Wednesday, January 11, 2017

ደፋ ቀና፣ ደረስ መለስ!! ወጋ ነቀል! የፍኖተ ራዲዮ ውቅታዊ ሀተታ

       
ደፋ ቀና፣ ደረስ መለስ!!
                                   ወጋ ነቀል!

የኢትዮጵያ ሕዝብ ትግል ረጅም ጉዞ የተጓዘ፣ ብዙም መስዋዕትነት የተከፈለ እዚህ የደረሰ ትግል ነው።  ዛሬም ከፍተኛው መስዋትነት እየተከፈለበት ያለም ነው። ሕዝባዊና አገራዊ ትግል የሚቋረጥ ደት አይደለም። ትግል መብት በተነፈገበት ሁኔታ ውስጥ ብቻ ይሆን፣ መብት በተከበረበት ህብረተሰብና በአንፃራዊ ደረጃ አደጉ በሚባሉ ገሮች ውስጥ ምር ይካሄዳል። ከዚህ በተረፈም የመደብ ራኔ በተወገደበት ሁኔታ የሰው ልጅ ከተፈጥሮ ር ግብግቡን ይቀጥላል። ይህ መሰሉ ግብግብ ግን ተፈጥሮን በአግባብ ይዞ ለሰው ልጆች  በሚጠቅም መንገድ ለመጠቀም እንጂ፣ በሰው ልጆች መሃል ያለውን መደባዊ ቅራኔ ለምፍታት አይደለም። ይህ እውነት ስለሆነም ነው፣ ሕዛባዊ ትግል የማይቋረጥ ሂደት ነው የሚባለው። ትግል በራሱ በጣም ውስብስብ ነው። የውስብስብነቱ ዋና መነሻ በተቃራኒዎች መሃል የሚካሄድ፣  ከፍተኛና ዋና  ቅራኔን፣ ከዝቅተኛ ቅራኔዎች ጋር አካቶ የያዘ በመሆኑም ጭምር ነው። ይህንን መሰል የቅራኔዎች አቀማመጥን አብጠርጥሮ አለማወቅ፣ በቅራኔዎች አፈታትም ላይ ትልቅ ተፅዕኖ ይኖረዋል። ይህን ማለትም ዋነኛው ቅራኔ በቅድሚያ ካልተፈታ ሁለተኛና ዝቅተኛ ቅራኔዎችን መፍታት ያዳግታል። አገራችንን እንደ ምሳሌ ስንጠቅስም ዋነኛው ቅራኔ ከወያኔ ግፈኛና ዘረኛ ገዢ ቡድን ጋር ያለው ቅራኔ ነው። የኢትዮጵያ ሕዝብ ወያኔ ይገርሰስ፣ ብሎ ለአመፅ ነሳ፣ የዚህ መሆን ዛሬ በደልና ግፍ እየፈፀመበት ካለው ወያኔያዊ አገዛዝ ለመገላገል ብቻ ሳይሆን፣ ለሚቀጥለውም ግግር ሁነኛ መሠረት ለመጣል የሚቻለው በዚሁ ጉዞ ውስጥ የተቃዋሚዎችን የህብረት ትግል መገንባት ሲቻል ነው

       በቅርብ ጊዜ ከተለያዩ ተቃዋሚ ነን ባዮች አካባቢ እንደሚሰማው አመፁ ተዳክሟል፣ ወያኔ ተቆጣጥሮታል፣ ወያኔ እሥርና ግድያውን የበለጠ ሰላፋፋመ ሕዝቡ ተስፋ የመቁረጥ ዝንባሌ እያሳየ ነው ∙∙∙ ወዘተ∙ የሚሉት ተበራክተዋል። እነዚህም ተከፍለው መታየት ይኖርባቸዋል። የመጀመሪያዎቹ በእውነትም ወያኔን የሚጠሉ ቢሆኑም፣ ያላቸው ንቃተ ህሊና ይህንን ሁኔታና የወያኔን የማጭበርበር ሮፓጋንዳ ለማየት ስላላስቻላቸው ነው። ሁለተኛዎቹ ክፍሎች ደግሞ ተማርን፣ አወቅን፣ ተመራመርን የሚሉ ቢሆኑም፥ ሀ) ለሆዳቸውና፣ ለኢዴሞክራሲያዊ ሥልጣን የሚሽቀዳደሙ፣ ለ) ለባዕዳን ጥቅምና ተልዕኮ የቆሙ፣ ወያኔን ጠግኖ በሥልጣን ለማቆየትና አጃቢ ለመሆን የተሠለፉ ናቸው። እነዚህኛዎቹ ለጊዜው ሥልጣን ላይ አይሁኑ እንጂ፣ ከወያኔ ባልተናነሰ ደረጃ ሕዝባዊ አመፁን እየጐዱ ያሉ የውስጥ መዥገሮች፣ የብብት ሥር እባቦች ናቸው
       በሶስተኛዎቹ ደረጃ የሚመደቡት ባዕዳን የምዕራቡ አገሮች ናቸው። ወያኔ ሥልጣን ላይ በነሱ ድጋፍ ከወጣ ጀምሮ፣ በመሳሪያ አቅርቦት፣ የሱን አፋኝና አረመኔ ሊሶችና የጦር ይሎች በማሰልጠን፣ መጠን የለሽ የመዋዕለ ነዋይ አቅርቦት ሲያደርጉለት ቆይተዋል። በኢትዮጵያ ሕዝብ ላይ የፈረዱት ፍርድ በዚህ ብቻ ተወስኖ የቀረም አይደለም። በነዚህ አገሮች የሚገኙ የሰብዓዊ መብት ተቋሞች ጭምር፣ በብዙ መቶ ስለሚቆጠሩ፣ በወያኔ የተለያየ እሥር ት ስለሚሰቃዩ፣ በወያኔ ጥይት ስለረገፉ ዜጐቻችን፣ መድረሻቸውና ደብዛቸው ስለጠፉ ወገኖቻችን፣ ከወያኔ ግፍና ግድያ ለመምለጥ በየባህሩ ሰምጠው ስለቀሩ ወጣት ልጆቻችን፣ በየአረብ አገር በዘይት እየተቀቀሉ በካራ ስለሚታረዱ እህቶቻችን ሲያወሩም ሆነ ሲያወሱ አይሰምም። ሰው እንደሰብዓዊነቱ በሰውነቱ መከበር እንዳለበት በየትምህርት ተቋሞቻቸው፣ በየዩነቨርስቲዎቻቸው ጭምር የሚሰበክ ቢሆንም፣ ስለአገራችን ሕዝብ በወያኔ አማካይነት መብቱ መጓደሉና መረገጡ፣ የዙን ማሰራጫዎቻቸው ጭምር ሲተነፍሱ አይሰማም። ምንግሥቶቻቸው ጭምር።
       በምዕራብ አገሮች እየተደገፈ ዳር የደረሰ ህዝባዊ አመፅ የተሳካበት፣ ዴሞክራሲ ዕውን ሆኖ የታየበት የታሪክ ዘመን እስካሁን አልታየም። የአረብ አገሮችን የቅርብ ጊዜ አመፅ እንዴት እንዳሰናከሉት፣ ያላቲን አሜሪካን የግራ አመፅና እንቅስቃሴ እንዴት እንዳከሸፉት፣ እምዬ አፍሪካን አገሮች በአንባገነን ገዢዎች እንዴት እንዳጥለቀለቋት ማየቱ ብቻ በቂ ነው። ዴሞክራሲያዊ ስርዐትን መደገፍማ ለነሱ ምን ይጠቅማል? እኛም አውቀናል ጉድጓድ ምስናል ያልነው ገና ከጥንቱ ነው። ህዝባዊ አመፅ የድሆች አመፅ ነው። ያልነው ገና ከጅምሩ ነው። ለነሱ (ለምዕራቡ) ጥቅም ማስጠበቂያ የሚሹት አምባገነናዊ ሥርዐትን ነው። በአራተኛ ደረጀ የሚጠቀሱት ፀረ ሕዝባዊ ዐመፅ ክፍሎች፣ ጠባቦችና ትምክህተኞች ናቸው
       አንድ የፓለቲካ እንቅስቃሴ፦ እኔ ካንተ እሻላለሁ ወይም እበልጣለሁ የሚል ጉንጭ አልፋ ንትርክ ውስጥ ከገባ አቋሙን መመርመር ተገቢ ነው። ብልጫውን ደግሞ በትግል ታሪኩና ለትግሉ ካለው የአላማ ፅናት አኳያ ማቅረብ ከፈለገም ይህም መመርመር የሚገባው ግዴታ ነው። በኛ አመላካከትና እምነት ግን ጥበትና ትምክህት ሕዝባዊ ሕዝባዊ ትግልን ጐጂዎች ናቸው። ሁለቱም የፅንፈኝነት አመለካከት ሕዝብን በዴሞክራሲያዊና ሀገራዊ አመላካከት አያዩም። መስፈርታቸውም ሆነ አቋማቸው የኔ ብሄር የበለጠ ተጨቁኗል፣ የኔ ብሄር አባል ብዙ ነው፣ የኔ ብሄር የመማር ዕድል ተነፍጓል፣ ለም መሬትና ማዕድናት በብዛት ያሉት በኔ ክልል ነው ∙∙∙ ወዘተ∙ ዝርዝሩ ብዙ ነው። የአንድን ሕዝብ እኩልነት ከፈለግን ደግሞ፣ በሕዝቦች እኩልነት ላይ የተመሠረተ ሀገራዊ ላዓላዊነትን በቅዳሚ መቀበል ግዴታ ነው። የሀገርን ላዓላዊነት ሳይቀበሉ፤ ለሕዝብ እኩልነት መቆምና ለዴሞክራሲ መታገል የሚታሰብ አይደለም።ዛሬ በሀገራችን ያለውን ሁኔታ ስናየው፣ ሁሉም ጠባቦች ግን ለዴሞክራሲ እንታገላለን ይላሉ። የሀገር ላዓላዊነት ባልተከበረበት ለዴሞክራሲ መታገል ምን ማለት ነው ብለን ስንጠይቃቸው፣ እንደ ሰጐን አናታቸውን ጉድጓድ ውስጥ ይቀብራሉ። ሁሉንም አሞኝቶ ለግንጠላ መንገድን ማዘጋጀት ይሏል ይህ ነው!! ለሁሉስ በዚህ መሥመር ለመጓዝ ማን ፈቀደላችሁ፣ ህዝቡስ በየትኛው ጉባዔ መረጣችሁ፣ ሲባሉ አሁንም መልሱ ዝምታ ነው። ሕዝቡ በአጠቃላይ ግን ለመብቱ መሟላትና ለሀገራዊ ነፃነቱ ትግሉን ቀጥሏል። ፍግሉን ያቋረጠበትም ጊዜ የለም። ባለፉት የታሪክ ዘመናትም በጋራ ታግሎ፤ በጋራ የሀገሩን ነፃነት አስከብሯል። ዛሬም ወያኔን እየታገለ፣ የሀገሩን ነፃነትና ዴሞክራሲያዊ መብቱን ለመቀዳጀት በጋራ እየተፋለመ ነው። ከዚህ ሕዝብ መወላዳችን ያኮራናል እንላለን!! ከጐን ቆመን እንታገላለን። ወደፊትም በዚሁ መንገድ እንቀጥላለን!!
       እስከዛሬም የተጐዳችው ኢትዮጵያ ነች እንጂ፣ እንድ ጐሳ አይደለም። የጐሣን መጐዳትና አለመጐዳት ማሳመን ያስቸግራል። ለኢትዮጵያ ሕዝብ ግን፣ ኢትዮጵያ ጥያቄ ሥር ገብታ አታውቅም። በሰሞኑ ተቃዋሚ ነን በሚሉት ሰፈር እየተራገበ ያለው ወሬ፣ ወያኔ እያደረ እየተጠናከረና የበለጠም ህዝብን እየፈጀ በመምጣቱ አመፁ ተዳክሟል። ህዝቡም በአመፁ ቀጣይነት ላይ ተስፋ እየቆረጠ መጥቷል የሚል ነው።
       በቂ የንድፈ ሃሳብ ግንዛቤና መሠረት ያጣ አባባል ሆኖ ነው እንጂ የህዝብ አመፅ አንድ ጊዜ ከጀመረና ሰፊውን ህዝብ ከዳር እስከዳር ሊያስነሳ ከቻለ፣ የሚቋረጥ ጉዳይ አይደለም። አንድ ጊዜ ቀዝቀዝ፣ ሌላ ጊዜ ሞቅ ኢያለ ወደ ነበልናልነት መለወጡ አይቀሬ ነው። ታጋይ ክፍሉም፣ ደፋ ቀና፣ ደረስ መለስ፣ ዋጋ ንቀል፣ እያለ ዛሬ ጠንካራ መስሎ የሚታየውን ጠባብና ዘረኛ ፀረ ኢትዮጵያ የወያኔ ቡድን እየመነመነ ወደ ከርሰ መቃብር መወርወሩ አይቀሬ ነው።
              ዛሬ የአመፁ ቀዳሚ ተግባሮች ምን መሆን አለባቸው?
ዛሬ አመፁ ያለበትን ደረጃ ስንመረምር ውስኝ ጊዜ ላይ ምድረሳችንን መገንዘብ ከባድ አይሆንም። በዚህ መሰሉ ጊዜም ትክክለኛ የስትራተጂና የታክትክ መንገድን መከተል ግዴታ ነው። የዓለም ሕዝቦች ታሪክ እንደሚያሳየን ስትራተጂና ታክቲክ ተለያይተው የሚታዩ አይደሉም። በብዙ መንገድ የተያያዘና የተሳሰሩ ናቸው። በአንዳንድ አገሮች ትግል በገጠር ይጀመራል። በሌሎች አገሮች ደግሞ በከተሞች ይጀመራል። ሁልጊዜ ግን አመፁ በከተሞች ተገባዶ ያልቃል። በዋናነት ዋናው ከተማ ሲያዝና፣ ጨቋኝና ግፈኛው መንግሥት ሁኔታውን መቆጣጠር ተስኖት ከፖለቲካው ወንበር እንዲወርድ ሲገደድ ማለት ነው። የጨቋኝ ገዢዎች ከሰልጣን መሰናበት በሁለት መንገድ ሊታይ የሚችል ነው። የመጀመሪያና የሚመረጠው መንገድ ጨቋኝ ገዢዎች ፈቃደኝነትን አሳይተው ሽግግሩ በሰላም ሲያልቅ ነው። የዚህ መሆን በቀጣይነት የደም መፍሰስን፣ የንብረት መውደምን ያስወግዳል።
       የዚህ መሆን ግን፣ ብልህነት፣ ለሀገርና ሕዝብ አሳቢነትን ከሁለቱም ወገን የሚጠይቅ ነው። ወያኔ ለህዝብም ሆነ ለሀገር አሳቢነት  ሲፈጠርም ጀምሮ በገደማው ያልደረሱ፣ ለሱ ባዕድ ሆነው የኖሩ ናቸው። ከምስረታው ጀምሮ ኢትዮጵያና ሕዛቦቿን አምርሮ የሚጠላና የሚፈራም እርኩስ መንፈስ፣ በምድር ላይ በብቸኝነት የቀረ ሣጥናኤል ነው። ወያኔ ከምሥርታው ጀምሮ ያለውን የቆሸሸ ታሪኩን ብንተወው፣ ስልጣን ላይ ከወጣ ጀምሮ የሰላምን በር ዘግቶ ኑ ሞክሩኝ እንዳለ አለ። ዛሬ ጊዜው፣ ቀንህን ጠብቅ እንሞክርሃለን ለሚሉት በአማራጩ ብቸኛ መንገድ ላይ የምንመክርበት ወቅት ነው። ይህም
       ሀ) በትላልቅ ከተሞች ያለውን ሕዝብ ማደራጀት፦
       ማንኛውም ሕዝባዊ ትግል ከታለመው ዓላማ ለመድረስ፣ መደራጀት እንዳለበት ግልፅ ነው። በሌላው አኳያ መደራጀት፣ ንቃትና ስነምግባር (dicipline) የተያያዙ ናቸው። የሚደራጀው ሕዝቡ ብቻ ሳይሆን የሚያደራጁት ድርጅቶችም ትግሉ በየደረሰበት ደረጃ የበለጠ መደራጀት፣ በማንበብና በመወያየት ንቃተ ህሊናቸውን ማሳደግ ይጠበቅባቸዋል። ውስጣዊ አለመግባባቶችን በአግባቡ ለመፍታት በራሱ የንቃተ ህሊናን እድገት የሚጠይቅ ነው። ድርጅታዊ ሚስጥሮችን፣ ሰነዶችን፣ በአግባብና በጥንቃቄ መያዝ ያሚገባቸውን ንብረቶች ሁሉ በአግባብ ለመያዝ ሥነምግባራዊ ዕድገትን ጠያቂ ነው።
       ለ) የመታጠቅና የማስታጠቅ ጥያ
       ኢትዮጵያን ከውስጥም ሆነ ከውጭ ጠላት መከላከል የሚጀመረው፣ እዚያው ኢትዮጵያ ውስጥ ነው። ለዚህ መሆን ሕዝቡን በሞላ የሚያጠቃልል ብሄራዊ ስትራተጂ ያስፈልጋል።
ሠፊው የኢትዮጵያ ህዝብም ሀቀኛ ተቃዋሚዎች ወያኔ ካለመሣሪያ ከሥልጣን እንደማይወገድ ከተገነዘቡት ቆይተዋል። በተቻለ መጠን ህዝቡን ማስታጠቅ ወሳኝ ነው። በከተሞች መሣሪያ በየቦታው ማከማቸት ያስፈልጋል። ይህ መሆን ያለበት በድርጅት አባሎች እጅ ነው። ዛሬ እንደሚታየው በገጠሩ የመሣሪያ ግብግብ እየተፋፋመ ነው። ለገጠር ትግሉም ተጨማሪ መሣሪያ ማስገኘት ከወያኔ ጋር ያለውን የኃይል ሚዝን ማዛባት ይቻላል።
የተለያየ አመለካተት ተቃዋሚ ነን በሚሉት ሰፈር የሚሰማ ቢሆንም፣ የኢትዮጵያ ሕዝብ ከወያኔ ጋር የገጠመውን ግብግብ በድል መወጣቱ የማይቀር ጉዳይ ነው።
ድል ምንጊዜም የሰፊው ሕዝብ ነው!!

የኢትዮጵያ ሕዝብ ያቸንፋል!!

No comments:

Post a Comment