Monday, January 30, 2017

Finote Radio... በወያኔ ኃይሎችና በህዝብ መካከል የተኩስ ልውውጥ ተካሄደ፣ ኢትዮጵያ ከፍተኛ ሙስና ካለባቸው ሀገሮች ተርታ


በወያኔ ኃይሎችና በህዝብ መካከል የተኩስ ልውውጥ ተካሄደ፣ ኢትዮጵያ ከፍተኛ ሙስና ካለባቸው ሀገሮች ተርታ፣ ኩዌት ውስጥ ኢትዮጵያዊቷ በስቅላት ተገደለች … 


ፍኖተ ዴሞክራሲ የኢትዮጵያ  አንድነት ድምጽ ሬዲዮ (ጥር 18 ቀን 2009 ዓ.ም.) – በባህር ዳር በወያኔ የጸጥታ ኃይሎች እና በሕዝብ ወገኖች መካከል የተኩስ ልውውጥ ተደረገ – ትራንስፓረንሲ ኢንተርናሽናል የተባለው ድርጅት ኢትዮጵያን ከፍተኛ ሙስና ከሚካሄድባቸው አገሮች መካከል መደባት – በኩዌት የሞት ቅጣት ከተፈጸባቸው መካከል አንደኛዋ ኢትዮጵያዊት መሆኗ ታወቀ – ሼኩን በመግደልና እስላማዊ መንግስት ለማቋቋም ሴራ በመጠንሰስ በሚል የሀሰት ክስ የተወነጀሉ ዜጎች የእስራት ቅጣት ተፈረደባቸው – በወያኔ አገዛዝ ሶማሌያ ውስጥ የተሰማሩ ወታደሮች ባካሄዱት ግድያ ላይ የአፍሪካ ህብረት ያደረገውን ምርመራ ይፋ እንዲያደርግ ሂውማን ራይትስ ዎች ጠየቀ – የአልሸባብ አባላት የአሜሪካ የስለላ ድርጅት አባሎች ናቸው ያሏችውን ሶስት ግለስቦች ገደሉ – የስራ ማቆም አድማ በማድረግ ላይ ያሉት የኬኒያ ዶክተሮችና ነርሶች እስከ አምስት ቀን ድረስ እንዲመለሱ ፍርድ ቤት አዘዘ።
ጥር 17 ቀን 2009 ዓ.ም. ከምሽቱ ሶስት ሰዓት አካባቢ በባህር ዳር ከተማ ቀበሌ 15 ማዘጋጃ ቤት አካባቢ ማንነታቸው ባልታወቀ የሕዝብ ወገኖችና በወያኔ የጸጥታ ኃይሎች መካከል የተኩስ ልውውጥ መደረጉ ታውቋል። ከወያኔ በኩል ምን ያህል እንደሞተና እንደቆሰለ ባይታወቅም የህዝቡ ወገን በኩል ሁለት ሰዎች መጎዳታቸው ይነገራል። በአካባቢው የጸጥታ ውጥረት የፈጠረ ቢሆንም ብሶት ያለበትን ሕዝብ ተስፋ ከፍ አድርጎታል ተብሏል። ዝርዝሩን እንደደረሰን እናሰማለን።
ትራንስፓረንሲ ኢንተርናሽናል የተባለው ድርጅት ረቡዕ ጥር 17 ቀን 2009 ዓ.ም. ይፋ ባደረገው አመታዊ ዘገባ በፈረንጆቹ 2016 ዓ.ም. በመንግስት ደረጃ ከፍተኛ ሙስና ከተካሄደባችው አገሮች ኢትዮጵያ አንዷ መሆኑን ዘግቧል። ጥናት ከተካሄደባችው 176 አገሮች መካከል ኢትዮጵያ 108ኛ ሆና ስትመደብ ዴንማርክ፤ ኒውዚላንድ፤ ፊንላንድ፤ ስዊድንና ሲወዘርላንድ የሙስናው ደረጃ በጣም ዝቅተኛ ሆኖ ከሚታይባቸው አገሮች መካከል በመጀመሪያው ተርታ የተመደቡ ናቸው። በኢትዮጵያውስጥ ሙስና በጣም ተስፋፍቶ የሚገኝ መሆኑን አገዛዙ ራሱ ያመነው ሲሆን ጥናቱ የወያኔ ቁንጮ አባላት በተለያየ ስልትና በድብቅ በየጊዜው ወደ ውጭ የሚያወጡትን የአገር ሀብት ቢያካትት ኑሮ ኢትዮጵያ ከመጨረሻዎቹ አገሮች መካከል ልትመደብ ትችል ነበር ተብሏል።
በዛሬው ቀን በኩዌት የሞት ቅጣት ከተፈጸባቸው ግልሰቦች መካከል አንደኛዋ ኢትዮጵያዊት መሆኗ ታውቋል። አማከል በሚል ስም የተጠቀሰችው ኢትዮጵያዊት በሞት የተቀጣችው በ2000 ዓ.ም. በአሰሪዋ ላይ የግድያ ወንጀል ፈጽማለች በሚል ክስ ነው። በወያኔ ባለስልጣኞች አሻሽጭነት ወደ መካከለኛው ምስራቅ በባርነት የሚሄዱ ኢትዮጵያውያን በአሰሪዎች ከፍተኛ በደል የሚደርስባቸው መሆኑ በየገዜው የተዘገበ ሲሆን ከሚደርስባቸው ግፍና ስቃይ መብዛት የተነሳ አንዳንዶቹ በደም ፍላት ርምጃዎች ሲወስዱ መቆየታቸውም የሚታወቅ ነው።
ሼክ ኑሩ ይማምን በመግደልና፤ የእስላማዊ መንግስት ለማቋቋም ሙከራ በማድረግ በሚል ክስ ተወንጅለው የነበሩ 13 የእስልምና ሃይማኖት ተከታዮች ከ 6 እስከ 16 ዓመት በሚድርስ እስራት እንዲቀጡ ፍርድ ቤት የወሰነባቸው መሆኑ ታውቋል። ግለሰቦቹ የሀሰት ክስ እንደተመሰረተባቸው በርካታ ወገኖች ሲገልጹ መቆየታቸው የሚታወቅ ነው። በተያያዘ ዜና የጋምቤላ መሬት ለባዕድ ከበርቴዎች መሸጡን በመቃወም የሚታወቁትና በሽብረተኛነት ክስ ተወንጅለው በእስር ላይ የሚገኙት አሞት አግዋ ጥር 10 ቀን 2009 ዓም. የወያኔው ጠቅላይ ፍርድ ቤት በ50 ሺ ብር ዋስትና ከእስር ተፈተው ጉዳያቸውን እንዲከራከሩ ቢወስንም የቅሊንጦ እስር ቤት እስካሁን ያልፈታቸው መሆኑ ታውቋል።
ሂውማን ራይትስ ዎች የተባለው የሰብአዊ መብት ተንከባካቢ ድርጅት ባለፈው ዓመት ሐምሌ ወር የወያኔ አገዛዝ በሱማሊያ ያሰማራቸው ወታደሮች 14 ሰላማዊ ሰዎችን መግደላቸውን ተከትሎ የአፍሪካ ኅብረት ሲያካሄደው የነበረውን የማጣራት ምርመራ ለሕዝብ ይፋ እንዲያደርግ ጠይቋል። ባለፈው ዓመት ሐምሌ 10 ቀን 2008 ዓ.ም. በሱማሊያ ከባይደዋ ከተማ 37 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በሚገኘው ዋርድንሌ በሚባለው መንደር ወታደሮቹ ምንም ዓይነት የተኩስ ጥቃት ሳይደርስባቸው በየቤታቸው የነበሩ 14 ነዋሪዎችን የገደሉ መሆናቸውንንና ብዛት ያላቸውን ማቁሰላቸውን የአይን እማኞች የመሰከሩ መሆናቸው ይታወቃል። ይህን መሰረት በማደረግ በሱማሊያ የሚገኘው የአፍሪካ ኅብረት የሰላም አስከባሪ ኃይል ወዲያውኑ የማጣራት ሂደት መጀመሩ የሚታወቅ ቢሆንም ውጤቱን ግን እስካሁን ይፋ ሳያደርግ ቆይቷል።

Saturday, January 21, 2017

እንጀራዬን በአዲስ ትሪ

   
አሰገደች ቶሎሳ
መቼም ዘንድሮ ጆሮአችን የማይሰማው፣ዓይናችን የማያየው የለው የኸው ደግሞ የወያኔ ካሚኔ የጭንቁን አዋጅ አውጆ፣የኢንተርኔት መረበን ዘግቶ የሚታፈሰውን አፍሶ፣ የሚተሰረዎን አስሮ የሚገደለውን ገድሎ ከጨረሰ በኃላ በፖርላማዬ ተቀምጨ ለአገር የሚበጅ ብልሀት መከርኩ ይለናል።
መምክራቸው ባልክፋ ነበር ማፅደቃቸው ግን አሁንም ፅኑ አቋማቸው አሳብቋል። እንድ ወዳጅ ድሮስ በገዥው የተተከለ አሁን ደግሞ ራሱ አፀደኩ ሲልህ አበጅህ ከማለት ሌላ ምን ምርጫ አልህ ብሎ ማለቱ ዕወነት ብሏል።
ይህንንማ መቺ አጣነው የህዝብን እኩልነት የሚያረጋግጥና እውነተኛውን ነፃ ዲሞክራሲ ሚያጐናፅፈን መንግስት ካቢኔነት ተነቅሎ ሌላ ይተካል አልን እንጂ…?  የተተከለውን መቺ አፅደቀልን አለን   ካቢኔነቱ ባለፈው ሀያ አምስት ዓመት እየተከለ፣እየበላ ፣እየጠጣ ብሎም እያደለበና እያፅደቀ ለሰፊው ህዝብ ጠብ የማይል ፍሬን ሳይስጥ መቆየቱ ከመንቀል ሌላ አማራጭ እንደሌለው ዛሬ ህዝቡ ጠንቅቆ ያውቃል።
አቶ ኃይለማሪያም የሰላም ችሎታቸውን ከቅርብ ግዜ በፌት በዳንስ ትርኢት እንዳሳዩን አስታውሳለሁ ዛሬ ድግሞ አሻሽለው በዕርግጥ አንባቢው እንጅ አፅዳቂው እሳቸው ባይሆኑም የሚኒስተሮችን የስልጣን ሰለሜ ስም እየጠሩ ሲያሽከረክሩ ውለዋል።
አይመጣም ገንፎ ከሜቴ ተርፎ እንዳለቸዋ አገልጋይ ካቢኔቱ አዲስ ትሪ ቀየረልን እንጂ የሚበላውንም የሚረግጠውንም የሚቀይር ሆኖ አልተገኘም። የአባገነን መንግስታት  የስልጣን ፍፃሜ ዕርምጃ በእጅጉ ተመሣሣይ ነው በመሆኑም የዛሬው የካቢኔነት ስያሜ ለስፊው ህዝብ የሚፈይደው ፋይዳ ባይኖርውም ለትግሉ ግን የምንግስቱን ግራ መጋባት አመልካች ነውና ትልቅ ምራፍ የድል ጉዞ መሆኑንም መርዳትየሰፊው አማራ ኦሮሞና የደቡብ ህዝጥያቄና የትግል ጉዞ እንዲ አደባባይ እያየ ህዝቦች ማንኞውንም ጥያቄአቸውን ካቀረንግስት እንደቀደመው ሁሉ መፍት ውን ምስጠትና ባግባቡ ለዳኘት ዝግጆ ው ይለናል

   ዳኛው ዝንጆሮ ፍርድ ቤቱደል
   እምን ተኩኖ ይነገራል በደል

እንዳሉ እንደ እብድ ውሻ በየ ዳናው እየተገደለ በየ እስር ቤቱ በዳቦ በእሳት እየጋየና እየተጐረ በሶቱን ለማን እና በምን ሁኔታ እንደሚናገር አቶ ይለማሪያም ደሳለኝ በሚቀጥለው የፖርላማ ስብሰባና ማንድ ፖስት አዋጃቸው ይነግሩን ይሆን በየተኛው ገር ታሪክ በግድና በ አፈና ጥቂት ግዜን የከረመ እንጂ የፈለገውን ውይም የተመኘውን ያህል የቆየ መንግስትን አለየንም የሰፊ ህዝብ ድምፅ መጣ ላለው ደራሽ ጐርፍ የማስጠንቀቂያ ነጐድጓድ ነው ተገድቦ ቆይ ኃይሎ ይጨምራል ይልቁኑም ተጠናክሮ የመጣል እንጅ ደ ኃላ አያፈገፍግም።

  ወያኔ እራሱ የተከለውን አፅድቆ ቀጥሎም ኮማንድ ስት ብሎ የክልክላ አዋጆን ባወጀብን በዚህ ጥቂት ግዜያት ውስጥ እንኳን በርካታ ወገኖቻችን የ አዋጆ ሰለባ ሆነዋል
ታዋቄ የነበረው የኡጋንዳው አምባገነን መሪ ዲ አሚን        ባታከብርኝ ችግር የለውም አገዛዙን መፍራት ግን ግዴታህ ነው እምቢ በልህ ምኑንም ያህል ብትሮጥ ከምተኩስው ጥይት በላይ አትፈጥንም  ብሎ እንዳለ ዛሬም የኛዎም መቃወም በቻ ሳይሆን አብሮ መቀመጥ አብሮ መስራትና አብሮ መኖርንም በ አዋጅ ከልከለውናል። በጠያፍ ድርጊታቸው እንዳልተከበሩ ቢያውቁቱም ያዛለቃቸው ይመስል ማስፈራራታቸውን ግን ቀጥለውበታል።

ሮፌሰር መራራ ጉዲና እና የርበኞች ግንቦት ቱ ፕሮፊስር ብርሀኑ ነጋ በ አንድ አዳራሽ መቀመጣቸው ይሆን ሰውዬውን ተጠያቂ ያደርጋቸው? እንግዲህ ተቃውሞ እንደ ተላላፌ በሽታ እንዳይዛመት መንግስታችን በነፍስ ወከፍ አዳራሽና ወንበር ብሎም መጓጓዥና ማደሪዎችንን እስከሚያዘጋጅልን ደረስ በተሰመረልን ርቀት ሆኖ መጠበቀ ግድ ሆንዋል  ወያኔ አልገባውም እንጄ የነፃነትና የኢዮጵያዊነት ፅናታታችን ያለው በደማችን ውስጥ ነው መቼውንም ከነ አቶ ኃይማርያም የፓርላማ ተከላ፣ነቀላና የ አዋጅ ጋጋታ የሚጠበቀው ቀቢፀ ተስፋ የለም። የትሪው መቀያየር ለእንጀራው ጣዕም የሚጨመረው ፋይዳ የለውም ይልቁኑም ህዝብ እያለ ያለው አገዛዙ ከስሩ መነቀል አለበ የተገባ ነው።

ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኖራለች።


ቸር ይግጠመን

Wednesday, January 11, 2017

ደፋ ቀና፣ ደረስ መለስ!! ወጋ ነቀል! የፍኖተ ራዲዮ ውቅታዊ ሀተታ

       
ደፋ ቀና፣ ደረስ መለስ!!
                                   ወጋ ነቀል!

የኢትዮጵያ ሕዝብ ትግል ረጅም ጉዞ የተጓዘ፣ ብዙም መስዋዕትነት የተከፈለ እዚህ የደረሰ ትግል ነው።  ዛሬም ከፍተኛው መስዋትነት እየተከፈለበት ያለም ነው። ሕዝባዊና አገራዊ ትግል የሚቋረጥ ደት አይደለም። ትግል መብት በተነፈገበት ሁኔታ ውስጥ ብቻ ይሆን፣ መብት በተከበረበት ህብረተሰብና በአንፃራዊ ደረጃ አደጉ በሚባሉ ገሮች ውስጥ ምር ይካሄዳል። ከዚህ በተረፈም የመደብ ራኔ በተወገደበት ሁኔታ የሰው ልጅ ከተፈጥሮ ር ግብግቡን ይቀጥላል። ይህ መሰሉ ግብግብ ግን ተፈጥሮን በአግባብ ይዞ ለሰው ልጆች  በሚጠቅም መንገድ ለመጠቀም እንጂ፣ በሰው ልጆች መሃል ያለውን መደባዊ ቅራኔ ለምፍታት አይደለም። ይህ እውነት ስለሆነም ነው፣ ሕዛባዊ ትግል የማይቋረጥ ሂደት ነው የሚባለው። ትግል በራሱ በጣም ውስብስብ ነው። የውስብስብነቱ ዋና መነሻ በተቃራኒዎች መሃል የሚካሄድ፣  ከፍተኛና ዋና  ቅራኔን፣ ከዝቅተኛ ቅራኔዎች ጋር አካቶ የያዘ በመሆኑም ጭምር ነው። ይህንን መሰል የቅራኔዎች አቀማመጥን አብጠርጥሮ አለማወቅ፣ በቅራኔዎች አፈታትም ላይ ትልቅ ተፅዕኖ ይኖረዋል። ይህን ማለትም ዋነኛው ቅራኔ በቅድሚያ ካልተፈታ ሁለተኛና ዝቅተኛ ቅራኔዎችን መፍታት ያዳግታል። አገራችንን እንደ ምሳሌ ስንጠቅስም ዋነኛው ቅራኔ ከወያኔ ግፈኛና ዘረኛ ገዢ ቡድን ጋር ያለው ቅራኔ ነው። የኢትዮጵያ ሕዝብ ወያኔ ይገርሰስ፣ ብሎ ለአመፅ ነሳ፣ የዚህ መሆን ዛሬ በደልና ግፍ እየፈፀመበት ካለው ወያኔያዊ አገዛዝ ለመገላገል ብቻ ሳይሆን፣ ለሚቀጥለውም ግግር ሁነኛ መሠረት ለመጣል የሚቻለው በዚሁ ጉዞ ውስጥ የተቃዋሚዎችን የህብረት ትግል መገንባት ሲቻል ነው

       በቅርብ ጊዜ ከተለያዩ ተቃዋሚ ነን ባዮች አካባቢ እንደሚሰማው አመፁ ተዳክሟል፣ ወያኔ ተቆጣጥሮታል፣ ወያኔ እሥርና ግድያውን የበለጠ ሰላፋፋመ ሕዝቡ ተስፋ የመቁረጥ ዝንባሌ እያሳየ ነው ∙∙∙ ወዘተ∙ የሚሉት ተበራክተዋል። እነዚህም ተከፍለው መታየት ይኖርባቸዋል። የመጀመሪያዎቹ በእውነትም ወያኔን የሚጠሉ ቢሆኑም፣ ያላቸው ንቃተ ህሊና ይህንን ሁኔታና የወያኔን የማጭበርበር ሮፓጋንዳ ለማየት ስላላስቻላቸው ነው። ሁለተኛዎቹ ክፍሎች ደግሞ ተማርን፣ አወቅን፣ ተመራመርን የሚሉ ቢሆኑም፥ ሀ) ለሆዳቸውና፣ ለኢዴሞክራሲያዊ ሥልጣን የሚሽቀዳደሙ፣ ለ) ለባዕዳን ጥቅምና ተልዕኮ የቆሙ፣ ወያኔን ጠግኖ በሥልጣን ለማቆየትና አጃቢ ለመሆን የተሠለፉ ናቸው። እነዚህኛዎቹ ለጊዜው ሥልጣን ላይ አይሁኑ እንጂ፣ ከወያኔ ባልተናነሰ ደረጃ ሕዝባዊ አመፁን እየጐዱ ያሉ የውስጥ መዥገሮች፣ የብብት ሥር እባቦች ናቸው
       በሶስተኛዎቹ ደረጃ የሚመደቡት ባዕዳን የምዕራቡ አገሮች ናቸው። ወያኔ ሥልጣን ላይ በነሱ ድጋፍ ከወጣ ጀምሮ፣ በመሳሪያ አቅርቦት፣ የሱን አፋኝና አረመኔ ሊሶችና የጦር ይሎች በማሰልጠን፣ መጠን የለሽ የመዋዕለ ነዋይ አቅርቦት ሲያደርጉለት ቆይተዋል። በኢትዮጵያ ሕዝብ ላይ የፈረዱት ፍርድ በዚህ ብቻ ተወስኖ የቀረም አይደለም። በነዚህ አገሮች የሚገኙ የሰብዓዊ መብት ተቋሞች ጭምር፣ በብዙ መቶ ስለሚቆጠሩ፣ በወያኔ የተለያየ እሥር ት ስለሚሰቃዩ፣ በወያኔ ጥይት ስለረገፉ ዜጐቻችን፣ መድረሻቸውና ደብዛቸው ስለጠፉ ወገኖቻችን፣ ከወያኔ ግፍና ግድያ ለመምለጥ በየባህሩ ሰምጠው ስለቀሩ ወጣት ልጆቻችን፣ በየአረብ አገር በዘይት እየተቀቀሉ በካራ ስለሚታረዱ እህቶቻችን ሲያወሩም ሆነ ሲያወሱ አይሰምም። ሰው እንደሰብዓዊነቱ በሰውነቱ መከበር እንዳለበት በየትምህርት ተቋሞቻቸው፣ በየዩነቨርስቲዎቻቸው ጭምር የሚሰበክ ቢሆንም፣ ስለአገራችን ሕዝብ በወያኔ አማካይነት መብቱ መጓደሉና መረገጡ፣ የዙን ማሰራጫዎቻቸው ጭምር ሲተነፍሱ አይሰማም። ምንግሥቶቻቸው ጭምር።
       በምዕራብ አገሮች እየተደገፈ ዳር የደረሰ ህዝባዊ አመፅ የተሳካበት፣ ዴሞክራሲ ዕውን ሆኖ የታየበት የታሪክ ዘመን እስካሁን አልታየም። የአረብ አገሮችን የቅርብ ጊዜ አመፅ እንዴት እንዳሰናከሉት፣ ያላቲን አሜሪካን የግራ አመፅና እንቅስቃሴ እንዴት እንዳከሸፉት፣ እምዬ አፍሪካን አገሮች በአንባገነን ገዢዎች እንዴት እንዳጥለቀለቋት ማየቱ ብቻ በቂ ነው። ዴሞክራሲያዊ ስርዐትን መደገፍማ ለነሱ ምን ይጠቅማል? እኛም አውቀናል ጉድጓድ ምስናል ያልነው ገና ከጥንቱ ነው። ህዝባዊ አመፅ የድሆች አመፅ ነው። ያልነው ገና ከጅምሩ ነው። ለነሱ (ለምዕራቡ) ጥቅም ማስጠበቂያ የሚሹት አምባገነናዊ ሥርዐትን ነው። በአራተኛ ደረጀ የሚጠቀሱት ፀረ ሕዝባዊ ዐመፅ ክፍሎች፣ ጠባቦችና ትምክህተኞች ናቸው
       አንድ የፓለቲካ እንቅስቃሴ፦ እኔ ካንተ እሻላለሁ ወይም እበልጣለሁ የሚል ጉንጭ አልፋ ንትርክ ውስጥ ከገባ አቋሙን መመርመር ተገቢ ነው። ብልጫውን ደግሞ በትግል ታሪኩና ለትግሉ ካለው የአላማ ፅናት አኳያ ማቅረብ ከፈለገም ይህም መመርመር የሚገባው ግዴታ ነው። በኛ አመላካከትና እምነት ግን ጥበትና ትምክህት ሕዝባዊ ሕዝባዊ ትግልን ጐጂዎች ናቸው። ሁለቱም የፅንፈኝነት አመለካከት ሕዝብን በዴሞክራሲያዊና ሀገራዊ አመላካከት አያዩም። መስፈርታቸውም ሆነ አቋማቸው የኔ ብሄር የበለጠ ተጨቁኗል፣ የኔ ብሄር አባል ብዙ ነው፣ የኔ ብሄር የመማር ዕድል ተነፍጓል፣ ለም መሬትና ማዕድናት በብዛት ያሉት በኔ ክልል ነው ∙∙∙ ወዘተ∙ ዝርዝሩ ብዙ ነው። የአንድን ሕዝብ እኩልነት ከፈለግን ደግሞ፣ በሕዝቦች እኩልነት ላይ የተመሠረተ ሀገራዊ ላዓላዊነትን በቅዳሚ መቀበል ግዴታ ነው። የሀገርን ላዓላዊነት ሳይቀበሉ፤ ለሕዝብ እኩልነት መቆምና ለዴሞክራሲ መታገል የሚታሰብ አይደለም።ዛሬ በሀገራችን ያለውን ሁኔታ ስናየው፣ ሁሉም ጠባቦች ግን ለዴሞክራሲ እንታገላለን ይላሉ። የሀገር ላዓላዊነት ባልተከበረበት ለዴሞክራሲ መታገል ምን ማለት ነው ብለን ስንጠይቃቸው፣ እንደ ሰጐን አናታቸውን ጉድጓድ ውስጥ ይቀብራሉ። ሁሉንም አሞኝቶ ለግንጠላ መንገድን ማዘጋጀት ይሏል ይህ ነው!! ለሁሉስ በዚህ መሥመር ለመጓዝ ማን ፈቀደላችሁ፣ ህዝቡስ በየትኛው ጉባዔ መረጣችሁ፣ ሲባሉ አሁንም መልሱ ዝምታ ነው። ሕዝቡ በአጠቃላይ ግን ለመብቱ መሟላትና ለሀገራዊ ነፃነቱ ትግሉን ቀጥሏል። ፍግሉን ያቋረጠበትም ጊዜ የለም። ባለፉት የታሪክ ዘመናትም በጋራ ታግሎ፤ በጋራ የሀገሩን ነፃነት አስከብሯል። ዛሬም ወያኔን እየታገለ፣ የሀገሩን ነፃነትና ዴሞክራሲያዊ መብቱን ለመቀዳጀት በጋራ እየተፋለመ ነው። ከዚህ ሕዝብ መወላዳችን ያኮራናል እንላለን!! ከጐን ቆመን እንታገላለን። ወደፊትም በዚሁ መንገድ እንቀጥላለን!!
       እስከዛሬም የተጐዳችው ኢትዮጵያ ነች እንጂ፣ እንድ ጐሳ አይደለም። የጐሣን መጐዳትና አለመጐዳት ማሳመን ያስቸግራል። ለኢትዮጵያ ሕዝብ ግን፣ ኢትዮጵያ ጥያቄ ሥር ገብታ አታውቅም። በሰሞኑ ተቃዋሚ ነን በሚሉት ሰፈር እየተራገበ ያለው ወሬ፣ ወያኔ እያደረ እየተጠናከረና የበለጠም ህዝብን እየፈጀ በመምጣቱ አመፁ ተዳክሟል። ህዝቡም በአመፁ ቀጣይነት ላይ ተስፋ እየቆረጠ መጥቷል የሚል ነው።
       በቂ የንድፈ ሃሳብ ግንዛቤና መሠረት ያጣ አባባል ሆኖ ነው እንጂ የህዝብ አመፅ አንድ ጊዜ ከጀመረና ሰፊውን ህዝብ ከዳር እስከዳር ሊያስነሳ ከቻለ፣ የሚቋረጥ ጉዳይ አይደለም። አንድ ጊዜ ቀዝቀዝ፣ ሌላ ጊዜ ሞቅ ኢያለ ወደ ነበልናልነት መለወጡ አይቀሬ ነው። ታጋይ ክፍሉም፣ ደፋ ቀና፣ ደረስ መለስ፣ ዋጋ ንቀል፣ እያለ ዛሬ ጠንካራ መስሎ የሚታየውን ጠባብና ዘረኛ ፀረ ኢትዮጵያ የወያኔ ቡድን እየመነመነ ወደ ከርሰ መቃብር መወርወሩ አይቀሬ ነው።
              ዛሬ የአመፁ ቀዳሚ ተግባሮች ምን መሆን አለባቸው?
ዛሬ አመፁ ያለበትን ደረጃ ስንመረምር ውስኝ ጊዜ ላይ ምድረሳችንን መገንዘብ ከባድ አይሆንም። በዚህ መሰሉ ጊዜም ትክክለኛ የስትራተጂና የታክትክ መንገድን መከተል ግዴታ ነው። የዓለም ሕዝቦች ታሪክ እንደሚያሳየን ስትራተጂና ታክቲክ ተለያይተው የሚታዩ አይደሉም። በብዙ መንገድ የተያያዘና የተሳሰሩ ናቸው። በአንዳንድ አገሮች ትግል በገጠር ይጀመራል። በሌሎች አገሮች ደግሞ በከተሞች ይጀመራል። ሁልጊዜ ግን አመፁ በከተሞች ተገባዶ ያልቃል። በዋናነት ዋናው ከተማ ሲያዝና፣ ጨቋኝና ግፈኛው መንግሥት ሁኔታውን መቆጣጠር ተስኖት ከፖለቲካው ወንበር እንዲወርድ ሲገደድ ማለት ነው። የጨቋኝ ገዢዎች ከሰልጣን መሰናበት በሁለት መንገድ ሊታይ የሚችል ነው። የመጀመሪያና የሚመረጠው መንገድ ጨቋኝ ገዢዎች ፈቃደኝነትን አሳይተው ሽግግሩ በሰላም ሲያልቅ ነው። የዚህ መሆን በቀጣይነት የደም መፍሰስን፣ የንብረት መውደምን ያስወግዳል።
       የዚህ መሆን ግን፣ ብልህነት፣ ለሀገርና ሕዝብ አሳቢነትን ከሁለቱም ወገን የሚጠይቅ ነው። ወያኔ ለህዝብም ሆነ ለሀገር አሳቢነት  ሲፈጠርም ጀምሮ በገደማው ያልደረሱ፣ ለሱ ባዕድ ሆነው የኖሩ ናቸው። ከምስረታው ጀምሮ ኢትዮጵያና ሕዛቦቿን አምርሮ የሚጠላና የሚፈራም እርኩስ መንፈስ፣ በምድር ላይ በብቸኝነት የቀረ ሣጥናኤል ነው። ወያኔ ከምሥርታው ጀምሮ ያለውን የቆሸሸ ታሪኩን ብንተወው፣ ስልጣን ላይ ከወጣ ጀምሮ የሰላምን በር ዘግቶ ኑ ሞክሩኝ እንዳለ አለ። ዛሬ ጊዜው፣ ቀንህን ጠብቅ እንሞክርሃለን ለሚሉት በአማራጩ ብቸኛ መንገድ ላይ የምንመክርበት ወቅት ነው። ይህም
       ሀ) በትላልቅ ከተሞች ያለውን ሕዝብ ማደራጀት፦
       ማንኛውም ሕዝባዊ ትግል ከታለመው ዓላማ ለመድረስ፣ መደራጀት እንዳለበት ግልፅ ነው። በሌላው አኳያ መደራጀት፣ ንቃትና ስነምግባር (dicipline) የተያያዙ ናቸው። የሚደራጀው ሕዝቡ ብቻ ሳይሆን የሚያደራጁት ድርጅቶችም ትግሉ በየደረሰበት ደረጃ የበለጠ መደራጀት፣ በማንበብና በመወያየት ንቃተ ህሊናቸውን ማሳደግ ይጠበቅባቸዋል። ውስጣዊ አለመግባባቶችን በአግባቡ ለመፍታት በራሱ የንቃተ ህሊናን እድገት የሚጠይቅ ነው። ድርጅታዊ ሚስጥሮችን፣ ሰነዶችን፣ በአግባብና በጥንቃቄ መያዝ ያሚገባቸውን ንብረቶች ሁሉ በአግባብ ለመያዝ ሥነምግባራዊ ዕድገትን ጠያቂ ነው።
       ለ) የመታጠቅና የማስታጠቅ ጥያ
       ኢትዮጵያን ከውስጥም ሆነ ከውጭ ጠላት መከላከል የሚጀመረው፣ እዚያው ኢትዮጵያ ውስጥ ነው። ለዚህ መሆን ሕዝቡን በሞላ የሚያጠቃልል ብሄራዊ ስትራተጂ ያስፈልጋል።
ሠፊው የኢትዮጵያ ህዝብም ሀቀኛ ተቃዋሚዎች ወያኔ ካለመሣሪያ ከሥልጣን እንደማይወገድ ከተገነዘቡት ቆይተዋል። በተቻለ መጠን ህዝቡን ማስታጠቅ ወሳኝ ነው። በከተሞች መሣሪያ በየቦታው ማከማቸት ያስፈልጋል። ይህ መሆን ያለበት በድርጅት አባሎች እጅ ነው። ዛሬ እንደሚታየው በገጠሩ የመሣሪያ ግብግብ እየተፋፋመ ነው። ለገጠር ትግሉም ተጨማሪ መሣሪያ ማስገኘት ከወያኔ ጋር ያለውን የኃይል ሚዝን ማዛባት ይቻላል።
የተለያየ አመለካተት ተቃዋሚ ነን በሚሉት ሰፈር የሚሰማ ቢሆንም፣ የኢትዮጵያ ሕዝብ ከወያኔ ጋር የገጠመውን ግብግብ በድል መወጣቱ የማይቀር ጉዳይ ነው።
ድል ምንጊዜም የሰፊው ሕዝብ ነው!!

የኢትዮጵያ ሕዝብ ያቸንፋል!!