውን የፈጠረው የህወሓትና ተባባሪው የኢህአዴግ አመራር ነው። ለምሳሌ፤ ከጅምሩ ህወሓት ህብረብሄር የሆኑ የፖለቲካ ፓርቲዎችን፤ አገር ወዳዶችን፤ ምሁራንን፤ የሞያና ሌሎች ተቋሞችን በማፈራረሱ። በምትካቸው ልክ በፋብሪካ እንደሚመረቱ አድርጎ ለራሱ የሚጠቅሙትን መተኪያዎች አገር አቀፍ በሆነ ደረጃ ዘርግቷል። ፓርላማውን ለራሱ መገልገያ አድርጎታል። ሕግ አዉጭው፤ ሕግ ተርጓሚው፤ ሕግ አስፈጻሚው ህወሓት ነው። ፊት ለፊት ለይስሙላ የሚያስቀምጣቸው ግለሰቦች ከሌሎች ብሄረሰቦች የተወጣጡ ናቸው ተብሎ እንዲታመን ያደርጋል። ይህን ሽፋን (Camouflage) ሕዝቡ ያውቀዋል። ፊት ለፊትና በጀርባ ሆነው ፖሊሲ የሚያወጡትና የሚተገብሩት የህወሓት አባላት ናቸው። የሚጠቀሙባቸው አባባሎች ብዙ ናቸው፤ “ሕገመንግሥቱን ለማስከበር፤ ለመደጋገፍ፤ እድገቱን ለመቀጠል፤ ሽብርተኞችን ለመቆጣጠር” ወዘተ። እናንተን ማን ይቆጣጠራል የሚል ተቋም ወይንም ግለሰብ የለም፤ አይታሰብም። በአንድ ትንተና ላይ ጋርዲያን የተባለው የእንግሊዝ ጋዜጣ በትክክል እንዳስቀመጠው፤ ይህ አገዛዝ ኦርዌልያን (Orwellian) ወይንም የፖሊስ መንግሥት (Police State) ከሆነ ሃያ አምስት ዓመታት ሆኖታል። ከህወሓት ውጭ ያሉት የኢህአዴግ አባል ድርጅቶች ቢቀበሉትም ባይቀበሉትም የበላዩ ወይንም አለቃው ህወሓት ነው። የህወሓትን የበላይነት የማይቀበል የኢህአዴግ አባል ፈልጎ ለማግኘት አይቻልም። “ኢህአደጎች ራሳችሁን ከአምባገነኑ ህወሓት ነጻ አውጡ” ያለ ግለሰብ ትዝ ይለኛል።
አራት፤ ህወሓት ቀላል ድርጅት አይደለም፤ ምስጢር ይጠብቃል። ጠንካራ ስለሆነ ከፋፍሎናል። ህወሓት ይደጋገፋል፤ ይጠቃቀማል። ሌሎቹን አባል ድርጅቶች የማሳመን ችሎታው የሚደነቅ ነው። ያስፈራራል ወይንም ያባብላል፤ ይገዛል፤ ያከብራል፤ ይደልላል፤ ያደኸያል ወይንም በስውር ያሸሻል፤ ያባርራል ወዘተ። አጭበርብሮም ሆነ አስፈራርቶ ምርጫዎችን ለበላይነት ይጠቀማል። ቅንጅትና ህብረት የዘጠና ሰባቱን ምርጫ አሸነፉ። ህወሓት ማሸነፋቸውን አልተቀበለም። የራሳቸው የአመራር ድክመት መኖሩ ባይካድም፤ የሕዝብን ድምጽ የሰረቀው ህወሓት ነው። የፖለቲካ ሙስና በጭካኔ! ተሸንፎ ያሸነፉትን ይቅርታ የሚጠይቅ አገዛዝ ስኬታማ የሆነው በራሱ ጥንካሬ ሳይሆን ተቃዋሚው የተከፋፈለ በመሆኑ፤ የውጭ ድጋፍ ስላለው፤ ህብረብሄር ድርጅቶችን በማፈኑ፤ በማፈራረሱና ቆራጥ የሆኑ አገር ወዳድ ድርጅቶችና መሪዎች ባለመኖራቸውና እንዳይኖሩ በመደረጋቸው ነው። በተደጋጋሚ የታየውና አሁንም የሚደገመው ክስተት አንድ ነው። በጎሳ ተከፋፍሎ ራስን ማጋለጥ የፖለቲካ ክስረት አስከትሏል። የተከፋፈለ ህብረተሰብና ተቃዋሚ ሁሌም የሚያገልግለው ህወሓትን ነው።
እንደገና በ2010 ተወዳዳሪዎችን አፍኖ፤ ከፋፍሎና አስሮ ምርጫውን 99.6 በመቶ አሸነፍኩ አለ። አምስት ዓመት ቆይቶ በለመደው የፖለቲካ ጮሌነት በ2015 ይባስ ብሎ 100 በመቶ “አሸነፍኩ” አለ። ምርጫን መሳቂያና መሳለቂያ አደረገ። ሕዝብን ፍጹም በሆነ ደረጃ ተስፋ አስቆረጠ። የብሄረሰብ እኩልነት ተብሎ ይጠራ የነበረው ስርዓት የኦሮሞ ተወላጅ የሆኑ ኢትዮጵያዊያን ሲታፈኑ፤ ሲገደሉ፤ ሲሰወሩና ሲሰደዱ የጎሳ ፖለቲካ አስተዳደር የማያዋጣ መሆኑን አስመሰከረ። አንዳንድ ተመልካቾች አዲስ ምርጫ “በኦሮሚያ ክልል ቢካሄድ ይመረጣል” ይላሉ። ስር ዓቱ ነጻና ፍትሃዊ ምርጫ የማይፈቅድ መሆኑ እየታወቀ አዲስ ምርጫ ዋጋ ቢስ ነው። የሚያዋጣው ስርዓቱን መለወጥ እንጅ የይስሙላ ምርጫ አይደለም። እንዲያውም የኢትዮጵያን ሕዝብ በተከታታይ ማታለል ነው።
አምስት፤ “ታዲያ ምን አለበት፤ ተቃዋሚው ደካማና የተከፋፈለ ከሆነ፤ ኢህአዴግ ለምን አያሸንፍም? ጠንካራ ፓርቲና መንግሥት ከሌለ ኢትዮጵያ እንደ ሶማሊያና ኬንያ ትሆናለች፤ በአመጸኞች፤ ተገንጣዮችና ሽብርተኞች ትጠቃለች። እድገቷ ያቆማል። የመበታተን አድሏ ይባባሳል። የትኛው ተቃዋሚ ነው ከገዢው ፓርቲ ጋር ሊነጻጸር የሚችል?” የሚሉ ጥያቄዎችና ትችቶች ይሰነዘራሉ። አግባብ አላቸው። በአንድ አገር ሁለት ወይንም ከዚያ በላይ መንግሥታት ሊኖሩ አይችልም። በአንድ ፌደረላዊ አገር የተለያዩ፤ ራሳቸውን እንደ ጎረቤት አገር የሚለዩ አገሮች ሊኖሩ አይችልም። ሁለት ወይንም ከዚያ በላይ የሚሆኑ ራሳቸውን እንደ ነጻ አገር የሚቆጥሩ አገሮች አሉ ከተባለ ኢትዮጵያ የምትባል አገር የለችም ማለት ነው። ቁም ነገሩ ወደዚህ ችግር ያሸጋገረን ማነው? ብለን ብንጠይቅ የክልሎች ሕገመንግሥት ያወጡት የጎሳ ስብስቦች ናቸው፤ ህወሓት፤ ሻቢያና ኦነግ። ይኼን በሚቀጥለው ሃተታየ አቀርባለሁ።
የዚህን የተሳሳተ የጎሳ ፖለቲካ ሂደትና ውጤት እያወቅን፤ አንዳንዶቻችን አውቀንም ይሁን ሳናውቅ እነዚህን መሰረታዊ ችግሮች የፈጠረውን ገዢ ፓርቲና የብሄር ተቃዋሚዎችን በቀላሉ እየሸነገልን ነው። ህወሓት፤ ኢህአዴግን መቃወም አግባብ አለው። ሆኖም፤ ለመቃወም ብቻ ሲባል ብሄርተኞችን፤ ሽብርተኞችን፤ አመፀኞችን፤ ተገንጣዮችን፤ የውጭ ጠላቶችን ወዘተ መደገፍ እንዴት ሊያዋጣ ይችላል? ከአብዛኛው ሕዝብ እኩልነት፤ ፍትህና ዲሞክራሲ ምኞት ጋር ምን ግንኙነት አለው? የአገሪቱን በክልል መከፋፈል ተቀብሎ ኢትዮጵያና ኢትዮጵያዊያን የሚሉትን እሴት የተመረኮዙ ስያሜዎች ለመጠቀም አለመቻል፤ ወይንም አለመፍቀድ የማንን ዘላቂ ግብ ያጠንክራል፤ ያገልግላል? ሕዝብን ከሕዝብ-- ኦሮሞውን ከአማራው፤ ሁለቱን ከትግራዩና ከሌላው ሕዝብ--ጋር በማገናኘት፤ በማስታረቅና በማስማማት ፋንታ እንዲጋጭ የምናደርግበት ምክንያት ምንድን ነው? ከጥንት ጀምሮ ዛሬ ኦሮምያ በሚባለው ክልል ብዙ ሚሊየኖች የኦሮሞ ብሄረሰብ ያልሆኑ ኢትዮጵያዊያን ይኖራሉ። የኦሮሞ ሕዝብ በጎንደር፤ በጎጃም፤ በወሎ፤ በሸዋና ሌሎች ቦታዎች ይኖራል። እነለያይ ብንል ማን ከማን ይለያያል። በመፈቃቀድና ተፈቃቅዶ ችግሮችን በጋራ ከመፍታት የበለጠ አማራጭ
የለም። አለያ፤ ከአንድ ችግር ወጥተን ወደሌላ ችግር መግባታችን አይቀርም። ያም ሆነ ይህ፤ የጎሳ ጥላቻና መከፋፈል ህይወትና ቆይታ የሚሰጠው እንቃወመዋለን ለምንለው ገዢ ፓርቲ ነው።
ለእውነተኛ ፍትህ ቆመናል ካልን መቀበል የሚኖርብን ተራው የኢትዮጵያ ሕዝብ የጎሳ ግጭት የማይፈልግ መሆኑን ነው። በሌላ በኩል ህወሓት ውስጥ ለውስጥ ኦሮሞ ያልሆነውን የሕብረተሰብ ክፍል የሌለ ጠላት ፈጥሮ “እኔን ካልደገፍክ ህልውናህ አስተማማኝ አይሆንም” የሚለውን የከፋፍለህ ግዛው ዘዴ መከላከል አለብን። አንዴ አኟኩን፤ ሌላ ጊዜ አማራውን፤ ሌላ ጊዜ የኦጋዴን ሶማሌውን፤ ሌላ ጊዜ የኦሞ ሸለቆ ኢትዮጵያዊውን፤ ሌላ ጊዜ የኦሮሞ ተወላጁን ወዘተ እያሰሩ፤ እያሳደዱ፤ እየወነጀሉ፤ እያፈራረሱ፤ ዜጎች በድብቅ እንዲሰወሩ እያደረጉ፤ ከደርግ በተለየ ጥበብ በማይታወቁ መንገዶች ተቃዋዋሚውን “እየሰወሩ” ተቃዋሚ ፓርቲ፤ ዲሞክራትና አገር ወዳድ የለም ማለት፤ ወይንም እየጨፈጨፉ አልጨፈጨፍኩም ማለት የፖለቲካ ጮሌነት ነው። ፈረንጆች ማኬቬሊያን የሆነ የፖለቲላ አመራር ይሉታል። የህወሓት አለቃዎችና ወራሾች ከዲሞክራቶችና አገር ወዳዶች ይልቅ ከአምባገነኖች ፈላስፋዎች የተማሩት ይልቃል።
ማኬአቬሊ (Machiavelli) 1513 The Prince በተባለው የፖለቲካ ፍልስፍና መጽሃፉ አንድ ቡድን ሌሎችን ፍጹም በሆነ ደረጃ የበላይ ሆኖ እንዴት እንደሚገዛ ትምህርት ያቀርባል። አራት የተለያዩ አምባገነን የሆኑ የመንግሥት ስርዓቶችን አጥንቶና መሰረት አድርጎ እያንዳንዳቸው እንዴት የበላይነታቸውን እንደሚያጠናክሩ ዘዴዎችን ይጠቁማል። ከእነዚህ መካከል ከፍተኛ ሚና ያለው የስለላና የወታደር ኃይል ተቋም ወሳኝ መሆኑን ይናገራል። ኃይል ያለው ይገዛል፤ ኃይል የሌለው ይገዛል የሚል መሆኑ ነው። ህወሓት ይኼን ጥበብ ሙሉ በሙሉ ተጠቅሞበታል፤ የአሜሪካ እርዳታ ለጥንካሬው መሰረት ሆኗል። ማኬያቬሊ እንዳለው የመሳሪያ የበላይነት በአንድ በኩል፤ በሌላ በኩል ግብረገብነት፤ ፍትህ፤ ሰብአዊነት አብረው አይሄዱም። የህወሓት ህልውናና አምባገነናዊው አገዛዝ እንዲቀጥል ከተፈለገ ህወሓት ጭካኔ ያለበት (Evil Political Actions) እርምጃ መውሰዱ የማይቀር ነው። ፈላስፋው ሁኔታዎች ሲለወጡ አምባገነን አገዛዝም እንደሚለወጥ ይናገራል። ሕዝብ በአንድ ድምጽ ተያይዞና ተባብሮ ከተነሳ የሚያቆመው ኃይል እንደሌለ ይታወቃል። በጎሳ መከፋፈላችን ይብቃ የምልበት መሰረታዊ ሃሳብ ይኼ ነው።
እርስ በርሳችን ከመጋጨት በላይ መጠየቅ ያለብን የሕዝብ ዐመጽ ተደጋጋሚ ሲሆንስ ህወሓት ራሱን ለመለወጥ ፍላጎት አለው ወይንስ የማኬያቬሊን ፍልስፍና ይከተላል? አላውቅም። የማውቀው የጭካኔ አገዛዝ ለጊዜው እርጋታ ቢፈጥርም መሰረታዊ የሆኑ ችግሮችን አይፈታም። መሰረታዊ ችግሮች የሚፈቱት የኢትዮጵያ ሕዝብ ለመብቱ በአንድ ድምጽ ሲነሳ ነው። በኦሮምያ፤ በጋምቤላ፤ በቤኒ ሻንጉል ጉሙዝ፤ በኦጋዴንና በሰሜን ጎንደር በተከታታይ የሚታየው የሕዝብ ዐመጽ ለገዢው ፓርቲ ስጋት እንደፈጠረ ይታያል። ሆኖም፤ ይህ ስጋት ወደ ለውጥ ሊሸጋገር የሚችለው የጎሳና ሌሎች ልሂቃን የእርስ በርስ ትችቱን ትተው ወደ አንድነትም ባይሆን ወደ እውነተኛ መተባበር ሲሸጋገሩ ነው። አንድነት ስል፤ ማንም ክፍል በተናጠል የአንድነት ጠበቃና ሃላፊ እንዳልሆነ ለማሳሰብ እፈልጋለሁ። የኢትዮጵያ ብሄራዊ አንድነትና ሉዐላዊነት የአንድ ወይንም የሁለት ብሄረሰብ ጉዳይ ብቻ አይደለም። የኢትዮጵያ ሕዝብ አንድነት ስል የሁሉም ሕዝቦች አንድነት ማለቴ ነው። ብሄራዊ አንድነት አስተማማኝ የሚሆነው የፌደራሉ መንግሥት መሪዎች የአገሪቱን ስብጥር ሕዝብ ሲወክሉ ነው። የአገርም ሆነ የሕዝብ ጥንካሬ መሰረት ኢትዮጵያዊያን “የእኔ መንግሥት ነው” ለማለት ሲችሉ ነው። የህወሓት ድክመት መሰረት የአንድ አናሳ ብሄረሰብ ፍጹም የበላይነት ነው።
ስድስት፤ በተከታታይ ጽሁፎቸ በማስረጃ እንዳሳየሁት፤ በሁሉም ወሳኝ በሆኑ የስለላና መረጃ፤ የመከላከያ፤ የፌደራል ፖሊስ፤ ቁልፍ የሆኑ ሚኒስትሪዎችና የአገር ንብረት ተቋሞች (State owned enterprises such as Ethiopian Airlines, Telecommunication etc.) ባለፉት ሃያ አምስት ዓመታት ፖሊሲና ውሳኔ ለማድረግ የሚችሉት ግለሰቦች ትግራዮች ናቸው። ይህ የአንድ ብሄረሰብ ፍጹም የሆነ የበላይነት በኢትዮጵያ ታሪክ ታይቶ የማይታወቅ ነው። ኢትዮጵያዊያን ብቻ ሳይሆኑ የውጭ ተመልካቾች ይኼ ሁኔታ አደገኛ መሆኑን በተደጋጋሚ አሳስበዋል። የኢትዮጵያን የመከላከያን ኃይል ተቋም ብቻ ብናይ ከኮሎኔል በላይ የበላይ እዙ አባላት ከሆኑት መካከል 97 በመቶ የሚሆኑት የህወሓት አብላት ወይንም ደጋፊዎች ናቸው፤ ከአንድ ብሄረሰብ የተወጣጡ ማለት ነው። (See on line “Ethiopia promotes 37 Senior Officers to the rank of general). ከአገሪቱ ዘላቂ ደህንነትና ከሕዝቧ አንድነት አንጻር ብናየው ይኼ ለትግራይ ሕዝብም አደገኛ ነው። ግልጽ ለማድረግ የምፈልገው የትግራይ ተወላጆች በእዙ ሚና አይኑራቸው ለማለት አይደለም። የእዙ ስብጥር የኢትዮጵያን ሕዝብ የሚወክል ይሁን ማለቴ ነው። ይህ ለኢትዮጵያ ደህንነት ወሳኝ ነው።
ሌሎቻችን፤ የህወሓት አባላትንና ደጋፊ ትግራዮችን ጨምሮ፤ መተቸት ያለብን “ለብሄረሰቦች እኩልነት” ቆምኩ የሚለው ህወሓት ይኼን የሚያስወቅስ ጎሳዊ አድልዎ በተደጋጋሚ መርህ ሲያደርግ አለመተማመንን እንደፈጠረና ይኼ አለመተማመን ወደ አደገኛ ሁኔታ እንደሚያመራ ማሳየትና መፍትሄ መፈለግ ነው። መተቸቱ ብቻ በቂ አይደለም። የእዙ ስብጥር ወሳኝ ነው ስል፤ የጋምቤላ ወይንም የጎንደር ወይንም የኦጋዴን ወይንም የኦሮምያ ወዘተ ሕዝብ የትግራይ አዛዦችን፤ ልዩ ኃይሉን አጋዚን በሚያዩበት ጊዜ ምን እንደሚሰማቸው ለማጤን ይቻላል። የተጎዱት “እኛና እነሱ” እያሉ ቢናገሩ እንዴት ይፈረድባቸዋል። “እኛና እነሱ” የሚለው እጅግ በጣም አደገኛ መሆኑን ሁላችንም መገንዘብ አለብን።
በኢኮኖሚውም ያለው ሁኔታ ተመሳሳይ ነው። የዘመናዊውን ኢኮኖሚ የበላይነት ጥልቀት ባለው መልኩ ብናየው የበላይነቱን የያዙት የህወሓት አባላት፤ ታማኞችና ደጋፊዎች ናቸው። እዚህ ላይ ጥንቃቄ ማድረግ አግባብ አለው። አንድ፤ የወፍ ዘራሽ ተጠቃሚዎች መኖራቸውን መካድ አንችልም። የኢኮኖሚው የበላይነት በአብዛኛው የህወሓት ልሂቃን ይሁን እንጅ ከሌሎች ጎሳዎች የተወጣጡ አዲስ ሃብታሞች እንዳሉ መካድ አይቻልም። ስርጭቱ የመደብ መልክ እየያዘ ነው---አማራም፤ ጉራጌም፤ ኦሮሞም፤ ወላይታም፤ ሶማሌም፤ ክርስቲያንም፤ ሙስለምም ወዘተ ተሳታፊ ነኝ የሚል የመደብ መልክ የያዘበት ሁኔታ ተፈጥሯል። በአጭሩ፤ የህወሓት የኢኮኖሚ የበላይነት ባይካድም፤ ኪራይ ሰብሳቢ ሲባል የህወሓት አባላት ብቻ ናቸው ከሚል የተሳሳተ ድምዳሜ ላይ እንዳንደርስ ማለቴ ነው። ሁለት፤ አብዛኛው የትግራይ ሕዝብ የኪራይ ሰብሳቢው ክበብ ወይንም ቡድን አባል አይደለም። በእኔ ግምት አብዛኛው የትግራይ ሕዝብ ድሃ ነው፤ ሰርቶ አደር ነው፤ አገር ወዳድ ነው፤ የታፈነና ነጻነት የሌለው ነው፤ ባህሉን የሚያከብር መንፈሳዊ ሕዝብ ነው። ባጭሩ፤ የህወሓትን የበላይነት ከትግራይ ሕዝብ ሁኔታ እንለየው።
በቅርቡ ጠቅላይ ሚንስትር ኃይለማሪያም ደሳለኝ ስለ አገሪቱ ሁኔታ፤ በተለይ በኦሮምያና ሌሎች አካባቢዎች ስለተከሰተው ሕዝባዊ አመጽ ሲናገሩ ችግሩን የፈጠረው ስርዓቱ፤ መንግሥቱና አመራሩ መሆኑን አስምረውበታል። እሳቸው ያሉት ህዝብን ለመሸንገል ካልሆነ በከፊልም ቢሆን ያሉትን እጋራለሁ። ለምስታወስ፤ ስለመጥፎ አስተዳደርና ስለ ኪራይ ሰብሳቢነት ባህልም ተመሳሳይ ትችት አድርገው ነበር። ትዝ እንደሚለኝ ከሆነ “እኛ ከዚህ ስንወጣ ልክ እንዳልሰማንሆነንወደራሳችንቡድኖችእንገባለን፤ለውጥአንዳናካሂድማነቆእንሆናለን”በለዋል። ምንምየረባለውጥ አልታየም። አሁንም ያሉት የችግሩ መንስኤ “እኛው ኢህአዴጎች ነን (We in EPRDF are to blame)” ነው። ይኼን በመለስ ዜናዊ አገዛዝ የማይታሰብ መናገር ቀላል አይደለም። አሁንም በህወሓት ውስጥ የሚገኙ ግትሮች የችግሩን ጥልቀትና ስፋት የተረዱት አይመስልም። ጠቅላይ ሚንስትር ተሹሞ አገሪቱን ያለምንም ጫና ለመምራትና መፍትሄዎችን ለመፈለገ ካልቻለ “ጉልቻ” መሆኑ ነው፤ ሰው ጉልቻ አይደለም። ሌላው ቢቀር ለህሊናው ተገዢ መሆን ግዴታው ነው። እሳቸእ ስለተናገሩ የገዢው ፓርቲ የበላይ ህወሓት ይለወጣል ብሎ ማሰብ ራስን ማታለል ነው።
የማይካደው የፖለቲካ ክስተት አንድ ነው። ቀደም ሲል በጎንደር፤ በጋምቤላ፤ በኦጋዴን፤ ባለፉት አምስት ወራት በኦሮምያና በአዲስ አበባ የተካሄደውና የሚካሄደው የሕዝብ እምቢተኛነት መሰረታዊ የሆኑ የፖሊሲ፤ የመዋቅር፤ የአስተዳደርና የኪራይ ሰብሳቢነት ውጤቶች ናቸው። ሕዝብ እንዲሁ በራሱ ላይ ፈርዶ ልደብደብ፤ ልታሰር፤ ልሰወር፤ ልገደል፤ ልሰደድ ወዘተ አይልም። ሕዝብን ወደ እምቢተኛነት የሚወስዱት የሚከተሉት ናቸው፤
 •   የፍትህ መጓደል፤ የሰብአዊ መብቶች መታፈን፤ የነጻነት አለመኖር
 •   ጭፍን የሆነ ጎሳዊ አድልዎ፤ ጉቦ፤ ሙስናና ከሕግ ውጭ ከአገር የሚወጣ ግዙፍ ኃብት
 •   የኑሮ ውድነት፤ የአቅርቦት ጉድለት
 •   የሰብአዊ ክብር መውደም፤ ስደት፤ በወጣት ሴቶች መነገድ
 •   የመልካም አስተዳደር መጉደል
 •   ችግሮችን በግድያ፤ በአፈና፤ ዜጎችን በመሰወር፤ በመደብደብ ለመፍታት መሞከር
 •   የመሬት ነጠቃና የዜጎች ከቀያቸው በተከታታይ መባረር፤ መገለል፤ መኖሪያ ማጣት
  በአጠቃላይ ስመለከተው የኢትዮጵያና የኢትዮጵያ ሕዝብ መሰረታዊ ችግር ስርዓቱ ነው። በኢትዮጵያ ሕዝብ መካከል ያለውን ጥቃቅን የተለመደ የባህል፤ የልምድ፤ የቋንቋ ወዘተ ልዩነት ወደማይታረቅ ልዩነት እንዲሸጋገር የምንጎተጉተው የፖለቲካ ልሂቃንና ምሁራን ጭምር ነን። በአገዛዝና በአመራር ደረጃ ሲታይ፤ ተቃርኖው በአንድ በኩል ህወሓት በበላይነት በሚመራው ኢህአዴግ እና በሌላ በኩል በሕዝብ መካከል ነው። ችግሩ ሊፈታ የሚችለው ሕዝብ የስልጣኑ ባለቤት ሲሆን ነው።
  ጠቅላይ ሚንስትሩ እንዳሉት ኢህአዴግ የፈጠረውን ችግር በእልክ፤ በጭካኔ፤ በማስፈራራት፤ በማሰር፤ በማቁሰል፤ በመሰወር ሊፈታው አይችልም። ሰውን ለመሰወር ቢቻልም ችግሩን ለመሰወር አይቻልም። ሊፈታ የሚችለው በፍትህ፤ በሕግ የበላይነትና በእውነተኛ ዲሞክራሳዊ አማራጭ ብቻ ነው።
  በቅርቡ ክራይስስ ግሩፕ የተባለው ተቋም እንዲህ ብሎ ነበር፤
page4image25728 page4image25888

“ልክ እንደጎረቤት አገሮች፤ ኢትዮጵያን የገጠማት የፖሊሲ አማራጭ ጉዳይ ነው። የውስጥ ችግሮችን ለመፍታት ስርዓት ወለድ ጉዳዮች መፈታት አለባቸው”። ጠቅላይ ሚንስትሩ በቅንነትም ሆነ ሌላ ችግሩን “የፈጠርነው እኛው ነን” ካሉ የሚመሩት ፓርቲ ደፍሮ ለሕዝብ የፖለቲካ የበላይነት ማጎብደድና መገዛት አለበት።
Ethiopia, like its immediate neighbours, is faced with difficult policy choices
involved in guarding against internal radicalisation through systematic (constitutionally questionable) interventions...The government, and donors keen to support global efforts against violent extremism, should always consider first, the risk of such interventions to the state’s neutrality as mediator..Above all, those backing interventions should always seek better understanding of what faith (ለምሳሌ) means to multi-ethnic, religiously diverse societies like (but not limited to) Ethiopia, in which the distinction between group and individual identity is often not well defined, and rival local actors are apt to make use of religious disputes where social and governmental constraints inhibit open political competition.” See Ethiopia: Governing
the Faithful. Crisis Group Africa Briefing N°117. Nairobi/Brussels, 22 February 2016 

Finote Democracy Voice of Ethiopian Unity Satellite Radio News

Finote Democracy Voice of Ethiopian Unity Satellite Radio News
ፍካሬ ዜና መጋቢት 11 ቀን 2008 ዓም.(March 20, 2016 Weekly NEWS)
# አመጽ በተለያዩ የሀገሪቱ አካባቢዎች እየተፋፋመ ቀጥሏል
# የተዘጋጀ ዶሮ ከውጭ ወደ ሀገር ውስጥ መግባትን አስመልክቶ የዶሮ አምራቾች መቃወማቸው ታወቀ
# በተንቀሳቃሽ ስልክ ገንዘብ የሚያሰባስቡ ድርጅቶች ተስፋ እየቆረጡ መሆኑ እየተነገረ ነው
# የተሰረቁ የጋራ መኖሪያ ቤቶች መያዛቸው አስተዛዛቢ መሆኑ እያነጋገረ ነው
# ሳሊኒ ኮንስትራክሽን የጊቤ አራት የኃይል ማመንጫ ግድብ ግንባታን በይፋ ተረከበ
# የአልቃይዳንና የአልሸባብን ዓላማ በኢትዮጵያ ውስጥ ለማራመድ ተንቀሳቅሰዋል የተባሉ ተፈረደባቸው
# በአይቮሪ ኮስት የታጠቁ ሰዎች የሰነዘሩት ጥቃት ጉዳት አደረሰ
# ሞሮክ የባንኪ ሙኑን መግለጫ ተቃወመች፤ ከሰላም አስከባሪ ኃይል ውስጥም ወታደሮቿን አስወጣች
# እና ሌሎች
ለዝርዝር ዜናዎች > ከታች ይጫኑ (to listen detail news click below)
To READ:  http://www.finote.org/FikarezenaMarch20_2016.pdf
To Listen PART 1:  http://finote.org/March20EVE_Hr1.mp3
To Listen PART 2:  http://finote.org/March20EVE_Hr2.mp3

Sunday, March 20, 2016

Finote Democracy Voice of Ethiopian Unity Satellite Radio News

Finote Democracy Voice of Ethiopian Unity Satellite Radio News
መጋቢት 10 ቀን 2008 ዓ.ም.ዜና (March 19, 2016 NEWS)
# የወያኔ ባለስልጣኖች ነጋዴዎችን ቀረጥ አልከፈላችሁም በማለት ንብረታቸውን ለመውረስ እየተዘጋጁ ነው።
# ተሰርተዋል ተብለው የተመዘገቡ የኮንዶሚኒየም ቤቶች አለመሰራታቸው ታወቀ
# የማዕዱ ምክትል መሪ አቶ ዘመነ ምህረቱ ከእስር ተፈቱ፤ አቶ በቀለ ገርባ ግን
# ለምርመራ በእስር እንዲቆዩ ተደረገ
# የአለም ባንክ ለወያኔ ተጨማሪ ብድር ሰጠ
# በቱርክ ኢስታንቡል ውስጥ የፈነዳው ቦምብ አምስት ሰዎች ገደለ 37 አቆሰለ
# በፓሪሱ የሽብር ተግባር ላይ ተሳታፊ የነበረው ግለስብ ተያዘ
# በብሩንዲ ሰቆቃዊ ድርጊት እየተስፋፋ መምጣቱን ተመድ ገለጸ
# በደቡብ ሩሲያ ግዛት አንድ የመንገደኞች አውሮፕላን ወድቆ በውስጡ የነበሩ 62 ሰዎች ሞቱ
ለዝርዝር ዜናዎች > ከታች ይጫኑ (to /read/listen detail news click below)
To Read:  http://www.finote.org/news.html
To Listen PART 1:  http://www.finote.org/March19EVE_Hr1.mp3
To Listen PART 2:  http://www.finote.org/March19EVE_Hr2.mp3

የአገር ሽማግሌ ድምፅ ሆኖ እንዲታይልኝ/ቢታይልኝ እወዳለሁ። አስፋ ጫቦ ለጠ/ሚኒስትር ኃይለማርያም።ግልጽ ደብዳቤ ለጠ/ሚኒስትር ኃይለማርያም – አስፋ ጫቦ

ይህን ደብዳቤ እንድጽፍልዎ ያስገደደኝ፣ ዛሬ አገራችን የገባችበት ማጥ ነዉ። ከፖለቲካነትን ይልቅ የ“ኧረ ምን ይሻላል! ኧረ  ምን ይበጃል !” ደብዳቤ አድርገው ቢያዩልኝ ደስ ይለኛል። እንደ መፍትሔ አፈላላጊ የአገር ሽማግሌ ድምፅ ሆኖ እንዲታይልኝ/ቢታይልኝ እወዳለሁ። ነውም!! ”የጋራ ቤታችን” እንዲህ ማጥ ውስጥ ስትዘፈቅ የሚያይ አገር ወዳድ ሁሉ ድምጹን የመስማት ግዴታ ያለበት ወቅት ላይ ነን ብዬ አምናለሁ። ከፖለቲካ አመለካከት ልዩነት ይልቅ የአገራችን የኢትዮጵያ መሰንበት፤ ከዚያም “በነጻነትዋ ለዘላለም ትኑር!” ማለት ይቅደም እንደማለት ነው። በደርግ ቋንቋ “ኢትዮጵያ ትቅደም!” እንደማለት!

ታዋቂዉና ዝነኛዉ የጥንቱ የቻይና ሊቅ ሱን ዡ (Sun Tzu) በ “የጦርነት ጥበብ “ (The Art of War) መጽሐፉ ከጻፈው ጠቅሼ ብጀምር የሚሻል መስለኝ፡-
“..ጠላትህን (ይቃወመኛል የምትለውን) የምታውቅ ከሆነ ፤ደግሞም ራስክን የምታውቅ ከሆነ የግጥሚያ ወጤት ከቶም አያጠራጥርም:: ሆኖም፤ ራስክን ብቻ አውቀህ ጠላት ነው (ተቃዋሚ ነው) የምትለውን የማታውቅ ከሆነ  አሸነፍኩ ባልክ ቁጥር ሽንፈት ያጋጥመሀል። ከዚህ ውጭ ግን ራስክንም ጠላቴ (ተቃዋሚዬ የምትለውን) የማታዉቃቸው ከሆነ በገጠምክ ቁጥር ሽንፈት እጣህ ይሆናል” ይላል፡፡
ከነጉዳንጉዱ የኢትዮጵያና የኢትዮጵያዊያን መንግስት ለማድረግ ሙከራ ያደረገ መንግስት ቢኖር ደርግ ብቻ ነበር  ለማለት የምንችል ይመስለለኛል። የስልጣን መሠረቱ ብሔረሰብ አልነበረም። ያም ሆኖ የብሔረሰብ ጭቆና መኖሩን ተቀብሏል። ተቀብሎም  በመላ- ምት ሳይሆን ጥናት ላይ በተመሠረት መፍትሔ ለመሻት ተንቀሳቅሷል። “የብሔረሰብ ጥናት ተቋም” (Institute)፤ በምርጥ የኢዮጵያ ምሁራን የሚመራ፣ አቋቁሟል። የዚያ ጥናት ውጤት ሰባት የመፍትሔ አማራጮች ያቀፈ ነበር። በጊዜያዊነትም ቢሆን ከነዚህ አማራጮች አንዱን  “የራስ ገዝ”  የሚለውን በስራ አውሎ ኢትዮጵያን በዚያ ለማስተዳደር ሞክሯል።
ኢሕአዴግ ከዚህ የደርግ ጥናት ውስጥ ሰባተኛ የነበረውን አማራጭ ወስዶ አገሪቱን “ክልል” በሚል  መጠሪያ ክልል አዋቀረ። ክልል ማለት በዚህኛው አገባቡ፣ለኔ፣ “አጥር ታጠረ!” እንደማለት ነው” “ድርሽ ትልና!  ድርሽ ትይና!” እንደማለት። ደርግ ለኃይለሥላሴ  ሲል እንደነበረው፤ “ውስጥ ውስጡን ሲብላላ የነበረው” ይኸዉ ላለፉት አራት ወራት ቁርጡ ለይቶለት መፈረካከስ ጀመረ። መንግስትዎን ይህ ነገር “ወትሮ ነበር እንጅ መጥኖ መደቆስ፤ አሁን ምን ይባላል ድስትን ጥዶ ማልቀሰ!”ን አስታወሰኝ። በዚህ ላይ መንግስትዎ አሁንም ሐሳብ- ወለድ ጠላቶች ላይ ጣቱን መጠንቆሉን ቀጠለ። ያ የተለምደ ስለሆነ አይገርመኝም። ሆኖም አዲስ ኪዳን ውስጥ ያለ አንድ ነገር ያስታውስኛል።” ሌላው አይን ውስጥ ያለ ትቢያ ከመጠቆምህ በፊት አንተ አይን ውስጥ የተጋረጠውን ግንድ መጀመሪያ አስውግድ!” የሚለው ነው።
በምሳሌ ለማስረዳት ልሞክር- “ተከለለ” ማለት “ታጠረ” ማለት ነው። ጋሞ “ካሎ” ይለዋል። ማስቃላ ከመድረሱ ወራት በፊት የከብቶች ማስማሪያ  መሐሉ ላይ አንድ እንጨት ይተከላል። ያንን በምሳሌ ለማስረዳት ልሞክር። ያ ቦታ/መስክ “ካሎ” ሆነ ማለት ነው። ያንን እንጨት መጀመሪያ የተከለው ባለስልጣን  እስኪነቅለው ከብት ድርሽ አይልበትም። ጎሜ/ ኃጢአት ነው የሚሆነው። ወንጀል/ሽብርተኝነት እንድምትሉት! ጋሞ ውስጥ ካሎ አይጣስም። ምክንያቱም ቀላል ነው። ሕዝቡ  የተቀበለው፣ ለዘመናትም ተቀብሎት የኖረው፤ እምነቱ ፤ንብረቱ ስለሆነ ነው።
ዛሬ በአገሬ፤ በኢትዮጵያ፣ ያለው በግሪክ ተረታ-ተረት (Mythology) ያለውን የፓንዶራን ሙዳይ (Pandora Box) ያስታውሰኛል። አማልክት እንደ ምርቃት/ እርግማን ሙዳይዋን በአለም ላይ በሚገኙ ክፋቶችና ተስፋ ሞልቶ ይሀጣታል። ፓንዶራ ቸኩላ ስከፍተው ክፋቶቹ ሁሉ በረው ወጡና እቡይ ስራቸውን ተያያዙት። ወያኔ በዚህ አዲስ የመንግስት አዋቃቀሩንና ሕግ መንግስቱ ያደረገው የፓንዶርን ሙዳይ እንደመክፈት መስሎ ይታየኛል። አንድ የሚያጽናናኝ ነጥብ ቢኖር ሙዳዩ ውስጥ አሁንም ተስፋ አለ። ኢሕአዴግ ብርታትን፣ ቅንነትን፤ “ለጋራ ቤታችን” ዘላቂነትን የሚፈልግ ቢሆን፤ይህችን ሙዳይዋ ውስጥ የተረፈቸውን ተስፋ አውጥቶ ተግባር ላይ ማዋል ብቻ ነው። የዚያን እለት፤ በዚያ ወቅት ፤የኢትዮጵያ ሕዝብ በተቃውሞ ሳይሆን በድጋፍ ከአጽናፍ እስከ አጽናፍ ይውጣል ብዬ አምናለሁ።  እኔ  ደግሞ በመሠረቱ ተስፋ መቁረጥ አላውቅበትም። ተስፋ የምቆርጥ ብሆን ይህንን ደብዳቤ ባልጻፍኩም!!
ጠቅላይ ሚኒስቴር ለነበሩት ለአቶ መለስ ዜናዊ፤የዛሬ ስንትና ስንት አመት በጻፍኩት ግልጽ ደብዳቤ አገሪቱን “አያድሩበት ቤት አያመሻሹበት አያፈርጉት!” ብዬ ነበር። እርስዎን ደግሞ “ላለፈ ክረምት ቤት አይሰራም!” ለማለት እፈልጋለሁ። ያለፈው ክረምት ቤቱን ነካካው እንጅ አላፈራረሰውም፤ ወይም ወደማፈራረስ አላቃረበውም ብዬ አምኜ ነው ይህንን ተረት የጠቀስኩት። እዚህ ተረት ውስጥ በውስጠ ታዋቂነት ያለው፤ ወይም አንድምታው “ያለፈው ክረምት ያናጋውን አይነት ቤት ደግመህ አትስራ!” የሚል ይመስለኛል። ማለትም እዚያ፤ ያለፈው ክረምት ቤት አወቃቀር ላይ/ውስጥ የነበረውን ደካማ ጎን አትድግመው ነው። ማለትም  “ካለፈው የግንባታ ስህተት ተማር!” ነው።
ከሆነ ደግሞ የግንባታው ስህተት ምን ነበር? ዙሪያውን ላለመዞር ስህተቱ ሕገ መንግስቱ ነው ! ስህተቱ ኢትዮጵያን በክልል ማዋቀሩ፤በብሔረሰብ ማካለሉ ነው!!
ኢትዮጵያን በብሔረሰብ ሲዋቅር ወያኔ የመጀመሪያ አልነበረም። በ1928 ኢትዮጵያን የወረረው የጣሊያን፤ የሙሶሉኒ አወቃቀር በብሔረሰብ ላይ የተመሠረተ ነበር። “የጣልያን የምስራቅ አፍሪካ ግዛት! (Africa Orientale Italiana” ይለዋል። ከ19ኛው ምእተ አመት ጀምሮ ብዙ የጣሊያን “ሊቃውንት” ያጠኑት ጥናት ውጤት መሆኑ ነበር። የጥናታቸው ውጤት ኢትዮጵያን በጎሳ በመከፋፈል እርስ በርሳቸው ማናቆርና እነሱ ሲባሉ እኛ አርፈን መግዛት ነው የሚል ነበር። ታሪክ እንደሚነግረን፤ የኢትዮጵያ ሕዝብ አብዛኛው ተባብሮ፤ ዱር-ገደል ገብቶ  ጣሊያንን አዋርዶ አባረረው። እንግሊዝም  በሰሜን በኩል የትግራይ- ትግሪኝን፣ በምስራቅ በኩል የታላቂትዋን ሶማሌ መርዝ ቀበረች/ረጨች። ባጭሩ ይህ በብሔረሰብ  መከፋፋል ከጠላቶቻችን የመጣ በመሆኑ ሞዴል አድርገን ልንቀበለው ከቶም አይገባም ለማለት ነው። ይህም ማለት   ለአዲሱ፤ መጭው ክርምት፣ የሚሰራው ቤት በጠላቶቻችን ንድፍ ላይ የተመሠረት ሳይሆን በኢትዮጵያ እሴት፤ በኢትዮጵያ እውነት ላይ መሆን አለበት ለማለት ነው። መሠረቱ፤ ጣሪያ፤ ግርግዳው፤ ታዛው የኛው ይሁን ነው። ዞር-ዞር ብሎ የማየት እንጅ ታሪካዊ እሴት ሞልቶ የተረፈን አገር ነን። ከልቤ ነው የምልዎት!!
ደርግን “ከነጉዳንጉዱ”ብዬ ነበር የገለጽኩት። ለጊዜው ለተነሳሁበት ጉዳይ ሲባል ጉዳንጉዱን ልተወውና በጎ ጎኖቹ ሊባሉ ከሚችሉት ጥቂቱን ልጥቀስ። ከሁሉ ሁሌ  ቁልጭ ብለው ከሚታዩኝ ውስጥ አብዮት አደባባይ ሰልፍ በተደረገ ቁጥር ከደርግ ሊቃናተ መንበሮች በስተቀኝ ፓትሪያርኩ አቡነ ተክለሐይማኖት፤ ከግራ ሐጂ ያሲን የክብር ቦታ ይዘው ተቀመጠው የማየው ነበር። በኢትዮጵያ ምድር የእምነት እኩልነት ለማየት ሲያልም ለነበረ እስልምና እንዲህ የክብር ቦታ አግኝቶ በአደባባይ ከማየት የተሻለ የሚያረካ ወቅት ይኖራል ብዬ አልገምትም። ከዚያም መስከርም 12ትን አረፋ፤ ታህሳስ 13ትን መውሊድ፣ ሰኔ 29ን ረመዳን ብሔራዊ በአል አድርጎ የደነገገዉ ደርግ ነበር።
የካቲቲ 25 ቀን 1967 የገጠር መሬት አዋጅና የትርፍ ቤቶችና የከተማ ቦታ አዋጅ ሌላው የሚጠቀስ ነበር። የነዚህ አዋጆች ትርጉም “መሬት ለአራሽ/ለባለቤቱ፣ የከተማ መኖሪያ ቤትን አናሳ ገቢ ያላቸው ጭምር ተከራይተው እንዲኖሩ ማድረግ ነበር።  ደርግ ወያኔን ጉድፉን አጥርቶ፤መንገዱን ጠራርጎና ዘርግቶ ጠበቀው ልንል የምንችል ይመስለኛል። ወያኔን ከጥቂት ማሻሻል/በስተቀር “ግፋ በለው!” ብቻ ነበር የሚጠበቀው። ታዲያ ምን ሆነ?
ከዚያ የሆነውን እርስዎ ደጋግመው ከተናገሩት አንዱን ብቻ ወስጄ ለመግለጽ እንድሞክር ይፈቀድልኝል። ቃል-በቃል ባልጠቅስዎትም “መንግስታችን የኪራይ ሰብሳቢ መንግስት ሆነ!” አሉ። እኔም ልሁን ማንኛውም ተቃዋሚ ወይም መንግስትዎ አሸባሪ የሚላቸዉም ቢሆኑ ይህንን መንግስት ከዚህ፣ እርስዎ ከገለጹት በተሻለ ሊገልጡት የሚቻላቸው አይመስለኝም።
ለመሆኑ እኒህ ኪራይ ሰብሳቢዎቹ እነማን ናቸዉ? የሚያከራዩት ምንን/ማንን ነው? ብሎ መጠየቅ ተገቢ ይመስለኛል። ብቻ የሚያከራዩት ቢኖር ነው አከራይተው ኪራይ የሚሰበስቡት። ይህ ደግሞ ራሱን በራሱ ገላጭ እውነት ነው። ከሆነ ደግሞ የሚያከራዩት ኢትዮጵያን ወይም የኢትዮጵያን መሬትና ቤት መሆኑ ነው። ተሳስቼም ከሆነ ልታረም ፈቃደኛ ነኝ። ልማት በሚባል ታላቅ አሳሳች ቃል ስር ዛሬ ብር ወይም ጉልበት ያለው የፈለገውን ያክል የገጠር መሬትና ቦታ ማግኘት እንደሚችል መንግስትዎ በአደባባይ የሚናገረውና አስፈጻሚ አዋጅም ያወጣለት ነው። በቅርቡ ያነበብኩት አንድ የአፍሪቃ የባለሚሊዮን ዶላር ሀብታሞች ዝርዝር ገርሞኝ ነበር። ባለሚሊዮን ዶላር ሀብታሞች ዝርዝር ውስጥ ኢትዮጵያዊያን የአንደኝነት  ስፍራ ይዘዋል። አሁን አንደኝነታችን በረዥም ሩጫ ብቻ ሳይሆን በዶላር ጭምር መሆኑ ነዉ/ሆነ።  እንደ ኢትዮጵያዊነቴ በዚህ ልኩራበት ወይስ ልፈርበት? ይህ ሁሉ የተቻለውን ‘በሕጉ’ መሠረት ባለመሬቶቹ ከመሬትና ቤት ንብረታቸው ተነቅለው ተጥለው ነው።  የመሬት ላራሹ አዋጅ፣ መሬት ለኪራይ ሰብሳቢ በሚል አዋጅ የተተካ አይመስልዎትም? የእስልምና ተከታዮችም  ከብዛታቸው የተነሳ ስማቸውን ልጠራ የማልችለውን ወህኒ ቤት ሞልተውታል።
በኢትዮጵያ ታሪክ ውስጥ ዘመነ መሳፍንት ተብሎ የተሰየመ አነሰም በዛ የመቶ አመት ታሪክ አለ። ይህም ማእከላዊ መንግስት የላላበት፤ የአካባቢ መሳፍንት የነገሱበት ዘመን ማለት ነው። ግዛቱን ለማስፋት፤ ወይም ጉልብቱን ለማሳየት፤ ወይም እኔ ካንተ በናቴም ባባቴም እበልጣለሁ በሚል ሰበብ አስባብ ጦርነት የሚከፋፈቱበት፤ ሚስኪኑ ኢትዮጵያዊ የሚያልቅበት ዘመን ነበር። ያንን ዘመን በር-ቀዳጅ የአድዋው ስሑል ሚካኤል ነበሩ።
ከዚያ ያለው እንደገና የማእከላዊ መንግስት መመስረት፤ ወይም ግዛት ማስፋት ዘመን ነበር። የዚህ አይነት ብሔራዊ መንግስት የመመስረት ሂደት (The Formation of National State) የሰው ልጅ ታሪክ ወጥ አካል ነዉ። ከነክፋቱ!! የአሁንዋ/የዛሬይቱ ኢትዮጵያም የዚያ ወጤት ነች። አሁን ከ120 አመት በላይ ሆኖታል። በዚህም የተነሳ ዛሬ ኢትዮጵያ በሚባለው አገር  ታይቶ ተስምቶ የማይታውቅ የብሔረሰብ አነባበሮ ተፈጥሯል። በዚህም 120 አመታት ውስጥ መጋባት፤ መገባባት፣ መግባባትና መዋለድ ብቻ ሳይሆን  አብሮ የመኖርና የመቻቻል  ስነ ልቦና (Psychological make up) ተፈጥሯል።
ይህንን የኢህአዴግ የክልል መንግስት፣ የታሪክና የማህበራዊ ሳይንስ ሊቃውንት ነገ ሲተነትኑት፤ ዘመን መሳፍንት ዳግማዊ የሚሉት ይመስለኛል። በአገር ደረጃ ወደፊት መራመድ ራሱ ከባድ መሆኑን ይሔው የምታዩት ነው። 200 አመት ወደ ኋላ ለመውሰድ መሞከር ግን የጤና አይመስለኝም። ኢትዮጵያና የኢትዮጵያ ህዝብ ዩጎዝላቪያ ይባል የነበረው አገር ህዝብ አይነት አይደለም። ያ ሕዝብና  መንግስት እንደዚያ የተፈረካከሰው የዛሬ 500 አመት በፊት የሆነ  የታሪክ በደል በማንዠጉና አላምጦ ባለመዋጡ ነበር። ቱርክም፤ ሊባኖስም፤ ሶሪያም፤ ኢራቅም አይደለም:: የኢትዮጵያ ሕዝብ ቂም በቀል ፤የነበረ ያልነበረ የሚያመንዥግ ህዝብ  አይደለም። አላምጦ ውጦ የታሪኩ አካል አድርጎ ወደፊት የሚራመድ ታላቅ “ይቅር ለግዜር!!” ተባባይ ህዝብ ነው።  የታላላቅ እምነቶቹም ሆነ የባሕላዊ እምነቶቹ መሠረቱ ይሔው ነው።
የእስልምና እምነት በአላት በደርግ ዘመን ወደ ብሔራዊው በአልነት መሸጋገራቸውን አንስቼ ነበር። አሁን በኢሕአዴግ ዘመን ደግሞ ምን እንደደረሰባቸውና በመድረስ ላይ እንዳሉ የሚያዉቁትና መላው አለምም የሚያዉቀው ስለሆነ ዝርዘሩ ውስጥ አለገባም። አንድ ነገር ብቻ ላስታውስዎት እወዳለሁ። ጠቅላይ ሚኒስቴር የነበሩት የመለስ ዜናውን “የመጨረሻ ኑዛዜ” ያንብቡ። ኑዛዜ ያልኩት ከማረፋቸው አንድ ይሁን ሁለት ወር በፊት ያደርጉት የሚኒስቴሮች ምክር ቤት ስብሰባ ቃለ ጉባዔ ነው። ይህንን ሚስጥራዊ ቃለ ጉባዔ ያነበብኩት ድሕረ ገጾች ላይ ተለጥፎ ነበር። ማመን ነበር ያቃተኝ!! ወይም አንድ ሰው “የመጨረሻው ደውል” እንደተደወለለት ሲያውቅ፤ “እውነቱን ተናግሬ ልሙት!” ያሰኘዋል ይሉናል። በዚያ ስበስባ ላይ የአቶ መለስ አስተያየት ከማውቃቸውና ከሚታውቁበት መለስ ለየት ያሉ ነበር። እውነት ብቻ ሳይሆን የሚስጥር እውነት ነበር። ይህ እውነት የመጀመሪያቸውም የመጨረሻቸውም ነበር ብዬ እገምታለሁ።
አቶ መለስ ያሉት ቢጨመቅ “ይህንን የእስልምና እምነት ችግር የቀየስነውና የፈጠርነው እኛው (መንግስት) ስለሆንን ከዚህ በኋላ ይወገድ!” የሚል ይሆናል። የተቃወመ ሰው ቢኖር አንድ ዶክተር ሽፈራው ተክለ ማርያም  የሚባሉ ነበሩ። የመከላከያ ሚኒስትሩ አቶ ሲራጅ ፈርጌሳ  መደገፍ ብቻ ሳይሆን ድርጊቱን አውግዘውና ይህንን ወሳኔ አድምቀው፤ አክርረው ደግፈዋል። ያም ሆኖ የእስልምና እምነት ተከታዮች ዛሬም አክራሪ ይሁን አሸባሪ (ልዩነት አልገባኝም፤ የገባውም ሰውም አላገኘሁም) በሚል እንደታጎሩ፤ያልታጎሩትም “ማነህ ባለ ሳምንት!”ን በመጠባበቅ እንደተሳቀቁ ናቸውና እባክዎን የአቶ መለሰን ኑዛዜ ስራ ላይ ያዉሉት። ከዚያ የተሻለ መፍትሔ የለምም!!
ይህንን ደብዳቤ  ጠቅላይ ሚኒስትር የነበሩት አቶ መለሰ ዜናዊ አንዴ ከተናገሩት ጠቅሼ ማጠቃለል ፈለግሁ። መለስ፤ በሆነ አጋጣሚ (ረስቸዋለሁ) “በሩም መስኮቱም ከተዘጋ ህዝቡ ግድግዳውን ሰብሮም ቢሆን ይወጣል” ነበር ያሉት። ቃለ በቃል መጥቀሴ ሳይሆን መንፈሱ ይሔው ነበር። ዛሬ በመላው ኢትዮጵያ የሚታየው ቃል በቃል ይሔው መሆኑ የሚያከራክር አይመስለኝም። በምድር ላይ የሚታየው ማስረጃ ይሔው ነው። በሰነዶች ላይ የሚታየው ይሔው ነው። ተቃዋሚዎች፣ መንግስት ግን አክራሪ ወይም አሸባሪ የሚላቸውም፣ የሚናገሩት ይህንኑ ነው። አገርና አለም አቀፍ የሰብአዊ መብት ተሟጋች አካላትም የሚሉት ይህንኑ ነው። እርስዎም በተደጋጋሚ በሚያደርጉት ንግግር የሚሉት መንፈሱ ሲነጠር ይሕንኑ ይመስላል።
ይህ ሁሉ ሲሰባሰብ አንድ እውነት የሚያሳይ ይመስለኛል። ይህንን ኢሕአፈግ “ልማት፣ እድገት” ያለውን ሕዝቡ አልተቀበለውም። ይህንን ኢሕአዴግ መቶ-ከመቶ(100%) ድምጽ አግኝቼ ምርጫ አሸንፌያለሁ ያለው ውሸት መሆኑ ነው። ውሸትም ባይሆን ትላንት መቶ-ከመቶ (100%) የደገፈ በማግስቱ መቶ-ለመቶ ፈንቅሎ አይነሳበትም ነበራ! ወደ ህዝቡ መግቢያ ሽፋን እንዲሆኑ የተፈጠሩት ለምሳሌም እንደ ኦሮሞ  ሕዝብ ዲሞክራሲያዊ ድርጅት  የተባለውን ሽፋን መስጠት ቀርቶ ራሳቸው የሚሸፈኑበት ያጡ መሆናቸውም እውነት ነው። “አባይ ማደሪያ የለው ግንድ ያገላብጣል”ን አስታወሰኝ። እዚህ ያላነሳሁትን ሌሎች ማስረጃዎች ሰብሰብ አድርገን ብናበራያቸው ይህ ኢሕአዴግ ያመጣው ስርአት አልሰራም ማለት ነው። “ለማንም አልበጀ!” ሆኗል እንደማለት ነው። አድሮ ከዋለ ደግሞ ካደረሰው በላይ ዘላቂና ጠላቂ ጉዳት ያመጣል የሚል ብርቱ ፍርሐት አለኝ።
እንደኔ እንደኔ መፍትሔው፤ መውጫው ችግሩን በድፍረት ፊት ለፊት መጋፈጥ ነው። አውቃለሁ! መጋፈጡ እንዲህ ቀላል አይመስለኝም! ድፍረቱም ብልሐቱም ላይኖር ይችላል። ያም ሆኖ ግን አማራጩ፤ ማለትም አድሮ ውሎ ጊዜ ይፈተዋል   በሚል የሚሰጥ የመተንፈሻ ጊዜ መግዣ ምክንያት መደርደር  የሚጸጽት አማራጭ ይፈጥራል።
ትላንትና ያደመጥኩትን አንድ ነገር ልጨምር ፈለግሁ:- ከሶቪየት ህብረት ዘመን ጀምሮ ሩሲያን የሚያውቁ፤ አሁን ጡረታ ላይ የሚገኙ ጋዜጠኛ አን ጋረለስ (Anne Garreles) ሰሞኑን Public Broadcasting System (PBS)  በተባለ ራዲዮ ጣቢያ  Fresh Air በሚባል ፕሮግራም ላይ ረዘም ያለ ቃለ መጠይቅ አድርገው ነበር። ለቃለ መጠይቁ ዋንኛ ምክንያት የፑቲን አገር “Putin Country” የሚል መጽሐፍ ደርሰው ስለነበር ነው።
ቭላድሚር ፑቲን የሩሲያ የአሁኑ ፕሬዚዳንት ናቸው። ጋረልስ በዚህ ምልልስ በዚያ አገር፣ በሩሲያ፣ ውስጥ የሚታየውን የፖለቲካና ሁሉ ዘርፍ አቀፍ ንቅዘት ይዘርዝራሉ። የፑቲንን ጨምሮ!   “ይህ ሁሉ ጉድ እያለ ሕዝቡ ፑቲንን እንዴት ያያል?” ለሚለው በሰጡት መልስ “ዛሬ በአለም ላይ ከሚገኙት መሪዎች ሁሉ በመላው የሀገሪቱ ህዝብ በጣም ተወዳጅነት ያለው መሪ ቢኖር ፑቲን ናቸዉ”አሉ። ምክንያቱን ሲጠይቁ “ከሳቸው በፊት የነበረው ፕሬዝዳንት፣ ቦሪስ የልሲን፣ ሰካራም ከመሆኑም ሌላዘራፊም ነበር። ዝርፊያው እንደቀጠለ ሆኑ ፑቲን በአገራችን፤ በሩሲያዊነታችን እንድንኮራ፣ እንድንኩራራ፣ አፋችንን ሞልተን ሩሲውያን ነን ለመለት አበቃን!” የሚል መልስ ሰጡ። ቃለ ምልልሱን ከጠቀስኩት ጣቢያ ማድመጥ የሚችሉ ይመስለኛል።
ለኛም የምንኮራባት፤ በጠፍ ጨረቃ ጥለን የማንፈጥጥባት፤ እንደወጣን የማምንቀረርባት፤ ለመመለስ የምንናፍቃት ኢትዮጵያን እንዲያስቡ፤ እንዲያልሙ፣ ወደዚያ የሚወስደውን መንገድ በሙሉ መስራት ባይችሉ እንኳን ጠረግ ጠረግ እንዲያደርጉ ከልብ እመኛለሁ። እመኝሎታለሁም!
ብርታት፤ ብልሐት እመኝላችኋለሁ! ለአገሬም የተሻለውን፤ የሚበጀውን፤ የሚያምረውን፣ የሚዘልቀውን የሚያዘልቀንን እመኝላታለሁ!
ኢትዮጵያ በሕዝቦችዋ ትብብር በነጻነትዋ ለዘለዓለም ትኑር!
ከአክብሮት ጋር

Thursday, March 17, 2016

ኢትዮጵያ ውስጥ የተፋፋመው ሕዝባዊ እምቢተኝነት ግቡን እንዲመታ! ( የፍኖተ ራዲዮ ሀተታ )

ኢትዮጵያ ዉስጥ የተቀጣጠለ ያለው ሕዝባዊ እምቢተኝነት የድርጅት፣ የአንድነትና የአመራር ያለህ ይላል።
ለትዉስታ ያህል 1997 . የነበረውን ክስተት ማስታወስ አሁን ላለንበት ታሪካዊ ዕራፍ ይጠቅማል።  በ1997 ዓም የኢትዮጵያ ሕዝብ በተለይም የአዲስ አባባ ሕዝብ በነቂስ ወጥቶ ቅንትንና ህብረትን ሲመርጥና ወያኔን አሥር ለባዶ ዘርሮ ሲያልፍ  በሁኔታው ያልተደሰተው በጠራራ ፀሓይ ቆፈን ይዞት የተንቀጠቀጠው ወያኔ ብቻ መሆኑን ናስታውሳለን። ቀጥሎም ድምጻችን አትሰርቁም በማለት ከወያኔ አጋዚ ጦር ጋር ግብግብ ሲገጥምና የሚቆጠር ዜጋ ሲታሰርና ወደ ሁለት መቶ የሚሆኑ ወጣቶች ሲገደሉ ከደሙ ንጹህ ነኝ  ያሉ ክፍሎች በርካታ ነበሩ። እየጋመ የመጣው እንቅስቃሴም የወያኔን የጎሳ ካርድ አቃጥሎ በምትኩ ኢትዮጵያንና ኢትዮጵያዊነ ከፍ ከፍ በማድረጉ ወያኔ ቅስሙ ተሰበረ ባዕዳን ደነገጡ የወያኔ ድጋፊም ብርክ ያዘው ሻቢያና ኦነጎች ከሩቅ አረገዱ።  አንጻሩም የተፋፋመዉን የትግል ስሜት ተጠቅሞ ወያኔን ለማስወገድ ይችል ዘንድ የተጠናከረ ባዊ ኅይል ባለመኖሩ ለአጋዚው ጦር ባለቤት ለሆነው ወያኔ ሲሳይ ሁኖ ቀረ።  በመሆኑም ከተማይቱ ጭር አለች። ወገን አንገቱን ደፋ። ይህ ነበር ሃቁ።  የተቃዋሚ መሪዎች የተባሉት ደግሞ ከፊሎቹ የወያኔ የውስጥ አርበኛ ሆነው ሲያገለግሉ፤ ከፊሎቹ ከሕዝብ ጀርባ ከባዕዳን ጋር ሲያሴሩ ግማሾቹ ተስፋ ቆርጠው ለወያኔ ዕጃቸውን ሲሰጡ የተወሰኑት ደግሞ 5ቱን ቀን የሙት ከተማ ተቃዉሞ በማክሸፍ ለሟቹ ስና በረከት ስምኦን የእጂ መንሻ ረጉት።  ዛሬም ቢሆን የተቃዋሚው ክፍል ካለፈው ስህተት ተምሮ ዕነኚህ  ሕዝብን በማንቃትና በማደራጀት ለወሳኙ ክፍል ሲያዘጋጀው እያየን አይደለንም  ዕዉነቱ ይነገር ከተባለ ደግሞ ወያኔ ሆዳሞችን ሁሉ በዘር ፖለቲካ እየቃኘ ወደ ድርጅቶች አሰርጎ በማስገባት እያንዳንዱን ድርጅት አቅመቢስ ሽባ እንዳደረገው ግጥም አድርገን እናዉቃለን። 
በሰላም መታገል፤ በወያኔ ሕግና ደንብ መሰረት ኮሽታ ሳያሰሙ፣ ጸጥና ለ ብሎ መገዛት እንደ ትግል ዘዴ መወሰዱም ይታያል  በአገር ክህደት ወንጀል ፍርድ-ቤት መቆምና መቀጣት ያልበትን ወያኔ የኢትዮጲያ መንግስት ነው ብሎ ሕጋዊ ሽፋን መስጠቱ  በአገርም በሕዝብም ያስጠይቃል እንላለን 
አገሬ ኢትዮጵያ ሞኝ   ተላላ 
የሞተልሽ ቀርቶ የገደለሽ በላ  እንዲሉ ኢሕአፓም በተወለደባት ብቻ ሳይሆን በሞተላት እናት አገሩ በነጻ እንዳይንቀሳቀስ በወያኔ ቀጭን ተእዛዝ ተከልክሎ ትግሉን በህቡዕ ለማጠናከር የሚችለውን እያደረገ ነው። ወያኔ ኢሕአፓ በአገሩ ላይ በይፋ እንዳይንቀሳቀሰ ያገደው  በእናት አገሩ አንድነት፣ ብሔራው ጥቅምና ዳርድንበሯ ላይ የማይደራደር መሆኑን በማወቁ ነው ዛሬስ ከ11 አመት በኋላ ምን ዕያየን ነው?
ዛሬም ዕንደትናንቱ፤ ዕንደ 1997ቱና ዕንደ 1966ቱ፤ በተመሳሳይ ያዉም በበለጠ በአገራችን ኢትዮጵያ ዉስጥ ከባድ የሆነ የለዉጥ ነጎድጓድ ዕየተሰማ ነው። የለውጡ ጠረን አገሪቱን አዉዷል! ዜጎች በየአሉበት አጭር የወያኔን የኅይወት ታሪክ ለመጬረስ ዕየተጠራሩና ዕየተናበቡ ትግላቼውን ቀጥለዋል። ስራዓቱም በዉስጥና በዉጭ ቅራኔዎች ተወጥሮ ሊፈነዳ ቀኑን ዕየቆጠረ መሆኑም ኃቅ ነው። ወያኔም በፍርሃት ሲናጥ፣ ሲንቀጠቀጥና ብርክ ይዞት ዕያየነው ወደታች ሲወርድና ሲሰጥም ዕየታዘብን ነው። በአንጻሩ ደግሞ  ወጣት ወንዱ ፣ ሴቱ   አዛዉንቱና ጎልማሣው ሁሉም በመነሳት በወያኔ ላይ አሻፈረኝ ማለቱና የፍርሃት ድባቡን  ሰብሮ ይቻላል ማለቱን ስናይ ልባችን በሃሴት ይሞላል! ኅሊናችን ይታደሳል! ተስፋችንንም ሰንቀን ለማይቀረው ፊልሚያ በወኔና በጋለ የትግል መንፈስ ዓለና ዕንላለን!! 
 በርግጥም ለሁሉም ጊዜ አለው፤ ልቡ ያበጠው ወያኔ በፍርሃት ሲርድ፣ በፍርሃት ይታማ የነበረው ሕዝብ ደግሞ ዕምኝ፣ አሻፈረኝ በማለት በወያኔ ላይ ሲያምፅና ሳንጃ ሲሰነዝር፤ ለማየት በቅተናል።  በየአድባባዩ ዕየወጣ መንገድና በሮችን ዕየዘጋ ወያኔና ግብረአበሮቹን መዉጫ መግቢያ ሲያሳጣቼውና ሲያርበደብዳቸው ከማየት የበለጠ ደስታ ካለ በይደር የምናየው ይሆናል ማለት ነው።          
በአጭሩ ወያኔ ስካሁን ድረሥ ይገዛ በነበረው መንገድ መቀጠል ከማይችልበት ደረጃ መድረሱና ሕዝቡም በስራዓቱ ላይ መነሳሳቱ ሥር-ነቀል የስራዓት ለውጥ ለመገላገል ኢትዮጵያ ምጥ ላይ መሆኗን ነው የሚያሳየው ማለት ነው። ይባስ ብሎም፣ ከእንቅርት ላይ ጄሮ ደግፍ ዕንዲሉ፣ በራሱ በወያኔና በተለጣፊ ድርጅቶች መካከል የጦዘው ሽኩቻ፤ ውጥረትና ትርምስ.፤ በራሱ በወያኔ ዉስጥ ያለው መረን የለቀቀው ቀውስ ጣራ መንካቱንም ጨምሮ  በሃገሪቱ ዉስጥ ያለጥርጥር የስርነቀል ለዉጥ መፈንዳቱ አይቀሬ መሆኑ ሃቅ ነው
ምንም ተባለ ምን፣ ዛሬ በአገራችን ኢትዮጵያ ዉስጥ እንደ ቋያ ዕሳት ዕየተቀጣጠለ ያለው ሕዝባዊ መነሳሳት በወያኔና ስራዓቱ ላይ ያነጣጠረ ለመሆኑም ክርክር አያሻዉም፣ ጥያቄ ዉስጥ መግባትም የለበትም።  ከታች ከቀበሌ ጀምሮ  እስከማዕከሉ ድረሥ በተዋቀረው ስርዓትና ሥርዓቱንም በሚያስኬዱ የቀበሌ ሹሞች፣  ካድሬዎች፣ ፖሊሶች፣ አጋዚ ጦር፤ ሰላዮችና ሃብት ነብረታቸው ላይ በቀጣይነት እየተወሰደ ያለው ርምጃ የሚያመላክተው ሌላ ሳይሆን ጸረ-ወያኔነትና ጸረ ስራዓቱ መሆኑን ብቻ ነው። በመሆኑም ይህ የተጄመረው ሕዝባዊ መነሳሳት ዓላማውን እንዳይስት፣ ማለትም የታለመለትን ግ ዕንዲመታ ከተፈለገ ደግሞ ሦስት አብይ ጉዳዮችን ግንዛቤ ዉስጥ ያስገባ፤ በአይነቱ፣ በስፋትና በጥልቀቱ ሁለገብና ኢዮጵያዊ የሆነ ብሄራዊ ስምምነት የግድ ይላል።  ዕነርሱም ሕዝዊ አንድነትን ማረጋገጥ፣ የፖለቲካ ድርጅቶች ሕብረትን መፍጠርና በቡድንም ሆነ በተናጠል ዕየተንቀሳቀሱ የሚገኙ ዜጎችን ሁሉ ያካተተ አንድ ሰፊ የትግል ማዕከል መፍጠር ናቼው። ይህ ብሄርዊ ስምምነት፣ በተሰጣጠረ መልክ ዕየተካሄደ ያለውን ሕዝባዊ ዕንቅስቃሴ መልክ አሲዞ፣ አቅጣጫ ሰጥቶ፣ ወያኔን ድቫቅ የመምታትና በስራተ ቀብሩ ላይም ሕዝባዊ ስራዓትን የመገንባት ሃላፊነት፣ መብትና ስልጣን ተክሞ ይጓዛል ማለት ነው።፡ አገር ወዳድ ድርጅቶችን፣ ልዩ ልዩ ሕዝባዊ ተቋማትን፣ ቡድንና ተራማጅና ታዋቂ ዜጎችን ያካተተ በመሆኑም በቀጣይነት መቋቋም ለአለበት ሰፊ የሽግግር መንግስት ምስረታና ቋሚ መንግስት ለማዋቀር ለሚደረገው ዝግጂት ሁሉ ብሄራዊ ዕርሾ ሁኖ ይቀጥላል ማለት ነው።  በመሆኑም ትግሉንም አቅጣጫ የመስጠትና በሂደትም ያልተካተቱትን የህብረተሰቭ ክፍሎች ሁሉ በእግረ-መንገዱ ዕየደመረ ሙሉ ኢትዮጵያዊ ገጽታና ይዘት ይዞ ዳር-ድንበሯን የአስጠበቀች ኢትዮጵያን፣ ዜጎች በሰላም፣ በነጻነት፣ በእኩልነትና በመከባበር የሚኖሩባትን አገር ለመመስረት የሚታገልና የሚያታግል ልዕለ-ኃይል ሁኖ ይወጣል ማለት ነው።
መነሻውን አውቆ፣ ጉዞውን አቅዶ፣ ግቡን ሳይስት ሕዝብን የድል ባለቤት ማድረግ የሚቻለዉም በተያያዘና ዕርስ በራሱ ዕየተናበበ በሚካሄድ የትግል ሰንሰለት ሲያያዝ ነው ማለት ነው።ህም ይሳካ ዘንድ  በአመኑበት ጸንተው፣ ለዕናት አገራቼውና ወገናቼው ሲሉ ሂወታቼዉን መስዋዕት ለማድረግ ቆርጠው ከተነሱ የቁርጥ ቀን ልጆች ብዙ ይጠበቃል።
ሌላው በአገራችን የሚገኙ የሲቭል፣ የሙያ፣ የሴቶችና የሃይማኖት ተቋማትና ማህቨራትን ሚና ይመለከታል።  ዕነኝህ ተቋማት በሂደት መቋቋም ለአለበት የሕዝብ አንድነት፣ የፖለቲካ ድርጅቶች ህብረትና ማዕከል ዋና ክፍል ሁነው ይዋቀራሉ ማለት ነው።  ብሄራዊና ታሪካዊ ግዳጃቼውን ለመወጣትም  በራሳቼው አነሳሽነት በውጭም በዉስጥም መንቀሳቀስ ያለባቼው ዛሬ ነው። አንደኛ በስራ፣ በሙያ፣ በሞራልና በዕምነት ዙሪያ የተሰባሰቡ በመሆናቼዉ የጠቅላላው ሕብረተሰብ የባህል፣ የሰነ-ልቦና፣ የወግ-ማዕረግና ማህበራዊ ግንኙነቶች ሁሉ ድምር ወጤቶች ናቼው ለማለት ይቻላል። ሁለተኛ በዕጾታ፣ በሥራ፣ በሙያና በሃይማኖት ዙሪያ የተደራጁ በመሆናቼው ለወያኔ የዘር፣ የጎሳና የቋንቋ ፖለቲካ ፍልስፍና ሳይሆን ለህብረብሄርዊ ድርጅቶችና ለብሔራዊ ትግሉ ቋሚ የሞራል፣ የቁሳቁስ፣ የገንዘብና የሰው ኃይል ምንጮች ሁነው የቅጥላሉ ማለት ነው።  በመሆናቼዉም በሂደት መፈጠር ለአለበት ማዕክልና በተዋረድ መፈጠር ለአለባቼው የትግል ማዕከሎች ሁሉ የደም ስርና ዕስትንፋስ በመሆን ብሄራዊና አገራዊ ሕይወት ሊሰጧቼው ይገባል ማለት ነው። ይህ ብቻ ሳይሆን ሕዝባዊ ትግሉ መልክ ኑሮት ሕግና ስራዓትን ጠብቆ ከሓዲዱ ሳይወጣ ታሪካዊ ተልዕኮውን ይመታ ዘንድ የትግሉ ዋልታና ማገር የመሆን አቅማዉም የሚናቅ አይደለም።  ሕዝቡ በየአለበት የራሱን አመራርም ሆነ የጎቨዝ አለቃ ዕየመረጠ ትግሉን በያለበት አጠናክሮ ይጓዝ ዘንድም በዕየርከኑ ለአለው ሕዝባዊ ዕንቅስቃሴም ድርጅታዊ ቅርጽ፣ የአስተዳደር ደንብና አመራርን በመስጠት ሊጫወቱ የሚችሉት ሚና ቀላል አይደለም። 

በአጠቃልይም  ይህ ትግል በግብር ይውጣ የተጄመረ ሳይሆን ለአለፉት 25 አመታት ተጠራቅሞ የቆየው ብሶት የወለደው የትግል መንፈስ መሆኑን ዕሳቤ ዉስጥ ያስገባ ታክቲክና ስትራቴጂ ነድፎ የሚንቀሳቀስ ጠንካራና ሁለገብ አመራር መፍጠር ለነገ የማይባል የቤት ሥራችን ነው።  ተልኮዉም የወያኔን ሰላዮች፣ አቅመ-ድሃ ካድሬወቻቸውንና በአጠቃላይ በአገር አቀፍ ደረጃ ያለዉን አፋኝ  መዋቅራቸውን ሁሉ ከጥቅም ዉጭ ማድረግና በወያኔ ስራአተ-ቀብር ላይ ሕዝባዊ፣ አገራዊና፤ ዴሞክራሲያዊ ስርአትን መገንባት ይሆናል ማለት ነው።  ትግሉ አቅጣጫውን ስቶ የዘረኞችና የጸረ-ኢትዮጵያ ኃይሎች ሲሳይ ከመሆን ሊድን የሚችለውም ሃላፊነት በሚሰማውና በሳል በሆነ አካል ሲመራ ብቻ መሆኑም ሊሰመርበት ይገባል።