Friday, April 29, 2016

የ25 አመቱ አጋጅ መሪ / ቢንያም ሙሉጌታ ከኖርዌይ


ወያኔ በቆርጦ ቀጥል የቅንብር መርሁ መሰረት የህዝብን ጥያቄና እሮሮ ከሚፈልገው የበሬ ወለደ ዘገባው ጋር በማዛመድ 25 ለሚያህሉ በአምባገነናዊነት በተሞሉ አመታት በብቸኝነት በተቆጣጠረው የሀገሪቱ ሚዲያዎች፤ በጋዜጣ፣ በራዲዮ፣ በቴሊቪዥን፣ እና በመሳሰሉት የመገናኛ አውታሮች እውነታውን በመደበቅ ህዝብን በማስመረር ይገኛል ይህ ብቻ አይደለም በኢትዮጵያ ሕዝብ ላይ የሚደርሰውን ወከባ የሰብአዊ መብቶች ጥሰት ከመገናኛ ብዙሀን አፈናው ጋር ተደምሮ በተለይም በአሁን ወቅት በተለያዩ የሀገሪቱ ክልሎች ላይ እየተደረገ ያለው አሰቃቂ ድርጊት ለአለም ሁሉ በገሀድ የሚታይ የአደባባይ ሚስጢር ሆኗል።

ነጻ ፕሬስ አልያም በጥቅሉ የመገናኛ ብዙሀን መድረኮች ህዝብን ከመንግስት ጋር እንዲሁም ግልፅነት በተሞላበት አካሔድ የመንግስትን አሰራር ለህዝብ እያቀበለ እያስተዋወቀ መካከለኛ በመሆን  የዜጎችን  አስተያየትና ጥያቄዎች ለሚመራው መንግስትና ለሚመለከታቸው አካላት ሁሉ ማስተላለፊያ ድልድይ ነው፡፡ መንግስትና ህዝብን አገናኝ፣ አስተያየትና ብሶትን መተንፈሻ፣ መፍትሄን መቀየሻ መሳሪያ ነው ፡፡ ነጻ ሚዲያ መልካም ሀሳቦች እንዲጎለብቱ፣ መታረም ያለባቸው ደግሞ እንዲታረሙ መጠቆሚያ ብርቱ ክንድም ጭምር ነው፡፡

ህዝብ ከገዢው  ወገን ትክክለኛ እና ወቅታዊ የሆኑትን መረጃዎን ለማግኘት እጅጉን ከባድ በሆነበት፤ ሒደቶችን  ከዜጋው በመደበቅ አሊያም በመሰወር በሀገራችን ምን እየተከናወነ እንደሆነ  የመገናኛ ብዙሀን አዋቂዎች ሙያቸውን ተጠቅመው  ለመግለጥ የሚያደርጉት ሁሉ ድምፃቸው ታፍኖ ትክክለኛው  የመረጃ ምንጭ ሆነው እንዳይሰሩ በማስፈራራት፤ይልቁንም ደግሞ ታላቅ ግፍ እና ውንጀላ እየተፈፀመባቸው ጋዜጠኞቻችንን እና ፀሀፍቶች በሙሉ ከአሽባሪ ጎራ ተመድበዋል። የህትመት ውጤቶች በእንዲህ አይነት  ውንጀላ መፈረጅ በራሱ በፍርድ የሚያስጠይቅ ጉዳይ ነው።  በእርግጥም ገዢው ፓርቲ  ለፕሬሱ ሆነ ለሚዲያው እድገት መጫዎት የሚገባው የራሱ ሚና ጎልቶ መውጣት በተገባው ነበር፤ ምክንያቱም የፕሬሱ እድገት የሀገሪቱን  አሰራር ዘመናዊ፣ ግልጽና ተጠያቂነት የሰፈነበት የማድረግ ሚናው የላቀ ስለሆነ ማለት ነው፡፡

የወያኔን ከወረቀቱ የማይከብድ  ህገ-መንግስት ተብዬውን ያየነው እንደሆን   ዜጎች በአመቻቸው መንገድ ሁሉ ሀሳብን በነጻነት የመግለጽ መብትን ሰጥቶ እንደገና በተግባር ግን መብቱን በአደባባይ እየጣሰ ይገኛል፡፡ ወያኔ ሌብነቱ መዝበራው ግድያውና ጭቆናው እንዲሁም በራሱ ላይ የሚቀርቡበትን ማናቸውም አይነት ትችት በመፍራት ጋዜጦችን እና መጽሔቶችን ይዘጋል፤ ያግዳል፤ ድህረ-ገጾችንብሎክያደርጋል፤ እንዲሁም ጋዜጠኞችን በተደጋጋሚ ለእስርና ለእንግልት፣ አንዳንዴም ለሞት እንዲዳረጉ በማድረግ የህዝብን መረጃ በነጻነት የማግኘትን መብት በከፋ ሁኔታ እያፈነ ይገኛል፡፡

በአንድ ያደገ ሀገር ብቃት ያለው ህዝብን የሚያገለግል ሚዲያ አለ፤ ህዝብም የመረጃ ነፃነት እንዳለው ያውቃል ይህንንም የሚያስፈጽም መንግሥት አለ። በመሆኑም መንግሥት ህዝብና ሚዲያ በመቀናጀት ብቃት ያለው መረጃ ለህዝብ ያደርሳሉ። እኛ ግን ለዚህ ፈፅሞ አልታደልም!!!

ወያኔ ከሚጠቀምባቸው የማገጃ ስልቶች የመጀመሪያውአዳዲስ ሕጎችን በማውጣት በነጻነት ሐሳብን መግለጽን መከልከል እና እንዲህ የሚያደርጉትንም ማሰር  ነው። ሌላው ደግሞ ሰዎችን በገንዘብ በመደለል ስለ መንግሥታቱ በጎ ነገር (እንዲጽፉ፣ እንዲናገሩ፣ እንዲያሰራጩ) ማድረግ እንዲሁም አሉታዊ ሐሳብ የሚያስፋፉትን ሰዎች ድረ ገጾች በዘዴ በመስረቅ (hijacking and hacking) በስማቸው ተገቢ ያልሆነ ነገር መለጠፍ የሚለው ነው። ይህንንም ዓለም በስፋት እየተጠቀመች ያለውን  ፌስ ብክ አንድ ሰው ከአንድ በላይ አካውንት በመክፈት ብሔርን ከብሔር ጎሳን ከጎሳ በማባላት እና በማጋጨት ደርጃ ወያኔ በዚህ ተልካሻ ስራ ተጠምዶ እንዳለ ግልፅ ነው። ይህም ድርጊት ተግባራዊ የሚሆንበት ወጪ የሚገኝውም ከደሀው  ሕዝቡ  በተነጠቀ ገንዘብ ነው። ማንነታቸው የማይታወቁ ሰዎችን በኢንተርኔት ላይ በማሰማራት የተለያዩ ደጋፊ ሐሳቦችን ማሰራጨት፣ የኢንተርኔት የውይይት አቅጣጫዎችን ማስቀየር፣ ተቃዋሚዎችን በተለያየ መንገድ ማዋረድ እና ክብራቸውን መንካት፣ ስለ ተቃዋሚዎች መሠረት የለሽ አሉባልታዎችን በመንዛት በአደባባይ ስለ ኢትዮጵያቸው እየታገሉ ያሉትን ስም ማበላሸት የወያኔ ዋነኛ እንቅስቃሴ ነው። ይህም ከፍርሀት የሚመጣ መሆኑን ሁሉም ይስማማበትል።

ወያኔ ከ20 ሚሊዩን ህዝብ በላይ  ተርቦ እህል እና ሌሎችም የልብስ የመጠለያ እንዲሁም የመድሀኒት እርዳታ ለማድረግ መረባረብ ሲገባው ከሀዲዎችን ቀጥሮ ለዚህ ሀገር በታኝ ተልዕኮው ማሰማራቱ ምን ያህል ስግብግብ እና ከፋፋይ መሆኑን በግልፅ የሚያሳይ ነው። በኢትዮጵያ ህዝብ ገንዘብ  ከሚሠሩት አፈና ባሻገር የማይደግፏቸውን ጦማርያን፣ የሚዲያ ተቋማት እና የፖለቲካ ፓርቲዎች የኢንተርኔት አድራሻዎች ማለትም ፌስቡክና ትዊተሮችን፣ ድረ ገጾችንና ብሎጎችን በመመዝበርም ይታወቃሉ። ወደ ተቃዋሚዎቻቸው የኢንተርኔት አድራሻዎች ሰብረው በመግባት የማይፈልጉትን ዘገባ፣ ዜና፣ ሐተታ ይለውጣሉ፤ የድረ ገጾቹን ባለቤቶች ሙያዊ ክብር ለማዋረድ እና ተቀባይነት ለማሳጣት የማይሆን ነገር ይለጥፋሉ፤ የሚለዋወጧቸውን -ሜይሎች ያነብባሉ፤ በክስ ወቅትም ለፍርድ ቤት በማስረጃነት የሚቀርቡት በተፈበረኩ የሀሰት ሰነዶች ምክንያት ደብዛቸው የጠፉ ምሁራን እጅግ ብዙ ናቸው። ይህንንም በመፍራት እና በመሸሽ በተገኘው አጋጣሚ ከሀገር ተሰደው በየበረሀውና በባህርም ሰጥመው የቀሩ ዜጎቻችንን ስናስብ በእጅጉ እናዝናለን። ከወያኔ አጋችነት እና አፋኝነት የተነሳ በዓለም ሁሉ የኢትዮጵያውያን አንገት እንዲደፋም ተደርጓል። ይህም የሚያሳየው ኢትዮጵያ ለዜጋ መብት ብሎም  እድገት የቆመ እና የሚታገል መሪ እንደሌላት ያስረዳል።

አጋጁ ማገድ ማንነቱ ነውና ሁሉን ያስራል ሲያሻው ለፖለቲካው መሰሪነት ሲል ይፈታል። በኢትዩጵያ ያልታገደ የለም። ለወያኔ እንቅፋት የሆነ ሁሉ ይያዛል፤ ብዙ የወንበዴ ብዕሮች ለሆዳቸው ያደሩቱ የፈራረሰውን ስርዐት ለመጠጋገን ቢሞክሩም እውነት ሁልጊዜም ትረታለችና ኢትዮጵያን ለ25 ዓመታት የሚመራው አጋጁ መሪ በኢትዮጵያውያን የተባበረ ክንድ ይገረሰሳል።
ኢትዩጵያ ለዘላለም ትኑር!!!
Monday, April 25, 2016

ጉንዳን ሳይገባ አመድ ነስንስ ( Finote radio )


በረዥም ዘመናት ታሪኳ፤ ሀገራችን ኢትዮጵያ፤ ጥቃት የደረሰባት፤ በአመዛኙ፤ ከባዕዳን ኃይሎች በበለጠ በሀገር ውስጥ ከሃዲያን ነበር ቢባል፤ ስህተት አይሆንም።  የውጭ ወራሪ  ኃይሎች ነፍጥ አንግበው  ሲመጡባት፤ የውስጥ ባንዳዎች ስጋጃ አንጥፈው ተቀለዋቸዋል።  ዋገምት ደግነው፤  ደሟን እየመጠጡ፤ ለበዕዳን ወራሪ ኃይሎች  አስተላልፈውላቸዋል ። የሀገሪቱን ውስጠ ምሥጢር እያሾለኩ አቀብለዋቸዋል። የሚገርመው ደግሞ፤ ይህንን የክኅደት ተግባር የፈፀሙት ፤ በአብላጫው፤ ገበሬዎችና ተራ ዜጎች ሳይሆኑ፤ ሹማምንቱና በኃላፊነት ቦታ የተቀመጡ ሰዎች ነበሩ።
ስማቸውን መጥቅስ፤ የዚህ ሐተታ ዓላማ ባለመሆኑ፤ ወደዚያ አናዘነብልም። ባንዳዎችና ሌሎች የጠላት ተባባሪዎች፤ በሀገሪቱ ላይ ያደረሱት  ጉዳትና ጥፋት በቀላሉ የሚገመት አልነበረም። አሁንም ያው ነው። የሕዝብና የሀገር ጠላት በአገዛዝ ደረጃ እስካለ ደረስ፤ ሰላይና ባንዳ፤ እንደ አሽን ክታብ መፈልፈሉ አይቀርም ። ጉንዳኑ ሳይገባ ፤ አመድ ሊነሰንስ ግዴታ ነው።  ያልነሰነሰ ተደመሰሰ! ያልጠረጠረ ተመነጠረ ! እንዳይሆን ሁሉም በያለበት ነቅቶ እራሱን እንዲጠብቅ እናሳስባለን !
 የሀገር ውስጥ ቀበኞች ቁጥራቸው እጅግ አነስተኛ ቢሆንም ቅሉ፤ ያስከተሉትና  ዛሬም እያስከተሉት ያለው  ጉዳት ግን  እንዲሁ በችልታ ሊታለፍ አይገባውም ።  ምክንያቱም ይህ ጥፋት፤ አሁንም በተጠናከረ መልኩ እንደቀጠለ  በመሄዱ ነው ። የጠላት ተባባሪዎችን ጥፋት ሊያቆመው ቀርቶ፤ አደጋውን እንኳ  በቅጡ  ሊገነዘብ የቻለ ማንም ኃይል  እንደሌለ  ስለምንገነዘብ፤ ሁኔታው በእጅጉ ያሳስበናል።  
 በየትኛውም ኅብረተስብ ውስጥ፣ በየአንዳንዱ 12ት ኀዋርያት፤ አንድ አንድ ይሁዳ ስለሚገኝ፤  በሀገራችንም የካሃዲያን መኖር አያስደንቅም። የግል ጥቅምን ከሀገርና ከሕዝብ ጥቅም  በላይ  በሚያስቀድም ኅብረተስብ  ውስጥ ፤ ሰብዕናቸውን  ለአላፊ-ጠፊ  ጥቅማ-ጥቅም የሚለውጡ ዜጎች እንደሚበረክቱ የታዘብነው ጉዳይ ሆኗል ።
 " አንድ ሎሌ ለሁለት ጌቶቹ  በዕኩል ታማኝነት ማገልገል እንደማይችል" ሁሉ፤ የመርኅ  ሰው ነኝ የሚልም ግለሰብ፤  የመርኅና የጥቅም ተገዥ ሊሆን አይችልም። አንዱን መርጦ፤ ሌላውን መተው  ይገባዋል ።  በሁለት ካራ  እየተበላ ብዙ ጊዜ መቆየት የሚቻል አይሆንም።  
ይህ ክስተት በኅብረተስቡ ውስጥ መኖሩን ከተገነዘብን ፤ በሕዝቡ ውስጥ ጉንዳኑ ከመግባቱ በፊት አመድ መነስነስ፤ እንደ መጀመሪያ የመከላካያ መስመር ሆኖ ሊያገልግል ይገባል። አመድ መነስነስ፤ ጉንዳን እንዳይገባ የሚረዳ ብልሃት ከሆነ፤ ሰላዮችም ሰርስርውእንዳይገቡ አስቀድሞ  ሰርሳሪዎቹንና ያሰማራቸውን  ኃይል  ጠንቅቆ  ማወቅ   አስፈላጊ  ነው ። 
የእነርሱን ማንነት ማውቁ  ብቻውን  ደግሞ በቂ አይደለም ። ሰላዮቹን የሚያሰማራችው ኃይል  በጉልህ  ማወቁ  አስቸጋሪ ላይሆን ይችል ይሆናል ።  ለስለላ የሚሰማሩትን  ሁሉንም ማወቁ ግን ቀላላ አይሆንም ። ምክንያቱም፤ የሚያሰማራቸው ኃይል፤ ከበቂ በላይ ገንዘብና መመሪያ ስለሚያፈስስላቸው፤ በኅብረተሰቡ ውስጥ ሕዝቡን መስለው ተመሳስለው፤ በልተው እያበሉ፤ ጠጥተው እያጠጡ፤ ስቅው እያሳቁ፤ አልቅሰው እያስለቀሱ፤ ድርና ማግ ሆነው ስለሚኖሩ፤ ሕዝቡን የማዘናጋት ዕድላቸው ሰፊ ነው ማለት ይቻላል ።
የዕለት ጉርስ፤ የዓመት ልብስ  የአረረበት ኅብረተስብ ደግሞ ፤ የሰላዮችና የወስላቶች መፍንጫ -መጫዎቻ  መሆኑ አያስገርምም።  በመሆኑም፤ ፀረ-ሕዝቦች ማንነታቸውን ሳያሳውቁ፤ እኩይ ድርጊታቸውን እየፈፀሙ ላልተወሰነ ጊዜ ለመቆየት የሚያግዳቸው ስጋት አይኖራቸውም ።  በመጨረሻ ሊነቃባቸው ቢችልም፤ እስከዚያው ድረስ  የሚያደረሱት ጉዳት ግን ቀላል አይሆንም ። ከዚያ ወዲያ፤  " ጅብ ከሄደ፤ ውሻ ቢጮኽ "  ምን ይጠቅማል  ?
ሀገራችን ኢትዮጵያ፤ ተሽቀርቅራ ተፈጥራ ግና ተጎሳቁላ የምትኖር ሀገር ነች። በሁሉም ገጽታው ሲመለከቷት፤ ቁስቁልናዋ የትየለሌ ነው። በአሳለፈችው ትዝታ ብቻ ለመኖር  እየፈለገች፤ አሁን ያለችበትን አስከፊ ሁኔታ ለማየት ተስኗታል ።   አሁን ያለውን ሁኔታ በቅጡ አለማየቷ ደግሞ፤ የወደፊቱን አጋጣሚ ተዘጋጅቶ ለመጠበቅ አልተሰናዳችም ። ትከሻ ሊሸከመው፤ ኅሊና ሊቀበለው፤ የማይችል ጥፋትና በደል እየተፈፀመባት፤ ከዚህ አሳርና መከራ ሊያላቅቃት የሚችል ኃይል  እስከሁን አልተፈጠረላትም።  የበደሏን ፅዋ ሊቃመሱላት የሚፈልጉ መሪዎች አላጋጠማትም  ። ይልቁንም ፤ " ኃጢአተኛ  ሳያሳድዱት ይሮጣል ። " እንደሚባለው፤ በፈታኝ ጊዜ፤ ለበላዒ- ሰብ እያጋለጧት ይሸሻሉ። ወንጀለኞች፤ ወንጀላቸው እያሳድዳቸው ይጠፋሉ።   ሀገር አጥፍተው እስኪጠፉ ደርስ ግን ጊዜና  ዕድል ሊሰጣቸው አይገባም ። ተባብሮ እነርሱን ማጥፋት ጊዜ ሊሰጠው አይገባም።
 ነዋሪዎቿም፤ "ትዕግስት ውቅያኖስን ያደርቃል። ተራሮችም በንነው ይጠፋሉ።"  የተሰኘውን ብኂል እያስተናገዱ፤  በቀቢፀ- ተስፋ መኖርን  ይመርጣሉ።  ሊሂቃኑና የፖለቲካ  ጠበብቶችም፤  " ብልጥን ማታለል ትርፉ ቂም ነው " የሚለውን ይትበሃል፤ እየዘነጉ፤  የሕዝቡን ፍቅር ፤ በሽንገላ  ምላሳቸው  ለመግዛት ይመኛሉ። ይህ ግን አይሆንም። ምክንያቱም ፤ የሕዝብን ፍቅር፤ ልብና አዕምሮ ማቸነፍ የሚቻለው ፤ መሥዋዕት  ከፍሎ  በማስመስከር እንጅ፤  ማር በተቀባ አታላይ ፕሮፓጋንዳ  አይደለም ።
ፕሮፓጋንዲስቶች፤ ሞታቸውን ማዘግየት ይችሉ እንደሆነ እንጅ፤ ማስቀረት ስማይሆንላቸው፤ እየሞቱ ይኖራሉ እንጅ፤ ሀገርንና ሕዝብን ከሞት ሊያድኑ አይችሉም። አጥፍቶ መጥፋት ደግሞ፤ የቅርብ ጊዜ የሀገሪቱ መሪዎች አሳፋሪ ታሪክ እየሆነ አልፏል ። " ውሻ ሊበላ ያልቻለውን  ይቀብራል ። " እንደሚባለው ፤ የኢትዮጵያ መሪዎች፤ ያላግባብ ያግበሰበሱትን ሥልጣን መሸክም እየተሳናቸው፤ ከነሥልጣናቸው ተቀብረው ይቀራሉ።  ፊውዳሎችና  ፋሽስቶች፤  ካግበሰበሱት ሥልጣናቸው ጋር ወደ ማይቀርላቸው  ከርሰ-መቃብር መውረዳቸውን  መገንዘብ፤ ለወደፊቱ ይጠቅማል። ወያኔዎቹም የፊተኞቹን ፈለግ እየተከተሉ ይጠፏታል።  ከሕዝብ አመፅ፤ ማንም ምድራዊ ኅይል ሊያድናቸው ከቶ አይችልም።
  የኢትዮጵያ  ሕዝብ  በባኅሉ ፤ መንግሥት የሚባለውን ተቋም ማክበሩ፤ በታሪክ የቆየ  ዕምነቱ ነበር ።  
" የሀገር ያለህ ! የመንግሥት ያለህ ፤
  በህግ አምላክ ! በመንግሥት አምላክ ! "
እያለ፤ እርስ በእርሱ እየተዳኘ፤ እየተስተዳደረ የኖረ ሕዝብ  ነበር።  ዳኝነት፤ ፍትኅ-ርትዕ ፤ የኅሊና ፍርድ፤ ሚዛናዊ መስተዳደር፤ የራሱ የግሉ ባኅሉና ታሪኩ ነበር። ይህ ደግሞ፤ ከጥንት-ከጧቱ ሲወርድ-ሲዋረድ የመጣ እንጅ፤ ዘመን አመጣሽ ፖለቲከኞችና የሥልጣን- ጥመኞች የሚያቀነቅኑት ረጋ-ሠርሽ፤  እንደ ዕንግዳ ደራሽ ፤  አይደለም።  
ሁሉ ጊዜ በታዛ ስር የበቀለ ሀረግ ሬሳ፤  ራሱን ችሎ ቆሞ አያውቅም። በራሱ ያልቆመ ደግሞ፤ ለሌላው ይጠቅማል ተብሎ አይታሰብም። ወያኔ የቆመው በምራባዉያኑ ድጋፍ ነው። የድጋፉ መሠረት ደግሞ፤ የጌታና ሎሌ ግንኙነት ነው። ይህን በውጭ ኃይል የሚደገፈውን አገዛዝ፤ የኢትዮጵያ ሕዝብ ሕጋዊ  ዕውቅና አልሰጠውም ። በህግ ያለቆመን ሥርዓትና አጋዛዝ በኃይል ማስወገድ ደግሞ አግባብ ብቻ ሳይሆን፤የሞራል ህግም ይደግፈዋል። " ጅብ ከሚበላህ ፤ ጅብ በልተህ ተቀድስ  "  ስለሆነ፤ ወያኔ ሀገሪቱን  አጥፍቶ ከመጥፋቱ በፊት አስቀድሞ እርሱን ማጥፋት፤ የኢትዮጵያ ሕዝብ ታሪካዊ ተልዕኮው ከሆነ ቆይቷል ። አጥፊን መቅጣት፤ በመንፈሳዊና ዓለማዊ ህግ የተደገፈ ነው።  የኢትዮጵያ ሕዝብ፤ የሞራል  ልዕልና ስለአለው፤ ሞራለ-ቢሶችን ለማስወገድ ግዴታ አለበት ተብሎ ይጠበቃል  ።
 መንግሥትና  ሕዝብ ፤ ድንበራቸውን ተካልለው፤ ሚዛናቸውን ጠብቀው፤ አቅማቸውን አመዛዝነው ፤  ባኅሪያቸውን አጣጥመው፤ ሚናቸውን አውቀው፤ ግዴታቸውንና ኃላፊነታቸውን ተገንዝበው  እስካልተገኙ ድረስ፤ በሠላም ለመኖር አይችሉም።  በጋራ ስምምነት ላይ የተመሰረተ አብሮነትን አክብረው መኖር ካልቻሉ፤ በአንዲት ሀገር መቆየት አይሆንላቸውም።  እዚያ ደረጃ ከደረሱ፤ በአጥፊና-ጠፊ  ጎራ  ተሰልፈው ፤  አንዱ  የሌላውን  መውደም  ለማየት  ይፈልጋል። " ዝሆኖች ሲፋተጉ፤ ሳሩ  ይደቅቃል  " ነውና፤  መንግሥትና ሕዝብ ሲራኩቱ፤ ሀገር ትጎዳለች ።  ይህ ደግሞ ለማንም  አይበጅም። ያ ስለተባለ ግን፤ ሀገርና ሕዝብ ዘለዓለማዊ መሆናቸው ዕርግጥ ነውና፤ እነርሱ እየኖሩ፤ ስምምነቱን ያበለሸው  መንግሥት መጥፋቱ አይቀሬ ነው ። ሀገርና ሕዝብ ምን ጊዜም ቢሆን አይጠፉም።
 ከዚህም በላይ፤ ኃላፊነት  የሚሰማቸውና አርቆ አስተዋይ የሆኑ ዜጎች ይህንን እድል ለሀገራቸውና ለሕዝባቸው አይመኙም።  በትግል የተሰማሩ ሀገር ወዳድ  ኃይሎችም ቢሆኑ፤ ትግላቸው ፤ ትዕግስት አስጨራሽ-  ተስፋ አስቆራጭ፤  ሊሆን የሚችል መሆኑን ቢገነዘቡትም፤ ከአድማስ ባሻገር እየተመለከቱ፤ ከሸለቆው መጨረሻ ብርሃን እንዳለ ያምናሉ። ብርኅታዊነትን ሰንቀው ይጓዛሉ። የድል ተስፋን አንግበው ይታገላሉ። የመጨረሻው አቸናፊዎች እንደሚሆኑም ያምናሉ። ኢትዮጵያ ሀገራቸው፤ የማንም ከሃዲ መጫወቻ ሆና አትቀርም በማለት በዕልኽ መታገላቸውን ይቀጥሉበታል ። 
እነርሱ ያላመኑበትን ለመቀበል እንደማይፈቅዱ ሁሉ፤  ሌላውም ሳያምንበት እንዲቀበል አይሹም፡፤ አያስገድዱም።  አይችሉምም።  ህይወት፤ ለማንም  ሙሉ በሙሉ የሰመረች ሆና አታውቅም ።  በየጊዜ መራራ ገፅታዋ ይከሰታል  ። የሕይወት መራራን፤ እየጎመዘዘም ቢሆን እየተጎነጩ መታገል የመጨረሻውን ድል ለመጎናፀፍ ያስችላል።  
ከሚገባው በላይ የጠነከረ  ዓላማ ፤ ምናልባት ወደ ጭካኔ እንዳያመራ ጥንቃቄ የሚያደርጉ፤ ብፁዓን ናቸው ባይባሉም ፤ ከአርቆ አስተዋዮች ደረጃ  ይመደባሉ። አክራሪ ብሄረተኝነትን   የሚያራምዱ ሁሉ  አወቁትም አላወቁትም ፤ ወደ ፋሽስት በኅርይ እንደሚለወጡ  በጊዜው  ሊገነዘቡት  ይገባቸዋል ። ይህንን ካልተገነዘቡ፤ አገር አጥፍተው እነርሱም ይጠፋሉ ። ይህንንም ከሙሶሊኒ  ፋሽዝም ና  ከሂትለር   ናሲዝም  ታሪክ ቢቀስሙ ይሻላቸዋል ። 
የዕይታ ልዩነት፤ የአስተሳስብ ልዩነት ሊያስከትል ስለሚችል ፤ ልዩነትን እያሰፉ ከመሄድ ይልቅ፤   እያጠበቡ ተቻችሎ መኖሩ ይመረጣል። ይኽች የብዙ ብሄር -ብሄር ስብ መኖሪያ የሆነች ሀገር፤ የሁሉም የጋራ እንድትሆን ከተፈለገ፤ ተቻችሎ ከመኖር የተሻለ ምርጫ አይኖርም። የእኛም ምርጫ ይኽው ነው፡፡  
በደልንና ጥፋትን፤ በአርምሞ መመልከት፤  ለጥፋቱ ተባባሪ እንደመሆን ስለምንቆጥረው  በሀገርና በሕዝብ ላይ የሚፈፀመውን  በደል እየተከታተልን  ለሕዝብ ማሳወቁን እንቀጥልበታለን ።  
ጉንዳኑ ሳይገባ አመድ እንዲነሰንስበት  ለሁሉም ጥሪ እናስተላልፋለን  ! 
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኖራለች !

Tuesday, April 19, 2016

የገዥና የበዝባዥ ስርዓት ይብቃ! ከዳዊት ከበደ(ኦስሎ ኖርዌ)


ከዳዊት ከበደ,ኦስሎ ኖርዌ
የገዥና የበዝባዥ ስርዓት ይብቃ!
ትግል ሲባል መቼስ ዘርፈ ብዙ ነው። አሁን ያለህበት የትግል ሁኔታ ላይ ራስህን ያገኘኸው እገሌ በሰራው ስህተት ወይም ባደረገብህ ክፉ ነገር እንደሆነ  ማሰብተውና ዓላማህ ላይ ማተኮር ያዋጣሃል። በህይወትህ ስለሆነው ነገር ሁሉ ሙሉ ሃላፊነት እስካልወስድክ ድረስ በትግሉ ዉስጥ ብዙ መሄድ አትችልም። ሰዎች ያደረጉልህ ያደረጉብህና የከለከሉህ ሁኔታዎች በራስህ ላይ ባለህ አመለካከት ተጽዕኖን እንዲያመጣ አትፍቀድለት። ላለህበት ሁኔታ የሌሎች ሰዎች መዋጮ እንዳለበት ጥርጥር የለውም። ሆኖም ታሪኩ እዚያ ላይ የሚያበቃው አንተ እዚያ በትግሉ ላይ ስትቆም ነው። የገዥና የበዝባዥ ስርዓት እንዲያበቃ ከፈለክ ትኩረትህ ሁሉ ትግል ላይ ሊሆን ይገባል። በአንተ ላይ የሚደረጉትን ነገሮች የመቆጣጠር እድል ባታገኝም ለሁኔታው የምትሰጠውን ምላሽ መቆጣጠር ትችላለህ። አንድን ሰው እንድታከብረው ይህ ሰው አንተን መምሰልና በሁሉ መልኩ ከአንተ ጋር አንድ መሆን የለበትም። መልኩ የቆዳው ቀለም አመለካከቱና ፍላጎቱና ከአንተ የተለየ የሆነን ሰው ማክበር የጨዋነት ሁሉ ጨዋነት ነው።
በሰዎች አመለካከት ሳትስማማ እነሱን ማክበር የሰዎችን ልዩ መሆን ለመቀማት ሳትሞክር አክብሮትን መስጠት እንዲሁም ሰዎች የሚወዱትን ነገር "ጠልተህ" እነሱን ግን ማክበር የራስን የላቀ ማንነት አመልካች ነው። እንደ ዘርና እንደ ቋንቋ የመሳሰሉት የሰው ልዩነቶች በጣም ጤናማ የሆኑና ልንቀበላቸው የሚገባን ልዩነቶች ናቸው። ላወቀበት ልዩነት ውበት ነው። አንዳንድ ጊዜ ግን ሰዎች የሚያሳዩት ልዩነት ከጤና ቢስ ሁኔታዎች ጋር ሊገናኝ ይችላል። ይህ ሁኔታ ሲከሰት እንኳ ሁኔታውን ጠልተህ እነሱን ግን ለአንድ ሰው ሊሰጥ በሚገባ አክብሮት ስትቀርባቸው ሃሳባቸውን የማስቀየር ተጽዕኖ የማሳደር ዕድል ታገኛለህ። ከገፋኸውና ከናቀከው ሰው ይልቅ ባከበርከው ሰው ላይ መልካም ተጽዕኖ የማሳደር ሰፊ ዕድል እንዳለህ አትዘንጋ። ልዩነት የማይቀር ጉዳይ ነው፣ መለያየትና መከፋፋት ግን የምርጫ ጉዳይ ነው። በአሁን ሰዓት ወያኔና ጽንፈኛ ተቃዋሚዎች የህዝብን መብት መጨፍለቅና የራሳቸውን ፍላጎት በሃይል በሕዝቡ ላይ መጫን ነው።ትክክለኛ ትግልና የበሰለ የፖለቲካ ውድድር አማራጭ ስፍራና ጊዜ ለመስጠት ፈቃደኝነቱ በእጅጉ ይጎላቸዋል። አቅጣጫውን የሳተ ጭፍን የሆነ ተቃውሞና ትግል ለኢትዮዽያ ህዝብ ምን ዓይነት አደጋ ሊያስከትል ይችላል? ብሎ ለመፈተሽና ለማመዛዘን ያልቻለ ስልጣን ፍለጋ በጥላቻና በስሜታዊነት ተሞልቶ የፈለገው ይምጣ በሚል እየሰገረ ያለ ጽንፈኛ ተቃዋሚ ለሃገርና ለሕዝብ ጠብ የሚል አንዳች ውጤት ያስገኛል ብሎ ማሰብ ከእባብ እንቁላል እርግብ መጠበቅ ይሆናል።
እንደ ወያኔ በበር ያልገባ ቤቱን ማየት በውስጡ ያለውን ማግኘት እንደማይችል ሁሉ አገርና ሕዝብን መሰረት ያላደረገ ጎጠኝነትንና ጽንፈኝነትን የሚያራምዱ የተቃዋሚ ሃይሎች ዴሞክራሲና ፍትህ ሰላም እናመጣለን ብሎ መድከም ከባህር ዘርቶ ፍሬን እንደመጠበቅ ይቆጠራል ነው የምለው። ትግል ማለት በኢትዮዽያውያን በራሳችቸው ተሞክሮና በደረሰባቸው ስቃይ የተቀሰቀሰ የኢትዮዽያ ህዝብ ትግል ነው። በህይወት የመኖር መብት ትግል ነው። = ለረዥም ዘመን አምባገነንነት ያስከተለውን የወያኔ ብዝበዛና ጭቆና የተንሰራፋበትን የፖለቲካ ሁኔታ በሰከነ አእምሮና በተረጋጋ ሁኔታ መገመት ይኖርብናል። ኢሕአፓ ምንጊዜም ለኢትዮዽያ ህዝብ የቆመው ከዘረኝነት የጸዳ ዴሞክራሲና ፍትህ እንዲሰፍን ብሎም እውን
page1image19408

እንዲሆን ነው። ምክኒያቱም የህዝባዊ እምቢታ ጉዞ አስደናቂ ውጤት በማምጣት ረገድ ተጠቃሽ ነው። የትግራይ ሪፐብሊክ መንግስት እመሰርታለሁ ሲል የግራ ፖለቲካን ጫፍ ይዞ የተነሳው ህውሖት ከመሰረቱ በአግባቡ ባልተጠና በተለይም ግልፅ እና የማያወላዳ ታሪካዊ የሆነውን የትግራይን ህዝብ የኢትዮዽያነት እምነት ማንነት ከግምት ያላስገባ የተሳሳተው መታጠፊያ ገና በጠዋቱ ከውልደቱ የጀመረ እንደሆነ ይስተዋላል።
ይህ ሲባል ቀዳማዊ ወያኔ የተነሳበት ዓላማ ዳህራይ ወያኔ ካቀነቀነው አስተሳሰብ ግልጽ ልዩነት እንደነበረው በመዘንጋት አይደለም። የዳህራይ ወያኔ አመለካከት ያለ አንድ እርማት መቀጠሉ ትላንት ብቻ ሳይሆን ዛሬም ኢትዮዽያን ዋጋ እያስከፈለ መሆኑ በግልጽ የሚስተዋል ነው። ወያኔ እንደ ድርጀት ያቀርብ የነበረው የማጭበርበር ጥሪ የነጻነት የኩልነት የዴሞክራሲ ጥሪ ስለነበረ በሌላ ፋሺስት ደርግ አምባገነናዊ አገዛዝ የፈጠረው ጫና ተዳምሮ ህዝባዊ ቁጣና እምቢተኝነት ማስከተሉን እንደምቹ የተጠቀሙት ከሞላ ጎደል የአንድ መንደር ስብስብ (ጎጠኞች)ሲሆኑ የተለየ አላማቸውን የማስፈጸሚያ ስልት ሊዘረጉበት ችለዋል። ይህ ስብስብ ያቀደውን አሳክቶ ያሰበበት ለመድረስ ማንኛውንም እርምጃ ከመውሰድ የማይቆጠብ እንቅስቃሴዎችን ሁሉ በጥርጣሬና በጠላትነት ስሜት የሚያይ ነበር። እንዲህ ያለው በመንደራዊ ቡድንተኝነት ላይ ተመስርቶ በታላቋ አገር ኢትዮዽያ ላይ በተለየ ስልት ወደ ስልጣን ለመምጣት የተነሳው አካል ከፍተኛው ዘመቻው የኢትዮዽያዊነት አስተሳሰብን በማጥፋት ላይ ያነጣጠረ ነበር አሁንም ቀጥሎል።
እርግጥ ነው ለዚህ ሀገራዊ ፖለቲካ ድቀት ተቃዋሚዎች ድርሻቸውን ሊወስዱ ይገባል። የኢትዮዽያ ህዝብ እንደ እባብ እየተቀጠቀጠ ሰብዓዊ ክብር ተነስቶ ውርደት የሚያጎናጽፍ አፋኝ ስርዓት ሀገር እያለማው ነው ሲል በምን መመዘኛ ለኢትዮዽያዊ ባህርያችን የሚስማማው? ሁልጊዜ ነገሮችን በጡንቻና በመሳሪያ ሃይል ለመፍታት ለማንበርከክ መሞከር የፍትህ ስርዓት እያዛቡ ንጹሐን በአገራቸው ነጻነት እንዳይሰማቸው በማድረግ የተረጋጋ ማህበረሰብ መፍጠር እንዴት ይሞከራል?
ወያኔ የድሃውን የግል ድርጀቶችን አቀጭጮ ከገበያ እያስወጣ ልማት እያለማሁ ነው ቢል የት ድረስ ያስኬዳል? ህዝቡን ቀን ከሌት ለዘውገኝነት እየሰበኩ በጎሳዎች መካከል የጥላቻ ግንብ የሚቆም ስርዓት እየዘረጉ የመለያየት አድማስ እያሰፉ አንድ የኢኮኖሚና የፖለቲካ ማህበረሰብ መፍጠር ህልም እውን ይሆናል? ተቃዋሚ ፓርቲዎችን በስልት እያፈረሱ በአፈና እያቀጨጩ ጥገኝነት እያስፈረሙ በእራስ ቅርጽ በእራስ አምሳል እያደራጁ መድበለ ፓርቲ የፖለቲካ ስርዓት በየት በኩል እውን እንዲሆን ይታሰባል? አበው ከአነጋገር ይፈረዳል፣ ከአያያዝ ይቀደዳል እንዲሉ በርካታ በአገር ውስጥ ያሉ የፖለቲካ ተቃዋሚ ፓርቲዎች አመራሮችን ሕዝቡ ተደጋጋሚ ኪሳራና ውድቀት ላይ እያገኛቸው ተከታዮቼ ናቸው የሚላቸው ብዙዎች ደጋፊዎቹ እንኳ ተስፋቸውን ሊጥልባቸው አልቻሉም ዋጋ አስከፍለውታልና። ምክኒያቱም ዛሬ ጥሩ የፖለቲካ አመራር አገኘን ሲል ነገ በእጅ አዙር የወያኔ ተለጣፊ ለሆዱ አዳሪ ሆኖ ይገኛል። ስለዚህ የገዥና የበዝባዥ ስርዓት እንዲያበቃ ትግሉን ለአታጋይ ይሰጠው።
የኢትዮዽያ ህዝብ የድል ባለቤት እስከሚሆን ድረስ ትግላችን ይቀጥላል!!