Thursday, March 3, 2016

ሀገርን ከውርደት ለማዳን ተደራጅተን እንታገል። EPRPYL

EPRPYL
EPRPYL
የኢትዮጵያ ሕዝባዊ አብዮታዊ ፓርቲ ወጣት ክንፍ ድርጅተ (ኢሕአፓ ወክንድ) Ethiopian Peoples Revolutionary Party Youth League (EPRP YL) 

ሀገርን ከውርደት ለማዳን ተደራጅተን እንታገል

የሀገር ተረካቢና የታሪክ ባለቤት የሆነው ወጣት ትውልድ ለሰብዓዊ መብቱና ለሀገሩ ካልታገለ ሁለቱንም ማጣቱ የማይቀር ነው። ሀገርም ሆነ መብት የሚከበረው በእያንዳንዱ ሀገር ወዳድ ዜጋ ነው። ያለፉት ወጣቶች እንደቀድሞ አባቶቻቸውና እናቶቻቸው በደማቸውና አጥንታቸው የሀገራቸውን ነፃነትና ከብር ላለማስደፈር መስዋዕትነት ሲከፍሉ ለመቆየታቸው ታሪክ በሰፊው የመዘገበው እውነታ ነው።
ዛሬ በኢትዮጵያ ሰፍኖ ያለው አጠቃላይ ሁኔታ ለሁሉም ግልፅ መሆኑ የሚያከራክር አይደለም። በዘረኝነት የተቃኘ ለቡድናዊ ጥቅሙ እንጂ ለኢትዮጵያ መልካምን የማይመኝ በሚያከናውነው ተግባር ሁሉ ኢትዮጵያን ወደ ጥፋት ጎዳና እየመራ ያለ ጎጠኛ፣ አምባገነናዊና ዘራፊ ቡድን ነው። ዛሬ ኢትዮጵያን እየገዛ ያለው የሕዝብን መብት ረግጦና ደፍጥጦ አገርንና ህዝብን ሸንሽኖ ለባእዳን ጥቃት አጋልጦ የሀገሪቷን አንጡራ ሀብት ውሀና መሬቷን ሳይቀር ለባእዳን እየቸበቸበ ከቀን ወደቀን በፀረ ህዝብ ፀረ ኢትዮጵያ አፍራሽ ተልእኮውን እየገፋ የሚገኝ አጥፊ ቡድን ነው።
ይህንን ዘረኛና አምባገነናዊ አገዛዝ ለማስወገድ የተደራጀ ህዝባዊ ትግል አስፈላጊ መሆኑ ለእኛ ለኢወክንድ ዓባላት ግልፅ ከሆነ ቢያንስ ድፍን አምስት ዓመታት አስቆጥሯል። እኛ የኢወክንድ ዓባላት ለምን ማንንና እንዴት መታግል እንዳለብን ጠንቅቀን የተረዳነው ገና ከፍጠረታችን መሆኑንንም ግልፅ ማድረግ እንወዳለን። ፍትህና ርትዕ በሌለበት ጭቆናና ብዝበዛ በሰፈነበት ሥርዓት ያለ ህዝባዊ ትግለ ድል ያለ ትግል መብትን ማስከበር እንደማይቻል የተረጋገጠ ነው።
የኢትዮጵያ ሕዝብ ማህበራዊ ፍትህን ለማምጣት ከፍተኛ መስዋዕትነትን ቢከፍልም አሁንም የመብቱ ባለቤት ሆኖ ነፃ በሆነ መንገድ ራሱን በራሱ ሊያሰተዳድር መሪዎቹን ሊመርጥ ወይም ሳይፈልጋቸው ደግሞ ከሥልጣን ሊያስወግዳቸው የሚችልባቸው ሁኔታዎች አልተፈጠሩም። የህግ የበላይነት አልሰፈነም። ዴሞክራሲያዊና ሰብአዊ መብቶቹ አልተከበሩም። በድህነት ረሃብ ድንቁርናና በሸታ እየማቀቀና ው። በሥልጣን ላይ ያለው ጠባብ ብሔርተኛ ቡድን በሚያራምደው የጎሳ ፖለቲካ ምክንያት ከተወሰኑ ብሔረሰቦች በመወለዳቸው ብቻ ወይም በፖለቲካ አቋማቸው የተነሳ በገፍ ከሥራ የሚባረሩበት አርሶ አደሩና ሠራተኛው ህዝብ እንዲሁም ሌሎች የህበረተሰብ ክፍሎች ለረዥም ዘመናት ከሚኖሩበትና ከተወለዱበት አካባቢ በግድ እንዲለቁ/እንዲፈናቀሉ የሚያደርገው ኢሰብአዊ እርምጃ እንደቀጠለ ነው።
የሀገሪቱ ዜጎች ከቦታ ወደ ቦታ ተዘዋውረው የመስራት/የመኖር መብት አገዛዙ በዘረጋው ዘረኛ የጎሳ ክልል ጨርሶ የማይታሰብ ሆኗል። አንዱ ብሔር/ ብሔረሰብ በሌላው ላይ እንዲነሳ የሚደረገው ግፊት ሀገሪቱን ከምንጊዜውም በላይ አስከፊና አደገኛ ሁኔታ ላይ ጥሏታል። ወያኔ በሀገር ውስጥም ሆነ በውጪ ያሉ ዲሞክራሲያዊ ሀይሎች በሀገሪቱ ፖለቲካ በነፃ የመሳተፍ መብት ከመንፈጉም ባሻገር የመጻፍ የመናገር ሃሳብን በነፃ የመግለፅና መደራጀት የሞከሩ ኢትዮጵያዊያን ሁሉ መጨረሻቸው እስራትና ግድያ፣ አፋናና ስቃይ መዳረግ የዕለት ተለት እጣ ፋንታቻው ከሆነ ዓመታት አስቆጥረዋል። ሃሳባቸውን በሰላማዊ ሰልፍ ለመግለፅ የሚወጡ ዜጎቻችን ምላሽ ጥይት ከሆነ ሰንብቷል። በዓለም የፕረስ ተቋሟት እየተወገዘ ያለው ጭራቃዊ የፕረስ ህግ አልበቃ ብሎ ሃሳብን በነፃ መግለጽ ጭራሺ አሸባሪነት ሆኗል። ህጉ እንዲህ በከፋ ሁኔታ የፕረስ መብትን በማፈኑ ወያኔ የነፃውን ፕረስ ዓባላት በመግደል በማሰቃየትና የስልኮቻቸውን መስመር በመጥለፍ የሚታሰሩና የሚሰደዱት ቁጥራቸው በርካታ ነው። ይህ ቁጥር ከዓለም ህዝብ ብዛት አንድ ሦስተኛውን ከያዘችው ቻይናና ከሰሀራ በታች ካሉ የአፍሪካ አገሮች በሙሉ ከታሰሩ ጋዜጠኞች ቁጥር የሚበልጥ ነው።
ወያኔ በሙያና በሠራተኛ ማህበራት እንዲሁም በሰብአዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶችና ተቋማት ላይ እያደረገ ያለው እንግልትና አፈና ከምንጊዜውም በበለጠ እተባባሰ መጥቷል። ለመምህራን መብት ይታገል የነበረውን ኢመማንና የሠራተኛው መብት ጠበቃ የነበረውን ኢሠማኮን በማፈራረሰና በዘር መሰፈርት የራሱን ተለጣፊ በመተካት በመምህራንና በሰራተኛው ላይ የሚደርሰውን በደልና እንግልት የሚያሰሙት የሙያና የሲቪክ ተቋማት ታፍነው እንዳይንቀሳቀሱ ከተደረገ ዓመታት አልፈዋል።
ወያኔ ዛሬም ከፖለቲካ ፓርቲዎች፣ ከሙያና ከሠራተኛ ማህበራት እንዲሁም ከሲቪክ ድርጅቶች ባሻገር ሃማኖትን ለዘረኛ ፖለቲካው ግብ ለመጠቀም በክርስትናና በእስልምና ሀይማኖት ተከታዮች መካካል ክፍፍል፣ ጥርጣሬ፣ጥላቻና ፍራቻ እንዲነግስ ካድሬዎቹንና የፀጥታ ተቋማቱን በሰፊው እያንቀሳቀሰ ይገኛል። በህዝብ ላይ የተጫነ የሥልጣን ልጓሙን ጨብጦ ከላይ ተሰይሞ ሲሻው የሚገድል ሲያሰኝው የሚያሰርና የሚያግዝ ከህዝብ ተነጥሎ የቆመ የማይከሰስ የማይገረሰስ ፍጡር ሆኖ ዓመታት አስቆጥሯል። ይህም በህዝብና በወያኔ መሀል ያለው ግኑኝነት የገዥኛ የተገዥ/ የጌታና የሎሌ ነው ተብሎ የተደነገገ አስመስሎታል።
የወያኔ ፖሊሲና አካሄድ በዴሞክራሲያዊ የአንድነት ሀይሎች ትግል ካልተገታና በዚህ መልክ የሚቀጥል ከሆነ ኢትዮጵያ እንደሀገር ህልውናዋን ልታጣ የምትችልበት ጊዜ ሩቅ ሊሆን እንደማይችል መገመት አያስቸግርም። ኢወክንድ የኢትዮጵያን የመበታተንና ህዝቧን ለዕርስ በርስ እልቂት እያዘጋጀ ያለውን የወያኔና ባዕዳን ደጋፊዎቹን ሴራ አጥብቆ ይቃወማል። ሁኔታውም በተደራጀ ህዝባዊ ትግል መለወጥ አለበት። ብልጭ ድርግም እያለ በይፋ የሚካሄደውን ትግል በህቡዕ ተደራጅቶ ሰፊ መሠረትና ቀጣይነት ባለው እንቅስቀሴ መታጀብ ይኖርበታል ብሎ በፅኑ ያምናል ።
ኢሕአፓ ወክንድ ድርጅቶች በተለይም ለትግል በተግባር የተሰማሩት ሀይሎች ህዝባዊ ትግሉን አንድ እርክን ከፍ ለማድረግ ለውጥ ፈላጊውንና የህበረተሰቡ አንቀሳቃሽ የሆነውን የሆነውን ወጣቱን ትውልድ በማደራጅት በኩል ከፖለቲካ ፍጆታ ያለፈ በተግባር የሚጠበቅባቸውን ሚና መወጣት ይኖርባቸዋል ብሎ ያምናል። ትግል በየፈርጁ ካልተፋፋመ የተለያዩ የህብረተስብ ክፍሎች ካልተደራጁና በትግሉ በተግባር ካልተሳተፉ ድርጅቶች አይጠናከሩም ድርጅት ካልጠነከረ ደግሞ የሕዝብ ትግል መሳሪያ/ ክንድ ላልቷል ማለት ነው።
ጉዟችን ከአዙሪት የሚወጣው በመስዋዕትነት መሆኑም ይታያል። ዛሬ ያለንበት የትግል ወቅት ጊዜን እውቀትንና የገንዘብ ሀይልን የሚጠይቅ ነው። ሀገር ማዳን ከባድና መራራ ነው። ለዓላማ ፀንቶ መቆምን፣ በተግባር በትግል መሰማመራትና የድርጅት አቅምን መገንባት ይጠይቃል። ብሎም እያንዳንዱ ዜጋ የበኩሉን አሰተዋጽዖ ማድረግ ይገባዋል።
የኢትዮጵያ ሕዝብ የሀገሩን ዳር ድንንበር ነፃነቱንና አንድነቱን ጠብቆና አስከብሮ ለማቆየት ሲፈፅመው የኖረ ከትውልድ ወደ ትውልድ ሲተላለፍ የመጣ አሁንም ያለና ወደፊትም የሚቀጥል የኢትዮጵያውያን የጀግነነት ተግባር ነው ። ለዚህ ክቡር ዓላማና ተግባር እውን መሆንና የላቀ 

መሰዋዕትነት ለመክፍል ኢሕአፓ ወክንድ ዝግጁነቱን ያረጋግጣል።
በተጠናከረ ትግልና መስዋዕትነት መብታችንንና ክብራችንን እናስመልስ 

Tel: 202-291-5832
5309 Georgia Ave. NW 2nd Fl. Washington DC 20011
E-mail: eprpylnew @gmail.com
Website: www.eprpyl.com

No comments:

Post a Comment