Monday, April 11, 2016

"መሪ ከሞተ፤ አገር ተበተነ! " የአምባገነኖች ፤ ዝማሬ !

 
ፍኖተ ዴሞክራሲ የኢትዮጵያ አንድነት ድምጽ
Finote Democracy Voice of Ethiopian Unity
Efdpu@aol.com www.Finote.org
በፍኖተ ዴሞክራሲ የኢትዮጵያ አንድነት ድምጽ መጋቢት 14 ቀን 2008 .. የተላለፈ ሐተታ
"መሪ ከሞተ፤ አገር ተበተነ! " የአምባገነኖች ፤ ዝማሬ !
በሀገራችን የቅርብ ጊዜ የፖለቲካ ሥልጣን በጨበጡና ምህዳሩን በሚቆጣጠሩ ግለሰብች አካባቢ ተደጋግሞ የሚሰራጭ ፕሮፓጋንዳ አለ። ይኸውም፤ " እኛ ከሌለን ሀገሪቱ ትፈርሳለች። ሕዝቧም ይበታተናል። ሰማይ ምድሩ ይደበላለቃል። የዓለም ፍፃሜ ይሆናል።" የሚል ሽብር መንዛት ነው። "ይህ ሁሉ መዓት ከሚመጣ፤ አሜን እያላቸሁ ተገዙ ።" የሚል ከንቱ ማስፈራሪያን ያዘለ ፕሮፓጋንዳ ማሰራጨት ለዕድሜያቸው መቀጠያ ይረዳናል ብለው ይገምታሉ ። ቀደም ሲል በነበረው ታሪካችንም፤ ይህ ሁኔታ የሀገራችንን መፈረካከስ በሚመኙ ባዕዳን ጠላቶች ሳይቀር ተደጋግሞ ሲነገር እንደነበር፤ የታሪክ ድርሳናት ያወሳሉ።
በዳግማዊ ሚኒልክ ዘመነ መንግስት መጨረሻ፤ ኢትዮጵያን ለቅኝ ግዛት ለመቀራመት ሲያቆበቁቡ የነበሩት፤ እንግሊዝ፤ ፈረንሳይና ጣሊያን፤ አዲስ አበባ በነበሩት ወኪሎቻቸው አማካኝነት፤ ይህንን ሽብር ሲነዙ እንደነበር ተደርሶባቸዋል። ድኅረ-ሚኒሊክ ኢትዮጵያ ግን እንደ ሀገር መቀጠሏን ቀጥላለች። አሁንም፤ መኖር አይበለውና እየኖረች ነው ። ወደፊትም መቀጠሏን ታውቅበታለች ።
ተፈራራቂ መሪዎች ቢከዱትም፤ ሕዝቡ እንደ ሕዝብ መኖሩን ቀጥሏል። የጭቆና አገዛዙን ተቋቁሞ ማለት ነው ። ሀገርንና ሕዝብን በአንድ ገፅ፤ የሀገር ጠላት የሆነውን ፀረ-ሕዝብ ሥርዓት ደግሞ በሌላ ገጽ እያዩ መፍረድ ተገቢ ነው። ገዥዎች ሲያልፉ ሲጠፉ፤ ሀገርና ሕዝብ ግን አላፊ ጠፊዎች አይደሉምና፤ መኖራቸውን ይቀጥላሉ። ለዚህም ፤ ነው ይህንን መሠረታዊ ሀቅ በመገንዘብ፤ የሕዝቡ መተባበርና ጨቋኙን አገዛዝ ማስውገድ፤ ጊዜ የሚሰጠው አይደለም ። የአሁኑን የሀገራችንን ችግር፤ ለመጭው ትውልድ ማውረስ፤ የታሪክ ወንጀል እንደመፈፀም ይቆጠራል ።
በኛ እምነት፤ እንደ ኢትዮጵያ ሕዝብ ያለ በታሪክ የበለፀገ ሀገር ለተተኪው ትውልድ ማውረስ ያለበት፤ ሠላምንና ነፃነትን፤ አንድነትንና ብልፅግናን እንጅ፤ መከፋፈልንና ድክመትን፤ ድኅነትንና ርሃበን ሊሆን አይገባውም። ሌላው እንኳ ለጊዜው ቢቀር፤ የሀገራችን ጨገሬታ መኖር አለበት። በዚህ ሃቅ፤ መላው ሕዝብ አጥብቆ እንደሚያምን፤ ስንገነዘብ ፤ ተስፋችንን ያለመልመዋል። አንድነቷ የተጠበቀውን ሀገራችንን ለማየት ፤ እየጓጓን እንታገላለን ! ይህንን ለማድረግ ደግሞ፤ ከማንም ፈቃድ አንጠይቅም ።
page1image16320 page1image16480 page1image16640 page1image16800 page1image16960 page1image17120 page1image17280
1
የመንግሥት ሥልጣን ተረክቤ፤ ሀገር አስተዳድራለሁ የሚል የፖለቲካ ተቋምም ይሁን ግለስብ፤ ከሁሉ አስቀድሞ መነሻ ሊያደርግ የሚገባው፤ የሀገሪቱን ታሪክና የሕዝቧንም ማንነትና ጠባይ፤ ባኅልና ዕምነት በጥልቅ መረዳትን ነው። እስካሁን የተከሰተው ችግር፤ ይህንን ጉዳይ በጥልቅ ካለመረዳት የመነጨ እንደሆነ የኢትዮጵያ ሕዝብ በሚገባ ተገንዝቦታል። ለዚህም በቂ ምክንያት አለው።
አሁን በሥልጣን ላይ ያሉት ግለሰቦች፤ ታሪክን እያፋለሱና እያጣመሙ በመከለስ ላይ ይገኛሉ ። በዚህ ምክንያት ፤ እነርሱ፤ ግራ ተጋብተው ሕዝቡንም ለማወናበድ ይጥራሉ። ይህም ድርጊት ፤ ለሀገሪቱ ኅልውና መናጋት ዓይነተኛ ምክንያት ሆኗል። ሕዝቡን ግራ እያጋቡ አቅጣጫውን እንዲስት ማድረግ ደግሞ ፤ ዒላማውን በነርሱ ላይ እንዳያነጣጥር ያደርገዋል። ይህም ፤ ለገዥዎች ጊዚያዊ ፋታን ይሰጣቸዋል። እነርሱ ፋታ እያገኙ በሄዱ ቁጥር ደግሞ፤ የህዝቡ ስቃይና መከራ እየበረከተ ይሄዳል። በዚያው መጠንም የሀገሪቱ የጥፋት ጎዳና እየተፋጠነ ይጓዛል። ዞሮ ዞሮ ተጎጅዎቹ ሀገርና ሕዝብ ይሆናሉ።
የሀገር ጥፋት ተከሰተ የሚባለው እኮ፤ መሬቱን ለባእዳን መሸጥ መለወጥ ብቻ ሳይሆን፤ የዜጎቿም መፍለስና መሰደድንም የሚያጠቃልል ነው። ቅኝ ገዥዎችና አምባገነኖች ደግሞ የሚፈልጉት፤ መሬቱንና በውስጡ የሚገኘውን የተፈጥሮ ሀብት ብቻ እንጅ፤ ነዋሪውን ሕዝብ አይደለም። ወያኔዎቹ ዛሬ የሚያደርጉትም ፤ ይኽንኑ ነው። የግዛት ማስፋፋት (Territorial Aggrandizement)፤ ታላቋን ትግራይ መፍጠር! በወሎ፤ በጎንደርና በአፋር ሬሳ ላይ፤ የትግራይን ህይወት ማንሰራራት! የትግራይን ህይወት መገንባት ! የትግራይን የበላይነት ማረጋገጥ ! ይህ ነው የወያኔ ስትራተጂያዊ ግብ ።
ደርግና ተባባሪዎቹ፤ ኢትዮጵያንና ሕዝቧን በጥልቀት ባለማወቃቸው የፈጠሩት ስህተትና ወንጀል፤ አሁን ሀገሪቱ ለገባችበት ሁለንተናዊ ችግሮች መሠረት ሆነው አልፈዋል። ግንባር-ቀደም ተጠያቂዎችም ሆነዋል ። ጠያቂና ተጠያቂ ሲገጣጠሙ ፤ እልባት ሊያገኝ ይችል ይሆናል።
ሂሳብ በማወራረድና ከተጠያቂነት ለመሸሽ መሞከር፤ ለዘለቂታው መፍትሄ ፍለጋ አይረዳም። የመጨረሻው ዕልባት ሊገኝ የሚችለው፤ የሕዝብ ጠላት የሆነው ቡድን፤ ከነሥርአቱ ተወግዶ በምትኩም ሁሉም ተቻችሎ በሰላም ሊኖር የሚቻልበት በሕዝቡ ፍላጎት ላይ የሚመሰረት አስተዳደር ሲመሰረት እንደሆነም ተደጋግሞ የተገለፀ ነው። ይህንን ለማድረግ ደግሞ የባዕዳን ጣልቃ - ገበነት የሚያስፈልገን ሕዝቦች አይደለንም። የራሳችንን ችግሮች ራሳችን መፍታት ካልቻልንማ፤ ምኑን ሕዝቦች ሆንን? ያውም የኢትዮጵያ ሕዝብ መሆናቸንን ለምንረዳው ሁሉ !
ለሕዝብ ተቆቁርቋሪና ለሀገር አሳቢ ያልሆኑ መሪዎች፤ ሁል ጊዜ ሕዝቡን አይወዱም። አያምኑም። ይልቁንም፤ ይፈሩታል። ይሸሹታል። ይንቁታል። ይከዱታል። ከዚህ ፍራቻና ጥላቻ በመነሳትም፤ የሥርዓታቸው መገለጫ የሆነውን ኃይልና ጉልበት ይጠቀማሉ ። የአገዛዛቸው ባህርይና ድርጊት መመስከሪያ የሆነውን ፤ አፈና፤ እስራትና ግድያ ያካሂዳሉ። ለራሳቸው መገልገያ እንዲሆን የፈጠሩትን ህግና ድንብ እንኳ ቢሆን አያከብሩም ። ህግና ድንብ፤ የሕዝብ ሉዋላዊነትም ሆነ የህግ የበላይነት ጉዳያቸው አይደለም። ከጫካ ስለመጡ፤ የጫካ ህግና ሥነ ልቦና ሰለባ ሆነዋል። ሆኖ መገኘትን ሳይሆን፤ መስሎ መታየትን ይመርጣሉ። አስመስሎ መታየትን በውሸትና ቅጥፈት እየለወሱ ለማቅረብ ይሞክራሉ።
2
" ፖለቲካ ማለት ውሸትና ቅጥፈት" መሆኑን ተቀብለውታል። ማታለልና ቅጥፈት፤ የአገዛዛቸው ዓይነተኛ ብልሃት እንደሆነ ያምኑበታል። መዋሸትና ቅጠፈት፤ ራስና ማዋረድ መሆኑን ካለመረዳታቸው የተነሳ፤ ሀገራቸውን አዋርደው፤ እነርሱም ለባዕዳን ተገዥዎች ሆነዋል። የራስን ሀገር ለባዕዳ ከመሸጥስ የከፋ ምን ውርደት ሊኖር ይችላል ? የኢትዮጵያ ህልውና ቀዳማይ- ድሃራይ የሆነውን ሕዝብ ከሀገሩ እንዲገነጠል፤ በፊርማው ከማጽደቅስ የበለጠ ምን ወንጀል ፤ ክኅደትና ውርደት ይኖራል ?
ተወደደም ተጠላ፤ ዛሬ ሀገሪቱን የሚቆጣጠሯት፤ የሚበዘብዟት እንደነኝህ የመሰሉ ግለሰቦች ናቸው። ስለሆነም እነዚህ ግለሰቦች በግድም ሆነ በውድ፤ መወገድ አለባቸው! እንዴት? የሚለውን ጥያቄ መመለስ ያለበት ግን፤ የሀገሩ ውርደትና ጥቃት የሚያቃጠለው ዜጋ ሁሉ እንደሆነ ማመን አለበት። ሀገርን የማዳኑ ጉዳይ የሁሉም ዜጋ ሃላፊነትና ግዴታም ነው። መሥዋዕት የመክፈሉ ዕዳም እንደዚሁ፤ የጠቅላላው ሕዝብ እንጅ፤ ለተደራጀው ክፍል ወይም ለተወሰነው ኃይል ብቻ የሚተው ጉዳይ አይደለም። ነፃነትን ያህል ታላቅ ነገር በውክልና የሚፈፀም ሊሆን አይችልም። የነፃነት ትግል፤ በስማ በለው፤ ቡታ በመስደድና በርቀት ከትትልና ቁጥጥር (Remote Control) የሚሳካ አይሆንም። ይህንን ጎምዛዥ ዕንቆቆ እያንገፈገፍም ቢሆን መዋጥ ያስፈልጋል ።
እንደ አንድንድ የእግር ኳስ ቡድን አጨዋወት ዘዴ፤ የባላጋራ ቡድን ተጨዋች፤ መስመር እንዲያልፍ (ኦፍ ሳይድ ሲስተም) በመጠቀም ድል አይገኝም። የቅርብ ክትትልን፤ የዕለት ተዕለት ቁጥጥርን፤ ወዲያውኑ አስፈላጊ የሆኑ ውሳኔዎችን፤ በፍጥነት መውሰድንና የሚያጋጥመውንም መሥዋዕት መክፈልን ይጠይቃል። የተቃውሞ ሰላማዊ ሠልፎችን ማድረግ፤ ለሞራል ማነቃቂያ የሚረዱ ግጥሞችንና ሽለላዎች የትግል አካል መሆናቸው ቢታመንበትም፤ ህገ - ወጥ የሆነውን ዘረኛ ወንበዴ ማስወገድ የሚቻለው ግን እርሱ በሚገባው ቋንቋ ሲያናግሩት ብቻ ነው። ይህንን ለማድረግ ግን፤ የተቃዋሚውን ጎራ ትብብርንና አንድነትን ይጠይቃል ።
ዕውነቱን ፍርጥርጥ አድርገን እንነጋገር ካልን ዘንዳ ፤ መላው ዓለም ፤ በሁለት ምክንያቶች ስለ እኛ መስማት ሰልችቶታል ። ይህን ሀቅ ደግሞ መካድ አንችልም ። የተለያዩ ምክንያቶችና ማጠየቂያዎችን ግን መደርደርና መተንተን እንችል ይሆናል። እውነቱን ግን አይቀይረውም። ዓለም፤ በሁለት ምክንያቶች አስልችተናል ስንል፤ ሀዘን እየተሰማን ነው ።
1. ስለ እኛ ርሀብና ጠኔ ዓለም መስማት ሰልችቶታል ።
2. ማብቂያ- ማቆሚያ ያልተገኘለት ሠላማዊ ሠልፋችንም አንግፍግፎታል ።
ሀገራችን የዓለም ኅብረተስብ አባል እንደመሆኗ መጠን፤ ችግሯን፤ ብሶቷን፤ በደሏን ጥቃቷን፤ ረሃብ ጥማቷን፤ ርዛት ህመሟን ሁሉ ለዓለም እያሳወቀች ርዳታ መጠይቋ አያስገርምም። አያስነቅፋትምም። ነገር ግን፤ ዘለዓለሟን፤ ራበኝ፤ ጠማኝ ፤ ታመምኩ- ደኸየሁ ፤ ተጨቆንኩ ተጠቃሁ፤ ተቆረስኩ ተበተንኩ፤ ተሰደድኩ፤ ተነጥቅሁ ወዘተ በማለት የማንነታችን መታወቂያ ልናደርገው በፍፁም አይገባም ። ይቅርታ የማይገባው ወንጀልም ነው። እንኳንስ ባዕዱ ዓለም ቀርቶ፤ እናትም ብትሆን ይሰለቻታል ብንልም ሀቁን መናገር በመሆኑ በዚህ የሚሞግተን ማንም ሊኖር አይችልም።
3
ከዚህ ብሄራዊ መታወቂያችን ከሆነብን ውርደትና ሀፍረት ለመላቀቅ ቆርጠን ማነሳት አለብን ። ሁሉ እያለን፤ ሁሉን ያጣን ሕዝቦች ሆነን፤ የዓለም ሕዝቦች መፈራረጃ መሆናችን ለሁሌም መቆም አለበት። ይህ ደግሞ የእያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ ዜጋ ቁርጠኛ ውሳኔ ሊሆን ይገባል። ቆርጠን ከተነሳን ደግሞ የሚያግድን ኃይል አይኖርም።
ወያኔዎቹ፤ ራሳቸውን የማታለል ክኅሎት ስላላቸው፤ ሌላውንም ማታለል እንችላለን ብለው ያምናሉ። "እንኳን ጦርነት መዋጋት፤ ጦርነትን ጠፍጥፈን መስራን እናውቅበታለን " ሲሉም ይመጻደቃሉ ። ይህንን ሀኬት ግን ፤ ኢትዮጵያ ሕዝብ " ምጥን ለእናቷ አስተማረች ! " ብሎ አሹፎባቸዋል ።
ይህ ሀቅ እንዳለ ሆኖ፤ ዛሬ፤ ከወያኔ 30 ዓመታት የሀገር ማጥፋት ወንጀል በኋላ፤ አሁንም ስለ ወያኔዎቹ ማንነት ፤ ባኅርይና ተግባር እየደጋገሙ ማውራት ብቻ፤ የትም እንዳላደረሰ መገንዘብ ይገባል። ገና ከጧቱ ከማለዳው ማንነቱ ስለታወቀ ጠላት እያነሱ መተረክ ፋይዳ የለውም። ሕዝቡም ማንነቱን ተረድቶ ፈርጆታል። ወያኔ ፤ የሀገርና የሕዝብ ጠላት በመሆኑ፤ በተቻለ ፍጥነት መወገድ አንዳለበት ፈርዶበታል። ይህንንም በራሱ በወያኔ የቀልድ ምርጫዎች ሁሉ ሳይቀር አስመስክሯል ።
ሕዝቡ፤ ወያኔን በራሱ ምርጫ ሳይቀር እንኳን፤ በተደገገሚ ያቸነፈው መሆኑ ቢታወቅም ፤ በተደጋጋሚ ድምፁን ተነጥቋል። ወያኔም በጡንቻ እንጅ በምርጫ ፍንክች እንደማይል አሳውቋል። ምዕራባውያን አሽቃባች አለቆቹም የሀሰት ምስክርነታቸውን ሰጥተውታል። ለወያኔ የግል ፍቅር ኖሯቸው ሳይሆን፤ ለራሳቸው ጥቅም ሲሉ እንደሆነ ዓለም ሁሉ የሚያውቀው ሀቅ ነው።
በኢትዮጵያ ዘመናዊ ታሪክ ፤ እንደ ወያኔ ፤ ለባዐዳን ታማኝ አገልጋይ እንደሌለ ማንም ደፍሮ ሊያስተባብል የሚችል አይገኝም ።
ወደ ሥልጣን ኮርቻ ለመውጣት ከመቆብቆብ በፊት፤ በመርኅ ላይ የተመሰረተ እምነት እንዲኖር ያስፈልጋል። ይህ ዕምነት ፤ የሀገር ፍቅርና የሕዝብ ታማኝነትን ያጠቃልላል። ይህ መርኅ ደግሞ፤ ከወያኔ ጋር ነብርና ፍየል ናቸው። አጥፊና ጠፊዎች ናቸው። አጥፊና ጠፊ ወደ ፊት በኢትዮጵያ ውስጥ ቦታ አይኖራቸውም። በኛ ሙሉ እምነት፤ ዘረኞች ይጠፏታል እንጅ፤ ኢትዮጵያ አትበታተንም። ዜጎቿም አይፋጁም። አይነጣጠሉም። የዘረኞች ሟርትና ምኞት አይፈፀምም ።
የሀገር ጠላቶችን ምኞት ለማምከን ግን፤ መሥዋዕትን ዕሳቤ ያደረገ ተግባር መፈፀም አስፈላጊ ነው። እስካሁን ይህ አልታየም። ውጤት ለማስመዝገብ ፤ ነባቢትን ወደ ድርጊት መለወጥ አለብን። ጥፋትም ሆነ ልማት የሚመጣው በድርጊት ነው ። ወያኔዎች በድርጊታቸው ኢትዮጵያን ሲያጠፉ፤ እኛ ደግሞ በድርጊታችን ሀገራችንን ማዳን ይጠበቅብናል። ይህንን ለማየት ሕዝቡ ይጮሃል። ሰሚ ግን አላገኘም ።
በታሪካችን ፤ በየወቅቱ ለሚመጡ መሪዎች ላይ እንደ የባኅርያቸውና ድርጊታቸው ሕዝብ ሃሳቡን ሲገልፅ ኖሯል ፦
" በኢያሱ ዳቦነውትራሱ፡ በዘውዲቱ ተደፋ ሌማቱ፤
4
በተፈሪ ጠፋ ፍርፋሪ ፤ በመንግሥቱ ሬሳ ጎትቱ ፤ በመለስ/ ለገሰ አገር ተቆረሰ ። "
የዱሮመሪዎች፤ሕዝብ ምንአለ? እረኛምንተናገረ? አዝማሪምንዘፈነ?ሀሚናምንለፈፈ?አልቃሽ ምን አስለቀሰች ? እያሉ ከሞላ ጎደል፤ የሕዝብን አመለካከት፤ ቅሬታና ተቃውሞ፤ የሚያዳምጡበት ዘዴና ብልሃት እንደ ነበራቸው አዛውንት አባቶች/ እናቶች ያወጋሉ። ይተርታሉ። ለትውልድ ያስተላልፋሉ ።
ዛሬ ያ የለም ። ያ መቅረቱ ብቻ ሳይሆን፤ የዓለም ኅብረተሰብ ፤ በተራቀቀው የመገናኛ ቴክኒዮሎጅ እየተጠቀመ በሚነገገርበት ዘመን፤ ወያኔዎቹ፤ የኢትዮጵያን ሕዝብ፤ የዚህን መገናኛ ጥብበ ተጠቃሚ አንዳይሆን ከልክለውታል ። ከውጩ ዓለም ጋር እንዳይገናኝ ፤ የኢንተርኔት፤ የሴል-ፎን፤ የፌስ -ቡክ ሌሎቹን ሶሻል ሚዲያና ውይይትን ሁሉ ዘግተውበታል ። ኢንፎርሜሽን/ እውቀት ኃይል መሆኑን ስለሚረዱት፤ ይህንን ኃይል ሕዝቡ እንዲያገኝ አይፈልጉም። የአገዛዝ ስልታቸው፤ ከፋፍለህ ግዛ ብቻ ሳይሆን፤ አደህይተህ፤ አድንቁረህና አዳክመህ ግዛን ጭምር ያካትታል ።
ቢጽፉት፤ ቢናገሩት፤ ቢያውቁት ቢያሳውቁት፤ ቢረዱት ቢያስረዱት፤ ቢያለቅሱት ቢያስለቅሱት ፤ የሀገራችን ዘርፈ-ብዙ ችግር እንዲሁ በቀላሉ ሊፈታ አይችልም። ሊፈታ የሚችለው፦
1. ኅብረትና ትብብር ወሳኝና አንገብጋቢ መሆኑን መረዳት ያስፈልጋል።
2ኛ፣ ኅብረትና ትብብር እንዲመጣ ከተፈለገ፤ እርስ በእርስ መጠላለፍ መቆም አለበት ።
3. ነበቢትን በድርጊት ካላስደገፉት ውጤት አይመዘገብም ።
4. የውጭ እርዳታን፤ እንደ ዓይነተኛ የትግል ስልት መቁጠር ከንቱነት ብቻ ሳይሆን፤ የዋህነትም ጭምር ነው።
5. በመካሄድ ላይ ያለው ሕዝባዊ አመፅ፤ ሁሉንም ባማከለ አመራር ካልተመራ፤ የተፈለገውን ውጤት ለማስመዝገብ ይቸግረዋል። የአንዱ ክፍል ትግል የመላው ሕዝብ ትግል አካል መሆኑን አምኖ መቀበል አዋቂነት ነው ።
6. ይጓተትም ይፍጠንም፤ የመጨረሻው ድል አድራጊ፤ የመላው ኢትዮጵያ ሕዝብ ትግል መሆኑን አምኖ መቀበል ያስፈልጋል !
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኖራለች !
5


No comments:

Post a Comment