Saturday, August 13, 2016

የሕዝብ ግዴታ እንዳይረሳ። ፍኖተ ራዲዮ


ለመላው የኢትዮጵያ ሕዝብ መድረስ ያለበት አስቸኳይና ወሳኝ መልዕክት ሀገራዊ ግዳጅን አንርሳ የሚል እንጂ ሌላ ሊሆን አይችልም ። ሀገራዊ ግዳጅ ምንድነው ? ኢትዮጵያን እንደ ሀገር፤ ጥንቶቹ እንዳስረከቡን መጠበቅ ማለት ነው ። ህልውናዋን፤ሉዓላዊነቷን ። ይህ ማለት ጊዜ ከሚጠይቀው ለውጥና መሻሻል ሀገራችንን ማራቅ ማለት ሳይሆን ለዕድገቷ የሚበጀውን ሁሉ እያደረግን ግን ከጥላቶቿል መከላከልና የመብ ሙሉ ሕዝብ ሀገር ማድረግ ማለት ነው ። ጥሪያችን ኢትዮጵያዊ ነው፤ለኢትዮጵያ ስርየት ።
እያንዳንዱ ሕብ በላዩ ላይ ጉብ ያለበት ስርዓት ዋጋው ነው የሚለውን ብሂል የምንቀበለው እንዳይደለ ግልጽ ነው ። መጥፎ አገዛዝ በራሱ ላይ ሲፍርበት ይገባዋል ማለት አይቻልም ። ሕዝብ የተጫነውን ስር አት የማስወገድ ግዳጅ ነው ያለበት ። ጫንቃውን ለጭቆና አመችቶና ሀገራዊ ወኔውን ሰልቦ ከተገኘ ለመከራው ራሱ ተጠያቂ መሆ ግን የሚያጠራጥር አይደለም ። ሕዝብ ቆናን የቀበል ግዴታ የለበትምና ፡፤ ሕዝብ ጦርነት ሰልችቶታል እያሉ የሚወጉትን፤ መብቱን ነጥቀው ዝምታን የሚያሳቅፉትን፤ ሀገሩን እያጠፉ ሽንፈትን የሚጭኑበትን መቀበል የለበትም። የለበትም ሳይሆን ከተቀበለ ራሱ በራሱ ላይ ፈረደ ማለት ይቻላል። ህዝብ ራሱን ሲያስከብር ሀገሩን ይጠብቃል፤ ሀገሩን ያስከብራል ። ሕዝብ ግን ጭቆናን ሲጭኑት በዝምታ ከተቀበለ ሀገሩን ያዋርዳል ። መሳቂያም ይሆናል በዓለም ደረጃ  ጨቋኞቹም ደንታ የላቸውምና ቀምበሩን  ያከብዳሉ እንጂ አይቀንሱለትም ። ይህ የተረጋጋጠ ነው ። ሕዝብ ለመደራጀት፤ ለማበርና ለመብቱና ለሀገሩ ለመነሳት ያለበትን ችግር ለመረዳት ብንችልም አንዱን አምባገነን 44 ዓመት፤ ሊለአውን 17 ዓመት፤ ቀጣዩን 24 ዓመት የመቻል የመሸከም ነገር ቢያንስ አነጋጋሪ መሆኑ አይቀርም ። ታሪካዊው ወኔ የት ገባ ? እምቢታ ምነዋ ባዳ አቅዋምና ቋንቋ ሆነች ? ለዚህ መልስ ካልተሰጠ ችግራችንን መቅረፍ የምንችል አንሆንም ።
ይህን ሀቅ /መቀበል ከቻልን ቁልጭ ግልጽ ብሎ የሚታየው ህዝብን በተመለከተ ምን እንደሚጠበቅ ነው ። ግዳጅ ። ጣሊያን ሀገራችንን ሲወር ግዳጃቸውን የተረዱ ዜጎች  ከርካሳ ብረታቸውን፤ ጦርና ጋሻቸውን አንስተው ዘመናዊ ነኝ ያውን ጦር ተጋፍጠው፤ በሚሊዮን አልቀው ግን የሀገራቸውን ነጻነት አስከበሩ ። በዚያው ደግሞ ስንቶቹ ሆዳቸውን አስቀድመው የወራዳ ባንዳነትን ካባ ለበሱ፤ ታሪክም እነሆ እስከዛሬ ታወግዛቸዋለች ። ህገር ማዳን ግዳጅ ሲመጣ ዜጎች ማወላወል ሳይሆን ማዳመጥና መቀበል ይጠበቅባቸዋል ። የማይመጣን ነጻ አውጪ ከባዕድ ከመጠበቅ ራሳቸው የሀገራቸው ባለቤትነታቸውን ተቀብለው መነሳት ነ የሚጠበቅባቸው ። ለዚህም ነው ለሕዝብ ጥሪ ሀገርን ለማዳን ተነሳ! ተነሺ! ሆኖ የሚገኘው ። ወያኔ በስልጣን የቆየው በራሱ የአፈና ሀይል ጥንካሬ ሳይሆን በሕዝብ ድክመት ነው ቢባል ስህተት አይሆንም ። ለድክመቱ ምክንያቶች ቢኖሩም ሕዝብ ይህን ሁኔታ ሊያስወግድ ቀን ተሌት ጥሮ ተጠናክሮ መውጣት ነበረበት፤ አለበት ። የህገር ጉዳይ፤ የህልውና ጉዳይ ነውና ። ለምን አልተቻለምን መርምሮ መፍትሔ መሻት የዜጎች ግዴታና ስራ ነው ። ማንም ከውጭ መጥ በተዓምር ተከስቶ ሕዝብን የሚታደግ አለነበረም፤ ኖርምም ። የድርጅቶች ህልውና ራሱ ከህዝብ የሚሰርጽ መሆኑም ይታወቃል ። ለምሳሌ ኢሕአፓ የትግል ውጤት ነጸብራቅ ነበር ። ሊያግልም የቻለው የህዝብ ትግል የወለደው ሆኖ ከህዝብ ጋር የተቆራኘው በመሆኑ ነበር ። የህዝብ ትግል ከደበዘዘ ይህን ትግል ሊመሩና ሊያጠናክሩ የሚችሉ ሀይሎች ደብዛችው ቢጠፋ የሚያስገርም አይሆንም ። ባለ አቅም መታገል ወሳኝ ነው ማለት ነው ።
አቅም የለንም፤ እሱ ያመጣውን እሱ ይመስልሰው በመሰረቱ የሽፈትና የለምተኝነት አቅዋሞችና አስተሳሰቦች ናቸው ። ራስን ዝቅ አድርጎ የመውሰድ ዝንባሌ። ግዙፍ መስሎ የሚሰየመውም ጠላት የሰዎች ስብስብ ነው ። ያነገበው ብረትም ሊነጠቅ የሚችል ነው ። ብረት ያነገበ ሁሉ የመተኮስም ወኔ አለው ማለትም አይደለም ። በአጭሩ ተራ ሰው ነው ጠላታችን፤አቅሙም በዚሁ ልክ ነው፡ ተናፊም ነው ተባብረን ካጠቃነው ። ይህን መረዳት ብቻ ሳይሆን ማመን ከቻልን ሀገራዊ ግዳጃችንን በሚገባ መፈጸም የምንችል እንሆናለን ። ነውናም ለኢትዮጵያ ሕዝብ የምናደርገው ጥሪ፤ በጋራ ለትግል እንነሳ፤ የሚከፋፍሉንን እናቸንፍ፤ ጠላት ወያኔን ለማጥቃት ባለን አቅም ሁሉ እንቀሳቀስ የሚል ይሆናል ። እምቢታ እናሰማ። እኛ ብዙ ሚሊዮች ነን፤እነሱ ጥቂቶች እሚንቶች ናቸው ። እንነሳባቸውና ድንፋታቸው ከንቱ መሆኑን እናሳይ ። አቅምና ጉልበት የሕዝብ ነው የሚለውን እንመን፤አንጠራጠር፡፤ ር ዞር ብለን የሊች ሕዝቦችን ትግል ስናይ ይህን የሕዝብ ሀያልነት እንረዳለን ። የራሳችንም ተመክሮ ይህንኑ ያረጋግጣል--አጼውም ደርግም የማይበገሩ ተብለው ግን በህዝብ ተቸንፈዋል ። ሕዝብ በጉልበቱ፤ በአቅሙ ላይ መተማመን አለበት ። ወያኔና  ቅጥረኞቹ ሕዝብ ሞራሉ እንዲደቅ፤ ሽንፈት እንዲውጠው፤ ቀቢጸ ተስፋ እንዲወረው፤ አቅመ ቢስነት እንዲሰማው ቅስቀሳቸውን ሲያጧጡፉም ቆይተዋል ። የወያኔ ምሁር ተብዬዎችም በየአቅጣጫው ይህንኑ ሲያስተጋቡ ቆይተው ሕዝብን ጎድተዋል ። ይን መርዝ መንቀል ማውጣትና በራስ አቅምና ችሎታ ላይ መተማመንን ማስፈን መቅደም አለበት። ቀቢጸ ተስፋ ያመጣውን ጨለምተኝነትና ተሽናፊነት አስወግዶ በሕዝብ ሀያልነት ላይ እምነትን አድሶ መገኘትም አስፈላጊ ነው ። ይህ እውን ከሆን ፍርሃታችንን እናቸንፋለን ። ፍርሀታችን ክተወገደ ደግሞ እንኳን አንድ ወያኔን ከነአጋሮቹም ሳይቀር ጠቅለን ምናጠፋቸው ይሆናሉ ።
የወያኔ መዋቅር ሆነ መሳሪያዎቹ ሁሉ በሕዝብ መሀል ያሉ ናቸው --ድክመታቸውም እዚህ ላይ ነው ። አፋኝ ወታድሮችና ፖሊሶቹን ሕዝብ ሊሰርስራቸው ይችላል ። በህብረተሰባዊ ማዕቀብም ሊያዳክማቸው እንደሚችል ተደጋግሞ የተነገረ ነው ። በስልትና በሰ ወያኔን የማዳምና የመከፋፈል እርምጃ ከተወሰደ ወያኔ መጎዳቱና መዳከሙ የማይቀር ነው ። በዝምታ መታየቱ ቀርቶ፤ እጅ አጣጥፎ ወያኔን የሚያስወግድ ተዓምር መጠበቁ አብቅቶ፤ ፍርሃት ተሸንፎ፤ የታሪክ ወኔን አድሶና ቆርጦ መንቀሳቀስ ከተቻለ ሀገር ከጥፋት ትድናለች። ያዙኝ ልቀቁኝ ያሉ እብሪተና አምባገነኖችም ከትቢያ ይደባለቃሉ ። ፍርዳቸውን ያገኛሉ ወይም ሀገርን አጋፍጦ እንደፈረጠጠውና ሓራሬ እንደገባው በስደት ይበሰብሳሉ ። የማይቀር ነው ።
ለኢትዮጵያ ሕዝብ በሞላ ጥሪ!!
ውድ ሀገራችን ወያኔ በሚል ጠላት ተይዛ ወደ ጥፋት እየተገፋች በምሆኑ 24 ዓመት በቃ ብለን በጋራ ህገራችንን ላዳን እንነሳ ። ክፍፍል ያብቃ ። አንገት ሰብሮ አቀርቅሮ መገዛት ያክትም ። ፍርሃት ይሸነፍ ። በወያኔ ላይ በጋራ ባለን አቅም ሁሉ ጉዳት ለማድረስ እንነሳ ። አመጽ መብትም ግዴታም ነው ። ሲበደል ያላመጸ ህዝብ አውቆ መብቱን ያስረከበ ያስረገ ነው ተብሏል ። ሀቅ ነው ። ሰዕናን መጠበቅ ማስከበር ግዴታ ነውና ። ቢጭኑት አህያ ቢጋልቡት ፈረስ የምናል ሕዝብ መሆን የለብንም ። ታሪካ[ችን ይህን ስለማይፈቅድ ወያኔ ይህን ሁሉ ዓመት እንዲገዛን እንዲጋልበን መፍቀዳችን በዓለም አቀፍ ደረጃ ያስገመተን በመሆኑ ማክተም አለበት ።  ዝምታ ለበግም ይላል የሀገራችን ሰው ። ጩኸት ሲያንስ ነው ወያኔ ካደረሰብን ግፍና መክራ ጋር ሲተያይ ። የባእድ ወዳጆቹ ቢገለን ቢጨፍጭፈን ግድ የላቸውም ። ቀደምም ኢትዮጵያን ስለማይወዱ ወያኔ ዓይነቱ የሚያዳክማት ሀይልን ደግፈውና አቅፈው ለስልጣን አብቅተዋልና የኢትዮጵያን ብሄራው ጥቅም የሚያጠብቅ መንግስት እንዲኖር አይፈልጉም ።ስለዚህ ከውጭ ነጻ አውጪ ወይም የነጻነት ትግል የሚረዱ አይመጡም ። በዚህ ላይ እርምን ማውጣት ተገቢ ነው ። ኢትዮጵያን የሚታደጋትና የሚያድናት የራሷ ሕዝብ ብቻ ነውና ለአመጽና ቆራጥ ትግል እንነሳ ነው የሚተላልፈው ጥሪ ።
የህዝብ አካል ሆነው በየምክንያቱ የወያኔ ወታደርና ፖሊስ የሆኑት፤የዘረኛው አገዛዝ በዘርና ጎጥ መሰረት መሳሪያ የሆኑትም ጭምር የህዝብን ድምጽና ሰቆቃ መስማት አለባቸው። አለቆቻቸው ቀውጢ ቀን ሲመጣ አጋፍጠዋቸው መጭ እንደሚሉ ወቅ አለባቸው ። ህዝብ ይህን ሊያስረዳቸውና ከሕዝብ ጎን ቆምን እንዲመርጡ መቀስቀስ ይኖርበታል ። ከውስ መሰርሰርና ማዳከም የሚባለው ይህ ነው ። ወታደሩና ፖሊሱ በቤተመንግስት ታፍኖ ያለ ባለመሆኑ ሕዝብ ሊደርስባቸው ይችላልና በወንጀል እንዳይጨማለቁ፤ አሁንም ቢሆን ሕዝብ ሊምራቸው ሊቀበላቸው እንደሚችል በስልት በመቀስቀስ ረታቸውን ወደ ህዝብ ሳይሆን ወደ ወያኔ እንዲያዞሩ ለማሳመን ጥረት መካሄድ አለበት ። ቀላል ስምሪት አይደለም ። ግን መደረግ መሞከር ያለበት ነው ። የወያኔ መኪያ ጦሩ፤ አፋኝ ሀይሉ ነው ። ጦሩ ደግሞ የወያኔ ቢባልም ሁሉም ለወያኔ ድርጅት አባልና ተግዢ የነበረ አይደለም ። በትግሬነት የተሰለፉት ያሉት ያህል የዚህ ጠባብነትና ወይም ክልል አባል ያልሆኑም ብዙ ናቸው ። በተለይ እነዚህ ላይ አተኩሮ በታታኝ እንቅስቃሴ ማድረግ ይቻላል ። መሞከርም አለበት ። ወያን ማዳከሚያው መንገድ አንዱ ጦሩንና አፋኝ ሀይሉም ማዳከም ነውና በቸልታ የሚታይ ተልዕኮ አይደለም ።
በአጭሩ ህዝብ የህገር ማዳን ግዴታ አለበትና ይህ ግዳጅ መቀበል አለበት ። ሁላችንን የሚመለከት ነው ። ለግዳጁ ዝግጁ ሆነን እንገኝ ።
ጸረ ወያኔ ትግል ይፋፋም !
ሀገራችንን እናድን !!


No comments:

Post a Comment