Sunday, March 6, 2016

Finote radio. የፍኖተ ፍካሬ ዜና ! የካቲት 27 ቀን 2008 ዓ.ም

part 1, http://www.finote.org/March06EVE_Hr1.mp3
part 2, http://www.finote.org/March06EVE_Hr2.mp3

አጫጭር ዜናዎች
 •   የስኳር ፋብሪካዎች ግንባታ የውሀ ሽታ መሆኑ ተነገረ፡፡
 •   ወያኔ በሀገሪቱ የተለያዩ አካባዎች የተነሳውን አመጽ ለማፈን በይፋ ባልታወጀ ወያደራዊ እዝ ስር ማዋሉ    ታወቀ፡፡
ፍካሬ ዜና
page1image3176
የካቲት 27 ቀን 2008 .
page1image3944 page1image4104 page1image4264 page1image4424
 •   የወያኔ አባላት ሀገ-ወጥ መጋዘኖችን እያስፋፉ መሆኑ እየተገረ ነው፡፡
 •   የእንግሊዙ ጠቅላይ ሚንስትር ዴቪድ ካሜሮን ወደ አዲስ አበባ መምጣት እያነጋገረ ነው
 •   የወልቃይት ሕዝብ በነፍስ ውጪ በነፍስግቢ ህይወት ውስጥ መሆኑ ታወቀ፡፡
 •   በጉራ ፈርዳ የማፈናቀል ዘመቻ ዳግም ተካሄደ፡፡
 •   በአዲስ አበባ የሕዝብ ማመላለሻ ሾፌሮች የመቱት የሥራ ማቆም አድማ ወያኔን ማራዱ ተገለጸ፡፡
 •   አዲስ አበባ ሰማንያ አምስት የወያኔ አባላት የሆኑ የመሬት ይዞታ ኃላፊዎችና ሠራተኞች
  መታሰራቸው ታወቀ፡
 •   የኢትዮጵያ ወንዞችና ዱሎሎዎች ከጊዜ ወደ ጊዜ በመርዛም ኬሚካሎች እየተበከሉ መሆኑ ተገለጠ፡፡
  አጫጭር ዜናዎች
ቅዳሜ የካቲት 26 ቀን ቴዲ አፍሮ የሙዚቃ ዝግጅት በግዮን ሆቴል ለማቅረብ የተያዘው ፕሮግራም በወያኔ መታገዱ ታወቀ፡፡ የሙዚቃ ዝግጅቱን ለማካሄድ ያዘጋጀው ሐበሻ ዊክሊ የተባለ ድርጅት ሲሆን ድርጅቱ ለአዲስ አበባ ከንቲባ ጽህፈት ቤት ቀደም ብሎ በደብዳቤ ያሳወቀ ቢሆንም የከንቲባው ጽህፈት ቤት ምንም ምላሽ ሳይሰጠው እንደ ከረመ ታውቋል፡፡ ወያኔ የቴዲ አፍሮን የሙዚቃ ዝግጅት ሲያግድ ይህ ለሦስተኛ ጊዜ መሆኑን በማስታወስ እንዲህ ያለው ድርጊት ከወያኔ ፀረ-ዲሞክራሲ ባህርይ የሚመነጭ መሆኑን ጉዳዩን በአንክሮ የሚከታተሉ የፖለቲካ ተንታኞች ያስረዳሉ፡፡
page1image13456 page1image13616 page1image13776 page1image13936 page1image14096 page1image14256 page1image14416 page1image14576 page1image14736
 •   በሻዕቢያ የታገቱት የከ 80 በላይ የሚሆኑ ኢትዮጵያውያን የወርቅ ማዕድን ፈላጊዎች በአስቸኳይ ካልተለቀቁ ግን ተመጣጣኝ እርምጃ እንወስዳለን በማለት ሲያስፈራራ የነበረው ወያኔ በዚህ ሳምንት የተፈቱ ስለመሆናቸው ይፋ መግለጫ ሰጥቷል። ሰዎቹ የተለቀቁት በሱዳን መንግስት ሽምግልና መሆኑ የሱዳን ጋዜጦች አጋልጠዋል።
 •   ሻዕቢያ በኢትዮጵያ ያለውን የፖለቲካ ሁኔታ በመመልከትና ወያኔ ወደ ውድቀቱ እየደረሰ ነው ብሎ በመገምገም በስሩ ያሉትን የግንጠላ ሀይሎች ተመልማዮችን በብዛት እንዲያመጡና እንዲያሰለጥኑ እየጎተጎተ ነው ተባለ። የሚመጣውን የሽግግር ሁኔታ መቆጣጠር አለባችሁ ባዩ ሻዕቢያ አማራዎች በብዛት ያሉባቸው ወይም በአማራዎች የሚመሩ ድርጅቶች ቦታ እንዳይኖራቸው መደረግ አለበት የሚል ዕቅድ ማውጣቱ ተጋልጧል ። ይህን የሻዕቢያ እቅድ የቅርብ ጊዜ ወዳጆቹ ሳውዲ አረቢያና ካታርም ይደግፋሉ የሚል መረጃ አለ ።
 •   
 • ሻዕቢያ ኢራንን ከድቶ ከሳውዲና ካታር ጋር ከተሰለፈ ወዲህ ኢራን በኤርትራ በኩል ለየመን ሁቲዎች ስትልክ የነበረውን መሳሪያ በሶማሊላንድ በኩል እየላከች መሆኑ ሲነገር ሶማሊላንድ በበኩሏ ግን ይህን መሳሪያ በከፊል ለሶማሊያው አሸባሪ ቡድን ለአልሸባብ እየሸጠች ነው ተብሏል ። ሶማሊላንድ ከሶማሊያ ተገነጠልኩ ባይና የወያኔም ወዳጅ ስትሆን ከቀን ወደቀን የቀውስ ማዕከል እየሆነችም ነው ተብሏል ። ሶማሊላንድ ለአልሸባብ ሁለቱም ክንፎች--ማለትም አልቃይዳ አባል ነኝ ለሚለውና ለዳኤሽ ወይም አይሲል ተከታይ ለሆነውም ክንፍ-- መሳሪያ እየሸጠች ነው ተብሏል ። የሳውዲና ኢራን ፉክቻ የአፍሪካ ቀንድን ይበልጥ እያመሰው ሲሆን የአሜሪካና ቻይና ፉክክር በጅቡቲም መዘዙ ብዙ ነው ሲሉ የፖለቲካ ታዛቢዎች ጠቁመዋል ። ሶማሊላንድ ለወያኔ ብዙ ኢትዮጵያዊ ስደተኞችን አፍሳ አስረክባለች።
 •   
 • ወያኔ ወደ ኪስማዮ ሶማሊያ 600 ተጨማሪ ወታደር ላኩ ያለው ሀሰት ሲሆን የላከው ከአንድ ሺ በላይ መሆኑ ተጠቁሟል ። ይህንንም ያደረገው በአሜሪካ ግፊት ሲሆን በአንድ በኩል ኬንያ ከሶማሊያያ ወታደር ለመሳብ ፍላጎት ማሳየቷ ምክንያት ነው ሲባል የቡሩንዲም ማገራገር ሌላ ምክንያት ነው ተብሏል ። የሀገሪቷን ችግር አሜሪካና ሩዋንዳ በሚፈልጉት ካልፈታ በሶማሊያ ከሚገኘው የተባበሩት መንግስታት ጦር የብሩንዲ ወታደሮች እንደሚባረሩ ለብሩንዲው መሪ ማስፈራሪያ የተነገረው መሆኑ ታውቋል። የቡሩንዲው መሪ ጥሩ ሲከፈል የነበረው ጦሩ ከሶማሊያ ተመልሶ በችግር ላይ ችግር እንዳይሆንበት ፈርቷልም ተብሏል ። በተባበሩትና በአፍሪካ ህብረት ስም በየቦታው የተሰማሩት የአፍሪካ ጦሮች ልክ እንደ ፈረንሳዮች ሀገሬውን ሴት በመድፈር ና በመደልም እየተከሰሱ ናቸው ። ወያኔ ላይቤሪያና ዳርፉር ሱዳን ውስጥ ጥሩ የሚከፈላቸውና በአብዛኛው ትግሬ የሆኑ ወታደሮችን አሰማርቶ እንዳለ ይታወቃል ።
 •   
 • እስራኤል በአፍሪካ ስደተኞች ላይ ግፍ እየፈጸመች ነው በሚል ውግዘት እየድረሰባት ነው ። በብዛት ከሱዳንና ኤርትራ መከራና ሞትን ተጋፍጠው ወደ እስራኤል የሚያቀኑትን ስደተኞች አስራ እንደምታሰቃይና አለውዴታቸውም ወደ መጡበትና ወደ ዩጋንዳን ርዋንዳ የምትመልሰው እስራኤል ስደተኞችን አስራ እንደምታሰቃይ የሰብዓዊ መብት ድርጅቶች አጋልጠዋል ። የደማችንን ጥራት ያባላሻሉ ባይዋና ዘረኛዋ እስራኤል ከዚህ ቀደም የአፍሪካ ስደተኞችን ካንሰር ማለቷ ይታወሳል ። በናዚ ጀርመን የደረሰባቸውን ዘንግተው ጀርመንን መሰሉ የተባሉት እስራኤሎች በስደተኞች ላይ የሚያሳዩት ጭካኔ የሚያስወግዛቸው ነውም ተብሏል ።
 •   በዚህ ሳምንት በእስራዔል አገር የሚገኙ በርካታ ትውልደ ኢትዮጵያውያን በሀምሌ 2006 ዓም የሴፍ ሳላምሳ ለተባለው ዜጋ ህይወት መጥፋት ምክንያት ነበር የተባለው የፖሊስ አባል በወንጀል እንዳይከሰስ የእስራኤል ባለስልጣኖች ያደረጉትን ውሳኔ በመቃወም ከፍተኛ የተቃውሞ ሰልፍ ያደረጉ መሆናቸው ታውቋል። በሰልፉ ላይ በነበረ ግጭት ከስምንት ሰዎች በላይ በፖሊስ ቁጥጥር ስር እንደዋሉ ተነግሯል። የዛሬ ሁለት ዓመት ዮሴፍ ሳላምሳ ራሱን ለማጥፋት ምክንያት የሆነው ቀደም ብሎ ፖሊስ ዮሴፍን በቁጥጥር ስር ለማድረግ የኤሌክትርክ ንዝረት የሚረጭ መሳሪያን በመጠቀም ራሱን እንዲሰት ስላደረገው ነው የሚል ማስረጃ ቢኖርም አቃቤ ህጉ ፖሊሱ በወንጀል እንዳይከሰስ የወሰነ መሆኑ ተገልጿል።፡
 •   
 • አንድ ስማቸውን መግለጽ ያልፈለጉ የተባበሩት መንግስታት ባለስልጣን በዚህ ሳምንት ለጋዜጠኞች በሰጠቱ መረጃ በደቡብ ሱዳን ግጭቱ ከተጀመረ ከ2006 ዓመተ ምህረት ጀምሮ ከ50 ሺ ሰዎች በላይ የሞቱ መሆናቸው ገልጸዋል። በባለስልጣኑ የተሰጠው ቁጥር ሌሎች የሰብአዊ እርዳታ ድርጅቶች ከሚያስቀምጡት ግምት በአምስት እጥፍ የላቀ መሆኑ ታውቋል። ባለስልጣኑ በደቡን ሱዳን ከ.4.2 ሚሊዮን በላይ ሕዝብ ስደተኛ የሆነ በመሆን ቤት ንብረቱን ጥሎ የተሰደደ መሆኑና እንዲሁም በከፍተኛ ደረጃ ህዝቡን ሊጨርስ የሚችል ረሃብ እየተከሰተ መሆኑን ገልጸዋል።

 • የስኳር ፋብሪካዎች ግንባታ የውሀ ሽታ መሆኑ ተነገረ፡፡
  2002 .. ጀምሮ የስኳር ምርትን ለማሳዳግ እንዳለመ የተነገረለት ይህን ሁሉ ዘመን ከወሬ ባለፈ ለፍሬ አለመብቃቱ ታወቀ፡፡ በወያኔ እየተሠሩ እንደሆነ ከሚነገርላቸው የልማት ተቋማት ከሚባሉት ውስጥ የሙስና ተቋማት የሚለው ስያሜ በትክክል ይገልጻቸዋል የሚሉ በርካታ ናቸው፡፡ የስኳር ልማት ድርጅቶች የሚመሩት በህወሀቱ ቁንጮ በዓባይ ፀሀይ መሆኑ ይታወቃል፡፡ ይህ ሰው በስኳር ልማት ሰም የተመደበውን ገንዘብ መመዝበር ብቻ ሳይሆን እንዳለ መጋጡን ድርጅቱ ውስጥ የሚሠሩ የሂሳብ ባለሙያዎች ያስረዳሉ፡፡ የመስኖ ቦዮች ለዝርፊያ እንዲያመች እስከ አምስት ጊዜ እየፈረሱ እየተገነቡ እንደሆነ ይታወቃል፡፡ ለፋብሪካዎቹ በሚያስፈልጉ ማሽነሪዎች ግዢ ስም ግምቱ በሚሊዮኞች ውስጥ የሚሆን ገንዘብ እንደተዘረፈ ለዚህ ሚስጥር ቅርብ የሆኑ ወገኖች በቁጭት ይናገራሉ፡፡ ብዙዎቹ ፋብሪካዎች በ2006 .. ምርት ማምረት እንደሚጀምሩ የተነገረ ሲሆን እስካሁን የቅባት እህሎች ተልከው መርዛም ዘይት ከቻይና እንደሚገባው ሁሉ ስኳርም ከውጪ እየገባ መሆኑን ተረድተናል፡፡ በተወሰኑ የስኳር ልማት ጣቢያዎች ፣ እንደ ጣና በለስ የመሳሰሉት የሸንኮራ አገዳው ጋሽቦ መሬት ላይ እየወደቀና እየተበላሸ መሆኑን ቅርብ የሆኑ ምንጮች በቁጭት ያስረዳሉ፡፡

 • ወያኔ በሀገሪቱ የተለያዩ አካባዎች የተነሳውን አመጽ ለማፈን በይፋ ባልታወጀ ወያደራዊ እዝ ስር ማዋሉ ታወቀ፡፡ በተለያዩ የሀገሪቱ አካባቢዎች ከህዳር ወር ጀምሮ እየተጋጋለ በመሄድ ላይ ያለውን ሕዝባዊ ተቃውሞ ለመቅጨት የወያኔ ዘብ የሆነው አረመኔውና ደም አፍሳሹ የአጋዚ ጦር የንፁሀን ህፃናትን፣ የለጋ ወጣቶችን፣ የገበሬዎችን፣ የሴቶችን፣ የሽማግሌዎችን ደም አፈሰሰ፡፡ ይህ አረመኔ ነፍሰ-ገዳይ ጦር እስካሁን በተለያዩ አካባቢዎች በአልሞ ተኳሾች የገደላቸው ዜጎች ቁጥር ከሦስት መቶ በላይ እንደሆነ ጉዳዩን በቅርብ የሚከታተሉ ወገኖች ያስረዳሉ፡፡ ከሁለት ሺ በላይ ሰዎች እንደቆሰሉና ወደ አምስት ሺ የሚጠጉ ሰዎች በግፍ እንደታሰሩም እነዚሁ ወገኖች ያስረዳሉ፡፡ ለመከላከያ ቅርብ ከሆኑ ሰዎች የተገኘው ማስረጃ በአርሲ፣ በሻሸመኔ፣ በጉጂ፣ በምስራቅ ሐረርጌ፣ በአምቦ፣ ወዘተ. አካባቢዎች የፌደራል ዩኒፎርም የለበሱ የአጋዚ ጦር አባላት አካባቢዎቹን እንደወረሩና በደርግ ዘመን ነፃ እርምጃ ይባል እንደነበረው ያላማረውን ሰው ተኩሰው መግደል እንደሚችሉ በቀጥታ በሳሞራ ዩኑስ መታዘዛቸው ይነገራል፡፡ ይህ የአጋዚ ጦር ሙሉ በሙሉ በትግራይ ሰዎች የተሞላ በመሆኑና እያደረገ ያለው አረመኔያዊ ድርጊት ቂም እያስቋጠረ መሆኑን መረዳት ችለናል፡፡ ዐርብ የካቲት 25 ቀን 2008 .. በጂማ ዩኒቭርሲቲ ተማሪዎች፣ በጉጂና በቦረና ወያኔ በኦሮሞ ህዝብ ላይ እየደረሰ ያለውን ጭፍጨፋ በመቃወም አመጽ መጀመራቸው ከአካባዎቹ የተገኘው የተገኘው መረጃ ያስረዳል፡፡ የሰው ልጆች በግፍ መገደል ማንኛውንም የሰው ዘር የሚያስቆጣ ቢሆንም በኦሮሞ ባህል ልጅ ከሀብት ሁሉ መጀመሪያ የሚሠጠው የአምላክ በረከት በመሁኑና ኦሮሞ እንኳን ከአብራኩ የወጣውን ሌላም ሰው ልጅን በጉዲፈቻ እንደ ልጁ አድርጎ የሚያሳድግ መሆኑን በመጥቀስ የአጋዚ ጦር በኦሮሞ ልጆችን በመግደሉ ሌላ ሳይሆን ኢትዮጵያን እንደገደለ ሊቆጠር እንደሚገባውና ሁሉም ኢትዮጵያዊ በተጀመረው ፀረ-ወያኔ ትግል ሊሳተፍ እንደሚገባው ያሳስባሉ፡፡ ይህ በእንዲህ እያለ ወያኔ የኦሮሚያ ፕሬዚደንት የነበረውን ዳባ ደበሌን በወያኔ ውሳኔ ከቦታው ላይ አንስቶ አስተሳሰቡ እንደ ወያኔ የሆነውንና በጨካኝነቱ የሚታወቀውን በከር ሻሌን አስቀምጧል፡፡
በተያያዘ ዜና የወያኔ ኦህዴድ ከፍተኛ ባለሥልጣኖች ኃላፊዎች በዚህ ሳምንት በናዘሬት የግምገማ ስብሰባ የጀመሩ መሆናቸው የተገለጸ ሲሆን ስብሰባው ከፍተኛ ጭቅጭቅና ንትርክ የነበረበት መሆኑ ተደርሶበታል። በወያኔ መሪዎች የተደረገው ሹም ሽር ብዙዎቹ የኦህዴድ ካድሬዎችን ያስቆጣና ያሳዘነ ቢሆንም ከስብሰባው በኋላ ተጨማሪ የወያኔ ሹመኞች ይባረራሉ ተብሎ ይጠበቃል። በተመሳሳይ ዜናም የብዓዴን ማዕከላዊ ኮሚቴ አባላትና እንዲሁም የአዲስ አበባ አስተዳድር የወያኔ ሹመኞች ስብሰባ ላይ ተቀምጠው መሰንበታቸው ታውቋል።
በሌላ በኩል ሕዝባዊ ተቃውሞው በዚህ ሳምንትም ተጠናክሮ ቀጥሏል። እሁድ ዕለት፤ በሐረርጌ ፤ በወለጋ በአርሲና በሸዋ የሚገኙ ልዩ ልዮ ከተሞች ውስጥ ተቃውሞ የቀጠለ ሲሆን የወያኔው ነፍስ ገዳይ አጋዚ ወታደሮች በየቦታው ግድያ ያካሄዱ ሲሆን በየከተሞቹ ከሕዝባዊ ተቃውሞችና ቁጣ ጀርባ እጃችሁ አለበት በማለት የልማት ሠራተኞችንና መምህራንን ሲያዋክቡ መሰንበታችው ታውቋል።

የወያኔ አባላት ሀገ-ወጥ መጋዘኖችን እያስፋፉ መሆኑ እየተገረ ነው፡፡
የወያኔ ከፍተኛ ሹመኞችና አባላት ከውጪ ወደ አገር ውስጥ በቦሌም ሆነ በጅቡቲ በኩል ዕቃ ሲያስገቡ በደም ካሳ ስም ከቀረጥ ነፃ እንደሚያስገቡ የታወቀ ነው፡፡ እነዚህ ዕቃዎች የሚከማቹት ንብረትነታቸው የወያኔ ካድሬዎች በሆኑ ትምህርት ቤቶችና የጤና ተቋማት ውስጥ መሆኑን ጉዳዩን በቅርበት የሚከታተሉ ወገኖች ያስረዳሉ፡፡ እነዚህ ጥቂት ምርጥ የትግራይ ተወላጆች ምንም ዓይነት ግብርና ቀረጥ ሳይከፍሉ አንዲህ በውንብድና በጠረራ ፀሀይ ይነግዳሉ፡፡ ይህን ጉዳይ የሚያውቁ ነጋዴዎች በየጊዜው በአንድ አገር ሁለት ዓይነት አስተዳደር ሊኖር እንደማይገባ እየተሟገቱ መሆኑ ይታወቃል፡፡ወያኔ ኢትዮጵያና ሕዝቧን በማጅራታቸው እያረደ እንደሆነ የሚያስረዱ ሰዎች ቁጥር ብዙ እንደሆነ ለማወቅ ተችሏል፡፡በሌላ በኩል ከወያኔው የፌዴሬሽን ምክር ቤት ያረጁ ዕቃዎችን ማከማቻ መጋዘን ውስጥ በርካታ ኮምፒዩተሮች የተዘረፉ መሆኑን የሪፖርተር ጋዜጣ በአምዱ ላይ አስፍሮ አውጥቷል። ኮምፒውተሮቹ የተዘረፉት መቼ በምን ዓይነት ሁኔታ እነማን እንደዘረፉት ገና በመጣራት ላይ ነው የተባለ ሲሆን የፌዴራል ፖሊስ ተብየው ጥብቅ ጥበቃ በሚያደርግበት አካባቢ በርካታ ኮምፒውተሮች መዘረፋቸው አነጋጋሪ ሆኗል። ዝርፊያውን ያካሄዱት የወያኔ የበላይ ባለስልጣኖች ናቸው የሚል ድምዳሜ ብዙዎቹ ይሰጣሉ።

የእንግሊዙ ጠቅላይ ሚንስትር ዴቪድ ካሜሮን ወደ አዲስ አበባ መምጣት እያነጋገረ ነው፡፡
ዴቪድ ካሜሮን በመጋቢት ወር ሦስተኛ ሳምንት ላይ ወደ አዲስ አበባ እንደሚመጣ ፕሮግራም መያዙ እየተነገረ ነው፡ ፡ እንግሊዝ ከአሜሪካ ቀጥላ በዓለም ውስጥ ቀውስ ፈጣሪና አራጋቢ እንደሆነች ይታወቃል፡፡ ጦርነቶች በተነሱ ቁጥር ለግዙፍ የጦርነት ቁሳቁስ አምራች ኩባያዎቿ ሰፊ ገበያ ይፈጠራል፡፡ እንግሊዝ የወያኔ ፖሊስን ከማሰልጠን አልፋ የወያኔ ሰላዮችን ዘጠና ከመቶ የሚሆኑትን በማስትሬት ዲግሪ ደረጃ እያሰለጠነች መሆኑ ይታወቃል፡፡ የዴቪድ ካሜሮን አጀንዳ የሚያተኩርበት መሪ ሀሳብ የፀጥታ ጉዳይ እንደሆነ ከሚወጡ መረጃዎች መገንዘብ ተችሏል፡፡ ከዚህ ተያያዥ የሆነው ዋናው ጉዳይ የአፍሪካ ቀንድ የፀጥታ ሁኔታ ላይ እንደሚያተኩር ታውቋል፡፡ በሀገሪቱ የተለያዩ አካባቢዎች እየከረረ በመሄድ ላይ ያለው ሕዝባዊ አመጽ፣ በሶማሌ አደጋ እያደረሰ ያለው አልሽባብ እየተጠናከረ መሄድ፣ እንዲሁም በተለያዩ የአገሪቱ አካባቢዎች እየተካሄዱ ያሉ ፀረ-ወያኔ እንቅስቃሴዎች በጽንፈኛ ኃይሎች የመጠለፍ አደጋ ሊያጋጥማቸው ይችላል የሚልም ስጋት ስላለ በዚህ ሁሉ ላይ ለመምከርና ወያኔ በመጠቀም ስጋቱን ለማምከን እንደሆነ ሁኔታውን በአንክሮ ያጤኑ የፖለቲካ ተንታኞች ያስረዳሉ፡፡ እንግሊዝ እሰካሁን ለወያኔ የምታደርገውን እርዳታ አስተጓጉላ እንደማታውቅና በየአመቱ ከሦስት መቶ ሃምሳ ሚሊዮን ዶላር በላይ በኢትዮጵያ ስም ለወያኔ ቁንጮዎች እንደምታጎርስ የታወቀ ነው፡፡ የእንግሊዝ ፖለቲካ ሁሌም ጸረ ኢትዮፕያ ሆኖእ የቀጠለ መሆኑንታዛቢዎች ያሳስባሉ ።

የወልቃይት ሕዝብ በነፍስ ውጪ በነፍስግቢ ህይወት ውስጥ መሆኑ ታወቀ፡፡
ወያኔ በሰፈራ ወደ ሁመራ፣ ዳንሻ፣ ወልቃይት፣ ጠገዴ፣ ማይካድራ፣ አከር የመጡ ትግሬዎች በግዴታ ሰልፍ እንዲወጡ በማድረግ የወልቃይት አማራዎችን እንዲያስፈራሩ አድርጓል፡፡ የወልቃይት ሕዝብ ጥያቄ አስተባበሪ ኮሚቴ አባላት የሆኑት አቶ ባየው ካሤና ጓደኞቹ ህገ-ወጥ የሆነ ጋዜጣ ይዛችኋል ተብለው መታሰራቸው ከአካባቢው ከተገኘው ዜና መረዳት ተችሏል፡፡ የአስተባባሪ ኮሚቴ አባላትም በየቀኑ እየተለቀሙ በመታሰር ላይ መሆናቸው ታውቋል፡፡ ይህ በእንዲህ እያለ በወልቃይት የአስባባሪ ኮሚቴ አባላት በግፍ መታሰራቸውን በመቃወም የተጠራው ስብሰባ ከወያኔ ሹመኞች ፍቃድ ቢነፈገውም ሕዝቡ ገንፍሎ በመውጣት ስብሰባው ዐርብ የካቲት 25 ቀን በጋለ ስሜት መሄዱን ተረድተናል፡፡ ወያኔ ከጎንደር በዘረፋቸው መሬቶች ሁሉ ትግራውያንን በሰፊው አስታጥቆ ማስፈሩንም ቀጥሎበታል ።
በጉራ ፈርዳ የማፈናቀል ዘመቻ ዳግም ተካሄደ፡፡
page5image17440 page5image17600 page5image17760 page5image17920
ከዚህ ቀደም በጉራ ፈርዳ ይኖሩ የነበሩ ሃያ ሁለት ሺ የሚጠጉ አማራ አርሶ አደሮች በ2005 .. እና በ2006 .. ከእርሻቸውና ከመኖሪያ ቀያቸው መፈናቀላቸው የሚታወስ ነው፡፡ እንዲሁም በ2007 .. ከሰባት መቶ በላይ የሚሆኑ መገደላቸው አይዘነጋም፡፡ በዚህ በየካቲት ወር ቤቶቻቸው ፈርሶባቸው ንብረታቸውንም መቀማታቸው ታወቀ፡፡ ይህን ድርጊት ፊት ለፊት ተጋፍጠው የተቃወሙ ከሰላሳ በላይ የሚሆኑ አርሶ አደሮች ታስረው እንደተደበደቡ ከስፍራው የተገኘው መረጃ ያስረዳል፡፡

በአዲስ አበባ የሕዝብ ማመላለሻ ሾፌሮች የመቱት የሥራ ማቆም አድማ ወያኔን ማራዱ ተገለጸ፡፡
በአዲስ አበባ የሚገኙ አስራ ሦስት የሚኒ ባስ ሾፌሮች ማህበራትና ሦስት የመካከለኛ ኦቶብስ ሾፌሮች ማህበራት ለሾፌሮቹ ሳይገለጽ ከዛሬ ሁለት ሳምንት ጀምሮ በሥራ ላይ እንዲው የተደረውን የትራፊክ ደምብ በመቃወም የመቱት አድማ ወያኔን ማንቀጥቀጡን መረዳት ተችሏል፡፡ አብዛኛዎቹ ደንቦች ከምዕራብ አገሮች በቀጥታ የተገለበጡ በመሆናቸው እዚህ ካለው አጠቃላይ ሁኔታ ጋር ሊጣጣሙ መቻላቸው ሳይመዛዘን በሥራ ላይ እንዲውሉ መደረጉ ሙሉ በሙሉ የወያኔ ሹመኞችን ድንቁርና አጋልጧል የሚሉ ወገኞች በርካታ ናቸው፡፡ ከደንቦቹ ውስጥ እራሱና ተሳፋዎቹ የደህንነት ቀበቶ ሳይታጠቁ መንዳት፣ ከፍተኛ ድምጥ ማሰማት፣ መንገደኛ ላይ ውሀ መርጨት፣ ወዘተ. የሚሉ ደንቦች ይገኙበታል፡፡ ቀበቶ ከሾፌሩ ወንበር ጋር ከተያያዘው በስተቀር መኪናዎቹ ሁሉ እንደሌላቸው እየታወቀ እንዲህ ያለ ደንብ ማውጣት ከመሳለቂያነት እንደማያተርፍ በሙያው ላይ የቆዩ ሰዎች ያስረዳሉ፡፡ የከተማዋ መንገዶች በየጊዜው እየተቆፋፈሩ ባለበት ሁኔታና መነገዶች ሁሉ እየጠበቡ በሄዱበት ሁኔታ ውሀ መርጨት ያስቀጣል የሚል ደንብ ማውጣት ከፈረሱ ጋሪውን ማስቀደም እንደ ብዙዎች ይናገራሉ፡፡ በተመሳሳይም ከፍተኛ ድምጽ ማሰማት የሚለው የምን ድምጽ እንደሆነ በግልጽ ያልተቀመጠ በመሆኑ ለወጣው ደንብ ሌላ የሚያብራራ ደንብ ሊያስፈልገው ነው፡፡ የጥፋት ነጥቦቹ ተመዝግበው አስራ አራት ሲሞሉ የመንጃ ፈቃድ ያስነጥቃል፡፡ በዚህ ሳቢያ ለትራፊክ ፖሊስ የሚከፈለው ጉቦ ወደ አምስት መቶ ብር እንዳሻቀበ መረዳት ተችሏል፡፡ ይህ በእዲህ እንዳለ በደሴ፣ በኮቦልቻ፣ በኩታ በር ወዘተ. የሚሰሩ የታክሲ ሾፌሮች ይህን ደንብ ተቃውመው ዐርብ የካቲት 25 ቀን የሥራ ማቆም አድማ እንደ መቱ ከደሴ ያገኘነው ዜና ያስረዳል፡፡ ይህ ተቃውሞ የሚስፋፋና ሌሎችንም የህብረተሰቡ ክፍሎች (ተማሪዎች፤አስተማሪዎች፤ የቢሮ ሰራተኞች ወዘተ) በህገር አቀፍ ደረጃ ይቀሰቅስ ይሆናል የሚል ተስፋ እየተጣለበት ነው ።

አዲስ አበባ ሰማንያ አምስት የወያኔ አባላት የሆኑ የመሬት ይዞታ ኃላፊዎችና ሠራተኞች መታሰራቸው ታወቀ፡፡
ከአሁን ቀደም በተለያዩ ጊዜያት የከተማዋን መሬት እንደ ግል ሀብታቸው ሲቸበችቡ የነበሩ ለይስሙላ እየታሰሩ መፈታታቸው አይዘነጋም፡፡ ከእነዚህ ውስጥ በጂማ ከተማ በርካታ ወጣቶች የጨፈጨፈው ቃሲም ፊጤ ይጠቀሳል፡፡ ይህ የወያኔ ሹመኛ የአዲስ አበባን መሬት እንዳሻው በግሉ ሲቸበችብ እንደነበር እራሱ የወያኔው ፀረ- ሙስና ኮሚሽን በቂ ማስረጃ እያሰባሰበ መሆኑ ሲታወቅ በአባዱላ አማካኝነት ወደ ቻይና ሄዶ እንዲደበቅ መደረጉ አይዘነጋም፡፡ ቻይና ወደ ሦስት ወር ከተቀመጠ በኋላ እንዲመስ ተደርጎ ቦሌ እንደደረሰ ተይዞ እንዲታሰር ተደረገ፡፡ በወያኔ ትእዛዝ የተከፈተው የክስ መዝገብ ተዘግቶ በነፃ እንዲለቀቅ ተደርጓል፡፡ ይህ ዘራፊ በአሁኑ ሰዓት የኦሮሚያ
page6image19256 page6image19416
የመሬት ይዞታ ኃላፊ ሆኖ መሾሙ ታውቋል፡፡ ወያኔ አሁን እንዳሰራቸው እየተነገረ ያለው ሰማንያ አምስት የመሬት ዘራፊ ወያኔዎች ነገ ተነገ ወዲያ ከእስር ይለቀቃሉ፡፡ እነዚህ የበታች የወያኔ ሹመኞች የሚዘርፉትን ገንዘብ ለከፍተኛና ለቁንጮ ወያኔዎች እንደሚያስተላልፉ የታወቀ ነው፡፡ በጋሙኛ እባጭ በእባጫም ምላጭ አይበጣም የሚለው አባባል ለዚህ ለዘራፊው የወያኔ ቡድን ተገቢ ምሳሌ መሆኑን የሚያስረዱ ብዙዎች ናቸው፡፡

የወያኔው ሹመኛ ፓትርያክ ማሕበረ-ቅዱሳን ለማፍረስ ደባ እየሰሩ መሆኑ ይፋ ሆነ፡፡
ወያኔ በሀይማኖቶች የውስጥ ጉዳይ እየገባ የምእመናንን አንድነት እየበጠበጠና እያወከ በሆኑ ዓለም ያወቀው ሆኗል፡፡ በተለይ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያንና የእስልምና ሀይማኖቶችን እንደ ወያኔ የፖለቲካ ተቋት ከተቆጠሩ አመታት አልፈዋል፡፡ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን በክፍተኛ ሁኔታ ምዝበራ የሚፈጽምበት እንደሆነ እየተገለጸ መሆኑ ይታወቃል፡፡ በየአድባራቱና በየገዳማቱ ከምእመናን በሙዳየ ምጽዋትና በአስራት በኩራት የሚገባው ገቢ በአለቆችና በጸሀፊዎች ይዘረፋል፡፡ በቤተክርቲያኗ ውስጥ ለከፍተኛ ሃላፊነት ለመሾም ከብቃት መለኪያዎቹ ውስጥ ዋነኛው የወያኔ አባል መሆን እንደሆነ ይታወቃል፡፡ ቤተክርስቲያኗን በቅርብ የሚከታተሉ ምእመናን እንደሚያስረዱት ከሀይማኖታዊ ስነ-ምግባር የወጣ ድርጊት ሲፈጽሙ ዝም ብሎ ማየት ተገቢ አለመሆኑን ከሚያስረዱና እርምት እንደደረግ ከሚጠይቁ መሀል ምህበረ-ቅዱሳን አንዱ መሆኑ ይነገራል፡፡ ማህበረ-ቅዱሳን የሀይማኖቱ ቀኖና እና ቱፊት ሲፋለስ በፊት ለፊት እያጋለጠ ስለሚሟገት በሙስና የተዘፈቁ የስም የሀይማኖት አባቶች በጠላጥነት እንደተነሱበት ውስጥ አዋቂዎች ያስረዳሉ፡፡ ሟቹ የወያኔው ቁንጮ በማህበሩ ላይ እርምጃ ለመውሰድ በአደባባይ መዛቱ አይዘነጋም፡፡ የወያኔው ሹመኛ ፓትርያርክ ማትያስ ከአሁን ቀደም በማህበሩ ላይ ከአንድ የሀይማት አባት የማይጠበቅ በዘለፋ የተሞላና ዛቻ ያዘለ ደብዳቤ መጻፋቸውን የሚያስታውሱ ወገኖች እንደሚሉት ከደብዳቤው ይዘት መረዳት የሚቻለው ደብዳቤው የተዘጋጀው በወያኔዎች እንደሆነና ፓትርያርኩ ፊርማቸውን ብቻ እንዳኖሩበት ይጠረጥራሉ፡፡ አሁን ድጋሚ ፓትርያርኩ የካቲት 16 ቀን በጻፉት ደብዳቤ በአምስ ቀናት ውስጥ ማህበሩ እሳቸውን ይቅርታ ጠይቆ ደብዳቤ ካልጻፈ በሌላቸው ሥልጣን ማህበሩን ለማፍረስ ዛቻ ያዘለ ደብዳቤ ጽፈዋል፡፡ የሀይማቱን ህግጋት ጠንቅቀው የሚያውቁ እንደሚያስረዱት የሀይማኖቱ የበላይ መሪ ቅዱስ ሲኖዶስ እንጅ አንድ ፓትርያክ አለመሆኑ እየታወቀ ይህ ሁሉ ዛቻ ጌታዋን የተማመነች በግ ላቷን አትደብቅም እንደሚባለው ፓትርያርኩ የሀይማኖት አባትነታቸውን ጥለው ለካድሬነት ሥራቸው በጣም እንደተጎነበሱ ያስረዳል የሚሉ ብዙዎች ናቸው፡፡
ይህ በዚህ እንዳለ በአዲስ አበባ የሚገኘው ሲኖዶስ ቋሚ አባላት ሳይታሰብ በድንገት ስብሰባ መቀመጣቸው ተገለጸ። ስብሰባው በድንገት የተካሄደው በአቡነ ናትናኤል ዕረፍተ ሞት ምክንያት ሲሆን በወያኔው ፓትርያርኩና በማሀበረ ቅዱሳን መካከል ስላለው ውዝግብ በዋናነት ይነጋገራል ተብሎ ይጠበቃል። በተጨማሪም ስለ ስለ ሰላም፤ በሕዝባዊ ተቃውሞና ቁጣ የተነሳ ስለተቃጠሉ አብያተ ክርስቲያናት፤ ስለድርቅና ረሃብ፤ በቤተክርስቲያኗ ውስጥ ስላለው የተዛባና ማዕከላዊነት ስለሌለው አሰራር፤ እንዲሁም ስለ ፓትርያርኩ የውጭ ጉዞ ይነጋገራል ተብሏል። ከቅርብ ጉዜ ወዲህ በፓትርያርኩና በሲኖዶሱ መካከል የሥራ አለመግባባት መፈጠሩ የታወቀ ሲሆን ፓትርያርኩ ያለ ቋሚው ሲኖዶስ ዕውቅና የሚወስዱት እርምጃና መግለጫ የቋሚ ሲኖዶስ አባላትን ያጠያየቀ ሆኗል። ለኢትዮጵያ ተወህዶ ኦሮትዶክስ ቤተ ክርስቲያን ቅርብ ነን የሚሉ ምንጮች ፓትርያርኩ ከመስመር እየወጡ እንደሆነና ከመንፈሳዊ መሪ ይልቅ የወያኔ ካድሬ እየሆኑ መምጣታቸውን ይገልጻሉ።
page7image19608

የኢትዮጵያ ወንዞችና ዱሎሎዎች ከጊዜ ወደ ጊዜ በመርዛም ኬሚካሎች እየተበከሉ መሆኑ ተገለጠ፡፡
ለሀገርና ለወገን ካለማሰብ በመጣ ዘጠና አምስት ከመቶ የሚሆኑት ወንዞችና ጅረቶች በመርዛም ኬሚካሎች እየተበከሉ እንደሆኑ በጉዳዩ ላይ ጥናት ያካሄዱ ይፋ ማድረጋቸው ታወቀ፡፡ በአዲስ አበባ ሳይቀር የቀበና፣ የቡልቡላ፣ የአቃቂ ወዘተ. ጅረቶች ከዛሬ አርባ አመት በፊት ኩልል ያለ ውሀ ይውርድባቸው እንደነበር የሚያስታውሱ ያስረዳሉ፡፡ በገጠር ገበሬዎች ለእራሳቸውም ሆነ ለከብቶቻቸው የሚጠቀሙባቸው ጅረቶች ያልተበኩ እንደነበሩ የታወቀ ነው፡፡ አሁን ሁኔታው እጅግ በሚያስፈራ መልኩ ተቀይሯል፡፡ ወንዞች በመበከላቸው ከብቶች ከአሁን ቀደም ታይቶ በማይታወቅ ሁኔታ እየተነፋፉ ወይ እየመነመኑ ይሞታሉ፡፡ የወንዝና የጅረት ውሀ ጠልፈው ማሳቸውን የሚያርሱ ገበሬዎች ምርታቸው ውሀ ሳያጣ እየጫጫ በቡቃያው ይረግፋል፡፡ እነሱንም ቆዳቸውን አይተውት የማያቁ የእከክ በሽታ እያሰቃያቸው መሆኑ ታውቋል፡፡ለዚህ ዓይነተኛ ምሳሌ የሚሆነው ደብረ ብርሀን ከመገባቱ በፊት የምትገኘው ጫጫ የምትባል ከተማ አቋርጦ የሚሄደውን ወንዝ በከተማዋ ዳርቻ ላይ የሚገኙ ኗሪዎች በመስኖ የወንዙን ውሀ በመጠቀም በአመት ሁለት ሦስቴ ያመርቱ እንደነበር የሚያስታውሱት ሲናገሩ በአሁኑ ሰዓት ይሄ የለም፡፡ በወንዙ ዳርቻ ላይ የተቋቋመ የአረቄ ፋብሪካ ወደ ወንዙ በሚለቀው የኬሚካል ዝቃጭ የወንዙ ውሀ ተበክሏል፡፡ ይህ የተበከለ ውሀ ሰብሉን እሳት እንደበላው ሳር ክው አድርጎ እያደረቀ ቢያስቸግራቸው ገበሬዎቹ ለአካባቢው የወያኔ ሹማምን አቤት ቢሉም የዝሆን ጆሮ እንጂ ሰሚ አላገኙም፡፡
የውጭ አገር ዜናዎች
 •   በደቡብ አፍሪካ በየአመቱ 600 000 (ስድስት መቶ ሺ) የሚሆኑ መንገደኞችን የሚያስተናግደው በምዕራብ ኬፕ የሚገኘው የጆርጅ አውሮፕላን ጣቢይ ከጸሐይ ብርሃን የኤሌክትሪክ ኃይል የሚያመነጭ መሳሪያ በመትከል እና ስራውን እንዲጀምር በማድረግ ከአፍሪካ የመጀመሪያ ሆኗል። በአሁኑ ወቅት አውሮፕላን ጣቢያው ከሚያስፈልገው ጠቅላላ የኤሌክትሪክ ኃይል ፍጆታ አርባ ከመቶ የሚሆነውን ከዚሁ መሳሪያ የሚያገኝ ሲሆን ከጥቂት ጊዜ በኋላ 100 ከመቶ የሚሆነው የኤሌክትሪክ ፍጆታ ከዚሁ መሳሪያ ይገኛል ተብሏል። ከጸሐይ ብርሃን የኤሌክትርክ ኃይል የሚያመነጨውን መሳሪያ ለመትከል አንድ ሚሊዮን ዶላር የፈጀ ሲሆን በቅርብ ጊዜ ውስጥ ሌሎች አውሮፕላን ጣቢያዎች ተመሳሳይ እርምጃ እንደሚወስዱ ይጠበቃል። የኤሌክትርክ ኃይል መሳሪያን በአየር ጣቢያዎች ላይ በመጠቀም ረገድ ቀዳሚዋ ህንድ ስትሆን ባለፈው ዓመት በኮቺን ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ጣቢያ ላይ በ9.5 ሚሊዮን ዶላር የተተከለው መሳሪያ በአይነቱ ከዓለም አንደኛ ነው ተብሏል።
 •   ወደ ፊት እንጓዝ (Go forward) በሚል ስም የሚጠራው የዩጋንዳ የተቃዋሚ ፓርቲ በዩጋንዳ የተደረገው ብሔራዊ ምርጫ ውድቅ መሆን አለበት በማለት በአገሪቱ የበላይ ፍርድ ቤት ላይ በዚህ ሳምንት ክስ የመሰረተ መሆኑ ታውቋል። ፓርቲውን በመወከል የተወዳደሩት የምርጫው ኮሚሽን አገኙ ካላቸው ድምጽ በላይ ማግኘታቸውን ያረጋገጡ መሆናቸውን በመዘርዘር ውድድሩ ማጭበርበር የተሞላበት የማስመሳያ ምርጫ ነበር በማለት ድርጅቱ ከሷል። ከድምጹ 35 ከመቶ አግኝተዋል ተብለው በሁለተኛ ደረጃ እንዲቀመጡ የተደረጉት የሌላው ፓርቲ መሪ ሚስተር ቢስጌ በቤቱ ውስጥ ታግተው ያሉ ሲሆን በፍርድ ቤት ክስ ማቅረብ ለመንግስቱ የህግ ሽፋን መስጠት ነው በሚል ምክንያት ጉዳዩን ወደፍርድ ቤት ለመውሰድ አንፈልግም ብለዋል። ፎረም ፎር ዴሞክራቲክ ቼንጅ የተባለው ቢሲጌ የሚመሩት ፓርቲ በርካታ አባላት ምርጫው የተጭበረበረ መሆኑን የሚያረጋግጡ ማስረጃዎች ሰብሰው ለፍርድ ቤት ሊያቀርቡ በሚዘጋጁበት ወቅት በድንገት በኡጋንዳ የጸጥታ ኃይሎች በቁጥጥር ስር መዋላቸው ይታወቃል። በርካታ ታዛቢዎች ምርጫው ማጭበረበር የበዛበት፤ ገለልተኛነት እና ግልጽነት የጎደለው፤ ከፍተኛ ማስፍራራትና የኃይል እርምጃ የነበረበት በመሆኑ ተአማኒነትና ተቀባይነት አይኖረውም ብለዋል።
 •   በተለያዩ የአፍሪካ አገሮች የተሰማሩት የተባበሩት መንግስታት የሰላም አስከባሪ ኃይል አባላት በሴቶች ላይ የሚፈጽሟቸው አስገድዶ የመድፈርና ሌሎች አስከፊ ተግባሮች እየተባባሱ መሄዳቸውን በዚህ ሳምንት የተሰራጨ አንድ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዘገባ ገለጸ። እንደአውሮፓውን ዘመን አቆጣጠር 2014 ላይ በተመድ የሰላም አስከባሪ ኃይሎች የተፈጸሙት ወንጀሎች 52 የነበሩ ሲሆን በ2015 ዓመተ ምህረት ይኸው ቁጥር ወደ 69 ከፍ ብሏል። ወንጀል ፈጻሚዎቹ ወታደራዊ መኮንኖች የዓለም አቀፍ የፖሊስ ኃይሎች እና ሌሎች ሰራተኞች እንዲሁም በፈቃደኛነት አለክፍያ የሚሰሩ ሰራተቾች ያሉትበት ሲሆን የመጡትን እንደፈረንሳይ ከመሳሰሉ የአውሮፓ አገሮችና ከሌሎች የአፍሪካ አገሮች ነው።

 •   የግብጽ የፀጥታ የጸጥታ ኃይል አባላት በዜጎች ላይ የሚያካሂዱት ድብደባ፤ እስራትና አለፍርድ ግድያ ከጊዜ ወደጊዜ እየተባባሰ የሄደ ሲሆን ማንነታቸውን በደበቁ የጸጥታ ኃይሎች እየተጠለፉ በድብቅ የሚገደሉ ዜጎች ቁጥርም እየጨመረ መጥቷል ተብሏል። በቅርቡ ቢኒ ሱኤፍ በምትባል በግብጽ ደቡባዊ ክፍል በምትገኝ ከተማ ጭንብል የለበሱ ፖሊሶች አንድ ስራው መሀንዲስ የሆነ ግለሰብን ከስራው ቦታው ወስደው ከአስራ አምስት ቀን በኋላ በመትረየስ ረሽነው የገደሉት መሆኑ ታውቋል። በግብጽ ውስጥ የፖሊሶች ስልጣን አደብ እያጣ መምጣቱና አሳሳቢ ደረጃ ላይ መድረሱን በርካታ ሰዎች የሚናገሩ ሲሆን የሕዝብ በደል እየተበራከተ ከመጣ ወደ አመጽ ሊያመራ የሚችበት መንገድ ሰፊ መሆኑን ይጠቅሳሉ። በጭለማ ዜጎችን ከየቤታቸው በማፈንና በቀን ከቤተሰቦች ጋር ፈላጊ ሆኖ መገኘት የወያኔ የጸጥታ ኃይሎች ገና ወደ ስልጣን ሲወጡ የተካኑበት ስልት መሆኑን ብዙዎቹ ያስታውሳሉ።
 •   
 • ለረጅም ዘመናት በሱዳን የፖሊቲካ መድረክ ላይ ታውቂ የነበሩት ሀሰን አልቱራቤ ቅዳሜ የካቲት 26 ቀን 2008 ዓም በልብ ድካም ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል። አልቱርቤ ሙስሊም ብራዘር ሆኦድ የተባለው የሱዳን የፖሊቲካ ቡድን መሪ በመሆን ለረጅም ጊዜ የቆዩ ከመሆናቸው ባላይ ከ27 ዓመት በፊት የአሁኑ ፕሬዚዳንት በሽርን ወደ ስልጣን ያመጣውን መፈንቅለ መንግስት የጠነሰሱና በተግባር ያዋሉ ናቸው በማለት ይነግርላቸዋል። ይሁን እንጅ ከጊዜ በኋላ ከበሽር ጋር በነበራችው ቅራኔ ከስልጣን መገለልና እስራት የደረሰባችው መሆኑ ይታወቃል። ቱራቤ የኢትዮጵያ ወዳጅ እንዳልነበሩም ይታወቃል። 

No comments:

Post a Comment