Wednesday, August 3, 2016

የነፍስ አድን ጩኸት ! የዛሬው የፍኖተ ራዲዮ ወቅታዊ ሀተታ                                                    የነፍስ  አድን  ጩኸት  !

አንድ ሰው የልብ ድካም መጥቶበት ይሁን ወይም በድንገተኛ አደጋ ለመሞት በሚጣጣርበት ወቅት ህይወቱን ለማትረፍ ሰዎች ጥረት ያደርሉ ።  ሀኪሞች- ነርሶች ፤ ቤተሰቦች፤  እስትንፋሱን  ለመመለስ  ይጥራሉ  ፡፡ ራወጣሉ  ። አፍን -ከአፋቸው  ገጥመው ይተነፍሱበታል      በሽተኛው ዕድለኛ ከሆነ ፤  ይተርፍ ይሆናል ።   ያ ካልሆነ  ግን  "ለንሰሀ -ሞት እንኳ ሳይበቃ " ሰናበታል ። 
 " ዋይ ዋይ እያሉ ሄዱ ፤
   ከሃጢዐታቸው  ሳይፀዱ ። "    
እየተባለ ይፍበታል ። ይቀለድበታል፡፡ ይሳለቁበታል ። ወትሮስ፤ ይብላኝ  ለሟች እንጅ፤ የሞተ ምን ዘመድ ይኖረዋል ?  አብሶማ ፤ እንደ ወያኔ በቁሙ የሞ  !  
 " ልመና፤ ሳሉ በቁመና "  እንዲሉ ፤ በህይውት እያሉ መልካም ራ ካልሰሩ፤  በፃዕረ- ሞት ጊዜ ቢፍጨረጨሩ  እርና የለውም።  ከንቱ  መፈራገጥ ነው።  ከተሰባበሩ በኋላ " ወይኔ አባ ስበር ! "  እያሉ ቢርበተበቱ ፤ ቢዳጭሩ ፤ ቢፎክሩ ፤ የሚይዙትን- የሚጨብጡትን ከጣት በስተቀር ፤ ገላጋይ አይመጣም። አዳኝ  አይገኝም።  የሩቅ  ዘመድ፤ የቅርብ ጉረቤት፤ አይደርስም። 
" ሳለ - አይሰጥ "  አጥንት  ጉሮሮ ያንቃል።   የንፁሃኑ አፅም  እሾኽ ሆኖ ይወጋል።  የኢትዮጵያ ሰማዕታት  ደም፤ ያቅበዘብዛል ።  የሕዝብ ሀዘን ይጎዳል ። የመጨረሻ ፍርዱንም ይሰጣል !
 
  "  አርባ አራቱ ደብር  አባ  ብየዕዝጊን፤
     ገዳማት ፤ አድባራት ፤  መካነ  ቢዘን ፤
     የቁልቢው ደብር፤  የአርሲ   ምዕመን፤
     አይጎዳም  መስሎሻል ፤ የሕዝቦች  ሀዘን ? " 
   የተባለውን የሕዝብ ምህላ፤  የሰማዕታት ማስጠንቀቂያ፤  የታሪክ ማስገንዘቢያ፤  የዚያን ትውልድ  መዝሙረ- ሐዋርያ፤ መገንዘብ በተገባ  ነበር ! ያ ግን ሳይሆን ቀረ።  ዘረኞች በዘረኝነት መርዝ  ስለተመረዙ፤ ከማይድኑበት ደረጃ ደርሰዋል። ሀገራችንን በዘር በሽታ መርዘው  ወደ መጥፊያቸው አፋፍ እየተጣደፉ በመሄድ ላይ ይገኛሉ ።
ወያኔዎቹ  ዛሬ፤ ከራስ ፀጉራቸው  እስከ እግር ጥፍራቸው ድረስ በተውሳክ  ተበክለዋል።   ፅኑ በሽታ  ቀስፎ ይዟቸዋል።  እዕምሯቸው በወንጀል ተመርዟል፡፡ ልባቸው በሃጢአት ተበክሏል።  ቆሽሿል።  ዐይናቸው በሞራ ተጋርዷል።  ታውሯል።  የአካባቢውን ዐየር የሚያሸቱበት  አፍንጫቸው  ሳይቀር ተግቷል ። ተደፍኗል። እጅ-እግራቸው ታስሯል።  ተደይኗል።  ዕኩይ አጋዛዛቸው ዕውር-ድንብሱን  ይቅበዘበዛል ። ይደናበራል።   ድርጅታዊ  መዋቅራቸውና ስንሰለቱ ፤ ወላልቋል።   ተፍረክርኳል።  በዘር ላይ የተዋቀሩት ተቋማትና መስርያ ቤቶች ሳይቀሩ እየተሰነጣጠቁ  በመሄድ ላይ ይገኛሉ ።
 የመከላካያ ሠራዊት የሚሉት  የወታደሮቹ  ስብስባቸውም ፤ እርስ በእርሱ እየተነታረከ፤ መሄዱ የአደባባይ ምሥጢር ከሆነ ቆይቷል ።  ባለፈው ሳምንት፤ ማዕጋቸው ከመቶ አለቃ እስከ ኮሎኔል የደረሱ 40 የሚሆኑ የጦር መኮንኖች በአድማ ተጠርጥረው ፤  እስር ቤት ተወርውረዋል።  የጭካኔ ተግባር-ግብረ ስየል- እየተፈፀመባቸው  መሆኑ  በሰፊው  ይነገራል ። ይኽ ሁኔታ በመከላካያ ሠራዊት ውስጥ መናጋትን አምጥቷል ። አንዱ ሌላውን አያምነውም።  ስጋት፤ፍርሃትና ጥርጣሬ ሰፍኗል።  መከባበር- መተባበር የሚባል ነገር ከጠፋ ቆይቷል ።  ወታደራዊ  ሥነሥርዓት   እና   የመንፈስ  አንድነት   የተባሉት ከወያኔ ሠራዊት መዝገበ -ቃላት ተሰርዘዋል ።     
በወያኔ ዳስ ስር የተጠለሉት  ሀረግ -ሬሳ  ድርጅቶችም የጉፋያ ሥጋ ሆነዋል ።  በተበከለ አየር  እየተነፈሱ ጤናማ ሆኖ መቀል ስለማይቻል ፤  ከሚመጣባቸው አደጋ  ለመሸሽ፤  የማምለጫ  ስልታቸውን    ለማፈላለግ፤  የየበኩላቸውን  ሩጫ ተያይዘውታል ።  ይኽንንም ትምህርት ፤ ትላንት ኢትዮጵያን  አጋፍጦ ከፈረጠጠው  ፤ ከመንግሥቱ  ሃይለማርያም ቀስመዋል።  " በአህያ ቆዳ የተሰራ ቤት ይፍረከረካል ጅብ የጮኽ  ዕለት።  " ነውና፤ በያቅጣጫው የተቀጣጠለው ሕዝባዊ አመፅ አርበትብቷቸዋል። እየተጋገለ መምጣቱን ተረድተው ፤ የነፍስ አድን  ኸት በማሰማት ላይ ይገኛሉ ።
 " በምትሰጥም  ጀልባ  የነበሩ ብልጥ አይጦች፤ አስቀድመው መዝለል ይጀምራሉ "  እንደተባለው፤  የወያኔን መጥፋት አስቀድመው የተገነዘቡ አንድ አንድ ጮሌዎች ፤ መክዳት መጀመራቸው በሰፊው ይነገራል።  ወትሮውንስ  ቢሆን፤ " ሙት ፤ሙታንን ይዞ ይሞታል "  ነውና ከሙት ጋር ከሚሞቱ፤አስቀድመው  ለማለጥ መሞከራቸው  አያስደንቅም። የጥቅመኝነት አንዱ ባኅርይ ነውና !  ባለፈው  ሣምንት ሁለት የወያኔ ቀንደኛ ባለ ሥልጣኖች  ቤተ ስቦቻቸውን ወደ አሜሪካ ለማሸሸስ  መሄዳቸው፤ የመረጃ ተከታታዮችና   ሌሎች የዓይን  ምስክሮች አርጋግጠውልናል    ከኢትዮጵያ  ሕዝብ  አመፅ  ለማምለጥ ሽሽቱ በሰፊው እንደሚቀጥል፤ ወትሮውኑም ቢሆን  ሳይታለም  የተፈታ ስለነበር ፤ ይኽ የወኔዎቹ  ፍርጠጣ ያልተጠበቀ  አልነበረም ።
ሆኖ፤ አሁንም  የወያኔን  ፅዐረ-ሞት  እስትንፋስ ለመዝራት የሚፍጨረጨሩ በለሥልጣኖች   የነፍስ-አድን ጩኸት ማሰማት ጀምረዋል። ፍፃሜ- ወያኔ፤ በልፅ  ከታያቸው ቀንደኛ ትግራዮች፤ መካከል አንዱ የሆነው የቀድሞው  የህውሃት ጀራል፤ በቅርቡ አንድ " ወያኔን አናድን ! " የሚል ኑዛዜ አስተለልፏል። ይኽንን የተማፅኖ ጽሁፍ በማኅበራዊ ገጾች ( ድረገጾች ) አስተላልፏል። ካሰፈራቸው የማታለያ   ማሰራሪያዎችና  ማስጠንቀቂያዎች መካከል የሚከተሉት  ዋና ዋናዎቹ ነበሩ።
ሀ.   1. ህወሃት  መንግስታችን  ችግር ወስጥ ገብቶብናል ። በሕዝብ ቁጣ ተወጥሯል።  ከመሞቱ በፊት ባስቸኳይ ልናድነው ይገባል ።
    2. ወያኔ ከሌለ ኢትዮጵያ  ትጠፋለች፡፡ እንደ ሀገር መቀጠሏም ያበቃላታል።  ሠላምና ፀጥታ ይደፈርሳል። ሕዝቧም  ይበታተናል    ዕርስ በዕርሱ ይፋጃል ። የትግራይ ሕዝብ ያልቃል። ሊያጠቁት ያደፈጡ፤ ጠላቶቹም ይጨርሱታል ። ሀብት- ንብረቱን ይዘርፉታ.።
   3.  ዴሞክራሲንና በልፅግንና  ያመጣልንን  ህገ መንግሥታችንን መጠበቅ ማስከበር ይኖርብናል ። በኢትዮጵያ ታሪክ የመጀመሪያውና ተወዳዳድሪ የሌለውን ሕገ መንግሥትና ሥር ዓቱን ከተቃጣበት  አድጋ ለመከላልከል ቆርጠን አንነሳ። 
ለ.  ከተቃጣብን  አድጋ ለመትረፍ  የሚከተለቱ  ስቸኳይ ርምጃዎች ሊወሰዱ ይገባል ሲልም ብጤዎቹን መክሯል
    1.     ሕገ መንግሥታችንን በማያናጋ መልኩ ፤ አንዳንድ የሕዝብ  ጥያቄዎች መመስ አለብን ።
    2.    መጠናቸው የተቆጠበ አንዳንድ  ናዊ ለውጥ  በማድረግ  የሕዝቡን ቁጣ ማስተንፈስ አለብን ።
    3.   ይኽንን  ማድረግ  ከቻልን ፤  ከተቃጣብን  አደጋ  ማምለጥ  እንችላለን   
የሚሉ የነፍስ አድን ጥሪ አስተላልፏል ። ለትግራይ ወገኖቹ ሁሉ !
ይህኽንን የማታለያ ጩኽት ጥቂት እበላ ባዮችና  ለመታለ የተዘጋጁ ሌሎች  ደላላች ሊያስተቡለት ሞክረዋል።  ራሳቸውን አታለው ሌሎቹንም ለታለል ጥረት ሲያደርጉ ተስተውሏል።  ጥቅመኞችና አሽቃባጮች  ንን ቢያደር  የሚያስደንቅ አይሆንም ። የነገሩ ሀቅ ግን ሌላ ነው ።  አንዳንድ ጥያቄዎች ሲነሱም፤ የሚሰጡ መልስ ተቃራኒውን ነው ።
እረ ለመሆኑ የማን መንግሥት ?   ማን  ቀርፆ  ማንስ ያፀደቀው ህገመንግሥት ?   ለማንስ  የሚጠቅም ህገመንግሥት ?  ኢትዮጵያን የሚያፈርስ፤ የወያኔ በህይወት መቀጠል ነው  ? ወይስ መወገድ ? ሕዝቧስ የሚበታተነው ወያኔ ከሥልጣኑ ሲወገድ ነው ? ወይስ በሥልጣኑ ሲቀጥል ነው ?    እረ ለመሆኑ፤ የኢትዮጵያን ሕዝብ  በዘርና ጎሳ ከፍፍሎ የሚያተራምሰው ማን ሆኖ ነው፤ ወያኔ ከሄደ፤ ኢትዮጵያ አለቀላት  የሚባለው ቀልድ ?  የወያኔው ጀኔራል፤ የኅወሃትን ካድሬዎች ሊያታልል ይችል ይሆናል፤ የኢትዮጵያን ሕዝብ ግን፤ማታለል ቀርቶ፤ ቀና ብሎ የማየት ስብዕና እንኳን የለውም።
ዘረኛው አዛዝ አስመርሮት ከዳር እስከዳር አምፆ በመነሳት እያርበተበተ የሚመጣውን  ሕዝባዊ አመፅና ቁጣ  ማብረድ የሚቻው፤ በጥገናዊ  ለውጥ ሳይሆን፤ በስር-ነቀል ብቻ ነው። ስር- ነቀል ሥርዓት አምጥቶ የተጠላን አገዛዝ ማስወገድ ደግሞ፤ ለኢትዮጵያ ሕዝብ አዲስ አይደለም።  ካሁን በፊት፤ ሁለት ጊዜ ታግሎ ሁለት ስር- ነቀል ሥርዓትንና  አገዛዝን አሽቀንጦሮ አስወግዷል ።
የወያኔ ተባባሪዎች፤ ደጋፊዎችና ሌሎች ስጋት ያደረባቸው ክፍሎች ፤ ከመጣው አደጋ  ለማምለጥ ከፈለጉ፤ የሚኖራቸው  የነፍስ -አድን ምርጫ አንድ ብቻ መሆኑን ሊያምኑት ይገባል።   ከሕዝባዊ አመፅ ሊተርፉ የሚችሉት የሚከተሉትን አስቸኳይ እርምጃዎች ሲወስዱ ብቻ ይሆናል።
1ኛ.  ባስቸኳይ ፤ ሁሉንም  ያካተተ፤ ያሳተፈ፤  ጠቅላላ ሀገር አቀፍ ጉባዔ  መጥራት። ይህ ጉባዔም፤ ሽግግር ዓላማን የሚያስፈፅም ይሆናል ። ይህ ክስተት በሌሎቹ ሀገሮችም  ተሞክሮ፤ ታሪካዊና  ዘላቂ ውጤትን አስመዝግቧል። በሀገራችንምም የማይሆንበት  አንዳችም ምክንያት ሊኖር አይችልም።
2ኛ.  የአምባገነን አገዛዝ መሳሪያና የሕዝብ መጨቆኛ የሆነውን  " ህግ መንግሥት " መሻር። በትኩም፤ ከሁሉም ሕዝባዊ ወገኖች የተውጣጣ፤ የሀሪቱንም  ዜጎች ፍላጎት ያካተተና የሚወክል  ጊዚያዊ  የመሸጋገሪያ ወቅት  ማዘጋጀት ። 
3ኛ. የሰሩትን ሕዝባዊ ወገኖች፤  ባስቸኳይ መፍታት። የተሰደዱት ዜጎች ሁሉም ሀገራቸው የመግባት መብትና ዕድል እንዲኖራቸው ማድረግ፡፡ ሁሉም በሀገሪቱ የፖለቲካ ሂደት እንዲሳተፉ ማድረግ።
ያ ሳይሆን ቀርቶ ግን፤  ኔ ፤ በግትርነት፤ በድንቁርና፤  በትዕቢም ተወጥሮ፤ የሕዝብን አመፅ፤ በኃይል እቆጠረዋሁ ብሎ ከተመኘ፤ በራሱና በወገኖቹ ላይ   የጥፋት ቁጣ የሚያመጣ መሆኑን ሊያውቀው ይገባል ። የነፍስ አድን ጩኸት የሚያሰሙ ጀኔራሎቹ ም ይኽንን ሃቅ ሊገነዘቡት፤ ሊረዱት ይገባቸዋል።  ለመንግሥቱ  ሃይለማርያም ልበጀ ድንቁርና፤ አጉል ትዕቢትና የመጨረሻ ጊዜ ድረሱልኝ  ኡኡታ ነርሱም እንደማይፈይድላቸው  ቢገነዘቡት ይሻላቸዋል። 
ይኽ ግንዛቤ እንዳለ ሆኖ ፤ ለመላው የኢትዮጵያ ሕዝብ የሚከተሉትን የማስገንዘቢያ መልዕክቶች እናስተላልፋለን ።
1ኛ.  ከምንጊዜውም በበለጠ እንድነትህን አጠንክረህ  የነፃነት ትግልህን ቀጥል ። የትግልህን አድማስ በምሥራቅ[ በምዕራብ፤ በደቡብና በሰሜን እያሰፋህ  በርትተህ ቀጥል።  ለወያኔ የድንፋታ ፕሮፓጋንዳ  አትበገር። ወገቡ የተሽመደመደ፡ ናላው ዞረ፤ ህሊናው የደነበዘ፤ ዘረኛ አገዛዝ  የሚያራምድ ተርበትባች ቡድን መሆኑ አትርሳ። ተባብረህ ከተነሳህ፤ የሚበግርህ   ምድራዊ ኃይል አይኖርም።
2ኛ. ሽማግሌና አስታራቂ ፤ አማላጅና  አደራዳሪዎች  አንዳያዘጉህ  ነቅተህ ትግህን ቀጥል። ፤ የተነሳህበት   ዓላማ፤ የአመጽህ ኢላማና ግብ ፤ ዘረኛውን አጋዘዝ በማስወገድ ፤ ኢትዮጵያ ሀገርህን ከተቃጣባት አጋ በማዳን ፤አንድነቷ  የተጠበቀ የዜጎቿ መብት የተከበረባት ኢትዮጵያን ማትረፍ ስለሆነ፤ በአሳቾችና ትጥቅ አስፈችዎች አንዳትታለል፤ ድልህንም እንዳትነጠቅ   ቅተህ ተብረህ ታገል ። የመጨረሻው ድል አድራጊ አንተው ራስህ መሆንህን  በጭራሽ አትዘንጋ !

ኢትዮጵያ ለዘለዓለም  ትኖራለች  ! 

No comments:

Post a Comment