Sunday, May 8, 2016

ነፃ ፕሬስ በሕዝባዊ ትግል ይገነባል!! (ኢሕአፓ-EPRP)


የኢትዮጵያ ሕዝባዊ አብዮታዊ ፓርቲ (ኢሕአፓ)
Ethiopian People ́s Revolutionary Party (EPRP)
ሚያዚያ 25 ቀን 2003 ዓ.ም.
ነፃ ፕሬስ በሕዝባዊ ትግል ይገነባል!!
በአለም አቀፍ ደረጃ በየአመቱ በሰላም ወዳድ ማህበርሰብ ዋና ተዋናይነት የሚከበሩና የሚዘከሩ መሰረታዊና ወሳኝነት ያላቸው የበአል ቀናቶች ይገኛሉ። ከነዚህም ውስጥ አንዱ በየአመቱ (ሚያዚያ 2 በሜይ 3 እለት የሚከበረው አለም አቀፍ የፕሬስ ቀን የተሰኘው የበአል አከባበር አንዱ ነው። ለቀኑ መከበር ምክንያት የሆኑ ማጠየቂያቸውና ለሕዝብ የሚያስተላልፉት መልዕክቶቻቸው ነፃነትን ለመጎናፀፍ በሚደረገው ትግል ውስጥ ጉልህ ሚና የሚጫወቱ ለመሆናቸው በርእሱ ላይ በየጊዜው የሚወጡ የተለያዩ በርካታ መጣጥፎች የሚያመላክቱት ናቸው።
ይህ በዛሬው ቀን የምናከብረው አለም አቀፍ የፕሬስ ነፃነት ቀን እንዲከበር የተወሰነው ደግሞ በዩኔሳኮ አቅራቢነት በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ጠቅላላ ስብሰባ በሴብቴምበር 1993 ዓ.ም. በወሰነው መሰረት ሲሆን ይኸው ከ1994 ዓ.ም. ጀምሮ በአለም አቀፍ ደረጃ እየተከበረ ይገኛል። በርግጥም ያለፉት 22 አመታት እንደሚያመላክቱት ዘንድሮም ይህ እለት በመላው አለም ለፕሬስ ነፃነት መከበር በሚንቀሳቀሱ ሕዝባዊና መንግሥታዊ ተቋማት አማካኝነት እየታወሰና እየተዘከረ ይገኛል። የኢሕ አፓ አባላትና ደጋፊዎች እንዲሁም ሀገር ወዳድ ኢትዮጵያዊያንም ይህንን ቀን አመቺ መስሎ ባገኙት ሁኔታ ያከብሩታል። ስማዕታቱንም ይዘከራሉ።
ይህ ቀን በተለይ እንደ ኢትዮጵያ በመሰሉ በአምባገነን ሥርአት በሚማቅቁ ሀገራት ዜጎች በይፋዊም ሆነ በሕቡእ መከበሩ የማጠየቂያውን ወሳኝነት የሚያመላክት ከመሆኑም በላይ ጋዜጠኞች ምን ያህል በነፃነት ሙያቸውን ተግባራዊ እንደሚያደርጉ የሚፈተንበት እንደሆነ በበርካታዎች ዘንድ የሚታመንበት ነው።
በዓለም አቀፈ ደረጃ ተከበሮ የሚውለው ይህ ቀን ለመብት መከበርና ለሰላም መስፈን በየቦታው ለሚዋደቁ ሰላም ወዳድ ኃይሎች የሚያስተላልፋቸው መልክቶች ተደጋግመው የሚጠቀሱ ናቸው። እነዚህም፡

1.. ነፃና የመድበላዊነትን ጠባይ የሚያንፀባርቅ በተግባርም የሚገለፅ ነፃ ፕሬስን መገንባት ለማንኛውም ሕብረተሰብ ሁሌም መሰረታዊ መሆኑ፤
2.. ለነፃ ፕሬስ ግንባታ ያለመታከት በፅናትና ያለማቋረጥ መታገል አማራጭ የለሽነቱን፡
3.. ይህ አላማ ተሳክቶ ሲገኝም እንደ አይን ብሌን መንከባከብ የማንኛውም ዜጋ ኃላፊነትና ግዴታ ስለመሆኑ፤

4.. በትግሉ ሂደት በነፃው ፕሬስ ጠላቶች ሕይወታቸውን ላጡና ለተለያዩ አካላዊም ሆነ የመንፈስ ጉዳት ለደረሰባቸው አባላቱ የትግል ታሪካቸውንና ገድላቸውንም ማስታወስና መዘከር፤
 5. የወደፊቱ ሀገር ተረካቢ የሆነው ወጣት ትውልድ የነሱን ፈለግ መከተሉ ለማህበራዊ እድገትና ሰላም መገኘት ወሳኝ መሆኑን፤ ለማመላከት ነው። ይህም ያለ ምክንያት አይደለም።
በአለም አቀፍ ደረጃ በርካታ በሙያው የሰለጠኑና ተመክሮን ያካበቱ የነፃው ፕሬስ አባላት ተገድለዋል፡ ለእስር፤ ለተለያዩ እንግልቶችና ለስደት ኑሮ ተዳርገዋል። በሀገራችን በኢትዮጵያም በተመሳሳይ ደረጃ የወያኔ አገዛዝ ገና በማቆጥቆጥ የነበረውን የነፃ ፕሬስ ሂደት በእንጭጩ የቀጨ ከመሆኑም በላይ በተለይም በ2007 ና በ2009 ዓ.ም. ባፀደቃቸው ሕጎች ተመስርቶ በጠቅላላ የሚዲያ ተቋማት ላይ ሙሉ ቁጥጥሩን ካሰፈነ በኋላ እስካሁን ድረስ በዚሁ ተግባሩ ቀጥሎበት ይገኛል። በነፃው ፕሬስ አባላትና፤ የዘመኑን የመገናኛና የመረጃ መለዋወጫ ቴክኖሎጂ ተጠቃሚ የሆኑ የኢንተርኔት ደረገፅ አዘጋጆች ላይየተለያዩ ማስረጃ የለሽ ምክንያቶችን እየፈበረከ በሽብር አራማጅነት፤ በፀረ ሰላም፡ ደህንነትና እድገት እንዲሁም በአክራሪነት እየከሰሱ ለተለያዩ መንፈሳዊና አካላዊ ጉዳት ዳርጓቸዋል። በሕዝብ ኃብት እንዲንቀሳቀሱ የተደረጉ የጋዜጣ፤ የሬዲዮና የቴሌቪዥን ተቋማት የሕዝብ መገልገያ ሳይሆኑ ለአገዛዙ ፕሮፓጋንዳ ማሰራጪያነት እየተጠቀመባቸው ይገኛል። ሕዝብ ዜና የማግኘት መብቱን ደፍጥጦበታል። አገዛዙን በተቹ፤ በአመጽ አነሳሽነት እየተፈረጁ ዝብጢያ ይወረወራሉ። ባለሥልጣናትን በድርጊቶቻቸውና በሚወስዷቸው ፖሊሲዎቻቸው መተቸት በአክራሪነትና በተቃዋሚ ደርጅት ልሳንነት ሆነ በፅንፈኝነት ይወነጀላሉ። በዚህም የተነሳ ጋዜጠኞች ራሳቸው በራሳቸው ሳንሱር የማድረግ ግዴታ ተጥሎባቸዋል። በፍርሀትና በሰቀቀን ለመኖር የተዳረጉ ናቸው። የሚዲያ ተቋማት የሕዝብ ብሶትና ችግር መፍትሄ ለማግኘት የመወያያ መድረክ እንዳይሆኑ ለሕብረተሰቡ አማራጭ የመረጃ ምንጭ ሆነው እንዳያገለግሉ የወያኔ ጋሬጣ ተደቅኖባቸዋል። በቅርቡም ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ተብዬ እንዲቀርብ የተደረገው የ“ኮምፒዩተር ወንጀል አዋጅ ረቂቅ ሕግ“ ውስጡን በቅርበት ለሚመለከተው ሐሳብን የመግለጽ ነፃነትን መሠረታዊ መርህ ክፉኛ ከሚፃረረው ከፀረ ሽብር ሕጉ እምብዛም ያልተለየ ነው ተብሎ እየተነገረለይ ያለ ሌላ ሊደቀን የታሰበ ጋሬጣ መሆኑ የሚያጠያይቅ አይሆንም።
2015 .. በወጣው የነፃ ፕሬስ ምደባ ኢትዮጵያ ከ180 ሀገራትውስጥ 142ኛ መመደቧ ይህንኑ ገላጭ ነው። የ 2014 ሆነ 2013 ዘገባም የሚያሳየው ይህንኑ የሚያረጋግጥ ሲሆን ምንም መሻሻል እንዳልተገኘ የሚያመላክት ነው።
የወያኔ አገዛዝ የነፃው ፕሬስ ጠላት ተብሎ የተወነጀለውም በነዚህና በሌሎች ምክንያት ነው የሩቁን ትተን በቅርቡ እንኳ የአዲስ አበባን አጎራባች ከተሞችን ወደ አዲስ አበባ ለመጠቅለል የወጣውን ማስተርፕላን በመቃወም በመላ ኢትዮጵያ በተለይም ደግሞ በኦሮሚያ ክልል ሕዝባዊ ተቃውሞና ቁጣ መቀስቀስና በዚሁ ምክንያት ከ 300 በላይ ዜጎች ተገድለው በሺህ የሚቆጠሩ መታሰርና መደብደብ፡በአማራ ክልል፤በወልቃዪት ጠገዴም ሆነ በደቡብ ኢትዮጵያ ገሙጎፋ ውስጥ የኮን ሶሕዝብ የመብትና የማንነት ጥያቄን በአግባቡ ባለመመለሱ በሕዝብና በገዥዎች መካከል ያለው ክፍተት መጨመሩና ውጥረቱም መናሩ፤በየጊዜው የሚገደሉና የሚታስሩ ሰዎችም ቁጥር እየጨመረ መምጣቱ ባጠቃላይ የወያኔ አገዛዝ በሚወስዳቸው ኢሰብአዊ እርምጃዎች ለሕዝብ እንዳይገለጹ በጋዜጠኞች ላይ የሚያደርጋቸው ጥብቅ ቁጥጥር ሰለ ነፃፕሬስ ሁኔታ በኢትዮጵያ በተደጋጋሚ የተጋለጠበት ክስተቶች ናቸው። በቅርቡም በተለያዩ የኢትዮጵያ ከተሞችና ዩኒቨርስቲዎች የተፈጸሙትን ግድያዎች የጅምላ እስሮችና ድብደባዎች በሚመለከት ሪፖርቶች ሾልከው ለሕዝብ ይፋ እየሆኑ ብቻ ሳይሆን አጥፍዎቹ ለሕግ እንዲቀርቡ፣ተጎጅዎቹም

አስፈላጊው ካሳ እንዲሰጣቸው የሚደረገው እንቅስቃሴ የሁኔታውን አሳሳቢነት በሚገባ የሚያሳይ እንደሆነ ግልፅ ነው።የወያኔ አገዛዝ የነፃው ፕሬስ ጠላት ተብሎ የተወነጀለውም በነዚህና በሌሎች መሰል ምክንያቶች ነው። ሎች መሰል ምክንያቶች ነው። በ 2015 .. በወጣው የነፃ ፕሬስ ምደባ ኢትዮጵያ ከ180 ሀገራትውስጥ 142ኛ መመደቧ ይህንኑ ገላጭ ነው። የ 2014 ሆነ 2013 ..ዘገባም የሚያሳየው ይህንኑ የሚያረጋግጥ ሲሆን ምንም መሻሻል እንዳልተገኘ የሚያመላክት ነው።
ኢሕ አፓ እንደ ሌሎች ሰላም ወዳድ ሃይሎች ሁሉ በሀገራችን የፖለቲካው መድረክ ለሕዝቡ በተለይም ደግሞ ለነፃው ፕሬስ አባላት ደህንነት የተመቻቸ እንዲሆን ይታገላል። ለዚህም በጋሬጣነት የተሸነቆረውን የወያኔ አገዛዝ አጥብቆ ያወግዛል። በዛሬው እለት አለም አቀፍ የፕሬስ ነፃነት ቀን ሲከበርና ሲዘከር ኢሕአፓ በኢትዮጵያ ኃሳብን በነፃ የመግለፅ መብት እንዲከበርና ከማናቸውም የፖለቲካ ኃይል ጣልቃ ገብነት የተላቀቀ ለሕሊናውና ለሕዝብ ተጠያቂ የሆነ ነፃ ፕሬስ እንዲኖር፤ አባላቱም ሕዝብ የማወቅ መብት አለው በሚለው መርህ ሥር ሥራቸውን በነፃነትና ደህንነታቸው ሳይደፈር የሚያከናውኑበት የፖለቲካ ምህዳር እንዲፍጠር መታገሉን ያለመታከት ይቀጥልበታል። በአሁኑ ወቅት የሕዝብ የመገናኛ ዘዴዎች በከፍተኛ ደረጃ ባደጉበት ነፃ ፕሬስን በተለያዩ ደረጃዎች ለማፈን የሚደረጉና እየተደረጉ ያሉ ማናቸውንም ጥረቶች ብሎም አባላቱንም በሽብርተኝነት ሥም ጥላሸት መቀባት ወንጀልና በሕግም የሚያስጠይቅ እንደሆነ በዚህ ክብረ በአል ቀን በጥብቅ ያሰምርበታል። ለተግባራዊነቱም የበኩላችንን አስተዋፅዖ ማበርከታችን የሚቀጥል ይሆናል።
ነፃ ፕሬስ በችሮታ ሳይሆን የትግል ውጤት ነው!! 

No comments:

Post a Comment