Thursday, June 2, 2016

www.finote.org

ፍኖተ ራዲዮ በየእለቱ የማያቋርጥ ወቅታዊ ዜናዎችን፣ሀተታዎችን፣የደብዳቤዎች አምድ
ቃለ መጠይቆች እና የተለያዩ ሀገራዊ ጉዳዩችን ከባህል ከኢኮኖሚ ከፖለቲካ ከስፖርት እና ከሙዚቃ ጋር በተገናኘ መልኩ በሳተላይት ስርጭቱ ያስደምጣል።
ሀሳባችሁን በሳምንታዊው የደብዳቤዎች አምድ ዝግጅት ላይ ማስተላለፍ የምትፈልጉ ዜጎች በሙሉ
Finote Democracy P.O.Box 73337 Washington DC 20056, USA
Web site: www.finote.org Email: efdpu@aol.com
Phone: 1-202-291-4217
ብላችሁ ብትፅፉ ይደርሳል።
አንድ አድማጭ ከእምድብር የላከው ትዝብት እንዲህ ነበር
ሰላም ፍኖተዎች፡፡
ወያኔ በኢትዮጵያ ሕዝብ ጫንቃ ላይ ከተፈናጠጠ ሃያ አምስት አመት ደፈነ፡፡ ይህ አረመኔ ቡድን በየከተማው ሕዝቡን በግዳጅ እየሰበሰበ የውሸት ጣቃውን እቀደደ ነው፡፡ ፎቶ አይዋሽም በሚል በየአውራ መንገዱ ድንኳኖችን ጥሎ የሟቹ አረመኔን ፣ የኮንዶሚኒየም ህንፃዎችን፣ የመንገዶችን፣ የፈረደባቸው የኤሌክትሪክ ኃይል ግድቦችን፣ የቻይና፣ የቱርክ፣ የህንድ፣ የወያኔ ፋብሪካዎችን ፎቶዎች ለጣጥፎ እያሳየ ይገኛል፡፡ የሚገርመው ወያኔ ከዓለም ባንክ፣ ከዓለም የገንዘብ ድርጅት፣ ከቻይና ባንኮች፣ ከህንድ ባንኮች፣ ከጣሊያን ባንኮች፣ ከፈረንሳይ ባንኮች፣ ከእንግሊዝ ባንኮች፣ ከጀርመን ባንኮች፣ ከደቡብ አፍሪካ ባንኮች፣ ከናይጄሪያ ባንኮች፣ ከአፍሪካ የልማት ባንክ፣ ከአሜሪካ ባንኮች፣ ወዘተ. የተበደረውን የሚያሳይ ምንም ዓይነት በግራፍ የተደገፈ መረጃ አለመቅረቡ ሕዝቡን አሳዝኗል፡፡ ወያኔ ኢትዮጵያን በእዳ ማጥ ውስጥ እንደዘፈቃት የሚታወቅ ነው፡፡ የወያኔ ቁንጮዎች በበድር ስም ገንዘብ ከውጪ ከማንኛውም አበዳሪ ድርጅት ከተገኘ ይቀበላሉ፡፡ ከእያንዳንዱ ብድር ላይ በትንሹ ሃምሳ ከመቶውን ውያኔዎቹ ይቀራመቱታል፡፡ እዳውን ለመከረኛው ሕዝብ ይተዉታል፡፡ ከዚህ በተጨማሪም በፎቶ ኤግዚቢሽኑ ላይ ወያኔ የጨፈጨፋቸውን ወጣቶችና ዜጎች ፎቶዎች አላቀረበም፡፡ የእነ ህግ ባለሙያው ተስፋዬ ታደሰን፣ የሰብአዊ መብት ተሟጋቹ አሰፋ ማሩን፣ የወጣት ታጋይዋን የሽብሬን፣ በሺህ የሚቆጠሩ በወያኔ የተገደሉ ወጣቶች ፎቶዎችን አላቀረበም፡፡ በአረካ፣ በበደኖ፣ በአርባ ጉጉ፣ በጋምቤላ፣ በአርባ ምንጭ፣ በጂማ፣ በአምቦ፣ በናዝሬት፣ በወልቃይት፣ በኦጋዴን፣ በአንዋር መስጊድ፣ በሻሸመኔ፣ በአርሲ፣ በትግራይ፣ በዴዴሳ፣ ወዘተ. የረሸናቸውንና ያረዳቸውን ወጣቶች ፎቶዎች አልጠፈም፡፡ ወያኔ በየወታደር ካምፑ ጥያቄ በመጠየቃቸው ምክንያት የረሸናቸውን መኮንኖችና ባለ ሌላ ማዕረግ ወታደሮች ፎቶዎችን አለጠፈም፡፡ ወያኔ የረሸናቸውን ፖሊሶችና የደህንነት ሠራተኞቹን ፎቶዎች አለጠፈም፡፡ ወያኔ ሆን ብሎ ያስፋፋቸውን የእርቃን ዳንኪራ ቤቶችን፣ የሀሺሽ ማጨሻ ቤቶችን ዝርዝር አልጠፈም፡፡ የወያኔ ቁንጮዎች የዘረፉት ገንዘብን ከባህር ማዶ ስውር ባንኮች መሸሸጋቸውንና መጠኑን የሚያሳይ ሰንጠረዥ አልጠፈም፡፡ በገሀድና በስውር እስር ቤቶች የሚያሰቃያቸውን ዜጎች ጋዜጠኞችን የፖለቲካ ድርጅቶች መሪዎችንና አባላትን፣ የሙስሊም መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ አባላትን፣ ፎቶዎች አልለጠፈም፡፡ የወያኔ ቁንጮዎች ቅምጦቻቸውን የሚሳይ ዝርዝር አልጠፈም፡፡ የኢትዮጵያ ሕዝብን ያታለሉ መስሏቸው በቴቪዥንና በሬድዮ የሚወሻክቱት አንሶ በዚህ የድንኳን የፎቶ ኤግዚቢሽን እየወሻከቱ ነው፡፡ ፎቶ ይዋሻል፡፡ ሕዝቡ ግን እውነቱን ያውቃል፡፡ ወያኔ የሕዝብ ደም መጣጭ አውሬ መሆኑ እንኳን ኢትዮጵያዊ ዓለም ያውቀዋል፡፡ ወያኔ ገዳይ፣ ወያኔ ደም አፍሳሽ፣ ወያኔ ዘራፊ፣ ወያኔ ተራ ወሮ በላ ቡድን ነው፡፡ ወያኔ ገበናውን ሙሉ ልብስ በመልበስና ክራቫት በማሰር ለመሸፈን ቢሞክርም የተነከረበት የሕዝብ ደም ነውና ይሸታል፡፡ ይህን የገማ የገለማ ዘረኛ ቡድን መንግለን ሕዝባዊ ስርዐት ለማስፈን እንታገላለን፡፡ ወያኔ ደመኛ ጠላታችን ነውና እንጠራርገዋለን፡፡
አበጋዝ ከእምድብር

No comments:

Post a Comment