Wednesday, July 27, 2016

ሕዝባዊ አመፅ ፤ ያለመሪ ድርጅት ግቡን ሊመታ አይችልም ! በፍኖተ ሬዲዩ የተላለፈ ወቅታዊ ሀተታ
 ቀደም ሲል የተካሄደውን ሕዝባዊ አመፅ ፤  በታሪክ መዝገብ ውስጥ እናቆየውና፤ ለአለፉት 25 ዓመታት ብቻ ወያኔን ለመጣል የተደረጉትን  እምቢተኝነቶችን ፤ እንኳን ብንመለከት ፤ ይኽ ነው የማይባል ተጋድሎን የተላበሱ አመፆች  ተካሂደዋል። ተከናውነዋል ። በዚህም፤ የብዙ ሕዝብ  ህይወት ፍቷል ። ግምቱ ልታወቀ የበርካታ የሀገር ሀብት-ንብረት ወድሟል ። የንፁሃን ዜጎች  ደም በግፍ ሷል  ።  መዳረሻቸው የት  እንደገባ የማይታወቁ ሠላማዊ  ኢትዮጵያውያን  የውሃ -ሽታ ሆነው ቀርተዋል።  ምናልባት  የስም ዘርዝራቸውን ሊያውቁ የሚችሉት  ቤተ ሰቦቻቸውና  የቅርብ ዘመዶቻቸው  ይሆኑ ይሆናል ።
  አልገዛም ባይነት ፤ በእንቢተኛነት እየታጀበ የሚካሄደው ሕዝባዊ አመፅ ፤አሁንም በየአቅጣጫው በመቀጣጠል  ላይ ይገኛል።   ይኽ ሕዝባዊ አመፅ፤ በመሠረቱ ግብታዊ ነው ለማለት ባያስደፍርም እንኳ፤ ብቃትንና ኃላፊነትን የተመረኮዘ አመራር  ባለመግኘቱ፤  በመሰነጣጠቅ ላይ ያለውን የወያኔን አገዛዝ መዋቅር ሊያናገው የሚችል ኃይል መሆኑን  ገና አላስመሰከረም ።  ፈጠነም  ዘገየ ፤ ማስማስከሩ ግን አይቀርም ። በወቅቱ ግን፤ የአገዛዙን አከርካሪ ኣጥንት ለመስበር የሚያስችል ኃይል በጁ አላስገባም ።  አመፁ፤ ከነባቢነት ወደ ተጨባጭ ድርጊት ገና አልተሸጋገረም።  ቋንጃ  ነካሽ ጥርስ፤  አከርካሪ አጥንት ሰባሪ ጡንቻ ፤ አላገኘም ።  ያ ቀን ሲመጣ ግን ፤ ያኔ  ወዮለት!!  
በአጭሩ፤ እስካሁን  የተከፈለው መሥዋዕት የተፈለገውን ውጤት አላስመዘገበ ። ይኽም ሊሆን የቻለው፤ ሕዝባዊውን እንቅስቃሴ ሊመራ የሚችል፤ አመራር  መታጣቱ እንደሆነ አያከራክርም ። ብቃት-ንቃት- ያለው፤ የሕዝብ ታማኝና አይበገሬ አመራር መኖር ፤ ለማነኛው ትግል ወሳኝ መሆኑን መዘርዘር አይኖርብንም። አውራ የሌለው ንብ እንደሚበታተን ሁሉ፤ ሕዝባዊ አመፅም ፤ መሪ ከሌለው ፤መቅኖ አይኖረውም። ይህንን ለመዳት ደግሞ፤ መፅሀፍ መግለጥን አይጠይቅም።
የመሪ ድርጅትን  አስፈላጊነትና ጠቃሚነት አስመልክቶ፤ የኢትዮጵያን ሕዝብ ለመምከር ብቃት ይኖረኛል የሚል ክፍል እንደሌለም አናምናለን ። ምክንያም፤  እስካሁን ድረስ ኢትዮጵያ ነፃነቷን ሳታስደፍር የቆየችው፤ በቆራጥ መሪዎችና በጀግና ሕዝቧ ትብብር እንደነበር እናውቃለንና !
የዛሬይቱ ኢትዮጵያ፤  ጀግና  ሕዝብ  እንጅ ፤  ዐመኔታ የሚጣልበት  ቆራጥ መሪ ድርጅት እስካሁን እንደሌላት  የታወቀ ነው ።  በዚህ ምክንያት አሁን፤ የሕዝቡ አመፅ ፤ አንድ ትልቅ አስፈላጊ ኃይል ጎድሎታል ። ያ እስካልተሟላ ድረስ ደግሞ ፤ትግሉ ያመረቃ ውጤት ያስመዘግባል ማለት አስቸጋሪ ነው ።  ሕዝቡ፤ የሚታመኑ መሪዎችን  ካላወጣ፤ ዕውተነኛ መሪ ድርጅትን በተውሶ  ማግኘት አይቻልም ። ካሁን በፊት፤ በተውሶ  የተላኩት የባዕዳን  ምልምሎች ፤ ለኢትዮጵያ ሕዝብ እንደማይጠቅሙ በወያኔዎቹ ተረጋግጧል ።
ዕውነተኛ መሬዎችን ለማግኘት ከተፈለገ ፤ የሚከተሉት  መሠረታዊ ጉዳዮች ቅድሚያ ሊሰጣቸው ይገባል ።
ሀ.  በኅብረተሰቡ  መካከል መተማመን እንዲኖር  ቅድሚያ  ሊሰጠው የግድ ነው ። ማነኛው ኅብረተሰ በሚገባ ተዋውቆ  እርስ በእርስ ከተማመነ ፤ ከመካከሉ ታማኝ መሪዎቹን ፤ ማውጣት- መምራጥ- መመራትና መተባበር - ብሎም ተፈላጊውን ውጤት ማስመዝገብ ይቻላል። ያ ካልሆነ ፤ ትርፉ፤እንደ ገበታ ውሃ ዋልሎ  መቅረት ነው  ! ፍላጎቱ ሁሉ፤ እንደ በ  ንብልብሊት/ የማይጨብጡት ተስፋ ሆኖ ይቀራል።
ለ.  በተቃዋሚ ድርጅቶች መካከልም እንደዚሁ፤ መተማመን መኖሩን ማረጋገጥ አለባቸው ። እስካሁን ድረስ ይኽ  ቁልፍ ጉዳይ፤ በመካከላቸው አልታየም። ያ በመሆኑ፤ እስካሁን ኅብረት ሊፈጥሩ አልተቻላቸውም።  መተማመን ከሌለ ደግሞ፤ እንኳንስ ኅበረት ፈጥሮ ቁም ነገር መስራት ይቅርና፤ በአንድ ሀገር ላይ በሠላም  መኖርም፤ ቢሆን  ያዳግታል። ይኽ ዘረኛ አዛዝ ደግሞ፤ ሕዝቡ  እርስ በእርሱ እንዲተማመን አይፈልግም፤ ይልቁንም፤ በቋንቋና በክልል እየከፋፈለው ዕኩይ ተግባሩን የቀጠለበት ሁኔታ ነው ያለው።  ይኽም በበኩሉ፤ ወያኔ እንደልቡ እንዲፏልል አስችሎታ ። ሀገሪቷም ጀግና አልባ መሬት መስላለች !
ሐ.  ከላይ በተጠቀሱት ምክንያቶች፤  ሕዝባዊው አመፅ  ባለቤት ሊያገኝ አልቻለም ። በየወቅቱ እየተቀጣጠለ የመምጣት  ክስተት ቢያሳይም፤ በጣይነት እየተጋጋለ መራመድ እያስቸገረው ነው።  ሕዝባዊ አመፅ ፤ በግብታዊነትም ይሁን ስ በስ በሂደት እየተጋጋለ ቢቀጥልም ፤ ዞሮ ዞሮ ሁነኛ መሪ ድርጅት እስካላገኘ  ድረስ ፤ ቅ- ድርግም፤ ከማለት የተሻለ ርምጃ መሳየት አልቻለም። አይችልምም ።
 ምናልባት  ውሎ-አድሮ፤ ይኽን ሁኔታ አድፍጦ የሚከታተል ማነኛውም ነጣቂ  ቡድን ክፍል ካለ ፤ ( አይኖርም ብሎ መሞኘት አይቻልምና )  በውጭ ባዕዳን ኃይሎች ድጋፍና ትብብር፤ ሥልጠናም  ሆነ  መመሪያ በማግኘት፤የባዕዳን  ጥቅም አስጠባቂ አልጋይ ሊሰየም የሚችልት ሁኔታ ሊከሰት ይችላል። ሁል ጊዜ " ከሞኝ በራፍ ፤ ብልሆች ሞፈር ስለሚቆርጡ " ባለቤት ያጣ ሕዝባዊ አመፅም እንዲሁ ፤  የሕዝቡን  አቸናፊነት  አድብተው በሚጠባበቁ ኩላዎች  መነጠቁ አይቀርም።  ይህ አጋሚ፤ ካሁን በፊት ፤ በሀገራችን ሁለት ጊዜ ተጽሟል።  እርሱም ፦
1ኛ. የስድሳ ስድስቱ  ገናናው የኢትዮጵያ ሕዝብ ዐብዮት፤ ሥልጣን ለመያዝ ባቋመጡ ፤ ጥቂት መኮንኖች ተነጥቆ ፤ ሀገራችን አሁን ለደረሰችበት  ቅት፤ ምክንያትና ድልዳል ሆኗል። ሕዝቡ በነፃ ተደጅቶ ሀገሩንና ነፃነቱን ጠብቆ፤  የሀገሪቱን አንድነት  አስከብሮ፤ ሥርዓተ- ዴሞክራሲ እንዳይመሰት መና ሆኖ ቀረ ።  ለአስራ ሰባት  ዓመታት መራራ ትግል ቢካሂድም ፤ የሕዝቡ አመፅ ትክክለኛ አቅጣ ይዞ ለድል መብቃት ባለመቻሉ  ሁለተኛዎች ነጣቂ ተኩላዎች  ጠቃ   ተበላ።  አመፁም ተኮላሽቶ  ደብዛው ጠፋ ።  አመጹን ካሄደው የምልዐተሕዝቡ ትርፍ ግን ፤ እየየ ሆኖ ቀረ !
2ኛ.  ስራ ሰባቱ   ዓመታት  ሕዝባዊ መራራ ትግል፤ ሁነኛ ሀገራዊ  መሪ ለማግኘቱ፤" የብሄር- ነፃ-አውጭ " ነኝ የሚል ብሄረተኛ ቡድን አድፍጦ ጠብቆ ፤  በባዕዳን ድጋፍና ትብብር ፤ ቀላጤና ትዕዛዝ ፤ የኢትዮጵያን ሕዝባዊ አመፅ ነጠቀው።  ይኽ ዘረኛ ቡድን የአገዛዙን መድረክ ከተቆጣጠረ ጀምሮ ፤ ላለፉት የመከራ ዓመታት የፈፀመውን፤ ሁሉም ስለሚያውቀው፤ በዚያ ላይ ሩ አሰልች ስለሚሆን ማለፉን መርጠናል
 ግን ፤ ዛሬስ ለሦስተኛ ጊዜ ይኽ የአሁኑ ሕዝባዊ አመፅ፤  በሌሎች አድፋጭ  ድኖች፤ የማይነጠቅበት ምን ምክንያት ይኖራል ? ይኽ አድፋጭ ቡድን፤ የት፤ መቸ፤ እንዴትስ እንደሚንቀሳቀስና  አድብቶ እንደሚጠቃ፤ ማን በዕርግጠኝነት ሊያውቅ ይችላል ?    እነዚህንና ተመሳሳይ ጥያቄዎችን  በኣጥጋቢ ሁኔታ ለመመለስ፤ በግድ ሕዝባዊው አመፅ ሁነኛ  መሪ ድርጅት የሚያስፈልገው  ለመሆኑና በጎጥ ሳይሆን በኢትዮጵያዊነት መሰረት መታገል መገባቱ ፤ አንድና ሁለት የሚባልበት  አይደለም ።                     
በዚህም ተባለ በዚያ፤ ምንም ተባለ፤ ምን ፤  የሕዝብ ብሶት ሞልቶ እየገነፈለ በሚመጣበት ጊዜ ሁሉ፤  መራራ አመፅ ፤ መካሄዱ የሚቀር አይደለም ፡፡   ከዚህም ጋር ተያይዘው፤  ከባድ  መሥዋዕትን  የሚጠይቁና ወደ ከፍተኛም ደረጃ የሚሸጋገሩ አመፆች  መምጣታቸው የሚያስደንቅ አልነበረም ።  የሕዝቡ ጥያቄ ተገቢውን መልስ እስካላገኘ ድረስ፤  ሕዝባዊው ትግል፤ በመረረ መልኩ እየተቀጣጠለ መሄዱን  ይቀጥላል ። አገዛዙ ደከመም አልደከመ፤ መግዛት እየተሳነው መጣም አልመጣ፤ ሕዝባዊው አመፅ በቀጣይነት እየተቃጠጠል መቀጠል አለበት።  ደግሞም ይቀጥላል !
አልዛም ባይነት፤  የመራራ አገዛዝ ውጤት ነው ።   አመፁ ግቡን እንዲመታ ካስፈለገ፤ የሕዝብ ታማኝ የሆኑ ድርጅቶች፤ አመራር ሊሰጡ ግድ ይላል። አመራር ማለት ድርጅት ነው። አመራርንና ድርጅትን ነጣጥሎ ማየት ከንቱ ትካዜ፤ ላላ ውዳሴ ይሆናል።  በድርጅት የሚመራ ሕዝባዊ እንቅስቃሴ አስተማማኝ ዓላማና ግብ ይኖረዋል።  የተነሳበትን አቅጣጫም ሊስት አይችልም።  ብቃትና ጥንካሬ ባለው አመራር ከተመራም፤ አሸናፊ እንጅ ተሸፊ የሚሆንበት ዕድሉ  የጠበበ ይሆናል።  
 ሰሞኑን፤ በሰሜናዊው  የሀገራችን ፤ ክፍል  በሆነው ጎንደር፤  የተቀጣጠለው ትግል ፤  በመላው የሀገሪቱ  ፤ግዛት ከሚካሄደው  ሀገራዊ ትግል ጋር፤ አንድ አካል-አንድ አምሳል  ሆኖ ቀጥሏል ።  የጎንደርን ሕዝብ ቅስም ለመስበር የታቀደው የወያኔ ጠላትነትም ሕዝቡን ሊበግረው - ሊያስበረግገው  እንዳልቻለ አስመስክሯል ።  ምናልባት ፤ ሊዘገይ ይችል ይሆናል እንጅ፤ ፍርድና በደል፤ በፍትኅ ሸንጎ ፤ ዐይን ለዐይን የሚተያዩበት ቀን ሩቅ አይሆንም። የፍትኅ ሸንጎ፤ የራሱን ጊዜ ጥብቆ ይመጣል። በተበደሉት ወገን ቆሞ፤ ለተገፉት፤ ለተበደሉት ፍርዱን ይሰጣል።  ኢትዮጵያ፤ ዘለዓለም ፍርድ የጎደለባት ፤ፍትኅ- ርትዕ ደብዛው የጠፋባት ፤ ምድራዊ - ሲዖል፤ ሀገረ- ጉግ-ማንጉግ ሆና አትቀርም ።
በጎንደር የተነሳው ሕዝባዊ አመፅ፤ እንደ አኩሽታራ ( የእሬት ስር ) የጠፋ መስሎ፤ነገር ግን  ውስጥ -ውስጡን የሚቀጣጠል ዕሳት ነው። እንደ ቋያ እየተየያዘ ፤ እየተቀጣጠለ ፤ እየለበለበ ፤ እየፈጀ፤ እያቃጠለ፤ እያኮማተረ እያንገበገበ፤ እያወደመ መሄዱን ይቀጥላል። ዋ ! ይብላኝ ለግፈኞች ።  እግዚኦ ! ለሀገር ጠላቶች !   ለፍርድ ሸንጎ መቅረባቸው አይቀርምና !
ሆድ የባሰው ሕዝብ፤ አንገቱን የደፋ ትውልድ፤ ውርደትና ጥቃት የተፈራረቁበት ኅብረተስብ ፤  ቆርጦ ከተነሳ፤ አምርሮ ከተጠራራ፤ የድረስልኝ -ልድረስልህ መልዕክት ካስተላለፈ፤ በኢትዮጵያዊነቱ መሰረት ካበረ፤ የመጣው ቢመጣ የሚገድበው አይኖርም። በሀገራዊ መልኩ ከወገን -  ኃይላት ጋር አመፁን እያቀነባበረ  ፤ መሬት የሚያናውጥ ፤ አርዕድ- አቅጥቅጥ ሆኖ እንደሚቀጥል፤ መጠራጠር አይቻልም ።   ዛሬ የጎንደር ሕዝብ፤
 ትውልዳችን  ቆላ፤  ወንዛችን  ተከዜ ፤
ምን መጣብናል እምቢ ባልን ጊዜ።
ሀገራችን ጦቢያ  ድንበሩ ባሶንዳ፤
የደም ካሣ አንጠይቅ መቸ አለብን  ዕዳ፡፡
ርቡሽ በገላባት  አፍሮ ተመለሰ ፤
ቱርኩም በቀይ ባህር ክንዳችን  ቀመሰ፤
ጣሊያንም  በአድዋ ፤  ደም ዕምባ አለቀሰ፤
ዳግመኛም  በማይጨው፤ በደም ተለወሰ ።
ያኔ መጣ  እንጅ መሬት ለመቀማት፤ ደም እያፈሰሰ ።
የመቅደላው  አፅም  መች ተበተና፤ መቸስ ተረሳና፤
 ከታሪክ ማህፀን   ይፈጠራል  ጀግና፤ ይወጣል ሳታና  !

እያለ   ለማይቀረው  ፍልሚያ   ይጣራል    እርስ በእርሱ ይጠራራል    ለኢትዮጵያውያን   ወገኖቹም   የአንድነቱ  መል ዕክቱን   ያስተላልፋል። የትብብር ጥያቄ  ይጠይቃል። ኸቱን ያሰማል።  ቡታውን ይሰዳል።   አዲስ ታሪክ ይጽፋል ።  ትዝብቱን መዘግባል።  ያስመዘግባል !

ያ እንዳለ ሆኖ፤ ከወያኔ ጋር  የሞት -ሽረት ተጋድሎውን፤ በቅድሚያ መጋተሩን ይቀጥልበታል።  ዞሮ-ዞሮ፤  የማንኛው ሕዝብ ነፃ  መውጣት፤  የቅድሚያ  ኃላፊነት ፤ያው ራሱ ሕዝቡ   በገዛ  እጁ ስለሚሆን፤  ይህንን ሀቅ ተግንዝቦ፤ የኢትዮጵያ ሕዝብ የጀመረውን  ትግል  ይቀጥላል ።  አይከፍሉ መሥዋዕት እየከፈለ  !
         አመፁ፤እተቀጣጠለ እንዲሄድ ካስፈለገ፤ በመጀመሪያ ጥኖ የመድረሱ ኃላፊነት  የኩታ-ገጠም  ናዎች  መሆኑ እንደተጠበቀ ሆኖ በመላው ሀገሪቱ ፤ ሕዝባዊው አመፅ ፤ እንደ መንር ዕሳት  መያያዝ አለበት። ይህ አመፅ ለኢትዮጵያ ትንሳዔ  የመለከት ድምፁን ያሰማል  ! ይኽ ድምፅ ፤ መላው  የሀገሪቱ  ዜጋ  የሚተባበርበት  መልዕከተ- ብሥራት ነው  !      ይኽ  አመፅ ፤ ፀረ-ወኔ ትግል ነው ።  የጎንደርን፤የጋምቤላን ፤ የአምቦ ሐርርን ወዘተ አመፅ ፤ ኢትዮጵያውያን  ኃይሎች  በሙሉ እንዲተባበሩት  ጥሪ እናስተላልፋለን !

ኢትዮጵያ  ለዘለዓለም ትኑር  !  

No comments:

Post a Comment