Friday, May 6, 2016

ትግል በየፈርጁ፤ የደብተራው ፀገዬ፣ የዋለልኝና የጥላሁን ብሎም የሀማ ቱማ ትንሣኤዎች


ትግል በየፈርጁ፤ የደብተራው ፀገዬ፣ የዋለልኝና የጥላሁን ብሎም የሀማ ቱማ ትንሣኤዎች
ከኦቦ አራዳ አባ ሻውል
ሚያዚያ ፳፫ ቀን ፪ሺህ፰ ዓ
.(ፋሲካ 2008 .)
May 1st 2016
የደብተራው ፀገዬ የአርነት አመራር መርሆ
በቅድሚያ ደብተራው ምን ማለት ነው፤ ደግሞስ ፀገየ ወይም ፀጋየ ማነው? የምትሉ አንባቢዎች እንዳአላችሁ ይገባኛል ስለዚህ ትንሽ ማብራሪያ ላድርግ፡ ፡ ደብተራ ማለት ላቅ ያለ አስተማሪ ማለት ሲሆን ብዙ ጊዜ የምጠቀምበትም በኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ውሰጥ የተከለለ ለማለት ይቻላል፡፡ አገልግሎቱም በድቁና፤ በመዝሙርና በዳንኬራ ላይ ያተኮረ ነው፡፡ ይህ ማለት የቤተ ክርስቲያኑ ዋና ኃላፊ ነው ማለት ይቻላል፡፡ ታዲያ እነዚህ በየዓላማቱ የሚገኙ ቤቱ ክርስቲያናት እንዴት ነው፣ አንድም ደብተራ የሌላቸው ብላችሁ እንደምትጠይቁ ይገባኛል፡፡ ምላሹ ትክክለኛ የቤተ ክርስቲያን ሥራ እየሰሩ አይደሉም ማለት ነው፡፡ ምዕመናን በካህናትና በዲያቆናት ይማራሉ፡፡ ካህናትና ዲያቆናት ማነው የሚያስተምራቸው ብላችሁ ጠይቁ፡፡ ደብተራዎች ነው መልሱ፡፡
የኮርፖረሽን ቤተ ክርስቲያናት ያለ “ፓስትር” እንደማይመሩ ወይንም “መስጊዶች” ያለ ሸኾች ወይንም ይሁዶች ያለ “ራባይ” እንደማይመሩ እየታወቀ ለምንድን ነው የኤትዮጵያ ቤቴ ክርስቲያኖች በደብተራዎች የማይመሩና የማይማሩ? ተብሎ ሲጠየቅ መልስ የለም ወይንም ደብተራ ጠንቋይ ማለት ነው እያሉ ሕዝበ - ኤትዮጵያ ስለተወናበደ ደብተራ የሚል ቃል ሲሰሙ ይበረግጋሉና ነው፡፡ ታዲያ ፀገዬ ደብተራው ማነው? ፀጋዬ ገብረ መድኅን ይባላል፡፡ በኢሕአፓ የተሰለፉ አብዛኛው በሥም ያውቁታል በአካል ግን አያውቁትም ምክንያቱም ኮሳሳ፣ትሁት፣ብቸኛና ሲበዛ ዴሞክራት ስለነበረና ልታይ ልታይ የሚል ሰው አልነበርምና ነው። የደብተራው ዋናው ተልእኮው ኪነት የሠፊው ሕዝብ መሆኑን ለማስረገጥ ነበር፡፡ ተልእኮው ተሳክቶለታል፡፡ ለምን ቢባል ዋና ጠላቶቹ እነ በረከት ስምኦን ሳይቀሩ ሕዝቡ እኛ ሳናውቀው ሁሉ ዘፋኝ ሆነዋል ብለዋል፡፡ ለወያኔ እና ለኢድሕን ኪነት ዘፈን ነው የሚመስላቸው፡፡ አይ ጉድ ስንቱን እናሳልፍ የኪነት ሰዎች ነን የሚሉ እንደነ ኃይሌ ገሪማ የመሳሰሉ ኢሕአፓ አገር አጥፊ ነበር፣ ነውም እያሉ ይኖራሉ፡፡ ምክንያቱም ኪነት የግል ነው ብለው ስለሚያምኑ፡፡ ለነገሩማ አንዱ የኢሕአፓ አመራር አባል ታዬ ፈንጦ ኪነት የግል ነው በማለት አባዝቶ ለመሸጥ ሞክሮ አልተሳካለትም፡፡ ስህተት ሁሉም ጋ አለ ማለት ነው፡፡ ፀፀት የምትባል ግን በይሁዳ እስካሪዮስ ካልሆነች በሌሎቻችን የለችም፡፡ ብናስብበት መልካም ነው፡፡
ታዲያ ደብተራው ከእነ ፀጋዬ ገብረመድህን (ሎሬት)፣ ከእነ ሙሉጌታ ሉሌ (ፀጋየ ገ/መድህን አርአያ) እያሉ ኢትዮጵያዊነተቸውን በህልም ዓለም ከኖሩ ግላዊ ባለኪነቶች ተከራክሮና ተማግቶ ኪነት ኤትዮጵያዊነት ላለበሰ፤ ለዚህ ሕዝባዊ ኪነት ወያኔና ሻዕቢያ የኛ የትግል ፍሬ ነው ብለው ሊነጥቁ የሚራራጡ፤ ስለ ደብተራው ፀገዬ ማን ይናገርለት፡፡ የኤትዮጵያ አብዮት በደርግ እንደከሸፈ ሁሉ አሁንም በሌሎች አካላት የኪነታችን ጥበብና እሴት መረን ለቆ ገደል እንዳይገባ እንሰጋለን፡፡ ደብተራው ፀገዬ እንደሆን አሁንም ህያው ነው፡፡ እንደነ ገብሩ አሥራት የመሰሉ እንዝህላሎችና አድር ባዮች የአመራር ደብተራው ሞተዋል፣ ገለነዋል ቢሉ ማን ሊሰማቸው፡፡ ደብተራው አለ፡፡ የት ነው ብላችሁ ብትጠይቁ በየደብሩ፣ በየቤተ ክርስቲያኑ፣ በመምህራኑና በተማሪዎች፤ በሠራተኞችና አቀባባይ ከበርቴዎች መንፈስና ህሊና አለ፡፡
ታሪኩን ለማሳጠር ደብተራው ፀገዬ የተወለደው በወርሃ የካቲት ስለሆነ የአመራር ተሰጥኦ ነበረው/አለው፡፡ የአመራር ተሰጥኦ ወይንም ፍላጎት ላለቸው የኢሕአፓ አባሎችና ደጋፊዎች የደብተራው ጥሩ ምሳሌ (አርአያነት) እንደሆነ ልገልጠላችሁ እችላለሁ፡፡ አነማን እንደሆናችሁ ራሳችሁ መርምራቸሁ ድረሱበት፡፡ ካስፈለገም ደብተራው የአርነት አመራር መሪ መሆኑን መነጋገርና መወያየት ይቻላል፡፡ ለኤርትራ አርነት (ከፈረንጆች ቅኝ ግዛትነት) ለቀረችው ኢትዮጵያ ነፃነት አዳምሮ INDEPENDENT ETHIOPIA ለማሰኘት የታገለና የመራ ፅንሀተ-ምሁር አካል ነበር፡፡የሚገርመው ነገር የኢሕአሰ ሠራዎት በኤርትራ በረሃዎች መሳሪያውን አውርዶ በሚንቀሳቀስበት ግዜ ደብተራው ሥራ ሳይፈታ “ንዑ ንትማሀር ቅዳሴሆሙ” ማለትም ምስጢራተ ቤተ ክርስቲያን መዝሙርና ዜማ እወቁ እያለ ያስተምር ነበር ብለው የነገሩኝ ሰዎች አሉ፡፡ ድብተራው ፀጋዬ በጦር እየተዋጋ ይኸንን አያደርግም የሚሉ አሉ፡፡ ደግሞም ማርኪሲሰት ነው እያሉ የሚቀባጅሩ እንዳሉ አውቃለሁ፡፡ የኤትዮጵያ አብዮት አካሄድ የማያውቁ ናቸውና ነው፡፡ አብዮተ-ኤትዮጵያ አገር በቀል ነበር ነውም፡፡ ሀሰት የሚል ካለ ይግጠመኝ፡፡
ደብተራው ፀገዬ የዚህ ዓለምና የመጪውን ዓለም በሚገባ የተረዳው ግለሰብ ነበር/ነው፡፡ ኤትዮጵያ (ኢትዮጵያና ኤርትራ ማለት ነው) ስለሆነ እንዳትደናገሩ፡፡ የላቲን ፊደላት EE አነባብ ስለቸገረኝ እና ነው፡፡ የካርል ማርክስ ትምሕረት ለዚህ ዓለም ሲሆን የኢየሱስ ደግሞ የመጪው ዓለም ነበር/ነውም፡፡ ታዲያ ደብተራው ፀገዬ ሁለቱም አጣምሮ በተግባር ያሳየን ታላቅ መምህርና አስተማnሪ ነው፡፡ ሀሰት ካላችሁ ነብይ በአገሩ አይከበርም ነው የምላችሁ፡፡ ሌላ የምላችሁ ነገር የለም፡፡
page1image27576
የዋለልኝ መኮነን ፍትሀ ፍለጋ
ዋለልኝ ማነው? ምንስ ሰርቶ አልፈዋል የሚሉ ጥያቄዎች እንደሚኖራችሁ እገምታለሁ፡፡ ምንም እንኳ ወያኔ ወሎን አቀርጦ አዲስ አበባ ሲገባ የዋለልኝ ጦር ብሎ ሰይሞ መንገዱን ጨርቅ ሆኖለት ቢገባም፣ ማታለል ሁሌም ስለማይሳካ አዲስ አበባ ከገባ በኋላም ዘዴው ስለታወቀበት እንደገና ለማታለል የደቡብ፣ የምዕራብ፣ የምሥራቅ ሕዝቦች እያለ በውጭ ልክፈት ትራይብ/ኤትኒክ ወዘተ እያለ እስከአሁን በዋለልኝ ሥም እየቸረቸረና እየነገደ ይገኛል፡፡
ችርቻሮው እያለቀ ሲሄድ እነሆ የኢትዮጵያ ሕዝብ አንድ ነን፣ ቋንቋና ዝርያ አይለያየንም አለ፡፡ ታዲያ የዋለልኝ ነው መፍትሔው የሚሉት ለምን ሆነ? ነጭ ውሸት መሆኑን ታወቀ፡፡ ታዲያ ስለ ዋለልኝ የግል ሕይወት ለማወቅ የመትሹ በአሲምባ ድህረ ገፅ ይመልከቱ፡፡ http://walilegnfordemocracia.com/index.html
በተረፈ ግን ኦሮሞዎች ነን የሚሉ ዋለልኝ ኦሮሞ ስለሆነ ነው አማራን ያዋረደ ሲሉ፣ አማሮች ነን የሚሉ ደግሞ ዋለልኝ አማራ ነበር ግና እኛን አዋርዳለሁ ብሎ ራሱን ነው ያዋረደው እያሉ ይገኛሉ፣ ደቡቦች ደግሞ እንዲያውም ዋለልኝ ነው ነፃ ያወጣን ሳይሉ ይቀራሉ ብዬ እገምታለሁ፡፡ ታዲያ ሀቁ ምንድን ነው?
ለነገሩ ሁሉም እውነትነት አላቸው ወይም ነበረባቸው፡፡ ለምን ቢባል ዋለልኝ የተወለደው በወርሃ ሚያዝያ ስለተወለደ ኮከቡ የፍትሕ ነው፡፡ ፍትሕ ደግሞ የሁሉም ቤተ ሰብና ኅብረተሰብ ፍላጎትና ምኞት ነውና፡፡ ታዲያ ዋለልኝ ለፍትሕ ፍለጋ አነበበ፣ ፃፈ፣ ተሟጎተ፣ታሰረ፣ እና በትግል ላይ ተሰዋ፡፡ ፍትሕ በምድረ ኤርትራም ጭምር መንገሥ አለባት ብሎ ስለአመነ ከተራማጅ ኤርትራውያን ጋርም አብሮ በትግል ተሰማራ፡፡ ይሕ ሐቅ ነው፡፡ ሐሰት የሚል ካለ በውይይትና በጹሁፍ ማስተናገድ ይቻላል፡፡
አንድ ጽሑፍ በቅርቡ እንዳአነበብኩት ሁለት ግለሰቦች ለኢትዮጵያ የተታገሉና ሁነኛ ወጤት ያስገኙ አቡነ ጵጥሮስና ዋለልኝ መኮነን ነበሩ እያለ ይተርካል፡፡ እውነትነት አለው ግና እነዚህ ግለሰቦች በሞሞታቸው ብቻ ሳይሆን በአስተማሩትና በአሳዩት ተግባራት የኢትዮጵያ ሕዝብ ተማርኮና ተመስጦ እምቢኝ ለቅኚ ገዥዎች፣ እምቢኝ ለፍትሕ ነሺዎችና አጉዳዩች በሚል መርሆ ተከትሎ እነሆ እስከ አሁንዋ ዕለትና ሰዓት እየታገለና እየተዋደቀና ይገኛል፡፡
ኢሕአፓና ኢሕአፓዎች አሁንም ቢሆን እንደ ዋለልኝ ፍትሕ የምትፈልጉና በየቀኑ ስሜታቹ ስለ ሞራልና ዲሲፕሊን የምታወሩ ዋለልኝ የፍትሕ አመራር አካል መሆኑን አትዘንጉ! አትዘንጉ!
የጥላሁን ግዛው እኩልነት ፍለጋ
ጥላሁን ግዛው ማለት የሣራ ግዛው ወንድም ነበር፡፡ ሣራ ግዛው ማለት ደግሞ የአፄ ኃይለ ሥላሴ ልጅ ልዑል መኮንን አግብታ ቤተ መንግሥት ገብታ እኩልነት የተጎናጸፈች ነበረች ማለት ይቻላል፡፡ ታዲያ ጥላሁን ምን ከፋው? ነው ጥያቄው፡፡ ተራ መደዴው ሰው ምቀኝነት ነው ይሉታል፡፡ እንኳን በዛን ግዜ አሁንም ቢሆን ሀበሻ ምቀኛ ነው እያሉ የሚያወሩና የሚያምኑ እንዳሉ የታወቀ ጉዳይ ነው፡፡ ጥላሁን ግን በወርሃ ጥር ስለተወለደ ዕምነቱና ፍላጎቱ መንፈሣዊ ስለሆነ በእኅቱና በአባቱ ምክንያት የኢትዮጵያ ሕዝብ እኩልነት አንማይጎናጸፍ ስለሚያውቅ ነው በአገሪትዋ እኩልነት ለማስገኘት ሲል ሕወቱን ያጣው፡፡ እኔ እስከማውቀው የኅብረተሰብና የማኅበረሰብ ጥናት በሚገባ ተከታትለዋል እንደዚሁም የአብዮት ቴዎሪና ታሪክ አንብበዋል፡፡ ገዳዮቹና አስገዳዮቹ አሁንም በሕወት ይኖራሉ፡፡ ልጁና የትግል ጓደኞቹ አሁንም የተለመውን እኩልነት ለማንገሥ በትግል ላይ ናቸው፡፡
ሀማ ቱማ ማነው? የሚፈልገውስ ምንድን ነው?
ስለ ማንነቱ ብዙም የማውቀው የለም በሕይወት ስለአለ ራሱ ቢገልጠው ይሻላል እላለሁ፡፡ የሚፈልገውንና የትግሉን ዓላማ ግን አውቀዋለሁ፡፡ እሱም የዕወቀት አመራር አካል ስለሆነ ግንዛቤውና ትግሉ በነፃነት ወይንም በዴሞክራሲያ ላይ የተመሠረተ መሆኑን አውቃለሁ፡፡እሱም ሀሰት ነው ካለ በኮከቡ ማመሳካከር ይቻላልና ነው፡፡
በተረፈ ኢሕአፓና ኢሕአፓዎች ዲሞክራሲና ዴሞክረሲያ (የሀማ ቱማ አዕምሮት) ለምትሹ ራሳችሁን በዕውቀት ለማዳበር ተዘጋጁ፡፡ ጊዜው አሁን ነው፡ ፡ ሕዝቡ በትግላችን አሳውቀነዋል፣ አደራጅተነዋል ብላችሁ አትዝናኑ፣ አትመጸደቁ፣ ገና የትጥቅ ትግል ይቀረናል፡፡ የትጥቅ ትግል ማለት ደግሞ ከዚህ ቀደም በድሉ ሞት ምክንያት የጻፍኩትን የኢሕአፓ ዕምነት፣ዕቅድና ዓላማ ይመለከታል፡፡ ድል የሚል ቃል ለኢሕአፓ ድርጅት ቀላል ነው ለኢሕአፓዎች ግና ከበድ ብሎአቸዋል፡፡ ለምን ቢባል ድርጅቱ የሚያስመዘግባቸው ድሎች ረቂቅ ብቻ ሳይሆኑ በሚዛን የሚለኩም በመሆናቸው፡፡ ድሉ ግና እንደየግለሰቡ አስተዋፅኦ በትጥቅ፣ ወይም በስንቅ አለበዚያም በብዕር የተተመነ ወይም የሚተመን ስለሆነ እገሌ ይህንን አድርገዋል/አበርክተዋል ለማለት ከባድ ነው፡፡ ጉዳዩ የሁሉም አስተዋፅኦ አለበት ለማለት ብቻ ነው የሚቻለው፡፡ የኢሕአፓ ዴሞክራሲያም እነዚህ ሦስቱ አንድላይ በቴክኖሎጂ ሲቀናጁ የትጥቅ ትግል ይባላሉ፡፡ አለበለዚያ እንደ ግንቦት 7 ውሃ መልስ ውሃ ቅዳ ይሆናል፡፡ የነቃና የተደራጀ የኢሕአፓ ሠራዊት እንደነበረ ማስታስ ያሻልና፡፡ እውነተኛ ታሪኩንም ማወቅ ያሻል፡፡ እስከዛሬ የኢሕአሰ ታሪክ አልተፃፈምና ነው፡፡
ማጠቃለያ ግንዛቤ
እኔ እስከማውቀው ድረስ ደብተራው ፀገዬና ዋለልኝ መኮነን የኢትዮጵያ ልዑላውነት (በደብተራው አንደበት) ለኢትዮጵያውያን ፍትሕ (በዋለልኝ አንደበት) የተመረዘና የተገነባ መሆኑን ነው፡፡ ደብተራው ልዑላውነት ሲል አንድነት ብቻ ማለቱ አልነበረም እንዲያውም ልዩነታችን ይለምልም (vive la difference) እያለ ነበር እስከ መጨረሻው ድረስ በትግል ዘመኑ የተዋደቀው። ቅርሱም ይኸው ለኛም ደርሶናል። የዋለልኝ የፍትሕ ፍለጋ ደግሞ

የአሁኖቹ አመጸኞችና ውሽታሞቹ እንደሚያናፍሱት በክልል አንቀጽ 39 ብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች እያሉ እነደሚያናፍሱት ሳይሆን የተማሪዎቹ ፕሬዝዳንት ጥላሁን ግዛው የእኩልነት ሕልምና ትግልም በሠፊው እየተቀጣጠለ ይገኛል።
የዚህ ሁላ ሞት፣ ሥቃይና ስደት ኢሕአፓና ኢሕአፓዎች ያፈሩት/ያመጡት ስላልሆነ እንደገና ሕዝቡ በሰከነ አዕምሮና ልቦና ቢያዩት ይመረጣል፡፡ አድራጊዎችና ችግር ፈጣሪዎች በንጉሠ ነገሠት ዘመን አምስት መቶ ነን ብለው ፎክረው የወደቁ፤ በወታደራዊ መንግሥት ደግሞ አንድ መቶ ሃያ ብቻ ነን ብለው ተመጻድቀው ለተንኮታኮቱ፤ የአሁንም ገዥዎቻችሁ ዘጠኝ ብቻ ነን እያሉ እያሾፉ እንጦርጦስ እንደሚጣሉ ማወቅ አለባቸው፡፡ ሀማ ቱማ ይቅርታ እንጠየቅ ለሚለው አባባል ትርጉሙ የሳተ አልነበረም፡፡ አባባሉ የኢሕአፓ ድርጅት ወክሎ እንጂ ኢሕአፓዎችን ወክሎ አልነበረም፡፡ አንድ አንድ ኢሕአፓዎች የከፋ ወንጀልና ሤራ ሰርተዋልና ነው፡፡ ታዲያ ድርጅቱ የፖለቲካ ሥልጣን ሳይኖረው እንዴት ወንጀልና ክፋት በሕዝቡ ላይ ሊያደርስ ይችላል፡፡ አባባሉ በደሉን ያደረሱ ድርጅቶችና መንግሥታት ለኤትዮጵያ ሕዝብ ይቅርታ ይጠይቁ ለማለት መሰለኝ፡፡ አልነበረም ካለ ደግሞ እራሱ ሊነግረን ይችላል፡፡
አርነት፣ ነፃነትና ፍትሕ የኢሕአፓና የኢሕአፓዎች ተልዕኮ፤ ራዕይና እሴት መሆናቸውን ማን ሊረሳው! የእኩልነቱ ጉዳይ ደግሞ በዴሞክራሲያ ይከናወናል፡፡
አሁንም እናቸንፋለን፡፡ መልካም ፋሲካ፡፡ 

No comments:

Post a Comment