Wednesday, July 6, 2016

ምሣር የበዛበት የመገናኛ ብዙሃን [Chopping Our Free Media]


ምሣር የበዛበት የመገናኛ ብዙሃን [Chopping Our Free Media]
page1image1144 page1image1304
የመገናኛ ብዙሃን፦ የሕትመት ውጤቶች (ጋዜጣና መጽሔት)በሬድዮና በቴሌቭዥን የሚተላለፉ እንዲሁም በኢንተርኔት የሚደረጉ የመረጃ ልውውጦች ማለት ነው።
የሃሳብ ነጻነትና የመገናኛ ብዙሃን መከበር የመብት ጥሰቶችን ለማጋለጥና ለዲሞክራሲያዊ ሥርዓት መሰረት ነው። ሀሳብን በነጻ የመግለጽ ነጻነት ለሰው ልጅ የተሰጠው ተፈጥሮአዊ ችሮታ ሲሆን ሰብአዊ መብትንና ክብርን የማስጠበቂያ መሳሪያ ነው።
ዜና የማግኘት መብት መኖር በተለያየ ደረጃ ለመልካም አስተዳደር መስፈን፣ የመንግሥት ተግባር ግልፅነትና የተጠያቂነት ግዴታ እንዲኖርበት አስተዋፅዖ ያበረክታል። በተለያዩ የመንግሥት ተቋማት ውስጥ የሚገኙ ችሎታ ቢስ ባለሥልጣናትን በነቂስ ለማውጣት፣ የሀገር ሀብት በባለሥልጣናት እንዳይባክን በአባላቱም እንዳይዘረፍ ነቅቶ ለመጠበቅና ለመከታተል፤ ከዚሁ ጋር በማያያዝም ሙስናን፣ ፍርደ ገምድልነትን፣ አድሎዎአዊነትን ለማጋለጥ ይረዳል። ከዚህ በተጨማሪ የተቀላጠፈ አስተዳደር ሂደትና የእድገት ጅማሮዎች ለፍሬ እንዲበቁ እንዲሁም ለተሻለ የኤኮኖሚ፣ የአስተዳደር አገልግሎትና ለተሻለ የሕግ ዋስትና መሰረት ይጥላል።
ነፃነቱን የተጎናፀፈ ማንኛውም ህብረተሰብ ፤ የዜና ምንጮቹ ነፃና ከማንኛውም ወገን ተፅዕኖ የሌለባቸው ተቋማት ከሆኑ የሥልጣን ብልሹነትንና በሙስና የሚታጀቡ ፀረ-ዴሞክራሲ ድርጊቶችን ለመቋቋም ብሎም ለማጋለጥ የሚቸግረው አይሆንም። ስለዚህም የዜና ማግኘት ነፃነት መኖር የተረጋጋ ማህበራዊ ምህዳር ስለሚፈጥር ለሕዝብ የፖለቲካ፣ ኤኮኖሚያዊና የፋይናንስ እድገት ያስገኛል።
የመገናኛ በዙሃን መብት መከበር ለአንድ ህብረተሰብ በጣም ጠቃሚና አስፈላጊ በመሆኑ የተለየ ሥፍራ ተሠጥቶት በዩኔሳኮ አቅራቢነት በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ጠቅላላ ስብሰባ በመስከረም 1993 .. በተወሰነው መሰረት ከ1994 .. ጀምሮ በአለም አቀፍ ደረጃ የአለም አቀፍ የፕሬስ ነፃነት ቀን እንዲከበር ሆኗል።
በሃገራችንም የነፃ ሚዲያ አመጣጥና ሂደት አሁን እስካለበት ድረስ፤ ሃሳብን በነፃነት ለመግልጽ ይደረጉ የነበሩና እየተደረጉ ያሉትን የተለያዩ ተሞክሮዎችን እንመለከታለን።
አብዛኛዎቹ ተሞክሮዎች የሚያሳዩን ገጽታ ለሌሎች እንዲናገሩና እንዲጽፉ የግድ መባልና በተጽዕኖ የሌሎችን እስትንፋስ የራስ አድርጎ የመተንፍስ ዓይነት ግዴታ ውስጥ መግባትና የታሪክ አጥፊነታቸው በመልካምነት ተፈርጆ በግድ እንዲነገር ማድረግ ነው። የመገናኛ አውታሮችን በመንግስት ቁጥጥር ስር በማድረግ መንግስትን እንዳይተቹ ተገምግመው እንዲወጡ፣ እንዲሁም የአምባገነኖች አስተሳሰብና አፈጻጸም በጭንቅላት ቀርቶ በጡንቻ መሆኑ ለነፃ ሃሳብ መብት መከበር ዋና ዋና ተግዳሮቶች ናቸው።
የወያኔ አገዛዝ የሕዝብን ሃሳብ የመግለጽ መብት ለመርገጥና ለመጨቆን ያለውን ኋይል ሁሉ ይጠቀማል። ቀስ በቀስ ሃገሪቱን በመዳፉ ስር ያስገባው ወያኔ ሃሳብን በነፃነት የመግለጽና የመገናኛ በዙሃን መብት መከበር ላሰበው ዓላማ ይህም ‘ኢትዮጵያንና ኢትዮጵያዊነትን’ የማጥፋትን ዘመቻን ለማራመድ እንቅፋት መሆኑን ለመረዳት ጊዜ አልፈጀበትም።
አንዲት ሃገር ኢትዮጵያ የምትገለጠው በሕዝቧ አንድነት፤ በትግል የጸናው የሕዝቧም አንድነት መገለጫው ህብረቱ ሲሆን የዚህ ኋይል ደግሞ የመረጃ ልውውጥ ነው። ወያኔ የሃገርና የሕዝብን አንድነት የመበተንና የሥልጣን ዕድሜውን የማርዘም ዓላማውን ከግብ ለማድረስ የመገናኛ ብዙሃን መከበር እንቅፋት ሆኖ ትልሙን እንደሚያጨናግፍበት ሲረዳ በሁሉም ዘርፍ የመረጃ ልውውጥን ማፈን ተግባሩ አደረገው።
ከአምሳለ ዓለሙ
ሰኔ 2008 .
page1image20416
1
የተለያዩ የህብረተሰብ ከፍሎች በፖለቲካው፣ በኢኮኖሚ፣ በማህበራዊው . . በመሳሰሉት በተለያየ ዘርፍ ሰፊውን ሕዝብ ስለ መብቱና ግዴታውን ለማሳወቅ የዘረጉትን የመረጃን አውታር ለመበጠስና ድምጻቸውን ለማቀብ የወረቀትን ዋጋ በመጨመር፣ የህትመት ዋጋን በእጥፍ በማሳደግ ነፃነትን ለማፈን ወያኔ ከተጠቀመባቸው ስልቶች ውስጥ የሚጠቀሱ ናቸው።
http://socepp.com/SOCEPP-09Janauary2009.pdf
ስለሆነም የአንድነት ኋይል የሆነውን የመረጃ ልውውጥ ለማጥፋት አሳታሚዎች ብቻ ሳይሆኑ አታሚ ድርጅቶችም በጥፋተኝነት ወንጀል በመከሰስና ከንግዱ ዓለም በመገለላቸው፣ የጋዜጠኞችና አሳታሚዎች ቀስ በቀስ መሰወርና መዳረሻቸውን የማጥፋት ዘመቻውም በቀላሉ የሚታይ አይደለም። አንዳንዶችም ሕይወታቸውን ለማትረፍ ከሃገር መውጣትን አማራጭ የሌለው አማራጭ አድርገው ተሰደዋል ።
http://www.socepp.com/may_3_2005.htm
የተቀሩትም የአገዛዙን ብልሹ አስተዳደር ማጋለጣቸውን እስከ 1997 .ም፤ በዲሞክራሲ ጭንብል የመብት ዝርፊያ ‘ምርጫ’ እስከተካሄደበት ድረስ ሕዝብ ማወቅ የሚገባውን ለማሳወቅ እየተማገዱ ኋላፊነታቸውን ተወጡ። በምርጫውም በወያኔ ላይ የደረሰው ሽንፈት በነፃ ሚዲያው ወይም በየሕዝብ መገናኛው ዕጣ ፈንታ ላይ ወሳኝ ሆነ።
ጠመንጃ በብዕር ሲተካ፣ ሕዝብ ግራና ቀኙን ሲለይና ወያኔ መፈናፈኛ ሲያጣ ሃሳብ በነፃ እንዳይንሸራሸር በእውነቱ መድረክ ቆመው ያሉትን ሁሉ ‘የምርጫን ሒደት አደናቅፋችኋል’፣ ‘ሕዝብን አሸብራችኋል’ ብሎ በአሸባሪነት በመፈረጅ ንጹሐንን
በገፍ አሰራቸው፣ ስየል ፈፀመባቸው፣ ገደላቸው፣ መዳረሻቸውም አጠፋ፣ ተሰደዱም። Freedom of the press is more than endangered in Ethiopia. The regime has blocked independent web sites, jams oppostion radios like Radio Finote, and hauls journalists to court under flimsy pretexts and imposes fines that they cannot pay. Worse still, journalists like Tesfaye Tadesse have been knifed to death while Berhanu Ijigu and others have been disappeared since the early 90s. http://www.socepp.com/SOCEPP-statement-on-the-world-press-day.pdf
የመገናኛ ብዙሃን መከበር ሰላማዊና ዴሞክራሲያዊ የሆነ የሥልጣን ሹም ሽረት እንዲኖር ምህዳሩን የሚያመቻች ብቻ ሳይሆን ለመልካም አስተዳደር መኖርም በጎ አስተዋፅዖ ያበረክታል። ለዚህም ነው ዜና የማግኘትና የማወቅ መብት የዴሞክራሲና የዕድገት መሰረት ነው ተብሎ በአንክሮ የሚነገረው።
page2image13808
in recent months and around 30 journalists have fled abroad since the start of the year
reflecting a government desire to make a clean sweep of independent media before
At least six publications have had to close
as a result of the biggest crackdown on the privately-owned press since 2005, one
parliamentary elections next May, local analysts say. https://rsf.org/en/news/ethiopian-
governments-witchhunt-against-privately-owned-media
page2image20632 page2image20792
ነገር ግን ለዚህ ሳይታደል መብቱን እየተበዘበዘ ባለው ሕዝብ ላይ በራሱ የማይተማመነው ወያኔ
ያስረዳል።
ይህ ዜና
የኮምፒውተር ስለላዎችን በማድረግ ወንጀል እየፈጸመ መሆኑን እንመለከታለን። በተለያዩ ጊዜያት በሃገር ውስጥና በመላው
የተራቀቁ የስለላ
ሶፍትዌሮችን በመልቀቅ የኮምፒውተሮችን ይዘት በመስረቅና የግል ግንኙነቶችንና ፖለቲካዊ እንቅስቃሴዎችን በመከታተል
ዓለም ያሉ ወንጀሉ የተፈጸመባቸው ኢትዮጵያውያን ጉዳዩን በያሉበት ለሚመለከተው ክፍል ማሳወቃቸውን
http://amharic.voanews.com/audio/Audio/378801.html
በፖለቲካው መስክ የበላይነትና አሸናፊነትን ለመጎናፀፍ መተማመኛ ይሆኑኛል ያላቸውን ሕግች አውጥቶ ተግባራዊ ካደረጋቸው መካከል የፀረ ሽብርተኝነት አዋጅ [Anti Terrorism Proclamation] አንዱ ነው። የወያኔ አገዛዝ በተለይም የሕዝብ ፍላጎትና ጥቅም እንዲከበር በሚንቀሳቀሱ ሀገር ወዳድ በሆኑ ዜጎች ባጠቃላይ በሕዝቡ ላይ መጠነ ሰፊ ሕገ ወጥ ተግባር እየፈፀመ የሚገኘውም በዚሁ ሕግ ላይ በመመስረት ነው።
2
በፀረ ሽብርተኝነት ሕጉ ውስጥ ያሰፈራቸው አንቀፆቹ እንዳሻው እንዲተረጉማቸው የተዘጋጁ በመሆናቸው ‘‘ተቃውሞ በማሰማት’’እና ‘‘በሽብር’’ መካከል ያሉትን መሰረታዊ ልዩነቶች አደንግዞ በመጠቀም እየተገለገለበት ይገኛል። http://www.refworld.org/docid/4ba799d32.html
page3image1912
On Wednesday 17 July 2013, members of the European Parliament’s Sub-committee
on Human Rights visited Ethiopia and urged the government to release journalists and
page3image4392
opposition activists imprisoned under the country’s Anti-Terrorism Proclamation No.
page3image5480
652/2009 (Anti-Terror Proclamation). The visit is an important reminder that despite
page3image6648
widely hailed progress on poverty reduction, the Ethiopian government continues to
punish free expression in violation of international law.
This discussion of the Anti-Terrorism Proclamation may seem semantic, but the result is
painfully real for the journalists and activists who face imprisonment for exercising basic
rights. It’s time to release them and amend the law.
http://www.freedom-
now.org/news/ethiopias-anti-terrorism-proclamation-and-the-right-to-freedom-of-
expression/
ዴሞክራሲያዊ ሥርአት በተመሰረተበትና በሠለጠኑት ሃገሮች ለመረጃ ልውውጥ ከፍ ያለ ቦታ የሚሰጠው ሲሆን መረጃውም ጥራት ያለው ነው። የመገናኛ ብዙሃንም መብት የተከበረ ነው። ስለሆነም ዜጎች ሀሳባቸውን ሥርአት ባለው መልክ ለመግለፅ ይችላሉ። ስለ ራሳቸውም ሆነ ስለሀገራቸው የወደፊት እጣ ፈንታና የቀን ተቀን ሁኔታ የመሳተፍ እድሉ የሰፋ ይሆናል። ስለ ብሔራዊ ደህንነት የራሳቸውን አስተዋፅዖ ያበረክታሉ። የሀገር እጣ ፈንታም ሆነ የሕዝብ ደህንነት፣ ለፖለቲካ ድርጅቶች፣ ለመንግሥት ወይም ለተለያዩ የመንግሥት ተቋማት ብቻ የሚተው አለመሆኑ በተግባር ይረጋገጣል።
ዜና የማግኘትና የማወቅ መብት እንደ ፖለቲካዊ ሰብአዊ መብት መሆኑ ከግንዛቤ ከተወሰደ የዴሞክራሲያዊን ሥርአት መሰረታዊ አካል ያደርገዋልና፤ ያለምንም ገደብ መከበር ያለበት የዜጎች መብት ነው። ይህ መብት እውቅና ተሰጥቶት ተግባራዊ ሲሆን የመንግሥት ተግባር ግልፅነት እንዲኖረውም ያግዛል። ከዚህ በላይ ደግሞ ዜና የማግኘትና የማወቅ መብት ለሌሎች ማህበራዊ፣ ኤኮኖሚያዊ መብቶችና አገልግሎቶች (ት/ቤት፣ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማትን ለመገንባት፣ የውሃና የመብራት መስመሮችን ለመዘርጋትና የኤሌክትሪክ ኃይል ምንጭን ግንባታ፣ ፍትሃዊ የሆኑ የሀብት ምንጭ ክፍፍል እንዲኖር ወዘተ) ሕዝብ በራሱ ፍላጎት ተጠቃሚ ብቻ ሳይሆን እንዴትም መገንባት እንደሚኖርባቸው ማጠየቂያዎቹ ናቸው። ማንኛውም ዜጋ መንግሥት የሚያደርጋቸውን ተግባራት ከነምክንያቶቻቸው የማወቅ መብት ሊከበርለት ይገባል። በአንድ ሀገር ይህ መብት ባልተከበረበት ሁኔታ ግን ስለ ዴሞክራሲና ሰብአዊ መብት መከበር ማውራት ለፕሮፓጋንዳ ፍጆታ ማዋል
ካልሆነ በስተቀር ትርጉም የለሽ ነው። ለምሳሌ ጋዜጠኛ ሙሉቀን ተስፋው በግንባታ ምክንያት ከመኖሪያ ቀያቸው የተፈናቀሉ ነዋሪዎችን ሁኔታ ለመዘግብ በሞከረበት ጊዜ የደረሰበትን እንመልከት።
New York, May 30, 2012--Ethiopian authorities have detained since Friday a reporter who sought to interview people evicted from their homes in a region where the government is building a contentious hydro-electric dam on the Blue Nile, according to a news report and the reporter's editor. The Committee to Protect Journalists said today that the case highlights authorities' disregard for the rule of law and its systematic efforts to suppress news critical of government officials.
Muluken Tesfaw, a reporter for the private weekly Ethio-Mihdar, is being held in a prison in the town of Asosa, capital of the Benishangul-Gumuz region, Getachew Worku, the paper's editor- in-chief, told CPJ. Muluken has not been formally charged or presented in court, Getachew said.
page3image30064
3
The detention appears to run counter to constitutional guarantees that a person be brought to court within 48 hours of arrest. https://cpj.org/2013/05/ethiopia-holds-reporter-covering-evictions-in- dam.php
page4image1976 page4image2136 page4image2296
ሕዝብ መንግሥት በሥራ ላይ የሚያውላቸውን ማናቸውናም ተግባራት ከነምክንያቶቻቸው እንዲያውቅ የመገናኛ ብዙሃን መከበር ዋስትና ሊሆን ይችላል። የካናዳና የኒውዜላንድ የዜና ኮሚሽኖች ተመክሮን በምሳሌነት ብንወስድ ምንም እንኳ ሕግን የማስፈፀም ሥልጣን ባይኖራቸውም በምክር ቤቱ የሚወጡ ሕጎች በሕዝቡ ባሕላዊ እሴት ላይ የተመረኮዙ እንዲሆኑ የሚያቀርቡት ምክርና አደራ በመንግሥትም ሆነ በሕብረተሰቡ የተለያዩ ክፍሎች የሚከበሩ ለመሆናቸው በርካታ ጥናቶች በምሳሌነታቸው የሚያቀርቧቸው ናቸው። በኢትዮጵያም ሆነ በሌሎች አምባገነን መሪዎች በሚገዟቸው ሃገሮች ግን ይህንን የመሰሉ ሁኔታዎች ተቀባይነት ስለማይኖራቸው የሚደነገጉ ሕጎች ዜና የማግኘትና የማወቅ መብትን አግባብነት ባለው መልኩ ተግባራዊ እንዳይሆንና ግልፅነትን የተላበሰ ሕብረተሰብ እንዳይገነባ በእንቅፋትነት እየተቸነከሩ የሕዝብን የበደል ቀን እያራዘሙ ናቸው።
በሃገራችን ኢትዮጵያ ጋዜጠኞችና ሌሎች የመገናኛ በዙሃን ባለሙያዎች ለመንግሥትም ሆነ ለሕዝብ ምክርና መረጃ የሚሰጡበት መድረክ ባለመኖሩና በሽብርተኛው የወያኔ አገዛዝ የፀረ- ሽብርተኝነት ሕግ በሥራ ላይ እንዲውል በመደረጉ፤ በዚህም አንሸዋሮ ባወጣው ሕግ በመንተራስ ለስልጣን አስጊ የመሰሉትን ሁሉ በማሰር፣ ስየል በመፈጸምና እንዳሻው ያሻውን ሁሉ በማድረግ ወንጀል ሲፈጽምበት እንመለከታለን።
The constitution and law provide for freedom of speech and press; however, authorities harassed, arrested, detained, charged, and prosecuted journalists and other persons whom they perceived as critical of the government, creating an environment where self-censorship negatively affected freedom of speech. Some journalists, editors, and publishers fled the country, fearing probable detention. At year’s end at least nine journalists and bloggers remained in detention; of these, two were arrested in February and charged in August. A journalist was convicted under the ATP and sentenced to seven years in prison. http://www.state.gov/documents/organization/252893.pdf
በተደጋጋሚ የተለያዩ ሀገራት መሪዎችና የመንግሥት ተወካዮች በኢትዮጵያ የሥራ ጉብኝት በሚያደርጉበት ወቅት ይህ መብት እንዲከበር በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ ለአገዛዙ ባለሥልጣናት ጥያቄ ማቅረባቸው የሚያሳየው የመብቱን መከበር አስፈላጊነት ብቻ ሳይሆን ጨርሶ አለመከበሩንና ወያኔ ጆሮው ላይ በሆዱ እንደተኛ ነው።
ወያኔ ሃቅን አልሰማም ብሎ ቢያስርም፣ ቢያሰቃይም፣ቢገድልም ሃሳብን በነፃ የመግልጽን መብት መከበርን እንጂ ማንም አካል ወደ መታፈን፣ ወደ መሰቃየትና መገደል መድረስ እንደሌለበት የሚያምነውን ትውልድ ግን ከመንገድ ሊያስቆመው አልቻለም። ሕዝብ የመገናኛ ብዙሃን ተጠቃሚነቱ ቀጣይነት እንዲኖረው ቴክኖሎጂውን በመጠቀም በሌላና በተሻለ መንገድ ዜናን ለማደርስ መጦመር ጀመረ። ይህ ሲሆን ግን ተግዳሮቱም በተመሳሳይ አብሮ ተጋረጠ።
በተለያዩ ድህረገጾች እንደተዘገበው የ ዞን 9 ጦማሪያን የሕዝብን መብት ለማሳወቅና ሃሣብን በነፃ የማስተላለፍ ሥራቸውን መንግሥት በሽብርተኝነት ወንጀል ፈርጆ በማሰር እንዲንገላቱ በማድረግ ራሱ ባወጣው ሕግ የማጭበርበር ወንጀል ሲፈጽም እንመለከታለን። https://rsf.org/en/news/ethiopian-governments-witchhunt-against- privately-owned-media
በገዢው ፓርቲ እየተሰቃየ ያለው ንጹሕ ዜጋ የሚታሰረውም፣ ስየል የሚፈጸምበትም፣ መዳረሻው የሚጠፋውም፣ የሚገደለውም ሆነ የሚሰደደው፤ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ መብቱን ስለተነጠቀ ብቻና ብቻ ነው። አንድ ሕዝብ የሃገሩን ሃብት የመጠቀም፣ መማርና መስራት፣ በአጠቃላይ በሃገሩ ላይ የዜግነት መብቱ ሙሉ በሙሉ ተከብሮና ተጠብቆ በመኖር ፈንታ የበይ ተመልካችና ሟች ለመሆን የሚዳረግ ከሆነ ከመጠየቅ አልፎ ማመጹ የ ‘ሽብርተኛ’ ስያሜ ከሚያሰጠው ይልቅ እውነተኛና ታማኝ ሊያሰኘው በተገባ ነበር። በተቃራኒው በሰውነትህ ሙሉነት አትጠቀም፤ ይህም አትመልከት፣ አትናገር፣
page4image24320 page4image24480 page4image24640
4
አትብላ፣ አትፃፍ፣ አታንብብ በቃ ምንም አታድርግ እየተባለ ነው። The journalists, who were arrested in multiple raids on Friday and Saturday, have been denied access to their family and lawyers and are being held at the Maekelawi federal detention center, according to local journalists. According to a report by Human Rights Watch, interrogators at Maekelawi routinely use torture to extract false confessions from detainees. The Ethiopian government denies the allegations. https://cpj.org/2014/04/ethiopia-jails-nine- journalists-renews-crackdown-o.php
page5image4296 page5image4456 page5image4616 page5image4776
በኢትዮጵያ ውስጥ ሃሳብን በነፃነት መግለጽና በሕይወት መቆየት በተጓዳኝ የማይከወኑ በመሆናቸው፤ ቀድሞ በአባይ ግድብ አካባቢ የተፈናቀሉትን ነዋሪዎች ሁኔታ ሲዘግብ ተይዞ በእስር እንደነበር ከላይ የተመለከትነው «የቀለም ቀንድ» የተሰኘዉን ሳምንታዊ የአማርኛ ጋዜጣ ዋና አዘጋጅ ጋዜጠኛ ሙሉቀን ተስፋው በቅርቡ ከሃገር መሰደዱ በሃገሪቱ ያለውን አፈናና ግድያ
ማሳያ ነው። ሙሉቀን ተስፋው ያጋጠመውን ሲገልጽ፦ I tried my best for the development of a free press in Ethiopia. Since 2012, I have worked as a columnist, reporter, editor and editor- in-chief in different newspapers like Ethio-Mihdar and Yekelem Qend and I've been featured on many other websites. While doing my job, I was jailed and tortured in 2012. And last year during the elections, security officers followed me.
Whenever I went to my home or came out, there were people around - that's why I had to hide in a monastery near Lake Tana. I was in hiding there for about two weeks. After the elections I returned to Addis. Since then I got a lot of intimidating phone calls and I was also physically attacked. I reported these intimidations to the human rights council and wrote about it in social media and in the newspaper. In my articles, I always speak about human rights violations, press freedom and so forth. I highly criticized the regime. http://www.dw.com/en/ethiopian-journalist-i-was-jailed-and-tortured/a- 19249671
page5image16416
ዜና የማግኘትና የማወቅ መብት በዓለም አቀፍ ደረጃ እውቅና ማግኘቱ አንድን ሕዝብ በማህበራዊና በኤኮኖሞያዊ እንቅስቃሴ ተካፋይ እንዲሆን፣ ለግሉንም ሆነ ለሕብረተሰቡ ማናቸውንም ዓይነት እድገት ለማስገኘት መሰረታዊ በመሆኑ፤ በኑሮ ሂደቱና የቀን ተቀን ኑሮዉን ለማሸነፍ በሚያደርጋቸው ማህበራዊ እንቅስቃሴዎቹ ከተቀበላቸው ባህላዊ ልማዶቹና እሴቶች ጋር ሳይጣረስ ተናብቦ ለመጓዝ ይረዳዋል።
በአንፃሩ ግን ወያኔ በሕዝብ ሀብት የሚንቀሳቀስ የዜና ተቋማትን በራሱ ሙሉ ቁጥጥር አድርጎ ለሕዝብ ዜና ለማድረስ እየጣሩ ያሉትን እያፈነ የመገናኛ ብዙሃንን ለራሱ የፕሮፓጋናዳ ፍጆታ ብቻ በማዋል፤ሕዝብን በማስተማር ፈንታ በመዝናኛ ሰበብ የሕዝብን ስነ-ልቡና ለመስለብ የሚጠቀምባቸው የውጪ ሃገር የመዝናኛ ዝግጅቶች [ የሆሊውድ ፊልሞች፣ የአክተሮች የዕለት ተዕለት ኑሮ፣ የእግር ኳስ ተጫዋቾች ታሪክ. . . ወዘተ] ያቀርባል።
ቀድሞውንም የነበረው ዕቅድና ዘመቻ ሃገር እንደ ሃገር ሉዓላዊነቷ ተከብሮ እንዳትኖርና እንድትጠፋ ስለነበር፤ ለዚህ ሁሉ ውጥንቅጥና ማስተካከያ ሳይበጅለት ‘ በእንቅርት ላይ ጆሮ ደግፍ’ እንዲሉ ከዚያም በባሰ መልኩን ቀይሮ ነገር ግን ከቀድሞው ጋር በተሰናሰለ መልኩ ተግባራዊ የሚሆን የመብት ማፈኛና ነፃነትን ከመሬት በታች የመቅበር የመርዶ ረቂቅ ቀርቧል።
ከዚህ በፊት በሌሎች የመገናኛ መስኮች ያካሄደውን አፈና በአዲስ መልኩ ለመተግበር በቅርቡ ባወጣው የኮምፒውተር ወንጀል ረቂቅ የመቆጣጠሪያ መረብ አድርጎ ሕዝቡ መፈናፈኛ እንዲያጣ ለማድረግ በጉዞ ላይ ይገኛል።
5

ወያኔ አስቀድሞ ያደርግ የነበረው፤ ስለ ሃገር መጠበቅ፣ ስለ ሕዝብ አንድነት፣ ስለ መብት መከበር፣ በመሳሰሉት ጉዳዮች ነቀፌታቸውን የገለጹ ዜጎችንና ሠላማዊ ሠልፍ የወጡትን ያለ ምክንያት ማሰር ነበር። ይህንንም በዜጎች ላይ የሚፈጽመውን ጭቆናና አፈና የሕጋዊ ጭንብል ለማልበስ የፀረ-ሽብርተኝነትን አዋጅ [Anti Terrorism Proclamation] በሥራ ላይ
በማዋል አፈናውን ቀጠለ። የኮምፒውተር ወንጀል ረቂቅም ከዚህ የተለየ አይደለም። አስቀድሞ ደረ-ገጾችን በመዝጋት፣ ጦማርያንን በማሠር፣ በፌስቡክ የተጻፉ የተለያዩ አመልካከቶችን መሠረት አድርጎ ዜጎችን በማሠር የመገናኛ በዙሃንን አፍኗል። ይህም ከተለያዩ የሰብዓዊ መብት መከበር ከሰፈነባቸው ዘንድ ነቀፌታን ስላበዛበት በሕጋዊ ሽፋን አፈናዎችን ለማካሄድ ይህን
የኮምፒውተር ወንጀል ረቂቅ [Computer Crime Proclamation Text Draft] አዘጋጅቷል። http://www.addisinsight.com/2016/05/ethiopia-computer-crime-proclamation-text-draft/
Inadditionto common sense legislation such as criminalizing the dissemination of child pornography, theft, and cyber attacks there is a clause concerning the distribution of material that incites a public disturbance aka protest that is raising some eyebrows.
መረሳት የሌለበት ደግሞ ይህ አሁን የኮምፒውተር ወንጀል ረቂቅ አውጥቶ ሕዝብ በነፃነት ሃሳቡን እንዳይገልጽ የሚከለክለው ወያኔ ከዚህ በፊት ራሱ የስለላ ሶፍትዌር እየተጠቀመ የኮምፒውተር ይዞታዎችን ሰብሮ በመግባት የሚሰርቅና የኮምፒውተር ተጠቃሚዎች የግል ግንኙነታቸውንና የፖለቲካ እንቅስቃሴያቸውን እየሰለለ ወንጀል የፈጸመ ሥርዓት ነው። ይህን ሁሉ የሚያደርገው የመገናኛ ብዙሃን መብት መከበር የወያኔን የግፍ ተግባራት እውነተኛ ምስሉን ቁልጭ አድርጎ የሚያሳይ የጠራ መስታወት በመሆኑ ይህን አስፈሪ መልኩን ላለማየትና ላለማሳየት አስቀድሞ ለመስበር ነው።
http://resurrectiontoethiopia.blogspot.no/2014/02/blog-post_21.html
የመገናኛ ብዙሃን የመከበር ዓላማና ጥቅም ሃገራችን ኢትዮጵያ አንድነቷ ተከብሮ፣ታሪኳ ተጠብቆ እንድትኖርና እንድታድግ እንዲሁም የሥልጣኔ ምንጭ ሆናም እንድትቀጥል ነው። ይህን ሁሉ ሃገር ወዳድ ኢትዮጲያዊ የሚፈልገው ነገር መሆኑ የሚያጠራጥር አይደለም። ፍላጎት ብቻ ግን ከግብ ስለማያደርስ አምባገነኖች በሕዝብ ጫንቃ ላይ ተፈናጠው የሥልጣን ዘመናቸውን ለማርዘም እንዳይችሉ እንዲሁም እየተሰናሰለ መጥቶ እዚህ የደረሰውን የአፈናና የውድመት ዘመቻ በዚሁ ለመግታት፤ በአንፃሩም ሕዝብ የዜግነት መብቱ ተከብሮ ያለምንም ፍርሃት ሃሳቡን በነፃነት የመግለጽ መብት እንዲኖረው ለማድረግና ዘለቄታዊ መፍትሔ ለማምጣት ሁሉም ዜጋ የራሱን ሚና የመወጣት የዜግነት ግዴታ አለበት። የሃገራችንን ዋስትና ለማስጠበቅ ችግሩን በተግባር መፍታት አለብን።
በመጀመሪያ ወገኖቻችንን አሁን ያለውን ሁኔታ በሚገባ እንዲረዱ በማድረግ ወይም በማሳወቅ የግንዛቤ እድገት እንዲኖር የማድረግ ኋላፊነትን መውሰድና ለመብቱ መከበር በህብረት በመነሣት በወያኔ ሥርዓት የትውልድ ታሪክ አይጻፍም ብለን በቁርጠኝነት ዓላማ በመነሣት ለተተኪው ትውልድም የምናሥረክበው ታሪክ መሥራት አለብን። በመቀጠልም በአንድነት በያለንበት ሃገር ላሉ መንግሥታትና የተለያዩ ድርጅቶች የመገናኛ ብዙሃን የደረሰበትን ችግር ደጋግሞ ማሳሰብና እንዲሁም በወያኔ ሥርዓት ላይ ተጽዕኖ እንዲያደርጉ መታገል ይጠበቅብናል።
ለመገናኛ ብዙሃን መብት መከበር የሚደረገው ትግል ያለማሰለስ ይቀጥል!!! 

1 comment: