Thursday, March 17, 2016

ኢትዮጵያ ውስጥ የተፋፋመው ሕዝባዊ እምቢተኝነት ግቡን እንዲመታ! ( የፍኖተ ራዲዮ ሀተታ )


ኢትዮጵያ ዉስጥ የተቀጣጠለ ያለው ሕዝባዊ እምቢተኝነት የድርጅት፣ የአንድነትና የአመራር ያለህ ይላል።
ለትዉስታ ያህል 1997 . የነበረውን ክስተት ማስታወስ አሁን ላለንበት ታሪካዊ ዕራፍ ይጠቅማል።  በ1997 ዓም የኢትዮጵያ ሕዝብ በተለይም የአዲስ አባባ ሕዝብ በነቂስ ወጥቶ ቅንትንና ህብረትን ሲመርጥና ወያኔን አሥር ለባዶ ዘርሮ ሲያልፍ  በሁኔታው ያልተደሰተው በጠራራ ፀሓይ ቆፈን ይዞት የተንቀጠቀጠው ወያኔ ብቻ መሆኑን ናስታውሳለን። ቀጥሎም ድምጻችን አትሰርቁም በማለት ከወያኔ አጋዚ ጦር ጋር ግብግብ ሲገጥምና የሚቆጠር ዜጋ ሲታሰርና ወደ ሁለት መቶ የሚሆኑ ወጣቶች ሲገደሉ ከደሙ ንጹህ ነኝ  ያሉ ክፍሎች በርካታ ነበሩ። እየጋመ የመጣው እንቅስቃሴም የወያኔን የጎሳ ካርድ አቃጥሎ በምትኩ ኢትዮጵያንና ኢትዮጵያዊነ ከፍ ከፍ በማድረጉ ወያኔ ቅስሙ ተሰበረ ባዕዳን ደነገጡ የወያኔ ድጋፊም ብርክ ያዘው ሻቢያና ኦነጎች ከሩቅ አረገዱ።  አንጻሩም የተፋፋመዉን የትግል ስሜት ተጠቅሞ ወያኔን ለማስወገድ ይችል ዘንድ የተጠናከረ ባዊ ኅይል ባለመኖሩ ለአጋዚው ጦር ባለቤት ለሆነው ወያኔ ሲሳይ ሁኖ ቀረ።  በመሆኑም ከተማይቱ ጭር አለች። ወገን አንገቱን ደፋ። ይህ ነበር ሃቁ።  የተቃዋሚ መሪዎች የተባሉት ደግሞ ከፊሎቹ የወያኔ የውስጥ አርበኛ ሆነው ሲያገለግሉ፤ ከፊሎቹ ከሕዝብ ጀርባ ከባዕዳን ጋር ሲያሴሩ ግማሾቹ ተስፋ ቆርጠው ለወያኔ ዕጃቸውን ሲሰጡ የተወሰኑት ደግሞ 5ቱን ቀን የሙት ከተማ ተቃዉሞ በማክሸፍ ለሟቹ ስና በረከት ስምኦን የእጂ መንሻ ረጉት።  ዛሬም ቢሆን የተቃዋሚው ክፍል ካለፈው ስህተት ተምሮ ዕነኚህ  ሕዝብን በማንቃትና በማደራጀት ለወሳኙ ክፍል ሲያዘጋጀው እያየን አይደለንም  ዕዉነቱ ይነገር ከተባለ ደግሞ ወያኔ ሆዳሞችን ሁሉ በዘር ፖለቲካ እየቃኘ ወደ ድርጅቶች አሰርጎ በማስገባት እያንዳንዱን ድርጅት አቅመቢስ ሽባ እንዳደረገው ግጥም አድርገን እናዉቃለን። 
በሰላም መታገል፤ በወያኔ ሕግና ደንብ መሰረት ኮሽታ ሳያሰሙ፣ ጸጥና ለ ብሎ መገዛት እንደ ትግል ዘዴ መወሰዱም ይታያል  በአገር ክህደት ወንጀል ፍርድ-ቤት መቆምና መቀጣት ያልበትን ወያኔ የኢትዮጲያ መንግስት ነው ብሎ ሕጋዊ ሽፋን መስጠቱ  በአገርም በሕዝብም ያስጠይቃል እንላለን 
አገሬ ኢትዮጵያ ሞኝ   ተላላ 
የሞተልሽ ቀርቶ የገደለሽ በላ  እንዲሉ ኢሕአፓም በተወለደባት ብቻ ሳይሆን በሞተላት እናት አገሩ በነጻ እንዳይንቀሳቀስ በወያኔ ቀጭን ተእዛዝ ተከልክሎ ትግሉን በህቡዕ ለማጠናከር የሚችለውን እያደረገ ነው። ወያኔ ኢሕአፓ በአገሩ ላይ በይፋ እንዳይንቀሳቀሰ ያገደው  በእናት አገሩ አንድነት፣ ብሔራው ጥቅምና ዳርድንበሯ ላይ የማይደራደር መሆኑን በማወቁ ነው ዛሬስ ከ11 አመት በኋላ ምን ዕያየን ነው?
ዛሬም ዕንደትናንቱ፤ ዕንደ 1997ቱና ዕንደ 1966ቱ፤ በተመሳሳይ ያዉም በበለጠ በአገራችን ኢትዮጵያ ዉስጥ ከባድ የሆነ የለዉጥ ነጎድጓድ ዕየተሰማ ነው። የለውጡ ጠረን አገሪቱን አዉዷል! ዜጎች በየአሉበት አጭር የወያኔን የኅይወት ታሪክ ለመጬረስ ዕየተጠራሩና ዕየተናበቡ ትግላቼውን ቀጥለዋል። ስራዓቱም በዉስጥና በዉጭ ቅራኔዎች ተወጥሮ ሊፈነዳ ቀኑን ዕየቆጠረ መሆኑም ኃቅ ነው። ወያኔም በፍርሃት ሲናጥ፣ ሲንቀጠቀጥና ብርክ ይዞት ዕያየነው ወደታች ሲወርድና ሲሰጥም ዕየታዘብን ነው። በአንጻሩ ደግሞ  ወጣት ወንዱ ፣ ሴቱ   አዛዉንቱና ጎልማሣው ሁሉም በመነሳት በወያኔ ላይ አሻፈረኝ ማለቱና የፍርሃት ድባቡን  ሰብሮ ይቻላል ማለቱን ስናይ ልባችን በሃሴት ይሞላል! ኅሊናችን ይታደሳል! ተስፋችንንም ሰንቀን ለማይቀረው ፊልሚያ በወኔና በጋለ የትግል መንፈስ ዓለና ዕንላለን!! 
 በርግጥም ለሁሉም ጊዜ አለው፤ ልቡ ያበጠው ወያኔ በፍርሃት ሲርድ፣ በፍርሃት ይታማ የነበረው ሕዝብ ደግሞ ዕምኝ፣ አሻፈረኝ በማለት በወያኔ ላይ ሲያምፅና ሳንጃ ሲሰነዝር፤ ለማየት በቅተናል።  በየአድባባዩ ዕየወጣ መንገድና በሮችን ዕየዘጋ ወያኔና ግብረአበሮቹን መዉጫ መግቢያ ሲያሳጣቼውና ሲያርበደብዳቸው ከማየት የበለጠ ደስታ ካለ በይደር የምናየው ይሆናል ማለት ነው።          
በአጭሩ ወያኔ ስካሁን ድረሥ ይገዛ በነበረው መንገድ መቀጠል ከማይችልበት ደረጃ መድረሱና ሕዝቡም በስራዓቱ ላይ መነሳሳቱ ሥር-ነቀል የስራዓት ለውጥ ለመገላገል ኢትዮጵያ ምጥ ላይ መሆኗን ነው የሚያሳየው ማለት ነው። ይባስ ብሎም፣ ከእንቅርት ላይ ጄሮ ደግፍ ዕንዲሉ፣ በራሱ በወያኔና በተለጣፊ ድርጅቶች መካከል የጦዘው ሽኩቻ፤ ውጥረትና ትርምስ.፤ በራሱ በወያኔ ዉስጥ ያለው መረን የለቀቀው ቀውስ ጣራ መንካቱንም ጨምሮ  በሃገሪቱ ዉስጥ ያለጥርጥር የስርነቀል ለዉጥ መፈንዳቱ አይቀሬ መሆኑ ሃቅ ነው
ምንም ተባለ ምን፣ ዛሬ በአገራችን ኢትዮጵያ ዉስጥ እንደ ቋያ ዕሳት ዕየተቀጣጠለ ያለው ሕዝባዊ መነሳሳት በወያኔና ስራዓቱ ላይ ያነጣጠረ ለመሆኑም ክርክር አያሻዉም፣ ጥያቄ ዉስጥ መግባትም የለበትም።  ከታች ከቀበሌ ጀምሮ  እስከማዕከሉ ድረሥ በተዋቀረው ስርዓትና ሥርዓቱንም በሚያስኬዱ የቀበሌ ሹሞች፣  ካድሬዎች፣ ፖሊሶች፣ አጋዚ ጦር፤ ሰላዮችና ሃብት ነብረታቸው ላይ በቀጣይነት እየተወሰደ ያለው ርምጃ የሚያመላክተው ሌላ ሳይሆን ጸረ-ወያኔነትና ጸረ ስራዓቱ መሆኑን ብቻ ነው። በመሆኑም ይህ የተጄመረው ሕዝባዊ መነሳሳት ዓላማውን እንዳይስት፣ ማለትም የታለመለትን ግ ዕንዲመታ ከተፈለገ ደግሞ ሦስት አብይ ጉዳዮችን ግንዛቤ ዉስጥ ያስገባ፤ በአይነቱ፣ በስፋትና በጥልቀቱ ሁለገብና ኢዮጵያዊ የሆነ ብሄራዊ ስምምነት የግድ ይላል።  ዕነርሱም ሕዝዊ አንድነትን ማረጋገጥ፣ የፖለቲካ ድርጅቶች ሕብረትን መፍጠርና በቡድንም ሆነ በተናጠል ዕየተንቀሳቀሱ የሚገኙ ዜጎችን ሁሉ ያካተተ አንድ ሰፊ የትግል ማዕከል መፍጠር ናቼው። ይህ ብሄርዊ ስምምነት፣ በተሰጣጠረ መልክ ዕየተካሄደ ያለውን ሕዝባዊ ዕንቅስቃሴ መልክ አሲዞ፣ አቅጣጫ ሰጥቶ፣ ወያኔን ድቫቅ የመምታትና በስራተ ቀብሩ ላይም ሕዝባዊ ስራዓትን የመገንባት ሃላፊነት፣ መብትና ስልጣን ተክሞ ይጓዛል ማለት ነው።፡ አገር ወዳድ ድርጅቶችን፣ ልዩ ልዩ ሕዝባዊ ተቋማትን፣ ቡድንና ተራማጅና ታዋቂ ዜጎችን ያካተተ በመሆኑም በቀጣይነት መቋቋም ለአለበት ሰፊ የሽግግር መንግስት ምስረታና ቋሚ መንግስት ለማዋቀር ለሚደረገው ዝግጂት ሁሉ ብሄራዊ ዕርሾ ሁኖ ይቀጥላል ማለት ነው።  በመሆኑም ትግሉንም አቅጣጫ የመስጠትና በሂደትም ያልተካተቱትን የህብረተሰቭ ክፍሎች ሁሉ በእግረ-መንገዱ ዕየደመረ ሙሉ ኢትዮጵያዊ ገጽታና ይዘት ይዞ ዳር-ድንበሯን የአስጠበቀች ኢትዮጵያን፣ ዜጎች በሰላም፣ በነጻነት፣ በእኩልነትና በመከባበር የሚኖሩባትን አገር ለመመስረት የሚታገልና የሚያታግል ልዕለ-ኃይል ሁኖ ይወጣል ማለት ነው።
መነሻውን አውቆ፣ ጉዞውን አቅዶ፣ ግቡን ሳይስት ሕዝብን የድል ባለቤት ማድረግ የሚቻለዉም በተያያዘና ዕርስ በራሱ ዕየተናበበ በሚካሄድ የትግል ሰንሰለት ሲያያዝ ነው ማለት ነው።ህም ይሳካ ዘንድ  በአመኑበት ጸንተው፣ ለዕናት አገራቼውና ወገናቼው ሲሉ ሂወታቼዉን መስዋዕት ለማድረግ ቆርጠው ከተነሱ የቁርጥ ቀን ልጆች ብዙ ይጠበቃል።
ሌላው በአገራችን የሚገኙ የሲቭል፣ የሙያ፣ የሴቶችና የሃይማኖት ተቋማትና ማህቨራትን ሚና ይመለከታል።  ዕነኝህ ተቋማት በሂደት መቋቋም ለአለበት የሕዝብ አንድነት፣ የፖለቲካ ድርጅቶች ህብረትና ማዕከል ዋና ክፍል ሁነው ይዋቀራሉ ማለት ነው።  ብሄራዊና ታሪካዊ ግዳጃቼውን ለመወጣትም  በራሳቼው አነሳሽነት በውጭም በዉስጥም መንቀሳቀስ ያለባቼው ዛሬ ነው። አንደኛ በስራ፣ በሙያ፣ በሞራልና በዕምነት ዙሪያ የተሰባሰቡ በመሆናቼዉ የጠቅላላው ሕብረተሰብ የባህል፣ የሰነ-ልቦና፣ የወግ-ማዕረግና ማህበራዊ ግንኙነቶች ሁሉ ድምር ወጤቶች ናቼው ለማለት ይቻላል። ሁለተኛ በዕጾታ፣ በሥራ፣ በሙያና በሃይማኖት ዙሪያ የተደራጁ በመሆናቼው ለወያኔ የዘር፣ የጎሳና የቋንቋ ፖለቲካ ፍልስፍና ሳይሆን ለህብረብሄርዊ ድርጅቶችና ለብሔራዊ ትግሉ ቋሚ የሞራል፣ የቁሳቁስ፣ የገንዘብና የሰው ኃይል ምንጮች ሁነው የቅጥላሉ ማለት ነው።  በመሆናቼዉም በሂደት መፈጠር ለአለበት ማዕክልና በተዋረድ መፈጠር ለአለባቼው የትግል ማዕከሎች ሁሉ የደም ስርና ዕስትንፋስ በመሆን ብሄራዊና አገራዊ ሕይወት ሊሰጧቼው ይገባል ማለት ነው። ይህ ብቻ ሳይሆን ሕዝባዊ ትግሉ መልክ ኑሮት ሕግና ስራዓትን ጠብቆ ከሓዲዱ ሳይወጣ ታሪካዊ ተልዕኮውን ይመታ ዘንድ የትግሉ ዋልታና ማገር የመሆን አቅማዉም የሚናቅ አይደለም።  ሕዝቡ በየአለበት የራሱን አመራርም ሆነ የጎቨዝ አለቃ ዕየመረጠ ትግሉን በያለበት አጠናክሮ ይጓዝ ዘንድም በዕየርከኑ ለአለው ሕዝባዊ ዕንቅስቃሴም ድርጅታዊ ቅርጽ፣ የአስተዳደር ደንብና አመራርን በመስጠት ሊጫወቱ የሚችሉት ሚና ቀላል አይደለም። 

በአጠቃልይም  ይህ ትግል በግብር ይውጣ የተጄመረ ሳይሆን ለአለፉት 25 አመታት ተጠራቅሞ የቆየው ብሶት የወለደው የትግል መንፈስ መሆኑን ዕሳቤ ዉስጥ ያስገባ ታክቲክና ስትራቴጂ ነድፎ የሚንቀሳቀስ ጠንካራና ሁለገብ አመራር መፍጠር ለነገ የማይባል የቤት ሥራችን ነው።  ተልኮዉም የወያኔን ሰላዮች፣ አቅመ-ድሃ ካድሬወቻቸውንና በአጠቃላይ በአገር አቀፍ ደረጃ ያለዉን አፋኝ  መዋቅራቸውን ሁሉ ከጥቅም ዉጭ ማድረግና በወያኔ ስራአተ-ቀብር ላይ ሕዝባዊ፣ አገራዊና፤ ዴሞክራሲያዊ ስርአትን መገንባት ይሆናል ማለት ነው።  ትግሉ አቅጣጫውን ስቶ የዘረኞችና የጸረ-ኢትዮጵያ ኃይሎች ሲሳይ ከመሆን ሊድን የሚችለውም ሃላፊነት በሚሰማውና በሳል በሆነ አካል ሲመራ ብቻ መሆኑም ሊሰመርበት ይገባል።    

No comments:

Post a Comment