Monday, April 4, 2016

ወቅታዊ የፍኖተ ዜና ትንትኔ። እናንብበው !!!

መጋቢት 24 ቀን 2008 ዓ.ም


Ø ዘረኛነትና አድልዎ ታማኝነትና ቡድናዊ አሠራር በተለመደበት የወያኔ ሥርዓት ውስጥ ለትግራይ ተወላጆች ልዩ እንክብካቤና ጥቅም እንዲያገኙ መደረጉ በተደጋጋሚ መዘገቡ ይታወሳል። በቅርብ ከሚያዚያ 8 ቀን 2008 ዓ.ም እስከ ሚያዚያ 9 ቀን 2008 ድረስ ባህርዳር ከተማ ለሚደረገው የጣና ፎረም የአፍሪካ ምባገነን መሪዎችና የታዋቂ ግለሰቦች ስብሰባ የወያኔው ደህንነት መስሪያ ቤቱ ለጥበቃ የትግራይ ተወላጆችን በብዛት መምረጡ ታውቋል። በዚህ ከአስራ አምስት ቀን በኋላ ይደረጋል በተባለው ስብሰባ ለጥበቃ የሚሰማሩ አባላት ጠቀም ያለ ገንዘብና አበል የሚከፈል በመሆኑ የትግራይ ደህንነት አባላት በብዛት ተመርጠዋል። የደህንነት ምንጮቹ፣ የትግራይ ተወላጆቹ በብዛት የተመረጡት ጥቅም እንዲያገኙ ብቻ ሳይሆን የአማራና የኦሮሞ ደህንነት አባላት ታማኝነታቸው አጠራጣሪ በመሆኑ ነው ይላሉ። የአፍሪካ አምባገነን መሪዎችና ታዋቂ ግለሰቦች ያሉበትን የጣና ፎረም ስብሰባን የቀድሞው የናይጀሪያ ፕሬዚዳንት ኦሊሲንጎ ኦባሳንጆ ይመሩታል ተብሏል።

Ø በአዲስ አበባ ከተማ የራ አጥነት ማስረጃ ለማግኘት የአምስት ቀን ስልጠና መውሰድ ግዴታ ነው ተባለ። ማስረጃውን የሚሰጠው የሚኖሩበት ቀበሌ ሲሆን እስከ ዛሬ ይራበት ከነበረው አሠራር የተለየ መሆኑንና ራአጡ ራ ካገኘ በሰለጠነበት ካልሆነ አትሰራም ተብሎ እንደሚከለልና እሰራለሁ ካለ ከቀበሌው ማስረጃ እንዲያቀርብ ይጠየቃል ተብሏል። ይህ የስራ አጥ ስልጠና የተባለው ለወያኔ የገንዘብ መሰብሰብያ ድርጅቶች ስራ የፈጠረ ከመሆን ውጭ ለአዲስ አበባ ስራአጦች የፈየደው ነገር አለመኖሩ፤ እንዲያውም የሥራ ዕድሉያገኙ ወጣቶች አንተ በዚህ ሙያ አሰለጠንክም፣ አንተ ለዚህ አትመጥንም እየተባሉ የሥራ ዕድሉን ከማጥበብ ውጭ የሰጠው ጠቀሜታ እንደሌለ ተገልጿል። ኢትዮጵያ ውስጥ በተለይ በከተሞች ከፍተኛ የሆነ የሥራ አጥ ቁጥር ያለ ሲሆን ወያኔ በሚከተለው ዘረኛና አምባገነን አድዊ አገዛዝ ምክንያት ስራ የማግኘት ዕድል በእጅጉ እንደጠበበ፤ ተወላጅነትና የፖለቲካ ታማኝነት ዋና መስፈሪያ መሆኑ ይታወቃል።

Ø በአባይ ወንዝ አጠቃቀምና በአባይ ግድብ ዙሪያ ወያኔና ግብጽ ያላቸውን ልዩነት ለማቻቻል ተደጋጋሚ የዲፕሎማቲክ ምንጮች እየገለጹ ባለበት ሰዓት የወያኔ አገዛዝ የዓባይ ግድብ ግንባታ ሲጠናቀቅ 6000 ሜጋ ዋት የኤሌክትሪክ ኃይል እንደሚያመርቱና 74 ቢሊዮን ኪዩቢክ ሚትር ውሃ ሊይዝ እንደሚችል እየገለጹ ነው። የወያኔ መሪዎች ግድብ ሲጀመር 5250 ሚጋዋት የኤሌክትሪክ ኃይል ያመርታል ይበሉ እንጅ አሁን ቁጥሩን ከ6000 በላይ ማለታቸው ታውቋል። ግድብ ከኃይል ማመንጫነት በተጨማሪ ለመስኖ ለዓሣ እርባታና ለትራንስፖርት ይውላል ይበሉ እንጅ የግብፅ መንግሥት ግድብ አሁንም በታሪካዊ የዓባይ ወንዝ ውሃ አጠቃቃሜ ላይ ችግር ይፈጥራል በማለት ተቃውውን በማሰማት ላይ ይገኛል። የቀድሞዎቹ የግብጽ ፕሬዚዳንቶች በአባይ ግድብ ላይ ወታደራዊ ኃይል መጠቀም እንደአማራጭ እንደሚወስዱት መግለጻቸው የሚታወስ ሲሆን የአሁኑ ግብጽ መሪዎች የበለጠ ለዲፕሎማሲ ለሕግና ለቴክኒካል ኮሚቴ ጥናት ጊዜ ይጡ እንጅ የከረረ ፍጫ ውስጥ እንደሚገባ የማይቀር መሆኑ ይነገራል። ወያኔ ስለ አባይ ግድብ ተጨማሪ ፕሮፓጋንዳ ለመንዛትና በተለይ ከውጭ ከሚኖሩ ኢትዮጵውያን ገንዝብ ለመሰብሰብ ግድ የተጀመረበት አምስተኛ ዓመት በማለት ስብሰባ ለመጥራት ማቀዱ ተገልጧል።


Ø በሶማሊያና በኬኒያ ወሰን አካባቢ  ጂብ እየተባለ በሚጠራው ቦታ የአሜሪካው ወታደራዊ ተቋም  ሰው አልባ መንኮራኩርን በመጠቀም  ሶስት የአልሸባብ መሪዎችን ይዟል የተባለ ተሽከርካሪን በማጥቃት የደመሰሰ መሆኑን አንድ የፔንታጎን ቃል አቀባይ ገልጿል። በተሽርካሪው ውስጥ ነበረበት ተብሎ የሚጠረጠረውና ለመግደል ኢላማ የተደረገው ሃሰን አሊ ዳሁር የተባለው የአልሸባብ መሪ ሲሆን ግለሰቡ በቅርቡ በሱማሊያ ውስጥ አሜሪካውያንን ጨምሮ በርከት ያሉ ሰዎች የገደሉትን  የቦምብ ጥቃቶች ሲያደራና ሲያስተባብር  የቆየ ነው ተብሏል። ተወሰደው እርምጃ  ስለደረሰው ጉዳት ዝርዝር መረጃ ቃል አቀባዩ  ገልጾ  ግምገማ እያካሄደ መሆኑን አብራርቷል። 

Ø በተያያዘ ዜና ዛሬ መጋቢት 24 ቀን 2008 ዓም  በኬኒያ ከአንደ ዓመት በፊት በጋሪሳ ዪኒቨርስቲ በአልሸባብ  ታጣቂዎች የተገድሉትን 148 ተማሪዎችና ሌሎች ሰራተኞች ለማስታወስ የተለያዩ ስነስርዓቶች ሲደረጉ ውለዋል። በኮሌጁ ቅጥር ግቢ ውስጥ በመቶ የሚቆጠሩ ሰዎች ተሰብስበው የሞቱትን ያስታወሱ  ሲሆን  በኬኒያ ዋና ከተማ በናይሮቢ የተገደሉትን ለማስታወስ የጸሎትና የሻማ መብራት ሥነ ስርዓቶች የተካሄዱ መሆናቸው ታውቋል።

Ø የደቡብ አፍሪካ ፕሬዚዳንት ጃኮብ ዙማ ትናንት መጋቢት 23 ቀን 2008 ዓም በቴሌቪዥን አማካይነት ለሕዝቡ ባደረጉት ንግግር በቅርቡ የግል መኖሪያ ቤታቸውን ለማሻሻል የተደረገው ግንባታ  በርካታ ውዝግብ ማስነሳቱን ገልጸው ለተፈጠረው ሁኔታ በይፋ ሕዝቡን ይቅርታ ጠይቀዋል። የደቡብ አፍሪካ የሕገ መንግስት ፍርድ ቤት ያስተላለፈውን የፍርድ ውሳኔ የሚቀበሉ መሆኑን ገልጸው ለመዋኛ ቦታና ለቲያትር መመልከቻው ሕንጻ የወጣውን ወጭ እንደሚከፍሉ ቃል ገብተዋል። ለዚህ ጉዳይ የተቋቋመ አንድ የጸረ ሙስና ተቋም የተጠቁስትን ሕንጻዎች ለመገንባት ከመንግስት ካዝና 23 ሚሊዮን ዶላር የወጣ መሆኑን ገልጾ ሚስተር ዙማ ይህንን ገንዘብ መክፈል ያለባቸው መሆኑን በማስረገጥ ትዕዛዝ ማስተላለፉ ይታወቃል።  በሚስተር ዙማ በኩል ገንዘቡን ለመክፈል ፈቃደኛነት ባለመገኘቱ ጉዳዩ ወደ ፍርድ ቤት ሄዶ የደቡብ አፍሪካ የሕገ መንግስት ፍርድ ቤት  ባለፈው ሐሙስ ሚስተር ዙማ የተጠቀሰውን ገንዘብ እንዲከፍሉ ውሳኔ ማስተላለፉ ይታወሳል። በሌላ በኩልም ሁለት ዋና ዋና የአገሪቱ ተቃዋሚ ፓርቲዎች ምክር ቤቱ ሚስተር ዙማ በስልጣን መባለግ ክስ ወንጅሎ ከስልጣን እንዲያባርራቸው አጀንዳ አስይዘው ውይይት እየተካሄደበት ነው። የሚስተር ዙማ የቴሌቪዥን ንግግር  ስልጣኔ በፈቃዴ ለቅቄያለሁ ሲሉ ለመስማት ጠብቆ የነበረውን ክፍል ያበሳጨ ቢሆንም ሚስተር ዙማ አሁንም ቢሆን ለምን ያህል ጊዜ በሥልጣን ይቆያሉ የሚለው ጥያቄ አሁንም አነጋጋሪ ሆኗል። ገሚሱ ሚስተር ዙማ በማጭበርበርና በማሳዘን የሕዝብን አስተያየት በማስቀየር በኩል የተካኑበት መሆኑን በተደጋጋሚ ያሳዩ በመሆናቸው በቅርቡ የተፈጠረውን ሁኔታ በተመሳሳይ መልክ ይወጡታል ሲል በአሁኑ ወቅት በፕሬዚዳንት እየተካሄደ ያለው ሙስናና ዓይን ያወጣ የዘመድ ስራ ይፋ በመውጣቱ ከዚህ ችግር የሚወጡበት መንገድ ጠባብ ነው የሚል ግምት የሚሰጡ በርካታ ናቸው።  ክፍሎች 

Ø በኮንጎ በተመድ የሰላም አስከባሪ ኃይል ውስጥ ተመድበው የሚሰሩት የታንዛኒያ ወታደሮች በእድሜ አነስተኛ የሆኑ ህጻናትን አስገድደው ደፍረዋል የሚል ክስ የቀረበባቸው መሆኑ ተገልጿል። ወንጀሉን ፈጽመዋል የተባሉት  ማቪቪ በተባለው መንደር አካባቢ የተሰማሩ የታንዛኒያ ወታደሮች ሲሆኑ ክሱ የተረጋገጠ ከሆነ አስፈላጊውን ርምጃ እንዲወስዱ ለታንዛኒያ እና ለኮንጎ መንግስት ባለስልጣኖች መረጃው መተላለፉን የተመድ ቃል አቀባይ ገልጿል። ተጠርጣሪዎቹ ከካምፕ እንዳይወጡ የተደረገ ሲሆን በደል ለደረሰባቸው ህጻናትም የስነ ልቡናና የማህበረሰባዎች ርዳታዎች እየተደረገላቸው መሆኑ ተነግሯል። የተመድ የሰላም አስከባሪ ኃይል አባላት በማዕከላዊ አፍሪካ ሪፐብሊክ እና በኮንጎ ተመሳሳይ ክሶች ሲቀርቡባቸው መቆየቱ አይዘነጋም። 

Ø በትናንትናው ዕለት መጋቢት 23 ቀን 2008 ዓም ሲካትሴሬ በተባለችው የናይጄሪያ ሰሜናዊ ግዛት ከተማ ከሶስት ወር በላይ አለምንም ፍርድ በግፍ የታሰሩት የሺያ ሃይማኖት ተከታይ መሪ ሚስተር ዛክዛኪ ከእስር እንዲፈቱ ሰላማዊ ስልፈኞች አደባባይ በመውጣት ጠይቀዋል። ከአንድ ሳምንት በፊት አንድ  የኮሎኔልነት ማዕረግ ያለው የናይጀሪያ ወታደራዊ መኮንን  በሺያ ሃይማኖት ተከታዮች ቡድን ተጠልፎ ከተወሰደ በኋላ ተገድሏል የሚለውን ክስ  ቡድኑ መካዱ ይታወቃል። የሺያ ሃይማኖት መሪ በቁጥጥር ስር የዋሉት በዚህ ዓመት ታህሣር ወር ውስጥ ሲሆን ለመታሰራቸው ምክንያት የሆነው የእምነቱ ተከታዮች አንድ የናይጄሪያ ጄኔራል ጠልፎ ለመያዝ መከራ አድርገዋል በሚል ነው። በወቅቱ በአካባቢው የነበረው የናይጄሪያ ወታደር ሶስት የሺያ መስጊዶችን  የደመሰሰ ሲሆን መሪውን ዛክሳኪን በሥስት ጥይት አቁሰለው ከመያዛቸውም በላይ የዛክዛኪን ልጆች ጨምሮ በርካታ ሰዎችን መግደላቸው ይታወቃል። የናይጄሪያ ፍርድ ቤት አንድ ተጠርጣሪ በ48 ሰዓት ውስጥ ፍርድ ቤት መቅረብ አለበት ብሎ ቢያዝም ከሶስት ወር በላይ የተቀመጡ መሆናቸው ታውቋል። ዛክዛኪ ከ 37 ዓመት በፊት ከኢራን ጎብኝተው ሲመለሱ የመሰረቱት የሺያ ሙስሊም ሃይማኖት በሚሊዮን የሚቆጠር ተከታዮች ቢኖሩትም በአካባቢው ከሚኖሩ የሱኒ ሙስሊም አባሎች ጋር ሲወዳደር በቁጥር አነስተኛ በመሆናቸው ከፍተኛ በደል የደረሰባቸው መሆኑ ይታወቃል። ባለፈው ሳምንት የሺያ ሃይማኖት እንቅስቃሴ የሚባለው ድርጅት በአካባቢው ከ 1000 ሰዎች በላይ ሰዎች በመገደላቸው በዐለም አቀፉ ፍርድ ቤት ክስ መመስረቱ ይታወሳል።




No comments:

Post a Comment