Monday, October 17, 2016

Finote Radio

#Finote Democracy ፍካሬ ዜናጥቅምት 6 ቀን 2009 ዓ.ም. . (October 16, 2016 Weekly NEWS SUMMARY)
 #ርዕሰ ዜና #ወያኔ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን ዝርዝር የተግባር መመሪያ አወጣ፤ የሕዝቡን አመጽና ትግል አያዳፍነውም ተባለ #ቦረና ውስጥ በሕዝቡ እና በታጣቂዎች መካከል ውጊያ መካሄዱ ታወቀ፤ በጎንደርም በተለያዩ አካባቢዎች ውጊያዎች እንዳሉ ይወራል #በአርሲ ነገሌ የወያኔ አግአዚ ጦር የትግራይ ተወላጆችን በጊዜያዊ ካምፕ ውስጥ እንዲቀመጡ አደረጉ # የወያኔ አገዛዝ ከፍተኛ የበጀት እጥረትና ገጠመው ተባለ  ###ዝርዝር ዜናዎች#####
#የወያኔ አገዛዝ ያወጣው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ የናዚው ጀርመኒ እና ሌሎች አምባገነን አገዛዞች በስራ ላይ አውለውት ከነበረው አረመኔያዊ አጋዛዝ የተለየ ባይሆንም ሕዝብን ለማስፈራራት የተደረገ እንጅ አገዛዙ ባለፉት ዓመታት ተግባራዊ ሲያደርጋቸው የነበሩ እርምጃዎች እንደሆኑ የተለያዩ ክፍሎች እየተቹበት ነው። በአገሪቱ ላይ ወታደራዊ አገዛዝ እንደሚከሰትና የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ እንደሚታወጅ ቀደም ብሎ የፍኖተ ዴሞክራሲ ራዲዮ ያገኘውን ምስጢራዊ መረጃ ዋቢ በማድረግ ለአድማጮች ዜናውን ማድረሱ ይታወሳል። በዚህ ሳምንት የወያኔ አገዛዝ አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ማወጁን ይፋ ያደረገ ሲሆን አዋጁን በበላይነት የሚመራው እነማን መሆናቸው ባይነገርም ከአንድ ብሔር የተውጣጡ የወያኔ ቀንደኛ መኮንኖች በብዛት የሚገኙበት ኮማንድ ፖስት በሚል ስም አንድ ወታደራዊ እዝ መመስረቱ ይፋ ሆኗል። በዚህ እዝ ስር ለሚቀጥሉት ስድስት ወራት የፍለጠው ቁረጠው አገዛዝ በዚህ እዝ ስር በበላይነት እየተመራ ይካሄዳል። ። የዜጎች መስረታዊ መብቶችን በመገደብ ለወያኔ አግአዚ ጦር ሙሉ ስልጣን የሚሰጠውም መመሪያ ይፋ ሆኗል። ከእነዚህም ውስጥ በኢሜል ሆነ በማህበራዊ መገናኛዎች መልክቶች መለዋወጥ፤ አሸባሪ የሚሏቸውን የተቃዋሚ ድርጅቶች ቴሌቪዥኖችና የራዲዮ ጣቢያዎች መስማት፤ ሰልፍና ስብሰባ ማካሄድ፤ በትምህርት ቤት በስፖርት አካባቢና በስራ ቦታ አድማ ማድረግ የተከለከለ መሆኑን ይገልጻል። የፖሊቲካ ድርጅቶችና የሃይማኖት መሪዎች ስለፖለቲካ ማውራት አይችሉም። ወታድሮች ፈቃድ ጠይቀው መሄድም መሰናበት አይችሉም፤ የውጭ አገር ዲፕሎማቶች ከአዲስ አበባ 40 ኪሎ ሜትር ርቀት በላይ አለፈቃድ መሄድ አይችሉም። ከማታው ሰዓት ጀምሮ እስከ ጠዋቱ 12 ሰዓት ድረስ በአንዳንድ አካባቢዎች የሰዓት እላፊ አዋጅ ይታወጃል የሚሉ ናቸው። ከአንዳንዶቹ በስተቀር ብዙዎች በወያኔ የተከለከሉና ለበርካታ ወገኖች ህይወት መጥፋት ምክንያት የነበሩ በመሆናቸው ብዙም አዲስ ሁኔታ ያልተፈጠረ መሆኑ ግልጽ ነው የሚሉ ወገኖች የተለየ ነገር ቢኖር በዕለት ተዕለት ሁኔታ ላይ በቀጥታ ውሳኔ እየወሰኑ ተግባራዊ የሚያድረጉት ለጥቅም ያደሩ አጨብጫዎችና አጫፋሪዎች ሳይሆኑ ከአንድ ብሔር የተውጣጣጡ ጥቂት የወያኔ ምርጥ ባለስልጣኖችና መኮንኖንች መሆናቸው ነው። የሕዝብ ብሶት ከፍተኛ ደረጃ ላ በመድረሱ የሚያካሄደውን ሕዝባዊ የተቃውሞ እንቅስቃሴ ሊለውጠው እንደማይችል እንዲያውም ትግሉ ተጠናክሮ ወደ ሌላ ደረጃ ከፍ ሊእንደሚችል ይተነብያሉ።
#በቦረና ዞን ጎሎሌ በሚባለው መንደር በወያኔ ወታደሮችና በሕዝባዊ ታጣቂዎች መካከል ጦርነት መካሄዱን ከአካባቢው የመጣ ዜና ይገልጻል። በጦርነቱ የቆሰሉ የወያኔ ወታደሮች በመኪና ተጭነው ወደ ሆስፒታል ሲወሰዱ ያዩ መሆናቸውን የአይን እማኞች አረጋግጠዋል። በጎንደርም የተለያዩ አካባቢዎች ውጊያዎች መኖራቸው እየተሰማ ነው።
#የወያኔ ባለስልጣኖች በምዕራብ አርሲ ነዋሪ የነበሩ የትግራይ ተወላጆችን ከየቤታቸው እየለቀሙ በጊዜያዊ ካምፑ ውስጥ ያስቀመጧቸው መሆኑን ከአካባቢው የተገኘው ዜና ይገልጻል። የተቻለ ሲሆን ብዙዎቹ አለፍላጎታቸው ተገደው መወሰዳቸውን ተናግረዋል ተብሏል። በተያያዘ ዜና ባለፉት ሁለት ቀናት በአርሲ ነገሌ ከ10 የበለጡ ሰዎች ተገድለው በየጥሻው የጣሉ መሆናቸው ተነግሯል።
#ለረጅም ጊዜ እየተቀጣጠለ ሲካሄድ በነበረው ሕዝባዊ አመጽና ተከትሎ በመጣው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ምክንያት የወያኔ አገዛዝ ከፍተኛ የበጀት እጥረት እየገጠመው መሆኑ ታውቋል። የአስርችኳይ ጊዜ አዋጁን ተግባራዊ ለማድረግ ለሰበሰባቸውና በየአቅጣጫው ላሰማራቸው ወታደሮችና ሚሊሺያዎች ወጭ ተጨማሪ በጀት በመመደቡና ገቢው እያሽቆለቆለ በመምጣቱ የበጀት እጥረት ተከስቶ በየቦታው የሚደረገው የካፒታል ወጭ ያልተሰጠ መሆኑን ውስጠ አዋቂ ምንጮች ገልጸዋል። ከዚህ በተጨማሪ በባህር ዳር የሚገኙ በርካታ የንግድ ተቋሞች ምርታቸውን ለመሸጥ ያቃታቸው መሆኑን የተናገሩ ሲሆን ከስድሳ በላይ የሚሆኑ ትላልቅ ሆቴሎችና ምግብ ቤቶች የባንክ ብድር መክፈል እንዳቃታቸው ተናግረዋል።
ለዝርዝር ዜናዎች > ከታች ይጫኑ (to listen detail news click below)
To Read: http://www.finote.org/Fikarezena.pdf
To Listen PART 1: http://www.finote.org/TodayPart1.mp3
To Listen PART 2: http://www.finote.org/TodayPart2.mp3

No comments:

Post a Comment