Tuesday, April 19, 2016

የገዥና የበዝባዥ ስርዓት ይብቃ! ከዳዊት ከበደ(ኦስሎ ኖርዌ)


ከዳዊት ከበደ,ኦስሎ ኖርዌ
የገዥና የበዝባዥ ስርዓት ይብቃ!
ትግል ሲባል መቼስ ዘርፈ ብዙ ነው። አሁን ያለህበት የትግል ሁኔታ ላይ ራስህን ያገኘኸው እገሌ በሰራው ስህተት ወይም ባደረገብህ ክፉ ነገር እንደሆነ  ማሰብተውና ዓላማህ ላይ ማተኮር ያዋጣሃል። በህይወትህ ስለሆነው ነገር ሁሉ ሙሉ ሃላፊነት እስካልወስድክ ድረስ በትግሉ ዉስጥ ብዙ መሄድ አትችልም። ሰዎች ያደረጉልህ ያደረጉብህና የከለከሉህ ሁኔታዎች በራስህ ላይ ባለህ አመለካከት ተጽዕኖን እንዲያመጣ አትፍቀድለት። ላለህበት ሁኔታ የሌሎች ሰዎች መዋጮ እንዳለበት ጥርጥር የለውም። ሆኖም ታሪኩ እዚያ ላይ የሚያበቃው አንተ እዚያ በትግሉ ላይ ስትቆም ነው። የገዥና የበዝባዥ ስርዓት እንዲያበቃ ከፈለክ ትኩረትህ ሁሉ ትግል ላይ ሊሆን ይገባል። በአንተ ላይ የሚደረጉትን ነገሮች የመቆጣጠር እድል ባታገኝም ለሁኔታው የምትሰጠውን ምላሽ መቆጣጠር ትችላለህ። አንድን ሰው እንድታከብረው ይህ ሰው አንተን መምሰልና በሁሉ መልኩ ከአንተ ጋር አንድ መሆን የለበትም። መልኩ የቆዳው ቀለም አመለካከቱና ፍላጎቱና ከአንተ የተለየ የሆነን ሰው ማክበር የጨዋነት ሁሉ ጨዋነት ነው።
በሰዎች አመለካከት ሳትስማማ እነሱን ማክበር የሰዎችን ልዩ መሆን ለመቀማት ሳትሞክር አክብሮትን መስጠት እንዲሁም ሰዎች የሚወዱትን ነገር "ጠልተህ" እነሱን ግን ማክበር የራስን የላቀ ማንነት አመልካች ነው። እንደ ዘርና እንደ ቋንቋ የመሳሰሉት የሰው ልዩነቶች በጣም ጤናማ የሆኑና ልንቀበላቸው የሚገባን ልዩነቶች ናቸው። ላወቀበት ልዩነት ውበት ነው። አንዳንድ ጊዜ ግን ሰዎች የሚያሳዩት ልዩነት ከጤና ቢስ ሁኔታዎች ጋር ሊገናኝ ይችላል። ይህ ሁኔታ ሲከሰት እንኳ ሁኔታውን ጠልተህ እነሱን ግን ለአንድ ሰው ሊሰጥ በሚገባ አክብሮት ስትቀርባቸው ሃሳባቸውን የማስቀየር ተጽዕኖ የማሳደር ዕድል ታገኛለህ። ከገፋኸውና ከናቀከው ሰው ይልቅ ባከበርከው ሰው ላይ መልካም ተጽዕኖ የማሳደር ሰፊ ዕድል እንዳለህ አትዘንጋ። ልዩነት የማይቀር ጉዳይ ነው፣ መለያየትና መከፋፋት ግን የምርጫ ጉዳይ ነው። በአሁን ሰዓት ወያኔና ጽንፈኛ ተቃዋሚዎች የህዝብን መብት መጨፍለቅና የራሳቸውን ፍላጎት በሃይል በሕዝቡ ላይ መጫን ነው።ትክክለኛ ትግልና የበሰለ የፖለቲካ ውድድር አማራጭ ስፍራና ጊዜ ለመስጠት ፈቃደኝነቱ በእጅጉ ይጎላቸዋል። አቅጣጫውን የሳተ ጭፍን የሆነ ተቃውሞና ትግል ለኢትዮዽያ ህዝብ ምን ዓይነት አደጋ ሊያስከትል ይችላል? ብሎ ለመፈተሽና ለማመዛዘን ያልቻለ ስልጣን ፍለጋ በጥላቻና በስሜታዊነት ተሞልቶ የፈለገው ይምጣ በሚል እየሰገረ ያለ ጽንፈኛ ተቃዋሚ ለሃገርና ለሕዝብ ጠብ የሚል አንዳች ውጤት ያስገኛል ብሎ ማሰብ ከእባብ እንቁላል እርግብ መጠበቅ ይሆናል።
እንደ ወያኔ በበር ያልገባ ቤቱን ማየት በውስጡ ያለውን ማግኘት እንደማይችል ሁሉ አገርና ሕዝብን መሰረት ያላደረገ ጎጠኝነትንና ጽንፈኝነትን የሚያራምዱ የተቃዋሚ ሃይሎች ዴሞክራሲና ፍትህ ሰላም እናመጣለን ብሎ መድከም ከባህር ዘርቶ ፍሬን እንደመጠበቅ ይቆጠራል ነው የምለው። ትግል ማለት በኢትዮዽያውያን በራሳችቸው ተሞክሮና በደረሰባቸው ስቃይ የተቀሰቀሰ የኢትዮዽያ ህዝብ ትግል ነው። በህይወት የመኖር መብት ትግል ነው። = ለረዥም ዘመን አምባገነንነት ያስከተለውን የወያኔ ብዝበዛና ጭቆና የተንሰራፋበትን የፖለቲካ ሁኔታ በሰከነ አእምሮና በተረጋጋ ሁኔታ መገመት ይኖርብናል። ኢሕአፓ ምንጊዜም ለኢትዮዽያ ህዝብ የቆመው ከዘረኝነት የጸዳ ዴሞክራሲና ፍትህ እንዲሰፍን ብሎም እውን
page1image19408

እንዲሆን ነው። ምክኒያቱም የህዝባዊ እምቢታ ጉዞ አስደናቂ ውጤት በማምጣት ረገድ ተጠቃሽ ነው። የትግራይ ሪፐብሊክ መንግስት እመሰርታለሁ ሲል የግራ ፖለቲካን ጫፍ ይዞ የተነሳው ህውሖት ከመሰረቱ በአግባቡ ባልተጠና በተለይም ግልፅ እና የማያወላዳ ታሪካዊ የሆነውን የትግራይን ህዝብ የኢትዮዽያነት እምነት ማንነት ከግምት ያላስገባ የተሳሳተው መታጠፊያ ገና በጠዋቱ ከውልደቱ የጀመረ እንደሆነ ይስተዋላል።
ይህ ሲባል ቀዳማዊ ወያኔ የተነሳበት ዓላማ ዳህራይ ወያኔ ካቀነቀነው አስተሳሰብ ግልጽ ልዩነት እንደነበረው በመዘንጋት አይደለም። የዳህራይ ወያኔ አመለካከት ያለ አንድ እርማት መቀጠሉ ትላንት ብቻ ሳይሆን ዛሬም ኢትዮዽያን ዋጋ እያስከፈለ መሆኑ በግልጽ የሚስተዋል ነው። ወያኔ እንደ ድርጀት ያቀርብ የነበረው የማጭበርበር ጥሪ የነጻነት የኩልነት የዴሞክራሲ ጥሪ ስለነበረ በሌላ ፋሺስት ደርግ አምባገነናዊ አገዛዝ የፈጠረው ጫና ተዳምሮ ህዝባዊ ቁጣና እምቢተኝነት ማስከተሉን እንደምቹ የተጠቀሙት ከሞላ ጎደል የአንድ መንደር ስብስብ (ጎጠኞች)ሲሆኑ የተለየ አላማቸውን የማስፈጸሚያ ስልት ሊዘረጉበት ችለዋል። ይህ ስብስብ ያቀደውን አሳክቶ ያሰበበት ለመድረስ ማንኛውንም እርምጃ ከመውሰድ የማይቆጠብ እንቅስቃሴዎችን ሁሉ በጥርጣሬና በጠላትነት ስሜት የሚያይ ነበር። እንዲህ ያለው በመንደራዊ ቡድንተኝነት ላይ ተመስርቶ በታላቋ አገር ኢትዮዽያ ላይ በተለየ ስልት ወደ ስልጣን ለመምጣት የተነሳው አካል ከፍተኛው ዘመቻው የኢትዮዽያዊነት አስተሳሰብን በማጥፋት ላይ ያነጣጠረ ነበር አሁንም ቀጥሎል።
እርግጥ ነው ለዚህ ሀገራዊ ፖለቲካ ድቀት ተቃዋሚዎች ድርሻቸውን ሊወስዱ ይገባል። የኢትዮዽያ ህዝብ እንደ እባብ እየተቀጠቀጠ ሰብዓዊ ክብር ተነስቶ ውርደት የሚያጎናጽፍ አፋኝ ስርዓት ሀገር እያለማው ነው ሲል በምን መመዘኛ ለኢትዮዽያዊ ባህርያችን የሚስማማው? ሁልጊዜ ነገሮችን በጡንቻና በመሳሪያ ሃይል ለመፍታት ለማንበርከክ መሞከር የፍትህ ስርዓት እያዛቡ ንጹሐን በአገራቸው ነጻነት እንዳይሰማቸው በማድረግ የተረጋጋ ማህበረሰብ መፍጠር እንዴት ይሞከራል?
ወያኔ የድሃውን የግል ድርጀቶችን አቀጭጮ ከገበያ እያስወጣ ልማት እያለማሁ ነው ቢል የት ድረስ ያስኬዳል? ህዝቡን ቀን ከሌት ለዘውገኝነት እየሰበኩ በጎሳዎች መካከል የጥላቻ ግንብ የሚቆም ስርዓት እየዘረጉ የመለያየት አድማስ እያሰፉ አንድ የኢኮኖሚና የፖለቲካ ማህበረሰብ መፍጠር ህልም እውን ይሆናል? ተቃዋሚ ፓርቲዎችን በስልት እያፈረሱ በአፈና እያቀጨጩ ጥገኝነት እያስፈረሙ በእራስ ቅርጽ በእራስ አምሳል እያደራጁ መድበለ ፓርቲ የፖለቲካ ስርዓት በየት በኩል እውን እንዲሆን ይታሰባል? አበው ከአነጋገር ይፈረዳል፣ ከአያያዝ ይቀደዳል እንዲሉ በርካታ በአገር ውስጥ ያሉ የፖለቲካ ተቃዋሚ ፓርቲዎች አመራሮችን ሕዝቡ ተደጋጋሚ ኪሳራና ውድቀት ላይ እያገኛቸው ተከታዮቼ ናቸው የሚላቸው ብዙዎች ደጋፊዎቹ እንኳ ተስፋቸውን ሊጥልባቸው አልቻሉም ዋጋ አስከፍለውታልና። ምክኒያቱም ዛሬ ጥሩ የፖለቲካ አመራር አገኘን ሲል ነገ በእጅ አዙር የወያኔ ተለጣፊ ለሆዱ አዳሪ ሆኖ ይገኛል። ስለዚህ የገዥና የበዝባዥ ስርዓት እንዲያበቃ ትግሉን ለአታጋይ ይሰጠው።
የኢትዮዽያ ህዝብ የድል ባለቤት እስከሚሆን ድረስ ትግላችን ይቀጥላል!! 

No comments:

Post a Comment