Sunday, October 23, 2016

ከተንኮለኛ ሰው ስንቅ አይቀላቅሉም ( አሰገደች ቶሎሳ )

የንብን ቀፎ ተንተርሰው የሚያደምጡትን የህዝብ ድምፅ እንደ እንቅልፍ ክኒን የሆነላቸው የወያኔ እብሪተኞች መሬትን ሽጠው የበሉት ስብና ጮማ ጆሮአቸውን ደፍኗቸው መልሰው ለራሳችን የህዝብ ተቆርቋሪ የድሆችን እምባ ጠባቂ ነን እያሉ ዛሬም በውድቀታቸው ዋዜማ የሀገር ብቸኛ አማራጭ እኛው ነን እያሉ ይቀልብናል:: ከጥንትም ይህ መሰሪ ዓላማው ብሄራዊ የሀገር ፍቅርና ህዝብን ያማከለ አልነበረምና በድቡሽት ላይ እንደተዋቀረ ቤት የውጭውን አሳምሮ የአልባ ኒያን ሶሾሊዝምን ፕሮግራም የገለበጠውን የትግራይን ሪፕብሊክ ሊመሰ ነበር የመከረው:: ሆኖም በዚህ ጠባብና ጨለምተኛ አላማው የመጀመሪያ ተጠያቂው የራሱን የትግራይህዝብ ነበር በዚህ በተዛባ አላማው  አባቱን ያላጣ፣ ልጇን ያላጣች እናት፣ ወንደሟን ያላጣች እህት የትግራይ ልጅ አልነበረም ምንም እንኳን ይህ ሁሉ ግፍ በራሱ በትግራይ ህዝብ ላይ የተፈፀመ ቢሆንም ዛሬ ያለውን የትግራይን ህዝብና የወያኔን ግንኙነት ስንመለከት የተለየ ሆኖ እናገኘዋለን::  በተለይም የትግራይ ምሁራን ክፍል ከወያኔ በፈሰሰላቸው መና በኢትዬጵያ ህዝብ ሀብት ናውዘው እየደረስ ያለው የጐሳ አስተዳደር ጥፋት አልታያቸው ብሏል::  በትግራይ ህዝብ ስም መነገይቁም ከማለት ይልቅ የሚካሄደውን የግፍ ጭካኔ የሚገባ ነው እያሉ ነው መደገፍ ተያይዘውታል::
በአንድ ወቅት የቀድሞው መሪያቸው መለስ ዜናዊ በራሱ አንደበት የህወሀት የመኖር ህልውናው የተመሰረተው የሌሎች ብሄሮች በተለይም አማራና ኦሮሞ ተስማምቶ የማይኖሩ ለታ ነውና ሁለቱ ብሔሮች ዘወትር እሳትና ጭድ ሆነው መቀጠል እንዳለባቸው የድርጅታችን እምነት ነው:: በዚህ ዙሪያ ድርጅቶታችን ጠንክሮ ሊሰራ ይገባል ሲል ተድምጧል:: በውጤቱም ህዝብን  በመከፋፈል ልዩነት የጠፋ የዘር፣ የጐሳ የኃይማኖት፣ የአውራጃ የቀበሌና የመንደር ግጭቶችን በመጠር እርስ በርሳቸው እያፋ ሰላምና ኢትዮጵያዊንትን አራርቀው እነርሱ የሀገሪቱን ሀብት ያጋብሳሉ ወያኔዎች ከሱዳን ጋር የትግራይ ድንበር ለመፍጠር በያዙት እቅድ መሠረት በአካባቢ የሚኖሩት የጎንደር አስተዳደር ወረዳዎች በተለይ የወልቃይት፣ ጠገዴና ሑመራ አካባቢ ኢትዮጵያውያንን በግፍ አስለቅቀው ለም የእርሻ መሬት በወረራ ይዘዋል። በሕዝቡ ላይ የሚፈጸመው ሁሉን አቀፍ ግፍ ተዘርዝሮ የሚያልቅ አይደለም፣ በይዘቱ ከኢጣሊያ ፋሽስት ያላነሰ ግፍ ከሕፃን እስከ ሽማግሌ ሳይለይ ቀጥሏል። ለዚህም ይመስላል የአካባቢው ህብረተሰብ፡-  በሆድም ያላችሁ በጫንቃም ያላችሁ  የወያኔን ነገር ትረሱታላችሁ በማለት የተቀኙት።
እንደሚታወቀው  ወያኔዎች የወረራ አድማስን በማስፋት በከፋ መልኩ በጠገዴ ሠሮቋና በታች አርማጭሆ አብደራፊ አካባቢ ተጨማሪ ሰፊ የእርሻ መሬት ፍለጋ ዘመቻው ላይ ተገተው እየሰሩበት ነው. በትግራይ መንግሥት የሰለጠኑ ሚሊሻዎችና በረከት ስምዖን የሚመራውና የአማራን ሕዝብ እወክላለሁ በሚለው ሆድ-አደር ብአዴን አስፈጻሚነት የመስፋፋት ዘመቻውን እውን ለማድረግ በከፋ መልኩ ከፍ ዝቅ እየተባለም ነው። ወረራውን በመቃወም መብታችን ይከበር ያሉትን የሀገሬው ሰዎች ትግራይ አሰልጥነው ባስታጠቋቸው ልዩ ሚሊሻዎች መግደልና እስርን ተያይዘውታል::  በዚህ ግጭት ብዙ ሰዎች ሞተዋል ተጎድተዋል፣ ውዝግቡም አልበረደም ይቀጥላል። ወያኔዎች በነደፉት ትግራይን የማስፋፋት አዲስ እና ቀጣይ ዓላማ ካሁን ቀደም በኃይል ይዘው የትግራይ ክልል ነው ብለው ከወረሩት ዳንሻ ከተማ ወደ ደቡብ ምዕራብ 103 ኪሎ ሜትር በረሃውን አቋርጦ ከአብደራፊ ጋር ለማገናኘት ብሎም ሰፋፊ የእርሻና የትግራይ ሠፈራ ለማካሄድ ታስቦ ሱር በተባለው የወያኔ የመንገድ ሥራ ተሰርቷል። ለዚህ መንገድ ሥራ የሚወጣውን $300 ሚሊዮን ብር ወጪ የኢትዮጵያ መንግሥት መድቧል። በዚህ ሳያቆም ከሰሜን ወደ ደቡብ የሱዳንን ጠረፍ እያዋሰነ ማለትም ከሑመራ ጫፍ ከልጉዲ ተነስቶ ወደ አብደራፊ የሚያገናኘው መንገድ በአስፋልት እየተሠራ ነው። የዚህ ወረራ ቅርጽ ሦስት ማዕዘን ቅርጽ የያዘ ሲሆን፣በዚህ አካሄድ የትግራይ ምድራዊ አቀማመጥ ተቀይሮ በእስራኤልና አረቦች ያለው ካርታ ዓይነት እየሆነ መጥቷል። ይህም ብቻ ሳይሆን መተማን አልፎ እስከ አባይ ግድብ ድረስ እንሄዳለን የሚል ህልም አላቸው። ይህ አዲስ ወረራ ለምን አስፈለገ ቢባል፣ ለም የሆነውንና ከሱዳን ጋር የሚያዋስነውን መሬት ወያኔዎች ይዘው ባለቤት የሆነው የአካባቢው ኑዋሪው ሕዝብ ከውጪ የንግድም ሆነ ሌላ ግንኙነት እንዳይኖረው በብቸኝነት ለመቆጣጠር መሆኑ ግልፅ ነው።
ከዚህ ባሻገር በስብሀት ነጋ  በሚንቀሳቀው በሦስት አቅጣጫ ትግራይን የማስፋት እቅድ የመቀሌን፣ የአዲግራትና የአክሱም ዩንቨርስቲዎች ይዞ ስራውን በዕቅዱ መሠረት በማካሄድ ይገኛል በዕቅ መሰረት የኬሚካል ኢንጅነሪግን ከአዲግራት ዩኒቨርስቲ ጋር በማስተሳሰር ደጀና ኬሚካል ኢንዱስትሪ በሚል መቋቋሙን፣ የማእድን ዘርፍ በሽሬ እንዳስላሴና ዓዲዳዕሮን ማዕከል ያደረገ፣ የጨርቃጨርቅና አልባሳት ማዕከልን ደግሞ ዓድዋ በማድረግ ከአክሱም ዩኒቨርስቲ ጋር በማስተሣሰር፣የብረታብረት ኢንጂነሪንግን እንዲሁ ከመቀሌ ዩኒቨርስቲ ጋር በማስተሳሰር የትኩረት አቅጣጫ ሆነው እንዲሠሩ እየተንቀሳቀሱ ነው ወያኔና ተባባሪዎች ግዛትን ለማስፋፋትና ሕዝብን በኃይል ለማፈናቀል ባላቸው ዕቅድ መሠረት በጎንደር ሰሜን-ምዕራብ ግዛት ጦር ማሥፈር ጀምረዋል። ወያኔዎችና ምሑሮቻቸው ሊገነዘቡት የሚገባ መሠረታዊ ጉዳይ አለ፣ የሌሎችን መሬትና ሰላም በወረራ አደፍርሶ የታሰበው የትግራይ ልማት እውን ሊሆን ከቶ አይልም። ትርፉ ውርደትና አጉል የጀብደኝነት ሥራ ሲሆን ውጤቱም አስከፊ ነው። አብሮ ተከባብሮ የሚኖርን እና የሚመሩትን ሕዝብ ሰላምና አንድነት ኃላፊነት በጎደለው የጀብደኝነት ተግባር ሊያደፈርሱ አይገባም። ከሁሉም በላይ የትግራይ ታላቅነት እና ልማት በሌሎች ኪሣራ ላይ የተቀመረ ሊሆን አይገባም። በእኛ አመለካከት የትግራይ ሕዝብ እራሱን ከዘረኛው የወያኔ መንግሥት መለየት አለበት። ይህም ማለት ወያኔ በትግራይ ስም የሚያካሂደውን ተስፋፊነትና ወረራ መቃወም፣ የጎሣ ፖለቲካን ሚዛናዊ ያልሆነ ዕድገትን እንደሌሎች ኢትዮጵያውያን በአደባባይ ወጥቶ መቃወም የግድ ይላል።  በኢትዩጰያዊነቱ የሚታመን ማንኛውም ዜጋ በፈለገውና በመረጠው ቦታ የመኖር መብቱም ሊጠበቅለት እንደሚገባ ሁሉ ነዋሪውም ብሄረስብም እንደሌሎቹ  ጐሳዎችን መኖር እንድሚችል ሊቀበሉት እንድሚገባ ግልፅ ነው ኢትዩጵያዊነቱ ከብሄር ማንነቱ ይቀድማል  በመሆኑም የትግራይ ህዝብ እንደ ማንኛውም ዜጋ በመረጠው አካባቢ መኖር ይችላል ነገር  ግን የሰፈርኩት ቦታ ሁሉ የትግራይ ግዛት የሚያደርግ ሥራና ዓላማ ከኢትዩጵያዊነት ውጭ ነው::
መሬቱ የእኔ ነው ከማለቱ ባሻገር በደራ የመሬት ገበያ ሽያጭ ከአፍሪካ ልቆ መገኘቱ አሳፋሪም አስገራሚም ነው ሽጦም የራሱን አቀንቃኞች ካዝና ሲያደልብ ተው የሚለው ስላጣ ከልካይ እንዳጣ በሬ ፋኗል:: ወያኔዎች ኢትዬጵያ  የምትባል ሀገር እንደ አገር መኖር እስካላቆመች ድረስ የጥፋት ዘመናቸውን አያቆምም የዛሬው የኦሮሞ ህዝብ ንቅናቄና አዲስ አበባ መሬት ሽያጭ ተቃውሞ ሳይነሳ ቀደም ብሎ ከሁመራ ጀምሮ ርዝመቱ  1600  እና እስክ  50   ስፋት ያለውን የጠረፍ መሬት ለሱዳን በስጦታ መልክ አስረክቧል:ከተንኩለኛ ሰው ስንቅ አይቀላቅም እንዲሎ የዛሬዎቹ ባለ ዜዎች የአረፍንበትን እንብላ ማለታቸው ሌላውን ብሔረሰብ ቢያስቆጣም አዲስ ነገር አይደልም: ዛሬ ዛሬ የወያኔ መሬት ያጭ ባለፈ ጭቆናና ግድያው ወደር እያጣ መቷል በመሆኑም  ጭቆናው ትግ ወልዷል ትግ አንድነትን፣ አንድነቱ ደግሞ አመፅን አመፅ ደግሞ የወያኔን መቃርን  እያቀረበው ነውና ትግላችንን መቀጠል ብቻኛ አማራጭ ነው::

ኢትዩጵያ ለዘላለም ትኖር!