Monday, June 6, 2016

ትግላችን ለምን? ( http://www.finote.org )ትግላችን ለምን?

በየማጠፊያው ስንደርስን በተለይም ጠላቶች የሚፈጥሩት ውዝንብር ሲስፋፋና ብዙሃኑን ሲያደናግር ትግላችን ለምን?የትስ
page1image5168
ደርሰናል ብሎ መጠየቁና ምላሽም ማግኘቱ አስፈልጊ ሆኖ ይገኛል ።
በህዳር 1984 ዓ.ም. ትግላችን ለምን ለሚለው ጥያቄ በመልዕክተ ኢሕ አፓ (ቅጽ1 ቁ 3) የሚከተለውን አስፍረን ነበር
"የ ኢትዮጵያ ታጋይ ልጆች ለዓመታት ያካሄዱት መራራ ትግልና ተከፈሉት ከባድ መስዋዕትነት ከድጡ ወደ ማጡ ለመሰጥ ወይም ከጭቃ ለመግባት አልመሆኑ ይታወቃል ።የቃላት ጋጋታ፤ሀተትዝ፤መግለጫ፤ አዋጅን የመመጻደቂያ ልፈፋዎች ሊጋርዱት ያልቻሉት ሀቅ ካለ ሀገራችን በአስከፊና በጣም አደገኛ ሁኔታ ላይ አንዳለች ነው ። ሰላምና መረግጋት ቢሉም በሰላም ፈንታ ጦርነት፤በመረጋጋት ፈንታ ብጥብጥ ሰፍኖ ይገኛል" ።
ይህን ያልነው ወያኒ አደናጋሪ ልፈፋውን ሲያጧጥፍና አጃቢዎቹም ሲያስተጋቡለት በነበረበት ጊዜ ነው ። ስለምና መረጋጋት እንዳልሰፈን ግልጽ ቢሆንም ዘርዘር አድርጎ ማስረዳቱም አስፈላጊ ነበር ። በመሆኑም መል ዕክቱ በመቀጠል የሚልከተለውን አስፍሮ ነበር ፤
" የዴሞክራሲ ጸሐይ አበራች ቢሉንም ጋርዶን የከረመው የኢዴሞክራሲያዊነት ደይን አሁንም እንዳልጠፋ ሊቃወም ከጅሎ ጥይት የዘነበበት፤ እገዳ የደረሰበት፤ የታሰረ የትጉላላ፤የተሰደደ ሁሉ የሚያውቀው ንው ። ለኢትዮጵያ ሉዓላዊነት ና አንድነት፤ለህዝቧ መብት፤ለእኩልነትና ደህንነት ገና ከጥዋቱ የጀመርነው ትግል፤የገባነው ቃል ኪዳን አሁንም ህያው ሆኖ መቀጠሉ ተገቢ እንጂ ሌላ ሆኖ አላገኘነውም። ትግላችን ቀጥሏል። የትግላችንንም መሰረትና ይዘት ደግሞ ከሁኔታዎች ለውጥ ጋር አገናዝብ ማረቡ የግድ ይሆናል።
ኢሕ አፓ በብሄር ብሄረሰቦች እኩልነት ላይ ለተመሰረተ ሀገራዊ አንድነት ይታገላል። ስለሆነም ኢትዮጵያ መንገንጠል አለባት፤ቅኝ ገዢ ሀገር ናት፤ሕዝቦቿ በአንድነት ሊኖሩ አይችሉም ወእተ የሚሉትን አቅዋሞች ሁሉ በጥብቅ ይቃወማል ። የኢትዮጵያ ሕዝብ ዴሞክራሲያዊ መብቱን ተቀዳጅቶና ነጽ ሆኖ ባልመከረበትና ባልወሰነበት ሁኔታም የኢትዮጵያን ግዛታዊ ክልል ለመቁረስ በተናጠል የሚደረጉ ውሳኔዎችን ኢሕአፓ አይቀበልም ።ኢሕ አፓ የመድብለ ስር ዓትን ለሚያንጸባርቅ ዲሞክራሲያዊ ሪፑብሊክ ይታገላል። ኢሕ አፓ በሃይማኖቶች እኩልነት የሚያምን ሲሆን በፖለቲካ ወይም በመንግስትና ሃይማኖት መሃል ሉነት መኖሩ መሰረታዊ ነው ይላል። ኢሕ አፓ በኤኮኖሚ መስክ በይጥ ኤኮኖሚ መርህ ያማንል ።ኢሕ አፓ ኢትዮጵያ የገለልተኝነት ፖሊሲ በመከተልጥቅሟን ለመጠበቅ ከሁሉም ሀገሮች ጋር የወዳጅነት ፖሊሲ መከተል አለባት ሲል በተ፤እይም ለአፍሪካ አንድነት ተገቢውን አስግተዋጾ ማድረግ ይገባታል ይላል ። 
ኢትዮጵያ ከውጭ ትቃት የሚከላልከል ከሕዝቡ የተውጣጣ፤ከፖለቲካ የራቀ ሙያተኛ ብሄራዊ ጦር ሊኖራት ይገባል ። ኢሕ አፓ በልዩ ልዩ ምክንያት በእድገት ደረጃቸው በጣም ዝቅ ያሉትን የሀግሪቷ ክፍሎችን ልዩ ትኩረት መስጠት ያሻል ይላል ። ሴቶች በእኩልነት ደረጃ በሀግሪቷ የፖለቲካ ኤኮኖሚያዊና ማህበረሰባዊ ህይወት ውስጥ ተሳትፏቸው እንዲረጋገጥ መደረግ አለብት ይላል ። ኢሕ አፓ የሚታገለው አንድ ፓርቲ ሥልጣን ጨብጦ በአውቅላችኋለሁ እብሪት በሕዝብ ላይ እንዲፈነጭ ሳይሆን ሕዝቡ ልዕልናው ተጠብቆ የሚበጀውን አስተዳደር በነጻ ምርጫ እንዲወስን ነው ። 
ትግላችን ለተሸራረፈ ጎዶሎ ዴሞክራሲ ወይም የይስሙላዴሞክራሲ ሳይሆን ዜግነታችንና ሌላውም መብታችን በሙሉ በሚከበርበት ላልተገደበ ዴሞክራሲ ነው ።
ኢሕአፓ የነበረውን ሁኔታ መሰረት አድርጎ አቅዋሙን በዝርዝር የገለጠው የትግሉን ይዘትና አቅጣጫ ለማሳየት፤ለማስጨበጥ ነበር ። የትግሉን ይዘት ሊያስገነዝብ የቻለው ተጨባጩ ሁኔታ በሚገባ በማጤን ነው ። ዛሬም ትግላችም ለምን ስንል (በመሰረቱ የተለወጠ ብዙ ባይኖርም ከወያኔ ልፈፋ ውጪ)ያኔም የያዝነውን የትግል መርሆዎች የሚያስተው የሁኔታ ለውጥ ወይም ክርሁለገብ ትግል ውጪ ሌላ የትግል ስልትን የሚያስይዝ ሁኔታ የለም ። እንዲያውም መለስ ብለን ወደ የካቲት 66 ስንመለከት ያኔ የሕዝብ መፈክር የንበሩት (መሬት ለአራሹ፤ዴሞክራሲ ለሕዝብ፤ እኩልነት፤ የሀገር ሉዓላዊነት ወዘተ) አሁንም ምላሽ አልባ ሆነው ይገኛሉ ።ለዚህም ነው ከያኔው የሚከተለውን አቅዋሜ ብሎ ያሰፈረው፡
" ኢሕ አፓ በደም የገበየውን ተመክሮ ገምግሞ፤ስህተቱን አርሞ፤አቅዋሙን ከኢትዮጵያና ኸሕዝቧ ጥቅምና ፍላጎት ጋር አስተካክሎ እየተአገለ ያለ ድርጅት ነው ። ኢሕ አፓ ከሰፊው የኢትዮጵያ ሕዝብ መሰረታዊ ፍላጎትና አቅዋም የተለየ አቅዋም የለውም ። ከሕዝብ ጋር ሆኖ የሚታገእውም ለሕዝቡ ዓላማ እንጂ ሌላ ተልእኮ ኖሮት ወይም እንደ ወያኔ/ለኢትዮጵያ ቆሜያለሁ እያለ በሽፍን ጽረ ኢትዮጵያ ፖሊሲዎችን ለማራመድ አይደለም።
ኢሕ አፓ ለእኩልነታ ለዴሞክራሲና በዚህ ላይ ለተመሰረተ የህገር አንድነትና ሰላም ይታገላል። ዴሞክራሲ የሕዝቡ አንድነትና ሰላም የማይነጣጠሉ ፤የማይገደቡና ቁሚ መፈክሮች፤መርሆዎች፤መመሪያዎች ናቸው "።
መሰረታዊ አቅዋሞች፤ትግላችን ለምን እንደሆነ የሚገልጹት፤ ግባችንን ጠቋሚዎቹ መሰረታዊ ለውጥን ባያሳዩም ወያኔ ባለፉት 25 ዓመታት ባሳየው የግፍ አገዛዝ ይዞታ መሰረት ፍልሚያችን እንዴትና ለምንስ ተጨማሪ መፈክሮች የሚለውን ማጤኑ ሊታለፍ የሚገባውው አይደለም ። በዋን ፈርጁ ግን ትግላችን የወያኔን ዘረኛ አገዛዝ ለማውደም ነው ። ለማለሳለስ ወይም በጥገና ለውጥ ለማሻሻል ሳይሆን
--ይህ የሚቻልና የሚሆን አይደለምና-- ስርዓቱን ድራሹን ለማጥፋት ነው ። በዚህ ላይ ግልጽነት ከቀደም ተግባር ላይ መደናገርና መወላወል ሊከተል አይችልም ። ወያኔ ሥልጣን ይዞ አጥፊ ስር ዓቱን ሊያደላድል ሲጥር ኢሕ አፓ ገና ከመጀመሪያውና እንዲያውም ሥልጣን ከመያዙ በፊት አደጋ መሆኑን አጋልጦ ለትግል ጠሯል ። በአንጻሩ ደግሞ ዛሬ ያዙን ልቀቁን ዋና ጸረ ወያኔ ነን ሊሉ ሚከጅሉና ድርጅቱንም ለማውገዝ ድፍረቱን ያገኙ ክፍሎች ያኔ ከወያኔ አብረው ወይም ከዚህ ከይሱ ድርጅት ጋር አብረው እየሰሩ እንደነበር የምናስታውስ መሆናችንም መጠቀስ አለበት ። መደገፍ ወይም መወላወል ሰፈነና ወያኔ በስልጣን ሳይደላደል በጋራ ታግሎ ለማስወገድ አልተቻለም ። የያኔ የወያነ ወዳጆችና ሕዝብ አደናጋሪዎች ምን ያህል ኢትዮጵያን እንደጎዱም መርሳት አያስፈልግም ።
ትግላችን ለተሸራረፈ ዴሞክራሲ ወይም በጽንፉ ደግሞ የኢትዮጵያን ህልውና ሚጻረር የግንጠላ ሂደትን ዕድል ለመስጠት አይደለም ። ደማችንን ልናፈስ የተዘጋጀነው ሰው በላ ካፒታሊዝምን በሕዝብ ላይ ለመጫን ወይም አንዱን አማብገነን ብሌላ ለመተካት አይደለም ፡፤ ለኢትዮጵያ ሙሉ ነጻነት እንጂ ሀግራችንን ለባእዳን ለመሸጥ አንታገልም ። አንወይንም በሌላ ስም ማለት ነው ። ወያኔን ስንታገል በዚያው ልክ የሕዝብን ጎራ እያመሱ ያሉትን የቀጥታ የእጅ አዙር ወዳጆቹንም ማጋለጥ፤ መታገል እንዳለብን ግልጽ ሆኖ አለ ። የወደቀው ፋሺስታዊ አገዛዝ የተረፉ መሪዎችና ወንጀለኛ ካድሬዎችም ሊያንሰራሩ እየተፈራገጡ ናቸውና ቸል ሳንል እነዚህን ትኋኖች የሚገባቸውን መስጠት ሌላ የማይናቅ ግዴታ ሆኖ ይገኛል ። ሀቁን
አውቆና ተናግሮ ሀገር ያድኗል ማለትም እንችላለን ። ጠላቶች ነጋ ጠባ ሊያደናግሩን ከቻሉን ሀገራችንን ሊነጥቁን መቻላቸው የሚጠበቅ ነው ። ከ 25 ዓመት የመከራ ተመክሮ በኋላም አሁንም በመድረክ ወጥቶ ከወያኔ ጋር የሰላም መፍሔ ለመፈለግ ተነስተናል ማለት ይህን የሚሉት ሰዎች ሰልፍ ከማን ጋር እንደሆነ ጠቋሚ ነው ።
ትግላችን ጸረ ወያኔና ጭፍሮቹ ነው !

ትግላችን ለኢትዮጵያና ለዴሞክራሲያዊ አንድነቷና ሉዓላዊነቷ ነው ።

No comments:

Post a Comment