Tuesday, March 8, 2016

Finote Democracy Voice of Ethiopian Unity Satellite Radio News የካቲት 28 ቀን 2008 ዓ.ም.ዜና (March 07, 2016 NEWS)

Finote Democracy Voice of Ethiopian Unity Satellite Radio News
የካቲት 28 ቀን 2008 ዓ.ም.ዜና (March 07, 2016 NEWS)
Ø በአዲስ አበባ የተጀመረውን በሌሎች የኢትዮጵያ ከተሞች የተካሄደው የታክሲዎች የሥራ ማቆም አድማ በዛሬው የካቲት 28 2008 ዕለት በጎንደር ውስጥ በጋይንት መደረጉ ታውቋል። የታክሲ ሹፌሮች አድማ በጋይንት ያለውን ትራንስፖርት ሙሉ በሙሉ የገታውና ያቆመው መሆኑ ሲታወቅ እጅግ ብዛት ያለው የወያኔ ፌዴራል ፖሊስ ውስጥ ወደ ዓለም በር በመግባት አካባቢውን የጦር ሠፈር አስመስሎት ይገኛል። የጎንደሩ የወያኔ የጸጥታና የፍትህ ቢሮ በመደናገጥ ከባህር ዳር ተጨማሪ ኃይል በመጠየቁ ዛሬ ማምሻውን ስምንት ከባድ ካሚዮኖች ልዩ የወያኔ የፖሊስ ኃይል ጭነው ዓለም በር እንደገቡ ከጋይንት የመጣው መረጃ አመልክቷል። ከዚህ በተጨማሪ የታክሲ ሾፌሮች የሥራ ማቆም አድማ በሌሎች የጎንደር ከተሞች በክምር ድንጋይና በደብር ታቦርም መደረጉ ተረጋግጧል። የፖሊቲካ ታዛቢዎች በየከተሞቹ የሚደረገው የተጠናጠል የሥራ ማቆም አድማ ወያኔን ጊዜ የሚሰጠውና ነጥሎ ለማጥቃትና ለመምታት የሚያመቸው በመሆኑ አንድ አጠቃላይ የሥራ ማቆም አድማ በማድረግ አገዛዙን ሽባ ማድረግ የማይታለፉ የትግል ስልትና ዘዴ መሆን ይገባዋል ይላሉ።
Ø የአዲስ አበባው ሲኖዶስ ያደረገውን ድንገተኛ አስቸኳይ የቋሚ ሲኖዶስ ጉባዔ በዛሬው ዕለት አጠናቅቆ መግለጫ ያወጣል ተብሎ ይጠበቃል። በቋሚ ሲኖዶስ እና በፓትሪያርኩ መካከል ከፍተኛ የሆነ የአሰራርና የሃሳብ ልዩነት ያለ ሲሆን ቋሚ ሲኖዶሱ አቡነ ማትያስ በማኅበር ቅዱሳን ላይ ያስተላለፏቸው መመርያዎችና የጠሯቸው ስብስባዎች ሁሉ ህገ ወጥ ናቸው በማለት የተቻቸው ሲሆን ከእንግዲህ ወዲህ የቤተ ክርስቲያኒቱን መዋቅር ጠብቀው እንዲሰሩና ኃላፊነታቸው እንዲወጡ አስጠንቅቋቸዋል። አቡነ ማትያስ አቤቱታዎችን ለመመልከት በማለት ራሳችው ብቻቸውን የጠሯቸው ስብሰባዎች ያስለፏቸው ውሳኔዎች የአቋም መግለጫዎች በሙሉ ህገ ወጥና ተቀባይነት የሌላቸው ናቸው ተብሏል። ከዚህ በተጨማሪ አቡነ ማትያስ የቋሚ ሲኖዶሱ አባላትን ለማሸማቀቅና ለማስፈራራት ያደረጉት ሙከራና በሠሯቸው ማዕከላዊነት ያልጠበቀ አሰራር አዋረዱን አሳፈሩን ተብለዋል። አቡነ ማትያስ ከልዩ ጽ/ቤታቸው ውስጥ ያለው አሠራርም ቋሚ ሲኖዶሱን እንዳሳስበቸው ገልጸዋል። ፓትርያርኩ ርእሰ መንበር ሆነው አባታዊ ኃላፊነት ከመወጣት ይልቅ ስፖንሰር ተገኘ በሚል ብቻ ጉዞ እንደሚደረግ ጠቅሰው ስህተቱ እንዲታረም ጠይቀዋል። በመጨረሻም አቡነ ማትያስ ህግ አክብረው ከሲኖዶሱ ጋር መክረውና ተነጋግረው እንዲሰሩ በጥብቅ አሳስበዋቸዋል። በአገሪቷ ላይ ስላለው ሰላም ጉዳይ የመከረ ሲሆን የተቃጠሉ ቤተ ክርስያናትን ጉዳይ የሚያጣራ ልዑክ መድቧል። ድንገተኛው አስቸኳይ ስብሰባ በዛሬው ዕለት መግለጫ ያወጣል ተብሎ ይጠበቃል።
Ø በኢትዮጵያ በተለያዩ ከተሞች ሲካሄዱ የነበሩ ሕዝባዊ ተቃውሞችን ለመግታት ተገቢ ርምጃ አልወሰዳችሁም የተባሉ ሁለት የኦህዴድ የማዕከላዊ ኮሚቴ አባላት ከኃላፊነት መነሳታቸው የሚታወስ ሲሆን በወያኔ አስገዳጅነት በሚካሄደው የወያኔ ኦህዴድ ማዕከላዊ ኮሚቴ ስብስባ ሌሎች ተጨማሪ የማዕከላዊ ኮሚቴ አባላት ሊባረሩ ወይም ሊታሰሩ ይችላሉ የሚል ግምት እየተሰጠ ነው። ወያኔ የኦህዴድ አመራር አባላትን አንገት አስደፍቶ ፍጹም ታዛዥ ለማድረግ የሚያካሄደው ስብሰባ በውጥረትና እርስ በርስ በመጠባበቅ በስጋት እየተካሄደ መሆኑ ታውቋል።
‪#‎በተመሳሳይ‬ ዜናም የወያኔው ብአዴን ማዕከላዊ ኮሚቴ አባላት በስብሰባና በግምገማ የተወጠሩ ሲሆን ከፍተኛ የብአዴን ካድሬዎች ከሥራና ከኃላፊነት ሊባረሩ ይችላሉ ተብሏል። የወያኔ መሪዎች የብአዴን መሪዎች ወያኔ ራሱ ያቀጣጠለው የቅማንት ማንነት ችግርን የብአዴን መሪዎች በአግባብ አልያዙም በሚል እየወቀሰ ሲሆን የወልቃይት እና የጠገዴ ወረዳዎችን ወደ ጎንደር እንዲቀላቀሉ ብአዴኖች ውስጣዊ ድጋፍ ሰጥተዋል ተብለው እየተወቀሱ መሆናቸው ታውቋል።
Ø በኢትዮጵያ የተባበሩት መንግስታት የምግብ እና የእርሻ ድርጅት ተወካይ የሆኑት ሚስተር አህማዱ ለሚቀጥለው የመኸር ወቅት መዘጋጃ በርካታ አካባቢዎች ድጋፍ የሚያስፈልጋቸው መሆኑን ገልጹ። የበልግ ዝናም ባለመኖሩ የተጎዱ አካባቢዎች መኖራችውን ጠቅሰው በሚቀጥለው የመኸር ወቅት ዝናም ከመጣ ወደ 7.5 ሚሊዮን የሚሆኑ ቤተሰቦች የዘር እህል ለማግኘትና ከብቶቻቸውን ለመመገብ እርዳታ ያስፈልጋችዋል ብለዋል። ለዚህ እርዳታ የታቀደው 50 ሚሊዮን ዶላር ሲሆን ከዚሁ ውስጥ 13 ሚሊዮን የሚሆን በያዝነው ወር ውስጥ እንደሚያስፈልግ ተገልጿል። ከተፈለገው ገንዘብ እስካሁን አስር ከመቶ እንኳ እንዳልገባ ተጠቅሷል።
Ø የቱኒዚያ የጸጥታ ኃይሎች ከሊቢያ በኩል ወሰን ጥሰው መጥተው ጥቃት ፈጽመዋል የተባሉ 21 የአይሲስ ታጣቂዎች መግደላቸውን አስታውቀዋል። ታጣቂዎች ጥቃቱን የፈጸሙት ቤን ጎርዳኔ በሚባለው ከተማ ውስጥ ባሉ የወታደራዊ ሰፈር ላይ እና ፖሊስ ጣቢያ ላይ ሲሆን በተኩስ ልውውጥም አራት ሰላማዊ ሰዎች የሞቱ መሆናቸው ተጠቅሷል። ባለፈው ሳምንት የአሲስ ኃይሎች ተመሳሳይ ጥቃት መፈጸማቸው የሚታወቅ ሲሆን ከጥቂት ጊዜ ወዲህ ቡድኑ በተከታታይ እያደረሰ ያለው ጥቃት አሳሳቢ ደረጃ ላይ መድረሱን የቱኒዚያ የገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስትር ቃል አቀባይ ገልጿል። የቱኒዚያ መንግስት በወሰን አካባቢ ጥልቀት ያለው ጉድጓድ በመቆፈር የጸጥታ ሁኔታውን ያጠናከረ ሲሆን ወደ ከተማዋ የሚያስገባውን በር በመዝጋትና በከተማዋ የሰዓት እላፊ አዋጅ በማወጅ እርምጃ የወሰደ መሆኑ ተነግሯል ።
#በተመሳሳይ ዜና የሞሮኮ የአገር ግዛት ሚኒስትር ቃል አቀባይ ሰኞ የካቲት 28 ቀን 2008 ዓም በሰጠው መግለጫ ህዝብ የሽብር ተግባር ለማካሄድ ሲያቅዱ ነበር ያላቸውን አምስት የአይሲስ አባላት በቁጥጥር ስር ያደረገ መሆኑን ገልጿል። አሸባሪዎቹ ፕሬሸር ኩከር በመጠቀም በገበያ ቦታዎች ፈንጅዎችን ለማፈንዳት ሲዘጋጁ ተይዘዋል ያለው መግለጫ በሊቢያ በአይሲስ አማካይነት ተጨማሪ ወታደራዊ ስልጠና ለመቀበል እቅድ የነበራቸው መሆኑም ተገልጿል።
Ø በሱማሊያ በላፕ ቶፕ ኮምፒውተር ላይ የተጠመደ ፈንጅ በአውሮፕላን ማረፊያ ፍተሻ ላይ እንዳለ በመፈንዳቱ ስድስት ሰዎች የቆሰሉ መሆናችው ተነገረ። ይህ የአልሸባብ ድርጊት ነው ተብሎ የሚነገርለት ጥቃት የተፈጸመው በለደወይን በሚባለው የሱማሊያ ከተማ ሲሆን የጸጥታ አባላት በተመሳሳይ ጊዜና ቦታ ሌሎች ሁለት ፈንጅዎችን አምከነዋል ተብሏል። ከቆሰሉት ስድስት ሰዎች ውስጥ ሁለቱ ፖሊሶች መሆኑ ታውቋል። ባለፈው ወር የአልሸባብ አባላት በላፕቶፕ ላይ ያጠመዱት ቦምብ በበረራ ላይ በነበረ አውሮፕላን ውስጥ በመፈንዳቱ በአካሉ ላይ የክፍተት አደጋ ተፈጥሮ አውሮፕላኑ በአስቸኳይ ለማረፍ የተገደደ መሆኑ ይታወሳል።
Ø አሌክ ባዴ የሚባሉት የናይጄሪያ የቀድሞ የመከላከያ ሚኒስትር ሰኞ የካቲት 28 ቀን አስር በሚሆኑ የሙስና ክሶች ተከሰው በናይጀሪያ ከፍተኛ ፍርድ ቤት የቀረቡ መሆናቸው ተገልጿል። ባዲህ 19.7 ሚሊዮን ዶላር የሆነ ገንዝብ በማጉደል የተከሰሱ ሲሆን ከክሶች ውስጥ አንደኛው በ2005 ዓም ለአየር ኃይል ከተመደበው በጀት ውስጥ 6.9 ሚሊዮን ዶላር ስርቀው በአቡጃ ውስጥ ከፍተኛ የሆነ የመኖሪያ ህንጻ አስርተውበታል የሚል ነው። በሚቀጥለው ሀሙስ በዋስ የመለቀቅ ማመልከታቸው እስከሚታይ ድረስ ባዲህ በእስር ቤት እንዲቆዩ ፍርድ ቤቱ አዟል። ቀደም ብሎ የአየር ኃይል ሃላፊ የነበሩት ባዴህ የመከላኪያ ሚንትስትር በመሆኑ የተሾሙት በ2006 ዓም በቀደሞ ፕሬዚዳንት ሲሆን ወደ ስልጣን ከመጡ በኋላ የናይጀሪያ ወታደራዊ ተቋም በመሳሪያና በጥይት ችግር ተዳክሞ በቦኮ ሃራም ተከታታይ የሆኑ ከፍተኛ ጥቃቶች ሲፈጸምበት መቆየቱ ይነገራል።
ለዝርዝር ዜናዎች > ከታች ይጫኑ (to read/listen detail news click below)
To read:  http://www.finote.org/news.html
To Listen PART 1:  http://finote.org/March07EVE_Hr1.mp3
To Listen PART 2:  http://finote.org/March07EVE_Hr2.mp3

No comments:

Post a Comment