Wednesday, September 21, 2016

ከእኛ በላይ ፉጨት ..... አፍ ማሞጥሞጥ! ከናሆም ግርማ

... ጅብ ብዙ ወለደች አሉ። ታዲያ ልጆችዋን አስቀድማ ስትጓዝ አንዳቸውም ሳይቀሩ ያነክሳል በሁኔታው በጣም አዝና ‘’ አያችሁ ልጆች ሁላችሁም ታነክሳላችሁ እናም ከእንግዲህ አረማመድ ከእኔ መማር አለባችሁ’’  ብላ ከፊታቸው ቀድማ ልታሳያቸው ሞከረች። ከእነርሱ በባሰ ሁኔታ ማነከሷን ያዩ ልጆች ..... ‘’ በነገርሽን ይበቃ ነበር’’ አሏት አሉ።
በዚህ በምኖርበት የምዕራቡ አገር ተወላጅ የሆነ አንድ ወዳጄ አንድ ቀን ‘’ለምንድን ነው ከሁሉም  ስሞቻችሁ ጎን ’’ዲሞክራሲያዊ የሚል ቃልን የምታስቀድሙት ብሎ ይሽው እስከዛሬ ልመልሰው ያልቻልኩትን ጥያቄ እንደጠየቀኝ አስታውሳለሁ። አብዮታዊ
ዲሞክራሲያዊ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ፣ ፍትሀዊ፣ ዲሞክራሲያዊ... ኧረ ስንቱ በስሙ ውስጥ ካለው ትርጓሜ እና ተግባራዊነቱ አንፃር በአለም ከመጨረሻዎቹ አስር አገራት አንዱ ሆነን ሳለን የሀገራችን ፓስፓርት /passport/ እንኳን ሳይቀር በፊቱ ገፅ ላይ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፓብሊክ ተብሎ  መገሸሩ እጅግ አስገራሚም አሳፋሪም ነው።
ከእኛ በላይ ፉጨት አፍን ማሞጥሞጥ ነው እንዲሉ ከክፋታቸው ይልቅ በጎነታቸውን ያጎላላቸው ይመስል ዛሬ የኢትዮጵያን የመገናኛ ብዙሀን ዜና ትእግስቱ ኖሮት ለአስር ደቂቃ ያደመጠ አንድ ሰው ሰላሳ ወዳጆቹን በየ እስርቤትና በየመቃብሩ እንዳልሸኘ ሁሉ ሰላሳ ግዜ ዲሞክራሲያዊ ውይይይ፣ ዲሞክራሲያዊ ልማት፣ ዲሞክራሲያዊ ትግል፣ ዲሞክራሲያዊ ምክክር፣ ዲሞክራሲያዊ ተሳትፎ..... ወዘተ የሚሉ ቃላትን መስማቱ አይቀሬ ነው ሌላው ቀርቶ 95 ሚሊዮን ህዝብን ይወክላል ብለው በሚዘምሩት ብሄራዊ መዝሙር ውስጥ እነ ዲሞክራሲ እነ ፍትህና የህዝብ ክብር የተሰኙ ቃላቶች ተሰልፈው ሲዜሙ ምን ያህል ወያኔ በዜማ እና በአሽሙር እያላገጠበት መሆኑን መረዳት ይቻላል።
በአሜሪካን የሚገኘው የአልበርት አነስታይን ተቋም በየወቅቱ የዲሞክራሲን ፅንሰ ሀሳብ በተለይ ሰሶስተኛው ዓለም አገሮች ከአምባ ገነንነት ወደ ዲሞክራሲ ሽግግር በሚል በተለታዩ ጊዜ የፅንሰ ሀሳብ ንድፎችን እየነደፈ ያስነብባል። እናም ታዲያ እ.ኤ.አ በሜይ 2010 በአራተኛ ህትመቱ ላይ በተለይ በአለም ታሪክ የሰው ልጆችን በደቦ በመግደል ወደር ያልተገኘለትን ጨካኙን ሂትለር ግራዚያኒን ጠቅሶ ሰውዬው ሰላም ነፃነትና ፍትህ የተሰኙ ቃላቶችን በንግግሩ ውስጥ በመጠቀም ወደር ያልተገኘለት እንደነበረ ያስነብበናል።
ታዋቂዋ የእንግሊዝ ገጣሚና አክቲቪስት አላይስ አስዋርድ /Alice osward/ ደግሞ ዲሞክራሲን በመልካም ዝናብ ትመስለዋለች። በተመጠነ ጠብታ፣ በሁሉም ስፍራ በእኩልነት ከላይ የሚወርድ ቢመስልም በጎ ሀገራት በሌሉበት ሀገራት ላይ ስሙ ብቻ ስለሚገን ጎርፍ ሆኖ ብዙሀኑን ጠራርጎ መጨረሱ አይቀሬ ነው ትለናለች።
ታዲያ ዛሬ ሀሳብን ለምን ተናገርክ ተብሎ  በየጎዳና በጥይት የሚቆላው ወገናችን የተፃረረው የትኛው ዲሞክራሲ ህገ መንግስት እንደሆነ ከቶም ሊገባን አልቻለም። ምክርና ቡጢ ለሰጪው ቀላል ነው እንዲሉ የዛሬው መንግስት ተብዬው ምክሩንም ቡጢውንም እራሱ እየሰጠ ዲሞክራሲ ዘንቦልሀልና እምልህን ብቻ አድምጥ ብሎ በግድያና በእስር ጎርፍ መጥረጉ በእጅግ ያሳዝናል።
መቼም የወያኔ ዲሞክራሲ ቃሉ ሲፈታ ከሰሙ ይልቅ ወርቁ ይልቃልና መንገድ በተቆፈረለት ጉድጓድ በተቀለሰለት መንገድ፣ በተማሰለት ቦይ መፍሰስ ብቻ ግድ ሆነ። በመሆኑም በቃኝ ያለ ህዝብ፣ ተበደልኩ ያለ ወገን ቀለቡ ጥይት እንጂ ከቶም ሰሚ ጆሮ አይደለም። ዲሞክራሲ ለወያኔ፣ ነፃነት ለህወሀት ሰሙ ነው እንጂ ወርቁ እኔ ያልኩትን ተቀበል፣ እኔ ያልኩህን ስማ፣ ያለ እኔ ማንም አያውቅልህም ማለት እንደሆነ ግልፅ ነው። የአገዛዙ ተጠቃሚና ባለ ካዝናዎች እንደ መሪያቸው የሚያነክሱና  ራስ ወዳዶች የራሱ ብሄር ዘሮች መሆናቸው እንኳንስ ሰፊው ህዝን አለም ሁሉ ጠንቅቆ ያውቀዋል።
ለአንድ ሀገር ማንነቱ በውስጡ ያለው ህዝብ ነው። ሀገር ያለ ህዝብ ህዝብ ደግሞ ያለሀገር አይኖርም። በመሆኑም የአንድ ሀገር ምሉእነት አገሩቷ በእኩልነት የሁሉም መሆን የቻለች ጊዜ ብቻ ነው። ወያኔ የመረጠውን ዘርና የተመቸውን አካል ብቻ ይዞ አገርን አስተዳድራለሁ ሊለን አይችልም። መሆኑም በዲሞክራሲ ስም ብቻ ሰፊውን ህዝብ የሚበላ በልቶም የሚጨርስ የአገዳ ትል እንጂ ከቶም ለህዝባችን የሚበጅ መንግስት እንዳልሆነ ልብ ሊሉ ይገባል።

ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኖራለች

Saturday, September 17, 2016

የሰረቁት ሥጋ ያስይዛል መረቁ ( አሰገደች ቶሎሳ ከኖርዌ )ከተሳፈርኩበት መኪና ላይ ሆኜ የሜዳውን ጅረት የተዋቡ ተራሮችንና ኮረብቶችን እያየሁ በሐሳቤ ርቄ በምናቤ ወደ አገሬ ነጐድኩ ማን ይሆን ለምለሚቱ አገሬ ብሎ የዘፈነው። ወዲያው የሀገራችንን ውበት የተዘፈነለንትና የተቀኝንለትን ያህል እንደሚገባ ያላጣጥምነው ለምን ይሆን ብዬ ድንገት እራሴን ጠየኩ የምዕራቡ አገራት ተፈጥሮ በለገሳቻቸው ውበታቸው ውስጥ አንድች ታላቅ ምስጢር እንዳለ ያስታውቃል መቼም ስብዓዊ ፍጡርና ተፈጥሮ የሚታረቀው ሰላምና ዕውነት ፣ፍትህና በጎ ህሊና ሲዋሀዱ ነው። ይኸው በኢትዩጵያ እንደሚታየው ልጓም ያጣ አምባገነንነት በተንሰራፋበት፤ መንግስት ብሎ ራሱን የሚጠራው ወንበዴው የወያኔ ቡድን እና ህዝብ ተለያይተው ነፃነትና ሰላም የሚናፍቅበት አገር ላይ ውበትን ማየት ፈፅሞ አይታለምም። ተፈጥሮ ጠረንዋንና መአዛዋን የሚያሽትላት ውበትና ለዛዋን የሚያይላት ገፅታዋን የሚጋራላት ትሻለች ሰባዊ ፍጡራንን፣ህዝብን ትፈልጋለች።
የአንድ ሀገር ትልቁ ሀበት ህዝብ ነው ማለዳ በስላም ወጥቶ አምሽቶ ወደ ማደሪያው የሚገባ ወገን ነው  ያኔ ሀገር ማለት ተፈጥሮ፤ተፈጥሮ ማለት አገር ይሆናል። ራሱ ወደ ሰማይ የሚያደርስ ግንብ እንስራ በምደርም ላይ ሳንበተን ስማችንን እናስጠራ ብለው እንዳሎት ባቢሎናዊያን ፈጣሪ ግንቡ እንዳይሰራ የፈለገው ከተማ እንዳያድግ ወይስ የሰው ሥልጣኔ እንዳይኖር እስቡ ይሆን የሚል ጥያቄ ሊጭርብን ይችላል ነገር ግን የፈጣሪ ሐሳብ ኣይደለም እርሱ የተመለከተው ሰዎች የተነሱበትን ፍላጉት እና ክፉ ሀሳብ ነበር
ታዲያ ከባቢሎን ዘመን ሐሳቤን ወደ አገሬ መልስ አድርጌ አገሬ ያለውን የወንበዴውን አገዛዝ ሥርዓት ማሰብ ጀመርኩኝ ዛሬ በኑሮ ውድነት በቀን አንድ ግዜ እህልን መቅመስ ላቃተው በአይኑ ብቻ የሚያየው ህንፃ እንደ ባቢሎን ብትገነቡለት ለሱ አንዳች ረብ የለውም መንግስት በባቢሎናዊ አይነት ትምክቱ ተይዞ ካልሆነ በስተቀር ከህንፃው በለይ በርካታ የተራቡ አንጀቶች ያልሞሉ ጐተራዎች የደረቁ ጉሮሮዎች አገር እያላቸው እንደሌላቸው የበላይ ገዢ የሆነው ዘር የፈለገበት ቦታ እንደፈለገው ሲያገኝ ከዚያም አልፎ የውጭ ባለ ሀብቶች መሬቱን ሲቆራመቱት ከቀየው ሲያባርሩት የህዝብ ልብ እንደደማ እንኳን ወያኔ ዓለም ጠንቅቆ ያውቃል።
በኮንደሚንየም ስም ኑሮዬ ብሎ ከሚኑርበት ከቀኤው እያፈናቀላችሁ ከጣራው እየበተናችሁ ማደሪያ ሰጠነው ከምትሉት ማደሪያውን የቀማችሁትን መብለጡ ግልፅ ሆኖ ሳለ በየመገናኛው ብዙሀኑና በየአደባባይ ቤት ሰጠንህ እያላችሁ ታደርቈታላችሁ። የሰረቁት ሥጋ ያስይዛል መረቁ እንዲሉ እንደ በዓል ቅርጫ የሰፊውን ደሀ መሬት ለባዕድና ለራሳችሁ ስዎች ቸብችባችሁ የገነባችሁት የግል መኖሪያና ድርጅት እንዲሁም በየባንኩና በየኪሳችሁ በየውጭ አገር ባንኮች ያከማቻችሁት ገንዘብ ወትሮም ተስርቆ የተበላ  ነውና ቀኑ ሲደርስ ተመልሶ ወደ ሰፌው ህዝብ መግባቱ አይቀሬ መሆኑን እየገጠማችሁ ያለው ህዝባዊ ትግል በዋቢነት ልታውቁት ይገባል።
ከብሔር እና ዘሬ ይልቅ ኢትዩጵያነቴን አበክረው የነገሩኝ ወላጆቼ አገር ዘሬን እንጂ ዘርሽ አገርሽን ይቀድማል ብለው ከቶም አላስተማሩኝም የአሁኖቹ ገዚዎች ለሌብነታቸው መች ዘንድ አባትሽ ኦሮሞ እናትሽ ደግሞ አማራ እያሎ ኢትዩጰያነቴን ሲያላግጡበት ማየቱ በእጅጉ ያሳዝናል። እንዲህ እንደ አሁኑ


ዘርን ቆጥሮ የአንድ ብሔር የበላይነት ሳይንሰራፋ ታግሎ ለስልጣን ያበቃው ኢትዬጵያዊ ነኝ ያለ ህዝብ እንጂ አንድ በሔር አልነበረም በመሆኑም ዛሬ እንዲህ ድምፁን ሊያስማ የውጣውን የአማራን የኦሮሞ ወጣት በየጕዳና እንዳበደ ውሻ በጥየት የምትቆሎት ለትግሎ መቀጣጠል ነዳጅ እንጅ ውሀ አለመሆ ልብ ልትሎትም ይገባል ከኛ በላይ ፎጨት አፍን ማሞጥሙጥ ነው እንዲሎ ወያኔ የዲሞክራሲ እድምታ ተንሸዋሮበት እኔ በቆፈርኩልህ ጉድጓድ ብቻ ሂድ እኔ በጠረኩልህ ጉዳና ንጎድ ይለናል ዜማውም የእኔ ፎጨቱም የኔ ጆሮውም የእኔ ነው ካለን ሰነበተ። ህዝቡ ምንን ይፈልጋል ምንንስ ይጠቃል ብሎ ከማለት ይልቅ የአምባ ገነን ጉዞ እንቅፋቶችን በጥይት አፈሙዝ መልቀሙን መርጧል ውጤቱ ምንኛ የከፋ መሆኑን ከማስተዋል ይልቅ መግደሉንም በእጅጉ ተያይዞታል ሩቅ እንኳን ሳንሄድ በዚሁ አህጉራችን አፍሪካ /ዘመን መጨረሻና መጀመሪያ ላይ የነበሩት ህዝባዊ አመፆቹ የተከፈለባቸው ዋጋና የፈሰሰው ደም እጅግ አሳዛኝ ቢሆንም የነ ማሊን ሴራሊዪን ዲክሞክራትክ ኮንጎን  የመንግስት ለውጥ ማየት የቅርብ አብነት ነው የተባ ጆሮና የሚያስተውል አይን ካለ  እውነተኛ ትግል በቆሰቆሱት ቁጥር ይብሳልና የሰውን ላብን ጉርሶ የት ደርሶ እንዲሉ ይህ ሁሉ የክፋት ግንባችሁ በጠንካራው የህዝብ ኃይል እንደ ባቢሎን ግንብ የሚፈርስበት ግዜ እሩቅ አይሆንም። ትግሉን አሁን ካለበት ደረጃ ከፍ ማድረግ ከተቻለ፤ በአጭር ጊዜ ውስጥ አንድ ዕመርታ ማሳየት ይቻላል። ለዚህ ተግባራዊነት መሳካት ሁላችንም ሀገር ወዳድ ኢትዩጵያዊያን ወያኔን በመቃወም ባለንበት ስፍራ ሁሉ በሁሉም አቅጣጫ እንታገል !

ኢትዮጵያ በሕዝቧ ተከብራ ትኖራለች !!