Tuesday, August 9, 2016

ከጨርቁ ምን አለን! የፍኖተ ራዲዮ የእለቱ ወቅታዊ ሀተታ


ከጨርቁ ምን አለን!

ወያኔዎች ከጨርቁ ምን አለን! እያሉ ሲዝናኑ ቆይተው፣ ህዝቡን ለማጭበርበር የባፎሜት የጥንቆላ ምልክታቸውን በሰንደቅ ዓላማው ላይ ለጥፈው፣ የአንድነት አርማ ነው እያሉ ሲያሾፉ፣ ቆይቶም ቢሆን፣ የአጋንንት አርማ መሆኑን ህዝብ ደረሰበት። የመቶ ዓመት ታሪክ ነው ታሪካችሁ ሲለን የሰነበተው፣ የወያኔ ቁንጮ፣ የሚሊኒየም በዓልን ሲደንስበት አሳየን። የክልል ባንዲራ እያሉ ለእያንዳንዱ ማህበረሰብ ያከፋፈሉትም ቢሆን ህዝቡ ከልቡ የተቀበለው ሳይሆን፣ ካድሬዎቻቸው ህዝብን እያዋዙ ለመዝረፍ፣ ኢትዮጵያን ለማዳከም፣ የተጠቀሙበት ዘዴአቸው መሆኑን፣ የብዝበዛ፣ የአፈና፣ የመብት ረገጣ፣ ምልክት መሆኑን አሳይተውናል። ድሮስ የሰይጣን ባንዲራ፣ ለሰው ልጆች ይጠቅማል ተብሎ እንዴት ይታሰባል? የህዝብ ጥያቄ ፍትሃዊ መንግስት ይኑረን፣ መሬታችን፣ ቋንቋችን፣ ባህላችን ይከበር እንጂ! የማንነት ጥያቄ አርማ የሆነውን፣ የብዙ አርበኞች ደምና አጥንት የተከሰከሰበትን፣ የነፃነት ምልክት ሆኖ ለጥቁር ህዝቦች በሙሉ ሲያገለግል የቆየውን አረንጓዴ ቢጫ ቀይ ሰንደቅ ዓላማን እንሻር የሚል አይደለም።
የኢትዮጵያ ሰንደቅ ዓላማ ሁሉንም የሚወክል ባይሆን ኖሮ እነ ገረሱ ዱኪ፣ እነ ፊታውራሪ ሀብተጊዮርጊስ፣ እነ ጎበና ዳጨው፣ እነ ጄኔራል ጃገማ ኬሎ፣ እነ ዑመር ሰመተር፣ እነ አበበ አረጋይ፣ እነ በላይ ዘለቀ፣ እነ ዘርዐይ ድረስ ወዘተ. ባልተዋጉለት ነበር። እነዚህ ሁሉ አርበኞች አምነውበት ያደረጉት እንጂ! በማንም ተፅዕኖ ደርሶባቸው የፈፀሙት፣ በማንም ተመርተው ያከናወኑት አይደለም። ራሳቸው የነፃነት አባወራዎች ነበሩ። ስለዚህም በኢትዮጵያ ሰንደቅ ዓላማ ማፈር በነዚህና በሌሎችም ጀግኖች አባቶች ማፈር ማለት ነው። የአርበኛ ገድል የሚያሳፍረው ባንዳ ብቻ ነው። አለበለዚያ ህዝብ በኩራትና በአክብሮት ነው የሚቀበለው። ስለዚህም ነው ወጣቱ፣ በውጭም በግቢም ሰንደቅ ዓላማውን አቅፎ፣ በየአደባባዩ ሲዘምር የሚታየው። ወያኔ የውጭ መላክተኛ በመሆኑ ጭነው የላኩትን ሸክሙን የጎንደር ወጣት አራግፎለታል። የኦሮምኛ ተናጋሪው ወጣትም በተመሳሳይ መልኩ ሰንደቅ ዓላማዋን ከፍ አድርጎ ይዞ ጥንት አያቶቹ የተዋጉላትን ኢትዮጵያ ከባዕድ ተንኮል ለማዳን መንቀሳቀስ ይኖርበታል። አንድ ቀረው የሚባል ነገር ያ ብቻ ነው። ኢትዮጵያ በነፃነት ያኖረች፣ ከውጭ ወራሪዎች እራሷን ጠብቃ የቆየችና፣ ዜጎቿን ያኮራች ሀገር እንጂ የሚታፈርባት አይደለችም። የሚያፍሩት ባንዳ የባንዳ ልጆች ብቻ ናቸው። ዓላማቸው አልተሳካላቸውምና። የአርበኛ ልጆች እርስ በርሳቸው የሚናበቡበት ቋንቋ አላቸው። የጎንደር አማራ ወጣቶችና የአዳማ ኦሮሞ ወጣቶች ሀቁን አውቀው፣ ስሜት ለስሜት ተገናኝተው፣ የሱ ደም የኔ ነው ተባብለው፣ ወንድሜን አትንኩት ተባብለው፣ ማንነታቸውን አስመስክረዋል።

ወያኔ የአማርኛ ቋንቋን ለማጥፋት ቢጥርም በአብዛኛው የተጠቀመበት በኦሮሞ ወጣቶች ላይ ነው። የትግራይ ወጣቶች አማርኛ ኦሮምኛ ሌላም እየተማሩ ለስለላ ሲጠቀሙበት፣ ኦሮሞውን ነጥለው ለማስቀረትና በፌዴራል አስተዳደር ውስጥ ድርሻ እንዳይኖረው፣ በየክልሉ እየሄደ ኢንቬስተር እንዳይሆን እንደልቡ በሌሎች ስፍራዎች እየተዟዟረ እንዳይሰራ፣ በአንድ አጥር ውስጥ ታስሮ እንዲቀመጥ ለማድረግ ተሰልቶ የተሰራ እንደሆነ ከኦሮሞ ወጣት የሚጠፋ ነገር አይደለም።

ችግር እየፈጠሩበት ያሉት በጠባብ ዘረኝነት ታውረው ከሌላው ወገኑ ጋር በጠላትነት እንዲተያይ ለማድረግ የሚሞክሩ ጠባብ ጎሰኞችና፣ ዘረኞች ለስልጣን ጥማቸው ማርኪያ ለማድረግ ወጣቱን በተለያየ መልክ ለማዘናጋት የሚጥሩ መሆኑ ነው። ከወያኔ ባልተሻለ መልኩ የውጭ ተልዕኮ ያላቸው የድርጅት መሪዎች ነን የሚሉ እንዳሉ፣ በወጣቱ ደም ደሞዛቸዉን የሚያገኙ እንዳሉ ግልፅ ነው። የሚያዋጣው የነዚህ አይነቶቹ፣ በህዝብ ልዩነት፣ በሀገር ጥፋት ላይ እንዲሰሩ ተልከው የመጡ መሆናቸውን አውቆ ማራቅ ነው። ህዝብ ሌላ ወያኔ፣ በላዩ ላይ ለመሾም አይታገልም፣ ፊትም አልታገለ። ኢትዮጵያ ለአንዴም ለሁልጊዜም ከምዝበራ፣ ከጭቆና ተላቃ፣ ህዝቧ በፈቀደው መሪ በምርጫ መተዳደር ያለባት ሀገር ለማድረግ ፊትም ብዙ ደም ፈሷል። አሁንም እየፈሰሰ ነው። ባንዶች በተለያየ ታክቲክ እየቀረቡ ህዝብን ያዋዛሉ። ወጣቱ ትግል ውስጥ ሲገባ ይህን የመሳሰለ ደባ፣ አጠገቡ ባለ ታጋይ ነኝ ባይ ሊፈፀም እንደሚችል መገንዘብ ተገቢ ነው። ይሉኝታና ጥቅም ለትግል አይበጁም። ስለዚህ የአዳማውና የጎንደሩ ወጣቶች የአዲስ አበባውና የሌሎቹም ስፍራዎች፣ ወጣቶች በበለጠ ሁኔታ ተቀራርበውና ተጠናክረው፣ ዓላማቸውን አስተካክለው መጓዝ ይጠበቅባቸዋል። ደምህ ደሜ ነው! ህይወትህ ህይወቴ ነው! ብሎ በአንድነት መነሳት የሀገር ልጆች ግዳጅ ነው። ከዚህ ውጭ የሚደረግ ትግል ወያኔን በስልጣን እንዲቆይ ማድረግ እንጂ ሌላ ፋይዳ አይኖረውም። ኢትዮጵያ በዘርና በጎሳ መከፋፈያ ዘመኗን ያለፈችው ገና ድሮ ነው።

የቋንቋ አገዛዝ ያሳየን ነገር ቢኖር፣ አንዱ ጎሳ በሌላው ላይ የበላይ አዛዥ ልሁን የሚሉ ግለሰቦችን፣ ሌቦችን፣ ዘራፊዎችን፣ ሀገር ሺያጮችን፣ ሲያስተናግድ እንጂ! ፍቅርን አንድነትን፣ አብሮነትን ለህዝብ ሲያስተምር አይደለም። ይህ ሁኔታ አገዛዙ ትግሬ በመሆኑ የተከሰተ የተለየ ድርጊት አይደለም። የትኛውም ብሄረሰብ በጎሳ ተደራጅቶ ስልጣን ከያዘ፣ የመጨረሻ ግቡ፣ ጥላቻን ማስፋፋት፣ እኔ የበላይ ነኝ ማለት ወዘተ. ነው። በዚህ በኩል የሁለቱ ብሄረሰቦች
የጎንደር የአማራ ወጣቶችና፣ የአዳማ የኦሮሞ ወጣቶች፣ ብራቮ! ወያኔ የከለለውን የቋንቋ ድምበር ጥሳችሁ፣ የራሳችሁ ቋንቋ ፈጥራችሁ መግባባታችሁ፣ አንዱ ከሌላው የተለየ ህይወት እንደሌለው ለማይገባው ሁሉ አሳይታችሁዋል።
ለሌሎቹም አርአያ እንደምትሆኑ ጥርጥር የለውም። የወያኔን የጥንቆላ ምልክት ያለውን ባንዲራ አሽቀንጥሮ ጥሎ የኢትዮጵያን ሰንደቅ ዓላማ በቦታው መተካት የትግሉ እምብርት ነው። የወያኔ ባንዲራ ካልወረደ እርኩስ መንፈስ በየሰዉ ላይ እንደነገሰ ይሰነብታል። አጋንንትን የሚያባርረው ጠበል ንፁሁ፣ ታሪካዊውና፣ ባለ ገድሉ፣ የአርበኞች ቅርስ የሆነው ቀስተ ደመናው የኢትዮጵያ ሰንደቅ ዓላማ ብቻ ነው።

ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር!

በተባበረ ትግል ህልውናችንን እናስከብራለን!!

No comments:

Post a Comment